ሽመልስ አብዲሳ በኦሮሚኛ ከሰጠዉ መግለጫ ትርጉም የተወሰደ❗❗👇
“ያረጀች እና የአንድ ወገን የነበረች ኢትዮጵያን ዳግም ለመመለስ የሚፍጨረጨሩ አካላት ላይመለሱ ከነሀሳባቸው ተቀብረዋል”
ትናንት ➡️ ከጎንደር፣ ባህር ዳር፣ ኮምቦልቻ፣ ሸዋሮቢት እና አዋሽ አርባ ውጭ የማቆያ ቦታ የለም
ዛሬ ➡️ በአዲስ አበባ እና በአማራ ክልል የማቆያ ስፍራዎች አሉ
ከሰሞኑ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሲሰራጩ ከነበሩ ምስሎች ጀርባ ያለው እውነታ እዚሁ ጋር ይገኛል።
ቀሪውስ ?
የህዳሴው ግድብ የመጨረሻው ዲዛይን ግድቡ የሚይዘው የዉኃ መጠን 74 ቢሊየን ሜ³ ሲሆን አሁን ላይ በተጠናቀቀው አራተኛው ሙሌት ድረስ ግድቡ የያዘው 40 ቢሊየን ሜ³ (54%) ብቻ ነው።
4ተኛው ዙር ሙሌት መጠናቀቅን አስመልክቶ አብይ ባስተላለፈዉ የ "እንኳን ደስ ያላችሁ" መልእክት "የሕዳሴው ግድብን አራተኛና #የመጨረሻ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ሳበሥር በታላቅ ደስታ ነው" ብሏል።
ቀሪው 33 ቢሊዮን ሜ³ ( 46%) ላይ ምን ተወስኖ ነው አራተኛው ሙሌት #የመጨረሻ የተባለው ? ይህንን ያህል ከፍ ያለ ብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ ላይ የተሰጠን ይፋዊ ገለጻ "ተራ የአገላለጽ ስህተት" አድርጎ መውሰድ ይቻላል?
#ቀሪውስ ?
ግልጽ ማብራሪያ ሊሰጥበት ይገባል!!!
(አርክቴክ ዮሐንስ መኮንን)
በሰሜን ሸዋ ዞን በማጀቴ ከ30 ያላነሱ ንጹሐን ዜጎች በመከላከያ ኀይሉ የቤት ለቤት ፍተሻ እንደተገደሉ ተገለጸ‼️
የኢትዮጵያ መከላከያ ኀይል ወታደሮች፣ በዐማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ማጀቴ ከተማ፣ ባለፈው ሳምንት እሑድ ባካሔዱት የቤት ለቤት ፍተሻ፣ 30 የሚደርሱ ንጹሐን ዜጎችን እንደገደሉ፣ ሮይተርስ ስድስት የአካባቢ ነዋሪዎችን በእማኝነት ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ የፌዴራል ኀይሎቹ፣ ከአንድ ወር በላይ ለሚኾን ጊዜ፣ ከዐማራ ክልል ታጣቂዎች ጋራ በሚያደርጉት ፍልሚያ ጥቃት እንደደረሰባቸው በዘገባው ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል መንግሥት እና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቃል አቀባዮች፣ በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን እንዲሰጡ፣ ሮይተርስ ባለፈው ዐርብ ቢጠይቃቸውም ምላሽ አላገኘም።
ሊደርስባቸው የሚችለውን አጸፋ በመፍራት ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ የማጀቴ ከተማ ነዋሪ ለሮይተርስ ሲናገሩ፣ ሕይወታቸው ካለፉት ሰዎች መካከል፣ ሕፃናት እና አዛውንቶች ይገኙበታል፤ አንዳቸውም ግን በሚሊሺያ ቡድን ውስጥ እንዳልተሳተፉ አመልክተዋል።
ከነዋሪዎቹ አንዱ፣ ወታደሮቹ ወንድሙን ሲገድሉ እንደተመለከተ ገልጿል፡፡ ሌሎች ነዋሪዎች ደግሞ፣ ፍተሻው በቀጠለበት ወቅት የተኩስ ድምፅ እንደሰሙና የግድያውን አፈጻጸምም ከጎረቤቶቻቸው እንደተረዱ ተናግረዋል።
Reuters
"270,000 ሰራዊት አለን" ጌታቸው ረዳ❗❗
በፕሪቶሪያ ስምምነት መሠረት የትግራይ ኃይሎች ትጥቅ ፈትተዋል እየተባለ ሲነገር ከቆዬ በኋላ በትናንትናው እለት አቶ ጌታቸው ረዳ 270,000 ሠራዊት እንዳላቸው ከመግልጫቸው ሰምቻለሁ፡፡
ለምታውቁት ሰው ሁሉ አጋሩ! ልዩነቱ እንዲህ ነው! የአማራ እውነትና የገዥዎቹ ጭካኔ እንዲህ ነው!
