ethio360media | Unsorted

Telegram-канал ethio360media - Ethio 360 Media

37564

ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር !!!

Subscribe to a channel

Ethio 360 Media

አስተሳሰባችሁ አይፈቅድም ‼️

"አማራ ወደ አዲስ አበባ አይገባም። ኢትዮጵያ ግን በቀይ ባሕር በኩል መውጫ ትፈልጋለች"

"6 ሚሊዮን የአዲስ አበባ ሕዝብ ከኦሮሞ መሬት  የገፈርሳና ለገዳዲን ውሃ  እንዳይጠቀም ማድረግ እንችላለን።  ነገር ግን እንደ ኢትዮጵያ ድንበርም ባይኖረን ባሕር በቅርብ ርቀት እያየን ቀይ ባህርን  አለመጠቀም አንችልም።"

"አዲስ አበባ ላይ ልዩ ጥቅም እንፈልጋለን።
ቀይ ባሕር ግን የጋራችን ነው።"

"ህገ መንግስቱ አይሻሻልም የፈለገ መገንጠል ይችላል። ከኤርትራና ጅቡቲ ጋር ግን አንድ አገር እንሆናለን"

"አማራ ተስፋፊ፣ አሁን የተፈጠረውን ሁኔታ ሳይረዳ የአባቶቸ ግዛት የሚል ነፍጠኛ ነው። በምኒልክ ዘመን የነበረው ግዛት የኢትዮጵያ አካል ነው እያለ በብሔር ብሔረሰቦች ላይ መጫን ይፈልጋል። ነገር ግን በአክሱም ዘመን የነበሩ አባቶቻችን ቀይ ባሕርን ገዝተዋል። አሉላም ድንበራችን ነው ብሏል። አሁንም እኛ እናስመልሳለን።"

"የመድሃኒያለም ያለሽ" አለ ፋሲል ደሞዝ። በጣም ተጣረሳችሁ። ተጠራመሳችሁኮ።  የነፍጠኛ የምትሉትና የኦነግ ኃሳብ ተላተመባችሁ።  አልሆነላችሁም አንተ።

የባሕር በርም የአገር አንድነትም ስነ ልቦና ይጠይቃል። በበታችነት ስሜት ስትናጥ እየዋልክ አገራዊ እሳቤ መያዝ አትችልም። አስተሳሰብህ አይፈቅድም። የልዩ ጥቅም ነው አስተሳሰብም። ቀበሌያም። ደቡብን ወደ ቀበሌ ስትመትር ከርመህ ጅኦ ፖለቲክስ፣ እንደ ራሺያ መስፋት ያምርሃል? የት ታመጣዋለህ!

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በወልቂጤ ትናንት የጀመረው ግጭት ዛሬም ቀጥሏል‼️

ወልቂጤ ከተማ ላይ ዛሬም በቀጠለው ግጭት አንድ የፌደራል ፖሊስ ህይወት ቀጥፏል።
ትላንት በተቀሰቀሰው እና ዛሬ ጠዋት በቀጠለው ግጭት ፀጥታ ሲያስከብር የነበረ አንድ የፌደራል ፖሊስ ወልቂጤ ከተማ ውኃ ጽህፈት ቤት አካባቢ በታጣቂ የቀቤና ወጣቶች በጥይት ተመቶ ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለህክምና በተወሰደበት ሕይወቱ ማለፏ ታውቋል።

በተጨማሪም በጥይት እና በፌሮ ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች በሆስፒታሉ ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን የከተማው አቃቤ ህግ አቶ ነስሩ ከማል እና ኢንስፔክተር ኤሊያስ ለተጨማሪ ህክምና ወደ ቡታጀራ ሆስፒታል ተዘዋውረዋል።

አቶ ነስሩ እና ኢንስፔክተር ኤሊያስ በጥይት የተመቱ ሲሆን የዞን ግብርና ባልደረባ የሆኑት አቶ ገዛኸኝ በቀቤና ወጣቶች ልቡ በፌሮ ተመቶ በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቀዶ ጥገና እየተደረገለት መሆኑን ከሆስፒታሉ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ልዩ ኃይሉ ጥቃት እየተፈፀመባቸው ያሉትን የከተማዋ ዳርቻዎች በመተው በሰላም ስራውን በመስራት ላይ የነበረውን የከተማዋን ህዝብ በአስለቃሽ ጭስ ጥቃት መፈፀሙ የከተማዋን ነዋሪዎች ግራ አጋብቷል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የአማራው ቀይ ባሕር አራት ኪሎ ነው‼️
==========================

አብይ አህመድ፣ አማራው ወደ አራት ኪሎ ጉዞ ጀምሯል ሲባል ጊዜ "ወደዚህ አትምጡ። አብረን ወደ ቀይ ባሕር እንሂድ" እያለ ነው።

መንገዱ ሰፊ ነው። መተላለፍ ይቻላልኮ!😄

ለጊዜው የአማራ ቀይ ባሕር በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነት፣ እንደ ዜጋ የመቆጠር፣ ተዘዋውሮ የመስራት መብት ነው።

