ethio360media | Unsorted

Telegram-канал ethio360media - Ethio 360 Media

37564

ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር !!!

Subscribe to a channel

Ethio 360 Media

Inbox‼️


በአማራ ክልል ዋና ከተማ ባህርዳር ላይ ቀበሌ 7 በእዚህ ሰዓት እጅግ ከፍተኛ የሆነ ተኩስ አለ።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በየቦታዉ ያለዉ አማራን የማዋከብ ሁኔታ ይሄንን ይመስላል::

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ደብረ ብርሃን መግቢያ ላይ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ ነው!

ከአዲስ አበባ ደብረ ብርሃን መግቢያ መንገድ ላይ በመከላከያ እና የመንግሥትን ውሳኔ ባልተቀበሉ ኃይሎች መካከል የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ ይገኛል።የተኩስ ልውውጡ የተጀመረው "መከላከያ ያልፋል አያልፍም" በሚል አለመግባባት መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ተኩሱ ከተጀመረ አንድ ሰዓት ያለፈው ሲሆን፤ የተኩስ ልውውጡ ዳሸን ቢራ ፋብሪካ አካባቢ የሚገኙ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል፣ፋኖ እና በመከላከያ መካከል ነው ተብሏል።መንግሥት የክልል ልዩ ኃይሎችን አፍርሶ በመከላከያ፣ በፌደራልና በክልል ፖሊስ ለማደራጀት ያሳለፈው ውሳኔ በተለይ በአማራ ክልል ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል።

በዚህም ውሳኔውን ያልተቀበሉ የክልሉ ልዩ ኃይል አባላት "ትጥቅ አንፈታም" በማለት ከእነ ትጥቃቸው ከአደረጃጀት መውጣታቸው ታውቋል። በተለያዩ የክልሉ ከተሞችም ባለፉት ተከታታይ ሦስት ቀናት የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ታይተዋል።በክልሉ የተፈጠረው ውጥረት ወደ ተኩስ ልውውጥ ማምራቱን ተከትሎ የተለያዩ አካላት ችግሩ እንዳይባባስ የክልሉ መንግሥትና የፌደራሉ መንግሥት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እየጠየቁ ይገኛሉ።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ስጋቱ ዛሬም በገሃድ መጥቷል

የአማራ ልዩ ኃይል ላይ ሲወሰን እንደ ቅድመ ሁኔታ ከተነሱት መካከል የትህነግ እና የኦነግ ሸኔ ጉዳይ ነው። ኦነግ ሲባል ስሙን ለመጠቀም ያህል እንጅ የኦሮሚያ ብልፅግና የሚያዘው ኃይል ነው። ይህ ኃይል በተለያዩ አካባቢዎች ጥቃት ከፍቷል።

1) አጣዬ ላይ በቡድን መሳርያ ጭምር ጥቃት ተከፍቷል። አጣዬ ላይ ጥቃት የሚከፍቱት ህዝብን ጭምር አስተባብረው ነው።

2) ትህነግ በሱዳን በኩል ኃይል አስጠግቷል።

3) ሆሮ ጉድሩ እና ምዕራብ ሸዋ ዞን በአማራዎች ላይ ጥቃት ተከፍቷል።

4) ጌታቸው ረዳ ትናንት ለትግራይ ቲቪ "ጠላትን ከወልቃይትና ራያ አስወጥተን እናሰፍራለን" ብሏል።

አማራ የመወረር ስጋት አለበት የተባለው፣ ቅድመ ሁኔታዎቹ የተቀመጡት ለዚሁ ነው። ህዝብ ውሳኔውን እየተቃወመ ባለበት ስጋቶቹ ግን እውን እየሆኑ ነው።

ህዝብ ግልብጥ ብሎ ወጥቶ የተቃወመው ስጋቱን ስለሚያውቅ ነው። ቅድመ ሁኔታ የተቀመጠው የሚመጣው ጥቃት ስለሚታወቅ ነው።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ህዝብ ሲያሸንፍ እንደዚህ ነው!

