ethio360media | Unsorted

Telegram-канал ethio360media - Ethio 360 Media

37564

ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር !!!

Subscribe to a channel

Ethio 360 Media

“ከራያ አላማጣ ህዝብ ፍላጎት ውጪ የሚመጣ ማንም የህወሓት አመራር ወደ አላማጣ አይገባም”። ወደ ከተማዋ ደፍረው ቢገቡም የሚጠብቃቸውን እርምጃ ያውቁታል ብለዋል።
ወያኔና የወያኔ ደጋፊ ወደ አካባቢያችን ቢመጣ ፍርድ የሚያገኘው ከራያ ወጣት እንጂ ከሌላ አካል አደለም።
⛔️ ወያኔና የወያኔ ደጋፊ ጥይት ታጥቆ በር ተኽላይን አይሻገርም።
⛔️ አሁን ያለው የግዚያዊ አስተዳደር መዋቅር የሚነሳው ህዝበ ውሳኔ የሚካሄድ ከሆነ በህዝበ ውሳኔ ወቅት ብቻ ነው።
⛔️ አሁን ያለው ግዚያዊ አስተዳደር የፌዴራል መንግስት አውቆት ይሁንታ ሰጥቶትና በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት እንጂ በጉልበት እንዳልሆነ ሁሉም ልያውቀው ይገባል።
⛔️ የወያኔ አመራር ዳግም አላማጣ የሚረግጠው የሰራውን ወንጀል አምኖ እጁን ለካቴና ለመስጠት እንጂ አከባቢውን ለመምራት አይመጣም ።
⛔️ ወያኔ የሰላም ስምምነቱ ጥሶ ድጋሚ ጦርነት አነሳለሁ በር ተኽላይን እሻገራለሁ ካለ ጠቡ ከጀግናው ሀገር መከላከያ ጋር እንጂ የራያ ወጣት ጋር አይሆንም።
-የአላማጣ ከተማ ከንቲባ እና የወሎ ራያ አማራ ወሰንና ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሃይሉ አበራ
ሚያዝያ 10/2015 ዓ.ም
=======≠========

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በሱዳኑ ግጭት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 144 መድረሱን ኮሚቴው ገለጸ

የሱዳን ዶክተሮች ኮሚቴ፣ በሱዳን በተቀሰቀሰው ግጭት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 144 ከፍ ማለቱን ገልጿል።

ኮሚቴው የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር 1409 መድረሱንም ጠቅሷል።

ነገርግን ተመድ የሟቾችን ቁጥር ወደ 185 ከፍ አድርጎታል።

በሱዳን ጦር እና በጀነራል ሀምዳን ዳጋሎ በሚመራው የፈጥኖ ደራሽ(አርኤስኤፍ) መካከል ባለፈው ቅዳሜ የተቀሰቀሰው ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ነው።

አሜሪካን ጨምሮ በርካታ ሀገራት ሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች ግጭት እንዲያቆሙ እየጠየቁ ነው።
ተመድ አሁን ላይ ድርድር ለመጀመር በሁለቱም ወገኖች በኩል ፍቃደኝነት የለም ብሏል(AlAin)።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ከ ሱዳኖች ለአብይ አህመድ የተላከ!!

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በሀመንቲ የሚመራው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር የሱዳን ብሮድካድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ህንጻ መያዙን አስታወቀ‼️


የሬዲዮና ቴሌቪዥን ማሰራጫው በኦምዱርማን ይገኛል።
በአሁኑ ወቅት በቴሌቪዥንና ሬዲዮ ጣቢያው አካባቢ ግጭት እንደሌለ የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ አስታውቋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ሱዳን እስካሁን 97 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል።

✔በካርቱም ውጊያ በመኖሪያ መንደሮች ጭምር እየተደረገ ነው።

✔ በሱዳን ባለፉት ሶስት ቀን የሞቱ ሰላማዊ ሰዎች ከ100 ተሻገረዋል። እጅግ በጣም በርካታ ሰዎች ተጎድተው ሆስፒታሎች ተጨናንቀዋል።

✔ የRSF የፖለቲካ አማካሪ የሱፍ ኢዛት ለአልጀዚራ በሰጡት ቃል ማንኛውም የተኩስ አቁም ለማድረግ በሠራዊቱ ውስጥ የ "አመራር መኖር"ን ይጠይቃል ብለዋል። " ሠራዊቱ ምንም ዓይነት አመራር የለውም። " ያሉት አማካሪው " የተኩስ አቁም መቼ እንደሚሆን የምንወስነው እኛ ብቻ ነን " ብለዋል።

✔  RSF " ወንጀለኛ ናቸው " ሲል የጠራቸውን አልቡርሃንን በቁጥጥር ስር ለማዋል ፍለጋ ላይ መሆኑን አሳውቋል።

✔ በጄነራል ቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር የRSF ሚሊሻዎች ሰላማዊ ሰዎችን ከለላ አድርገው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን በመግለፅ ሰላማዊ ሰዎች እንዳይጎዱ ጥብቅ በሆነ ወታደራዊ ጥንቃቄ ኦፕሬሽኑን እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
(አልጀዚራ፣ቢቢሲ፣ቲክቫህ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በሰሜኑ ጦርነት ላይ በነበርንበት ጊዜ መሬታችንን የያዘው በጄኔራል ቡርሃን የሚመራው የሱዳን መከላከያ ሀይል ተበትኗል። በገዳሪፍ ስር የሰፈረው ወታደር ተመልሶ ከሰላ ወደ ሚባል ቦታ ሄዷል። ይህ ማለት መንግስት አካባቢው ላይ ሰላም አስከባሪ መስሎ ቦታዎችን መልሶ መቆጣጠር ይችላል። ይዞ መደራደር እና ሰጥቶ መደራደር ከፍተኛ ልዩነት አላቸው። ጦርነቱ በዚህ ከቀጠለ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ስደተኞች መግባታቸው አይቀርም፣ ስለዚህ መሰራት ያለበት ነገር ካለ አሁን ነው።
ሚያዝያ 7/2015 ዓ.ም
=======≠========

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በሱዳን ያሉ ኢትዮጵያዊያን ከግጭት አከባቢዎች እንዲርቁና ከእንቅስቃሴ እንዲቆጠቡ ማሳሰቢያ ተለለፈ።
ካርቱምን ጨምሮ በተለያዩ የሱዳን ግዛቶች ከፍተኛ ግጭት ተፈጥሯል።
ከተፈጠረው ግጭት ጋር በተያያዘ ሊያጋጥም ከሚችል አደጋ  እራስን መጠበቅ አስፈላጊ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ከግጭት አካባቢዎች በመራቅና ከእንቅስቃሴ በመቆጠብ እራሳቸውን ከአደጋ እንዲጠብቁ  በካርቱም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳስቧል።
ሚያዝያ 7/2015 ዓ.ም
=======≠========

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በወለጋ ከትላንት ሌሊት ጀምሮ ማንነትን መሰረት ያደረገ ግድያ ዳግም አገርሽቷል። በተለይ አንገርጉትን እና ቱሉጋና በተባለችው ከተማ በርካታ ዜጎች መገደላቸውን መረጃ ደርሶናል። ያነጋገርናቸው ሰዎች ግድያውን የሚፈጽሙት የመከላከያ ሰራዊት ልብስ የለበሱ ናቸው ብለዋል።
ሚያዝያ 6/2015 ዓ.ም
=======≠========

Читать полностью…

Ethio 360 Media

መቻል ነው እንግዲህ…!

