ethio360media | Unsorted

Telegram-канал ethio360media - Ethio 360 Media

37564

ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር !!!

Subscribe to a channel

Ethio 360 Media

አማርኛ❗❗❗
ሩሲያ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በትምህርት ቤቶቿ አማርኛን ማስተማር እንደምትጀምር ገለጸች‼️
ሶስት የሞስኮ ትምህርት ቤቶች አማርኛ እና ስዋህሊ ቋንቋዎችን ማስተማር እንጀምራለን ብለዋል
ሩሲያ አማርኛ ቋንቋ በመጀመሪያ ድግሪ ደረጃ ለማስተማር መወሰኗ ይታወሳል
ሩሲያ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በትምህርት ቤቶቿ አማርኛን ማስተማር እንደምትጀምር ገለጸች።
 ትምህርት ቤት ስዋህሊ ቋንቋን ሁለተኛው የውጭ ቋንቋ አድርጎ ያስተምራል ተብሏል።
እንዲሁም 1522 የተሰኘው ትምህርት ቤት ደግሞ አማርኛ ቋንቋን እንደሚያስተምር ተገልጿል።
ሩሲያ የአፍሪካ እና ሞስኮን ወዳጅነት ለማጠናከር በሳምንት አንድ ወይም ሁለት የትምህርት ክፍለ ጊዜዎች ለአፍሪካ ቋንቋዎች ማስተማሪያ እንዲውሉ ይደረጋል ብላለች።
ሩሲያ በቀጣይም በምዕራብ አፍሪካ ሰፊ ተናጋሪ ያለው ዩርባ ቋንቋን ማስተማር እንደምትጀምር ገልጻለች።
በመቀጥልም ሶማልኛ እና የዙሉ ቋንቋዎችን በሩሲያ ትምህርት ቤቶች ለማስተማር የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ እንደሆነም ከዚህ በፊት ተናግራለች።
ሌላኛዋ የሩቅ ምስራቋ ሀገር ቻይና አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ድግሪ ደረጃ ማስተማር እንደምትጀምር መግለጿ ይታወሳል።
አማርኛ ቋንቋ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) ከሚሰጡ 101 የውጭ ቋንቋ ትምህርቶች አንዱ ሆኖ ይሰጣልም ተብሏል።
ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ባሳለፍነው ግንቦት ወር ላይ ወደ ቤጂንግ ለጉብኝት ባቀኑበት ወቅት ለቻይናውያን ተማሪዎች የተዘጋጁ የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጽሃፍት መመረቃቸው አይዘነጋም።
የማስተማሪያ መጽሀፍቱ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ ለቻይናውያን ተማሪዎች የተዘጋጁ እንደሆኑ በወቅቱ ተገልጾም ነበር።
AlAin

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አርቲስት አቡሽ ዘለቀ እንዲህ ይላል!!

ውሃ ሞልቶ ባገር ቀድተሽ 'ማትጨርሺው
ምነው በሰው እንባ ሊጡን አቦካሽው ?

ቢኾን መልካም ነበር ብትሆኚ እንደቃልሽ
እሞትልሽ ነበር እንኳን ልቀየምሽ

እንዳይዘም አንገትሽ ትራስ ኾነሽ ክንዴ
ዘውዱን ስትጭኚ ተረሳሽ ወይ ባንዴ

በሰፊው ልቤ ላይ እኔ ስተክልሽ
በመንደሬ ልብቀል ለምን ትያለሽ

በ27 አውታር ተቃኝታ ክራሬ
ላንቺ ስል የኾንኩት ይታያል ሰንበሬ

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ዐብይ አህመድ በረከት ስምኦንን አማራ ክልል ባለው ሁኔታ አማካሪ አድርጎታል።

የአማራውን መዋቅር ለማፍረስ ከሱ የተሻለ ሰው የለም ብሎ እየሰራበት ነው።

አማራ እንደ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለጊዜው ከፌደራል መንግስቱ ጋር የወገነው ካድሬ አይቀርለትም።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የደፈጣ ጥቃት‼️

በምዕራብ ወሎ መካነሰላም ልዩ ስሙ ቦረድ በሚባል ወንዝ አካባቢ በአካባቢው በሚንቀሳቀስ የመከላከያ ሠራዊት ላይ የደፈጣ ጥቃት መድረሱን ምንጮች ገልጸዋል። በዚህም ከባድ የሰብዓዊ እና የቁሳዊ ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል።
በርካታ አምቡላንሶች ሲመላለሱ ማየታቸውን ተናግረዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ብልፅግና ለሌላ ዙር የዘር ፍጅት ዝግጅት ላይ ነው።

ከ15 ሺህ እስከ 20 ሺህ የሚሆን የመከላከያ ዩኒፎርም እና ጫማ አብይ አህመድ ወደ ትግራይ መላኩን የህወሓት ውስጥ አዋቂ የሆነ የውጭ አገር ጋዜጠኛ አጋልጧል።

አማራ ክልልን በወረረበት ወቅት ንፁሃንን የጨፈጨፈው የትህነግ ኃይልን እገዛ አብይ አህመድ ፈልጓል።

ይህ ኃይል አማራ ክልል ገብቶ ምን እንደሚያደርግ እሙን ነው።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ብልቱ የተቆረጠው ወጣት❗❗
በሰሜን ወሎ በላሊበላ ዳቦ ከተማ አንድ ወጣት ብልቱ በመቆረጡ ህዝቡን አስቆጥቷል።
የከተማው አመራር ሰሞኑን በነበረ ስብሰባ ላይ ለምን ይህ ተደረገ ተብለው ሲጠየቁ ይሄ መከላከያ ሰራዊት ከሚከፍለው መስዋዕትነት አንፃር ሲያንስ ነው ማለታቸው አነጋጋሪ ሆኗል ብለዋል።