የመግለጫ ጋጋታው ቀጥሏል። የሚገርመው ግን ከዚህ በስተጀርባም የሚሰሩት ነው። በሀሳብና አጀንዳ የበላይነት የተበለጠው ገዥው ፓርቲ ይህ ህገወጥ ውሳኔውን ህጋዊ ለማስመሰል ብዙ እየደከመ ነው። አንደኛው ለአባላቱ አስተያየት ፅፎ አሰራጩ እስከማለት የደረሰ ነው። በየመግለጫው እየሄዳችሁ ለጥፉት ተብለው ትዕዛዝ ወርዶላቸዋል። በክፍለ ከተማ፣ በዞን አስተያየት ተፅፎ ሲታደል ውሏል። የገዥው ፓርቲ ብቻ ሳይሆን ከምትፅፉት ስር አውጋዥ፣ ከፋፋይ ወዘተ አስተያየት ከበዛባችሁ ከኦህዴድ ቢሮ የወጣ እንጅ የግለሰብ እንዳልሆነ ተረዱት። ይህንም ማታ ውጤት ብለው ይገመግሙታል።

መግለጫው ተደራሽ እንዲሆን አስተያየት በተደራጀ መልኩ እየፃፉ የሀሳብ የበላይነት እንዲወስዱ መሆኑ ነው። አይቻልም! ከዚህም በተጨማሪ የመግለጫው ዋና ፍሬ ሀሳብ የተባለውን በተለያየ መልኩ እንዲወጣም ያደርጋሉ። ነገር ግን ውሳኔያቸውን ህገወጥ ከመሆን አያድነውም።

ህዝብ በነቂስ ወጥቶ እየተቃወመ የሚገኘውን ጉዳይ በክፍለ ከተማ፣ በዞን ተደራጅቶ አስተያየት በመስጠት የአጀንዳ የበላይነት መውሰድ አይቻልም።

ጉዳዩ ግልፅ ነው!

1) ዓለም አቀፍ ህግ ተጥሶ ትህነግ ትጥቅ እንዳይፈታ ተደርጓል። መከላከያ ሰራዊቱ ከትግራይና ከአማራ አካባቢዎች ወጥቷል። ትህነግ ከትግራይና ሱዳን እየተዘጋጀ ነው። በዚህ ወቅት ህዝብን ለማስመታት የተደረገውን ውሳኔ ህዝብ አልቀበልም ብሏል።

2) ኦነግ ሸኔ ትጥቅ አልፈታም

3) አማራዎች እየተፈናቀሉ ነው። እነዚህና ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች ቀርበዋል።

ከዚህ ባሻገር ብልፅግና ልዩ ኃይል ላይ የመወሰን መብት የለውም። የአማራ ምክር ቤት አልተቀበለውም። ህዝብ አልተቀበለውም። የሚያዋጣው ውሳኔውን መሻር ነው።

የኦሮሚያ ካድሬን አደራጅቶ አስተያየት እንዲሰጥ፣ የሀሰት መረጃ እንዲያሰራጭ፣ በጎጥ እንዲከፋፍል፣ የሚፅፉትን እንዲዘልፍ በማድረግ ለውጥ ማምጣት አይቻልም።

አደባባይ የወጣን ህዝብ አስተያየት ፅፎ ለአባል በማሰራጨት ማሸነፍ አይቻልም። ይህ ሁሉ ድካምም ህዝብ በአንድነት ከጫፍ ጫፍ ወጥቶ በመቃወሙ የመጣ ነው። ህዝብ እያሸነፈ ስለሆነ ነው።

(ጌታቸዉ ሽፈራዉ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

#የሱፍ ኢብራሂም👏👏👏👏👏👏

ለአለፉት ሁለት አመታት እና ከዚያ በላይ ህዝባችን በጦርነት ውስጥ ቆይቷል ። የወደመው አልተተካም ፣ የፈረሰው አልተጠገነም ። የመልሶ ማቋቋም ስራዎች እንኳን በፌድራል መንግስቱ በኩል በተገቢው ሁኔታ ትኩረት አልተሰጣቸውም። ይህንን ሁሉ መከራ ላሳለፈ ህዝብ ዛሬ ላይ ይሄ ተጨማሪ የጥፋት አጀንዳ አይገባውም ነበር ።

