በትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ለመመስረት ለሁለት ቀናት የቆየው ኮንፈረንስ የተጠናቀቀ ሲሆን የካቢኔ ስብስብ ይፋ አድርጓል። አሁን ባለው ሂደት ከህወሓት በኩል ዶክተር ደብረጽዮን ፕሬዚዳንት እንዲሁም የትግራይ ሰራዊት ዋና አዛዥ የሆኑት ጄኔራል ታደሰ ወረደ ምክትል አስተዳዳሪ የመሆን እድላቸው ሰፊ ነው። ሌሎች ፖለቲካዊ ተሳትፎ የሌላቸው ተቋማት ለምሳሌ ውሃ እና ልማት፣ መልሶ ማቋቋም፣ ባህል እና ቱሪዝም፣ ስፖርት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር...እነዚህ ተቋማት በትግራይ ክልል ለሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተሰጠ ሲሆን ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ የፖለቲካውን ዘርፍ አሁንም ህወሃት የወሰደ ስለሆነ አንቀበለውም፣የብልፅግና መንግሥት የደቡብ አፍሪካውን ስምምነት ጥሶታል የሚል ተቃውሞ እያሰሙ ነው። ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ህወሃት ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ተቋሙን ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ በመውሰዱ የተለየ ነገር አላየንበትም ሲሉ ተደምጠዋል።
Читать полностью…መረጃ ከዋቻሞ ዩንቨርስቲ‼️
የአካባቢው ተወላጆች እና በግቢው ውስጥ ያሉ local ተማሪዎች አማራ ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ጥቃት እያደረሡብን ነው አሁን ብዙዎች ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው ይገኛሉ ግቢ ውስጥ ያለነውን ዶርም እየሰበሩ እየተደበደብን ነው ቆስለው ሆስፒታል የሚታከሙ ለጆችም አሉ እኛንም ግቢ ውስጥ ድብደባ እየተፈፀመብን ነው።
ካፌ ሁሉ ተዘግቷል፣ በተለይ ለግቢዉ አዲስ የሆኑ ተማሪዎች እየተሰቃዩ ነው።
(መረጃዉ ከዩኒቨርስቲዉ ተማሪዎች የተገኘ ነዉ)
ወንድም፥ በሰላም እረፍ!
በዳግማዊ ምኒልክ መሰናዶ ትምህርት ቤት የፊዚክስ መምህር የሆነው ወንድማችን መኳንንት ወዳጅ (ሚሊዮን) የአድዋ የድል በዓል ለማክበር ወደ ምኒልክ አደባባይ እንደሄደ በዚያው አስቀሩት
ለቤተሰቦቹና ለጓደኞቹ መፅናናትን እመኛለሁ።
የወንድማችን አስክሬን በአቤት ሆስፒታል ከቆዬ በኋላ ወደ ትውልድ አካባቢው ጎንደር- ጋይንት ተሸኝቷል።
© Melkamu Tsegaye
አድዋ የ ጥቁር ህዝቦች ድል እንኳን አደረሰን✊🏾
#1888ec
“The triumph at Adwa was not just a military victory, but it was a triumph of the human spirit.” – Nelson Mandela
ከደቡብ ሱዳን የተነሱ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በድጋሚ ወደ ጋምቤላ ክልል ዘልቀው በመግባት ግድያ ፈጸሙ። ታጣቂዎቹ በአኝዋ ዞን ዲማ ወረዳ በፈጸሙት ጥቃት፣ አንድ ሰው ገድለው ሌላ አንድ ሰው ማቁሰላቸውን የክልሉ መንግሥት መናገሩን ዶይቸቨለ ዘግቧል። የክልሉ ጸጥታ ኃይሎች ከታጣቂዎቹ ጋር ባደረጉት ተኩስ ልውውጥ፣ አምስት ታጣቂዎች ተገድለዋል መባሉን ዘገባው ጠቅሷል። የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል ሰዎችን እንደሚገድሉ፣ ሕጻናትን አፍነው እንደሚወስዱና ከብቶችን እንደሚዘርፉ በተደጋጋሚ ሲነገር ቆይቷል።
የካቲት 22/2015 ዓ.ም
====================
ወደ መቀሌ አቀኑ‼️
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት ወደ መቐለ አቀኑ።
ቅዱስነታቸው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትንና ሊቃውንትን አስከትለው በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት ወደ መቐለ ሲጓዙ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የኒውዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው ከቅዱስነታቸው ቡራኬ ተቀብለዋል ።
ምንጭ: ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
የካቲት 22/2015 ዓ.ም
