✨አንተ በእግዚአብሔር እጅ ያለህና በመዳፉ ላይ የተቀረጽህ ነህ። [ ኢሳ 49፣16 ] እርሱ ከክንፎቹም በታች ተማምነህ እንድትጠለል አድርጎሃል [መዝ 90 ] እርሱ በቀንና በሌሊት ከአንተ ጋር ነው መውጣትና መግባትህንም ይጠብቃል። [ መዝ 120 ] እርሱ ስለሚወድህም ልጄ ብሎ ጠርቶሃል. [1ኛ ዮሐ 3፥1 ] እርሱ እረኛህ ስለሆነም ምንም የሚያሳጣህ ነገር የለም ። [ መዝ 22፥1] እኛ ሁላችን የእግዚአብሔር ስለሆንን የጋጣው በጎች ነን እርሱም መልካም እረኛ ስለሆነ በጎቹን አይዘነጋም እንደ አባትነቱም ልጆቹን አይረሳም ።
ለመንጋው ሁሉ በጎ እንደሚመኝ እንደ መልካም እረኛ እግዚአብሔርም በፍጥረታቱ በሙሉ ያለምንም ጥርጥር በዝምታ ይሠራል። ይሁን እንጂ ሰዎች በመከራ ውስጥ ሆነው የእግዚአብሔር መልስ ከዘገየባቸው እንደማይሰራ አድርገው ያስባሉ። እነርሱ እግዚአብሔር አይሰራም ብለው በሚያስቡበት ሰዓት ሁሉ እርሱ ግን ለእነርሱ በጥልቅ እየሰራ ነው። ሰዎች ይህንን ስለማይገነዘቡ የእግዚአብሔርን ሥራና የስራውን ውጤት ፈጥነው ለማየት ይፈልጋሉ። እነዚህ ሰዎች ግን በእምነታቸው ያመኑትን በዓይነቻቸው እስኪመለከቱ ድረስ ሊቆዩ ይገባቸዋል። "
እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ በርታ ልብህም ይጽና እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፡፡" መዝ 26 ፥ 14።
አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
📌የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
🚌 እናስተዋውቃችሁ
የምስካበ ቅዱሳን መድኃኔዓለም ገዳም ታሪክ
የምስካበ ቅዱሳን ዮርዲያኖስ መድኃኔዓለም ገዳም በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በሞጃና ወደራ ወረዳ በፈላገነት ቀበሌ የሚገኝ ገዳም ነው። ከአዲስ አበባ ወደ 206 ኪ.ሜ ርቀት አካባቢም ይገኛል።
ገዳሙ አሁን የታነጸበት አካባቢ ከገዳሙ መታነጽ በፊት በአጽመ ቅዱሳን መግቢያ ማለትም በስተምእራብ ካለው አንድ የጽድና አንድ የወይራ ዛፍ ውጪ በአካባቢው የሚታይ ነገር አልነበረም። ይሁን እንጂ በአካባቢው ያሉ ቀደምት አባቶች በየጊዜው ድንቅ ነገር ይገጥማቸዋል። ልዩ መኣዛ ያለው ነገ ይሸታቸዋል ። የከበሮ ድምጽ ይሰማሉ። ከዚህም ሌላ ግዙፍ ነጭ አሞራ ከማይታወቅ አካባቢ ትኩስ አስክሬን ይዞ በመምጣት በቅድሚያ ከገዳሙ ፊት ለፊት ካለ ውጭንጫ ውድማ ሜዳ ላይ ካስቀመጠ በኋላ ቀጥታ ከወይራው አጠገብ ያለው ዋሻ ውስጥ አጽመ ቅዱሳንን በክብር ሲያስቀምጥ ይመለከታሉ። አምላክ ፈቅዶ ወደስፍራው ቢሄዱ የተለያዩ የመግነዝ አይነቶች በበፍታ፡ በቆዳና በሸራ የተገነዙ የቅዱሳን አባቶች አጽም ከነመጻሕፍታቸው እና መቁጠሪያቸው እያበራ በክብር አርፎ አልባብ አልባብ እየሸተተ ያገኛሉ።
የአካባቢው በስተምስራቅ ከወንዙ ማዶ በዘንዶ ሲጠበቅ በስተምእራቡ ደግሞ በነብር ይጠበቅ ነበር። ቦታው በእግዚአብሔር ቸርነትና በቅዱሳን ጸሎት ከጥፋት ሲጠበቅ ኖሮ እግዚአብሔር ፈቃዱ ሲሆን በዘመናችን የቦታው ክብር ተገልጧል። ገዳሙ ከዚህ በፊት አስክሬን ዋሻ እና ዮርዲያኖስ አጽመ ቅዱሳን መድኃኔዓለም ገዳም ተብሎ ይጠራ ነበር።
የቦታው ጥንተ ታሪክ
ገዳሙ የተመሰረተበት ጊዜ በትክክል የማይታወቅ ሲሆን በአህመድ ግራኝ ወረራ ወቅት ሸሽተው በመጡ ቅዱሳን አባቶች መመስረሩን የሚናገሩ አሉ። ይህንን ሲገልጡ ሶስት ቅዱሳን ውሃ ማውጫ ለሚባል አካባቢ ጽላቶችንና ነዋየ ቅዱሳትን አሽሽተው በገዳሙ አካባቢ በማረፍ ብዙ ተጋድሎ መፈጸማቸውን ይነግራሉ። ከእነርሱም መካከል አባብሩ መስቀል የተባሉት ከበረት ላም ስለጠፋባቸው ከመጨነቃቸው የተነሳ ሱባዔ ገብተው ምስጢሩን ኣንዲገልጥላቸው በጸሎት ሲጠይቁ ፈጣሪ ላሚቱ በጠፋችበት በስድስት ወሯ በአጽመ ቅዱሳኑ ዋሻ ስር እንደሚያገኟት ይገልጽላቸዋል። በራእይ እንዳዩትም ላሚቱን ጥጃ ይዛ ከተባለው በር ላይ ያገኟታል። በዚህ ግዜ የመንፈስ ቅዱስ ምሪት ነው ብለው በማመን ከጎንደር አሽሽተው ያመጧቸውን ጽላቶቹንና ነዋየ ቅዱሳቱን ከዝርፊያና ቃጠሎ ለመታደግ በዋሻው ውስጥ እንደሰወሩትና በዚያው የገዳሙ መሰረት እንደተጣለ ያስረዳሉ።
ስለ ገዳሙ በአዲስ መልክ መታነጽ
መጋቢ ተክለጻድቅ ሸዋረጋ የተባሉ አባት በጸሎት ላይ ሳሉ አሁን ዋሻው በተፈለፈለበት አካባቢ የነጭ አውራ ዶሮ አምሳል ከሰማይ ሲወርድ ይመለከታሉ። ወደቦታው እንዲሄዱ ሲታዘዙም ስለጉዳዩ ከታላላቅ አባቶች ጋር በመሆን ሱባኤ ይይዙና ፈቃደ እግዚአብሔር መሆኑን ይረዳሉ። አስፈላጊውን ነገር አሟልተው ቦታውን ከተረከቡም በኋላ መድኃኔዓለም ከመረጣቸው ጋር በመሆን መጋቢት 20/1998 ዓ.ም ስራው ተጀምሮ በዚያው አመት የቤተክርስቲያኑ ስራ ተጠናቀቀ ። በጥቅምት 1999 ዓ/ም ዋሻውን የመፈልፈል ስራ ተጀመረ ። ሁሉም ተባብሮም ብዙ ችግሮችን በእግዚአብሔር ቸርነት እያለፉ መፈልፈላቸውን ሲቀጥሉ በመሃል ሲመቱት እንደመብረቅ ብልጭ የሚል ቋጥኝ ይገጥማቸዋል። በዚያን ጊዜ ኃይልን ወደሚሰጥ ምስጢርም ወደሚገልጥ አምላክ በመጸለይ በእግዚአብሔር ቸርነትና በእመቤታችን አማላጅነት ድንጋዩ በተፈናቀለበት ቦታ ለአራት ተከታታይ ቀናት ነጠብጣብ እንደወረደና ብዙዎች ጠብጠብ የሚለውን ተቀብተው በብዙ መፈወሳቸውን ይገልፃሉ።
በቁፋሮው ወቅት በእግዚአብሔር መሪነት ሊሰሩ ከቻሉት መቅደሶች አንደኛው የመድኃኔዓለም ቤተ መቅደስ ሲቆፈር በጣሪያው ላይ ከሚቆፈረው ዐለት የተለየ ቀለም ያለው ባለ ክብ ቅርጽ ብርሃናማ ዐለት ተገኝቷል። ይሄውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአይሁዶች ግፍና መከራን እስራትንና ግርፋትን ሲቀበል አይሁድ በራሱ ላይ የደፋለት የእሾህ አክሊል ምሳሌ ነው። ቁፋሮው አመት ከ ስምንት ወር ወስዶ ቅዳሴ ቤቱ ግንቦት 27 ቀን 2000 ዓ/ም በሃገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ አቡነ ኤፍሬም መልካም ፈቃድ በአፋር ክልል ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ አቡነ ዮናስ ተባርኮ ከብሯል።
ፍልፍል ዋሻው 4000 ( አራት ሺህ) ካ.ሜ የሚደርስ ስፋት እንዳለው የሚገመት ሲሆን በውስጡ ሶስት ፍልፍል ቤተመቅደሶችን ይዟል።
