ዛሬ በራያ አላማጣ ሰልፍ ተደርጓል‼✍ወያኔ ማንነታችን ብቻ አደለም ሃይማኖታችንም አሳጥቶን ነበር። ከእንግዲህ መንግስታዊ ስርዓቱ ብቻ ሲይሆን ሃይማኖታዊ ስርዓቱም ፊቱን ወደ ትግራይ አይዞርም። ሀገረ ስብከታችን ወደ ወልዲያ ይዙርል። እኛ ኩሩ አማራዎች ነን። የኛ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆስ ናቸው በሚል አላማ ያለው ህዝባዊ ሰልፍ በአላማጣ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
Читать полностью…ጋዜጠኛ ገነት አስማማው የየኔታ ዩቱቭ ዜና አቅራቢ በፌድራል ፖሊስ ፀረ ሽብር ግብረሃይል ታፍና ታስራለች!
ጋዜጠኛ ገነት ጥርስ የተነከሰባት ብ/ጀ ተፈራ ማሞን በተኛበት ኢንተርቪው በማድረጎ ብቻ ነው የታፈነችው!!
የአማራ ሕዝብ ጊዜ ሳያጠፋ በአንድነት ወጥቶ ከጠባቂውን ጎን መሰለፍ፣ ለልዩ ኃይሉ ደጀን መሆኑን ማሳዬት ይጠበቅበታል።
ከረፈደ በኋላ መጮህ ትርጉም የለውም።
የአማራ ልዩ ሀይል ትጥቅ እንዲፈታ የክልሉ መንግሥት መስማማቱ ታውቋል፣
ሰሞኑን በባህርዳር በተደረገው ስብሰባም ተወስኗል።
በአንዳንድ ቦታም መሳሪያ ጥርነፋም ተጀምሯል። ይሄን ለማስፈፀም በጄኔራል አበባው ታደሰ የሚመራ ግብረሀይል ተቋቁሟል። በዚህም የአማራ ልዩ ሀይል ትጥቁን በአንድ ወር ውስጥ ለመከላከያ ሰራዊት አስረክቦ እንዲጨርስ እየተሰራ ነው።
በአንፃሩ ደግሞ በየከተሞች የሚገኙ የአድማ ብተና አባላት የተሻለ ስልጠና ወስደው ከተሞችን የሚጠብቁ ይሆናል ሲሉ ምንጮች ገልፀዋል።
ወደ መከላከያ ሰራዊት እና መደበኛ ፖሊስ የሚገቡ የልዩ አባላት የተጠበቀ ነው።
ኮረም‼️
በወፍላ ኮረምና ዛታ ወረዳዎች" አማራ ነን፣ይህ ማንነት ለእኔ ብቻ የተሰጠ መብት ነው። ሀገሬም እንድታከብርልኝ የምጠይቀው ይህንን ብቻ ነው" በሚሉ ዛሬ ጠዋት ጀምሮ ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።
የክልል ልዩ ሀይል‼️
የሌሎች ክልሎች ልዩ ኃይሎች ትጥቅ ይፈታሉ፤ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ግን ሁኔታዎች ስለማይፈቅዱ ትጥቅ አይፈታም ተብሏል።
ትናንት በተደረገው ስብሰባ የተሃድሶ ኮምሽኑ ኃላፊ ተሾመ ቶጋ በሰጠው መግለጫ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አሁን ላይ ትጥቅ እንደማይፈታ ገልፆአል። በዋነኛነት ትኩረት የተደረገው ሌሎቹ ላይ ሲሆን የኦሮሚያ "ሁኔታዎች ሲመቻቹ" ነው ተብሏል። "ሁኔታዎች አልተመቻቹም" ብለዋል።
አንድ የሀገር መሪ ሆኖ በስልጣን ላይ ያለ ሰው
"ኢትዮጵያን ማፍረስ ከፈለግን ማንም አያግደንም" ብሎ በአደባባይ ዝቶ በስልጣን እንዲቀጥል ከተፈቀደለት በኢትዮጵያ ውስጥ ማድረግ ፈልጎ ማድረግ የማይችለው ምንሞ ነገር ሊኖር አይችልም። ስለሆነም ግለሰቡ በስልጣን እንዲቆይ እስከተፈቀደለት ድረስ ምንም አይነት ወንጀል ቢፈፅም ሊገርመን አይገባም።
(ይልቃል ጌትነት)
#ልዩ ዜና‼️
የክልል ልዮ ሀይል የተባለው ወታደራዊ አደረጃጀት መሉ በሙሉ እንዲፈርስ ትዕዛዝ ተላልፏል። ልዮ ሀይሉ ሲፈርስ ወደ መደበኛ መከላከያ ስራዊት የሚቀላቀሉ ሲሆን የቀረው መደበኛ ፖሊስ ሆኖ ይቀጥላል። ልዮ ሀይሉ የያዛቸውን የስራ ድርሻ ፌደራል ፖሊስና መከላከያ ስራዊት ይረከባቸዋል።
አንድ ፖሊስ ( በፌደራል ፖሊስ ዕዝ የሚመራ) አንድ የኢትዮዽያ መከላከያ ስራዊት ብቻ ሆነው ይቀጥላሉ።
ይሄንን ዜና እንዴት አዩት???