"…ዛሬ ከሰዓት በኋላ ላይ በዐማራ ክልል በኦሮሚያ ልዩ ዞን ውስጥ በመጀመሪያ ሃገር ሰላም ብለው ወደ ሸዋ ሮቢት በመጓዝ ላይ የነበሩ በቁጥር 3 የሚሆኑ የዐማራ ልዩ ኃይል አባላትን ኦሮሞዎቹ የኦሮሞ ነፃ አውጪ ነን ባዮቹ የአቢይ አሕመድ የሽመልስ አብዲሳ ፕላን ቢ ዐማራ መቅጫ መሳሪያዎቹ ሸኔዎች ሰንበቴ በልጪ ላይ መኪና አስቁመው ከመኪናም ውስጥ በዐማራ ሽማግሌዎች ውትወታ መሳሪያ አውርደው ወደ ቤተሰቦቻቸው በመመለስ ላይ የነበሩ ምስኪን የዐማራ ልዩ ኃይል ታዳጊ ወጣቶችን ከመኪና አውርደው በዚህ መልኩ በአደባባይ ረሽነዋቸዋል ተብሏል። ይሄ አንደኛው ነው።

"…በሌላ ዜናም ከአደረጃጀት ወጥተው፣ በሰላም ወደ ቤተሰባችን እንመለሳለን ብለው፣ መሣሪያ ለብአዴን አስረክበው ለበዓል ወደ ቤተሰብ በመመለስ ላይ ነበሩ የተባሉ ሌሎች አንድ መኪና ሙሉ የዐማራ ልዩ ኃይሎች ጅብውኃ ድልድይ ላይ ሲደርሱ የኦሮሞ ነፃ አውጪዎቹ ጠብቀው ለወሬ ነጋሪ ሳያስቀሩ እንደጨፈጨፏቸውም ተሰምቷል። ለወሬ ነጋሪ የተረፈ አንድም የዐማራ ልዩ ኃይል አለ ነው የተባለው።

"…እነዚህ ምስኪን ተቆርቋሪ አልባ ምስኪን የዐማራ ልዩ ኃይል አባላት ከበጤ ጀምሮ የጥይት እሩምታ እየተተኮሰባቸውም ቢሆን በተቻለ አቅም ለማምለጥ የሞከሩ ቢሆንም ከግራኝ አሕመድ ልጆች ከኦሮሞዎቹ ጭፍጨፋ እንዳላመለጡ ነው የተነገረው። ምን ይደረግ እንግዲህ…? መቻል ነው። ምከረው ምከረው እምቢ ካለ ምን ይደረግ…?

"…ሰንበቴ ላይ ገርቢ በሚባል ሥፍራም አንድ የዐማራ ልዩ ኃይል አባልን በልዩ ዞኑ የሚኖሩት የኦሮሞ ነፃ አውጪ ነን ባይ ኦረሮሞዎች በዱላ ቀጥቅጠው እንደገደሉትም ተነግሯል። ለዚህ ጥይትም አላባከኑ። ቀጥሎ የብአዴን ፋኖዎች እና እነ ምሬ ወዳጆን ማየት ነው። ብቻ ወየው ወየው እንዳይሉ ከወዲሁ ሽማግሌ መላክ ነው።

"…በሌላ ዜና ይህ በእንዲህ እንዳለ ስማቸው ለጊዜው ያልተገለጸ 3 የብአዴን ከፍተኛ ባለ ሥልጣናት ሐሰተኛ የህክምና ማስረጃ በማጻፍ በቦሌ በኩል ከሃገር ሊወጡ ሲሉ በኦህዴድኦነግ የደኅንነት ኃይሎች መመለሳቸውም ተሰምቷል። የትአባክ ልትሄድ…? የት ልትፈረጥጥ ነው አንት አሳራጅ ጀዝባ…? ገና የኢዜማ፣ የግንቦት 7፣ የዐብን አመራሮች በአጠቃላይ አብይን አምነው በሰሜኑ ጦርነት ላይ የተሳተፉ በሙሉ ጋዜጠኛ በለው አርቲስት፣ ባለሃብት ወዘተረፈ የእጃቸውን ሳይሰጧቸው የሚቀር አይመስለኝም። በቁም እስር የተቀመጠው ዶር ይልቃል መታመሙ፣ ጀነራል አበባውም አደጋ እንደደረሰበት መነገሩ። ብርሃኑ ጁላም እንደዚያው ነው መባል መሰማቱ አደጋ እንዳለ ፍንጭ የሚሰጥ ነው። ሂዊ ሆዬ ከመሃይም ልጇ ከአብይ ጋር ሆና በሰሜኑ ጦርነት ላይ የተሳተፉ፣ አርቲስት በለው፣ ባለሃብት፣ ቄስ በለው መነኩሴ፣ ሼክ በለው ኡስታዝ ትበቀላቸዋለች ተብሎ ይጠበቃል። በተለይ በሽማግሌ፣ በታቦት፣ በመስቀል፣ በኡስታዝ በሼክ ተታለህ ባዶ እጅህን ካገኙህ ያሳዩሃል። ጠብቅ።

"…የሆነው ሆኖ የዐማራ ትግል አይቆምም። ላቁምህም ብትለው አይቆምም። ትናንት እንዳልኩት የዐማራን ትግል ከትግሬ ነፃ አውጪዋ ከትህነግ እና ከኦሮሞ ነፃ አውጪ ነን ባዮች ኦነጎች ጋር ስናነፃፅረው በአጭር ጊዜ እጅግ ፈጣንና አስደናቂ እድገት ያመጣ መሆኑን መዘንጋት የለብንም። ዐማራ በሙሉ ልቡ ዐማራ ነኝ ብሎ በአደባባይ በድፍረት መነጋር ከጀመረ ገና አምስት ወይ ስድስት ዓመት ቢሆነው ነው። ጨክኖ በመንግሥት ላይ መተኮስ ከጀመረ ደግሞ ገና አንድ ሳምንት ቢሆነው ነው። እናም ውሎ ሲያድር የዐማራውን ኃይል መላሽ አይኖረውም ባይ ነኝ።

