emislene | Unsorted

Telegram-канал emislene - Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

-

ይህ ይፋዊ የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት ገጽ ነው፡፡ በዚህ ገጽ - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት የጠበቁ ትምህርቶችን እናሰራጫለን፡፡ - የቅድስት ቤተክስቲያናችን እና የሰንበት ት/ቤቱን እንቅስቃሴ ወቅታዊ መረጃ እናደርስበታለን፡፡ ገጹን ለሌሎችም እያጋራችሁ የቤተክርስቲያናችንን አገልግሎት እናፋጥን፡፡ @EMislene_28Bot

Subscribe to a channel

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

የአማኑኤል ወዳጅ እግዚአብሔር ምስሌነ አስተምራኛለች፥ ከማዕዷ ተካፍያለው፥ አገልግሎቷን እወዳለው፥ እደግፋለው የሚል የልጆቿን በአንድነት መሰባሰብ የሚወድ ሰው፤ እንኳን ሊቀር ለቀሩት የሚቆጭበት አቅም ላጡት ስፖንሰር ሆኖ ባልንጀሮቹን የሚጋብዝበት የእማማ ምስሌነ ልጆች መሰባሰቢያ ጉዞ።

8ኛው ፍኖተ ሕይወት ታህሳስ 13 ነው። ልጇ ስለሆንክ/ሽ አትቀርም/ሪም ለማስታወስ ያህል ነው።

ግብዣውም የእርሷ ነው ተሰናድታ አሰናድታ እየጠበቀችን ነው።

አትቀሩም አይደል?

egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

8ኛው ዙር ፍኖተ ሕይወት መንፈሳዊ ጉዞ

"ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው" ዕብ 5፥10

ወደ:- ጥንታዊትና ታሪካዊት ስእለት ሰሚዋ ሆለታ ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን

📌 ከአዲስ አበባ በ35 ኪ ሜ ቅርብ ርቀት የሚገኝ ቤተክርስቲያን ሲሆን ቤተክርስቲያኑ ከዋናው መንገድ እጅግ ቅርብ በሆነ ቦታ ይገኛል። የቤተክርስቲያኑ ሊቃውንት አባቶች እና የአካባቢው ምእመናንም በጉጉት እየጠበቁ ይገኛሉ •።

የጉዞ ቀን:- ታኅሳስ 13 2017ዓ.ም 

የጉዞ ዋጋ መስተንግዶን ጨምሮ :- 430 ብር

"በአካል መገኘት ባይችሉ እንኳ መባዎትን እናደርሳለን"

ለበለጠ መረጃ

📱0930483649
📱0946817753
📱0919481630
📱0942388191   ላይ ያገኙናል።

https://youtu.be/O6pMSXeHPes?sub_confirmation=1

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

ከፍተኛ የሃይማኖት ነፃነት ችግር አለባት ተብላ በምትታማው ኤርትራ ውስጥ ፈቃድ ከተሰጣቸው አራት የእምነት ተቋማት መካከል አንዱ የሆነችው የኤርትራ ቤተክርስቲያን በኅዳር ፴/፳፻፲፯ ዓ. ም. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስን ፮ኛው ፓትርያርክ አድርጋ መርጣለች።

በዚህ ምርጫ ላይ 85 የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን ጨምሮ የየገዳማቱ ተወካዮች፣ የአኅጉረ ስብከት ተወካዮች፣ የነገረ መለኮት ተወካዮች በተገኙበት ተካሂዷል።

በምርጫው ላይ በብፁዕ አቡነ ዳንኤል የማዲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ የሚመራ 5 የግብፅ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የተገኙ ሲሆን በምርጫው ላይ ከቀረቡት ዕጩ ፓትርያርኮች

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ: ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ባስልዮስ: የመንበረ ፓትርያርክ ዋና ሥራ አስኪያጅ
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ: የደቡብ መንደፍራ ሊቀጳጳስ መካከል ብፁዕ አቡነ ባስሎዮስ ፮ኛው ፓትርያርክ ሆነው ተመርጠዋል።

የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. ጀምሮ ኤርትራ ከኢትዮጵያ መገንጠልና በሁለቱ ሀገራት መካል በተከሰተ ግንኙነት መሻከር ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ተነጥላ እስከ ፲፱፻፺፩ በግብፅ ቤተክርስቲያን ሥር የነበረች ሲሆን ከ፲፱፻፺፩ ዓ.ም. ጀምሮ በኢትዮጵያ እና ግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ዕውቅና በአፍሪካ ምድር ሦስተኛዋ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መንበረ ፓትርያርክ ሆናለች።

የቤተክርስቲያኒቱ የመጀመሪያው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ፊሊጶስ ከ፲፱፻፺፩ ጀምሮ ለሁለት ዓመት፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ያዕቆብ ለ 2 ዓመት በፓትርያርክነት መርተው ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉ ሲሆን ሦስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ አትናቴዎስ ከተሾሙ ሁለት ዓመት በኋላ በሀገሪቱ መንግስት ጫና ከፕትርክና እንዲነሱ ተደርገዋል።

የኤርትራ ቅዱስ ሲኖዶስ ዘግየት ብሎም በቅዱስነታቸው ላይ ያስተላለፈው ውግዘት ቤተክርስቲያንን ለሁለት የከፈለ ሲሆን በርካታ በአሜሪካ፣ አውሮፓና፣ አውስትራሊያ የሚገኙ ጳጳሳት፣ ማኀበረ ካህናትና ምዕመናን ውግዘቱን በመቃወም ከእርሳቸው በኋላ የተነሱትን ሁለት ፓትርያርኮች ማለትም ለ፯ ዓመታት ቤተክርስቲያኗን ለመሯት ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስና በተሾሙ በዓመታቸው ላረፉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ዕውቅና ሳይሰጡ ቀርተዋል።

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ አትናቴዎስ ውግዘት፣ የ፰ ዓመታት ግዞትና ፖለቲካዊ የቁም እስር የኤርትራ ቤተክርስቲያንን ከአኀት አብያተ ክርስቲያናትና ከዓለም አቀፉ ማኀበረሰብ መገለልና ጫና በማምጣቱ ምክንያት ቤተክርስቲያኒቷ ላለፉት ሁለት ዓመታት ያለ ፓትርያርክ በዓቃቤ መንበር እየተመራች ግንኙነቷን ማደስ ላይ ትኩረቷን ስታደርግ ቆይታለች።

እኒሁ በዲያስፖራው የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አኅጉረ ስብከቶች ከ፮ኛው የፓትርያርክ ምርጫ ቀደም ብሎ ባወጡት መግለጫ በ፳፻፲፭ ዓ.ም. ያረፉት የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ አትናቴዎስ ውግዘት ባልተነሳበትና ዕርቀ ሰላም ባልተከናወነበት የሚካሄደውን ምርጫ እንደማይቀበሉት አሳውቀዋል።

የ፮ኛው ፓትርያርክ በዓለ ሲመት በጥር ፲፰/፳፻፲፯ በታላቁ የአስመራ ርእሰ አድባራት ቅድስት ማርያም ካቴድራል ይካሄዳል።

የብጹዕ አቡነ ባስሊዮስን መመረጥ በታህሳስ ፪ ሳምንታዊ የረቡዕ ትምህርት ታላቅ ስኬት ብለው የጠሩት የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ታዎድሮስ የኤርትራ ቤተክርስቲያን ለተልዕኮዋ፣ ለአንድነቷና ለክርስቶስ ክብር እንድትተጋ ጥሪያቸውን ያቀረቡ ሲሆን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክም ለመላው የኤርትራ የካህናትና ምእመናን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን አስተላፈዋል።

ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ

/channel/EMislene

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

🗓ታኅሣሥ 3 - 2017 ዓ.ም.

⏰ከምሽቱ 12:15 ጀምሮ

🪧በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ

የጀርባው ዋጋ 1100 ብር
          በቅናሽ 1000  ብር

መጽሐፉን በሰንበት ት/ቤቱ ሱቅ ያገኙታል።

ቅናሹ የሚቆየው እስከ ዳሰሳው ቀን ወይም ዛሬ ማታ ድረስ  ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን።

ለበለጠ መረጃ 0989196891

ወይም በቴሌግራም : @memmsuk

ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ

/channel/EMislene

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

ስንቶቻችን ነን ቤተክርስቲያናችን የምትጠቀምባቸውን ንዋየ ቅድሳት ምሥጢራቸውን የምናቀው?