#Inbox❗
ይሄዉልህ እኛ ህይዎታችን የምንመራዉ በአዲስ አበባና አካባቢዋ ባሉ ከተሞች ሎተሪ በማዞር ነዉ አብዛኞቻችን ሎተሪ የምንረከበዉ ከሎተሪ ቅርንጫፍ ሲሆን አንዳንዴ ደግሞ ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ፈቃድ ከሰጣቸዉ መቶ ሻጭ ከሚባሉ አከፋፋዮች እንረከባለን። አሁን ምንም ባላወቅነዉ ሁኔታ ፋኖ ናችሁ ለስለላ ነዉ የምትዞሩ ሰላዮች ናችሁ እየተባልነ መስራት አልቻልነም የያዛችሁት ሎተሪም መጣራት አለበት እየተባለ እየተወሰደብን ነው። እኛ የምንረከበው ከአስተዳደሩ ቅርንጫፍእና ፈቃድ ከተሰጠዉ አካል ቢሆንም የምንይዘዉ ሎተሪ በተቋሙ እዉቅና የለዉም ፎርጅድ ሎተሪ ነዉ የምታዞሩ እየተባልነ ይሄን ምክኒያት አድርገዉ በብሄራችን ብቻ እየተመረጥነ ጥቃት ደርሶብናል። እባካችሁ ድምፅ ሁኑን ሎተሪ አዙረን ለበላነ ብሄራችን ታይቶ እየተሳደድነ ነዉ።
✔- በደቡብ ኦሞ ዞን እስካሁን ባለው መረጃ ምክንያቱ በውል ባልታወቀ በሽታ በሐመር ወረዳ በሦስት ቀበሌያት ከ4 ሺህ 5 መቶ በላይ በጎችና ፍየሎች ሞተዋል። ቀሪ ሌሎች እንስሳት ላይ አደጋው እንዳይዛመት የዞኑ አስተዳደር ከሪጅናል ላብራቶሪ ጋር በመቀናጀት የክትባት አገልግሎት እንዲሰጥ በመስስማማት እየተሠራ መሆኑን ገልጿል።
✔- በዞኑ ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ዝናብ ባለመዝነቡ ከ3 መቶ 37 ሺህ በላይ የማህብረሰብ አካላትና ከ2 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ እንስሳት ለድረቅ ተጋላጭ ሆነዋል።
✔- በአሁኑ ወቅት በአንፃራዊ መልኩ እየጣለ ያለው ዝናብ ጎርፍ አስከትሎ ሌላ ጉዳት እንዳያስከትል ብሎም ደቡብ፣ ሰሜንና ባካ ዳውላ አሪ ወረዳዎች ላይ የመሬት መንሸራተትና ናዳ ሊያስከትል እንደሚችል ተሰግቷል። ለዚህም የወረዳ አመራር አካላት ከወዲሁ መፍትሄው ዙሪያ እንዲሰሩ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
✔- የብሄራዊ ሜቲዮሮሎጂ ትንበያ የዝናቡ መጠን ጠንከር ባለ መልኩ በዞኑ እንደሚቀጥል ይጠቁሟል።
✔- በዞኑ ናፀማይ ወረዳ ሉቃ ቀበሌ ምሽት ላይ በተከሰተ ጎርፍ እስከአሁን 7 መቶ ማህብረሰብ አካላት መፈናቀላቸውንና ከ250 በላይ እንስሳት መሞታቸው ተገልጿል።
✔- ለተፈናቃዮቹ አፋጣኝ ድጋፍ እንዲደረግላቸው የጠየቁት ተጎጂዎች ጎርፉ ለውሃ ወለድና መሰል የጤና ችግር ሊያስከትል ስለሚችል ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ድጋፍ እንዲደረግ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል።
( የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት)
የአማራ ክልል ልዩ ኃይል የቀድሞ ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ በውጭ አገር ሕክምና እንዳያገኙ ተከልክለዋል በማለት ቤተሰቦቻቸው ክስ ሊመሠርቱ መሆኑን ቪኦኤ ዘግቧል። ብ/ጀኔራል ተፈራ ወደ ውጭ አገር ሂደው ሕክምና እንዲያገኙ የሐኪሞች ቦርድ ትዕዛዝ የጻፈላቸው፣ ከአራት ወራት በፊት እንደነበር መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ብ/ጀኔራል ተፈራ ለሕክምና ሊጓዙ የነበሩት ወደ እስራኤል እንደነበር የተናገሩት ባለቤታቸው መነን ኃይሌ፣ የውጭ ጉዞ ክልከላ ትዕዛዙ የመጣው "ከበላይ አካል" ስለመሆኑ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ እንደተነገራቸው ገልጸዋል ተብሏል።
Читать полностью…Inbox‼️
አዲስ በተመሰረተው የሸገር ከተማ አስተዳደር ጨምሮ በአዲስ አበባ ዙሪያ በርካታ መስጅዶችን የማፍረስ ዘመቻ ተጀምሯል። ለአብነት ያክል አዲስ ተመሰረተ በተባለው ሸገር ከተማ አስተዳደር በረመዿኑ ኮዬ ፈጬ ላይ መስጂድ አፍርሰው ሙስሊሙን እያንገላቱት ነው:: የመስጂዱን ኢማም ጨምሮ በርካቶች (30+) ለእስር ተዳርገዋል:: የአካባቢው ሙስሊም ማኅበረሰብ በኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በመገኘት ድምጻቸውን አሰምተዋል።
ደራ‼️
#በኦሮሚያ ክልል ታጣቂዎች ሸዋ ደራ ጉንደ መስቀል ጥቃት መፈጸማቸው ተነገረ!!!
