“አማርኛ ቋንቋን ለአፍሪካ ህብረት የስራ ቋንቋ!”
**
አማርኛን የአፍሪካ ህብረት የስራ ቋንቋ ለማድረግ እየሞገተች ያለችው እውቋ ኒጀራዊቷ ጋዜጠኛ ፀሃፊና የፊልም ባለሙያዋ ራህማቶ ኬታ አዲስ አበባ ትገኛለች።
ራህማቶ ኬታ ፊልሞቿን ጭምር ወደ አማርኛ በመተርጎም አማርኛ ቋንቋን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማስተዋወቅ ላይ የምትገኝ ሲሆን ባገኘችው መድረክ ሁሉ የአፍሪካን ጉዳይ በመስበክ ከአፍሪካም በተለየ ሁኔታ የአማርኛ ቋንቋ የህብረቱ ይፋዊ የስራ ቋንቋ መሆን እንዳለበት በመሞገት ትታወቃለች።
በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ለመታደም አዲስ አበባ የተገኘችው ይህች ባለ ራእይ ሴት የታሪክ ባለሙያዎች፣ ጋዜጠኞች፣ የማህበረሰብ አንቂዎችና የመንግስት ሀላፊዎች በተገኙበት አማርኛ ቋንቋን የአፍሪካ ህብረት የስራ ቋንቋ ለማድረግ ያከናወነቻቸውን ተግባራትና ቀጣይ እቅዷን በተመለከተ የፊታችን ማክሰኞ የካቲት 14/2015 መግለጫና ማብራሪያ እንደምትሰጥ የዝግጅቱ አስተባባሪ ጋዜጠኛ ጌራ ጌታቸው ለሸገር ታይምስ ሚዲያ ገልፆአል።
በመሆኑም በመግለጫው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የሚድያ ባለሙያዎች እስከ ነገ ሰኞ የካቲት13/2015 ከቀኑ 6:00 ድረስ ብቻ በ 09-47-50-59-92 በመደወል መመዝገብ እንደሚጠበቅባቸው አስተባባሪው ጠቁሟል።
"ስምምነቱ ተጥሷል፣ ቤተክርስቲያንን ጠብቁ በፀሎት ትጉ" ቅዱስ ሲኖዶስ
"የብሔር ብሔረሰቦች ኤጼስ ቆጶሳት ሿሚዎች ነን ያሉ 3 ሊቃነጳጳሳት ዛሬ የሰጡትን መግለጫ እስካላስተባበሉ ድረስ ከቤተክህነት እንዲወጡ ይደረጋል" ቅዱስ ሲኖዶስ
"25 ተሿሚዎች ውግዘታቸው አልተነሳም፣ አቶነታቸውም አልተሻረም። ወደፊት በሂደት ይታያል ነው እንጅ አሁን ውግዘታቸው ተነስቷል አልተባለም።" ብጽኡ አቡነ አብርሐም
የካቲት 10/2015 ዓ.ም
የዘመናችን የእሾኽ አክሊል
ከዛሬ 40 ዓመታት በፊት የሸዋ ክፍለ ሀገር ሊቀጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ (2ኛ) በዝዋይ ገዳም ለዲያቆናት እና ካህናት ሃይማኖት ከምግባር እየመረመሩ ክህነት ይሰጡ ነበር።
ለሹመት ከቀረቡት መካከል አንደኛው በወጉ ያለተማረ በምግባርም ያልሰመረ አንድ እጩ አግኝተው "ዘንድሮ አልሾምህም። ለሚቀጥለው ዓመት በደምብ ተምረህ፣ በምግባርም ሰክነህ ስትመጣ ትሾማለህ" ብለው መለሱት።
አብረውት የመጡት ወዳጅ ዘመዶቹ ተሰብስበው ብፁዕነታቸውን "እባክዎ ከነ ችግሩም ቢሆን ይሹሙልን። ወገኖቹም ይጣሉናል። እርሱ ካልተሾመ
ቤተክርስቲያናችንም ትዘጋለች" ሲሉ በማስተዛዘን ልመና አቀረቡ።
አቡነ ጎርጎርዮስ ግን "የወገኖቹን ቁጣ ፈርቼ በሃይማኖቱ ያለጸና በምግባሩ ያልቀናን ሰው ካህን እንዲሆን ሾሜ ቤተክርስቲያኒቱ ላይ የማይነቀል እሾኽ ከምተክልባት ለጊዜው ብትዘጋ ይሻላል። ወደፊት የተሻለ እና ለክህነት የተገባ ሰው አግኝተን ስንሾም ያኔ ይከፍታታል።" ብለው መለሷቸው።
ዛሬ ላይ ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለሁለት ካልሰነጠቅናት ብለው ቁም ስቅሏን የሚያሳዩዋት ግለሰቦች በሃይማኖት ጽናታቸው፤ በምግባርም መቅናታቸው የተመሠከረላቸው መሆኑ ሳይረጋገጥ የሆነ ወገንን ለማስደሰት በይድረስ ይድረስ የተሾሙ እንደነበሩ አሁን እሾኹ ደርሶ ሲወጋን ተረድተነዋል። ለቤተክርስቲያኒቱ የእሾኽ አክሊል ሆነው እየወጓትና እያደሟት ነውና!
