መልካም ማድረግን ለሌሎችም ማካፈልን አትርሱ!!! ዕብ 13፥16
📷ሰንበት ት/ቤታችን እግዚአብሔር ምስሌነ ሰባተኛውን ዙር የፍኖተ ሕይወት ጉዞ በትላንትናው ዕለት አካሔደ።
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ
🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
በውጊያ ላይ የቆሰለ ወታደር ቁስሉ ይድንለት ዘንድ ለሐኪም ማሳየትን አያፍርም፡፡ ንጉሡም ቢሆን ከቁስሉ የዳነን ወታደር ወደ ሰራዊቱ መልሶ ይቆጥረዋል እንጂ አይተወውም፡፡ እንደዚሁ ሁሉ ጠላታችን ሰይጣን ያገኘው፣ በኃጢአት የጣለው ሰውም ኃጢአቱን በመናዘዝ የንስሐን መድኃኒት ተቀብሎ መዳንን ማፈር የለበትም፡፡
ቆስሎ ቁስሉን መናገር ያፈረና በቶሎ መድኃኒት ያልተደረገለት ወታደር ቁስሉ ወደ ካንሰር ይለወጥና አመርቅዞ መላ ሰውነቱን በመምታት ይጎዳዋል፡፡ ጉዳቱን ቶሎ የተናገረ ታማሚ ግን ታክሞ በመዳን ወደ ጦር ሜዳው ይመለሳል፡፡ ቁስሉን ባለመታከሙ ወደ ካንሰር የተለወጠበትና ያመረቀዘበት ሰው ግን ሊድን አይችልምና ወደ ጦር ሜዳው ሊመለስ አይችልም፡፡
እንደዚሁ ሁሉ በተጋድሎ ውስጥ ያለ ሰው እንደ ወታደር ነው። በተጋድሎ ውስጥ ያለ ሰው በኃጢአት ወድቆ "በኃጢአት ወድቄአለሁ" ብሎ የተናዘዘ የንስሓን መድኃኒት ያገኛል፡፡ ኃጢአቱን የደበቀ ግን ሊድን አይችልም፡፡ ምክንያቱም ታማሚው መድኃኒት አግኝቶ ከቍስሉ ሁሉ ይድን ዘንድ በሽታውን ሁለት ዲናር ወስዶ ለሚያክመው ባለ መድኃኒት አልተናገረምና።"
(በእንተ ንስሐ ገጽ 52)
🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
🎙ዜና ምስሌነ
የካቴድራላችን ቅጽረ ግቢ የአስፓልት እድሳት ሥራ በይፋ ተጀመረ።
“የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን . . .” ነህምያ 2፥20 ለረጅም ጊዜያት ሲጠበቅ የነበረውና በቤተክርስቲያኗ ቅን ልጆች ርብርብ የገንዘብ ማሰባሰቡ ሥራ የተከናወነለት የአስፓልት ሥራ ተጀምሯል፡፡ ይህን የአስፓልት ግንባታ ከሐሳብ ጀምሮ የጠነሰሱትና የገንዘብ አሰባሰብ ሒደቱን የመሩት የቤተክርስቲያኗ ልጆች በሥራው መጀመር የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
በቅን ሐሳብ ተጀምሮ ለመልካም ፍሬ የበቃውን ጅምር፤ የካቴድራላችን አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ኪሮስ ጸጋዬ በሰጡት ጠንካራ መንፈሳዊ አመራር፤ የሰበካ ጉባዔውና የልማት ኮሚቴው የጨረታ ሒደቱን በመከታተል ለዚህ እንዲበቃ ማድረግ መቻላቸው የሚያስመሰግናቸው መሆኑን ምእመናን ገልጸዋል፡፡
በተያያዘም በቀጣይ በሚኖሩ የልማት ሥራዎች ላይ ምእመናን እና የደብሩ አካላት በመንፈሳዊ አንድነት በጋራ እንዲቆሙ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
📎ሳማ ብሔረ ሕያዋን እግዚአ ለሰንበት ገዳም (ሳማ ሰንበት)
ሰንበትን የሰራት፣ በሰንበተ ክርስቲያን (እሑድ) መፍጠርን አሐዱ ብሎ የጀመረ፣ በሰንበተ ክርስቲያን ከሙታን ተለይቶ የተነሳ፣ በሰንበተ ክርስቲያን መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት ልኮ ቤተክርስቲያንን የመሠረታት የሰንበት ጌታዋ (እግዚእ ለሰንበት) ኢየሱስ ክርስቶስ በሰንበተ ክርስቲያን ይህችን ዓለም ለማሳለፍ እንደሚመጣ አምናና ተዘጋጅታ የምትጠብቀው ቅድስት ቤተክርስቲያን ይህንን ለክርስቲያኖች ሁሉ የዘወትር ጉጉት የሆነውን የምጽአቱን ነገር ለማዘከር ከየዕለት አዋጇ ባሻገር በዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት በምልዐት በዓል አድርጋ ታነሳዋለች።
የገዳሙን ታሪክ በድኅረ ገጻችን ላይ ያንብቡ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ሳማ ብሔረ ሕያዋን እግዚአ ለሰንበት ገዳም
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ!!
የዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት #ደብረ_ዘይት ይባላል ፡፡
ደብረ ዘይት ማለት የወይራ ዛፍ የበዛበት ተራራ ማለት ነው ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌ በዚህ ዓለም እየተዘዋወረ በሚያስተምርበት ሰዓት ከቅዱሳን ሐዋርያት ስለ ዓለም ፍፃሜ ምልክቶች የቀረበለትን ጥያቄ አስመልክቶ መልስ የሰጠበትን ዕለት በማስታወስ የሚከበር እሁድ ነው። “ እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው ። ንገረን ይህ መቼ ይሆናል ? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድን ነው ? አሉት ። ” ማቴ. ፳፬፥፫
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የዓለም ፍፃሜ መድረስን አስመልክተው የሚታዩ ምልክቶችን በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ነግሯቸዋል ፡፡
ማቴ. ፳፬፥፬
🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
📌መጋቢት 27
በዚህ ቀን መጋቢት 27 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ከወደቀበት የኃጢአት አዘቅት ሊያወጣው ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም ስጋን ነስቶ ሳይገባው በበረት ተወልዶ፤ ስደታችንን ሊያስቀር ሳይገባው ተሰዶ፤ በክፉዎች አይሁድ ምክር ተከሶ በባህርይው መንገላታት የማይገባው አምላክ ለኛ ሲል የተንገላታና የተደበደበ፣ በጥፊ የተመታ፣ የተዘባበቱበት፣ ምራቅ የተተፋበት፣ እርጥብ መስቀል ተሸክሞ ከሄሮድስ ወደ ጲላጦስ እየተመላለሰ ከዚያም በቀራንዮ የራስ ቅል በምትባል ሥፍራ ተሰቅሎ ለኛ ሲል ሞታችንን በሞቱ ሽሮ በዋጋ ገዝቶናል። /ማቴ. 27፥1፣ ማር.15 ፥1፣ ሉቃ. 23፥1፣ ዮሐ.19፥ 1/
"ጌታዬና መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ የደረሰበትን ጉስቁልና ሊተካከል የሚችል ጉስቁልና እንደምን ያለ ነው? ቀላያት ፊቱን በተመለከቱ ጊዜ የሚንቀጠቀጡለት ፀሐይ ብርሃኗን የምትከለክልለት : ጨረቃ የምታለቅስለት : ከዋክብት የሚረግፉለት : ክፉዎች አይሁድ ተፉበት : እጃቸውን አክርረው መቱት : ከስድብ ሁሉ የከፋ ስድብ ሰደቡት:: ስድባቸው እንዲሁ የቃላት ብቻ አልነበረምና ምራቅና ቡጢም አለበት እንጂ : ይህ ብቻ አይደለም : - ክርስቶስ ሆይ በጥፊ የመታህ ማን ነው? ትንቢት ተናገርልን ¡ የሚል ስላቅም አለበትና:: ጌታዬና ንጉሤ መከራ ያልደረሰበት አካል አልነበረውም:: ጭንቅላቱ ላይ የእሾኽ አክሊል ደፉበት : ፊቱን በጥፊ መቱት ፡ ትከሻውን መስቀል አሸከሙት : እጁን በችንካር ቸነከሩት : እግሩን በምስማር ቸነከሩት : አፉን ኮምጣጤ አጠጡት : መላ አካላቱን በጅራፍ ገረፉት ::
ወዮ ! እንዲህ ያለ መውደድ እንደምን ያለ ፍቅር ነው፡፡ "
✍ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
"አቤቱ፥ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት፥ ወደ ጕድጓድም እንዳልወርድ አዳንኸኝ።" [መዝ.፴፥፫]
📌የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
📌የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
''እግዚአብሔር አምላካችን አዳምን እና ሔዋንን ኃያል ነውና በቃሉ ማዳን እየቻለ ለምን መሰቀል(ስቅለት) አስፈለገው?''