ዛሬ ለሊት ደራ ራቾ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ታጣቂዎች የአማራዎችን ቤት እየመረጡ ሲያቃጥሉ አድረዋል።
እነዚህ ሀይሎች ቤቶችን ሲያቃጥሉ አድረው አሁን ላይ ወደ ሮብ ገበያ መግባታቸው ታውቋል።
ታጣቂዎቹ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሰዎችን አግተው መውሰዳቸውን ገልፀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ እስከ አሁን በመንግሥት በኩል የተደረገ መከላከል እንደሌለ ነዋሪዎች ገልፀዋል።
በመሆኑም በአካባቢው ያለው ህዝብ ከደረሰው ጥፋት የባሰ ነገር እንዳይከሰት ጥንቃቄ ማድረግ አለበት፣መንግስት ተገቢውን ትኩረት መስጠት አለበት ሲሉ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳድር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ የስራ መመርያ ለመቀበል እና ለአጠቃላይ ውይይት ትላንት አዲስ አበባ መግባታቸው ተሰምቷል።
Читать полностью…ኢዜማ በድብቅና በጥድፊያ የአማራን ልዩ ኃይል ማፍረስ ዋጋ ያስከፍሏል ብሏል‼️
የክልል ልዩ ኃይሎች ወደ ህጋዊ የፀጥታ መዋቅር ሥር መግባታቸውን ከልባችን የምንደግፈው ውሳኔ ሆኖ እያለ ፤ አተገባበሩ ፈንጅ የማምከን ያህል ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚፈልግ ግን ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ኹሉ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ በተለይም በሀገራችን ሥር ከሰደደው የዘውግ ፖለቲካ ጡዘት አኳያ አፈጻጻሙ በተጠና መልኩ መኾን አለበት፡፡
እንደምሳሌ የምናነሳው በቅርቡ ከአሸባሪነት መዝገብ እንዲፋቅ የተደረገው የህወሓት ቡድን በሚቆጣጠራቸው መገናኛ ብዙኃን በኩል በአሁኑ ወቅት በአማራ ክልል ሥር ያሉ አካባቢዎችን ስለማስመለስ እንደሚሠራ በስፋት እያስተጋባ ባለበት በዚህ ወቅት፤ ይህንን ውሳኔ በጥድፊያ እና በድብቅ ተግባራዊ ለማድረግ መሞከር አደገኛ ውጤት እንደሚያመጣ የፌደራል መንግሥት ሊገነዘበው ይገባል፡፡ ህወሓት የታጠቃቸውን መሣሪያዎች መፍታቱ በግልጽ ባልታወቀበት ሁኔታ የትግራይ አዋሳኝ ክልሎች ዳግም የመወረር ስጋት ቢያድረባቸው የሚያስወቅስ አይደለም ፡፡ ስለዚህም የውሳኔውን አፈጻጸም ቅደም ተከተል በተመለከተ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ኢዜማ ያምናል፡፡
ከላይ በጠቀስነውና ይህን በመሰሉ ሌሎች ምክንያቶች የተጀመረው በጎ እርምጃ አላስፈላጊ ውጥንቅጥ ፈጥሮ ሌላ ሀገራዊ አደጋ እንዳይጋብዝ የሚከተሉት ጥንቃቄዎች እንዲደረጉ እናሳስባለን፡፡