ያለፈ አልፏል! አሁንም ቢሆን ባለሥልጣናትን ለማስደሰት ወይንም የአጃቢዎቻቸውን ጩኸት በመፍራት እንኳንስ ጵጵስና ዲቁና ለማይገባቸው፤ ከእግዚአብ ልጅነታቸው ይልቅ የብሔረሰብ ልጅነታቸው ደርሶ ለሚንጣቸው ዘውገኞች የክህነት ሹመት መስጠት በክርስቶስ መቅደስ ጉልላት ላይ ሌላ ተጨማሪ መርዛማ እሾኽ አክሊል እንደመድፋት ይቆጠራል።
(የኔታ ቡሩክ)
በአዋሽ ባንክ በአቶ ሳዊሮስ ስም በተከፈተ ሂሳብ ዉስጥ 24 ሚሊዮን አራት መቶ ሺ ብር ተገኘ ::
Читать полностью…በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት (EOTC TV) የኦሮሚኛ ቋንቋ ጋዜጠኛ
ዲ/ን ዮሴፍ ከተማ ታሰረ።
ዛሬ ሰኞ የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 አካባቢ በሥራ ጉዳይ በመንቀሳቀስ ላይ እያለ መካኒሳ አካባቢ ለጥያቄ እንፈልግሃለን የሚሉ የመንግሥት የጸጥታ አካላት እንደወሰዱት ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ዘግቧል።
የኦሮሚኛ ቋንቋ ጋዜጠኛ ዲ/ን ዮሴፍ ከተማ በወቅታዊ ጉዳይ ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተደጋጋሚ ቃለ ምልልሶች በማድረግ ወደ ምእመናን ሲያደርስ ቆይቷል።
(EOTC TV)
ቅዱስ ሲኖዶስ ከደቂቃዎች በኋላ መግለጫ ይሰጣል። መግለጫዎቹን ከሥር ያሉ ሊንኮችን ሰብስክራይብ በማድረግ ተከታተሉ። የዩቲዩብ ቻናሉ ትክክለኛው የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኅን ነው።
EOTC TV ➽ የዩቲዮብ ገጽ
http://www.youtube.com/c/eotctv
ታዋቂው አሜሪካዊ ፖለቲከኛ ከረን ፕራይስ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጎን እንደሚቆሙ ገልጸዋል።
Читать полностью…በተለይ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች መልእክት አለን፦ የቅዱስ ሲኖዶስን አቅጣጫ ብቻ በመከተል የአባቶችን ትእዛዝ እንፈፅም። የተለያዩ እምነቶች ተከታይ ለሆናችሁ ኢትዮጵያውያንም በጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ እየተፈፀመ ያለውን መንግስታዊ ድጋፍ ውንብድና በማውገዝ ላሳያችሁት አብሮነት ላቅ ያለ ክብርና ምስጋና እናቀርባለን።
Читать полностью…አቶ በረከት ስምኦን ከእስር ተፈቱ ‼️
ላለፉት አራት ዓመታት በእስር ላይ የቆዩት አቶ በረከት ስምኦን “የአመክሮ ጊዜያቸውን ጨርሰው” ዛሬ ረቡዕ ጥር 17፤ 2015 ጠዋት ከባህር ዳር ማረሚያ ቤት መፈታታቸውን ጠበቃቸው ህይወት ሊላይ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ።
ጥር 17/2015 ዓ.ም
==============
አንገር ጉትን‼
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን አንገር ጉትን ከተማ በማንነታቸው ምክንያት ታስረዋል የተባሉ ከ200 በላይ ሰዎች፣ ያሉበትን ሁኔታ እንደማይታወቅ የአካባቢው ነዋሪዎች መግለፃቸውን አዲስ ማለዳ ዘግቧል፡፡
እስር ቤት ገብቶ ያልተደበደበ የለም የሚሉት አካባቢው ነዋሪዎች፣ ከድብደባ ብዛት የሞተ ሰው አለ ሲባል መስማታቸውን ጠቁመዋል፡፡
ቴዲ ዮ ሰሞኑን በለቀቀዉ ሙዚቃ ምክንያት በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋለ ለማወቅ ተችሏል::
Читать полностью…የህወሓት አዲስ እንቅስቃሴ‼️
እነሱ ደቡባዊ ትግራይ በለው በሚጠሩት ኩኩፍቱ በሚባል አካባቢ በ6 መኪና ታጣቂዎችን ከመቀሌ አምጥቷል። ወደ ጨርጨር መስመርም በተመሳሳይ በርካታ ታጣቂዎች ሰፍረዋል።
በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ለምሳሌ ላዕላይ ሀያና፣ታህታይ ሀያና፣ኩኩፍቱ እና በርተክላይ በሚባሉ አካባቢዎች ሰሞኑን እንደ አዲስ ምሽግ እየተቆፈረ ያለባቸው ቦታዎች ናቸው። የእነዚህ ታጣቂዎች ስምሪት ደግሞ ኮረም እና አላማጣን በቆረጣ ለመያዝ እንደታሰበ ነው የወጡ መረጃዎች የሚጠቁሙት። በተለይ አርሚ 24 እና አረጋሽ አርሚ የሚባለው በርካታ ወጣቶችን በመሰብሰብ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
#Ethio News
አዩ ዘሀበሻ
ሐሳብ ያላትን ሴት በመናገሯ ምክኒያት ማሠር የናንተን አናሳነት፣ የእርሷንም ገናናነት ብቻ ይገልጻል። ደካሞች!