በላሊበላ ከተማ ዛሬ ሁሉም የመንግሥት ሰራተኞች ለስብሰባ ተጠርተዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ደራ❗❗

ቅዳሜ ዕለት ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ በደራ ወረዳ አደሬ ገመቹ፣ ባቡ ድሬ እና ሰለልኩላ በተባሉ ሥፍራዎች በኩል ግንቢ እንዳቆ እና ባላ ወደተባሉ ቦታዎች ከገቡ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ውስጥ በርካታ  አባላት መገደላቸውን የዓይን እማኞች አስረድተዋል፡፡

በጉንደ መስቀል ከተማ በርካታ የፋኖ ታጣቂዎች መኖራቸው የተነገረ ሲሆን፤ የመንግሥት የፀጥታ ሀይል ወደ ቦታው እያቀና መሆኑን  ለማወቅ ተችሏል፡፡

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የፌዴራል መንግስትና የአማራ ክልል ፋኖ ግጭት ያሳሰባት አሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልክተኛ ማይክ ሀመርን ወደ ኬንያና ኢትዮጵያ ላከች። ማይክ ሀመር ኢጋድን፣ የአፍሪካ ህብረትን እና የኢትዮጵያ መንግስትን ያናግራል።
በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ብራስልስ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ሲመክሩ መቆየታቸው የሚታወስ ነው።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ከወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ምሁራን ማህበር የተሰጠ የአቋም መግለጫ‼️
የአሸንዳ በዐልን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚንስቴር የሆኑት ዶ/ር አብርሐም በላይ ያስተላለፉት መልዕክት የስራ ኃላፊነታቸው እና ተቋሙን የማይመጥን ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ በመሰረቱ የአሸንዳ፣ አሸንድየ እና ሶለል በዓላት በሰሜን ኢትዮጵያ የአከባቢው ኃይማኖታዊ ትውፊት፣ ባህል እና መገለጫ የሆነው ክብረ በዐል ወደ ፖለቲካ እና ብሔር በማውረድ የፌደራል መንግስት ባለስልጣን ሆነው እያለ በትግርኛ ቋንቋ ለትውልድ ክልላቸው የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱን ወቅታዊ ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያላስገባ ብሄራቸውን ማዕከል ያደረገ ከኢትዮጵያዊነት ዝቅ ያለ መልዕክት ነው፡፡
ይህን መሰረት በማድረግ በመልዕክታቸው መጨረሻ ማስገንዘብ የፈለጉትን የተሳሳተ ዕይታ እና የግል ውሳኔ አንድ በአንድ እናያለን፡፡

ነጥብ 1 ላይ የተቀመጠው የአከባቢው ማንነት እና ወሰን ጥያቄ በተመለከተ ጥያቄ አለኝ የሚል አካል ካለ በህግ እና በህገ መንግስቱ መሠረት እንዲመለስ እየተሰራ ይገኛል፤ በማለት የተገለፀዉ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት እና ራያ ህዝብ ከ4 አስርት አመታት በላይ ያካሄደው ትግል የካደ በመሰረቱ ህውኃታዊ የሆነ አስተሳሰብ ነው፡፡
ነጥብ 2 ላይ ያስቀመጡት ’’የተፈናቀለ ህዝባችን’’ የሚለው አገላለፅ ወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ህዝብ ያፈናቀለው ህዝብ የለም፡፡ ይልቁንስ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ህዝብ አማራ በመሆኑ ብቻ በጅምላ ሲገደል፣ ሲፈናቀል እና ሲሳደድ በአጭሩ ማንነትን የማፅዳት ዐለምአቀፍ ወንጀል የተካሄደበት፤ በማንነቱ ምክንያት ግፍ እና መከራ የተቀበለ ህዝብ ነው፡፡ የአጭር ግዜ ማሳያ የሚሆነው በማይካድራ የተፈፀመው የጦር ወንጀል/war crime and crime against humanity/ ነው፡፡
ነጥብ 4 ላይ ሪፈረንደምን በተመለከተ በእርሱ አባባል ትግራይ የሚገኘው የተፈናቀለ ህዝብ ወደ ወልቃይት ጠገዴ ጠለምት በመሄድ ህዝበ ውሳኔ ለምን ያካሂዳል? የማንነት ጥያቄው የአማራ ህዝብ አካል የሆነው የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት እንጂ አንድ ትግሬ ለምን ሪፈረንደም ይመርጣል?
የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ህዝብ Petition በማሰባሰብ ያለ ማንነታችን እና ያለ ፍላጎታችን በትግራይ ክልል ተካልለናል፤ ማንነታችን አማራ ነው በማለት ህጋዊ ጥያቄ አቅርቧል፡፡ ስለዚህ የማንነት ጥያቄ በሚመለስባቸው አግባብ መሰረት በአስቸኳይ ፌደሬሽን ምክር ቤት ህዝቡን በማነጋገር እና ጥናት በማድረግ ምላሽ መስጠት ይገበዋል፡፡
ነጥብ 5 ባለጉዳይ እና ባለቤት ነኝ የሚል አካል በማለት የተገለፀው አባባል ሰፊውን የአማራ ህዝብ አይመጥንም፡፡ የአማራ ህዝብ እና መንግስት የወሰን እና ማንነት ጥያቄዎች በህጋዊ መንገድ ምላሽ እንዲሰጠው እየሰራ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ስለዚህ የክልሉ ህዝብ እና መንግስት በወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ራያ ጥያቄ ባለቤት ነው። ስለሆነም ምንስቴሩ ሁለቱም ክልሎች በእኩልነት እና ፍትኃዊነት መመልከት ሲገባቸዉ፤ ለተመደቡበት ክብር እና ፕሮቶኮል በማይመጥን መልኩ ውግንና አሳይተዋል።
ማጠቃሊያ
በፕሪቶርያው ስምምነት መሰረት አንቀፅ 10/4 መሰረት The parties commit to resolving issues of contested areas in accordance with the constitution the Federal Democratic Republic of Ethiopia.
ነጥብ 3 የተቀመጠው የአከባቢው አስተዳደር ህገ ወጥ እና መፍረስ አለበት በማለት የተገለፀዉ፤ የአከባቢዉ አስተዳደር የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ህዝብ ውድ መስዋዕትነት እና ዋጋ በመክፈል በደሙ የተገኘ እንጂ ችሮታ አይደለም፡፡ በመጨረሻም ህጋዊ ውክልና በመስጠት፤ የማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሜቴ በማቋቋም ጥያቄዉን ህጋዊ በመሆነ መልኩ አቅርቧል። በቅርቡ በተካሄደው የሰሜኑ ጦርነትም ከመላ ኢትዮጵያውያን ጎን በጋራ  በመቆም አማራ መሆኑ በተግባር አሳይቷል፡፡
የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት እና ራያ ህዝብ ጥያቄዎች በህግ እንዲፈቱ እንጂ ህግ በማስከበር ሰበብ ይሁን ምክንያት የህዝቦች የማንነት ጥያቄ እንዲደፈጠጥ የሚፈቅድ ነባራዊ ሁኔታ የለም፡፡
በመሆኑም ሚንስቴሩ የተሰጣቸውን ስልጣን እና ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ለግል ፍላጎታቸው እና ለህውኃት መቆማቸው ያስመሰከሩበት መግለጫ ነው፡፡ በመሆኑ ይህንን በመገንዘብ አስቸኳይ እርምት እና ሚዛናዊ አገራዊ ዕይታ እንዲላብሱ በአንክሮ እንጠይቃለን፡፡
እናመሰግናለን!

