"…ሰሜን ሸዋ ይፋት ሰሞኑን ከሃዲው አበባው ታደሰ የሃገር ሽማግሌ ሰብስቦ "ፋኖዎችን አንነካቸውም ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ አድርጉ" ይላቸዋል። ግድየለም ጫካው ተስማምቷቸዋል እዚያው ይቀመጡ ለእነሱ አትጨነቁ ብለው ይመልሱለታል። ብዙ ዘበዘበ፣ ዘበዘበ አባ ከና የሚለው ሲያጣ ለአለቆቹ ሊነግር ወደ ሸገር ተመልሷል አሉ።
"…አራዳዎቹ አሁን የዐማራን አንድነት እና ምርር ብሎ መሬት የረገጠ ትግል መጀመሩን ሲያውቁ ትግሉን ለማፍረስ እና ለማኮላሸት የተለመደውን ኢትዮጵያዊነት የሚሉትን ዐማራ ማደንዘዣ ኪኒን ሊያውጡት ነቢይ መስለው ካባም ደርበው ከቺሳ ሊሉ ነው። አራዳው ከዐረቦቹና ከግብጽ ጋር ተነጋግሮ ልክ ግብፅ ኢትዮጵያን እንደምትወር፣ አረቦቹም ለእርሷ እንደሚያግዙ ዓይነት ጨዋታ ሊጫወት ካርዷን መዞ ሊመጣ ነው። ከዚያ ሰሞኑን ዘፈኑንም፣ መዝሙሩም ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ነው የሚለው። "እኛ ኢትዮጵያውያን በሃገር ውስጥ ችግር ቢኖርብንም የፈለገ ብንገዳደል የውጭ ወራሪ በመጣ ጊዜ አንድ ላይ ነው የምንቆመው፣ ፋኖ ተሰባሰብ፣ መከላከያ ግባ፣ ተቀላቀል። በተለይ ዐማራ ወንዱ፣ አንበሳው፣ ጎሹ፣ ነበሩ፣ ዝሆኑ ብላ ብላ ብሎ ሊዘበዝበው ነው።
"…ግብፅና የአረብ ሊግ አጀንዳውን አስተኩሰዋል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደግሞ ጉዳዩን ማንጫጫት ጀምሯል። ከዚያ የአሚኮው ጋዜጠኛ ታርቆ ክንዴ በአሚኮ፣ እነ መጋቤ ሀዲስ እሸቱ በብሔራዊ ቲያትር፣ እነ ናቲ፣ ቶሚ፣ ጌትነት ደግሞ በፌስቡክ "ኢትዮጵያዬ እማማዬ፣ ከአንቺ በፊት ምንትስዬ ሊሉን ነው። ዐማራ እንዳትዘናጋ። አትመጣም እንጂ ግብፅ ደፍራ ብትመጣ እንኳ እንደ ኦሮሞና ትግሬ ቦለጢቀኞች መታወቂያ አይታ አታርድህም። የጀመርከውን ትግል 4ኪሎ ሳታደርስ ወደኋላ እንዳትመለስ። ከግብፅ እና ከአረብ ጋር አረቡ አቢይ አይጣላም። ሲፎግርህ ነው ነግሬሃለሁ።
"…ሞኝህን ብላ በለው…!
ሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋሮቢት እና ራሳ‼
ሰሞኑን በሰሜን ሸዋ ዞን በሸዋሮቢት እና በራሳ አካባቢ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ሰዎች እንደሞቱ ይታወቃል።
ይህንን ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ትናንት ከደብረ ሲና ዝቅ ብሎ ጭራሜዳ በምትባል አካባቢ የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች ጭምር በተገኙበት የየአካባቢውን ሽማግሌዎች ጠርተው ጉዳዩ በሽምግልና እንዲፈታ እና ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ካሉ ወደ ቤታቸው ይመለሱ፣ማንም አይነካቸውም የሚል ነገር የተነሳ ሲሆን ሽማግሌዎቹ በበኩላቸው ባለፈው ጉዳዩ በሽምግልና እንዲፈታ ከተስማማን በኋላ ባልጠበቅነው መልኩ ሰሞኑን የሀገር ሽማግሌዎችን ጨምሮ በሞት አጥተናል።
አሁን ምን ማስተማመኛ ነገር ተገኝቶ ነው ለሽምግልና የምንቀመጠው የሚል ቅሬታ አንስተው ተለያይተዋል።
በሸዋሮቢት ከተማ ትናንት ማታ ጀምሮ የኔትወርክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት እየሰራ አለመሆኑን ነዋሪዎቹ ተናገሩ።
ውሃም ከጠፋ ሶስት ቀን ሆኗታል ብለዋል።
ትህነግ ነገ ሰልፍ ሊያደርግ ነው‼
ሰልፉ ከትግራይ ቀበሌዎች በሚሊዮን ህዝብ ሰብስቦ ወልቃይት ለማስፈር ያቀደውን ለማሳካት ነው። እውነታው ግን ቁልጭ ያለ ነው።
የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ቁጥር በራሱ በትህነግ ዘመን የተዛባው የህዝብ ቆጠራን እንኳን ብንወስድ የትህነግን ቅዠት ነው የሚያሳየው።
ተፈናቃይ የሚለው አብዛኛው ንፁሃንን ጨፍጭፎ የሸሸ እና በህግ የሚፈለገዉን ነዉ።
አዲስ አበባ‼️
በቤተክነቱ አካባቢ በርካታ የፀጥታ ሀይሎች እንዳሉ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።
ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ የመጨረሻ የምልዐተ ጉባዔ የሚያካሂድ ሲሆን አጨቃጫቂ የሆነው የሹመት ጉዳይ ዛሬ ያልቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ሰበር
የማህበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን ጣቢያ ታገደ‼
መንግስት በሀይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ሲገባ እግር በእግር እየተከተለ ሲያጋልጠዉ መቆየቱ ይታወቃል::
አሁን ቀጣይ በተለይ ለ ነገ በቤተክርስቲያን ላይ ላሰበዉ ሴራ ይመቸዉ ዘንድ የማህበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን ጣቢያን አግዶታል::
ሱሉልታ‼
ሱሉልታ ከተማ ከ8 አመት በፊት የሰራውን ቤት ምንም እንኳን ህጋዊ ቢሆንም ሊፈርስ እንደሆነ መረጃ ይደርሰዋል::
ይህ ሰው ሙሉ ቤተሰቡን ከእነ እቃው አውጥቶ ሌላ ቦታ ያስቀምጣል።
ይኸን የሰሙ አፍራሽ ግብርሃል ሰውየው ቀድሞ እቃ አሽሽቷል ይፍረስ ብሎ ወስኗል ማለት ነው ብለው 5 አፍራሽ ሃይል ወደ ሰውየው ቤት ይሄዳል ።
ሰውየው ቤተሰቡን አሸሸ እንጂ እሱ መኖር ቤቱ ዉስጥ መኖር አላቆመም ነበር::
አፍራሾቹ ቤቱን አንኳኩተው ሲገቡ ያገኙት እና ቤትህ ህጋዊ መሆኑን ልናረጋግጥ ነው የመጣነው ብለው ጠየቁ ግለሰቡም ህጋዊ ቤት ነው ብሎ ያሉትን ማስረጃዎች አሳየ ከዚህ በኋላ ዋናውን ኦርጅናል የቤቱን ካርታ አሳየን ብለው ጠየቁ።
ይህንን ማድረግ የምችለው ቢሮ ሄደን ነው እዛ ላሳያችሁ ብሎ ሲመልስ አይሆንም አሁን አምጣ ብለው ያዙት ሰውየው በሃይልም ቢሆን ሊወስዱት እንዳሰቡ ስለገባው እሺ ላምጣ ብሎ ካርታውን ሰጣቸው አፍራሾችም ፊትለፊቱ ካርታውን ቀዳደው ጣሉለት እሱም ቀድሞ የተዘጋጀ በመሆኑ ያስቀመጠውን መሳሪያ ተጠቅሞ 4 ቱን ገደላቸው፣ አንዱ ከፉኛ ተጎድቶ ጎረቤት ገብቶ አመለጠ።
ግለሰቡም መኪና አስነስቶ ተሰውሯል።
አፍራሽ ግብርሃይሉ አስካሁን የዚህን ግለሰብ ቤት ለማፍረስ አልደፈረም፣ እሱም አልተያዘም።
#ሰበር
አቶ አምሃ ዳኜው የባልደራስ ፕሬዝዳንት ተደርገው ተሾሙ።
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ ለእጩነት ከቀረቡት ሶስት አባላቶቹ ውስጥ በም/ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ አምሃ ዳኜውን ፕሬዝዳንቱ አድርጎ መርጧል።
ለእጩነት የቀረቡት አባላት አቶ በቃሉ አዳነ፣ አቶ አምሃ ዳኜው እና አቶ ሳምሶን ገረመው ነበሩ። ከእነዚህም ውስጥ በአብላጫ ድምፅ አቶ አምሃ ዳኜውን ለቀጣይ 3 አመታት በፕሬዝዳንትነት እንዲያገለግሉ ተመርጠዋል።
ትላንት ማምሻውን ዓለም ባንክ አካባቢ ተጨማሪ ሁለት መስጂዶች ፈርሱ‼️
በቀድሞ ዓለም ባንክ ኮ/ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በአሁኑ በሸገር ከተማ ስር በተካተተው አካባቢ የሚገኙትን ጀበል እና ዳሩል አርቀመ መስጂዶች መፍረሳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለጀይሉ ቲቪ ገልፀዋል ።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሼህ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ከዚህ በኋላ እኛን ሳያማክሩ አንድም መስጂድ አይፈርስም ማለታቸው ይታወሳል ።
የባልደራስ ፓርቲ መስራች እስክድር ነጋ <<የአሁኑ መንግስት በአማራ ተወላጆች ላይ ግፍ እየፈፀመ ነው።
በተለይ ስርዓቱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንና ነባሩ እስልምና አባቶችና ምዕመናን ላይ ማዋከብ እየፈፀመ ነው።
መነሻችንን አማራ መዳረሻችንን ኢትዮጵያ አድርገን የአማራ ህዝባዊ ግንባር መስርተን ወደ ትግል ገብተናል፣በውጭ ሃገር ያለውን ድጋፍ ለሚመሩት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ተባበሯቸው >> በማለት ትናንት ምሽት በድምፅ ተናግሯል።በይፋ ወደ ትግል መግባቱንም አሳውቋል።
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተለቋል።
