ethio360media | Unsorted

Telegram-канал ethio360media - Ethio 360 Media

37564

ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር !!!

Subscribe to a channel

Ethio 360 Media

ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች፤ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በአፋጣኝ እንዲፈታ ጥሪ አቀረበ‼

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን በአፋጣኝ እንዲፈቱ ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ሲፒጄ (CPJ) ጥሪ አቀረበ። መቀመጫውን በአሜሪካ ኒውዮርክ ያደረገው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ትላንት አርብ ባወጣው መግለጫ “በአገር ውስጥና በውጪ ያሉ የፕሬስ አባላትን ማዋከብ እንዲያቆሙ” ለኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጥሪ አስተላልፏል።

“የአማራ ድምጽ” የተባለው በዩቲዩብ የሚተላለፍ የግል መገናኛ ብዙኃን መስራች እና አርታኢ የሆነው ጎበዜ፤ ሚያዝያ 28፤ 2015 በጅቡቲ በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ይፋ እንዳደረጉ ሲፒጄ በመግለጫው ጠቅሷል። የጋዜጠኛው ጠበቃ አዲሱ አልማው፤ ጎበዜ ከጅቡቲ ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፎ መሰጠቱን እና በአዲስ አበባ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ በእስር ላይ እንደሚገኝ ለሲፒጄ ተናግረዋል።

“የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን ዝም ለማሰኘት እና ለመበቀል በድፍረት ድንበር ተሻግረዋል” ያሉት ከሰሃራ በረሃ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገራት የሲፒጄ ተወካይ ሙቶኪ ሙሞ፤ እስሩ “በስደት ደህንነት ፈልገው ከሀገራቸው በሄዱ ጋዜጠኞች ላይ ስጋት ይፈጥራል” ብለዋል። “ጎበዜ ያለመዘግየት ሊፈታ ይገባል” ያሉት የሲፒጄ ተወካይ የኢትዮጵያ እና የጅቡቲ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ስለዋለበት እና ተላልፎ ስለተሰጠበት ሁኔታ ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

እዉነታዉ ይሄ ነዉ‼

ጌታቸው ረዳ ሰሞኑን በመቀሌ የነበረው ስብሰባ ትናንት ማብቃቱን ተከትሎ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በዚህ ማብራሪያቸው ወልቃይት# እና ራያን# በስምምነቱ መሰረት በቅርቡ እንደሚረከቡ በተለይ በራያ አካባቢ የነበረው የአማራ ሀይል መውጣቱን እና በቅርቡ ፖለቲካዊ እና አስተዳደራዊ መዋቅር እንደሚዘረጋ በማጠቃለያው ላይ መናገራቸው ተሰምቷል። ይሄ አንዱ የመልሶ ማቋቋም እቅድ ነው ብለዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ምስራቅ አማራ ፋኖ‼️


የፀጥት ዘርፍ ሃላፊዎች እና የሚመለከታቸው አመራሮች ሰሞኑን በምስራቅ አማራ ፋኖ ላይ የተደረገው ኦፕሬሽን ለምን እንዳልተሳካ ግምገማ አካሂደዋል።

በዚህም ህዝቡ እና ወጣቱ ከፋኖ ጎን በመሆኑ፣የመንግሥት እና የክልሉ የፀጥታ አካላት ስራቸውን በአግባቡ አለመስራታቸው እና በማህበራዊ ሚዲያ የመረጃ የበላይነት በመወሰዱ ነው" የሚሉ ግምገማዎችን አስቀምጠዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ሰሞኑን መከላከያ ከፋኖ መሳፍንት ተስፉ ጋር በተደረገ ውይይት እና ሽምግልና መሰረት መከላከያ ሰራዊት ከበባ ማድረጉን ትቶ ይወጣል ባሉት መሰረት በዚህም ሀርብበር ኬላ የነበረው መከላከያ ሰራዊት ትናንት ለቆ ወጥቷል።

በዚህ ስምምነት ላይ እነ መሳፍንት ተስፉ የቡድን መሳሪያቸውን በገንዘብ ልዋጭ ለመንግሥት ሊያስረክቡ ከስምምነት ተደርሷል እየተባለ የሚወራው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

መምህር ያረጋል አበጋዝ እንደጻፉት

#Ethiopia | ''የአሁኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባዔ፣ በእግዚአብሔርም በሕዝብም በታሪክም ፊት የሚያስመሰግንና ተጠቃሽ የሆነ መልካም ሥራ (አለዚያም ደግሞ [አያደድርገውና] የማይሽር ተወቃሽ ጠባሳ ታሪክ) የምትጽፉበት ወቅት ነው፡፡''

ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ዘመኑን የዋጀ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ለመስጠት ያላትን ሁለንተናዊ ዐቅም በእጅጉ ሊያሳልጥ የሚችል ጥናት ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ከመቅረቡ በፊት ሚያዚያ መጨረሻ ላይ ቀርቦ ነበር፡፡ ይህ የስትራቴጂክ (መሪ ዕቅድ) ጥናት በዘርፉ አሉ በሚባሉ ከፍተኛ የምጣኔ ሀብትና የስልታዊ ዐቅድ ባለሞያዎች እንዲሁም በቤ/ክ ሊቃውንት ብዙ ተደክሞበት የተሠራ ነው፡፡

ይህ የተዘጋጀው የመንፈሳዊ ልማት እና የማኅበራዊ ልማት ዕቅድ ይኸንኑ አገልግሎት በሥራ ላይ ለማዋል ከሚያስፈልገው የአደረጃጀት አወቃቀር ጋር የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ አብርሃም እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ባሉበት ቀርቦ ነበር፡፡ ሆኖም እነዚህ ብፁዓን አባቶች የቀረበውን የመንፈሳዊና ማኅበራዊ ልማት ዕቅድ ቢያመሰግኑትም የሚተገበርበትን የመዋቅር (አሠራር) ጉዳይ ግን እንደማይቀበሉት ገልጸዋል፡፡ ዕቅድ የሚተገበርበት መንገድ ከሌለ ጥናት ብቻውን ምን ፋይዳ አለው? በዚህ ሁኔታ ጥናቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ የመቅረብ ዕድሉ ሩቅ ሊሆን ይችላል ማለት ነው፡፡

