ኢኮኖሚያችን??
አለማቀፉ የኢኮኖሚክስ ባለሞያ Steve Hanke የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት inflation 48% በመሆን በታሪክ ያልታየ ዝቅጠት እንደገጠመው ገለፀ።
በአስቸኳይ ሊታረም የሚገባ‼️
አረመኔው ዐቢይ አሕመድ በፋኖ መሪዎች ላይ የድሮን ጥቃት የሚፈጽመው በፌስቡክና ዩቱብ የሚለቀቁ የፋኖ መሪዎች ፎቶዎች በሳተላይት ከሚያገኘው መረጃ ጋር በማገናዘብ መሆኑን ስንቶቻችን እናውቃለን?
የኦሮሙማው አረመኔያዊ አገዛዝ መሬት ላይ ስለሚደረገው ማናቸውም እንቅስቃሴ ከሳተላይት የሚያገኘው መረጃ ልክ በካሜራ እንደተነሳ ፎቶ ጥርት ብሎ የሚታይና የማናቸውንም ሰው ገጽታ መለየት የሚያስችል ጭምር ነው።
አረመኔው አገዛዝ ለእርድ የሚፈልጋቸውን የአማራ ሕዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች በድሮን ደፍጥጦ ለማንደድ የሚፈልገው ነገር ቢኖር የሚንቀሳቀሱበትን አካባቢና ገጽታቸውን የሚያሳይ የቅርብ ፎቶ ብቻ ነው። የፋኖ መሪዎች የሚንቀሳቀሱበትን አድራሻና ገጽታቸውን የሚያሳይ በተለይም የቅርብ ፎቶ ካገኘ በሳተላይት የሚያገኘውን የአርበኞቹን ምስል በፌስቡክና ዩቱብ ከሚለቀቁ የቅርብ ፎቶዎች ጋር በማገናዘብ የድሮን ጥቃት ይፈጽማል።
ባጭሩ የፋኖ መሪዎችና አብረዋቸው የተሰለፉ አርበኞች የቅርብም ይሁን የሩቅ፤ የቡድንም ይሁን የግል ፎቶዎች፤ የሚንቀሳቀሱበት የትግል አካባቢና የሸመቁበት ምሽግ መረጃ በፌስቡክና በዩቱብ መለቀቁ አረመኔው አገዛዝ በሚፈጽመው የድሮን ጥቃት እንዳይስታቸው ከማድረግ የዘለለ ፋይዳ የለውም።
ሆኖም ግን ይየሕዝብ የቁርጥ ቀን ልጆችን ገጽታ፣ አለባበስ፣ ስም፣ አድራሻ፣ ፎቶና ንግግር፤ ሰማዕት የኾኑትን አርበኞች ማንነትና ምንነት በፌስቡክና በዩቱብ ሲያሰራጩ መዋል ትግል የሚመስላቸው ፌስቡከሮችና ዩቱበሮች ድርጊታቸው ቆመንለታል ብለው የሚያስቡትን ሕዝብ እንጂ አረመኔውን አገዛዝ የሚጎዳ አለመኾኑ ገና የተገለጠላቸው አይመስልም። በሌላ አነጋገር የፋኖ መሪን ፎቶና የሚንስቀሳቀስበትን አካባቢ በፌስቡክና በዩቱብ የሚያሰራጩ ቢኖሩ ለአረመኔው ዐቢይ አሕመድ የድሮን እርድ እያቀረቡት መኾኑን ሊያውቁት ይገባል።
ይህን ማስታወሻ እንድጽፍ ያስገደደኝም አረመኔው አገዛዝ በደኅንነትና በስለላ መረቡ ሊያገኘውን የማይችለውን የፋኖ ስም፣ ማንነት፣ አድራሻ፣ መልክ፣ ንግግር፣ ወዘተ በፌስቡክና በዩቱብ እያሰጡ የሕዝብ የቁርጥ ቀን ልጆችን የእሳት ራት እንዲኾኑ እያደረጉና ሕዝባዊ ተጋድሎውን እየጎዱ የሚገኙት እነዚህ እየታገሉ እየመሰላቸው አውቀውም ይኹን ሳያውቁ ሕዝባቸውን ሲጎዱና አገዛዙን ሲጠቅሙ የሚውሉ ኃላፊነት የጎደላቸው ፌስቡከሮችና ዩቱበሮች በሕዝባዊ ተጋድሎ ላይ እያደረሱት ያለው ጉዳት ዝም ተብሎ ከማይታለፍበት ደረጃ ላይ በመድረሱ ነው።
(አቻምየለህ ታምሩ)
መስከረም 30‼️
የ ኦነግ ጦር እስከ መስከረም 30 የፋኖ መሪዎችን የመያዝ እና በተለያዩ ዘዴዎች የመበታተን ስራ ይሰራል ብሎ ዘመቻ መጀመራቸው ታውቋል።
ውጤቱን አብረን የምናየው ይሆናል።
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም‼️
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለምን ከኢትዮጵያ ወስደው በርካታ የአፍሪካ አገራት ያውለበልቡታል። የነፃነት ምልክት፣ የፓን አፍሪካኒዝም መለያ ነው! የጥቁር አርማ ነው!