ትላንት ምሽት ከመኖሪያ ቤቱ በጸጥታ ኃይሎች ተይዞ የተወሰደው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ ምሽት አምስት ሰዓት ገደማ መለቀቁን ታወቀ።
ተመስገን ለ“ጥያቄ ትፈለጋለህ” በሚል፤ በአዲስ አበባ ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ ወደሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ተወስዶ ለሁለት ሰዓት ገደማ መቆየቱን ገልጿል።
ተመስገን ከዚህ ቀደም በፍርድ ቤት ነጻ በተባለበት ክስ ጋር በተያያዘ፤ ይግባኝ እንደተጠየቀበት ዛሬ ምሽት በፖሊስ እንደተገለጸለት አስረድቷል። በዚህ ክስ ይግባኝ የቀረበለት ጠቅላይ ፍርድ ቤት መዝገቡን በሚያዝያ 12፤ 2015 ዘግቶት እንደነበር ተመስገን አስታውሷል። ይህም ሆኖ ጉዳዩ እንደገና በጠቅላይ ፍርድ ቤት እንደሚታይ በፖሊስ እንደተነገረው ተመስገን ገልጿል !!
ለዚህም ሲባል ሰኞ በአካል የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ እንዲቀርብ መጠየቁን እና ይህንኑ የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ላይ መፈረሙንም ጋዜጠኛው አስታውቋል!!
የአፋኙ ቡድን ሚስጥር!
ኢ መደበኛማ ይሄውልህ!
ፅንፈኛማ ይሄውልህ!
አገር እየተመራ ያለው በዚህ መልክ ነው። እነዚህን ምስሎች ከአንከር ሚዲያ ነው የወሰድናቸው። የኦሮሚያው አፋኝ ቡድን ነው። ከኦሮሚያ እስከ አዲስ አበባ፣ ሸገር ሲቲ ከሚለው እስከ አማራ ክልል ተደራጅቶ ይሰልላል።
አዲስ አበባ ላይ ቤትና ቦታ እንዴት እንደሚነጥቅ ይወያያል። በየመስርያ ቤቱ የራሱን አባላት ይሰገስጋል። በሀሰት እየሰለሉ ያሳፍናሉ።
የፌደራል የጋራ ግብረ ኃይል የሚባለውን የሚመሩት እነዚህ ናቸው። ከኦሮሚያ ክልል እስከ ፌደራል ፀጥታና የፓርቲ አባል፣ አክታቪስት ወዘተ ተደራጅተዋል። የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ኃላፊ ኃይሉ አዱኛ መረጃውን ለክልል አመራሮች ያደርሳል። የክልል አመራሩ የፌደራል ግብረኃይል ለሚባለው ይሰጣል። የፌደራሉ መግለጫ የሚያወጣው ይህ የኦሮሚያው ማፍያ ቡድን የሚሰራውን ነው።
የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ የፌደራል ፀጥታ አባላት፣ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ብልፅግና በሙሉ ስራቸው አማራን በጥቆማ ማሳፈን ነው። ይህ ስራቸው በፌደራልም በክልልም የተመሰገነ፣ እየተደገፈ ያለ ሆኗል። ቡድኑ ማን ይባላል? "ORO abbichuu team"
ኢመደበኛ አደረጃጀት ማለት ይሄ ነው። በአማራና ኦርቶዶክስ ጥላቻ የናወዘ ቡድን አማራን በሀሰት ፈርጆ የፌደራል ፀጥታ ያስራል። መረጃው ከአንከር ሚዲያ የተወሰደ ነው። ሄዳችሁ ተመልከቱት።
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በጸጥታ ኃይሎች ተይዞ ተወሰደ‼️
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ቅዳሜ ምሽት ሁለት ሰዓት ገደማ ግንቦት 12፤ 2015 ከመኖሪያ ቤቱ በጸጥታ ኃይሎች ተይዞ መወሰዱን የዓይን እማኞች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። ተመስገንን የወሰዱት በሁለት ፒክ አፕ ተጨነው የመጡ እና የፖሊስ ደንብ ልብስ የለበሱ የጸጥታ ኃይሎች መሆናቸውን ገልጸዋል።
እስከ ምሽት ድረስ ከቅርብ ጓደኞቹ የነበረው ተመስገን፤ በአዲስ አበባ ጃንሜዳ አካባቢ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በሚገባበት ወቅት፤ የግቢ ዙሪያው በጸጥታ ኃይሎች ተከብቦ ማግኘቱን የዓይን እማኞቹ ተናግረዋል።
ዘገባው የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ነው።
አቡነ አብረሃም እና አቡነ ጴጥሮስ በእኛ ዘመን የቤተክርስቲያን ህግ ከሚጣስ እና የቤተክርስቲያንን ስርዓት ያልተከተለ ሹመቶችን ከማፅደቅ ስልጣናችንን ብንለቅ ይሻላል ማለታቸውን ምንጮች ገለፁ።
