በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተክርስቲያን በዋዜማው የሚቀርበውን እጅግ ጥልቅ ምስጢር የያዘውን በአንድ ልብ በአንድ ቃል ለማመስገን ይረዳን ዘንድ ይህ ስርዓተ ማኅሌት እንደሚከተለው ቀርቧል።
📌ሥርዓተ ማኅሌትና የንግሥ በዓሉን በቀጥታ ስርጭት ከምሽት 3 ሰዓት ጀምሮ ይጠብቁን።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የበጎ አድራጎት እና ሞያ አገልግሎት ክፍል የትምህርት ቁሳቁስ ማግኘት ላልቻሉ 105 ተማሪዎች ድጋፍ አደረገ፡፡ በቀጣይም በገዳም ለሚገኙ ተማሪዎች ድጋፍ የምናደርግ መሆኑን እየገለፅን በዚህ በጎ ሥራ ለተሳተፋችሁ አባላትና ምእመናን በአማኑኤል ስም ክብረት ይስጥልን እንላለን፡፡
፩. በቀጣይ በሚኖሩ አገልግሎቶችም ተሳታፊ ይሆኑ!
፪. የሚያስቧቸው በጎ ሥራዎችም ካሉ በእኛ በኩል ማድረግ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
https://vm.tiktok.com/ZMh8eBwfA/
"ኢንኀድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ"
📌
እንኳን ለ2017 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን አደረሳችሁ
የአንደኛ ዓመት
የተከታታይ ትምህርት መክፈቻ
መርሐ ግብር
ማክሰኞ ከምሽት 12:30
መስከረም 7 ጀምሮ
2017 ዓ.ም.
በሰንበት ት/ቤቱ
አዳራሽ
https://linktw.in/KpUbbr
"ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ"
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
የደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት
ለ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሐ ግብር የሦስት ዓመት ተከታታይ ትምህርት ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቆ
እርሶን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡
የምዝገባ ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ
👉 ከነሐሴ 17/2016 ዓ.ም - መስከረም 26/ 2017 ዓ.ም
ዘወትር ከሰኞ - እሑድ ከቀኑ 11፡00 - ምሽት 2፡00
በሰንበት ት/ቤቱ ትምህርት እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል
ትምህርቱ የሚሰጥባቸው ቀናት
ለ1ኛ ዓመት ተማሪዎች ማግሰኞ፣ ረቡዕ እና ዐርብ
ለ2ኛ እና 3ኛ ዓመት ተማሪዎች ሰኞ፣ ረቡዕ እና ዐርብ
ከምሽቱ 12፡30 - 2፡00
ማሳሰቢያ
ለመመዝገብ ሲመጡ ሁለት ጉርድ ፎቶ ይዘው ይምጡ፡፡
ከተጠቀሱት የምዝገባ ቀናት ውጪ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ትምህርቱ የሚጀምረው
ለ2ኛ እና 3ኛ ዓመት ተማሪዎች ሰኞ መስከረም 6/2017 ዓ.ም
ለ1ኛ ዓመት ተማሪዎች ማክሰኞ መስከረም 7/2017 ዓ.ም
ለበለጠ መረጃ
0935948821
0919599742
0923646828
"ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ"
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ዐሠርቱ ወሰብዓቱ ዓመተ ምሕረት
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤ በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤ እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤት የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ፡፡
ሁለመናችንን በሐዲስ ምግብና እየመገበ የሚጠብቀን አምላካችን እግዚአብሔር እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ 2016 ዓ.ም. ወደ ዘመነ ማቴዎስ 2017 ዓ.ም. በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!
‹‹ሐድሱ መንፈሰ ልብክሙ፤ የልባችሁን መንፈሳዊ አእምሮ አድሱ›› (ኤፌ. ፬÷፳፫)፤
በገሃዱ ዓለም በግልጽ እንደምናስተውለው ከሞላ ጎደል የማያረጅ የለም የማይታደስም የለም፤ መታደስ ባይኖር ኖሮ ሕይወታውያን ፍጡራን በሕይወት መቀጠል አይችሉም ነበር፤ የዘመን መታደስም የሥነ ፍጥረት አንዱ አካል ነው፤
እኛ ሰዎችም የሕዳሴው መሪዎች ሆነን የተሾምንባትን ምድር በየጊዜው በልማት እንድናድሳት እግዚብሔር አዞናል፤
የሃይማኖት ትልቁ ተስፋም መታደስ ላይ የተመሠረተ ነው፤ ዘመንም እንደ ሌላው ያረጃል፤ ይታደሳልም፤ “ወናሁ እገብር ኵሎ ሐዲሰ እነሆ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ” የሚለው የእግዚአብሔር ቃልም የዚህ አስረጅ ነው፤ በዚህ ሕገ እግዚአብሔር መሠረት እነሆ አሮጌውን ዘመን የምንሸኝበት አዲሱን ዘመን ደግሞ የምንቀበልበት ምዕራፍ ላይ ነን፤
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን
ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፡-
ፍጥረታትን በማደስ ሕይወትን የማስቀጠል ሥልጣን በዋናነት የእግዚአብሔር ብቻ መሆኑ ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም፤ ይሁን እንጂ ሰውም ሥነ ፍጥረትን በማደስና በማጐስቈል ረገድ ያለው ሚና ቀላል አይደለም፤ ይህም ሰው በምድር ላይ እንዲሠለጥን ወይም ፍጥረትን እንዲገዛና እንዲመራ በፈጣሪ ከተሰጠው ሥልጣን የሚመነጭ ነው፤