አሁን የአማራ የሕልውና ስጋት አብይ ነው።

አሁን ለአማራው ቀዳሚው ተግባር በሕይወት የመኖር እና ስርአተ መንግስቱን የመቀየር ነው።

በሕይወት መኖር ሲችል፣ ዋና ከተማው አዲስ አበባ መግባት ሲችል፣ እንደ ዜጋ መቆጠር ሲችል ከዛ ስለ ባሕርም ሆነ ውቅያኖስ እንደ አስፈላጊነቱ ከወገኖቹ ጋር ሊያስብበት ይችላል።

አማራ ገፈርሳና ለገዳዲ  ውሃ አታገኝም እየተባለ  የአብይን  የቀይ ባሕር የቀን ቅዠት አይቃዥም።
ቀይ ባህር ብቻውን ሄዶ መዋኘት ይችላል።

የ ኤርትራ መንግስት የ አማራን ትግል መደገፍ ማገዝ አለበት።

መልእክቱን ለ በሻሻው የፋራ አራዳ አድርሱለት‼️

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አጣዬ‼️

በሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ዙሪያ ይምሎ፡በርግቢ ፡መሀል ወንዝና አካባቢው በፋኖ እና መከላከያ ሠራዊት መካከል ውጊያ ተቀስቅሷል።

የውጊያው መነሻ በመከላከያ ሠራዊት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ያስከተለ የደፈጣ ጥቃት በመፈፀሙ ነው ተብሏል።

በውጊያው ምክንያት ከአጣዬ ወደ መንዝ መሃል ሜዳ የሚያስወጣው መንገድ ተዘግቷል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ምንጃር‼️

በምንጃር አረርቲ ከተማ ትላንት ሌሊት ላይ በመከላከያ ሰራዊት ላይ የደፈጣ ጥቃት ደርሷል።

በተለይ ከሰም በሚባለው ቦታ በተፈፀመው የደፈጣ ጥቃት በበርካታ የኦሮሙማ ሰራዊት ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በኢትዮጵያ አሁንም የዘር ማጥፋት ወንጀል ከፍተኛ ስጋት አለ ሲሉ #የመንግስታቱ ድርጅት ልዩ አማካሪ አስጠነቀቁ‼️

በፌደራል መንግስቱ ወታደሮች እና በሀገሪቱ በተለያዩ አከባቢዎች የሚገኙ ታጣቂዎች መካከል የቀጠለ ውጊይ እየተካሄደ መሆኑ በኢትዮጵያ አሁንም የዘር ማጥፋት እና ተያያዠ አሰቃቂ ወንጀሎች ስጋት ከፍተኛ ሁኔታ አጥልቷል ሲሉ የመንግስታቱ ድርጅት የዘር ማጥፋት መከላከል ልዩ አማካሪ #ዋይሪሙ ንደሪቱ አስጠነቀቁ።

ልዩ አማካሪው አሊስ ዋይሪሙ ንደሪቱ #በትግራይ፣ #አማራ፣ #አፋር እና #ኦሮምያ ስጋቱ ከፍተኛ መሆኑን እና የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመፈጸም አስቻይ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።

ከአመት በፊት የተፈረመው የሰላም ስምምነት ባመዛኙ አልተሳካም ማለት በሚቻልበት ደረጃ ላይ ይገኛል ብለዋል አማካሪዋ።

ከኢትዮጵያ እየተፈጸሙ ስላሉት ወንጀሎች የተመለከቱ የሚደርሱን ሪፖርቶች እጅግ የሚረብሹ ናቸው ሲሉ የገለጹት ልዩ አማካሪዋ በአፋጣኝ ሁኔታውን ለመከላከል እርምጃ ሊወሰድ ይገባዋል ብለዋል። አለም አቀፉ ማህበረሰብ በጉዳዩ ላይ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው ጥሪ ማቅረብ እወዳሉ ሲሉ ገልጸዋል።

እየደረሱን ካሉ ሪፖርቶች መካከል ሙሉ ቤተሰብ ግድያ የተፈጸመባቸው ይገኛሉ ያሉት አማካሪዋ ቤተሰቦች በሚወዷቸው ወገኖቻቸው ላይ የሚፈጸምን አሰቃቂ ተግባር እንዲመለከቱም ይደረጋል፣ በተጨማሪም ሙሉ መንደር ተፈናቅሎ ቤቱን ጥሎ እንዲሰደድ ይደረጋል ሲሉ እየተፈጸመ ስላለው ግፍ አስታውቀዋል።
አዲስ ስታንዳርድ (Amharic)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ጃማ እና ወረኢሉ‼️

ከትናንት በስተያ የጃማ እና የወረኢሉ የወረዳ እና የከተማ አመራሮች ለብልፅግና ስልጠና ወደ ድሬዳዋ ለመሄድ ጉዞ ሲጀምሩ በፋኖ መያዛቸውን ተከትሎ ሌሎች የዞን አመራሮች የአድማ ብተና እጀባ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል ተብሏል። ይሄ ሁኔታ በዞን አመራሮች ላይ ድንጋጤ መፍጠሩ ተሰምቷል። ስልጠናው ላይ በተጠቀሰው ጊዜ ለመድረስም ፈተና ሆኗል ተብሏል።

የተያዙትን አመራሮች ለማስለቀቅ በተደጋጋሚ የተኩስ ልውውጥ ቢደረግም እስካሁን አልተሳካም።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ደቡብ ወሎ‼️