እነርሱም የመድኃኔዓለም፡ የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሃንስ እና የ ቅድስት አርሴማ ቤተ መቅደስ ናቸው። ወደዋሻው ስንገባ በመጀመርያ ገድል ቤቱን የምናገኝ ሲሆን ይህ ክፍል ክብ ሆኖ ጣራው በሀረግ ሥራ የተጌጠና እጅግ ውብ የሆነ ነው። በመቀጠልም ከውስጥ በቀኝ የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሃንስን በግራ ደግሞ የቅድስት አርሴማን ቤተመቅደስ እናገኛለን። ከመካከል ደግሞ በክብ ቅርጽ የተፈለፈለው በዕፀ መስቀሉ የተከበበው እና ልዩ ግርማ ሞገስ ያለውን የመድኃኔዓለምን ቤተመቅደስ እናገኛለን። የዋሻውን የውስጥ ለውስጥ መተላለፊያ ኮሪደሮች ስፋት አምዶች ውበትና በግድግዳው ላይ የተፈለፈሉ መስቀሎች እና ቅዱሳት ስእሎች ከዋሻ ፡የተፈለፈሉትን መንበሮች ስንመለከትና የውሃ ልክ አጠባበቁንና የዋሻውም ተፈጥሯዊ ቀለም ስናይ በእርግጥም የመንፈስ ቅዱስ ስራ መሆኑን እንዳንጠራጠር ያደርገናል።
ዋሻው ውስጥ ለውስጥ መድረሻ ጥግ የሌለው በመሆኑ ርዝመቱን መንገር አይቻልም። ብዙ ያልተገለጡ ምስጢራትንም ይዟል። የአጽመ ቅዱሳን ዋሻም ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚያገናኝ አባቶች ያስረዳሉ።
"ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ"
🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም
ከ መጋቢት 26 እስከ ሚያዝያ 5
ለ ደብረ ዘይት (ምዝገባ ተጀምሯል)
- የታደሰ ፓስፖርት ፣ 2 ከለር ፎቶ ግራፍ
- 85,000 ብር (ለትኬት ፣ ለቪዛ ፣ለመመዝገቢያ ፣ ለጉዞ ኢንሹራንስ )
እና
- 1650 USD ዶላር ኢየሩሳሌም ሲደረስ የሚከፈል ( ለ ሆቴል ፣ለምግብ ፣
ለትራንስፖርት ፣ለአስጎብኚ ጉብኝት ቦታ የሚከፈል ፣ የመጠመቂያ ልብስ)
አዘጋጅ :- የ/ደ/ገ/ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት ከ ዮድ አቢሲኒያ አስጎብኚ እና የጉዞ ወኪል ጋር በመተባበር
ስልክ :- 0921899103/0946817753/091 3734590/0910067211
🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
💚💛❤️ፍጡነ ረድኤት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና አድዋ ድል 💚💛❤️
..........አንድ ጣልያናዊ ተዋጊም ‹‹በነጭ ፈረስ ተቀምጦ ወደ ቀኝና ወደ ግራ እየተመላለሰ ወደ ጦርነቱ ግቡ ኢጣሊያኖችን ማርኩ እያለ ትእዛዝ ሲሰጥና ሲዋጋን የዋለ ማነው?›› ብሎ መጠየቁ እየተገለጸ የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ አጋዥነት መገለጹም እዚህ ላይ መነሣት የሚገባው ነው። (በአድዋጦርነትና ድል…፣፶፫)። ይህንንም በአንድ ባለ ቅኔ፡- ‹‹ኃይል ውእቱ ዘጊዮርጊስ፣ አኮኑ ኵዕናት በላዔ ሮማዊት ነፍስ፣ ዘጌዴዎን ምኒልክ ዘአውረደ በዐውደ ሮምያ ጠለ ደም እምርእስ። (በአድዋ ጦርነትና ድል…፣ ፶፪)። (የሮማዊትን ነፍስ (ሰውነት) የበላ (ድል ያደረገ) የጊዮርጊስ ኃይል እንጂ ጦር አይደለም፣የጌዴዎን ምሳሌ ምኒልክ በሮምያ አደባባይ ከራስ ላይ እስካወረደ ጠብታ ደም።) ተብሎ የተነገረ ነው። የአድዋ ድል ብሔራዊና ዓለም ዐቀፋዊ ትሩፋቱ ባሻገር ሃይማኖታዊ ትሩፋቱም መነገር የሚገባው ነው።
እንኳን ለታላቁ ሰማዕት የኢትዮጵያ ገበዝ ለሊቀ ሰማዕታት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ!!!
ቤተክርስቲያን ለአድዋ ድል የነበራትን አስተዋጽዖ በድኅረ ገጻችን ላይ ያንብቡ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉ቅዱስ ጊዮርጊስና የአድዋ ድል👈
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ
✨የብርሃን እናቱ ሆይ ካንቺ በነሳው ስጋ እኛነታችንን አከበረ፡፡መዐዛሽ ስቦት አንችን በወደደ ጊዜ ድኅነታችን ተሰራ፡፡
✨ድንግል ሆይ እውነተኛው የሕይወት እንጀራ : ጣፋጩን የነፍስ መጠጥ አማናዊው የፅድቅ ብርሀን የፈነጠቀብሽ ነሽና ከትውልድ መሀል ብፅዕናሽን እንናገራለን፡፡
✨ጥማችንን የቆረጠ ጥዑም ወይን፡ረሀባችንን ያጠፋ እውነተኛው መብል ካንቺ ወጥቶልናልና እንወድሻለን፡፡
✨ምስራቃዊት በራችን ሆይ ከሴቶች አንችን የሚመስል የለም፡፡ባንቺ ላይ ስለተደረገልን ታላቅ ነገር ዛሬም ለዘላለምም ስምሽን እናገናለን፡፡
✨ዝምተኛይቱ ድንግል ሆይ አንቺ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ የአይሁድ ሴቶች አይደለሽም።በትሕትና ተልመሽ በንፅሕና አጊጠሽ የባህርያችንን መመኪያ ያስገኘሽልን የፅድቅ በራችን ነሽ።
✨አንችን ማመስገን የነፍስ ምግብ የህሊና እርካታ ነው።ስናመሰግንሽ እናርፋለን ስናርፍ እናመሰግንሻለን።ክብርሽ ከሰማይ ምስጋናሽም ከአርያም ነውና አንችን ለማመስገን ልቦናችን ይብራ።
✨ኦ ማርያም በእንተዝ ናፈቅረኪ ወናዐብየኪ እስመ ወለድኪ ለነ መብልዐ ፅድቅ ዘበአማን ወስቴ ሕይወት ዘበአማን
/channel/EMislene
ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያን ህልውና በላይ የሚያስቀድመው አንዳች ነገር የሌለ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን የገጠማትን ፈተና ለማለፍ የሚጠበቅበትን መንፈሳዊ ግዴታ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ትላንት የካቲት 19/2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።
ማኅበሩ በመግለጫው የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን መንፈሳዊ አንድነት የጠየቀ ሲሆን "ቤተ ክርስቲያንን በማይጠቅማት ጉዳይ የግል ፍላጎትንና ምድራዊ ዓላማን መሠረት አድርገው ከቤተ ክርስቲያን ሕግና ቀኖና ውጭ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊን ለመተካት፣ ፓትርያርክ ለመሾምና የመሳሰሉትን ለመፈጸም" የሚንቀሳቀሱ ያላቸውን "አንዳንድ አባቶች" ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በማሳሰብ ጉዳዩንም በመከታተል መረጃውን ለምእመናን አደርሳለሁ ብሏል።፡፡
ይመለከታቸዋል ላላቸው ሌሎች የቤተ ክርስቲያን አካለትም ጥሪውን አስተላልፏል።
1. የተከበራችሁ አበው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሆይ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ “በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፡፡ እንዳለ በዚህ ታላቅ የፈተና ወቅት የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለማስጠበቅ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጣችሁን ኃላፊነት ለመወጣት ምእመናንን አቅጣጫ በመስጠት የቀደሙ አባቶቻችሁን ፈለግ በመከተል ዛሬም በጽናት እንድትተጉ፤ ያከበረቻችሁን ቤተ ክርስቲያን በአንድነት ሆናችሁ እንድትጠብቁ በልጅነት መንፈስ በትሕትና እንጠይቃለን፡፡ በተጨማሪም የአባትነት የዋህ ልቦናችሁን በመጠቀም ያዘኑ፣ የጠቀሙ፣የተቆረቆሩ መስለው ቀርበው የግል ፍላጎታቸውን ለመፈጸም የሚጥሩ ስለሚኖሩ ሁሉንም በጥንቃቄ እንድትመረምሩ፤ቀኖች ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን በመዋጀት አንድነታችሁን እንድታጠነክሩና በቤተክርስቲያን ዙሪያ ስለሚፈጠሩ ችግሮች በጥልቀት እንድትወያዩና እንድትመካከሩ እናሳሰስባለን።
