አቶ ልደቱ አያሌው
"የባልበበላውም ጭሬ ልበትነው ፖለቲካ" በሚል የጻፈውን ሁሉም ሊያነበው ይገባል። ልደቱ ካነሳቸው ወሳኝ ነጥቦች መካከል፦
- የአዲስ አበባ ከንቲባዎች ከተማዋን ሲያዩ ኒውዮርክንና ፓሪስን እንዳዩ በደስታ የሚደመሙ የገጠር ካድሬዎች ናቸው
- ከአቶ ተፈራ ዋልዋ ጀምሮ እስከ የአሁኗ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ድረስ ለአዲስ አበባ የተሾሙላት ከንቲባዎች በሙሉ ከክልል የመጡና እንኳንስ የከተማ አስተዳደርን የከተማ ኑሮንም በቅጡ የማያውቁ ናቸው።
- ባልተፃፈ ህግ መሰረትም ላለፉት 18 ተከታታይ ዓመታት በቋሚነት የአዲስ አበባ ከንቲባዎች ኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ብቻ እንዲሆኑ ተደርጓል።
~ የኦሮሞ ህዝብ እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ህዝብ ገና ያልተፈቱ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች አሁንም ያሉት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ዛሬ ላይ ግን ከሌላው ህዝብ በተለዬ ተበዳይና አልቃሽ ሆኖ ሊቀርብ አይገባውም።
~ <...እንድትፈጠር የምትታሰበው " አገረ-ኦሮሚያ " ሰዎች ዜግነታቸውንና ባህላቸውን ካልቀየሩ በስተቀር ሊኖሩባት የማይችሉ በዓለም ብቸኛዋና የመጀመሪያዋ አገር የምትሆን መሆኑን ነው።
~ የአዲስ አበባ ጉዳይ ዘላቂና አስተማማኝ መፍትሔ በቀላሉ ሊያገኝ የሚችለው የመገንጠል ጥያቄ ተወግዶ አገሩም ሆነ የአገሩ ርዕሰ ከተማ የጋራ መኖሪያችን መሆኑን አምነን ስንቀበል ብቻ ነው።
~ ....ስለሆነም በአንድ አገር በእኩልነት አብሮ ለመኖርና የህዝቡን ተጨባጭ ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት ከተፈለገ በአገር ደረጃ የመገንጠልን ጥያቄ፣ በአዲስ አበባ ደረጃ ደግሞ አዲስ አበባን " ፊንፊኔ " ብሎ ከመጥራት ጀምሮ " አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት " እስከሚለው ድረስ ያሉ ህገ ወጥና ምክንያታዊ ያልሆኑ ተያያዥ ጥያቄዎችን እርግፍ አድርጎ መተው ያስፈልጋል።
~ <..በእኔ በኩልም እንደ አንድ የአገርና የህዝብ ህልውና የሚያስጨንቀው ዜጋና የፖለቲካ ሰው ለዚህ ዓይነቱ ትግል ስኬታማነት የሚጠበቅብኝን ሁሉ ለመወጣት ዝግጁ ነኝ። እናንተስ፡? መልሳችሁ አዎንታ ከሆነ መቼና እንዴት ወደ ተግባር መግባት እንዲቻል በግልፅና በፍጥነት እንወያይበት። ጊዜ የለንም።
በውስጥ መስመር የሚደርሱን መረጃዎች እጅግ አሳዛኝ ናቸው‼️
ለማን አቤት ይበላል ዛሬ 15/07/2015 ሰበታ ሜታ ከ 200 በላይ ቤቶች ፈርሶ ህዝብ መንገድ ላይ ወድቋል። አሁንም ከ40 አመታት በላይ የኖርንበትን ቤት በሰባት ቀን ውስጥ ለቃችሁ ውጡ ተብሎ ተለጥፎብናል ምን እናድርግ ወዴት እንሂድ ? ተወልደን ያደግንባት ቦታ ለቀን ወዴት እንሂድ ለማንስ አቤት እንበል? ይዞታ ነዉ ለምን ታፈርሱብናላችሁ ስንል ከላይ ኮታ ተሰቶን ነዉ ይላሉ። በር ፣ መስኮት እና ቆርቆሮ ሽጠው እየተከፋፈሉ ነዉ ።