1) መንግሥት የክልል ልዩ ኃይሎችን ወደ ህጋዊ የፀጥታ መዋቅር ውስጥ ለማካተት የወሰነውን ውሳኔ እስካመነበት እና ሌላ ድብቅ የፖለቲካ ሴራ ከሌለ በስተቀር፤ ውሳኔውን በድብቅ ለማስፈጸም የሚያደርገው እንቅስቃሴ አላስፈላጊ ውዥንብር እንዱሁም ግጭት ከመፍጠር ያለፈ ፋይዳ እንደሌለው መገንዘብ አለበት፡፡ ሰለሆነም ልዩ ኃይሉን ወደመደበኛነት ለመቀየር የሚከተለውን ፍኖተካርታ ደረጃ በደረጃ አካሄዱን ለህዝብ በተደጋጋሚና ግልፅ በሆነ መልኩ በተለያዩ ቋንቋዎች ማብራሪያ መሰጠት አለበት። ይህ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚፈጠረውን ውዥንብር ከማጥፋቱም በላይ በመንግስት እና በሂደቱም ላይ ያለውን ጥርጣሬ ይቀንሳል ብለን እናምናለን።
2) የሁሉንም ክልሎች ልዩ ኃይሎች ወደ ህጋዊ የጸጥታ ተቋማት ውስጥ ማካተት የሚኖረውን ሀገራዊ ጠቀሜታ እና አፈጻጸም በተመለከተ ከኹሉም የክልል መንግሥታት ኃላፊዎች እና የፀጥታ ተቋማት ጋር ተነጋግሮ መግባባት ላይ መድረስ በቅድሚያ ሊኾን እንደሚገባ ለማስታወስ እንወዳለን፡፡
3) የጉዳዩን ሀገራዊ ፋይዳ ለሚመለከታቸው የሀገራችን የፖለቲካ ልሂቃን ከማስረዳት ጀምሮ፤ ይህንን ውሳኔ ሰበብ በማድረግ ሊሸረቡ ከሚችሉ ፖለቲካዊ ደባዎች መታቀብም በከፍተኛ ደረጃ ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ከአንዳንድ የፖለቲካ ተዋንያን እየተሰማ እንዳለው “የአንዱን ክልል ልዩ ኃይል አፍርሶ ሌላኛውን በድብቅ የማጠናከር ሴራ” እንዳይኖር ማድረግ እንደሚገባም ውሳኔውን ለሚያስፈጽሙ የሀገር መከላከያ እና የፌደራል ፖሊስ አዛዦች በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
4) የክልሎች ልዩ ኃይሎች ወደ ፌደራል እና የክልል የፀጥታ መዋቅር ውስጥ በሚገቡበት ይሁን የሲቪል ማህበረሰቡን በሚቀላቀሉበት ጊዜ አስተማማኝ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርኃግብር ወይም ተሃድሶ ሊከናወን ይገባል፡፡ የክልል ልዩ ኃይሎች አባላት ወደ ህጋዊ የፀጥታ መዋቅር ዕዝ ሥር እንዲገቡ የተደረገበትን ሀገራዊ ፋይዳ ማሳወቅ፤ የሚኖራቸውን የግልፅነት ጥያቄ መመለስ እና የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውን በተመለከተ ማስተማመኛ መስጠትም በውዥንብር ምክንያት ሊፈጠሩ የሚችሉ ተግዳሮቶችን እንደሚያስቀር መገንዘብም ከመንግሥት አካላት ይጠበቃል፡፡
5) በብልፅግና ፓርቲ ውስጥ ያለውን ሽኩቻ ከፍ ሲል ወደ መንግስት ብሎም ወደ ህዝብ ውስጥ ተሰራጭቶ ለሀገር ስጋት እንዳይፈጥር፤ የፌደራሉ መንግሥት ይህንን ውሳኔ ለማስፈጸም የሚያደርገው ተግባራዊ እንቅስቃሴ በጥድፊያ እንዲሁም በማንአለብኝነት ሳይኾን በመግባባት፤ በመተማመን እና በግልጸኝነት መንፈስ ሊኾን ይገባል፡፡ ይህን ባለማድረግ ለሚፈጠር ውዥንብር፤ ግጭት እና ውድመት የፌደራሉ መንግሥት ተጠያቂ መኾኑን ተገንዝቦ ውሳኔውን በጥንቃቄ እንዲያስፈጽም እናሳስባለን፡፡
ዐማራን ሁሉ የሚጠብቀው ይሄ ነው…!
