ብልፅግና በመፍረስ ላይ ነው።
ስርዓቱ መበስበሱን ማሣያ ነው።
የሠላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ስዩም መስፍን ስልጣናቸው ትተው ከሀገር መሰደዳቸው ተሰማ‼️
ዶ/ር ስዩም መስፍን ለስራ ወደ ቡርንድ በሄዱበት ነው የጠፉት።ወደ ሀገር ተመልሰው ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜው እንዳለፈም ከተቋማቸው የተገኘ መረጃ ይጠቁማል።ትናንት ታሕሳስ 13/2016 በወጣ መረጃ ዶ/ር ስዩም አሜሪካ መግባታቸው ተሰምቷል።
ሌላኛው የሰላም ሚንስቴር ዲኤታ አቶ ታዬ ደንደአ መታሰራቸው አይዘነጋም።
======================
ምዕራብ ጎጃም ‼️
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ መከላከያ ሰራዊት ለጊዚያዊ ማረፊያ በሚጠቀምበት የኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ትናንት ምሽት 3:00 አካባቢ በፋኖ ተዋጊዎች የደፈጣ ጥቃት ተፈፅሞ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ ጉዳት ደርሷል።
በካምፑ የነበረው ከፍተኛ ቁጥር ያለው መሳሪያ ከነ ተተኳሹ በፋኖ ተዋጊዎች ተወስዷል።
======================
ፋኖ እንዲህ ነው‼️
የትግራይ ተወላጅ የቀድሞ የመከላከያ አባላት በፋኖ ታጣቂዎች ከእስር ነጻ እንደወጡ ተናገሩ ‼️
በዐማራ ክልል በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ዳንግላ ከተማ ታስረው ከቆዩበት እስር ቤት፣ በፋኖ ታጣቂዎች ነጻ እንደወጡ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩ የትግራይ ተወላጆች ተናገሩ።
ከ18 ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ ተፈርዶባቸው እንደነበር የገለጹት ተወላጆቹ፣ የታሰሩትም “በማንነታችን የተነሣ ነው፤” ብለዋል፡፡
የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የዐማራ ክልል መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን በበኩላቸው፣ ከዳንግላ ከተማ ማረሚያ ቤት ያመለጡ ታራሚዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፣ ድርጊቱም፣ “ሕገ ወጥ” ሲሉ በጠሯቸው ቡድኖች እንደተፈጸመ ገልጸዋል፡፡
ለትግራይ ተወላጅ የፖለቲካ እስረኞች የሕግ ድጋፍ ለመስጠት የተቋቋመው የጠበቆች ቡድን አስተባባሪ ደግሞ፣ በትግራይ ክልል ተቀስቅሶ ከነበረው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋራ በተገናኘ፣ የትግራይ ተወላጅ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩ እስረኞች፣ የዳንግላ ከተማን ጨምሮ በመላ አገሪቱ መኖራቸው እንደሚያውቅ ዶይቸቬለ ዘግቧል።
======================
አብይ አሕመድ የመከላከያ አባላትን በአማራ ክልል ከ ፋኖ ጋር እየተደረገ ባለው ጦርነት በዚህ መልኩ እያስጨፈጨፋቸዉ ነው።
ነፍስ ይማር
"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በሰው ደም የሚጫወቱ አረመኔ ናቸው" - ታዬ ደንደአ
የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ ታዬ ደንደዓ ከስሳ መሰናበታቸውን አስመልክቶ በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን << በተናገሩት የማይኖሩ ብቻ ሳይሆን በሰዉ ደም የሚጫወቱ አረመኔ መሆንዎን ተረድቻለሁ >> ሲሉ ወንጅለዋቸዋል።
ታዬ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የደረሳተውን የስንብት ደብዳቤ አያይዘው ባሰራጩት መልዕክት << እዉነት መስሎኝ በሀገር ህልውና ስም ሲያካሄዱ የነበረዉንና ኢትዮጵያውያንን ከማገዳደል አልፎ ሀገሪቷን ያደቀቃትን ከንቱ ጦርነት ሳዳምቅልዎ በነበረበት ወቅት ሲያወድሱኝ ነበር >> ሲሉ አስታውሰዋል።
<< ዛሬ ነገሩ ገብቶኝ የወንድማማቾች መገዳደል ይቆም ዘንድ ለሰላም በመወገኔ ከስልጣን አነሱኝ >> በማለት ኮንነዋል።
የታዬ ፅሁፍ ሲቀጥል << ለወንበርና ለመኪና በመገዛት ኦሮሞን በኦሮሞ ለማጥፋትና ኦሮሞን ከወንድሞቹ ጋር ለማጣላት የሚጫወቱትን ቁማር እያየሁ ዝም ባለማለቴ እጅግ ደስተኛ ነኝ:፤ ስለነበረን አጭር ቆይታ አመሰግናለሁ >> ብለዋል።
<< እስካለሁ ድረስ ለሰላምና ለህዝቦች ወንድማማችነት የማደርገዉ ትግል ይቀጥላል! >> በማለት መልዕክታቸውን ቋጭተዋል።
