አዲሱ የጉራጌ ፓርቲ ተመሰረተ‼️
አዲሱ ጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትህ ፓርቲ አገር ዓቀፍ ፓርቲ ሆኖ ትናንት በአዲስ አበባ በይፋ ተመስርቷል። ፓርቲው ትናንት ባካሄደው የምስረታ ጉባኤ፣ የጉራጌ ሕዝብን የክልልነት ጥያቄ ባጭር ጊዜ ውስጥ እውን ለማድረግ እና የጉራጌ ሕዝብ በአገሪቲ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መስኮች ጉልህ አስተዋጽዖ እንዲያደርግ በርትቶ እንደሚሠራ ከምስረታው ቀደም ብሎ የምስረታ ኮሚቴው ለዋዜማ ተናግሯል። ፓርቲው የምስረታ ጉባኤውን ያካሄደው፣ ምርጫ ቦርድ ጊዜያዊ እውቅና ከሰጠው ከጥቂት ወራት በኋላ ነው። የፓርቲው መስራች ጉባኤ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱን የመረጠ ሲሆን፣ የፓርቲውን መተዳደሪያ ደንብና የፖለቲካ ፕሮግራም አጽድቋል።
መጋቢት 4/2015 ዓ.ም
================
መረጃ‼️
ሰሞኑን በአማራ ክልል በኦሮሚያ አስተዳደር ልዩ ዞን ውስጥ በተለያዩ ሰዋራ እና በረሃማ አካባቢዎች ኦነግ ሸኔ ስልጠናዎችን እያካሄደ እንደሚገኝ የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በዚህ አካባቢ ካሁን በፊት በተፈጠረው የፀጥታ ችግር እና ጉዳት የሚታወቅ ስለሆነ ጥንቃቄ ቢደረግ መልካም ነው እንላለን።
መጋቢት 4/2015 ዓ.ም
====================
ከኢትዮጵያ ወደ አረብ ሀገር ሄደው የሚሰሩ እህቶቻችን ዝቅተኛ ክፍያ‼️
ወደ ሳኡዲ የተላኩ ኢትዮዽያዊያን የቤት ሰራተኞች ስፖንሰር ከሁሉም አገራት ዝቅተኛ ክፍያን በያዘ ዋጋ ነው የተላኩት። ከዚህ በታች በምስል እንደምታዮት ከሆነ አንዲት ኢትዮዽያዊ የቤት ሰራተኛ ለመውሰድ 6,900 የሳኡዲ እሪያል ብቻ ነው የሚከፍሉት።
አንዲት የኢንዶኔዥያ ሰራተኛ ለመውሰድ 17ሺ 288 ሪያል ሲከፍሉ አፍሪካዊቷ የኬኒያ ልጆች ደግሞ 7500 ሪያል ይከፈላቸዋል። ከሌሎች አገሮች ሲሰላ የሀገራችን ልጆች ከኬኒያ በ100ሪያል ዝቅ ባለ የክፍያ ዋጋ ይይዛሉ በመሰረቱ ይህ ክፍያ አሁን ባለው ኢኮኖሚ ምንም አይነት ጥቅም የሚያስገኝ ሳይሆን ዜጋን በግልፅ አጫርቶ የመሸጥ ያህል ነው። ስለዚህ ነውር ግን አንድም ትንፍሽ ያለ አመራር የለም።
(ሱሌማን አብደላ)
መጋቢት 4/2015 ዓ.ም
====================
በኦሮሚያ ክልል የጉጂ ዞን የአገር ሽማግሌዎችና አባ ገዳዎች አዲስ በተዋቀረው ምሥራቅ ጉጂ ዞን ላይ ያላቸውን ቅሬታ ለፌደራሉና ለክልሉ መንግሥት ማቅረባቸውን ትናንት አዲስ አበባ ላይ በሰጡት መግለጫ መናገራቸውን ተዘግቧል። የአገር ሽማግሌዎቹ፣ የክልሉ መንግሥት የአዲሱን የምሥራቅ ቦረና ዞን ስያሜ እለውጣለሁ ማለቱን ሽማግሌዎቹ ተናግረዋል። አዲሱ ምሥራቅ ቦረና ዞን በቅርቡ የተደራጀው፣ ከቦረና፣ ጉጂ እና ባሌ ዞኖች አንዳንድ ቦታዎችን በማካተት ሲሆን፣ ሦስቱ ዞኖች ተመካክረው የዞኑ ስያሜ እንደሚቀየር እንደተነገራቸው የአገር ሽማግሌዎቹ ገልጸዋል። የጉጂ ዞን ዋና ከተማ ነገሌ ቦረና በአዲሱ ዞን ስር መካለሏንና ጉጂ ዞን ዋና ከተማውን አዶላ ሬዴ ላይ እንዲያደርግ የተወሰነውን ውሳኔ በመቃወም፣ በጉጂ ዞን የተቃውሞ ሰልፎችን ሲያደርጉ ሰንብተዋል።
መጋቢት 1/2015 ዓ.ም
====================
ከጋርመንት አካባቢ ከ100 በላይ ባጃጆቻንችን ተጭነው ወዴት እንደተወሰዱ አናውቅም ሲሉ የባጃጅ ባለንብረቶች ገልፀዋል። የባጃጅ ሹፌሮቹም እየተፈለጉ እየታሰሩ ነው።
የካቲት 30/2015 ዓ.ም
====================
#ሲዳማ‼️#ጭሬ❗