መንግስት ልክ እንደ ተራ ግለሰብ "ይዋጣልን"  እያለ ከህዝብ ጋር ትከሻ የሚለካካውን ነገር በፍጥነት ማቆም አለበት ። መፍትሔውም የህዝብን ጥያቄ በማዳመጥ ውሳኔውን በድጋሜ ማጤን እና ነገሮችን ወደ ነበሩት ለመመለስ የማረጋጋት ስራዎችን መስራት ከመንግስት ይጠበቃል ።

በተጨማሪም መንግስት ከእልህ እና ግብግቡ ባሻገር ማስተካከል የሚገባው ነገር ተራ የመሸዋወድ ጨዋታውን ሊያቆም ይገባል ።  ህዝብ በግልፅ የሚያውቀውን ነገር እንደ አቶ ሬድዋን አይነት የህወሐት ባልንጀሮች እልህ በተሞላበት መንገድ በአደባባይ " ህወሐት የፀጥታ ችግር ስላለበት ትጥቅ አይፈታም " ብለው እንዳረጋገጡልን በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ህወሐት ትጥቅ አልፈታም ። የህወሐት ከእነ ትጥቁ መቀመጥ ደግሞ እናንተ አፍላ ፍቅር ላይ ስለሆናችሁ ስጋትነቱ ባይታያችሁም  እኛ ግን የጥንተ ጠላታችን ባህሪ ጠንቅቀን ስለምናውቅ  ጨዋታ ቀይሩ !!!

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ደሴ ሰላማዊ ሰልፍ በመደረግ ላይ ነዉ❗
Happening right now❗
ሚያዝያ 2/2015 ዓ.ም
=======≠=================

Читать полностью…

Ethio 360 Media

እባካችሁ ተው ብለን እንለምናችሁ‼️

#Ethiopia | "ቤት አፍርሶ ቤት ለመገንባት መሞከር ኃጢያት ነው። የክፍለ ከተማው፣ የወረዳው ባለሥልጣን ይሄ ሁሉ ቤት ሲሰራ የት ነበር? ... መቀጣት ያለበት አካል ተትቶ፥ ዛሬ በግሬደር መታረሱ ያሳዝናል። እባካችሁ ተው ብለን እንለምናችሁ"

አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በቆቦ የተኩስ ልውውጥ መደረጉን ሮይተርስ ምንጮችን ጠቅሶ ዘገበ።
ሚያዝያ 1/2015 ዓ.ም
=======≠=================

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ደብረብርሃን ወደ አዲስ አበባ መንገዱ ጠዋት ጀምሮ እስካሁን ሙሉ ለሙሉ ዝግ ነው። በምን ምክንያት እንደጠፋ ባይታወቅም ጠዋት ጀምሮ ሙሉ ከተማው እስካሁን መብራት የለም።
ሚያዝያ 1/2015 ዓ.ም
=======≠=================

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ይሄ ሁሉ ነገር ከመፈጠሩ በፊት የውሳኔው ባለቤቶች ቆም ብለው እንዲያስቡበት እና ህዝባችን ዋጋ እንደሚያስከፍል ለማሳሰብ ሞክረናል ።

ጥድፊያው የበዛ ነበር ፤ በክልል ካቢኔ ደረጃ ውሳኔው አንዴ ተወስኗል መረጃው እንዲኖራችሁ ነው በሚል የተድበሰበሰ ውይይት እንዲታለፍ ተደርጓል ። ይሄ ታሪካዊ እጥፋት ነው ካቢኔውም ሆነ የክልል ም/ቤቱ ውሳኔ ማሳለፍ እንደሚገባው ወቅቱንም ያገናዘበ እንዲሆን አሳስበናል ለመስማት ፍቃደኛ የሆነ አካል ባይኖርም ።