Читать полностью…የእስር መረጃ
ዛሬ 04/04/2015 መምህርት እና ጋዜጠኛ መስከረም አበራ በድጋሚ በአዲስ አበባ በተለምዶ መጠሪያው ሃያ ሁለት አከባቢ ከቀኑ 10:30 አብረን ከነበርንበት በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውላለች።ፖሊሶቹም ወደ ፌደራል ወንጀል ምርመራ እንደሚወስዷት ገልፀውልኛል።
(የባለቤቷ የፌስቡክ ፖስት )
በቤተ ክርስቲያን ብቻ እንዳይመስላችሁ!
ይሄ ጉድ ደግሞ በመንግስት መስርያ ቤት ነው። ፓትሪያርኩ እያሉ የሆነ የኦሮሚያ ቀበሌ መሽጋችሁ የራሳችሁን ሹሙ የሚለው ብሔርተኛ በየመስርያ ቤተ መሽጎም ተመሳሳይ ስራ እየሰራ ነው ተብሏል።
ከስር የምትመለከቱት ስምምነት የመንግስት መስርያ ቤቶች ከሚያውቁት ውጭ በጓዳ የተደረገ ስምምነት ነው ተብሏል። ኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር (ሚኒስቴር ዲኤታው- ባይሳ)፣የትምህርት ሚኒስቴር (ሚኒስቴር ደኤታው ሳሙኤል) ጋር የተፈራረሙት ነው። የሁለቱ መስርያ ቤት መሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና በለጠ ሞላን ትተው ሁለቱ ምክትሎች ከክልላቸው ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ተፈራርመዋል። ስምምነቱ በኦሮሚያ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ መምህራን በእነዚህ የመንግስት ተቋማት ሙሉ ወጭ ፒ ኤች ዲ እንዲማሩ የሚያደርግ ነው።
የት አባቱና፣ አውቶቡስ እንዲያመጣ ለአንድ ባለሀብት በሌለ የውጭ ምንዛሬ 72 ሚሊዮን ዶላር አውጥቶ መስጠት ብቻውን አይበቃም ብለዋል። ዋና ኃላፊው ሰማም አልሰማም በልዩ ሁኔታ በፌደራል ተቋም ፒ ኤች ዲ እንይዛለን ብለዋል።
(ጌታቸዉ ሽፈራው)
የአማራ ብልፅግና ስብሰባ‼️
ዛሬው የአማራ ክልል ብልፅግና ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በጠራው የአመራሮች ስብሰባ የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ግርማ የሺ ጥላ የክልሉን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እያሱ መስፍንን ከስብሰባ አዳራሹ በጥበቃ እንዳስወጧቸው አንድ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የፓርቲው አባል ለአማራ ድምፅ ገልፀዋል።
ከስብሰባ አዳራሹ አንዲወጡ የተደረጉት አቶ እያሱ መስፍን ከወር በፊት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብድሳ በባህርዳር ከተማ በነበራቸው የጋራ ስብሰባ ላይ "የኦሮሚያ ክልል መንግስት በአማራ ህዝብ ሞት ቀጥታ እጁ አለበት " በሚል ጠንካራ ትችት በመሰንዘራቸው ምክኒያት ጥርስ ተነክሶባቸው መቆየቱን ነው የአማራ ድምፅ ምንጮች የገለፁት።
በዛሬው እለት በተጠራው ስብሰባ አቶ ግርማ የሺ ጥላ አቶ እያሱ መስፍንን "የሌሎች አጀንዳ አስፈፃሚ ነህ ፣ ባለፈው የኦሮሚያ ክልል አመራሮችን በመድረክ በመዝለፍ አመራሩ እርስ በእርሱ እንዲጠራጠር እና እንዳይተማመን አድርገሀል። ዛሬም ይህንኑ አጀንዳ ይዘህ ነው የመጣኸው" በሚል በፀጥታ ኃይሎች ተገዶ እንዲወጣ መደረጉን የስብሰባው ተሳታፊዎች ለአማራ ድምፅ ገልፀዋል።
==================
ሌላውን ጨርሰው ነው ወደ ቤተ ክርስቲያን የመጡት!