"…እናትሽ እንዲህ ትሁን…? ምንአባሽ ነው? የምን አባሽ የፍርድ ቤት ትእዛዝ ነው? በላት፣ በደንብ ውገራት እያለ አንዲትን ሴት በአደባባይ እያዋረደ፣ እየጠፈጠፈ የሚወስደው አረመኔው የኦሮሙማ መንግሥት ነው።
"…ገነት አስማማው በሙያዋ በየኔታ ቲዩብ ወያኔ ህወሓትን በግልጽ የሞገተች፣ ዜና በመሥራት ሠራዊቱን ያነቃቃች ጋዜጠኛ ናት። ጋዜጠኛዋ በቅርቡ ህክምና የተከለከሉትን የዐማራ ልዩ ኃይል አዛዥ የጄነራል ተፈራ ማሞን ቤታቸው ሄዳ የጠየቀችም ባለሙያ ናት። ገነት አስማማውን ዛሬ ዐማራ እና ኦርቶዶክስ በመሆኗ እንዲህ እያዋረዱ፣ እየጠፈጠፉ ወደማይታወቅ ሥፍራ የወሰዷት።
"…በነገራችን ላይ የህወሓት የቀድሞ አፋኝ ቡድኖች ዐማራን ብቻ እየነጠሉ እንዲበቀሉ አቢይ አሕመድ ወደ ሥራ መልሷቸዋል። በጦርነቱ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ የሂዊን ጉዞ የገቱ በሙሉ ከያሉበት ይለቀማሉ። እነ አንዳርጋቸው ጽጌና ስዩም ተሾመ ሁላ አይቀርላቸውም። ወያኔ በአቢይ በኩል ትበቀላለች። እነፍሬወይኒም ከሰሞኑን የዐማራ ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል።
"…ዐማራ ይሄን የጥጋበኛ፣ የነውረኛ፣ ለኢትዮጵያ የማይመጥን ሃገር አጥፊ፣ የሰው ክብር የሌለው፣ ሕግም የማይገዛው፣ ሰብአዊነት የማይሰማው፣ ዱርዬ፣ ቦዘኔ፣ መደዴ ነውረኛ ስብስብ ለመበቀል ዛሬውኑ ቆርጦ ካልተነሣ ይሄ በሁሉም ዐማራ ቤት ሰሞኑን ጠብቅ።
"…የብአዴን ካድሬ የሚድን መስሎት ወደ አዲስ አበባ ፈርጥጧል። ኦነግ ራሱ ይበላዋል። የኦሮሞ ልዩ ኃይል፣ TDF ደግሞ የዐማራ ልዩ ኃይንና መከላከያን በመምሰል ወደ ዐማራ ክልል እየተመመ ነው። ውጤቱን አብሮ ማየት ነው። ልብ በል በወለጋም፣ በትግራይም፣ በመከላከያም ሟችም ገዳይም ወታደር ኦርቶዶክሱ ነው። እስላምና ጴንጤ ከዳር ቆሞ ያያል።
"…አይዞኝ ገነት አስማማው…! ድል ለዐማራ፣ ድል ለኢትዮጵያ…! 💪💪🏿💪
(ዘመድኩን በቀለ)
አስቸኳይ❗❗❗
ዉድ የአማራ ህዝብ ኢንቴርኔት ሙሉ ለሙሉ መዘጋቱ የማይቀር ነዉ::
ከልዩ ሀይል እና ከፋኖ ጋር ለመገናኘት መረጃ የምትለዋወጥበትን መንገድ አሁኑኑ እንድትቀይስ በአስቸኳይ እናሳስባለን !!!
ሩሲያ የፀጥታው ም/ቤት ፕሬዝዳንት በመሆኗ የተደናገጠችው ዩክሬን ሁኔታው “ የዓለም ህዝብን በጥፊ እንደመምታት ነው” ብላለች‼️
ሩሲያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የሚያዝያ ወር ፕሬዳንት ስፍራን ተረክባለች።
ዩክሬን ለሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት የወሩ ፐሬዝዳንትነት ስፍራ እንዳይሰጣት ለማድረግ በርካታ ጥረቶችን ብታደርግም ሳይሳካ ቀርቷል ነው የተባለው።
የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዘዳንትንት በሩሲያ መያዝ ያስደገጣት ዩክሬን በበኩሏ፤ “የወሩ ምርጥ ቀልድ ነው” በማለት አጣጥላለች።