        የማህበረሰባችን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመፍታት እንተጋለን!                                      
                          
            የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ምሁራን ማህበር

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በወልቃይት-ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የሚጠናከር እንጂ የሚፈርስ ተቋም የለም!

(በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፣ ከወልቃይት-ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ)

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደርና ሕዝብ ‹በአንድ እጅ ነጻነት፣ በሌላው እጅ ልማትን ማረጋገጥ እንደሚቻል› ከድኀረ-ነጻነት ጀምሮ በተግባር ሲያሳይ ቆይቷል፡፡ ዞናችን ካለበት መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥና ከኢትዮጵያ ውስጣዊና ውጫዊ ሁኔታዎች አኳያ የኢትዮጵያ አገራዊ ደህንነት መጠበቂያ ቁልፍ በር ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡ ይህን ወሳኝ ሚናውን ከባለድርሻ አካላት ጋር ሆኖ አጠናክሮ ይቀጥላል።

ዛሬ በጀት የማይበግረው፤ አሸባሪ የማይደፍረው ማኀበረሰብ መገንባት የተቻለው፤ የዞናችን አመራር እና ሕዝቡ አንድ ልብ መካሪ፤ አንድ ቃል ነጋሪ መሆን በመቻላቸው ነው፡፡

የወልቃይት-ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር እና መላ ሕዝቡ ወደ ጨለማው ዘመን ላለመመለስ የወትሮ ዝግጁነት አቅሙን በማሳደግ ላይ ነው፡፡

ዛሬ በዓይን ጥቅሻ መግባባት የሚችል ምሽግም ሆነ የእርሻ ካምፕ ላይ ውሎ ሲያድር ዓላማን የሚያስቀድም ለነጻነቱ ሞትን የናቀ ሁለገብ የማንነቱ ዘብ፤ የሰላም አርበኛ በመገንባት ላይ እንገኛለን፡፡ 

ጀግንነትን በደም የወረሰ፣ አስተዋይነትን፣ አርቆ-አሳቢነትን እና ትዕግሥትን የታደለው ጀግናው የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ሕዝብ የገፋውን ጥሎ፣ የተጫነውን አሽቀንጥሮ ተወልዶ ባደገበት፣ ታሪክና የትግል ቃል ኪዳን በተቀበለበት ሥፍራ ልማት ላይ ነው፡፡ ሰላሙንም ሆነ ልማቱን እኩል ለማስኬድ የሰብል ማሳው ላይ ይውላል፤ ምሽግ ውስጥ ያድራል፡፡ በአንድ እጁ የነጻነት ትግል በሌላ እጁ የልማት ትግል እያደረገ የሚገኘው ሕዝባችን የአሸናፊ ትውልድ ግንባታው በሁሉም ዘርፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

በዚህ ሁሉ ትግል ውስጥ የአማራ ሕዝብ ለዘመናት የታገለላቸውን የወሰንና ማንነት ጥያቄዎች ከማጣጣል ጀምሮ ለዳግም ወረራ አሳልፎ ለመስጠት የሚደረጉ አሻጥሮችና ደባዎችን በከፍተኛ ትግስት ስንከታተል ቆይተናል፡፡ በተለይም አገሪቱ ያለችበትን መንታ መንገድ በመረዳት የጠብ-አጫሪና ትንኮሳ ድርጊቶችን በማስተዋልና በጥበብ ታግሰናል፡፡ ወደፊትም የማንነት ትግላችን ደጋፊ የሆኑ ፍትሕ ወዳድ ኢትዮጵያዊያንን ይዘን ለዘላቂ ሰላም ዘብ እንቆማለን፡፡

ነገር ግን ነሐሴ 16/2015 ዓ.ም የመከላከያ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ያስተላለፉት መልዕክት አሳዛኝ፣ ፍጹም ኃላፊነት የጎደለው ነው፡፡ መከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ የአሸንዳ በዓልን አስመልክቶ በትግርኛ ቋንቋ ያስተላለፉት መልዕክት የአማራ ክልል ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ አድርጎ የተላለፈ አደገኛ መልዕክት ነው፡፡