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ልደቱ አያሌው‼️‼️


አቶ ልደቱ አያሌው ወደ ኢትዮጵያ በመመለስና እጃቸውን በሽብርተኝነት ለከሳሳቸው መንግስት እጃቸውን በመስጠት በፍትህ አደባባይ እንደሚሟገቱ አሳወቁ።
"ከአገዛዙ አፈና፣ እስርና ግድያ ሸሽቶ በማምለጥ የሚመጣ መፍትሄ የለም። ትግላችን ሰላማዊና ህጋዊ እስከሆነ ድረስ በገፍ እየታሰርንና እየሞትን አገዛዙ በሀይልና በአፈና ሊያሸንፈን እንደማይችል ተስፋ ልናስቆርጠው ይገባል። በዚህ መጠን ዋጋ ለመክፈል ካልቆረጥን በስተቀር የአገርና የህዝብ ህልውና ከጥፋት ሊድን አይችልምና።

ይህንን በለጋ የልጅነት ዘመኔ ለራሴ የገባሁትን የትግል ቃል-ኪዳንና የምታመንለትን የሰላማዊነትና ህጋዊነት መርህ መሰረት በማድረግ ወደ አገሬ ለመመለስና የዶ/ር ዐቢይን የፈጠራ የአሸባሪነት ክስ እንደተለመደው በፍትህ አደባባይ ለመጋፈጥ ወስኛለሁ።

ስለሆነም በታሰርኩ ቁጥር ከእኔ በላይ ስቃዬን የምትሰቃዩ ቤተ-ዘመዶቸ፣ ጓደኞቸ፣ የሃሳብ ደጋፊዎቸና የትግል አጋሮቸ ይህንን ውሳኔዬን የሞኝነት፣ የአጉል ጀብደኝነት ወይም የመንግስትን የጭካኔ ደረጃ በአግባቡ ያለመረዳት ድክመት አድርጋችሁ እንዳታዩብኝና ያልተገባ ጫና እንዳትፈጥሩብኝ በዚህ አጋጣሚ በአክብሮት እማፀናለሁ። ይህንን ውሳኔ በሚገባ አስቤበትና ከልቤ አምኘበት የወሰንኩት ስለሆነ በሞራል ልታግዙኝ ይገባል እንጂ ልታዝኑልኝም ሆነ ልታዝኑብኝ አይገባም እላለሁ። "

Читать полностью…

Ethio 360 Media

"ኢንተርፖል ሰዎችን የማሰርም ሆነ አሳልፎ የመስጠት ስልጣን የለውም"
የአማራ ማህበር በአሜሪካ፤ "የጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን ጉዳይ በተመለከተ Interpolን በማነጋገር የመንግሥት የሰላም እና ደህንነት ጥምር ግብረ ሃይል ጎበዜን ለመያዝ ኢንተርፖል ተባባሪ ነበር ብሎ ያሰራጨው ዜና ከእውነት የራቀ መሆኑን ለማረጋገጥ መቻሉን" በትዊተር ገጹ ላይ አስታውቋል። መንግስት ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን በኢንተርፖል ትብብር ከጅቡቲ ይዞ ማሰሩን መግለጹ አይዘነጋም።
ጉዳዩን ያጣራው በአሜሪካ የአማራ ማህበር ከተቋሙ ጋር ያደረጉት የኢሜል ልውውጥ ከላይ ተቀምጧል።
=======
After contacting INTERPOL HQ regarding the case of journalist Gobeze Sisay, Amhara Association in America(AAA)has been able to verify that the government peace and security joint taskforce's claim of collaborating with Interpol to apprehend Gobeze in Djibouti is untrue.

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ቴዎድሮስ ካሳሁን ( Teddy Afro ) አዲስ አልበም ሊያወጣ ነው

አልበሙ በሰዋሰው መተግበሪያ በኩል እንደሚወጣ ተነግሯል። አዲሱ አልበም "ኢትዮሪካ" የሚል መጠሪያ እንደተሰጠውም ታውቋል::

Читать полностью…

Ethio 360 Media

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…የዐማራ ክልልን በተመለከተ ተደጋግሞ የሚነሣ ነገር አለ። ያም ምንድነው ያልን እንደሆነ "የዐማራ ክልል መሪዎች ለምንድነው በሚመሩት ሕዝብ ላይ ጨካኝ፣ አረመኔ የሆኑት? ለምንድነው እንደ ኦሮሞ፣ እንደ ትግሬና ደቡብ ወንድሞቻቸው ቢያንስ ከሌላ ነገድ ተወልደውም እንኳ ቢሆን መሪ ሆነው ለተሾሙበት ለዐማራ ነገድ ጥብቅና የማይቆሙት? ለሰላሙ፣ ዲሞክራሲና ለልማቱ የማይተጉት? ለምንድነው ሌሎቹ ለሚመሩት ሕዝብ ሽንጣቸውን ገትረው እንደሚሟሟቱት፣ እንደሚሟገቱት የዐማራዎቹም የማይሟገቱት ብለው ሲጠይቁ ይደመጣል። ለዚህ ጉዳይ መልስ ለመስጠት የበኩሌን ሚጢጢ ሃሳብ ለመሸጥ ነው በርዕሰ አንቀጽ የመጣሁት።

"…እውነት ነው ለምሳሌ አቢይ አህመድ የወሎ ዐማራ ነው ኦሮሞነትን በኦሮሞ ምድር ላይ በመወለዱ እና ኦሮሚኛ ቋንቋ በመናገሩ ብቻ ኦሮሞነትን የተቀበለ የዐማራ ሰው ነው። መለስ ዜናዊ ኤርትግ፣ ስብሐት ነጋ ኤርትግ፣ ቴዎድሮስ አድሓኖም፣ ኬሪያ ኢብራሂም ወዘተ ኤርትግ ናቸው። ገብሩ አሥራት፣ ጌታቸው ረዳ ወዘተ ዐማትግ ናቸው። ነገር ግን እነዚህ ግለሰቦች በተሾሙበት ክልል ለተሾሙበት ሕዝብ እጅግ ሲበዛ ታማኝ ደማቸውን የሚሰጡ፣ የሰጡም እስከሞትም የታመኑ ናቸው።