አብን እና ኢዜማ በጋራ ለመምከር ተስማሙ‼️
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በሀገራዊ ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ የመጀመሪያ ዙር ገንቢ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፆቻቸው ላይ አስታውቀዋል።
በቀጣይም #በሚያግባቡ_ሀገራዊ_ጉዳዮች ላይ ውይይቶችን ለማድረግና #የጋራ_አቋም ለመያዝ ከስምምነት ላይ መደረሳቸውንም ገልፀዋል።
ሁለቱ ፓርቲዎች የ " ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ / ህወሓት " ን ከሽብርተኝነት መዝገብ መሰረዝን በቅድሚያ የተቃወሙ ፓርቲዎች ናቸው።
ፓርቲዎቹ ተቃውሟቸውን በየተናጠል ባወጡት በመግለጫ አሳውቀዋል።
ይህ ከተሰማ ከሰዓታት በኃላ ነው ሁለቱ ፓርቲዎች በሚያግባቡ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይቶችን ለማድረግና የጋራ አቋም ለመያዝ ከስምምነት ላይ እንደደረሱ የተነገረው።
በደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኘው ከፍተኛ ቁጥር ላለው ተፈናቃይ ለእለት ደራሽ ድጋፍ በስፋት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ‼️
የደብረ ብርሃን ከተማ ከንቲባ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፀጋዬ በየነ እንደገለፁት ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ከኦሮሚያ ክልል ማንነት ተኮር በሆነ ጥቃት በርካታ ተፈናቃይ ከተማችን ውስጥ እየፈለሰ ይገኛል እነዚህም ተፈናቃዮች በአራቱ የህዝብ መገልገያ አዳራሾች እና
2ት ግዙፍ የኢንቨስትመንት ሼድ ውስጥ የሰው ልጅ መኖር ካለበት የመኖር ሁኔታ ባነሰ መልኩ ባለብን ችግር መነሻነት እየኖሩ ይገኛሉ ብለዋል ።
በዘንድሮ አመትም መፍትሔ ይሆናል ያልነውን 6.5 ሄክታር ከክልሉ መንግስት እና ከአለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅቶች ተፈናቃዮችን ለመያዝ ቢያንስ ቁጥራቸው 4000 የሚጠጉትን ወደ አንድ ለማስፈር ተጨማሪ ጥረት እያደረግን እንገኛል ያሉት አቶ ፀጋዬ በየነ በቅርቡም በማደሪያ ባለማረፋቸው በጅብ የተነከሱ እንዳሉ በዝናብ እና ብርድ ምክንያት ፍፁም ለመኖር አስቸጋሪ እየኖሩ እንዳለ አንስተዋል ።
ተፈናቃዮች ከጊዜ ጊዜ እየጨመሩ ደጋፊ አካላት ደግሞ ቆይታውን ተከትሎ እየቀነሰ የመጣበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን ብለው ለዚህም ደጋፊ አካላት ውጪ ያሉ ሀገር ወዳዶች እና በሀገር ውስጥ ያሉ ድርጅቶች ግለሰቦች በተቻለ መጠን አሁን ያለውን ችግር ለመቅረፍ እንዲያግዙንና በቀጣይም ህይወታቸው በተረጋጋ ሁኔታ ላይ እስኪገኙ ድረስ በተቻለ አቅም ክፉውን ቀን ተሻግረው ሰላም ሆኖ ህይወታቸውን እንዲቀጥሉ የእለት ደራሽ ምግብ ድጋፍ እንዲያደርጉ እናሳስባለን ሲሉ ገልፀዋል ።
ደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር
መንግሥት በግማሽ ዓመት 100 ቢሊዮን ብር ያህል ቀጥታ ብድር መውሰዱ ታወቀ❗
በዘንድሮ በጀት ዓመት የመጀመርያዎቹ ሁለት ሩብ ዓመታት ወይም ግማሽ ዓመት ውስጥ መንግሥት ወደ 100 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ፣ ከብሔራዊ ባንክ በቀጥታ ብድር (ገንዘብ በማተም) መውሰዱን ሪፖርተር ነው ያስነበበው።
ብሊንከን ኢትዮጵያ ከመጡ ሳምንት ሳይሆናቸው የሚከተለውን ብለዋል❗👇
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ክልል ታጣቂዎች እና የኤርትራ ሠራዊት በትግራይ ክልል ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ጾታዊ ጥቃትን ጨምሮ "በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን" ፈጽመዋል በማለት ፈርጀዋል። በተለይ የአማራ ክልል ኃይሎች፣ በምዕራብ ትግራይ "ሰዎችን በግዳጅ የማፈናቀል" እና "የብሄር ማጽዳት ወንጀሎችን" መፈጸማቸውን ብሊንከን ጨምረው ገልጸዋል። ብሊንከን፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ክልል ታጣቂዎች፣ የትግራይ ኃይሎችና የኤርትራ ሠራዊት ደሞ፣ "የጦር ወንጀሎችን" ፈጽመዋል ብለዋል። ፍረጃው፣ በአሜሪካ ፖሊሲ ላይ ወዲያውኑ የሚያስከትለው ለውጥ አይኖርም ተብሏል። ብሊንከን፣ ወንጀሎቹን የፈጸሙ አካላት በሕግ መጠየቅ አለባቸው ብለዋል። ብሊንከን ይህን የተናገሩት፣ ዓመታዊውን የዓለም ሰብዓዊ መብቶች ሪፖርት ይፋ ባደረጉበት ወቅት ነው።
አሳፋሪዉ የኦነግ መንግስት ግፍ !!!!
መምርህር ታዬ ቦጋለ ላይ የተፈጸመው ድርጊት እጅግ አሳፋሪ የዱርዬ ተግባር ነዉ ያሳዝናል:: ታዬ ቢፈለግ እንኳን መጥሪያ ብትልኩለት ህግን ጥሶ የሚቀር ሳይሆን በግንባር ቀርቦ ለምን ፈለጋችሁኝ የሚል ትውልድን የሚያንጽ መምህር ነው::
2000 አባውራዎች በማንነታቸው ምክንያት ከአዲስ አበባ ሊፈናቀሉ ነው!
(ጌታቸዉ ሽፈራዉ)
አዲስ አበባ "የአርሶ አደር ልጅ" እየተባለ ከኦሮሚያ በርካታ ህዝብ ቤትና መሬት ተሰጥቶታል።
ኮንዶሚኒየም ታድሏል።
አገር አፍራሽ ለነበረው ሁሉ መታሰቢያ ወተዘ እየተባለ መስርያ ቤት ተሰጥቶታል። ዋቆ ጉቱ የሚባለው ከዚያድባሬ ጋር ሆኖ አገር ሲወጋ ጀኔራል ጃገማ ኬሎ አንቆ ያመጣው ሰው ስቴዲዬም አካባቢ "ዋቆ ጉቱ ፋውንዴሽን" ተብሎ አንድ ግቢ ተሰጥቶታል። ቦታ ለመያዝ ነው።
የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ሰራተኞች ቤት ተሰጥቷቸዋል።
በርካታ ሺህ መምራን ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ ተደርጓል።
የሀሰት መታወቂያ የተሰራለት ሁሉ ቦታና ቤት ተሰጥቷቸዋል።
የፈለጉትን ሁሉ አድርገው የቀረውን የህፃናት ኳስ መጫዎቻ ሜዳ ሳይቀር አርሶ አደሩ ገብቶ እንዲያርሰው አድርገዋል።
ከተማ ውስጥ የፈለጉትን ሲሰገስጉ ህገወጥነት አልተባሉም። አርሶ አደሩን እግር ኳስ ሜዳ እረስ ሲሉት ህገወጥ አልተባለው። ኮንዶሚኒዬም በአጣና ሲቀሙ ህገወጥ አልተባለም። ህዝብ በቁጠባ የሰራውን ቤት ለራሳቸው ሰው ሲያድሉ ህገወጥ አልተባለም። አማራዎች በገንዘባቸው የሰሩት ህጋዊ ቤት ግን ህገወጥ ተብሎ እየፈረሰ ነው። ህገወጥ ያስባላቸው ማንነታቸው ብቻ ነው። በአፍሪካ መዲና የዘር ማፅዳት በዚህ መጠን እየተፈፀመ ነው።
