ethio360media | Unsorted

Telegram-канал ethio360media - Ethio 360 Media

37564

ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር !!!

Subscribe to a channel

Ethio 360 Media

አለምባንክ የኢትዮጵያ መንግስትን ሰላም እንዲያሰፍን ጠየቀ‼️


ዓለም ባንክ የኢትዮጵያ መንግሥት ለአገሪቱ ችግሮች ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን የሚያሰፍኑ መፍትሄዎችን እንዲያመጣ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። በመላ አገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ መኾኑን የገለጠው ባንኩ፣ የሰላም ግንባታ፣ የእርቅና ዘላቂ ልማት መርሃ ግብሮችን መደገፉን እንደሚቀጥል ገልጧል። ባንኩ ድጋፍ የሚደግፋቸው ዘርፎች፣ የሁሉንም ሕዝብ ፍላጎቶች የሚመልሱ ስለመኾናቸውና ከመድልዖ የጸዱ፣ በሕዝባዊ ምክክርና አሳታፊነት ላይ መመስረታቸውን፣ የንብረት ባለቤትነት፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት መስፈኑን በቅድሚያ እንደሚያረጋግጥ አመልክቷል። ባንኩ እንደ ትምህርት፣ ጤና፣ የምግብ ዋስትና፣ ንጹህ የመጠጥ ውሃ፣ ሴቶችን ማብቃትና የማኅበራዊና የአካባቢ ጥበቃ የመሳሰሉ መሠረታዊ አገልግሎቶችን በማገዝ ላይ እገኛለኹ ብሏል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ኦህዴድ ሀጁ ሙፍቲ ላይ መፈንቅለ መጅሊስ አድርጎ ያመጣው የአዲሱ መጅሊስ መሪ ልጅ ነው። በሸገር ከተማ ከ30 በላይ መስጊድ መፍረሱን ተከትሎ በመስጊድ መፍረስ እንዲህ ቀልዷል። ቁርስ ሰዓት አባቱ የነገረውን መሆኑ ነው።

ኦህዴድ ሰሞኑን ሲኖዶሱ ልክ እንደመጅሊሱ መሆን አለበት ብሏል። ከእምነቱ ኦሮሙማን የሚያስቀድም ማለት ነው። የኢብራሂም ቱፉ ልጅ የቀረ መስጊድ ቢኖር "ከዚህ ጋ ያልፈረሰ አለ" ብሎ ይጠቁማል።

መጅሊሱን እንዲህ መጫዎቻ ያደረጉ ሲኖዶሱንም በተመሳሳይ እየሰሩበት ነው። ነገ ቤተ ክርስቲያን ሲቃጠልና ሲፈርስ የሚቀልዱትን ነው የፈለጓቸው።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ወለጋ ሆሮ ጉደሮ ዞን ነዋሪዎች በፀጥታ ስጋት ውስጥ ነን ብለዋል።

ከሚኖሩበት በቅርብ ርቀት "ከፍተኛ" የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ኢትዮጵያ በምግብ ዋጋ ማሻቀብ እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ ገብታለች። መንግስቷ ፈርሶ ባልተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ ያለችው ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ መካከል ያለው ልዩነት ከፍተኛ ነው።

በአዲስ አበባ አንድ እንቁላል ከ14 ብር እስከ 16 ብር እየተሸጠ ነው። አአ አሁን በአፍሪካ ለመኖር እጅግ ውዷ ከተማ ተብላለች። ይህ የምግብ ውድነት እየጨመረ መምጣቱ የሚቀር አይመስልም።
ገዢዎቻችን ቅንጡ ፕሮጄክቶችና ቤተመንግስት ግንባታ ላይ ስለሆኑ ደሃ ተኮር መፍትሄ የሚያመጡ ነገር አይደለም።

የሚበላው ያጣ ህዝብ መሪውን ይበላል የሚለውን ምክር የሚሰሙበት ጆሮ የላቸውም።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ልብ በሉ…!