ሚኒስትሩ የፌዴራል መንግስት ኃላፊነት ይዘው ሳለ ፍፁም ለአንድ ወገን ያደላ መልዕክት ማስተላለፋቸው ኃላፊነት የጎደለውና የአማራ ክልልን ወደለየለት ግጭት ለማስገባት ሆን ተብሎ የተላለፈ መልዕክት ነው፡፡

መከላከያ ሚኒስትሩ ያስተላለፉትን መልዕክት፣ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር አማራ ክልልን ወደለየለት ብጥብጥና ግጭት እንዲያመራ ሆን ተብሎ የተረጨ መርዘኛ መልዕክት እንደሆነ ያምናል፡፡

ሚኒስትሩ ይህንን መልዕክት ማስተላለፍ የሚችሉበት ምንም ዓይነት ሕጋዊ ኃላፊነት ሳይኖራቸው አንዱን አካል ህገ-ወጥ ሌላውን ደግሞ ሕጋዊ ብሎ መፈረጅ ከፌዴራል ወርደው ለአንድ ክልል/ለተወለዱበት ብሔር/ መወገን አመላካች ሆኖ አግንተነዋል፡፡ የአማራ ሕዝብን የእውነትና የፍትህ ጥያቄ የካደ ነው፡፡

በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የተቋቋመው መንግስታዊ መዋቅር በሰዎች/በበጎፍቃድ የተቸረው ሳይሆን ለዘመናት በተከፈለው ውድ መስዋዕትነት የተገኘ መሆኑን ሚኒስትሩ የዘነጉት ይመስላል፡፡

በቅርቡ በክልላችን የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከሚከለክላቸው ጉዳዮች አንዱ ለተጨማሪ ሁከትና ብጥብጥ የሚጋብዙ ንግግሮችን መከልከሉ እሙን ነው፡፡ የመከላከያ ሚኒስትሩ መልዕክት ግን የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በግልፅና በአደባባይ የሚጥስ ሕገ-ወጥ ድርጊት ሆኖ አግንተነዋል፡፡ ሚኒስትሩ ፌዴራሉ መንግስት ከሰጣቸው ኃላፊነት ውጪ ተገቢ ያልሆነ መልዕክት በማስተላለፋቸው የአማራን ሕዝብ ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል፡፡

አሁን በክልላችን የተፈጠረው ግጭት እንዲሁ የሚታይ ሳይሆን የአማራን ህልውና የሚፈታተኑ (መሰደድና መፈናቀል፤ እንደሕዝብ መናቅና መገፋት) እንዲሁም መሰረታዊ የእውነት፣ የፍትሕና የርትዕ ጥያቄዎች ባለመመለሳቸውና በመጓተታቸው የተነሳ በመሆኑ የሚሻለው እና የሚበጀው መንግሥት ለለውጡ ፅንስና መወለድ መሰረት የሆኑትን የሕዝብ ጥያቄዎች ለመፍታት መጣር ለሰላማዊ ንግግር ልቡና አዕምሮው ክፍት አድርጎ መቅረብ ይመረጣል፡፡ ብቸኛው የሰላም መንገድ የአማራ ሕዝብን ጥያቄ መመለስ ነው፡፡

ይሁን እንጂ አሁን ባለንበት ነባራዊ ሁኔታ ተቋማዊ ሰርጎ-ገብነት የወቅቱ ፈተና ሆኖ ተገልጧል፡፡

የበላይነትን ለምዶ የኖረው ትሕነግ ኢ-ፍትሐዊ ፍላጎቶቹን ለማስፈጸም በመንግሥታዊ ተቋማት ለእርሱ እኩይ ዓላማ የተሰለፉ አንዳንድ አካላትን በመጠቀም ከተቋማዊ ኃላፊነታቸው ባፈነገጠ መልኩ ለሰላም ፀር የሆኑ መልዕክቶችን በየመድረኩ መሰማታቸው እንደሕዝብ አጠቃላይ የአማራ ህዝብን እንደአስተዳደር የወልቃይት-ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደርን አሳስቧልም አስቆጥቷልም፡፡

ስለሆነም፡-

1) የወልቃይት-ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የትንሿ ኢትዮጵያ ተምሳሌት የሆነ፣ በርካታ የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች በላባቸው ሰርተው የሚኖሩበት በመሆኑ፣ ዞኑ ካለው መልክዓምድራዊ አቀማመጥና የአካባቢው ሰላም ሆኖ መቆየት እረፍት የነሳው ጠላት በተለያየ መንገድ አስርጎ የሚያስገባቸውን ሰርጎ-ገቦችን የመመንጠርና በዞኑ የሕግ የበላይነትን የማስከበር የውስጥ ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን!!

2) በዞኑ ስር የሚገኙ የመደበኛ ፖሊስ፣ የሚሊሻ እና የሠላም አሰከባሪ ኃይላችን የሥራ ላይ ስልጠና በተለይም የሠላም አሰከባሪ ኃይል ግንባታችን ተጠናክሮ ይቀጥላል፤ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የጸጥታ ኃይላችን ሕዝቡን በጀግንነት ይጠብቃል፤ በሰብዓዊነት ማገለግሉን አጠናክሮ ይቀጥላል!!

3) ልማት፣ ሰላምና ደኅንነት ሳይነጣጠሉ የሚቀጥሉ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ስለሆነም የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ሕዝብ የትኛውም ችግር የማይበግረው እና ከዓላማው የማይናወጥ ሆኖ ቋሚና ዘላቂ ታሪክ መስራቱን ይቀጥላል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ የህልውናችን ዘብ መሆን የሚችሉ የተቋማት ግንባታ ስራዎቻችን ሕግና ሥርዓትን ተከትሎ የተቋም ግንባታችን ይቀጥላል!!

