ethio360media | Unsorted

Telegram-канал ethio360media - Ethio 360 Media

37564

ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር !!!

Subscribe to a channel

Ethio 360 Media

አዲስ አበባ‼️‼️


በአዲስ አበባ የሚገኙ መምህራን በሙሉ አርብ እና ቅዳሜ ስብሰባ ተጠርቷል በስብሰባው ላይ ምንም አይነት ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ይዞ መግባት ተከልክሏል ዛሬ የት/ቤት ር/መምህራን ተሰብስበው ገለፃ ተደርጎላቸዋል። መቅረት በጥብቅ የተከለከለ ነው ተብሏል።
ሚያዝያ 19/2015 ዓ.ም
=======≠========

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ይፋት‼️


በአጣዬ ዙሪያ አርሶአምባ እና አላላ በሚባሉ አካባቢዎች ታጣቂዎች ሰሞኑን እርሻ ላይ በነበሩ አርሶአደሮች ላይ በከፈቱት ተኩስ ሰባት ሰዎች ቆስለዋል። ከብቶችንም ነድተው ወስደዋል። ይህ የሆነው ልዩ ሀይሉ ከአካባቢው ከወጣ በኋላ ነው ይላሉ። አካባቢው አሁን ላይ በኮማንድ ፖስት ስር እንደሆነ ይታወቃል።
ሚያዝያ 18/2015 ዓ.ም
=======≠========

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ከ120 በላይ የገጠር ወረዳዎችና 200 የሚደርሱ ከተሞች አሉን።

ከተሞችን ለሰላማዊ፤ ሰፊውን ገጠር ደግሞ ለትጥቅ ትግል መድቦ የተናበበ ተጋድሎ ማድረግ ይበጃል። ለምሳሌ በ200 ከተሞች በተመሳሳይ ቀን አድማዎችን እና ሰላማዊ ሰልፎችን በየጊዜው ብናደርግ በስርዓቱ ፖለቲካል-ኢኮኖሚና የፀጥታ መዋቅር ውስጥ የሚፈጥረው ጫና በጣም ከባድ ነው።

ይህ ሁኔታ በሚካሄድበት ሰዓት ደግሞ 120 የገጠር ወረዳ ቀበሌዎች ውስጥ የትጥቅ ትግል አራማጅ አርበኞች የሽምቅ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ስርዓቱ ሊቋቋመው ወደማይችለው ውጥረት ውስጥ ይገባል። ይህ ውጥረት ደግሞ ከውስጥ የመፈረካከስ አደጋ እንዲያጋጥመው ያደርጋል። ወጥ የእዝ ሰንሰለትና ፖለቲካዊ ክንፍ ያለው የትጥቅ ትግል አራማጅ ድርጅት ተፈጥሮ ሁሉንም ፋኖዎች፣ የቀድሞ የልዩ ኃይልና የፌደራል የፀጥታ አባል የነበሩ አማሮችን በውስጡ ማቀፍ ይኖርበታል።
ድርጅቱ ዋና ቤዙን ምዕራብ አማራ ላይ በማድረግ ከወልቃይት እስከ መተከል ነፃ ቀጠናዎችን በቀላሉ መፍጠር ይችላል። ከምዕራብ አማራ ስምሪት የሚወስዱ የዚሁ ድርጅት ክፍሎች በሁሉም የአማራ ገጠሮች ላይ በትናንሽና ፈጣን አሀዱዎች ተልዕኮ መፈፀም ይችላሉ። ቀዳሚ ስራቸውም የገጠሩን ህዝብ ማንቃት፣ ማደራጀትና መመልመል ይሆናል። ይህን ለመርዳት ዳያስፖራው ወደ ገጠሪቱ አማራ ስርጭቱ የሚደርስ የራድዮ ጣብያ ማቋቋም ይችላል።