==================
ከደቡብ ሱዳን ድንበር የተሻገሩ ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል ጥቃት ማድረሳቸው ተሰማ‼️
የደቡብ ሱዳን ሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ ውስጥ ጥቃት ማድረሳቸውን የጋምቤላ ክልል ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል፡፡
ጥቃቱ ቅዳሜ የካቲት 18 ምሽት ላይ በዲማ ወረዳ ቦይ ቀበሌ የደረሰ እንደሆነ ያስታወቁት የቢሮው ምክትል ኃላፊ ኡቶው ኡኮት፣ ታጣቂዎቹ ባደረሱት ጥቃት አንድ ሰው መግዳላቸውንና ሌሎች ጉዳቶችን ማድረሳቸውን ተናግረዋል፡፡
በታጣቂ ቡድኑ ላይ በአጸፋው በተወሰደ ምላሽ አምስት ታጣቂዎች እንደተገደሉ የተሰማ ሲሆን፣ ሦስት ክላሽንኮቭ መሳሪያ መማረኩ ተነግሯል፡፡ ይህንን የአጸፋ ምላሽ የወሰዱት የአካባቢው ሚሊሻዎች እንደሆኑም ተሰምቷል፡፡
የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል ተደጋጋሚ ጥቃቶችን የሚያደርሱ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ በተለይም በበጋ ወራት ድንበር እያለፉ በርካታ ጉዳቶችን ያደርሳሉ፡፡
በክልሉ ካለው የመንግሥት መደበኛ የጸጥታ ኃይል በተጨማሪ የኃይል ድጋፍ እንደሚያስፈልግ የተናገሩት ምክትል ኃላፊው፣ በአካባቢው ያሉ ሚሊሻዎች ታጣቂዎችን ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
በጋምቤላ ክልል ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን የሚጋሩት ድንበር ሰፊ የሚባል በመሆኑ ሌሎች ተመሳሳይ ጥቃቶች ሊፈጸሙ እንደሚችሉ የተናገሩት ምክትል ኃላፊው፣ በተለይም በአኙዋና ኑዌር ዞኖች ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈጸም የአካባቢው ሚሊሻና ኅብረተሰብ በንቃት አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ከዓመታት በፊት በኑዌር እና አኙዋ ዞኖች ውስጥ በመግባት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሕፃናት አፍነው የወሰዱት የሙርሌ ታጣቂዎች፣ ከ170 በላይ ሰዎች መግደላቸው ይታወሳል፡፡
ታጣቂዎቹ ወደ ጋምቤላ ክልል በመግባት በነዋሪዎች ላይ ከሚፈጸሙት ጥቃት በተጨማሪ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የቀንድ ከብቶች በተደጋጋሚ ዘርፈው እንደሚወስዱ ይነገራል።
የካቲት 21/2015 ዓ.ም
==================
ከራያ የደረሰን መረጃ‼️
በራያ የተላያዩ አካባቢዎች ማለትም በኩኩፍቱ፣ፀአዳሜዳ፣መቻሬ፣በእንባጣራ፣ኡራኤል ሰፈር በሚባሉ ቦታዎች የህወሓት ታጣቂዎች በብዛት ሰፍረው ይገኛሉ ሲሉ ምንጮች ገልፀዋል። በእነዚህ አካባቢዎች ህወሃት አዳዲስ ስልጠናዎች እና ሰራዊት የማደራጀት ስራ ሰሞኑን ማየሉን ምንጮች ገልፀዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የህወሓት አመራሮች ለሰራዊታቸው እቅዳችን በስምምነቱ መሰረት እየሄደ ነው፣ የአማራ ልዩ ሀይል ከአላማጣ እና አካባቢው ሰሞኑን ይወጣሉ፣እኛ ተመልሰን ህዝባችንን እናስተዳድራለን የሚል አቅጣጫ ለሠራዊታቸው እንደሰጡ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።
በፃግብጂ አካባቢም ከሚሊሻዎች ጋር አልፎ አልፎ ትንኮሳ መኖሩን ተናግረዋል።
#እኛ-ግን-እንላለን-አማራ-እና-ትግሬ-ያለፈዉ_ይበቃችሃል-በጋራ-ሆናችሁ-ነዉ-መታገል-ያለባችሁ!!
©
የካቲት 21/2015 ዓ.ም
==================
መንግሥት ለአርሶ አደሩ የስንዴ መሸጫ ዋጋ አስገዳጅ ተመን አወጣ!
መንግሥት አርሶ አደሩ የስንዴ ምርቱን በመንግሥት ለሚተዳደሩ ኅብረት ሥራ ማኅበራት በተተመነላቸው ዝቅተኛ ዋጋ እንዳቀርቡ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ በአማራ ክልል አንድ ኩንታል ስንዴ 3 ሺሕ 200 ብር እንዲሸጥ መወሰኑን አዲስ ማለዳ የክልሉ ግብርና ቢሮ አረጋግጣለች፡፡
ቢሮው የክልሉ የስንዴ ግዥ አስተባባሪ ግብረ ኃይል በወሰነው ውሳኔ መሰረት፣ በገበያው ላይ የስንዴ ምርት መግዣ ዋጋ ከ3 ሺሕ 800 ብር እስከ 4 ሺሕ ብር የደረሰ መሆኑን ገልጾ፣ ለዋጋ ንረቱ ዋነኛ ምክንያት የስንዴ ነጋዴዎችና የዱቄት ፋብሪካ ነጋዴዎች የሚያደርጉት ግብይት ነው ብሏል፡፡