4) ወልቃይት ጠገዴ ላይ ትንኮሳ ለማድረግ፤ ለዳግም ወረራ ተጋላጭ እንድንሆን በዘመናት የማንነት ትግል የቆመውን የዞኑን መዋቅር ለማፍረስ የሚሞክሩ አካላት ፍላጎታቸው ፈጽሞ አይሳካም፡፡ በተለይም በተቋማት ውስጥ ሰርገው-የገቡ የጨለማው ዘመን ናፋቂዎች የአካባቢያችንን ሰላም ለማደፍረስ የሚያደርጓቸው ጠብ-አጫሪ ንግግሮች ቀቢጸ ተስፋ ሙከራዎች ከመሆን እንደማይዘሉ እናስረግጣለን!!

5) ነጻነት የመስዋዕትነት ውጤት ነው፡፡ በዙሪያችን ያለው አንጻራዊ ሰላም የሕዝብ ትጋት ውጤት ነው፡፡ ህልውናን ለማስከበር፣ ነጻነትን ለማጽናት፣ ሁሌም ቢሆን ራስን ትርጉም ላለው መስዋዕትነት ማዘጋጀት ይገባል፡፡

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የ ወልቃይት እና የራያን ጉዳይ በሚመለከት ‼️

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በምስራቅ ጉራጌ ዞን 14 ሰዎች በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መገደላቸው ተነገረ‼️‼️
በቅርቡ በተዋቅረው ምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራውና መንግሥት “ኦነግ ሸኔ” በሚል በአሸባሪነት የፈረጀው ኃይል 14 የአካባቢው ነዋሪዎችን አግቶ በመውሰድ መግደሉን ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡

ታጣቂዎቹ ጥቃቱን የፈጸሙት ነሐሴ 13/2015 በኦሮሚያ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አዋሳኝ አካባቢ በሚገኙ ዱግዳ፣ መቂ እና ጢያ ትክል ድንጋይ ተብለው በሚጠሩ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ቦታዎች ላይ መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

“የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ‘ለመንግሥት አካላት መረጃ ትሰጣላችሁ’ በሚል 16 ሰዎችን በምሽት አግተው ከወሰዱ በኋላ፤ ኹለቱ ድብደባ ቢፈጸምባቸውም ‘ነጻ ናችሁ’ በሚል ሲለቀቁ፣ ቀሪዎቹ ተገድለዋል” ነው ያሉት።

የታጣቂ ቡድኑ አባላት ከላይ ወደተጠቁሱት አካባቢዎች በምሽት በመግባት አግቶ ከመውሰድ እና ከመግደል በተጨማሪ፤ ነዋሪዎቹ አካባቢውን ለቀው እንዲሰደዱ ድብደባና ዘረፋ እንደሚፈጽሙባቸውም ተናግረዋል።

“ከኦሮሚያ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አዋሳኝ የሚገኙ ነዋሪዎችን ከአካባቢው በማፈናቀል መሬቱን የራሳቸው ለማድረግ ነው ተደጋጋሚ ጥቃት እየፈጸሙ ያሉት፡፡” ያሉት አንድ ሥማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ነዋሪ፤ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ በሚፈጽሙት ድብደባና ዘረፋ በኦሮሚያ ክልል ወሰን አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ከአካባቢያቸው እየተፈናቀሉ ነው ብለዋል።

በተለይም በኹለቱ ክልሎች አዋሳኝ ቦታዎች ከሚኖረው ሕዝብ የክስታኔ ጉራጌ ብሔር ተወላጆች ዋነኛ የጥቃቱ ሰለባ ናቸው የተባለ ሲሆን፤ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ወደ ሶዶ ወረዳ በሚገቡበት ቦታ የሚገኙ በመሆናቸው የመጀመሪያዎቹ ተጠቂ መሆናቸው ተመላክቷል።

ታጣቂዎቹ በነዋሪዎች ቤት ምሽት በመግባት “ገንዘብ እና የጦር መሳሪያ አምጡ፣ ካላመጣችሁ ትገደላላችሁ፡፡” እያሉ እያሰቃዩ ነውም ተብሏል።

የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በአካባቢው ከጥር 2015 ጀምሮ በተደጋጋሚ ጥቃት እያደረሱ መሆኑን የገለጹት ነዋሪዎች፤ “ከባለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ ግን የሚፈጽሙት ግድያ እና እገታ ተባብሷል” ሲሉ ገልጸዋል።

ታጣቂዎቹ ነዋሪዎችን አግተው በመውሰድ ከ200 እስከ 300 ሺሕ ብር እንደሚጠይቁ በመጥቀስም፤ በአካባቢው በቂ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ባለመኖራቸው ችግሩ ተባብሶ መቀጠሉን ተናግረዋል። 

በምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ሠላምና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዳዊት ጉግሳ፤ “ግድያው እና እገታው የተፈጸመው እኛ አካባቢ አይደለም” ካሉ በኋላ፣ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

አዲስ ማለዳ

Читать полностью…

Ethio 360 Media

#NewsUpdate‼️
እነ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና ጋዜጠኛ ዓባይ ዘውዱን ጨምሮ በርካታ  እስረኞች  ወደ አዋሽ አርባ ተወሰዱ‼️

ትናንት ‹ፍርድ ቤት› ይቀርባሉ ተብለው የነበሩ  የአማራ ሚዲያ ማዕከል ዋና አዘጋጅ ዓባይ ዘውዱ ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል  አቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል ዶ/ካሳ ተሻገርን ጨምሮ በሰሞኑ የታሰሩት ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች  ወደ አዋሽ አርባ መወሰዳቸው ታውቋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የአማራ ክልል ምክር ቤት ለአስቸኳይ ስብሰባ መጠራቱን ትናንት መዘገባችን ይታወሳል።
በዚህ ስብሰባ ላይ ክልሉን በበላይነት የሚመራ አዲስ ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ሌሎች አዳዲስ ሹመቶች እንደሚኖሩ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በፒያሳ የሚገኘዉ የአራዳ ህንጻ በመፍረስ ላይ ነዉ‼️