ሰሞኑን እየተካሄደ ያለው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ የቀጠለ ሲሆን በብዙ አጨቃጫቂ ጉዳዮች ሳይቋጭ በመጪው ሰኞም ይካሄዳል። አዲስ በሚሾሙ ፓፓሳት ዙሪያ ብዙ አነጋጋሪ ጉዳዮች እየተነሱ ነው።
Update‼️
ዛሬ ጠዋት በጸጥታ ኃይሎች ከቢሯቸው የተወሰዱት ዲ/ን ብርሃኑ አድማሱ ተለቀቁ‼️
ዛሬ ጥዋት ከሥራ ቦታቸው <<ለጥያቄ ትፈለጋለህ>> ተብለው በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎ የተወሰዱት ዲ/ን ብርሃኑ አድማሱ መለቀቃቸውን አዲስ ማለዳ አረጋግጣለች፡፡
ዲ/ር ብርሃኑ በአሁኑ ሰዓት ወደ ቢሯቸው መመለሳቸውን አዲስ ማለዳ ያረገጋጠች ሲሆን፤ የጸጥታ ኃይሎች የት ወስደዋቸው እንደነበር ማወቅ አልተቻለም፡፡
ዲ/ን ብርሃኑ የሀገሬ ቴሌቭዥን ሥራ አስኪያጅና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ አሉ ከሚባሉ ታዋቂና ተጽዖኖ ፈጣሪ መምህራን መካከል አንዱ ሲሆኑ፤ ከሰሞነኛው የቤተክርስቲያኗ ወቅታዊ ጉዳይ ጋር በተገኛኘ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ሀሳባቸውን አስፍረው ነበር፡፡
የእስር ዜና‼️
የሀገሬ ቴሌቪዥን ሥራ አስኪያጅና ዕውቁ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መምህር ብርሃኑ አድማስ ዛሬ ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓም በፀጥታ ኀይሎች ከቢሯቸው መወሰዳቸውን ዋዜማ ከአይን እማኞች ሰምታለች። መ/ር ብርሃኑ የተወሰዱት "ለጥያቄ ትፈለጋለህ" ተብለው መሆኑንም ሰምተናል።
ዋዜማ ራዲዮ
መስጊድ በማፍረስና ሲኖዶስ በማተራመስ ኢትዮጵያን ማፍረስ እንጂ ታላቋን ኦሮሚያ መቀለስ አይቻልም።
ዛሬ በየወሕኒው ያጎርካቸውና ቤታቸውን እያፈረስክ ያባረርካቸው ወገኖችም ግንባር ፈጥረው መመለሳቸው አይቀርም።
(አሳዬ ደርቤ)
ከደቡብ ሱዳን በመነሳት የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ወደ ጋምቤላ ክልል ኑዌር ዞን የገቡ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ስምንት ሰዎችን ገድለው 13 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ማድረሳቸውን የጋምቤላ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ‼️
የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኡቶው ኡኮት እንዳሉት ታጣቂዎቹ ድንበር ጥሰው በመግባት ዛሬ ማምሻውን በማኩዌይ ወረዳ ቢልኬች ቀበሌ 3 ሰዓት ተኩል ገደማ ሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት አድርሰው በዋንቱዋ ወረዳ መተሀር ከተማ መካነየሱስ ቤተክርስቲያን ደግሞ ስምንት ሰዎችን ገድለው 11 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት አድርሰዋል ብለዋል።
ታጣቂዎቹ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያደርሱ የአካባቢው ማህበረሰብ ከአካባቢው ሚሊሻ ጋር በመሆን ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ አክለው ገልፀዋል፡፡
አቶ ኡቶው አክለውም “ክልሉ በአሁኑ ሰዓት የፀጥታ ሀይሉን በማቀናጀት ሰላምና ፀጥታ የማስከበር ስራውን እየሰራ ሲሆን ጥቃት አድራሾች ላይ እርምጃ ለመውሰድ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም አስታውቀዋል።
ድንበሩ ሰፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሌሎች አካባቢዎችም ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈጸም መንግስት ከሚያደርገው ጥረት በተጓዳኝ ህብረተሰቡ በንቃት አካባቢውን እንዲጠብቅ አቶ ኡቶው አሳስበዋል።
የመንግስት እግድ በማሕበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ላይ
ለመሆኑ ሕጉ ወይም አዋጁ ምን ይላል፣
መንግስት በእሁድ ደብዳቤ አርቅቆ፣ እሁድ ደብዳቤ ለመጻፍ ምን አተጋው?