በዘር ተወክለው የተሰበሰቡ የፓርቲ ስራ አስፈፃሚዎች የወሰኑት ውሳኔ "ልዩ ሐይሉ ብሔር ተኮር ነው " የሚል ስላቅም አለበት ። ከፈረሱ ጋሪው እንደሚሉት የዘር ፖለቲካ ገዥ ሃሳብ ሆኖ በቆመበት እና ዋነኛው ችግርም ከዚሁ የዘር ፖለቲካ የሚቀዳ ሆኖ እያለ የዘሬን አትንኩብኝ የብሔር ሐይል ግን አጠፋለሁ ብሎ መነሳት ከስጋው ፆመኛ ነኝ ከመረቁ ግን አቅምሱኝ እንደማለት ነው ።

ህዝባችን ከስጋት ባልተላቀቀበት እና የክህደት ሐይሎች ዛሬም አድብተው በሚጠብቁን ሁኔታ አጥንት ተሰብስቦ ፌድሬሽን ምክር ቤት ላይ በሚወስንበት ሀገር የህዝባችን ትግል የአጥንት አቢዮት ብሎ ለማጣጣል መሞከር ትርጉም አልባ መሆኑን ተረድቶ በሐይል ለማስገበር የሚደረግን እንቅስቃሴ በፍጥነት ማቆም ይገባል።
የአብን ከፍተኛ አመራር እና የአማራ ክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ ጣሂር መሃመድ
=======≠=================

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አሜሪካ በሳዑዲ አረቢያ የመከዳት ስሜት እንደተሰማት ገለፀች‼️


ሳዑዲ አረቢያ ከአሜሪካ ባላንጣዎች ከሚባሉት ኢራንና ሶሪያ ጋር ግንኙነቷን አድሳለች። የሲ.አይ.ኤ ዳይሬክተር ዊሊያም በርንስ ወደ ሪያድ አቅንተው ለሳዑዲ አረቢያ ስሞታ አቅርበዋል ብሏል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ከደብረማርቆስ ተጨማሪ ምስል❗
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ከሸዋሮቢት ከተማ ወጣ ብሎ መንገድ ተዘግቷል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ወደ ጎጃም መስመር የሚያስኬደው የአባይ ማዶ ደጀን በዚህ መልኩ መንገድ ተዘግቷል።

ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን ለወዳጅዎ ያጋሩ::

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የዘንድሮዉ ነገር ጉድ እኮ ነዉ:: ቤቷ ከተቀመጠችበት አፍነዉ ወስደዉ ወታደራዊ ስልጠና እና የተኩስ ልምምድ ስታሰለጠን ያዝናት ብሎ መክሰስ ምን ማለት ነዉ???

መስከረም አበራ “ለኢ-መደበኛ አደረጃጀቶች ወታደራዊ ስልጠና እና የተኩስ ልምምድ ስትሰጥ ነበር” ሲል ፖሊስ ወነጀለ ‼️
ከትላንት በስቲያ እሁድ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለችው የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዋ መስከረም አበራ፤ “ሁከት እና ብጥብጥ በማነሳሳት ወንጀል” ተጠርጥራ በፍርድ ቤት 13 የምርመራ ቀናት ተፈቀደባት። መስከረምን ፍርድ ቤት ያቀረባት የፌደራል ፖሊስ፤ “ተጠርጣሪዋ ለኢ-መደበኛ አደረጃጀቶች ወታደራዊ ስልጠና እና የተኩስ ልምምድ ስትሰጥ ነበር” ሲል ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።

ፖሊስ ዛሬ ማክሰኞ ሚያዚያ 3፤ 2015፤ በመስከረም ላይ ውንጀላውን ያቀረበው፤ ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው። በችሎቱ መስከረምን ወክለው የቀረቡት ጠበቃዋ አቶ ሄኖክ አክሊሉ በበኩላቸው ፍርድ ቤቱ የደንበኛቸውን የዋስትና መብት እንዲጠብቅ ጠይቀዋል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ኮምቦልቻ ከተማ ተቃውሞው ዛሬም እንደቀጠለ ነው።
ሚያዝያ 3/2015 ዓ.ም
=======≠=================