በፒያሳ የሚገኘዉ ጥንታዊዉ የአራዳ ህንጻ በመፍረስ ላይ መሆኑን ነዋሪዎች በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻቸው እያጋሩት ይገኛሉ ።

ህንፃው ከለሊት ጀምሮ ነው ፈረሳው የተጀመረው። በርካቶችም ቅሬታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ ።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በኡጋንዳ ግብረሰዶም ፈጽሟል የተባለው ወጣት የሞት ቅጣት እንደሚጠብቀው ተነገረ❗❗

የ20 አመቱ ወጣት በአዲሱ የሀገሪቱ የጸረ ግብረሰዶም ህግ በሞት ሊቀጣ የሚችል የመጀመሪያው ግለሰብ ይሆናል።

ኡጋንዳ በግንቦት ወር ያጸደቀችው ህግ የአለም ባንክ ብድርን አስከልክሏታል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሸን በኢትዮጵያ በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ያለው የ#ሰብአዊ መብት ሁኔታ መባባሱ በጣም አሳስቦናል ሲል ትናንት በቲውተር አካውንቱ አሳውቋል። ባለስልጣናት የጅምላ እስራት እንዲያቆሙ፣የነጻነት መነፈግ በህግ እንዲታይ እና በዘፈቀደ የታሰሩትን እንዲፈቱ እንጠይቃለን ብሏል።
👇👇👇

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አማራን እየጨፈጨፉ ያሉት የዐብይ አህመድ ቅጥረኛ ወታደሮች!

አማራ ንፁሃን ላይ ከባድ መሳርያ እየተተኮሰ ንፁሃን በጅምላ እያለቁ ነው። ሸዋ (ለሚ)፣ ደብረማርቆስና ደብረታቦር፣ ቆቦ በርካታ ንፁሃን በከባድ መሳርያ አልቀዋል። ተቋማት ወድመዋል። የአርሶ አደሩ ቤትና እንሰሳት  በከባድ መሳርያ ሆን ተብሎ እየተመቱ ነው። ይህን የአማራ ሕዝብ  ከቁስል አድኖ የላካቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጭምር ያማረረ ነው። ብዙዎች መሳርያቸውን እየሸጡ ጠፍተዋል። ይህን የሚያደርጉ የዐብይ ቅጥረኞች ግን ሞልተዋል። መደበኛ መከላከያ ሆነው በጥላቻ ከተሰበኩት ባሻገር ቅጥረኛ ሰራዊት ተሰማርቷል።

አንዱና የመጀመርያው ከህወሓት ጋር በነበረው ጦርነት በመላ ኢትዮጵያ ታስረው የነበሩ የትግራይ ተወላጅ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩ ናቸው። አብይ ሲያስገርፋቸው ከርሞ አሁን በገንዘብ ገዝቶ አማራ ሕዝብ ላይ የዘር ፍጅት እንዲፈፅሙ እያደረገ ነው። ከባድ መሳርያ ልምድ ያላቸው እነዚህ ቅጥረኞች ናቸው!  በበቀል ንፁሃንን እንደፈለጉ እየጨፈጨፉ ነው።

የትግራይ ተወላጆች የመከላከያ ሰራዊት አባል የነበሩት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አልተፈቱም ነበር። አማራውን ለመውጋት ሲል ፈትቷቸዋል። የታሰሩበት ሁለት አመት ስራ ላይ እንደነበሩ ተቆጥሮ የሁለት አመት ደሞዝ ተከፍሏቸዋል። እድገት ተጠብቆላቸው ስራ ላይ እንደነበሩ ተደርጎ በሁለት አመት ያገኙት ነበር የተባለው ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል። ይህ በግልፅ ቅጥረኝነት ነው።

በቅርቡ ደግሞ ወደ ትግራይ 20 ሺህ የሚደርስ የመከላከያ ዩኒፎርምና ጫማ ተልኳል። ትህነግ ያሰናበታቸውንም ሆነ በካምፕ ያሉትን ወደ አማራ ክልል ሊያመጣ እንደሆነ ተገምቷል።

ከኦነግ ሸኔ ተማረኩ እያሉ የሚያሳዩትን፣ በየ ክልሉ ጡረታ የወጡትን ሳይቀር የአመታት ደሞዝ ከፍለው አማራ ክልል ላይ አሰማርተዋል።  እነ ሽመልስ የፈጠሩት የኦነግ ሸኔ ክንፍን እንደሚጠቀሙበት ይታወቃል።

የአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ጭፍጨፋ እየተፈፀመ ያለው በገንዘብ በተገዙ ወታደሮች ጭምር ነው። በየትኛውም ዓለም በገንዘብ የሚገዙ ወታደሮች ከተገኙ ያመጧቸዋል። ይህ በግልፅ ሆን ተብሎ ሕዝብን ለመምታት የተደረገ ዘመቻ ስለመሆኑ ማሳያ ነው።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በአፍሪካዊቷ ጋቦን ወታደሩ የምርጫ ውጤቱን አልቀበልም በማለት በመፈንቅለ መንግስት ወደ ስልጣን መጥቷል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በመቐለ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ‼️

በጦርነቱ ወቅት “የህወሓት አመራሮች ተጠቅመው ጣሉን” በሚል በመቐለ ከተማ ተቃቀወሞ ተቀሰቀስቅሷል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የአቡሽ ዘለቀ አልበም በአዲስ አበባ እንደይሸጥ መከልከሉን አርቲስቱ በማህበራዊ ሚዲያ ገፁ አሳወቀ‼️
የሚከተለው የአቡሽ ዘለቀ መልዕክት ነው 👇