የትጥቅ ትግል አራማጅ አርበኞች (ፋኖዎች) እንደማንኛውም ሸማቂ ድርጅት የከተማ የስለላና የፈዳይን ኦፐሬሽን ማካሄድ ከፈለጉም የህዝቡን ደህንነት በሚጠብቁ ህቡዕ እንቅስቃሴዎች ሊከውኑት ይገባል።
ከዚህ ውጭ ክላሽ አንግቦ በከተማ መንጎማለል፤ ሰላማዊ ሰልፍን በክላሽ ማጀብ is just a joke! You are making us laughing stock. ሊቆም ይገባል። ትግል ከሆነ የምር ይሁን። የአማራ ህዝብ የመደራደር አቅም ከፍ የሚያደርግ... ዓለም አቀፍ የትግል ስታንዳርዶችን የጠበቀ ቅርፅ ያለው አብዮት ሊሆን ይገባል።


(አማን ገሰሰ ያሲን)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የሁለት ቅጥረኛ ፖሊሶች ህይወት አለፈ‼️

ከትናንት በስተያ ከምሽቱ 2:00 አካባቢ ከእነ ትጥቁ የነበረ አንድን የአማራ ልዩ ሃይል አባልን ትጥቅ እንዲፈታ ለማሸማገል የተንቀሳቀሱ ሁለት የቆላድባ ከተማ አስተዳደር የፖሊስ አባላት ተገደሉ።የአማራ ልዩ ሀይሉ ትጥቄን አልሰጥም በማለቱ በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ የሁለቱም የፖሊስ አባላት ህይወታቸው አልፏል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አልበሽር ከእስር ቤት አመለጡ‼️


የቀድሞው የሱዳን መሪን ዑመር ሀሰን አልበሽርን ጨምሮ የቀድሞ የሱዳን ባለስልጣት ከኩፐር እስር ቤት ሆነ ብሎ እንዲያመልጡ ያደረገው የቡርሃን አስተዳደር ነው ሲል የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር (RSF) ዛሬ ባወጣው መግለጫ አውግዟል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚገኙበት የሱዳን አል-ሁዳ ወህኒ ቤት ተሰበረ‼️


ከካርቱም በስተምስራቅ የሚገኙ አካባቢዎች በጀነራል አህመድ ሃምዳን ዳጋሎ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ትልቁ የአል-ሁዳ ወህኒ ቤት መሰበሩ ተሰምቷል።

እስር ቤቱ ብዙ ኢትየጵየዊያን በሱዳን የፀጥታ ኃይሎች የሚታሰሩበት ሲሆን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ እስረኞቹ እንዲለቀቁ ማድረጉን ተሰምቷል።

ከካርቱም 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በኦምዱሩማን መንገድ የሚገኝና የወንጀለኛ ቡድን መሪዎች፣ አደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪዎች እና ከመኖሪያ ፈቃድ ጋር በተገናኘ ብዙ ኢትዮጵያውያን የሚታሰሩበት እንደነበረ ምንጮቻችን ተናግረዋል።

የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ እስረኞቹን ማስለቀቁን ተከትሎ ሃሳባቸውን የሰጡ ምንጮች ታስረው ለነበሩት ኢትዮጵያውያን መፈታት በጎ ቢሆንም በከባድ ወንጀል የታሰሩ ሰዎችም መፈታታቸው ስጋት ፈጥሯል።

ግጭቱ ከተጀመረ ጀምሮ 15 የሚደርሱ ኢትዮጵያዊያን በጦርነቱ መገደላቸው የተገለፀ ሲሆን በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ በቂ መረጃ እየሰጠ ባለመሆኑና ስለተገደሉት ዜጎች ጉዳይ መንግስት ያለው ነገር አለመኖሩ በኢትዮጵያውያኑ ዘንድ ትችቶች እንዲሰነዘሩ አድርጓል።በግጭቱ መባባስ ምክንያት ሀገራት ዜጎቻቸውን ከሀገሪቱ እያስወጡ ሲሆን አሁን የኢትዮጵያ መንግስትም ዜጎቹን ለመታደግ ሀገራዊ ግብረ ሀይል ማቋቋሙን ይፋ አድርጓል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ኤርትራ ጦሯን ወደ ሱዳን ድንበር አስጠግታለች‼️