ምንም እንኳን ይህ የስንብት ደብዳቤ በይፋዊ ገፃቸው ይሰሬጭ እንጂ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት በኩል ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የተሰጠ ይፋዊ ማረጋገጫ የለም።
አሻም ቲቪ
በአማራ ክልል የተጣለው የኢንተርኔት እገዳ በአስቸኳይ እንዲነሳ ሲሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ተቆርቋሪዎች ጠየቁ‼️
ጥያቄውን ያቀረቡት ከ150 ሃገራት የተውጣጡ ወደ 300 የሚሆኑ ለሰብአዊ መብቶች መከበር የሚሟገቱ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ናቸው። የእገዳ ተግባሩ ከሌሎች የአፍሪቃ ሃገራት በኢትዮጵያ የከፋ መሆኑ ተገልጿል። እገዳውን በማውገዝም (Access Now) እና (#KeepItOn coalition) የተባሉ ሁለት ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ግልጽ ደብዳቤ ከጻፉ ወራት ተቆጥረዋል። የኢንተርኔት እገዳው ግን እንደቀጠለ ነው ።
«…በአማራ ክልል ላይ የተጣለውን የኢንተርኔት እገዳ ያለአንዳች ማንገራገር፣ መስመሮቹን በአስቸኳይ እንዲከፍቱ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን አህመድን እንጠይቃለን፡፡ የአፍሪካ ሕብረት ድርጅትም መሠረታዊ የሆኑ ሰበኣዊ መብቶችም በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲከበሩና በሥራ ላይ እንዲውሉም ፣ጋዜጠኞችም ሥራቸውን አለ.አንዳች ቁጥጥር ተዘዋውረው እንዲሠሩ፣ ድርጅቱም ጣልቃ ገብቶ -በቻርተሩ ውል መሠረት- ተጽዕኖ እዚያ እንዲያደርግ እኛ እንጠይቃለን፡፡» ይህን ያሉት የኤሲሲኢኤሰ ናው በምጻሩ - ACCESS NOW የተባል ድርጅት ተጠሪ ወይዘሮ ፊሊሲያ አንቶኒዮ ናቸው፡፡
ከ150 አገራት የተወጣጡ፣ወደ 300 የሚጠጉ ለሰበኣዊ መብት መከበር የሚሟገቱ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተሰባስበው በቅርቡ ያወጡት የጋራ መግለጫ፣ ከሓምሌ ወር ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በኢትዮጵያ - በአማራ ክልል የኢንተርኔት መስመሮች እዚያ እንደተዘጉ ጽሑፉ መለስ ብሎ በሰነዱ ላይ ያስታውሳል፡፡ በብዙ የሚቆጠሩ ሰዎች እዚያ እንደሞቱ፣ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ በጅምላ ታፍሰው እንደ ታሰሩ-የተባበሩት መንግሥታትን ሰነድ- ማሥረጃ አድርጎ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያን መንግሥት ከሷል፡፡
በ ኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በርካታ ንፁሃን አማሮች በዘግናኝ ሁኔታ በሸኔ ተጨፈጨፉ‼️
በኦሮሚያ ክልል አሩሲ ዞን ከበቆጂ ከተማ በ11 ኪሎሜትር ላይ በምትገኝ ትንሽ መንደር የሸኔ ታጣቂዎች ገብተው ከ28 በላይ ንፁሃን አማሮችን በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።
ከሟቾቹ ውስጥ ነፍሰጡር እናት እንዲሁም አረጋውያን ወንዶች እና ሴቶች እና ህፃናትም ጭምር ተጨፍጭፈዋል ብለዋል።
ግድያውን የፈፀሙት አማራ ናችሁ ተብለን ነው ብለዋል።
ከሞት የተረፉትም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ናቸው።
( የፋኖ ትግል መቀጠል እና መደገፍ አለበት መፍትሄው እሱ ብቻ ነው። )
ደካማው የኢትዮጵያ መሪ ሀገር መምራት እንዴት እንደሆነ ከኬንያ ቢማርስ??
ኬኒያ የ 12 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ከአለም ባንክ አግኝታለች።
ኢትዮጵያ ላለባት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ድጋፍ ብትጠይቅም ከጦርነት ባለመውጣቷ ይኸው ከጀርመን ባዶ እጁን እየተንከለከለ ተመልሷል።
👆ከላይ የቀጠለ…✍✍✍… የተባለው እውነቱን ሕዝቡ እንዲያውቅ ይሁን። ጃልመሮ የወጣው መከላከያውና የጃልመሮ ሠራዊት ለ17 ተከታታይ ሰዓታት እልህ አስጨራሽ ውጊያ ከተደረገ በኋላ ነው። ለጊዜው ኦሮሞዎቹ ባላወቁት ሁኔታ በጁንታው ጊዜ በራያ እና ሰቆጣ ግንባር የነበረው፣ በዲሲፒሊን ሓላፊነቱን ሲወጣ የነበረው ጦር ነበር የተላከው። ጦሩ እየቀፈፈው ቢሄድም እንደተለመደው በኦነግ ሸኔ ቀለበት ውስጥ ገብቶ ሊደመሰስ አልቻለም። ጦሩ ጆሮውን በጥጥ ደፍኖ ወጥሮ ለ17 ሰዓታት ያህል ተዋግቶ የኦነግ ሸኔን ጦር ደምስሶ ወደ ገደለው ሊገባ ሲል የቀይ መስቀል አውሮጵላን መጥታ ጃልመሮን ከወለጋ ጫካ አውጥታው ይዛው ሄዳለች። በውጊያው ላይ የነበረው የመከላከያ ሠራዊት ይሄን ጉድ ለወዲያው አላወቁም ነበር። ኋላ ላይ ሲሰሙ ግን ለምን ብለው ሲጠይቁ "ተሸንፏል፣ ብዙ መረጃ ማውጣት ስላለበት ነው ቀይ መስቀል የመጣው፣ እጅ ሰጥቷል፣ ሊደራደር ነው እረፉ እንደተባሉ ነው የተነገረው። በዚህ ሁኔታ የተቆጡትን የሠራዊቱን አባላት ከሥፍራው አውጥተው አሁን ወስደው ጋምቤላ በረሃ ውስጥ ያለበቂ ስንቅና ውኃ ለስልጠና ተፈልጋችኃል፣ አዲስ ሰልጣኞችን ትጠረንፋላችሁ ተብለው ተወስደው ተወርውረዋል።
"…ፋኖ እየፏለለብን ኦሮሞ ሸኔ ሲባል ደመሰስነው መባል የለበትም። ሸኔን እንዲህ ወጥራችሁ እንደምትዋጉት ለፋኖ ጊዜ ሲሆን እጃችሁ ቄጤማ፣ አይናችሁ ጨለማ የሚሆነው ለምንድነው? በማለት ቀንም ማታም ሙቀቱ ጨርቅ በሚያስጥል በረሃ ወስደው አስቀምጠዋቸዋል። አሁን ኦነግ በቀጠናው እደፈለገ እንዳሻው እየሆነ ነው። ስንቅም ትጥቅም እያገኘ ራሱን እንዲያደራጅ ተፈቅዶለታል። ምክንያቱም ጠንኳራ የሚባለውን የመከላከያ ክፍል ከግንባር አውጥተው ከውጊያ ውጭ አድርገውታል።
"…የመከላከያ ሠራዊቱ ሸኔን ሳይደመስስ እንዲወጣ ከተደረገ በኋላ ኦነግ ሸኔ ዛሬ ኖሌን እየዘረፉ ነው። ማኮ ወረዳን ሙሉ በሙሉም ተቆጣጥረዋል። ብዙ ንፁሐንም ተገድለዋል። በማኮና በኖሌ ያለውን ጨርሰው ወደ ዳጋ ወረዳ እየገሰገሱ ነው። ሸኔዎቹን የሚያስቆም ምንም ኃይል የለም። የተመደበውም እንዲነሣ ተደርጓል። ከደጋ ማኮ 18 ኪሎሜትር ርቀት ነው። ብዛታቸው ለጉድ ነው። አሁን ግን የኦሮሞ ብልጽግና የቡኖ በደሌ የመኮ ወረዳ ሙሉ በሙሉ በሸኔ ስር እንዲገባ አድርጓል። በፋኖ መገስገስ፣ ያለመሰበርም ተናደዋል። እናም ዘመዴ ፋኖ አስቸኳይ እርምጃ ይውሰድ። ሰሞኑን የፋኖ መሪዎች ሞት ከተሰማም በዚህ በስልክ ምክንያት ብቻ ነው የሚሆነው። ፍጠኑ።
"…ሌላው የተወሰነው ውሳኔ ደግሞ የተከፈለው ሁሉ መስዋዕትነት ተከፍሎ፣ የወጣው ሁሉ ወጪ ወጥቶ በተገኘው መንገድ በትግሉ ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ በውጭ ሃገር የሚገኙ ጋዜጠኞችና ማኅበረሰብ አንቂዎችን መመረዝ፣ መግደል የሚል ውሳኔም ተላልፏል። ለዚህ ደግሞ ቁጥር አንድ ላይ የተቀመጣችሁት አንተ ዘመድኩን በቀለና ከአሜሪካ ሀብታሙ አያሌው ናችሁ። ደረጀ ሀብተወልድም ምን እንዳስቀየማቸው ባይታወቅም ስሙ ተነሥቷል። በተቻለ መጠን ራሳችሁን ብትጠብቁም ተብሏል።
"…ዘመድኩንን በተመለከተ የተቀመጠው ግምገማ ሊገኝበት ይችላል ተብሎ የሚጠበቀው አንድ ብቸኛ ስፍራ ቤተ ክርስቲያን ነበር። እዚያ ከታየ ቆይቷል። ጓደኛም የለው። በየትኛውም የኮሚዩኒቲ ስብሰባ ላይ፣ ሰላማዊ ሰልፎች፣ የመጽሐፍ ምረቃ፣ ሠርግና ልቅሶም ላይ አይገኝም። ሆቴልም አይበላም፣ ካፌም ሬስቶራንትም አይጠቀምም፣ እንደ መጠጥ ቤት ጭፈራና ኮንሰርቶችም ላይ፣ መንፈሳዊ ዓለማዊም ቦታ አይገኝም የሚል ግምገማ አስቀምጠዋል ተብሏል። በተለይ አንተና ሃብታሙ አያሌው ከእግዚአብሔር ጋር ጥንቃቄ አድርጉ የሚል ነው ምክሩ። እኔም አልኳቸው።
"…ለሁሉም መረጃ እግዚአብሔር ያክብራችሁ። ነገር ግን እኔን በተመለከተ “…እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፥ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፥ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።” መዝ 127፥1። ሺ ሞት ቢታወጅ ከቀኔ አላልፍም። እኔ ራሴን ጠበቄ አላድንም። የሚገርመው የአቢይ ብልፅግና ፓርቲ ወዳጅ የሆነ ሰው ሆቴል ያማረኝን ምግብ ሄጄ በቅርቡ በልቻለሁ። አሁንም ካማረኝ ሳይሸክከኝ ሄጄ እበላለሁ። ወጥ ቤቷ ስሜ ሲጠራ የሚነስራት ሴት እንደሆነች አውቃለሁ። ፍፁም የምትጠላኝ ጴንጤ ናት። ሳልጠራጠር ባርኬ ስመ ሥላሴን ጠርቼ ከጓደኞቼ ጋር ቅርጥፍ አድርጌ በልቻለሁ። ይሄ ከሆነ 15 ቀን እንኳ አይሞላውም።
"…በከተማዬ ቅርብ የሆነ የትግራይ ተወላጅ የወያኔ ደጋፊዎች ምግብ ቤት አለ። ያማረኝን ምግብ ሄጄ በልቻለሁ። እበላለሁ። የኤርትራውያን ሬስቶራንት ሄጄ እጠቀማለሁ። ሆላንድም ፈረንሳይም አሜሪካም ሲርበኝ አማትቤ በልቻለሁ። እበላለሁ። ጀርባዬን ማጅራቴንም እመታለሁ ብዬ ወደ ኋላ ተገላምጬ አላውቅም። አንዳንድ የአውቶቡስ ሹፌር ሀበሾች ሲያዩኝ፣ በባቡር ጣቢያም ሲያገኙኝ ሲደነግጡም አያለሁ። ኮፍያና መነጽርም አልጠቀምም። ነፃ ሰው ነኝ። እኔን ይገድል ዘንድ የፈለገ ሰው እኔ ለመገደል ምቹ ነኝ። መጠጥ ቤት፣ ዳንስቤት አያገኘኝም እንጂ በጀርመን ምድር በነፃነት ነው የምንቀሳቀሰው። እኔ መርዞ፣ ተኩሶ የሚገድለኝ ስጠባበቅ በትንታም መሞት አለ እኮ። ስንቴ ከትንታ አምልጫለሁ። ቀኔ ከደረሰ ፍግም ነው የምለው። እናም እኔን በተመለከተ አልፈራም ሳይሆን በዚህ በኩል አልሰጋም። ሰግቼስ ምን አባቴ ላመጣ…? ከአምላኬ የተወሰነልኝን ቀን እንደሁ አላልፋት። ሃውልት ሆኜ አልቀር። ሟች ፈራሽ፣ በስባሽ ሥጋ ለባሽ ሰው እኮ ነኝ።