ሁለቱ ፎቶዎች የሰማይና የምድር ያህል ርቀት አላቸው። የመጀመርያው አዲስ አበባ ላይ ከሚፈርሱት የ2000 አማራዎች ቤት መካከል ነው። ሁለተኛው ፎቶ መሃል አዲስ አበባ አርሶ አደሩ የእግር ኳስ ሜዳንም ሳይቀር አርሰህ ዝራው ተብሎ ሜዳውን ሲያርሰው ነው። አሁን ያለውን ሁኔታ በደንብ የሚገልፅ ነው። አማራው የኖረበት ህጋዊ ቤት በሌሊት እየፈረሰ ይፈናቀላል። ኦህዴድ አርሶ አደሩ ከተማ ውስጥ ያለን የህዝብ ሜዳ በቀን እንዲያርስ ያሰማራዋል።
ራያ አላማጣ‼️
ነገ መጋቢት 10/2015 ዓ.ም በአላማጣ ከተማ ከጠዋቱ 3:00 ሰላማዊ ሰልፍ መጠራቱ ተሰምቷል። የሰላማዊ ሰልፉ አላማ የማንነት እና የወሰን ጥያቄዎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ለማሳሰብ ነው ተብሏል። በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በ100ሺ የሚቆጠሩ ዜጎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ።
ሰበር❗
አዲሱ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳን የሽግግር መሪ (ፕሬዚዳንት) አድርጎ ሾሙዋል። ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ፕሬዚዳንት ካልሆንኩ ብሎ ሞቼ እገኛለሁ ቢልም በፌደራል መንግሥቱ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። ጌታቸው ረዳ በአብላጫ ድምፅ ተመርጧል
ምንጭ:- አዩ ዘሀበሻ።
የታሪክ መምህርሩ ታዬ ቦጋለ ታፈኑ
መጋቢት 8/2018 ዓ.ም:- ታዋቂው የታሪክ መምህርና አክቲቪስት ታዬ ቦጋለ ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች ታፈኑ።
የታሪክ መምህርና አክቲቪስት ታዬ ቦጋለ ልጃቸን ከትምህርት ቤት አውጥተው በታክሲ ወደ ቤታቸው እየሄዱ ባለበት ቦሌ ብራስ ዮድ አቢሲኒያ አካባቢ ሲደርሱ ከነልጃቸው ቦርሳና ምሳ እቃ እንደያዙ አፍሰው እንደወሰዷቸው ተሰምቷል።
መምህር ታዬን የወሰዷቸው ሲቪል የለበሱ የታጠቁ ግለሰቦች ናቸው ተብሏል።
የታክሲ ሾፌራቸው ምንድነው? ብሎ ለመጠየቅ ሲሞክር መሳሪያ አውጥተው እንዳስፈራርቱ እና ልጃቸውን ይዞ ወደ ቤት እንደወሰደ ገልጿል።
ከደራ የደረሰን መረጃ‼️
አሁን ላይ በደራ ጉንደ መስቀል ልዩ ቦታዉ ደረባና ጎለልቻ በሚባል ቀበሌ መሀል ኮቲቻዉ ላይ በአሁን ሰአት ተኩስ አለ እና ፀጥታ አካል ወደዚህ አከባቢ ትኩረት ቢያደርግ ጥሩ ነዉ ትኩረት ለደራ ያስፈልጋል ትናንት ቄሮ ነን የሚሉ ራሳቸዉን አደራጅተዉ ሰዉ አግተዋል ካምፕ ሀለልቱ ካቢ ቀበሌ ብርጄ ነን ባዮች ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ካምፕ አድርገዉ ሲረብሹ ነበር ትኩረት ይሻል ደራ ።
መጋቢት 6/2015 ዓ.ም
==================
በአማራ ላይ የታቀደው ዘር ማጥፋት ሰበብ ተሰጠው!