እነ አዳነች አቤቤ አንድ አውቶቡስ በ19 ሚሊየን ብር ገዝተው እንዳመጡ አድርገው ዜና እያሰራጩ ነው። ኮንትራት ወስዶ ያመጣው የተባለው የአንድ ኦሮሞ ባለሀብት ንብረት የሆነ ብራይተን ትሬዲን የሚባል ነው። ከእጥፍ በላይ እንዲያተርፍ አድርገው ሀብት ይፈጥሩለታል። ለአላማቸው ገንዘብ ያዋጣል። ይሄ ለእነሱ እጅግ ቀላሉ ነገር ነው። ከስር ያሉት ሌሎች የራሳቸው የዘረፋ ማስረጃዎች ናቸው።
1) መሬት እንዳይሸጥ የሚል እግድ በአደባባይ ይወጣል። በውስጥ ይወያዩና የእነሱ ሰዎች ተዘጋጁ ይባላሉ። እግዱ በውስጥ ደብዳቤ ይነሳል። እግዱ የተነሳበት ደብዳቤ በአደባባይ እንዳይታወቅ ይደረጋል። የእነሱ ሰዎች መሬት በውድ ይሸጣሉ። ሸጠው ሲጨርሱ ሌላ "መሬት እንዳይሸጥ" የሚል እግድ በአደባባይ ይወጣል። "እንዴ የባለፈው እግድ መቸ ተነሳ? ብለው የጠየቁ ቢሮ ደብዳቤ ያሳዩዋቸዋል። እንዲህ አድርገው ከተማውን ሸጠውታል።
2) ከወራት በፊት መኪናን ጨምሮ ከውጭ የሚመጡ ቁሳቁሶች ታግደው ነበር። የመኪና ዋጋ ጣራ ሲነካ "አሁን ነው ሀብት መፍጠር" ብለው በውስጥ ተነጋግረው የእነሱን ሰዎች ተዘጋጁ ብለው፣ የውጭ ምንዛሬ በጓዳ ፈቅደውላቸው ለተወሰነ ጊዜ ከፈቱት። መኪና አመጡ። ከቀረጥ ነፃ አስገብተው አተረፉበት። እንደገና እግድ ጣሉ። በእጥፍ ከሸጡ በኋላ።
3) ሲሚንቶ በህገወጥ መንገድ ተሸጠ ወዘተ እየተባለ በመንግስትም ደረጃ እየተለፈፈ ነበር። ዋናዎቹ ግን ራሳቸው ናቸው። ወጣቶችን አደራጁ፣ ፖሊስ፣ ደህንነት ወዘተ እንዲያግዛቸው ተደርጎ በጥቁር ገበያ እንዲሸጡ ተፈቀደላቸው። ሀብት ፈጠሩበት።
4) ኬኛ የሚባል የአልኮል ፋብሪካ እያቋቋሙ ነው። 7 ቢሊዮን ብር የተበደሩት ከአንድ የመንግስት ባንክ ነው።
5) ሻሸመኔ የትራክተር መገጣጠሚያን ያቆሙት ከልማት ባንክ ተበድረው ነው። ትራክተሩ ተገጣጥሞ ሲያልቅ ወጣቶችን ያደራጁና ልማት ባንክ እንዲያበድራቸው ተደርጎ ይገዙታል። በልማት ባንክ ብድር ከፋብሪካ እስከ ሽያጭ ድረስ።
ይህ ምሳሌ ነው። በኢኮኖሚው እያንዳንዱን ነገር በህገወጥ መንገድ ሳይቀር ወስደው ጨርሰዋል። ሁሉን ወስደው ነው ወደ ቤተ ክርስቲያን የመጡት።
ሀብት የፈጠሩለት ለተወገዘ ቡድንም ይሁን ለሌላ ገንዘብ የማዋጣት ግዴታ አለበት። ሀብት የፈጠሩለት እነሱ ናቸው። የኦሮሚያ ክልል ቴሌቶን ወዘተ ብሎ አይጠይቅም።"ይህን ያህል ታዋጣለህ!" ብሎ ግዴታ ነው የሚጥለው።
ኃይማኖት በሀራጅ ሊሸጡ ከመምጣታቸው በፊት ያልሸጡት፣ ያላተረፉበት ነገር የለም።
በመጨረሻ እስክስታም ባለቤት ተገኘላት😀
የሁለተኛ ክፍል የአማርኛ መፅሀፍ ነዉ አሉ
ከኢንሳ የመጣ አዲስ መረጃ…!
"…ዘመዴ እንደምንም ብለህ ይሄን መረጃ ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እና ለሕዝቡ አድርስ። መንግሥት በቅዱስ ሲኖዶስ አባቶች እና በአንተ ላይ ዶክመንተሪ እንዲሠራ አዟል። በአባቶች ላይ የውሸት ድምጽ ማስመሰል ሊሠራ ያቀደ ሲሆን ሲሠራም 2 ዋና ዋና ነገሮችን አስቦ ነው።
1ኛ፥ ለማኅበረሰቡ በውሸት እነዚህ አባቶች የፖለቲካ ንክኪ አጀንዳ እንዳሏቸው ለማስረዳት፥
2፥ የኦሮሞን ህዝብ እንደሰው እንደማይቆጥሩት የሚያሳይ ድምጽ ለማውጣት ነው።
"…በዚህም የታሰበው በማኅበረሰቡ ብቻ ሳይሆን የሲኖዶሱ አባቶች እርስ በእርሳቸው መተማመን እንዲያጡ ለማድረግ የታሰበ ነው። እናም ስልክ ደግሞ 100% በኢትዮቴሌኮም የፎቶጋለሪ ሳይቀር መመልከት ይችላሉ። እንዲህ መጠቀም ከጀመሩ 1 አመት አልፏቸዋል።
"…የInsa cyber security specialist ከሰለሞን ሶካ የ insa director encrypted መልዕክት ተልኳል። ይህም የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት አባቶች እንዲሁም የሃይማኖት ተቆርቋሪዎች accounts check እንዲያደረጉ፣ እንቅስቃሴያቸው እንዲጠና፣ እንዲሁም የማኅበረሰብ አንቂዎች ጭምር እንዲበረበር፣ ከዚያውስጥ ደግሞ ዘመዴ ላይ Documentary ለመሥራት Vulnerability እየፈለጉ ነው። በቅርቡም በአቡነ ማቲያስና በአቡነ አብርሃም ላይ የተሠራ voice over ለማኅበረሰቡ ለማውጣት በዝግጅት ላይ ናቸው።
