ertugrulethiopia | Unsorted

Telegram-канал ertugrulethiopia - አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

14898

የተለያዩ ትምህርት እና ታሪክ አዘል የሆኑ ቪዲዮዎች ይተላለፉበታል

Subscribe to a channel

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

ረመዳን 28


🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔

የአላህ ያጎደልነው ብዙ አለ፣ነገ ብለን የተዘናጋነው ብዙ ነውና አንተ በእዝነትህ ሙላልን

🤲🤲🤲🤲🤲🤲

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

ወቅታዊ መልዕክት‼
==============
(ለሌሎችም አሰራጩት! ከምንዳው ተቋዳሽ ትሆናላችሁ!)
||
✍ ዛሬ ሐሙስ ከመጝሪብ ሶላት በኋላ አሁን ይሄ ምሽቱ የጁሙዓህ ቀን ሌሊት ነው። በተጨማሪም የረመዿን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ከሆኑት መካከል አንዱ ነው። በተጨማሪም ለይተ-ል-ቀድር ይበልጥ ከምትጠበቅባቸው ነጠላ ቀናት (ዊትር) መካከል አንዱ የሆነው 23ኛው ሌሊት ነው።
ታዲያ ይሄን ቀን ከሌሎቹ ምን ይለየዋል?

የጁሙዓህ ሌሊት ከዐሽረ-ል-አዋኺር መካከል ከነጠላዎቹ ቀናት ከአንዱ ጋር ከገጠመ ለይለተ-ል-ቀድር ከሌላው በበለጠ መልኩ ትጠበቃለች።



*بعد مغرب اليوم الخميس  .. ستكون ليلة الثالث والعشرين وتوافق ليلة الجمعة، فتوافقت ليلة وتر وليلة جمعة*
وقد نقل ابن رجب في لطائف المعارف عن ابن هبيرة أنه قال :
ኢብኑ ረጀብ አል-ሃንበሊ ለጧኢፉ-ል-መዓሪፍ በተባለው ዕውቅ ኪታቡ ላይ ከአቡ ሁበይራህ የሚከተለውን አስተላልፏል፦

«
*إذا وافقت ليلة الجمعة ليلة وتر فهي أرجى من غيرها في أن تكون ليلة القدر .*
«የጁሙዓህ ሌሊት ከነጠላዎቹ (የዐሽረ-ል-አዋኺር) ሌሊት ጋር ከተገጣጠመች፤ ከሌሎች (ሌሊቶች) ይበልጥ ለይለተ-ል-ቀድር ትሆናለች ተብሎ ይከጀላል።»


*ويقول شيخ الاسلام ابن تيمية :
ታላቁ የኢስላም ሊቅ ሸይኹ-ል-ኢስላም ኢብኑ ተይሚይተም እንዲህ ይላል፦
إذا وافقت ليلة الجمعة احدى ليالي الوتر من العشر الأواخر فهي أحرى أن تكون ليلة القدر بإذن الله.*
«የጁሙዓህ ሌሊት ከመጨረሻዎቹ አስሮች ውስጥ ከነጠላዎቹ ሌሊቶች ጋር ከገጠመች፤ በአላህ ፈቃድ ይበልጥ ለይተ-ል-ቀድር ትሆናለች ተብሎ ትጓጓለች (ትጠበቃለች)!»

*وفي حديث المساء للشيخ عبدالعزيز بن باز رحمه الله(239) قال بعض أهل العلم: إن كان في الأوتار ليلة الجمعة كانت آكد وأقرب أن تكون ليلة القدر، لذا ينبغي لنا أن نعني بهذه الليالي ولاسیما هذه الليلة وأن يكون لنا فيها حظ ونصيب من الإجتهاد  في الخير.*

በአጭሩ የጁሙዓህ ሌሊት ከነጠላዎቹ የመጨረሻዎቹ አስሮች ሌሊቶች ጋር ከገጠመች ያቺ ሌሊት ለይለተ-ል-ቀድር የመሆን እድሏ በጣም ትልቅ ነው። ለለይለተ-ል-ቀድርን ይበልጥ የቀረበች ናትና ሌሊቷን ቁርኣን በመቅራት፣ በተሃጁድና መሰል ዒባዳዎች ሕያው ማድረግ ላይ እንበርታ። ይህ ሌሊት ደግሞ አሁን ያለንበት ሌሊት ስለሆነ እኛም እንበርታ፤ ሌሎችንም እናበርታ፤ መልዕክቱንም እናድርስ።

አላህ ለሁላችንም ይወፍቀን!

وفقني الله وأياكم لقيام ليلة القدر إيمانا وإحتسابا..!!.

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

ነገ ዕሁድ ረመዳን 18/1444 ሂጅሪ

ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ኢሙታወር
🌟መድረካችን በወንድና ሴት  ታዳጊዎች የቁርአን ቲላዋ ይዋባል

🌟በመሻይኾች፣ ዱዓቶችና የመጅሊስ አመራሮች ይደምቃል

●ልብ ይበሉ●
👉 ቀድመው አዳራሹ ውስጥ ለታደሙ 30 እንግዶቻችን ልዩ ሽልማት አዘጋጅተናልና እንዳያረፍዱ

ኢማም አልቡኻሪ ኢስላሚክ አሶሴሽን

ቴሌግራም👉
/channel/ethiobukhari2020

ዩትዩብ👉
albukharitube9848" rel="nofollow">https://youtube.com/@albukharitube9848

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

የ ረመዳን የየቀኑ ክስተቶች ።#Ramadhan 15.

1 ታላቁ ሶሀቢይ ( ሀሰን ኢብን አልይ ) በ 3 ኛ አመተ ሂጅራ የተወለዱበት ቀን።

2 በ 37 ኛዉ አመተ ሂጅራ ታላቁ ሶሀቢይ ( ሙሀመድ ኢብን አቡበክር ) በ ግብፅ ሀገር ላይ የተሾሙበት ቀን።

3 ታላቁ ሶሀቢይ ( አብደላህ እቢን ዑመር ) በዛዉ አመት በ 37 ኛዉ ዘመተ ሂጅራ የሞቱበት ቀን።

4 ታላቁ የ ኢስላም ጠቢብ ና  በ ዘርፋ ብዙ ነገራቶች  እስልምናን ሲያገለግሉ የነበሩ ኢማም ( አቡበክር አልከዋሪዚም ) በ 383 አመተ ሂጀራ ወደ አኬራ የሄዱበት ቀን።