አዳነች የተናገረችው ቀድማ በኦ ኤም ኤን በሀሰት ዜና ያሰራችውን ነው። የተቀናጀ የዘር ማፅዳት ዘመቻ ላይ ናቸው። የባጃጅ ሾፌሮችን አስወጥተዋል። በሚቀጥለው ደግሞ ጉሊት ነጋዴዎች፣ ሊስትሮና ሎተሪ የሚሰሩትን ሳይቀር ለማስወጣት መታቀዱ ታውቋል።
ይህን የዘር ማፅዳት ወንጀል ሰበብ ሰጥተውታል። ኦነግም ስልጣን ላይ ያሉትም እኩል እየተናገሩ ነው። ለህክምና፣ ለገበያም፣ ቤተሰቦቹን ጠይቆ ወደ ስራ ገበታው የሚመለሰውም አማራ መፈንቅለ መንግስት ሊያደርግ ነው ተብሎ ሰበብ ተሰጥቶት በማንነቱ እየተጠቃ ነው።
ይህ የሚሆነው በኢትዮጵያ ዋና ከተማ፣ በአፍሪካ መዲና፣ አዲስ አበባ ላይ ነው። ይህን የዘር ማፅዳት፣ ለቀጣይ የታሰበውን የዘር ፍጅት ከአሁኑ ማስቆም ያስፈልጋል። ቄስ ሳይቀር እየደበደበ እንዲመልስ የተነገረው የፀጥታ ኃይል የዚህ የሀሰት ትርክታቸው አካል ነው። ታዝዞ ነው።
አማራ በአገሩ የመንቀሳቀስ መብቱ ታግዷል። ደግሞ የፀጥታ ስጋት ወዳለበት ቀበሌ አይደለም እንዳይሄድ የታገደው። ወደ አዲስ አበባ፣ ወደ ዋና ከተማው እንዳይገባ ነው። ተንቀሳቅሶ የመስራት መሰረታዊ መብቱ ስልጣን ላይ ባሉት እንዲህ በይፋ ታግዷል።
(ጌታቸዉ ሽፈራዉ)
ካህኑ በድንጋይ ተወግረው ተገደሉ!
#Ethiopia | በአዲስ አበባ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ መጋቢት 14/2015 ዓ.ም ቀሲስ ዐባይ መለሰ የተባሉ ካህን ቅዳሴ ጨርሰው ወደ ቤታቸው በመሄድ ላይ እንዳሉ በድንጋይ ተወግረው ሕይወታቸው ማለፉን የዐይን እማኞች ገለፁ።
የሆርሲሳ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የነበሩት ቀሲስ ዐባይ መለሰ ሕይወታቸው ሲያልፍ ችግሩ ታወቀ እንጂ አስቀድሞ በአካባቢው አገልጋዮች ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ይደርስ እንደነበር መረጃ ሰጭዎቻችን ገልፀዋል።
ካህኑ በድንጋይ ተደብድበው እያሉ ምስልና ቪዲዮ ለማስረጃ ለመያዝ ቢሞክሩም በአካባቢው የፀጥታ ኃይሎች ሞባይል እየተሰበሰበ መሰረዙንም ነግረውናል።
©ማኅበረ ቅዱሳን
#መረጃ‼️
በደረሰን ጥቆማ መሰረት አቃቂ ቃሊቲ 04 አካባቢ ካርታ ያለውን ቤት ጭምር እያፈረሱ ነው። ሕዝብ በሕግ አምላክ እያለ እየጮኸ ነው።
(ዘ-ሐበሻ)
ፈጣሪ ይማርህ ጀግናዉ ጀኔራል ተፈራ ማሞ
ይች ሐገር ለባለውለታዋ እንዲህ ናት።
ከአገር ወጥተህ እንዳትታከም መከልከልህን በጥብቅ እንቃወማለን!!!!