በጭሬ ወረዳ የሲዳማና ኦሮሚያ አዋሳኝ አከባቢዎች በተነሳዉ ግጭት የሲዳማ ተዎላጆች መሞታቸዉን ምንጮች ገለጹ‼️
በጭሬ ወረዳ በሲዳማና ኦሮሚያ አዋሳኝ አከባቢዎች በተነሳ ግጭት ሕዝቦች ለሞት፤ ለስደትና ለተለያዩ ሰብዓዊ ችግሮች ላይ መዉደቃቸዉን ምንጮች ገልፀዋል።
የካቲት 30/2015 ዓ.ም
====================
• ግባችን ~ 200 ሺ ዶላር ነው።
• እስከ አሁን 260 ደጋግ ነፍሶች 31,174 ዶላር ለግሰዋል።
• ይሄ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የገባው ሳይቆጠር የሆነ ነው። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…ስጡ… ስጡ…ስጡ…! እግዚአብሔር ይስጣችሁ።
https://gofund.me/9f5c8ff8
• የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ 1000525914619
ምስጋናና ብርታት ይሁን !!
---------------------------
-------- #ሼር አድርጉት #አዛምት
ኮሜዲያን እሸቱ ፣ ያሬድ ሹመቴ፣ ሚካኤል ሚሊዮን፣ አርቲስት ሸዊት እና ሌሎች በርካታ አርቲስቶች ያስተባበሩትን የመቄዶኒያን ፕሮጀክት የመርጃ ፕሮግራም በማዋጣትም ሆነ ሊንክ ሼር በማድረግ የተሳተፋችሁ፣ በየሚዲያው ያስተዋወቃችሁ። ሁላችሁም ምስጋና ይገባችኋል።
------
💚💛❤
አሁን የምትችሉት ሁሉ ተሳተፉ…
አገር ውስጥ በ7979
----
GOFUND ME : https://gofund.me/216b39ce
----
Cash App: 240-840-6256
----
Zelle: 240-840-6256
----
WEGEN FUND : https://www.wegenfund.com/causes/lamaqeedoneyaa-hhenetsaa-bare-enaa-masekote-eneget/
ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ - የ2023 ‹‹የዓለም አቀፍ የጀግና ሴቶች ሽልማት›› (International Women of Courage/IWOC Awards) አሸናፊ
#Ethiopia | መምህርት፣ ጋዜጠኛና አክቲቪስት መዓዛ መሐመድ የ2023 የ‹‹ዓለም አቀፍ የጀግና ሴቶች ሽልማት (International Women of Courage/IWOC Awards)›› አሸናፊ ሆናለች፡፡
‹‹ዓለም አቀፍ የጀግና ሴቶች ሽልማት›› በመላው ዓለም ከባድ አደጋዎችንና ፈተናዎችን ተቋቁመው ሰላም፣ ፍትህ፣ ሰብዓዊ መብቶች፣ የፆታ እኩልነት እና የሴቶች ተጠቃሚነት እንዲከበሩና እንዲሰፍኑ ልዩ ጥንካሬ፣ ጀግንነትና የአመራር ጥበብ ላሳዩ ሴቶች የሚበረከት ሽልማት ነው፡፡
ሽልማቱ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚዘጋጅ ሲሆን፣ ዘንድሮ ለ17ኛ ጊዜ የሚካሄድ ይሆናል፡፡ እስካሁን ድረስም ከ80 ሀገራት የተገኙ ከ180 በላይ ጀግና ሴቶችን እውቅና ሰጥቷል፡፡ በዘንድሮው ሽልማት ከአራት አህጉራት የተገኙ 11 ጀግና ሴቶች እና አንድ የሴቶች ቡድን እውቅና ይሰ’ጣቸዋል፡፡
ለሽልማቱ የሚመረጡት ሴቶች የሚታጩት በየሀገራቱ በሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች ሲሆን፤ የመጨረሻዎቹ አሸናፊዎች የሚመረጡት ደግሞ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣናትና ባለሙያዎች ነው፡፡ የሽልማቱ አሸናፊዎች "International Visitor Leadership Program (IVLP)" በተባለው መርሃ ግብር በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች በመዘዋወር ከሴቶች አደረጃጀቶች አመራሮች ጋር ይወያያሉ፤የልምድ ልውውጥ ያደርጋሉ፡፡
