etconp | Unsorted

Telegram-канал etconp - ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

28628

🔨እጅግ ጠቃሚ የ ኮንስትራክሽን ትምህርቶች 💵የ ኮንስትራክሽን እቃዎች ሻጭ እና ገዢ ሚገናኙበት 📐ውብ ውብ የ ቤት ዲዛይናኖች 💻ሶፍትዌሮችና ሴታፖችን 📙መፅሃፍቶች 🎬ቪድዮዎቾ ምታገኙበት ቻናል 📨ሃሳብና ኣስተያየት @ETCONpBOT ፃፉልን ☎ +251925446661 📌ጨረታ ና ስራ @ETCONpWORK 📃 ለ መወያያ @COTMp 📍ዲጂታል ቤተ መፅሃፍ @ETCONpDigitalLibrary_Bot

Subscribe to a channel

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

👉የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅን ለቋሚ ኮሚቴ ተመራ

ግንባታ ከማከናወናቸው አስቀድመው ቤት የሚሸጡ ሪል ስቴት አልሚዎች፤ ከደንበኞቻቸው የሚሰበስቡትን ገንዘብ በዝግ የባንክ አካውንት እንዲያስቀምጡ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ።

አዲሱ ረቂቅ አዋጅ፤ ቤት ለመገንባት የመሬት የይዞታ ማረጋገጫ እና የግንባታ ፈቃድ ያላገኙ የሪል ስቴት አልሚዎች ደንበኞችን እንዳይመዘግቡ እና ቅድመ ክፍያ እንዳይሰበስቡም ይከለክላል።

“የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ” የተሰኘው ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ዛሬ ሐሙስ መስከረም 30/2017 ዓ.ም. በተደረገው የፓርላማው አራተኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመጀመሪያ መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው።

በአሁኑ ጊዜ ባለው አሠራር መሠረት የንግድ ፈቃድ በማውጣት ብቻ ወደ ሪል ስቴት ገበያው ሲቀላቀሉ የነበሩት አልሚዎች፤ በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ “የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ” የማውጣት ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

የአገር ውስጥም ሆነ የውጭ ባለሀብት ሪል ስቴት አልሚዎች ይህንን ፈቃድ ለማግኘት ቢያንስ 50 ቤቶችን ገንብተው የሚያስከረክቡ መሆን እንዳለባቸው ረቂቅ ላይ ሰፍሯል።

ረቂቁ፤ “የሪል ስቴት አልሚው በቤት ቅድሚያ ሽያጭ ስልት ለመሥራት መፈለጉን አግባብ ላለው አካል አሳውቆ ፈቃድ ማግኘት [አለበት]” ሲል አዲሱን ሕግ ግዴታ አስቀምጧል።

የቅድመ ሽያጭ ዘዴን መጠቀም የሚፈልጉት ሪል ስቴት አልሚዎች፤ ከቤት ገዢዎች የሚሰበስቡት ገንዘብ የሚቀመጥበት የባንክ ሂሳብ እና የገንዘብ አወጣጥ ላይም አስገዳጅ አሠራር በረቂቅ አዋጁ ተጥሎባቸዋል።

አልሚዎቹ ከቤት ገዢዎች የሚሰበስቡትን ገንዘብ “የዝግ የባንክ ሂሳብ ገቢ ማደረግ ወይም ማስያዝ” እንዳለባቸው ረቂቅ ሕጉ ላይ ሰፍሯል።

ከዚህም ባሻገር በቅድሚያ የተሸጠው ቤት ተገንብቶ ለተጠቃሚዎች እስከሚተላለፍ ድረስ የቤት የመሥሪያ ቦታው የይዞታ ማስረጃ “በሚመለከተው አካል እንዳይሸጥ፣ እንዳይለወጥ” እንደሚታገድ ረቂቁ ይገልጻል።

ቤት ቀድመው በሚሸጡ ሪል ስቴት አልሚዎች ላይ እነዚህ አስገዳጅ አሠራሮች የተቀመጡት “ደንበኞች የሚደርስባቸውን እንግልት እና ኪሳራ ለመቀነስ በማሰብ” እንደሆነ የአዋጁ ማብራሪያ ያስረዳል።

በረቂቁ መሠረት፤ የሪል ስቴት አልሚዎች ግንባታው 80 በመቶ ላይ ያልደረሰን ቤት ለደንበኞች እንዳያስተላልፉ ተከልክለዋል።

ረቂቁ፤ “ያለደንበኛው ፍላጎት እና ፈቃድ አጠቃላይ ግንባታው ቢያንስ 80 በመቶ ያልተጠናቀቀ ቤት ለደንበኞች ሊያስተላልፍ አይችልም” ይህንን ለማድረግ በቅድሚያ ደንበኛው መስማማት እንዳለበት ያመለክታል።

ሪል ስቴት አልሚዎች ቤት ገዢዎችን መመመዝገብ እና ቅድመ ክፍያ መሰብሰብ የሚችሉበት ጊዜም ቅድመ ሁኔታ ተቀምጦበታል።

Via BBC Amharic

@etconp

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

👉አንድን ጨረታ የሚያሸንፈው ዝቅተኛ ዋጋ አቅራቢ ተጫራች ወይስ ከመሐንዲሱ ግምት ተቀራራቢ የሆነ ዋጋ ያስገባ ተጫራች?