በሀሰት ላወናበዱት ወገን ሁሉ አድርሱ! ጦርነቱ ይህን ይመስላል! የአማራ አርሶ አደር የተማረኩትን እንዳትነኩ ይላል። የገዥዎቹ ኃይል ንፁሃንን ይረሽናል። አደራ! ይህን ለምታውቁት ሰው ሁሉ አጋሩ!
የአማራ አርሶ አደር የተማረከ ወታደርም ምንም እንዳይደርስበት ይመክራል!
የመከላከያ ሰራዊቱ ተሰብስቦ ወጣቶችን ይጨፈጭፋል።
ጥቃቱ እንደቀጠለ ነው❗
በጋምቤላ ማጃንግ ዞን ጎደሬ ወረዳ በአማራ ተወላጆች ላይ ጥቃቱ ዛሬም እንደቀጠለ መሆኑን ገልፀውልናል። የሟቾች ቁጥር 7 ደርሷል ብለዋል።
ኮካኮላ የሸራተን የአዲስ አመት ዋዜማ ኮንሰርት ስፖንሰር መሰረዙን ገለፀ
ስፓንሰርሺፕ አጋርነት መሰረዛችንን ስለማሳወቅ
በአዲሱ ዓመት ዋዜማ በሸራተን አዲስ ሊከናወን የተሰናዳውን የሙዚቃ ድግስ ድርጅታችን ኮካ-ኮላ ቤቭሬጅስ አፍሪካ~ኢትዮጵያ ስፖንሰር አጋር የነበረ መሆኑ ይታወሳል።
ነገር ግን በልዩ ልዩ ምክንያቶች የስፓንሰርሺፕ አጋርነታችንን የሰረዝን መሆኑንና የፕሮግራሙ አጋር አለመሆናችንን እናሳውቃለን።
ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ አማ (ኮካ-ኮላ ቤቨሬጅስ አፍሪካ~ኢትዮጵያ)
ከጋምቤላ❗❗
በጋምቤላ ክልል ማጃንግ ዞን ጎደሬ ወረዳ ትናንት በአማራ ተወላጆች ላይ ብቻ በደረሰ ጥቃት እስካሁን አምስት ሰዎች ተገድለዋል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።
ዛሬም ተጨማሪ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀሩ ጠቅሰው ወደ አካባቢው የፀጥታ ሀይል እንዲሰማራ ጠይቀዋል።
"ሀገሬ በዚህ ሁኔታ እያለች የመዝፈን ሞራል የለኝም" ሲል አንጋፋው ድምፃዊ ነዋይ ደበበ ከተጋበዘበት የአዲስ አመት ኮንሰርት ራሱን እንዳገለለ ማስታወቁ ተሰምቷል።<<ሠላም እንዲመጣ የበኩላችንን ጥረት እናድርግ>> ማለቱም ታውቋል።
Читать полностью…በሰሜን ሸዋ ዞን ሰላድንጋይ ዙሪያ ትናንት ጨምሮ ሰሞኑን ከፍተኛ ውጊያ እንደነበር የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።
በዚህ ውጊያ በፋኖ በኩል የደረሰው ጉዳት ባይታወቅም በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች ላይ ግን ከባድ ሰብዓዊ ጉዳት መድረሱን የአይን እማኞች ገልፀዋል።
በፃድቃኔ ማሪያም የሚገኙ ፀበልተኞችም ገዳሙን ለቀው እንዲወጡ ፋኖ ትዕዛዝ አስተላልፏል ብለዋል።
#EHRC
አዋሽ አርባ ላይ ታስረው የሚገኙ አብዛኞቹ እስረኞች ለእስር የተዳረጉት #በብሔር ማንነታቸው ብቻ መሆኑን እንደሚያምኑ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለን ጨምሮ 5 የኮሚሽኑ ባለሙያዎች የሚገኙበት ቡድን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት በቁጥጥር ሥር ውለው አዋሽ አርባ አካባቢ በሚገኘው የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ ውስጥ ተይዘው የሚገኙትን ታሳሪዎች ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ጎብኝቷል።
እነዚህ ታሳሪዎች ፦
- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ፣
- የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለው፣
- የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ካሳ ተሻገር፤
- ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው፣ ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ፣ እና ቴዎድሮስ ዘርፉ፤
- የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባል አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ አቶ በለጠ ጌትነት፤
- በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በኃላፊነት ይሠሩ የነበሩት አቶ ከፋለ እሱባለውን ጨምሮ በአጠቃላይ 53 ወንድ እስረኞች ሲሆኑ ከአዲስ አበባ ከተማና ከአማራ ክልል የተለያዩ ቦታዎች በተለያየ ጊዜ ተይዘው ከነሐሴ 15 ቀን እስከ ነሐሴ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ አዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ የሚገኝ ጊዜያዊ / መደበኛ ያልሆነ ማቆያ ጣቢያ የተወሰዱ ናቸው፡፡
ኮሚሽኑ በተለመደው አሠራሩ መሠረት ታሳሪዎቹን ለብቻቸው አነጋግሯል፣ ቦታውን ጎብኝቷል እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸውን የፖሊስ ኃላፊዎች አነጋግሯል፡፡
የፖሊስ ኃላፊዎች ለኮሚሽኑ እንደገለጹት ፤ ታሳሪዎችን ወደዚህ ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያ ማምጣት ያስፈለገው አዲስ አበባ የሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ማቆያ ጣቢያ ላይ ከፍተኛ መጣበብ በመፈጠሩ መሆኑን ገልጸዋል።
ታሳሪዎች ምን አሉ ?
እጅግ አብዛኛዎቹ ታሳሪዎች ብሔራቸው #አማራ፣ እምነታቸው ኦርቶዶክስ ክርስቲያን መሆኑንና ለእስር የተዳረጉት ደግሞ #በብሔር ማንነታቸው ብቻ መሆኑን እንደሚያምኑ ገልጸዋል።
ከፊሎቹ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተያዙበትና ቤታቸው በተበረበረበት ወቅት በራሳቸውና በቤተሰብ አባል ላይ ድብደባ፣ ብሔር ተኮር ስድብ፣ ማጉላላት፣ ዛቻና ማስፈራራት እንደደረሰባቸው ሆኖም በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ከሆነ በኋላ የተፈጸመ ድብደባ ወይም አካላዊ ጥቃት አለመኖሩን አመልክተዋል።
ከፊሎቹ በተለይም ከአማራ ክልል ተይዘው የመጡ ሰዎች ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ ቤተሰቦቻቸው የት እንዳሉ እንኳን እንደማያውቁ አስረድተዋል።
ታሳሪዎቹ የአዋሽ አርባ አካባቢ እጅግ ከፍተኛ ሙቀት ያለው በመሆኑና ከአካባቢው የአየር ጠባይ እንዲሁም ቦታው የወታደራዊ ካምፕ እንጂ መደበኛ የተጠርጣሪዎች ማቆያ ስፍራ ስላልሆነ ለጤንነታቸው፣ ለደኀንነታቸውና ለሕይወታቸው ሥጋት እንዳላቸው፣ አልባሳትን ጨምሮ ከቤተስብ የሚፈልጉትን አቅርቦት ለማግኘት እንዳልቻሉ፣ ከፊሎቹ በሥራቸውም ሆነ በግል ሕይወታቸው ፈጽሞ በፖለቲካ ነክ ጉዳይ ተሳትፎ እንደሌሉና እንዴት ለእስር እንደበቁ መገረማቸውንና መደንገጣቸውን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ፤ ከፖሊስ ኃፊዎች ጋር ውይይት ያደረገ ሲሆን በእስር ወቅት ተፈጽመዋል ስለተባሉ የሥነ ምግባር ጥሰቶች ተገቢው ማጣራት እንዲደረግ፣ ታሳሪዎቹ ከቤተሰብ ለሚፈልጉት አቅርቦት አዲስ አበባ በሚገኘው የፖሊስ ቢሮ አማካኝነት እንዲመቻች፣ ከቤተስብ መገናኛ ስልክና ጉብኝት ለሚፈልጉም በአፋጣኝ እንደሚመቻች መግባባት ላይ ተደርሷል።
(ከኢሰመኮ የተላከልን መግለጫ ከላይ ተያይዟል)
" የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች ፈተናው በኦንላይን ይሰጣል (ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ) " - የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ‼️
ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን #በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች በ #ኦንላይን እንደሚሰጥ አሳውቋል።
ይህን ያሳወቁት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ናቸው።
ሚኒስትሩ ፤ በ2016 የትምህርት ዘመን አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በሁሉም የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንደሚሆን አሳውቀዋል።
ለዚህም ተግባራዊነት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ጠቁመዋል።
ፕ/ር ብርሃኑ ፤ በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ ጠቁመው የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች ፈተናው በኦንላይን እንደሚሰጥም ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ፤ ከአዲሱ የትምህርት ስርዓት ጋር በተያያዘ በመጽሐፍት ሕትመትና ስርጭት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ ነው በዋል።
በመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የመጽሐፍት እጥረት ማጋጠሙን የጠቆሙት ሚኒስትሩ ፤ ችግሩ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ እንዳያጋጥም ቀደም ብሎ ጨረታ በማውጣት መጽሐፍትን በወቅቱ ለማድረስ እየተሠራ ነው ብለዋል።
መጽሐፍት እስከ መስከረም ወር መጨረሻ ድረስ እንደሚቀርቡ የትምህርት ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡
tikvah
‹‹ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ግድያና በሴቶች ላይ የሚደርስ ፆታዊ ጥቃት ቀጥሏል ›› -ኢሰመጉ‼️
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ(ኢሰመጉ) ‹‹ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ማለትም ባህርዳር፣ መራዊ፣ ደምበጫ፣ አማኑኤል፣ ሉማሜ፣ ደብረማርቆስ፣ ፍኖተሰላም፣ ብቸና፣ ደብረታቦር፣ ወረታ፣ አዲስ ዘመን እና ሌሎችም አካባቢዎች ላይ ግድያ፣ እገታ፣ እስር፣ ዘረፋ እንዲሁም በሴቶች ላይ የሚደርስ ጾታዊ ጥቃት መቀጠሉን ›› ካሰባሰብሁት መረጃዎች ለመረዳት ችያለሁ ብሏል፡፡