"…ይሄ የምታዩት መከላከያ (የኦሮሙማ) ጦር ወደ ሰሜን ሸዋ ራሳ ወደ ዐማሮቹ መንደር ትጥቅ ካላስፈታሁ ብሎ በዚህ መልኩ እየተመመ ያለ ሟች ሠራዊት ነው።

• ቀጥሎ በኦሮሚያ እየሆነ ያለውን ደግሞ ይመልከቱ።

"…ራሳ የሸዋ አንበሳ…  እንዳይወጣ…! …💪🏿💪💪🏿

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በሸገር ከተማ ቤታቸው እየፈረሰባቸው ያሉ ሰዎችን እዛው አካባቢ ማስጠጋት እና ቤት ማከራየት 15,000 ብር እና የሶስት ወር እስራት ያስቀጣል እንደተባሉ ሰምተናል።

ያው በግልፅ "አካባቢውን ለቃችሁ ውጡ ነው።"

ይሄ ግፍ መጨረሻው የቱ ጋር እና መቼ ይሆን?

EliasMeseret

Читать полностью…

Ethio 360 Media

እነዚህ በሸገር ከተማ እየፈረሱ ያሉት መስጊዶች በአማራ ክልል መንግስት የፈረሱ ቢሆን ኖሮ እንጥልህ እስኪታይ ትጮህ ነበር። ክንፍህ እስኪለቅ ዳንኪራ ትመታ ነበረ። ዘረኛ ሁሉ‼ "መስጊድ የአላህ ቤት ነው! አታፍርሱ‼" ለማለት አፍራሹ ማነው ብለህ የፖለቲካ ቁማር አትቆምር‼ ግፍን አውግዝ‼

(ሙክታሮቪች ኦስማኖቫ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ሸዋሮቢት❗❗

አሁን በዚህ ሰዓት ሸዋሮቢት ከተማ ከፍተኛ የሆነ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ እንደሆነ ምንጮች ገልፀዋል።

ጠዋት ማፉድ ላይ ነበር አሁን ሸዋሮቢት ከተማ እና በራሳ መንገድ ነው የተኩስ ድምጽ የሚሰማው።

እንደ መረጃ ምንጫችን ገለፃ ተኩሱ በመከላከያ እና በፋኖዎች መካከል መሆኑን አረጋግጧል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ሰበር ዜና ነው…!

"…ዋናውን የጅቡቲ አዲስ አበባን መንገድ ለመያዝ ኦነግ ሸኔና መከላከያ በወለንጪቲ ከተማ ከባድ ጦርነት እያደረጉ ነው።

"…ልብ በል ወለንጪቲ ነው ያልኩዋችሁ። ሰሞኑን በደብረዘይት ከፖሊስ ተዋግተው እስረኛ ያስለቀቁት ኦነግ ሽሜዎች ዘሬ ደግሞ በወለንጪቲ እየተጠዛጠዙ ነው። ስልክ ደውዬ የምሰማው የቀለጠ ጦርነት ነው። እናንተም ደውላችሁ አረጋግጡ።

"…ሁሉም ሰው ወደ ቤቱ ስለገባ እስከአሁን ስለደረሰ ጉዳት የተሰማ የታወቀ ነገር የለም። ምንአልባት በወለንጪቲ ከተማ የሚታረድ ኦርቶዶክስና ዐማራ ሊኖር ይችላል። ለማንኛውም ጦርነቱ ሲበርድ እንሰማዋለን።

"…በተለይ በመከላከያ ውስጥ ያላችሁ የደቡብ እና የዐማራ ልጆች በቤተሰብ ፀብ መካከል ገብታችሁ ጭዳ ከመሆን ራሳችሁን ጠብቁም ተብላችኋል። ሰሞኑን ከዐማራ ልዩ ኃይል ተቀንሰው መከላከያ የገቡ ራብተኛና ደናቁርት የዐማራ ልዩ ኃይል አባላት ጭዳ ይሆናሉም ተብሎም ይሰጋል። አልሰማ ያለውን ይበለው። ይጥረገው። ኤትአባቱንስና።