💫ጨረታ ለተቋራጮች በሁለት አይነት መንገድ ሊፈጸም ይችላል።

⭐️አንደኛ ግልጽ ጨረታ ሲሆን ማንኛውም ብቁ የሆነ፣ ህጋዊ ፍቃድ ያለው እና ፍላጎት ያለው ተቋራጭ መሳተፍ የሚችልበት በጋዜጣ ወይም በአካባቢው ባሉ የማታወቂያ መንገዶች ወይም በማህበራዊ መገናኛ ድረገጾች (website) ላይ በሚለቀቅ የተጫራችነት ግብዣ ጥሪ (Invitation to Tender) አማካኝነት ተጫራቾች ኩል ዕድል ተሰጥቷቸው እንዲሳተፉ የሚጋበዙበት ሂደት ሲሆን

⭐️ሁለተኛው ውስን ጨረታ የሚባል ነው። ውስን ጨረታ አንድ ተጋባዥ ወይም ውስን ቁጥር ያላቸው ልዩ መስፈርት የተሰጣቸው ተጫራቾች ጋር በሚደረግ ድርድር ወይም የመለያ ጨረታ አማካኝነት የሚከናወን የጨረታ አይነት ነው።

📜በግልጽ ጨረታ ሂደት ደግሞ አጫራቹ አካል ሁለት አይነት መንገድን ሊጠቀም ይችላል።

🏷[አንደኛው] ፖስት ኳሊፊኬሽን (Post Qualification) የሚባል ሲሆን ሥራው ቀለል ያለ እና ማንኛውም ተጫራች ሊያከናውነው የሚችል ከሆነ ቅድሚያ ኢኮኖሚያው (የገንዘብ) መጠናቸውን መመዘን ነው።

⏺በዚህ ሂደት ቅድሚያ ቅንሽ ዋጋ ያስገቡ ተጫራቾች ተለይተው እነዚያ ደግሞ በቴክኒካዊ ልኬት ተመዝነው አሸናፊ የሚለይበት መንገድ ነው።

🏷[ሁለተኛው] ፕረ ኳሊፊኬሽን (Pre-Qualification) የሚባለው ደግሞ ማንኛውም ተጫራች ቅድሚያ በቴክኒካዊ ልኬት ተመዝነው በኋላ በገንዘብ ዝቅተኛ ያስገባው አሸናፊ የሚሆንበት የጨረታ ምዘና መንገድ ነው።

⏺በመሆኑ ይህ ሂደት በፌደራል የግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የወጣው መመሪያ ክፍል አምስት (5) ንዑስ ክፍል (1), (2) እና (3) ላይ በዝርዝር የተብራራ ነው።

🚧በመሆኑም በጨረታ ሰነዶች ምዘና (Bid Response Document Evaluation) ሂደት ላይ ተጫራቾት እንደጨረታ ሰነዱ አወጣጥ ተመስርቶ በቅድሚያ ዝቅተኛ ዋጋ ያስገቡትን በመምረጥ (Post Qualification ሂደትን በመከተል) በቴክኒካል ሰነዳቸው አXእናፊውን የሚለይበትን መንገድ ሊከተል ይችላል።

▶️አልያም ደግሞ Pre-Qualification ሂደትን በመከተል ቅድሚያ የቴክኒካል ሰነዳቸው ታይቶ ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ብቻ ተለይተው ዝቅተኛ ገንዘብ ባስገባ (Lowest bidder) የሚለዩበት መንገድ ነው።

▶️ይህ ሁለቱም መንገድ በግል ፕሮጀክቶችም ይሁን በመንግሥት ፕሮጀችቶች ላይ ተግባራዊ ሊደረጉ የሚችሉና ህጋዊ እውቅና ያላቸው መንገዶች ናቸው።

▶️የጨረታውን አከፋፈት በተመለከተ በ ክፍል 2 (2.2.1.5) ላይ እንደተብራራው ቃለጉባኤ ተይዞ፣ የጨረታውን አከፋፈት ሂደት ላይ ውይይት ከተካሄደባቸው ጉዳዮች በተጨማሪ ጨረታው ሲከፍተ የተገኙ ተጫራቾች ወይምህጋዊ ወኪሎቻቸው ስለጨረታው አከፋፈት ሂደት የሚያብራራ ቃለጉባኤ ላይ ስማቸውን እና ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይገባቸዋል። etconp

❇️አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የመሐንዲስን ግምት ያማከለ የጨረታ ሰነዶች ምዘና የሚካሄድበት አጋጣሚ አለ።

⏺ይህም Federation Internationale Des Ingenieurs Conseil – FIDIC አንቀጽ 14 ላይ እንደተገለጸው ተጫራቾች መሐንዲሱ ገምቶ ያስቀመጠውን የግንባታ ዋጋ (Engineering Estimation of Construction Cost) እንደመነሻ በመቁጠር ተጫራቾች ከግምቱ በታች ከ20% በታችን የቀነሰ ዋጋ እንዳያስገቡ ወይም ከግምቱ በላይ ከ20% በላይ እንዳይጨምሩ ገደብ በማስቀመጥ ከዚህ እሳቤ ውጪ የሆኑትን የተጫራቾች ሰነዶች በመጣል በዚህ ክፍተተ (interval) ውስጥ ያሉትን ብቻ የማወዳደር ሥራ የሚሰሩበት መንገድ ነው። etconp

⏹ቢሆንም ግን ይህ አካሄድ ግምቱን ባወጣው መሐንዲስ (ግለሰብ) ጥንቃቄ እና እውቀት ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ብዙ ክፍተቶች የሚፈጠሩበት ቢሆንም  የፌደራል መንግስት የግዢ መመሪያ ቀድሞ በነበረው በዚህ አሰራር ላይ ግልጽ ማብራሪያ ሳያስቀምጥ አልፎታል።

❇️ለማንኛውም አስተያየትዎ  እና ሀሳብዎ ይጻፉልን!