"…ወደ ዐማራ ክልል ስንመጣ ግን የተለየ ጠባይ፣ የተለየ ማንነት፣ የተለየ ስብዕና ነው የምናገኘው። ክልሉ በራሱ እንዲቆም አይፈለግም። ክልሉ ውስጥ የሚኖረው የዐማራ ነገድ በክልሉ የሥልጣን እርከን ስፍራም የለው። የክልሉ የዐማራ አመራሮች ቀደም ሲል በሕወሓት በጥንቃቄ ተመርጠው የተፈጠሩ፣ የተሠሩ ናቸው። ብልፅግናም ያንኑ የህወሓትን ፖሊሲ ነው ያስቀጠለው። ሕዝባቸውን የሚፀየፉ፣ በመረረ ጣላቻም የተሞሉ፣ ሊበቀሉት የሚፈልጉትን ሕዝብ የሚመሩ ናቸው በወረንጦ ተለቅመው እንዲመሩት የሚደረጉት። ምሳሌም እናንሳ ብዙዎች እንደሚሉት፦

"…አገኘሁ ተሻገር (የቅማንት ዐማራ ማንነት ያለው) ሰካራም በትግሬ የተመረጠ፣ በመለስዜናዊ በበረከት ስምኦን የተመለመለ ነው ይሉታል። ተመስገን ጥሩነህ፣ ሰማ ጥሩነህ፣ ኢንጂነር ሀብታሙ፣ ይልቃል ከፍአለ የጎጃም አገው ሸንጎ አባላት ሲሆኑ ጄነራል አበባው ታደሰ ደግሞ በአባቱ የሀውዜን ትግሬና በእናቱ የዋግኽምራ አገው ሸንጎ አባል ነው ይሉታል። ደመቀ መኮንን ምንጩ የባሌ ኦሮሞ ሲሆን ወሎ ተወልዶ በ77 ድርቅ ቤተሰቡ ቻግኒ ጎጃም ያደገ ነው ይባላል። መለስ ዜናዊና በረከት ስምኦን እጅግ የደከሙበት የእንግሊዝ የስለላ ድርጅት ከቦታው ንቅንቅ እንዲል የማይፈልገው ሰው ነው ይሉታል። እስላም ሆኖ ያውም ፅንፈኛ ዐማራ ጠል እስላም። እነዚህ ሰዎች ሙሉ ዐማራ ያለመሆናቸው ችግር የለውም ምክንያቱም ሌሎቹም እንዲሁ ናቸውና። በኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ንፁሕ ሌላ ዘር ያልተቀላቀለብኝ ነኝ የሚል የለም። ሆኖም ግን ሌሎቹ ለተሾሙበት ክልል ሕዝብ ሟች ሲሆኑ እነዚህ ለምን ገዳይ ሆኑ? ነው ጥያቄው።

"…እነዚህ የዐማራ ሕዝብ ገዢዎች የራሳቸውን የሆነ ወሳኝ ኔትወርክ ፈጥረውም ነው ዐማራውን ቀፍድደው የያዙት። ከባዱ ነገር ይሄን ኔትወርክ ማፈራረሱ ላይ ነው። የዞን፣ የወረዳ፣ በቀበሌ ስምሪት፣ በፖሊስ ተቋማት፣ በተለይ ደግሞ በዞንና በወረዳ ወሳኙ ስፍራ ከዚያም ወረድ ሲል በቀበሌ በሚገኙ ማዘዣ ጣቢያዎች፣ ከፍ ሲል በልዩ ኃይል እና በአድማ ብተና፣ በዞን፣ በወረዳና በቀበሌ ካቢኔ ውስጥ በቀጥታ የመሳተፍ እና የማዘዙን ሥልጣን የተቆጣጠሩት እነዚህ ኃይሎች ናቸው። አሁን ከቀበሌ እስከ ክልል ወሳኙን የዐማራ የሥልጣን እርከን በብዛት እንዲቆጣጠሩ የተደረጉት እነዚህ በዐማራ ጥላቻ ያበዱ፣ ዐማራ ማንነት እንዲጠፋ፣ ክልሉም ፍርስርሱ እንዲወጣ በሚተጉ በደም ማንነታቸው የቅማንት፣ የአገው ሸንጎ፣ የከሚሴ ኦሮሞ እና የአርጎባ ተወላጅ የሆኑ ግለሰቦች ናቸው። እነዚህ አካላት በአሁኑ ጊዜ በክልሉ የፀጥታና የፖሊስ ተቋማት ውስጥ ወሳኞቹ አካላት ናቸው።

"…እንደ ድንገት በእነዚህ ተቋማት ውስጥ የገቡ ዐማሮች ከተገኙ በፍጥነት ነው እርምጃ የሚወሰድባቸው። ሳይታወቁ፣ የደም ማንነታቸው ሳይጣራ ተሽሎክሉከው አልፈው ሥልጣን የሚይዙ ካሉም በዲሞክራትነታቸው፣ በእኩልነት፣ በፍትሕ አቀንቃኝነታቸው ወዲያው ይታወቃሉ። ዐማራ ክልል ላይ ሆኖ ስለክልሉ መበደል፣ መጨቆን፣ ስለ ሕዝቡ መፈናቀል፣ መሰደድ፣ መገረፍ፣ መታረድ መናገር የጀምር ሰው ያኔ ዐማራ መሆኑ ይታወቃል። ዶር አምባቸው፣ ምግባሩ ከበደ፣ አቶ እዘዝ ዋሴ፣ ጄነራል አሳምነው ጽጌ ሰለባ የሆኑት በእነዚሁ የዐማራ ማንነት በሌላቸው ቀድሞ በህወሓትና ኋላ በአዲሱ ባርያ አሳዳሪያቸው በኦህዴድ ኦነግ አማካኝነት በተሾሙ ፀረ ዐማራ ኃይሎች ነው።