ዛሬም ዓለማችን በመታደስ ያይደለ በማርጀት ላይ የምትገኘው ከሰዎች ድርጊት የተነሣ እንደሆነ እንገነዘባለን፤ የአየሩ መለወጥ፣ የበረዶው መቅለጥ፣ የሙቀቱ ማሻቀብ፣ የዝናሙ ማጥለቅለቅ፣ የባሕሩ መናወጥ ወዘተ. እየተፈጠረ ያለው ኃላፊነት ከጐደለው የሰው አጠቃቀም የተነሣ እንደሆነም ተደጋግሞ እየተነገረን ነው፤ እኛም በዓይናችን እያየን ነው፤ ከዚህ በተለየ ደግሞ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ሰው ምድረ በዳውን ወደ ሐመልማለ ገነት ሲቀይር የሚስተዋልበት ሌላ ገጽታ አለ፤ ይህ የሚያሳየው ሰው በሥነ ፍጥረት ላይ የማደስና የማጐስቈል ብሎም የማጥፋት ሚና ያለው መሆኑን ነው፤ ሰውም እንደሌላው ሥነ ፍጥረት የሚያረጅም የሚታደስም ነው፤ ይህም በብዙ አቅጣጫ ሊከሠት ይችላል፤
ሰዎች በተናጠልም ሆነ በጋራ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ሁለቱንም ማለትም ማርጀትና መታደስን ሊያስተናግዱ ይችላሉ፤ ሰዎች በመንፈሳዊ፣ በኢኮኖሚያዊ በማኅበራዊና በመልካም አስተዳደር ወዘተ. የላቀ ዕድገትን ሲያስመዘግቡ በመታደስ ላይ እንደሆኑ ይታወቃል፤ የዚህ ተቃራኒ የሆነውን ይዘው እየተጓዙ ከሆነ ደግሞ ተቃራኒውን ወይም ማርጀትን እያስተናገዱ እንደሆነ ይታወቃል፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ ሰዎች በመንፈሳቸውም ሆነ በአእምሮአቸው፣ በነፍሳቸውም ሆነ በአካላቸው በመታደስ እንዲኖሩ እንጂ እርጅና እንዲጫጫናቸው አይፈልግምና “የልባችሁን መንፈስ አድሱ” በማለት ያስተምረናል፤
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን
ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት!
የክርስትና ሃይማኖት የመጨረሻው ግብ የፍጥረት መታደስ ነው፤ ይህም ማለት የሃይማኖቱ አስተምህሮ መዳረሻ ከሞት በኋላ ትንሣኤ ከዚያም ፍጻሜና እንከን የሌለው ጣዕመ ሕይወት አለ ብሎ ሰውን ለዘላለማዊ ሕዳሴ ማብቃት ነው ማለት ነው፤ ከዚህ አንጻር የሰው የመጨረሻ ዕድሉ ማርጀት ሳይሆን መታደስ እንደሆነ እንገነዘባለን፤
እግዚአብሔር የሰውንና የፍጥረታትን መታደስ የሚሻው በሰማያዊው ዓለም ብቻ ሳይሆን በምድራዊው ዓለምም ጭምር ነው፤ ለዚህም ነው በየወቅቱ የሥነ ፍጥረትን ውበት እያደሰ የሚመግበን፤ አሁን ትልቁ ጥያቄ የሚሆነው እኛስ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለመታደስ ተዘጋጅተናል ወይ? የሚለው ነው፤ ዛሬ እያንዳንዳችን ይህንን ጥያቄ አንሥተን ኅሊናችንን በጥልቀት መጠየቅ አለብን፤ በዚህም ሳናበቃ መልሱን በትክክል ማግኘት አለብን፤ በሁለንተናችን ለመታደስም ቈራጥ ውሳኔ በራሳችን ላይ ማሳለፍ አለብን፤
አዲሱ ዘመን አዲስና ብሩህ የሆነ የደስታ ሕይወት ሊያጐናጽፈን የሚችለው በዚህ መንፈስ ተቀብለን ስንጠቀምበት ነው፤
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን
ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት!
እኛ ኢትዮጵያውያን ለብዙ ዘመናት የታደሱ ያይደሉ በርካታ ዓመታት ተጭነውን አልፈዋል፤ ቀድሞ እንበልጣቸው ከነበሩ አህጉር በታች ሆነንም በርካታ ዓመታትን አስቈጥረናል፤
የእርስ በርስ ግጭት፣ ረኃብ፣ ጦርነት፣ ድህነት፣ ኋላ ቀርነት የመልካም አስተዳደር እጦት በዓለም ፊት ልዩ መለያችን ሆኖአል፤ ዛሬም ከዚህ አልተላቀቅንም ብቻ ሳይሆን እንዲያውም አጠናክረን ለማስቀጠል ውል የገባን እስክንመስል ድረስ እየቀጠልንበት እንገኛለን፤
በእውነቱ እንዲህ የመሰለ ልምድ ልናፍርበትና ንስሐ ልንገባበት እንጂ ልናስቀጥለው አይገባም፤
በተፈጥሮ የታደለች ሁሉንም አሟልታ የምትገኝ ኢትዮጵያን የመሰለች ሀገር ይዘን ከሰው በታች ሆነን ስንገኝ በስንፍናችሁ ከምንባል በቀር የሀብተ ጸጋ እጥረት አለባችሁ የሚለን አናገኝም፤ ስለዚህ አሁንም ለኢትዮጵያውያን ልጆቻችን በአጽንዖት የምናስተላልፈው መልእክት ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውን አይደለም ለዓለም የሚተርፍ ሀብተ ጸጋ አላትና ለኔ ለኔ በመባባል የሕዝባችንን ሰቆቃው አናስረዝም፤ ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ናት የሚለውን ጥሬ ሓቅ በደምብ አላምጠን መዋጥ አለብን፣ ከዚያም በእኩልነትና በአንድነት ሀገራችንን እናድስ፤ ከሌሎች በደባል የሚመጡ ነገሮችን ሳይሆን የሀገሪቱ በሆኑ ዕሤቶች እንመራ፤
ለበርካታ ዓመታት የተሸከምነው ደባል የአስተዳደር ስልት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የሚጣጣም ሆኖ አልተገኘም፤
የኢትዮጵያ ሕዝብ ከምንም ከማንም በላይ በፈጣሪው እንደሚመካ እሱንም አጥብቆ እንደሚያምን ልኂቃኖቻችን ተገንዘቡልን፤ እኛ ኢትዮጵያውያን ከሦስት ሺሕ ዓመታት በላይ ባስቆጠረ ታሪካችን ከእግዚአብሔር ተለይተን አናውቅም፤ በዚህም ተጠቃሚዎች እንጂ ተጐጂዎች የሆንበት ጊዜ የለም፤ በለመደው እምነት ባህልና ዕሤት ሕዝቡን ብንመራው ሁሉም ነገር ቀላል ይሆንልናል፤ ከዚህ ውጭ እንምራህ ብንለው ግን ያጋጠመንን ችግር ማስቀጠል ነው የሚሆነው፤ ስለዚህ የሁሉም መነሻ ማለትም የክፋትም ሆነ የደግነት መነሻ ውሳጣዊ አእምሮአችን ነውና እሱን በማደስ በአዲሱ ዓመት አገራችንን እንድናድስ በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
በመጨረሻም
አዲሱ ዘመን በሃይማኖት መንፈስ ግጭትን በውይይት፤ መለያየትን በአንድነት፤ አለመግባባትን በዕርቅ ፈትተን በመታደስ ማማ ላይ የቆመ ማኅበረ ሰብን ለመገንባት ሁላችንም ጥረት እንድናደርግ በእግዚአብሔር ስም መልእክታችንን እናስተላልፋለን፡፡
አዲሱ ዓመት የሰላም የዕርቅ የእኩልነትና የአንድነት ያድርግልን፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!
