ethio360media | Unsorted

Telegram-канал ethio360media - Ethio 360 Media

37564

ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር !!!

Subscribe to a channel

Ethio 360 Media

የሚዲያ ባለሙያዎችን ማዋከቡ እጅግ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ‼️


የሚዲያ ባለሙያዎችን ማዋከቡ እጅግ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ገለጹ፡፡

ዶ/ር ዳንኤል ይህን ያሉት በትናንትናው ዕለት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ31ኛው የተከበረውን የፕሬስ ነጻነት አስመለክቶ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ባዘጋጀው መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

በኢትዮጵያ የሚዲያ ነጻነት በአሁኑ ወቅት አደጋ ውስጥ መግባቱን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ፤ በአሁኑ ወቅት ቢያንስ ስምንት ጋዜጠኞች በእስር ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ በእስር ላይ ከሚገኙት ጋዜጠኞች በተጨማሪ በመንግሥት በመሳደድ ላይ ያሉ ጋዜጠኞች ስለመኖራቸውም ጠቁመዋል፡፡

የሚዲያ ነጻነት ለሰብዓዊ መብቶች መከበር መሰረት መሆኑን ያስታወሱት ኮሚሽነሩ፤ ከአራት ዓመት በፊት የታየው የነጻነት ዝንባሌ በሂደት አደገኛ ወደሆነ ሁኔታ መለወጡን ጠቁመዋል፡፡ በወቅቱ የታየውን የሚዲያ ነጻነት ዝንባሌ ተከትሎ የተሻሻለው የሚዲያ አዋጅ ትልቅ ለውጥ የታየበት ቢሆንም፤ አፈጻጸሙ ላይ በርካታ ከፍተቶች መታየታቸውን ተናግረዋል፡፡

በሕጉ አፈጻጸም ላይ ከታዩ ከፍተቶች መካከል ጋዜጠኞች በአዋጁ ላይ የተሰጣቸውን መብት በግልጽ የሚጥሱ እስሮችና ተገቢ ያልሆነ ወከባ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን በአዋጁ ላይ በሚዲያ ላይ በቀረበ ይዘት የተፈጸመ ወንጀል ሲኖር፤ ከእስር በፊት ክስ መቅረብ ያለበት ቢሆንም አሁን እየታየ ያለው ከዚያ በተቃራኒ መሆኑን ዳንኤል ገልጸዋል፡፡

ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ከሚዲያ ነጻነት የሚቀዳ ሲሆን፤ ከሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ የሚመዘንበት ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡ የሚዲያ ሕግ ጥሩ ቢሆንም፤ አፈጻጻሙ ላይ በርካታ ክፍትቶች ታይተውበታል።

“ቅድመ ክስ እስር በሕጉ ቢከለከልም መንግሥት ይህን ሕግ በተደጋጋሚ ጥሶታል” ያሉት ዳንኤል፣ ችግሩን አሁንም ተባብሶ መቀጠሉ አሳሳቢ ከመሆኑ ባሻገር ችግሩን ለመቀልበስ ብዙ ሥራ እንደሚጠይቅም አመላክተዋል፡፡


አዲስ ማለዳ

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ብርጋዴል ጀነራል ተፈራ ማሞ ለህክምና ወደ ውጭ እንዲሄዱ በፍርድ ቤት ተፈቅዷል!


ከወራት በፊት ለህክምና ወደ እስራኤል ሃገር ለመሄድ ወደ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ያቀኑት ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ ከሃገር እንዳይወጡ መከልከላቸው ይታወቃል።
ይህንንም ተከትሎ ጀነራል ተፈራ ማሞ ክስ መስርተዋል።
ፍርድ ቤቱም በጀነራል ተፈራ ማሞ ላይ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በህገወጥ መልክ ክልከላ ፈፅመዋል ብሏል።
በዚህም ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ ከሃገር የመውጣት በህግ የተሰጣቸውን መብት የገደበ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ከአገር ወጥተው እንዲታከሙ ሲል ፍርድቤቱ ወስኗል።

ሚያዚያ 25/2015 ዓ.ም
=======≠========

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አስቸኳይ የወልቃይት መረጃ‼️
=========================


ከትናንት ጀምሮ የትግራይ ታጣቂዎች ወደ ወልቃይት እየተጠጉ መሆኑን መረጃዎች እየወጡ ነው። ድሽቃ፣ብሬን እና ሞርታር የያዙ ታጣቂዎች በኦራል መኪና እንዲሁም ከኦራል ቦቲ መኪና ጋር በብዛት ተጠግተዋል።


ሚያዝያ 25/2015 ዓ.ም
=======≠========

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የሱዳን ተፋላሚዎች በድጋሚ የተኩስ አቁሙን ጥሰውታል፡፡

ለተኩስ አቁሙ በድጋሚ መጣስ ተፋላሚዎቹ በአንተ ነህ ፤ አንተ ነህ እየተካሰሱ መሆኑን ዘ ቴሌግራፍ ፅፏል፡፡

ርዕሰ ከተማዋ ካርቱምም በጦር አውድማነቷ ቀጥላለች፡፡

የመንግስት ጦር አውሮፕላኖች በምህፃሩ RSF የተሰኘውን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ይዞታዎች መደብደባቸው ተሰምቷል፡፡

ጦሩም በግላጭ አማፂ ሲል የጠራውን የፈጥኖ ደራሽ ሀይል ታጣቂዎች ከካርቱም ጠራርጎ ለማስወጣት ዘመቻ እያካሄደ መሆኑን እወቁልኝ ብሏል፡፡

ታዋቂው ምጣኔ ሐብታዊ አከናዋኝ እና በጎ አድራጊ ሞ ኢብራሂም ሱዳን ወደለየለት የእርስ በርስ ጦርነት እያመራች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሞ ኢብራሂም ግጭቱ ወደ ክፍለ አህጉራዊ ቀውስነት እንዲሸጋገር ሊፈቀድ አይገባም ማለታቸው በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

የኔነህ ከበደ

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ከዓለም ሀገራት ከህዝብ ብዛቷ አንፃር በርካታ ሰራዊትን በመያዝ ኤርትራ ቀዳሚ ሆነች‼️