"…ዓይኖቼ ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ ረዳቴ ከወዴት ይምጣ?ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። እግርህን ለመናወጥ አይሰጠውም፤ የሚጠብቅህም አይተኛም። እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፋምም። እግዚአብሔር ይጠብቅሃል፥ እግዚአብሔርም በቀኝ እጅህ በኩል ይጋርድሃል። ፀሐይ በቀን አያቃጥልህም ጨረቃም በሌሊት። እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፥ ነፍስህንም ይጠብቃታል። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም እግዚአብሔር መውጣትህና መግባትህን ይጠብቃል። መዝ 121፥ 1-8 ደግሞም፦
"…እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል። ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ። በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል። በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ፤ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው። ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአብሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ። እያልኩ አጭሯን ጸሎቴን ትዝ ትዝ ያለኝ ቀን መፈጸሜን አልዘነጋም።
"…አለቀ። አከተመ። ይኸው ነው ጸሎቴም። ከሃቅ ጋር እሞታለሁ። ኢትዮጵያዊ እንደሆንኩ፣ ዘረኛ ሳልሆን፣ ደሀ ተበደለ ፍርድ ተጓደለ እንዳልኩ እሞታለሁ። ሞት የተፈጥሮ ፀጋ ነው። ለማናችንም አይቀርም። ሞትን ሸሽተን አናመልጠውም። ከባህር ስለተጣልን አንሞትም፣ ከእሳት ስለተወረወርን አንሞትም፣ መርዝ ስለነደፈን አንሞትም፣ ከአንበሳ ጉድጓድ ስለተጣልን አንሞትም፣ ስለታሰርን አንሞትም። የምንሞተው ቀናችን ሲደርስ ብቻ ነው። ለሞታችን የዳቦ ስም ይሰጠዋል እንጂ ሞትንና የሞታችንን ቀን አናልፈውም። የውጭ ጠላት ሲጠብቅ በዘመዱ፣ በቤተሰቡ የሚገደለው የትየለሌ አይደል እንዴ። ጠበቂ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ብዙዎች ሞትን ፈርተው ነው ሃገርና ትውልድ እየገደሉ ያሉት። አከተመ።
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው…!
213 የምክር ቤት አባላት ወንበር ካለ ተወካይ ባዶ ሆኗል‼️
በመንግስት ዕቅድና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ፤ የፋሽስቱን አብይ ማብራሪያና ምላሽ ላይ እየተካሄደ ባለው የህዝብ ተ/ም/ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ 334 የምክር ቤት አባላት የተገኙ ሲሆን ፣ 213 የምክር ቤት አባላት ወንበር በዛሬው ዕለት ክፍት ሆነው ካለ ተወካይ ባዶ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ገና ብቻውን ይቀራል
የኦሮሚያ ልዩ ሀይል‼️
የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ተኩሶ በገደለው የሸኔ አባል ላይ በእንደዚህ አይነት አረመኔያዊ ተግባር የራሱን ዘር በእሳት ካቃጠለ አማራ ክልል ገብቶ ምን ሊያደርግ እንደሚችል አስበው።
አሁን አማራ ክልል በመከላከያ ስም እየተዋጋ ያለው የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ልብሱን እየቀየረ የመከላከያን ዩኒፎርም በመልበስ ነው።
ፋኖ ግን ስትማርከው ተሳስቼ ነው ሳላውቅ ነው ቢልህ እንዳትሰማው እንዲህ አይነት ነውረኛ አረመኔ ሰው በላ እስከወዲያኛው ነው መሸኘት ያለበት።
ላሊበላ‼️
በላሊበላ ከተማ በርካታ ሱቆች የመከላከያ መለዮ በለበሱ በአብይ ወንበር ጠባቂ ወታደሮች ከፍተኛ ዝርፊያ እንደተፈፀመ ከበርካታ ነዋሪዎች የደረሰን አሳማኝ ጥቆማ ያሳያል።
አስቸኳይ ሼር ይደረግ‼️