ክልሉ ለዋጋ ንረቱ ያስቀራል ያለውን ውሳኔ ያስተላለፈ ሲሆን፤ በዚህም በኅብረት ሥራ ማኅበራት በኩል የስንዴ ግዥ እስከሚጠናቀቅ እነዚህ አካላት ግብይት እንዲያቆሙ ቁጥጥር እንዲደረግበት ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡
አርሶ አደሩ የስንዴ ምርቱን በወጣለት ዋጋ መሰረት ለኅብረት ሥራ እንዳቀርብ ውሳኔ የተላለፈው በፌደራል መንግሥት ደረጃ መሆኑም ተሰምቷል፡፡ መንግሥት የአርሶ አደሩን የትርፍ ህዳግ ጨምሮ አንድ ኩንታል ስንዴ በ3 ሺሕ 200 ብር እንዲገዛ በገንዘብ ሚኒስቴር መወሰኑ ተጠቁሟል፡፡
ይህ ውሳኔ በሌሎች ክልሎችም የተላለፈ ሲሆን፣ በኦሮሚያ ክልል አርሶ አደሩ አንድ ኩንታል ስንዴ በ3 ሺሕ 500 ብር ለኅብረት ሥራ ማኅበራት እንዲያቀርብ ተወስኗል፡፡ ክልሉ ከአርሶ አደሩ በተመነው ዋጋ የገዛውን ስንዴ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር ለውጭ ገበያ አቀርበዋለሁ ላለው የስንዴ ገበያ ማቅረብ ጀምሯል፡፡
በወቅታዊ የስንዴ መግዣ ዋጋ እና ውሳኔው ተመጣጣኝ ባለመሆኑ የመሰረታዊ ሕብረት ሥራ ማኅበራት እና ዩኒየኖች የተቀመጠላቸውን አምስት በመቶ የትርፍ ህዳግ ጨምሮ ኩንታል በ3 ሺሕ 350 ብር ግዥ ይፈጽማሉ ተብሏል፡፡
የፌደራል መንግሥት ክልሎች ከአርሶ አደሩ በተቆረጠ ዋጋ ስንዴ እንዲገዙ የፋይናንስ አቅርቦት ያቀረበ ሲሆን፣ ለአማራ ክልል ስንዴ መግዣ ብቻ ገንዘብ ሚኒስቴር 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መላኩ ተሰምቷል፡፡
አርሶ አደሩ መንግሥት ያቀረበውን የዋጋ ተመን ላይ ቅሬታ እንዳለው፣ አዲስ ማለዳ ካነጋገረቻቸው አርሶ አደሮች ሰምታለች፡፡ ምንም እንኳን እንደየአካባቢው ቢለያይም መንግሥት የገበያ ዋጋ ከመተመኑ በፊት አንድ ኩንታል ስንዴ በነጻ ገበያ ከ4 ሺሕ እስከ 5 ሺሕ ብር ተሸጧል፡፡
አርሶ አደሩ ያመረተውን ስንዴ ለገበያ አቅርቦ እራሱ በወሰነው ዋጋ ነጻ በሆነ ሕጋዊ ገበያ መሸጥ እንዳይችል የመንግሥት ዋጋ ተመን ይከለክላል፡፡ መንግሥት ይህን የገበያ ገደብ የጣለው በተመነው ዋጋ ከአርሶ አደሩ ስንዴ ሰብስቦ ስንዴ ለውጭ ገበያ አቀርባለሁ ያለውን እቅዱን ለማሳካት መሆኑ ተሰምቷል፡፡
መንግሥት እንዳስታቀው ከኢትዮጵያ ፍጆታ የሚተርፍ የስንዴ ምርት ስላለ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ጀምሬያለሁ ብሏል፡፡ ይሁን እንጂ ብዙዎች ከመንግሥትን ሀሳብ በተቃራኒ፣ ከ20 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ተረጅ ሆኖ የውጭ ረጅዎችን እጅ በሚጠብቅበት ሁኔታና ብዙዎች በተራቡበት ሁኔታ ከፍጆታ ተርፎ ለውጭ ገበያ መቅረቡን አይቀበሉም፡፡
የካቲት 20/2015 ዓ.ም
==================
#እውነታው ኢቢሲ ከትናንት ጀምሮ "ኦፕን ማጋዚን የሚባል የህንድ መፅሄት በአፍሪካ የዲሞክራሲያዊ መሪዎችን ዝርዝር ይፋ አደረገ፣ ጠ/ሚር ዐቢይ አህመድን በ1ኛ ደረጃ ላይ አስቀመጠ" የሚል ዘገባ ይዞ ሲወዘውዘው ነበር።
የእሱን መረጃ ይዘው ደግሞ የሀገሬ የሶሻል ሚድያ ገፆች እና የዩትዩብ ቻናሎች ሲቀባበሉት ነበር። ከኢቢሲ በተጨማሪ አዲስ ሚድያ ኔትዎርክ፣ የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን ቢሮ፣ ኦቢኤን አማርኛ... ወዘተ መረጃውን ሲያጋሩ ነበር።
የመፅሄቱ ዋና ኤዲተር ኤስ ፕራሳናራጃን በዚህ ዙርያ መረጃ ለኢትዮጵያ ቼክ ማምሻውን ያደረሰ ሲሆን "እኛ እንዲህ አይነት መረጃ አላወጣንም፣ የእኛም ዘገባ አይደለም። ይህንን ልናረጋግጥላችሁ እንችላለን" የሚል ምላሽ ልኳል።
በዲጂታል መልኩ የታተሙ የመፅሄቱን የቅርብ ግዜ ህትመቶች የተመለከትኩ ሲሆን የተጠቀሰው አይነት መረጃ ይዘው እንዳልወጡ ማየት ይቻላል።
ከሁሉም የሚገርመው ግን የዚህ ሀሰተኛ መረጃ መነሻ በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ ዶ/ር አለሙ ስሜ ስም ተመሳስሎ በተከፈተ አንድ ሀሰተኛ የትዊተር አካውንት የተሰራጨ ሀሰተኛ መረጃ መሆኑን ማየት ይቻላል። ይህ አካውንት ደግሞ ሀሰተኛ እንደሆነ ኢትዮጵያ ቼክ በተከታታይ መረጃዎችን አቅርቦ ነበር።
ይቺን እንኳን ሳያጣሩ ለሚልዮን ተከታታዮች መረጃ ማቅረብ አይከብድም... ወይም እንደ ክበበው ገዳ አባባል "አይሰቀጥጥም"?