ከ3.6 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ኤርትራ 202,000 ንቁ የታጠቁ ሃይሎች(Active personal) አላት።  ይህ ማለት ከ1,000 ነዋሪዎች ውስጥ 55.8% ንቁ የታጠቀ ሃይል አላት ማለት ነው። በንፅፅር ዩናይትድ ስቴትስ ከ1,000 ነዋሪዎች 4.2 ንቁ ወታደር አላት። እነዚህ አሃዞች ከአለም አቀፍ የስትራቴጂ ጥናት ተቋም ወታደራዊ ሚዛን 2022 የህዝብ ቁጥርን በመጠቀም የተስተካከለ ሪፖርት በወታደራዊ ሰራተኞች መረጃ ላይ የተመሰረቱ ናቸው።
በነፍስ ወከፍ ኤርትራ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት ያደረጋት ሀገሪቱ የምትከተለው አስገዳጅ ወታደራዊ አገልግሎት ህጎች ምክንያት መሆኑ ተነግሯል። ኤርትራ እድሜያቸው ከ18 እስከ 40 ላሉ ዜጎች የውትድርና ስልጠና አገልግሎት ትሰጣለች ሲል ሲአይኤ በጥናቱ ላይ ይገልጻል።
የኤርትራ ወታደራዊ ኃይል ንቁ ወታደራዊ ሠራተኞች (Active military manpower) በጠቅላላው  ግምት ውስጥ ከገቡ 169 አገሮች ውስጥ 22 ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በንፅፅር የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ኃይል በዓለም ላይ በሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ወደ 1.4 ሚሊዮን የሚጠጉ ንቁ የታጠቁ ወታደሮች አሏት።


ሚያዝያ 24/2015 ዓ.ም
=======≠========

Читать полностью…

Ethio 360 Media

እናት ፓርቲ ፌደራል መንግሥቱ በአማራ ክልል ውስጥ የጀመረውን "የጅምላ እስር፣ የትጥቅ ማስፈታት ዘመቻ፣ የድርጅቶችና ግለሰቦችን የገንዘብ እንቅስቃሴ የማገድ ሂደት" እንዲያቆም ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

ፓርቲው፣ መንግሥት "በማንአለብኝነት አካሄዱ ቀጥሎ በአገርና በሕዝብ ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም ዓይነት ጥፋትና ውድመት ከተጠያቂነት አያመልጥም" በማለት አስጠንቅቋል። ፓርቲው፣ በአንዳንድ ክልሎች በገዥው ፓርቲ ባለሥልጣናት ላይ በተፈጸሙ ግድያዎች ላይ "ምርምራ ባልተካሄደበትና ጥፋተኞች ባልተለዩበት ኹኔታ" ይደረጋሉ ያላቸው ፍረጃዎች "የፍትህ አሰጣጡን እንደሚያዛቡ" በመግለጽም በመግለጫው ተችቷል።

(Wazema)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ጋሽ አሰግድ… !
"…ዛሬ እኮ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው። ቅዳሴው ሳያልቅ ለውጊያው መልስ አንሰጥም ያሉት የማጀቴ የይፋት ጀግኖች የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ቀኝ እጅ የነበሩት አርበኛና ደራሲ እነ ጋሽ አሰግድ ቅዳሴው ካለቀ፣ ተአምረ ማርያምን ሰምተው፣ በመስቀል ተባርከው፣ ወደ ማይቀረው ፍልሚያ ገብተዋል።

"…እስከ አሁን በከባድ መሳሪያ የገበሬ ቤት ከመምታት፣ ዛፍ ቅጠሉን ተራራውን ከመናድ በዘለለ አንድም ፋኖ ጫፉ አልተነካም። መንግሥት ቁስለኞቹን እያነሣ ነው። ሟቾቹንም እየለቀመ ነው።

"…በጫካ የነበሩት ባለ ጉዱሩዎቹ የጨነቀ ቀን ሲመጣ ከተማ መርመስመስ ጀምረዋል። መከላከያው ሕዝብ ላይ አልተኩስም ማለቱም ተሰምቷል። አቢይ አሕመድ አልታዘዝም የሚል ወታደር ከተገኘ እርምጃ ውሰዱበት፣ ረሽኑት ብሎ ትእዛዝ መስጠቱም ተሰምቷል። የብአዴን የታች አመራሮችን ኦሮሙማው መከላከያ ማሰር ጀምሯል። ነገሩ ቀልጧል። የዓድዋው ዘማች ሊቀ ሰማእት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተጎጂው ሃቅ ካለው ከዐማራው ጎን ቆሟል። ድንጋጤ በብልፅግና ቤት ወድቋል።

"…እየዋለ ሲያድር ተአምር እንሰማለን። በጫት የደነዘዘ የእኔዎቹን የሐረርጌ ቆቱ ወታደሮች ጫት የሌለበት ሸዋ አምጥተውት "ሃይ አቦ ተዉና እያለ መሣሪያውን በ3ሺም በ2ሺ እየሸጠ ልብስ ቀይሮ እየፈረጠጠም ነው ተብሏል። መከላከያውን መቀለብ ሕዝቡ ስላቆመ እነ ሽመልስ አብዲሳ ለወታደሩ ፎርጅድ ብር ሰጥተው ገዝተው እንዲበሉ ቢያደርጉም አሁን ብሩ ፎርጅድ መሆኑ በመታወቁ ነጋዴውና ወታደሩ ተፋጧል።

"…ዝርዝር ውሎውን ቆይቼ ይዤ እመለሳለሁ። እናንተ ግን ለማጀቴ፣ ለይፋት ጀግኖች፣ ለምኒልክ ዘሮች፣ ለአንበሶቹ ሞራል ስጡልኝ። አልቃሾች ጥፉ ከዚህ ድራሽ አባታችሁ ይጥፋና ጥፉ። ምድረ ጠንቋሊ ሁላ። ነጻነት በነፃ፣ በብላሽ አይገኝም።