የ2023 የ‹‹ዓለም አቀፍ የጀግና ሴቶች ሽልማት (International Women of Courage/IWOC Awards)›› አሸናፊዎች፡-
1. ዶ/ር ዘካሪያ ሒክመት (አፍጋኒስታን) - [በቱርክዬ የሚኖሩ]
2. አልባ ሩዳ (አርጀንቲና)
3. ፕ/ር ዳንኤላ ዳርላን - መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ
4. ዶሪስ ሪዮስ - ኮስታ ሪካ
5. መዓዛ መሐመድ - ኢትዮጵያ
6. ሐዲል አብደልአዚዝ - ዮርዳኖስ
7. ባክዛን ቶሬጎዚና - ካዛኪስታን
8. ዳተክ ራስ አዲባ ራድዚ - ማሌዢያ
9. ብ/ጀኔራል ቦሎር ጋንቦልድ - ሞንጎሊያ
10. ቢያንካ ዛሌውስካ - ፖላንድ
11. ዩሊያ ፓይቪስካ - ዩክሬይን
ሴት ኢራናውያን የተቃውሞ ሰልፈኞች [እንደቡድን] ደግሞ ‹‹የማድሊን ኦልብራይት መታሰቢያ የክብር ሽልማት››ን ይቀበላሉ፡፡
(ሙሉጌታ አንበርብር)
በኡጋንዳ የሚገኘው ሴሬሬ ከተማ ፖሊስ ከአንድ መቶ በላይ የቤተክርስቲያን አባላት ወደኢትዮጵያ ገብተው በመጥፋታቸው ምርመራ ማድረግ መጀመሩን አስታወቀ፡፡
የአካባቢው ፖሊስ ቃል አቀባይ ኦስካር አጌካ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስረዱት እነዚህ ሰዎች ወንጌልን ለመስበክ በሚል ምክንያት ወደኢትዮጵያ የሄዱት ‹‹ክሪስት ዲሲፕሊንስ ቸርች›› በተሰኘው የሀይማኖት ተቋም አማካኝነት ነው፡፡ በሁለት ፓስተሮች የተመሰረተውና የሚመራው ይህ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮቹን ‹‹እግዚአብሄር ወደኢትዮጵያ ሄዳችሁ ወንጌልን እንድታስፋፉ አዟል›› የሚል ስብከት መስጠቱን የገለፁት ቃል አቀባዩ ይህንን ስብከት ተከትሎ ካለፈው የፈረንጆች ወር ማለትም ፌብሩዋሪ አንስቶ ከመቶ በላይ ኡጋንዳዊያን የቤተክርስቲያኑ አማኞች ወደኢትዮጵያ መሄዳቸውን አስረድተዋል፡፡
ቃል አቀባዩ ሲናገሩ ‹‹በዚህ ጉዞ ላይ የተሳተፉት ሰዎች እያንዳንዳቸው ለጉዞ ሰነድ በሚል ሁለት ሚሊዮን ሽልንግ እንዲከፍሉ ተደርገዋል፡፡ ይህንን ያህል ገንዘብ ከፍለው አንድ ከረጢት ዱቄት ብቻ ይዘው ወደኢትዮጵያ ገብተዋል፡፡›› ካሉ በኋላ ይህንን ገንዘብ ለማሟላት አንዳንዶቹ ከብቶቻቸውን ወይንም ቤታቸውንና የቤት እቃዎቻቸውን መሸጣቸውን ገልፀዋል፡፡
እነዚህ ከአንድ መቶ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ወደኢትዮጵያ ከሄዱ በኋላ ድምፃቸው እንደጠፋና የት እንዳሉ እንደማይታወቅ የጠቆሙት ቃል አቀባዩ የቤተክርስቲያኑ ፓስተሮችም መሰወራቸውን አስታውቀዋል፡፡ አሁን በፓስተሮቹ ላይ በይፋ ክስ እንደተመሰረተና በፖሊስ እየታደኑ እንደሚገኙና ወደኢትዮጵያ የሄዱትንም ሰዎች ለመፈለግ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ መናገራቸውን ኢንዲፔንደንት ኡጋንዳ ዛሬ ዘግቧል፡፡
(ዘሐበሻ)
#Ethiopia #Amhara #Region
//የክልሉ መንግስት በቀደመው መንገድ መጓዝ አዋጭ አለመሆኑን በሚገባ አይቶ በሙሉ አቅሙ ስራ ላይ ገብቷል።በመሆኑም የክልሉ መንግስት የሚሰራቸውን ስራዎች በየአደባባዩ መናገር አያስፈልገውም //
- በአብክመ የር/መስተዳድሩ አማካሪ አቶ ደሳለኝ አስራደ
የካቲት 27/2015 ዓ.ም
====================
የኦሮሚያ ክልል በአዲስ መልኩ ባዋቀረው የከተሞች ሽግሽግ ምክንያት የጉጂ ነዋሪዎች ይሄን ውሳኔ በመቃወም ቤት የመቀመጥ አድማ ጀምረዋል። የመኪና እንቅስቃሴም ተገድቧል።
የካቲት 26/2015 ዓ.ም
====================
ራስ ጋይንት ትናንት በአድዋ በዓል ላይ መስዋዕት የሆነውን የመ/ር መኳንንትን አስከሬን ተቀብለዋል!