*በኢንቦክስ ጥያቄ ሲበዛ ጎራ አልኩ፣ አሁን ወደ social media break/detox
(ኤሊያስ መሰረት)
የባልደራስ ፓርቲ መሥራች እና ሊቀመንበር እስክንድር ነጋ በቡሬ ከተማ በፖሊስ ተይዞ ወደ ባህርዳር ከተማ መወሰዱ ተነግሯል።
ይህ ሁሉ እንግልት ለህዝብ ነው።
#መረጃ‼️
በአዲስ አበባ ሽሮሜዳ የሚገኙ የሀገር ባህል ልብስ መሸጫ ሱቆች በበላይ አካል ትዕዛዝ እየታሸጉ ነው።
የፊታችን የካቲት 23 የጥቁሮች ታላቅ የድል በዓል የሆነው የአድዋ በዓልን ለማክበር አዲስ አበቤ በታላቅ ጉጉት ላይ ይገኛል።
ይሁን እንጂ የድሉ መሃንዲስ የሆነውን የዳግማዊ አጤ ምኒልክ ምስል ያለበትነሰ፣አረንጓዴ ቢጫ እና ቀይ ያለበት እንዲሁም ሌሎች ተዛማጅ ልብሶች የሚሸጡ ሱቆች ናቸው እየተለዮ ከሰሞኑን መዘጋት የጀመሩት።
በሽሮሜዳ የሚገኙ ነጋዴዎች እና አዲስ አበቤዎች ላይ ይህ ድርጊት ታላቅ ቁጣ ፈጥሯል።
የካቲት 17/2015 ዓ.ም
==================
ኮሜርስ ለአዋሽ ባንክ‼️
የ80 ዓመቱን ባለታሪክ ተቋም አዋሽ ባንክ በባለስልጣናት ደጀንነት አፈርሶ ህንፃ ሊሰራበት መሆኑ ተሰምቷል።
አዲስ አበባ ከተማ ዋቢ ሸበሌ አከባቢ የሚኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ንግድ ስራ ትምህርት ቤት (ኮሜርስ) የተሰኘው የትምህርት ተቋም ፈርሶ ነው አዋሽ ባንክ ህንጻ ሊገነባበት መሆኑ የተሰማው።
ባንኩ ከዚህ ይህንኑ ታሪካዊ ተቋም አፍርሶ ህንጻ ለመገንባት ያደረገው ጥረት፣ የአገር ቅርስ ተቆርቋሪዎች ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት ከመፍረስ የተረፈ መሆኑን ያስታወሰው የአዲስ ማለዳ ዘገባ አሁንም ላይ በድጋሚ ህጋዊ መንገድን ባልተከተለ ሁኔታ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረከተውን አንጋፋ ተቋም ለማፍረስ ጫፍ መደረሱ ተሰምቷል፡፡
ጉዳዩ እንዳይሰማ ወይም ህዝብ ጆሮ እንዳይደረስ ለተቋሙ ሃላፊዎች ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ታውቋል። ጉዳዩ የባለሥልጣናት ፖለቲካዊ ውሳኔ እንደሆነ ተሰምቷል።
የካቲት 17/2015 ዓ.ም
==================
በስንዴ እጥረት ምክንያት የዱቄት ፋብሪካዎች ስራ እያቆሙ ነው ተባለ፡፡
መንግስት በስንዴ ምርት ላይ ከፍተኛ ለውጥ አምጥቼ ለኤክስፖርት ደርሻለሁ ቢልም የሃገር ውስጥ ፋብሪካዎች ግን በምርት አጥረት እየተቸገሩ እንደሚገኙ እየገለጹ ነው፡፡
በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የስንዴ ምርት በብዛት እንዲመረት ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ሲሆን ለኤክስፖርት የሚሆን ስንዴ እንዲያዘጋጁም ክልሎች ኮታ እንደተጣለባቸው ሲነገር ነበር፡፡
በቅርቡም ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በተገኙበት ከኦሮሚያ ክልል የስንዴ ምርትን ወደ ውጭ መላክ መጀመሩ አይዘነጋም፡፡
ይህ በሆነ ማግስት ግን የዱቄት፣ፓስታና መኮሮኒ አምራች ፋብሪካዎች የስንዴ ምርት እጥረት ገጥሞናል፤በዚህም ስራ ለማቆም ተገደናል ብለዋል፡፡
የዱቄትና የዱቄት ውጤቶች አምራቾች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ሙሉነህ ለማ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፤ ስንዴ በአሁኑ ወቅት ኮንትሮባንድ ሆኗል፤ማንም እንደፈለገ መግዛትም ሆነ መሸጥ አይችልም ብለዋል፡፡
መንግስት ለኤክስፖርት የሚሆን ስንዴን ለማግኘት ሲል ዩኒዮኖች ብቻ እንዲገዙ ፈቀደ፣ለዱቄት አምራቾችም በዩኒዮኖች በኩል ታገኛላችሁ ተባሉ፣በኋላም 12 ባለሃብቶች ተመርጠው ወደ ስራ ገቡ፣ዱቄት አምራቾች ግን ስንዴ ሊያገኙ አልቻሉም ብለዋል፡፡
ይህ ችግር ከተፈጠረ 2 ወራትን አስቆጥሯል የሚሉት አቶ ሙሉነህ፣አምራቾች በእጃቸው ያለችውን ስንዴ እየቆጠቡ ሲጠቀሙ ቆይተው አሁን ላይ ስራ ማቆም ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡በዚህም በዳቦ ላይ የሚስተዋለው ጭማሬ እንዳለ ሆኖ የ1 ኪሎ መኮሮኒ ዋጋ ከ40 ብር ወደ 80 ብር ከፍ እንዲል አድርጎታል ነው የተባለው፡፡
እንደ አቶ ሙሉነህ ገለጻ በአሁኑ ወቅት ስንዴ እንደ ኮንትሮባንድ ተቆጥሮ በየኬላዎች በፍተሻ እየተያዘ ነው፡፡ በዚህም አምራቾች ገዝተው መተቀም አይችሉም፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች መጋዘን ላይ ስንዴ የተገኘባቸው ዱቄት ፋብሪካዎችም ሆነ ነጋዴዎች በህገ ወጥ መንገድ ግብይት ፈጽማችኋል በሚል ወከባ እየደረሰባቸው እንደሚገኝም አንስተዋል፡፡
በመሆኑም ከሁሉም ነፊት የሃገር ውስጥ ፍላጎትን ማሟላት ይቀድማልና ችግሩን ለመፍታት መንግስት ትኩረት እንዲሰጥ አቶ ሙሉነህ ጠይቀዋል፡፡
(ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 )
የካቲት 15/2015 ዓ.ም
==================
በዓድዋ በዓል ላይ የጸጥታ ኃይሎች በፈጸሙት ድርጊት ተጠያቂ እንዲሆኑ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ጠየቀ፡፡
በ127ኛው የዓድዋ ድል በዓል ላይ በመንግሥት የጸጥታ አካላት የተፈጠረውን ችግር አስመለክቶ ባወጣው መግለጫ፣ የጸጥታ ኃይሎች ከገደብ ያለፈ ድርጊት ፈጽመዋል ብሏል፡፡
በበዓሉ ላይ አላስፈላጊ ኃይል የተጠቀሙ እና ከመጠን ያለፈ እርምጃ የወሰዱ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች፣ በሕግ ተጠያቂ ከመሆናቸው በተጨማሪ በሕግ አስከባሪዎች መሰል አደጋዎች እንዳይከሰቱ አስፈላጊ ሥልጠና ማግኘት አለባቸው ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ፣ በበዓሉ ላይ የተከሰቱትን ክስተቶች አስመልክተው በሰጡት ሀሳብ፣ የጸጥታ ኃይሎች በዓሉን ለማክበር በወጣው ሕዝብ ላይ ከልክ ያለፈ አላስፈላጊ ድብደባ፣ አስለቃሽ ጭስ፣ ጥይትና ሌሎች ከመጠን ያለፉ እምጃዎችን መውሰዳቸውን ጠቁመዋል፡፡
በተወሰደው እርምጃ በዕድሜ የገፉ አዛውንቶችና ህጻናት ሳይቀሩ ጉዳት ማስተናገዳቸውን ጠቅሰው፣ ቢያንስ አንድ ሰው መገደሉን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡
በርካታ ሰዎችም የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲሉ ኮሚሽነሩ አክለዋል፡፡
በምኒልክ አደባባይ የዓድዋን ድል ለማክበር፣ እንዲሁም በአቅራቢያው በሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ሃይማኖታዊ በዓል ለማክበር የተሰበሰበው ሕዝብ በኃይል መበተኑን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡
አሜሪካ ከቻይና ጋር ወደ ጦርነት መግባቷ እርግጥ ወደ መሆኑ መቃረቡን አስታውቃለች‼️
ዋሽንግተን ከቻይና ጋር ሊኖራት ስለሚችለው ጦርነትም እቅድ በማውጣት ላይ እንደምትገኝ ነው የተነገረው።
የአሜሪካ መከላከያ ሚንስትር ዋና ጸሀፊ ክሪስቲን ዋርሙዝ ጦርነቱ አይቀሬ መሆኑን የሚያሳይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ከቢጂንግ ጋር የሚደረገውን ጦርነት በድል ለመደምደምም አሜሪካ ተጨማሪ ወታደሮቿን በእስያ ለማስፈርና የበይነ መረብ ጥቃቶችን በስፋት ለማካሄድ ስለማሰቧ ዋና ጸሃፊው ተናግረዋል።
የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) መልእክት
የአክብሮት ሰላምታዬን በማስቀደም በሀገር ውስጥ እና በመላው ዓለም ለምትገኙ ውድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለ 127ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ የሚል መልዕክቴን ሳስተላልፍ በታላቅ ብሔራዊ ኩራት ነው::
የዘንድሮውን የ127ኛው የአድዋ ድል በአልን ስናከብር ሀገራችን ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ እንደ ሀገር የመቀጠል እጣዋ ከፍተኛ አደጋ ላይ የወደቀበት ወቅት መሆኑን አፅንኦት በመስጠት እና ቀደምት አባቶቻችን በታላቅ ተጋድሎ እና መስዋዕትነት ያቆዩልንን የጋራ ሀገራችንን ከመቼውም ጊዜ በላቀ የመጠበቅ እንዲሁም ከገጠማት እጅግ ፈታኝ የህልውና አደጋ የመታደግ ታላቅ ታሪካዊ ሃላፊነት እና አደራ በኛ ትውልድ ትከሻ ላይ መውደቁን ከግምት ውስጥ በማስገባት ሊሆን ይገባል::
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ቴዎድሮስ ካሳሁን
(ቴዲ አፍሮ)
ጉጂ‼️
በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ሻኪሶ ከተማ ዛሬ አዲሱን የክልሉን መንግስት ውሳኔ የሚቃወም ሰልፍ እየተከናወነ ይገኛል።
የካቲት 22/2015 ዓ.ም
==================
የኦሮሚያ ክልል መንግስት አዲስ የአስተዳደር ወሰን ባወጣ ማግስት በጉጂ ዞን በቦሬ ከተማ በተደረገ ተቃውሞ 4 ሰዎች በክልሉ የፀጥታ አካላት ተገድለዋል። እስከ ዛሬ የጉጂ ዞን ዋና ከተማ ሆኖ እያገለገለ ያለውን የነገሌን ከተማ እና የሊበን ወረዳን ከጉጂ ነጥቆ አስተዳደሩም ወደ አዶላ እንዲዞር ማድረጉን በመቃወም ነው።
የካቲት 22/2015 ዓ.ም
==================
በአዲስ አበባ የአድዋ ቲሸርት እንዳያትሙ በፖሊስ መከልከላቸውን ማተሚያ ቤቶች ገለፁ‼️
በአዲስ አበባ የሚገኙ ማተሚያ ቤቶች በሚቀጥለው ሐሙስ ለ127ኛ ጊዜ ለሚከበረው ለአድዋ በዓል ቲሸርት እንዳያትሙ በፖሊስ መከልከላቸውን ገልጸዋል፡፡
