ethio360media | Unsorted

Telegram-канал ethio360media - Ethio 360 Media

37564

ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር !!!

Subscribe to a channel

Ethio 360 Media

ወጣቱ ተዋናይ  ታሪኩ ብርሃኑ/ባባ/ በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።
ታሪኩ በርካታ የአማርኛ ፊልሞችን  በመስራት ይታወቃል።ለቤተሰቡና አድናቂዎቹ መፅናናቱን ይስጥልን።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በወልንጭቲ ዙሪያ ቤቶች እየተቃጠሉ ነው!

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን በምትገኘዋ የወለንጭቲ ከተማ ዙሪያ ቤቶች እየተቃጠሉ እንደሚገኝ ነዋሪዎቹ ለአዲስ ማለዳ ገለጹ፡፡በርካታ ህዝብ ከገጠር ቀበሌዎች ተፈናቅሎ ወደ ከተማዋ መግባቱን ተናግረዋል፡፡ በከተማዋ ዙሪያ በሚገኙ ቀበሌዎች የፀጥታ ችግር ከተከሰተ አምስት ቀን ሆኖታል ያሉት ነዋሪዎቹ፣ ቤቶች በሌሊት እየተቃጠሉ ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የተከመረ የጤፍ ጭድ እየተቃጠለ እንደሆነና ከብቶችም እየተዘረፉ መሆኑን ጠቅሰው፣ ድርጊቱ ወደ ከተማው እየተጠጋ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡
ከወለንጭቲ ከተማ በቅርብ እርቀት ከፍተኛ የጥይት ተኩስ ድምጽ እንደሚሰማቸው ነው የገለጹት፡፡

ወገሬ ማርያም፣ ቡታ ደንቆሬ እና ቡታ ኩርፋ ከሚባሉ አካባቢዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ተፈናቅሎ ወደ ከተማዋ መግባቱ የተነገረ ሲሆን፣ ተፈናቃዮች ትምህርት ቤት ውስጥ ተጠልለው እንደነበር ተሰምቷል፡፡

ወደ አጎራባች የአማራ ክልል አካባቢዎች የሄዱ መኖራቸውንም አዲስ ማለዳ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በአካባቢው ከፍተኛ የደህንነት ስጋት እንዳለ በመጥቀስም በተለይ በከረዩ አካባቢ መንገድ ላይ ዘረፋና እገታ መባባሱን ተመላክቷል፡፡

ከአንድ ሳምንት በፊትም በአካባቢው በሚሰራ የመንገድ ሥራ ላይ የነበሩ ከ25 በላይ ሠራተኞች በኦነግ ሸኔ ታግተው እንደተወሰዱም ተነግሯል፡፡ ነዋሪዎቹ ቤታችንን ዘግተን ነው ወደ ከተማ የገባነው ያሉ ሲሆን፣ እስካሁን መንግሥት ምንም ባለማድረጉ ሰላምና ደህንነታችንን ሊያስጠብቅልን ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ 

Via Addis Maleda

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ምስራቅ ወለጋ በሀገር መላከያ ቁጥጥር ስር ከምትገኘው አንገር ጉትን ከተማ የሚኒሻ አስተባባሪዎች "ለደህንነታችሁ ነው" በሚል እየተያዙ ወደ ነቀምት ማረሚያ ቤት እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑ ታውቋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ዛሬም ጭፍጨፋው ቀጥሏል❗
ዛሬ ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ከማለዳው ጀምሮ ይኸው የኦሮምያ መንግስት ይሁንታ ያለው ቡድን ንፁሃን ወገኖቻችንን በደም ጎርፍ ማጠቡን ተያይዞታል።

ህዝባችንም ድምፁን ከፍ አድርጎ መከላከያው እንድዲደርስልን ድምፅ አሰሙለን በማለት እየጮሁ ነው።

ይህ ዛሬ ጠዋት የጀመረው ጭፍጨፋ ጉትን አካባቢ መከላከያው በመስፈሩ በሌላው በኩል ከተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች የተሰባሰበው አራጅ ቡድን ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ የሚገኙ የአማራ ተወላጆችን ለመጨፍጨፍ እስከዛሬው እለት በከተማው ዙሪያ መሽጎ ዛሬ ከጧቱ 12:00 ስዓት ጀምሮ ጭፍጨፋውን ቀጥሏል::
ህዳር 29/2015 ዓ.ም
==============

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የኦነግ ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ ለ #VOA አሁን የሰጠው ማብራሪያ እንዲህ ይላል፦
"የኦሮሚያ ልዩሀይል ከአራት ኪሎ ትዕዛዝ ሳይጠብቅ ከእኛ ጋር ተቀናጅቶ ርምጃ እየወሰደ ነው።አሁን የኦሮሚያ ልዩ ሀይል የአምባገነን ስልጣን መጠበቅ ትቶ ከህዝቡ ጋር ሆኖ በምዕራብ ወለጋ ሆሮ ጉድሩ መልካም ስራ ላይ ነው።እነርሱም ስራ ላይ ናቸው።እኛም ስራ ላይ ነን"