"…ለዚህ ነው አገኘሁ ተሻገር እንደፈለገ ሰክሮ፣ ሰርቆ፣ ቀባጥሮ የማይነካው። ገና ክልሉ ያለቅጥ ሰፍቷል ተብሎ 8 ቦታ ሊሸነሽኑት መሆኑን ስትሰሙ ደግሞ ጉድ ትላላችሁ። ሲጠቃለል ዐማራ ትግሉን ከባድ የሚያደርግበት ይሄ ነው። ዐማራን የሚያሸንፈውም፣ የሚፈታተነውም ለዘመናት በተሠራበት መዋቅራዊ አስተዳደራዊ ሴራ ምክንያት ነው። ዐማራ ትግሉን ፈታኝ የሚያደርግበት ይሄን የሴራ መስመር በጸሎትም፣ በዱአም፣ በጉልበትም ቢሆን በጥበብ በጣጥሶ የራሱን የጸጥታ መዋቅር መዘርጋት ሲችል ብቻ ነው። ሌላው ቢቀር ፓርላማ ተመርጠው የሚገቡት እንኳ ለምሳሌ እንደ ዶር ሂሩት ካሰው አይነቷ በግልፅ "ዐማራ ጨቋኝ ነበረ" ብላ ዐማራውን ምረጠኝ ብላ የምረጡኝ ቅስቀሳም አድርጋ ጨቋኙ ዐማራም በደቡብ ጎንደር መርጧት የአበባ ምንጣፍ ተነጥፎላት ጨቋኙን ዐማራ ወክላ ፓርላማ የገባች ሴት ናት። ፓርላማ ገብተው ስለ ዐማራ መጨቆን የሚተነፍስ ሰው ካገኛችሁ እሱ በደም ማንነቱ ዐማራ ነው። ዝም፣ ጭጭ፣ የሚሉት በሙሉ ግን በጥንቃቄ ተመርጠው የዐማራን መጥፋት፣ የክልሉን መፍረስ፣ መድቀቅ፣ መበተን የሚፈልጉ አማርኛ ተናጋሪ ኃይላት ናቸው የሚሉ መተርጉማን አሉ።

"…እንግዲህ ይሄን ዐማሮች ሲያዩት ከባድ ነገር ግን ደግሞ ወስኖ ካመረረ፣ ጥርሱንም ነክሶ ቆርጦ ከታገለ ኢምንት የሆነ ሴራ ለመበጣጠስ ቀናትም አይፈጅበትም። በአንድ ጎን እያመረተ፣ ሌላውንም እየመከተ በሌላ ጎን ደግሞ ውስጡን እያጠራ መታገል ከጀመረ ድል አፍንጫው ስር ነው የምትንከላወሰው። ቢያንስ እነዚህ ፀረ ዐማራ የዐማራ ሹመኞች እንደ ትግሬና ኦሮሞ ሹመኞች ከነገዱ ባይወለዱ እንኳ እንደእነሱ ለሚመሩት ሕዝብ እንዲጨነቁ ማድረግ ተገቢ ነው። ሙፈሪያት ካሚል እንኳ ግማሽ የጅማ ኦሮሞ ሆና ለስልጤ ደሟን የምትሰጥ መሆኗን እነ ሂሩት ካሰው ቢረዱ መልካም ነው እላለሁ። እኔ የምጽፈው ጦማር ይመራል ነገር ግን ምንም ማድረግ አልችልም። ፈርዶብኝ ነው። እኔ አይስክሬም ብቻ አይደለም የምሸጠው። ኮሶ፣ እንቆቆ፣ ግራዋም፣ እሬትም እሸጣለው። ለወያኔና ለኦነግ ሰዎች ደግሞ በረኪናና የአይጥ መርዝ በስፋት አቀርባለሁ። 1 ሜትር ገመድም በተመጣጣኝ ዋጋ አቀርብላቸዋለሁ። ታነቅ…

"…ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ… አሸበርቲው።

(ዘመድኩን በቀለ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

"እውነት እና ንጋት እያደር ይጠራል"

-ከአቶ ግርማ የሺጥላ ሞት ጋር ተያይዞ የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ሰሞኑን የለቀቀው እና የነ ምሬ ወዳጆ ነው የተባለው የስልክ ምልልስ ውሸት መሆኑ በምርመራ ተረጋገጠ።
የስልክ ምልልሱ ውሸት መሆኑን ያረጋገጠው፤በዩናይትድስቴትስ ካሊፎርኒያ የሚገኘው እና "ዲጂ ፎረንሲክ ኤክፐርትስ" የተሰኘው ታዋቂው የኦዲዮና ቪዲዮ ምርመራ አገልግሎት ተቋም ነው።
እነሆ፦

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አብይ አህመድ የሸኔን ጦር በዚህ መልኩ እያደራጀ ነዉ:: ነቃ በል አማራ!!

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ዛሬ በደቡብ ወሎ ዞን ጃማ ደጎሎ ከትማ ጠዋት ላይ ህዝብ ለድጋፍ ሰልፍ አልወጣም ሲል ከገጠር ማዳበሪያ እንሰጣለን ብለው አስመጥተው  ሰልፍ እንዲያደርጉ አድርገዋቸዋል።
====================
አሳፋሪ መንግስት

Читать полностью…

Ethio 360 Media

መልእክቱ ለሁሉም እንዲደርስ ያድርጉ!!!

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አፋር‼️

መከላከያ የማረካቸውን የትግራይ ምርኮኞች ዛሬ ለሊት ወደ ሀገራቸው ሸኘ።

ዛሬ ለሊት 7 ስዓት ሐሙስ በግምት ከ60-70 በሚሆን አውቶብስ ተጭነው ከአዋሽ አርባ በሎጊያ አፍዴራ አድርገው ወደ መቀሌ ተሸኝተዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ በአማራ ክልል እየተደረገ ያለው የህግ ማስከበር ዘመቻ በንፁሃን ላይ ሞት እንዱሁም በንብረት ላይ ውድመት ማስከተሉን ገለፁ። ኮሚሽነሩ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተልኩት ነው ብለዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የግድያ ዜና…!