ታሪክህን በደማቁ ቀይ ቀለም ፅፍህ አልፈሃል።
ነፍስ ይማር ወንድማችን😥
ልዩ መረጃ‼️
በብፁዕ አቡነ አብርሃም የሚመራው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ቡድን ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ጋር ስብሰባ ተቀመጠ::
Inbox‼️
መቀመጫውን አዲስ አበባ ኡራኤል አካባቢ ያደረገው የኦሮሚያ ጤና ቢሮ እሳት ተነስቷል።
የካቲት 24/2015 ዓ.ም
የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር አንቶኒዮ ብሊንከን ነገ አዲስ አበባ እንደሚገቡ የአሜሪካ ኢምባሲ በኢትዮጵያ አሳውቋል።
መጋቢት 4/2015 ዓ.ም
====================
የፊታችን ረቡዕ አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንደሚካሔድ ተገለጸ‼️
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ረቡዕ መጋቢት 6/2015 አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ እንደሚካሄድ አስታውቋል።
በዚህም መሠረት ቅዱስ ሲኖዶሱ በአዲስ አበባ አቅራቢያና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት ከላይ በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ላይ በቅዱስ ሲኖዶስ አዳራሽ እንዲገኙ ጥሪውን ማቅረቡን የቤተክርስቲያኗ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ዘግቧል።
መጋቢት 4/2015 ዓ.ም
====================
የሰሜን ኮሪያው መሪ የሀገሪቱ ጦር ለእውነተኛ ጦርነት ዝግጅት እንዲያደርግ ትእዛዝ አስተላለፉ‼️
መሪው ኪም ጆንግ ኡን የሀገሪቱ ጦር የሚያደርገውን ወታደራዊ ልምምድ እና ሙከራዎች አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ማለታቸውን ኬ.ሲ.ኤን.ኤ ዘግቧል።
የሀገሪቱ የከባድ መሰሳሪያ ዩኒት ለሁለት ከፍተኛ ተልእኮዎች መዘጋጀት እንዳለበትም ነው መሪው በመልእክታቸው ያስታወቁት።
የመጀመሪያው ተልእኮ ጦርነትን ቀድሞ ተከላክሎ ማስቀረት ሲሆን፤ ሁለተኛው ተልእኮ ደግሞ ጦርነት ውስጥ የበላይት ለመውሰድ እንደሆነም አስታውቀዋል ነው የተባለው።
መጋቢት 3/2015 ዓ.ም
====================
በደራ ወረዳ ከፍተኛ ስጋት መስፈኑ ተነገረ‼️
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ተደጋጋሚ ጥቃት የሚያደርሰው ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን በወረዳው ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩን የአካባቢው ነዋሪዎች የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
በወረዳው ውስጥ በምትገኘው ባቡ ድሬ ቀበሌ በርካታ የሆኑ የሸኔ ታጣቂዎች ከተለያየ ቦታ እየመጡ መሰባሰባቸውን የተናገሩት ነዋሪዎቹ ከዚህ ቀበሌ ባሻገር ሰው በማይኖርባቸው በረሃዎች በርካታ ታጣቂዎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡
የሸኔ ታጣቂዎች አጎራባች ከሆኑ የሰሜን ሸዋ ወረዳዎች ወደ ደራ ወረዳ እየገቡ እንደሆነ የተናገሩት ምንጮች፣ የታጣቂዎቹ ብዛት ከዚህ በፊት ከታዩት የበለጠ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ይህም በነዋሪዎች ላይ ስጋት ፈጥሯል ያሉት ምንጮች፣ የሸኔ ታጣቂዎች ከዚህ በፊት በወረዳዋ ነዋሪዎች ላይ ከሚያደርሱት ጥቃት አንጻር ስጋቱ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል መንግስት ለሸኔ ታጣቂዎች ያቀረበውን ጥሪ በመቀበል እጃቸወን ለፖሊስ ከሰጡ ታጣቂዎች መካከልም የተሀድሶ ስልጠና ሳይሰጣቸው ከኅብረሰተቡ ጋር መቀላቀላቸውን የተናገሩት ምንጮች፣ በጉዳዩ ዙሪያ በመንግስት አካላት ጥንቃቄ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡
ከቀናት በፊት የወረዳው ነዋሪዎች በሸኔ ታጣቂዎች እየታፈኑ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን፣ የታፈኑት ሰዎች እስከ 300 ሺሕ ብር የሚደርስ የማስለቀቂያ ክፍያ እየተከፈለላቸው መለቀቃቸው ተሰምቷል፡፡
ባለፉት አስራ አምስት ቀናት ውስጥም ሌላ የአፈና ዜና ያልተሰማ ቢሆንም አሁንም ስጋቶች እንዳሉ ምንጮች ተናግረዋል፡፡
የካቲት 30/2015 ዓ.ም
====================
"ሰው ነው የሚናፍቀኝ...."