• ድል ለዐማራ…! ወጥር፣ መክት፣ አንክት…! 👏👏👏

(ዘመድኩን በቀለ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ እንደዚሁም ከደሴ አቅጣጫ ወደ አዲስ አበባ የምትጓዙ መንገደኞች ማጀቴ አካባቢ የፀጥታ ችግር መኖሩ ስለተሰማ ሰላም መሆኑን እያረጋገጣችሁ ቢሆን መልካም ነው።

ማጀቴ የተፈጠረው ጉዳይ<< የመከላከያ አመራሮች ትናንት ከህዝቡ ጋር ተወያይተው ነበር፣ይህንን ተከትሎ እንደቆቦው ፍቃድ የሌለው ትጥቅ እንሰበስባከን ሲሉ ከአካባቢው የፋኖ አባላት ጋር አለመግባባት ተፈጥራል።ሂደቱ ምወደ ተኩስ ልውውጥ ተቀይሯል።>>

ከነዋሪዎች የሰማነዉ መረጃ ይሄንን ነው።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የላባደሮች ቀን ‼



✔ኢትዮጵያ ለ47ኛ ዓለም ደግሞ ለ133ኛ ግዜ በዛሬው እለት ሚያዝያ 23/2015 ተከብሮ ይውላል ::

✔ የስራ ሰዓት ስምንት ሠዓት ይሁን ብለው በአሜሪካ ቺካጎ ሰላማዊ ሰልፍ በወጡ ሰዎች ላይ የግድያ እርምጃ የተወሰደው የዛሬ 136 ዓመት ልክ በዛሬው ቀን እንደነበር ታሪክ ያስረዳል።

✔በእለቱ የአራት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ሃያ ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው የነበረ ሲሆን ይሄ የ8:00ሰዓት የስራ ሰዓት ይከበር በሚል የቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ ሰራተኞች እየተጠቀሙበት ይገኛል።

✔እለቱን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ ሰራተኛች ማህበራት በአዲስ አበባ ሊያደርገው የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ተከልክሏል።የሰልፉ አላማ የስራ ግብር ይቀነስ፣የኑሮ ውድነቱ ሰራተኞችን እየፈተነ በመሆኑ እርምጃዎች ይወሰዱ፣የሰራተኞች ጥቅም ይከበር የሚል ነበር።

✔ ✔መልካም የላባደሮች ቀን!!!✔✔

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ኢሠማኮ የሠራተኞች ቀንን እንዳያከብር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መከልከሉን አስታወቀ‼️


የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ነገ ሰኞ ሚያዚያ 22/2015 በመስቀል አደባባይ የሠራተኞች ቀንን በማስመልከት ለማክበር የያዘው ፕሮግራም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መከልከሉን ገለጸ።

ኮንፌዴሬሽኑ በየዓመቱ ሚያዝያ 23 የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ቀን፣ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ለማክበር ፕሮግራም መያዙን አስታውቆ ነበር።

ይሁን እንጂ በዓሉን በሰላማዊ ሰልፍ ለማክበር ዝግጅት ከጨረሰ በኋላ፣ ፕሮግራሙ እንዳይከናወን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ መከልከሉን አዲስ ማለዳ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።

የዘንድሮው የሠራተኞች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ134ኛ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ48ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን፣ ኢሠማኮ በ ዓሉን "ለሠራተኞች መሠረታዊ ጥያቄዎች አፋጣኝ መፍትሄ" በሚል መሪ ቃል ለማክበር መዘጋጀቱን በሰጠው መግለጫ ገልጾ ነበር።

መሪ ቃሉ የተመረጠው በአሁኑ ወቅት የተከሰተዉ የኑሮ ዉድነትና የሠራተኞች መብት መጣስን በተመለከተ ለመንግሥት በማቅረብ መፍትሔ እንዲያገኙ ለማድረግ መሆኑም ተመልክቷል።

የኢሠማኮ ጠቅላይ ምክር ቤት መጋቢት 28/2015 ባካሄደዉ መደበኛ ስብሰባ በሠራተኞች ዋና ዋና ችግሮች ላይ ተወያይቶ፣ የዘንድሮው በዓል በሰላማዊ ሰልፍ በአደባባይ እንዲከበርና የሠራተኛው ጥያቄዎች ለሚመለከታቸዉ የመንግሥት አካላት እዲቀርብ ወስኖ ነበር።

ኢሠማኮ የሠራተኛ መብቶች እንዳከበሩ በተደጋጋሚ ለሚመለከታቸው አካላት ጥሪ ሲያቀርብ የነበረ ሲሆን፤ በተለይ የዋጋ ንረት ተከትሎ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ እንዲሻሻል መጠየቁም የሚታወስ ነው።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በቆቦ ከተማ መከላከያ ሰራዊት ቤት ለቤት ፍተሻ እያካሄደ እንደሚገኝ ነዋሪዎቹ ገልፀውልናል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ሰበር መረጃ ነው…!

"…የብርሃኑ ጁላ መከላከያ የምሥራቅ ዐማራ ፋኖ የምሬ ወዳጆን ቤተሰብ ሳያፍኑ እንዳልቀረ ተነገረ። መከላለያው መብራት አጥፍቶ ካፈናቸው ቤተሰቦቹ መካከል፦

"…የ8 ወር ነፍሰጡት ባለቤቱን ወ/ሮ ደርብን፣ እህቱ አንጉታ፣ አያቶቿ ወይም የአባቷ እና የእናቷ አባት እናቶች፣ አዛውንት መነኮሳት እና ከዚህም በላይ ከ15 የበለጠ ቤተሰብ አው ያለው 6 ህፃናት ናቸው።

"…ዛሬ ምሽት 2:00 ማታ ሲሆን ቅድሚያ የከተማውን ሙሉ መብራት አጥፍተው 1 ሻለቃ ጦር ሙሉ መንደሩን ወርሮ በኮማንድ ፖስት በለችው ከታማ ውስጥ ያሉ ቤተሰቦቹን ይዘው መሄዳቸው ተነግሯል። የዓይን ምስክሮች እንደተናገሩት ከሆነ ወደቤቱ በዙ መኪና እየተመላለሰ የነበረ ሲሆን 2 ጊዜ  የጥይት ተኩስም መስማታቸውን ተናግረዋል። መብራት በመጥፋቱ እና መንቀሳቀስ ስለማይቻል በትክክል በእርግጠኝነት የወሰዱት የሰው ብዛት ለጊዜው አለመታወቁም ተነግሯል።