"…የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 08 ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አለባቸው አሞኘ ነው ዋለ የተባለ የብአዴን አባል በዛሬው ዕለት በቢሮው ውስጥ ባለ ጉዳይ እያስተናገደ ባለበት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 /33 ክላስተር የማኅበረስብ አቀፍ ፓሊስ ኦፊሰር በሆነው ብራኦል በሚባል ኦሮሞ ፓሊስ መገደሉ ተነግሯል። ገዳዩ ቀብረር ብሎ ነፍጠኛን ማጽዳት ጀምረናል ማለቱም ተሰምቷል። ወዳጄ አብዮት ልጇን ትበላለች ማለት እኮ ይሄው ነው።

"…በተለይ ብአዴን ወይ ከሕዝቡ አልሆነ፣ ወይ መንግሥት አያድነው እንዲሁ ተራ በተራ እየተለቀመ ይበላል። የሚያሳዝነው ነገር እንደ ትግሬና ኦሮሞ የሚያዝንላቸው፣ የሚያለቅስላቸው ወገን እንኳ የለም። አዛኜን ብአዴንነት ማለት መረገም ነው።

"…ሌሎች ደሳስ የማይሉ ዜናዎችም አሉ። ግን ይቅር። ይቆየን።

(ዘመድኩን በቀለ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ሰበር መረጃ
==========

አስር በመቶ የሚሆነዉ ካምፕ ከገባዉ የአማራ ልዩ ሀይል በጊዜያዊነት ካረፈበት ካምፕ ከነ ትጥቁ መሰወር መጀመሩ ተነገረ::

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ኦሮሚያ‼️


ሙስና ኢንቨስተሮችን እያስወጣ ነው❗
በኦሮሚያ ክልል በሙስና ምክንያት በርካታ የውጪ ባለሃብቶች ጥለው እየወጡ ነው። ለዚህ ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ በየመስሪያ ቤቱ ህጋዊ ያልሆነ ክፍያ በጊዜው እየተጠየቁ በመሆኑ በመማረራቸው ነው ተብሏል።
ለምሳሌ በዱከም ኢንደስትሪ ፓርክ ውስጥ ጉዳይ ለማስፈፀም ሁል ጊዜ ገንዘብ እንጠየቃለን፣ በፓርኩ ዝርፊያ ይፈፀማል። በዚህ የተማረሩ 51 ባለሀብቶች ለቀው ወደ ኡጋንዳ መሰደዳቸውን የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ከላይ የቀጠለ
==========

ከዚሁም ጋር የቤተ ክርስቲያን ችግሮችን በየዘርፉ እያጠና ዘላቂ መፍትሔዎች ላይ እንዲሠራ በቅርብ ጊዜ የተቋቋመውና በጣም ብዙ ሥራዎችን እየሠራ ያለው ግብረ ኃይልም በአዎንታ እንደማይታይና ሥራዎቹ የሚተገበሩ የመሆን ዕድላቸው ሩቅ መሆኑን በግልጽ እየሰማን ነው፡፡ ከዚህ የተነሣም አሁን ባለው የቤተ ክህነት አስተዳደር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መዋቅራዊ አሠራር በተለያዩ ውስጣዊና ውጫዊ ምክንያቶች የተነሣ ከገባበት የተወሳሰበ ችግር የመውጣትና ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት የሚፈጽም አካል የመሆን ዕድል እንደማይኖረው ቁርጡን አሳውቀዋል (አሁን ባለው መዋቅር እስካሁን ያልቆረጠላቸው ካሉ ለማለት ነው እንጂ ብዙዎቻችንስ ቁርጣችንን ካወቅን ዘመናት ተቆጥረዋል)፡፡

በዚሁ የዘላቂ መፍትሔ ግብረ ኃይል ሥር ባለ አንድ ክፍል በጥሩ ጥናት ተዘጋጅቶ የቀረበው የኤጲስ ቆጶሳት አመራረጥ ሂደት ረቂቅ መመሪያንም በመልካም እንዳልተቀበሉት ተሰምቷል፡፡ በየዘርፉ ብዙ መሥራት የሚችሉ ልጆች እያሏት ግን ቤተ ክርስቲያኒቱ የእነርሱ ብቻ የግል ድርጅት በምትመስላቸው አካላት ምክንያት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ይህን ሁሉ ከባድ ዋጋ እየከፈለች የምትቀጥለው እስከ መቼ ይሆን? አሁን የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደራዊ መዋቅር ያለበት ሁኔታ የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በ1940ቹና 50ዎቹ የነበረችበትን የተመሰቃቀለ ሁኔታ የሚመስል ነው፡፡

በዚሁም ላይ በአሁኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ የኤጲስ ቆጶሳት አመራረጥ ሂደቱ የሚፈጸምበት መመሪያ አስቀድሞ ሳይጽድቅ ወደ ኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ የሚገባ ከሆነ፣ ቤተ ክርስቲያንን እጅግ በጣም ለከፋሰ አደጋ አሳልፈው መስጠታቸው ነው፡፡ በዚያውም ላይ ከሕገ ወጦቹ እናካትታለን የሚባል ከሆነ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኒቱን አንድነት ለማፍረስ በሚደረገው ክፉ ሥራ ላይ የስምምነት ፊርማ እንደ ማስቀመጥ ነው፡፡ በአጠቃላይ ያለው ሂደት መቃብሯን እንደ ሙሴ መቃብር መሰወር እንዳይሆን በእጅጉ ያስጨንቃል!