‹‹ ይህ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ የሚደርስ ሲሆን በተለይ ሴቶችን ተጋላጭ ያደረገ መሆኑን፣ በተጨማሪም ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች እንቅስቃሴዎች የተገደቡ መሆናቸውንም ›› አክሏል፡፡
ጉባዔው ‹‹ በተዘረዘሩት ሁሉም ጉዳዮች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ስራን በመስራት አሕዛዊ መረጃዎችን የያዘ ዝርዝር ዘገባን እንደሚያዘጋጅ ›› ገልፆል፡፡
ኢሰመጉ ባስቀመጠው ምክረሃሳብ ‹‹ የፌደራልና የአማራ ክልል መንግስታት በአማራ ክልል በንጹሀን ላይ እየደረሰ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በቂ ትኩረት በመስጠት የሰዎች በህይወት የመኖር መብትን እንዲያከብሩና እንዲያስከብሩ ›› ጠይቋል፡፡
‹‹ በአማራ ክልል እየተስተዋለ ያለውን የንጹሃን እልቂት፣ የንብረት ውድመትና በአጠቃላይ የሰላም እጦት ከዚህ የከፋ ሁኔታ ላይ ከመድረሱ በፊት በጦርነት መፍትሄ ላይ መድረስ እንደማይቻል ታውቆ በመንግስት እና በታጣቂ ሀይሎች መካከል ውይይት በማድረግ ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጠው ›› አሳስቧል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ሰለዳ በሌላቸው መኪናዎች ጭምር በርካታ ሰዎች እየተወሰዱ እና ወደ አልታወቀ ቦታ እየተሰወሩ ነው ብሏል።
ጉባዔው መግለጫውን ሲያጠቃልል ‹‹ በመጨረሻም መንግስት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 አፈጻጸምን በቅርበት በመከታተል አዋጁን ያለአግባብ በስፋት በመተርጎም ለሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ምክንያት እንደይሆንና ስልጣንን አላግባብ ለመጠቀም በሮችን እንዳይከፍት ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር እንዲያደርግ ›› ጥሪውን አቅርቧል፡፡
ሸገር ሲቲ ገላን አካባቢ በሁለት የተለያዩ መጋዘኖች ከ10,000በ በላይ እስረኞች እንደሚገኙ ተሰምቷል።በተስቦና በኮሌራ የሰው ህይወት መጥፋቱ ተሰምቷል።ይህንን በተመለከተ ኢሰመጉ ትናንት በሰጠው መግለጫ የጅምላ እስርና እንግልት ሊቆም እንደሚገባ ጠይቋል።
Читать полностью…በአማራ ክልል የተቋረጠው የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲጀመር ከ300 በላይ የሚሆኑ አለምአቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጠየቁ❗❗
ከ300 በላይ የሚሆኑ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አባል የሆኑበት የ #KeepItOn ጥምረት እንዲሁም 48 ድርጅቶች በፈረሙት ጥሪ በአማራ ክልል የተቋረጠው የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲጀመር ጥያቄ ቀርቧል።
ከ105 ሀገራት የተወጣጡት ተሟጋች ድርጅቶች እንዲሁም ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገራት የተሳተፉት ፈራሚዎቹ፤ በአማራ ክልል በግጭት ምክንያት የተቋረጠው የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲጀመር ነው ለመንግስት ጥሪ ያቀረቡት።
"አክሰስ ናው" በመባል የሚታወቀው የዜጎች ሲቪል መብት ተከራካሪ ድርጅት ከሌሎች የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ጋር በመሆን በጉዳዩ ላይ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።
ተሟጋቾቹ በጥምረት ባወጡት የጋራ የአቋም መግለጫ በግጭት ወቅት የኢንተርኔት የአገልግሎትን ማቋረጥ ዜጎች አስፈላጊ መረጃን እንዳያገኙ በማድረግ የመረጃ ፍሰትን የሚገድብ እንደሆነ አሳውቀዋል።
በመግለጫው በአማራ ክልል ግጭቱ ከተጀመረበት ከነሀሴ ወር አንስቶ የኢንተርኔት አገልግሎት እንደተቋረጠ ተገልጿል።
የኢንተርኔት አገልግሎትን መዝጋት የዜጎችን መብት መጣስ እንደሆነ የገለፁት ተሟጋቾቹ በግጭት ወቅት የመረጃ ፍሰትን ለማደላደልና የኢንተርኔት አገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ መንግስት ከምንግዜውም በላይ ቁርጠኛ አቋም መያዝ እንዳለበት አሳስበዋል።
🌻🌻🌻 እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ! 🌻🌻🌻
አዲሱ ዓመት የሰላም፥ የደስታ ፥ የብርሀን ዓመት፤ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!
ከአዲስ አበባ እና ከአዲሱ ሸገር ሲቲ ፋኖ ናችሁ፣ፋኖን ትግፋላችሁ ተብለው በገላን ከግርብና ፅህፈት ቤቱ በስተቀኝ በኩል በጅምላ ታስረው በዚህ መልኩ ይታያል። የታሰሩበት ቦታ በጣም በመጨናነቁ መኝታ እንኳን በየተራ ነው የሚተኙት፣በዚህም የኮሌራ በሽታ ተከስቶ የሞቱም አሉ።
አሳዛኝ ነው።
በሰሜን ሸዋ ዞን ጅሁር እንዋሪ ዛሬም በከባድ መሳሪያ የታገዘ ውጊያ መኖሩን የመረጃ ምንጮቼ ገልፀዋል። መከላከያ ሰራዊት እንዋሪ ከተማ የገባ ሲሆን በነበረው ዉጊያ ከባድ መሳሪያ በነዋሪዎች ቤት ላይ አርፎ 9 ሰዎች ሞተዋል ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መኮይ እና መንዝ ግሼ አዋሳኝ ቦታ አፍላ ውጊያ አለ ብለዋል። በተለይ ቁንዲ ተራራ ላይ የከባድ መሳሪያ ድብደባ አለ ብለዋል።
ጌታቸው ረዳ የህወሓት አመራሮች አላሰሩኝም አሉ❗❗❗👇
ትናንት ከሰጡት መግለጫ 👇
መንግስት የማያውቀው እስር ቤቶች አሉ። የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ መንግሥት የማያውቃቸውን ማረሚያ ቤቶች በማቋቋም ከባድ ወንጀል እየሠሩ ያሉ እንዳሉም ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል። በትግራይ ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ አቶ ጌታቸው ረዳ በሰላማዊ መንገድ ህዝብን ለማሸበር ከባድ ወንጀል እየተፈፀመ ነው ብለዋል። ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ ሌብነት እና ዘረፋ በትግራይ መጠነ ሰፊ ነው ብለዋል። በተጨማሪም የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የህብረተሰቡን ፀጥታ ለማደፍረስ እና ሀብትና ንብረትን በሃይል ለመዝረፍ መንግስት የማያውቃቸውን ማረሚያ ቤቶች በማቋቋም ከፍተኛ ወንጀል እየሰሩ ያሉ እንዳሉ ተናግረዋል። ይሄን የሚፈፅሙት ደግሞ በደብረፂዎን እና በሞንጀሪኖ የሚመራ እንደሆነ ተጠቁሟል።
ጌታቸው ረዳ አክለውም የመዋቅር እንቅፋት እንደገጠማቸው እና በህወሃት አመራሮች እንቅፋት መስራት እንዳልቻሉ ገልጸዋል። በህወሓት አመራሮች እና በጌታቸው ረዳ መካከል ያለው ሽኩቻ ገሃድ የወጣ ይመስላል። የህወሓት አመራሮች ከዚህ በፊት ጌታቸው ረዳ የአብይ ተላላኪ ነው በማለት ሲያብለጠለጥሉት መክረማቸውን በተደጋጋሚ መዘገ ይታወሳል።
👉ዛሬ መቀሌ በታጣቂዎች ተጥለቅልቃለች፣እስሩ ቀጥሏል። ጌታቸው ረዳ ሁሉንም ነገር ያፈነዱት ይመስላል።
የፌደራሉ መንግሥቱ ጣልቃ ገብቶ ጌታቸው ረዳን ይታደግ ይሆን?? አብረን የምናየው ይሆናል።
በረኸት ወረዳ‼️
በሰሜን ሸዋ ዞን በረኸት ወረዳ መተህብላ ከተማ ትናንት ጠዋት በፋኖ እና በወረዳው የፀጥታ ሀይል ጋር ለአጭር ጊዜ የቆየ ከፍተኛ ተኩስ እንደነበር የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።
በዚህ ተኩስ የወረዳው የሰላም እና ፀጥታ ሃለፊን ጨምሮ ሚሊሻዎች ሞተዋል።
የወረዳው ዋና ከተማ የሆነችው መተህብላ ከተማ ከትናንት ጀምሮ በፋኖ ቁጥጥር ስር መሆኑን ከነዋሪዎቹ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
ተሰርዟል‼️ cancelled❗
በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል የሚዘጋጀው ኮንሰርት ተሰርዟል። ትኬት ሽያጭ እንዲቆም ተደርጓል። አዘጋጆቹ ዛሬ መግለጫ ይሰጣሉ!
በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ለሊቱን ከፍተኛ ተኩስ እንደነበር እና የወረዳው ወንጀል መርማሪ ፖሊስን ጨምሮ ሌሎች ፖሊሶች ተገድለዋል።
በአረርቲ ከተማ ዛሬ ምንም እንቅስቃሴ የሌለ ሲሆን በከተማዋ በርካታ የፋኖ አባላት ከተማውን እንደተቆጣጠሩ የመረጃ ምንጮቹ ገልፀዋል።
የማቀርበውን የሙዚቃ ስራ ሰርዤአለሁ‼️
#Ethiopia | እኔ ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ጳጉሜ 6 በሸራተን አዲስ ለአዲስ ዓመት ዋዜማ የሙዚቃ ስራዬን ለማቅረብ ተፈራርሜ የተዘጋጀሁ ቢሆንም ይህን ስራ በመሰረዜ የሚያስከፍለኝ ዋጋ ቢኖርም ከሁሉም በላይ በቃሏ የምመራላት ቤትክርስትያን ሀይማኖት አባቶቼን ትዕዛዝ በመቀበል የማቀርበውን የሙዚቃ ስራ ሰርዤአለሁ !
ለውድ አድናቂዎቼ እንዲሁም የፕሮግራሙ አዘጋጆች ይቅርታ እየጠየኩ በሌላ ዝግጅት እንደማስደስታችሁ እና እንደምንገናኝ ስገልፅላችሁ በታላቅ አክብሮት እና ምስጋና ነው!
ኩኩ ሰብስቤ
የድል ዜና ከሸዋ
"…በፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የቅርብ ረዳት፣ ከ28 በላይ መጻሕፍት በደረሱት በአርበኛ አሰግድ የሚመራው የሸዋ ፋኖ ዛሬ በዕለተ ሰንበት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን ልብስ አልብሰው ያሰማሩትን የኦሮሙማ ጦር 6:00 ሰዓት በፈጀ ውጊያ ደምስሶታል። አለቀ።
"…ጦርነቱ የተጀመረው ልክ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ሲሆን በሁለት ግምባር ላይ በጥብቅ ዲሲፒሊን በተመራ የውጊያ ስልት ከኦሮሙማው መከላከያ ምሽግ ድረስ በመሄድ ነው። አንደኛው ምሽግ ከማጀቴ በስተ ሰሜን ቁርቁር በምትባል ቦታ ላይ የነበረ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ማጀቴ ከተማ ዳሩ ላይ ወርልድ ቪዥን ከነበረበት በሰው ቁመት ልክ በተሠራ ምሽግ ውስጥ የነበረውን የጠላት ጦር ነው የደመሰሱት።
"…ከሳምንታት በፊት በወጣው የጦር ዕቅድ መሠረት፣ ቀደም ሲል ከነ መገናኛ ሬድዮአቸው በፋኖዎቹ ከተማረኩ የመከላከያ አመራሮች፣ በሌሎችም መንገዶች በተገኙ መረጃዎች መሰረት በማድረግ ቁርቁር እና ማጀቴ የነበረውን የአቢይ ብራኑ ጁላ ጦር ሌሊቱን ተጠግተው አድረው ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ሲሆን በተመሳሳይ ሰዓት ሁለቱም ቦታ የነበረውን ሁለት ሻለቃ ጦር ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ሲሆን ደምስሰው አውድመውታል። ብዙ ተተኳሽና የጦር መሣሪያም በእጃቸው አስገብተዋል።
"…በዚህ የጨሰው፣ ያበደው የብርሃኑ የምርኮኛው ጦር በከሚሴ፣ በአጣዬ፣ በመኮይ ያከማቸውን ከፍተኛ ጦር ወደ ማጀቴ ያንቀሳቀሰ ሲሆን ከጦሩም ጋር በልዩ ዞኑ የሚኖሩትን፣ ከአሩሲ፣ ከባሌ፣ ከጅማ፣ ከሃረርጌና የወለጋ አምጥቶ ያሰፈራቸውን ኦነጎች አሰልፎ በከባድ መሳሪያ እየታገዘ ወደ ማጀቴ ተንቀሳቅሷል። ተራራው ነደደ ነው የሚሉት ፋኖዎቹ።
"…ብስጩው የአቢይ ጦር እና ኦነጎቹ አሁን በዚህ ሰዓት ማርምድር የተባለች ከተማን እያነደዱ ሲሆን ዐማራ የተባለም ኗሪ እየረሸኑ ነው ተብሏል።
• ወይ ፍንከች…✊
አየር መንገድ ትልቁ መርህ ጥንቃቄ ነው።
ጀብደኝነት አያስሞግስም። የብዙዎችን ህይወት በእጁ ያለ አካል በሰው ህይወት
አይቆምርም። ሌሎቹ ያልደፈሩትን መድፈር ጀግና አያሰኝም። የአየር መንገዳችን ከአደጋ ነፃ የመሆን ሪከርድ ጥንቃቄ ያስገኘው ነው። የፋና ዜና በአለማቀፍ አቬይሺን መርህ ውርደትን ማቆለጳጰስ ነው‼