ዛሬ የጻሕል እና የጽዋዕ አገልግሎታቸውንና ምሥጢርን እንመልከት።

ጻሕል :- ከወርቅ፣ ከብር ፣ ከነሐስ እና ከብረት የሚሰራ ጎድጓዳ ወይም ዝርግ ወጭት/ሳሕን ነው። ጻሕል የኅብስቱ ማስቀመጫና ማክበሪያ ሆኖ ልዩ ክብርና ምሥጢር አለው።
ምሥጢሩ:- ጻሕል የእመቤታችን ምሳሌነው፤ እመቤታችን ጌታን በማህፀኗ የመሸከሟ ምሳሌ ነው፤ ጌታችን የተወለደበት ግርግም የጻሕል ምሳሌ ነው፤ተወልዶ አድሮበታልና። ማቴ. ፲፬÷፰ ፣ ማቴ. ፳፫÷፳፭

ጽዋዕ :- ከወርቅ ፣ ከነሐስ፣ ከመዳብና ከብረትይሠራል ፤ ለመጠጫ የሚሆን በተለይ ለቁርባን ጊዜ  የጌታችን ክቡር ደሙን የሚይዝ፣ የሚከብርበት ቅዱስ ዕቃ ነው። ምሥጢሩ የእመቤታችን ማሕፀን ነው። አብሳሪው መልአክ ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መጥቶ ሲያበስር እርሷ “እኔ ድንግል ሳለሁ ይህ እንዴት ይሆናል?” ባለችው ጊዜ መልአኩም “መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል። ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።” ሉቃ. ፩÷፴፭ ሲላት እመቤታችንም “እነሆ የጌታ ባርያ  እንደ  ቃልህ ይሁንልኝ” ሉቃ. ፩÷፴፰ ባለችው ጊዜ አካላዊ ቃል በማሕፀኗ አደረ። የደመ-መለኮት ማደሪያ ጽዋውም የማሕፀነ ማርያም ምሳሌ ሆኗል።

በዕለተ ሐሙስ ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ  “ይኼ በነገው ዕለት ለዓለም ድኅነት የሚፈሰው ደሜ ነው፤ ሁላችሁም ጠጡት” ማቴ. ፳፮÷፳፯ በጽዋዕ የሚቀርብበትም ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለኛ ኃጢያትና በደል ማስተስረያ በዕለተ ዓርብ በዕፀ መስቀል ላይ ደሙን ሲያፈስ መላእክት የሚንጠባጠበውን ክቡር ደሙን የተቀበሉበት ጽዋዕ ስለሆነ ነው። ራዕይ፲፮÷፩

/channel/EMislene

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

🗓ታኅሣሥ 3 - 2017 ዓ.ም

⏰ከምሽቱ 12:15 ጀምሮ

🪧በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ።

ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ

📌የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

https://youtu.be/RlWa2il21Jw?si=mol1_tWQ6Xi1aye7?sub_confirmation=1

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

https://www.youtube.com/channel/UCNjEKBSeBmsSGrHdlN3aSpQ?sub_confirmation=1

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

ምጽዋትን መስጠት

from debregelila.org

👇👇👇👇👇👇👇

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

https://youtu.be/gVLjHkGz54U?si=W8yX1kfDP1ipCPwZ

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

  #47ኛው_ዙር 3 ቀን ቀረው

📪በደብረ ገሊላ ቅዱስ ዐማኑኤል ካቴድራል

EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

በቅርብ ቀን...

ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ

egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

ንዋየ-ቅድሳት ከሁለት ቃላት የወጣ ሲሆን
ንዋይ:- ማለት ቅርስ ንብረት ጥሬ ዕቃ ማለት ነው።
ቅድሳት:- ማለት ደግሞ ቅድስና ክብር ንጹሕ ጸጋ ያላቸው መሆናቸውን የሚያመለክት ነው።

ንዋየ ቅድሳት ከተመረጡ የተመረጠ ከተለዩ የተለየ ለዘለዓለሙ ስሙ የሚኖርበት ምርጥ ዕቃ ማለት ነው። ይህም ስለሆነ ነው ዕቃው ወደ ቤተመቅደስ ሲገባ ተባርኮና ተጸልዮበት የሚገባው። ከቡራኬ በኋላ ግን ተራ ዕቃ የነበረው ንዋየ ቅድሳት ሆኖ ለቤተመቅደስ የአምልኮ ሥርዓት መፈጸሚያ የክብር ዕቃ በመሆን ለአገልግሎት ይውላል። ንዋየ ቅድሳት በአጠቃላይ ለቤተ መቅደስ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች የሚጠሩበት ስም ነው።