ትናንት በደቡብ ወሎ ዞን ሳይንት ዴንሳ ከተማ ውስጥ የፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ በፋኖ አባላት ላይ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት እያደረጉ ባሉበት በፋኖ ተዋጊዎች ድንገተኛ ጥቃት ተፈፅሞ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

በጉዳቱም የወረዳው የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊ፣ የፖሊስ አስተባባሪ እና የሚሊሻ አስተባባሪው እና ሌሎች አባሎች ህይወታቸው አልፏል።

ጥቃቱ የተፈፀመው በፖሊስ ጣቢያው ተሰብስበው ስምሪት እየወሰዱ ባለበት ሰዓት ከቀኑ 8:30 ገደማ ነው ተብሏል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ምስራቅ ጠለምት‼️

በምስራቅ ጠለምት ፍየልውሃ አካባቢ ሰሞኑን በርካታ የህወሓት ታጣቂዎች መጠጋታቸው ታውቋል።

በደደቢት በኩል በጥቅሉ 4 አርሚ ሰራዊት ተጠግቷል ተብሏል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የአማራ ክልል የስልክ ጉዳይ‼️
መንግስት እውነት ለክልሉ ህዝብ አስቦ ነው??

የአማራ ክልል ስልክ ተቋርጦባቸው የነበሩ አካባቢዎች ዛሬ ተለቆላቸዋል።

የተለቀቀበት ዋነኛው ምክንያት ግን የፋኖ አመራሮች የት እንዳሉ ማወቅ ስላልቻለ ነው። በጠቅላላው አመራሮቹ ብቻ ሳይሆን የሌሎቹንም አባላት እንቅስቃሴ ለማወቅ እንዲመቸው ነው።

ስለዚህ የፋኖ አባላት ስልክ ከመያዝ እና ከመጠቀም መታቀብ አለባቸው።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በእስራኤል እና በፍልስጤም ሃማስ መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት እየተባባሰ መጥቷል።

ሀገራት የተለያዩ አቋማቸውን እያንፀባረቁ ይገኛሉ።

#ኢራን ፍልስጤም እና እየሩሳሌም ነፃ እስኪወጡ " ከፍልስጤም ተዋጊዎች ጎን ነኝ " ብላለች። #አሜሪካ በበኩሏ ከእስራኤል ጎን እንደሆነች ገልጻ የማያወላዳ ድጋፏን እንደምታደርግ አሳውቃለች።

የሁለቱ ሀገራት ጎረቤቶች ሁኔታውን በእንክሮ እየተከታተሉ በተጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ።

ይህ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ ዓለም አቀፍ ይዞታን ሳይዝ እንደማይቀር ተሰግቷል።

ከመሸ የተሰሙ አዳዲስ መረጃዎች ምንድናቸው ?

- እስራኤል ጋዛ ላይ እየወሰደች ባለው የአፀፋ እርምጃ 232 ፍልስጤማውያን ሲገደሉ፣ 1697 ቆስለዋል ፤ በርካቶች ለህይወታቸውን የሚያሰጋ ጉዳት ላይ ናቸው።

- ሃማስ ባካሄደው ወታደራዊ ኦፕሬሽን የተገደሉ እስራኤላውያን ቁጥር ወደ 200 ማሻቀቡ ተሰምቷል።

- እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ውስጥ የኃይል አቅርቦት በማቋረጧ ሆስፒታሎች ተጎጂዎችን ለማከም እየተፈተኑ ይገኛሉ ተብሏል። በጋዛ ኤሌክትሪክ እንዲቋረጥ ያዘዘው የእስራኤል ኢነርጂ ሚኒስቴር ነው።

- ፍልስጤም ፤ አንድ የ13 ዓመት ልጅን ጨምሮ 4 ፍልስጤማውያን በ " ዌስት ባንክ ' በእስራኤል ወታደሮች መገደላቸውን አሳውቃለች።

- የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላ ኻሚኒ አማካሪ ያህያ ራሂም ሳፋቪ " የፍልስጤም ተዋጊዎች በእስራኤል ላይ ከዓመታት በኋላ ትልቁን ጥቃት በማድረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ " ብለዋል።  " የፍልስጤም ተዋጊዎችን እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን። " ያሉት አማካሪው " ፍልስጤም እና እየሩሳሌም ነፃ እስኪወጡ ድረስ ከፍልስጤም ተዋጊዎች ጎን እንቆማለን። " ብለዋል። ኢራን የሃማስን ኦፕሬሽን " የሚያኮራ " ብላለች።

- ሃማስ በእስራኤል ላይ ከፈትኩ ያለውን ኦፕሬሽን ተከትሎ ከኢራን፣ ቴህራን ከፍተኛ የሆነ ደስታን የሚገልጹ ቪድዮዎች ወጥተዋል። በቪድዮዎቹ ቴህራን ውስጥ ርችት ሲተኮስ እና ሰዎች ደስታቸውን ሲገልጹ ይታያል (ቪድዮ ከላይ ተያይዟል)።

- አሜሪካ በዚህ ወቅት ከእስራኤል መንግሥት እና ህዝብ ጋር መሆኗን በመግለፅ የማያወላዳ ድጋፏን እንደምታደርግ አሳውቃለች። የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ተኩስ እንዲቆም ጠይቃለች። ቱርክ በንፁሃን ሞት ማዘኗን ገልጻ ግጭቱ ወደ ቀጠናው ሳይስፋፋ እንዲበርድ ድጋፏን እንደምታደርግ አሳውቃለች።