ኤርትራ በሱዳን የተከሰተውን ጦርነት ምክንያት በማድረግ ካሳላ ወደ ሚባል የሱዳን አዋሳኝ ድንበር በርካታ ሰራዊት ሰሞኑን አስጠግታለች። ካሳላ የሚባለው ቦታ አሁን ላይ በሱዳን የሚተዳደር ቢሆንም ካሳላ በታሪክ የኤርትራ ነው ብለው የሚያምኑም አሉ። ሱዳናዊያን ደግሞ ኤርትራ ጦሯን ያስጠጋችው ካሳላን በሀይል ለመውረር ነው እያሉ ይገኛሉ። ኤርትራ ግን ጦሯ ዳር ድንበሯን ለማስከበር እንዳስጠጋች ምንጮች ገልጸዋል።
ሚያዝያ 14/2015 ዓ.ም
=======≠========

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በሱዳን ያሉ የውጭ ዜጎችን በኢትዮጵያ ድንበር በኩል ማስወጣት ተጀመረ‼️
ከካርቱም ዜጎቻቸውን በአየር ትራንስፖርት ለማውጣት ያልተሳካላቸው ሀገራት በየብስ ትራንስፖርት በኢትዮጵያ ድንበር በኩል እያስወጡ መሆኑን አል ዐይን ከምንጮቹ ያገኘው መረጃ ያመላክታል። ሀገራት ዜጎቻቸውን እያስወጡ ያሉት በጋላባት-መተማ በኩል ነው ተብሏል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ስምንተኛ ቀኑን በያዘው በዛሬው ቀን የRSF ወታደሮች በአልሁዳን እስርቤት ላይ ጥቃት በማድረስ እስረኞችን አስፈትተዋል ሲሉ የSAF ( Sudanese Armed Forces) ቃል አቀባይ ተናግረዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አሜሪካ ከሱዳን ጦርነት ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ጦር ወደ ጂቡቲ ልትልክ ነው ተባለ‼️

አሜሪካ ከሱዳን ቀውስ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ጦር ወደ ጂቡቲ ልትልክ እንደሆነ ተነግሯል።

ወደ ጂቡቲ የሚላከው ጦር በሱዳን ያለውን ሁኔታ በቅርበት የሚከታተል እና አሜሪካ ዜጎቿን ከሱዳን ማውጣንተ በሚያስፈልግበት ወቅት ድጋፍ የሚሰጥ ነው ተብሏል።

ቅዳሜ እለት በሱዳን ጦር ኃይሎችእና በፈጥኖ ደራሽ ሰራዊቱ (አርኤስኤፍ) መካከል ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ በሀገሪቱ ዋና ከተማ ካርቱም፣ አጎራባች በሆነችው ኦምዱርማን እና በሌሎችም አካባቢዎች ከባድ ውጊያ አለ።

የዓለም ጤና ድርጅት የሱዳን ጤና ጥበቃ ሚንስቴርን ጠቅሶ እንዳለው በግጭቱ 300 ገደማ ሰዎች ሲገደሉ፤ ከ2 ሽህ 600 በላይ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።AlAin

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ለመላዉ ሙስሊም ማህበረሰብ እንኳን ለዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ያኔ ለትህነግ ሲሆን "አዲስ አበባን ሊይዝ ነው።" ብለው ዲፕሎማቶቻቸውን ያስወጡ የምዕራባውያን አገራት ከሱዳን ዲፕሎማቶችን የማስወጣት ነገር ብዙም እያሳሰባቸው አይደለም። ይልቁን መኪና እና የኤምባሲ አጥር ተመታብን ነው ቅሬታቸው።

ለትህነግ ፕሮፖጋንዳ ተብሎ የተመድ ሰራተኞች ሳይቀር በየግቢዎቻቸው ስፖርት እየሰሩ ( ከግጭት ለማምለጥ) ያሳዩ ነበር። ካርቱም በጀት ስትነድ የግጭቱን ያህል ጫጫታ አላሰሙም።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ማስታወቂያ
==========

ባለደረባችን የነበረዉን እና አሁን በግሉ አዲስ ኮምፓስ ሚዲያ በሚል መንቀሳቀስ የጀመረዉን የኤርሚያስ ለገሰን የመረጃ ቻናል ጆይን በማድረግ እንድናበረታታዉ እንጠይቃለን:: ሊንኩን ከታች አያይዘነዋል::

/channel/addiscompas

Читать полностью…

Ethio 360 Media

Ayidde cambalaalla!