ክርስቶስን ብቻ የተሸከማችሁና እርሱን ብቻ የምታስቀድሙ እውነተኛ ብፁዓን አባቶቻችን ሆይ፤ የአሁኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባዔ፣ በእግዚአብሔርም በሕዝብም በታሪክም ፊት የሚያስመሰግንና ተጠቃሽ የሆነ መልካም ሥራ (አለዚያም ደግሞ [አያደድርገውና] የማይሽር ተወቃሽ ጠባሳ ታሪክ) የምትጽፉበት ወቅት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን እነ ቅዱስ አትናቴዎስን፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን፣ ቅዱስ ዲዮስቆሮስን፣ ቅዱስ ሳዊሮስ ዘንጾኪያን፣ . . . በእጅጉ የምትፈልግበት ወቅት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

ብፁዓን አባቶቻችን ሆይ፣ እኛ ልጆቻችሁ በዚህ ምልዐተ ጉባኤ ቤተ ክርስቲያን በላይዋ ላይ ያንዣበቡባትን ከባባድ ፈተናዎች፣ በጌታ መቃብር ላይ አይሁድ ጭነዋቸው እንደ ነበሩት ድንጋዮች ገለባብጣችሁ የቤተ ክርስቲያን አሠራር ከገባበት ውስብስብ ችግር የሚወጣበትን ትንሣኤ ታሳዩናላችሁ ብለን እንጠብቃለን!

Читать полностью…

Ethio 360 Media

መሸፋፈን አያስፈልግም!!!

1) እነ ሽመልስ አብዲሳ በቀጥተኛ ትዕዛዝ አዲስ አበባ ላይ እያመጡ እንደሚያስገቡት ካድሬ፣ ተሃድሶውንም፣ የሀሰት ነብዩንም፣ አባገዳውንም፣ ያኮረፉትን የኃይማኖት አባቶችንም አደራጅተው "ሲኖዶሱ ይሹምልን" ብለዋል። ሲኖዶሱ የሚሾመው በእምነቱ መሰረት እንጅ በፖለቲካ አይደለም ተብለዋል። ካልሆነ ሲኖዶሱ ይፈርሳል እያሉ እየዛቱ ነው። የመንፈስ ቅዱስን ተግባር የካድሬ ምደባ አድርገውታል።

2) ትህነግ በድሮን ሲቀጠቅጠው ከነበረው ጋር ታርቆ፣ የትግራይ አባቶች ግን ቤተ ክርስትያንን እየወቀሱ ነው። ጌታቸው ረዳ ከአብይ አህመድ ጋር እየዋለ የትግራይ አባቶች ሲኖዶሱን ለጦርነት ተጠያቂ አድርጓል። ይህ እየሆነ ያለው ትህነግ በቤተ ክርስትያን አባቶች በኩል ጩኸቱን ማስቀጠል ስለፈለገ ነው። የሚያሳዝነው ደግሞ እነዚህ አባቶች ከትግራይ ውጭ ጦርነት የነበረ አይመስላቸውም። መነኩሴ የደፈረው፣ ቄስ የገደለው ትህነግ ለእነሱ ቅዱስ ነው።

3) ባለፈው የተወገዘው ቡድን ጋር በነበረው ችግር የፌደራል መንግስት ባለስልጣናት በጌታቸው ረዳ እና ታደሰ ወረደ በኩል "የትግራይ አባቶችም የራሳቸውን ቤተ ክርስትያን ያቋቁሙና የ"ብሔር ብሔረሰብ ሲኖዶስን ያግዙ" ተብሎ ተሰርቶበታል። አሁን ሁለቱ ተገንጣይ ሲኖዶስ ሆነው ሹመትና ይቅርታ እየጠነቁ ነው።

4) በጣም በሚከረፋ ሁኔታ በእምነት ስም ጥላቻው ህዝብ ላይ ነው። "በአማርኛ ቋንቋ ስብከት"፣ "ከጎጃምና ጎንደር እየተመደቡ" እየተባለ በሀሰት ጥላቻ የሚነዛው ህዝብ ላይ ነው።

ቤተ ክርስቲያን ከባለፈው የከፉ አደጋ ተደቅኖባታል። የሲኖዶሱ መግለጫ በርካታ ህመምን አጭቆ የያዘ ነው። እውነታው ቤተ ክርስቲያን በግድ ተገንጣይ ሹሚ ተብላ ትዕዛዝ መጥቶባት፣ አይሆንም ብላለች። ችግሩ ግን ቀላል አይደለም።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ትላንት በነበረው ስብሰባ ኣቶ ጌታቸው ረዳ በመቐለ የህወሓት ኣመራር ጋር በነበረ ስብሰባ ከባድ ተቋውሞ ደረሳቸው። ከተሳታፊዎች መሃል "ኣንተ ኣትወክለንም ተላላኪ ነህ መሪዎቻችን ይመለሱልን" በማለት ኣስደንጋጭ ግርግር ተፈጥሯል ነበር

(ሰለሞን ወልደገሪማ)።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርሰቲያን ላይ ከባለፈው የከበደ ጥፋት ታቅዷል። የማያፍሩት ገዥዎች "መፈንቅለ መንግስት ልታደርግብን ነው።" በሚል ጠላት አድርገው ሲሰሩባት ቆይተዋል። የኦሮሚያ ብልፅግና እና ህወሓት ተቀናጅተው የጀመሩትን ሴራ በቅርቡ ወደ አደባባይ ሊያመጡት ነው።

የቤ ክርስትያን ጉዳይ በሰላም ተፈታ ከተባለ በኋላ "መንግስት" ከኦነግና ህወሓት ጋር ታርቆ አማራና ኦርቶዶክስ ላይ ጥቃት መፈፀምን ነው የያዘው። አማራውን ነጥዬ መትቻለሁ ያለው "መንግስት" በቅርብ ሳምንታት በሙሉ አቅሙ ቤተ ክርስቲያን ላይ ሊዞር ነው። እነ ሽመልስ አብዲሳ በክልል መዋቅራቸው እምነት የሌላቸውን ሰዎች ጭምር መልምለው ለተወገዘው ቡድን ሲያግዙ ሰንብተዋል። የፌደራል መንግስት ይህን ፕርጀክት እያገዘ ይገኛል።

(ጌታቸዉ ሽፈራዉ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ባለፈው ሳምንት ሚያዝያ 26 ከሰዓት የብልፅግና ከፍተኛ አመራሮች ዝግ ስብሰባ አድርገው ነበር‼️