- NATO አጋሬ ናት ባለው እስራኤል ላይ የተፈፀመው የአሸባሪዎች ጥቃት መሆኑን ገልጾ ከተጎጂዎች ጋር እንደሚቆም እስራኤልን እራሷን የመከላከል መብት እንዳላት ገልጿል።

- የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ የፍልስጤም ህዝብ ከ " ሰፋሪዎች እና ወራሪ ወታደሮች ሽብር " እራሱን የመከላከል መብት አለው ብለዋል።

- የእስራኤል ትምህርት ሚኒስቴር ነገ በመላው ሀገሪቱ ትምህርት እንዲዘጋ መወሰኑ ታውቋል።

በእስራኤል እና ሃማስ መካከል ወታደራዊ ግጭቱ የተነሳው ሃማስ ድንገተኛ እና ባለፉት በርካታ አመታት ታይቶ የማይታወቅ የተቀናጀ ኦፕሬሽን እስራኤል ላይ ከጀመረ በኃላ ነው።

ሃማስ ጦርነቱ " ከወራሪ ጋር የሚደረግ ጦርነት ነው " ብሏል። ፍልስጤማውያን ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ለደረሰባቸው ግፍ ሁሉ ምላሽ ነው ሲልም ገልጿል።

የእስራኤል ሀገር መከላከያ ሚንስቴር " ሃማስ ከባድ ስህተት ሰርቷል ፤ ለዚህም የከፋ ዋጋ እንደሚከፍል እና ለውጤቱም ሙሉ ኃላፊነቱን ይወስዳል " ካለ በኃላ የአየር ጥቃቶችን ጨምሮ የአፀፋ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ጎጃም‼️

በአባይ መነሻ መሆነችሁ ሰከላ አካባቢ ከፍተኛ ውጊያ የተኩስ ልውውጥ እንዳለ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

"…ሰላም ዘመዴ እንዴት ነህ…? ትናንት በሰጠንህ መረጃ መሠረት ባጫ ደበሌና አበባው ታደሰ ተያይዘው ወጡ ያልንህ እውነት ነው። አበባውን ግን ዛሬ ከአቶ ተመስገን ጥሩነህ ጋር ባልደረቦቻችን ባህርዳር ላይ እንዳዩአቸው ሲናገሩ ተደምጧል።

"…በተረፈ ዛሬ ይልማ መርዳሳ፣ ባጫ ደበሌ እና ሺመልስ አብዲሳ በብርሃኑ ጁላ ቢሮ ስብሰባ ላይ ውለዋል። በፋኖ ላይ ለማሳበብ ሲሉ ኢሬቻ ላይ ትንሽ ግርግር ሊፈጥሩ ሳያስቡ አልቀሩም። እንዲያም ሆኖ ባትሪያቸው አልቋል። ጄል ተስፋዬ አያሌውም ከሄደበት ከዱባይ ተመልሶ ዛሬ ሥራ ጀምሯል። ይሄ ማለት ይህችን 3ቀን ሃገር ምድሩን ሕዝቡን በኢሬቻ ወሬ ጠምደው እነሱ ግን በዐማራ ክልል ላይ ከድሮን ባሻገር የአየር ጥቃት ጭምር ሊኖር ስለሚችል ዐማራ ጥንቃቄ ያደርግ ዘንድ መልእክት አስተላልፍልን።

"…የቄሶቹን መታረድ ጨምሮ አዳዲስ ዘግናኝ፣ ዘግናኝ አጀንዳ ሁሉ ሊፈጥሩ ይችላሉ። ወያኔን ደብረዘይት እሬቻ ላይ በጥብጠው ከኦሮሞ ጋር እንደለያዩዋት አሁንም ኢሬቻ ላይ ያንኑ መንገድ ሊደግሙት ይችላሉ። እናም ስለዚህ በኢሬቻም ጉዳይ ሕዝቡ በሰላም ያሳልፍ ዘንድ ምክንያት ያሳጣቸው። አዳዲስ አጀንዳም ፈጥረው የሚያስጮሁት በእንዳንተ ተሰሚነት ባለው ሰው በኩል ነውና አታጯጩሁት። እንደ ሱሌማን መታፈን ዓይነቱ ዜና በአንተ ፔጅ መዘገብ ነበረበት ብለን አናምን። ካጠፋን ግን ለመታረም ዝግጁ ነን ጓድ… በማለት ተሰነባብተናል።

"…ሌሎች ወፎቼ ደግሞ እንዲህ ብለዋል። ዘመዴ ከትናንት ጀምሮ ቁጥራቸው እጅግ ብዙ የሆኑ በሲቃ እና በጣር የተጀቡ፣ በደም የተነከሩም በሚዘገንን ሁኔታ አካላቸው የተቆራረጡ ወታደሮች በጦር ኃይሎች ሆስፒታል እየተራገፉ ነው። "ፋኖ የት እንዳለ ሳናውቅ በ15 ደቂቃ 1ክፍለ ጦር ይደመሰሳል። በቃ ሠራዊቱ እንኳን ሊወጋ ከመኪና መውረድ አለመውረዱን እርግጠኛ አይደለም።