ይህ ምልክት የሚጠላው ድሮ በፋሽስት ጣሊያን አሁን በኦሮሞ ብሔርተኞች ነው። የኦሮሞ ብሔርተኝነት በስሪቱ ፀረ አማራ ብቻ አይደለም። ፀረ ኢትዮጵያ ብቻ አይደለም። ከፓን አፍሪካም ተፃራሪ ነው። ፓን አፍሪካኒዝም አድዋን ብቻ ሳይሆን አጤ ምኒልክን አወድሶ፣ አንግሶ፣ የኢትዮጵያን ደማቅ ቀለም አርማው አድርጎ የሚነሳ አስተሳሰብ ነው።
አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ቀለሙን እያቃጠሉ የፓን አረብ (ግብፅ) መለያን ሲሰቅሉ አይግረማችሁ። ትንሽ ሊያስገርም የሚችለው ግብፅ ራሷ ይህን ያህል ደማቁን የኢትዮጵያ ቀለም የማትጠላው መሆኑ ነው። ሞክረው! ካይሮ ውስጥ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ አያሳስርም! የለበስከውን አውልቀው አያቃጥሉትም። ጣሊያን ውስጥ በነፃነት ታውለበልበዋለህ!
ይህ ምንም ያልተጨመረበት የጠራ፣ የተንጠራራ ሀቅ ነው! ልታስተባብል እንዳታገላብጠው! ራስክን ያምሃል!
ደሴ‼️
ደሴ ሰሞኑን ቤት ለቤት ፍተሻ እየተካሄደ ነው። በዚህም ከትናንት በስተያ ቧንቧ ውሃ አካባቢ ፍተሻ እያካሄዱ በነበሩ የፀጥታ አካላት ላይ በ ፋኖ ተዋጊዎች ከፍተኛ ጥቃት ተፈፅሞ በርካታ የፀጥታ ሀይሎች ሞተዋል።
በዚህ የተነሳ ፍተሻው እንዲቆም ተደርጓል ተብሏል።
ደራ‼️
15 ሰዎች ተገድለዋል‼️
በደራ ወረዳ ኦነግ ሸኔ የአማራ ተወላጆችን ከፋኖ ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል ትናንት ቆሮ በሚባለው መንደር ከ10 በላይ ቤቶችን በእሳት ማውደማቸውን ከአካባቢው ነዋሪዎች የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።
ሳላይሽ የሚባለው ከተማ ላይ እስካሁን በደረሰን መረጃ 6 እንዲሁም ሰለልኩላ የምትባለው ከተማ ላይ 9 ሰዎች ተገድለዋል።
ትናንት ይሄን ጥቃት ከፈፀሙ በኋላ ከተማዋን ለቀው መውጣታቸውን ጠቅሰው አሁንም ከፍተኛ ውጥረት አለ ሲሉ በስፍራው የሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል።
እሬቻን ካላከበራችሁ ማትሪክ አትፈተኑም‼️
አዲስአበባ ሰሚት ፍየል ቤት የሚገኘው በሻሌ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪዎችን ወደ ቡራዩ ሄዳችሁ እሬቻን ታከብራላችሁ ካለበለዚያ አስራ ሁለተኛ ክፍል ማትሪክ አትፈተኑም እያሉን ነው ብለዋል።
የፋኖ ተዋጊዎች ለኢትዮ-ቴሌኮም ጥሪ አቀረቡ‼️‼️
የፋኖ አባላት በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የኔትወርክ አገልግሎት ማቋረጡ ተቀባይነት እንደሌለው ገልፀው ኢትዮ ቴሌኮም ይሄን ነገር ካላስተካከለ በቴሌኮም ተቋማት ላይ እርምጃ ለመውሰድ እንገደዳለን ሲሉ ገልጸዋል።
ጎንደር ታች አርማጭሆ‼️