ህወሓት ግንባር የቆዩ ታጣቂዎቹን ፖሊስ እንዲሆኑ እያደረገ ነው ተባለ‼️
ህወሓት በሰሜኑ ጦርነት ወቅት በግንባር ሲዋጉ የቆዩ ታጣቂዎችን የፖሊስ መታወቂያ በመስጠት በየከተሞች እየመደበ ነው ተባለ፡፡
ህወሓት በሰላም ስምምነቱ መሰረት ትጥቅ መፍታት ስላለበት ታጣቂዎቹ ትጥቅ እንዳይፈቱ ለማድረግ በፖሊስነት እየመደባቸው መሆኑን አዲስ ማለዳ ከምንጮች ሰምታለች፡፡
ህወሓት ታጣቂዎቹን በጊዜያዊ መንግሥት መዋቅሩ ውስጥ አስገብቶ ደሞዝ እንዲከፈላቸው ለማድረግ እየሰራ ነው የተባለ ሲሆን፣ ግንባር ላይ ሲዋጉ ከነበሩ ታጣቂዎች መካከል "በፖሊስነት ኮረም ተመድበናል በቅርቡ እንመጣለን" ያሉ መኖራቸውን አዲስ ማለዳ ከአካባቢው ነዋሪዎች አረጋግጣለች፡፡
በሌላ በኩል ሰሞኑን ከአበርገሌ በገዛ ፈቃዳቸው የወጡ የህወሓት ታጣቂዎች ከጻግብጂ ግን ሊወጡ እንዳልቻሉ ተመላክቷል፡፡
በዋግኽምራ ዞን የምትገኘዋ የጻግብጂ ወረዳ ኮረምና አላማጣን ለመቆጣጠር ስትራቴጂክ መሆኗን ተከትሎ ህወሓት ሊወጣ አልቻለም የሚል አስተያየታቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
ህወሓት ከጻግብጂ በተጨማሪ ኮረም ውስጥ ስድስት የገጠር ቀበሌዎችን እያስተዳደረ እንደሚገኝም ተነግሯል፡፡
በእነዚህ ቀበሌዎችም የመሬት ግብር የሚሰበስብ ሲሆን፣ ለህዝብ ከሚመጣው እርዳታ ላይም ቀንሶ የሚወስድ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ 15 ኪሎ ግራም እህል ከሚያገኙ ግለሰቦች 5 ኪሎ ግራም የሚሆነውን እንደሚወስድ ተነግሯል፡፡
ህወሓት የሰላም ስምምነቱን የሚያከበር ከሆነ ህወሓት ከጻግብጂ ወረዳ እንዲሁም ከስድስቱ ቀበሌዎች መውጣት እንደነበረበት ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡
አክለውም፣ "ህወሓት መሳሪያ አስረክቧል የሚባለው ነገር ትክክል አይደልም፣ ከኮረም ዘጠኝ ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ በርካታ የህወሓት ታጣቂዎቹ አሉ፣ ዛቻ እየነዙ ያሉትም በቅርቡ ኮረምና አላማጣን እንደሚይዙ ነው።" ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ጠቁመዋል
(አዲስ ማለዳ)፡፡
ብራዚልና ቻይና በዶላር ላለመገበያየት ተስማሙ‼️
ቻይና ከአሜሪካ ጋር ያላት ግንኙነት ወደ መካረር ማምራቱን ተከትሎ ከዚህ በፊት በአሜሪካ ዶላር ስታደርጋቸው የነበሩ የንግድ ልውውጦችን በመቀየር ላይ ትገኛለች።
ቤጂንግ ከዚህ በፊት ከሩሲያ፣ ሳውዲ አረቢያ እና ሌሎችም ሀገራት ጋር የመገበያያ ገንዘቧን በዩዋን እና ከዶላር ውጭ እንዲሆን አድርጋለች።
አሁን ደግሞ ከላቲን አሜሪካዋ ባለ ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት ከሆነችው ብራዚል ጋር ዶላርን ላለመጠቀም ተስማምታለች ሲል ኤኤፍፒ ዘግቧል።
ሴራዉ እንደቀጠለ ነዉ❗❗❗
የአማራ ክልል መንግስት እና ህዝብ ከፊትለፊቱ ለሚጠብቀዉ መራር የህልዉና ትግል እራሱን ማዘጋጀት ይኖርበታል!!!