መልሱም :-
✍️ እውነት ነው እግዚአብሔር አምላካችን እዛው በመንበረ ክብሩ እያለ ሁሉንም ማዳን ይችል ነበር፡፡ ማንም ቢሆን ይህን አድርግ ብሎም ሊያዘው የሚችል የለም፡፡ የገዛ ባህርዪው ግን አስገድዶት ሰው ሆኖ እኛን ለማዳን መጥቷል፡፡ ለመሰቀል መጀመሪያ ሰው መሆን ስለሚያስፈልግ ጥያቄውን ሰፋ አድርገን ለምን ሰው መሆን አስፈለገው፡ ለምንስ ይህ ሁሉ ስቃይ መቀበል አስፈለገው ብለን መልሱን እንመለከታለን፡፡ ስለብዙ ምክንያቶች ይህን አድርጓል። እነርሱም የሚከተሉት ናቸው፡
👉 ፍቅር፡ አባ ሕርያቆስ "ፍቅር ሰሐቦ ለወልድ ኃያል እመንበሩ ወአብጽሖ እስከ ለሞት፡ ኃያል ወልድን ከመንበሩ ፍቅር ሳበው ለሞትም አደረሰው" እንዳለው የመጀመሪያውና ዋነኛው ምክንያት ፍቅር ነው፡፡ አምላካችን ከመንበሩ ሆኖ በቃሉ ቢያድን አምላክነቱን እንጂ ፍቅሩን በጎላ አያሳይም ነበር፡፡ የደካማውን ሰው ሥጋ ለብሶ፡ 33 ዓመት ከ3 ወር በምድር ተመላልሶ፡ ምድር ላይ ታይቶ በማይታወቅ ወደፊትም ሊታይ በማይችል ሕማም እና ስቃይን ተቀብሎ በመስቀል ተሰቅሎ ሞቶ መቀበሩ ግን ፍቅሩን በጎላ ያሳያል፡፡ ለዚህም ነው አባቶቻችን "አዳም እንኳን በደለ ባይበድል ኖሮ ይህን ሁሉ ፍቅር ማየት አንችልም ነበር" የሚሉት፡፡
👉 ለትምህርት፡ አምላካችን ሰው በሆነበት ዘመን ለእኛ አርዓያ የሚሆኑ ብዙ ስራዎችን ሰርቷል፡፡ ከሰራቸው በኋላም ሐዋርያትን "ከመዝ ግበሩ፡ እናንተም እንደዚሁ አድርጉ" (ዮሐ 13፥15) ብሎ ብዙ ትምህርቶችን ሰጥቶናል፡፡ ለምሳሌ፡ ፍቅርን፡ በጌተ ሴማኒ ጸልዮ መጸለይን፡ የሐዋርያቱን እግር አጥቦ ትሁት መሆንን፡ በገዳመ ቆሮንጦስ ጾሞ መጾምን፡ ከጾመ በኋላ የዲያብሎስ ፈተናን ድል አድርጎ ፈተናን ድል ማድረግን፡ አስተምሮ እንዴት ማስተማር እንዳለብን፡ ተጠምቆ፥ ቆርቦ ምሥጢራት መፈጸምን እንዲሁም በርካታ ነገሮችን አሳይቶናል፡፡ እኚህን ስራዎች በትእዛዙ ብቻ ቢሆን ኖሮ ይከብደን ነብር ነገር ግን በዮሐ 1፥17 እንደተገለጸው እሱ ራሱ እነዚህን ትእዛዛት ፈጻሚ ሆኖ ነው ያሳየን፡፡ ስራዎቹን ደግሞ እንደእኛ ሰው ሆኖ መፈጸሙ ለእኛ ትልቅ አርዓያ ይሆነናል፡፡ ለዚህ ነው አባቶቻችን "እነዚህ ስራዎችን በአምላክነቱ ፈጽሟቸው ቢሆን ኖሮ አያስደንቅም ነበር ነገር ግን የእኛን ደካማ ባህርይ ተዋህዶ መሆኑ ያስደንቃል" የሚሉት፡፡
👉 ጥበብን በጥበብ ለመሻር፡ ዲያብሎስ አዳምንና ሔዋን በእባብ ውስጥ ተሸሸጎ እንዳሳታቸው አምላካችንም የሰውን ሥጋ ተዋህዶ ዲያብሎስን አታሎታል፡፡ ይህም ዲያብሎስ ጌታችን በመስቀል ላይ ሲሞት ተራ ሰው መስሎት ነፍሱን ለመውሰድ ሲመጣ በሥጋው ቢሞትም በመንፈስ ሕያው ነበርና እዛው አስሮት ድል ነስቶታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሞት በሰው በተሰራ ስራ የመጣ ነበርና አዳኙም ሰው መሆን ነበረበት፡ ፍጡር ደግሞ ፍጡርን ማዳን ስለማይችል አዳኙ አምላክ መሆን ነበረበት፡፡ ስለዚህ ሁለቱንም በሚያሟላ መልኩ አምላክ ሲሆን ሰውን ተዋህዶ አዳነን፡፡
👉 ትንቢተ ነቢያትን ለመፈጸም፡ ነቢያት በብዙ አይነት መልኩ ስለጌታችን አመጣጥና እንዴት እንደሚያድነን ጽፈው ነበር። ታዲያ ያን ሁሉ ሽሮ በኃያልነቱ ቢያድነን ኖሮ የእግዚአብሔር አፍ የተባሉትን ነቢያቶቹን ሐሰተኛ ባስባላቸው ነበር፡፡ ለነቢያት ያልተናገውን የማይፈጽም፡ የተናገረውን የማያስቀር አምላካችን ግን ነቢያት ባለሟሎቹ ናቸውና የተናገሩትን ሁሉ ፈጽሟል፡፡