"…ለማንኛውም ጎበዝ ዓይናችሁን ነገው የባህርዳረ የብአዴን ስብሰባ ላይ ብቻ አትትከሉ። አዲስ አበባ ዙሪያና ቤተ ክህነቱ ላይ ትከሉ። ተናግሬአለሁ።

(ዘመድኩን በቀለ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ሰሞኑን በሽሮሜዳ ከ600 በላይ ሱቆች ህገወጥ ናቸው በሚል መፍረሳቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የጫካ ፕሮጀክት

(መሳይ መኮንን)

የጫካ ፕሮጀክት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካለሟቸው ቅንጡ ፕሮጀክቶች ትልቁ ነው። የኢትዮጵያን ዓመታዊ በጀት ሁለት እጥፍ ይስተካከላል። ገንዘቡ ከየት ይመጣል የሚለው ከጠቅላይ ሚኒስትሩና ሰጪዎች በቀር የሚያውቀው ፈጣሪ ብቻ ነው።

… ይህ የጫካ ፕሮጀክት አሁን ባለው ዋጋ 850ቢሊየን ብር ወይም 15ቢሊየን ዶላር የምሚፈጅ ነው። ስራው ተጀምሮ እስኪያልቅ ከአንድ ትሪሊየን ብር ሊሻገር እንደሚችል ነው ባለሙያዎች የሚገልጹት። ይህን ብር ይዘን ሂሳቡን በተለያዩ ለኢትዮጵያውያን የህይወይትና ሞት ሽረት በሆኑ ጉዳዮች እንመንዝረው። በዶላር ያለውን ሂሳብ ወስደን ማለት ነው።

* 15 ቢሊየን ዶላር፥ ሶስት የህዳሴ ግድብን ይገነባል።
* 1 ቢሊየን ዶላሩ 20 ሆስፒታሎችን በየክልሉ ማቆም ያስችላል።
* ሌላ 1 ቢሊየን ዶላሩ በርካታ ደረጃቸውን የጠበቁ ዩኒቨርስቲዎችን ያቋቁማል።
* 1 ቢሊየን ዶላር በትግራይ፡ በአማራና በአፋር ክልሎች የወደሙ ሁሉንም ትምህርት ቤቶች መልሶ በተሻለ መልኩ ለመገንባት ያስችላል።
* 1 ቢሊየን ዶላር የኮይሻ ሀይድሮ ኤሊክትሪክ ፕሮጀክት ግንባታን እንዲጠናቀቅ ያደርጋል።
* በ1 ቢሊየን ዶላር 3 ነጥብ 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ስንዴ ይገዛል። ለ20 ሚሊየን የተራቡ ዜጎቻችን ከአምስት ወራት በላይ ቀለብ እንዲኖራቸው ያደርጋል።
* 1 ቢሊየን ዶላር 4ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ስኳር ለመግዛት ያስችለናል።
* 1 ቢሊየን ዶላር 2ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ዩሪያ ማዳበሪያ ይገዛልናል። አርስ አደሮቻችን ተንበሸበሹ ማለት ነው።

እንግዲህ እስከአሁን የተጠቀምነው 6 ቢሊየን ዶላሩን ብቻ ነው። 9 ቢሊየን ዶላር ይቀረናል። እንቀጥል ይሆን?

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ራያ‼

ራያ አላማጣ ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ።

በሰልፉ ላይ የበጀት፣ የማንነት እና ሌሎች ጉዳዮችን አንሰተው መፍትሔ ይሰጠን ብለዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ትህነግና ኦህዴድ ሽርሽር በማብዛታቸው ምን አስጨነቀን?

1) ያ ሁሉን ማድረግ እችላለሁ ይል የነበር ትህነግ ኦህዴድ ስር ሲርመጠመጥ ምኑ ያናድዳል?

2) ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሃዬ፣ አይነስውሩን አስመላሽን ወዘተ ከተማረኩ በኋላ "ግንባር ግንባሩን ብለህ ጣል" ያለው ብርሃኑ ጁላ። ታዲያ ከተማረከ በኋላ አመራሩ የተረሸነበት ሳይጨንቀው አንተ ለምን ይደብርሃል?

3) በድሮን ሲቀጠቅጠው የከረመ ኃይል ጋር ሲጨፍር ውሎ ቢያድር የራሱ የትህነግ ደጋፊ ሞራሉ ካልተነካ አንተ ምን አስጨነቀህ?

በግሌ ትህነግ ከኦህዴድ ጋር የጀመረውን ስመለከት ደስታ ነው የሚሰማኝ። የአቅም ማነስ ነው እንዲህ የሚያደርገው። ግንባር ግንባሩን ብለህ ጣለው ብሎ ከፈረደበት ጋር ነው ውሎው። በድሮን ካሳደደው ጋር ነው የሚልመጠመጠው። አቅም ቢኖረው ይህን አያደርግም ነበር። የመጨረሻ የሞራል ውድቀት ነው።

የስዩም መስፍን፣ የአባይ ፀሃዬ ወዘተ አድናቂ፣ አንድ ሚሊዮን ወጣት ያለቀበት ራሱ የትህነግ ደጋፊ ሳይቆነጥጠው ሌላው ቅር ሊለው አይገባም።

(ጌታቸዉ ሽፈራዉ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አላማጣ‼️

ነገ በአላማጣ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ይካሄዳል የሚል መረጃ ደርሶናል። በጀት ይለቀቅ፣የማንነት ጥያቂያችን ይመለሱ እና በራያ ህዝብ ላይ ከፍተኛ በደል የፈፀሙ የህወሓት አመራሮች በማይጨው እና አካባቢው ይገኛሉ ለህግ ይቅረቡ" በሚሉ ጉዳዮች ላይ ሰልፍ እንደሚካሄድ የደረሰን መረጃ ያመላክታል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ቤታቸው የፈረሰባቸው ባልና ሚስት ትላንት ማታ ተገደሉ።

በሰበታ ከተማ በኬንተሪ ደረቶ በሚባል ቦታ የአቶ መሀመድና የጎረቤቶቹ ቤቶች የፈረሱት ከትላንት በስቲያ ነበረ። ሙሉ ሰፈሩ ፈርሶ አልቋል ማለትም ይቻላል። አቶ መሀመድም እዛ ሰፈር ከገባ ወደ 18 አመት አካባቢ ሆኖታል።

ቤት ከፈረሰባቸው ሰዎች መሀከል የአቶ መሀመድ አብደላን ጨምሮ የሁለት ቤተሰብ አባላት ቤታቸዉ ከፈረሰባቸዉ በሆላ የሚሄዱበት አጥተው ተቸግረዋል። ትላንት ከሰአትም አብዛኛው እቃቸውን ወደ ገጠር ከጫኑ በኋላ ሰፈራቸዉ በሚገኝ አንድ ፊኒሽንጉ ያላለቀ የሪልስቴት ፎቅ ግራውንዱ ላይ ቦታ ያለ በመሆኑ በባለቤቱ መልካም ፍቃድ "ቤት እስክታገኙ "እዛ ግቡ" ብሎዋቸዉ ገቡ።

ማታ ፖሊሶች መጥተው እነመሀመድ የተኙበትን የህንፃውን በር መደብደብ ጀመሩ። መሀመድም ማንነታቸውን ለማጣራት በመጠየቅ ላይ እያለ በሩ በሀይል ተሰበረ። በመቀጠልም አቶ መሀመድ አብደላ እንዲሁም ባለቤቱ ለቢባ ጀማል በጥይት ተመቱ ።