"…በቀደም ዕለት በእነ አካለወልድ የተሰጠው መግለጫ ተመልክቶ ከመግለጫው በፊት እነ ሽመልስ አብዲሳ የነገሯቸው ነገር "እኛ ውስጥ ውስጡን እንጨርሰዋለን እናንተ ግን ግፉበት። ወደ ኋላ የሚል በህይወቱ ላይ እንደፈረደ ይቁጠር። አንዴ ገብተንበታል ዳር ሳናደርስ አንመለስም። የብልፅግናን ፈጥረን ወደ አራት ኪሎ የመጣነው በዚሁ መንገድ ነው። አዲሲቱን ኦሮሚያ ለመፍጠር በሚደረገው ሂደት ላይ የእናንተ ድርሻ ቀላል አይደለም። በርቱ ነበር ያላቸው። ከኢትዮጵያ ጋር አብሮ መኖር ካልተቻለ ዐማራን ለትግሬና ለሱዳን ሰጥተን፣ ሱማሌ ወደ ፈለገበት እንዲሄድ አድርገን፣ ደቡብን ከእኛ ጋር ቀላቅለን በኃይ ግማሽ ደቡብ ወሎን እና አዲስ አበባን ጨምሮ ይዘን መገንጠል ነው።" ይሄ ሕገ መንግሥታዊ መብታችን ነው። ማንም አያስቆመንም። ምንም አትስጉ ነው ያላቸው። መነኩሴዎቹ አሁን ታግተው ነው ያሉት።
"…ዘመዴ Voice over ን በተመለከተ እንደምንም ብለህ ለቅዱስ ሲኖዶሱም ለኅበረተሰቡም ቀድመህ ማድረስ አለብህ። መንግሥት ቅዱስ ሲኖዶሱን ከህዝቡ ለመነጠል እንደ ዋነኛ መንገድ ነው ሊጠቀመው ያሰበው። ይህም ስል የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አባቶች በኩራት እንዳይቃወሙት አንገት ማስደፊያ ነው። መረጃው ቀድሞ ከወጣ የጨጓራ በሽተኞች ከመሆን በዘለለ ምንም አባታቸው አያመጡም። የሚገርምህ እኔ ሃይማኖቴ አይደለም። ነገር ግን ሰዎቹ ሊፈጥሩ ያሰቡት ምስቅልቅል ስላሳሰበኝ ነው። በአሁን ወቅት ደግሞ በጣም የምት ሰማው እና ታማኝ የመረጃ ምንጭ ስለሆንክ ብዬ ነው ወዳንተ መምጣቴ።
"…በአጠቃላይ ስለዚህ ሥራ የሚያውቁ ሰዎች 3 የኮምፒዩተር ስፔሻሊስቶች፣ አንድ ስሙን ከሰሞኑ ስሙን የምነግርህ አርቲስት የድምጽ የአባቶችን ድምፅ የማስመሰሉን ሥራ እንዲሠራ ተመርጧል። አርቲስቱን በፎቶ እሰጥሃለሁ። አርቲስቱ ያስመሰለውን የአባቶች ድምጽ ወደ ኮምፒዩተራቸው አስገብተው ነው በስልክ እንደተነጋገሩ የሚያስመስሉት። ንግግሩ ኦሮሞን የሚያንቋሽሽ አድርገው እንዲሠራ ነው የታዘዘው። ድምፁ ከተሠራ በኋላ አርቲስቱ ይገደላል ወይ መርፌ ወግተው ያጀዝቡታልም ተብሏል። አዛዡ ሰለሞን ሶካ እና ከሱ በላይ ያሉ ሰዎች ናቸው።
"…አንተን በተመለከተ ኢንተርኔት ላይ ባለህ እንቅስቃሴ የተውካቸውን ኮቴዎች ተከተለው አካውንት መጥለፍ ሲሆን፣ በዚያም ሳታውቅባቸው የሚችሉትን ያህል መረጃ መውሰድ ነው። ካልቻሉ ደግሞ ሶሻል enginering የሚባለውም ቴክኒክ በመጠቀም ነው ሊመጡብህ ያሰቡት። በዚህም ወዳጅ መስለዉ መረጃው መመዝበር ነው። ከዛ በራስህ መረጃ documentary ሠርተው ያንተ ተከታዮች ላይ conspiracy መፍጠር። ይሄን ካሳካን ቢያንስ እንደ ጉድ ከሚከተሉህ ሰዎች ከብዙ ሚልዮኖቹ ቢያንስ ግማሽ የሚሆነው ሰው ከአንተ መራቅ ነው የፈለጉት።
"…ያንተከትሎ ከዚያ በኋላ በዋና ዋና መገናኛ ብዙሃን ሚዲያዎች የሠሩትን documentary አንተን ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ አሸባሪ ማሳየት ነው የፈለጉት። በዚህም ዋና ዓላማው አንተን በወንጀለኛ፣ በዘር አጥፊነት ለመፈረጅ ነው። ጭቅጭቅ ነበረባቸው። ልጁ ለዚህ ፍረጃ አይመችም የሚል ነገር ተነሥቶም ነበር። ነገርግን አቶ ሰሎሞን ሶካ ይገባናል ነገርግን ሌላ የተሻለ ምርጫ የለንም ስለዚህ በዚሁ ግፉበት የሚል መመሪያ ሰጥቷቸዋል።