"…እስከዚያው ግን የተዘበራረቀው ቦታ ቦታውን እስኪይዝ ድረስ እዚህም፣ እዚያም መንገራገጮች ይኖራሉ። እሱ ነገር የሚጠበቅ ነው። ተፈጥሮአዊም ነው። ዐማራን ወደ እዚህ ከፍታ ያወጣው በኦሮሞ ነፃ አውጪዎች እና በትግሬ ነፃ አውጪዎች መለብለቡ፣ መገረፉ፣ መፈናቀሉ፣ መታረዱ፣ መሰደዱ፣ መጨፍጨፉ፣ መዋረዱና መሰቃየቱ ነው። ዐማራን ለዚህ ፈጣን ደረጃ ያበቃው ይሄ ነው። እንጂ በጋለ ብረት ብትተኩሰው ጭራሽ አይሰማህም ነበር። አሁንም ህወሓት ከላይ፣ ኦነግ፣ ኦህዴድ ከግራ ከቀኝ ከታች፣ ብአዴን ከውስጥ፣ ሱዳን ከውጭ ደኅና አድርገው ሲያዋክቡት፣ አስገድደው ሲደፍሩት ለመፍትሄ ለነፃነት ዋጋ መክፈል ይጀምራል። የውስጥ አንድነቱን ያጠነክራል። መሪ ይወልዳል። በቀላሉ የማንም መንገደኛ የማያሞኘውም ይሆናል።

"…ዐማራው ማድረግ አለበት የምለው ሌላው ነገር። አሁን በእርቅ መሣሪያህን አውርድ እንደተባለ ሰምተናል። ያወረዱ እንዳሉ ሁሉ ሚልዮኖች አሁንም መሣሪያቸውን አላወረዱም። በተለይ ሽማግሌ ነነ፣ የሃይማኖት አባቶች ነነ፣ ብለው ዐማራን በዕርቅ ሰበብ ያጀዘቡ ሽማግሌዎችን ህወሓት እና መከላከያ ተመሳጥረው ዳግም ሌላ ውዝግብ የሚፈጥሩ ከሆነ እነዚያን ሽማግሌ ነን ያሉ የሃይማኖት አባቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች ምነዋ፣ ምነ ቃላችሁን አጠፋችሁ ብለው እንዲጠይቋቸው ወደ ፈንጂ ወረዳው ከፊት መላክ ነው። ሽማግሌ ጥይት ማብረድ አለበት ባይ ነኝ። አለቀ።

"…እንግዲህ ትጥቅ ከፈቱ በኋላ ወታደር ነኝ አይባልም። ሱሪ ካወለቁ፣ ቀበቶ ከፈቱም በኋላ ወንድ ነኝ፣ ጀግና ነኝ አይባልም። ዐማራ ቢታጠቅ ጠላት ሲመጣ ሊመክትበት ነው እንጂ ባንክ ሊዘርፍበት አይደለም። እናም ጠላትህ እስከ አፍንጫው ታጥቆ አንተ ሌጣህን ከቀረህ በኋላ ብአዴን አሳስቶኝ ነው፣ የብፁዕ አቡነ እንትና ወእገሌ ግዝት ፈርቼ ነው፣ ጳጳስና ቄስ፣ ሼክ እና ኡስታዝ፣ የሃገር፣ የመንደር፣ የቀዬው ሽማግሌና ፓስተር አሳስቶኝ ነው አይሠራም። ትጥቅ ያልፈታ እሱ በደንብ አድርጎ ያራውጥህሃል። ይጨረግድህሃል። መዋጥ ነው እንግዲህ።

"…የሚገርመው አሁን ነገሩ ያልገባው የዐማራ ሚሊሻ ነው። የዐማራ ሚሊሻ ምንም የሰማው ነገር የለም። የዐማራ ሚሊሻ የሚሰማው የቀበሌውን ጠርናፊ ነው። ከልዩ ኃይሉ ጋር ሉታኮስ፣ ከፋኖ ጋር ሊገጥም የነበረው ሚሊሻው ነበር። ይሄ ደግሞ የዐማራ ወጣቶች ስህተት ነው። እሱ በፌስቡክ የነቃውን ገጠር ወርዶ ገበሬውን አላነቃም። የዐማራ አንቂ ከተማ ተወዝፎ የቢራ ቡቱሌ አንገት አንቆ መዘብዘብ እንጂ ገጠር ወርዶ ሥራ መሥራቱ ላይ የለበትም። ከተማ ከተማውን ብቻ መርመጥመጥ ነው። ይሄ ርሚጦ። በዚህ ምክንያት ሚሊሻው ምንም የሚያውቀው ነገር የለም።

"…መንግሥትን አምኖ፣ አሁን ሽማግሌም አምኖ፣ ትጥቁን ከፈታ በኋላ ተገደልኩ፣ ተጨፈጨፍኩ ለሚል ልዩ ኃይል ማዘን አይገባም። ይልቅ ሌሎች ያልፈቱት ቢፈቱ የሚደርስባቸውን ሰቆቃ እያሳያ በጥልቀት እንዲታገሉ ማድረጉ ላይ ነው መበርታት። ማልቀስ የሚፈልግ የዐማራ ልዩ ኃይል እና ፋኖ ካለ ከአሁን በኋላ ተደብቆ ቢያለቅስ መልካም ነው። ሸጋም ነው። ሰው አትረብሹ። ጎረቤት መንደሩንም አትበጥብጡ። ስንት ዓመት ሙሉ ለዐማራ ይለቀሳል…? ማልቀስም ሱስ ይሆናል እንዴ? ከምር ያስጠላል።

• መቻል ነው አባቴ።

(ዘመድኩን በቀለ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን የዶክተሬር ዲግሪ ለመሰረዝ በቂ ማስረጃ መኖሩ ተገለጸ❗❗❗

ጥያቄ ሲነሳበት የነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የዶክተሬት ዲግሪን ሊያሰርዝ የሚችል በቂ የጥናት “ስርቆት” ማስረጃ ማግኘቱን የዓለም ሰላም ፋውንዴሽን አስታወቀ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እ.ኤ.አ. በ2017 የዶክተሬት ዲግሪያቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላም እና ደህንነት ጥናት ተቋም (IPSS) ከተቀበሉበት ጊዜ አንስቶ፤ በዶክትሬት ዲግሪያቸው ላይ የሕጋዊነት  ጥያቄዎች ሲነሱ እንደነበር ተቋሙ አስታውሷል፡፡

ፋውነዴሽኑ ከዚህ በፊት ጥያቄ ሲነሳበት የነበረውን የጠቅላይ ሚኒስትሩን የዶክተሬት ድግሪ ላይ ሰፊ ማጣራት በማድረግ ያገኘው ማስረጃ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥናት እንደገና ሊመረምር የሚችልበት በቂ ማስረጃ ማግኘቱን ጠቁሟል፡፡

ተቋሙ የዶክትሬት ዲግሪውን ለማገድ ወይም ለመሻር በቂ ነው ያለውን ማስረጃ ሲያቀርብ፤ በሌሎች ጥናቶች ላይ የተጠቀሱ ጽሑፎች በቀጥታና በጥቂት ማሻሻያ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥናት ላይ ተደግመው መገኘታቸው በማስረጃ አስደግፎ አብራርቷል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የዶክተሬት መመረቂያ ፅሑፍ ላይ “የሌብነት” ምልክቶች እንዳሉ ባደረገው ማጠራት መታዘቡን ፋውንዴሽኑ ይፋ ባደረገበት ጽሑፍ ላይ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጉዳዩን እንደገና ሊመለከት የሚችልበትን ሁኔታ ጠቁሟል፡፡