"…ሁኔታውን ለማጣራት ወደ አርበኛ የዋርካው የምሬ ወዳጆ ዘንድ ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ ያደረግኩ ሲሆን መስመሩ ከአገልግሎት መስጫ ክልል በመሆኑ ከምሬ ላረጋግጥ አልቻልኩም።

"…አይደለም እስር ጭፍጨፋም የዐማራን የነፃነት ጉዞ አያስቆመውም። አለቀ።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ሁለቱ የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ከትናንት እኩለ ሌሊት ጀምሮ በድጋሚ ያራዘሙትን የ72 ሰዓታት ተኩስ አቁም ሳያከብሩ እንደቀሩ የውጭ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ካርቱም ዛሬም በከባድ መሳሪያ ተኩስ ስትናጥ እንደዋለች ዘገባዎቹ አመልክተዋል። በምዕራብ ዳርፉር ግዛት በኹለቱ ወገኖች መካከል የቀጠለው ግጭት ደሞ፣ የጎሳ ግጭት መቀስቀሱን ተመድ ገልጧል(ዋዜማ)።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ ትምህርት የለም

ከመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተውጣጡ የትምህርት አመራሮች መምህራን እና ሠራተኞች የሳይንስ ሙዚየምን እየጎበኙ ነው።

አመራርና ሠራተኞቹ ከሣይንስ ሙዚየም በተጨማሪ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤትንም የሚጎበኙ ሲሆን ከጉብኝቱ በኋላም ውይይት እንደሚካሄድ ታውቋል።በመቀጠልም ጥብቅ ስብሰባ ያደርጋሉ ተብሏል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ሰበር ዜና❗


የአማራ ክልል የብልፅግና ሃላፊ እና ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ግርማ የሺጥላ ከመሃልሜዳ ሲመጡ ጓሳ በተባለ አካባቢ በተተኮሰባቸው ጥይት ተገደሉ::
መሃልሜዳ ሆስፒታል ለህክምና ቢገቡም ህይወታቸው ሊተርፍ አልቻለም።

በተጨማሪም‼️
ከአቶ ግርማ የሺጥላ በተጨማሪ በመኪናው ውስጥ ከነበሩት ጠባቂዎቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው ውስጥ አራት ሰዎች ሞተዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አስቸኳይ መረጃ‼️


የሸዋ ሰላም እና የልማት ማህበር(ሸዋሰማ) ፣የአማራ ተማሪዎች ማህበር ፣የአማራ ወጣቶች ማህበር እና የአማራ በጎ አድራጎትና ልማት ማህበር የባንክ አካውንታቸው እንዲመረመር የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ለሁሉም ባንኮች በፃፈው ደብዳቤ አዝዟል። እነዚህን የሲቪክ ማህበራት በፀረ-ሽብር ወንጀል ጠርጥሬያቸዋለሁ ብሏል።


ሚያዚያ 26/2015 ዓ.ም
=======≠========

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አማራው ላይ የሚደረገው ዘመቻ ከአቶ ግርማ የሺጥላ ሞት ጋር ግንኙነት የለውም። የአቶ ግርማን ሞት አማራው ላይ የጀመሩትን ዘመቻ ማጠናከሪያ ነው ያደረጉት።

#አማራው ላይ ዘመቻ የተጀመረው በጦርነቱ ወቅት ያሳየው ስነልቦና ስላስፈራቸው ነው። ብርሃኑ ጁላ መሃል አገር እየተዝናና ከባድ መሳርያ አዘርፎ አገር ሲያስወጋ የአማራ አርሶ አደር በዱላና መጥረቢያ ጭምር ከሰራዊቱ የተቀማ መሳርያ አስመልሷል።

#ገዥዎቹ ሁለት ልብ ሲሆኑ አገር ቤት ያለው ብቻ ሳይሆን በውጭ ይኖር የነበረው አማራ ወደ ጦር ሜዳ መጥቷል።

#በጦርነቱ ወቅት የአማራውን አቅም የተመለከቱት ገዥዎች አማራ ከጦርነት ማግስት በዚህ ስነ ልቦናው ከተመለሰ አደገኛ ነው ብለው ፈርተዋል። ሰላማዊውን ዜጋ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገባ በመከልከል "ፅንፈኛ ፋኖ፣ኤርትራ ያሰለጠነችው" ማለት የጀመሩት በዚህ ፍርሃት ምክንያት ነው።

#አማራው የጠነከረ ስነ ልቦና እንዳለው ቢያውቁም የአማራ ብልፅግና አብሯቸው የሚውል እንኩቶ ጥርቅም እንደሆነ ያውቁታል። አንድ ቀን "ትግል ወዘተ" ብሎ መግለጫ አወጣ። ከዛ በኋላ የት እንዳለ አይታወቅም።

#ገዥዎቹ ዘመቻውን በጦርኑ ስነ ልቦና ሰግተው ቢጀምሩትም የመከላከያ ሰራዊት አባላት በቁርጥ ቀን ማን አብሮት እንደነበር ያውቃል። ምንም እንኳ ዕዙ በአማራ ህዝብ ላይ የጥላቻ ወዝ በጠገቡት የሚመራ ቢሆንም በደንብ ከተሰራበት የመከላከያ ሰራዊቱ አባላት የህዝብን ውለታ ያውቁታል። በዚህ ዘመቻ በርካታ ምልክቶች ታይተዋል።

#አሁንም መታወቅ ያለበት ህዝብ ሲፈጅ የከረመን ኦነግ በዓለም አቀፍ መድረክ እየተደራደረ፣ አገር ያዳነን ኃይል ለመምታት የሚደረገው አካሄድ አገር ከማፍረስ ውጭ አላማውም ውጤቱም አያምርም። ገዥዎቹ አማራውን ከየ አቅጣጫው አዳክመው ርስቶቹን አስረክበው አንገቱን አስደፍተው

"ስልጣናችን ቀና ብሎ እንዳያይ እናደርገዋለን"