***
እንደ ብሮድካስት አዋጁ ፣ ችግር ላለበቸው ( ችግር ቢኖር እንኳን)ሚድያዎች የመጀመርያ ው እርምጃ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ነው፡፡
በመቀጠልም፣ ሚድያው አስተያየቱን በጽሁፍ እንዲሰጥ ይጠየቃል፡፡ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያው ተሰጥቶት ማስተካከያ ካላደረገ ይታገዳል፡፡
ይህ እግድ በእሁድ እንዲህ ተቻኩሎ የወጣበት ምክንያት ሌላ ነገር ከኋላው ያለ ይመስላል።
ህጋዊ መንገዶችን ሁሉ ስቷል ኦርቶዶክሶች ነገሮችን በንቃት መከታተል አለባቸዉ በተለይ ነገ!!!
የሰው ልጆችን ምድራዊ ህይወት ለማሻሻል ብለው ፖለቲከኞችን ፊትለፊት ተጋፍጠው ወጣቶች የህይወት መስዕዋትነት በሚከፍሉባት ኢትዮጵያ ውስጥ መንፈሳዊ አባቶች መንፈሳዊ ሹመት ለመስጠት የዘር ፖለቲከኛውን የአብይ አህመድን ፈቃድ እና የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለማጣጣም ተቸግረው እየተጨነቁ ነው። የሚል ዜና መስማት እንደ አንድ ክርስቲያን" አምላኬ በዚህ ዘመን ለምን ፈጠርከኝ ?" ያስብላል።
(ይልቃል ጌትነት)
"…መሪ ኖረም አልኖረ፣ አባት ኖረም አልኖረ ምእመኑ ግን ለሰማእትነት ቆርጦ፣ ወስኖ እንዳለ አለ። ይሄ የአንድ የልደታ አጥቢያ የተዋሕዶ ሠራዊት ነው። የጥንት አይደለም ሁለት ሦስት ወር ቢሆነው ነው። አለ ሕዝቡ።
"…አባ ሩፋኤል ( የቀድሞው አምሳሉ) አቢይ አሕመድ፣ ደመላሽ ገብረ ሚካኤል፣ ሽመልስ አብዲሳ፣ ደመቀ መኮንን እና ብናልፍ አንዷለም እንዲያውቁት ይሁን።
"…ከኢትዮጵያ ሁሉም ነገር ተቆርጦ፣ ተቆርጦ አልቋል። ሰንደቅ ዓላማ ሳይቀር ተቆርጦ ወድቋል። እስልምና ኦሮሞ ዐማራ፣ ጴንጤነት ደቡብ እና ኦሮሞ ተብሎ ቤት ለይቷል። በኢትዮጵያ አሁን የቀረው ሕዝብን ከሕዝብ የሚያስተሳስረው ብቸኛው ገመድ ኦሮቶዶክሳዊነት ብቻ ነው። መናፍቅ አህዛብ ገዢዎቹ ከውስጥ ተኩላዎች ጋር ግንባር ፈጥረው እየባተሉ ያሉት ያንን የቀረ ብቻ ገመድ ለመበጠስ ነው።
"…ነገ ሰኞ የኢትዮጵያ ጉዳይ ይለይላታል። ጳጳሳቱ ያፈርሷታል ወይም እንደ ንስር አድሰው ይታደጓታል። የኢትዮጵያ የቀረው ብቸኛው የአንድነት ገመድ በቅዱስ ሲኖዶሱ እጅ ነው። ሕዝቡ ግን በያለበት እንደ ጸና አለ። ለሁሉም ነገር ዝግጁ ነው።
የማን ቤት ፈርሶ የማን ሊበጂ
የአውሬ መፈንጫ ይሆናል እንጂ
(ዘመድኩን በቀለ)
"ርዕሰ አንቀጽ"
"…በሽታ ህመሙን ያልተናገረ መድኃኒት አይገኝለትም። ማስታገሻ ካልሆነ በቀር ለታማሚ ይሄን ይሆናል የታመመው ተብሎም በግምት ፈውስ የሚሰጠው መድኃኒት አይታዘዝለትም፣ አይሰጠውምም። አደጋ አለው።
"…ባለፈው በጾመ ነነዌ መባቻ ላይ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሞኛል ብላ በይፋ የልጆቿን ርዳታ ጠይቃ ነበር። በሽታዎቿንም ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍሯ ድረስ አንድ በአንድ ዘርዝራም ለዓለሙ ሁሉ ይፋ አድርጋ ነግራን ነበር። በዓለሙ ሁሉ የሚኖሩ ልጇቿም፣ ወዳጆቿም፣ አድናቂዎቿም በሙሉ ለህመሟ መፍትሄ ነው ባሉት መንገድ ሁሉ ተረባርበውላታል። ጥቁር ከል የለበሱላት አሉ። የታሰሩላት አሉ። በሽታው ልጆቿን በሻሸመኔ፣ በዓለም ገና፣ በጅማ፣ በአሰበ ተፈሪ፣ በወለጋ በአዲስ አበባም ገሚሱን ለእስር፣ ገሚሱን ለመቀጥቀጥ፣ ጥቂት የማይባሉትን ደግሞ ለሞት ዳርጎ አልፏል። የማትሞተውን የቤተ ክርስቲያንን ሞት ከምናይ ብለው ልጆቿ በበሽታው ተጨፍጨፈው በሃላል ሰይሰቀቁ በጥብአት ሞተውላታል። በልጆቿ እስራት፣ ድብደባ፣ ከሥራ መፈናቀል፣ ሞትም ህመሙ ለጊዜው ያለፈ መስሎም ታይቷል።