የንዋየ ቅድሳትን አዘገጃጀትና አጠቃቀም በድኅረ ገጻችን ላይ ያንብቡ።

👉ንዋየ ቅድሳት

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

📚ከመደርደሪያችን

🗓ሐሙስ ኅዳር 5 - 2017 ዓ.ም

⏰ከምሽቱ 12:30

🪧በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ።

ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ

📌የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

🎙በደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት የሕፃናት እና ማዕከላዊ ክፍል የቀዳማይ ፩ እና ፪ አባላት በኅዳር 29 እና በታኅሣሥ 5 ወደ መልዕልተ አድባራት ዳግማዊ ጎልጎታ ቀራንዮ መድኃኔዓለም እና ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ የአንድነት ጉዞ አካሄደዋል።

   በጉዞውም ስለደብሩ አመሠራረት ታሪክ ሰምተው በደብሩ የሚገኘውን ሙዚየም የጎበኙ ሲሆን ከጉብኝቱም በኋላ በተመረጠ ርዕስ ውይይት አካሄደው ልዩ ልዩ መርሐ ግብራት ከቀረቡ በኋላ በሰላም ወደ ደብራችን ተመልሰዋል።


egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

https://vm.tiktok.com/ZMkFoajkx/

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

🎙በሰንበት ት/ቤታችን የተዘጋጀው ከመደርደሪያችን የተሰኘው የመጽሐፍ ዳሰሳ መርሐ ግብር በትላንትናው ዕለት ተከናውኗል ።

በመርሐ ግብሩም  "አሐቲ ድንግል" የተሰኘው መጽሐፍ በዮሴፍ ፍስሐ አማካኝነት በልዩ እና ባማረ ሁኔታ ተዳሷል።

ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ!

egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

🎙የኤርትራው አዲሱ የፓትርያርክ ምርጫና ፈተናዎቹ

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

https://youtu.be/O6pMSXeHPes?sub_confirmation=1

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

🎙በደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤታችን በሚገኙት መንፈሳዊ ማኅበራት እሑድ  ኅዳር 29 - 2017 ዓ.ም ልዩ የአንድነት መርሐ ግብር የተከናወነ ሲሆን በዕለቱም  ዝማሬ፣ ቃለ መጠይቅና መነባንብን ጨምሮ ሌሎች መርሐ ግብራት በማኅበራቱ አባላት ቀርበዋል።

ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ!

የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ መግባት፡

from debregelila.org

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

📚ከመደርደሪያችን

🗓ታኅሣሥ 3 - 2017 ዓ.ም

⏰ከምሽቱ 12:15 ጀምሮ

🪧በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ።

ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ

📌የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

ከንስሐ ርቀን ይቅርታን አናገኝም፤ ንስሐ ለተጠመቁ ሰዎች ከጥምቀት በኋላ የተሰጠች ሀብት ናት፡፡ ይህንንም የሚያስረዳ ነገር በጥምቀት ከእግዚአብሔር ከምትገኝ ልጅነት ሁለተኛ ማዕረግ ናት፡፡ በሃይማኖት ገንዘብ ያደረግነው የመንግሥተ ሰማይ መያዣ ናት፡፡

በንስሐ ምክንያት የእግዚአብሔርን ቸርነት እናገኛለን፡፡ ንስሐ ለሚሿት ሰዎች የተከፈተች የይቅርታ በር ናት፡፡ በንስሐ በርነት ከፈጣሪ ወደሚገኝ ቸርነት እንቀርባለን፡፡ መከላከያ ከሚሆን ከንስሐ ርቀን ይቅርታን አናገኝም፡፡

አምላክ የጻፈው መጽሐፍ እንደተናገረ ሁላችን በድለናልና ያለ ዋጋ በይቅርታው ከኃጢአት እንነጻለን፡፡ ንስሐ እግዚአብሔርን በመፍራት፣ በሃይማኖትና በልቡና የምትገኝ ሁለተኛ ጸጋ ናት፡፡ ሀብታተ ምስጢራት ከሚገኙበት ከመንፈሳዊ ፍቅር እስክንደርስ ድረስ የሚጠብቀን መንፈሳዊ ዕውቀት ነው፡፡