ብለው አስበዋል። የዘመቻው አላማ ይሄ ነው። የሚሣካ የሚሆን ግን አይደለም።


(ጌታቸዉ ሽፈራዉ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ድርጅትን (ሲ.ፒ.ጄ) ጨምሮ 47 የመብት ተከራካሪ ድርጅቶች በኢትዮጵያ የተቋረጠው የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲጀምር ጠየቁ፡፡


እነዚሁ ተቋማት ሚያዚያ 27 ቀን 2023 እ.አ.አ. ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በፃፉት ግልፅ ደብዳቤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እና የሚመለከታቸው ተቋማት ሁሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ የኢንተርኔት እና የዲጂታል አገልግሎት አማራጮችን ሁልጊዜም፣ ያለምንም ገደብ እንዲጠቀም አስፈላጊ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጠይቀዋል፡፡
‹ ኪፒ-ኢት-ኦን-ኳሊሽን › የተሰኘውና 300 የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ህብረት አባል መሆናቸውን የገለፁት ተቋማቱ ‹ በተለይም በትግራይና አማራ ክልሎች ኢንተርነት መዝጋትን እንደጦር መሠሪያ መጠቀም በተመለከተ አንገብጋቢ የጥሪ ደውል እያሰማን ነው › ሲሉ በደብዳቤው አመልክተዋል፡፡
‹ ክፍት፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ታማኝና ተደራሽ የኢንተርኔት አገልግሎት የሰብዓዊ መብቶች ለመጠበቅ ወሳኝ መሆኑን› አስምረውበታል፡፡


ሚያዝያ 24/2015 ዓ.ም
=======≠========

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ሸዋሮቢት‼️


ሸዋሮቢት በዚህ ሰዓት በከባድ መሳሪያ የታገዘ ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ እየተሰማ ይገኛል።


ሚያዝያ 24/2015 ዓ.ም
=======≠========

Читать полностью…

Ethio 360 Media

መንግሥት ከኦነግ ሸኔ ጋር እያደረገው ያለውን የድርድር ሂደትና ስምምነቱን በተመለከተ ለሕዝቡ ግልፅ መረጃ እንዲሰጥ ኢዜማ አሳሰበ‼️
መንግሥት ባለፈው ሳምንት ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ቦታዎች በሚንቀሳቀሰውና የተለያዩ ሽብር ተግባራትን በማከናወኑ በኢፌዴሪ ሕ/ተ/ም/ቤት አሸባሪ ተብሎ ከተፈረጀው መንግሥት ኦነግ ሸኔ ብሎ ከሚለው እራሱን የኦሮም ነፃነት ሰራዊት ብሎ ከሚጠራው ታጣቂ ቡድን ጋር ችግሮችን በውይይት ለመፍታት በታንዛኒያ መቀመጡን ማስታወቁ ይታወሳል።

ይህንንም አስመልክቶ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ ፓርቲው ጥቅምት 24 /2015 የፕሪቶሪያው ስምምነት ሊደረግ መሆኑን ተከትሎ ‹‹በሌሎች የአገሪቷ ክፍሎች ያሉ የታጠቁ ኃይሎችም ጋር በሰላማዊ ንግግር መፍትሔ የሚያገኝበት መንገድ ላይ በአፅንኦት መስራት ያስፈልጋል›› ሲል ጥሪ ማቅረቡን አስታውሷል፡፡

ፓርቲው በመግለጫው፤ አሁንም ሰላም የሰፈነባት እና ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን ለማየት ከተፈለገ የትኛውም ዓይነት የሃሳብ ልዩነቶች ከአፈሙዝ ተላቀው ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ መቅረብ እንዳለባቸው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንደሚያምን አስታውቋል፡፡

በተለይም ባለፉት ጥቂት ዓመታት በኦሮሚያ ክልል በተደጋጋሚ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት ክቡር የሆነው ሕይወታቸውን ሲያጡ ንብረታቸውም ሲወድምና ከቀያቸው ሲፈናቀሉ በገሀድ መታየቱን የገለጸው ኢዜማ፤ <<መንግሥትም በተደጋጋሚ የተፈፀሙትን በደሎች ይህ ታጣቂ ቡድን ሲፈፅማቸው እንደነበር ከማሳወቁ አንፃር ይህን መሰል የዜጎች ሰቆቃ የሚያስቆም ድርድር ውስጥ መግባቱን የምናበረታታው ነው።>> ብሏል።

ፓርቲው አክሎም፤ <<ገዢው ፓርቲ ብልጽግና አገራችንን መምራት የጀመረበትን ጊዜ ጨምሮ ባለፉት አምስት ዓመታት በተለያየ ጊዜ የሚፈጸሙ እንዲህ አይነት ድርድሮች ግልጽነት ሲጎድላቸው እና አፈፃፀማቸው በተገቢ ሁኔታ ሳይከናወን ቀርቶ ብዥታዎችን ሲፈጥር ተመልክተናል፡፡>> ሲል ገልጿል።

<<በቅርብ ጊዜ እንኳ መንግሥት ከሕወሓት ጋር ድርድር አድርጌ ሰላም አውርጃለሁ ባለበት የፕሪቶሪያው ስምምነት እንደ ስምምነቱ ያልተፈጸሙ ጉዳዮችን አስተውለናል፡፡ ሂደቱም ምን ላይ እንደሆነ አሁንም ድረስ በግልፅ አይታወቅም፡፡>> ያለው ኢዜማ፤ በዚህ ምክንያትም ፓርታውን ጨምሮ የተለያዩ አካላት ላይ አሁንም ድረስ ከፍተኛ ቅሬታን እያስነሳ መሆኑን ገልጿል፡፡

ስለሆነም መንግሥት ከዚህ ቀደም በለውጡ ሰሞን ኦነግ ከኤርትራ ወደ አገር ቤት ከገባ በኋላ <<በስምምነቱ መሠረት አልተፈጸመልኝም>> ሲል እንደነበረው ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር፤ በተለይም ከሕወሓት ጋር ከተደረገው ስምምነት ልምዶች መነሻ በማድረግ፣ የድርድሩን ሂደትና ስምምነቱን በተመለከተ ህዝቡ ሊኖረው የሚገባውን ግልፅ መረጃ ፤ እነማን እየተሳተፉ እንደሆነ፣ የስምምነቱን ይዘት፣ እንዴት እንደሚፈጸም እና በአፈፃፀሙም ጊዜ ተግባራዊነቱን ለዜጎች ተገቢና በቂ መረጃን በማስተላለፍ ከተጨማሪ ውዥንብርና ትርምስ ማኅበረሰቡን እንዲጠበቅ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አሳስቧል፡፡

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ለመከላከያው አድርሱልኝ…!