እንኳን ለሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ በዓል ለሆነው ፊቼ ጫምባላላ በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን። መልካም በዓል!
Hawalle Fichee-Cambaalaallate Ayaanira keerunni iillishinonke.

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የተመድ ዋና ጸሀፊ ወደ ትግራይ ለመጓዝ ይዘውት የነበረው እቅድ፤ በኢትዮጵያ መንግስት “ውድቅ መደረጉን” አንድ ምስጢራዊ ሰነድ አጋለጠ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ፤ ወደ ትግራይ ለመጓዝ የያዙት እቅድ በኢትዮጵያ መንግስት ውድቅ በመደረጉ “ክፉኛ ተበሳጭተው” እንደነበር “ዋሽንግተን ፖስት” ጋዜጣ የተመለከተው አንድ ምስጢራዊ ሰነድ አጋለጠ። የዋና ጸሀፊው ጥያቄ በኢትዮጵያ መንግስት ተቀባይነት አለማግኘቱን በመግለጽ ለጉተሬዝ ደብዳቤ የጻፉላቸው፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን መሆናቸው በዚሁ ምስጢራዊ ሰነድ ይፋ ተደርጓል።

ጉተሬዝ የትግራይ ጉብኝታቸው መሰረዙን ጨምሮ በሌሎች ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የነበሯቸውን መስተጋብሮች የያዙት ምስጢራዊ ሰነዶች አፈትልከው የወጡት ከአሜሪካ መንግስት እጅ ነው። “ዲስኮርድ” በተሰኘው የመልዕክት መለዋወጫ “ሰርቨር” የተለቀቁትን እነዚህን ሰነዶች ያወጣው፤ የማሳቹሴትስ የአየር ኃይል ብሔራዊ ዘብ ባልደረባ የነበረ የ21 ዓመት ወጣት ነው።

አሜሪካ “በወዳጆቿ እና አጋሮቿ ላይ ስታካሄድ የቆየችውን ስለላ ያጋለጡ ናቸው” ከተባለላቸው ሰነዶች መካከል አራቱ፤ ከጉተሬዝ ጋር የተያያዙ መሆናቸውን “ዋሽንግተን ፖስት” ትላንት ሰኞ ባወጣው ዘገባ አስታውቋል። የካቲት 10፤ 2015 የተጠናቀረ አንድ ሪፖርትን በማሳያነት የጠቀሰው ዘገባው፤ ጉተሬዝ ወደ ትግራይ ሊያደርጉት ያቀዱት ጉዞ መሰረዙን በተመለከተ፤ በወቅቱ በተመድ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩትን ታዬ ታዬ አጽቀስላሴን ለመጋፈጥ ፈልገው እንደነበር አትቷል።

ጉተሬዝ ወደ ትግራይ ሊያቀኑ አቅደው የነበረው፤ በክልሉ የነበረውን ጦርነት ላስቆመው የሰላም ስምምነት ያላቸውን ድጋፍ ለመግለጽ ነበር ተብሏል። ንደ “ዋሽንግተን ፖስት” ዘገባ ከሆነ የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ እቅድ የተጨናገፈው፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጉብኝቱን ውድቅ የሚያደርግ ደብዳቤ ከላኩላቸው በኋላ ነው(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)።
ሚያዝያ 11/2015 ዓ.ም
=======≠========

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የ35 የአማራ፣ 2 የአፋር ባለሃብቶችና ድርጅቶች የባንክ አካውንት ታገደ‼️


የአማራ ሕዝብ ትግልን ሊደግፉ ይችላሉ በሚል አካውታቸው ታግዷል። የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዛሬ ለሁሉም ባንኮች በጻፈው ደብዳቤ የ35 የአማራ ባለሃብቶች እንዲሁም 2 የአፋር ባለሃብቶች በባንክ ያላቸው ገንዘብ እንዲታገድ ለሁሉም ባንኮች ተፅፏል። ደብዳቤውን ተመልከቱት።
የሞቱ ሰዎችም ጭምር በእገዳው ስማቸው ተጠቅሷል።