አሜን::
" ነገር ግን በጎ ሥራ ለሚያደርጉ ሁሉ ምስጋናና ክብር ሰላምም ይሆንላቸዋል" ሮሜ ፪÷፲
መልካም ሥራ የሠሩ ተሸለሙ።
በየዓመቱ መልካም ላደረጉ አካላት ሰንበት ትምህርት ቤታችን የደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ምስጋና እንደምታቀርብ ይታወቃል። ዘንድሮም በጎ ላደረጉ ማኅበራት፣ ተቋማት፣ የደብር አስተዳዳሪ እንዲሁም ምእመናን በምስጋና መርሐ ግብር ላይ አመስግናለች ። በዚህ መርሐግብር የተለያዩ አካላት የተሸለሙ ሲሆን ከእነዚህ በጥቂቱ:
፩. ሊቀ ሥልጣናት ቆሞስ አባ ኪሮስ ጸጋዬ (የደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል ዋና አስተዳዳሪ) ምእመናን ስብከተ ወንጌልን በተሻለ ደረጃ በማዳረስ፣ ደብሩ ለዘመናት በተጠማበት የልማት ሥራ ላይ የተሻለ በማበርከት እንዲሁም ለሰንበት ትምህር ቤቱ አገልግሎት ለትውልድ የሚሆን ጉልህ አስተዋጽዖ በማድረግ እና በደብሩ ዘመኑን የዋጀ በሳል አመራር በማከናወን፣
፪. ለማኅበረ ማርያም ዘጴጥሮስ ወጳውሎስ፣
፫. ለአበበች ጎበና የረድኤች ድርጅት (Charity)፣
፬. ለኮሜዲያን እሸቱ መለሰ
ከዚህ በተጨማሪ ያለፋትን ሦስት ዓመታት በሥራ አመራር እና በንኡስ ተጠሪነት እንዲሁም በተለያዩ የኮሚቴ ሥራዎች ያገለገሉ አባላትን አመስግናለች።
ኢንኀድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ!
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
✨✨እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት በሰላም አደረሰን✨✨
‹‹በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፡፡›› መዝ 67(68)፡33፡፡‹‹ አምላክ በእልልታ፣ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ፡፡ ዘምሩ፣ ለአምላካችን ዘምሩ ፤ ዘምሩ ፣ ለንጉሣችን ዘምሩ፡፡ እግዚአብሔር ለምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና ፤ በማስተዋል ዘምሩ፡፡ እግዚአብሔር በአሕዛብ ላይ ነገሠ ፤ እግዚአብሔር በቅድስናው ዙፋን ይቀመጣል፡፡ ›› መዝ 47፡5-8፡፡
‹‹ እነሆም አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ፡፡ እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው፡፡ ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ፡፡ እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፣ ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ፡፡ ›› ሉቃ 23፡50-53፡፡
‹‹ ዕርገት ›› የሚለው ቃል ዐረገ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ‹‹ ከፍ ከፍ አለ ፣ ወደ ሰማይ ወጣ ›› ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በአንቀጸ ብርሃን ላይ ‹‹ በስምሽ በመለመን በመማጸን የሰው ልጆችን ጸሎት ያሳርጋሉ ›› እንዲል፡፡ እንዲሁም በእሁድ ውዳሴ ማርያም ላይ ‹‹ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያሳረገ›› እንዳለ፡፡
በተጨማሪም በራእይ 8፡4 ላይ ‹‹የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር በመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ›› በማለት ዐረገ የሚለውን ቃል በአማርኛ ‹‹ወጣ›› በማለት ይገልጸዋል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ..............
ሙሉውን 👉 በዓለ ዕርገት
/channel/EMislene
🎙 በደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የእኅቶች ጉባዔ ክፍል የተዘጋጀው "ዝክረ ቅዱሳን አንስት" የተሰኘው መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ተካሔደ።
🏡በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
✨ዝክረ ቅዱሳት አንስት✨
የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት "ዝክረ ቅዱሳት አንስት" የተሰኘ ልዩ መርሐ ግብር አዘጋጅቶ ይጠብቅዎታል።
ለዕለቱም፡
👉መዝሙር
👉ኪነ ጥበብ
👉ቃለ መጠይቅና ሌሎች መርሐ ግብራት ተዘጋጅተዋል።
🗓 እሑድ ሰኔ 2 -2016 ዓ.ም
⏰ጠዋቱ 3:30
📌 በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
🌼መንፈሳዊ ጉባዔ🌼
በደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት ለማኅበራት የሚዘጋጅ
የአንድነት መንፈሳዊ ጉባዔ
📆 መስከረም 12, 2017 ዓ.ም.