******
ባለፈው እሁድ ጋሽ ታዲዎስን ልንጠይቅ ወደ ቂሊንጦ ጎራ ብለን ነበረ። ፍተሻውን አልፈን ከገባን በኋላ ረዘም ያለ ጉዞ የሚጠይቀውን የታሰሩበትን ዞን ሶስት ስንቃረብ ጭርታው አንዳች ደስ የማይል ነገር ይናገራል። "ማንን ልጥራላችሁ?" አለን ከውጭ የቆመው ጠባቂ፣ ነገርነው፣ ገባብሎ ተጣራና ተመለሰ።
ጋሽ ታዲዮስ ብቅ አሉ። ፀጉራቸው ከማደጉ በቀር ደህና አካላዊ ሁኔታ ላይ ናቸው። በንቁ አይኖቻቸው ቃኜት ሲያደርጉ እጄን አነሳሁላቸው። ወዲያው ቀልጠፍ ብለው መጡ። እኔን ሰላም ብለውኝ አብሮኝ ያለውን እንግዳ ግራ በመጋባት ማየት ጀመሩ። እሳቸው እንደማያውቁት እሱ ግን የከፈሉለት ዋጋ ግድ ብሎት ሊጠይቃቸው እንደመጣ ነገራቸው "አመሰግናለሁ የኔ ጌታ" አሉ በትህትና። "ኧረ! እንኳን እርስዎን ቤተሰብም መጠየቅ ነበረብን" አላቸው። "ምን ቤተሰብ ጋ ብትሄዱ ሻይ ቡና ተፈልቶላችሁ ትመጣላችሁ ይሆናል እንጅ እነሱ ምን ጥየቃ ይፈልጋሉ ብለህ ነው አሉት"
ወዲያው ወደ እኔ ዞረው ስሜን ጠርተው "እንዴት ነሽ!መቼ ተፈታሽ?" አሉኝ። "ቆየሁ እኮ! እርስዎ እንዴት ነዎት?" አልኩኝ ። "አካል ይደክም ይሆናል እንጅ በመንፈስ ጠንካራ ነኝ፣ ስለጠየቃችሁኝ አመሰግናለሁ፣እዚህ ስንሆን ሰው ይናፍቀናል ፣እንዲህ ስትመጡና ስትጠይቁን ደስ ይላል" አሉኝ ጠያቂ በናፈቀ ቅላፄ። እዳ ተሰማኝ ፣ሃፍረት ነገርም ሽው አለኝ።
ቀጠሉ "እኔ ሰው ነው የሚናፍቀኝ፣ ፍትህማ ቢናፈቅስ ከየት ይገኛል? አሁን አሁን የሚያደርጉኝን ዝም ብዬ ማየት ጀምሬያለሁ" አሉኝ። አብሮኝ የመጣው ሰው በሃዘን አንገቱን ሲደፋ አየሁት ። ስለፍርድ ቤት ጉዳይ ጠየቅኳቸው። "አንዷ ተከላካይ ምስክር ነሽ፣ ክሱን ወስደሽ አንብቢና መጥሪያ ሲደርሰሽ መገኘት ነው፣ታለማ አልነገረሽም? " አሉኝ ፈርጠም ብለው ። ታለማ ጠበቃቸው ናቸው። "ነግረውኛል፣ እሽ እገኛለሁ" አልኩኝ ። አይበገሬነታቸው፣ንቁነታቸው ገረመኝ!!! "በሉ ሂዱ ይበቃል ፣ሲመቻችሁ ብቅ በሉ መቼም በቶሎ የሚለቀኝስ አልመሰለኝም" አሉ እንደመሳቅ ብለው። ሰው እንደናፈቃቸው አስተዋልኩ፣ልቤ አዘነ! "ፍትህ ከፈጣሪ ነው ይፈታሉ ፣እኔ መጥቼ እጠይቅዎታለሁ" ብዬ ተሰናብተን ወጣን።
ጠንካራው ሰው በእጅጉ ሰው ይናፍቃቸዋል፣ ለምን እንደታሰሩ የሚገባው፣ውለታ የሚከብደው ሁሉ ሊጠይቃቸው ይገባል። ማስፈታት በሰው እጅ ነው፣መጠየቅ ግን በእጃችን ነው!