"…አሁን በሽታው በጠነከረ መልኩ ዳግም ተከስቷል። ባለፈው ጊዜ ልጆቼ አሞኛል፣ አልቻልኩም፣ ደግፉኝ፣ ጸልዩልኝ ብላ ልጆቿን የወተወተችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ ግን ዝም፣ ጭጭ፣ ጮጋ ብላለች። ልጆቿ ናቸው ከመሪዎቿ በተባራሪ፣ በድብቅ የሚያገኙትን የህመሟን ዜና በሽኩሽኩታ የሚያወሩት። በለሆሳስ የሚያወሩት። ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወዘተረፈ እንደ ባለፈው ጊዜ አሁን ትኩስ መረጃም አይሰጡም። የቤተ ክርስቲያኗ ሚዲያ መሪ ፋንታሁን ሙጬ አስቀድሞ ወደ አሜሪካ እንዲሄድ ተደርጓል። ይመለስ ወይ እዚያው ፏ ሽር ብትን ይበል የታወቀ ነገር የለም። ስለዚህ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልሣን ሚዲያውም ዝም ብሏል። አፉም ተለጉሟል። ያ በየደቂቃው ሚሊዮኖች የሚጎበኙት የቤተ ክርስቲያኒቱም የሶሻል ሚዲያ ገፅ ጭጭ ብሏል። እናም የአደጋውን ጥልቀት የሚያስረዳ ጠፍቷል።
"…ቆይ ራሳቸው እንደባለፈው ለምን አይነግሩንም? ያለፈው ጊዜ በልደታ፣ በኡራኤል ብቻ መንገድ ዘግቶ በሽታውን ያስደገጠው ሕዝብ ዛሬም እኮ በቦታው አለ። እንደ የአዋሽ ወንዝ አልሰመጠም፣ አልተነነም እኮ። ምንድነው ዝምታው? አቡነ አብርሃም እንዲህ አሉ። አቡነ እገሌ እንዲህ አሉ፣ ከጎናቸው ልንቆም ይገባል ብሎ አቡኖቹ ሲናገሩ ያልሰማነውን ቃል ለምን እንድናጮህላቸው ተፈለገ? ምንድነው ያስፈራቸው? ይናገሩ። ወጥተው ይንገሩን። አልያ ግን የበሽታው ተባባሪ ገዳይ ቫይረስ ራሳቸውም ጭምር እኮ ናቸው። በአንደበታቸው ሳይናገሩ፣ ሳንሰማቸው በቱርጁማን፣ በአፈ ቀላጤ የሚነገርላቸው ጀብዱ ተቀባይነት የለውም። ኋላ ላይ እኔ እኮ እንዲህ ብዬ ነበር ብሎ መደስኮር ዋጋ የለውም። እኩል ነው ተጠያቂነቱ።
"…ወረርሽኙ መጀመሪያ የሚበላው ራሳቸውን ነው። የሚያጠፋው፣ የሚቀረጥፈው ራሳቸው ነው። ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአንድም በሌላም ምክንያት ትተርፋለች። ፈተናውንም በኩራት ትሻገረዋለች። እናንተ ግን ትበላላችሁ። ዘንዶው መጀመሪያ የሚውጠው እናንተኑ ነው። የበሽታው ፀባይ መጀመሪያ ከሕዝብ፣ ከደጋፊ ይለይሃል፣ ያጣላሃል፣ ያኮራርፍሃል። ከዚያ ብቻህን አግኝቶ ይቀረጥፍህሃል። ያኔ ብትጮህ ሰሚ የለህም። ስለዚህ አሁኑኑ ፍጠኑ። ኢትዮጵያን አንድ በማድረግ እስከአሁን ፀንታ የቀረችው ቤተ ክርስቲያን ብቻ ነበረች። እሷኑ ለመበጠስ በሽታው የሚያደርገውን ወረራ ለመከላከል ይቻል ዘንድ በአፈቀላጤ፣ በፌስቡክ እና በዩቲዩብ ደላላ የውትወታ ሥራ መሥራት ሳይሆን ራሳችሁ ተገልጻችሁ መግለጫ ስጡን። የምትሉትን እንስማችሁ። ልክ እንደ ዘመነ ነነዌው ከፈረሱ እፍ እንስማው። ይህ የእኔ የዘመዴ ጥሪም ጥያቄም ነው። አድማጭ ተመልካቾች የራሳችሁን ደግሞ አስፍሩ። እኔም በተራዬ በኮመንት መስጫ ሰንዱቁ ላይ አፍጥቼ ልጠብቃችሁ።
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው።
(ዘመድኩን በቀለ)
በቋሚ ሲኖዶስ የተቋቋመው ዐብይ ኮሚቴ የተሰጠው መግለጫ
<<በከፍተኛ ትዕግስት ስናልፋቸው የነበሩ አባቶች ዛሬም ቤተክርስቲያን ውስጥ ሆነው ቤተክርስቲያንን ሲገፉ በዝምታ የምናይበት ሂደት አይኖርም፡፡>>
ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ችግርን ለመቅረፍ በቋሚ ሲኖዶስ የተቋቋመው ዐብይ ኮሚቴ በኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሂደት ላይ መግለጫ አወጣ።