2. ከዚህ ውጭ ቤተ ክርስቲያንን በማይጠቅማት ጉዳይ የግል ፍላጎትንና ምድራዊ ዓላማን መሠረት አድርጋችሁ ከቤተ ክርስቲያን ሕግና ቀኖና ውጭ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊን ለመተካት፣ ፓትርያርክ ለመሾምና የመሳሰሉትን ለመፈጸም የምትንቀሳቀሱ አንዳንድ አባቶች ከድርጊታችሁ እንድትታቀቡ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ ማኅበራችን ይህንን ጉዳይ እየተከታተለ መረጃውን ለምእመናን የሚያደርስ መሆኑንም በዚሁ አጋጣሚ እንገልጻለን፡፡
3. ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ መምህራነ ወንጌል፣ ካህናት ሆይ በጸሎትና በትምህርት ምእመናንን በማጽናናት፤ ከእውነት ጋር በመቆም እውነታውን በማሳየት ምእመናን ለቤተ ክርስቲያን ዘብ እንዲቆሙ በማድረግ ድርሻችሁን እንድትወጡ እናሳስባለን።
4. ውድ ምእመናንና የማኅበራችን አባላት የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ በዚህ ዘመን ቤተ ክርስቲያንን ከአሳዳጆቿ የመጠበቁ ዋነኛ ኃላፊነት በዘመኑ ባለን ብፁዓን አባቶች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርሰቲያን፣ ካህናትና ምእመናን ሁላችን እጅ ላይ ወድቆአል፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ ለአባቶችና ለካህናት ትተን “እኔ አያገባኝም፤ አይመለከተኝም” ልንል አይገባም፡፡ ሁሉም በየድርሻው ቤተክርስቲያኑን ለመጠበቅ መትጋት አለበት፡፡ በቤተ ክርስቲያን ላይ የደረሰውን ጥፋትና ሊመጣ ያለውን ፈተና አስቀድሞ በመረዳት ቅዱስ ሲኖዶስ ቀደም ሲል በወሰነው መሠረት በየአጥቢያችን፤ በተለያየ መልኩ በመደራጀት፤ በቤተክርስቲያን ላይ ጥፋት ለማድረስ የሚመጡትን በመከላከል የቤተ ክርስቲያንን ስደት ለማስቆም መንፈሳዊ ግዴታችንን እንድንወጣ እንጠይቃለን፡፡
5. በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በልዩ ልዩ አገልግሎት እየተሳተፋችሁ ያላችሁ ሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ ማኅበራትና ሌሎችም ሁላችንም አንድነታችንን በመጠበቅ በጋራ አገልግሎቶችን በመፈጸም ድርሻችንን እንድንወጣ ለተግባራዊነቱ ጥሪ እናቀርባላን፡፡
6. ገዳም ድረስ ገብቶ መሣሪያ ያልያዙና: ራሳቸውን እንደሞቱ ቆጥረው እየኖሩ ያሉ መነኮሳት ላይ ግድያ የፈጸመ ማንኛውም የታጠቀ ኃይል (መደበኛም ይሁን ኢመደበኛ: በግልም ይሁን በቡድን: አማኝም ይሁን ኢአማኝ) ድርጊቱ ከሰውነት ተፈጥሮ የወጣ ነው፡፡ ምናኔንና የክህነት ክብርን በተቃረነ መልኩ ሰብእና የጎደለው ጥቃት ማድረስ ኢትዮጵያዊ ባህልም አይደለም፡፡ ጥቅም የሌለው ከንቱ ተግባር ነው፡፡ በዚህ የሚገኝ የፖለቲካ ትርፍ ይኖራል ብለን አናምንም፡፡ ጤነኛ በሆነ አእምሮ ታስቦ የተፈጸመ ነው ማለትም አይቻልም፡፡ ማስተዋል ተወስዶባቸው እውቀት ተሰውሮባቸው እንጂ ይህንን ማድረግ ቀርቶ ማሰቡም የሙት ሐሳብ ነው፡፡ ቀድሞ የሞተው ሟቹ ሳይሆን ገዳዩ ነው፡፡ በዚህ መንገድ የቤተ ክርስቲያን አማኞች ሲበዙ እንጂ ሲያንሱ በታሪክ አልታየም:: ይህ ድርጊት ክርስቲያኖችን ሲያጠነክር እንጂ ሲያዳክም ታይቶ አይታወቅም፡፡ መጽሐፍ “ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንን ቤት ገፋው በዓለት ላይ ስለተመሠረተ አልወደቀም ” ባለው መሠረት ቤተክርስቲያን በጽኑ ዐለት ላይ የተመሠረተች ስለሆነ አታሽነፏትም። ዲዮቅልጥያኖስም አላጠፋትም:: ዲያብሎስም ዝናሩን እንዲሁ ጨረሰ:: ስለዚህ አትድከሙ: አትሳቱም እናንተ ሳትወለዱ የነበረች ቤተ ክርስቲያን እናንተ አልፋችሁም እንደ እናንተ ላሉት በስሑት መንገድ ለሚጓዙት ሁሉ እየጸለች ትቀጥላለች:: ሐሳቧም፣ ሥራዋም፣ ዓላማዋም፣ ግቧም ሰማያዊ ነውና።
በመጨረሻም ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያን ህልውና በላይ የሚያስቀድመው አንዳች ነገር የሌለ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን የገጠማትን ፈተና ለማለፍ ከሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያን አካላት ጋር በመናበብ የሚጠበቅበትን መንፈሳዊ ግዴታ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን በዚሁ አጋጣማ እያሳወቅን፥ የሁላችንም የመሰባሰብና የአገልግሎት ማእከል ቤተ ክርስቲያን በመሆኗ ከሁሉም ነገር በፊት ቅድሚያ ሰጥተን ሊመጣ ካለው አደጋ ቤተ ክርስቲያናችንን የመጠበቅ ኀላፊነት በትጋት እንወጣ ሲል ማኅበረ ቅዱሳን በመግለጫው ጥሪ አቅርቧል፡፡
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
✨ የነነዌ ሰዎችና እኛ ✨
ከነነዌ ሰዎች በላይ ማን ክፉ ነበር? ከእነርሱ በላይ አላዋቂስ ማን ነበር? ("ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ" ተብለው ተጠርተዋልና፡፡) ነገር ግን እነዚህ አሕዛብ፣ እነዚህ አላዋቂ፣ እነዚህ አንድ ሰውስ እንኳን የጥበብን ነገር አስተምሮአቸው የማያውቁ፣ እነዚህ ከማንም ይኹን ከማን እንደዚህ ዓይነት ትእዛዝን ያልተቀበሉ ሰዎች ነቢዩ፡- “በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች” ሲል በሰሙት ጊዜ ክፉ ልማዳቸውን ኹሉ በሦስት ቀናት ውስጥ አስወግደዋል (ዮና.3፥4)፡፡