ማር ይስሐቅ

EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

📚ከመደርደሪያችን

🗓ታኅሣሥ 3 - 2017 ዓ.ም

⏰ከምሽቱ 12:15 ጀምሮ

🪧በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ።

ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ

📌የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

📎ኅዳር 6

✨✨✨እንኳን ክብር ይግባውና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከአረጋዊው ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ከስደት በሚመለሱ ጊዜ ወደ ደብረ ቊስቋም ገብተው በመንገድ ጒዞ ካገኛቸውም ድካም ላረፉበት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን✨✨

📌እናስተዋውቃችሁ

አስደናቂውን የ እንጦጦ መንበረ ንግሥት ቁስቋም ማርያም ቤተ ክርስቲያን ታሪክ በድኅረ ገጻችን ላይ ያንብቡ።

👉እንጦጦ መንበረ ንግሥት ቁስቋም ማርያም ቤተ ክርስቲያን👈

      🌺መልካም በዓል🌺

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

የቅዱስ ጳውሎስ ሦስት ጉዞዎች

የመጀመሪያው ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ከተመለሰ በኋላ በልዑል እግዚአብሔር ጥሪ በአህዛብ ሀገር ወንጌልን ለመስበክ ከበርናባስ ጋር ወጡ፡፡ ሐዋ ፲፫÷፩-፫ በዚህ ጉዞአቸው በጠቅላላ ወደ ፪ ሺህ ኪ.ሜ. የሚደርስ መንገድ በእግር ተጉዘዋል። ጉዞው የተከናወነው በ፵፮ ዓ.ም. አካባቢ ሲሆን ከ፲፬ የማያንሱ ሀገሮችን ጎብኝተዋል።

ሁለተኛው ጉዞ በ፶ ዓ.ም. ገደማ ከሲላስ ጋር ያደረገው ጉዞ ነው፡፡ በጉዞው ከ፲፰ የማያንሱ ከተሞች የተጎበኙ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ገላትያ ፣ ጢሮስና ፣ ኤፌሶን፣ ቆሮንቶስ፣ ልስጥራ ፣ ኢየሩሳሌም፣ አንጾኪያ ይገኙበታል፡፡ ደቀመዝሙሩን ጢሞቴዎስን ያገኘው በዚህ ጉዞው በልስጥራ ከተማ ሊያስተምሩ ነው።

ሦስተኛውን ጉዞ ያደረገው በ፶፬ ዓ.ም. ሲሆን ብዙ ሀገሮችን በጉዞው አካትቷል፡፡ በዚህ ጉዞው ከልዩ ልዩ ሀገር ክርስቲያኖች የሰበሰበውን ዕርዳታ ለኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን ይዞ ሲመለስ በኢየሩሳሌም የፋሲካ በዓል ስለነበር ከየሀገሩ የመጡ አይሁድ ቅዱስ ጳውሎስን ተቃወሙት። ተቃውሞውን ለመግታት በአይሁድ ህግ በቤተመቅደስ የመንጻት ሥርዓት መፈጸም ጀመሩ፡፡ ነገር ግን ከአህዛብ ወገን የነበረውን ደቀመዝሙሩን ጢሞቴዎስን ወደ መቅደስ ያስገባው መስሏቸው ተቃውሟቸው በረታ። በዚህ የተነሳ ከተማዋ ታወከች፡፡ ሐዋ ፪÷፳፱ በሁከቱ የተነሳ ሐዋርያው ጳውሎስ በ፶፰ ዓ.ም. ለሮም እስር ተዳርጓል። ሁለት ዓመት በቁም እስር ቆይቶ ከሮማ ሕግ ጋር የሚቃወም ምንም ዓይነት ወንጀል ስላልተገኘበት በነጻ ተለቋል፡፡

egziabhermeslene28" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

📌ነገ ሐሙስ አመሻሹን 12:30 ላይ ልባቹ መልካሙን ያደምጥ ዘንድ ፤ ከመጻሕፍት ጋር ለሚኖረን ወግ እግሮቻቹን ወደ ደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል ምሯቸው ።

ጥበብን በሚሰጠው አምላክ ፊት በጠቢባን አጻጻፍ እየተደመምንና ጽሑፍ እየመረመርን ለነፍስ ስንቅ የሚሆኑንን መጻሕፍት አብረን እንመገባለን። በተጨማሪም ለእናንተ ያልነውን ጥቁር እንግዳ ጋብዘናል። መቅረት ያስቆጫል!


ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ

📌የዩቲዩብ ቻናል፡
EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

🎙በደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል የእግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤታችን ባሳለፍነው እሑድ የነዳያንን ገላ የማጠብ ፣ የልብስ እደላ እና የጸጉር መቁረጥ መርሐ ግብር አከናውኗል።

በአጠቃላይ አገልግሎቱ 217 የሚሆኑ ሰዎችን ያዳረሰ ሲሆን በዕለቱም 75 ለሚሆኑ ነዳያን የስኳር እና የደም ግፊት ምርመራ ተደርጓል ።

ስለሁሉም እግዚአብሔር ይመስገን።

EMislene" rel="nofollow">http://youtube.com/@EMislene

Читать полностью…

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ

‎ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ በዛግዌ ሥርወ መንግሥት ከነገሡ ፲፩ ነገሥታት አንዱ ሲሆን ከመጨረሻውም ፪ኛ ነው:: እርሱን በ12ኛው መቶ ክ/ዘመን የወለዱት ቅዱሱ ንጉሥ ሐርቤ (ገብረ ማርያም) እና መርኬዛ ናቸው:: ዘመኑ ቅድስና በላስታ ዙሪያ የመላበት በመሆኑ ቅዱስ ሐርቤ ከመመነኑ በፊት ነበር ነአኩቶ ለአብን የወለደው::

    እናቱ መርኬዛ እርሱን ልትወልድ ምጥ ተይዛ ሳለ ጆሮዋ ቅዳሴን ይሰማ ነበር:: ቅዳሴው ሲጀመር የጀመራት ምጥ ድርገት ሲወርዱ (ሥጋ ወደሙ ሲሰጥ) ተፈታላትና ልጇን ተገላገለች:: ሕፃኑን አንስታ ስትታቀፈው ዲያቆኑ ማቁረቡን ፈጽሞ "ነአኩቶ" እያለ ሲዞር ሰማችው::  እዚያው ላይም 'ነአኩቶ ለአብ' (አብን እናመስግነው) ስትል ስም አወጣችለት:: ወዲያው ግን አባቱ ቅዱስ ሐርቤ መንግሥቱን ለቅዱስ ላሊበላ ሰጥቶ በረሃ በመግባቱ ቅዱሱ ሕፃን ወደ አጎቱ ላሊበላ ቤተ መንግስት ውስጥ ገባ::

     የቅዱስ ላሊበላ ቤት ደግሞ በቅድስና ያጌጠ ነውና ከእርሱና ከሚስቱ (ቅድስት መስቀል ክብራ) ሕፃኑ ነአኩቶ ለአብ ምናኔና ፍቅረ ክርስቶስን ተማረ:: በዘመኑ ብዙ ሊቃውንት ስለ ነበሩ ቅዱሳት መጻሕፍትን በደንብ አጠና:: ክህነት ተቀብሎ ቤተ ክርስቲያንን ሲያገለግልም ዕድሜው 30 ደረሰ::

    በወቅቱ ቅዱስ ላሊበላና ባለቤቱ መስቀል ክብራ ልጃቸው ይትባረክ እያለ ንግሥናቸውን ለቅዱስ ነአኩቶ ለአብ አወረሱ:: ቅዱሱ ነአኩቶ ለአብም ምን እንደሚሠራ ሲያስብ አንድ ነገር ተገለጠለት:: ቤተ መንግስቱን እንደሚገባ ካደራጀ በኋላ በቤት ውስጥ አንድ ጉድጓድን በቁመቱ ልክ አስቆፈረ:: በውስጡም በ4 አቅጣጫ ጦሮችን ተከለባቸው:: ድንግል ካህን ነበረና ቀን ቀን ሃገር ሲያስተዳድር፣ ቅዳሴ ሲቀድስ፣ በጾም ይውላል:: ሌሊት ደግሞ ወዳስቆፈረው ቦታ ገብቶ ያለማቁዋረጥ እየጸለየ ይሰግዳል:: ወደ ምድር ሲሰግድ በፊቱ ያለው ጦር ይወጋዋል:: ቀና ሲል ደግሞ የጀርባው ይቀበለዋል:: እንዲህ እያለ የፈጣሪውን ሕማማት ይካፈላል:: በተለይ ዐርብ ዐርብ ሲሆን ደሙ፤ እንባውና ላበቱ ተቀላቅሎ ይፈስ ነበር:: እርሱ መስቀሉን ተሸክሞ ጌታውን ይከተል ዘንድ መርጧልና::