"…ሽንታሙ ኦነግ ሸኔ፣ ፈርጣጩ፣ ፈሪው፣ ነፍሰጡር ገዳዩ፣ የአቢይ አሕመድ የሽመልስ አብዲሳው ፕላን ቢ፣ ዐማራ ማጽጃ ማሽኑ ኦነግ ሸኔ ዛሬ እንደ ወንድ ተቆጥሮ ከዐማራ ጠሉ የግራኝ አህመድ የልጅ ልጅ ከስልጤው የወያኔ ቂጥ ላሽ ከሬድዋን ሁሴን ጋር ለድርድር ታንዛኒያ የከተመው መከላከያን በምታዩት መልኩ በኦሮሞ ምድር እንዲህ ጨፍጭፎት ነው።

"…መከላከያ የወንድሞችህን ደም መበቀያ ጊዜው አሁን በሉት። ንገሩት። ከዐማራው፣ ከታረደው፣ ከተገደለው፣ ከተጨፈጨፈው፣ ከተፈናቀለው ጎን ቁም በሉት። ለፍትሕ፣ ለዲሞክራሲ፣ ለእኩልነት ከሚታገሉት ዐማሮች ጎን ቁም በሉት።

• ዐማራ ያሸንፋል። ኢትዮጵያ ከነፍሰበላ ልቡሰ ሥጋ ጋኔኑ አቢይ አሕመድ አገዛዝም ነጻ ትወጣለች።

"…ድል ለዐማራ…!💪🏿💪💪🏿💪

(ዘመድኩን በቀለ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

"…ዐማራ ሃቅ አለው…!

"…የዐማራን ዘር አራጆቹ፣ ጨፍጫፊዎቹ ለፍርድ የማይቀርቡ ከሆነ፣ አማሮቹ ፍትሕም የማያገኙ ከሆነ አማራጫቸው ራስን ከመጥፋት መከላከል ነው። የአማራ አራጅ ሲበቃው፣ ሲሰለቸው በድርድር ስም ለሌላ አራጅ አሳልፎ ሰጥቶ የሚሸበለል ከሆነ ዐማራ ፍትሕ በኦትዮጵያ ይሰፍን ዘንድ እስከደም ጠብታ መታገል አለበት።

"…በቀል የእግዚአብሔር ነው። ሆኖም ግን አራጆችን ለፍርድ በማቅረብ አረመኔው አቢይ ገድሎ የቀበራትን ፍትሕ አክሞ ነፍስም ዘርቶባት ወንጀለኛ ነፍሰ ገዳዮችን መበቀል አለበት። እናም ዐማራ ሃቅ አለው። ከዐማራ ጎን መቆም ጽድቅ ነው።

"…ይሄን እያየህ የምትተኛ ዐማራም ሆንክ ሌላ ከአሁኑ ለእውነተኛ ፍትሕ፣ ነፃነት እና ዲሞክራሲ ካልታገልክ አራጆቹ በየደጃፍህ ይመጡልሃል። ይሄን ዘግናኝ ፎቶ ገጠር ለሚገኘው የዐማራ ሚሊሻ አሳዩልኝ። ጋብዙልኝ። ለገበሬው አቅርቡልኝ።

"…መከላከያም ተመልከተው። እየው። በጊዜም ከንፁሐን ጎን ቁም። አምባገነኖች እንደሆነ ተወደደም ተጠላም መወገዳቸው አይቀርም።

"…እኔ ዘመዴ ከጭቁኑ ዐማራ ከጎኑ ሳይሆን ከፊት ለፊቱ ነኝ። ዐማራ ሃቅ አለው። ያሸንፋል፣ ድል ከእርሱ ጋር ነች።

• ወጥር፣ መክት፣ አንክት…!💪💪🏿💪

(ዘመድኩን በቀለ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ማጀቴ…!💪💪🏿💪

"…ሸዋ ጠላትን አደረገው አሸዋ። አስቀድመን ተናግረና፣ ተናግረናል፣ ተናግረናል። በል ሬሳህን ልቀም። በል ቁስለኛህን ሰብስብ፣ ፍጠን ፈርጥጥ አንት የሰው ልክ አያውቄ። በል ንካው አንት የምርኮኛ ሽንታም የሽንታም ልጅ። በል አልኩህ ፍጠን። ተመለስ ፈርጥጥ አንት ፈርጣጭ የፈርጣጭ ልጅ። አንት ከመቀሌ እስከ ሞላሌ ሯጭ አሯሯጭ።

"…ሕዝብ ላይ ትተኩሳለህ ሕዝብ ራሱ መልስ ይሰጥሃል። አርህን ነው የሚያበላህ። በል ሞክረው። ሩጥ አንት ቅዘናም የቅዘናም ልጅ። የሰው ልክ የጀግና ጥግ የማታውቅ የደርግ ምርኮኛ። በል አልኩህ። ሸዋ የእሳት ጉማጅ፣ ሸዋ የምኒሊክ ዘር። አርበድብደው ይሄን ዲቃላ ባንዳ የባንዳ ልጅ።

"…ኮራሁ። ኮራው በማጀቴ፣ በይፋት። ኮራሁ አልኩህ አባቴ። ጎንደር የመሳፍንት ዘር ለብልበው ይሄን እንገፍ እነከፍ የሰው ልክ አያውቄ እንጭጭ። በለው ይሄን ጫታም ሽንታም አረቄያም። አሳየው፣ አሳጣው መድረሻ። በለው አልኩህ። አትሂድበት እንጂ ከመጣብህማ አትማረው። አትማርከው። ሚስትህን ሊደፍር፣ ሊያርድ የሚመጣውን አትማረው። አሳየው ክንድህን። በአንድ ፋኖ ሺውን ጎፍላ ኩታራ አሳደው። ልቀም መሳሪያህን፣ ተረከበው። ተቀበለው።