የኬንያ ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው‼️
በጎረቤት ኬንያ የተቀሰቀሰው ጸረ-መንግሥት የቃውሞ ትናንትም ተባብሶ ቀጥሏል። የተቃዋሚው መሪ ራይላ ኦዲንጋ ለቀጣዩ ሰኞ አራተኛውን አገር ዓቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ ጠርተዋል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ልዩ ልዑክ ሴናተር ክሪስ ኩንስ ወደ ናይሮቢ አቅንተው ውጥረቱን ለማብረድ ያደረጉት ሙከራ አለመሳካቱን የኬንያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ኩንስ ተልዕኳቸው የሽምግልና ጥረት ስለመኾኑ በይፋ ባይገልጡም፣ ከአገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪጋቲ ጋሻጉዋ እና ከራይላ ኦዲንጋ ጋር መነጋገራቸውን ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ይህንኑ ውይይት ተከትሎ፣ ምክትል ፕሬዝዳንቱ መንግሥት የተቃውሞ ሰልፉን ከሚያስተባብሩት ኦዲንጋ ጋር "በሥልጣን መጋራት" ዙሪያ ንግግር እንደማይኖረው ተናግረዋል ተብሏል።
የኦነግ ሰራዊት የጠ/ሚሩን የሰላም ጥሪ ቅጥፈት ነው ሲስል አጣጣለ‼️
መንግሥት ኦነግ ሸኔ ከሚለው እና እራሱን ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከሚለው ታጣቂ ቡድን ጋር ሰላም ለመፍጠር መንግሥታቸውከፍተኛ ፍላጎት እንዳለውም ገልጸዋል። በአንጻሩ የኦሮሞ ነጻነት ጦር በመንግሥት የተገለጸውን የሰላም ፍላጎት እንደሚጠራጠር ገልፀዋል ይኽን አስመልክተው ለአሶሲየትድ ፕረስ አስተያየታቸውን የሰጡት የቡድኑ ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩን አስተያየት «ጊዜውን ያልጠበቀና ከእውነታው ጋር የማይጣጣም» ነው ያሉት። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቡድኑን አመራሮች ለማግኘት 10 ጊዜ ተደረገ ያሉት የሰላም ውይይት ሙከራም እውነተኛ አይደለም ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል። እንደውም መንግሥታቸው በተለያዩ አካባቢዎች አሸማጋይ ኮሚቴዎችን በማሰማራት የኦሮሞ ነጻነት ጦር ተዋጊዎችን ለማነጋገር እና እጃቸውን እንዲሰጡ ለማሳመን መሞክሩንም ገልጸዋል። ቃል አቀባዩ ቡድኑ ለውይይት ዝግጁ መሆኑን የገለጹ ሲሆን የታሰበው የሰላም ስምምነት እንዲሳካም ዓለም አቀፍ የሦስተኛ ወገን አደራዳሪነት እንደሚያስፈልግም አጽንኦት ሰጥተዋል። ከኦሮሚያ ክልል የተወከሉ የምክር ቤት አባላት በተለያዩ ጊዜያት መንግሥት ሸኔ ከሚለው ቡድን ጋር የሰላም ድርድር እንዲያደርግ፤ በቅርቡም እንዲሁ የአፍሪቃ ኅብረት በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነቱን ለማስቆም ከህወሃት ጋር መንግሥት እንዳደራደረ ሁሉ፤ በኦሮሚያ ክልልም ሰላም እንዲወርድ ተመሳሳይ ሚና እንዲጫወት በደብዳቤ መጠየቃቸው ይታወሳል።
ክርስቲያን ታደለ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ያቀረቡት ጥያቄ‼️
ዛሬ መጋቢት 19 ቀን 2015 ዓ.ም እየተካሄደ ባለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበ ጥያቄ፤
**
አመሰግናለሁ የተከበሩ አፈጉባዔ፤
አመሰግናለሁ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር፤
ጥያቄዬን ከማቅረቤ በፊት ስለጥያቄዬ ትንሽ ማለት እፈልጋለሁ። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በዚህ ምክር ቤት እና በተለያዩ መድረኮች ስለእርስዎና ስለሚመሩት የአስፈፃሚ መንግስት ተጠየቅ ሲቀርብብዎ ለተጠየቁ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ጠያቂዎችን የሚያጥላላ አስተያየት ሲያራምዱ፤ አለፍ ሲልም ተጠየቅ የቀረበብዎት የወጡበት ብሔርን በመጥላት እንደሆነ አድርገው ምላሽ መስጠትዎ የቅርብ ትዝታ ነው። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ቀጥዬ የማቀርብልዎ ጥያቄ ራስዎንና መንግስትዎን የሚመለከት እንጂ ሌላ ማንንም የማይመለከት መሆኑን ማረጋገጥ እፈልጋለሁ። እኔም ጥያቄውን የማቀርብልዎት በብሔር አይደለም። ምላሽ ሲሰጡም የመንግስት ግልበጣ ለማድረግ የተሼረበ ሴራ ነው የሚል እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ። ጥያቄዬ የሚከተለው ነው።
የዜጎችን ደኅንነት እና የአገርን ሉዓላዊነት መጠበቅ ዝቅተኛ የመንግስት ኃላፊነት ሆኖ ሳለ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ይገደላሉ፤ ይፈናቀላሉ፤ ቤታቸው ይፈርሳል፤ ንብረታቸውም ይወድማል። የአገር ሉዓላዊነትን በሚዳፈር መልኩ የጎረቤት አገራት ሰራዊቶች በኢትዮጵያ ሰሜን ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ወሰኖች በርካታ ኪሎሜትሮችን ዘልቀው በመግባት ወረራ ፈጽመዋል። አሁን ላይ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የዜጎች ደኅንነትና የአገር ሉዓላዊነት ዋነኛ የስጋት ምንጭ ሆኖ የምናየው ራሱ መንግስትን ነው። እርስዎ በአፍዎ «ኢትዮጵያ አትፈርስም» ቢሉንም በተግባር ግን ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነት በመንግስትዎ እየተናዱ ነው። የበርካታ አገራት መሪዎቸ መሰል ኃላፊነትን በወጉ ያለመወጣት ጉድለት ሲያሳዩ ሕዝብን ይቅርታ ጠይቀው ሥልጣናቸውን ሲለቁ ይታያል። በአገራችንም የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተመሳሳይ ሕዝባዊ ተጠየቅ ሲቀርብባቸው ሥልጣን መልቀቃቸው ይታወሳል።
እርስዎስ ሥልጣንዎን በመልቀቅ የመፍትሔው አካል ለመሆን አላሰቡም ወይ? በሰብአዊነት ላይ በተፈፀሙ እንዲሁም የማንነት ተኮር የዘር ማጥፋት፣ የዘር ማጽዳትና የማንነት ማሳሳት ወንጀሎች ተጠያቂ ለመሆን ምን ያህል ዝግጁ ነዎት?