(መስከረም አበራ)
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ነሰቦ ወረዳ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት በትንሹ 13 ሰዎች ተገደሉ‼️
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ነሰቦ ወረዳ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት በትንሹ 13 ሰዎች መገደላቸው ታውቋል።
በወረዳው ቦጬሳ በተባለ ቀበሌ ውስጥ የተፈጸመው ጥቃት በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መፈጸሙ የተነገረ ሲሆን፣ በደረሰው ጥቃት ከሞቱት ውስጥ አብዛኞቹ አርሶ አደሮች መሆናቸውን የአይን አማኞች ተናግረዋል፡፡
ግድያው የተፈጸመው ለስብሰባ ትፈለጋላችሁ በሚል በቀበሌው መስተዳድር ጥሪ ከተደረገላቸው በኋላ መሆኑን ከነዋሪዎቹ ተሰምቷል፡፡
አርሶ አደሮቹ በተሰበሰቡበት፣ ከተለያዩ አቅጣጫዎች በተከፈተው ተኩስ ሦስት ሰዎች ወዲያው መሞታቸው ታውቋል፡፡ የተቀሩት አሥር ሰዎች ደግሞ በመሸሽ ላይ እንዳሉ በጥይት ተመትተው መሞታቸውን ከዓይን እማኞች የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
በጥቃቱ በጥይት ተመተው የቆሰሉ በርካታ ሰዎች ሲዳማ ክልል ውስጥ ወደሚገኘው አጎራባች የጭሪ ወረዳ ጤና ጣቢያ መወሰዳቸውም ተጠቁሟል፡፡ ቀላል አካል ጉዳት የደረሰባቸው 28 ተጎጂዎች ሕክምና የተደረገላቸው ሲሆን፣ 11 ሰዎች ደግሞ ለተጨማሪ ህክምና ወደ ሀዋሳ ከተማና እና ቦና ወረዳ ሆስፒታሎች መላካቸው ተመላክቷል፡፡
የጥቃቱ መንስኤም በአካባቢዉ የሚኖሩ የሲዳማ ተወላጅ የሆኑ አርሶ አደሮችን፣ አካባቢውን ለቃችሁ ውጡ በሚል ምክንያት መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
የካቲት 29/2015 ዓ.ም
====================
አሊያንስ ፎር ኮፊ ኤክሰለንስ" የተሰኘው ዓለማቀፍ ኩባንያ ኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን የዘንድሮው የቡና ጥራት ውድድርና ጨረታ እንደማይካሄድ እንደገለጠለት አስታውቋል። የዘንድሮው ውድድርና ጨረታ የማይካሄደው፣ በኢትዮጵያ ባሉ "ነባራዊ ወቅታዊ ሁኔታዎች" ሳቢያ እንደሆነ ኩባንያው ገልጧል። ኩባንያው ባለፉት ሦስት ዓመታት ባካሄዳቸው የቡና ጥራት ውድድሮችና ጨረታዎች ለአርሶ አደሮች ሦስት ሚሊዮን ዶላር ማስገኘቱን ገልጧል። ባለፈው የአውሮፓዊያን ዓመት 1 ሺህ 741 የቡና ናሙናዎች ለውድድር ቀርበው፣ 1 ሚሊዮን 370 ሺህ ዶላር ግምት ያላቸው 30 ናሙናዎች ማሸነፋቸውንና አንድ ኪሎ ግራም ቡና የተሸጠበት ከፍተኛ ዋጋ 880 ዶላር እንደነበር ድርጅቱ ጠቅሷል።
Читать полностью…አማራ ክልል‼️
የአማራ ክልል ምክርቤት መደበኛ ጉባኤውን ነገ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል❗
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት 6ኛው ዙር 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባዔውን በነገው እለት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።
ምክርቤቱ በ5ኛ መደበኛ ጉባዔው የክልሉን የሴክተር መስሪያ ቤቶች እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አዳምጦ ይመክራል።
በተጨማሪም ምክርቤቱ በሌሎች ወቅታዊ ክልላዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክሮ የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ልዩ ልዩ ሹመቶችን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
የካቲት 28/2015 ዓ.ም
====================
ነገ በሁለት የጉጂ ዞኖች ትልቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠርቷል።