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች እና በጋዜጠኞች ላይ በመንግሥት የጸጥታ አካላት እየተፈጸመ ያለውን የዘፈቀደ እስራት እንዲቆም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ጠየቀ‼️


ማዕከሉ ሕጋዊ ሥርዓትን ያልተከተለ እስር፣ አፍኖ መሰወር፣ አግቶ ለሰዓታት አቆይቶ መልቀቅ፣ አፍኖ ወዳልታወቁ ሥፍራዎች በመውሰድ ድብደባ መፈጸም፣ ለቀናት ፍርድ ቤት ሳያቀርቡ አሥሮ ማቆየት፣ ፍርድ ቤት በዋስትና የለቀቃቸውን ሰዎች አግዶ መያዝና የመሳሰሉትን ተግባራትን መንግሥት እንዲያስቆም ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል፡፡

የተጠቀሱትን ሕገ-ወጥ ተግባራት በፈጸሙ የጸጥታ አካላት ላይም ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስድ የጠየቀው ማዕከሉ፣ መንግሥት በቅርቡ ያሰራቸውን ጋዜጠኞችና የመብት ተሟጋቾች ይለቃል ተብሎ ሲጠነበቅ፣ በትላንትናው ዕለት መምህርት እና የፖለቲካ ተንታኝ የሆነችው መስከረም አበራ ከመኖሪያ ቤቷ በፖሊሶች ተይዛ መወሰዷን ከቤተሰቦቿ ለማረጋገጥ ችያለሁ ብሏል፡፡

ማዕከሉ እነዚህ አይነት ድርጊቶች በሕገ መንግስቱ እውቅና የተሰጣቸውንና ሙሉ ጥበቃ የተደረገላቸውን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እና የሚዲያ ነጻነትን የሚመለከቱትን ድንጋጌዎች የሚጥሱ እና ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ስምምነቶች ፈርማ የተቀበለቻቸውንም ግዴታዎች የጣሱ መሆናቸውን ገልጿል፡፡

የቀጠለው የጅምላ እስር በጋዜጠኞች፣ በማኅበረሰብ አንቂዎች እና ሃሳባቸውን በነጻነት በመግለጽ ፖለቲካዊ ትንተና በሚያደርጉ ሰዎች ላይ ተጠናክሮ መቀጠሉ ማዕከሉ ክፉኛ አሳስቦል ብሏል፡፡ በአንድ አገር ውስጥ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ሊገነባ፣ የአገር ሉዓላዊነትም ሊጠበቅ፣ ሰላም ሊሰፍን እና የፖከቲካ መረጋጋትም ሊፈጠር የሚችለው ዜጎች፤ በተለይም በሚዲያዎች ላይ ሃሳባቸውን የሚገልጹ ጋዜጠኞች፣ የማህበረሰብ አንቂዎች፣ ምሁራን እና የፖለቲካ ተንታኞች በመንግሥት አሰራሮች ፖሊሲዎች ላይ ሃሳባቸውን በነጻነት መግለጽ ሲችሉ እና የማኅበረሰቡንም ስሜት ሲያንጸባርቁ መሆኑንም ገልጿል፡፡

በመሆኑም፤ መንግሥት በጸጥታ አካላቱ በኩል በጋዜጠኞችና የመብት ተሟጋቾች ላይ፤ በተለይም ሴት የመብት ተሟጋቾች ላይ የሚፈጽሙትን ተደጋጋሚ እሥር፣ እንግልት፣ ማዋከብ፣ ዛቻና ማስፈራሪያዎች፣ ድብደባ እና አግቶ የመሰወር ተግባራት እንዲያስቆም እና የሚዲያ ነጻነትን እንዲያረጋግጥ ማዕከሉ አሳስቧል፡፡

የታሰሩ የመብት ተሟጋቾች መስከረም አበራን እና ጋዜጠኛ ገነት አስማማውን ጨምሮ ሌሎቹም በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ የተያዙ ጋዜጠኞች በአፋጣኝ ከእስር እንዲለቀቁም ማዕከሉ መንግሥትን ጠይቋል፡፡

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አማራ የሚታገልበት ከበቂ በላይ የሆነ ምክንያት አለዉ❗❗❗