አመሰግናለሁ!
የንግድ ባንክ ተፈታኞች ቅሬታ‼️
<<ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የፅሁፍ ፈተና ተፈትነን ወደ ቃል ፈተኛ አልፈን ተጠራን፣ወደ ፈተና ከመግባታችን በፊት ፎርም አምጥተው ሙሉ ተባልን በፎርሙ ላይ ብሄር የሚል አለው።ዋና አላማው ብሄራችንን ለይቶ ለማወቅ ነበር።በቃል ፈተናው ላይ እንደፈለጉ አንዱን በአማርኛ ሌላውን እንግሊዝኛ ፈተኑ።ውጤት ንገሩን ስንል ከለከሉን።ባንኩ በዚህ ደረጃ ይሆናል ብለን አናስብም ነበር>>
በባንኩ ለቅጥር የተፈተኑ ተመራቂዎች ለኢሳት ከተናገሩት የተወሰደ
በቦረና እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ በተለያዩ አከባቢዎች በሰውና በእንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ተሰማ።
በዞኑ ለረጅም ጊዜ ከቆየው ድርቅ የተረፉት የቦረና ከብቶች በተለያዩ ቦታዎች በጣለው ከባድ ዝናብ በጎርፍ መወሰዳቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመላክታል።
ከዚህም በተጨማሪ ህብረተሰቡ በመጠለያ እጦት ለከፋ ችግር መዳረጉ ታውቋል።
በዞኑ የኮሌራና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች መከሰትም ህዝቡን ስጋት ውስጥ ከትቷል።
ወሎ ኮምቦልቻ በ53 ሄክታር መሬት ላይ ሊገነባ የነበረው ደረቅ ወደብ በጀት ወደ ጅማ መዛወሩን ሰማሁ።በነገራችን ላይ የኮምቦልቻ ደረቅ ወደብ ዲዛይኑ ያለቀው በ2009 ዓም ነበር።ፕሮጀክቱ ከኮምቦልቻ ተሰርዞ ወደ ጅማ የተወሰደው ብዙ ወጭ ጠይቋል በሚል ነው ተብሏል።በጉዳዩ ላይ የከተማው እና የክልሉ አመራሮች ምንም ሳይሉ ፀጥ ብለዋል።የመሬት ካሳ በዛ ከተባለም አማራጭ አቅርቦ ሰበብ አልባ ማድረግ ሲገባ ሂደቱን በዝምታ ማለፍ ተገቢ አልነበረም።አሁንም ጥያቄውን አደራጅቶ በማቅረብ ተደጋጋሚነት ያለው ጥያቄ ማቅረብ ይገባል።ዝም ካልክ የአካባቢው አለመልማት ተመችቶሃል ማለት ነው። መንግስትኮ የአዋሽ ኮምቦልቻ ሀራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክትንም ባላዬ ለማለፍ እየሞከረ ነው፣ያሳዝናል
(wasu mohammed)።
የመከላከያ ሰራዊትን የጨፈጨፈዉ ቡድን አባል የሆነዉ ስብሃት ነጋ ለህክምና አሜሪካ ገብቷል። በተቃራኒዉ ደሞ ሀገርን ከመፍረስ የታደገዉ ብ/ጄኔራል ተፈራ ማሞ ደግሞ እግሩ ላይ ባለዉ ባልወጣዉ ጥይት ምክንያት ሀገር ዉስጥ በስቃይ ላየ ይገኛል::
ገንዘብ እሩዱኝ አላልኩም፣ወደ ዉጪ ሄጄ እንድታከም ብቻ ይፈቀድልኝ እያለ ተከልክሏል። እግሩ ላይ በተደጋጋሚ በጥይት ቆስሎ ስለነበር ነርቩ ተነክቶ ለመንቀሳቀስ ተቸግሯል። በሽታው ወደ ነርቭ በመቀየሩ የተሻለ ህክምና ያስፈልገዋል።
ሆኖም ግን የአብይ አህመድ መንግስት ጀነራሉን ዉጪ ሀገር ሄዶ እንዳይታከም ከልክሎታል::