በራያ መሆኒ እና ጨርጨር መስመር ሰዐዳሜዳ፣ዴላ ቦራሰለዋ እንዲሁም በዋግኸምራ ሰምረ፣ጭላ እና ደለጎት በሚባሉ አካባቢዎች ሰሞኑን የህወሓት ታጣቂዎች ሰፋ ያለ ስልጠና እየወሰዱ ይገኛሉ ብለዋል የመረጃ ምንጮች። ከዚህ ባሻገር ታጣቂዎችን ሲቪል በመምሰል አስርጎ ማስገባት እየታየ ነው ብለዋል። ህወሃት ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ61 ተቃውሞ ከሽብርተኝነት መዝገብ መሰረዙ ይታወሳል።
Читать полностью…የኡጋንዳ ፓርላማ በአገሪቱ ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል እንዲሆን የሚያደርገውን ረቂቅ ሕግ አጸደቀ።
በጸደቀው አዲሱ ሕግ መሠረት የተመሳሳይ ጾታ ዝንባሌ ያለው ዜጋ ዘለግ ያለ የእስር ጊዜ ይጠብቀዋል።
#Keneya_protest‼️‼️
ዛሬ በኬንያ በኑሮ ውድነት የተማረሩ ተቃዋሚ ሰልፈኞች አደባባይ ወጥተው ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል። የኬንያ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ራይላ ኦዲንጋ ለአገሪቱ የኑሮ ውድነት መንግሥትን ተጠያቂ በማድረግና ባለፈው ነሐሴ የተደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተጭበርብሯል በማለት በጠሩት ሰልፍ፣ አንድ ተቃዋሚ ሰልፈኜ በፖሊስ ጥይት እንደተገደለ የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። የተቃውሞ ሰልፉን ተከትሎ፣ ኦዲንጋ መንግሥት የኑሮ ውድነቱን እስኪያሻሽል ድረስ ዕለተ ሰኞ የተቃውሞ ሰልፍ ቀን ሆኖ ይቀጥላል ብማለት ተናግረዋል።
ወልቃይት❗አሳዛኝ መረጃ‼️
ሱዳን የሚገኘው የሳምሬ ቡድን ከ5 በላይ የቀን ሰራተኞችንና 2500 ኩንታል ጥጥ በእሳት አቃጠለ።
በወልቃይት ጠገዴ (በሁመራ) በኩል ከሱዳን ጋር በሚያዋሰነው የሱዳን ጠረፍ እርሻ የአካባቢ፥ በስደተኛ/በተፈናቃይ ስም በሱዳን ተጠልሎ የሚገኘው የህወሃት ክንፍ የሆነው የሳምሬ ቡድን አባላት የቀን ሰራተኛ በመምሰል በቀን 09/07/2015 "አቶ ነጋ ባንቲሁን" ወደ ተባለው የወልቃይት ጠገዴ ባለሀብት የእርሻ ካምፕ ሰርገው በመግባት ከ5 በላይ የእርሻ ካምፑ የቀን ሰራተኞችን ባለሀብቱ ዘንድሮ ወዳመረተው 2500 ኩንታል የጥጥ ክምር ወስደው በመጨመር በእሳት አቃጥለዋቸው መሰወራቸውን ከስፍራው የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል።
በዚህም መሰረት 2500 ኩንታል የባለሀብቱ ጥጥ ሙሉ በቃጠሎው የወደመ ሲሆን፤ አንድ የቀን ሰራተኛ በምስሉ እንደምታዩት ተቃጥሎ ወዲያዉኑ ሂወቱ ሲያልፍ ቀሪዎቹ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ሁመራ ሆስፒታል ገብተዋል