5 ታላቁ አሊም ኢማም ( ፈክሩዲን አራዚ ) በ 543 አመተ ሂጀራ የተወለዱበት ቀን ።

6 በ እስልምና ታርክ ዉስጥ በ ስነ ፁሁፍ ና በ ግጥሙ ዘርፍ ታዋቂ የነበሩ ና እስልምናን ሲያገለግሉ የቆዩ ( ኢሊያ አቡ ማዲ ) በ 1306 አመተ ሂጀፋ ያረፉበት ቀን ።

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

✨✨✨✨🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌙✨✨✨✨✨✨✨✨🌙🌙🌙🌙🌙

የፊታችን እሁድ ጦር ሀይሎች አዲስ አበባ መጅሊስ ወረድ ብሎ በሚገኘው ኢሙ ታወር አዳራሽ የአሸናፊዎች አሸናፊ የቁርኣን ሂፍዝ ውድድር በታላላቅ መሻይኾች ሙሐደራ ታጅቦ ደምቆ ይውላል
✨✨✨✨🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌙✨✨✨✨✨✨✨✨🌙🌙🌙🌙🌙

እርሶም ከቤተሰቦና ከወዳጅ ዘመድዎ ጋር በመሆን ረመዳን 18 ከቁርኣን ጋር እንዲያሳልፉ ተጋብዘዋል።

🌟🌙✨🌟🌙✨🌟🌙✨🌟🌙✨🌟🌙✨🌟🌙✨🌟🌙✨🌟🌙✨🌟🌙✨🌟🌙✨🌟🌙✨🌟🌙✨

ረመዳን ሙባረክ

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

ኢላሂ!
🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲
ካንተ መራቄ ሲረዝም ዳግም አትመልሰኝም ብዬ ተስፋ መቁረጤን ማረኝ!
ጠላቶቼ በአንድነት ዘምተውብኝ መሸሸጊያ ሲያሳጡኝ እርዳታህን መተሰፍ ማቆሜን ማረኝ!
ስጦታህ ሲዘገይ የቀደመ ውለታህን መዘንጋቴን ማረኝ!
ከክፋቴ ጋር የቅጣትህ ውርጅብኝ መተማመኔን ማረኝ!
መልካም ሥራ ሳይኖረኝ በወንጀል እየቦካሁ ሳለሁ ለራሴ ትልቅ ስፍራ መስጠቴን ማረኝ!

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

#እስልምና_በብራዚል

ብራዚል በጣም የምታውቋት በምንድን ነው ? በእርዝመቱ ተወዳዳሪ በሌለው የእየሱስ ክርስቶስ ሀውልቷ ? ወይንስ የአለም ሳንባ በሚባለው የአማዞን ጫካና በግዝፈቱ አቻ በሌለው የአማዞን ወንዝ ? ወይንስ የእግርኳስ ንጉሱ ፔሌን ጨምሮ በበርካታ የእግርኳስ ከዋክብቶቿ ?  ወይንስ ቸኮሌታማ ከለር ባላቸው ቆነጃጅቶቿ ? በርግጥ ብራዚል በነዚህ ሁሉ ነገሮች እጅግ ዝነኛ ነች ።

ዛሬ ግን ለመሆኑ ብራዚልና እስልምና ግንኙነታቸው ምን ይመስላል ስንል ወደ ላቲን አሜሪካዊቷ ሀብታምና ግዙፍ ሀገር በምናብ እንጓዛለን ። ይሄን ሁለት ቀን ላቲን አሜሪካን እየጎበኘን አይደል ። ትላንት አርጀንቲና ዛሬ ብራዚል ! ከሪዮ ደጀኔሮ እስከ ሳኦ ፖሎ እና ብራዚሊያ ። ብራዚል ህዝቦቿም መልክአምድሯም የሚያምረው ምድር !

ልክ እንደ ጎረቤቷ አርጀንቲና ሁሉ ብራዚልም የቅኝ ግዛት ውጤት ናት ። ለነገሩ ሀገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ ከጥቂት የአለም ሀገራት ውጭ አብዛኛው የአለም ሀገር የቅኝ ግዛት ውጤት ነው ። እናም አርጀንቲናና የተቀረውን የአሜሪካ አህጉር ስፔይን እንደገዛቺው ሁሉ ትልቋን ብራዚልን ደግሞ ትንሿ ፖርቺጋል ለረጂም አመታት ገዝታት ማንነቷን ሰርታት ሂዳለች ።

ፖርቹጋል ብራዚልን በአምሳሏ ፈጥራታለች ብንል አላጋነንም ። ባህሏን አስረክባት ፤ ቋንቋዋን አውርሳት ፤ በሀይማኖቷ አጥምቃት አብዛኛውን ዜጎቿን ጥላላት ወይንም ጥላባት ነው የተመለሰቺው ። እናም የብራዚል ህዝብ ልክ እንደ ፖርቹጋል ሁሉ ፖርቺጋልኛ ይናገራል የካቶላክ እምነትን ተቀብሎም ኢየሱስ ክርስቶስን ያመልካል ።

የብራዚል ህዝብ ከ 64 % በላይ ነጭ አውሮፓዊ ዝርያ ያለው ሲሆን ከ 31 % በላይ ደግሞ ጥቁር አፍሪካዊ ዝርያ አለው ።

የብራዚል እስልምና ከአፍሪካ ይመዘዛል ። ያኔ ፖርቹጋልና ስፔይን ሀያል በሆኑበት ወቅት አፍሪካን በባርነት እንደጉድ አግዘውት ነበር ። እናም ወደ ሰሜንና ደቡብ አሜሪካ ከተላኩ ከ 40 ሚሊዮን ባርያዎች ውስጥ 3 ሚሊዮን ባርያዎች የተጋዙት ወደ ብራዚል ነበር ። ከተጓዙት ሶስት ሚሊዮን የአፍሪካ ባርያዎች ውስጥ ታድያ ሙስሊሞችም ነበሩበትና እስልምናቸውን እንደያዙ ብራዚል ከተሙ ። በፖርቹጋል እንደ እቃ እንደ ሸቀጥ እንደ እንሰ*ሳት ተነግደው !!