ዘማዊው ንጹህ፣ ደፋሩ ትሑት፣ ስስታሙና ጨቋኙ ራሱን የሚገዛና ደገኛ፣ ሐኬተኛውም ትጉህ ኾነ፡፡ እነዚህ ሰዎች በርግጥ ያሻሻሉት ክፋታቸውን ኹሉ እንጂ አንዱን ወይም ኹለቱን ወይም ሦስቱን ወይም አራቱን አይደለም፡፡ “እንዲህ የሚልስ የት አለ?” ብሎ የሚጠይቅ ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ እኔም እንዲህ ብዬ እመልስለታለሁ፡- እነርሱን ሲወቅሳቸው የነበረውና፣ “የክፋታቸውም ጩኸት እስከ አርያም ድረስ ወጥቷል” ብሎ የተናገረው ነቢይ መልሶ ደግሞ የዚሁ ፍጹም ተቃራኒ የኾነን ምስክርነት አስቀምጧልና፤ እንዲህ ሲል፡- “እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደ ተመለሱ ሥራቸውን አየ” (ዮና.1፡5፣ 3፡10)፡፡ ተመልከት! ከዝሙት ወይም ከአመንዝራነት ወይም ከሌብነት ራቁ አላለም፤ “ከክፉ መንገዳቸው” እንጂ፡፡ እንዴትስ ከዚያ ሊርቁ ቻሉ? ይህን እግዚአብሔር ያውቋል እንጂ ሰው ሊመረምረው አይችልም፡፡
እንግዲህ አሕዛብ በሦስት ቀናት ውስጥ ብቻ ክፋታቸውን ኹሉ ማስወገድ ከቻሉ፥ ለአያሌ ቀናት የተመከርንና የተዘከርን እኛ ግን አንዲት ክፉ ልማድን [ለምሳሌ መሐላን] ሳናስወግድ ስንቀር ልናፍር አይገባንምን? ከዚህም በላይ እነዚህ ሰዎች ቀድሞ ክፋታቸው ጣሪያ ደርሶ ነበር፤ “የክፋታቸውም ጩኸት እስከ አርያም ድረስ ወጥቷል” የሚለውን ስትሰማ ከክፋታቸው ብዛት በቀር ሌላ ምንም ልትገነዘብ አትችልምና፡፡ ነገር ግን በሦስት ቀናት ውስጥ ወደ መልካም ምግባር ፍጽምና መድረስ ተችሏቸዋል፡፡ ፈሪሐ እግዚአብሔር ባለበት ቀናት ወይም የጊዜ ብዛት አያስፈልግምና፡፡ በተቃራኒው ይህ ፍርሐት በሌለበት ደግሞ የጊዜ ብዛት ምንም ጥቅም የለውም፡፡
የዛጉ ብረቶችን በውኃ ብቻ የሚያጥባቸው ሰው ምንም ያህል ጊዜ እነርሱን በማጠብ ቢያሳልፍም እነዚያን ዝገቶች ኹሉ ማስለቀቅ አይቻለውም፡፡ ወደ እሳት ጨምሮ የሚያወጣቸው ሰው ግን አዲስ ከተሠሩ ብረቶችም ጭምር ሳይቀር እጅግ ጽሩያን ያደርጋቸዋል፡፡ በኃጢአት የዛገ ልብም እንዲሁ በትንሽ በትንሹና በግድየለሽነት ኾኖ ዕለት ዕለት ንስሐ ቢገባም ምንም ጥቅም አያገኝም፡፡ ራሱን ወደ እቶን - ይኸውም ወደ ፈሪሐ እግዚአብሔር የሚጥል ከኾነ ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ ኹሉንም ማስወገድ ይቻለዋል፡፡
(በእንተ ምክንያተ ሐውልታት፥ ፳:፳፩ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው)
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ!!
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
✨ ትዕቢተኞችን በታተናቸው ✨
✨ ልዩ የአድዋ የኪነ ጥበብ ምሽት ✨
📌በደብረ ገሊላ ቅዱስ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰ/ት ቤት
📅 ሐሙስ የካቲት 21 /2016
⏰ 11፡30 ጀምሮ
📌በሰንበት ትምህርት ቤቱ አዳራሽ።
መግቢያ :- 50 ብር
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ
🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
"ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለሃይማኖት ቤተሰቦች መልካም እናድርግ" ገላ 6፥10
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000397123964 (ዮናስ አበራ)
አቢሲኒያ ባንክ 22535927 (ዮናስ አበራ)
ለበለጠ መረጃ ፡
📱0910 85 82 19
📱0913 72 00 15 ላይ ይደውሉ።
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ!!!
🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.comS/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
👉ለመብልነት የምንጠቀመውን ሥጋ ከክርስቲያን ሥጋ ቤት ለምን እንገዛለን❓
👉ጾም የእግዚአብሔር ጊዜ ነውን❓
👉ጾመ ነነዌ ለምን ይጾማል❓
👉እኛ ከነነዌ ሰዎች ምንን እንማራለን❓
👉ለወጣቶች ራስንና ልብን ስለመጠበቅ
👉የማኅበረ ሥላሴ ገዳምን መስርተው እንደ መሶበ ወርቅ ከፍ አድርገው ያስባረኩት ታላቅ አባት ማናቸው? መች ይታሰባሉ?
👉ቤተ ክርስቲያን የጦርነት የድል በዓልን ለምን ታከብራለች❓
👉ፍጡነ ረድኤት ቅዱስ ጊዮርጊስና የአድዋ ድል
👉የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ታሪክ
👉ሰንበት ት/ቤት እንዴት ተመሰረተ❓
👉ተአምረ ማርያም- ዘከመ ነሥአት ኪዳነ ምሕረት እምኃበ ወልዳ
👉ተረት ተረት
👉የመዝሙር ግጥም
👉ወግና ሌሎችንም
በቅጽ 1 ዲጂታል መጽሔታችን ይጠብቁ....
የቴሌግራም ቻናል
/channel/EMislene
📎ነፍሴን የት ልውሰዳት
“አጥብቄ ፈለግሁ . . . ደከምሁ፤ እጅግም ባዘንሁ፤ ዙሪያ ገባውን ሁሉ እየቃኘሁ የዓለምን ዳርቻዎች ሁሉ አማተርሁ፤ . . . ነገር ግን ነፍሴን እፎይ ብዬ አሳርፋት ዘንድ እሸሸግበት ጥግ አጣሁ የደከመ መንፈሴን ሰላም አሰፍንበት ዘንድ ማረፊያ ወደብ አጣሁ . . አዎ እጅግ ባተትሁ ነፍሴን ከደካማው ሥጋዬ እሥር አላቅቄ ነጻነትን አጎናጽፋት ዘንድ ማረፊያው የሥጋ ሸክም ማራገፊያው ከቶ ወዴት ነው? “ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል” (ማር. ፰፥፴፮) እንዲል ቅዱስ መጽሐፍ በዚህ ምድራዊ ዓለም የሚዳሰስ፣ የሚላስ፣ የሚቀመስ ይጣፍጥ ዘንድ ግን ከቶ በማይቻለው የዓለም ግሳንግስ የተወረረችና ዝላ የደከመች ነፍሴን ምኞት፣ ዝሙትና ፍቅረ ንዋይ የተሰኙ ወንበዴዎች ደብድበው ያቆሰሏትን ድኩም ነፍሴን ዘይቱን አፍስሶ ቁስሌን ወደሚያክምልኝ ያ ደግና ርኅሩኅ ሳምራዊ አደርሳት ዘንድ ከቶ የት ልሂድ፡፡” (ሉቃ. ፲፥፴፫) እያሉ አባ ሞገሴ ረዘም ባለ ንግግራቸው ድምፃቸውን ጎላ አድርገው ያወራሉ፡፡
አባ ሞገሴ ከሰው ጋር ያሉ መስሎኝ ትቻቸው ልሄድ ስል ብቻቸውን ናቸው። አመማቸው እንዴ ብዬ ልጠይቃቸው ስል ዐይናቸውን ወደሰማይ ቀና አድርገው ከነበሩበት ስሜት ማንም የሚያናውጻቸው ያለ አይመስልም። አባ ሞገሴ በአንድ ታዋቂና ታላቅ ደብር ጸሎት አሳራጊ አባት ናቸው። በዚህ ታላቅ ደብር ቄሰ ገበዝ ሆነው ለረጅም ጊዜ ካገለገሉ በኋላ የጸሎት አሳራጊ አባት እንዲሆኑ በካህናቱ ፈቃድ ከሰሞነኛነት ተለይተው የሚኖሩ አባት ናቸው። ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ቅዱስ አባት ለአርባ ዓመት ቆመው የጸለዩበት ቦታ ነው ከሚባል ጫካ ቆመው እየጸለዩ ነው። እኔም ስሜታቸውን ከምረብሽ በጽሞና ማዳመጡና ከጸሎታቸው በረከት መቀበሉ የተሻለ ነው ብዬ ማዳመጥ ጀመርሁ። አባ ከብሉያት ከሐዲሳት እየጠቃቀሱ ልመናቸውን ቀጠሉ።
ሰው መሆንን እና የሰውነትን ልክ በሚበላና በሚጠጣ በሚግብሰበስ ከንቱና ሕይወት የለሽ በድን በሆነ መስፈሪያ የሚመዝን ዓለም የታከተች ብኩን ነፍሴን አሳርፋት፤ ሰላም እሰጣት ዘንድ የት ልሂድ የት ልድረስ ፡፡ ታላቁን ቅዱስ መጽሐፍ ባገላበጥሁ ጊዜ
👉ሙሉውን ያንብቡ
📖ስለ እርሱ አንብቡ !