ሚያዝያ 18/2015 ዓ.ም
=======≠========

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በ ሰሜን ጎንደር ዳባት ከተማ አንድ የመከላከያ ወታደር ሜጀር ጀነራሉን ገድሎ ከአካባቢዉ እንደተሰወረ ተሰምቷል::

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች የ72 ሰዓት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደረሱ‼️


የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ለ72 ሰዓት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን አስታወቁ።

በተቀናቃኝ ጎራ ተሰልፈው እየተፋለሙ ያሉት የሱዳን ጦርና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የተኩስ አቁም ስምምነት ሰኞ እኩለ ሌሊት እንደተጀመረ ተገልጿል።

በሱዳን ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ የአሁኑን ጨምሮ ቢያንስ ለሦስት ጊዜ ያህል የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር ፤ እስካሁን የነበሩት የተኩስ አቁም ስምምነቶች ተፋርሰው ውጊያው ቀጥሎም ቆይቷል።

በመደበኛው ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል ለ48 ሰዓታት ያህል ድርድር ከተደረገ በኋላም የአሁነኛው የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መደረሱን ብሊንከን ገልጸዋል።

ሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች የተኩስ አቁም ስምምነቱን ተግባራዊ እንደሚያደርጉ በተናጠል አስታውቀዋል።

ጦርነቱ ሚያዝያ 7/ 2015 ዓ.ም ከተቀሰቀሰበት እለት ጀምሮ ቢያንስ ከ400 በላይ ዜጎች ሕይወት መቀጠፉን ቢቢሲ ዘግቧል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

“የሱዳንን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ”- ጄነራል ዳጋሎ

ራፒድ ሰፖርት ፎርስ (አር.ኤስ.ኤፍ) ተብሎ በሚጠራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ዋና አዛዥ ጄነራል መሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ “የሱዳንን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ” አሉ።

ጄነራል መሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ በሱዳን እየተካሄደ ባለው ጦርነት ዙሪያ ከስካይ ኒውስ ጋር በነበራቸው ቆይታ “አሁን ላይ እየተዋጋን ያለነው ከሱዳን ጦር ጋር ሳይሆን ከቅጥረኛ ኃይሎች ጋር ነው፤ ምክንያቱም 90 በመቶ የሱዳን ጦር ከጥቅም ውጪ ሆኗል” ብለዋል።

ዳጋሎ አክለውም፤ “ከዚህ በኋላ ከሱዳን ጦር ዋና አዛዣ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ጋር ተቀምጦ መነጋገር ምንም ዋጋ እንደሌለውና አልቡርሃን ከዚህ በኋላ ያለው አማራጭ እጅ መስጠት ብቻ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

“ጦርነት አልፈልግም ነበር፣ ከጦርነት ይልቅ ሰላም እና መረጋጋትን ነው የምመርጠው” ያሉት ዳጋሎ፤ “ወደ ጦርነት እንድንገባ የገፋፋን አልቡርሃን ነው፤ አሁን ግን እጁ ላይ ምንም አልቀረለትም” ሲሉም ተናግረዋል Alain።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

"ከኦነግ ጋር በታንዛንያ ነገ ድርድር እናደርጋለን" አብይ :)

የአማራ ፍራቻ ገና ከግንድ ጋርም ያስተቃቅፍሃል!