•እህዕ…
(ዘመድኩን በቀለ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ሰሜን ሸዋ‼️

በሰሜን ሸዋ ዞን አንኮበር ወረዳ አልዩአምባ ዙሪያ ትናንት ጀምሮ ከፍተኛ ውጊያ መኖሩን የደረሰን መረጃ ይጠቁማል። ዛሬም የከባድ መሳሪያ ተኩስ ይሰማል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

"ሱሉልታ ከተማ  9 ሰዎች በሸኔ ታገቱ፣ለእያንዳንዱ ታጋች 300 ሺሕ ብር ተጠይቋል።" ነዋሪዎች

በኦሮሚያ ክልል አዲስ በተዋቀረው ሸገር ከተማ ሱሉልታ ክፍለ ከተማ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው እና በመንግሥት “ኦነግ ሸኔ” ተብሎ በአሸባሪነት የተፈረጀው ታጣቂ ቡድን፤ ከሱሉልታ ከተማ 9 ሰዎችን አፍኖ መውሰዱን የአካባው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

ታጣቂ ቡድኑ ድርጊቱን የፈጸመው ማክሰኞ መስከረም 22/2016 በከተማ መስተዳድሩ በተለምዶ አዲሱ ኬላ ወጥም ቆዳ ፋብሪካ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እንደሆነ ነዋሪዎቹ አውስተዋል፡፡

ታጣቂ ቡድኑ ወደ ስፍራ ያቀናው መስከረም 22 ለ23 አጥቢያ ሌሊት ስድስት ሰዓት አካባቢ እንደሆነ የገለጹት ነዋሪዎቹ፤ እስካሁን ድረስ ቁጥራቸው 9 መሆኑ የተረጋገጠ ሰዎችን ወደ ቤታቸው ዘልቆ በመግባት አፍኖ መውሰዱን አስረድተዋል፡፡

በሰዓቱ በአካባው ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበርም በመግለጽ፤ ይሁንና የታፈኑትን ሰዎች ማስጣል እንዳልተቻለ ገልጸዋል፡፡

ለነዚሁ ለተወሰዱ ሰዎች ለእያንዳንዳቸው 300 ሺሕ ብር መጠየቃቸውን እና ቤተሰብ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እንዳሉ የአካባቢው ነዋሪዎች አውስተዋል፡፡
    
(አዲስ ማለዳ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ደቡብ ጎንደር‼️

በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ክምር ድንጋይ በሚባል አካባቢ ሲሰለጥኑ የነበሩ የሚሊሻ አባላት ትናንት አብዛኞቹ በፋኖ ተወስደው የነበረ ሲሆን መሳሪያቸውን ለፋኖ አባላት ካስረከቡ በኋላ ዛሬ አብዛኞቹ ተለቀዋል ተብሏል።

በተኩስ ልውውጥ ደግሞ ሶስት የሚሊሻ አባላት ተሰውተዋል ተብሏል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ባህር ዳር ፈለገህይወት ሆስፒታል‼️

በባህር ዳር የሚገኘው ፈለገህይወት ሆስፒታል የጦር ካምፕ ሆነ።

በባህር ዳር የሚገኘው ፈለገህይወት ሆስፒታል ውስጥ የሚገኙ ፅኑ ታካሚዎችን እና የሆስፒታሉ ሰራተኞችን በማስወጣት የአገዛዙ ሰራዊት ሆስፒታሉን ሙሉ በሙሉ የጦር ካምፕ አድርጎታል።

በሆስፒታሉ የነበሩ ወጣት ታካሚዎችን ፋኖ ናችሁ በማለት በአገዛዙ ሰራዊት ተረሽነዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

"…እስራኤል እየጠየቀች ያለው በሃማስ ድንገተኛ ጥቃት የተፈጸመብኝን ጭፍጨፋ እንዴት ታየዋለህ ነው። ተንፍስ፣ መሃል ሰፋሪ አትሁን ነው። አባው ደግሞ የወሃቢ እስላም ስለሆነ ጨንቆታል። ጨንቆትም አልቀረም አጀንዳ ለማስቀየር ወደ ቀይ ባሕር ካልዘመትኩኝ ሞቼ እገኛለሁ እያለ ነው።

"…ህወሓትም አብሬህ እዘምታለሁ እያለችው ነው። አቢይ አሕመድ ከቀይ ባሕር በኋላ ወልቃይት እና ራያን አስረክብሻለሁ ተብላ በኦሮሙማው ቃል የተገባላት ህወሓትም አቢይ አሕመድ ያለበሳትን የመከላከያ ሠራዊት ዩኒፎርም እና ፈረሰ የተባለውን የዐማራ ልዩ ኃይል ዩኒፎርም ለብሳ በልብስ ዐማራ እና የኢትዮጵያ መከላከያ በደም እና በማንነት ትግሬ፣ በዓላማ ገንጣይ፣ በሰራዊት ቲዲኤፍ ሆና አርሚ 17 የተቧለ ሟችና ጉንድሽ ሊሆን የተዘጋጀ ሠራዊት ሰብስባ ማይ አይኒ የተባለ ሥፍራ አከማችታለች። አይ ትግሬ ሞኙ…

"…እስራኤልን እንዳይደግፍ ዓረቦቹም፣ ኦነጎቹና ስልጤዎችም አይምሩትም። ዓረቦቹን እንዳይደግፍ እስራኤል ብቻዋን አይደለችም። የጨነቀለት ነው የመጣው በአቢይ አሕመድ ቤት።

"…ዐማራ ግን ዕድለኛ የሆነ ፍጥረት ነው። ይሄን የደነበረ እብድ የሚመራው ግራ የተገባ የኦሮሞ ሠራዊት ይከካዋል።

"…መልአከ ሞት አቢይ ሆይ ተናገር… የኢትዮጵያ ትንሣኤዋ አብሳሪ ዐማራ ሆይ ወጥር። ቀይ ባሕር አቢይና ሠራዊቱ ለኢሬቻ በዓል ሂደው ይስገዱበት፣ አንተ ግን መጀመሪያ ህልውናህን አስቀድም።

• አቢይ ሆይ አቋምህን ለአረቡም ሆነ ለእስራኤል ግለጽ … ትግሬ ሆይ ዳግም ማቅ ለመልበስ አትጣደፍ… ዐማራ ሆይ ለህልውናህ ስትል የዚህን መልአከ ሞት ሠራዊት እንደየአመጣጡ… ልክ እንደ ቡልጋው፣ እንደ ምንጃር እንደበረከት፣ ልክ እንደ ጎጃም አዴቱ መክት… አንክት…💪🏿✊💪
(ዘመድኩን በቀለ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ደቡብ ወሎ‼️

በደቡብ ወሎ አማራ ሳይንት ወረዳ ዴንሳ ባሳለፍነው ማክሰኞ በፖሊስ አባላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ያስከተለ የደፈጣ ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ እስከዛሬ ድረስ ከባድ ውጊያ እየተደረገ ነው።

መከላከያ ሰራዊት ከዴንሳ ወጥቷል። በአካባቢው ትናንት ጀምሮ የኔትወርክ አገልግሎት ተቋርጧል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ደብረታቦር‼️

በደቡብ ጎንደር ደብታቦር ከተማ የእቴጌ ጣይቱ ክፍለከተማ ምሽት አካባቢ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር እና በዚህ የተኩስ ልውውጥ የክፍለከተማው የሚሊሻ ፅህፈት ቤት ሃላፊ መሞቱ ታውቋል።

በዚህ የተነሳ በደብረታቦር ከተማ ውጥረት እንዳለ ታውቋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አቶ አሰማኸኝ አስረስ ከሀገር መዉጣታቸው ተሰማ‼️
#Ethiopia የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና የቋሚ ኮሚቴዉ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አሰማኸኝ አስረስ ከሀገር መዉጣታቸዉን አስታወቁ።

የአማራ ክልል ኮምኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ ሆነዉ ያገለገሉት አቶ አሰማኸኝ አስረስ  በአማራ ክልል ከተፈጠረዉ ክስተት ጋር ተያይዞ  የወጣዉ የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት  በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በሚፀድቅበት ጊዜ አለመገኘታቸዉን የገለፁ ሲሆን በአሁኑ ሰዐትም ክልሉ ካለበት ነባራዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ  መንግስት ጥቃት ወይም እስር ሊያደርስባቸዉ እንደሆነ በመስጋት እና እኔም ያገለገልኩት ስርዐት ሀገር እያፈረሰ ነዉ ብለዉ በማመናቸው ምክንያት ከሀገር ለመሰደድ መገደዳቸዉን ለበይነ መረብ ሚዲያዎች በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

አመራሩ በአማራ ክልል በአሁን ሰዐት መንግስት የለም ያሉ ሲሆን ህዝቡም የኔትወርክን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን በማያገኝበት ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረዋል።
Roha

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የሰሜን ሸዋ ዞን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ “ከሰሞኑ ያወጣሁትን ዘገባ ከበላይ አካል በደረሰብኝ ጫና አንስቻለሁ” አለ❗❗
በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ “ከወሎ እና ከሰሜን ሸዋ ዞን ተነስተው ወደ አዲስ አበባ በሚገቡ መንገደኞች ላይ ድብደባ እና ዝርፊያ ተፈጽሞባቸው እንዲመለሱ ተደርገዋል” በሚል ያወጣነውን ዘገባ፤ ከበላይ አካል በደረሰብን ጫና እንድናነሳ ተገደናል ሲል ለአዲስ ማለዳ ገልጿል፡፡

ሥማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ የሰሜን ሸዋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ባለሙያ፤ “ሰሞኑን ከአማራ ክልል ደሴና አካባቢው እንዲሁም ከደብረ ብርሃን መናኸሪያ ተነስተው ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ ተጓዦች፤ ከኦሮሚያ ክልል እስከ አዲስ አበባ ባሉት አገር አቋራጭ መንገዶች ዘረፋና ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል፡፡” ብለዋል፡፡

በተጓዦች ላይ የደረሰውን ዘረፋና ድብደባ በተመለከተ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑትን መንገደኞች በደብረብርሃን መናኸሪያ እና አካባቢው ተዘዋውረን አነጋግረን ዘገባ ሰርተን ነበር ሲል መምሪያው አሳውቋል፡፡

“ዘገባውን በዞኑ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የማሕበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የለጠፍን ቢሆንም፤ የዞን እና የክልሉ የበላይ ኃላፊዎች ባደረሱብን ጫና ዘገባውን እንድናነሳ አስገድዶናል፡፡” ብለዋል፡፡