⌚️ ከቀኑ 6:00 እስከ 8:00
የት ነው የሚከናወነው?
=> በጻድቃን ሰንበቴ አዳራሽ
((በዚህ ሰማያዊ ማዕድ ላይ በአንድነቱ ውስጥ የምትሳተፉም ሆነ የማትሳተፉ ማኅበራት ተጋብዛችኋል::))
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
የደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል
እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት
መንፈሳዊ ጉዞ
🌼እንኳን አደረሳችሁ🌼
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
🌼እንኳን አደረሳችሁ🌼
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
🎙በደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል የእግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤታችን ከዚህ በኋላ የሚጠቀምበትን የመለያ ምልክት(Logo) በትላንትናው ዕለት ይፋ አደረገ።
ከዚህ በተያያዘ ሰንበት ት/ቤቱ አዲስ ባስተዋወቀው አርማ ላይ ያሉትን ምልክቶች ምክንያት እንደዚህ ይገልጻል።
ጉልላት፡ በዚህ አርማ ላይ የቀራንዮ ምሳሌ የሆነውንና በቤተ ክርስቲያን አናት ላይ የሚገኘውን ጉልላት በግዝፈት ለመጠቀም የተሞከረ ሲሆን በተጨማሪም የደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል የቤተ መቅደስ መለያ የሆነው አሰራር ተካትቷል። ይህም ከተጠቀምነው የዜማ መሳሪያ ጋር ለማስኬድ ምቹ ነው፡፡
ወንጌል፡ይህም የሰንበት ት/ቤት ተቀዳሚና ዋነኛው ተልዕኮ የሐዋርያት አገልግሎት የሆነውን ወንጌልን ለማሳየት ነው።
የዜማ መሳሪያ፡ ይህም በተመሳሳይ የሰንበት ት/ት ቤት አገልግሎት እንደመሆኑ መጠን ዝማሬውን የሚገልጹ ንዋያተ ቅድሳትን ከሎጎ ስራው ጋር ተስማሚ በሆነ መንገድ ለመጠቀም ተሞክሯል፡፡
በመጨረሻም ከታች የምንመለከታቸው ሦስት ደረጃዎች የቤተ መቅደሱን ዐውደ ምሕረት (የምሕረቱን አደባባይ) ለማሳየት የተሰራ ነው፡፡
📌በመጨረሻም የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት ከዚህ በኋላ የሚጠቀመው አርማ ይህንን እንደሆነ ለማሳወቅ እንወዳለን።
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል
/channel/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ፤ አሜን!
የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል
እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት
"የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነው"
፩ኛ ቆሮ ፩:፲፰
✨ መንፈሳዊ የበዓለ ንግሥ ጉዞ ✨
ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም
🗓 ከመስከረም 18 እስከ መስከረም 24/2017 ዓ.ም.
የጉዞው ዋጋ: 5450 ብር ግሸን ላይ ማረፊያ ቦታ እና ሙሉ መስተንግዶን ጨምሮ
የምዝገባ ቦታ:
🏠 በሰንበት ት/ቤቱ ሱቅ(ከታችኛው በር በስተግራ) እና
🏠 አሜን መንፈሳዊ መዝሙር ቤት (ከዋናው በር በስተቀኝ)
ለበለጠ መረጃ 📲
0913692410 / 0946817753
0919481630 / 0933186478 ይደውሉ።
📖ወደ ቤተክርስቲያን አዘውትራችሁ የምትመጡ ይህን ልመናዬን ስሙ፤ ሰነፍ የኾኑትን ወደ ቤተ ክርስቲያን የመሄድን አስፈላጊነት አስተምሯቸው፡፡ የትምህርቷን ውበት ቀምሳችኋልና እናንተ ያወቃችሁትን ሳያውቁ እንዳይቀሩ፡፡
ቤተክርስቲያን ሀኪም ቤት እንጂ የነፍስ ፍርድ ቤት አይደለችም። የኃጢአትን ስርየት ትሰጣለች እንጂ ኃጢአትን አትፈርድም፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ እንደምናገኘው ምስጋና በሕይወታችን ውስጥ እንደዚህ ያለ አስደሳች ነገር የለም፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ፣ ደስተኞች ደስታቸው ይበዛላቸዋል፡፡ የሚጨነቁት፤ ያዘኑት፣ ሰላምን ያገኛሉ፡፡ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ፤ የተቸገሩ ሰዎች እፎይታ ያገኛሉ፤ ኹሉም ከተሸከሙት ያርፋሉ፡፡
ቤተክርስቲያን ኹሉን ታቅፋለች፡፡ ውስጥ ከሆንክ ተኩላው አይገባም፣ ብትሄድ ግን አራዊቶች ይይዙሃል፡፡ ከቤተክርስቲያን አትራቅ፣ ከቤተክርስቲያን የሚበልጥ ምንም ነገር የለም። ቤተክርስቲያን ተስፋህ ናት፡፡ ቤተክርስቲያን መዳንህ ናት፡፡ ቤተክርስቲያን ከሰማያት ከፍ ትላለች፡፡ ቤተክርስቲያን ከድንጋይ ትከብዳለች፡፡ ቤተክርስቲያን ከዓለም ትስፋለች፡፡ ቤተ ክርስቲያን አታረጅም፣ ነገር ግን ሁልጊዜ እራሷን ታድሳለች፡፡
"እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበዳችሁ፤ በመከራና በኃጢአታችሁ የከበደ ኹሉ' ወደ እኔ ኑ" ይላል እግዚአብሔር፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ፡፡" (ማቴ ፲፩፥፳፰)