በዚህም ዩኒቨርስቲው ፕላጂያሪዝምን ወይም የሰው ጥናት ስርቆትን በሚከለክለው አሰራር እንደ ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች የዶክትሬት ዲግሪያቸውን መሰረዝ እንደሚል ተጠቁሟል፡፡ በኹለተኛ ደረጃ እንደ አማራጭ የተጠቆመው፤ ጥናቱ እንደገና ተሻሽሎ ድጋሚ እንዲሰራ በማድረግ እሰከዚያው የዶክተሬት ዲግሪ ማገድ ነው፡፡

የመመረቂያ ጥናቱ “Social Capital and its Role in Traditional Conflict Resolution: The Case of Inter-religious Conflict in Jimma Zone of the Oromia Regional State in Ethiopia” በሚል ርዕስ የተሰራ ሲሆን፤ የጥናቱ ትኩርት ማኅበራዊ ካፒታል በባህላዊ የግጭት አፈታት ውስጥ ያለው ሚና ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡

“ፕላጂያሪዝም” የሰውን ጽሑፍ ወይም ሥራ መስረቅ ወይም የራስ አስመስሎ ማቀረብ የሚል ተቀራራቢ ትርጉም የሚሰጠው ሲሆን፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥናትም ይህ አይነቱ ችግር እንደታየበት ፋይንደሽኑ ትናንት ይፋ ባደረገው ጽሑፍ አስታውቋል፡፡

የዓለም ሰላም ፋውንዴሽን በጠቅላይ ሚኒስትሩ የዶክተሬት ዲግሪ ላይ ያቀረባቸውን ማስረጃዎች ለመመልከት 👉 https://t.co/rnnNneqRIl
(በመርሻ ጥሩነህ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የተዋቀረ መዋቅር በቀጣይ ጊዚያት የራያ እና የፀለምት አካባቢዎችን ለማስተዳደር ማዘጋጀቱ ተገልጿል። አዲሱ መዋቅር ከሽሬ ተነስቶ በመጪዎቹ ቀናት ወደ ጠለምት በማቅናት አስተዳደራዊ ተቋሞችን እንደሚረከቡ ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪ አዲሱ መዋቅር በዓልን ኮረም እናሳልፋለን ያሉ ሲሆን ከዛም ወደ አላማጣ ከተማ በመግባት አስተዳደራዊ መዋቅሮችን ለመረከብ እቅድ እንዳላቸው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።
ሚያዝያ 5/2015 ዓ.ም
=======≠============

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ትጥቅ መፍታት ያለበት ማን ነው?

ኦሮሚያ ውስጥ ትናንት በፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት ተፈፅሟል። በተጠና መልኩ ከወለንጭቲ ወደ መተሃራ በመንቀሳቀስ ላይ የነበሩ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት ጥቃት ደርሶባቸዋል። ጥቃቱ በተጠና መልኩ የተደረገ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን 50 ያህል የፌደራል ፖሊስ አባላት ተገድለው፣ ከ40 ያላነሱ ቆስለዋል። ከተገደሉት መካከል አመራሮችም እንዳሉ የተገለፀ ሲሆን መሳርያዎቻቸው ተወስደዋል።

ኦነግ ሸኔ ተብሎ የሚነገርለት የክልሉ መዋቅር የሚደግፈው ኃይል ትጥቅ ሳይፈታ ነው የሌሎቹ ክልሎች በተለይም የአማራ ልዩ ኃይል ወደ ሌሎች የፀጥታ መዋቅሮች ይጠቃለል የሚሉን።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ከአዲስ አበባ ኮንዶሚኒዬም ዕጣ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ በ“ከባድ የሙስና ወንጀል” ከተከሰሱ ግለሰቦች ውስጥ አምስቱ በፍርድ ቤት ነጻ ተባሉ
የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክ ሙያና ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉቀን ሀብቱን ጨምሮ፥ ከኮንዶሚኒዬም ዕጣ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ “ከባድ የሙስና ወንጀል” ክስ የተመሰረተባቸው አምስት ግለሰቦች በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነጻ ተባሉ።
በዚሁ መዝገብ ክስ ከቀረበባቸው ግለሰቦች መካከል አንድ ተከሳሽ በሌሉበት ጥፋተኛ ሲባሉ፥ ቀሪ አምስት ተከሳሾች ደግሞ የተከሰሱበት ድንጋጌ ተቀይሮ እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ በይኗል።

Federal Ethics and Anti-Corruption Commission

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አቶ ስንታየሁ ቸኮል ተፈቱ

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ሀለፊ እና የስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ ስንታየሁ ቸኩል በግፍ ከቆዩበት የ2 ወራት እስር ወጥተው ቤተሰቦቻቸውን ተቀላቅለዋል።

=======≠=================

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በደብረብርሃን ከተማ ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቃሉ ተፈናቃዮችን ከመከላከያ በተፈፀመ ጥቃት የሁለት ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። ሌሎች ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል
(ደብረብርሃን ታይምስ)።
ምስል:- ከፋይል

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የኢትዮጵያ መንግስት የኢንተርኔት አገልግሎት ማቋረጡ ሰብአዊ መብት የሚጥስ ነው ሲል አምንስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት በተመረጡ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ የጣለዉን ማዕቀብ እንዲያነሳም ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት ጠይቋል።

አምንስቲ ኢንተርናሽናል እንደሚለዉ የኢትዮጵያ መንግስት እገዳዉን ከጣለ 3ኛ ወሩን ይዟል።

እገዳዉ ሰዎች መረጃ እንዳያገኙ መገደብን ጨምሮ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን የመጠቀምና ያለመጠቀም የሰብአዊ መብትን የሚጥስ ነዉ ብሏል።

የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዉሞን በሰላማዊ ሰልፍ የመግለፅ መብትን እንዲያከብርና የታሰሩ የመገናኛ ዘዴ ባለሙያዎችን እንዲፈታ አምንስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ።

ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት ትናንት ማምሻ ባወጣዉ መገለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ባለፈዉ ሳምንት አማራ ክልል በተፈጠረዉ ሁከት ምክንያት ያሰሯቸዉን 7 የመገናኛ ዘዴ ባልደረቦች ባስቸኳይ እንዲፈቱ፣ ከእስረኞቹ ባንዷ ላይ ተፈፀመ የተባለዉን አካላዊ ጥቃት እንዲያጣሩ ጠይቋል።

መግለጫዉ  እንዳለዉ  ባለስልጣናቱ «ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትንና ሁሉም ወገን በሰላማዊ መንገድ የመቃወም መብቱን ማስከበር አለባቸዉ።

»ባለፈዉ ሳምንት በአማራ ክልል የመብት ጥሰትና ሁከት መቀስቀሱ እንዳሳሰበዉ የመብት ተሟጋቹ ድርጅት አስታዉቋል።

በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተኩስ ልዉዉጥ መደረጉ፣ የሰብአዊ ርዳታ አቀባይ ድርጅት ሰራተኞችን ጨምሮ ሰዎች መገደላቸዉ፣ አዲስ አበባ ዉስጥ ሰዎች በጅምላ መታሰራቸዉንም ድርጅቱ «አሳሳቢ» ብሎታል።