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አሜሪካ ሠራተኞቿን በማስወጣት በካርቱም የሚገኘውን ኢምባሲዋን በይፋ ዘጋች‼️


በካርቱም የሚገኘው የዋሽንግተን ኤምባሲ እንዲሁም ጥቂት ቁጥር ያላቸው ዲፕሎማሲያዊ ሰራተኞች ከሀገር እንዲወጡ መደረጋቸውን የዩኤስ ባለስልጣናት ትናንት አስታውቀዋል።
ጦርነቱ ከ100 ያላነሱ አሜሪካዊያን ማፈናቀሉን ባለሥልጣናቱ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
"በካርቱም ኢምባሲ የተመደቡትን ሁሉንም የአሜሪካ ሰራተኞች እና ጥገኞች አስወጥተናል" ሲሉ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የማኔጅመንት ምክትል ፀሀፊ ጆን ባስ ተናግረዋል።
ዋሽንግተን በፀጥታው ስጋቶች ምክንያት ኢምባሲው ከትናንት ቅዳሜ ጀምሮ ስራውን እንዲያቆም ወስናለች ሲል ባስ ተናግሯል።

መረጃው የ ሮይተርስ ነው::

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ከ10 በላይ ሄሊኮፕተሮች ዛሬ ደሴ ዙሪያ ለብዙ ደቂቃዎች መታየታቸውን ነዋሪዎቹ ገልፀውልናል። በገራዶ አካባቢም አድርገው ወደ ሱዳን ድንበር ሳያቀኑ እንዳልቀሩ ገልፀዋል። የቅኝት ስራ እንደሚሰሩ ይገመታል።
ሚያዝያ 14/2015 ዓ.ም
=======≠========

Читать полностью…

Ethio 360 Media

"የውጭ አገራት ዜጎች ከካርቱም ሊወጡ ነው"- የሱዳን ጦር

ሳምንት የደፈነው የሱዳን ጦርነት ተፋፍሞ ከመቀጠሉ ጋር ተያይዞ የውጭ አገራት ዜጎቻቸውን ከመዲናዋ ካርቱም ሊያስወጡ ነው።የአሜሪካ፣ የእንግሊዝ፣ የፈረንሳይ እና የቻይና ዲፕሎማቶች እና ዜጎች ከሱዳን ሊወጡ መሆኑንም የሱዳን ጦር ባወጣው መግለጫው አስታውቋል።የሱዳን ጦር አዛዥ አብደል ፈታህ አል ቡርሃን የውጭ አገር ዜጎቹ “በሚቀጥሉት ሰአታት ውስጥ” የሚወጡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እና ለማስተባበር ተስማምተዋል ።

ሳዑዲ አረቢያም በሱዳን ያሉ ዜጎቿን “ከወንድም” ሱዳን አገር ልታስወጣ በዝግጅ ላይ መሆኗን አስታውቃለች።የሳዑዲ አረቢያ ዲፕሎማቶች ሱዳንን ለቀው መውጣታቸውን የሱዳን ጦር አስታውቋል።

የአውሮፓ ህብረት ዜጎቹን ከካርቱም ለማስወጣት እቅድ መንደፉን አስታውቋል።አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን እንዳሉ የህብረቱን አባል አገራት ዜጎችም ለማስወጣት የተለያዩ አማራጮችን እያጤኑ እንደሚገኙም ነው።በካርቱም ወደ 1 ሺህ 500 የሚጠጉ የህብረቱ አባል አገራት ዜጎች ይገኛሉ።ሰባት የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት በሱዳን ተልዕኮ አላቸው።የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አና ባየርቦኮክ ዜጎችን ለማስወጣት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መደረስ ቀዳሚ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።

ግጭቱ ከተከሰተበት ሚያዝያ 7፣ 2015 ዓ.ም ጀምሮ የካርቱም አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደተዘጋ ይገኛል።

አሜሪካ የዲፕሎማቲክ ሰራተኞች ካርቱምን ለቀው እንዲወጡ ለማድረግ ውሳኔ ላይ እንዳልደረሰች ገልጻለች።ባለስልጣናቱ ከኤምባሲው ሰራተኞች ውጭ ያሉ ሌሎች የአሜሪካ ዜጎች ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ በራሳቸው እንዲዘጋጁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።ባለስልጣናቱ ይህንን ይበሉ እንጂ አሜሪካ ዜጎቿን ለማስወጣት በዝግጅት ላይ መሆኑን ዘገባዎች አሳይተዋል።የአሜሪካ ጦር የኤምባሲውን ሰራተኞች ከካርቱም ለማስወጣት እየተዘጋጀ መሆኑንም ተዘግቧል።የአሜሪካ ወታደሮች በጂቡቲ ወደሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ እየተወሰዱ እንደሆነም የአገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