በማሕበራዊ ትስስር ገጾቻቸው አጋርተውት የነበረው ዘገባ ምንም አይነት ስህተት የሌለበት እንደነበርም የጠቆሙ ሲሆን፤ ድብደባና ዘረፋ የተፈጸመባቸው ተጓዦች የአማራ ክልል መታወቂያ የያዙ እንደነበሩም ተናግረዋል፡፡

ድርጊቱ የተፈመው ከደብረብርሃን ወደ አዲስ አበባ በሚወስደው መንገድ በኦሮሚያ እና አማራ ክልል አዋሳኝ በምትገኝ ሸኖ ከተማ ላይ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

“ከድብደባው የተረፉት ተጓዞች ለምግብና መጓጓዣ የሚሆን ገንዘብ፤ በደብረብርሃን መናኸሪያ ውስጥ ሌሎች ተጓዞችን ርዳታ ሲጠይቁም አስተውለናል፡፡” ብለዋል፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የደብረ ብርሃን መናኸሪያ የህዝብ ትራንስፖርት ስምሪት ቡድን መሪ ስዩም ተፈራ በበኩላቸው፤ “ሰሞኑን ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ ተጓዦች ድብደባ እና ዝርፊያ፣ ደርሶባቸዋል፡፡” ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

እስካሁን ከ3 ሺሕ በላይ ተጓዦች መመለሳቸውን እና ከእነዚህም ውስጥ አስራ አንድ ተሳፋሪዎች በደረሰባቸው ድብደባ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጸዋል፡፡

ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ከተከለከሉት ሰዎች መካከል የዩንቨርሲቲ ተማሪዎች በብዛት እንደሚገኙበት ገልጸው፤ ድርጊቱ ትናንት ሰኞ መስከረም 29/2016 ቀጥሎ መዋሉንም ጠቁመዋል፡፡

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የሰሜን ሸዋ ዞን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ “ከሰሞኑ ያወጣሁትን ዘገባ ከበላይ አካል በደረሰብኝ ጫና አንስቻለሁ” አለ❗❗
በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ “ከወሎ እና ከሰሜን ሸዋ ዞን ተነስተው ወደ አዲስ አበባ በሚገቡ መንገደኞች ላይ ድብደባ እና ዝርፊያ ተፈጽሞባቸው እንዲመለሱ ተደርገዋል” በሚል ያወጣነውን ዘገባ፤ ከበላይ አካል በደረሰብን ጫና እንድናነሳ ተገደናል ሲል ለአዲስ ማለዳ ገልጿል፡፡

ሥማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ የሰሜን ሸዋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ባለሙያ፤ “ሰሞኑን ከአማራ ክልል ደሴና አካባቢው እንዲሁም ከደብረ ብርሃን መናኸሪያ ተነስተው ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ ተጓዦች፤ ከኦሮሚያ ክልል እስከ አዲስ አበባ ባሉት አገር አቋራጭ መንገዶች ዘረፋና ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል፡፡” ብለዋል፡፡

በተጓዦች ላይ የደረሰውን ዘረፋና ድብደባ በተመለከተ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑትን መንገደኞች በደብረብርሃን መናኸሪያ እና አካባቢው ተዘዋውረን አነጋግረን ዘገባ ሰርተን ነበር ሲል መምሪያው አሳውቋል፡፡

“ዘገባውን በዞኑ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የማሕበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የለጠፍን ቢሆንም፤ የዞን እና የክልሉ የበላይ ኃላፊዎች ባደረሱብን ጫና ዘገባውን እንድናነሳ አስገድዶናል፡፡” ብለዋል፡፡

በማሕበራዊ ትስስር ገጾቻቸው አጋርተውት የነበረው ዘገባ ምንም አይነት ስህተት የሌለበት እንደነበርም የጠቆሙ ሲሆን፤ ድብደባና ዘረፋ የተፈጸመባቸው ተጓዦች የአማራ ክልል መታወቂያ የያዙ እንደነበሩም ተናግረዋል፡፡

ድርጊቱ የተፈመው ከደብረብርሃን ወደ አዲስ አበባ በሚወስደው መንገድ በኦሮሚያ እና አማራ ክልል አዋሳኝ በምትገኝ ሸኖ ከተማ ላይ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

“ከድብደባው የተረፉት ተጓዞች ለምግብና መጓጓዣ የሚሆን ገንዘብ፤ በደብረብርሃን መናኸሪያ ውስጥ ሌሎች ተጓዞችን ርዳታ ሲጠይቁም አስተውለናል፡፡” ብለዋል፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የደብረ ብርሃን መናኸሪያ የህዝብ ትራንስፖርት ስምሪት ቡድን መሪ ስዩም ተፈራ በበኩላቸው፤ “ሰሞኑን ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ ተጓዦች ድብደባ እና ዝርፊያ፣ ደርሶባቸዋል፡፡” ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

እስካሁን ከ3 ሺሕ በላይ ተጓዦች መመለሳቸውን እና ከእነዚህም ውስጥ አስራ አንድ ተሳፋሪዎች በደረሰባቸው ድብደባ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጸዋል፡፡

ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ከተከለከሉት ሰዎች መካከል የዩንቨርሲቲ ተማሪዎች በብዛት እንደሚገኙበት ገልጸው፤ ድርጊቱ ትናንት ሰኞ መስከረም 29/2016 ቀጥሎ መዋሉንም ጠቁመዋል፡፡