📜ለ ስራ እና ጨረታዎች ምንለቅበት ቻናል ለመቀላቀል👉 @ETCONpWORK

📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT

💫ቲክቶክ:👇

www.tiktok.com/@etconp7

@etconp

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

👉40 በመቶ የአዲስአበባ ከተማ ክፍል ፈራሽ ነዉ ተባለ

🚧በፈረሳዉ የተነሳ 300 ሺህ ሰዎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ይነካሉ

40 በመቶ የአዲስአበባ ክፍል ፈራሽ መሆኑን መሠረት ሚዲያ ምንጮች ነግረዉኛል ሲል ዘግቧል። የዜና ምንጩ ፈረሳዉ በሁለተኛዉ ምዕራፍ የአዲስአበባ የኮሪደር ልማት መስመሮች የተነሳ ነዉ ብሏል።

የኮሪደር ልማቱን ለመከወን ከ 110 ቢሊዮን ብር በላይ ይጠይቃል መባሉንም ዳጉ ጆርናል ከዘገባዉ ሰምቷል። በዚህም የተነሳ 300 ሺህ ሰዎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ይነካሉ ብሏል። በዚህም መሰረት በፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎችም ተጎጂዎችም ሊኖሩ ይችላሉ ተብሏል። በመጀመሪያዉ ዙር የኮሪደር ልማት ቀደምት የአዲስአበባ ሰፈሮች መፍረሳቸዉ ይታወቃል።

በአጠቃላይ በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት 2817 ሄክታር የቦታ ስፋት ሲኖረው 132 ኪሎሜትር ርዝመትን እንደሚሸፍን መዘገባችን አይዘነጋም።

@etconp

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

👉ECWC Research Competition

/channel/ETCONp/11712

@etconp

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

👉ደቡብ ሱዳንና ኡጋንዳ በነጭ አባይ ላይ በ98 ሚሊየን ዶላር ግድብ ሊገነቡ መሆኑ ተሰምቷል።

🏷ጥቁር አባይና ነጭ አባይ ሱዳን ላይ ሲገኙ ጥቁር አባይ 100% መገኛው ኢትዮጵያ ነች::

@etconp

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

👉PLINTH BEAM AND IT'S FUNCTIONS

🚧A plinth beam is a horizontal structural element that is typically constructed at the plinth level of a building, which is the level of the ground floor.

▶️It connects the walls of the building and serves several important purposes:

🌟Functions Of Plinth Beam

⏺Load Distribution: Plinth beams help distribute the load of the walls and any additional loads (like floors and roofs) evenly to the foundation. This reduces the risk of differential settlement and improves the overall stability of the structure.

⏺Lateral Stability: They provide lateral stability to the walls, helping to resist horizontal forces such as wind or seismic loads.

This is particularly important in regions prone to earthquakes or strong winds.

⏺Prevention of Cracks: By providing a continuous and rigid support, plinth beams help minimize cracking in walls due to settlement or temperature changes.

⏺Elevation of Walls: They elevate the walls above ground level, protecting them from moisture and water damage, which is crucial in areas with high water tables or flooding risks.

⏺Integration with Foundation: Plinth beams are often integrated with the foundation, creating a more robust and cohesive structural system that enhances the overall durability of the building.

@etconp

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

👉ቢቸና - ቁይ መገንጠያ

🚧ምስራቅ ጎጃም ዞን ብቸና ከተማ ሳይደርስ "ቁይ መገንጠያ" በሚባል ቦታ የ አስፋልት መንገዱ በመንሸራተቱ በሚታየው መልኩ ከአገልግሎት ውጭ ሆኗል።

Via Wasu

@etconp

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

Difference Between Cost plus And Lump som

@etcop 👇

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

👉Lemi National Cement unveils ambitious expansion plans following historic $600 million greenfield investment

🏷Lemi National Cement, which was the first to invest a significant amount in a greenfield project and formally opened a week ago, plans to expand further in order to increase its output by double.

⏺The facility was built with a USD 600 million joint venture (JV) investment by the leading Ethiopian industrial conglomerate East African Holding and Hong Kong-based Western International Holdings.

Via capital ethiopia

@etconp

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

ሁሉን በአንድ ቦታ የሚያገኙበት እና ለሁሉም ቅርብ

ምን ይፈልጋሉ?

፦ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

፦ላሜራ ማስቆራረጥ ማስበሳት ወይንስ ማሳጠፍ ከፈለጉ እንዳያስቡ ሁሉንም ማሽኖች አስገብተናል

፦ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ ማስበጀት ወይንም ማሳጠፍ ካሰቡ ለሱም ማሽኑ በጃችን ነዉ

፦ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን የሚሰሩ ብቁ ባለሙያዎችም አሉን

ይደዉሉልን ያማክሩን

ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

0904040477
0911016833

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

" The Claim Digger (Schedule Comparison) Tool in Primavera P6 "

🛠 What is the Claim Digger Tool?
The Claim Digger Tool is designed to analyze and extract relevant data from your project schedules, making it easier to identify delays, assess impacts, and support claims effectively.

✅ Advantages:
1-Data Visualization: Simplifies complex data, helping stakeholders understand project timelines and impacts.
2-Enhanced Reporting: Generates detailed reports that highlight key areas of concern, making claims clearer and more robust.
3-Efficiency: Saves time by automating data extraction and analysis, allowing planners to focus on strategic decision-making.

⚠️ Cons:
1-Learning Curve: Requires familiarity with both Primavera P6 and the tool itself, which may take time to master.
2-Data Dependency: The effectiveness of the tool hinges on the quality and completeness of the underlying project data.

📈 When to Use the Claim Digger Tool:
A-Delay Analysis: When assessing the cause and extent of delays, helping determine liability and supporting claims.
B-Change Orders: Analyzing the impact of changes on project timelines to substantiate requests for extensions.
C-Contract Disputes: Providing clear visual evidence during negotiations to support claims or defenses.