ከኢትዮጵያን አልፎ የጥቁሮች ኩራትና የነጻነት ተምሳሌት ተደርጎ የሚወሰደው የአድዋ ድል በዓል በየዓመቱ የካቲት 23 በተለይ በአዲስ አበባ በድምቀት ይከበራል፡፡ ይሁን እንጂ ዘንድሮ ለ127ኛ ጊዜ የሚከበረው ይኸው የአደዋ ድል በዓል ከወዲሁ ውዝግቦች ተነስተውበታል።
በዘንድሮው ክብረ በዓል ላይ ቲሸርቶቹን አትመው ለገበያ በሚያቀርቡ የህትመት ቤቶች ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተጽዕኖ እየደረሰባቸው መሆኑን አዲስ ማለዳ በዘርፉ ላይ ከተሰማሩ ሰዎች ሰምታለች ብሏል፡፡
ይህ ተጽዕኖ የሥራ ቦታ ከማሸግ፣ የቲሸርት ህትመት ሲያትሙ የተገኙ ሰዎችን እስከማሰር የደረሰ ሲሆን፣ በተለይ ከትላንትና ጀምሮ ፖሊስ በየማተሚያ ቤቱ እየዞረ ለማተሚያ ቤቶች ማስጠንቂያ ሰጥቷል፡፡
የካቲት 21/2015 ዓ.ም
==================
እስካሁን 72 አመራሮች ታግደዋል‼️
በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ከ72 በላይ አመራሮች መታገዳቸው ተሰምቷል። ለዚህ መነሻው ደግሞ ከጥር 14 ጀምሮ በቤተክርስቲያን ላይ የተከሰተውን ችግር ተከትሎ ቤተክርስቲያን ባስተላለፈችው መልዕክት መሰረት ጥቁር ለብሳችሁ ታይታችኋል፣አክራሪ ሃይማኖተኛ እና ብሄርተኝነትን አንፀባርቃችኋል በሚል ነው ከስራ የታገዱት ተብሏል። ሰሞኑን የወረዳ አመራሮች ግምገማ እየተካሄደ ሲሆን ግምገማው በሁሉም የወረዳ እና የቀበሌ አመራሮች ላይ እንደሚቀጥል ተሰምቷል። በዚህም በግምገማው መሰረት ተጨማሪ እግድ ሊኖር እንደሚችል ይገመታል።
የካቲት 20/2015 ዓ.ም
==================
ቦሌ ፋና ሸማቾች የህዝብ መዝናኛ ማእከል ፈረሰ፡፡
ላለፉት 50 አመታት ለህብረተሰቡ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ቦሌ ፋና ሸማቾች ማህበር መፍረሱን ኢትዮ ኤፍ ኤም በቦታው ተገኝቶ አረጋግጧል፡፡
ከዚህ በፊት ይህ የህዝብ መዝናኛ ማዕከል የመፍረሱ ጉዳይ ለማህበራቱ በተነገራቸው ሰዓት ከወረዳው ጋር ውጥረት ውስጥ መግባታቸው አይዘነጋም፡፡
ከ4ሺህ 500 በላይ አባላት ያሉት ይህ ማህበር ከዚህ ማዕከል በተጨማሪም ሌሎች የመዝናኛ ማዕከላትን እያስተዳደረም ይገኛል፡፡
መዝናኛ ማዕከሉ በውስጡ የቴኒስ ሜዳዎችና የሠርግ አዳራሾች የነበረው ሲሆን፣ 17/19 መዝናኛ ማዕከል ብቻ 207 ሠራተኞች ነበሩት፡፡
የሙዚቃ ኮንሰርቶችን ጨምሮ የተለያዩ ሁነቶች የሚካሄዱበት የፋና ፓርክ የሚተዳደረው በ17/23 የመዝናኛ ማዕከል ሥር ነው፡፡
ማዕከላቱ የሚገኙበት የቦሌ ወረዳ ሦስት የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽሕፈት ቤት፣ ፓርኮቹን ለሚያስተዳድረው ለቦሌ ፋና ሸማች በጻፈው ደብዳቤ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ መጋቢት 17 ቀን 2014 ዓ.ም መሬቱ እንዲሰጠው መጠየቁን አስታውቆ ነበር፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ በፋና ሸማቾች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ሥር የሚተዳደሩት 17/19 እና 17/23 መዝናኛ ማዕከላትን መሬት፣ ሞል፣ አፓርትመንት፣ እንዲሁም ለባለአምስት ኮከብ ሆቴል ግንባታ፣ ለኢንቨስተሮች ለመስጠት እንደሚፈልግ በደብዳቤው ጠይቆ እንደነበር ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
ደብዳቤው እንደሚያስረዳው የሁለቱ መዝናኛ ማዕከላት፣ መሬቱ የተፈለገው በኤምደብልዩኤስ (MWS) ትሬዲንግ ለሚገነባ ሞልና አፓርትመንት፣ እንዲሁም በበቀለ ለገሰና አገሩ አበበ ለሚገነባ ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ነው ተብሏል፡፡
የማህበሩ አባላት ቦታው ማልማት ከተፈለገም የማልማት አቅም እንዳለቸው ተናግረው፣ የህዝብ መተንፈሻ የሆነን ማዕከል ማፈረስ ለህዝቡ አለማሰብ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ቦሌ ሸማች መዝናኛ ማዕከል ፊት ለፊት አስገንብቷቸው የነበሩ ሱቆች እንዲሁም ለህዝቡ አገልግሎት ይሰጥባቸው የነበሩ አዳራሾች እየፈረሱ እንደሚገኙ አትዮ ኤፍ ኤም ቦታው ድረስ ተገኝቶ አረጋግጧል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም ማዕከላቱ የሚገኙበት የቦሌ ወረዳ ሦስት የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ስለዚህ ጉዳይ ማብራሪያ ለማግኘት የወረዳው ሃላፊዎችን በስልክ ለማግኝት ተደጋጋሚ ሙከራ ያደረግን ቢሆንም ሊሳካልን አልቻለም፡፡
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 20 ቀን 2015 ዓ.ም
ሰበር ዜና!!!