Читать полностью…

Ethio 360 Media

9  አመራሮች ታገቱ‼️

የወረኢሉ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ከእነምክትሉ፣የጃማ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ከነምክትሉና የድርጂት ሃላፊውን ጨምሮ፣የከላላ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪና ምክትሉ  ከስራቸው የሚገኙ የብልፅግና  አመራሮችን ጨምሮ በጠቅላላው 9  አመራሮች ወደ ደሴ ሲሄዱ መንገድ ላይ በአልታወቁ ሀይሎች ታግተው ተወስደዋል ተብሏል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

እስካሁን 313 ፍልስጥኤማውያን እና 300 እስራኤላውያን ህይወታቸውን ማጣታቸው ተዘግቧል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የአብይ መንግስት በሌብነቱ ምክንያት በእርዳታ ስርጭት ላለመሳተፍ መስማማቱ ተገለጸ‼️

በኢትዮጵያ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ካሳለፍነው ግንቦት ወር ጀምሮ የመጋዝን ስርቆት ተፈጽሞብናል በሚል እርዳታ መስጠት አቁመው ነበር፡፡

እርዳታ መቆሙን ተከትሎም ስደተኞች እና የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ረሀብን ጨምሮ ተረጂዎች ህይወታቸውን እስከማጣት መድረሳቸው በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡

በእርዳታ እህል ስርቆቱ ላይ የፌደራል እና የክልል መንግስታት ባለስልጣናት እጃቸው እንዳለበት በወቅቱ በረድኤት ድርጅቶቹ በኩል ተገልጾም ነበር፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ለተረጂዎች የተቀመጠን እህል ወደ ጎረቤት ሀገር ይላክ እንደነበርም የተገለጸ ሲሆን የፌደራል መንግስት በወቅቱ የቀረበበትን ክስ ውድቅ አድርጓል፡፡

የአሜሪካ የልማት ተራድዖ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) ዛሬ ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ያቋረጠውን የምግብ እርዳታ ዳግም ለማስጀመር መወሰኑን አስታውቋል።
Alain

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ራያ ቆቦ ከባድ ውጊያ ተቀስቅሷል‼️

በቆቦ ከተማ ዙሪያ ከሌሊቱ 9:00 ጀምሮ በ3ቦታዎች ማለትም በጠዘጠዛ፥መደፈራና ካራይላ ላይ ከባድ ውጊያ እየተደረገ ነው። 

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ሰበር የአፈና ዜና…!

"…ሰላም ነው ዘመዴ…እንዴት ነህ…? ሱሌይማን ትናንትና በሳዑዲ ተይዟል ብለው ጓደኞቹ ደወሉልኝ በማለት ባለቤቱ ወሮ ሃያት መልእክት አስቀምጣልኛለች። ዜናውን የሠራሁትም ባለቤቱ ስለነገረችኝ ነው።

"…ሱሌማን አብደላ መጀመሪያ በሕዳሴው ግድብ እና በጁንታው ጦርነት ጊዜ ከሃገሩ ጎን ተሰልፎ የብልፅግናን መንግሥት ይደግፍ የነበረ ሲሆን፣ የብልፅግና አገዛዝ በገዛ ዘሮቹ ላይ የጅምላ ጭፍጨፋና የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸሙን አጠናክሮ በመቀጠሉ ምክንያት ልጁ በግልጽ ወጥቶ አገዛዙን መቃወም መጀመሩ ይታወቃል።

"…የሱሌማንን ተቃውሞ ተከትሎ በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆነው አቶ ሌንጮ (ሰልመዋል አሉ) ሱሌማንን በማገት ወደ ኢትዮጵያ ሊወስዱት ዘመቻ እንደጀመሩም ከሱሌማንና ከሱሌማን የቅርብ ሰዎች ሰምቼ ነበር።

"…አንድ ቀን ሳዑዲዎች አሳልፈው እንደሚሰጡት ይናገር የነበረው ሱሌማን ከአምባሳደር ሌንጮ ዛቻና እሱን የማደን ዘመቻ ሲበረታበት ሱሌማን ልጁን እና ነፍሰጡር ባለቤቱን ትቶ ከቤት በመውጣት በሰዋራ ስፍራ ሆኖ ትግሉን እንደቀጠለ አስታውሳለሁ። ሆኖም ዛሬ ከባለቤቱ የደረሰኝ መልእክት በማን እንደሆነ ባይታወቅም ሱሌማን አብደላ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል። ተጨማሪ መረጃ ካለ ይዤ እመለሰላሁ። "…ዩቲዩበሮች፣ ፌስቡከሮች፣ ሚዲያዎችም ስለሱሌማን መያዝ ስትዘግቡ ምንጭ መጥቀሱን እንዳትረሱ። ✍✍✍

"…ለማንኛውም ጉዳዩን እየተከታተልኩ ለማቅረብ እሞክራለሁ። ዐማራንና የዐማራን ድምጾች በማሰር፣ በማፈን፣ በመግደልም የዐማራን ትግል ማቆም አይቻልም።

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

(ዘመድኩን በቀለ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ትግራይን ለዳግም ጦርነት የማዘጋጀት ጉዳይ‼️

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ባጫ ደበሌ ለፋኖ የሰጠው ምክር ባስቸኳይ መተግበር ያለበት‼️

Читать полностью…
Subscribe to a channel