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ህወሃት 5 አርሚ ጦር ወደ ወልቃይት
3አርሚ ጦር ወደ ራያ አስጠግቷል
(መሳይ መኮንን)።
ሚያዝያ 2/2015 ዓ.ም
=======≠=================

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ደብረብርሃን‼️

ደብረብርሃን የተቃውሞ ሰልፉ ዛሬም ቀጥሏል።
ሚያዝያ 2/2015 ዓ.ም
=======≠=================

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ፤
____

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ከአማራ ልዩ ኃይል ጋር በተያያዘ የገዥው ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያሳለፈውን ውሳኔ እና ውሳኔውን ለማስፈጸም እየወሰዳቸው ያሉ እርምጃዎችን በሚመለከት በተከታታይ አቋሙን ግልጽ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ እንዲሁም የአማራ ክልልን ለከፍተኛ አለመረጋጋት እና የጸጥታ መድፈረስ ያጋለጠው ፣ ፍጹም ኃላፊነት የጎደለው እና አደገኛ የሆነው የገዥው ፓርቲ ውሳኔ እስኪቀለበስ ድረስ እና ተገቢው መፍትሄ እስኪገኝ ድረስ ድርጅታችን አብን አስፈላጊውን ጥረት እና ትግል እንደሚያደረግ ማሳወቁ ይታወቃል፡፡ ድርጅታችን አብን ሁኔታውን በከፍተኛ ትኩረት እየተከታተለ ሲሆን ፣ ገዥው ፓርቲ እና የፌዴራሉ መንግስት ስህተቱን ከማረም እና መፍትሄ ከማፈላለግ ይልቅ ከጥፋት ላይ ጥፋት እየጨመረ ችግሩን እያወሳሳበ እና ክልሉን ለከፍተኛ አለመረጋጋት እና የጸጥታ መደፍረስ እየዳረገው ይገኛል፡፡ በዛሬው እለትም በበርካት የአማራ ክልል ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች የተካሄዱ ሲሆን ፣ በተለያዩ አካባቢዎች መደበኛ እንቅስቃሴዎች ተስተጓጉለው ውለዋል፡፡ በተለይም በራያ ቆቦ ከተማ ውስጥና በዙሪያው በከባድ መሳሪያ ጭምር የታገዘ ተኩስ ሲደረግ የዋለ ሲሆን ይህ በከተሞች ውስጥና አቅራቢያ የሚደረግ የከባድ መሳሪያ ተኩስ በአስቸኳይ እንዲቆም እናሳስባለን።