"…ያስቸገረ ብአዴን ካለ ከጠላት እኩል እየው። ወደ ኋላ እንዳትመለስ። ለመንግሥትነት ታገል። ዙሩን ቀይረው። ሽማግሌ ሆኖ የሚመጣውን ጳጳስ ሼክ ለምን አይሆንም ዶሮ ጠባቂ አድርገው። ማንንም አትስማ። ዐማራ ሆይ አንተ ፍትሕ ዐዋቂ ታላቅ ሕዝብ ነሕና ይሄ ሕገ አራዊት ጀዝባ ከፍት የሆነ አገዛዝ ቀጥቅጦ፣ ደብድቦ፣ ወግሮ፣ ገድሎ የቀበራትን ፍትሕ ከመቃብር አውጥተህ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ነፍስ ዝራባቸው። ተስፋቸውን አለምልም።

"…የሚሸነፍ መንግሥት እንጂ የሚሸነፍ ሕዝብ የለም…! ወጥር ዐማራዬ፣ ተከላከል፣ መክት፣ በመጨረሻም አንክት።

•ኤት’አባክ እንካ ቅመስ…!

(ዘመድኩን በቀለ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ጀርመን ከ2 ሚሊየን በላይ ሰራተኞችን እንደምትፈልግ ገለጸች‼️


በአውሮፓ የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤቷ ጀርመን የገጠማትን የሰራተኞች እጥረት ለመፍታት የስደተኞችን ፖሊስ እስከማሻሻል እንደምትደርስ አስታውቃለች፡፡

የሚሻሻለው የስደተኞች ፖሊሲም ሀገሪቱ የገጠማትን የሰራተኞች እጥረት በአጭር ጊዜ መፍታት እንደሚያስችላት ነው የተገለጸው።

በርሊን አዳዲስ ሰራተኞችን ለመቅጠር የተለያዩ መስፈርቶችን ያወጣች ሲሆን፥ የስራ ዘርፎቹንም ይፋ አድርጋለች።
ሰሞኑን የጀርመኑ መራሄ-መንግስት ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ።
ሚያዝያ 23/2015 ዓ.ም
=======≠========

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የመከላከያ ሠራዊት በአማራ ክልል ቆቦ ወረዳ ኦፕሬሽን መጀመሩ ተገለጸ‼️
አርብ ሚያዚያ 20/2015 ማምሻውን ጀምሮ መከላከያ ሠራዊት በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ወረዳ በነዋሪዎች ላይ የቤት ለቤት ፍተሻ እያደረገ መሆኑን አዲስ ማለዳ ከሥፍራው ነዋሪዎች አረጋግጣለች፡፡

<<የአማራ ክልል ብልፅግና ጽሕት ቤት ኃላፊ ግርማ የሺጥላን የገደላችሁት እናንተ ናችሁ።>> በማለት ፋኖዎች እየተሳደዱ እና ቤተሰቦቻቸውም እየታሰሩ መሆኑን ነው ነዋሪዎች የገለጹት፡፡

በዚህም፤ ከአርብ ዕለት ጀምሮ እስከ ትናንት ምሽት ድረስ ከቆቦ ወደ አላማጣም ይሁን ወደ ወልድያ ለመሄድ መንገድ ተዘግቶ እንደነበር የገለጹት ነዋሪዎቹ፤ ከቀናት በፊት ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በሽምግልና ታርቀው ወደማህበረሰቡ የተቀላቀሉ የፋኖ አባላትም እየተሳደዱ ነው ብለዋል፡፡

ከአስር በላይ የፋኖ አባላት ቤተሰቦች ለእስር እንደተዳረጉም ጠቅሰው፣ ሌሊት በሚደረገው የቤት ለቤት ፍተሻ በተለይ ሴቶች እየተሳቀቁ እንደሆነ ተናግረዋል።

<<ሰውዬው የተገደሉት ሰሜን ሸዋ ሆኖ ሳለ ገዳዮቹ ቆቦ ውስጥ ናቸው ብሎ ማህበረሰቡን ሰላም መንሳት ተገቢ አይደለም።>> ያሉት ነዋሪዎቹ እየተደረገ ያለው ነገር ህዝብን ለአመጽ ከማነሳሳት ውጭ ፋይዳ የለውም ብለዋል፡፡

<<እንደ ሸኔ ያሉ ታጣቂ ኃይሎች ዜጎችን ከቀያቸው እያፈናቀሉ እና መንገድ ላይ እያገቱ ብዙ ጥፋት የሚያደርሱ ኃይሎችን ችላ በማለት፤ ምንም ባልተፈጠረበት ቆቦ ላይ ይህን ሁሉ ግርግር መፍጠር የመንግሥት አካሄድ ፍትሃዊነት የጎደለው አገዛዝ መሆኑን በተግባር የሚያሳይ ነው።>> ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

በዚህ ወቅት ተዘግተው የነበሩ መንገዶች ተከፍተው መደበኛ እንቅስቃሴ የቀጠለ ቢሆንም ማህበረሰቡ አሁንም መደናገጥና ስጋት ላይ ነው ተብሏል።

ከአማራ ክልል ብልፅግና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ግርማ የሺጥላ መገደል በኋላ፤ የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በአማራ ክልል ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን በማፍረስ ክልላዊ ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር በሚጥሩ ጽንፈኛ ኃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰድኩኝ ነው ሲል ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ግብረ ኃይሉ ‹‹ፅንፈኛ ኃይሎች›› ብሎ የሚጠራቸው አካላት የአማራ ሕዝብ የልማትና የሰላም ተጠቃሚ እንዳይሆንና የተረጋጋ ሕይወት እንዳይኖረው እንዲሁም በመንግሥት የሚወሰኑ ውሳኔዎች እንዳይተገበሩ እንቅፋት ሲፈጥሩ መቆየታቸን ነው የገለጸው፡፡