ይህንን ድምጽ ከመስማት የበለጠ ምን ደስታን ሊሰጠን ይችላል? ከዚህ ግብዣ የበለጠ ጣፋጭ ምንድነው? ጌታ ወደ ቤተክርስቲያን የሚጠራችሁ ለታላቅ ግብዣ ነው፡፡ ከትግል ወደ እረፍት፣ ከስቃይ ወደ እፎይታ ያሸጋግራችኋል፡፡ ከኃጢአታችሁ ሸክም ያገላግላችኋል፡፡ ጭንቀትን በምስጋና፣ ሐዘንንም በደስታ ይፈውሳል፡፡ለክርስቶስ ከሚኖረው በቀር በእውነት ነጻ፣ በእውነት ደስተኛ የሆነ ማን ነው? እንዲህ ያለው ሰው ክፋትን ኹሉ ያሸንፋል ምንም አይፈራም!ቤተ ክርስቲያን ለኹሉም መጠጊያ ሆና ቆማለች፡፡
የአምላክን ትዕዛዝ የምትፈጽም መልካም ሰው ከሆንክ ቅድስናህን ለመጠበቅ ግባ፤ ኃጢአተኛ ከሆንህ መዳንን ለማግኘት እርምጃህን ፈጠን አድርገው:: የቤተክርስቲያንን ትምህርት ሳይሰሙስ እንዴት ነፍስን ወደ መልካም መንገድ መምራት ይቻላል?የእግዚአብሔር ቃል 'ብርሃን' በመባል ይጠራል፤ ፀሐይ ከምታፈልቀውና እኛም ከምናየው ብርሃን፣ እጅግ በጣም የከበረ ብርሃን፣ የነፍሳችንን ጥልቀት የሚያበራ ነው፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ ስለዚህ እውነት እንዲህ ሲል መስክሯል፣ “በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው::"
ከእናንተ መካከል በታማኝነት ቤተ ክርስቲያን የምታገለግሉ፤ 'ስራ በዛብኝ፣ ልመጣ አልችልም' እንዳይሉ ሌሎቹን ምከሩ፡፡ ወደ ንጉሡ ግብዣ የተጋበዙ ግን መምጣት ያልቻሉትን እንደ ምሳሌ እንመልከት፡፡ አንደኛው አምስት ጥማድ በሬዎችን ሊገዛ እንደሄደ ተናገረ፣ ሌላው አዲስ መሬትን ሊገዛ እንደሄደ ሲናገር ሌላው ደግሞ ሚስት ማግባቱን ተናገረ፡፡ ምክንያታቸው ምንም ይሁን ምን፣ ንጉሡ ግብዣውን ንቀው ስለቀሩ የሚታገሳቸው ይመስልሃል? እናም ንጉሡን በሰበብ አስባቡ አታናዱት፡፡
ከጊዜህ ላይ አንድ ሰዓት ያህል እንኳን መቆጠብ ያቅትሃል? ቤተክርስቲያንን ከተሳለሙ በኋላ ወደ ሥራ መሄድ በእውነት ይህን ያህል ከባድ ነውን? አንድ ሰው ወርቅ፣ ብር፣ ማር ወይም ወይን በነጻ እየሰጠ ነው ቢባል፤ ማንም ሳይቀድማችሁ ለመድረስ አትቸኩልም? ነገር ግን፣ ከወርቅ የሚበልጥ፣ ከማርም ከወተትም የሚጣፍጠውን የእግዚአብሔርን ቃል ለማድመጥ ወደ ቤተክርስቲያን የምትመጡት አልፎ አልፎ ነው፡፡
ስለዚህም፣ ይህን ችላ ማለታችሁን አውግዣለሁ፤ ለእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ያላችሁን ግድየለሽነት እቃወማለሁ፡፡ ከመንፈሳዊ ትምህርቶቿ በመራቃችሁ፣ በውስጣችሁ የእግዚአብሔር ፍራቻ የለም፤ እግዚአብሔርን የማትፈራ ነፍስም ለኃጢአት የተገዛች ትሆናለችና ነፍሳችንን እንጠብቃት፡፡
✍ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው
/channel/EMislene
"ለምኑ ይሰጣችኋል ፡ ፈልጉ ታገኛላችሁም፡ ደጅ ምቱ ይከፈትላችኋልም።" ማቴ 7፥7
📌ለ6ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ
የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት ሕጻናትና ማዕከላዊ ክፍል ከፈተናው አስቀድሞ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የጸሎት መርሐ ግብር አዘጋጅቷል።
🗓 ከሰኔ 9 እስከ ሰኔ 11, 2016 ዓ.ም
🕐 ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ
📍 በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ
በመርሐ ግብሩ ላይ በፈተና ወቅት ማድረግ ስለሚገቡ ነገሮች ከታላላቅ እኅትና ወንድሞች ገለጻ ይደረጋል።
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ!
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
📎እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት በሰላም አደረሰን እያልን የንግሥ በዓሉ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በየትኞቹ ገዳማትና አድባራት እንደሚከበር ልንጠቁማችሁ ወደድን።
1)ማሕደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ልደታ /ክ/ከ ልደታ
2) አቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤ/ክ
ልዩ ስም፦አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ጋራው መድኃኔዓለም
3)መካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ መካኒሳ
4) የካ ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት እና መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን
ልዩ ስም፡- የካ ወረዳ 9
5)ጃቴ መካነ ሕይወት ቅድስት ኪዳነምሕረት ካቴድራል
ልዩ ስም፦አቃቂ ክ/ከ 08
6) ገነተ ኢየሱስና ገነተ ማርያም አብያተ ክርስቲያናት
ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ፈረንሳይ 41 ኢየሱስ
7)ገዳመ ኢየሱስ
ልዩ ስም፡-ልደታ ክ/ከ ሆላንድ ኤምባሲ
©ንግሥ
http://www.debregelila.org
ነገ ሰኞ ከምሽቱ 2:00 ላይ ይጠብቁን!