ዛሬ ሚያዚያ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) “ከጊዚያዊ መፍትሄ ዘላቂ ጥቅም አይገኝም” በሚል በስማቸው ባወጡት መግለጫ ፣ “ዘላቂ መፍትሄ” ብለው የሰየሙትን የአማራ ክልል ልዩ ኃይልን ትጥቅ የማስፈታት ውሳኔ “ዋጋ ተከፍሎም ቢሆን ተግባራዊ እንደሚደረግ እና የህግ ማስከበር እርምጃ እንደሚወሰድ” በመግለጽ ፓርቲያቸው ያሳለፈው ውሳኔ በአማራ ክልል ለፈጠረው አለመረጋጋት እና የጸጥታ መድፈረስ ኃላፊነት ሳይወስዱ ቀርተዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው የልዩ ኃይል አባላትን ወደ ሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች እንዲገቡ ለማድረግ ተገቢው ዝግጅት እንደተደረገበት ፣ የልዩ ኃይል አመራሮች እና አባላት እንደ ተወያዩበት ፣ የልዩ ኃይል አባላት ወደ መረጡት ተቋም (የሀገር መከላከያ ሠራዊት ፣ የፌዴራል ፖሊስ  ወይም የክልል ፖሊስ) ለመቀላቀል ምርጫ እንደተሰጣቸው እና ውሳኔው በሁሉም ክልሎች የሚገኙ ሁሉንም የልዩ ኃይል ፖሊሶችን የሚመለከት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ነገር ግን የማስፈጸሚያ እቅድ ነው የተባለው ሰነድ እንኳ በፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት ደረጃ ውይይት የተደረገበት ትናንት ቅዳሜ መጋቢት 30 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በፌዴራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት መሆኑ ሲታይ ፣ ለአማራ ክልል ልዩ ኃይል አባላት “ትጥቃችሁን ፍቱ” ከሚል ትዕዛዝ በቀር እንኳን ምርጫ መረጃ እንኳን የሰጣቸው አካል እንደሌለ የሚታወቅ መሆኑ እና ከአማራ ክልል በስተቀር በየትኛውም ክልል ልዩ ኃይሎችን ትጥቅ የማስፈታትም ሆነ ወይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚሉት “ወደ ተለያዩ ተቋማት የማስገባት” እንቅስቃሴ የሌለ መሆኑ ሲታይ ፣ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያወጡት መግለጫ እውነትነት የሌለው መሆኑን እና በድርጅታች አብን የቀደመ ግምገማ መሰረት የክልል ልዩ ኃይሎችን ለማፍረስ የተላለፈው ውሳኔ በሁሉም ክልሎች ልዩ ኃይሎች ላይ በእኩል ደረጃ ተፈጻሚ የማይሆን እና የውሳኔው ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ የአማራ ልዩ ኃይልን ትጥቅ ማስፈታት እና መበተን መሆኑን አረጋግጧል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስተሩ በመግለጫቸው “የልዩ ሃይል አደረጃጀት አስፈላጊ አይደለም ማለት ፣ የልዩ ሃይል አባላት አያስፈልጉም ማለት አይደለም” ቢሉም ፣ በተግባር የአማራ ክልል ልዩ ኃይልን በሚመለከት ያሳለፉት ውሳኔ እና ውሳኔውን ለማስፈጸም እየሄዱበት ያለው መንገድ የአማራ ልዩ ኃይል ፖሊስ የሀገር አንድነትን እና ኅልውና ለማስከበር የከፈለውን መስዋዕትነት እና ግዙፍ አስተዋጽኦ የካደ ፣ በግዳጅ ላይ እና በካምፕ ውስጥ የሚገኙ የልዩ ኃይል አባላትን የዕለት ስንቅ ፣ ሎጂስቲክ እና ደሞዝ ነፍጎ ለርሃብ እና ለእንግልት እንዲዳረጉ ያደረገ ፍጹም ክብረ ነክ ተግባር ሲሆን ፣ እንኳንስ ለቀጣይ ሀገራዊ ተልዕኮ የማዘጋጀት ፍላጎት አይደለም ዝቅተኛውን የግበረ-ገብ እና ጨዋነት መመዘኛ የማያሟላ ፣ ልዩ ኃይሉን ተስፋ በማስቆረጥ እና በማበሳጨት ለመበተን እና ክልሉን የቀውስ እና የትርምስ ቀጠና የማድረግ ተልዕኮ ያለው ውሳኔ ሁኖ አግኝተንዋል፡፡

ይህም የክልሉ መንግስት የሚቆጣጠረውን እና የሚመራውን ኃይል በመበተን ፣ በእዝ የማይመራ እና መንግስት የማይቆጣጠረውን ኃይል ለመፍጠር እና ክልሉን ወደ ቀውስ እና ትርምስ ለመውሰድ የሚደረግ ጥረት ሆኖ የሚቆጠር ነው፡፡ ስለሆነም የገዥው ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ እና ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሳለፉትን ፍጹም ኃላፊነት የጎደለው ውሳኔ እና ውሳኔውን ለማስፈጸም እየሄዱበት ያለ ፍጹም አደገኛ ከሆነ መንገድ እንዲቆጠቡ እና ቆም ብለው እንዲያስቡ እያሳሰብን ፣ ፓርቲያችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን የሚከተሉትን ጥሪዎች በድጋሜ ያስተላልፋል:-

1. ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔያቸውን በይፋ እንዲሰርዙ ፣ ውሳኔው ስለመሰረዙ በአደባባይ እንዲገልጹ እና የአማራ ልዩ ኃይል አባላት እና የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ወደ ካምፓቻቸው እና ወደ ግዳጅ ቦታቸው እንዲመለሱ በይፋ ጥሪ እንዲያደርጉ፤