ስለ መከላከያ ምርኮኞች‼️
አንድ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ ፋኖ የሚማርካቸውን በተለይ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን እንዲሁም መሳሪያወቻቸውን ከ ጂፒኤስ አቅጣጫ ጠቋሚ ነፃ መሆናቸውን ሳያረጋግጡ መጠቀም እጅግ አደገኛ ነው ሲሉ ተናገሩ።
መሳሪያውን ከመጠቀም በፊት አስፈላጊውን ፍተሻ ማድረግ እና በአብዛኛው የመከላከያ ዩኒፎርሞችም ጂፒኤስ አቅጣጫ ጠቋሚ የተገጠመላቸው በመሆኑ በማቃጠል ማስወገድ ተገቢ ነው ብለዋል።
እንዲሁም ምርኮኛ የመከላከያ አባሎችን ወደ ፋኖ መቀላቀል ተገቢ አይደለም ብለዋል።
ጎጃም‼️
ትናንት በአዋበል ወረዳ ሉማማ እንዲሁም ቁይ መገንጠያ በተደረገ ውጊያ በርካታ ሰብዓዊ ጉዳት ደርሷል።
በተለይ በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች ላይ የፋኖ ተዋጊዎች ከፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት አድርሰዋል ተብሏል።
ከአምስት በላይ ንፁሃን ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል።
ጎጃም‼️
ጎጃምን ከፅንፈኛው ሀይል ለማፅዳት የመጨረሻው ዘመቻ በሚል በአብይ አሕመድ ሠራዊት የተከፈተው መጠነ ሰፊ ጥቃት እየተመከተ ነው።
በአራት አቅጣጫዎች የገባው የአገዛዙ ሰራዊት በአራቱም አቅጣጫዎች በለስ ሳይቀናው በከፍተኛ ኪሳራ እየተመታ መሆኑን ከታማኝ ምንጮች ማረጋገጥ ተችሏል።
መዳረሻውን ቋሪት አድርጎ የገባው ይህ ሠራዊት በህዝብ ማእበል እንዲሁም በፋኖ ሰራዊት ፊት አውራሪነት የተመከተ ሲሆን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምርኮኛ መመዝገቡንም ለማወቅ ተችሏል።
የሸኔው መንግስት እንዲህ ማድረግ ጀምሯል
ከአዲስ አበባ‼️
አዲስ አበባ 4 ጓደኞች ከአንድ ግሮሰሪ አፍሰው ፖሊስ ጣቢያ አስገቧቸው።
ሒደን ስንጠይቅ እያሉ የሉም ተባልን። ከአንዳንድ ሰው መረጃ ስናጣራ መከላከያ ሊሰለጥኑ እንደሆነ ሰማን አንደኛው የሀብታም ልጅ ነበርና ብር ከፍሎ ተመለሰ ሶስቶች የት እንደሔዱ አይታወቅም ።
======================
እነ ጁላ በፍርሀት ሊሞቱ ነው😂
አይ ሸኔ‼️
የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ትምህርት በተገቢው ልክ አላስተማረም በሚል እና በሌሎች ምክንያቶች የቅዱስ ሚካኤል ትምህርት ቤቶችን ፍቃድ መሰረዙን ተቆጣጣሪው መስሪያ ቤት ተናገረ፡፡
ትምህርት ቤቱ በበኩሉ አፋን ኦሮሞ በአዲስ አበባ ባሉ ትምህርት ቤቶች እንዲሰጥ ከተማ አስተዳደሩ መመሪያ ያወጣው ዘንድሮ መሆኑን በመጥቀስ እኔ ግን ከአምና ጀምሮ ትምህርት እየሰጠሁ ነው፤ የሚቀርብብኝ ክስም ሃሰት ነው ብሏል፡፡
ለምን ትምህርት ቤቱን መዝጋት እንደተፈለገም አልገባኝም ሲል ለሸገር ተናግሯል።
======================
ከባድ ውጊያ በምዕራብ ጎጃም‼️‼️
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ደጋዳሞት ወረዳ ፈረስቤት ከተማ እጅግ ከባድ ውጊያ እየተደረገ መሆኑን ከነዋሪዎቹ ለማረጋገጥ ተችሏል።
የመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች ፈረስ ቤት ከተማዋን ለቆ ወጥቶ ወደ ዳር ላይ ሰፍሮ ምሽግ ሰርተው የነበሩ ቢሆንም የፋኖ ተዋጊዎች አባላት በአረፋ መስመር,በደምበጫ መስመር,በባህርዳር መስመር እና ፍላጢት ስላሴ በሚባል ገጠራማና እጅግ ኮረብታማ ስፍራ በመሰባሰብና ድንገተኛ ተኩስ በመክፈት ከፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት ደርሷል ብለዋል።
የፋኖ ተዋጊዎችአስደናቂ ውጊያ አድርገዋል ተብሏል።
የኔትወርክ አገልግሎትም ተቋርጧል ብለዋል። በከተማዋ የፋኖ ተዋጊዎች አባላት ይተያሉ ብለዋል።
ወደ ገጠሩ ከባድ መሳሪያ እየተተኮሰ ነው ብለዋል።
ውጊያው ከተጀመረ ዛሬ 3ኛ ቀኑን ይዟል ሲሉ ነዋሪዎቹ ገልፀዋል።
ዘንድሮማ ጉድ ነው በቁማቸው ሊያብዱ ነው‼️
አይ ጁላ ማፈሪያ ጫታም 😂😂
ብርሀኑ ጁላ ኮንፊውዝድ እና ኮንቪንስን በተግባር ሲያሳይ!!
ፋኖ ግን ወጥር💪💪💪እንደዚሀ አስጨንቀው
ለአማራ ህዝብ የተከፈለ መስዋእትነት‼️
1. ዶ/ር ስመኘው ዓለምነው የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የአማራ ሐኪሞች ማኅበር አመራር
2. አቶ ክርስትያን ታደለ የአብን አመራር እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል
3.አቶ ዮሀንስ ቧያለው የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል።
በአዋሽ አርባ እስር ቤት በዚህ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።
ትግሉ ይቀጥላል‼️
ፎቶ:- ከማህበራዊ ሚዲያ
=================
ሰሜን ወሎ‼️
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ጋዞ ወረዳ እስታይሽ ከተማ ትናንት ለሊት ላይ ፖሊስ ጣቢያው አካባቢ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።
በዚህም ፖሊስ ጣቢያውን ሲጠብቁ የነበሩ የሚሊሻ አባላት በፋኖ ተዋጊዎች በደረሰባቸው ጥቃት ተሰውተዋል።
በፖሊስ ጣቢያው የነበረ ብዛት ያለው መሳሪያም ተወስዷል ብለዋል።
በታላቁ ሩጫ ተሳታፊ ከነበሩት መካከል 12ቱ ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር በሚል መታሰራቸው ተገለጸ‼️
የ አብይ አህመድ ጨፍጫፊ እና አፋኝ መንግስት ባላፈው ሳምንት እሁድ ህዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም #በአዲስ አበባ ተካሂዶ በነበረው ታላቁ ሩጫ ተሳታፊ የነበሩን መፎክር ሲያሰሙ ከነበሩት መካከል 12 የሚሆኑትን ለእስር መዳረጋቸው ተገለጸ።
ጀርመን‼️
ጀርመን ለቡድን 20 ሀገራት ስብሰባ ለመገኘት የሄደው የኦነጉ ጨፍጫፊ ተቃውሞ እንደደረሰበት የጀርመን ድምፅ ዶቾቬሌ ዘግቧል።
"ርዕሰ አንቀጽ”
"…የዛሬው ርዕሰ አንቀጽ የሚያጠነጥነው በፋኖ አባላት፣ በፋኖ አመራሮችና እነሱን በማናቸውም መንገድ በሚያገኙ አክቲቪስቶች፣ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ አመራሮች፣ እኔን ጨምሮ በዐማራ ትግል ላይ ወጥረን በምንንቀሳቀስ ግለሰቦች ላይ የሚያጠነጥን ርዕሰ አንቀጽ ነው።
"…በምድርም በሰማይም ብሎ በጥርሱም ነክሶ በጥፍሩም ቧጥጦ ሊያሸንፈው ያልቻለውን የዐማራ ፋኖ ከተቻለ ድርድር ብሎ በአርቴፊሻል፣ ከአንገት በላይ መርዙን በጉንጩ ደብቆ የበግ ለምድ ለብሶ ተኩላው ሕይወቱን ለማስቀጠል ሲል ድርድር ከመመኮሩ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ዳንኤል ክስረት "መከላከያ በአንድም በሌላ መልኩ በሆነ ዘዴ ተጠቅሞ ጦርነቱን ይጨርሰዋል እንዳለው፣ እነ ናትናኤል መኮንንም ሰሞኑን የሚሰማ የምሥራች አለ እያሉ የሚፎክሩበት የተለየ የተባለ ልዩ የሆነ ኦፕሬሽን በፋኖ፣ በፋኖ አመራሮችና በፋኖ የጦር መሪዎች ላይ ለመውሰድ መዘጋጀቱ ተሰምቷል። የሚማረክ ፋኖ፣ የፋኖ አለቃ፣ የሚሞት የፋኖ መሪ መጥፋቱ አገዛዙን አሳብዶታል። እናም በዚህ ሳምንት ይሄን በመፈጸም እንደምንም የፋኖ አመራሮችን በመግደል የዐማራን ፋኖና ሕዝብ ቅስም መስበር እንደሚፈለግ ነው የተሰማው። ታጋይ ይሞታል ትግሉ ግን ይቀጥላል የሚለውን የትግል ጥቅስ ዘንግተውታል ማለት ነው።
"…ዛሬ ባለቀው የደኅነነት መሥሪያ ቤቱና የመከላከያ ደኅንነት ቢሮ ጥብቅ ስብሰባ ላይ ከተነሡት ጉዳዮች መካከል በዋናነት ታዋቂ ፋኖዎችንና የፋኖ አመራሮችን በልዩ ሁናቴ በቴክኖሎጂ በታገዘ መሣሪያ ነጥሎ መምታት ለነገ የማይባል በፍጥነት ሊተገበር እንደሚገባ ነው የተወሰነው። ስለዚህ ማንኛውም ወደ ትግል የገባ በተለይ በደኅናው ዘመን ከብአዴን አመራሮች፣ ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶች ጋር ይነጋገር፣ ይደዋወልበት የነበረውን ስልክ ከነ ሲም ካርዱ ማራቅ፣ ማራቅ ብቻ ሳይሆን ከነስልኩ ማስወገድ ወይም ከትግሉ አካባቢ ማራቅ እንዳለበትም ተጠቁሟል። ለዚሁ ተብሎ አዲስ የኮሚዩኒኬሽን መጥለፊያ ቴክኖሎጂ ከወዳጁ ከተባበሩት ኤምሬትስ ማስገባቱ ነው የተነገረው።
"…እደግመዋለሁ ከህወሓት የጁንታ ትግል ጊዜ ጀምሮ ከብአዴን አመራር፣ በውጭ ሃገር ከሚገኙ ጋዜጠኞች ጋር፣ በአፍሪካ፣ በአሜሪካ፣ በአውሮጳና በአረብ ሃገራት ከሚገኙ የፋኖን ትግል ከሚደግፉ ሰዎች፣ ግለሰቦች እና አክቲቪስቶች እኔ ዘመድኩን በቀለን ጨምሮ ከ360 ከነሃብታሙ አያሌው ጋር፣ ከግንቦት 7ቶቹ ከእነ መሳይ መኮንን፣ ከአበበ ገላው ጋር እና ከእነ መዓዛ መሀመድ፣ ከትሪፕል ኤዎች ጋር፣ ከአበበ በለው፣ ከዳያስጶራ ማናቸውም ጋር ይገናኙበት የነበረውን ስልክ ከአጠገባቸው ያስወግዱ ያርቁም ተብሏል። ሌላ የመገናኛ ዘዴ ይፍጠሩ የሚል መረጃ ነው የመጣው።