በማዕከላዊ ጎንደር ታች አርማጭሆ ዛሬም ውጊያ ቀጥሏል። የበርበር-ሰግ ቀበሌ ሊቀመንበር ለአካባቢው ፋኖች መረጃ ሰጥተሃል፣ ለስልጠና ትብብር አድርገሃል ተብሎ በመከላከያ ተረሽኗል።
ጎጎት ፓርቲ ከጉራጌ ዞን ወጥተው በሚመሰረቱ ልዩ ወረዳዎች የጉራጌዎች መብት እየተጣሰ ይገኛል አለ❗❗
ጎጎት ለጉራጌ አንድነትና ፍትህ ፓርቲ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በልዩ ወረዳ ምስረታ እና በወልቂጤ ወሰን ጉዳይ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ ከጉራጌ ዞን ወጥተው በሚመሰረቱ ልዩ ወረዳዎች የጉራጌዎች መብት እየተጣሰ ይገኛል ሲል ገልጿል።
ፓርቲው፤ ሕገ ወጥነትን በሕገ ወጥ መንገድ ለማረም አሳዛኝ የሕግ እና የመብት ጥሰት እየተፈጸመ እንደሚገኝም አስታውቋል፡፡
ለአዳዲስ አደረጃጀቶች በመርህ ደረጃ የተቀመጡ ጉዳዮች በአፈፃጸም ደረጃ በግልጽ እየተጣሱ እንደሚገኙም በመጥቀስ፤ ከጉራጌ ዞን ወጥተው በራሳቸው ልዩ ወረዳዎች እንዲዋቀሩ በተደረጉ አደረጃጀቶች ውስጥ የጉራጌዎች መብት በግልጽ መደፍጠጡን አመላክቷል፡፡
በዚህም “ቀቤና ልዩ ወረዳ በተባለው አደረጃጀት ብዙሃኑ ነዋሪዎች ጉራጌ ሆነው ሳለ ማንነታቸውን በወረዳው ስያሜ እና አመሰራረት ረገድ እንዲደበቅ በማድረግ ማንነት የመፋቅ ሥራ ተሰርቶባቸዋል።” ያለው ፓርቲው፤ በተመሳሳይ በማረቆ ልዩ ወረዳ የሚገኙ ጉራጌዎችም ይህ መርህ እና ሕግ ያልተከተለ አሰራር ከወዲሁ የግጭት መነሻ እየሆነ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
“በቀቤና እና በማረቆ ልዩ ወረዳዎች የተካለሉ ጉራጌዎች አዲሱን አደረጃጀት በግልጽ እየተቃወሙት ቢሆንም፤ በልዩ ወረዳዎች አወቃቀር፣ አሰያየም እና የስልጣን ክፍፍል ውስጥ ተሳትፎ እንዳያደርጉ ተደርገዋል።” ሲልም ገልጿል፡፡
በዚህም ጎጎት የክልሉም ሆነ ከክልሉ በታች የተዋቀሩ አደረጃጀቶች ሕዝባዊ ተቀባይነት አላቸው የላቸውም ለማለት፤ መጀመሪያ ነፃና ገለልተኛ ሕዝብ ውሳኔ መደረግ አለበት ብሎ እንደሚያምን አስታውቋል።
የአዳዲሶቹ ልዩ ወረዳዎች አሰያየም፣ አደረጃጀት፣ የማዕከላት ምርጫ እና ስያሜ እንዲሁም የስልጣን እና የሐብት ክፍፍል በውስጣቸው ያሉ ጉራጌዎችን ባገለለ መንገድ እየተፈጸመ መሆኑን ገልጿል፡፡
ስለሆነም በልዩ ወረዳዎቹ የተካለሉ ጉራጌዎች በአዳዲሶቹ አደረጃጀቶች ለመቀጠል፣ የራሳቸው አዲስ አደረጃጀት ለመፍጠር ወይም ከአጎራባች የጉራጌ ወረዳዎች ጋር ለመካለል ፍላጎታቸው በሕዝበ ውሳኔ እንዲያረጋግጡ ሕዝበ ውሳኔ እንዲደራጅላቸው ፓርቲው ጠይቋል፡፡
“የወልቂጤ ከተማ ወሰን ጉዳይ ሌለው መሰረታዊ ጉዳይ ነው።” ያለው ጎጎት ፓርቲ፤ “ከቀቤና ልዩ ወረዳ ይፋዊ ምስረታ ጎን ለጎን የልዩ ወረዳው እና ወልቂጤ ከተማ ወሰን የማስከበር ሥራ አሳሪ በሆነ ኹኔታ ማጠናቀቅ በኹለቱ አጎራባች ሕዝቦች መካከል ዘላቂ ሰላም እና ትብብር ለማስፈን ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡” ብሏል።