አርብ እለት የአሜሪካ የጦር ሰራዊት ጀነራል ማርክ ሚሌይ ከጦር አዛዡ ጄነራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን ጋር በሱዳን ስላሉት አሜሪካውያን ደህንነት ተወያይተዋል።ፔንታጎን በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።

[BBC]

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ጦርነቱ በቀጠለባት ሱዳን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ካርቱምን ለቀው እየወጡ ነው
=========================


በካርቱም ተቀማጭነቱን ያደረገው ጋዜጠኛ መሀመድ አላሚን ለቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ሬድዮ እንደተናገረው የተኩስ አቁም ስምምነት ተብሎ ቢታወጅም የተኩስ እሩምታው እንዳልቆመ ነው። “በእርግጥ እየተካሄደ ያለው ውጊያ አሰቃቂ ነው። ተፋላሚ ወገኖች በየቦታው በዘፈቀደ እየተኮሱ ነው” የሚለው ጋዜጠኛው “እኔ ራሴ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከካርቱም እየወጡ ወደ አጎራባች ግዛቶች ለመጓዝ ሲጣደፉ አይቻለሁ” ብሏል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ሩሲያ “ደቡብ ኮሪያ ዩክሬንን ካስታጠቀች ሰሜን ኮሪያን ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን አስታጥቃለሁ” ስትል ዛተች

ደቡብ ኮሪያ ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ለመስጠት ሁኔታዎችን እየገመገመች መሆኑን ከሰሞኑ አስታውቃለች።

ይህንን ተከትሎ ሩሲያ ዛሬ ባወጣችው መግለጫ ደቡብ ኮሪያ ለዩክሬን የጦር መሳሪያ እንዳትሰጥ አስጠንቅቃለች።

ደቡብ ኮሪያ የሩሲያን ማስጠንቀቂያ ችላ ብላ ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ከሰጠች ሞስኮ ለሰሜን ኮሪያ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ እንደምታስታጥቅ ገልጻለች።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ኤርትራ በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ ገባች እያለ የሚነዛነዘው ትህነግ የአልቡርሃን ቅጥረኛ ሆኖ በሱዳን ግጭት ተሳታፊ ሆኗል።

በየካምፑ የነበረው የትህነግ ታጣቂ በሱዳን ጦርነት ተሳትፎ እያደረገ ነው።

እነ ጌታቸው ረዳ ከመቀሌ እንደ አገር መሪ ለሱዳን መልዕክት ያስተላለፉት የቀረ ኃይላቸው ከአልቡርሃን ጎን አሰልፈው ነው። ነገ ከጦርነት መልስ ያግዘናል ብለው ብቻ ሳይሆን በአልቡርሃን ይሁንታ ነው ያሉት።

ባለፈው ጦርነት አንድ ሚሊዮን አስፈጅቶ አሁን ደግሞ በቅጥረኛ ወታደርነት አሰልፎታል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኢትዮጵያ እያደረገችው ያለው የሴቶች የጅምላ ምልመላ ያሳስበናል አሉ‼️


የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች የሳውዲ አረቢያን ደካማ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ኢትዮጵያ እያደረገችው ያለው የሴት ሠራተኞች የጅምላ ምልመላ ያሳስበናል ሲሉ ገለጹ፡፡

አሁንም ቢሆን በርካታ ስደተኛ ሠራተኞች በሳውዲ አረቢያ ከሠራተኛ ሕጎች የተገለሉና በዘመናዊ ባርነት ስርዓት ለጥቃት የተጋለጡ ናቸው ተብሏል፡፡

<ካፋላ> በተሰኘው ስርዓት አንድ ሠራተኛ በደል ቢደርስባት እና ከአሠሪዎቿ ብትሸሽ ፓስፖርቷን ጨምሮ የተለያዩ የሰነድ መረጃዎቿን እንድታጣ እንደሚደረግ እና ይህ ስርዓት አሁንም ለውጥ እንዳልተደረገበት ነው የተገለጸው፡፡

