በዙሪያዬ ያለው ነገሬ ይህን ባይነግሬኝ
ነገርሽ ሞተ ተቀበረ በቃ ብለኝ
አዲስ ነገር ማድረግ ሁልጊዜ ልማድ ፡ ያለው ጌታ
ዛሬም በዙፋኑ ይዠ ይተጋል ስለ እኔ ከፍታ (፪x)
አዝ፦ እኔ የማምነው ጨለማሽ ይበራል ያለኝን ነው (፪x)
እኔ የማምነው ተራራሽ ይናዳል ያለኝን ነው (፪x)
አላምንም ሁኔታን አላምንም ችግሬን
እግዚአብሔርን አምነዋለሁ ይሰራል ነገሬን (፪x)
እግዚአብሔርን አምነዋለሁ ይከፍታል መቃብሬን (፪x)
ልቤን ልጣል እንጂ በሚያስጥለው ጌታ
በእርሱ ተደግፌ ጉልበቴን ላበርታ
ታምራት ያሳየኛል ጌታ (፬x)
በደረቁ አጥንቶች ነፍስን መዝራት
እንደ ሰው ሲታሰብ በምን ጉልበት
እንደ እግዚአብሔር ግን ቀላል ነው
እጁ ድንቅ ይሰራል ትልቅ ነው
ልጅ መውለድ በዘጠና ዓመት
ለሣራ ከባድ ነው ሲገመት
ግን እግዚአብሔር ካለ ሆነ ነው
ታምር የሚሰራ ጌታ ነው [1]
እርሱ ትልቅ ነው እግዚአብሔር ከሁኔታ በላይ
ኧረ እርሱ ትልቅ ነው እግዚአብሔር ከሁኔታ በላይ
ያልታሰበ ነገር ያደርጋል በሞተው ነገር ላይ (፪x)
አዝ፦ እኔ የማምነው ጨለማሽ ይበራል ያለኝን ነው (፪x)
እኔ የማምነው ተራራሽ ይናዳል ያለኝን ነው (፪x)
አላምንም ሁኔታን አላምንም ችግሬን
እግዚአብሔርን አምነዋለሁ ይሰራል ነገሬን (፪x)
እግዚአብሔርን አምነዋለሁ ይከፍታል መቃብሬን (፪x)
ልቤን ልጣል እንጂ በሚያስጥለው ፡ ጌታ
በእርሱ ተደግፌ ጉልበቴን ላበርታ
ታምራት ያሳየኛል ጌታ (፬x)
በSola Scriptura ጉዳይ ማንኛውንም አይነት ጥያቄ ለማስተናገድ ስላሰብን ጥያቄ ያላችሁ ሁሉ @redeemed9 በዚህ ጠይቁ።
በዛውም መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ በሚለው አንዳንድ ጠቃሚ ሀሳቦችን እንድናሳውቃችሁ ይረዳናል