የመንግስት ኃይላትም ሆኑ ሌሎች ታጣቂዎች «የሰብአዊ ርዳታ ሰራተኞችን ያለማጥቃት ኃላፊነት አለባቸዉ።» ይላል መግለጫዉ።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

#sudan_news
በሱዳን የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ተደበደበ‼️
በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ብረት ለበስ ተሽከርካሪው " ሆን ተብሎ " በጥይት መደብደቡን ኢምባሲው ያስታወቀ ሲሆን ድርጊቱን የፈፀመው ሄሜቲ የሚመሩት RSF ቡድን መሆኑን ኤምባሲው ለአል አረቢያ ገልጿል።

ኤምባሲው ተሽከርካሪው በ100 ጥይት መደብደቡን ገልጾ ድብደባው ያደረሰው ምንም ጉዳት የለም ብሏል።

በሌላ በኩል ፤ የአሜሪካ መንግሥት ጦርነት ውስጥ ካለችው ሱዳን ዜጎቹን የማስወጣት እቅድ እንደሌለው ዋይትሃውስ አሳውቋል።

በተያያዘ ዜና በሱዳን ካርቱም ሚገኙት የአውሮፓ ህብረት (EU) አምባሳደር በመኖሪያ ቤታቸው ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ተሰምቷል ።

አምባሳደሩ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ያሳወቁት የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ዲፕሎማት ጆሴፕ ቦሬል ናቸው (በትዊተር ገፃቸው)።

ቦሬል ስለ ጥቃቱ ምንም አይነት ዝርዝር ነገር ባይገልጹም አምባሳደሩ ግን " ደህና ናቸው " ብለዋል።

የዲፕሎማቲክ ቦታዎችን እና ሰራተኞችን ደህንነት ማስጠበቅ የሱዳን ባለስልጣናት ቀዳሚ ኃላፊነት ነውም ሲሉ ገልጸዋል።

ምንም እንኳን ቦሬል ፤ በሱዳን የአውሮፓ ህብረት አምባሳደርን ስም ባይፅፉም ስማቸው አይዳን ኦሃራ የሚባሉ ሲሆን የ #አየርላንድ ዲፕሎማት ናቸው።

ቦሬል ካርቱም ውስጥ የተፈፀመው ጥቃት ፤ በሌሎች ሀገራት የሚሰሩ ዲፕሎማቶች ጥበቃን የሚደነግገውን የተመድ ስምምነት የ " ቪይና ኮንቬንሽን " በእጅጉ የጣሰ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ የአውሮፓ ህብረት ቃል አቀባይ ናቢላ ማስራሊ ለAFP በሰጡት ቃል " የሰራተኞች ደህንነት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው " ብለዋል፤ የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት ልዑካን ቡድን ከካርቱም እንዲወጣ እንዳልተደረገ ተናግረዋል።
ቃል አቀባይዋ ፤ በሱዳን ያለው የፀጥታ እና ደህንነት ሁኔታ እየተገመገመ ነው ብለዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ማርከን የለቀቅናቸው የግብፅ ጀት አብራሪዎች እየደበደቡን ነው- አህሜቲ‼️


ማርከን የለቀቅናቸው የግብፅ አየር ሀይሎች አሁን እየደበደቡን ነው። 31 ጊዜም አየሮቹ የተነሱት ከግብፅ ነው። ሂሳብ እናወራርዳለን። ረመዳን ነው እያሉ እያለቀሱ ስንቸገር ነው የለቀቅናቸው። ነገ ግን ብንማርካቸው አንለቃቸውም። አሁን እየተደራጀን ነው። እየተከላከልን እንጅ የምንጠራበትን የጃንጃዊ ጥቃታችንን አልጀመርንም። ቡረሀን ደውሎ ውጊያ እናቁምና አብይ አህመድና መሀመድ ቢን ዛይድ ያደራድሩን ብሎ ለፀሀፊየ ነግሮታል። እጅህ ላይ የፍትህ ገመድ ሳላጠልቅ አልደራደርም ብየዋለሁ።
ግብፅ ግን እድሉን ተጠቅማ የሱዳንን ተቋሞች በአየር ጥቃት እያወደመች ነው። የሱዳን ህዝብ በሲሲ ለሚመራው ጦርነት እራሱን ያዘጋጅ ሁሉንም በድል እናጠናቅቀዋለን ብሎ ነው ደጋፊና ተዋጊዎቹን ያፅናናቸወወ። ሱዳን ውስጥ ባለው ጦርነት እስካሁን
5 ኢትዮዽያዊያን ተገድለዋል።
ሱሌማን አብደላ
ሚያዝያ 9/2015 ዓ.ም
=======≠========

Читать полностью…

Ethio 360 Media

Inbox‼️#ራያ‼️
አዲሱ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ራያን ሊረከብ አርሚ 44ኛ እሚባለውን ጦሩን አስጠግቷል፣ህወሀት ከኮረም እስከ ዋጃ ያለውን የራያ ከተሞች እሚያስተዳድሩለትን የዞን፣የወረዳ እና የቀበሌ አመራሮችን ከወዲሁ አዘጋጅቷል።
አማራ ክልል ያስቀመጣቸው የፀጥታ አካላት እና አለማጣን ጨምሮ በተለያዩ የራያ ቀበሌዎች የተመደቡ የሲቪል አመራሮች ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ መተላለፉ ተሰምቷል(Ayu zehabesha)።
ሚያዝያ 9/2015 ዓ.ም
=======≠========

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በሀገር ውስጥ እና በመላው ዓለም ለምትገኙ ውድ ኢትዮጵያውያን የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ።

በዓሉን የፍቅር ያድርግልን!

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የሱዳኑ አርኤስኤፍ ሁሉም ካምፖቹን መቆጣጠሩን አስታወቀ‼️
የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ሁሉንም ካምፖቹን መቆጣጠሩን እና በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

በሱዳን መንግስት ጦርና በጀነራል ሀምዳን ደጋሎ በሚመራው አርኤስኤፍ ጦር መካከል የነበረው የሁለት ቀናት ወታደራዊ ፍጥጫ ዛሬ ወደ ግጭት አምርቷል።

ጀነራል ሃምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) የሱዳን ጦር መሪውን ጀነራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ለፍትህ እስካላቀረብን ድረስ ትግሉ አይቆምም ማለታቸውንም ሬውተርስ ዘግቧል።

በግጭቱ እስካሁን ሶስት ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የሱዳን ዶክሮች ገልጸዋል (አልአይን።
ሚያዝያ 7/2015 ዓ.ም
=======≠========