አፍሪካዊያን ሙስሊሞች ብራዚል እንደደረሱ ሀይማኖታቸውን መተግበር ቀላል አልሆነላቸውም ። የባሪያ ጌቶቻቼው ኢስላምን እንዳይተገብሩ ከለከሏቸው ። ግና የሚገርማችሁ እነዚያ ሙስሊም ባሪያዎች ከየትኛውም ማህበረሰብ በላይ የተማሩና መፃፍና ማንበብ የሚችሉ ነበሩ ። የባሪያ ጌቶቻቼው እንኳ የነርሱን ያክል Literate አልነበሩም ። እናም ሙስሊሞቹ በድብቅ በመገናኘት ሀይማኖታቸውን እየተማማሩ እተፃፃፉ ለመቶ አመታት ማቆየት ቻሉ ።

ሌላው የብራዚል ሙስሊሞች ሲነሱ ልክ እንደ አርጀንቲና ሁሉ የስፔን ስደተኛ ሙስሊሞችም ይነሳሉ ። የስፔይን ጭቆናን በማምለጥ ሙስሊሞቹ ያልተሰደዱበት ሀገር አልበረም ። ብራዚል አንዷ መዳረሻቸው ነበረ ። በዚያ ጫካ ውስጥ እምየታቸውን ይዘው ለመቆየት ሲሉ አትላንቲክ ውቅያኖስን አቆራርጠው የሞቱት ሞተው የተረፉት እዚያ ከተሙ ። ሲያሳዝኑ !!

ሌላው ከብራዚል ሙስሊሞች ጋር የሚነሳው የሶሪያ ፣ ሊባኖስና ፍልስጥኤም ስደተኛ ሙስሊሞ ናቸው ።
በአሁኑ ሰአት ከብራዚል ሙስሊሞች ውስጥ ከ 80% በላይ ነጮች ሲሆኑ ከ 10 % በላይ የሚሆኑት ደግሞ ጥቁሮች ናቸው ። የጥቁር ሙስሊሞች ቁጥር ያነሰው የባርነት ስርአት ካበቃ በሗላ ብዙዎቹ ወደ እናት አህጉራቸው አፍሪካ ስለተመለሱ ነው ።

የብራዚል ሙስሊሞች አጠቃላይ ቁጥራቸው ከሀገሪቱ ህዝብ አንፃር በጣም ጥቂት የሚባሉ ናቸው ። የብራዚል ሙስሊሞች ቦዛት 200,000 አካባቢ ናቸው የሚሉ መረጃዎች ቢሆንም የብራዚል እስልምና ጉዳዮች  ግን የብራዚል ሙስሊሞች ከ 800,000 እስከ 1.5 ሚሊዮን እንደሚሆኑ አስታውቋል ።
ኢስላም ቡብራዚል በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ ይገኛል ። ይህም የሆነው ወደ እስልምና የሚገቡ ብራዚላዊያን ቁጥራቸው እየጨመረ በመሆኑ ነው ። በሺዎች የሚቆጠሩ ብራዚላዊያን በየአመቱ ወደ እስልምና ይገባሉ ። የብራዚል ሙስሊሞችም ቢሆኑ ከቁጥራቸው በላይ ጠንካራና ስለሃይማኖታቸውም በቂ ግንዛቤ ያላቸው ናቸው ።

ብራዚል የሀይማኖት ነፃነትን የምታከብር ሀገር ናት ። እናም የብራዚል ሙስሊሞች ልክ እንደማንኛውም ብራዚላዊ እኩል መብትና ነፃነት አላቸው ። መስጅጆችና ትምህርት ቤቶችን በነፃነት መገንባት ይችላሉ ። በአሁኑ ሰአት በብራዚል ከ 150 በላይ መሳጅዶችም አሉ ።

የብራዚል መሪዎች የሀይማኖት ነፃነትን በማክበር በኩል ትልቅ ምሳሌ የሚሆኑ ናቸው ። ከአመት በፊት አንድ ኢስላምን የሚያጥላላ ፊልም ተሰርቶ ነበር ። ያ ፊልም በዩቲዩብ መለቀቁ ብዙዎችን አስቆጥቶ ነበር ። ይህንን ድርጊት ያወዘው  የብራዚል ፍርድ ቤት በዩቲዩብ ላይ ክስ መስርቶ ዩቲዩብ በ 10 ቀን ውስጥ ፊልሙን እንዲያጠፋ ውሳኔ ማሳለፉ አስገራሚው የብራዚል ገድል ነበር ። ይህንን ሙስሊም ሀገራት እንኳ አላደረጉትም ነበር ።

የቀድሞዋ የብራዚል ፕሬዚዳንት ድልማ ሩዌሴፍ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ምእራባውያንን " ኢስላም ጠሎች " በማለት ያወገዘች መሪ ናት ። ላቲኖች ለፍትህ ያደሉ ህዝቦች ናቸው ።

ይህንሰ መረጃ ለናንተ ለማድረስ በዋቢት የሀርቫርጅ የኒቨርስቲ ጥናትን ፣ Huriyet daily news , Wikipedia እና ሌሎችም የመረጃ ምንጮችን በዋቢነት ተጠቅሚያለሁ ።

Seid Mohammed

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

ይህንን ወንድማችንን የምታውቁ የድሬዳዋ ሰዎች ካላችሁ ጥቆማ አድርጉልን

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

መልካም ረመዳን

🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙✨✨✨✨✨✨✨🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟✨✨✨🌟✨✨✨✨✨✨✨🌙🌙🌙🌙✨
የተለያዩ ቻናሎች ባጣራነው መሰረት ጨረቃ ዛሬ ባለመታየቷ ምክንያት ረመዳን የመጀመሪያ ቀን ሀሙስ መሆኑ ተረጋግጧል

🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙✨✨✨✨✨✨✨🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟✨✨✨🌟✨✨✨✨✨✨✨🌙🌙🌙🌙✨

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

➨ #ALPARSLAN_BÜYÜK_SELÇUKLU1
━━━━━━━━━
➠ #ክፍል_96

➠ #አማረኛ_ትርጉም

━━━━━━━━━━

➠ share /channel/ertugrulethiopia
║▌║█║║▌║█║║▌║█║║▌║

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

ድንቅ የቁርአን አንቀጽ
👇👇👇👇👇

ይህ (ቁርኣን) ለሰዎች ገላጭ ነው፡፡ (ሊመከሩበት)፣ በእርሱም ሊስፈራሩበት፣ እርሱም አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት፣ የአእምሮ ባለቤቶችም ሊገሰፁበት (የተወረደ) ነው፡፡
==========================
https://youtu.be/ggASG1irBIw

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

🎬   ኩሩሉሽ ዑስማን
         ጥራት     HD 

🎵        አማርኛ ትርጉም (በአንድ ድምፅ)

ምእራፍ 4

⏸⏩ ክፍል 177


http://t.me/ertugrulethiopia

ዩቲዩብ ቻናላችንን ይቀላለቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/channel/UCR1_qbjujV6Z_ypHrTJMTKw