ቃል በቃል የተወሰደ ነው።
የአማራ ብሄር ተወላጅ ተብለው የቀረቡትም የሚሉት ይህንን ነው።" እየገደለን ያለው የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ከሸኔ ጋር ሆኖ ነው" በማለት ለ VOA ያስረዳሉ።
ህዳር 29/2015 ዓ.ም
==============

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ሰላሌ ፍቼ‼️
በሰላሌ ፍቼ ግጭት ተከስቷል
ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል የሚወስደው የጎጃም መስመር ፍቼ ዙሪያ ቱሉ ሚሊ የሚባል አካባቢ ከፍተኛ ተኩስ በመከፈቱ መንገዱ ተዘግቷል።
እስካሁን በደረሰን መረጃ 4 አሽከርካሪዎች ታፍነው ተወስደዋል።አጣርተው ይጓዙ።
==============

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አዲስ አበባ‼️
ተደጋጋሚ የጥይት ቶክስ ድምፅ ተስምቷል ፤ በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት አለ። አምቡላንስ እየተመላለሰ ነው።
በአዲስ አበባ ት/ቤቶች የኦሮሚያ ክልላዊ መዝሙር ዘምሩ፣ አንዘምርም በሚል ረብሻዎች ተበራክተዋል።
ከታች የምታዩት ቪድዮ በዛሬው ዕለት ኅዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም ፈረንሳይ ጉራራ አካባቢ በሚገኘው የከፍተኛ 12 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተፈጠረ ነው።
ህዳር 27/2015 ዓ.ም
================

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በስዩም ሃሳብ 1000% እስማማለሁ…!!

"…ከዚህ በኋላ የሚመጣው ዐማራ ማንንም የማይሰማ በቀለኛ ዐማራ ነው። መሞትን ለምዶ ለምዶ፣ መታረድን ለምዶ ለምዶ ቋቅ ሲለው እስቲ ደግሞ እኔም መግደልን ልሞክረው ብሎ በበቀል የሚመጣ ዐማራ ነው።

"…ዐማራን ለማብሸቅ፣ ለማናደድ ብለህ እንደ ቀልድ በፌስቡክ፣ በዩቲዩብ፣ በሚዲያ በአፍህ ስትጸዳዳበት የኖርክ፣ በሞቱ ስትሳለቅ የከረምክ የእጅህን የምታገኝበት በተራህ የምትሳቀቅበት ዘመን ነው እየመጣ ያለው። ኔቶ ያማያስቆመው በበቀል የሰከረን ዐማራን አሁን ታየዋለህ።

"…መንግሥትን ጠብቀኝ ሲለው እምቢ አልጠብቅህም የተባለ፣ ሙት ለአስከሬንህ ችግኝ እተክልሃለሁ ተብሎ በአረመኔው ዐቢይ አሕመድ የተቀለደበት ዐማራ አሁን እየመጣልህ ነው። ዘሩን ከጥፋት የሚታደግ ዐማራ ተፈጥሯል። በግሬደር የተቀበረ፣ ሜዳ ሙሉ አስከሬኑ የታረደ ዐማራ አሁን ማንንም አይሰማም። ንፍጦ ቻለው።

"…ሰልፍ ብትወጣ፣ ሠራዊት ብታሰማራ አሁን ተፈጥሮ እየመጣ ያለውን በቀለኛ ዐማራ ነፃነት፣ ፍትህ፣ እኩልነት ፈላጊ ስለሆነ እንደ ህውሓት እንደ ኦነግ ለመከበር ሲል አረመኔም ከአረመኔም በላይ ሆኖ ተፈጥሮ መጥቷል። ለሃጮ ቻለው። እንደቀልድክበት፣ እንደዘረፍከው፣ እንዳስለቀስከው አትኖርም። አሁን አንተም በተራህ ታለቅሳታለህ። የማይጠቅም ጩኸትም ትጮሃታለህ።