ምንጭ:- አዩ ዘሀበሻ
በድሮው አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አሁን ሸገር ብለው በሚጠሩት ቦታ ልዩ ስሙ ገላን ኮንዶሚኒየም ሰፈራ በሚባለው አካባቢ በትንሹ ከ2000 ሁለት ሺ የሚሆን ቤት ቀብተው በሁለት ቀን ለቃችሁ ዉጡ ብለዋል።
Читать полностью…የሀገሪቱ ወርቅ በባእዳን እየተዘረፈ ነው‼️
ከኢትዮጵያ እስከ ዱባይ የተዘረጋው የወንጀል ሰንሰለት ውስጥ መሪ ተዋንያኑ የቻይና ተወላጆች መሆናቸውን ጥናቱ ያሳያል ። እነዚህ ዘራፊዎች በተለይ በጋምቤላ እና በቤን ሻንጉል ጉሙዝ የተከማቸውን የወርቅ ማዕድን ያለ ከልካይ እያፈሱ በጎረቤት ሀገራት በኩል በማዉጣት የዱባይ፣ የህንድ እና የቻይና የወርቅ ገበያን መቆጣጠራቸው የአደባባይ ምስጢር ሆኗል።
በቤን ሻንጉል ጉምዝ የዘረፋው ቡድን አለቃ ሱዛን ትባላለች። ሴትየዋ የክልሉን መንግሰት የማዘዝ ስልጣን እንዳላት የአይን እማኞች ይናገራሉ። የራስዋን ሀይል በማደራጀት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን የወርቅ አምራቾችን ጭምር ከአካባቢው ማባረርዋን የሚኒሰቴሩ ምንጮች መስክረዋል። ይህች የቻይና ተወላጅ የክልሉን መንግስት በጉልበት አልያም በጥቅም በመያዝ አቅም አልባ እንዲሆን አድርጋ የሀገሪቱን የወርቅ ክምችት እያሟጠጠችው ትገኛለች።
በጋምቤላ የተሰማራችው ደግሞ ቼሪ (በፎቶ ያለችው) ትባላለች። ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ወንጀል ሶስት አመት ተፈርዶባት ከእስር የተለቀቀች ፍርደኛ ናት። የክልሉን የጸጥታ ሀይል የግልዋ እስኪመስል የማዘዝ ስልጣን አግኝታ ወርቁን ቀን እና ሌሊት በማፈስ ላይ እንደምትገኝ የአይን እማኞች ይመሰክራሉ።
በጋምቤላ ክልል የዲማ ወረዳ ማዕድን ጽ/ቤት ኃላፊና የወረዳው ኮማንድ ፖስት ምክትል ሰብሳቢ አቶ ኡቦንግ ኡቶው ባለፈው ሳምንት ለዶይቼ ቬሌ ሲናገሩ የተሰጣቸውን ፈቃድ ለህገወጥ ተግባር አውለዋል የተባሉና በወርቅ ማውጣት ሥራ ተሰማርተው የነበሩ አካላት ፈቃዳቸው መሰረዙን ገልፀዉ ነበር፡፡
እንደ አቶ ኡቦንግ በወረዳው ከነበሩ 47 አነስተኛ የወርቅ አምራቾች ውስጥ 36ቱ የተሰጣቸው ፈቃድ ተሰርዞ ከስራ እንዲሰናበቱ መደረጉን፣በወርቅ ግብይት ማእከል ከተሰማሩት 34 ማዕከላት መካከል 33 በህገወጥ ስራ ተሰማርተው በመገኘታቸው ፈቃዳቸው መሰረዙንም አስረድተዋል፡፡ ይህ ገለፃ ግን ለሜዲያ ፍጆታ ካልሆነ በስተቀር በተግባር የሚታየው ግን ሌላ ነው።
ፍቃዳቸውን ከተነጠቁት ከነዚህ ሀገወጥ የወርቅ አምራች እና ነጋዴዊች ውስጥ ቼሪ አንድዋ ብትሆንም ፈቃድዋ ተሰርዞም ስራዋን አላቆመችም። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት በክልሉ ሀይል ጥበቃ እየተደረገላት የዲማን ወርቅ በተጠናከረ መልክ እየዘረፈች ትገኛለች ( ዘሀበሻ)።