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

➨ #ALPARSLAN_BÜYÜK_SELÇUKLU1
━━━━━━━━━
➠ #ክፍል_93

➠ #አማረኛ_ትርጉም

━━━━━━━━━━

➠ share /channel/ertugrulethiopia
║▌║█║║▌║█║║▌║█║║▌║

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

Barbaros:
ባርባሮስ  BARBAROSLAR
🎬🎬🎬🎬🎬🎬🎬🎬🎬
🛥🛥🛥🛥🛥🛥🛥🛥🛥

አማርኛ ትርጉም

🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢

ክፍል 84

🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌

ቴሌግራም ቻናላችን
👇👇👇👇👇
T.me/ertugrulethiopia

ዩቲዩብ ቻናላችን
==========================
https://youtube.com/channel/UCR1_qbjujV6Z_ypHrTJMTKw

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

🎬   ኩሩሉሽ ዑስማን
         ጥራት     HD 

🎵        አማርኛ ትርጉም (በአንድ ድምፅ)

ምእራፍ 4

⏸⏩ ክፍል 176


http://t.me/ertugrulethiopia

ዩቲዩብ ቻናላችንን ይቀላለቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/channel/UCR1_qbjujV6Z_ypHrTJMTKw

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

۞ قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِن رَّحْمَةِ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ
በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡
(ሱረቱ ዙመር 53)

በዚህች በተከበረች ወር ሰዎች ከጀሀነም ነፃ በሚባሉባቸው በቀሩት ጥቂት ቀናት ከሚጠቀሙ እና ከአላህ እዝነት ተስፋ ከማይቆርጡ ባሮቹ ያድርገን
❤️❤️❤️اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وآله وصحبه أجمعين ❤️❤️❤️
የረመዷን የመጨረሻ ጁምዓችን ሊሆን ይችላል እና በሰለዋት በካህፍ በዱዓ የምናደምቀው ያማረ እና የተዋበ የረመዷን ጁምዓ ይሁንልን!!!

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

በድር እውነት ከሐሰት የተለየበት ታላቅ ክስተት

ረመዳን 17 የዋለ ታሪካዊ የድል ቀን!

የመካ ሙሽሪኮች የጭቆና በትራቸውን መዘርጋት የጀመሩት የአላህ መልዕክተኛ ሰዎችን ወደ ኢሰላም መጥራት በጀመሩበት ቅፅበት ነበር። የሰው ልጆችን በሰብዓዊነታቸው የተቸራቸውን የማሰብና የማመን ነፃነት መንጠቅ የሁሉም አምባገነኖች ሁነኛ ባህሪ ነው። የመካ ሹማምንትም የፈለጉትንና የመረጡትን ማመን በጀመሩ ንፁሀን ላይ ‹‹የእኛን እምነት ተከተሉ! እኛ የምናስበውን አስቡ!›› በሚል ትዕቢት አቅመ ደካሞች ላይ የጭቆና ቀንበር ጫኑ። እስራት፣ ድብደባ፣ ከማህበራዊ ህይወት ማግለል ወዘተ ‹‹የፈለግነውን በነፃነት የማመን መብት አለን›› ባሉ ንፁሀን ላይ ያሳረፉት የግፍ አለንጋ ነበር።

ከእምነታቸው እንዲመለሱ፣ የያዙትን ጎዳና እንዲለቁ የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችለውን የስቃይ ዶፍ አዘነቡባቸው። በደሉ ሲበረታ፣ ጭቆናው ሲያይል የአላህ መልዕከተኛ (ሰዐወ) እና ባልደረቦቻቸው እምነታቸውን በነፃነት ወደሚያራምዱበት አገር ተሰደዱ - ሀብትና ንብረትን፣ ዘመድ አዝማድና የትውልድ መንደርን ጥሎ የእምነት ነፃነትን በመሻት የተደረገ ቅዱስ ጉዞ!

በትዕቢት የተሞሉት የመካ ሹማምንት ግን በበደል አለንጋ ገርፈው ያባረሯቸው ንፁሀን አሁንም በነፃነት እንዲኖሩ አልፈቀዱም።ሰላም የሚሹ ንፁሀንን ለመበጥበጥ ተንኳሽ እጃቸው ከመካ መዲና መዘርጋቱን ቀጠለ፡፡ ሙእሚኖች በስደት ዓለም ጥለው የወጡትን ሐብት ንብረታቸውን ለማስመለስ ካደረጉት ጥረት ጋር ተደምሮ ሊያጠቃቸው የመጣውን ኃይል ለመመከት ይዘጋጁ ጀመር፡፡ ጭቆናው አንገብግቧቸዋልና ነፃነታቸውን ለማስከበር የትግል መሰናዶ ማድረግ ጀመሩ - በዚያ በተቀደሰው የረመዳን ወር!

የሰው ልጅ በራሱ ላይ ድል ሲቀዳጅ፣ ነፍሱን በቁጥጥሩ ስር ሲያውል ውጫዊ ጠላቱን በቀላሉ መርታት ይችላል። በራስ ላይ ድል መቀዳጀት፣ ነፍስን በቁጥጥር ስር ማዋል ግን ብዙ ትግልን ይጠይቃል። ወርሀ ረመዳን ለዚህ ታላቅ ትግል ስኬታማነት ምቹ የሆነ ምህዳር ያለው ወር ነው።

ስጋ በርሀብ መዳከሙ፣ ነፍስ ከእኩይ ተግባራት ስንቅ መታቀቧ፣ የሰው ልጅ ጠላት የሆነው ሸይጣን መታሰሩ እና ማህበረሰቡ ውስጥ የሚሰፍነው የመልካም ስራ ተነሳሽነት ተደማምረው የሰው ልጅ ራሱን ድል እንዲያደርግ ነፍሱን በማረቅ ተገዢው እንዲያደርጋት ያስችላል።

በዚሁ የረመዳን ወር ከራስ ጋር የሚደረገውን ትግልና አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ያደረጉት የአላህ መልዕክተኛና ባልደረቦቸቸው የማይነጥፍ ፅናት ታጥቀው የጌታቸውን እርዳታ ተማምነው ጨቋኛቸውን ለመርታት ዘመቱ። በዚሁ የረመዳን ወር 17ኛው ቀን ከጨቋኛቸው ጋር ፊት ለፊት ተጋጠሙ። በዳይና ተበዳይ፣ እውነትና ሀሰት በተቃራኒ ጎራ ተሰልፈው ተፋለሙ። የዓላማ ፅናት፣ የአሸናፊነት ስነ ልቦና ከወኔ እና ብርታት ጋር የታጠቁት ሶሀቦች ምንም እንኳ ቁሳዊ ስንቃቸው አናሳ ቢሆንም ለእምነት ነፃነትና ጭቆናን ለማስወገድ ያደረጉትን ትግል በድል አጠናቀቁ። ታሪክ የበድርን ዘመቻ በተምሳሌትነት እንዲቀር አደረገው።

በድር ዘውታሪ ተምሳሌትና የማይነጥፍ አብነት ነው። ጭቆና ምንም እንኳ ገዝፎ ቢታይም ፅናትና ብርታትን በተላበሱ ተበዳዮች የተባበረ ክንድ የሚናድ መሆኑን ያስተምረናል፡፡ ወርሀ ረመዳን የድል ወር መሆኑን ያውጅልናል። በድር ታጋዮች በራስ ላይ ድልን በመቀዳጀት፣ ነፍስን በመግራት፣ ትዕግስትን በመማርና ፅናትን በመላበስ ጭቆናን በፍትህ ለመተካት ባደረጉት ትግል ድል የተቀዳጁበት የታሪክ ገጠመኝ ነው።

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

🌙🌙 ١٧  رمضان ١٤٤٤  🌙

أيها الصائم القائم

احرص على كمال صيامك فما هي إلا أيام ثم تطوى الصحائف
ومن الغبن والخسارة ان ينقضي رمضان وانت خسران احرص على مابقى.

༼࿄ཽ༽ 🌙 رمضاااان🌙  ༼࿄ཽ༽

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

የ ረመዳን የየቀኑ ክስተቶች ።#Ramadhan 13.

1 - በ 791 አመተ ሂጅራ ሱልጣን ( ሙራዱል አወል ጋዚ ኢብን ኡስማን ኢብን ኦርጦግሮል ) በ 36 እድሜያቸዉ የሞቱበት ቀን ።

2 - ኸሊፋ ( ዑመር ኢብን አልኸጣብ ) በ 15 አመተ ሂጅራ  በይቱል መቅድስን የድረሰቡት ቀን።

3 - በ ደዉላ ኡስማንያ ዘመን ግብፅ ሀገርን ሲያስተዳድሩ የነበሩ ኑጉስ (  ሙሀመድ አሊ ባሻ )
የሞቱበት ቀን።

4 - በ 91 አመተ ሂጅራ ( ሀጃጅ ኢብን ዩሱፍ ) የሞቱበት ቀን።

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

የ ረመዳን የየቀኑ ክስተቶች  #Ramadhan 11

1 -  በ 9 ኛዉ አመተ ሂጅራ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ)  ከ ተቡክ ዘመቻ ከተመለሱ ብኋላ ፣ የ ሰቂፍ ወፍድ/ጀመዓ መዲና መጥተዉ  እስልምናን የተቀበሉበት ቀን ።

2 -  በ ደዉላ ዑመዊያ ዘመን  በ 94 አመተ ሂጅራ ታላቁ ታቢዕይ ( ሰዒድ ኢብን ጁበይር ) በ ሀጃጅ ቢን ዩሱፍ የ ተገደሉበት ቀን ።

3 - በ 986 አመተ ሂጅራ የ ዑስማኒያ ደዉላ ከ ደዉለቱል  ( ሰፈዋንያ) ጋር ባደሩጉት ትልቅ ዉጊያ በመጨረሻ ዑስማንዮች አሸነፉ።

በዚህ ጦርነት ከ  ሰፍዋንዮች ወደ 15 ሺ የሚጠጋ የ ጦር ሰራዊት አልቀዋል።

( ደዉላ ሰፈዋንያ)  ማለት  በ ኢራን ሀገር የ ሺዓን መዝሀብ አስተምህሮት ለማስፋፋት የተመሰረተ ነበረ።

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

ሌሊት ነው። ከጥቂቶች በቀር የአደም ልጆች ሁሉ በተኙበት ቅፅበት አንዲት ከጌታዋ ጋር እምታወጋ እንስት ቤት ሌባ ገብቶ ወዲህ ወድያ ይዋልላል። እንስት ሰላት ላይ ናት። (135 አመተ ሂጅራ)

ከቤቱ የገባው ሌባ ቤቱን ሲያስስ ቆይቶ ከአንዲት የውሀ ማንቆርቆርያ ውጭ ባለማግኘቱ ባዶ እጁን ሊወጣ ሲል እንስት ሰላቷን አጠናቅቃ ቀና አለች።

«ለመዝረፍ መጥተህ እንደሆን እባክህ ባዶ እጅህን እንዳትወጣ!» ብላ ተማፀነች።
«ምንም እኮ የለም ቤትሽ ውስጥ» ብሎ በግርምት መለሰላት።

«አንተ ምስኪን! ሂድ እስኪ በዚህ ማንቆርቆርያ ዉዱ አድርግ'ና እዚያች ክፍል ሂደህ ሁለት ረከዐ ስገድ፤ ባዶ እጅህን አትወጣም» ሌባዋን ልትካድም ምትፍጨረጨር ሴት ተናገረች።

ከመስገጃዋ ንቅንቅ አላለችም፤ የሰማያት ደጆች ደንበኛ የሆነውን እጇን ወደ ላይ ከፍ አድርጋ፦ «ጌታዬ! ይሄ ሰው እኔ ዘንድ መጥቶ ምንም አላገኘም። ከበርህ እንዲቆም ልኬዋለሁ'ና ከፀጋህ እና ከምንዳው ለግሰው» አለች።

ሌባው ውዱውን አጠናቅቆ ሰላት ጀምሯል። ያዘዘችውን ሁለት ረከዓ ሰግዶ ሲጥመው ይደጋግም ጀመር 4 ረከዐ፣ 6 ረከዐ፣ 10 ረከዐ...ፈጅር ደረሰ።

«እሺ! ሌሊቱ እንዴት ነበር?» ብላ ጠየቀችው።
«እጌታዬ ዘንድ ተዋርጄ እና ተዋድቄ ቆምኩ፤ ይቅርታዬን ተቀብሎኝ ስሜቴን ጠገነው። ውጥኔም ተሳክቷል» ብሎ ትቷት ወጣ።

እጆቿ ዳግም ወደ ሰማይ ተዘረጉ፦ «ሰዪዲ! ያ መውላይ! ይህ ሰው ውስን ሰዐታትን ከፊትህ ቢቆም ተቀበልከው፤ እኔ እስካወቅኩህ ድረስ ከፊትህ ከመቆም ተወግጄ አላውቅም። ታድያ ተቀብለኸኝ ይሁን?» በምታውቀው ወግ ጌታዋን በጥያቄ ያዘችው።

ከጀርባዋ ጥሪ ተስተጋባ፦«አንቺ ራቢዓ! ስላንቺ ስንል ተቀብለነዋል፣ ባንቺው ምክንያትም አስጠግተነዋል»