👉 ለመቀደስ፡ አምላካችን ወደእኛ በመጣ ጊዜ ብዙ በረከትን ይዞልን መጥቷል፡፡ ገና በጽንሰቱና በልደቱ በመላእክትና በሰው ዘንድ የነበረውን ጸብ አጥፍቶ አብረው እንዲያመሰግኑ አድርጓል። ከዚህ በተጨማሪ ተረግማ የነበረቺውን ምድር በእግሩ ተመላልሶ ቀድሷታል፡ አየር ላይ የነበሩትን አጋንንት ለማጥፋት ከምድር ከፍ ብሎ ተሰቅሏል፡ ኃጢአተኞችን ቀድሷል፡ ወደ ምድር ሰላም፡ ፍቅር፡ አንድነትን ይዞ መጥቷል፡፡
✍️ በአጠቃላይ አምላካችን ለእኛ በገለጸልን እና ባልገለጸልን ነገሮች ምክንያት ሰው መሆን አስፈልጎታል፡፡ ከዚህ ሁሉ ግን ፍቅሩን ተረድተን ሁልጊዜ ሕማሙን እያሰብንና የተከፈለለን ውለታ እያሰብን ዳግመኛ በእኛ ኃጢአት እንዳናሰቃየው ንስሐ ገብተን በከፈተልን የድኅነት መንገድ ሄደን መንግሥተ ሰማያትን ለመውረስ መትጋት አለብን፡፡ አለበለዚያ በዚህ ሁሉ የመዳን ስራ ውስጥ ተሳታፊ አንሆንም፡፡
📌ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
📌የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
📌የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
📚የመጽሐፍ ጥቆማ
ርእስ:- መራሒ ሁለንተናዊ የልጆች አስተዳደግ (ከውልደት እስከ 18 ዓመት)
አዘጋጅ - መምህር ሳምሶን ወርቁ
የገጽ ብዛት - 417
የሽፋን ዋጋ - 680ብር
ይዘት - መጽሐፉ በአምስት ክፍሎች የተከፋፈለና በውስጡ ብዙ ርእሰ ጉዳዮችን የሚያነሱ ምዕራፎችን ያካተተ ሲሆን የልጆች አስተዳደግ ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮ አንጻር እንዴት መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል። በተጨማሪም ልጆቻችን ፈሪሐ እግዚአብሔር ፣ ግብረ ገብና ፍቅረ እግዚአብሔር ያላቸው እንዲሆኑ የምንቀርጽበትን እንዲሁም ጾም ፣ጸሎትና ምጽዋትን የምናስተምርበትን መንገድና ሌሎች አካላዊ ፣ አእምሮአዊና ማኅበራዊ እድገታቸውን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ትምህርት ይሰጣል።
📌ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
📌የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
📌የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
✨መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ሳማ ሰንበት ገዳም✨
አዘጋጅ- የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት
🗓መነሻ ቀን ፡ 28 - 07 - 16
🗓የመመለሻ ቀን ፡ 29 - 07- 16 ከንግሥ በኋላ
የመመዝገቢያ ዋጋ
💰 ለአዳር ጉዞ 850 ብር
💰 ለደርሶ መልስ 950 ብር
የመመዝገቢያ ቦታ -በሰንበት ት/ቤቱ ሱቅ እና በአሜን መንፈሳዊ መዝሙር ቤት
ለበለጠ መረጃ 📱0946 81 7752
📱0910 06 72 11
📱0913 73 45 90
📱0933 18 64 78
📱 0921 89 91 03 ይደውሉ።
🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
#መጻጉዕ የዐቢይ ጾም የአራተኛ ሳምንት!!
🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
ንጋት (መንፈሳዊ ትረካ)
መፈገግ ከንጋት በኋላ ላለች ቀን ባህሪዋ ነው ምን ብትዳምን የምትረጨው ብርሃን የምታጋባው ሙቀት ባይኖራት እንኳን ጨርሶ አትጨልምም ያ ነው ማታ ከሚለው ስያሜ የሚለያት በእርግጥ ውስጧ የተሸከመቻቸው የሐሳብ ክምሮች በኗሪው ልቦና ውስጥ ወይ ብርሃን ወይ ጨለማ ያደርጋት ይሆን እንጂ ለንጋት ብርሃን የማጣት ባህሪ ማን ሰጥቷል ? ልብ ግን የፀሐይ መውጣት ሳያሞቃት የዝናቡ ውሽንፍር ቁብም ሳይሰጣት እንዳች ነገር እንደደፈነው ጆሮ ጥቂት ብቻ ኦያደመጠች እንዲሁ ሳታገናዝብ መኖር ትችል እንደሆን የሚጠይቅ ካለ የሰማ የሰፈር ሰው ሁሉ ምሳሌ ስጥ ቢባል እጁን ወደ እኔ ይቀስራል በእርግጥ እውነት ነው። እኔጋር ቀን አዘቅዝቃች የማሰላሰል እና ነገርን የማጤን ለዛ ካጣሁ ጊዜያት ከመቆጠር ዘለዋል “እንግዲ በተዋት ጊዜ ይተዋት” እያሉ የሚያዝኑልኝ ሰዎች ሁሉ የትላንት እኔነቴን እያስታወሱ አይናቸውን አይኔ ላይ ቀስረው ምራቅ ይመ’ጣሉ ።
አዎ ብቻ መሆንን ወድጄ እራሴን ከአብሮነት ገትቼ እራሴ ላይ ቆልፌያለሁ ስላጣኋቸው ነገሮች ሳስብ አለኝ የምለው መስመር እንኳን ሳስቶ ሊበጠስ የደረሰ ክር ይመስለኛል በቃ ለእኔ መቋጨት ያልቻለኩት የማቆም ጫፍ ቆሜ ለመፈጥፈጥ የፊሽካ ድምጽ የምጠብቅ አይነት ሰው ነኝ ለምን አትበሉኝ ምክንያቹን ልክ አይደለሽም ለሚለኝ ውስጠቴ እንኳን በቂ አይደሉም ለራሴ በቂ ያሆንኩና ያለኝ የተነጠቀብኝ ሰው እንደሆንኩ ብቻ ነው ሚሰማኝ።
በማለዳ ክፍሌ የምትገባዋ ፀሐይ ለመንጋቱ ምልክት ናት ከዚያ በዘለለ ሙቀቷ ሰርጾኝ አያውቅም እንደውም ታደክመኛለች ሌላ የማይገፋ ቀን ይዛብኝ ትመጣለች ሰውነቴ በግድ ወዲህ ወዲያ ይበል እንጂ በትርጉም የሚሰራው ስራ አልነበረውም ክፍሌ ራሴ ለራሴ እያለቀስኩ የቀበርኩባት መቃብሬ ሆናለች። ለነብሳቸው ያደሩ ቤተሰቦቼ ቢሰለቹም እንዳልሞት በግድ ይመግቡኛል። ሌላ በኑሮዬ የማስታውሳቸው ነገሮች ደሞ የጠያቂ ድምጾች ናቸው ” ያቺ ልጅ እንዴት ናት እንደው ምንም ለውጥ የላት” የሁሉም ሰው ወሬ መጀመሪያ ናት። ” አለች ምንም ለውጥ የላት እንደተለጎመች ይንን ሆንኩ እንዲህም ተደረኩ አትል ግራ የገባው ነገር ነው እኛም እኮ ተጨነቅን ” ይላሉ ለመጣ ሁሉ ።ለምጄዋለሁ አልጋዬ ላይ ያስቀረኝን ድባቴ ወድጄ ተገዛሁለት እሱም ወደሽ ከተደፋሽ እያለ ይረግጠኛል ።
ሌሊቱ ከድቅድቅ ጨለማ ጋር ቢሆንም ምን እንዳስፈነጠረኝ የማላውቀው ስሜት ከዘመናት አልጋዬ አስነስቶ መስኮት ላይ ገተረኝ ከአንዳድ የሰማይ ከዋክብት በቀር የሚታይ ነገር የለም ጸጥ ረጭ ያለ ጨለማ።
የቆምኳቸው ሰዓታት ቢበዙም የድካም ስሜት ግን የለኝም ጨለማ ውስጥ የዛለ ስጋዬን መቆሜ ውስጥ ደግሞ የድሮ ትጋት እና ጽኑ ስሜቴ
👉ሙሉውን ያንብቡ
"ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ"
📖ከንግግር የሚበልጥ ዝምታ (ሕማማት ገጽ 177)
‹‹ከመቀየም ይልቅ የዋህነት የምትወድ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የትግስትህ መጠኑን አውቅ ዘንድ የአፍ መዝጊያ ቁልፍ የሆነች ዝምታን ስጠኝ››ይላሉ የመልክአ ኢየሱስ ደራሲ። ጌታችን አይሁድ በሐሰት ክሶች ደጋግመው ሲከሱት፤ ሲሰድቡት፤ሲዘብቱበት የታገሰውን የትዕግስቱን መጠን እንዴት ልንረዳው እንችላለን?