"ሰላም ሰላም እንዴት ናችሁ! በትናትናው እለት እንደ አባቴ እወድሻለሁ የተሰኜው አዲሱ አልበሜ በአዲስ አበባ እንዳይሸጥ በፖሊስ ተከልክሏል እንዲህ ስለሆነ ለሀገሬ እና ለህዝቦቿ ያለኝ ፍቅር አይቀንስም እንደ አባቴ እወድሻለሁ።"

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የፖሊስ አዛዡ ተገደሉ❗❗

በትናንትናው ዕለት በደቡብ ጎንደር የፋርጣ ወርዳ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር፣አንድ መርማሪ ፖሊስ እና ትራፊክ ፖሊስ የነበሩ በድምሩ 3 የፖሊስ አባላት መገደላቸው ተረጋግጧል።
በአካባቢው ምንም አይነት ውጊያ የለም ያሉት ምንጮቹ ግድያው የተፈፀመው መስሪያቤታቸው አካባቢ ነው ብለዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል የሆኑት አቶ በቀለ በአሜሪካ ጥገኝነት መጠየቃቸው ተነግሯል።በውጭ አገር ሆነው የፓርቲውን ሥልጣን ይዘው መቀጠጣለቸው ጠቃሚ ስላልሆነ እራሳቸውን ከፓርቲው ለማግለል መወሰናቸውን ተናግረዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የወልቃይት-ጠገዴ ሕዝብ ወደኋላ ላይመለስ ነጻ ወጥቷል፤ ይሁን እንጂ ወደኋላ ሊመልሱን ለሚያስቡ የጨለማው ዘመን አበጋዞች አንበገርም፡፡ በግራ በቀኝ  ሲነሳብን የነበረውን ትንኮሳ እየመከትን ለዛሬው የልማት ፍሬ እንደበቃነው፤ ነገም ትርጉም በሚሰጥ መስዋዕትነታችን ነጻነታችን ተከብሮ፤ ልማታችን ሰፍቶ ይቀጥላል፡፡ የትኛውም የፖለቲካ ሴራ ቢደገስ፤ ዙሪያ ገባው በክህደት ቢሞላ እውነተኛና ፍትሐዊ ጥያቄ ያነገበው ጀግናው የወልቃይት-ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ሕዝብ ለጸሎትና ለተኩስ እንጂ ለጠላቶቹ አይንበረከክም!!

በመጨረሻም!

የወልቃይት-ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደርና ሕዝቡ ሰላሙንንና ልማቱን እኩል አስጠብቆ ለመጓዝ አደረጃጀቶቹን አስፍቶ በመስራት ላይ ነው፡፡ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ያለርስቱ ተፈጥሮ ካበጀለት ወንዙ ተከዜ አልፎ አይሻገርም፡፡

ወልቃይት ጠገዴ የትንሿ ኢትዮጵያ ተምሳሌት ሆኖ ሁሉም ብሄረሰቦች በላባቸው የሚኖሩበት የሰላም ምድር ሆኖ እንዲቀጥል ስትራቴጂዊ አመራርን የማረጋገጥ ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

ከዚህ ውጭ እንደ አማራነቱ ተፈጥሮ ካበጀለት የተከዜ ወሰኑ፤ አያት ቅድመ አያቶቹ ባወረሱት ርስቱ ላይ ተራምዶ ለወረራ ለሚመጣ የግዛት ተስፋፊ ኃይል ግን ተገቢውን የመከላከል ሥራ እንሰራለን፡፡

ሕዝባችን በሰላሙና በነጻነቱ ላይ ከመጡበት አይታገስም፣ ስለሆነም በጠንካራ የሥነ-ልቦና ዝግጅት አካባቢውን ነቅቶ መጠበቁን ይቀጥላል!!

በወልቃይት-ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የሚጠናከር እንጂ የሚፈርስ ተቋም የለም!

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፣ ከወልቃይት-ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ

Читать полностью…

Ethio 360 Media

"…አገዛዙ በስብሷል። በሽቋልም። ከእንግዲህ ወደተራ አሸባሪነት ነው የሚወርደው። እናም መጠንቀቁ አይከፋም። በዐማራ ክልሉ ጦርነት አገዛዙ ሁሉን ነገር አጥቷል። ከትግሬም ጋር ገጥሞ የሚያደርገው ብሽሽቅ ለራሱ ሰዎች የሚጥም አልሆነም። እናም አሁን ዐማሮች ከምንጊዜውም በላይ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በአስቸኳይ ንገር።

"…የፋኖን ስም በመላው ዓለም መንግሥታትና መገናኛ ብዙሃን ዘንድ በመልካም መነሣቱ፣ ባንክ ያለመዝረፉ፣ እንደትግሬና እንደ ኦሮሞ ነፃ አውጪዎች የገዛ ሴቶቹን የ80 ዓመት አሮጊት ጭምር አለመድፈሩ፣ ከኅብተሰቡ ቀምቶ ያለመብላቱ፣ ከአረመኔው መከላከያ ተብዬው የአቢይ ገረድ ራሱ የተለየ መሆኑ፣ ዲሲፒሊኑም ስላስመሰገነው አገዛዙን አብሽቆታል። ስለሆነም ፋኖን አሸባሪ ነው ለማሰኘት ከውሳኔ አልፎ ገዳይ ስኳድ አዘጋጅተው ወደ ትግበራ አምርተዋል።

"…የገዳይ ስኳዱ የመጀመሪያ ተግባር በዐማራ ክልል የተጀመረውን ጦርነት አስመልክቶ ብልፅግና በሚጠራቸው በትኛውም ስብሰባ ላይ የሚገኙ የዐማራ ሙሑራን፣ ባላሃብቶች፣ የእምነት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የክልሉ የጦር መኮንኖች፣ የራሱ የብልጽግና አመራሮች እንዲመቱና በፋኖ እንዲሳበብ ነው የወሰኑት። በስብሰባዎቹም ላይ በከባድ መሳሪያና በቦንብ የሚመታ ከ250 በላይ ተልዕኮ የተሰጣቸው የዐማራ ልዩ ኃይልን ልብስ የለበሱ ገዳዮች በባህርዳር ተዘጋጅተው እየተጠባበቁ ነው። ኦፕሬሽኑን ከፈጸሙ በኋላ ፋኖ ፈጸመው በማለት ዶክመንተሪ ለመሥራትም የኦሮሞ ጋዜጠኞች በስፍራው ተዘጋጅተዋል። የቦንብ ፍንዳታውን በኦሮሚያም ፈጽመው ዐማራ ነው ለማለት ወስነዋል።

"…በመጨረሻም በፋኖ ላይ ፖታሲየም ሰልፈር የተባለ ኬሚካል እየተጠቀሙ ስለሆነ ፋኖ የሚኪና ጉዞ ማቆም አለበት። ሸራ ወይም ፌስታል ለኪሚካል ርጭቱ መከላከያ መያዝ አለበት ተብላችኋል።

•ደውላችሁ አድርሷቸው።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አማራ ክልል‼

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የቆላ ደባ ከተማ ከንቲባ አቶ ከድር ዛሬ ካልታወቁ ሰዎች በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸው ተሰምቷል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

🌼🌼 ለአዲስ ዓመት ልዩ ቅናሽ🌼 🌼
⭐️  ከመገናኛ ወደ ኢንግሊዝ ኢንባሲ መንገድ ላይ  75% ግንባታው የተጠናቀቀ አፓርትመንት ይዘን ቀርበናል
👉በ30%  ቅድሚያ ክፍያ ብቻ ቤትዎን ይግዙ
👉ባለ 3 መኝታ ቤቶች
👉ካርታ የተዘጋጀላቸው
👉በ6 ዙር ረጋ ብለው የሚከፍሉበት አማራጭ
👉በቂ የመኪና ማቆሚያ
👉ጂምናዚየም
👉በ4 ቱም ማዕዘን ከተማውን የሚያስቃኝ ሰፊ ሰገነት
👉ደረጃቸውን የጠበቁ ሊፍቶች
👉አስተማማኝ ጀነሬተር
👉የከርሰ ምድር ውሀ
📞ይደውሉ ከጠበቁት በላይ ሆኖ ያገኙታል
0964784722

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የአክሲዮን ድርሻዎችን መግዛት  የሚያስገኛቸው ጥቅሞች
*
💰 ገንዘባችንን ከግሽበት ለመጠበቅ
ገንዘባችንን ባንክ ከማስቀምጥ አክሲዮኖችን በመግዛት ኢንቨስት ብናደርግ  ትርፍ እናገኛለን፡፡ ትርፉ ከዋጋ ግሽበቱ  በላይ ሥለሚሆን አክሲዮኖችን በመግዛት ሀብታችንን ከግሽበት/inflation መጠበቅ ያስችለናል፡፡
💰 አክሲዮን ሰርተፊኬታችንን እንደ ማስያዣ(ኮላተራል) በመጠቀም ብድር መውሰድ እንችላለን፡፡ በገንዘባችን ቀጥታ ኢንቨስት ከማድረግ በገንዘባችን አክሲዮን ገዝተን ሰርተፊኬቱን በማስያዝ ከባንክ ተበድረን ብንሰራ ትርፋችንን  ማሳደግ እንችላለን፡፡ በአክሲዮን ሰርተፍኬት ተበድረን ሥንሰራ ከኢንቨስትመንት ከምናገኘው ትርፍ በተጨማሪ አመታዊ ትርፍ ተካፋይ በመሆን ድርብ ትርፍ እናገኛለን፡፡
💰 የጡረታ ዘመናችንን ምቹ ለማድረግ
ባንኮች ኢንሹራንሶችና ሌሎች ግዙፍ ኩባንያዎች ላይ በወጣትነታችንና ጎልማሳነት ዘመናችን ኢንቨስት ማድረግ በጡረታ ዘመናችን በሌሎች ላይ የሚኖረንን ጥገኝነት እንድንቀንስ እንዲሁም ሥራ እየሰራን በነበረ ዘመናችን የነበረንን ምቾት ጠብቀን የተዋበ የጡረታ ዕድሜ እንድናሳልፍ ያግዘናል፡፡ 
💰 ለልጆቻችን አሥተማማኝ ጥሪት ለማስቀመጥ
ባንኮች ኢንሹራንሶችና ሌሎች ግዙፍ ኩባንያዎች ላይ በልጆቻችን ሥም ኢንቨስት በማድረግ ልጆቻችን 18 ዓመት ሲሞላቸው ያለምንም ችግር ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉና የራሳቸውን ሥራ ለመጀመር የሚያስችል ጥሪት ለማቆየት ይረዳል፡፡
💰 የገዙትን አክሲዮን በፈለጉት ጊዜ አትርፈው በመሸጥ ወደ ብር(ካሽ) መቀየር ይቻላል፡፡
💰 አክሲዮኑን በፈለጉት ጊዜ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ወደ ፈለጉት ሰው ማዛወር ይቻላል፡፡
💰 አክሲዮንን እንደማንኛውም ሐብት በውርስ ማስተላለፍ እንዲሁም በልጆች ስም አክሲዮን በመግዛት ለወደፊት ህይወታቸው መሠረት መጣል ይቻላል፡፡

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የቀድሞው የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ኃላፊ ኮሎኔል አለበል አማረ ከነአጃቢዎቻቸው ባለፈው ሐሙስ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቤተሰቦቻቸው ገለጹ። ሆኖም ያሉበትን ማወቅ እንዳልቻሉ አመልክተዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አትሌት ሲፈን ለ ኦነግ/ለኦሮሚያ ካልሆነ ለ ኢትዮጵያ የመሮጥ ፍላጎት የለኝም አለች።

ጉድ ነው ዘንድሮ መቼስ የማንሰማው የለም‼️

Читать полностью…
Subscribe to a channel