"…ዛሬ voice over እንዲሰሩ ከታዙት መካከል ከinsa ፕሮጀክቶች በሙሉ ወደ እኛ ወደ ኦሮምያ ደኅንነት ቢሮ እንዲመጡ ተደርጓል። በኦሮሚያ ደህንነት ቢሮ እንዲሠራ የተፈለገው አቶ ተመስገን በሚሠራው የደኅንነት ቢሮ መተማመን በማጣታቸውና ዐማሮቹ እንደ ፓርቲም፣ እንደ ክልልም ለእኛ ለኦሮሚያ ብልጽግና የሚያሳዩት እንቅስቃሴ እጅግ መተማመን ስለጠፋበት ነው። አቶ ደመቀ ከእነ አቢይ ያፈነገጠ ይመስለኛል። አቶ ተመስገንም በጎጃሜዎቹ የተጠለፈ ነው ብለው አያምኑትም። በመከላከያውም ስንጥቃት አለ። የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ በአባቶች ጥበብ አለፈ እንጂ ከህዝቡ ይልቅ ጦሩ ነበር የሚፋጀው።
"…በኦሮሚያ ደኅንነት ቢሮ የሚሠሩት ከቱርክ ተምረው የመጡ እንዲሁም የቀድሞ insa ላይ የነበሩ ሰዎች ናቸው። አንተ አሁን መረጃውን ለማኅበረሰቡ እና ለቅዱስ ሲኖዶሱ አሳውቅ። ዘመዴ ፍጠን ትናንት ምሳ ሰዓት ላይ ሙሉ ለሙሉ ፕሮጀክቶቹን በአጠቃላይ ወደ እኛ ኦሮሚያ ደህንነት ቢሮ መጥቷል። ሁሉም ያነቡሃል። ግትርነትህን፣ ሃቅህን ይወዱታል፣ እልህህ ደስስ ይላቸዋል። የሚጠሉት ሴራቸውን ስለምታፈራርሰው ነው። በፊት በፊት ጓደኛህ ስለሆነ ዳንኤል ክብረት ነው መረጃ የሚሰጠው ብለው ይሟገቱ ነበር። አሁን አሁን ግን በተለይ ዳንኤል ላይ ከጻፍክ በኋላ ስለ ዳንኤል እንደ አዲስ መረጃ ካንተ ስላገኙ በአንተ ላይ ክትትልና የመረጃ ምንጮችህን ለማወቅ እንቅልፍ አጥተዋል። ነገር ግን ምንም ዱካ ሊያገኙ አልቻሉም። የአንስ ልዩ ነው። በርታ ዘመዴ። ህዝቡ አስቀድሞ ተጠንቅቆ እንዲጠብቅ አንተ ይሄን ቀድመህ አውጣሁ።
"…ስላለኝ አውጥቼዋለሁ። እኔን በተመለከተ ግን በ email የምጻጻፈው ከጀርመን መንግሥት ለሥራ ጉዳዮች ብቻ ነው። ለማንም በኢሜል መልስ ሰጥቼ አላውቅም። ሲበረብሩ ውለው ቢያድሩ የሚጣሉት ከጀርመን መንግሥት ጋር ነው። በተረፈ በስልኬ ላይ የሚቀመጥ ምንም የተለየ ነገር የለኝም። የማገኛቸውን መረጃዎች ሃገር የሚያፈርሱትን በመደበቅ ነው በስሱ እንዲደነግጡ፣ ንስሀም እንዲገቡ የምለቅላቸው። የብዙዎቹን ነውር ሁላ ደብቄያለሁ። እነሱ አሸባሪ ሲሉኝ እኔ ደግሞ እየቀፈፈኝ ገመድ ፈልገው ይታነቁ ዘንድ የሚያደርጋቸው መረጃዎችንም እለቃለሁ።
(ዘመድኩን በቀለ)
አብይ ማለት እኮ ወታደሮቹ ቤተ_መንግስት የሄዱ ጊዜ አብሮአቸዉ ፑሽ አፕ ሰርቶ በ ቲቪ እየሳቀ አቅፎ መግለጫ ሰቶ ከዛ ከስንተኛዉ ቀን በሃላ ለቃቅሞ እስርቤት ያጎረ ሰዉ ነዉ::
ወዳጄ ምን ለማለት ነዉ በጭራሽ አትመኑት ቂመኛ እና በቀለኛ ነዉ::
እንደዉም ቅዱስ ሲኖዶሱ ከሚሰጠዉ መግለጫ በፊት የመንግስት መግለጫ መቅደም አለበት:: ቃሉን ለህዝብ ይስጥ መልእክታችን ነዉ አለቀ!!
ውጤቱን ዛሬ ምሽት 5:30 ይለቀቃ
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን ተማሪዎች ከዛሬ ለሊት ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል።
ተፈታኞች ከዛሬ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም #ከሌሊቱ 5፡30 ጀምሮ ፡-
• በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ወይም
• በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም
• በቴሌግራም ላይ /channel/eaesbot
ማየት የሚችሉ መሆኑን ተገልጿል።
ማሳሰቢያ፡-
• ማንኛውም ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በአካል መምጣት ሳያስፈልግ እስከ ጥር 26/2015 ዓ.ም ድረስ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ላይ Compliant የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል።
• ተማሪዎች ፤ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አድራሻ ላይ ብቻ እንዲጠቀሙ #ከተመሳሳይ እና #የተዛባ_መረጃ ለማሰራጫት ከሚሞክሩ አካላት እራሳቸውን እንዲጠብቁ መልዕክት ተላልፏል።
ምንጭ ፦ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ!