ቴዲ አፍሮ 1,000.000.00 ብር ለቦረና
#ዓድዋ_127_ለቦረና
ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ ለዘንድሮ የዓድዋ ድል በዓል መታሰቢያ ለቦረና ወገኖች አስቸኳይ ድጋፍ የሚውል 1,000,000.00 (አንድ ሚልየን) ብር ለግሷል።
የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ቴዲ አፍሮ የዘንድሮን የዓድዋ ድል በዓል መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ በድርቅ ሳቢያ አስቸኳይ እርዳታ ለሚፈልገው የቦረና ሕዝባችን የ1ሚልየን ብር ድጋፍ አድርጓል።
በዳግማዊ አፄ ምኒልክ መሪነት መላው ኢትዮጵያዊ በአንድነት ዓድዋ ላይ ወራሪን ድባቅ በመምታቱ በዓለም የነጻነት መድብል ውስጥ ኢትዮጵያ የታሪክ ማማ ላይ መስፈር ችላለች። 127ኛው የዓድዋ ድል በዓል በምናከብርበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያዊያን ኹሉ በትብብር እና በአንድነት በመቆም የአያቶቻችንን አደራ መጠበቅ ይገባናል።
በዘንድሮው የዓድዋ ድል በዓል እንደ ወትሮው ኹሉ የአፍሪካ የነጻነት ፈር ቀዳጅ የጥቁር ሕዝብ ኹሉ ኩራት በሆኑት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ አደባባይ ላይ ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ እንደሚያከብር በመተማመን ሕዝባችን በዓሉን በታልቅ ክብር ሲዘክር የዓድዋ ጀግኖችን አንድነት በመውረስ በድርቅ ሳቢያ ለችግር የተጋረጠውን የቦረና ሕዝባችን በአስቸኳይ እንዲታደግ ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል።
ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ ለዚህ ዘመቻ የመጀመሪያውን 1,000,000.00 (አንድ ሚልየን) ብር በመለገስ ፈር ቀዳጅ በመኾኑ የተሰማንን ኩራት እና ደስታ ለመግለጽ እንወዳለን።
በዝርዝር እንመለስበታለን።
Via - ያሬድ ሹመቴ
#ዓድዋ_127_ለቦረና
የማይበላሹ ደረቅ ምግቦችን በመያዝ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማሕበር ልገሳዎቻችሁን ይዛችሁልን ኑ!!!
#ዓድዋ_127_ለቦረና
#BORENA
#Ethiopia
#Guzo_Adwa
#ቅድሚያ_ለሰብአዊነት
#የሰብአዊ_ድጋፍ_ጥምረት
#የኢትዮጵያ_ቀይ_መስቀል_ማኅበር
#Ethiopia | ከእስክንድር ነጋ ባለቤት ወ/ሮ ሰርካለም ፉሲል የተላለፈ ጥሪ
ለወራት ከሕዝብ ዕይታ ተሰውሮ የነበረው አንጋፋው ጋዜጠኛ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እንዲሁም የባልደራስ ፓርቲ መሥራች እና ሊቀመንበር ሆኖ ያገለገለው እስክንድር ነጋ በጎጃም ክፍለ ሃገር በቡሬ ከተማ በዐማራ ልዩ ኃይል ፖሊሶች ተይዞ ወደ ባህርዳር ከተማ መወሰዱ ተነግሯል።
.***
ከእስክንድር ነጋ ባለቤት ወ/ሮ ሰርካለም ፉሲል የተላለፈ ጥሪ
ለመላው ኢትዮጵያውያን ለአማራ ክልል መንግስት!
"እስክንድር ዘመኑን ሙሉ አንድ ቀን እንኳ እፎይ ሳይል ቤቱንና ልጁን ከሃገርና ሕዝብ አይበልጥብኝም ብሎ ሲከፍል ስለኖረው መስዋዕትነት ሁሉም የሚያውቀው ጉዳይ ነው።
እስክንድር በሃገሪቱ ለመጣው ለውጥ የራሱን አሻራ ያኖረ ቢሆን ም በግ*ር*ግር ስልጣን የያዘው ተረኛ ዘረኛው የኦሮሙማ መንግስት ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መልኩ እስክንድር የሚያደርገውን ትግል እንዲያካሂድ እድል ነፍጎታል።
በሕይወትም እንዳይቆይ ለማጥፋት የነበረውን እቅድ እስክን ድር አስቀድሞ በማወቁ ከከተማ ተሰዶ በገጠር እንዲቀመጥ አስገድዶት ቆይቷል።
በዛሬው ዕለት በአማራ ክልል ልዩ ኃይል እስክንድር መታሰሩን ተረጋግጧል። መታሰር ለእስክንድር አዲስ ባይሆንም የአማራ ክልል መንግስት ለዘረኛውና ለተረኛው የኦሮሙማ የፌዴራል መንግስት አሳልፎ እንዳይሰጠው በጥብቅ አደራ ማለት እፈል ጋለሁ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም መላው የአማራ ሕዝብ እስክንድር ለገዳዮች ተላልፎ እንዳይሰጥ በነጻም እንዲለቀቅ በሚቻለውና ባለህ አቅም እንድትረባረብ እንጠይቃለን።"
ሰርካለም ፋሲል
አድዋን የማራከስ አቅም የላቸውም!