በዚህ #ስብሰባ የአማራ ብልፅግና መሪዎች "የብልፅግና ወጥ ባልሆነ አቋም ምክንያት ለህዝባችን መረጃ ለመስጠት ተቸግረናል ማለታቸው ተሰምቷል። ለዚህም እንደ ዋና ሃሳብ ያነሱት የወልቃይት እና የራያ ጉዳይ ሲሆን አምና ሲባል የነበረው ሌላ አሁን እየተባለ ያለው ደግሞ ሌላ በመሆኑ ለህዝባችን በተጨባጭ ለመናገር የሚየስችል ወጥ መረጃ ባለመኖሩ ህዝብ በእኛ ላይ መተማመኛ እንዲያጣ አድርጎታል። ለዚህ መነሻው ብልፅግና ወጥ አቋሙን ባለማሳወቁ ነው፣የሰሞኑን የክልሉን የፀጥታ ሁኔታ እንኳን ብናይ ህዝቡ በወልቃይት እና #በራያ ጉዳይ መተማመኛ ነገር  ሳይኖር የቡድን ትጥቅ አናስረክብም ብለው የተፈጠረው ሁኔታ ይታወቃል። ይህ የሆነው ስለ ወልቃይት እና ራያ ብልፅግና በራሱ ወጥ መረጃ እና መተማመኛ የሚሆን ነገር ባለመስጠቱ ነው፣እኛ የምናምነው በቡድን ስራ ነው፣ወቅታዊ አሰላለፍን ተከትሎ መሄድ አያዋጣም፣ይሄ አካሄድ ዋጋ እያስከፈለን ነው"የሚል ቅሬታ በቀጥታ አቅርበዋል።
ምናልባት ሰሞኑን በአማራ ክልል በዞን እና በየከተሞች ስብስብ ሊጠራ ይችላል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አጣዬ# አከባቢ ዛሬም ይምለዋ ቀበሌ ላይ መከላከያው ከፋኖዎቹ ጋር የተኩስ ልውውጥ እያደረጉ ነው።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ለኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት ግልፅ ደብዳቤ ልኳል።

የሸገር ከተማ አስተዳደር የጀመረውን መስጂዶችን የማፍረስ ተግባሩን በአስቸኳይ እንዲያቆም፣ የፈረሱትንም በራሱ ወጪ መልሶ እንዲያሰራ፣ ህዝበ ሙስሊሙንም በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ እንዲሁም መስጂድና መድረሳ የማፍረስ ሂደቱ እንዲቆም ለሁሉም የኦሮሚያ አከባቢዎች መመሪያ እንዲሰጥ የተከበሩ ሼህ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በደብዳቤ ጠይቀዋል።

በደብዳቤው የተገለፁ እስካሁን የፈረሱ መስጂዶች:

1. በሸገር ከተማ ኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ዉንዴሳ ወረዳ ልዩ ስፍራ ቀርሳ በቀን 14/07/15

2. በሸገር ከተማ ሰበታ ክፍለ ከተማ መጉላ ቶውፊቅ መስጂድ 19/08/15

3. በሸገር ከተማ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ወረዳ ልዩ ስሙ አን ኢ ሳይት ሰላም መስጂድ በቀን 24/08/25

4. በሸገር ከተማ ቡራዩ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ አሸዋ ሜዳ በቀን 25/08/15 መፍረሳቸውና ጉዳዩ ከአቅሙ በላይ መሆኑን አሳውቋል።

Mohammed Abate

Читать полностью…

Ethio 360 Media

እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በመንግስት ሸኔ በሚል የሚጠራው ታጣቂ ቡድን በሞጆና በመቂ ከተሞች መሀል ጥቃት መፈጸሙንና አራት ተሽከርካሪዎችን ማቃጠሉን መረጃ ደርሶናል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ዛሬ ጠዋት ከነጋ 27/08/15 ከ 12 ሰዓት ጀምሮ በጉባላፍቶ ወረዳ ወዜት ሰንሰለታማ ተራሮች ላይ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ከፍተኛ ተኩስ በፋኖና በመከላከያ ተከፍቷል::

ወዜት ማለት በወልደያና በደላንታ መካከል የምትገኝ ገጠራማ ቀበሌ ናት።
====================

ድል ለተገፋዉ እና ለተጨቆነው‼

Читать полностью…

Ethio 360 Media

<<ውጥረቶች በሰላማዊ ውይይት እንጂ በጠመንጃ አፈሙዝ አይረግቡም!>> ኢዜማ



በአማራ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ሰላምና መረጋጋት እንደሌለና ዜጎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ እንዳልቻሉ መንግሥታዊ ሥራዎች ማከናወን አስቸጋሪ ሆኖ ኅብረተሰቡ ስጋት ውስጥ እንደወደቀ በአካባቢው ከሚገኙ ከተለያዩ ምንጮች መረጃዎች ደርሰውናል።

እንደሚታወቀው ክልሉ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተፈጠረው ጦርነት ገፈት ቀማሽ ነበር። ይህን ተከትሎም በድህረ ጦርነት ወቅት መሠራት ያለባቸው አያሌ ተግባራት ካለመከናወናቸው ጋር ተያይዞ የጦርነቱ ጠባሳ አሁንም የሚታይ ነው። ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላም ቢሆን በትግራይ እና በአማራ ክልል አካባቢ ላይ ያሉ የቅራኔ ቦታዎች "ምን አይነት መፍትሔ ያገኛሉ?" የሚለው ሐሳብ በክልሉ ላይ ከፍተኛ ውጥረት ፈጥሮ የተለያዩ መላ ምቶች እየተሰጡ ጉዳዩን እያጦዙት እንደሚገኝ የሚታወቅ ነው።