የኦሮሚያ ክልል አዲስ የዘረጋው የአስተዳደር መዋቅር ፣
ከፍተኛ ተቋሞ ገጥሞታል። ትናንተ ቤት የመቀመጥና ገበያ ያለመውጣት አድማ ተካሄዶ ነበረ።
ዛሬ በተነሳ ተቃውሞ ወጣቶች መገደላቸው ተሰምቷል።
አዲሱ ዞን የጉጂን መሬት አሳልፎ የሰጠ ነው፣ አላማከረንም በሚል ከፍተኛ ቁጣ አለ።
ይህ ተቃውሞ ከቀጠለ በድርቅ የተጎዳውን አካባቢ የእርዳታ እህል ማቅረብ ያስቸግረዋል።
መንግስት አፋጣኝ የውይይትና የሰላም መፍትሄ ይውሰድ እየተባለ ይገኛል።
Via:-ሙክታሮቪች
የካቲት 27/2015 ዓ.ም
====================
#China‼️
ቻይና ከታይዋን ጋር በሰላማዊ መንገድ መዋሃድ እንደምትፈልግ ገለጸች‼️
የቻይናው ጠቅላይ ሚንስትር ሊ ኬኪያንግ ከታይዋን ጋር “ሰላማዊ ውህደት” ለማድረግ ቃል ገብተዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ የታይዋንን ነፃነት በመቃወም ቆራጥ እርምጃዎችን እንደሚወስዱም ቃል ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚንስትር ሊ በቻይና ፓርላማ ዓመታዊ ስብሰባ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ቤጂንግ “አንድ ቻይና” በሚለው መርህ ላይ እንደምትጸና ገልጸዋል። መርሁ ታይዋን የቻይና አካል መሆኗን ይገልጻል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በንግግራቸው በቀጥታ ወታደራዊ እርምጃን በተመለከተ ያሉት ነገር የለም። መንግስት “የታይዋንን ጥያቄ ለመፍታት” የፓርቲያችንን ፖሊሲ ተግባራዊ በማድረግ “የታይዋንን ነጻነት በመቃወም ቆራጥ እርምጃዎችን በመውሰድ ዉህደትን መደገፍ አለበት” ሲሉ ወደ ሦስት ሽህ ለሚጠጉ ልዑካን ተናግረዋል። "ባህር ተሻጋሪ ግንኙነቶችን በሰላማዊ መንገድ ማጎልበት እና የቻይናን ሰላማዊ የውህደት ሂደትን ማሳደግ አለብን" ብለዋል።
ሮይተርስ እንደዘገበው አብዛኛው የታይዋን ህዝብ በቻይና የመግዛት ፍላጎት የለውም። ቻይናም ደሴቲቱን በእሷ ቁጥጥር ስር ለማድረግ የኃይል እርምጃ መጠቀምን ከአማራጮች ፈጽሞ አልተወችም ተብሏል።
የታይዋን ፕሬዚደንት ሳይ ኢንግ-ወን ከቻይና ጋር ለመነጋገር ደጋግመው ጥሪ ማቅረባቸው የተነገረ ሲሆን፤ ቤጂንግ ደሴቲቷን ተገንጣይ መሆኗን ስላመነች ውድቅ አድርጋለች ተብሏል።የታይዋን መንግስት የቤጂንግን የይገባኛል ጥያቄ አጥብቆ የሚቃወም ሲሆን፤ እጣ ፈንታዋን የደሴቲቱ 23 ሚሊዮን ህዝብ ብቻ ሊወስን ይችላል ብሏል።
" ለእኛም የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ይድረሱልን " - የዳዋ ዞን አስተዳደር
በሶማሌ ክልል ዳዋ ዞን አስተዳደር ባጋጠመ ድርቅ በርካታ እንስሳት የሞቱ ሲሆን የሰዎች ሕይወትም አደጋ ላይ መውደቁ ተገልጿል።
የዞኑ አስተዳደር ያለው ሁኔታ ከአቅም በላይ መሆኑን አስታውቋል።
ከኦሮሚያ የቦረና ዞን ጋር የሚዋሰነው ዞኑ፣ በድርቅ የተነሳ ከሚሞቱ እንስሳት አልፎ ሰዎች #ለሆስፒታል እየተዳረጉ መሆኑን ገልጿል፡፡
የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ሀቢቻ ለሪፖርተር የሰጡት ቃል ፦
" የድርቁ ጉዳት ከዞኑ አቅም በላይ ነው።
ዞናችን ከቦረና ጋር በሁለት ወረዳዎች በኩል ይዋሰናል፡፡ ወደ 700 ሺሕ የሚጠጋ አርብቶ አደር ነዋሪ ያለው ሲሆን፣ ለ3 ተከታታይ ዓመታት የደረሰው ድርቅ ከብቱን በሙሉ ጨርሶበታል።
በክልሉ አደጋ ሥጋት ቢሮና በተለያዩ የዕርዳታ ድርጅቶች ርብርብ ዘንድሮ ለድርቁ ተጎጂዎች ዕርዳታ እየቀረበ ነው ይሁን እንጂ ዕርዳታው በቂ አይደለም። ችግሩም ከአቅም በላይ ነው።
በኦሮሚያ ክልል ለሚገኘው ለአጎራባቻችን ቦረና ዞን በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ እንዳለው ሁሉ፣ ለእኛም የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ይድረሱልን። "