እግዚአብሔር በሃሳባችሁ ውስጥ እንዲኖር ስለ እርሱ አብዝታችሁ አንብቡ ።
እርሱን ለማወቅ ስለ እርሱ አንብቡ ። እርሱን ካላወቃችሁት እንዴት እርሱን ልትወዱት ትችላላችሁ ?
ስለ እርሱ አንብቡ ፤ ስታነቡ ግን በሳይንሳዊ ወይም በፍልስፍና ጠባይ አታንብቡ ወይም ደግሞ ስለ እርሱ ጥናታዊ ጽሑፍ ወይም ትምህርት ለመስጠት አታንብቡ ። ነገር ግን ወደ እርሱ ጥልቀት ለመግባት ወይም እርሱ ወደ እናንተ ጥልቀት እንዲገባ አንብቡ .. ለነፍሳችሁ ውድ የሆኑትን የእርሱን ባሕርያት ለማወቅ ስትሉ አንብቡ ይህ እውቀት አሳባችሁ ከእርሱ ጋር እንዲጣበቅና ፍቅሩ ከእናንተ ልብ ጋር እንዲቀናጅ ያደርግላችኋልና ። ስለ ስምምነቱ ስትሉም አንብቡ ። ከወደዱት ሰዎች ጋር ስላለው ግንኙነት በጠላቶቹ ላይ ስላለው አቋም ስትሉ አንብቡ ! በጽሑፎች ውስጥ ስለ እርሱ " ውበትህ ከሰው ልጆች ይልቅ ያምራል ..." [ መዝ 44፡2] የሚለውን ቃል በማንበብ የእርሱን ውበት ታውቁ ዘንድ አንብቡ ።
እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቀምሳችሁ ታዩ ዘንድ ስለ እርሱ አንብቡ ። ታዲያ ንባባችሁ ለልባችሁ ምግብ እንዲሆን እንጂ እንዲሁ ተራ ንባብ እንዲሆን አትፍቀዱ ።
ስለ እግዚአብሔር ብዙ ካነበባችሁ በእርሱ ዘንድ ያለውን ፍጹምነት በሙሉ ታገኛላችሁ ። እርሱን ስለምትወዱትም በሰለሞን መዝሙር ውስጥ ካለችው ድንግል ጋር አብራችሁ "...እርሱ ፈጽሞ ያማረ ነው " [ መኃ 5፡16] ትላላችሁ ።
ከወደዳችሁት ስለ እርሱ ማንበባችሁን ትቀጥላላችሁ ። እግዚአብሔር ስለ እርሱ የሚያነቡትን ስለ እርሱ ዜና የሚጠይቁትን ከእርሱ ታሪኮች መካከል አንዱን ለማወቅ የሚናፍቁትንና እርሱን የሚያደንቁትን ሰዎች ይወዳቸዋል ። ስለ እርሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ወይም ከአባቶች ብሒሎች ወይም ከቤተክርስቲያንና ከቅዱሳን ታሪክ ልታነቡ ትችላላችሁ ። በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የእግዚአብሔር እጅ ለመዳሰስ ስትሞክሩ በጥበቡ በኃይሉና በርኅራኄው ውስጥ እንደምትወዱት ታውቃላችሁ ።
✍አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ !!
የቴሌግራም ቻናል
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
"ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለሃይማኖት ቤተሰቦች መልካም እናድርግ" ገላ 6፥10
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000397123964 (ዮናስ አበራ)
አቢሲኒያ ባንክ 22535927 (ዮናስ አበራ)
ለበለጠ መረጃ ፡
📱0910 85 82 19
📱0913 72 00 15 ላይ ይደውሉ።
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ!!!
🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.comS/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
አቡነ አምደ ሥላሴ
አቡነ ዓምደ ሥላሴ የተወለዱት ጎጃም ሲሆን በአጤ (ዐፄ) ሱስንዮስ ዘመን የነበሩ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ያደርጉ የነበሩ ገዳማዊ መነኵሴ ናቸው፡፡
ጻድቁ ማኅበረ ሥላሴን ያቀኑ ታላቅ አባት ሲሆኑ በተለይም አንድ የሚታወቁበት ትልቅ ታሪክ አላቸው፡፡ እርሱም አጤ (ዐፄ) ሱስንዮስ ካቶሊካውያን ደግፈው 8ሺህ የአገራችንን ሊቃውንት በአንድ ቀን ባሳረዱ ጊዜ ንጉሡ ወዲያው "ኦርቶዶክስ ይርከስ ካቶሊክ ይንገስ" ብሎ ያወጀበት ምላሱ ተጎልጉሎ ወጣ፡፡ እንደ አርዮስም ሆዱ አብጦ አንጀቱ ተልቶ ሊሞት ባለ ሰዓት አቡነ ዓምደ ሥላሴ አዘዞ ድረስ ሄደው "ፋሲል ይንገሥ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ትመለስ የሱስንዮስም ምላስ ይመለስ" በማለት ተጎልጉሎ የወጣውን ምላሱን በመስቀላቸው ቢባርኩት ምላሱ ተመልሶለታል፡፡
አጤ (ዐፄ) ሱስንዮስ ግን ለካደበት ክህደት ቅጣቱ ነውና በመቅሰፍቱ ሳይድን በዚያው ታሞ ማቆ ማቆ ክፉ አሟሟት ሞቷል፡፡ ከዚህ በኋላ አቡነ ዓምደ ሥላሴ የአጤ (ዐፄ) ፋሲልን ሹመትና ሃይማኖትን በአዋጅ፡አጽንተው ተመልሰው ወደ ገዳማቸው ማኅበረ ሥላሴ ገዳም ገብተዋል፡፡
አጤ (ዐፄ) ፋሲልንም የማኅበረ ሥላሴን ገዳም ግዛቱን ከሱዳን እስከ ጣቁሳ ድረስ እንዲሆን በአዋጅ ወስነው ሰጥተውት እንደነበርና በደግ መንግስት እንደተወሰደ ይነገራል።
በደርቡሾች ወረራ ጊዜ እንግሊዞች አጋጣሚውን ተጠቅመው የአቡነ ዓምደ ሥላሴን ቅዱስ ገድል ዘርፈው በመውሰዳቸው ገድላቸው በእንግሊዝ አገር ይገኛል፡፡
ጻድቁ የካቲት27 ቀን ያረፉ ሲሆን ዐፅማቸው በዚያው በመሠረቱት በማኅበረ ሥላሴ ገዳም በክብር ተቀምጧል፡፡
ከአቡነ ዓምደ ሥላሴ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸው ይማረን!።
ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን
/channel/EMislene
🎙በደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል
እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የተከታታይ ትምህርት ተማሪዎች ( ቀዳማይ፣ ካልዓይ ፣ሣልሣይ) መንፈሳዊ የአንድነት ጉዞ ወደ ምስር ምድር ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም ባሳለፍነው እሑድ፥ የካቲት 24 ቀን ተከናወነ።
በዕለቱም የተለያዩ መርሐ ግብራት የተካሄዱ ሲሆን በመጨረሻም ለገዳሙ ተማሪዎች አስተዋጽዖ በማበርከት መርሐግብሩ ተጠናቋል።
📷የካቲት 24/2016 ዓ.ም
ምስር ምድር ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም
"ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ"
/channel/EMislene
🎙 የዝክረ አድዋ መርሐግብር በደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት ተካሔዷል። በእለቱም በዓሉን የሚያወሱ የኪነጥበብ መርሐግብራት ለታዳሚዎች ቀርበዋል።
🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
✨ ትዕቢተኞችን በታተናቸው ✨
✨ ልዩ የአድዋ የኪነ ጥበብ ምሽት ✨