2. በፌዴራል መንግስቱ ውሳኔ እና ትዕዛዝ ከስራ ውጭ የሆኑት የአማራ ልዩ ኃይል ከፍተኛ አመራሮች ፣ የብርጌድ እና የክፍለ ጦር አዛዦች ወደ ኃላፊነታቸው እና ምድብ ቦታቸው እንዲመለሱ እንዲደረግ፤

3. የክልሉ መንግስት ለልዩ ኃይሉ  አስፈላጊ የሆኑ የስንቅ እና ሎጂስቲክ እንዲያቀርብ እና ደሞዝ እንዲከፍል፤

4. በካምፕ እና በግዳጅ ቦታችሁ ላይ የምትገኙ ውድ የአማራ ክልል የልዩ ኃይል ፖሊስ አመራሮች እና አባላት ሠራዊቱ እንዲበተን የሚደረጉ ጥረቶችን እና የፕሮፖጋንዳ ጥቃቶችን በመቋቋም በተለመደው ሥነ-ምግባር ፣ ዲስፕሊን እና ጨዋነት የሠራዊቱን የእዝ ሰንሰለት አክብራችሁ እና ጠብቃችሁ ከህዝባችሁ ጎን እንድትቆሙ፤

5. ለሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት እና አመራሮች በሙሉ በግፍ እየተጠቃ ካለው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና ከአማራ ሕዝብ ጎን እንድትቆሙ እና ለግጭት ከሚጋብዙ ማናቸውም ሁኔታዎች እንድትቆጠቡ፤

6. የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የዞን እና የወረዳ አመራሮች በሙሉ በዚህ ፈታኝ ወቅት ከልዩ ኃይል ፖሊስ ሰራዊት እና ከሕዝባችሁ ጎን እንድትቆሙ፤ 

7. የአማራ ሕዝብ በየአካባቢው ላሉት የልዩ ኃይል አባላት አስፈላጊውን ስንቅ እና ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ድርጅታችን አብን ጥሪውን ያቀርባል።

አብን ጉዳዩን በቅርበትና በንቃት እየተከታተለው መሆኑን እየገለፀ መንግስት ውሳኔውን እስኪቀለብስ እና ሁኔታዎች እስኪስተካከሉ ድረስ ተከታታይ ሰላማዊ ትግል የሚያደርግ መሆኑን ያሳውቃል። ድርጅታችን አብን መላው የአማራ ሕዝብ እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ከሀገር ወዳዱ የአማራ ልዩ ኃይል ጎን እንድትቆሙ የከበረ ጥሪውን ያቀርብላችኋል።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)
አዲስ አበባ ፣ ሸዋ ፣ ኢትዮጵያ
ሚያዚያ 1 ቀን 2015 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio 360 Media

መስከረም አበራን ለሦስተኛ ጊዜ አፍነው ወስደዋታል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ስለ አማራ ብሄርተኝነት.......

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ምንጃር ልዩ ሃይላችን ትጥቅ አይፈታም በሚል ሰልፍ ወጥተዋል።
ሚያዝያ 1/2015 ዓ.ም
=======≠=================

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የጎንደር እናቶች ለልዩ ሀይሉ በዚህ መልኩ ምግብ ካምፕ ድረስ በመውሰድ አድርሰዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በጎጃም ሉማሜ ኤዋበል የተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ ነው።
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ኦሮሞ ይሄንን ታጥቆ አማራን ትጥቅ ፍታ ማለት ትንሽ አይከብድም????

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ጎጃም ቢቸና ላይ ተቃውሞ እየተካሄደ ነው።
መጋቢት 29 ቀን 2015 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የአማራ ልዩ ሀይል በዚህ ወቅት ትጥቅ መፍታት የለበትም በሚል በሸዋ ይፋት የራሳ ነዋሪዎች ሰልፍ መውጣቸው ታውቋል።

Читать полностью…
Subscribe to a channel