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ምስራቅ ጠለምት ደገገብራይ በሚባል አካባቢ የትግራይ ታጣቂዎች መጠጋታቸውን ምንጮች ገልጸዋል። አርሚ 11 እና አርሚ 17 የሚባሉ ወይም ደግሞ በስያሜ ፅናት እና ቀይ ኮኮብ የሚባሉ የሰራዊት አደረጃጀት እንደሆኑ ምንጮቹ ገልጸዋል። በተለይ ላለፉት ሁለት ቀናት በተፈናቃይ ስም በርካታ ታጣቂዎችን ወደ አካባቢው አስርገው ለማስገባት እየሰሩ ነው ብለዋል። ለዚህ ደግሞ ልዩ ሀይሉ ከአካባቢው መውጣቱን ተከትሎ ይችን እንደ ክፍተት በመጠቀም ነው እየተጠጉ ያሉት ብለዋል።
ይሄንን የሚያስፈፅሙት በትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የተዋቀሩ እና መቀመጫቸውን እንደአባጉና  በሚል አካባቢ ያሉ አመራሮች ናቸው ሲሉ ምንጮች አክለው ገልጸዋል። እነዚህ አመራሮች ሰሞኑን ወደ መቀሌ ሄደው አቅጣጫ ተቀብለው እንደመጡ ታውቋል።
የአካባቢው ነዋሪዎችም የልዩ ሀይሉን መውጣት ተከትሎ መከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢ እንዲገባ ጠይቀዋል።
ሚያዝያ 6/2015 ዓ.ም
=======≠========

Читать полностью…

Ethio 360 Media

መንግስት የጋዜጠኞችን “እስር እና እንግልት” እንዲያቆም የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበር ጠየቀ

መንግስት “ያለምንም የህግ አግባብ” ያሰራቸውን የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችን “በአስቸኳይ እንዲፈታ” የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበር ጠየቀ። ማህበሩ ዛሬ አርብ ሚያዝያ 6፤ 2015 ባወጣው መግለጫ፤ መንግስት በመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ላይ የሚያደርሰውን ማሸማቀቅም እንዲያቆም ተመሳሳይ ጥያቄ አቅርቧል።

ማህበሩ በዛሬው መግለጫው፤ በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች የሚሰሩበት “አውድ እየጠበበ” መምጣቱን ገልጿል። ጋዜጠኞች ስራቸውን በነጻነት እንዳይሰሩ፤ “በመንግስት የጸጥታ አካላት እየተሸማቀቁ እንግልት እየደረሰባቸው” መሆኑን መታዘቡንም አመልክቷል።

ለዚህም በማሳያነት የማህበሩ መስራችና የስራ አስፈጻሚ አባል የሆነውን ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻውን ጨምሮ ስድስት ጋዜጠኞች በአሁኑ ወቅት በመንግስት ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቅሷል። የማህበሩ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ እና የ“አራት ኪሎ ሚዲያ” መስራች ከሆነው ዳዊት በተጨማሪ መግለጫው በስም የዘረዘራቸው ጋዜጠኞች፤ አራጋው ሲሳይ፣ ገነት አስማማው፣ ጌትነት አሻግሬ፣ በየነ ወልዴ እና ቴዎድሮስ አስፋውን ነው(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)።
ሚያዝያ 6/2015 ዓ.ም
=======≠========

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አዲሱ የትግራይ ክልል አስተዳደር ለኮረምና አላማጣ አመራር በመመደብ ላይ ነው ተባለ‼️
በኮረም የነበሩ የአማራ ልዩ ኃይሎች ጠቅለው መውጣታቸውን እንዲሁም የፋኖን መበተን ተከትሎ ህወሓት ለኮረምና አላማጣ አመራር በመመደብ ላይ ነው ሲሉ በሥፍራው ያሉ ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገለጹ፡፡

በዚህም ህብረተሰቡ ተረብሿል ያሉት ነዋሪዎቹ፤ “የመከላከያ ሠራዊት እኛ አለን ተረጋጉ እያለ ቢሆንም፣ መንግሥት እያደረገ ያለው እና በህወሓት በኩል እየተወራ ያለው የተናበበ ስለሆነ ህዝቡ ማመን አልቻለም።” ብለዋል፡፡

ህወሓት “የአማራ ልዩ ኃይል ከኮረምና አላማጣ ከወጣ እና ፋኖ ከተበተነ መከላከያ ቦታውን ተረክቦ ቆይቶ ለትግራይ ክልል ይመልሳል” ሲል ነው የከረመው ያሉት ነዋሪዎች፤ “የፌደራል መንግሥቱም ይህን እያስፈጸመ እንዳለ ነው የምናምነው።” በማለት ያላቸውን ከፍተኛ ስጋት ገልጸዋል፡፡

መንግሥት ኮረምና አላማጣን ለህወሓት አሳልፎ ለመስጠት በእርግጠኝነት እኛ የማናውቀው ሴራ እየሰራ እንደሆነ ነው የምናምነውም ብለዋል፡፡

ነዋሪዎቹ ለገበያ ከሚመጡ የማይጨው ነዋሪዎች እንዲሁም እየደወሉ አመራርና ፖሊስ ተመድቦልናል በቅርቡ ወደ ቦታችሁ ትሄዳላችሁ ተብለናል ከሚሉ ሰዎች አረጋግጠናል ባሉት መሰረት፤ ህወሓት በአማጣና ኮረም ለሚገኙ ወረዳዎች በሙሉ ካቢኔ አዋቅሮና ፖሊስ መድቦ ጨርሷል ብለዋል፡፡

ኮረም የነበሩ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት ትናንት ጠቅልለው መውጣታቸውን ጠቁመው፤ አላማጣ ውስጥ ያሉት የአማራ ልዩ ኃይልም በጥቂት ቀናት ውስጥ ይወጣል ነው ያሉት፡፡

ወልድያ ከተማ የሚገኙ የአማራ ልዩ ኃይል አባላትም ወደ መከላከያ ሠራዊት አልያም ወደ ፌደራል ፖሊስ ወይም ደግሞ ወደ ክልል ፖሊስ ለመግባት ፎርም እንዲሞሉ እየተደረገ ይገኛል፡፡
አዲስ ማለዳ

Читать полностью…

Ethio 360 Media

መከላከያው ሲመታ…!

"…የሰላምና እርቅ ወሬ ከች ብለዋል። እርቅን የመሰለ ነገር እኮ የለም። እርቅ ከማን ጋር የሚለው ነው እንጂ ጥያቄው እርቅማ ጽድቅ እኮ ነው። ብቻ ነገ ተሸወድኩ፣ ሽማግሌ አምነን ብሎ እየዬ፣ ድረሱልኝ፣ ወየው ወየው የሚል ጫጫታ እንዳይሰማ እንጂ እርቅማ መልካም ነው።

"…ለምናልባቱ ነገ ወያኔ አላማጣ ስትገባ፣ ራያን ስትወር፣ ሰሜን ወሎን ጠብጥባ ስትገርፍ እሪሪ፣ ቋቀምበጭ አትበል እንጂ ሰላምማ ማን ይጠላል? ደግሞም ማልቀስ ከፈለግክም በር ዘግተህ ማልቀስ ነው እንጂ በየዩቲዩቡ፣ በየፌስቡኩ እየዞሩ ማልቀስ፣ ደረት መድቃት ጎረቤት መበጥበጡ ነውር ነው።