በአለፉት ሁለት ሦስት ቀናት በአባቶች ዘንድ ውይይት ተደርጎበት ስምምነት ላይ ሳይደረስበት የቀረው የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሂደትን አስመልክቶ በተደረገው ውይይት ላይ በአባቶች የተፈጠረው የሐሳብ መከፋፈልና አለመግባባት ሁኔታ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ለኮሚቴው በእጅጉ እያሳሰበው ይገኛል ሲል ከ10 በላይ ማኅበራትን የወከለው ኮሚቴው በመግለጫው ጠቅሷል።
በየጊዜው በሚነሱ ወሳኝ የቅድስት ቤተክርስቲያን አጀንዳዎች ውስጥ ለቅድስት ቤተክርስቲያን ጀርባቸውን የሚሰጡ፣ በቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ ሆነው ዓለማዊ አጀንዳ የሚያራምዱና ከዛሬ ነገ የቤተክርስቲያንን ፍቅርና ምህረት ተረድተው ወደልባቸው ይመለሳሉ በማለት በከፍተኛ ትዕግስት ስናልፋቸው የነበሩ አባቶች ዛሬም ቤተክርስቲያን ውስጥ ሆነው ቤተክርስቲያንን ሲገፉ በዝምታ የምናይበት ሂደት አይኖርም ያለው ኮሚቴው በዚህ ታሪካዊ ወቅት ለቅድስት ቤተክርስቲያን መቆም ሲገባችሁ እየሰማችሁ እንዳልሰማችሁ ሆናችሁ በዝምታ የምትመለከቱ አባቶችም ሆነ ዋነኛ የችግሩ አካላት የሆናችሁ አባቶች በእግዚአብሔርም በታሪክም በእኛም በልጆቻችሁ የሚያስጠይቃችሁ መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን ሲል አፅንዖት ሰጥቷል።
ቤተክርስቲያን ከማይጠፋ ዘር በክርስቶስ ደም የተመሠረተች እንጂ እንደ ፖለቲካ ምክር ቤት በዘር በጎሣ የተመሠረተች አይደለችም። ቤተክርስቲያን የሁሉም ለሁሉም ነች ያለው ዐብይ ኮሚቴው ዛሬ በወከባና በጫና ለተለየ ብሔርና ጎሣ ተለይቶ የኢጲስ ቆጶስ ሲመት ቢሰጥ ነገ በዚህ ሰበብ ቤተክርስቲያንን ለመከፋፈል ዘርና ቋንቋን መሠረት አድርጎ የሚከተለውን ጥያቄና በጥንታዊት ሐዋርያዊት ዓለም አቀፋዊት አንዲት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የተነጣጠረውን የፈተና እና የመከራ ማእበል መመለስም መዳኘትም ይከብዳል ብሏል።
ይህን ጽንፍ የወጣ አጀንዳ በድምጽ ብልጫ በማስወሰን ሕገ ቤተ ክርስቲያንን እና ቀኖናን በመጣስ መፍትሔ የሚያመጡ መስሎአቸው የሚተጉ አባቶችም ቤተክርስቲያንን ወደማትወጣው መከራና ፈተና እየገፏት እንደሆነ ሊረዱት ይገባል ብለን እናምናለን።
በዚህ መግለጫ ብፀዓን አባቶችንን በታላቅ ትህትና ዐቢይ ኮሚቴው ማሳሰብ የሚፈልገው ይህ አጀንዳ አስተዳደራዊ ሳይሆን ሃይማኖታዊ/ዶግማዊ እና ሥርዓታዊ/ቀኖናዊ አጀንዳ በመሆኑ በሕገ ቅድስት ቤተክርስቲያን አንቀፅ 19፡ 5፡ ሐ መሰረት በሙሉ ድምጽ እንጂ በድምፅ ብልጫ ስምምነት ተደርጎበት ውሳኔ ላይ ሊደረስ የማይገባው አጀንዳ መሆኑንም ኮሚቴው በሚገባ ያምናል፡፡
በተለይም ይህ አለመግባባት እየሰፋ መጥቶ ውሳኔው በድምጽ ብልጫ የሚደረግ ከሆነ ሕገ ቤተክርስቲያንን እና ቀኖና ጥሰትን ስለሚያመጣ፤ ውጤቱም በብፁዓን አባቶች መካከል ያለውን መከፋፈል አስፍቶ ቤተክርስቲያንን ወደ ከባድ ፈተና የሚያደርስ ጉዳይ በመሆኑ ብፁዓን አባቶች በፍፁም መከባበር፤ ምድራዊ እና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ፍጹም ጸያፍ እና የተወገዙ በሆኑ ጉዳዮች፣ዘርን፣ ቋንቋን፣ ጎጥን ፖለቲካን፣የግል ጥቅምንና ፍላጎትን ሳይሆን የረቂቃኑ እና ግዙፋኑ፤ የሰማያውያን እና የምድራውያን ልዩ ጉባኤ፤አንዲት የክርስቶስ አካል የሆነችውን ቅድስት ቤተክርስቲያንን ማዕከል በማድረግ ብቻ አንድ ልብ አንድ ሐሳብ ሆናችሁ በእርጋታ በመነጋገር ለቅድስት ቤተክርስቲያን የሚጠቅም ውሳኔ በአንድ ድምፅ ሰጥታችሁ እንደምትወጡና የአሁኑንም ሆነ የሚመጣውንም ትውልድ የመከራ ቀንበር እንደምታቀሉ ባለሙሉ ተስፋ ነን፡፡
መግለጫው ከቅዱስ ሲኖዶስ የምንጠብሸው ውጤት በማለት ዐራት ነጥቦችን ዘርዝሯል።