ይህች ሴት ራቢዐተል ዐደዊያ ናት። ለጌታዋ ፍቅር ነፍሷን የሰዋች ድንቅ ማንነት፣ የውዴታ መስዋዕት፣ የአላህ ተዐምር...።

አምልኮዋ ከእዩልኝ ብቻ ሳይሆን ከቅጣት ፍራቻ እና ከምንዳ ክጀላም ፀድቶ የተጥራራም ነበር። ጀነትን ከጅላ እና እሳትን ፈርታ ሳይሆን በውዴታው ተጠምዳ እንደምታመልከው እንዲህ ስትል ታወጋው ነበር፦

«ጌታዬ! ጀነትን ብቻ ከጅዬ ካመለክሁህ፤ ጀነትን ንሳኝ። ግና ውዴታህን ብቻ ከጅዬ እማመልክህ እንደሆን እባክህ ፊትህን ከማየት አትንፈገኝ» የኢኽላስ ላይኛው ክፍል።

ሰዎቹ ቋንቋቸው ይለያል። የሚናገሯትን ንግግር በቅኔ አስመላሽ ተርጓሚ ካልተፈሰረልህ ሳትረዳው ሰምቶ-አደር ብቻ ትሆናለህ።

የጌታዋን ፍቅር በቋንቋዋ ዘውትር ስታዜም ሰምቶ ማይደመም ጃሂል፣ ዐሊም፣ ዐቢድ፣ ዓሪፍ የለም'ና ከመጀመርያው ምድብ ላይ ቆሜ እንዲህ ስትል ተደመምኩ።

ሁለት አይነት ውዶች አንተን ወደድኩህ
አንዱን ለፍላጎቴ አንዱን ለክብርህ

ለፍላጎት ብዬ የሰየምኩልህ
ስጠመድልህ ነው እያወደስኩህ

ለክብርህም ብዬ አንተን የወደድኩህ
ግርጆህን ገፈኸው አንተን እስካይህ
*                *              ***
አልመሰገንም በዚህም በዝያኛው፤
በዚህም በዝያኛው ምስጋና ያንተ ነው።

ዐጂ....ብ ራቢዓ! ቃላቶችሽን ዐጅበው የወጡ ትንፋሾች ጀነት ላይ የተተከሉ ዛፎችን አስዘምረው የዐርሹን ቀበሌያት እንደሚያስተጋቡ የቀልቤ ስሜት ምስካሪ ነው።

ትንፋሽ እሚግራ ውሀ አጣጭ የማያሻት ራቢዓ  ዘመናትን በብቸኝነት ከጌታዋ ጋር ስታወጋ ታሳልፋለች።

ብቻዋን ሁና ከምትዋልልበት የፍቅር ግዛት ውስጥ ለቀልቧ እንጂ ለስጋ ግድ የሌላት እንስት የሰው ዘያሪ ቢጎበኛት በፍቅሯ አብዮት ትዘምራለች፦

የልቤ አንደበት ላንተ አውጊ ነው
ለዘያሪ ሰዎች ስጋዬን ትችያለው

ስጋዬን ለ'ንግዳ አጫዋች ሳደርገው
ቀልቤን ለወዳጄ «አውጋ» እለዋለሁ።

ዑለማኦች ከፊቷ ሲቀርቡ ያቀረቅራሉ፣ ሙፈሲሮች ምክርን ሲሹ ከቀዬዋ ደጅ ይጠናሉ፣ ሙሐዲሶች አክባሪዎቿ ናቸው...። ያላህ ወዳጅ የምድር ተወካይ ትመስል፤ ሰዎቹ ማዕከል አድርገዋታል።
     *                                    **

ማሊክ ኢብኑ ዲናር፣ ሀሰነል በስሪይ እና ሸቂቅ አል በለኪይ ከራቢዓ ቀዬ ተሰይመዋል። (ትላልቅ ዑለማኦች) ራቢዓ ህመም ጠንቶባት ካልጋዋ ተቆራኝታለች።

«ወዳጁ በሚሰነዝረው ዱላ ትዕግስት እሚያጣ ሰው እውን ወዳጅ አይደለም። » ሲል ወቀሳ ቢጤ ማፅናኛ ለራቢዓ ሰነዘረላት ሀስነል በስሪይ። (አላህ ባመጣው በሽታ ታገሺ እያላት እኮ ነው! ፖ...አላወቃትም መሰል!)

«ይኼ የራስ ወዳድነት ሽታ ያለው ንግግር ነው» አለች፤ ተናግረህ ሙተኻል አይነት ቅኔ አዘል ዘዬ ባለው ለዛ።

«ወዳጁ በሚሰነዝርበት ዱላ ያላመሰገነ ሰው እውን ወዳጅ አይደለም» ብሎ ለማሻሻል ሞከረ ሸቂቅ የሀሰንን ንግግር ተንተርሶ። በበሽታው አመስግኚ እያላት ነው።

«ያንተው ትንሽ ከዝያኛው ይሻላል» አለችው፤ ምስጋና ብርቋ እንዳልሆነ ሰሙን ከማሩ ሳትለይ እያስነበበችው።

« ወዳጁ በሚሰነዝርበት ዱላ የማይረካ ሰው እውን ወዳጅ አይደለም» ሲል ማሊክ የጓደኞቹን ንግግር አሻሽሎ መጣ።

ከጓደኞቹ የተሻለ ፈሊጥ ይዞ ቢቀርብም፤ ራቢዓ ሀገር ስጡኝ ሳትል እንቆቅልሹን ልትፈታላቸው ልሳናኗን አስታጠቀች።

«ወዳጁ ከሚሰነዝርበት ዱላ ይልቅ በወዳጁ እይታ ያልተመሰጠ ሰው እውን ወዳጅ አይደለም» እስቲ ድገማት....አይጥምም? አያስደምም? ፉቀሀኦቹን እንዲህ ግራ ምታጋባ ልሳነ-ብርቱ እህት ናት ራቢዓ።
*                        *                        ***

ምትኖረው ለመሞት ነው፤ ምትሞተው ያ የጓጓችለትን የጌታዋን ፊት ለማየት ነው። አሟሟቷ እንጂ አኗኗሯ አሳስቧት አያውቅም።

በተጎሳቆለ እና በተጨናበሰ ገፅታ ሁና በጎዳናዎች ላይ ስትጓዝ ከሊቀ-ሊቃውንቱ ሱፍያን አስ-ሰውሪይ ራቢዓን አገኛት።

«ጉስቁልና እና ችግር የፀኑብሽ ይመስላል። እዝያ ጎተቤትሽ ያለውን ባለፀጋ እንዲደጉምሺ ብትጠይቂው ጥሩ ነበር።» አላት እዝነት በተቀላቀለበት ስሜት።

«ሱፍያን!! የምን ጉስቅልና ነው እምትለው? ልቅና እንጂ ጉስቅልና የሌለበት፣ ሀብት እንጂ ድህነት የለሌለበት ኢስላም ላይ አይደል እንዴ ያለሁት?