"…ሽማግሌዎችም ነገ ምነው ምነው ቃል ታጠፈብን ብትሉ የሚሰማችሁ የለም። ሕዝቡም ቢሆን ፋኖን ሳትረዳ፣ ሳትደግፍ፣ ፋኖ አልተዋደቀልኝም ብለህ ማለቃቀሱን ተወው። የአንተን ልጅ ከተማ ቤት ተከራይተህ አስቀምጠህ ፋኖን የስኳር መግዣ፣ ዩኒፎርሙን ሁላ ሳትቀይርለት ነፃ እንዲያወጣህ አትጠብቅ። ነፃነት በነፃ በብላሽ አይገኝም።

"…ሥርዓቱ እንደሁ በስብሷል። ማስተዳደር አይችልም። ተወደደም ተጠላም በቅርቡ ይወድቃል። ኦነግ ሸኔም ትግሉን ቀጥሏል። ከትናንት ወዲያ መተሃራ ላይ ከ50 በላይ የፌደራል ፖሊስ ረፍርፎ እንደ ቅጠል አርግፎ መሣሪያቸውን ተረክቦ እዚያው ጫካ ተቀምጧል። የተረሸኑት የፌደራል ፖሊሶች አብዛኛዎቹ የዐማራና የደቡብ ልጆች መሆናቸውም ተነግሯል።

"…የዐማራ ልዩ ኃይል መሣሪያውን ለመከላከያ ያስረክብና መከላከያን አልያም ፌደራል ፖሊስን ይቀላቀላል። ከዚያ ዘመናዊ መሣሪያ ይሰጠውና ኦሮሚያ ኦነግ ሸኔን እንዲዋጋ ይላካል። ከዚያ እዚያው ከጀርባው ተመትቶ ይጸዳል። ያለ ኪሳራ ሪፎርም ማለት ይሄም አይደል?

• ወሬው እውነት ከሆነ ወንድሜ ምሬ እንኳን ወደ ሰላማዊ ኑሮ ተመለስክ። ትግሉን ግን ጠኔ፣ ችጋርና ፍትህ ማጣት ያስቀጥሉታል።

(ዘመድኩን በቀለ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

"…ይሄ በኦሮሚያ ክልል በወለጋ እንደ ቆሻሻ፣ እንደ ጥራጊ የሚጸዳው፣ የሚጨፈጨፈው የዐማራ እስላሞች የሬሳ ክምር ነው። ዐማራ ከሆንክ እስላም ሁን ክርስቲያን፣ ሼክ ሁን ቄስ ትገደላለህ፣ ትጸዳለህ፣ ትረሸናለህ።

"…የኦሮሞና የስልጤ እስላም የዐማራ እስላም በመጨፍጨፉ ጮቤ ረገጣ ላይ ናቸው። በአዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሞው ኦነግብልፅግና የእስላም መስጊድ አፍርሷል። በረመዳን ፆም የእስላሞችን ቤት በግሬደር አፍርሷል። የኦሮሞ እስላም አክቲቪስቶች ግን ትንፍሽ አላሉም። አህመዲን ጀበል አፍራሾቹ የኦሮሞ እስላሞች ስለሆኑ ትንፍሽ አላለም። በወለጋ እስላም ወሃቢያው ከአሩሲ ሄዶ ኦነግ ነኝ፣ ኦሮሞን ነፃ ላወጣነው ብሎ እስላም ዐማራውን አላህ ወደአክበር እያለ ጨፍጭፏል። የጅማው የወሎ እስላም አብይ አህመድም በወለጋ ለታረዱት የዐማራ እስላሞች ለሬሳቸው ጥላ እንዲሆናቸው ችግኝ እንተክላለን ብሎ ያሾፈው ትናንት ነው።

"…እናም ዐማራ የሚታገለው ለላንቲካ አይደለም። እንግዲህ ዐማራ የሚታገለው በፅንፈኛ ኦሮሞ ነኝ ባይ አረመኔዎች እንዲህ ከመጨፍጨፍ ራሱን ለመዳን ነው። የዐማራ ትግል በአንዴ ላይሳካ ይችላል። አለቃም፣ የትግሉንም መሪ ላያገኝ ይችላል። ነገር ግን የአንበሳውን ጥርስ ነቅንቆታል። የተነቀነቀ ጥርስ ደግሞ የጊዜ ጉዳይ እንጂ መውለቁ አይቀርም።

"…በወለጋ ዐማሮችን እንዲህ ከመጨፍጨፋቸው በፊት በቅድሚያ ያደረጓቸው ሃብታቸውን ነበር የዘረፉት፣ ከብቶቻቸውን፣ እህላቸውን ነበር። ጎጆ ቤቶቻቸውን በእሳት አቃጠሉት፣ ለበለቡት፣ አወደሙት። ከዚያ ነው በመጨረሻ እንዲህ የረሸኗቸው። እስላም ዐማሮችን የጨፈጨፏቸው። የእነዚህ ሟች ልጆች ደብረ ብርሃን ያለ ወላጅ ቀርተዋል። ያለአሳዳጊም ቀርተዋል። እነዚህን ህጻናት ሳይቀር ማን እንዲህ እንዳደረጋቸው በቀል እያስተማሩ ማሳደግ የዐማራው ፈንታ ነው።

• ድል ለዐማራው…! 💪🏿💪

(ዘመድኩን በቀለ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ሱዳን ያለው የወያነ ኃይል ለወረራ እየተዘጋጀ ነው!

ከዳያስፖራ የሄዱ ሁለት የትህነግ ወኪሎችና ሶስት ከደቡብ ሱዳን ወደ ሱዳን የሄዱ የድሮ የሰላም አስከባሪ ወታደራዊ አመራሮች ከሱዳን የትህነግ ካምፕ ወደ ግብፅ ከሄዱ አራተኛ ቀናቸው ነው።

ሌሎች ሱዳን ውስጥ የነበሩ የኢትዮጵያ ታጣቂ ቡድኖች ከሱዳን መንግስት ጋር በተደረገ ስምምነት ከሱዳን እንዲወጡ ሲደረግ ትህነግ ብቻ ነው ከእነ ትጥቁ ያለው። ይህ የትህነግ ኃይል ትጥቅ እንዳይፈታ የተደረገው በኢትዮጵያ መንግስት ነው። ይህ ታጣቂ ከየካቲት 11 ጀምሮ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ተደርጎለት፣ ከስደተኛ እየመለመለ እየተዘጋጀ ነው። በዚህ ሁኔታ ነው የአማራ ልዩ ኃይል ላይ ውሳኔ የተላለፈው። አማራውን ለማስጠቃት የተሸረበ ሴራ ነው የምንለው በመረጃ ነው። የፈለገ ቢሆን ግን ባለፈው እንዳደረግነው እንደ ህዝብ ቅስሙን ሰብረን እንመልሰዋለን። ብልፅግና በዚህ አካሄዱ አገር ካላፈረሰ በስተቀር ለሌላ ዙር ባርነት የተዘጋጀ ህዝብ የለም። አገር ሲፈርስ ተለይቶ የሚጎዳ ያለ ከመሰለውም ተሳስቷል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አውሮፓ ከአሜሪካ ተጽዕኖ ልትላቀቅ ይገባል- የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት‼️


የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ኡርሱላ ቮንደረሊን ወደ ቻይና አቅንተው ከፕሬዝዳንት ሺ ጅምፒንግ ጋር መምከራቸው ይታወሳል፡፡

ፐሬዝዳንት ማክሮን የቤጂንግ ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ባሉበት አውሮፕላን ውስጥ የነበረው የፖለቲኮ ጋዜጠኛ ቃለመጠይቅ አድርጎላቸው እንደነበር ተገልጿል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በዚህ ጊዜ እንዳሉት አውሮፓ በአሜሪካ ላይ ጥገኛ መሆኗን ያመኑ ሲሆን ይህ ግን ትክክል አለመሆኑን እና ሊስተካከል ይገባል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡
ሚያዝያ 4/2015 ዓ.ም
=======≠=================

Читать полностью…

Ethio 360 Media

"ከአዲስ አበባ ዙሪያና ከኦሮሚያ ክልል ቤት የፈረሰባቸው ተፈናቃዮች በመበራከታቸው ለማስተናገድ ተቸግረናል"
👉 የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር
**
ከ28 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች በችግር ውስጥ የሚገኙበት ደብረብርሃን ከተማ ከአዲስ አበባ ዙሪያና ከኦሮሚያ ክልል ተጨማሪ ተፈናቃዮችን በመቀበሉ ለማስተናገድ መቸገሩን እና  ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት የከተማዋ አስተዳደር ማሳወቁን አዲስ ዘይቤ አስነብባለች።

በደብረብርሃን ከተማ ከ1 ዓመት በላይ በመጠለያ ጣብያ የቆዩ ተፈናቃዮች የሚገኙ ሲሆን እስከአሁን ድረስ የደብረብርሃን ከተማ ህዝብና ከአንዳንድ ድርጅቶች ውጭ መንግስት ተገቢውን ድጋፍ እያደረገላቸው ባለመሆኑ ለችግር በመጋለጣቸውን ተፈናቅዮች ቅሬታቸውን ማቅረባቸውንም ነው አዲስ ዘይቤ የገለፀችው።

በደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት የተፈናቃዮች አስተባባሪ አቶ አንተነህ ገብረእግዚአብሄር በተለይ ለአዲስ ዘይቤ እንደገለፁት በከተማዋ ከሰዎች ተጠግተውና ቤት ተከራይተው የሚኖሩትን ሳይጨምር ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ በ6 መጠለያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ከ28 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ይገኛሉ።

አብዛኛዎቹ ተፈናቃዮች 1 ዓመት ከ6 ወር በላይ በመጠለያ ጣቢያ መቆየታቸውንና ቀደም ሲል በከተማው ነዋሪና በጎ ፈቃደኞች ድጋፍ ይደረግላቸው እንደነበረ የሚገልፁት አስተባባሪው በጊዜ ርዝመት “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ከበጎ ፍቃደኞች፣ የሀይማኖት ተቋማትና ሌሎች መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ውጭ ዘንድሮ በፌደራሉም ሆነ በክልል መንግስት የተደረገ ድጋፍ አለመኖሩንና የክልሉ መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግ በተደጋጋሚ ቢጠየቅም ምላሽ አለመስጠቱን ማወቅ ተችሏል።

በተጨማሪ በአዲስ አበባ ዙሪያ ቤታቸው የፈረሰባቸው አዳዲስ ተፈናቃዮች እየመጡ ነው ያሉት የተፈናቃዮች አስተባባሪው፣ እነዚህን ተፈናቃዮች የከተማ አስተዳዳሩ ማስተናገድ ባለመቻሉ ለከፋ ችግር መዳረጋቸውን ገልፀዋል።

የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ለዓለም የምግብ ድርጅት የድጋፍ ጥያቄ ቢያቀርብም የክልሉ መንግስት ከአቅሜ በላይ ነው ባለማለቱ ድጋፍ ማድረግ እንደማይችል ተገልፆላቸዋል።

“ከአዲስ አበባ ዙሪያ እና ከኦሮሚያ ክልል የሚመጡ ተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ የክልሉ መንግስት ከፌዴራል መንግስት ጋር ተነጋግሮ ከአቅሙ በላይ መሆኑን ለዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቆ እገዛ እንዲደረግ” አስተባባሪው ጥሪ አቅርበዋል።
አዲስ ዘይቤ

Читать полностью…

Ethio 360 Media

እኛም ያልነው ይህኑ ነው ፤ ደጀን ከሆንነውና አብረነው ከተሰለፍነው የመከላከያ ሰራዊትም የምንጠብቀውም ይህንን እንዲል ነው!

የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ #ሌተናል_ጀኔራል_መሰለ_መሰረት (ሲዳማ) እና የ6ኛ ዕዝ ዋና አዛዥ #ሜጀር_ጀኔራል_ተስፋየ_ወልደማርያምን (ሃድያ) መጋቢት 29, 2015 ዓ.ም የሰጡት አስተያየት ፦👇👇👇

<< ‘የአማራ ልዩ ኃይል እንዴት ትጥቁን እንቀማው!’ በሚል የአብይ አህመድ ቡድን ባዘጋጀው ውይይት ላይ ይህ ልዩ ኃይል የሰራዊታችን ክንድ ሆኖ ታሪክ የሰራ ኃይልን በዚህ መልኩ ክብሩን በሚነካ መንገድ ትጥቅህን ፍታ ማለት ለእኔ እጅግ ይከብደኛል:: መንግስት የሰጠኝን ግዳጅ ተቀብየ በጎንደር በኩል ሰራዊት ይዥ ስዘምት ይህ ኃይል ባይኖር ኖሩ አሁን ላይ የምናየው ነገር በፍፁም አይኖርም ነበር:: ይህንን ኃይል ትጥቅ መፍታት ወይም መልሶ መደራጀት ካስፈለገ ጊዜ ወስድን ከህዝቡና ከሰራዊቱ ጋር ተመካክሮ መሆን አለበት:: ትልቅ ስህተን እንዳንሰራ ስጋት አለኝ፡፡ >> // የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል_ጀኔራል_መሰለ_መሰረት//

<< መንግስት የጦር ሜዳ ጀብዱ የሽለመኝ የአማራ ፋኖና ልዩ ኃይል በጋራ በሰራነው ስራ ነው:: ይህንን ልዩ ኃይል በዚህ መንገድ ትጥቅህን ፍታ ማለት ለወደፊቱ ጀግናን ማምከን ነው የሚሆነው:: እኔ ዕዜን #በድሬ_ሮቃ ግንባር ይዠ ስዋጋ የአማራ ፋኖና ልዩ ኃይል የሰራውን የውጊያ ታሪክ እኔም: ሰራዊቱም ያውቃል:: መንግስት እኛንም ባያደክመን: አሁን ላይ እየትሄደበት ያለው ትጥቅ የማስፈታት መንግድ እጅግ አደገኛ ነው: መንግስት ይህንን ጉዳይ ቢያጤንበት መልካም ነው! >>// ሜጀር ጀኔራል ተሰፋየ ወልደማርያም//

እናመሠግናለን!🙏

@ዘሪሁን ገሰሰ

Читать полностью…
Subscribe to a channel