ይህ ውጥረት ባለበት ሁኔታ እንደ መልካም እርምጃ ሊወሰድና ድጋፍ ሊቸረው የሚገባውን የክልሎች ልዩ ኃይል ወደ ፌደራል ፀጥታ መዋቅር ውስጥ የመካተት ሂደት የተከናወነበት ደካማ መንገድ የፈጠረው ውዥንብር ኅብረተሰቡን ከፍተኛ ስጋትና ጥርጣሬ ውስጥ ጨምሮታል። ይባስ ብሎም በክልሉ ውስጥ በፋኖ አደረጃጀት ስም የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች እና በአማራ ብሔርተኝነት ፖለቲካ ውስጥ እጃቸውን የሚያስገቡ ኃይሎች ያገኙትን ቀዳዳ ተጠቅመው ያስተጋቡት አደገኛ ትርክት የሰው ሕይወት እስከ መቅጠፍ አድርሷል። በእነዚህ "ካልደፈረሰ አይጠራም" ባይ ኃይሎች አማካኝነትም ለሀገራቸው እና ሕዝባቸው መስዋዕትነት የከፈሉ እውነተኛ ፋኖዎች በጅምላ በፅንፈኝነት እንዲታዩ ተደርጓል። ትላንት ሀገር በጭንቅ ውስጥ ስታልፍ አብረው አጥንታቸውን ከከሰከሱ፣ ደማቸውን ካፈሰሱ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ጋርም ግጭቶች እንዲፈጥሩ ምክንያት እየሆኑ ይገኛሉ።

በአማራ ክልል ፖለቲካ ውስጥ እጃቸውን ሰድደው እንዳሻቸው የሚፈነጩ፣ ኃላፊነት የማይሰማቸው፣ በመንግስት ውስጥና ከመንግስት ውጪ ያሉ ጽንፈኛ ዘውጌ ብሔርተኛ ኃይሎች በሚያቀነቅኑት ፅንፍ የወጣ ትርክት እና እንቅስቃሴ ንፁሃን ዜጎች መከራቸውን ሊበሉ አይገባም። በክልሉ ሰላም ለማስከበር እየተንቀሳቀሰ ያለው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ለሕዝቡ አለኝታና መከታው ሆኖ መስዋዕትነት እንደከፈለ ለማህበረሰቡ መንገር ለቀባሪው ማርዳት ነው፡፡ ጽንፈኛ ዘውጌ ብሔርተኝነት አንዱ መገለጫው ብሔራዊ እሴት ያላቸው ተቋማትን በዘውግ መነፅር እያዩ ማጥላላትና ከህዝብ ጋር ሆድና ጀርባ እንዲሆኑ ማድረግ መሆኑን ህዝቡ ልብ ሊል ይገባል።

ከሁሉም በላይ መንግሥት ትልቅ ኃላፊነት እንዳለበት በመረዳት ጉዳዮቹን በትዕግስት እና በሆደ ሰፊነት በማስተናገድ፣ ህግና ሥርዓት እንዲከበር በመስራት ተጨማሪ የሰው ሕይወትም ሆነ የንብረት ውድመት ተከስቶ አላስፈላጊ ትርምስ እንዳይኖር የሚቻለውን ጥንቃቄ በማድረግ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አንጠይቃለን።

ከጠብመንጃ አፈ ሙዝና በጉልበት የሚመጣ መፍትሔ እንደሌለ በመረዳት ሁሉም ወገኖቻችን በሰላማዊ መንገድ መነጋገርና መመካከር ባህል በማድረግ ችግሮችን መፍታት ይኖርብናል። መንግሥት ከህወሓት እና እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ብሎ ከሚጠራው ኃይል ጋር የተፈጠሩ ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት የሄደበትን የውይይት መንገድ ሁሌም ቅድሚያ ቢሰጠው መልካም መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።

ይህ ማለት ግን ወንጀለኞች ያሻቸውን ሕገ ወጥ ተግባር እየፈጸሙና የሰው ሕይወት እየቀጠፉ በሰላም ስም እንዲከለሉ ሊፈቀድ ይገባል ማለት አይደለም፡፡ በኅብረተሰቡ ላይ የሚፈጸሙ ተራ ወንጀሎች፣ ግድያዎች እና ዝርፊያዎች ሕጋዊ በሆነ መንገድ ፍርድ የሚገባቸው እንደሆነ በፅኑ እናምናለን።

በጋዜጠኝነት፣ በአክቲቪስትነት እና በፖለቲከኛነት በንቃት የምትሳተፉ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ ያላችሁ አካላት ሁሉ ሕዝብን ለበለጠ አደጋ ከሚያጋልጡ ተግባራትና ቅስቀሳዎች በመቆጠብ አዎንታዊ ሚና እንድትወጡ እየጠየቅን፤ ለሚመለከታቸሁ አካላት ሁሉ ከግጭት መለስ ያሉ ሰላማዊ መንገዶችን ሁሉ እንድታስቀድሙ ጥሪ እናቀርባለን።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ተጨማሪ አስቸኳይ መረጃ‼


የትግራይ ታጣቂዎች ዛሬ በፒካፕ መኪና ላይ የተጠመዱ መሳሪያዎችን ጨምሮ ተተኳሾችን ወደ ተከዜ ድንበር አስጠግተዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች በአካባቢው ለሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት ጀነራሎች ማሳወቃቸውን እና እስካሁን በቂ ምላሽ እንዳላገኙ ይናገራሉ።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገ‼️


በሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ላይ የግድያ ሙከራ ተፈጸመ፡፡
ከተጀመረ 15 ወራት የሞላው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት በየጊዜው አዳዲስ ክስተቶችን ማስተናገዱን ቀጥሏል፡፡
በሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን መኖሪያ በሆነው የክሬምሊን ቤተ መንግስት ላይ የድሮን ጥቃት ለመፈጸም ሙከራ መደረጉ ተገልጿል፡፡
እንደ ራሺያ ቱዴይ ዘገባ ከሆነ የድሮን ጥቃቱ ያነጣጠረው በሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ፑቲን ላይ ሲሆን ፕሬዝዳንቱ በስፍራው እንዳልነበሩ ተጠቅሷል፡፡
የቤተ መንግስቱ ቃል አቀባይ ድሚትሪ ፔስኮቭ፥ ጥቃቱን በሁለት ድሮኖች ለመፈጸም ጥረት ቢደረግም የሩሲያ ጦር በወሰደው እርምጃ ድሮኖቹ መመታታቸውን ተናግረዋል።

Читать полностью…
Subscribe to a channel