ወላሂ ዱንያ በእጁ የሆነችውን ጌታ ከ'ሷ ስጠኝ ብዬ ጠይቄው አላውቅም። ታድያ እንዴት ነው ዱንያ በእጁ ያልሆነችውን መክሉቅ ምጠይቀ?» ዝም ያስብላል።

የዛሬውን ሳይሆን የትናንትን ተሰዉፍ በተግባር ተውናው ዳግም በዱንያ ላይ አምሳያዋ ላይደገም አሻራዋን ትታ ያለፈችው ራቢዓ ዐጃኢቦችዋ በ'ስክሪን ሰሌዳዎች ከሚበተኑ ፊደላት የላቀ ነው።

Sefwan Ahmedin
_____

ንጭ፦
تذﻛﺮﺓ ﺍﻷﻭﻟﻴﺎﺀ
حلية الأولياء وطبقات الأصفياء
احياء علوم الدين

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

🌟🌙🌟🌙🌟🌙🌟🌙⭐️💫⭐️🌟💫🌟🌟🌟⭐️🌟🌟☀️✨🌙🌙🌟🌟🌟🌟⭐️💫⭐️

ተራዊህ 1


🌟🌙🌟🌙🌟🌙🌟🌙⭐️💫⭐️🌟💫🌟🌟🌟⭐️🌟🌟☀️✨🌙🌙🌟🌟🌟🌟⭐️💫⭐️

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

#የኢራቅ_መወረር_ሲታወስ !

የአሜሪካ እውነተኛ ፍላጎት ምኝ ነበር ?

ከዛሬ 20 አመት እ.ኤ.አ 2003 ነበር አሜሪካ አጋሮቿን አሰልፋ የሳዳም ሁሰይኗ ኢራቅ ላይ የዘመተቺው ። አሜሪካን አጅበው የቀድሞ ጌታዋ የአሁን ሎሌዋ እንግሊዝ ፤ ተላላኪዎቿ አውስትራሊያና ፖላንድ አብረው በኢራቅ ላይ ዘመቱ ።

አሜሪካ 300,000 ጦሯን እንግላዝ 45,000 ጦሯን አውስትራሊያ 2,000 ጦሯን እንድሁም ፖላንድ በመቶዎች የሚቆጠሩ ልዩ ጦሯን አሰልፈው ሊበሏት ከቋመጧት ኢራቅ ገሰገሱ ። ከዚያው ኢራቅ ደግሞ የኩርድ ፒሽሚርጋ ተዋጊዎች 70,000 ጦር አሜሪካን ተቀላቀሉ ። ከ 400,000 ጦር በላይ ኢራቅን ወረራት ። ረዳት አልባው የሳዳም ጦር ይህን ሁሉ ጦር መጋፈጥ ግድ ሆነበት !

በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ ከጨካኞቹ የሚመደበው የጊዜ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆርጅ ደብሊዉ ቡሽ ኢራቅን ጅምላ ጨራሽ መሳሪያ አላት በማለት ነው ጦር የጠማውን ሀያል ጦራቸውን እንዲዘምት ያዘዙት ። አሜራካ ጉዳዩን ለተመድ ጠቅላላ ጉባኤ አቅርባ የአለምን ድጋፍ ለማግኘት ብትጥርም አለም ግን ውሸችሽን ነው በማለት እምቢ ለአሜሪካ አለ ። ግና ምን ዋጋ አለው ። አሜሪካ በራሷ አለም ነበረች !!

አሜሪካ የጅምላ ጨራሽ መሳሪያን የውሸት ምክንያት አድርጋ ታቅርብ እንጅ እውነተኛ ሞክንያቶቿ ሶስት ነበሩ ።
1 አጓጊውን የኢራቅ ነዳጅ ና የተፈጥሮ ሀብት መቆጣጠር  ። ኢራቅ ያኔ በነዳጅ ባህር ውስጥ እየዋኘች ነበር ። በአለም ቁንጭ የነዳጅ አምራች የሆነቺዋ ኢራቅ አሜሪካን አጓጉታታለችና ለብዙ ትውልድ የሚተርፍ ነዳጅን አንቆርቁራ ለመውሰድ ይቻላት ዘንድ ሰቡብ ፈጥራ መውረር ነበረባት ። የሳዳም ሁሰይን ፉከራና ጉራ የጦር ግስጋሴዋን እንደማይመክተው አውቃዋለችና ፈፀመቺው !

2 ዶላርን መታደግ :- በጊዜው የአሜሪካ ዶላር ቁልቁል እየተምዘገዘገ የበጀት ክፍተቷም በታሪክ የወረደበት ነበር ። በተለይ የአውሮፓ ህብረት እንደ አንድ የኢኮኖሚ ማህበር ሆኖ ወጥቶ ዩሮ የሚባልን መገበያያ ሲፈጥር ዶላር መንገዳገድ ጀምሮ ነበር ። ለዶላር ራስ ምታት የሆነው ደግሞ ነዳጅ የሚያመርቱ ሀገራት ከዶላር በተጨማሪ በሌላ መገበያያ ገንዘቦች መገበያያት መጀመራቸው ነበር  ። ዋነኛዋ ደግሞ ኢራቅ ነበረች ። ስለዚህ ኢራቅ መመታት ነበረባት ለሌላውም ትምህርት ሆና ዶላርን መገዳደር የሚያመጣውን መዘዝ ማስተማሪያ መሆን ነበረባት ። ይህንን አሜሪካ ከአጋሮቿ ጋር ፈፀሙት !

3 በመካከለኛው ምስራቅ የጦር ካምፕ በመመስረት የአሜሪካን ልእለሀያልነት ማረጋገጥ ፦ የመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና እጅግ ስትራቴጂካዊ ቀጠና ነው ። መካከለኛው ምስራቅን የተቆጣጠረ አለምን እንደሚቆጣጠር ከሰው ልጅ ሲፈጠር ጀምሮ የተመሰከረ እውነታ ነው ። እናም አሜሪካ እዚያ ታሪካዊ ምድር ላይ እግሯን ብትተክል ወደ ምስራቅ ቻይናን ወደ ሰሜን ሩሲያና ኢራንን ገልመጥ እያደረገች አረቦችን እያሽቆጠቆጠች ከነዳጁ ምንጭ ላይ ተቀምጣ መቆጣጠር ያስችላታል ። የሆርሙዝ ሰረሰጥን በእይታ ውስጥ ማስገባት ለአሜሪካ ትርጉሙ የትየለሌ ነው ።

አሜሪካ እነዚህን ሶስት ድብቅ ፍላጎቷች ይዛ ኢራቅ ላይ ዘመተች ። የኢራቅን ጦር ከአጋሮቿ ጋር በመተባበር ለመደምሰስ አንድ ፈጀባት ። ከዚያም ሳዳምን በማስወገድ በቁጥጥር ስር ካደረገቺው በሗላ የአረፋ ቀን እንዲሰቀል አስደረገቺው ።

በዚያ ጦርነት አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ኢራቃዊያን በአሜሪካ ህይወታቸውን ተነጠቁ ። ኢራቅ ላታገግም ተደቆሰች ! ላትጠገን ፈራረሰች ! ላታበራ ጨለመች !