"…ሌላው የፋኖ አመራር አለቆች በማናቸውም መንገድ የመገናኛ ሬድዮ በራሳቸው እጅ እንዳይጠቀሙ። የመገናኛ ራዲዮው በአብዛኛው የተገኘው ከህወሓት እና ከሟች የመከላከያ ሠራዊት እጅ ነው። እናም ለአደጋ ለመጋለጥ አመቺ ስለሆነ በምንም መንገድ አመራሮቹ ራዲዮ በእጃቸው እንዳይዙ ይነገራቸው። አንዳንድ ቦታ እንዲያውም ሬድዮውን የሸጠው ወይም ያቀረበው የህወሓት ሴል ነው እንደሆነ ታውቋል። ውስጡ ቺፕስ የተገጠመ ነው። ስለዚህ ይጠንቀቁ። በዚህ አካባቢ እጅግ በጣም ወሳኝ እና ታማኝ ሰው መመደብ፣ ራዲዮ መጠቀሙ የግድ ከሆነ ግን ራዲዮ የሚይዘው ሰው ከአመራሮቹ በጣም በራቀ ሁኔታ ይጠቀም ዘንድ ይነገር ነው የተባለው። ራዲዮ ብቻ ሳይሆን ከአመራሮቹ አካባቢ ስልክ የሚጠቀም ሰው ካለም እሱም የግድ ከሆነ በብዙ ርቀት ይሁን ተብላችኋል።
"…ሌላው ከመከላከያ ወደ ፋኖ መንደር በወዶ ገብነትም ሆነ በምርኮ የሚቀላቀል ማንኛውም የመከላከያ አባል፣ ከተራ ወታደር እስከ አዛዦች ድረስ ማንኛውም አዲስ ገቢ የፋኖን ትግል ተቀላቃይ ሰው በፍጹም ወደ ፋኖ አዛዦቹ እንዳይቀርብ ይደረግ። ከመሪዎቹ ጋር እንዳይጨባበጡ፣ ምንም አይነት ንኪኪም እንዳይኖራቸው፣ ልብሳቸው ተብጠርጥሮ ይወገድ፣ መሳሪያዎቹም ተፈታትተው ይፈተሹ፣ ተማራኪዎቹም ሆነ ወዶ ገቦቹ ከፊት መስመር ውጊያ ሲኖር ይሰለፉ እንጂ ከፋኖ ጀርባ እንዳይሰለፉ ይደረግ ተብላችኋል።
"…ማንኛውም የፋኖ ቡድን፣ ወይም ሻለቃ ወይም ብርጌድ ምንም ዓይነት ስብሰባ በፍጹም በቀን ብርሃን እንዳይሰበሰብ። ስብሰባዎች በሙሉ በጨለማ ይሁኑ። አመራሮቹም ዋሻን መጠለያ ያድርጉ። እንደ እህል አጨዳ የመሳሰሉትንም ቀን ቀን አለመከወን፣ ለምሳሌ በጎጃም ደባይ ጥላትክን ወረዳ ደቦዛ በምትባል የገጠር ቀበሌ በእርሻ ሥራ ላይ የነበሩ አራት የአንድ ቤተሰብ አባላት ትናንት ማለትም 05/03/2016ዓ.ም የአቢይ አህመድ አራጅ ሠራዊት በከባድ መሳሪያ የገደለው ሆን ብሎ ነው። በዚህ መልኩ ሞት የበዛበት የጎጃም ሰው ለዚህ መፍትሔው ብሎ ያመጣው እንደ ደንበጫና አካባቢው አርሶ አደሮች ቀን ቀን እየታገሉ ማታ ማታ የአጨዳ ሥራ እየሠሩ ነው። ሁሉም ቦታ እንዲህ ይደረግ። የጎጃም ሰው የትራፊክ መንገዱን ቀኙን ይዞ የሚጓዝ ነው። ለኅብረተሰቡ አንድ ላይ ሰብሰብ ብሎ መሄድ ያቆም ዘንድ ቢነገረው የሚተገብር የሚሰማ ነው። ይነገረው።
"…ካሁን ቀደም በሰሜን ሸዋ እና በጎጃም የተለያዩ አካባቢዎች በድሮን ንጹሐን ሰዎች እንደገደሉት ሁሉ አሁንም እየገደሉ ነው። ለምሳሌ ማክሰኞ አመሻሽ በ4 /3/2016 ዓም በሰሜን ወሎ ሲሪንቃ አካባቢ ልዩ ስሙ ጉባራ አካባቢ በትምህርት ቤት ላይ የድሮን ቦንብ ጥለው ብዙ ንፁሃንን ጨፍጭፈዋል። በተለያዩ አካባቢዎች በድሮንና እበከባድ መሳሪያና ንፁሀን እየተጨፈጨፉ ነው። አብዛኛው አጨዳ ሥራ ላይ በደቦ የሚሠሩ ናቸው የሚገደሉት። ሕዝቡ ዘሩን ሊያጠፋ ብልፅግና እንዳወጀበት ተረድቷል። ትግሉም እየሠፋ ሕዝባዊ እየሆነ ነው። በንጹሐን መገደል ሁሉም ዐማራ እንዲነሣ ተደርጓል።
"…ድሮን ደንገት መጥታ አይደለም የምታጠቃው። መጀመሪያ አካባቢውን ፎቶ አንሥታ ለሲችዌሽን ሩሙ ሲስተም ታስተላልፋለች። ከዚያ ነው እነ ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ወስነው፣ ዶር አብርሃም ፈርሞበት ቦንቧን የምትጥለው። ትግሬ ያለቀው በዚህ መንገድ ነው። በቃ ፋኖ ስብሰባ እንኳን ሲያደርግ ለሊት ሰው በማይንቀሳቀስበት ሰዓት ይሁን። ምክንያቱም መረጃ ሰጪው ከእነርሱው ጋር ተመሳስሎ እዚያው አካባቢ ነው የሚመደበው። ፋኖ የሁሉንም ታጋይ ሞባይል ስልክ መጠርነፍ አለበት። ከወሳኝ ሰዎች በቀር ሁሉም ተዋጊ ፋኖ ለምን ስልክ ይጠቀማል? ለምን ቤተሰብ ጓደኛ ፍቅረኛ ጋር ይደውላል? የሚጠቀመው የኢትዮጵያ ቴሌን እኮ ነው። የቤተሰብ፣ የቅርብ ጓደኛ ሁሉ ስልክ ይጠለፋል። አይደለም የኢትዮጵያ ሲም ካርድ የሳታላይቱም ስልክ ቢሆን ከ7 ደቂቃ በላይ ካወራህበት ሊጠለፍ ይችላል። መገናኛ አስፈላጊ ቢሆንም ጥንቃቄም ግን አስፈላጊ ነው።
"…መረጃ የሚሰጠው ከዚያው ከመካከላቸው ነው። ከዚያ ነው ወደ ድሮን ፕሮሰስ የሚደረገው። ፋኖ አለ ብለው የነገሯቸው አካባቢ ድሮኗን ይልካሉ። ፎቶውን በቀጥታ አይተው ነው የሚታዘዘው። ዘመዴ አሁን በቀደም ተስፋዬ አያሌው ምን ይላል መሰለህ። ከሲቹየሽን ሩም ደውለውለት አሁን እንጣለው ሲሉት እስኪቆይ በደንብ ይሰብሰቡ ብዛታቸው ስንት ይሆናል? በቃ በደንብ ይሰባሰቡ ከዚያ ይጣላል እንጂ ባዶ ሜዳ ላይ እየጣልን አጉል ውጤት አልባ ኪሳራ ላይ እየወደቅን ነው ሲል ተሰምቷል። በለሊት የድምፅ ሞገድ እንደሚጨምር ስለሚጨምር የድሮኗን ድምፅም ለመስማት ይቻላል። ሁለተኛ ከአስተኳሾች እይታም ይሰወራሉ። ስለዚህ ይሄን መልእክት ደጋግመህ አስተላልፍ ነው የሚሉኝ የመረጃ ምንጮቼ። ሌላው የኦነግ ሸኔው ጃልመሮም ለመደራደር ወጣ…👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍
የለገጣፎ ለገዳዲ የድሀ ቤት አስፈራሽ ከነጠባቂው ተገደለ‼️
በአዲስ አበባ ዙሪያ በሸገር ሲቲ በተለምዶ አጠራር 44 ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራው ህገወጥ ናቸው የተባሉ ቤቶችን ዋና አስፈራሽ የነበረው አሁን በዋና ሀላፊነት አስቀምጠውት የነበረው አቶ ሹሜ አበራ እና የሱ ጠባቄ የነበረ ሚሊሻ ትናንት ከምሽቱ 4:00 አካባቢ ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸውን የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።
ይህ ሰው ሸገር ሲቲ ከተማ ቤታቸው የፈረሰባቸው ቦታ ይሰጣቸው ሲባል እሱ ሞቼ እገኛለሁ ያለ ሰው ነው ሲሉ ነው የመረጃ ምንጮች የገለፁት።
ትናንት ምሽት በአካባቢው ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ጀምሮ ለሰዓታት የቆየ ከፍተኛ ተኩስ መሰማቱን ነው ምንጮች የገለፁት።
ሀይቅ‼️
በአሁኑ ሰዓት በደቡብ ወሎ ሀይቅ ከተማ ወጣ ብሎ ከፍተኛ የሆነ የተኩስ ልውውጥ እንዳለ ከነዋሪዎቹ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት በጦርነት ምክንያት የአደጋ ስጋት ላይ መሆናቸውን አሳወቀች❗❗
” ቅዱሱን ቅርስ መጠበቅና የአባቶቻችንን አደራ እንዳንበላ በአካባቢው የጦርነት ድምጽ እንዳይሰማ መደረግ አለበት ” – ብፁዕነታቸው
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት በጦርነት ምክንያት የአደጋ ስጋት ላይ መሆናቸውን አሳወቀች።
ቤተክርስቲያኗ ፤ በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የሚገኙት የቅዱስ ላላበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በ900 ዓመታት ውስጥ ብዙ መከራን ተሻግረው የጣሊያን ወረራን አልፈዋል እንዲሁም በየዘመናቱ በተፈጠሩ የእርስበርስ ጦርነቶች ጉዳት ሳያደርሱባቸው እዚህ ደርሰዋል ብላለች።
ይሁን እንጂ አሁን ባለበንበት ዘመን በአካባቢው በተፈጠረው ከፍተኛ የሰላም እጦትና ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ የአደጋ ሥጋት ላይ መውደቃቸውን በይፋ አሳውቃለች።
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ የቅዱስ ላላበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በጦርነት ምክንያት በከፍተኛ የአደጋ ሥጋት ላይ መውደቃቸውን ገልጸው ፤ ቅዱሱን ቅርስ ከስጋት ነጻ ለማድረግ ይቻል ዘንድ ሁሉም አካል ወደ #ሰላም_መድረክ መምጣት እንዳለበት በቅድሚያ ጠቁመዋል።
” ይህ ካልሆነ ግን ቅዱሱን ቅርስ መጠበቅና የአባቶቻችንን አደራ እንዳንበላ በአካባቢው የጦርነት ድምጽ እንዳይሰማ መደረግ አለበት ” ብለዋል።
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ላሊበላ ቅርስና የአምልኮ ቦታ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባለድርሻ አካላት ቅዱሱ ቅርስ ከአደጋ ስጋት ውጭ እንዲሆን ዓለም አቀፍ ተቋማት የመንግስት አካላት እንዲሁም የቅዱሱ ቅርስ የጋራ ሀብትነት የሚያሳስበው ሁሉ በጉዳዩ ላይ በጎ ተጽእኖ በማሳደር ድምጽ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።
ለመንግስት ቅርብ በሆኑና በገዥው ፓርቲ በሚተዳደሩ የመገናኛ ብዙሀን ሲሰሩ የነበሩ አራት ጋዜጠኞች ሀገር ጥለው መኮብለላቸውን ከተለያዩ ምንጮች አረጋግጠናል።
ዋዜማ
ጎጃም‼️
በጎጃም በሁሉም ዞኖች ከኦሮሙማው ሰራዊት ጋር ለነፃነቱ እየተዋደቀ ይገኛል።
በጎጃም በሁሉም ዞኖች በሚባል ደረጃ ከትናንት በስተያ ጀምሮ ውጊያ ተቀስቅሷል።
በዋናነት በደጋዳሞት ቋሪት፣ይልማናዴንሳ፣ሞጣ(ምላጭበር)፣በደንበጫ(ቅቤገደል)፣ቢቡኝ(አረፋ መድሃኒዓለም ሽሜ አቦ)፣ቡሬ፣ቲሊሊ(ዛሬ ለሊት 11:00 ጀምሮ)፣አዋበል ወረዳ(ሉማሜ)፣ደጀን ወረዳ(ልዩ ስሙ ትጭት)፣መርጦለማሪያም፣ቢቸና(ቁይ መገንጠያ)---- እና ሌሎች አካባቢዎች ውጊያ እየተካሄደ ነው።
ውጊያውን ተከትሎ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ተገድቧል።
ከደብረማርቆስ ከተማ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ትናንት ጀምሮ ተቋርጧል።
ድል ለፋኖ ‼️
ድል ለአማራ‼️