ጩኸቱን ሰምታ ከመጡት ጎረቤቶች መሀል አራስ የሆነችው ሉባባ ብላቱ በጥይት ተመታ ስትሞት ባለቤቷ ደግሞ ከቆሰለ በኋላ አምልጧል።

በጻውሎስ ሆስፒታል ያደረውን አስክሬን አሁን ተቀብለናል።

ተስፋ ነዳ - ከጳውሎስ ሆስፒታል።

Emat Gurage Media

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ሀጅ ሙፍቲን ከመጅሊሱ አስወግደው መስጊድ ሲፈርስ ምንም የማይሉትን እንደተኩት ሁሉ፣ በሲኖዶሱ ላይም እየታሰበ ያለው ተመሳሳይ ነው። መመዘኛው ኃይማኖቱ ሳይሆን ኦሮሙማ ነው። አሁንም ቤተ ክርስቲያን ሲፈርስ ምንም የማይለውን ነው የፈለጉት።

በኦሮሞኛ የሚሰብክ ሳይሆን ኦሮሙማን የሚሰብክ ነው የተፈለገው።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በወልቃይት የዘር ፍጅት ወንጀሉን የሚረሳው የለም። ወንጀለኞችን እንደ ንፁህ የሚቀበል አይኖርም‼

በወልቃይት ጠገዴ አማራ ላይ የተፈፀመው ግፍ በሚገባ አልተነገረም። በርካታ ኢትዮጵያውያን አያውቁትም። ይህን ግፍ የፈፀመው ትህነግ በወንጀሉ ሳይጠየቅ፣ በደሉ ለተፈፀመባቸው ካሳና ይቅርታ ሳይደረግ ከወልቃይት ጠገዴ ያልተፈናቀለን በትግራይ ቀበሌዎች ሰብስቦ "ተፈናቃይ መልሱልኝ" እያለ ነው። ሰሞኑን ወልቃይት ጠገዴን በማያውቁት የትግራይ አካባቢዎችም "ተፈናቃይ ይመለስ" ተብሎ ሰልፍ ሊደረግ ነው።

እጅግ በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ይህን ሁሉ ዘግናኝ ወንጀል ፈፅመው ወደ ሱዳን የሸሹትም ከሱዳን በሚስጥር ወደ ትግራይ ተሻግረው ከዛ ወደ ወልቃይት እንዲመለሱ "መንግስት" እየሰራ ነው። ይህ ሁሉ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፍትህ ሳያገኝ ወንጀለኞችን ከሱዳን ወደ ትግራይ ተንከባክቦ የማያሳልፈው መንግስት ለነገም የዘር ፍጅት እያበረታታ መሆኑ ግልፅ ነው።

ይህ ዘግናኝ ግፍ በአማራነቱ ምክንያት የተፈፀመበት ህዝብ ፍትሕ ይፈልጋል። ገና የጠፉ ቤተሰቦቻቸውን ደብዛ ያላወቁ አሉ። ይህን በደል የሚረሳ፣ ወንጀለኞቹን እንደ ንፁህ የሚቀበል አይኖርም።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ጋዜጠኛ እና የህግ ባለሙያ አበበ ገላዉ ከ መሳይ መኮንን ጋር የነበረዉ ቆይታ!!

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ይሄ ደግሞ ኦሮሚያ ነዉ!!

የነ አብይ አህመድ አማራን ከምድር እንዲያጠፋላቸዉ ያዘጋጁት ሰራዊት ነዉ:: አሁንም በመንግስት ድጋፍ በስልጠና ላይ ያለ ነዉ::

መፍትሄዉ እንደ ህዝብ ተባብሮ እና ተናቦ መስራት ብቻ ነዉ:: አማራ ነፃ የሚያወጣህ ነፍጥህ ብቻ ነዉ:: ድል ያለ መስዋእትነት አይገኝም::
አማራ ክልል ትጥቅ ለማስፈታት ከመነሳታችሁ በፊት መጀመሪያ የራሳችሁን ክልል አፅዱ!!