ይሁን እንጂ በተለይ ግብረ ኃይሉ በክልሉ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ካሳወቀ በኋላ በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ግራ መጋባት መፈጠሩን አዲስ ማለዳ ተገንዝባለች፡፡

ብዙዎች <<ምን እየተካሄደ ነው>> የሚል ጥያቄ እያነሱ ሲሆን፤ ጽንፈኛ ተብለው የሚጠሩ አካላትም እነማን እንደሆኑ መንግሥት በግልጽ እንዲያሳውቅ ጠይቀዋል፡፡

መንግሥት ሰበብ ፈልጎ የፋኖ አባላትን ለመምታት እንዲሁም ክልሉን የቀውስ ማዕከል ለማድረግ የታሰበ ተገቢ ያልሆነ አካሄድ ነው የሚሉም በርካታ ቅሬታዎች እየተነሱ ይገኛል፡፡
(አዲስ ማለዳ

Читать полностью…

Ethio 360 Media

Once ብአዴን always ብአዴን፤

ብአዴኖች በወያኔ ግዜ የሚያስተዳድሩትን ሕዝብ የትኽምከት ኃይል እያሉ ለ30 ዓመታት ሲመቱና ሲያስመቱ ኖሩ።

አሁን በኦሮሙማው ኦሕዴድ ግዜ ደግሞ ጌቶቻቸው የሚሉትን እየተከተሉ ጽንፈኛ ኃይል በማለት አማራውን ፈርጀው አሳልፈው ሰጥተዋል::

ብአዴናዊ አስተሳሰብ በጊዜ ሒደት የማይቀየር የሎሌነት መንፈስ ነው። ድሮ የመለስን ንግግር እንደ በቀቀን ይደግሙ ነበር አሁን የኮ/ል ዐብይንና የሽመልስ አብዲሳን አፍ እየተከተሉ ማስተጋባት። ብአዴን ሁሌም ብአዴን ነው።

(ሙሉቀን ተስፋዉ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ያልታወቁ ሀይሎች…!

"…በኦሮሚያ ሲሆን ያውም በወለጋ ገዳዮች "ስማቸው ያልታወቁ ሀይሎች" የሚል ነው። በቀን በጠራራ ፀሐይ እየደፉ፣ ሺዎችን እየጨፈጨፉ ስማቸው ያልታወቁ ኃይሎች ነው።

"…ዐማራ ክልል ሲሆን ገዳዮቹ 😂😂😂 ከመግደላቸው በፊት ሁላ ስም ወጥቶላቸው ሊነገረን ይችላል። ነውጠኛ ጽንፈኞች አላለም አቢይ አህመድ።

"…ፖሊስ ምርመራ ማድረግ እንኳ አይችልም። ገዳዩ አቢይ ቸኮለ። ቸኮለና ተበጠረቀ። ዳይሬክተሩና ደራሲው ፊልሙን አስበላው።

"…አሁን ያልታወቁት ሀይሎች ታንዛኒያ ከአቢይ ጋር በመደራደር ላይ ናቸው። ነውጠኞቹ ጽንፈኞች ደግሞ ድሮን እየተዘጋጀላቸው፣ ታንክ እያሟቀላቸው፣ የኦነግ ሠራዊት በመከላከያ ካባ ሊርመሰመስባቸው ነው።

"…ሞክራት… ! ለወሬ ነጋሪ አይተርፈውም ዐማራ። ብአዴናውያን ተጠንቀቁ። ከአቢይ አሕመድ ጋር እንዳትጨረገዱ።

"…ያልታወቁ ሀይሎች ምደረ ጠንቋሊ ሁላ ደኅና አያሳድራችሁ…!


(ዘመድኩን በቀለ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ሶዶ ጉራጌ‼️

ኦነግ ሸኔ በሶዶ ጉራጌ ጉዳት እያደረሰ ነው።


ሰሞኑ በስዶ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌያት በተለይም ጥያና ሚካኤል ሰመሮ ቀበሌ ታዋቂው አርሶ አደር ታሌ ሲማ እና ሌሎችንም የአካባቢ ነዋሪዎች በኦነግ ሸኔ ታፍነው የት እንዳደረሷቸው አይታወቅም።

ሚያዝያ 20/2015 ዓ.ም
=======≠========

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ትላንት ከ አማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ የነበረ የኛ ባስ በአሮምያ ክልል መተሀራ አካባቢ ሙሉ ሰው እንደያዘ በታጣቂዎች ታግቶ ተወስዷል።

ሚያዝያ 20/2015 ዓ.ም
=======≠========

Читать полностью…

Ethio 360 Media

"…የዛንዚባሩ "ለራስ ከራስ ጋር ድርድሩ"

በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው ተብሏል። ኦነግ ሸኔ በአንዴ እሺ አለ እንዳይባል ጥቂት ይግደረደራል። መሳሪያውንም ያወርዳል። ከዚያ ወደ መከላከያ ይገባል።

ከዚያ ብርሀኑ ጁላ ዐማራን መሣሪያውን ያስፈታል፣ ፋኖና የዐማራ ልዩ ኃይልም ትጥቅ አውረደው ወደ መከላከያ ይገባሉ። ከዚያ ኦነግ ሸኔ አዛዥ በሆነበት መከላከያ ዐማራን ከጀርባው ይረመርማል:: ስሌታቸዉ ይሄ ነዉ

ከኦነግ ጋር የሚደረገዉ ድርድር የዉሸት ድራማ ነዉ የአማራን ትጥቅ ለማስፈታት ብቻ የፈጠሩት ነዉ::

መንግስት ኦነግ ትጥቅ ፈቷል የቀረዉ የአማራ ልዩ ሀይል እና ፋኖ ነዉ ቢል እንዳትሰማዉ ቁማር ነዉ::

የሚያዋጣህ ትጥቅህን ጠበቅ አድርገህ መያዝ ብቻ ነዉ:: ነፃ የሚያወጣህ ነፍጥህ ብቻ ነዉ::

ነቃ በል ተናበብ አማራ!!!

Читать полностью…
Subscribe to a channel