ሊንኩን ከዚህ በታች ያገኙታል!
👇👇👇👇👇👇👇👇
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
በመምህር ዘላለም ወንድሙ
#share
#subscribe
#Like
📖 ሠላሳ ዓመት ከጌታ ጋር
እመቤታችን ጌታን ጸንሳ ከወለደችው በኋላ እስከ ሠላሳ ዓመቱ ድረስ እንደ ልጅነቱ እያገለገላት ፣ እንደ አምላክነቱ እያገለገለችው አብራው በአንድ ቤት ውስጥ ኖራለች፡፡
ሌላውን እንተወውና ይኼ ነገር ብቻ ለማሰብ ያስጨንቃል! ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ አንድ ቤት ውስጥ መኖር እንዴት ያለ ነገር ነው? ልብ በሉ ድንግል ማርያም ጠዋት ከእንቅልፍዋ ስትነቃ "እንዴት አደርህ?" የምትለው ፈጣሪዋን ነበር:: ማታ ስትተኛ "ደህና እደሪ" የሚላትም አምላክዋ ነበር:: የማይተኛው ትጉሕ እረኛ በተኛች ጊዜ ሕፃን ሆኖ ከአጠገብዋ ያደረ ከእመቤታችን በቀር ማን አለ?
ኪሩቤልና ሱራፌል ቅዱስ ቅዱስ የሚሉትን አምላክ እንደ እናት "እሹሩሩ" ብላ ያስተኛች እርስዋ ነበረች:: ምድርን በአበባ ልብስ የሚያስጌጠውን ጌታ በተኛበት ያለበሰችውም እርስዋ ነበረች:: ዓለምን በእጆቹ የያዘውን ጌታ ክንዶችዋን ያንተራሰችው እርስዋ ነበረች:: እነዚያን ሌሊቶች ድንግል ማርያም እንዴት አሳልፋ ይሆን? በሕልምም በእውንም ከፈጣሪ ጋር ማሳለፍ እንዴት ያለ ጸጋ ነው?
ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ነው፡፡ እመቤታችን ከልጅዋ ጋር ለሠላሳ ዓመታት አብራ በአንድ ቤት ስትኖር የነበራቸው ንግግር ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር እንደመሆኑ ጸሎትም ጭምር ነበር፡፡
የጠዋትና ማታ ጸሎትሽ ከልጅሽ ጋር ማውራት የሆነልሽ : ልጅሽ የሚሠጥሽ መልስ የፈጣሪ መልስ የሆነልሽ እመቤቴ ሆይ ስላንቺ ክብር ማሰብ ምንኛ ያስጨንቃል?
እስቲ ረጋ ብላችሁ አስቡት! እመቤታችን እና ጌታችን በእነዚያ ሁሉ ዓመታት ምን ሊነጋገሩ ይችሉ ነበር? ከእርስዋ በቀር ማን ይነግረናል? ድንግል ሆይ አንቺ ካልነገርሽን ማን ይነግረናል? ለማዕድ ስትቀመጡ ምን ብሎ ጸልዮ ይሆን? እንደ ሐዋርያቱ ቆርሶ ሠጥቶሽ ይሆን? ውኃን እንዲጠጣ ሞልተሽ ስትሠጪው ውቅያኖስን እንዴት በውኃ እንደሞላ ነግሮሽ ይሆን?
በእርግጥ በእነዚያ ዓመታት ክርስቶስ ለእናቱ ምን ምን ሲነግራትስ ኖሮ ይሆን? ስለየትኛውስ ምሥጢር ሲገልጥላት ነበር? ገና የዐሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ሳለ በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ያነጋገሩት የአይሁድ መምህራን ‹በማስተዋሉና በመልሱ ሲገረሙ ነበር› እመቤታችን ከሕጻንነቱ ጀምሮ እስከ ሠላሳ ዓመቱ ድረስ አብራው ስትኖር በስንቱ ነገር ስትደነቅ ኖራ ይሆን? /ሉቃ. ፪፥፵፯/
እንደ መንፈሳዊት እናት ድንግል ማርያም ለልጅዋ የትኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እየነገረች አሳድጋው ይሆን? ሙሴ ስላያት ዕፀ ጳጦስ ታሪክ አልነገረችው ይሆን? ታሪኩን ሰምቶ "ያቺ ዕፅ አንቺ ነሽ እሳቱ ደግሞ እኔ ነኝ"ብሏት ይሆን? ውኃ ስለፈለቀበትና እስራኤል ስለጠጡበት ዓለት ነግራው ይሆን? እርሱስ "ያ ዓለት እኮ እኔ ነበርሁ" ብሎአት ይሆን?
ብሉይን ስታነብ ሐዲስን እየተረጎመ እንደ ኤማሁስ መንገደኞች ልብዋን አቃጥሎት ይሆን? ሉቃ. ፳፬፥፴፪/ ጠቢበ ጠቢባን ሊቀ ሊቃውንት ኢየሱስ ክርስቶስ በቤትሽ ጉባኤ የዘረጋብሽና ያስተማረሽ ድንግል ሆይ አንቺ እንደሆንሽ በልብሽ ከመጠበቅ ውጪ ብዙ አትናገሪም:: ሆኖም ልጅሽ ምን ምሥጢር ነግሮሽ ይሆን?