ባላጠፋኸው ስትከሰስ፤ ያላደረከውን አድርገሃል እየተባለ ለሞት በሚያደርስ ክስ ስትወቀስ በዝምታ መሸከም እጅግ ከባድ ነው፡፡እናም በብስጭት እና በምሬት ራስህን ለመከላከል መሞከርህ አይቀርም፡፡ምናልባትም ከመናገር አልፈህ ከሳሾችህን፤የሚሰድቡህን፤የሚተፉብህን ሁሉ መሬት ተሰንጥቃ እንድትውጣቸው ማድረግ ብትችል ከማድረግ አትመለስም፡፡
ጌታችን ግን ሁሉን ማድረግ ሲቻለው በዝምታ ተቀበለ፡፡‹‹ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው?ይህ ያህል ትዕግስት እንደምን ያለ ትዕግስት ነው?›› እያልን በቅዳሴያችን ከማድነቅ በቀር ምን ልንል እንችላለን፡፡
የጌታችን ዝምታ ከአይሁድ ንግግር ይልቅ የጲላጦስን ልብ ገዛው የጌታችን ትዕግስት ጲላጦስን አስጨነቀው፡፡እንደ ሎሎች ተከሳሾች ሕይወቱን ለማዳን በገዢው ፊት በዕንባ የማይማጸን ክሶቹን ለማስተባበል የማይሞክር ከሳሾቹን መልሶ እየከሰሰ ራሱን ነጻ ለማውጣት የማይፍጨረጨር በሰንሰለት ታስሮ እየተጎተተ እንኳን ከሚጎትቱት ጋር የማይታገል ሞት ሊያስፈርድበት በሚችል ወንበር ፊት ቀርቦ
👉ሙሉውን ያንብቡ
"ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ"
የያዕቆብና የድንግል ማርያም ኃዘን ሲነጻጸር
የአበው አለቃ የያዕቆብ ለቅሶ ዛሬ ታደሰች አለ፡፡ ወዳጆቼ ሆይ ፦ ድንግል ማርያም በድንግልና ስለፀነሰችው ልጇ ለምን አታለቅስም? ድንግል ማርያም ስለሳመችው ልጇ ለምን አታለቅስም ፤ ድንግል ማርያም አምላካዊ በሆነ አፉ የድንግልና ጡቷን (ወተቷን) ስለሰጠችው ልጇ ለምን አታለቅስም?
ድንግል ማርያም በቤተልሔም በረት ስለተወለደው ልጇ ለምን አታለቅስም? ዘጠኝ ወር በማሕፀኗ ስለተሸከመችው ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስም? ራሄል ስንኳ ፈጽማ ስላልሳመቻቸው ልጆቿ አለቀሰች፡፡ ድንግል ማርያም ከቦታ ወደ ቦታ ይዛው ስለተሰደደች ልጇ ለምን አታለቅስ?
እንደ ሰው ሁሉ በእቅፏ ስለታቀፈችው ልጇ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ? መቃብራቸውን ፈጽማ ስላላየችው ልጆቿ ራሄል ለምን አለቀሰች?፡፡ ድንግል ማርያም አንድ በሆነው ልጇ መቃብር በር ለምን አታለቅስ? ያማረ ጽሕም የነበረው ሽማግሌ ለቅሶ ዛሬ በድንግል ዘንድ ታደሰ፡፡
ያዕቆብ ወንድሞቹ ሲያስሩት ወደ ዮሴፍ አልተመለከተም፡፡ ድንግል ግን ልጇን በመስቀል ተቸንክሮ ተመለከተችው፡፡ ያዕቆብ በእርሱ ላይ ያለቅስ ዘንድ በጥልቅ ጉድጓድ እያለ አላየውም፡፡ ድንግል ግን በአይሁድ ጉባኤ መካከል ተሰቅሎ ተመለከተችው፡፡
ያዕቆብ ዮሴፍን ወንድሞቹ ሲያራቁቱት አላየም ፤ ድንግል ግን የሚመክራቸው ባጡ በአይሁድ ጉባኤ መካከል ራቁት ሆኖ ልጇን ተመለከተችው፡፡ ያዕቆብ ልብሱን በሌላ ደም ነክረው ዮሴፍን ወንድሞቹ በሃያ ብር ሲሸጡት አላየም፡፡ በእርሱ ላይም አለቀሰ ፤ ልብሱንም ቀደደ፡፡ አምላካዊ ደም ግን ማርያም ስለ እርሱ በምታለቅስበት ዐለት ላይ ፈሰሰ፡፡ ድንግል ያየችውን ሌላውን ልብስም ለልጇ ዛሬ አለበሱት፡፡ ልብሶቹንም ለየራሳቸው ተካፈሉ፡፡
የዮሴፍ ወንድምቹስ በሸጡት ጊዜ ተጸጸቱ፡፡ ደቂቀ እስራኤል ግን ጌታቸውን በሸጡት ጊዜ አላለቀሱም፤ አልተጸጸቱም፡፡ የያዕቆብ ልጆች ወንድማቸው በነገሠ ጊዜ ተደሠቱ ፤ አይሁድ ግን ጌታቸው ከመቃብር በተነሣ ጊዜ አልተደሰቱም፡፡ ድንግል ሆይ በልጅሽ መቃብር ላይ ያለቀስሽው ለቅሶ በእውነት ጥዑም ነው ፤ በመላእክት ዘንድም ድምፅሽ ያማረ ነው፡፡
(ርቱዓ ሃይማኖት)
🔎ፌስቡክ ገጽ➠https://m.facebook.com/EMislene