0ቢይ ኮሚቴው በጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም. ከተከናወነው ሕገ ወጥ የኤጲስ ቆጶሳት ሢመት ጋር በተያያዘ በቤተ ክርስቲያን ላይ የተጋረጠው አደጋ መነሻ አድርጎ የተቋቋመ ሲሆን ከ10 በላይ ማኅበራትን ማለትም ከሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት፣ ከነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የምዕመናን ኅብረት፣ ማኅበረ ቅዱሳን፣ ጴጥሮሳውያን ኀብረት፣ የጎልማሶች እና ወጣቶች ማኅበር፣ ከወልዳ ዳንዲ አቦቲ፣ ከደጆችሽ አይዘጉ ማኅበር፣ ከሕግ ባለሙያዎች እንዲሁም ከጠቅላይ ቤተ ክህነት የተለያዩ መምሪያዎች የተወጣጣ ነው።
(ማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን)
በመንግስት በጀት የሚሰራው አባ ቶርቤ እንዲህ ነው የሚያስበው።
ይህ ቡድን የኦሮሚያ ክልልና የፌደራል የኦሮም አመራር ያደራጀው ነው። ስሙም "oro abbichu" ነው። ኦርቶዶክስን፣ አማራን እንዲህ ነው የሚያስባቸው። "ምርጥ ስራ እየሰራ ነው።" ተብሎ መወደሱን በመልዕክት መለዋወጫው ተቀምጧል።
በዚህ ወቅት ኦርቶዶክስ ላይ እየፈፀመ ያለው ተግባር በዚህ ጥላቻው መሰረት ነው። የኦሮሞ የክልልና የፌደራል ፀጥታና የፓርቲ ሰዎች የተካተቱበት ቡድን ነው።
ከራያ‼️
ዛሬ በራያ መሆኒ የህወሃት አርሚ 24/ኮር1 ስብሰባ ነበር።
በዚህ ስብሰባ ላይ"በትግራይ ክልል የወታደራዊ ስልጠና እየተካሄደ ነው"(ከእነሱ ወታደር አንደበት የሰማነዉ)
ለይስሙላ የተወሰኑ ከባድ መሣሪያ ያስረከቡ ቢሆንም አብዛኛዉ በእጃቸው ነው ያለው ሲሉ ምንጮች ከስፍራው አድርሰዋል።
በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው ያለፈ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ቁጥር 20 ደረሰ‼️
በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ዛሬ ጠዋት በደረሰ የትራክ አደረጋ ህይወታቸው ያለፈ የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ብዛት 20 መድረሱ ተገለጸ።
መምህራኑን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ተሸከርካሪ ጋረ ዋሻ በተባለ አካባቢ መንገዱን ስቶ ገደል ውስጥ በመግባቱ እስካሁን የ20 መምህራን ህይወት ማለፉንም የመደ ዋለቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አህመድ ከሊል ተናግረዋል።
ህይወታቸው ካለፈ መምህራን በተጨማሪም 20 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳጥ መድረሱን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል።
የሞቱት መምህራን ከፍተኛ ልምድ እና በመማር ማስተማር ላይ ብዙ ልምድ ያላቸው ናቸው ተብሏል።
ኦሮሚያ (አርሲ ዞን)‼️
ዛሬ አዳሩን በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በቆጂ ከተማ ከ5:00 እስከ ሰባት ሰዓት ድረስ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ነበር። ተኩሱን የጀመረው እራሱን የኦሮሞ ነፃ አውጪ ሰራዊት ብሎ የሚጠራው ሲሆን በዚህ የተኩስ ልውውጥ አንድ የቀበሌ አመራር መገደሉን ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
የተኩሱ አላማ እስረኞችን ለማስፈታት ነበር ተብሏል።
በዚህም በፖሊስ ጣቢያ የነበሩ እስረኞችን አስለቅቀዋል፣ከፖሊስ አባላትም የሞቱ አሉ።