Читать полностью…

Ethio 360 Media

መረጃ❗👇👇


በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፈራታና ግድም ወረዳ ጀብውሀ ቀበሌ በባለፈው በተፈጠረው የፀጥታ ችግር የተፈናቀሉ የአማራ ቤቶችን ከኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የመጡ ሰዎች የጤና ጣቢያውን የኬጂ ትምህርት ቤቱን እና የአማራ ቤቶችን እየለዮ በማፍረሰ እንጨቱን እና ቆርቆሮውን ወስደዋል፣በተለይ ሰሞኑን ከግንቦት 8-11 ባሉት ቀናት ውስጥ ተባብሷል።

መፍትሔ ያሻዋል ሲሉ ነዋሪዎቹ መረጃ አድርሰዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አንድ ግለሰብ 7 የህገወጥ ቤት አፍራሽ ግብረሀይሎችን ገደለ‼️💪💪


በአዲስ አበባ ለገጣፎ ቤቱን በማፍረስ ላይ የነበሩ አፍራሽ ግብረሀይሎችን ማፍረስ እንዲያቆሙ ለማድረግ ሲከላከል ሚስቱ ተወው ይገሉሀል በማለት መሀል ትገባለች። ቤት አፍራሾቹ አባውራውን ለመምታት የተኮሱት ጥይት እሱን ስቶ ሚስቱን ይገድላታል።
በዚህ የተበሳጨው ባል 7 ቱን ግብርሀይል ገድሏቸው ተሰውሯል ሲሉ ምንጮች ገልፀዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አስቸኳይ ልዩ መረጃ‼

መንግስት ትላንት እና ዛሬ በ ራሳ እና ሸዋሮቢት ፋኖ ላይ በማዘናጋት ያደረገዉን የማጥቃት ሙከራ ተጠናክሮ የመቀጠል እድሉ ሰፊ ነዉ ይላል የደረሰን የመረጃ ምንጫችን::

ለዚህም በዋነኛነት የህዝቡ ትኩረት ነገ ሀሙስ በባህርዳር በሚደረገዉ በአማራ ብልፅግና ስብሰባ ነዉ በሚል ነዉ::

ስለዚህ መላዉ የአማራ ህዝባዊ ሀይል ፈጣን መረጃ በመለዋወጥ ከወትሮዉ በተለየ በንቃት መጠበቅ የተሻለ ነዉ:: የድሮን ጥቃት የመኖር እድሉ ሰፊ ስለሚሆን አንድ ቦታ መሰብሰቡ ተገቢ አይደለም::

መረጃዉን ለሌሎች እንዲደርስ ያጋሩ!!

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ሰበር❗❗

ህወሃትን እናድን በሚል ዶክተር ደብረፂዎን፣አለም ገበረዋሃድ እና ሞንጀሪኖ በትግራይ ያሉ ከተሞችን ተከፋፍለው ሰሞኑን ስብሰባ እያካሄዱ ነው‼️
ዶክተር ደብረፂዎን የሽሬ አካባቢ ከተሞችን፣ሞንጀሪኖ የማይጨው አካባቢ ከተሞችን እና አለም ገ/ዋሀድ አድዋ ያሉ ከተሞችን ይዘው ስብሰባ እያደረጉ ነው። የስብሰባው አላማ ህወሃትን ህጋዊ ፓርቲ ለማድረግ እና ፓርቲውን ለመታደግ ነው ተብሏል። ጌታቸው ረዳ ብልፅግና ነው፣ እኛን ማማከር ትቷል .....የሚል ዘመቻ እንደጀመሩበት ታውቋል። ህወሃት በርካታ እናቶች ልጆቻቸውን የገበሩበት ድርጅት ነው ወደ ህጋዊ ሰውነት መመለስ አለበት፣ህወሃት ከፈረሰ ታላቋ ትግራይ የለችም... በማለት ወጣቶችን እየሰበሰቡ ማወያየት ጀምረዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የእነ ረዳት ፕ/ር ሲሳይ የርሃብ አድማ‼️


ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸውን ጨምሮ 40 የሚሆኑ እስረኞች የርሃብ አድማ መጀመራቸው ተነገረ
በአማራ ክልል ከልዩ ሃይል መፍረስና ፋኖን ትጥቅ ከማስፈታት ጋር ተያይዞ ለእስር የተዳረጉ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች የርሃብ አድማ መጀመራቸው ተነግሯል።
እስረኞቹ የርሃብ አድማውን ማድረግ የጀመሩት በአማራ ክልል የሚካሄደውን እስርና አፈና በመቃወም መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ለሮሃ ቲቪ ተናግረዋል።
ከዛሬ ሰኞ ግንቦት ሰባት ጀምሮ እስከ ረቡእ ግንቦት 9 የሚቀጥል መሆኑንም ነግረውናል።
በዚህም " ሽብር፣ ሁከትና ብጥብጥ ፈጥራችኃል እየተባለ የአማራ ሙሁራንን፣ ጋዜጠኞችንና ወጣቶችን እንዲሁም የቀን ሠራተኞችን ማሰር ይቁም" በሚል እነ ረ/ፕ ሲሳይን ጨምሮ 40 የሚሆኑ ታስረው የሚገኙ የአማራ ሙሁራንና ሌሎች እስረኞች ናቸው የርሃብ አድማውን የጀመሩት።
አድማውን አስመልክቶ ስለጉዳዩ ያውቁ እንደሆን ያናገርናቸው የእስረኞቹ ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝም ጉዳዩን ከእስረኞቹ ቤተሰቦች ከሰሙ በኋላ ወደ እስር ቤት በማምራት አድማ መጀመራቸውን እንዳረጋገጡ ነግረውናል።


ሮሃ ቲቪ

Читать полностью…

Ethio 360 Media

መለስ ዜናዊን ጨምሮ የህወሓት አመራሮችና አክቲቪስቶች ስለ ወልቃይት ጠገዴ ያመኗቸው ሃቆች https://youtu.be/xrGxCorTwJY

Читать полностью…

Ethio 360 Media

"መጀመሪያ ቤታችሁ አይፈርስም 5ሺ ብር የልማት ክፈሉ ብለውን ከህዝቡ ከ 10 ሚሊየን ብር በላይ ሰበሰቡ ።

ከአፍራሾች መሀከል አንዱን ዛሬ ልታፈርሱ ከሆነ ለምን ብር ተቀበላችሁን አይፈርስም ብላችሁ ሲሉት ታዲያ አፍራሾች በነጻ ነው እንዴ ሚያፈርሱት ለእነሱ ምን ይከፈላቸው ብሎ ተሳለቀ።

ከቤት ፈረሳው በላይ አፍራሽ ግብረ ሃይሉ ሲያፈርሱ የሚናገሩት የጥላቻ ንግግር ልብ ያቆስላል፣ ለንግግራቸው መልስ የሚሰጣቸው ሰው ላይ ደሞ የሚያወርዱት የዱላ ውርጅብኝ በእጅጉ ይዘገንናል። ለዚህም ሰው በዝምታ በጥልቀት እያሰበ ዝም ብሎ ይመለከታቸዋል ወላሂ በአይኔ የተመለከትኩት ነው።"

Via Mualana Ramzi Ahmed
Photo: File

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለ4 ቀናት የስራ ጉብኝት ወደ ቻይና አቀኑ።

ፕሬዝደንት ሺን ፒንግ ባቀረቡላቸው ግብዣ መሰረት ዛሬ ቤጂንግ ገብተዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ለገጣፎ‼️

በለገጣፎ 44ማዞሪያ አካባቢ ከትላንት ማለትም ሀሙስ ቀን ጀምረው ቤት የማፍረሰ ዘመቻው ጀምረዋል። ጊዚያዊ ማረፊያ እንኳን ሳይመቻች ዜጎች ለከፍተኛ ወጪ እና እንግልት እየተዳረጉ ነው።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