🔍 Example Scenarios:
*Scenario 1: A contractor faces a delay due to unforeseen site conditions.*

Using the Claim Digger Tool, the planner can analyze the schedule to demonstrate the impact of these conditions and justify a time extension.

*Scenario 2: A project encounters multiple change orders.*

By utilizing the tool, the planner can effectively visualize the cumulative effect of these changes on the overall schedule, aiding in negotiations with stakeholders
@etconp

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

👉ዛሬ አለምአቀፍ የ ኪነ ህንፃ ቀን ነው

🚧የአለምአቀፍ የኪነህንጻን ቀን ስናከብር በተለያዩ የአገራችን ክፍል ያለን  ኪነህንጻ ባለሙያዎች ለሙያው የሚከተሉትን 10 ነጥቦች ለመከወን መተባበር  ይጠበቅብናል።

1. የኪነህንጻ ትምህርት እንዲዘምን ማድረግ፣

2. ለሙያው ተገቢው የምዘና እና የፍቃድ ምስክር እንዲሰጠው ማድረግ፣

3. ለባለሙያዎች ተገቢውን ተከታታይ ስልጠና ማሰጠት፣

4. ሙያዊ ክፍያ እንደተቀረው አለም ሁሉ በእኛም አገር  ከግንባታ መቶኛ ጋር እንዲያዝልን ስራ መስራት፣

5. ከተማዊ እና ኪነህንጻዊ ቅርጾች የሚመዘገቡበትን እና የሚጠበቁበትን አግባቦች ከባለድርሻ አካላቶች ጋር ተቀራርቦ ማፈላለግ፣

6. ባለሙያዎች የ BIM እንዲሁም መሰረታዊ የንድፍ ሶፍትዌሮችን ጨምሮ  የሌሎች ቴክኖሎጂ ሶፍትዌሮች በቅናሽ የሚያገኙበት ዘይቤ ማመላከት፣

7. የውጭ ግዙፍ የንድፍ ድርጅቶች አገር ውስጥ ገብተው በሚሰሩበት ወቅት ከ አገራዊ ድርጅቶች ጋር ተጣምረው የሚሰሩበት አመላካች ፍኖተ ካርታ ላይ መምከር።

የሚገቡ ከሆነ ደግሞ በዘርፈ ብዙ ችግሮች የተተበተቡ የአገር ውስጥ  አማካሪዎች ጠንክረው የሚቆዩበትን አማራጭ ማዘጋጀት፣

8. ሰ.አ. (artificial intelligence) ከኪነህንጻ ጋር ያለውን ቁርኝት በቅጡ አውቆ መዘጋጀት፣

9. ከዴስክቶፕ ወደ ክላውድ ኮምፒውቲንግ የሚደረገውን ሽግግር ማቀላጠፍ፣

10. የሙያ ፈቃድ እስካላቸው ድረስ ወጣት ነዳፍያን በትላልቅ የንድፍ ውድድሮች ላይ በራሳቸው መወዳደር እንዲችሉ ማድረግ። ናቸው።

መልካም አለምአቀፍ የኪነህንጻ ቀን!

@etconp

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

በአዋሽ ፈንታሌ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የተወሰኑ ቤቶችን ማፍረሱን ሰመራ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ

በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው ትናንት ምሽት የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የተወሰኑ መኖሪያ ቤቶችን ማፍረሱን ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ባወጣው መረጃው አመልክቷል።

በመሬት መንቀጥቀጡ መሬት መሰንጠቁንም ዩኒቨርቲው ዛሬ ሰኞ ማለዳ አስታውቋል።

በፈንታሌ ተራራ ላይ ተከስቶ ንዝረቱ አዲስ አበባ ከተማ ድረስ የተሰማው የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ከሁለት ሳምንታት በላይ በተለያየ አጋጣሚ መከሰቱን ባለሞያዎቹ ገልፀዋል። ትናንት መስከረም 26/2017 ምሽት 2፡10 ገደማ የተከሰተው በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 9 የተመዘገበበት ነበር።

ከሰሞኑ የሚስተዋለው የመሬት መንቀጥቀጥ በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው ከፍተኛ ሥጋት ፈጥሯል ያለው ዩኒቨርሲቲው፣ አደጋው በተከሰተበት ሳቡሬ ቀበሌ  ተገኝቶ መረጃ የመሰብሰብ እና ለማህበረሰቡ ጥንቃቄ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ መሥራቱንም ገልጿል።

የዩኒቨርሲቲው ጂኦሎጂስቶች ነዋሪዎች ከፈንታሌ ኮረብታማ ቦታ እና ከከሰም ግድብ ርቀው እንዲቆዩ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

እሑድ ምሽት የተከሰተውና በአዲስ አበባ በነዋሪዎች ላይ መደናገጥ የፈጠረው የመሬት መንቀጥጠጥ ለ18 ሴኮንድ የቆየ እንደነበረ ባለሞያዎች ተናግረዋል።

@etconp

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

👉የኮንስትራክሽን ንግድ ፍቃድ ያላቸው ተቋማት የገቢ ግብር (Income Tax) የሚከፍሉት ምንያህል ነው?