ሀብታሟ ሀገር ወደ ድህነት አሮንቃ ተዠዘፈቀች ። የአሜሪካ ወታደሮች ጥብቅ ሙስሊም እንስቶችን በጀምላ ደፈሩ አሰቃዩ የወሲብ ባሪያም አደረጓቸው ። የስልጣኔ ጅረቷ ኢራቅ ከሞንጎሎች በሗላ ጨካኝ ጦርን ዳግም አስተናገደች ።

አሜሪካ ግን ከዚያ ጦርነት በሗላ ወደታች እንጅ ወደላይ መሄድን አልሆነላትም ። እነቻይና አፍንጫዋ ሶር እስኪገቡ አለምም አሜሪካን እንዲታዘብና ውሸታምነቷን እንዲያረጋግጥ ያደረገ ክስቱት ሆኖ ይኖራል ።

Seid Mohammed Alhabeshiy

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

ውድ ቤተሰቦቻችን እንኳን ለተከበረው የረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ


እስከ አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት ረመዳን የመጀመሪያ ቀን ወደ ሀሙስ ያደላ ይመስላል፣

አላህ በሰላም ያድርሰን

ረመዳን ሙባረክ

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

➨ #ALPARSLAN_BÜYÜK_SELÇUKLU1
━━━━━━━━━
➠ #ክፍል_95

➠ #አማረኛ_ትርጉም

━━━━━━━━━━

➠ share /channel/ertugrulethiopia
║▌║█║║▌║█║║▌║█║║▌║

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

🎬   ኩሩሉሽ ዑስማን
         ጥራት     HD 

🎵        አማርኛ ትርጉም (በአንድ ድምፅ)

ምእራፍ 4

⏸⏩ ክፍል 178


http://t.me/ertugrulethiopia

ዩቲዩብ ቻናላችንን ይቀላለቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/channel/UCR1_qbjujV6Z_ypHrTJMTKw

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

➨ #ALPARSLAN_BÜYÜK_SELÇUKLU1
━━━━━━━━━
➠ #ክፍል_94

➠ #አማረኛ_ትርጉም

━━━━━━━━━━

➠ share /channel/ertugrulethiopia
║▌║█║║▌║█║║▌║█║║▌║

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

ሙሀመድ ቢን ሰልማን የቱርኩን ሙስጦፋ ከማል አታቱርክን ለመሆን እየሰራ ይገኛል ።
አታቱርክ እስልምናን ከቱርክ ህዝብ ለመነጣጠል ያደረጋቸውን ስትራቴጂዎች ቢን ሰልማንም ቀስ በቀስ እየፈፀማቸው ነው ።

አታቱርክ ከተጠቀመው መንገድ አንዱ የቱርክ ህዝብ የእስልምና ስልጣኔን ትቶ በምእራባውያን ስልጣኔ ፍቅር እንዲወድቅ ማድረግ ነበር ። ለዚያም የምእራባውያን ባህል በቱርክ እንዲሰርፅ ሁሉንም ነገር አድርጓል ። የቱርክኛ ቋንቋ ከአረብኛ ፊደል ይልቅ በላቲንኛ እንዲፃፍ ከማድረግ ጀምሮ ኢስላም ነክ ቃላቶች በሙሉ ከቱርክ እንዲወገዱና ሀይማኖታዊ ተግባራት ሳይቀር በአረብኛ እንዳይፈፅሙ እስከማድረግ ደርሷል ። የምእራባዊያን የፊልምና ሌሎች የጥቡብ ስራዎች በቱርክ እንዲስፋፉና ከምእራባውያን አለባበስ ውጭ ቱርኮች እንዳይለብሱ እስከማድረግ ደርሷል ።

የሙሀመድ ቢን ሰልማን አካሔድ ከዚህ የተለየ አይደለም ። የሳኡዲ ህዝብ በምእራባውያን ስልጣኔ እንዲወድቅ ከፍተኛ የሆነ የባህል አብዮት እያደረገ ነው ። በሀገሪቱ የምእራባውያን የሙዚቃ ኮንሰርቶችና የፊልም ኢንዱስትሪዎች እንዲስፋፉ እያደረጉ ነው ። በተቃራኒው ኢስላማዊ እንቅስቃሴዎች ከእለት ወደ እለት እየተገቱ ኡለማዎች የነበራቸው ስልጣን እንዲወገድ እያደረገ ብዙዎችንም እያሰረና እያሰደደ ነው ።

አሁን ቢን ሰልማን በሳኡዲ የሚገዳደረው የሌለው ሀያል ሰው ነው ልክ እንደያኔው አታቱርክ !

አታቱርክ ቱርክን ከእስልምና መነጠል እንደቻለው ቢን ሰልማን ሳኡዲን ከኢስላም መነጠል ይቻለው ይሆን ??

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

Barbaros:
ባርባሮስ  BARBAROSLAR
🎬🎬🎬🎬🎬🎬🎬🎬🎬
🛥🛥🛥🛥🛥🛥🛥🛥🛥

አማርኛ ትርጉም

🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢

ክፍል 83

🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌

ቴሌግራም ቻናላችን
👇👇👇👇👇
T.me/ertugrulethiopia

ዩቲዩብ ቻናላችን
==========================
https://youtube.com/channel/UCR1_qbjujV6Z_ypHrTJMTKw

Читать полностью…

አርጦግሮል ኢትዮጵያ|| ertugrul ethiopia

🎬   ኩሩሉሽ ዑስማን
         ጥራት     HD 

🎵        አማርኛ ትርጉም (በአንድ ድምፅ)

ምእራፍ 4

⏸⏩ ክፍል 175


http://t.me/ertugrulethiopia

ዩቲዩብ ቻናላችንን ይቀላለቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/channel/UCR1_qbjujV6Z_ypHrTJMTKw

Читать полностью…
Subscribe to a channel