"…አንት እከካም የሆንክ ህፃናት ነፍሰጡር፣ አረጋዊ ገዳይ ሽንታም የሽንታም ልጅ አዎ በቀለኛ ዐማራ፣ ለኢትዮጵያ ሲል በትግሬዋ ህወሓት፣ በኦሮሞው ኦነግ ሲታረድ የኖረው ብድር መላሽ፣ ደም መላሽ እሳተ ነበልባል ዐማራ ተፈጥሮ እየመጣልህ ነው። ዐማራ ሲታረድ ቁጭ ብለህ የሳቅክ፣ ያላገጥክ ሁላ አሁን ድንኳን ጥለህ አልቅስ።
(ዘመድኩን በቀለ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የፌደራል መንግስት በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ የወለጋ አካባቢዎች በአማራ ተወላጆች ላይ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ጭፍጨፋ በአፋጣኝ እንዲያስቆም አብን ይጠይቃል፣
**
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ የወለጋ አካባቢዎች የአማራ ተወላጆች ላይ እየተፈፀመ ያለው ማንነትን መሰረት ያደረገ የዘር ጭፍጨፋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እና እየሰፋ ይገኛል:: የኦሮሚያ ክልል መንግስት በወለጋ እና ሌሎች አካባቢዎች በንፁሃን አማሮች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጭፍጨፋ፣ ማፈናቀል፣ እገታ እና ንብረት ዝርፊያ ለማስቆም ፍላጎት እና አቅም እንደሌለው በተደጋጋሚ ጊዜ ታይቷል፣ ቀላል የማይባለው የክልሉ መዋቅርም የጭፍጨፋው ተሳታፊና ሽፋን ሰጭ ሆኗል ። ጭፍጨፋው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቶ በዚህ ሳምንት እጅግ አደገኛ ወደ ሆነ ደረጃ ተሸጋግሯል። የክልሉ መንግስት ክልሉ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን ማንነት፣ ዘር እና ኃይማኖት ሳይለይ እኩል የመጠበቅ እና ከለላ የመስጠት መንግስታዊ ግዴታውን መወጣት ሳይችል ቀርቶ የአማራ ተወላጆች በተለይ የመከራ ዶፍ እየወረደባቸው ይገኛል። ስለሆነም የፌደራል መንግስት በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ያለውን የዘር ጭፍጨፋ በአስቸኳይ ጣልቃ ገብቶ ማስቆም እና ጥፋተኞች ላይ እርምጃ መውሰድ ይገባዋል ሲል አብን በጥብቅ ያሳስባል። የፌደራል መንግስት በኦሮሚያ ክልል አመራሮች ላይ ተጠያቂነትን እንዲያረጋግጥ አብን እያሳሰበ የወገኖቻችንን ሕይወት ለመታደግ ጭፍጨፋ እየተፈጸመ ባለባቸው አካባቢዎች የመከላከያ ሠራዊት በፍጥነት ማሰማራት እንዳለበት አብን ያሳስባል።

ንቅናቄው ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ ዝርዝር መረጃ በማሰባሰብ ላይ ሲሆን፣ በቅርቡም ሰፋ እና ዘርዘር ያለ መግለጫ የሚያወጣ መሆኑን እያሳወቀ፣ ችግሩ በፍጥነት እልባት እንዲያገኝ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የሚችለውን ሁሉ ማድረጉን የሚቀጥል ይሆናል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

እንዲህ ግልጥልጥ እያለ ሲመጣ ጥሩ ነው።

1) አማራዎች ተጠቅተዋል። አጥቂውን ኃይል የላከው የኦሮሚያ ክልል መንግስት ነው።

2) ንፁሃን አማራዎችን ለማጥቃት ከአማራ ክልል የመጡ ታጣቂዎች እያሉ ሲቀሰቅሱ የዋሉት ሀሰት ነው። ይህን ቅስቀሳ ኦነግ ከርሞበታል። ዛሬ ሲነዙት የዋሉት የኦነግ "ሸኔ"ን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ነው። የዚህን ፕሮፖጋንዳ ሀሰትን ራሳቸው አረጋግጠዋል። የኦሮሚያ ክልል ራሱ ያስታጠቃቸውን ነው ለማስፈታት የሞከረው እያሉን ነው።

3) የኦሮሚያ ክልል ኃይል የላከው ራሱ ያስታጠቃቸውን ሚሊሻዎችን መሳርያ ለማስፈታት ነው ብለውናል። አላማው ሌላ ነው እንጅ እውነት ቢሆን ኖሮ እንኳ፤ ልብ በሉ። የሆነው እንዲህ ነው። ወለጋ ውስጥ መንግስት ለሚሊሻ ስልጠና ሰጥቷል። ኦነግን በፀጥታ ኃይሉ መከላከል ያልቻለው መንግስት ይህን አምኖበት ነው ያደረገው። መንግስት ሲጨንቀው አማራዎችም እንደሌላው በመንግስት ሰልጥነዋል። ከሰለጠኑ በኋላ መንግስት ባሰለጠናቸው መሰረተት ራሳቸውን ከኦነግ ጨፍጫፊ ለመከላከል ጥረት አድርገዋል። እንግዲህ የእነዚህ አማራዎች ጥፋት ከተባለ ጥፋታተው ራሳቸውን ከኦነግ መከላከል ብቻ ነው።

4) የክልሉ ኃይል በአካባቢው አልነበረው። እነደረጀ እንደሚሉን የኦሮሚያ ክልል ኃይል የላከው መንግስት ያስታጠቃቸውን ሚሊሻዎች መሳርያ ለማስፈታት ነው። በአካባቢው አማራዎች ነው የሚኖሩት። የመንግስት ኃይል በሌለበት፣ ኦነግ ወለጋ ብቻ ሳይሆን ሸዋ ችግር እየፈጠረ ባለበት ኦነግን እየመከቱ ያሉ ሚሊሻዎችን መሳርያ ለማስፈታት የተሞከረው ኦነግ እንደፈለገ ንፁሃንን እንዲፈጅ ካልሆነ በስተቀር ሌላ አላማ አለው ብሎ መገመት አይቻልም።