     ከተጋድሎው ጎን ለጐጎ ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ አብያተ ክርስቲያናትንም ያንጽ ነበር:: በተለይ በ፲፪፻፲፩ ዓ.ም.  አካባቢ ያነጻት አሸተን ማርያም ልዩ ናት:: እርሷን ካነጸ በኋላ ከቤተ መንግሥቱ በደመና ሠረገላ ተጭኖ እየሔደ ያጥናት፣ ይቀድስባትም ነበር:: ታዲያ አንድ ቀን አጥኖ ከቤተ መቅደስ ሲወጣ ብዙ ቅዱሳን መቅደሱን ከበው ተመለከተ:: እርሱም "ወገኖቼ! ከወዴት መወጣችሁ?" ቢላቸው "መዐዛ እጣንህን አሽተን መጣን" ሲሉ መለሱለት:: በዚህ ምክንያትም እስከ ዛሬ ድረስ "አሽተን (አሸተን) ማርያም" ስትባል ትኖራለች::

     ዛሬ ታቦቱ ያለበት ገዳሙም በእርሱ የታነጸ ሲሆን እጅግ ተአምረኛ ቦታ ነው:: ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ የነገሠው በ፴ ዓመቱ ነው:: ለ፵ ዓመታት በእንዲህ ያለ ቅድስና ኑሮ ፸ ዓመት ሞላው:: በዚህ ጊዜም ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ሰላምታንም ሰጠው::

     "ወዳጄ ነአኩቶ ለአብ! አንተ ስለ እኔ ፍቅር ለ፵ ዓመታት መከራን ተቀብለሃልና ሞት አያገኝህም፤ ክፍልህ ከነ ኤልያስ ጋር ነውና:: የሚያከብርህን አከብረዋለሁ:: ደጅህን የሳመውን፣ ይህ ቢያቅተው በሩቁ ሆኖ በአድናቆት የተመኘህን፣ መታሰቢያህን ያደረገውን ሁሉ እምርልሃለሁ" አለው:: ቀጥሎም "ይህች ቤት አንተ ስትደማ እንደኖርክባት እርሷም እስከ ምጽዓት ድረስ ለመታሰቢያህ ስትደማ ትኑር" አለው:: እነሆ ዛሬም ድረስ ከመቅደሱ ጸበል ይንጠበጠባል:: ለዚህም ደግሞ እኛ ኃጥአን ምስክሮች ነን:: ሳይገባን የቅዱሱን ደጅ ተመልክተናልና::

     ቅዱስ ነአኩቶ ለአብም የዚህን ዓለም ተጋድሎውን ፈጽሞ ወደ ብሔረ ሕያዋን መላእክት ወስደዉታል:: የተሰወረበትን ዕለት ስንክሳር ኅዳር ፩ ሲያደርገው አንዳንድ መዛግብት ደግሞ በ፫ ነው ይላሉ:: በዙፋኑም ላይ የአጎቱ የላሊበላ ልጅ አፄ ይትባረክ ተተክቷል።

ይህ ቅዱስ ንጉሥ ሆኖ ሳለ ገዳማዊ ሕይወትን በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ያሳየ ንጹሕና ድንግል  ጻድቅ ነው። የጦር መሪ ሳለ በእጁ ደም ያልፈሰሰ ፍቅር ማለት ለእርሱ ክርስቶስ ብቻ የሆነ ነበር። የሃገር መሪ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት እንደመሆኑ እጅግ ጊዜው የተጣበበ ቢሆንም  ለክርስትናው ጊዜ ያጣ ሰው አልነበረም::

እኛ ቤተ ክርስቲያንን "በሐኪ" ለማለት (ለመሳለም) እንኳ 'ጊዜ የለኝም' ስንል እርሱ ግን አብያተ ክርስቲያናትን ይፈለፍል፣ ያንጽ፣ በክህነቱ ያገለግል፣ በማዕጠንት ያጥን፣ ለረጅም ሰዓትም ይጸልይና በቀኝና በግራ  ጦር እየተከለ ይሰግድ ነበር። ታድያ ይህ ቅዱስ ለእኛ እንደምን ያለ ተሞክሮ በጎ አርአያ ነው?

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

/channel/EMislene

Читать полностью…
Subscribe to a channel