መልካም በዓል እንዲሆን እንመኛለን!
"እባብ ለመደ ተብሎ..."
ትህነግ ጫካ በገባ ጊዜ፣ ስለ እሱ አትፃፉ አብቅቶለታል ብለው የሚጨቀጭቁን ሰዎች ነበሩ። ተመልሶ ሌላ ወ*ረ*ራ* ፈፀመ። አሁንም ሰላም ሰላም ስላለ ብቻ "ሰራዊቱን እንዳታስመቱት" ከማለት አንቦዝንም። በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ትህነግ ቃል ገብቶ የፈፀመው የለም።
1) መሳርያ አስረክብ ሲባል ጊዜ ወስዶ መሳርያ ደብቋል። በየሰፈሩ እየዞሩ ህጋዊ አስመስሎ አስታጥቋል። ካስረከበም የተወሰኑትን አስረክቦ ቀሪውን በድሮን አውድማችሁብኛል ይላል።
2) ተኩስ ይቁምልኝ ብሎ የለመነው ትህነግ ነው። ተኩስ አቁመናል ሊል አይችልም።
3)ሉአላዊነት አከብራለሁ ብሎ ነገር ግን ትግራይን እንደ አገር፣ ራሱን እንደ መንግስት ቆጥሮ አሁንም ራሱን የትግራይ መንግስት እያለ ቀጥሏል።
4) እርዳታ ብቻ ሳይሆን በፓትሮልና በተደራጀ መልኩ የነዋሪዎችን ሀብት እየዘረፈ ነው።
5) ከሁሉም አዲስ ምልምል እያሰለጠነ ነው። ትህነግ ከቻለ ሌላ ዙር ጦርነት ያውጃል። ካልሆነ ደግሞ አንዳንዶቹ አፈነገጡብኝ እያለ ሰራዊቱን ያስመታል።
6) በሰላም ስምምነቱ ሂደት ሊተነተኑ የሚችሉ በርካታ ጉዳዮች አሉ። በሚዲያ ለማስመሰል የሚደረጉት ብዙ ናቸው። በርካታ ዓለምን እፎይ ሊያሰኙ ነው የተባሉ የሰላም ስምምነቶች ተካሂደዋል። አብዛኛዎቹ ፈርሰዋል። ይህኛውም በታንክና በድሮን የተደባደቡ ኃይሎች መካከል የተደረገ ነው። ትህነግ ስምምነቱ የተወሰኑ ጉዳዮች እስኪሟላለት እንጅ የሚገዛበት መርሁ አይደለም። "እባብ ለመደ ተብሎ በኪስ አይያዝም" እንደሚባለው ነው። ትህነግ ሰራዊቱን የመታው ድግስ አዘጋጅቶ ሲጋብዝ አምሽቶ ነው። ሰላም ከወረደ እሰየው ነው። ነገር ግን ሚዲያውን ወቅታዊ የሰላም ዜና ስለሞላው ተዘናግቶ ዳግም የሚመታ የዋህ የለም።
ዋናው አለመዘናጋቱ ነው። ሰላም ከፈጠረ ይፈጥራል። ካልፈጠረም ይቀምሳታል ብሎ ተዘጋጅቶ መጠበቅ ነው።
(ጌታቸዉ ሽፈራዉ)
ሼር‼️😱
ለአዲስ አበባ ት/ት ቤቶች ጥብቅ ትዕዛዝ ተላለፈ‼️
በኦሮሞ መዝሙር እና በማንዲራው ጉዳይ እየተፈጠረ ያለውን ግጭት እና የትምህርት መስተጓጐል ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ያሉ ትምህርት ቤቶች በጥብቅ ድስፕሊን እንዲመሩ ትዕዛዝ ተላልፏል።
✅ ይህ በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ተፈርሞ የተላለፈው ደብዳቤ ሁሉም ተማሪዎች እና መምህራን በጥብቅ ክትትል እንዲደረግባቸው ያዛል።
✅በዚህም መሰረት ላረፈደ ተማሪ እና አንድ ቀን ለቀረ ተማሪ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል።
✅እንዲሁም ሁለት ቀን ያረፈደ እና የቀረ በወላጅ ፊት የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጠው ያዛል።
✅ከሁለት ቀን በላይ የቀረ እና ያረፈደ በመመሪያው መሰረት ቅጣት እንደሚተላለፍበት ያዛል።
✅በትምህርት ቤቶች በር ላይ ጥብቅ ፍተሻ ይደረጋል፣ ተማሪዎች ርችት፣ስልክ እና ፊኛ ይዘው እንዳይገቡ ያዛል።
✅የትምህርት አመራር፣ መምህራንና ሰራተኞች በሙሉ የሥራ ስዓታቸውን አክብረ፣ የመማር ማስተማር ሥራቸውን እንዲያከናውኑ ትብቅ ትዕዛዝ የተሰጣቸውም ሲሆን፤ በዚህም ማርፈድ፣ መቅረትና የሥራ ስዓት ሳያልቅ ከትምህርት ቤት ግቢ መውጣት የተከለከለ ነው ተብሏል፡፡
✅የትምህርት ቢሮ ኃላፊው ትዕዛዝ ባስተላለፉበት ደብዳቤ፣ ያስተላፉትን ትዕዛዝ የማያስፈጽም በየደረጃው የተቀመጠ የትምህርት ቤት አመራርም ተጠያቂ እንደሚሆን አሳስበዋል፡፡
ሰሞኑን የኦሮሞ ማንዲራ ይሰቀላል አይሰቀልም፣የኦሮሞ መዝሙር አንዘምርም በማለት በርካታ ተማሪዎች ከትምህርት ቤት መቅረታቸው ይታወቃል። ከዚህ በተጨማሪ በረብሻው ውስጥ ተሳትፈዋል የተባሉ መምህራን እና ተማሪዎችም ታስረዋል።
ታህሳስ 12/2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ‼
ነገ ሰኞ ታህሳስ 10/2015 በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኙ 523 ትምህርት ቤቶች የኦሮሚያ ክልልን አርማ የመስቀል እና መዝሙር የማዘመር ስራ እንደሚከናወን ተሰምቷል።በሂደቱ ላይ እንቅፋት ለሚሆኑ አካላት በቂ የፀጥታ ኃይል መሰማራቱ ታውቋል(ዋሱ መሃመድ)።
Teddy Afro 🥺
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም አንዴ ምን አሉ?