መልካም ማድረግን ለሌሎችም ማካፈልን አትርሱ!!! ዕብ 13፥16
📷ሰባተኛ ዙር ፍኖተ ሕይወት ጉዞ
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ
🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
📌ገብር ኄር -የዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት።
‹‹ጌታውን ደስ ያሰኘ ታማኝና ቸር አገልጋይ ማነው?›› ቅዱስ ያሬድ
🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
✨ ሴሚናሩ የሚሰጠው የሙስሊም ወንድሞቻችን በዓል በሚውልበት ዕለት
አይደለም መቅረት ማርፈድ ያስቆጫል
እህቴ ሆይ እህትሽን ይዘሽ ነይ
ወንድሜ ሆይ ወንድምህን ይዘህ ና
✨መንፈሳዊ ጉዞ ወደ መካነ ሕይወት መድኃኔዓለምና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን✨
🗓ሚያዚያ 13 - 2016 ዓ.ም
💰 የጉዞ ዋጋ - 350 ብር
📌በተጨማሪም በዕለቱ በመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ተቋም የሚገኙ ወገኖቻችንን የምንጎበኝ ይሆናል።
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ
🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
ከመላእክት ጋራ
ከመላእክት ጋራ ሲገለጥ በሰማይ
ፀንተን እንጠብቀው ክብሩን ሁሉ እንድናይ
በግርማ ሲመጣ በአስደንጋጭ ሁኔታ
ወዮልሽ ነፍሴ ሆይ ወየው የዛን ለታ
ኧኸ ምስጋና ይድረስ ሁልጊዜ ጠዋት ማታ
ሃሌ ሃሌ ሉያ የሠራዊት ጌታ (፪)
ሰማይና ምድር ከፊቱ ሲሸሹ
መግቢያ አጥቶ ይጮሃል ትልቁ ትንሹ
ጻድቃን ሲደሰቱ የኃጥአን ፋንታ
ሆኖ ጠበቃቸው ለቅሶና ዋይታ
አዝ======
ስለማይታወቅ አምላክ አመጣጥህ
በመንፈስህ አፅናን ፀንተን እንጠብቅህ
ሰይጣን እንዳይገዛን በመንግሥትህ ቦታ
እግዚኦ ከልለን ከለቅሶ ከዋይታ
ሊቀመዘምራን ይልማ ኃይሉ
✨እርሱ የሕይወት መገኛ፣ የሰንበት ጌታ ነውና ያን ጊዜ በኃጢአት ከመሞት ይራራልን፡፡
🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
✨ቅዱስ ዐማኑኤል✨
ፍጥረታትን ሁሉ የፈጠረ፣ ያበጃጀ፣ የመሠረተ፤ ያሳመረም እርሱ ነው። ለዐፈር ሕይወትን የሰጠ፣ መሬትም የዘሩባትን ታበቅል ዘንድ ዕፅዋትንም ታስገኝ ዘንድ ሕዋስን የሰጣት እርሱ ነው፡፡ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ይንቀሳቀስ ዘንድ አካልን የሰጠ እርሱ ነው። ሁሉም ፍጥረታት በተሰጣቸው ቦታ ውስጥ ይኖሩ ዘንድ ለሁሉም የፍጥረታት ዘሮች ቦታ ከፍሉ የሰጣቸው እርሱ ነው፡፡
ፍጥረታት ሁሉ የራሳቸው መልክ ይኖራቸው ዘንድ መለያ ቍጥር ሳያደርግባቸው የሁሉንም ፊት የተለያየ እንዲሆን ያደረገ እርሱ ነው፡፡ የሁሉንም ዘሮች ሕሊና ያደሰ እርሱ ነው። ጥበብን ሁሉ የዘራ እርሱ ነው። ሰማያትን የዘረጋ፣ በብርሃናትም ያስጌጣቸው እርሱ ነው፡፡ ለፍጥረታት ሁሉ ስም የሰጠ፣ ምድርም ሊደረስበት የማይቻል ምንጭ ታመነጭ ዘንድ የሰጣት እርሱ ነው።
ተራሮችን የቀረጸ፣ ከፍታዎችንም የሠራ እርሱ ነው። ሣሮችን የሚያዝዝ፣ ዛፎች እንዲበቅሉ፣ ፍሬም እንዲያፈሩ የሚያደርግ፣ እንዲበስሉም ፍሬዎችም እንዲያድጉ የሚያደርግ እሱ ነው። የፍሬዎች ጣዕም እንዲለያይ የሚያደርግ፣ ለአበቦችም መልክ እና ቅርፅ የሚሰጥ እርሱ ነው።
ሰማያትን በእጆቹ የሚለካ፣ በኃይሉ ሁሉን የሚለካ ሲሆን እርሱ ግን የማይለካ፣ እርሱ የማይወሰን ሲሆን የመሬትን ዐፈር አንዳች ሳትጎድል በእጆቹ የሚገድብ የሚለካም እርሱ ነው።