📌በደብረ ገሊላ ቅዱስ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰ/ት ቤት
📅 ሐሙስ የካቲት 21 /2016
⏰ 11፡30 ጀምሮ
📌በሰንበት ትምህርት ቤቱ አዳራሽ።
መግቢያ :- 50 ብር
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ
🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
📌እየጾሙ አለመጾም
ተወዳጆች ሆይ! እየጾሙ የጾምን ፍሬ ፃማ የማያገኙበት ኹኔታ እንዳለ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያላችሁኝ እንደ ኾነም፦
👉ከምግበ ሥጋ ተከልክለን ከምግበ ኃጢአት ያልተከለከልን እንደ ኾነ፣
👉 ከጥሉላት ርቀን ነዳያንን ያልጎበኘን እንደ ኾነ፣
👉 ወይን ከመጠጣት ታቅበን በክፉ መሻት ከመስከር ያልራቅን እንደ ኾነ፣
👉 ጀምበር እስክትጠልቅ ድረስ ከእኽል ከውኃ ርቀን በዓይናችን መልካም ያልኾኑ ትእይንቶችን ከማየት ያልጾምን እንደ ኾነ ነው ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እመልስላችኋለሁ፡፡
ስለዚህ እየጾሙ እንዲህ አለመጾም እንዳለ ዕወቁ፤ ተረዱም፡፡
✍ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
("ንስሐ እና ምጽዋት" ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ፡፡)
የበረከት ጾም ይሁንልን።
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
የነነዌ ጾም
እግዚአብሔር አምላካችን ወዶ እና ፈቅዶ ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ለሆነው የነነዌ ጾም አድርሶናል፡፡ ሦስት ቀናት የሚጾመው ይህ ጾም የነነዌን ሕዝብ ከጥፋት መመለስ፣ የእግዚአብሔርን ምሕረት እንዲሁም የነቢዩ ዮናስን የዋህነት ያስረዳናል፡፡
በዚያን ዘመን የነነዌ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት የተወገዙ ተግባራትን ይፈጽሙ ነበር፤ ለጣዖታት መስገድና መሠዋት፣ ጥንቆላን ማስፋፋት፣ ሥር እየማሱ ቅጠል እየበጠሱ የሰዎችን አኗኗር ማጎሳቆልና ማዘበራረቅ፣ በዘፈን፣ ስካር፣ በዝሙትና ሌሎች የሥጋ ፈቃዳትን በራስና በሌሎች ላይ መፈጸምም የተለመደ ምግባራቸውም ነበር፡፡ (ገላ ፭÷፲፯-፲፱)
በዚህም ጊዜ እግዚአብሔር አምላክ በእነርሱ ተቆጥቶ የነነዌን ከተማ ሊያጠፋት ቀረበ፤ ሆኖም ግን የፈጣሪ ቸርነትና ምሕረት አያልቅምና በንስሓ ይመለሱ ዘንድ ነቢዩ ዮናስን ወደ እነርሱ ላከው፡፡ ‹‹ተነስተህ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ የክፋታቸውም ጩኸት ወደ ፊቴ ወጥቶአልና ለእነርሱ ስበክ›› አለው፡፡ ነቢዩ ዮናስ ግን ይህን አምላካዊ ትእዛዝ ሳያከብር ከአምላኩ ይሸሽ ዘንድ ወደ ተርሴስ ተነሣ፤ ወደ ኢዮጴም ወረደ፡፡ እንደ ስሙ ርግብ የዋህ የሆነው ዮናስ በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች ብሎ ካስተማረ በኋላ አምላክ መሐሪ ነውና ቢምራቸው ሐሰተኛ እንዳይባል ፈርቶ ከአምላክ መሸሽን መረጠ፡፡ እዚህ ጋር ልናስተውለው የሚገባው ነቢዩ ዮናስ ለመሸሽ የመረጠበትን ምክንያት ነው፡፡
የእርሱ ጭንቀት ‹‹ዛሬ ነነዌ ትጠፋለች ብዬ ሳትጠፋ ብትቀር ወደፊት ማን ለቃሉ እና ለትንቢት ይገዛል፤ ነቢያተ እግዚአብሔርንስ ማን ያደምጣል፤ ማንስ ያከብራቸዋል›› የሚል ነው፡፡ ለአምላኩም ያለው ቀናኢነት እና ጭንቀት እስከ አለመታዘዝ እና መኮብለል አደረሰው፡፡ (ዮና. ፩፥፪) ወደ ተርሴስም የምታልፍ መርከብ አግኝቶ ተሳፈረ፤ በመርከቡ ላይ እያለም እግዚአብሔር መርከቧን በማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡
ከዮናስ ጋር ተሳፍረው የነበሩ ነጋድያንም ያላቸውን ሀብት ወደ ባሕሩ መጣል ጀመሩ፤ በዚህ ጊዜ ዮናስ በእርሱ ጥፋት ምክንያት ማዕበሉን መነሣቱን በመረዳት ‹‹ማዕበሉ በእኔ ምክንያት የመጣ ስለሆነ ንብረታችሁን ሳይሆን እኔን ወደ ባሕር ጣሉኝ›› አላቸው፡፡ እነርሱም ‹‹ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ፣ ንጹሕም ደም በእኛ ላይ እንዳይደረግብን አይሆንም›› አሉ፡፡ ወደ ባሕሩ ለመጣል ዕጣ በተጣጣሉ ጊዜም ዕጣው በዮናስ ላይ ስለ ወጣ ነጋድያኑ ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ከመቅጽበትም ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን ዋጠው፤ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊትም በእርሱ ውስጥ ተቀመጠ፤ በዓሣ አንባሪው ሆድ ውስጥም ሆነም ወደ እግዚአብሔር ይጸልይ ነበር፡፡ በሦስተኛውም ቀን ዓሣ አንባሪው ዮናስን ከባሕሩ ዳርቻ ወስዶ ተፋው፡፡
ዮናስም ነነዌ መድረሱን ባወቀ ጊዜ ከእግዚአብሔር መሸሽ አለመቻሉን ተረድቶ ወደ ከተማው በመሄድ የነነዌ ሰዎችን ንስሓ እንዲገቡ ይሰብክ ጀመር፡፡ ‹‹ዮናስም ተነሥቶ እንደ እግዚአብሔር ቃል ወደ ነነዌ ሄደ፤ ነነዌም ታላቅ ከተማ ነበረች፤ የቅጥርዋም ዙሪያ በእግር የሦስት ቀን መንገድ ያህል ነበር፡፡ ዮናስም የአንድ ቀን መንገድ ያህል ወደ ከተማዪቱ ውስጥ ሊገባ ጀመረ፤ ጮኾም፥ በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች›› እንዲል፡፡ (ዮና. ፩፥፲፪፣ ፫፥፫)
የነነዌ ሰዎችም ቃሉን ሰሙ፤ ‹‹የነነዌ ሰዎችም እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም አዋጅ ነገሩ፤ ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ፤ንጉሡም ከዙፋኑ ተነሥቶ መጎናጸፊያውን አውልቆ ማቅም ለበሰ፤ በአመድም ላይ ተቀመጠ›› ተብሎ እንደተነገረም ንስሓ ገቡ፤ እግዚአብሔር አምላክም ይቅር ብሎ ከጥፋት አዳናቸው፡፡ (ዮና. ፫÷፭-፮)
ነገር ግን ዮናስ በዚህ አልተደሰተም፡፡ የነነዌን መዳን አልተቀበለም፡፡ ሕዝቡም አስመሳይ እና ሐሰተኛ ነቢይ ነው ብለው እንዳይገምቱ ፈርቶ ነበር፡፡ ስለዚህም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ‹‹አቤቱ፥ በሀገሬ ሳለሁ የተናገርሁት ይህ አልነበረምን? አንተ ቸርና ይቅር ባይ፥ ታጋሽም፥ ምሕረትህ የበዛ፥ ከክፉው ነገርም የምትመለስ አምላክ እንደ ሆንህ ዐውቄ ነበርና ስለዚህ ወደ ተረሴስ ለመኰብለል ፈጥኜ ነበር፡፡ አሁንም አቤቱ! ከሕይወት ሞት ይሻለኛልና እባክህ! ነፍሴ ከእኔ ውሰድ፡፡ እግዚአብሔርም ዮናስን ፈጽመህ ታዝናለህን?›› አለው፡፡ (ዮና.፬፥፪-፬)