በሰሜን ሸዋ ዞን በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ ከማጀቴ ፋኖ ናችሁ ተብለው የፊጢኝ ታስረው መረሸናቸው ታውቋል። በዚህ ድርጊት ህዝቡ በመቆጣቱ ትናንት ተኩስ ተከፍቶ እንደነበር ታውቋል። የተረሸኑት ወጣቶች 4 ይሆናሉ ተብሏል።
ከማጀቴ ወደ መንዝ በሚያስወጣው መንገድ ትናንት ጀምሮ ውጊያ ያለ ሲሆን ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ጉዳት ደርሶባቸው ገደል ሲገቡ ማየታቸውን የአይን እማኞች ገልፀዋል።
እነ አቶ ክርስቲያን እስካሁን በትክክል ያሉበት እንደማይታወቅ ኢሰመጉ ገለፀ‼️
በአማራ ክልል እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ እንደ አስፈላጊነቱ በየትኛውም የአገሪቱ አካባቢ ተፈጻሚ ይሆናል የተባለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ተከትሎ በአዲስ አበባ በጅምላ ከታሰሩ የአማራ ተወላጆች መካከል የተሰወሩ እና ወደ አዋሽ አርባ የተወሰዱ ሰዎች እንዳሉ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) አስታውቋል።
ኢሰመጉ ከአስቸኳይ አዋጁ ጋር በተያያዘ በርካታ የጅምላ እስሮች እየተፈጸሙ እንደሆነ ትናንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። እየተፈጸሙ ያሉት እስሮች “የሕግ ሥነ ሥርዓት ያልተከተሉ እና አንዳንዶቹም አስገድዶ የመሰወር ባህርይ” እንዳላቸው ኢሰመጉ
በርካታ የታሳሪ ቤተሰቦች እንደነገሩት አስፍሯል።
በከተማዋ በአዲስ አበባ ፖሊስ እና በፌደራል ፖሊስ አንዳንዶቹም የሰሌዳ ቁጥር በሌላቸው መኪኖች አፋር ክልል ወደሚገኝ አዋሽ አርባ የተወሰዱ እንዳሉ ነው ከቤተሰቦች መረጃ የሰበሰበው። ኢሰመጉ የቤተሰቦቹን ቅሬታ አስመልክቶ የሚመለከታቸውን የመንግሥት አካላት በደብዳቤ ማብራሪያ ቢጠይቅም ምላሽ እንዳላገኘ ነው በመግለጫው ያካተተው።
ከእነዚህም መካከል ነሐሴ 04/2015 ዓ.ም. በፌደራል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር የዋለው ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ ወደ አዋሽ አርባ መወሰዱን ከቤተሰቦቹ ሰምቷል። ጋዜጠኛው ነሐሴ 15/ 2015 ዓ.ም ወደ አዋሽ አርባ መወሰዱንም ቤተሰቦቹ ከተለያዩ ምንጮች እንደሰሙ ነገር ግን ማረጋገጥም እንዳልቻሉ አስፍሯል።
ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ ሐምሌ 30/2015 ዓ.ም. በቁጥጥር ስር የዋለው የአልፋ ሚዲያ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን ባለቤት የሆነው ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ያለበት እንደማይታወቅ ተገልጿል። እንዲሁም አቶ ዳንኤል መላኩ የተባለ ግለሰብ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አካባቢ በሥራ ላይ እያለ ነሐሴ 15/2015 ዓ.ም. ሁለት ሰሌዳ በሌላቸው መኪናዎች በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ተወስዶ ያለበት እንደማይታወቅም አስፍሯል።
በተጨማሪም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ካሳ ተሻገር ያለመከሰስ መብታቸው እንዳልተነሳ እንዲሁም ያሉበትን ማወቅ እንዳልተቻለ ኢሰመጉ አስታውቋል።
የምክር ቤት አባላቱ ነሐሴ 15/2015 ዓ.ም. ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም፣ ፖሊስ ግለሰቦቹን አለማቅረቡን እና ያሉበት እንዳልታወቀ ነው ኢሰመጉ የገለጸው።