እነ አጤ ምኒልክ እንዳይወሱ መድረኩን እያጨናንቀው ብለዋል። አድዋን በችርቻሮ
ሊሸጡት፣ መትረው ሊከፋፈሉት ይሞክራሉ። አድዋማ ግዙፍ ነው።
ይህ እየተሰራ ያለው ታቅዶበት ነው። "ውሃብያ" የተባለው ውርጋጥ ቡድን ከኦነግ ተራኪዎች ጋር ሆኖ ታሪክን ለመካፈል በእቅድ እየሰራ ይገኛል። ይህ ቁጭ ብለው አስበውበት፣ ኮሚቴ ተዋቅሮ፣ ሚና ተከፋፍለው የሚሰሩት ነው። አጤ ምኒልክና ጣይቱ የማይነሱበት አድዋ ፈልገው ነው። ደማቁ የአድዋ ክብረ በዓል ስለሚያስደነግጣቸው በየፊናቸው ከፋፍለው ሊያቀዘቅዙት ነው ፍላጎታቸው። ግን አይሳካም። አድዋ ግዙፍ ነው።
የማንነት ችግር በሚያንቆራጥጣቸው፣ በዓለም ያሉ ጥቁሮችን የሚያኮራ የአገራቸው ታሪክ በሚያስቀይማቸው በየጓዳው ተሰብስበው የሚያሳንሱት አይደለም።
ጦርነቱ ዛሬ ቢሆን ውሃብያና የኦነግ ፖለቲከኞች የበአድዋ ድል የተሳተፉት ጀግኖች ይልቅ ወራሪውን ይመርጣሉ። የታሪክ ድርሻን እንቦጭቅ ብለው የሚሰሩት እነዚህ ጉዶች እነ ሞሶሎኒ በህይዎት ቢኖሩ "ምን እናድርግ?" ብለው ሚና ይከፋፈላሉ።
ባለፈው የአፋርና አማራ ሙስሊም ሲጨፈጨፍ፣ መስጊድ ሲያቃጥል፣ ሸሆችን በግድ አረቄ ሲግታቸው እነ አህመድን ሙፍቲን ላይ ሴራ እየሸረቡ የድብቅ ስልጠና እየሰጡ ነው። ስልጠናዎቹን በቪዲዮ ጭምር ማጋራቴ ይታወሳል። የድሮው ፋሽስት ቢመጣ አሁንም በጓዳ ለጠባብ ቡድን ጥቅም ይዶልታሉ እንጅ የአገር ዳር ድንበርና ሉአላዊነት አያገባቸውም። አሁን አድዋን አከብራለሁ ብሎ በትንንሽ አዳራሽ የተቀመጠው ቡድን ድል ያደረጉ የኢትዮጵያ ነገስታትን ሲወቅስ የሚውል፣ ከአድዋ አላማ ጋር የተጠላ ነው። አድዋን ሊያከብሩት ሳይሆን ሊያረክሱት ነው የፈለጉት። አድዋ ወርቅ ነው። በውሃብያና ኦነግ ጭቃ የማይበላሽ ዓለምን ያስደመመ፣ ታሪክን የቀየረ ታሪክ ነው። ሰድበውት አልሆንላቸው ሲል፣ የእኛ አስመስለን እናበላሸው ብለው ነው። ግን ግዙፍ ነው። ተሸክመው መቅበር አይችሉም! አይደለም ይህ በማንነት ደዌ የሚሰቃይ በታችነት ስሜት ሞክሮት አድዋን ምዕራባውያን ሞክረው፣ ሞክረው አላራከሱትም።
(ጌታቸዉ ሽፈራዉ)
በአዲስ አበባ ዙሪያ በዘመቻ በተካሄደው የቤት ፈረሳ በርካታ ዜጎች ሜዳ ላይ ወድቀናል ሲሉ ገለጹ
ባለፉት ተካታታይ ሳምንታት በአዲስ አበባ እና በቅርቡ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ አካባቢዎችን አካቶ በተመሰረተው ሸገር ከተማ፣ በዘመቻ በተካሄደው ቤት የማፍረስ ተግባር በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን መጠለያ አጥተው ሜዳ ላይ መበተናቸውን አዲስ ማለዳ ከችግሩ ሰላበዎች ሰምታለች፡፡
ምንም አንኳን ከዚህ ቀደም መንግሥት ሕገ ወጥ ወይም የጨረቃ ቤት ያላቸው ቦታዎች ላይ የሚሰሩ ቤቶችን የሚያፈርስ ቢሆንም፣ የሰሞኑ ቤት ፈረሳ በአራቱም ማዕዘን በዘመቻ የተካሄደ ነው ተብሏል፡፡
በዚህ ቤት የማፍረስ ዘመቻ መንግሥት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአካባቢው ቤቶችን ማፍረሱ በርካታ ህጻናትና ሴቶችን ጨምሮ ኑሯቸውን በሜዳ ላይ እንዳደርጉ አስገድዷቸዋል። ከሰፈረሰባቸው ሰዎች መካከል የተወሰኑት ወደ ዘመድ የመጠጋትና ቤት የመከራየት ዕድል ቢያገኙም አብዛኛዎቹ ግን ሜዳ ላይ ተበትነው እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡
ምንም እንኳን የፈረሱ ቤቶች ሕገ ወጥ ናቸው ተብሎ መፍረስ ካለባቸው እንኳን እንደ ዜጋ ማረፊያ የመፈለጊያ ጊዜ ተስጥቶ በአግባቡ መሆን እንደነበረበት ሜዳ ላይ ተበትነናል ያሉት ሰዎች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡
ማንኛውም ዜጋ መጠለያ የማግኘት ሰብዓዊ መብት ያለው ቢሆንም፣ በአዲስ አበባና ዙሪያዋ መንግሥት ሕገ ወጥ ናቸው ብሎ ባፈረሳቸው ቤቶች ምክንያት የዜጎች መጠለያ የማግኘት ሰብዓዊ መብት ጥሰት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ሰለመሆኑ ቢሰማም፤ መንግሥት ድርጊቱን ቀጥሎበታል፡፡
አዲስ ማለዳ
የካቲት 17/2015 ዓ.ም
==================
“…እንኳን መታገድ መሞት አለ”
**
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የህግና ቴክኒክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የድጋፍና ክትትል ቅሬታ አቤቱታ አፈታት ስራ አመራር ባለሙያ የሆኑት በለጡ ዘለቀ በፌስ ቡክ ገጻቸው ከስራና ደሞዝ መታገዳቸውን የሚገልፀውን ደብዳቤ አያይዘው ከዚህ በታች የሰፈረውን መልእክታቸውን አጋርተዋል።
👉🏾“የአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ጥቁር ልብስ ለብሳችሁ ቢሮ አትገቡም ለምን ተባልን በሚል ድምፄን በማሰማቴ ከስራና ደመወዝ የሚያግድ ደብዳቤው በተፃፈ በ13 ቀኑ ዛሬ ማገጃው ደርሶኛል እንኳን መታገድ መሞት አለ።”