5) እውነታው ተኩሱ ሚሊሻዎች ላይ አልነበረም። የተገደለው፣ የተፈናቀለው ያልታጠቀው ህዝብ ነው። የተጠቃው ያልታጠቀው ነው። ኢላማው ሚሊሻ አይደለም። እንዲያውም በሚያሳዝን መልኩ ሆን ብለው የህዝብ ለማድረግ ሰርተውበታል።

የሚገርመው መከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው የገባው ንፁሃንን ከኦነግ ሊከላከል አይደለም። እነደረጀ የክልሉ መንግስት ላከው ያሉት ኃይል ንፁሃንን ስላጠቃ ነው። ዛሬ የተጠቃው ህዝብ በሚከፍለው ግብር ጥይትና ስንቅ የሚገዛለት ኃይል ሲያጠቃው ነው መከላከያ ጣልቃ የገባው። ኦሮሚያ ክልል ከዚህ ደረጃ ደርሷል።

(ከስር የተያያዘው መረጃ እንዲሁ የአልፎ ሂያጅ አስተያየት አይደለም። የውስጥ አዋቂያቸው ነው።)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ወለጋ!!!
=======
ወለጋ ኦነግ ሸኔ እና በከፊል የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ዩኒፎርም የለበሱ በጋራ በመሆን አማራዉን እየጨፈጨፉት ነዉ:: መከላከያዉ ስለማያድነዉ ለአማራዉ አጋዥ ሀይል ፋኖም ቢሆን ሊገባለት ግድ ይላል::

Читать полностью…

Ethio 360 Media

"ለአማራ ህዝብ የወረደ ሰላም፣ ያለቀ ጦርነት የለም። የህወሃት ወራሪ ሀይል በ5 የተለያዩ ቦታዎች ወራሪ እያሰለጠነ እንደሆነ መረጃው አለን።" - ፋኖ ምሬ ወዳጆ
የምስራቅ አማራ ፋኖ ትጥቅ ይፍታ የሚሉ እንዳሉ በጭምጭምታ ሰምቻለሁ። መጀመሪያ ታንክ እና መድፍ የታጠቀውን የህወሃት ወራሪ ትጥቁን ያስፈቱ። የአማራ ህዝብ ከስጋት ነፃ ከሆነ እኛ ከመሳሪያ ጋር ፍቅር የለንም። ነገር ግን እየሆነ ያለው በተቃራኒው ነው። የህወሃት ወራሪ ሀይል በ5 የተለያዩ ቦታዎች ወራሪ እያሰለጠነ እንደሆነ መረጃው አለን።
እዚሁ ራያ መሆኒ አካባቢ ሳይቀር ጦር እያሰለጠነ ነው። ይሄ የሚሰለጥን ሀይል ለማንም አይደለም። አማራን ለመውረር፣ የአማራ እናቶችን ለመድፈር ነው። ይሄን እያየሁ ጦሬን የምበትን የዋህ አይደለሁም።
ወደ ግል ህይወቴ ልመለስ ብል፣ የአማራን እናቶች ክብር ለመጠበቅ በራያ ምድር የተሰው የአማራ ወጣቶች አጥንት አያስቀምጠኝም። በመሆኑም ለአማራ ያለቀ ትግል የለም። ለአማራ ህዝብ የወረደ ሰላም የለም።
የለበስነው ዩኒፎርም 9 ወር አልፎታል። ተቀያሪ የለንም። በቂ ስንቅ የለንም። የምስራቅ አማራ ፋኖ የመላው የአማራ ህዝብ ፋኖ ነው። በመሆኑም እኛ በሚዲያ እየወጣን እስክንለምን አትጠብቁ። መለመን እያሳቀቀን ነው፣በርካታ ጀግኖች ልጆቻቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ጥለው ተሰውተዋል። በርካታ ቁስለኛ አለን። የቻላችሁ አግዙን ብሏል። ህወሃት ትጥቅ ከፈታ እኛም ሰላም እናገኛለን፣ህወሃት ትጥቅ እስካልታ ድረስ እረፍት የለንም ብሏል
(ከ የአማራ ድምፅ ከተናገረው የተወሰደ)
===================

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በትግራይ ለ17 ቀናት ስልጠና የወሰዱ ታጣቂዎች በጦርነቱ የተጓደሉ ክፍለጦሮችን እና አርሚዎችን መቀላቀላቸው ታውቋል። በተለይ በመቀሌ ዙሪያ አግበት፣ደንጎላት፣ ገረብግብ እና ኩያ በሚባሉ አካባቢዎች ነው ስልጠናውን ወስደው የተቀላቀሉት። በተለይ ኩያ በሚባለው ማሰልጠኛ ቦታ የሰለጠኑት ሰልጣኞች ልዩ ሰልጣኞች ናቸው ተብሏል። ከስምምነቱ አፈፃፀም አንፃር ህወሃት በሰባት ቀናት ውስጥ ከባድ መሳሪያ እንዲያስረክብ በስምምነቱ የተፈረመ ቢሆንም የማስረከቢያ ጊዜው ዛሬ ተጠናቋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ከምዕራብ ወለጋ ከሸኔ ጥቃት ሸሽተው ወደ አዲስ አበባ ይመጡ የነበሩ ንፁሃን መታገታቸው ተሰምቷል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

እነዚህ መረጃች ህወሓት ዳግም ጦርነት ስለመቀስቀሱ ይጠቁሙ ይሆን ?

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀው ህወሓት በተለያዩ አስገዳጅ ምክንያቶች አጣብቂኝ ውስጥ በመግባቱ የሰላም ስምምነት ፊርማ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ መፈረሙ ይታወሳል፡፡ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አፈፃፀም ዝርዝር ዕቅድ ላይ በኬንያ ናይሮቢ ለቀናት የተካሄደው ውይይትም በስምምነት ፊርማ ተቋጭቷል፡፡ ኢትዮጵያ ለሰላም ስምምነቱ ተፈጻሚነት ያላትን ቁርጠኝነት በተለያየ መንገድ የገለጸች ሲሆን፤ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴም ገብታለች፡፡

አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ግን ህወሓት በአደባባይ ለሰላም ስምምነቱ ተገዢ መሆኑን እየገለጸ ሲለው በህቡዕ ሲያሰኘው ደግሞ በግልጽ ከሰላም ስምምነቱ ተቃራኒ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ይገኛል፡፡

ህወሓት ከሚቆጣጠራቸው የትግራይ አካባቢዎች የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የቡድኑ ታጣቂዎች በሚንቀሳቀሱበት የኮረም ግንባር በሰሰላ ስምረት፣ ሰላም በቃልስ፣ ደንቃ እና አድሺን ቀበሌዎች በርካታ የአካባቢው ወጣቶች በግዳጅ ታፍሰው ለውትድርና ስልጠና ወደ ማይጨው አቅጣጫ ተወስደዋል።
ህወሓት በተለያዩ አካባቢዎች ኃይል የማደራጀት እና ምልመላ የማካሄድ እንዲሁም ከማኅበረሰቡ በማስገደድ ቀለብ የመውሰድ እንቅስቃሴውን የቀጠለ ሲሆን፤ በማይጨው፣ በመሆኒ እና በመቀሌ ዙሪያ የወጣቶች አፈሳ እያካሄደ ይገኛል፡፡ የታፈሱት ወጣቶችም ወደ ገረብ ግባ ማሰልጠኛ እየተወሰዱ እንደሆነ ታውቋል፡፡



ህወሓትን በተመለከተበጥንቃቄ መፈተሽና መታየት እንዳለበት ይመክራሉ፡፡ ህወሓት በሰላም ስምምነቱ መሰረት ትጥቅ እንደሚፈታ መስማማቱ ለይምሰል ሊሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬያቸውንም ይገልጻሉ፡፡ እኛም ከላይ የተጠቀሱት መረጃች ህወሓት ዳግም ጦርነት ስለመቀስቀሱ ይጠቁሙ ይሆን ? እንላለን፡፡

ሱሌማን አብደላ

Читать полностью…

Ethio 360 Media

#UPDATE ከሰሞኑ በወለጋ እየተፈፀመ ባለው ግድያ፣ መፈናቀል እና ስደት ዙርያ ትናንት ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ መረጃ ሰጥተው ሲወጡ የነበሩ ቁጥራቸው ከ22 የሚበልጥ ሰዎች በፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የአይን እማኞች አሳውቀውናል።

ከታሳሪዎቹ መሀል አንዳንዶቹ አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ (ጎማ ቁጠባ አካባቢ)፣ ሌሎቹ ደግሞ የት እንደተወሰዱ እንደማይታወቅ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ጠቃሚ መረጃ‼️
የሽንትዎ ቀለም ስለሰውነትዎ ጤና ምን ይነግርዎታል❓
ሽንት ኩላሊት ደምን አጣርቶ የሚያስወጣው ፈሳሽ ሲሆን 95% ውሀ 5% ኤሌክትሮላይቶች እና ቆሻሻዎች ናቸው። ጤናማ እና በቂ ፈሳሽ በሚዎስዱበት ጊዜ ሽንትዎ ብዙ የጎላ ቀለም በሌለው እና ነጣ ያለ ቢጫ ቀለም መካከል ነው::

በቂ ፈሳሽን በማይወስዱበት ጊዜ ሽንትዎ ይበልጥ የተከማቸ ሲሆን ወደ ጠቆር ያለ ቢጫ ወይም የዓምበር ቀለም ይለወጣል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የሽንት ቀለም እና መጠን እየዎሰዱ ያሉትን የውሀ መጠን ፣ ምግብ ፣ ቫይታሚን ጠቋሚ ነው። የተወሰኑ ምግቦች ፣ አንቲባዮቲኮች ፣ የህክምና ሁኔታዎች እና ቀለሞች እንዲሁ ለጊዜው የሽንት ቀለም ይቀይራሉ፡፡

ከዚህ ቀጥሎ የተለያዩ የሽንት ቀለም አይነቶች እና ምክንያቶች እናያለን።

1. በጣም_ነጭ ከሆነ ከመጠን በላይ ውሀ እየጠጡ እንደሆነ ያመለክታል። ይህም የተለያዩ በደም ውስጥ የሚገኙ ንጥረ ነገሮችን በተለይም ፓታሽየም እና ሶድየም መጠናቸው እንዲያንስ ያደርጋል ይህም የልብ ጡንቻን ይጎዳል።

2. ጥቁር_ቢጫ - ይህም በቂ ውሀ እየወሰዱ እንዳልሆነ ወይም ኬቶን በሽንት ውስጥ መኖር ሊሆን ይችላል። በቂ ውሀ አለመውሰድ ደግሞ ለኩላሊት ጠጠር ፣ የሰውነት ፈሳሽ መቀነስ ፣ የኤሌክትሮላይት መዛባት ያስከትላል። ኬቶን የሚፈጠረው ሰዉነታችን በቂ የሆነ ስኳር (glucose ) ሳያገኝ ሲቀር እና ቅባትን (fat) የሰውነት ሴሎች ለጉልበት ማመንጫነት ሲጠቀሙበት ነው። ይህም በሽንት መልክ ይወጣል። ከፍተኛ የኬቶን መጠን አደገኛ የስኳር በሽታ ጉዳትን (DKA) ተከትሎ ሊመጣ ይችላል። አነስተኛ መጠን ከሆነ ለረጅም ጊዜ ካልተመገብን ሊከሰት ይችላል።

3. ደማቅ_ቢጫ - ከበቂ በላይ ሰው ሰራሽ ቫይተሚን ቢ እየወሰዱ ከሆነ ሊከሰት ይችላል።

4. ቀይ - ይህ የሚፈጠረው ደም በሽንት ውስጥ ሲኖር ነው። ይህም በኩላሊት ጠጠር ፣ የኩላሊት እና የሽንት ፊኛ ኢንፌክሽን ፣ የፕሮስቴት እጢ ካንሰር ፣ የኩላሊት ካንሰር ፣ ከባድ ስፓርት እና የመሳሰሉት።

5. ጥቁር_ብርቱካናማ/ቡናማ - የጉበት ችግር ያመለክታል። የጉበት ፣ የሀሞት ቀረጢትና የቱቦዎች ችግር ተከትሎ የቢሊሩቢን በደም ውስጥ መብዛት ጋር ተያይዞ የሚከሰት ነው።

6. ሀምራዊ - አነስተኛ ደም በሽንት ውስጥ ሲኖር ወይም ቀይ ስር ከበላን

7. ሰማያዊ - የካልስየም መብዛት /hypercalcemia

8. አረፋ_ካለ - ፕሮቲን በሽንት ውስጥ መኖር ፤ ይህም የኩላሊት ቁስለት ፣ የኩላሊት ጠጠር ፣ የልብ እና የኩላሊት መድከም ፣ የተለያዩ የካንሰር አይነቶች

9. ብዙ_የሚሸኑ_ከሆነ - በሽንት ውስጥ የስኳር መኖር ምልክት ሊሆን ይችላል ፤ ይህም የስኳር በሽታ ያመለክታል።
ከወደዱት ለሌሎች ያጋሩ❗

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የብልጽግና ባለሥልጣናት በወለጋ በአማራ ላይ የሚፈጽሙትንና የሚያስፈጽሙትን የዘር ፍጅት በ«ጽንፈኛ ፋኖ» ተረክ መሸፋፈን አይቻላቸውም። ይዘገይ ካልሆነ በስተቀር ከወንጀል ተጠያቂነትም አያመልጡም።

(ባለፉት ዓመታት ወለጋ በፌዴራል መንግስት ኮማንድ ፖስት ስር ያለ መሆኑን ሁሉም በቁምነገር እንዲመዘግበው ማስታዎስ እፈልጋለሁ።)
ክርስቲያን ታደለ

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አዳነች በሀዋሳ ከሰጡት መግለጫ❗❗
-የኦሮሞ ባህል በሌሎች ላይ እየተጫነ አይደለም።
-የአዲስ አበባ ህዝብ ልጆቹን ይምከር(የኦሮሞ ባንዲራ ሲሰቀል አይረብሹ)።
-የሸኔ፣የፅንፈኛው ፋኖ እና የምዕራባውያን እጅ ያለበት አጀንዳ ነው የሚል በመግለጨዋ ተናግራለች።
አነዚህ ሰዎች ወደ እልቂት እንዳይወስዱን ያስፈራል፣ሁሉም ነገር በውይይት ካልሆነ መጨረሻው አያምርም።
ህዝብ አድምጡ። ህዝብን ማድመጥ ይቅደም፣በባንዲራ የተነሳ የትምህርት ቤት መስተዋት መሰበር የለበትም። ቆም ብሎ ማሰብ ተገቢ ነው።
ህዳር 29/2015 ዓ.ም
==============

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በኦሮሚያ ክልል"ግጭቶችና ጥቃቶች"የሚከሰቱባቸው ቦታዎች መጨመራቸውን ኢሰመኮ ገለጸ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዛሬ ባወጣው ሪፖርት በኦሮሚያ ክልል ከዚህ ቀደም ጥቃትና ግጭት የተከሰተባቸውን እና እየተከሰተባየው ያሉ 36 ወረዳዎች መመዝገቡን ገልጿል።

ኢሰመኮ ከሐምሌ ወር 2014 ዓ.ም እስከ ኅዳር ወር 2015 ዓ.ም ድረስ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ ግጭቶችና ጥቃቶች መቀጠላቸውን በሪፖርቱ አስታውቋል።
ኢሰመኮ “በአካል ተገኝቶ ምርመራ ለማካሄድ ባልቻለባቸው አካባቢዎች ደግሞ ተጎጂዎችን፣ የተጎጂ ቤተሰቦችን፣ ከእነዚህ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ነዋሪዎችን፣ የዐይን እማኞችንና የመንግሥት ኃላፊዎችን ጨምሮ የተለያዩ ምንጮችን በማነጋገር የቃል እና የጽሑፍ መረጃና ማስረጃዎችን” እንደሰበሰበ አስታውቋል።

በኦሮሚያ ክልል እስካሁን 13 ዞኖች ውስጥ ባሉ 36 ወረዳዎች ላይ ግጭቶች ተከስተው በሰውና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል ብሏል ኢሰመኮ፡፡

በተለይም በሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ በምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ በሰሜን ሸዋ፣ በቄለም ወለጋ ዞን፣ ኢሉ አባቦራ ዞን፣ በቡኖ በደሌ ዞን፣ በምሥራቅ ሸዋ፣ በምዕራብ ሸዋ፣ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ በአርሲ ዞን እና በሁለቱ የጉጂ ዞኖች ውስጥ ግጭቶች ተከስተዋል ብሏል፡፡

ኢሰመኮ ግጭት ከተከሰተባቸው ወረዳዎች መካከልም በኪረሙ፣ ጊዳ አያና፣ አልጌ፣ ሁሩሙ፣ በአሙሩ፣ ሆሮ ቡሉቅ፣ ጃርደጋ ጃርቴ፣ ቦሰት፣ ግንደበረት፣ ጮቢ፣ ደራ፣ ኩዩ፣ መርቲ ጀጁ እና የአርሲ ዞን አጎራባች ወረዳዎችን የሚደርሱ ግጭቶችና ጥቃቶችን በመከታተል ላይ እንደሚገኝ ጠቅሷል፡፡

ኢሰመኮ ግጭቶቹና ጥቃቶቹ የሚከሰቱባቸው አካባቢዎች ስፋት ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመሩን እና የሚያስከትሉት የሰብአዊ መብቶች ቀውስ ደረጃ አስከፊነት ነው ብሏል፡፡
በእነዚህ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ቡድኖች በአይነታቸውና በቁጥራቸው የመጨመር ወይም የመወሳሰብ አዝማምያ ማሳየታቸውም ኢሰመኮ በሪፖርቱ አስታውቋል።

በተለያዩ ወቅቶች የተለያዩ ቡድኖች ሙሉ ቀበሌዎችን ወይም ወረዳዎችን ጭምር ተቆጣጥረው የቆዩ መሆናቸው የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶቹን አባብሶታልም ብሏል ኢሰመኮ።

እንዲሁም መንግስት ተመጣጣኝና የተጎዱ ሰዎችን ብዛትና አካባቢዎችንም የሚመጥን ምርመራ ማድረግ እንዳልቻለ አስታውቋል።

ኢሰመኮ ባወጣው ሪፖርት የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች፣ ራሳቸውን ለመከላከል የታጠቁ የአካባው ኃይሎች፣ በአካባቢው በተለምዶ የአማራ ታጣቂዎች ናቸው የሚባሉት እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊ( ሸኔ) እንደሚንቀሳቀሱ ገልጿል።

ኢሰመኮ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እና ታጣቂ ቡድኖቹ እርስበእርሳቸው በሚያደርጉት ውጊና እና በሌላ ወቅት በጠናጠል በሚያደርሱት ጥቃት በርካታ ንጹሃን ለሞት፣ ለመፈናቀል እና ለንብረት ውድመት ተዳርገዋል ብሏል፡፡

ከሰሞኑ በምስራቅ ወለጋ በተለያዩ አካባዎች በተፈጸመ ጥቃት በርካታ ሰዎች ሲገደሉ፣ በርካቶች መገናቀላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የአለም ሚዲያዎች ከጫፍ ጫፍ በወለጋ የአማራን ጭፍጨፋ እንዲህ እየዘገቡ ባለበት ሁኔታ የሀገር ዉስጥ የመንግስት እና የግል ሚዲያዎች ስለ መኪና ማቆሚያ ፓርኪንግ ምርቃት ነዉ የሚያወሩት ስለ አለም ዋንጫ ነዉ የሚዘግቡት:: ያሳዝናል!

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ወለጋ❗❗
ምን አይነት ስቃይ ነው፣ይሄ ጭካኔ በምን ይገለፃል❗😥
================

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የስዩምን ሀሳብ እንዴት አያችሁት?? መቶ ፐርሰንት የሚያስማማ ሀሳብ ነዉ!!

Читать полностью…

Ethio 360 Media

Inbox

<<....አንገር ጉትን ንፁሃን እየደረሰባቸው ያለውን ሰቆቃ ለመግለፅ ትናንት ከተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች ወደ ሰብአዊ መብት ተሟጋች ቢሮ የሄዱ ወንድሞች በፖሊስ ተይዘው ልደታ ተስረዋል።… ጥፋትም ጥቃትም በዛ…>>

Читать полностью…

Ethio 360 Media

መንግስት የሰው ደም ካልፈሰሰ፣የንፁሃን ሀብት ንብረታቸው ወድሞ ካልተፈናቀሉ በአጥፊ ላይ እርምጃ የማይወሰድበት ምክንያት ለገዳይ ከመተባበር ተለይቶ የሚታይ አይመስለንም።

ለምሳሌ ምስራቅ ወለጋ አንገር ጉትን ከተማ ከነቀምት ያለው ርቀት 2:30—3:00 ሰዓት ይፈጃል።መከላከያ ሠራዊቱ በዚህ ቦታ ላይ እያለ አንገር ጉትን ለ24 ሰዓታት ዜጎች ሲገደሉ ዝም ተብሎ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ነው የተላከው።አሁንም ዙሪያውን አልቆመም።መንግስት የዜጎቹን ደህንነት ካላስጠበቀ ገዥነቱ ጥያቄ ውስጥ ነው።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ህወሃት የተበላሹ ከባድ መሳሪያዎችን ለማስረከብ በአንፃሩ ደግሞ የሚሰሩትን በአንዳንድ ቦታዎች እየቀበረ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል። ከዚህ በተጨማሪ ትጥቅ የሚፈቱ እና የማይፈቱ ብሎ የለያቸው ታጣቂዎች እንዳሉም ከሰሞኑ ባደረጋቸው ህዝባዊ ስብሰባዎች የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

================

Читать полностью…

Ethio 360 Media

#ኳታር‼️
አሜሪካዊው ጋዜጠኛ፡- "በለበስኩት ቲሸርት ምክንያት የአሜሪካን ጨዋታ ለማየት ወደ ስታዲየም እንዳልገባ ተከልክያለሁ የሀገሬን ጨዋታ መመልከት ከፈለክ ቲሸርትህን ቀይር ተባልኩ።"
ቲሸርቱ የግብረሰዶማውያን አርማ ያለበት ነው።
====================

Читать полностью…

Ethio 360 Media

<<…በትግራይ የታጠቁ ሀይሎች መዘናጋት የለባቸውም።ራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው…>>

አቶ ጌታቸው ረዳ
በትግርኛ ከሰጠው መግለጫ የተወሰደ

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ወለጋ ሆሮ ጉዱሩ ጃርቴ ጃርደጋ በንፁሃን ንብረት ላይ የተፈፀመ ጥቃት ነው።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ሆሮ ጉዱሩ

የሸኔ ታጣቂዎች ከ30 በላይ ሰዎችን ገደሉ

ከሳምንት በፊት በአንድ ቀበሌ ውስጥ በሸኔ ስም ከሚንቀሳቀሱ ሀይሎች ጋር ተኩስ ነበር፡፡

ከተወሰነ ቀናት በኃላ ደግሞ አሊቦ ከተማ እና አካባቢው ላይ የነበሩ የመንግስት ሀይሎች ወደ ዞን እንሄዳለን ብለው ጥለው ሲወጡ በፋኖ ስም የሚንቀሳቃሱ ከእዛው የተደራጁና ከሌላ ቦታ የመጡ ሐይሎች ወደ ከተማ መጥተው ጉዳት አድርሰዋል፡፡

በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ጃርዳጋ ጃርተ ወረዳ እና በምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ ውስጥ ታጣቂዎች ከ30 በላይ ሰዎችን መግደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ 

በሆሮ ጉዱሩ ዞን ጃርዳጋ ጃርተ ከባለፈው ማክሰኞ ጀምሮ ከሌላ አካባቢ መጡ በተባሉ ሀይሎች በተከታታይ ለሶስት ቀናት በደረሰው ጥቃት በአንድ ሰፈር የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉን ወደ ሻምቡ የሸሹ ነዋሪ ለDWተናግረዋል፡፡

Читать полностью…
Subscribe to a channel