🏷የኢትዮጵያ ገቢዮች ሚኒስቴር ከገቢ ላይ በሚገኝ ግብር አከፋፈል አዋጅ ቁጥር 979/2016 (under the income tax proclamation No. 979/2016) አንቀጽ ቁጥር 19 (2) ሥር ከመወዝ የሚገኝ ገቢ ግብር፣ ከሕንጻ ኪራይ እና መሰል አገልግሎቶች የሚገኝ ገቢ ግብር፣ ከንግድ ሥራ ገቢ የሚገኝ ግብር እና ከሌሎች ልዩ ልዩ ሥራ የሚገኝን ገቢ ግብር አከፋፈል አርቅቋል።

⏺በዚህ ውስጥ የግንባታ ሥራ አማካሪዎች፣ የሕንጻ የመንገድ እና ሌሎች የሲቪል ምህንድስና ሥራ ተቋራጮች፣ እና የሕንጻ መሳሪያና ግብአት አቅራቢዎች በንግድ ሥራ ሥር የሚጠቃለሉ ናቸው።

🏷በመሆኑም ዓመታዊ ገቢያቸው ከ0 – 7200 ብር የሆኑ ምንም አይነት ግብር የማይከፍሉ፣ ከ7201 – 19800 ብር ዓመታዊ ገቢ 10% ግብር፣ ከ19801 – 38400 ብር ገቢ ያላቸው 15% ግብር፣ ከ38401 – 63000 ገቢ ያላቸው 20% ገቢ፣ ከ63001 – 93600 ብር ዓመታዊ ገቢ 25% ግብር፣ ከ93601 – 130800 ብር ገቢ 30% ግብር፣ ከ130800 በላይ ዓመታዊ ገቢ ያላቸው 35% የገቢ ግብር ክፍያ እንዲከፍሉ ይገደዳሉ።

🚧ነባራዊ ሁኔታ፦ በሀገራችን የቫት ምዝገባ መመሪያ መሰረት መነሻ ካፒታል አንድ ሚሊዮን ብር ስለሚያስፈልግ ብዙዎቹ የኮንስትራክሽን ንግድ ፍቃድ ያላቸው አማካሪዎች፣ ተቋራጮች እና አቅራቢዎች ይህንን ያሟሉ ስላልሆነ በቁርጥ ግምት የገቢ ግብር የሚከፍሉ ናቸው።

⏺በዚህ ሂደት ውስጥ የድርጅቱ ገቢ የሚወሰነው ገማቹ አካል በሚኖረው መረጃ እና እይታ መጠን የተወሰነ ስለሚሆን የወጣው የገቢ ሰሌዳ ከግምት ውስጥ ሲገባ አይስተዋልም።

⭐️ብዙ ጊዜ 30% አካባቢ የገቢ ግብር ተግባራዊ የሚደረግ ሆኖ ይስተዋላል።

❇️ለማንኛውም አስተያየትዎ  እና ሀሳብዎ ይጻፉልን!

📜ለ ስራ እና ጨረታዎች ምንለቅበት ቻናል ለመቀላቀል👉 @ETCONpWORK

📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT

💫ቲክቶክ:👇

www.tiktok.com/@etconp7

@etconp

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

👉URGENT VACANCY

⭐️We Need Office Engineer

/channel/ETCONpWORK/2285

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

👉ይህ ከላይ በ ምስል ያያዝነው ህንፃ ካክተስ ታወር (Kaktus towers) ይባላል ኮፐንሀገን ዴንማርክ የሚገኝ ሲሆን በ BIG ብያርክ ኢንገልስ ግሩፕ የተነደፈ የጋራ መኖርያ ህንጻ ነው።

💫ጠቅላላ የያዘው የ አባ ወራ ብዛት 495 ሲሆን የ ህንፃው ቁመት 80 ሜትር ነው።

🚧በረጅም ህንጻዎች ምክርቤት እና በኧርባን ሀቢታት ስብሰባ ላይ ምርጡ የአውሮፓ ከፍተኛ ፎቅ ሽልማትን ተቀብሏል።

🏷በየወለሉ መሽከርከሩ እንዲሁም እያንዳንዱ ወለል የተለየ አጠቃላይ ቅርጽ ማግኘቱ ለህንጻው ውበት ልህቀት አስተዋጽኦ አድርገዋል።

🔰ንድፉን ስንመለከት የ እውቁ ዴንማርካዊ ነዳፊ የ ብያርክ ኢንገልስ ስራ መሆኑን መገመት አያዳግትም።

@etconp

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

👉በ መቐለ ከተማ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ተጀመረ

🚧በ መቐለ ከተማ በ2 ነጥብ 1ቢሊዮን ብር በጀት የአስፋልት መንገድ ግንባታ መጀመሩን በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የመቐለ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

💫የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ የመሰረተ ልማት አማካሪ አቶ ሀፍቱ መብራህቱ እንደገለፁት፤ በከተማዋ በ2017 በጀት ዓመት 9 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ለመገንባት የተያዘውን እቅድ ተግባራዊ ማድረግ ተጀምሯል።

Via EBC

@etconp

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

👉ሁሉን በአንድ ቦታ የሚያገኙበት እና ለሁሉም ቅርብ

🔰ምን ይፈልጋሉ?

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ ማስቆራረጥ ማስበሳት ወይንም ማሳጠፍ ከፈለጉ  እንዳያስቡ ሁሉንም ማሽኖች አስገብተናል

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ ማስበጀት ወይንም ማሳጠፍ ካሰቡ ለሱም ማሽኑ በጃችን ነዉ

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን የሚሰሩ ብቁ ባለሙያዎችም አሉን

☎️ይደዉሉልን ያማክሩን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ 1. መርካቶ
                   ቁ.1 አየር ጤና
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

👉አስደሳች ዜና

🏷በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ተግባራዊ ምርምር እና ፈጠራን ለማበረታታት ይፈልጋል።

⭐️ለዚህም የ ኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን (ECWC) ከሰራተኞች አዳዲስ የምርምር ሀሳቦችን በማስተዋወቅ ቀጣይነት ያለው ሙያዊ እድገት እና እውቀትን የማጎልበት ፖሊሲውን በማስቀጠል ግልፅ ውድድር እንደሚካሄድ አስታውቋል።