“መንግሥት አሁንም ሕዝብ እንዲያከብር እና እንዲያደምጥ የጠየቀው ፓርቲው፤ መንግሥት ለእነዚህ ሕዝባዊ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ መላውን የጉራጌ ሕዝብ ያሳተፈ ሰላማዊ የመብት ትግል ንቅናቄ ለማድረግ እንደሚገደድ አሳስቧል፡፡
ፓርቲው “የአዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታ ሂደት በፌደራሉም ሆነ በነባሩ ክልል ሕገ መንግሥታት አዲስ ክልል ለመመስረትም ሆነ የነባሩ ክልል ሕገ መንግሥት ለማሻሻል የተቀመጡ መስፈርቶች የማያሟላ ፍጹም የለየለት አምባገነናዊ ጨፍላቂነት የታየበት” መሆኑን ገልጿል።
የሰማዕታቱ የአባ ተክለ አብ እና የቀሲስ መሠረት ጸሎተ ፍትሐት በአዳማ ቦኩ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በአዳማ ዙሪያ ወረዳ ቤተ ክህነት በመካነ ቅዱሳን አርቱ ቅድስት አርሴማ በግፍ የተገደሉት የታላቁ የጸሎት አባት የአባ ተክለ አብ እና የቀሲስ መሠረት ጸሎተ ፍትሐት በቦኩ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ዛሬ ከቅዳሴ በኋላ ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ ቀሲስ መሠረት በቦኩ ቅዱስ ሚካኤል ፡ አባ ተክለ አብ ደግሞ በምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ሥርዓተ ቀብራቸው ይፈጸማል፡፡
የታገቱ ሁለት አገልጋዮችና ተጨማሪ በልዩ ልዩ ሥራ የሚተዳደሩ ግለሰቦች ግን እስካሁን አለመለቀቃቸውንና የት እንደሚገኙ እንደማይታወቅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የሰማዕታቱ በረከት አይለየን አሜን!
ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ ( አዳማ - ኢትዮጵያ)
መስከረም 25/2016 ዓ.ም
ከምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የሚተላለፍ
ያኔ "አርሶአደሩ እንዲያመርት በሚል ከትግራይ ወጥተናል።" ብለው ነበር። የአማራ አርሶአደር ግን እንዲያርስም፣ እንዲሰበስብም አልተፈለገም።
እንዲያውም አማራውን አስርበን፣ አደህይተን ነው መግዛት የምንችለው ብለው አምነዋል። ጦርነቱ ሕዝብ ላይ የታወጀ ነው የምንለው ያለ ምክንያት አይደለም። ጦርነቱ በቀጥታ ሕዝብ ላይ የታወጀ ነው!
አሁንም በሚጀምሩት ጦርነት የአማራ አርሶ አደርን ለመሰብሰብ የደረሰ ሰብል በከባድ መሳርያ እያጋዩ መቀጠል ፈልገዋል። ከዛም ሕዝብ መብቱን ሳይሆን የሚበላውን እርዳታ በመጠየቅ ይጠመዳል ብለው ያስባሉ። አማራው ግን ሌላ ነው ስነ ልቦናው።
"ከርሃብ ጦርነት ይሻላል" የሚል ሕዝብ ነው!