ኢሰመጉ በአማራ ክልል በመከላከያ እና በፋኖ መካከል እየተካሄደ ባለው ውግያ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እየደረሱ እንደሚገኝ በመግለጫው አካቷል።
በባሕር ዳር፣ መራዊ፣ ደምበጫ፣ አማኑኤል፣ ሉማሜ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ፍኖተ ሰላም፣ ብቸና፣ ደብረ ታቦር፣ ወረታ፣ አዲስ ዘመን እና ሌሎችም አካባቢዎች ላይ ግድያ፣ እገታ፣ እስር፣ ዘረፋ እንዲሁም በሴቶች ላይ የሚደርስ ጾታዊ ጥቃት ቀጥሏል ብሏል። በእነዚህ አካባቢዎች እንቅስቃሴ መገደቡን ያተተው መግለጫው ተጨማሪ የምርመራ ሥራ በማከናወን ዘርዘር ያለ ሪፖርት እንደሚያቀርብ ጠቁሟል።
ኢሰመጉ “በአማራ ክልል እየተስተዋለ ያለውን የንጹሃን እልቂት፣ የንብረት ውድመት እና በአጠቃላይ የሰላም እጦት ከዚህ የከፋ ሁኔታ ላይ ከመድረሱ በፊት በጦርነት መፍትሄ ላይ መድረስ እንደማይቻል ታውቆ በመንግሥት እና በፋኖ መካከል ውይይት በማድረግ ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጠው” ጠይቋል።
ሌላው ኢሰመጉ በመግለጫው ያካተተው ጉዳይ አዲስ የተመሠረተው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋር በተያያዘ እየተነሱ ያሉ የሰብዓዊ የመብት ጥሰቶችን ነው።
በጋሞ ዞን በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ቀደም ሲል በገበሬ ማኅበር ተከልሎ ሲተዳደር የቆየውን ቆላ ሻራ ቀበሌን ወደ አርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ለመከለል በሚል በተፈጠረ አለመግባባት ከነሐሴ 12/2015 ዓ.ም. ጀምሮ የፌደራል ፖሊስ፣ የአካባቢው ፖሊስ እና አድማ በታኝ ኃይል በጋራ ወደ ቀበሌው በመግባት በነዋሪዎች ላይ ተኩስ ከፍተው በርካታ ሰዎች መግደላቸው ሰፍሯል።
ኢሰመጉ በአዲስ አበባና በሌሎች አካባቢዎች በፀጥታ አካላት የሚፈጸሙ ሕግን ያልተከተሉ የጅምላ እስሮች፣ አስገድዶ የመሰወር ድርጊቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ እና የታሰሩ ሰዎች ያሉበት ስፍራ ይፋ እንዲደረግ ጠይቋል።
ዘንድሮ መቼስ የፋኖ ነገር ጉድ ነው
በፀሎት የተጀመረው ስብሰባ❗❗
ትናንት በቀን 25/2015 ዓ.ም በግብርና ሚኒስቴር የስብሰባ አዳራሽ ስብሰባ ተደርጎ የነበረ ሲሆን ሰብሳቢዎቹ ፕሮፌሰር እያሱ እና ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሳ ሲሆኑ ስብሰባው ደግሞ ከግብርና ሚኒስቴር ሰራተኞች ጋር ነው። ይህ ስብሰባ ከመጀመሩ በፊት ፀሎት ተደርጓል ተብሏል። ፀሎቱ ደግሞ👉 ልባችንን የሚጎተትተውን ጨለማ ይገፈፍ፣ሀገራችን በከፍታ ትብረር" በሚል ፀሎት ተደርጓል ብለዋል።
ይህ ከተደረገ በኋላ አሁን በሀገሪቱ የተከሰተው ችግር የድህረጦርነት እንደሆነ እና ጥያቄዎችን ፖለቲካዊ መነሻ በማድረግ የትጥቅ ትግል እንደተጀመረ ገልፀው። በትጥቅ ትግል ስልጣን እንደማይገኝ ከገለፁ በኋላ "ፋኖ አራት ኪሎ ከመጣና ስልጣን የሚይዝ ከሆነ ወደ ኬኒያ ሂደን የትጥቅ ትግል እንጀመራለን" የሚል ንግግር ዶ/ር ፍቅሩ ተናግሯል ብለዋል።
"... ፋኖ ተሳክቶለት ወደ ስልጣን ቢመጣ ኬንያ ሄደን እንታገላለን እንጅ ዝም ብለን አናይም፤ ካልሆነም ኢትዮጵያ እንደ ዩጎዝላቪያ ትሆናለች፤ ከእናንተ ከሰራተኞች ጋር ራሱ ሰላም ካልሰበካችሁ እንደ ደርግና ኢህአፓ እንደ መኢሶን እንተላለቃለን፡፡" ሲሉ ተደምጠዋል ብለዋል።