‹‹ሳውዲ አረቢያ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በዘፈቀደ በማሰር እና አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ለእንግልትና ለሞት በመዳረግ፤ ሌሎችንም በመደብደብ ከአገሯ እንዲወጡ አድርጋለች›› ሲሉ የስደተኞች መብት ተመራማሪ ናድያ ሃርድማን ለአልጀዚራ አስረድተዋል፡፡

ስለሆነም ኢትዮጵያ ይህን ዓይነት አስከፊ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ወደለባት ሳውዲ አረቢያ 500 ሺሕ ሴት ሠራተኞችን ለመላክ ማቀዷን የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎቹ ኮንነዋል፡፡

ከኢትዮጵያ የሚላኩት ሴት ሠራተኞች ከሳውዲ አረቢያ የሠራተኛ ጥበቃ ሕጎች የተገለሉ ናቸው የተባለ ሲሆን፤ ለሚደርስባቸው በደልም ምንም ዓይነት ሕጋዊ መፍትሔ የሌላቸው መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ሠራተኞችን ለተሳዳቢ አሠሪዎች አሳልፎ የሚሰጠውን የካፋላ ስርዓትን ማፍረስን ጨምሮ ሙሉ ጥበቃን ለማረጋገጥ መፍትሔ መፈለግ አለበት ያሉት የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች፣ በውሸት የጥበቃና ዋስትና ከለላ ሴቶችን ወደ ስደት መገፋፋት የለበትም ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት በዘንድሮው በጀት ዓመት የ500 ሺሕ ሴቶችን የጉዞ ወጪ ችሎ ወደ ሳውዲ አረቢያ ለመላክ ሥልጠና በመስጠት ላይ ሲሆን፣ የመጀምሪያ ተጓዦች ባለፈው መጋቢት ወር አጋማሽ ላይ መጓዛቸው ተመላክቷል፡፡

በ266 ዶላር ወርሃዊ ክፍያ ለቤት ሠራተኝነት የሚሄዱት የኢትዮጵያ ሴቶች፣ ከ18 እስከ 40 ዓመት እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሲሆን፣ የኮሌጅና የዩንቨርሲቲ ምሩቃንንም ያካተተ ነው፡፡

ሠልጣኞች ከመንግሥት በኩል እድሉ ሊያመልጣቸው የማይገባ የሕይወት ዘመን ወርቃማ እድል ነው መባላቸውን ገልጸዋል፡፡

በፈርንጆች 2020 የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት በሳውዲ አረቢያ እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ስቃይና መገደል ካረጋገጠ በኋላ የአገሪቱን የሰብዓዊ መብት አያያዝ የሚያወግዝ ውሳኔ አሳልፎ ነበር፡፡
አዲስ ማለዳ

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የ ኢንተርኔት ነገር በአማራ ክልል
======================

ጎንደር ከተማ በቪፒኤን የሞባይል ኢንተርኔት ከተቋረጠ 15 ቀን እንዳለፈው ተሰምቷል።

ሰሜን ወሎ ወልዲያ 2ኛ ቀኑን ይዟል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የሱዳን ተፋላሚዎች ለ24 ሰአት እንዲቆይ የደረሱት የተኩስ አቁም ስምምነት ተጣሰ‼️


የሱዳን ተኩስ አቁም ተግባራዊ ሊሆን ትንሽ ሲቀረው የተፈጠረው ተኩስ ስምምነቱ ተግባራዊ እንዳይሆን አድርጎታል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በካርቱም የሚገኙ 59 ሆስፒታሎች ውስጥ 39 ሆስፒታሎች አገልግሎት መስጠት አቁመዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አዲስ አበባ ዪኒቨርስቲ‼️


አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ማንነትን መሰረት ያደረገ እስር መደረጉ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።

ዛሬ አመሻሽ ዮሃንስ የሚባል የህግ ተማሪ መታሰሩን ምንጮች ገልፀዋል።
ተማሪዎቹ ወጥተን ለመግባት ስጋት አድሮብናል ብለዋል።

ሚያዝያ 10/2015 ዓ.ም
=======≠========

Читать полностью…
Subscribe to a channel