ሸኖ‼️
ሸኖ አካባቢ ትናንት የዕርስ በርስ ተኩስ ተከፍቶ እንደነበር እና በዚህ ተኩስ ጉዳት መድረሱን ኢትዮኒውስ ዘግቧል።
የተኩሱ መነሻ ደግሞ ለግዳጅ የመጡ የተወሰኑ የሰራዊት አባላት በመጥፋታቸው እንደሆነ እና እነሱን ፍለጋ አሰሳ በሚደረግበት ሰዓት አለመግባባት ተፈጥሮ የእርስ በርስ ተኩስ ተከፍቶ ሰብዓዊ ጉዳት መድረሱን ዘገባው ይጠቅሳል።
የጠፉት የሰራዊት አባላት ለሽንት ወርደው እረፍት ላይ ባሉበት ሰዓት ነው ተብሏል።
በሶዶ ወረዳ አሥር ቀበሌዎች በኦነግ ሸኔ ቁጥጥር ሥር መሆናቸው ተገለጸ‼️
በቅርቡ በተዋቀረው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ፤ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ የሚጠራውና በመንግሥት "ኦነግ ሸኔ" በሚል በአሸባሪነት የተፈረጀው ሃይል በሶዶ ወረዳ ሥር የሚገኙ አስር ቀበሌዎችን መቆጣጠሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡
ነዋሪዎቹ እንደገለጹት፤ "ኦነግ ሸኔ ባለፉት ኹለት ዓመታት በሶዶ ወረዳ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ወጣ ገባ እያለ ሲንቀሲቀስ የቆየ ቢሆንም፤ አሁን ላይ ግን በወረዳ ሥር የሚገኙ አስር ቀበሌዎችን ተቆጣጥሮ ግድያና ዘረፋ እየፈጸመ ነው።" ብለዋል፡፡
በታጣቂዎቹ ቁጥጥር ሥር ከሆኑት ቀበሌዎች መካከል ዱግዳ ገርዬ፣ ዱግዳ ጎሮ፣ ዱባ ጥሙጋ፣ አሽከዴ፣ አማውቴ ላልዬ፣ ሞረጌ፣ ሰመሮ ኤጀርሳ፣ በርበር፣ ቦኖ እንዲሁም አይገዶ የሚባሉት የሶዶ ወረዳ ቀበሌዎች የክልሉ መንግሥት የማይገባባቸውና የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የሚንቀሳቀሱባቸው መሆናቸውን ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
በአስቸኳይ ዐዋጁ የአዋሽ አርባ እስረኞች ደኅንነት እንደሚያሳስባቸው ቤተሰቦቻቸው ገለጹ‼️
ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር መጨረሻ በዐማራ ክልል ላይ ከተደነገገውና እንዳስፈላጊነቱ በሌሎች ቦታዎችም ተፈጻሚነት እንደሚኖረው በተገለጸው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ተይዘው በአዋሽ አርባ የታሰሩ ሰዎችን በአካል እንዳላገኟኛቸውና ደኅንነታቸው እንደሚያሳስባቸው፣ ቤተሰቦቻቸው ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ፡፡
አስተያየታቸውን ከሰጡን የታሳሪ ቤተሰቦች መካከል አንዳንዶቹ፣ ታሳሪ የቤተሰባቸውን አባል በስልክ እንዳገኙ ሲገልጹ፣ ሌሎቹ ደግሞ በስልክም አግኝተዋቸው እንደማያውቁ ተናግረዋል፡፡
ታሳሪዎቹ፣ ከአያያዛቸው አንስቶ በእስር ላይ ይደርስብናል ያሏቸውን በደሎች ለመቃወም፣ ዛሬ የረኀብ አድማ እንደሚጀምሩ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በማኅበራዊ ብዙኃን መገናኛ ተጋርቷል፡፡ ይህም ጭንቀት እንደፈጠረባቸው ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል፡፡
ከታሳሪ ጠበቆች አንዱ ሰሎሞን ገዛኽኝ፣ በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ምክንያት ታሳሪዎቹን ማግኘት ስላልተፈቀደላቸው፣ ስለ ረኀብ አድማው በቀጥታ መረጃ ማግኘት እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡ኢሰመኮ ጉዳዩን እንደሚከታተል አስታውቋል፡፡