ሊደረስበት በማይቻል ዕውቀት የተራሮችን ክብደታቸውን፣ የከፍታዎችንም ሚዛን የሚያውቅ እርሱ ነው፡፡ የባሕርን ውኃዎች አንድ ላይ የሰበሰበ፣ በባሕር ጥልቀት ውስጥ ያሉትን ፍጥረታት ሁሉ እያንዳንዳቸውን የሚያውቅ፣ እኛ ልንለካው የማንችለው የባሕር ውኃ በእርሱ ፊት ግን እንደ ጠብታ የሆነ ነው፡፡
✍ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
📌ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
📌የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
📌የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
✨መንፈሳዊ ጉዞ ወደ መካነ ሕይወት መድኃኔዓለምና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን✨
🗓ሚያዚያ 13 - 2016 ዓ.ም
💰 የጉዞ ዋጋ - 350 ብር
📌በተጨማሪም በዕለቱ በመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ተቋም የሚገኙ ወገኖቻችንን የምንጎበኝ ይሆናል።
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ
🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
ዐውደ ወንጌል ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
🎙የመናገሻ ገነት ጽጌ ሰንበት ትምህርት ቤት በልማት ምክንያት ቤታቸው ለፈረሰባቸው አባላቱ፣ ተማሪዎች፣ ወላጆችና የአካባቢው ወጣቶች የምክክር እና የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል።
ቀን:- እሑድ መጋቢት 22
ሰዓት:- ከ7:30 ጀምሮ
ቦታ:- በመናገሻ ገነተ ጽጌ ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ
🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
አልፋና ኦሜጋ
አልፋና ኦሜጋ ፈጣሪ የሆንክ
በከሃዲዎች እጅ ተይዘህ ቀረብክ
ተገፋህ ተደፋህ በጥፊ ተመታህ
እየደበደቡ ክርስቶስ ሆይ አሉህ
ጽድቅን ስለ ሠራህ በወንጀል ከሰሱህ
ለአዳም ቤዛ ብለህ ብዙ ተንገላታህ
ቅዱሳን እጆችህ የፊጥኝ ታስረው
እንደ በግ ተጎተትክ ልትምራቸው
የትም ቦታ ያለህ ሁሉን የምታውቅ
ፊትህን ሸፈኑህ ለመመጻደቅ
በዓውደ ምኲናን ከጲላጦስ ዘንድ
አሳልፈው ሰጡህ አጋልጠው ለፍርድ
ከሐና ቀያፋ ከመሳፍንቱ ደጅ
ከእነ ሄሮድስ ዘንድ አቀረቡህ በአዋጅ
ግርፋት ሕማሙ አልበቃ ብሎህ
በመስቀል ላይ ልትውል ተፈረደብህ
ሳዶርና አላዶር ዳናትና አዴራ
ተፈልገው መጡ ለችንካር በተራ
የሰላም ባለቤት ደረትህ ተወጋ
ሊያያዝ በችንካር እጅህ ተዘረጋ
ግፈኞች አይሁዶች በአንተ ላይ ቀለዱ
ምራቅን ተፉብህ እራስህን ሊጎዱ፤
🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
✨የምልክት ቋንቋ ስልጠና✨
የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የምልክት ቋንቋ ስልጠና አዘጋጅቷል።
ወርኃዊ ክፍያ - 150 ብር
የመመዝገቢያ ቦታ - በሰንበት ት/ቤቱ ሱቅ
ትምህርቱ ማክሰኞ ፡ ሀሙስና ቅዳሜ ይሰጣል።
ለበለጠ መረጃ ፡
📱 09 46 38 48 94 ላይ ይደውሉ።
📌ትምህርቱ መጋቢት 17 ይጀመራል።
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ!!!
/channel/EMislene