ዳዋ ዞን በሥሩ ሞያሌ፣ ሙባረክ፣ ካደዱማና ሁደት የተባሉ አራት ወረዳዎች ያሉት ሲሆን ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ዝናብ ባለማግኘቱ ትልቁ የዳዋ ወንዝ ጭምር ደርቋል።
ድርቅ የሚቋቋሙ ግመሎችን ጨምሮ ከብቶችና ፍየሎች በከፍተኛ ቁጥር ማለቃቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።
እነዚህ 6'ቱ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት ዮሴፍ አስማረ (ጆሲ)፣ ማርሸት ዳሰው፣ ጋሸው መንበሩ፣ አድነት ደመቀ፣ ዮሐንስ አዲስ እና ዘላለም አሻግሬ የጥምቀት ዋዜማ ቀን ከተያዙ ጀምሮ ምርመራ ሲደርግባቸው ቆዩ እስካሁን ምንም ነገር አልተገኘባቸውም። ባለፈው ፍ/ቤት የዋስትና መብታቸውን ጠብቆላቸው እያለ እንደገና "ሽብርተኝነት" የሚል ክስ አመጥተው እዛው በማረሚያ ቤት ለመቆየት ተገደዋል። ፍርድ ቤት የፈቀደውን ዋስትና መብት ከተከለከሉ በኋላ ዛሬ 13'ኛ ቀናቸው ነው ምንም አይነት ክስ እስካሁን አልተመሠረተባቸውም። በምርመራ ሂደት ምንም አይነት ወንጀል እንደሌለባቸው እየታወቀ ፍርድቤቱም የዋስትና መብታቸውን ጠብቆላቸው እያለ ያለምንም ምክንያት እነዚህን የልዩ ኃይል አባላት ማንገላታት ትክክል አይመስለንም። የፍትሕ ሥርዓቱ ሕጉን ተከትሎ መተግበር እንጂ ያለበት በግለሰቦች ፈቃድ ላይ የተመሠረተ መሆን የለበትም። እነዚህ ልጆች ዋጋ ሲከፍሉ የቆዩ፣ በተለይም የአማራ ልዩ ኃይል አዲስ ምልምሎችን እያሰለጠኑ በተደጋጋሚ ያስመረቁ ባለውለታዎች መሆኑ እየታወቀ በዘፈቀደ አስሮ ማቆዬት ኢ-ሞራላዊ ነው።
Читать полностью…የዓድዋን የድል በዓል ለማክበር የሄደን ወጣት በቀን በብርሃን በስናይፐር አናቱን መተዉታል።
"…እነ ኮማንደር ሰለሞን ለዚህ አረመኔያዊ ድርጊታቸው ስራቸዉ እንደሚከፍላቸዉ አንጠራጠርም አብይ አህመድም የእጁን ያገኛል!!
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ሰሞኑን የአማራ(በኦሮሚያ ኢንቨስት እያደረጉ ያሉ) እና የኦሮሚያ ክልል ባለሃብቶችን በተናጥል ሰብስበው ማወያየታቸው ታውቋል።
በውይይታቸውም ኢመደበኛ ሀይሎች በህገወጥ መንገድ እየተደራጁ እንደሆነ፣ ስልጣናችንን በህገወጥ መንገድ ለመንጠቅ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ለተሰብሳቢ ባለሀብቶች አስታውቀዋል። እናንተ ባለሀብቶች ሃብት ከማፍራት ባሻገር ይሄን ስርዓት መጠበቅ አለባችሁ። ለኢንቨስትመንት እንቅፋት የሆኑ ችግሮችን ለምሳሌ የውሃ፣የመሬት፣የመብራት እና መሰል ችግሮችን የኦሮሚያ ክልልም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም እነዚህን ችግሮች በቶሎ ለመፍታት እንሰራለን" የሚል ጠቅለል ያለ ሀሳብ መስጠታቸው ታውቋል።
የካቲት 24/2015 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት መግለጫ‼️
"የቤተ ክርስቲያን በዓል እንዲረበሽ እና ምእመናን ሕይወታቸውን እንዲያጡ እንዲሁም እንዲጎዱ ያደረገው ከመንግሥት የጸጥታ መዋቅር የተተኮሰው አስለቃሽ ጭስ እና ጥይት መሆኑ ለሁሉም የታወቀ ሆኖ እያለ ጉዳዩን ወደ ሌላ አካል ለማላከክ የተሄደበትን ርቀት ቤተክርስቲያን በፍጹም የምትቀበለው አይሆንም፡፡"
የመንግሥት የጸጥታ አካል በቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ አስለቃሽ ጭስ በመተኮስ ምእመናን ላይ ጉዳት ሲያደርስ እና የቤተክርስቲያንን ክብር ሲያጎድፍ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡
በዚህ ድርጊት መንግሥት በጸጥታ መዋቅሩ ውስጥ ያሉ እና መንግሥትንና ሕዝብን እንዲሁም ተገቢ ያልሆነ ያለመግባባት የሚያባብሱትን ግለሰቦች እና አመራሮች ለይቶ እርምት ከመውሰድ ይልቅ ሕዝብና መንግሥትን ሆድና ጀርባ የሚያደርግ ተግባሩን አስፋፍቶ ቀጥሏል፡፡
©ብፁዕ አቡነ ሄኖክ
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