📜የዚህ ማስታወቂያ አላማ የ ECWC ሰራተኞችን የጋራ እውቀትን ማበረታታት ነው ወደተወሰኑ የምርምር ጭብጦች የሚያጠኑ የምርምር ሀሳቦችን እንድታቀርቡ ይጋብዛል።

💫ይህ ጥሪ የኮርፖሬሽኖቻችንን አሠራር ለማሻሻል አዲስ አስተሳሰብን የሚያነሳሳ እና ተግባራዊ መፍትሄዎችን ያበረታታል።
ሽልማቶች፡-

❇️1ኛ አሸናፊ፡ 200,000 ብር
❇️2ኛ አሸናፊ፡ 150,000 ብር
❇️3ኛ አሸናፊ፡ 100,000 ብር

📜የምርምር ገጽታዎች፡-

⏺የግንባታ ቁሳቁስ
⏺የግንባታ ቴክኖሎጂ
⏺የግንባታ ዘዴ
⏺የግንባታ አስተዳደር

🚧ውሎች እና ሁኔታዎች፡-

⏺ብቁነት፡ ይህ ጥሪ ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ሰራተኞች ክፍት ነው።

⏺የዳኝነት መስፈርት፡ ወረቀቶች የሚገመገሙት በዋናነት፣ ከጭብጡ አግባብነት፣ የጥናት ጥልቀት፣ የአቀራረብ ግልፅነት እና ተግባራዊ እንድምታዎች በባለሙያዎች ቡድን ነው።

⏺የማስረከቢያ መስፈርቶች፡ ወረቀቶች ኦሪጅናል ያልታተሙ መሆን አለባቸው፣ እና ከተጠቀሱት የምርምር ጭብጦች አንዱን የሚያብራራ ለማንኛውም ጆርናል ወይም አሳታሚ መሆን የለበትም፡ የግንባታ ቁሳቁስ፣ የግንባታ ቴክኖሎጂ፣ የግንባታ ዘዴ ወይም የግንባታ አስተዳደር።

⏺መብቶች እና ፈቃዶች፡- ወረቀት በማቅረብ ተሳታፊዎች ገንዘቡን ይሰጣሉ፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ደግሞ ይዘቱን አሳትሞ ለፓተንት ወይም ለስራ ማስኬጃነት የመጠቀም መብት አለው።

⭐️መስፈርቱን የሚያሟላው ፕሮፖዛል/ወረቀት/ጥናት ሙሉ ወረቀቱን ለማቅረብ ይነገራል።

⏺ብቁ አለመሆን፡ የማስረከቢያ መመሪያዎችን የማያሟሉ፣ ከቀነ-ገደቡ በኋላ የሚቀርቡ፣ ወይም የሀሰት ወሬዎችን የሚያሳዩ ወይም የትኛውንም አይነት ታማኝነት የጎደላቸው ወረቀቶች ውድቅ ይሆናሉ።

🏷የማስረከቢያ ቀን

• የማስረከቢያ የመጨረሻ ቀን፡ ኖቬምበር 5፣ 2024

ፕሮፖዛሉን ሲያዘጋጁ፣ ከዚህ በታች የተያያዘውን ቅጽ ይጠቀሙ።

📩በኢሜል ያስገቡ፡- projm2021@gmail.com ወይም rkmt2017@gmail.com ይላኩ

• አስቻለው መርሻ፣ ስልክ ቁጥር +251 912 687699 ወይም
• አንሙት ሞላ፣ ስልክ ቁ. +251 964 063944

@etconp

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

👉የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ማስፈጸሚያ ህግጋት

💫ማንኛውም በኮንስትራክሽን ዘርፍ ውስጥ የሚሳተፍ ድርጅትም ሆነ የመንግስት አካል እንዲሁም ግለሰብ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ውስጥ የተዘረጉ የአሠራር ሥርዓቶች አዋጆችን፣ ደንቦችን፣ ስታንዳርዶች፣ ኮዶች፣ መመሪያዎችን አክብሮ መስራት የሚጠበቅበት ሲሆን እነዚህ የሕግ ማእቀፎች በዋናነት የሚከተሉትን የማስፈጸሚያ ስርዓት ያካትታል፡፡

🚧የፌዴራል መንግሰት ፕሮጅክት አስታዳደር እና አመራር ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1210/2012

🚧የኢትዮጵያ ህንፃ አዋጅ ቁጥር 624/2001

🚧የኢትዮጵያ የውሃ ሀብት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 197/1992፣

🚧የኢንቨስትመንት እና ተያያዥ ህግጋት፣

🚧ከኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ግዥና የውል አስተዳደር ጋር ተያያዥነት ያላቸው ህግጋት፡፡

🚧የተቀናጀ መሠረተ ልማት ማስተባበሪያ አዋጅ ቁጥር 857/2006፡-

🚧በሚኒስቴር መስሪያቤቱ በዘርፉ ተዘጋጅተው የወጡ ደንቦችና መመሪያዎች፣

🏷ሌሎች ከዘርፉ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ህግጋቶች፡፡

❇️ለማንኛውም አስተያየትዎ  እና ሀሳብዎ ይጻፉልን!