አድማውንና የታሳሪ ቤተሰቦችን ቅሬታ አስመልክቶ፣ ከመንግሥት አካል ምላሽ እና አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የኢዜማ ሊቀ መንበር ዶር. ጫኔ ከበደ በቁጥጥር ሥር የዋሉት፣ “በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ መሠረት በኮማንድ ፖስቱ ተጠርጥረው እንደኾነ አረጋግጫለኹ፤” ሲል ፓርቲው አስታውቋል፡፡
VOA
ኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል‼️
የኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎችን በሚያዋስነው የባቢሌ አካባቢ፤ በሁለቱ ክልሎች የጸጥታ ኃይሎች መካከል መስከረም 7፤ 2016 ዓ.ም በተደረገ የተኩስ ልውውጥ፤ ቢያንስ ስድስት ሰዎች መገደላቸውን እና በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ። በተኩስ ልውውጡ ህይወታቸውን ያጡት ሰዎች በቆሎጂ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ የሚኖሩ እንደነበሩ ኮሚሽኑ ገልጿል።
መንግስታዊው የሰብዓዊ መብት ተቋም ይህን የገለጸው ዛሬ ሰኞ መስከረም 21፤ 2016 ባወጣው መግለጫ ነው። ኢሰመኮ በዚሁ መግለጫው በወቅቱ በነበረው የተኩስ ልውውጥ ከተፈናቃዮች በተጨማሪ በአካባቢው በሚኖሩ የሲቪል ሰዎች ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት መድረሱን ይፋ አድርጓል።
(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
በሀይቅ ከተማ የደፈጣ ጥቃት‼️
ትናንት በሀይቅ ከተማ አቅራቢያ ጃሪ በሚባል ቦታ የደፈጣ ጥቃት ተፈፅሞ በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።
ዛሬም በተመሳሳይ መርሳ ዙሪያ ኒኒ በር ላይ የደፈጣ ጥቃት ተፈፅሞ በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች እና ተሽከርካሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።
ተሽከርካሪዎቹ ከደሴ አቅጣጫ ወደ ወልዲያ ሲጓዙ ነው የደፈጣ ጥቃት የተፈፀመባቸው።
ወደ አዲስ አበባ መግባት ተከልክሏል‼️
ከሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ወደ አዲስ አበባ መግባት መከልከላቸውን ተሳፋሪዎች መናገራቸውን የተለያዮ ምንጮች ዘግበዋል።
ሰሜን ሸዋ‼️
በሰሜን ሸዋ ዞን ከ30 በላይ የመንግሥት ሰራተኞች ታስረዋል።
ታሳሪዎቹ ለአመራርነት ተመድበው አንቀበልም ያሉ፣ለፋኖ መረጃ ትሰጣላችሁ እንዲሁም ትደግፋላችሁ በሚል የተጠረጠሩ ናቸው ተብሏል።
በሰሜን ወሎ‼️
ከትናንት ጀምሮ በሰሜን ወሎ ዞን ግዳን፣ኩልመስክ እና ሙጃ ዛሬም ከፍተኛ ውጊያ እንዳለ ታውቋል። በእነዚህ አካባቢዎች የስልክ አገልግሎት ተቋርጧል።
ደቡብ ጎንደር‼️
በደቡብ ጎንደር በደራ ወረዳ አምባሳሌ ከተማ የፋኖ አባላት ገብተው በፖሊስ ጣቢያው ላይ ድንገተኛ ጥቃት ከፍተው ብዛት ያለው መሳሪያ ወስደዋል።
ይሄን ለማስቆም ተኩስ በከፈቱ የሚሊሻ አባላት ላይም ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል እርምጃም ተወስዶባቸዋል።
ወልዲያ‼️
ባለፈው ሳምንት ጎንደር በር አካባቢ በተፈፀመው የቦንብ ጥቃት ተጠርጥረው የነበሩ ታሳሪዎች ትናንት ለሊት በነበረ የተኩስ ልውውጥ እንዲያመልጡ ተደርጓል።
ተጠርጥረው ታስረው የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጭምር ነበሩ ተብሏል።