"እኔ የጥበብ ሰው ብዬ የምገልፀው አንድ ሰው ጥቀስ ብባል ቴዲ አፍሮን ነው"
የቴዲ የጥበብ መነፅር ሁሌ ይገርመኛል። ትልቅ ሀሳብን በአጭር እና በሚገርም አገላለፅ ቁጭ ያደርገዋል።
ለምሳሌ USA 🇺🇸 Live ኮንስርት ላይ ስለ አዲስ አበባ እንዲህ ብሎ አዜመ 👇
🎸🎷
አፍሪካን አክሎ የተሰፋው ልብሱ
ኢትዮጵያን አክሎ የተሰፋው ልብሱ
ከምኔው ከምኔው ጠበበሽ ቀሚሱ
አዲሳባ ነበር የጥንቱ ስምሽ
ሁሉ አገርሽ ነበር የጥንቱ ስምሽ
አሁን ከምንጊዜው የኔነሽ አሉሽ::
🎵🎺
💚💛❤
ወዳጄ አዲስ አበባ ስትመሰረት አፄ ሚኒልክ ባወጁት አዋጅ ላይ እንዲህ የሚል አገላለፅ ነበረ
"አበልጄ ሆይ ናና ጎሮቤት ሁነኝ"
በዚህ መሰረት ከአራቱም አቅጣጫ ብሄርብሄረሰቦች አዲስ አበባን ሁሉ ሐገርሽ አደረጓት።
አዲስ አበባ የሁሉ አፍሪካዊ መዲና ናት። የአለም የዲፕሎማሲ ከተማ ናት። ይህ ሊሆን የቻለው ኢትዮጵያን እንድታክል ደምና አጥንት የተከሰከሰባት የመስዋዕትነት ከተማ ስለሆነች ነው።
ቴዲ የገባው ይህ ታላቅ ሚስጢርን ነው። ለሚገባው ትልቅ መልዕክት አስተላልፏል።
ሐገር የሁላችን ናት። አዲስ አበባ የሁላችንም ናት። ኢትዮጵያ የሁላችንም ናት 🙏
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር 🙏
በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለተፈጠሩ ችግሮች የከተማ አስተዳደሩ ተጠያቂ ነው ሲል እንባ ጠባቂ ተቋም አሳሰበ
ከኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማ መሰቀል እና መዝሙር መዘመር ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ለሚፈጠሩ ችግሮች ብቸኛው ተጠያቂ የከተማ አስተዳደሩ ነው ሲል የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አሳሰበ።
ተቋሙ ባወጣው መግለጫ ተማሪዎችን ለማስገደድ በሚፈፀሙ ድርጊቶች በተማሪዎች እና በትምህርት ቤት ንብረቶች ላይ ለሚደርሱ ጥፋቶች “ተጠያቂው የከተማ አስተዳደሩ እንጂ ሌላ ውጫዊ አካል” አይደለም ብሏል።
እንባ ጠባቂ ተቋሙ አክሎም የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ከተማ የሚያገኛቸው ልዩ ጥቅሞች እና የአፈፃፀም ስርዓት በልተቀመጠለት ሁኔታ የክልሉ ባንዲራ እና መዝሙር በከተማዋ እንዲፈፀም የሚያስገድዱ “ግለሰብ ባለስልጣናት” በመኖራቸው የከተማ አስተዳደሩ ትኩረት እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል።
የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ባወጣው መግለጫ የአንድ አካባቢ ችግር በድርድር ከተፈታ ለሌላ አካባቢ የማይሰራበት እንዲሁም የአደረጃጀት ጥያቄ የአንዱ በህገ መንግስቱ ተፈቶ የሌላው የማይፈታበት ምክንያቶች አይኖሩም ብሏል።
የተቋሙ መግለጫ ከነዚህ በተጨማሪ በህግ የበላይነት፣ በዜጎች ደህንነት እንዲሁም በሙስናና ብልሹ አሰራር እና ሌሎችም ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጓል።
ታህሳስ 04 ቀን 2015 ዓ.ም