📜ለ ስራ እና ጨረታዎች ምንለቅበት ቻናል ለመቀላቀል👉 @ETCONpWORK

📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT

💫ቲክቶክ:👇

www.tiktok.com/@etconp7

@etconp

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

👉ታሪካዊው አፍሪካ ፓርክ (AFRICA PARK)

🏷አፍሪካ ፓርክ በመሃል አዲስ አበባ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ፊት ለፊት በሚገኝ መንገድ አካፋይ ላይ በ45,707 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚገኙ ሦስት ፓርኮችን (ኢትዮጵያ ፓርክ፣ አዲስ አበባ ፓርክና አፍሪካ ፓርክ) ያካተተ ሆኖ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን የሚተዳደሩ ፓርክ ነው፡፡

🚧ቦታው ለብዙ ጊዜ በመናፈሻነት ሲገለግል የቆየ ቢሆንም፣ በተለይ በ1997 ዓ.ም በሼህ አሊ አላሙዲ ሙሐመድ ድጋፍ ደረጃውን የጠበቀ ዲዛይን ተዘጋጅቶለት እንዲለማ ከተደረገ በኋላ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ አገልግሎቶች ተጨምረውለት በፓርክነት/በመዝናኛ ስፍራነት እንዲያገለግል ተደርጓል፡፡

❇️ፓርኩ ለሰርግ፣ ለልደት፣ ለምረቃ፣ ለኮንሰርት፣ ለኢግዚቢሽን፣ ለባዛር ወዘተ ምቹ አስተማማኝና በቂ ስፍራዎች ያሉት ሲሆን፣ በተለይ በግቢው ውስጥ ዘመናዊና ደህንነታቸው የተጠበቁ የሕፃናት መጫዎቻዎችና ጣፋጭ የሕፃናት ምግቦች፣ የካፍቴሪያ አገልግሎቶች፣ ውብና ማራኪ የሆኑ አረንጓዴ ስፈራዎች፣ በጽሞና ዝግ ብለው በመራመድ ንጹሕ አየር የሚወሰዱበት ምቹ የመራመጃ መንገድ ወዘተ ይገኙበታል፡፡

⭐️አፍሪካ ፓርክን ለየት ከሚያደርጉት ውስጥ የመጀመሪያውን የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን የመሠረቱ የአፍሪካ መሪዎችና የአፍሪካ ህብረትን የመሠረቱ የአፍሪካ መሪዎች የተከሏቸው የመሪዎቹ ስም የተፃፉባቸው ታሪካዊ ቅርስ የሆኑ ዛፎች የሚገኙበት ስፍራ መሆኑ ነው፡፡

@etconp

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

💼 Cost-Plus vs Lump-Sum Contracts: Which One is Right for Your Next Construction Project? 🏗

🚧In the world of construction, choosing the right contract type can make all the difference between a smooth project and one riddled with surprises.

The two most commonly debated contract types are Cost-Plus and Lump-Sum—but which one fits your project best?

⭐️🔄 Cost-Plus Contract

In a cost-plus arrangement, the contractor is reimbursed for actual costs incurred (materials, labor, etc.), plus an agreed fee. This is perfect for projects with uncertain scopes or those prone to changes.

✅ Why choose Cost-Plus?

Flexibility: Ideal for evolving designs.

Transparency: Clear breakdowns of real-time costs.

Adaptability: Great for unforeseen challenges.

⚠️ Things to watch for:

Risk of cost overruns.

Less certainty for total expenses.

⭐️💵 Lump-Sum Contract

With a lump-sum contract, the price is fixed from the start—this approach is favored for projects with well-defined scopes and minimal anticipated changes.

✅ Why choose Lump-Sum?

Cost certainty: Budget is fixed, protecting against increases.

Contractor bears more risk: Reduces financial surprises for the client.

Efficiency: Well-suited for tightly scoped projects.


⚠️ Things to watch for:

Less flexibility for changes.

Can lead to disputes if unexpected conditions arise.


How do you choose?
It comes down to your project's scope, complexity, and flexibility needs. Cost-Plus offers adaptability in uncertain projects, while Lump-Sum delivers predictability when everything is mapped out.

@etconp

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

👉በአዲስ አበባ የሁለተኛ ዙር የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ስምንት ኮሪደሮች ይለማሉ

🚧ልማቱ በአጠቃላይ 132 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው

🚧ለግል ቤት ተነሺዎች 5 ቢሊየን ብር ካሳ ተዘጋጅቷል

🏷የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት፣ በአዲስ አበባ የሁለተኛ ዙር የኮሪደር ልማት ስምንት ኮሪደሮች ይለማሉ።

⏺የመጀመሪያው ኮሪደር ካሳንቺስ መስቀል አደባባይ ሜክሲኮ ቸርችል አራት ኪሎ እስጢፋኖስ ኮሪደር እና መልሶ ማልማት ኮሪደር መሆኑን ገልጸዋል።

⭐️ሁለተኛው ሳውዝጌት መገናኛ ሃያ ሁለት መስቀል አደባባይ ልማት ኮሪደር መሆኑን ጠቅሰው ሶስተኛው ከሲኤምሲ ሰሚት ጎሮ ቦሌ ቪአይፕ እና የአዲስ አፍሪካ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ኤግዚቢሽን ማዕከል ኮሪደር እንደሚለማ ተናግረዋል።

❇️አራተኛው ከሳር ቤት ካርል አደባባይ ብስራተ ገብርኤል አቦ ማዞሪያ ላፍቶ አደባባይ ፉሪ አደባባይ መሆኑን በመግለጽ አምስተኛው አንበሳ ጋራጅ ጃክሮስ ጎሮ ልማት ኮሪደር እንደሚለማ ጠቁመዋል።

❇️ስድስተኛው ኮሪደር አራት ኪሎ ሽሮ ሜዳ እንጦጦ ማሪያም እጽዋት ማዕከል ልማት ኮሪደር እንደሚለማ ገልጸዋል።

❇️ሰባተኛው ቀበና ወንዝ ዳርቻ ልማት ኮሪደር እንደሚለማ የገለጹት ከንቲባዋ ስምንተኛው እንጦጦ ፒኮክ ወንዝ ዳርቻ ልማት ኮሪደር እንደሚለማ ተናግረዋል።

📜በአጠቃላይ የሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ኮሪደሩ 2 ሺህ 817 ሄክታር እንደሚሸፍን ጠቅሰው የኮሪደሩ ርዝመት 132 ኪሎ ሜትር ይረዝማል ብለዋል።

⏺በልማቱ ለሚነሱ የግል ባለይዞታዎች 5 ቢሊየን ብር የሚደርስ ካሳ በጀት መያዙን በመግለጽ 100 ሄክታር የሚጠጋ ምትክ መሬትና የሁለት አመት የቤት ኪራይ ክፍያም እንደተዘጋጀላቸው ገልጸዋል፡፡

Via EPA

@etconp

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

👉ልዩ የምሕንድስና ጥበብ የታየበት የቻይናው ሺዚጉዋን ተንሳፋፊ ድልድይ ከፍተኛ የቱሪስት መስህብ እየሆነ ነው።

🚧በሁቤይ ግዛት በቻይና ቺንግጂያንግ ወንዝ ላይ የተሠራው የሺዚጉዋን ተንሳፋፊ ድልድይ እስከ 2.8 ቶን ክብደት ያላቸው መኪናዎችን ማስተናገድ የሚችል ነው።

🏷ከ 8 ዓመት በፊት ግንባታው የተጠናቀቀው የሺዚጉዋን ተንሳፋፊ ድልድይ ለተሽከርካሪም ሆነ ለእግረኛ ክፍት በመሆን አገልግሎት መስጠት መጀመሩንም ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል።

⏺የሺዚጉዋን ተንሳፋፊ ድልድይ "ረጅሙ የሕልም ድልድይ" በመባልም ይታወቃል።

⏺በኪንግጂያንግ ወንዝ ላይ በእግር ወይም በተሸከርካሪ ለመጓዝ ለሚፈልጉ ዜጎች እና ቱሪስቶች ድልድዩ ጥሩ ዕድል ጥሯል።

💫እ.አ.አ በ2016 የተከፈተው ይህ ድልድይ 500 ሜትር እርዝመት እና 4.5 ሜትር ስፋት አለው።

🚧የድልድዩ ስፋቱ አንድ መኪና እና ከግራና ቀኝ እግረኞችን እንዲያሳልፍ ተደርጎ የተገነባ ሲሆን በውኃ ላይ መንዳትን ለሚወዱ ቱሪስቶች መስህብ እየሆነ መምጣቱም ይነገራል።

🌟ከድልድዩ ጎን ለጎንም በሐይቁ ላይ ባሉ ጀልባዎች የትራንስፖርት አገልግሎት መሰጠቱ ለተሳፋሪው አማራጭ ከመስጠቱ ባለፈ የተለየ ውበት አጎናፅፎታልም።

⭐️ድልድዩ አሽከርካሪዎችም ሆነ እግረኞች ምንም ዓይነት ስጋት እንዳይኖርባቸው የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን የተጠቀመ ሲሆን አሽከርካሪዎች በድልድዩ ላይ የተጣለውን የፍጥነት ገደብ እንዲያከብሩ ይጠበቃል።

@etconp

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

👉Earthquake behavior of buildings

@etconp

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

How is that earthquake is a load ?

Answer for this question

It’s only one page written in Amharic and English

@etconp

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከ715 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ያስገነባቸውን የተለያዩ ፕሮጀክቶች አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ህንፃ፣ የተማሪዎች ማደሪያ ህንፃ፣ የከፍተኛ አመራሮች መኖሪያ ቤት እና የህፃናት ማቆያ ማዕከል አስመርቋል።

የተመረቀው G+6 የአስተዳዳር ህንፃ 180 ቢሮዎች ያሉትና ሁሉንም የተቋሙን የአስተዳደር ክፍሎች በአንድ ቦታ በመያዝ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ከማል አብዱራሂም (ዶ/ር) ገልፀዋል።

G+4 የሆነ የተማሪዎች ማደሪያ ህንፃ የተመረቀ ሲሆን፤ ከ1,200 በላይ ተማሪዎችን መያዝ ይችላል ተብሏል።

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ካስመረቃቸው ፕሮጀክቶች በተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ-ሙከራ እና የስፖርት ማዘውተሪያ አካዳሚ ግንባታ እያከናወነ መሆኑ ተገልጿል።

Via ኢፕድ

@etconp

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

👉የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በመጀመሪያ ዙር የ 2.5 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ማጠናቀቁን ገለፀ

🚧የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ለኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ተመራጭ በሆነችው ከተማ በመጀመሪያ ዙር ሁለት ነጥብ አምስት ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ማጠናቀቁን አስታውቋል።

⏺ከተማ አስተዳደሩ የሁለተኛ ዙር የኮሪደር ልማት ስራን በመንግስት፣ በልማት ድርጅቶች፣ በባለሀብቱና በህብተሰቡ የጋራ አቅም መጀመሩን ጠቅሷል፡፡

⏺የከተማ አስተዳደሩ የፅዱ፣ ውብና ለማህበረሰብ ምቹ ከተማ ግንባታን ለማረጋገጥ የኮሪደር ልማቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ከከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል።

@etconp

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

👉A typical building project will include the following

🚧A.Substructure

1.Excavation & Earth work
2.Concrete Work
3.Masonry Work

🚧B.Super structure

1.Concrete work
2.Roofing
3.Masonry works
4.Metal Work
5.Finishing work
6.Glazing
7.Electrical Installation
8.Carpentry & Joinery
9.Sanitary Installation
10.Fence Work

💫General factors to be considered for determining depth of foundation are:

1.Load applied from structure to the foundation
2.Bearing capacity of soil
3.Depth of water level below the ground surface
4.Types of soil and depth of layers in case of layered soil
5.Depth of adjacent foundation

@etconp

Читать полностью…

ETCONp - Ethiopian Construction Work Professionals

/channel/ETCONpWORK/2284

Читать полностью…
Subscribe to a channel