"እንደ ፋኖ አስተሳሰብ ገዳዩም አማራ፣ ሟቹም አማራ እንዲሆን አንፈልግም። ይሄ የእስካሁን መርሃችን ነው። የአማራን አመራር አንገድልም።" - ፋኖ ምሬ ወዳጆ💪💪💪

ገና ቁስላችን ሳይደርቅ በፋኖ ላይ ጦርነት ከፍተውብናል።

ህዝባችን ከውድመቱ ሳያገግም ሌላ ውድመት ታውጆበታል። አማራ በህብረት ቆሞ፣ ለውጥ ማምጣት አለበት። ፋኖን መደገፍ አለበት።

የአማራ ህዝብ ሕግ ያለ እንዳይመስለው። ህግ የለም። እኔ በግሌ ለመሞት ነው የተነሳሁት። የሚያሳፍረው ግን የ3 አመት ልጄ ሳይቀር ታፍኗል። ይሄ የሚያሳየው በኦነጎች ዘንድ ህግም፣ ሞራልም አለመኖሩን ነው። አማራ የሚያስከብረው ኃይሉ ብቻ ነው። የሚያዋጣው መደራጀቱ ብቻ ነው።

አሁን ላይ ኢትዮጵያን የሚወደው ትክክለኛው የመከላከያ ሰራዊት የለም። አብዛኛው ሰራዊት ጥቅምት 24 በህወሃት ተረሽኗል። የቀረው ባለፉት ሁለት አመታት አልቋል። የተወሰኑ የተረፉ ቢኖሩም ወደ አማራ ህዝብ አንተኩስም በማለታቸው እየተረሸኑ ነው።

አሁን የመከላከያን ዩኒፎርም ለብሶ ወረራ የከፈተብን በብሔር ጥላቻ ያበደው የኦሮሞ ልዩ ኃይል ነው።

ሌላው ጠላት ይበቃናል። ስለዚህ የአማራን አመራር አንገድልም። የአማራን አመራር መግደል ብንፈልግ፣ በህወሃት ወረራ ጊዜ ህዝቡን ለጅብ ሰጥተው ቀድመው የፈረጠጡ አመራሮችን ነበር የምንገድላቸው። መግደል ብንፈልግ ኖሮ በክፉ ቀን የፈረጠጡት አመራሮች፣ ተመልሰው ስልጣን ሲይዙ ነበር የምንገድላቸው።

እንደ ፋኖ አስተሳሰብ ገዳዩም አማራ፣ ሟቹም አማራ እንዲሆን አንፈልግም። ይሄ የእስካሁን መርሃችን ነው። የአማራ አመራሮችም ከስህተታቸው ይወጣሉ በሚል እየጠበቅናቸው ነው። ነገር ግን የአማራ አመራሮች ዝምታችንን ካለመቻል ቆጥረው ዛሬም እንደ ትናንቱ እየተላላክን፣ ፋኖን እያሳደድን፣ የህዝብ ጥያቄ እያፈንን እንቀጥላለን ካሉ መርሃችንን ልንቀይር እንችላለን።

( ፋኖ ምሬ ወዳጆ - ከአዲስ ድምፅ ጋር ካደረገው የስልክ ቃለምልልስ ላይ የተወሰደ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወረዳ እና በቀለቤ ደረጃ ለትግራይ ክልል መልሶ ግንባታ ከባላሀብቶች፣ከደመወዝ እንዲሁም ሰራተኛውን በማወያየት የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ እንዲሰራ መመሪያ መውረዱን የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።

ለአማራ ክልል እና ለአፋር ክልል ተብሎ ጥያቄ የተነሳ ቢሆንም አሁን የትግራይ ክልል ብቻ ነው በመልሶ ግንባታ ዕቅድ የተያዘው የሚል ምላሽ ተሰጥቶታል ሲሉ ምንጮች ገልጸዋል።
======================

Читать полностью…
Subscribe to a channel