ኤልሳቤጥ እንኳን ዮሐንስን ጸንሳ ስለጽንሱ የምትለው ብዙ ነገር ነበራት:: ፈጣሪ በአንቺ ዘንድ ያደረ ድንግል ሆይ አንቺስ ምን ትነግሪን ይሆን? "የመለኮት እሳት በሆድሽ ባደረ ጊዜ ልብሱ እሳት ቀሚሱ እሳት ነው:: እንደምን አላቃጠለሽም? የኪሩቤል ዙፋን በሆድሽ ውስጥ ወዴት ተዘረጋ? በግራ ነው ወይንስ በቀኝ? ታናሽ አካል ስትሆኚ ይህ ሁሉ እንዴት ሊሆን ይችላል?" እያልን ከአባ ሕርያቆስ ጋር እንጠይቅሻለን::
እንዳንቺ ፈጣሪውን የሚያውቅ ፍጡር የለምና የዓለም የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት : የነገረ መለኮት ምሁራን : የወንጌሉ ተንታኞች ሁሉ ከአንቺ እግር ወድቀው እንደ አዲስ ስለ ክርስቶስ ሊማሩ ይገባቸዋል:: ልህቅተ ሊቃውንት እመቤታችን ሆይ ሊቃውንት ሁሉ ያንቺ ተማሪዎች ናቸው:: ባለ ቅኔዎች ሁሉ ባንቺ ፊት ገና ፊደል አልቆጠሩም:: ሰውና መላእክት አንድ ላይ ተሰልፈው "ብርቱ የሚሆን በአንቺ ያደረገውን ታላቅ ነገር" ሊሰሙ ይጠባበቃሉ:: ወዳጄ ጥቅስ ፍለጋህን ትተህ እግዚአብሔርን በእቅፍዋ ከያዘችው ቃሉን በሹክሹክታ በጆሮዋ ከሰማችው ድንግል እግር ሥር እንደ እኔ ብትደፋ ይሻልሃል:: የእግዚአብሔርን እጆች ይዛ የመጀመሪያዎቹን የሕፃንነት እርምጃዎቹን እንዲራመድ የመራችውን ድንግል መቆም ያቃተንን ደካሞች እንድትመራን አብረን ደጅ ብንጠናት ይሻላል::
እነ ጴጥሮስ በቅዱሱ የታቦር ተራራ ከጌታ ጋር ነበሩ ፊቱ ሲያበራ አይተው በዚህ ካልኖርን ብለው ተመኝተው : ኤልያስና ሙሴን አግኝተው ነበር:: ሠላሳ ዓመት ከጌታ ጋር የኖርሽው እመቤታችን ሆይ የልጅሽ ልብሱ ስንት ቀን አብርቶ ይሆን? ከነቢያትስ እነማንን አምጥቶ አሳይቶሽ ይሆን? እንደ ጴጥሮስ "ሦስት ዳስ እንሥራ" የማትይዋ የእግዚአብሔር ማደሪያ ድንኳን ሆይ ቤትሽ ደብረ ታቦር ሆኖልሻልና ልጅሽ ምን አሳይቶሽ ይሆን? ከእግዚአብሔር አብ "ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሚው" የሚል ድምፅ መስማት የማያስፈልግሽ "ለእኔም ልጄ ነው" ማለት የምትችይዋ እናት ሆይ እንደ እግዚአብሔር አብ "የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ" ለማለት ሥልጣን የተሠጠሽ ሆይ ሠላሳ ዓመት ከጌታ ጋር መኖርሽን ባሰብሁ ጊዜ ጠባብዋ ሕሊናዬ ኃጢአት ያደቀቃት ሰውነቴ እጅግ ተጨነቀች::
ዮሐንስ በፍጥሞ ደሴት ብዙ ራእይ አይቶ "በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርኩ" ብሎ ጻፈ:: ሠላሳ ዓመታት የጌታ ቀን የሆነላት በመንፈስ የነበረች ድንግልስ ስንት ራእይ አይታ ይሆን?
መላ የሰውነታችን አካል ሁሉ አፍ ቢሆን የእርስዋን ክብርና ምስጋና ተናግረን መፈጸም አንችልም:፡
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የቴሌግራም ቻናል
/channel/EMislene
"ለምኑ ይሰጣችኋል ፡ ፈልጉ ታገኛላችሁም፡ ደጅ ምቱ ይከፈትላችኋልም።" ማቴ 7፥7
📌ለ8ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ
የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት ሕጻናትና ማዕከላዊ ክፍል ከፈተናው አስቀድሞ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የጸሎት መርሐ ግብር አዘጋጅቷል።
🗓 ከሰኔ 1 እስከ ሰኔ 3, 2016 ዓ.ም
🕐 ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ
📍 በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ
በመርሐ ግብሩ ላይ በፈተና ወቅት ማድረግ ስለሚገቡ ነገሮች ከታላላቅ እኅትና ወንድሞች ገለጻ ይደረጋል።
ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ!
የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅዱሳን አበው ሐዋርያት ትውፊት በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በርካታ አጀንዳዎችን በመቅረጽ ውይይት ሲያካሄድ ሰንብቷል፡፡
ምልዓተ ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት፣ ለመንፈሳዊ ዕድገትና ለምእመናን ደኅንነት ትኩረት በመስጠት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
፩.በቅድስት ቤተ ክርስቲያንና በሀገራችን መንግሥት መካከል ሊኖር ስለሚገባው መልካም የሥራ ግንኙነት በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሚመካከር የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ልዑክ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፤
፪.በመላው ሀገራችን በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንደቀጠለ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን በእጅጉ አሳዝኗል፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት ተቆጥበው የተፈጠረውን አለመግባባትና ግጭት በውይይትና በምክክር እንዲፈቱ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንኦት ጥሪውን ያቀርባል፤
፫.በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት ምክንያት ለፈረሱ የቤተ ክርስቲያናችን ይዞታዎች የከተማ አስተዳደሩ ምትክ ቦታ በመስጠትና ቤተ ክርስቲያናችን ወደ መልሶ ማልማት እንድትገባ ድጋፍ በማድረግ፤ በተለይም ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ በፈረሰው የጽርሐ ምኒልክ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕንፃ ምትክ በከተማ አስተዳደሩ ሙሉ ወጭ ተጨማሪ ምድር ቤትና የቦታ ስፋት ያለው B+G+4 ሕንፃ ገንብቶ ለማስረከብ ቃል በመግባትና የቤተ ክርስቲያናችን የበላይ ኃላፊ አባቶች በተገኙበት የመሠረት ድንጋይ እንዲጣል ማድርጋቸውን ቅዱስ ሲኖዶስ ከምስጋና ጋር የተቀበለው ሲሆን በተሰጠን ምትክ ቦታ ላይም የከተማው ፕላን በሚፈቅደው መሠረት የመልሶ ማልማት ሥራው እንዲከናወን ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
፬.የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተቋቋመበት አዋጅ መረዳት እንደሚቻለው ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ ሁኔታ ሀገራዊ ችግሮችን በምክክርና በውይይት ለመፍታት የተቋቋመ መሆኑን ተረድተናል፡፡ ይሁን እንጅ ሀገረ መንግሥትን ከመመሥረት ጀምሮ በአስታራቂነትና በሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ለሆነችው እናት ቤተ ክርስቲያን እስከአሁን ድረስ በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ ሳይኖር ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታንና አጀንዳ መረጣ አጠናቆ ወደ ምክክር ትግበራ እየገባ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን ቅር አሰኝቷል፡፡ በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡
፭.የብፁዓን አባቶች የዝውውርና የአህጉረ ስብከት ሥያሜን አስምልክቶ የቀረቡ ጥያቄዎችን ምልዐተ ጉበኤው ተመልክቶ ተገቢውን ውሳኔ አሳልፏል፤
፮.የሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በሰፊው ከተወያየ በኋላ በረቂቅ አዋጁ ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ብሎ ያመነባቸውን የማሻሻያ ሐሳቦች በማዘጋጀት ለሚመለከተው መንግሥታዊ ተቋም እንዲላክና ረቂቅ አዋጁ ከመጽደቁ በፊት የተሰጡት የማሻሻያ ሐሳቦች በረቂቁ ስለመካተታቸው ክትትል የሚያደርግ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡
፯.በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ተመሥርቶ አባታዊ ምክርና ተግሣጽ ማስተላለፍ ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው መሆኑ ቢታወቅም በሀገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተፈጠሩ አለመግባባቶች የተከሰቱትን ወቅታዊ ችግሮች አስመልክቶ እየተላለፉ ያሉ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ መልእክቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ የማይቀበላቸውና በጥብቅ የሚቃወማቸው መሆኑን እየገለጸ ወደፊት እንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጸም ለማድረግ ይቻል ዘንድ ወጥ የሆነ የመግለጫ አሰጣጥና የትምህርተ ወንጌል ተልእኮ ሕገ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምልዐተ ጉበኤ እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
፰.ግብረ ሰዶማዊነትና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ የሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣ ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃዱ በተገለጠባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ የተከለከለ፣ በቀኖናተ ቤተ ክርስቲያን፣ በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች፣ በሥነ ልቦና ደንቦች የተወገዘ፣ ሥነ አእምሮዊ ሚዛንን የሚያዛባ፣ ግለሰባዊ ማንነትን፣ ቤተሰባዊ ሕይወትን፣ ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ እያወገዘ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና የግብረ ሰዶማዊነትን ኃጢአት በተመለከተ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ ዓለም አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
፱.በደቡብ የሀገራችን ክፍል የቤተ ክርስቲያኒቱን አብነት ትምህርት ከማስፋፋትና ከፍ ያለ መዐርግ ከመስጠት አንፃር የጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት የዝጊቲ ደብረ ሰላም አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የአራቱ ጉባኤያት ማስመስከሪያ ትምህርት ቤት እንዲሆን በቀረበው ጥናት መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ ለምሥክር ጉባኤ ቤቱ ዕውቅና በመስጠት ወደ ትግበራ እንዲገባ ወስኗል፡፡
፲.ከሀገራችን ውጭ ባሉ አህጉረ ሰብከት መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚላኩ አገልጋዮች በክፍሉ ሊቀጳጳስ ሲጠየቅ በሙያ ብቃታቸው፣ በምግባራቸውና በመንፈሳዊነታቸው የተመሰከረላቸው አገልጋዮች ከሁሉም አህጉረ ስብከት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አቅራቢነት በውድድር እየተለዩ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲላኩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
፲፩.የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ የዐሥር ዓመት መሪ ዕቅድ በማጽደቅ ወደ ትግበራ እንዲገባ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ በዚሁም መሠረት ለአፈጻጸሙ ያመች ዘንድ በባለሙያዎች ተዘጋጅቶ የቀረበውን መዋቅራዊ አደረጃጀት በማጽደቅ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑና በቃለ ዓዋዲው ተካቶ ሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
፲፪.በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተዘጋጅቶ የቀረበውን የ2017 ዓ.ም. ዓመታዊ በጀት በማጽደቅ በሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
በአጠቃላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ላለፉት ተከታታይ ቀናት በመንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየትና ተገቢውን ውሳኔ በማስተላለፍ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በጸሎት አጠናቅቋል፡፡ መሐሪና ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን፣ ለሕዝባችን፣ ለዓለሙ ሁሉ ሰላሙን፣ ፍቅሩንና አንድነቱን ይስጥልን፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ.l።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ግንቦት ፳፱ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. ኢትዮጵያ አዲስ አበባ
✍የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
📌 የቴሌግራም ቻናል፡
/channel/EMislene
📌 የዩቲዩብ ቻናል፡
http://youtube.com/
@EMislene