ከዚህ በኋላም ነቢዩ ዮናስ ከከተማ ወጣ፤ በምሥራቅ በኩል ትንሽ ዳስ ሠራ እና ከጥላዋ በታች ተቀመጠ፡፡
እግዚአብሔር ለከተማይቱ እንደሚራራ ወይም ለእርሱ ብሎ ያጠፋው እንደሆነ ለማየት ፈለገ፡፡ እግዚአብሔር ግን አንድ ቅል እንዲያድግ እና ዮናስን ከፀሐይ እንዲያስጠልለው አደረገ፡፡ ዮናስም ስለ ቅሉ እና ከጥላው በታች ስለተቀመጠበት ቦታ ተደሰተ፡፡ ሆኖም እግዚአብሔር አምላክ ዮናስ የተጠለበበትን ቅል ትል እንዲመታውና እንዲደርቅ አደረገ፡፡
በቀጣዩ ቀን ነፋስ እና ፀሐይ ዮናስን አሳቃየው፡፡ ይህም የእግዚአብሔር ትእዛዝ ነበር፤ ዳግምም ዮናስ ተስፋ በመቍረጥ ሞቱን ተመኘ፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለው፤ ‹‹አንተ ትበቅል ዘንድ ላልደከምክባት፥ ላላሳደግሃትም፥ በአንድ ሌሊት ለበቀለች፥ በአንድ ሌሊትም ለደረቀችው ቅል አዝነሃል፡፡ እኔስ ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ ከመቶ ሃያ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን?›› አለው፡፡ ነቢዩ ዮናስ ያኔ ወንዶች፣ ሴቶች እና ትናንሽ ሕፃናት ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ውድ መሆናቸውን፣ የእርሱን ሕልውና የማያውቁትን እንኳን እንደሚያውቃቸው ተረዳ፡፡ (ዮና.፬፥፲-፲፩)
እኛም ይህን ጾም እንደነነዌ ሰዎች ከልባችን ብንጾም ከእግዚአብሔር ይቅርታንና ምሕረትን ለማግኘት ይረዳናል፡፡ ከበደላችን ብንመለስ እና ንስሓ ብንገባ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ይቅርታና ምሕረትን የባሕርይ ገንዘቡ ስለሆነ ‹‹ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ይቅር እላችኋለሁ፤›› ብሎ ይቅር ይለናል፡፡ ከዚህም ባሻገር አሁን ካለንበት የችግር አረንቋ፣ ቸነፈር እንዲሁም ጦርነት ይታደገን ዘንድ በጾም እና ስግደት እንማጸነው፡፡
አምላካችን እግዚአብሔር ጾሙን በሰላም አስጀምሮ ያስጨርሰን፤ አሜን፡፡
በዲያቆን ፍቅረሚካኤል ዘየደ
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ
🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
✨✨✨የካቲት 16 የሚከበረውን የእናታችን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ዓመታዊ ክብረ በዓል በማስመልከት በኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተክርስቲያን በዋዜማው የሚቀርበውን እጅግ ጥልቅ ምስጢር የያዘውን ቃለ ማኅሌትና ዋይ ዜማን በአንድ ልብ በአንድ ቃል፡ለማመስገን ይረዳን ዘንድ ይህ ስርዓተ ማኅሌት እንደሚከተለው ቀርቧል።
📌 የዚህ ታላቅ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት የተዘጋጀው በደ/ገ/ ቅዱስ ዐማኑኤል የግቢ ባህል መሰረት በመሆኑ ግር እንዳይላችሁ እንላለን።
🌸 መልካም በዓል🌸
🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
ያከብርዋ ለሰንበት
ያከብርዋ ለሰንበት መላእክት
በሰማያት ጻድቃን በውስተ ገነት /2/
ወኵሉ ፍጥረት ዓሳት ወአናብርት
እለ ውስተ ደይን ያእረፉ ባቲ
እስመ ባቲ አእረፈ እምኩሉ ግብሩ
#ትርጉም
ያከብሯታል ሰንበትን መላእክት በሰማያት
ጻድቃን በገነት /2/
ፍጥረታት በሙሉ አሳዎችና አንበሪዎች
በመቃብር ያሉ ያከብሯታል አምላክ በእርሷ እንዳረፈ ከሥራው ሁሉ
መልካም ዕለተ ሰንበት🙏
/channel/EMislene2
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ
እግዚአብሔር ምስሌነን መሰባሰባችን አንተው!
📌እናስተዋውቃችሁ
የጮቢ መካነ ሕይወት በዓታ ለማርያም የአንድነት ገዳም
መካነ ሕይወት ጮቢ በዓታ ለማርያም አንድነት ገዳም የተመሠረተው በእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ በ፲፱፻፺፫ ዓ.ም. ነው፡፡ መሥራቹም የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ሣልሳዊ ናቸው፡፡ አሁን እየተጠራበት ያለውን ስያሜ ያገኘው ግን ሰኔ ፬/፲፱፻፺፰ ዓ.ም ነው፡፡ ዛሬ የሚታየው ልማት ከመምጣቱና ከመስፋፋቱ በፊት ቦታው ጠፍ እና ምንም የሌለበት የእርሻ መሬት ነበር፡፡
በወቅቱ ፭ እናቶች እና ሁለት አባቶች በጊዜው ቡታጅራ ማረሚያ ቤት ለእስር ከተዳረጉ እና የእስር ጊዜቸውን ጨርሰው በነጻ ከተለቀቁ በኋላ ወደ ሥፍራው በማቅናት አከባቢውን ሲቃኙ አስቀድሞ ቦታው ለእግዚአብሔር ማደሪያ የተመረጠ መሆኑን በመረዳት በእኒሁ አባቶች እና እናቶች ተነሣሽነት በብፁእ አቡነ ጎርጎርዮስ ሣልስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መልካም ፈቃድ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ፡፡
ለሐሳቡ እውን መሆን አቶ አማረ ዱቤ የሚባሉ የአከባቢው ነዋሪ እና የሀገር ሽማግሌ የሆኑ የአባቶችን ሐሳብ በመቀበል የራሳቸውን የእርሻ መሬት ለቤተ ክርስቲያኑ በመስጠት አሁን ያለችው የቤተ ክርስቲያን መቃኞ ሰኔ ፲፭/ ፲፱፻፺፭ ዓ.ም. ተጀምሮ በ፮ ወር ታንጾ ታኅሣሥ ፫ ቀን ፲፱፻፺፮ ዓ.ም. ተጠናቆ ቅዳሴ ቤቷ ተከበረ፡፡
በተለይ የገዳሙ አበ ምኔት መ/ር አባ ተ/ሥላሴ በሳል የአመራር ሰጪነት በአባ ገ/እግዚአብሔር እና አባ ኃ/ገብርኤል አጋዥነት የመጀመሪያ ተግባር የነበረው የገዳሙን ይዞታ ማስፋፋት ስለነበር እስከ ፲፱፻፺፰ ዓ.ም. ይህን ዐቢይ ተግባር በሰፊው ቀጥለውበታል፡፡ የገዳሙ ይዞታ ፹፩.፸፱ (ሰማንያ አንድ ነጥብ ሰባ ዘጠኝ) ሄክታር ሲሆን የይዞታ ማረጋገጫ ደብተርም ተሰጥቶታል፡፡ ወደ ፊትም ይዞታን የማስፋቱ ሥራ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ የእኒህ አባቶች ምኞት እና ራእይ ለትውልዱ አርዓያ የሚሆንና ለችግረኞች መጠጊያ ሊሆን የሚችል ገዳም መመሥረት በመሆኑ ከሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ጎን ለጎን ተግባር ቤት እና የእናቶች ማደሪያ ሠሩ፡፡
ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ገዳሙ፣ የገዳሙ መናንያንና ልማት የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ገጽታ ሆኑ፡፡
ገዳሙ የአንድነት ገዳም በመሆኑ ጠንካራ የአንድነት ሥርዓት አለው፡፡ በዚህ ገዳም ቁሪት (የግል ሀብት) አጥብቆ የተከለከለ ነው፡፡ በገዳሙ በምናኔ የሚኖርም ሆነ በእንግድነት የመጣ ማንኛውም ሰው የገዳሙን የአንድነት ስርዓት የማክበር ግደታ አለበት። ምዕመናን ወደ ገዳሙ ሲመጡ በመናንያን ላይ መሰናክል እንዳይሆኑ ክትትል ይደረግባቸዋል፡፡ የጠበልተኞች ማረፊያ ለብቻ የተዘጋጀ ሲሆን ወደ እናቶች ገዳም መግባት በጥብቅ ይከለከላል፡፡
ማንኛውም የማኅበር አባል ለግል ጉዳይ በልዩ ልዩ ምክንያትና ችግሮች ወደ ሌላ ቦታ ደርሶ ለመመለስ ያሰበ እንደሆነ አስቀድሞ መምህሩን ወይም መጋቢውን ወይም ሊቀ አርድዕቱን ማስፈቀድ ይኖርበታል፡፡ መናንያን ፫ ዓመት እና ከዚያ በላይ ገዳሙን ካገለገሉ በየዓመቱ በገዳሙ ወጪ ተሸፍኖላቸው ታሪካዊ ገዳማት በመጎብኘት ከበረከት እንዲሳተፉ ይደረጋል፡፡ ለእናቶችም ወርኃዊ የንጽሕና መጠበቂያ በወቅቱ ይሟላላቸዋል፡፡ ከአቅም በላይ ከሆነ ግን ወደ ገዳሙ አስተዳደር ቀርቦ ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡
ወደ ገዳሙ ለመግባት የሚፈልጉ መናንያን በገዳሙ ሕግና ሥርዓት መሠረት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኝ ሆኖ በሃይማኖቱ ሕጸጽ የሌለበት፣ በገዳሙ ደንብ ለመተዳደር ፈቃደኛ የሆነ፣ ከመጣበት አካባቢ ማንነቱን የሚያስረዳ በቂ ማስረጃ ያለው መሆን አለበት፡፡ ከሌላ ገዳም የሚመጣ መናኒ የማኅበሩ አባል ለመሆን ሲያመለክት ከመጣበት ገዳም በቂ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ አንድ የማኅበር አባል የገዳም ነዋሪነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ወረቀት ሚያገኘው በገዳሙ ውስጥ አባል ሆኖ ቢያንስ አንድ ዓመት የቆየ እንደሆነ ነው፡፡
በገዳሙ የጸሎት ሥርዐት በቀን ሰባት ጊዜ የሚጸለይ ሲሆን፤ እነዚህም በመዓልት በ፫፣ በ፮፣ በ፱፣ በ፲፩፣ በሌሊት በ፫፣ በ፮፣ በ፱ ናቸው፡፡ ዘወትር በጠዋት ኪዳን ይደረሳል፡፡ መነኰሳይያት የማታ ጉባኤ እና ትምህርት አላቸው፡፡በገዳሙ መናንያን ከሰኞ እስከ ዓርብ በሁለት ቀን አንድ ጊዜ በ፱ ሰዓት፣ ቅዳሜ እና እሑድ በ፫ ሰዓት አንድ ዳቤ የሚሰጣቸው ሲሆን፣ በሥራ ላይ ለሚሰማሩት ግን በየቀኑ ምሳ ላይ እንጀራ ይሰጣቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለአብነት ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ እንጀራ ይሰጣቸዋል፡፡
መናንያኑ የሚለብሱት ሁሉም አንድ አይነት የሆነ እና በገዳሙ መናንያን ከቅጠላቅጠል በሚዘጋጅ ቀለም የሚነከር ቀይ ቡኒ ቀለም ያለው አቡጀዲ ሲሆን፤ አሰፋፉም የገዳማውያንን ሥርዓት የተከተለ ነው፡፡
በአጋጣሚ በመናንያን መካከል አለመግባባት ቢፈጠር በራሳቸው እንዲፈቱ ይደረጋል፡፡ ነገር ግን ከገዳሙ ሥርዐት የወጣ መናኒን እንደ ጥፋቱ መጠን የተለያዩ ቅጣቶች ይሰጡታል፡፡ እነዚህም የጉልበት ሥራ (እንጨት ለቀማ፣ ፅዳት እና የመሳሰሉት)፣ ስግደት፣ በእግር ብረት መታሰር ሲሆኑ፣ ከነዚህም ቅጣቶች ጎን ለጎን ተግሣፅ እና ምክርን ያካትታል።
ገዳሙ መናንያን የሚመሩበት የራሱ የመተዳደሪያ የውስጥ ደንብ አለው፡፡ በመዋቅር ደረጃ ከገዳሙ አስተዳደር መምህር ጀምሮ የምርፋቅ አባቶች፣ ጸሐፊ፣ መጋቢ፣ ሒሳብ ሹም፣ ገንዘብ ያዥ፣ ኦዲተር፣ ዕቃ ግዢ ኃላፊ፣ ዕቃ ቤት ጠባቂ የሚል መዋቅር ተበጅቶለታል፡፡ የውስጥ ደንቡ የገንዘብ እና የዕቃ ወጪ አጠባበቅ፣ የገዳሙ ሥራና ሊቀ አርድዕቶች፣ ስለ ገዳሙ ፀጥታ አጠባበቅና ቅጣት፣ የአዲስ አባላት አቀባበል፣ ወደ ገዳሙ ስለሚመጡ እንግዶች፣ ስለ ሴቶች ገዳም፣ ስለ ገዳሙ አርድዕቶች፣ ስለ ሕመምተኞች፣ ደካሞችና ባሕታውያን፣ ስለ ውርስ ገንዘብ፣ ስለ ልማት፣ ስለ ትምህርት፣ ስለ መቁነንና የዓመት ልብስ፣ ስለ ስብሰባ፣ ስለ ፈቃድ፣ ስለ ጸሎተ ማኅበር፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት፣ አቤቱታ ስለማቅረብ፣ ስለ ሥራና ዕቅድ ግምገማ፣ ስለ ሥራ ሪፖርት፣ ስለ ግል ቁሪት (የግል ሀብት)፣ ስለ ወንዶችና ሴቶች ገዳም ክልል፣ ስለ ገዳሙ ተጠሪነት በስፋት ያብራራል፡፡
ምንጭ ሐመር መጽሔት
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ!!!
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.comS/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
✨✨ብሒለ አበው✨✨
👉 ከቁጣ፡ ከችኮላና ከጥድፊያ ራስህን ትቆጣጠራለህ። ፈጥነህም አትናገር ፡ ፈጥነህም አስተያየት አትሰንዝር፡ ሌሎች ሰዎች ሲናገሩ ጣልቃ አትግባ። እርግጠኛ ባልሆንክበት ነገር ላይ ውሳኔ አታስተላልፍ፡፡ / አቡነ ሺኖዳ/
👉 ትዕግስት ከሰፊ አእምሮ፡ ግበ ሰፊ ከመሆን የሚገኝ ነው። /ማር ይስሃቅ/
👉ሰዎች ከሚወቅሷቸው ዳኞች ይልቅ የገዛ ህሊናቸው እየወቀሰ የሚያሰቃያቸው እጅግ ብዙህ ናቸው። /አንጋረ ፈላስፋ/
👉 ትዕግስት የመልካምነት ዘውድ ነው። /ዮሃንስ አፈወርቅ/
👉ሳትዘራ ምርት የምትመለከት ከሆነ ትጸጸታለህ፡ የመዝራትን ጊዜ አባክነሃልና። /አቡነ ሺኖዳ/
👉የሃጥያት መጀመርያና መንደርደርያው ግድየለሽነት፡ አለመጠንቀቅ ነው። / አባ ጴሜን/
👉መርከብ ያለ ምስማር ሊሰራ እንደማይችል ሁሉ ድኅነትም ያለ ትሕትና ሊገኝ አይችልም። /ቅድስት ስንቀሌጢቃ/
👉ክርስትያን በተፈጥሮ የማስተዋል፡ የአርምሞ የጥንቃቄ እና የሰላም ሰው ነው። /ቀለሜንጦስ ዘእስክንድርያ/
👉እርሱ ጻድቅ የሆነ አምላክ ተስፋን ሲሰጥ እታለል ይሆንን ብሎ መጠራጠር ለማን ይቻለዋል! ሊሰጠን ባይፈልግ ኖሮ እንለምነው ዘንድ ባላሻው ነበር፡ /አውግስጦስ/
🔎ፌስቡክ ገጽ➠https://m.facebook.com/EMislene
📌ከጥር 26-28 በደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ትምህርት ቤት ሕጻናትና ታዳጊዎች አገልግሎት ዙሪያ የተዘጋጀው አስደናቂ ዐውደ ርእይ በተለያዩ ምክንያቶች አምልጧችኋል?
📌ዛሬ ማታ በዩቲዩብ ገጻችን ይጠብቁን።
👇👇👇👇👇
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene