የመከላከያ ሰራዊት ትናንት ትጥቅ ያስረከቡ የህወሓት ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ መግባታቸውን እና ከባድ መሳሪያዎችን መረከቡን ገልጿል።
(ህወሀት ለመከላከያ"አሮጌ እና 100 የማይሞላ መሳሪያ ያስረከቡ ቢሆንም ለፕሮፖጋንዳ ለመጠቀም እንዲመቸዉ ትጥቅ አስፈትቻለሁ ለማለት ነዉ")
እዉነታዉ❗
ነገር ግን በደደቢት እና በጠለምት አከባቢ በኮለኔል አፈራ እና በጄኔራል አይነኩሉ የሚመሩ ታጣቂዎች ወልቃይት ሳይመለስ ይሄን አንቀበልም እንዳሉ ተሰምቷል።
ጊዚያዊ አስተዳደሩ (ጌታቸዉ ረዳ) በበኩሉ #ወልቃይትን የፌደራል መንግሥቱ በቅርቡ ያስረክበናል::
ትጥቅ አስረክባችሁ ወደ ተሃድሶ ግቡ የሚል ምላሽ እንደሰጣቸው ተሰምቷል።
" የእምነት ተቋማትን በዚህ ልክ የተዳፈር መንግስት የለም !"‼
በኩዌት የኢትዮጵያ አምባሳደር ኡስታዝ ሐሰን ታጁ መልዕክት!..,,,,,,,,,,,,,
"በአዲሱ የሸገር ከተማ በመንግስት የፈረሱና እየፈረሱ የሚገኙ በርካታ መስጊዶችን ጉዳይ በተመለከተ በዛሬዉ ዕለት በተለያዩ መስጊዶች ድምጻቸዉን ባሰሙ ሙስሊሞች ላይ በተወሰደዉ የሀይል እርምጃ በደረሰዉ የሞትና የመቁሰል አደጋ የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽኩ ለሞቱት ጀነትን፣ ለቆሰሉት ፈዉስን፣ ለቤተሰቦቻቸዉም መጽናናትን እመኛለሁ፡፡
የተከበሩና የተቀደሱ ቤተዕምነቶችን ቅጽር ጥሶ መግባትና የዕምነት ተቋማትን በዚህ ልክ መዳፈር ከዘመነ-ኢህአዴግ በስተቀር በየትኛዉም የሀገራችን የመንግስት ሥርዓት ታሪክ ተፈጽሞ የማያዉቅ ሲሆን፣ ዉጤቱም ለማንም የማይበጅና በዉስብስብ ፈተናዎች ዉስጥ እያለፈች ባለችዉ ሀገራችን ላይ ተጨማሪ የመከራ ሸክም መጫን በመሆኑ የሚመለከተዉ አካል ነገሩን ቆም ብሎ ሊያጤነዉ ይገባል፡፡
አላህ ሀገራችንን ሠላም ያድርግልን!!!"
። ©ኡስታዝ ሀሰን ታጁ
=====================
የቀሲስ አክሊል ዳምጠው ክስ ጉዳይ...!
ቀሲስ አክሊል ዳምጠው ከወራት በፊት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ተፈጥረው የነበሩ ወቅታዊ ችግሮችን ለመፍታት በጠቅላይ ቤተክህነት ፅ/ቤት የተቋቋመ አቢይ ኮሚቴን በሰብሳቢነት እንዲመሩ የተመረጡ እጅግ የተከበሩ አባት ናቸው። ከሰኞ ግንቦት 14 ጀምሮ በቁጥጥር ስር ውለው ይገኛሉ።
ቀሲስ አክሊል ዳምጠው ተጠርጥረው የተያዙበትን የወንጀል ክስ የያዘ ወረቀት ተመለከትኩ፣ እንዲህ ይላል:
- የራሱን የፖለቲካ አላማ በማራመድ ህዝብ በመንግስት ላይ እምነት እንዳይኖረው በማድረግ
- ህገ-መንግስቱን እና ህገ-መንግስታዊ ስርአቱን በሀይል ለመቀየር
- ህዝብን አሳምፆ መንገድ እንዲዘጋ በማድረግ
- የስራ ማቆም አድማ በመቀስቀስ
- በተቀናጀ መልኩ የፖለቲካ ቅስቀሳ በማድረግ
- ተከታታይ እና ቀጣይነት ያለው አመፅ በማድረግ እና
- ለሁከት እና ብጥብጥ ድርጊት ማስፈፀሚያ የሚሆን በውጭ ሀገር እና በሀገር ውስጥ ገቢ እንዲሰባሰብ በማድረግ
- ህዝብ ለአመፅ እንዲነሳሳ በማድረግ
- ፅንፈኝነትን በማስተጋባት
- የፖለቲካ ተከታዮችን መመልመል እና ማደራጀት
- (ይቺ ታስቃለች...) ወታደራዊ ስልጠና እንዲሰለጥኑ በማድረግ
- የጦር መሳርያ በማስታጠቅ
- የታጠቁ ፅንፈኛ ሀይሎችን በተለያዩ መንገድ በመገናኘት ተልዕኮ መስጠት
- ወደ አዲስ አበባ ከተማ እና ሌሎች ቦታዎች ሁከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር መንቀሳቀስ።
በፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ላይ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 14 ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አስታወቀ‼️
በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በሚገኘው ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ላይ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት፤ 11 የፋብሪካው ሰራተኞች እና ሶስት የአካባቢው ነዋሪዎች እንደተገደሉ ማረጋገጡን የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስታወቀ። ፋብሪካው በተፈጸመበት በዚሁ ጥቃት እና ዘረፋ ምክንያት ስራ ማቋሙም ተገልጿል።
ከአዲስ አበባ በ350 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ላይ ጥቃቱ የተፈጸመው ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ግንቦት 12፤ 2015 መሆኑን የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የህዝብ ግንኙነት እና ተሳትፎ ክፍል ኃላፊ አቶ ረታ ደመቀ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። ፋብሪካው ባለፈው 2014 ዓ.ም እና በዚህ ዓመት ተመሳሳይ ጥቃቶችን ቢያስተናግድም፤ የአሁኑ ከዚህ ቀደም ከነበሩት “ከበድ ያለ” እንደሆነ ተነግሯል።
የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ እና በስሩ ያለው የሸንኮራ አገዳ እርሻ፤ በአጠቃላይ በ67 ሺህ ሄክታር ይዞታ ላይ ያረፈ ነው። የቀደሙት ጥቃቶች ይበልጥኑ ኢላማ የሚያደርጉት የፋብሪካው እርሻ ላይ እንደነበር የሚናገሩት አቶ ረታ፤ ታጣቂዎቹ “የአገዳ እና የእርሻ ማሽነሪዎችን የማቃጠል” ድርጊት ይፈጽሙ እንደነበር ያስታውሳሉ። የአሁኑ ከዚህ ቀደም ከነበሩት የሚለየው ታጣቂዎቹ ጥቃቶቹን የፈጸሙት ወደ ፋብሪካ ጭምር ገብተው መሆኑን ያስረዳሉ።
ዘገባው የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ነው
ተቃውሞ በአንዋር መስጊድ‼
አንዋር መስጊድ አዲስ አበባ በተቃውሞ ላይ የነበሩ ሙስሊሞችን ለመበተን የጥይት ተኩስ በመተኮሱ ከፍተኛ ግርግር ተፈጥሯል።
ሸዋሮቢት❗
ትናንት በሸዋሮቢት ከተማ የመከላከያ ጄኔራሎች የአካባቢውን ሽማግሌዎች ሰብስበው ነበር።
በዚህ ስብሰባ ላይ ጄኔራል አበባው ለሽማግሌዎቹ ልጆቻችሁን ሰብስቡ፣ምከሩ፣የቡድን መሳሪያ ያስረከቡ ካልሆነ ግን እርምጃ ለመውሰድ እንገደዳለን፣ በዚህ ቅር እንዳይላችሁ ማለቱ ተሰምቷል።
ሽማግሌዎቹ በበኩላቸው አካባቢው አሁንም ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት ያለበት ነው፣በጦርነቱ ወቅት ማርከህ ታጠቅ ያላችሁትን አሁን መሳሪያ አስረከቡ መባሉ ለመንግሥት ክህደት አይሆንበትም" የሚሉ ጥያቄዎችን ሽማግሌዎቹ አንስተዋል።
በሰሜን ሸዋ ዞን በሸዋሮቢት ከተማ ህግ ለማስከበር በሚል የገባዉ መከላከያ ህብረተሰቡን እየዘረፈ ይገኛል❗
በሰሜን ሸዋ ዞን በሸዋሮቢት ከተማ ከፍተኛ ቅሬታ እየተነሳ ነው።
ሰሞኑን ህግ ለማስከበር በሚል ወደ ከተማ የገባው የፀጥታ ሀይል የከተማው አስተዳደር ላይ ከፍተኛ ጫና እየመጣበት እንደሆነ ተገልጿል።
የፀጥታ ሀይሎቹ ወጪያችንን የከተማ አስተዳደሩ ነው የሚከፍለው በማለት ሆቴሎች እየገቡ በነፃ በልተው እየወጡ ነው፣ የመሳሪያ አሰሳም ተደርጎ ፍቃድ ያላቸው መሳሪዎችን ጭምር እየተወሰዱ ነው ህብረተሰቡ ይናገራል።
ይገርማል በ ኳስ ሰበብ ፖለቲካ‼
የአማራን አንድነት የሚከፋፍልና ምንም አይነት ሕዝባዊ ግብ የሌለው ጥቃት ከተፈጸመ ጥቃቱን ማን እንዳሰናደው ለማወቅ አምስት ሰከንድ ማሰብ በቂዬ ነው። "መላው አማራን ለማጥፋት የጎንደር እና የጎጃም አማራን ማባላት" የሚል ፕሮጀክት ተነድፎ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ ቆየ እኮ።
(አሳዬ ደርቤ)
"የብልጽግና አጃቢ ሆኖ አገር ማፍረስ ሰለቸን" በሚል አቋም ከኢዜማ አባልነት እራሳቸውን ያገለሉ...
1.አቶ የሽዋስ አሰፋ
2.አቶ ሀብታሙ ኪታባ
3.አቶ ተክሌ በቀለ
4.አቶ ዳንኤል ሺበሺ
5.አቶ ኑሪ ሙደሲር
6. አቶ የጁአልጋው ጀመረ
7. ወ/ሮ ናንሲ ውድነህ
"አልፎ አልፎ ሽፍታ ወይም ሌባ ሊኖር ይችላል እንጂ ጥቃት የሚባል ነገር የለም፣ ሁሉም አካባቢ ሰላም ነው።"
ይህን ያሉት የኦሮሚያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ሲሆኑ በሪፖርተር ጋዜጣ ስለ ሰሞንኛው የበቆጂ፣ ቢሾፍቱ እና ወለንጪቲ ጥቃቶች ተጠይቀው የመለሱት ነው።
እውነታውስ?
በእነዚህ ከተሞች ካሉ ነዋሪዎች ሲደርሱኝ የነበሩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በተለይ በምሽት ወቅት "በታጠቁ" ሀይሎች በተፈፀሙ ጥቃቶች በርካታ የፀጥታ አካላት እና ንፁሀን ዜጎች ተገድለዋል፣ እስር ቤቶች ተሰብረው ታሳሪዎች ተፈተዋል፣ በርካታ የነዚህ ከተሞች ነዋሪዎች የጥይት እና የከባድ መሳርያ ድምፅ እየሰሙ የጭንቅ ቀናቶችን እና ምሽቶችን አሳልፈዋል።
እውነታው ይሄ ነው።
Via Tikvah/Reporter
ትግራይ ክልል እነ ጌቾ አማርኛ ቋንቋን አናስተምርም በማለት ከስርዓተ ትምህርታቸው ሲያስወጡት የፑቲን ሞስኮ እኔ ልጀምር ነው ብላለች።
👇
በሩሲያ የሞስኮ ትምህርት ቤቶች ከመስከረም ጀምሮ አማርኛ ቋንቋን ማስተማር ሊጀምሩ መሆኑ ተገለጸ፡፡
እንደ ኤፍቢሲ ዘገባ የእስያ እና አፍሪካ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አሌክሲ ማስሎቭ ከፈረንጆቹ መስከረም 2023 ጀምሮ ቢያንስ አራት የሞስኮ ትምህርት ቤቶች ለህጻናት የአማርኛ እና የስዋሂሊ ቋንቋ ማስተማር እንደሚጀምሩ ይፋ አድርገዋል።
ወደ አፍሪካ በፍጥነት ፊትን ለማዞር ከኢኮኖሚው ጋር በቀጥታ ሊሰሩ የሚችሉ ባለሙያዎችን ማፍራት ያስፈልጋል ሲሉም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
አፍሪካ አንድ ትልቅ አህጉር ብቻ ሳትሆን የተለያዩ ቋንቋ፣ ባህል፣ ሃይማኖት እና ህብረ ብሔራዊ ማንነቶች ያሉባት አህጉር መሆኗን መገንዘብ ይገባል ብለዋል፡፡
ትግራይ ያሉት የአሜሪካን ባንዴራ እና የእርዳታ ድርጅት ባንዴራ በመያዝ በክራንች " ሀይ ሎጋ! እያሉ በሚመስል የተሰለፉ ሲሆን በተመሳሳይ ከማይካድራ አማራን ጨፍጭፎ ወደ ሱዳን የገባው የህውሃት የሳምሪ ቡድን ክንፍ በሱዳን ተጠልሎበት የነበረውን ካምፕ በእሳት አጋይተውታል። ምን አልባት ይህ ቡድን መጠለያውን ያቃጠለው የመጨረሻ እድል ወደ ወልቃይት ሰርጎ በመግባት ጥቃት ሊሞክር ይችላል። አለያም መጠለያው ስለተቃጠለ ወደ ኢትዮጵያ አስገቡን ብሎ ለፌደራል መንግስቱ አቤቱታ ሊያቀርብ ወይም ተመቻችቶለት ሊሆን ይችላል።
Читать полностью…ሰሞኑን በወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት አካባቢዎች ሰላማዊ ሰልፍ ሊደረግ መሆኑን ምንጮች ገለፁ‼
የሰልፉ አላማ የማንነት ጥያቂያችን በአስቸኳይ ምላሽ ይሰጠው፣የሁለት አመት በጀት ይለቀቅ፣በጠለምት እና በወልቃይት ግፍ እና በደል የፈፀሙ የቀድሞ የህወሓት አመራሮች ለፍርድ ይቀረቡ የሚል ነው ተብሏል።
'በአንድ ልብ፤ በአንድ ሃሳብ የተወሰነ ነው !'
(ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ፥ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ)
'ሁላችንም ተወያይተንበት፣ 'ቤተክርስቲያንን የሚጠቅማት ምንድነው?' ብለን በአንድ ልብ በአንድ ሃሳብ የወሰንነው ነው። በእውነት ደስ የሚል ነበር፤ ለዚህም እግዚአብሔርን እናመሰግናለን።
ብዘዎች የተጨነቃችሁ ምዕመናን እንደነበራችሁ እናውቃለን፤ አንዳንዴ እውነት ነው፤
(ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ(ዶ/ር)፥ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ)
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት አስቸኳይ ጉባዔውን በዑማ ሆቴል እያካሄደ ነው።
በጉባኤው ላይ የተንሱ ሃሳቦች...
❝መስጂድ ማለት ቤታችን ነው። እየተማፀንን ኧረ እባካችሁ እንማከር እያልን ...❞
በዛሬው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመጅሊሱ ፕሬዝዳንት ሼይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ እነዚህን ሀሳቦች አንስተዋል
❝ሰላም ስላልፈለጉ ሙስሊሙን በመናቅ የሙስሊሙን ብቸኛ መሪ በመናቅ በማናለብኝነት ሄዶ መስጂዶችን አፍርሶ ወደ ሀገር ማፍረስ እየተዘጋጁ እንደሆነ ይታያል።❞
❝ሙስሊም ሰላም እና ሰላም ነው። ሰላም ወዳድ ብቻ ሳይሆን የሰላም ዘብ ነው።❞
❝የሰላም ዘብ ስንል ደግሞ ሲነኩትም አይናካም ሲነኩት አይሰማም ብሎ አልፎ መስጂዳችንን ለማፍረስ እንዲህ በተሟላ ድፍረት በፍፁም! አይሳካለትም ታግሰናልና ታግሰናል። ይህንን ስል በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ በአ.አ ዙሪያ ያሉት በሸገር ከተማ የፈረሰ መስጂዳችን ቁጥሩ እያደገ መጥቶ ይሄን ያህል ዛሬ መድረሱ ነገ ይተዋሉ ዛሬ ይተዋሉ እንነጋገራለን እንመካከራለን ሰላምን እንመርጣለን በሰላም እንሄዳለን ከሚል አንፃር እንጂ ፍራቻ እንዳልሆነ ሊያውቁ ይገባል።❞
❝ያለኛ ፍቃድ አንድም መስጂዳችን ሊፈርስ አይችልም። እኛ እንፈርሳለን እንጂ መስጃዳችን ሊፈርስ አይችልም።❞ ❝የፈረሱ መስጂዶቻችን ይተካሉ።❞
❝ህይወታቸው ለህልፈት የበቁ ልጆቻችን አላህ በጀነት ይቀበላቸው። የቆሰሉትን አላህ ያሽራቸው። ቤተሰቦቻቸው ሰብር አላህ ይስጣቸው።❞
❝ህግን እናከብራለን። ህግ እና ህግን ተመርኩዘን መብታችን እናስከብራለን።❞
❝ማን ሆነ ማንም ሊንቀን አንፈቅድለትም ከፈለገ እራሱን መናቅ መብቱ ነው።❞
❝ይሄን የመጣብንን ፈተና ለመመከት ለመመለስ እኛ ሙስሊሞች በትዕግስት በሰከነ መንፈስ በመነጋገር በመደማመጥ በመከባበር ስንሄድ እና ስንሄድ ብቻ ነው።❞
❝ተለያይተን የምናመጣው ጉድ የለም። ተለያይተን ተከፋፍለን ወላሂ የምናመጣው ውድቀት እንጂ ነስር የለም።❞
❝ጠንካራ ተቋም እናመጣለን ትግላችን ያ ነው። አምጥተናል አይደለም መንገድ ላይ ነን። ከናንተ ጋር ነን። ግን (ጠንካራ ተቋም የምናመጣው) በአሉባልታ አይደለም በሶሻል ሚዲያ አይደለም ተቀራርበን ተነጋግረን ነው።❞
❝ኡለማዎች አሉን እኛ! በቂ ኡለማዎች አሉን! ማናችን ነን ኡለማዎችን ተጠግተን (የጠየቅነው?) አንዳንዱ ሶሻል ሚዲያ ላይ ጀሀድ ያውጃሉ! ማነው ጀሀድ ማወጅ የሚችለው? የትኛው ኡለማ ነው ፈትዋ የሰጣችሁ?❞
❝እኔ ለስልጣኔ አይደለም። ገደል ይግባ ስልጣኔ!❞
❝እራሴን እራሴ ነኝ ማስተዳድረው ማንም አይቀልበኝም።❞
❝ያም ሆነ ይህ የማንደራደርበትን ልንገራችሁ? መስጂዳችን መልሶ ይተካል ነው የምላችሁ። የቀሩት መስጂዶች ይፈርሳሉ (ለሚባለው) በፍፁም!❞
❝ለተከሰተውም ነገር መፍትሄ ከናንተ ጋር ዛሬ ነው የምናበጀው።
በወቅታዊ ጉዳይ ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ‼️
መብቱን በሰላማዊ መንገድ ለመጠየቅ በወጣ ህዝብ ሙስሊም ላይ የተወሰደው እርምጃ ፍፅም ተቀባይነት የሌለው ፣ ኢ-ፍትሃዊና ኢ-ዲሞክራሲያዊ በመሆኑ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ያወግዛል።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ሲቲ የመስጅድ ፈረሳ እንዲቆምና የፈረሱትም በአስቸኳይ መተኪያ እንዲሰጣቸው እንዲሁም በጉዳዩ ዙሪያ የሚመለከታቸው አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በተደጋጋሚ በደብዳቤ ለሚመለከተው አካል ለማሳወቅ የተሞከረ ሲሆን የመስጅድ ፈረሳው ባለመቆሙ ህዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞውን በዛሬው እለት በአደባባይ ድምፁን በሰላማዊ መንገድ አሰምቷል።
ይህንንም ሰላማዊ የመብት ጥያቄ ተከትሎ በታላቁ አንዋር መስጅድ የፀጥታ አካል በወሰዱት ኢ-ህገ መንግስታዊ እና ኢ ሰብአዊ እርምጃ የሰው ሂይወት አልፋል፣ብዙሃን ቆስለዋል።
በመሆኑም ይህንን አስከፊ ጥቃት የፈፀሙ እና ያስፈፀሙ የፅጥታ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ አጥብቀን እንጠይቃለን ።
በቀጣይም የሚመለከተው አካል በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ እየተከናወነ ያለውን ድርጊት እንዲያስቆምነና ወደ ውይይት በመምጣት ስር ነቀል የእርምትና እርምጃ ተጠናክሮ እንዲተገበር አጥብቀን እንጠይቃለን።
የሀይማኖት ጉዳይ እና የእምነት ተቋማት ጉዳይ ሁሌም ቢሆን በስክነት መታየት ሲገባው ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በእምነት በተቋማቱ ጉዳይ ሲከተሉት የነበረውን አካያሄድ እንደ ተሞክሮ ከመውሰድ ይልቅ በዚህ አከያሄድ የተሰራው አስነዋሪ ተግባር የሀገራችንን ብሎም የከተማችንን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ እየጣለ ይገኛል።
በሸገር ከተማ መስጅድን በተመለከተ እየተከናወነ ያለው ድርጊት፣ሀላፊነት የጎደለው፣የህዝበ ሙስሊሙን ክብር ያዋረደ፣ሀገራችን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ፣የመንግስት የለውጥ ሪፎርምን ወደ ሀላ የሚመልስ በመሆኑ ጉዳዩ እንደ ሀገር ሊታሰብበት ይገባል።
በዛሬውም እለት በመስጅድ ፈረሳ ሳቢያ በሰላማዊ መንገድ መብቱን ለመጠየቅ በወጣው ህዝበ ሙስሊም ላይ በተወሰደው ኢ-ህገ መንግስታዊ እርምጃ ሒይወታቸው ላለፉ አላህ (ሱ.ወ) ጀነትን እንዲወፍቃቸው፣ለመላው ህዝበ ሙስሊም መፅናናትን እንመኛለን።
የከተማችንም ህዝበ ሙስሊሙ በቀጣይ ጉዳዩን በሰከነ መንፈስ እንዲከታተል አደራ እንላለን።
ግንቦት 18/2015
አሳዛኝ ዜና‼
ይህ ወንድማችን ዛሬ አንዋር መስጊድ በነበረዉ ተቃዉሞ ላይ በመንግስት ወታደር ደረቱን በጥይት ተመቶ የተገደለ ነው::
የአብይ አህመድ መንግስት ማንአለብኝነቱን ቀጥሎበታል ከወያኔ እንኳን ሊማር አልቻለም::
አላህ ነፍሱን ይማርልን
ዛሬ አንዋር መስጊድ የሆነ ነዉ,,,,
"…ከወለጋው እና ከሻሸመኔው አንፃር ካየነው እንደውም ይሄ በጣም ዕድለኛ ነው። መስጊድ አታፍርስብኝ ብለህ ስለጠየቅክ ብቻ እግርህን ቆምጦ ከጣለልህ በእውነት እልሃለሁ አንተ ዕድለኛ ነህ። ወለጋ እኮ ቢሆን እስላም ሆነህ እዚያ በመገኘትህ ብቻ በተለይ የወሎ ዐማራ እስላም ከሆንክ ከነዘር ማንዘርህ እርድ ነው የሚጠብቅህ። ከዚያ በፓርላማ ለአስከሬንህ ችግኝ እንዴት እንደሚተከልልህ ይወያይልህ ነበር። ከምር ዕድለኛ ነው።
"…መጅሊሱ እኮ ራሱ ኮሚቴ ነው። ያውም አፍራሽ ኮሚቴ። ኦሮሞ አደል መጅሊሱ። አፍራሽ ግብረ ኃይሉ ውስጥ ራሱ ሳይኖርበት አይቀርም። ታላቋ ኦሮሚያን ለመመስረት ደፋ ቀና ከሚለው ኮሚቴ ውስጥ ነው እኮ አለበት የሚሉ መተርጉማን አሉ።
• ዕድለኛ ነህ ወንድሜ…! ተርፈሃል…!
የውሃ፥ የዘይትና የአልባሳት ሽያጭ እንዲሁም ሚራክል መኒ በማለት የሃሰት አስተምሮት ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ታገዱ‼
ባማ ሆሊ ፋየር ኢንተርናሽናል ቸርች ዋና መሪ ዮሴፍ ኪዳኔ /ጆሲ/ ከታገዱት ውስጥ ነው።
ጋድስ ላይት ግሎሪ ኢንተርናሽና ቤተክርስቲያን የተባለውና በኢዮብ ጭሮ /ጆይ ጭሮ/ ዋና መሪነት በሚመራው ቤተ ክርስቲያን በተፈጸሙ ጥፋቶች ዙሪያ ከግለሰቡና ከቤተ ክርስቲያኗ ቦርድ አባላት ጋር በተደረገው ውይይት መሠረት ስህተታቸውን አርመው ለመቀጠል በጽሁፍ ማሳወቃቸውን ብስራት ሬዲዮ ዘግቧል።
እስራኤል ዳንሳ የተባሉ ግለሰብ በተደጋጋሚ በፈጸሟቸው ጥፋቶች ዙሪያ በተደጋጋሚ ውይይት ተደርጎ ለነበረባቸው ስሁት አካሄድ ስህተት የተባለውን ሁሉ እንደሚያርሙ በሚዲያቸው ወጥተው ይቅርታ እንደሚጠይቁ በማሳወቃቸው፥ ጉዳያቸውም በፍርድ ቤት የተያዘ ስለሆነ፥ ከፍርድ ቤት ውሳኔ በኋላ ካውንስሉ በመተዳደሪያ ደንቡና በአባላት የሥነ ምግባር መመሪያ መሠረት ተጨማሪ ውሳኔ የሚሰጥ ሆኖ ከአስተምህሮና ልምምድ ጋር በተያያዘ ለተነሳባቸው ጥያቄ መታረማቸውንና መስተካከላቸውን መግለጫው ከተሰጠበት ከግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ሁለቱም ለሁለት ወራት በራሳቸው ሚዲያ በግልጽ እንዲያሳውቁ ሆኖ ይህንን ማድረግ ካልቻሉ ካውንስሉ ያለ ተጨማሪ ውይይትና መግለጫ ቀጣይ እርምጃ እንደሚወስድ በመግለጫው ገልጿል።
“የሲዳማ ብቸኛው ነጻ አውጭ” እና ሲዳማን ለማሻገር ብሎም ነጻ ለማውጣት የተደራጀ ትግል እናደርጋለን በማለት አንድ አገልጋይን ለመሾም በሚል ተጽፎ በማህበራዊ ድረ ገጽ በመዘዋወር ላይ ያለ ደብዳቤ የወንጌላዊያን አማኞችን ገጽታ የሚያጠለሽ መሆኑ መግለጫው ጠቅሶ ይህን ስም የያዘ ተቋም ከየትኛውም የካውንስሉ አባል ቤተ ክርስቲያንም ሆን ህብረት ጋር ግኑኝነት የሌለው መሆኑን አሳውቋል።
Via: ዳጉ ጆርናል
ቦንቡ ፈነዳ መባልን በሰማሁ ጊዜ…!
"…በቀጥታ የሮጥኩት ወደ ዥልጦቹ ሠፈር ነው። ወደ ኦነጎቹ መንደር። በዚያም በደረስኩ ጊዜ እንደ ጠረጠርኩት በፈንዳው ቦንብ የጦስ ዶሮ አዘጋጅተው፣ በጭንቅላታቸው ላይ በዋቀ ጉራቻ ስም 4ቴ አዙረው ወደ ዓባይ ማዶ ሰዎች ሲጥሉ ደረስኩ። ግምቴ ትክክል ነበር።
"…ቦንቡን የወረወሩት የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች (ጎንደሮቹ) ናቸው። ይሄንንም ያደረጉት በእነ ዶር አምባቸው ሞት ቂም ስለያዙ ነው ብለው በቃ በእነርሱ ቤት በሚልዮን የሚቆጠር በጀት ያፈሰሱበትን አጀንዳ ፈጥረው ራሳቸውን በራሳቸው ሲያረኩ ደረስኩ። ዥል ሁላ።
"…አሁን ከሌሎች ክልሎች በአንጻራዊነት ሰላማዊ በነበረው ዐማራ ክልል ውስጥ የሚፈጠር ማንኛውም ሽብር ተጠያቂዎቹ ብአዴንና ብልፅግና ናቸው። ቀደም ብለው የዐማራ ልዩ ኃይልን አፍርሰዋል። ፋኖ ወደ በረሃ ገብቷል። ፀጥታው ኦሮሚኛ ተናጋሪ በሆነውና የመከላከያ ሰራዊት ልብስ በለበሰው በኦሮሞ ልዩ ኃይል ሥር ወድቋል። መሳሪያ ፍተሻ በሚል ሰበብ በሸዋ ሮቢት የግለሰቦች ቤት በአበባው ታደሰ ሰራዊት ወርቅና ብር ሳይቀር እየተዘረፉ ነው። የበረከት ስምኦን ልጆች በይፋ ሥራቸውን ጀምረዋል። ጎግል ላይ የዐማራ ክልል ካርታን በማንአለብኝነት እየቀየሩ ነው። ልዩ ዞኑ፣ ደብረ ብርሃንን ጭምር በኦሮሞ ስር አድርገውታል።
"…ገና አይደለም ቦንብ ሌላም መዓት ያዘንባሉ። ወኅኒ ቤቶች የሚጠበቁት በኦሮሞ ፖሊስ ይሆናል። የሆነ ቀን ከመኝታችሁ ስትነሡ "በወኅኒ ቤቱ በተነሣ ድንገተኛ የእሳት ተቃጥሎ ወይም እስረኞች ለማምለጥ ባደረጉት ሙከራ" የተወሰኑ እስረኞች ሕይወታቸው አለፈ ልትባሉ ትችላላችሁ። የኦሮሞና የትግሬ የሴራ ቦለጢቃ እንደእኔ የገባውማ የለም።
"…አሸበርቲም አይደለሁ? የአሸበርቲ ሴራማ አይጠፋኝም። እህዕ… ይሄ የእኔ የአሸበርቲው ዘመዴ መላምት ነው። እናንተስ…?
ዘንድሮ መቼስ ጉድ ነዉ‼
የጉግል የካርታ መተግበሪያ ሙሉ ሸዋን በኦሮሚያ ክልል ውስጥ አካቶ አዉጥቷል።
ይህ የተደረገው በኢትዮጵያ ካርታ ስራዎች ኤጀንሲ አማካኝነት ነው።
ከዚህን ቀደም የተለያዩ ክልሎች የመሬት ክፍሎችን በኦሮሞ ክልል የሚገኝ እንደሆነ አድርጎ የተሳሳተ መረጃ ለተጠቃሚዎች ሲያደርስ የቆየው ይህ ኤጀንሲ በጉግል ካርታ መተግበርያ ላይ ዛሬ ደግሞ የሸዋን ሙሉ መሬቶች ወደ ኦሮሚያ አካልሎ አቅርቧል።
ይህ ተቋም ካሁን በፊትም በተመሳሳይ መልኩ ደብረብርሃንን ከአማራ ክልል አውጥቶ ለኦሮሞ ክልል በሰጠው ተመሳሳይ የጉግል ካርታ ላይ የኢትዮጵያ ካርታ ሥራዎች ኤጀንሲ ማብራሪያ እንዲሰጠው የአማራ ክልል መንግስት መጠየቁ ይታወሳል።
የአሁን ለየት የሚያደርገዉ ሙሉ የሸዋ ግዛቶችን ጠቅልሎ ለኦሮሞ ክልል ማስረከቡ ነዉ።
ጠለምት‼️
በምስራቅ ጠለምት ወረዳ አሁን ያለውን ሰላም እንዳይደናቀፍ ከጫጨሬ ማህበረሰብ ጋር ወይይት አካሄደ‼️
በምስራቅ ጠለምት ወረዳ ጫጨሬ ቀበሌ ነዋሪዎች በህዎኃት ታጣቂዎች ተከቦ የመንቀሳቀስ መብቱ ተነፍጎ የነበረው ህዝባችን በወረዳው ሰላም አስከባሪና ህዝባዊ ፖሊስ ነፃ ወጥቷል።
የምስራቅ ጠለምት ምክትል አስተዳዳሪና የሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሰለሞን አታላይ በዉይይቱ እንደገለጹት የጠለምትን ህዝብ ነፃ ለማውጣት የአማራ ጀግኖች ውድ ህይወታቸውን ገብረዋል፤ ስለሆነም ህይወት ተከፍሎበት የተገኘ ሰላምና ነፃነት ማህበረሰባችን የሰላም ዋጋ አሳንሶ ሳይገነዘብ በራሱ ሰላሙን ማሰጠበቅ ይኖርበታል ብለዋል::
ሃላፊው አክለውም እስከ ዛሬ በጠላት ተከበህ እስር?፣ ድብደባና ዝርፊያ ሲደርስብህ የነበርከው ህዝባችን ከዛሬ በሗላ በሰላም የመኖር እድልህ ከአብራክህ የወጣ ሰላም አስከባሪና ህዝባዊ ፖሊስ ተረጋግጦልሃል፤ ቀጣይነቱም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
አቶ ሰለሞን አታላይ ከፊት ለፊታችን ያለው የህዎኃት ታጣቂ የጠለምት ህዝብ እያደረገው ያለውን ሁለንተናዊ ትግል እንቅፋትም ሆነ ስጋት ሊሆን አይችልም፤ ምናልባት የሰላም ጠንቅ ሊሆን ይችል ይሆናል። የፀረ ሰላም ተግባሩ ከቀጠለበት በነበልበሉ የወረዳችን ሰላም አስከባሪ አለንጋ ይገረፋል ተገርፎም አይቶታልና!
የተከበርከው የምስስራቅ ጠለምት ህዝብ በወርቃማ የአማራ ህዝብ የጀግንነት እሴት ተላብሰህ የተበተነውን የህዎኃት ታጣቂ አሳልፈህ ለህግ የመስጠት ተግባርህ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
በደም የተከበረ ወሰንና ማንነታችን በላባችን ማስጠበቅ ይጠበቅብናልም ብለዋል ሃላፊው።
የምስራቅ ጠለምት ወረዳ ሚሊሻ ፅ/ቤት ሃላፊ አሰር አለቃ አደራው ጥጋቡ በበኩላቸውም ሰላም አስከባሪያችን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ፀረ ሰላም ሃይሎችን በመመንጠር ላይ ይገኛል። ስለሆነም ህዝባችን በህዝባዊ እሴት ከተገነባ ከሰላም ሃይላችን ጎን በመሰለፍ የፀጥታ መዋቅራችን አይንና ጀሮ ሆነን ፀረ ሰለላም ሃይሎችን መፈናፈኛ ማሳጣት ይጠበቅብናል ብለዋል
የፅ/ቤት ሃላፊው አክለዉም የምስራቅ ጠለምት ህዝብ የእለት ከእለት ተግባሩን በሰላማዊ መንገድ እንዲያከናውን ከፀጥታ ሃይላችን የሚጠበቀውን ሁሉ ለመፈፀም ዝግጁ ነን፤ ህዝባችንም ለባንዳዎችና ተላላኪዎች ጀሮ ሳይሰጥ በክቡር መስዋእትነት የተገኘ ክብሩን እና ማንነቱን ለአፍታም ሊዘነጋ የማይገባ ጉዳይ ነው ሲሉ ተናግረዋል::
በመጨረሻም የውይይቱ ተሳታፊ ማህበረሰብ የወረዳችን ሰላም እንከን የለሽ ነው ብንል ማጋነን አይሆንብንም፤ ሰላም አስከባሪያችን እና ህዝባዊ ፖሊሳችን ደህንነታችን ለመጠበቅ እያደረገው ያለው ተደጋጋሚ ስምሪት እያመሰገን ቀጣይም በአማራ ክልል መሬት ያለው ተስፋ የቆረጠ እና በመበተን ላይ ያለው የወያኔ ሃይል መንግስት መላ ሊለን ይገባል የሶስቱ ቀበሌ ህዝብ ስቃይ ላይ ነው በየቀኑ ሰው በርሃብና በታጣቂዎች ሬሽን ሸክም እየሞተ ይገኛል መፍትሄ ሲል በምሬት ተናግረውል::
መረጃዉ፦ የምስራቅ ጠለምት ወረዳ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ነዉ።
=======================
"19 መስጅዶች ፈርሰዋል::"
የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአዲሱ የሸገር ሲቲ ከተማ አስተዳደር ከረመዳን 1 ጀምሮ የፈረሱ መስጂዶች ቁጥር 19 መድረሳቸውን አስታውቋል።
ምክር ቤቱ ትናንት ግንቦት 15/2015 አዲስ አበባ በሚገኘው ዋና ፅህፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ በከተማ አስተዳደሩ እየተካሄደ ያለውን የመስጂድ ፈረሳ ያወገዘ ሲሆን፤ በተለያዩ ጊዜያት ለሚመለከተው አካል አቤቱታውን ቢያቀርብም በጉዳዩ ላይ እስካሁን በጎ ምላሽ አለማግኘቱን በማንሳት ድርጊቱ አሁንም በአስቸኳይ እንዲቆም በድጋሚ ጠይቋል።በመላው ኦሮሚያ የመጭው ጁምዓ ኹጥባዎች መስጂድ ፈረሳውን የተመለከቱ እንዲሆኑ መልዕክት ተላልፏል።
በምዕራብ በኦሮሚያ በአማራ ዜጎች ላይ ከተፈፀመው ግድያ ጀርባ እራሱን "የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጦር አዛዥ" ብሎ የሚጠራው ፈቀደ አብዲሳ መኖሩን ዋሺንግተን ፖስት አጋለጠ‼️
በምዕራብ ኦሮሚያ፣ በአማራ ላይ ከተፈፀመው ግድያዎች ጀርባ እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጦር አዛዥ ብሎ የሚጠራው #ፈቀደ አብዲሳ እና ሃይሎቹ መኖራቸውን ዋሺንግተን ፖስት በዘገባው አመላከተ፡፡
ዘገባው ፈቀደ አብዲሳ እና ሃይሎቹ በክልሉ የሚኖሩ የ #አማራ ተወላጆችን በተደጋጋሚ በጅምላ ሲገድሉ እንደነበር ነዋሪዎች መግለፃቸውን አስታውቋል፡፡
ባሳለፍነው አመትኦሮሞና የአማራ ብሄር ሰዎችን አሰባጥራ በምታኖረው አጋምሳ ከተማ በኦሮሞ አማፂያን የሚደገፈው የፈቀደ ታጣቂዎች በደርዘን የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆችን መግደላቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል ብሏል፡፡
“እነዚህ የሞቱት ንፁሀን አማራ ጎረቤቶቻችን ነበሩ” ሲል የተናገረው አንድ የኦሮሞ ነዋሪ " ለተፈጠረው ነገር ተጠያቂው ፈቀደ ነው" ሲል ኮንኗል፡፡
ነገ ትግራይ ክልል የሚደረገው ሠልፍ
① ከወልቃይትና ራያ ተፈናቅለው መቀሌ የሚገኙ ዜጎች ይመለሱ፣አካባቢው ይዞታችን ነው።
② በስርቆትና ዝርፊያ ምክንያት ከሰሞኑ የተቋረጠው የሰብዓዊ እርዳታ በተለይ በመቀሌ፣ዓብይ ዓዲ ፣ ዓዲግራት እና ሽሬ ይጀመርልን በሚሉ ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩር ተሰምቷል።