Inbox‼️
እባካቹ ድምፅ ሁኑን በድሮው አቃቂ ቃሊቲ ከ ከተማ አሁን ሸገር ብለው በሚጠሩት ቦታ ልዩ ስሙ ገላን ኮንዶሚኒየም ሰፈራ በሚባለው አካባቢ ዛሬ መተው በትንሹ ከ2000 ሁለት ሺ የሚሆን ቤታችንን ቀብተው በሁለት ቀን ለቃችሁ ዉጡ ተባልን፣ ምን ውስጥ እንግባ‼️
የኦሮሚያ ሚልሻ የ አማራን ቤት ካፈረሱ በሃላ በጭፈራ ደስታቸዉን እየገለፁ ነዉ::
ሴቶች እህቶቻችን በስደት በ አረብ ሀገር ሌሎቹም የተለያየ ስራ እየሰሩ ያፈሩትን ሀብት እንዲህ እያፈረሱባቸዉ ነዉ::
ወዴት እየተሄደ ነዉ?? አፋጣኝ መፍትሄ ያስፈልገዋል!!
ጎጎት ፓርቲ ከተመሰረተ 24 ሰዓት ሳይሞላው አመራሮቹ ለእስር ተዳርገዋል‼️🙉
በባለፈው ዕሁድ ዕለት የተመሠረተው አዲሱ ጎጎት የጉራጌ አንድነትና ፍትህ ፓርቲ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ትናንት 12 አመራሮቼን አስረውብኝ ነበር ማለቱን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል። ፓርቲው ትናንት ታሠሩ ካላቸው አመራሮቹ መካከል፣ 10ሩ ተለቀው ሁለቱ ግን እስካሁንም እንደታሠሩ መሆኑን መግለጡን ዘገባው አመልክቷል። የፓርቲው አመራሮች ታሠሩ የተባለው፣ በአዲስ አበባው የፓርቲው ምስረታ ጉባኤ ተሳትፈው ወደመጡበት አካባቢ በመመለስ ላይ ሳሉ መሆኑን ፓርቲው መናገሩን ዘገባው ጨምሮ ጠቅሷል።
መጋቢት 5/2015 ዓ.ም
===================
ከንቲባ አዳነች፤ ምን እያሉን ነው??
"ከአንዳንድ ክልሎች ወደ አዲስ አበባ የሚደረገው ከፍተኛ ፍልሰት መንግሥትን በመጣል በኃይል ሥልጣን ለመቆጣጠር ያለመ ነው።" ወይዘሮ አዳነች አቤቤ
ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ ሰዎች በተደጋጋሚ "ወደ አዲስ አበባ"አትገቡም እየተባሉ ተንገላተው መመለሳቸው ሕዝባዊ ቅሬታና ቁጣ መቀስቀሱ ይታወቃል። ለዚህ ህገወጥ የማናለብኝት ድርጊት ወይዘሮ አዳነች ዛሬ ሰበብ አስቀምጠዋል። ከንቲባዋ ለማስመሰል ከአንዳንድ ክልሎች ይበሉ እንጂ ከአማራ ክልል ተጓዦች ውጭ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ የታገዱ የሌሎች ክልል ተጓዦች የሉም። የተጠቀሰው ስጋት እውነት ቢሆን እንኳ-እገዳና ክልከላ መጣል የነበረበት፤ ሽብርተኞች ከሚፈነጬበት ከኦሮሚያ ክልል የሚደረግ ጉዞ እንጂ ከአማራ ክልል አልነበረም።
ለማንኛውም እነ አዳነች የነ OMM ን ውሃ የማይቋጥር የውሸት ዲስኩር ማስተጋባት ከቀጠሉ ምን ይባላል? እንዲህ እየሸፈጡ መሄድ ከመረጡ፤ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላቸው።