#ቻይና ጡረታ የወጡ የኔቶ አየር ሀይል አብራሪዎችን መቅጠሯ ተገለጸ‼️
ጡረታ የወጡ የአውሮፓ ሀገራት አየር ሀይል አብራሪዎች ከየትኛውም ሀገር ጋር የመስራት ህጋዊ መብት አላቸው ቢባልም ከቻይና ጋር መስራታቸው ሊቆም እንደሚገባ ተገልጿል ቻይና ጡረታ የወጡ የኔቶ አየር ሀይል አብራሪዎችን መቅጠሯ ተገለጸ፡፡
ዶቸቪለ የጀርመንን መከላከያ ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሆነ ቻይና የአውሮፓን ወታደራዊ ሚስጥሮችን ልታገኝ የሚያስችላትን ድርጊት እየፈጸመች ነው ተብሏል፡፡
ቻይናና አሜሪካ ወደ ጦርነት ካመሩ ለዓለም ከባድ ውድመት እንደሚሆን ተገለጸ
በርካታ የጀርመን፣ የብሪታንያ እና አሜሪካ የቀድሞ አየር ሀይል አብራሪዎች ከቻይና ጋር የስራ ውል ፈጽመው ወደ ቤጂንግ አምርተዋል ተብሏል፡፡
ይህም ቻይና ከነዚህ አብራሪዎች የአውሮፓን ወይም ኔቶን ወታደራዊ እውቀቶች እና ቴክኒኮችን በቀላሉ እንድታገኝ ያስችላታል የተባለ ሲሆን ድርጊቱ በአስቸኳይ ሊቆም እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
የቀድሞ የአውሮፓ ሀገራት የጦር አውሮፕላን አብራሪዎች በጡረታ ከተሰናበቱ በኋላ ከየትኛውም ሀገር ወይም ተቋማት ጋር የመስራት መብት ቢኖራቸውን ከቻይና ጋር መስራታቸው ግን ስጋት መሆኑን የጀርመን መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በመሆኑም ከቻይና ጋር እየሰሩ ያሉ የቀድሞ የጦር አውሮፕላን አብራሪዎች ውላቸውን እንዲያቋርጡ እና በቀጣይ ሌሎች ወደ ቤጂንግ እንዳያመሩ ሊከለከሉ ይገባልም ተብሏል፡፡
የኔቶ አባል ሀገራት በሲንጋፖር በተካሄደው የዓለም የደህንነት ጉባኤ ላይ ከመከሩ በኋላ የቻይና ድርጊት እንዳሳሰባቸው ተገልጿል፡፤
ቻይና በበኩሏ ከውጭ ሀገራት ባለሙያዎች ጋር መስራቴ አዲስ አይደለም ጡረታ ከወጡ ከቀድሞ የኔቶ ወይም የአውሮፓ ሀገራት አብራሪዎች ጋር ስሰራ ብዙ አመታትን አስቆጥሬያለሁ ስትል ምላሽ ሰጥታለች፡፡
የቻይና ጦር ከኔቶ እና ከአሜሪካ የጦር አባላት ስልጠናዎችን ማግኘት ከጀመረ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ አስቆጥሯል፣ ድርጊቱ ቻይና በምዕራባዊያን በጠላትነት ከመፈረጇም በፊት የነበረ እንደሆነም አክላለች፡፡
የ "ጉማ አዋርድ" አዘጋጅ ዮናስ ብርሃነ ትናንት ምሽት በስካይ ላይት ሆቴል ከተካሄደው የሽልማት ስነ ስርአት በኋላ ለእስር ተዳርጓል።
በስፍራው ከነበሩ ሰዎች በደረሰኝ መረጃ መሰረት ዮናስን ሲቪል የለበሱ ደህንነቶች ከምሽቱ 5 ሰአት ገደማ ከነባለቤቱ አስረው ወስደዋቸዋል። ባለቤቱ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ብትፈታም ዮናስ አንበሳ ጋራዥ አካባቢ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኝ ታውቋል።
በትናንትናው ፕሮግራም ላይ "ልጅ ማኛ" በሚል የምትታወቀው ቲክቶከር ባደረገችው ሜካፕ ምክንያት "ልጅቷን አምጡ" በሚል አዘጋጆቹ ተጠይቀው እንደነበር እና እስሩም ከእሱ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል በስፍራው የነበሩ ግለሰቦች እና ሌሎች ምንጮች አረጋግጠውልኛል።
የኔ ጥያቄ:
- ሜካፕ ተቀብቶም ይሁን ፒካፕ ተኮናትሮ ሀሳብን ሰላማዊ በሆነ መንገድ መግለፅ በቃ ተከልክሏል?
- የፕሮግራሙ አዘጋጅ የተለያየ ልብስ ለብሶ እና ሜካፕ ተቀብቶ ለሚመጣው የሀገር ህዝብ ሁሉ ሀላፊነት አለበት?
ኤሊያስ መሰረት
Shocking news‼️
በአፍሪካ ከ 1ሚሊዮን በላይ ሴቶች እንዳይወልዱ(infertile) እንዲሆኑ በማድረግ የአለም ጤና ድርጅት (WHO ) ከፍተኛ ሚና መጫወቱን The " children health defense" የተባለ ተቋም በቲውቲር አካውንቱ አሳውቋል።
ይሄን ያደረገው በዋናነት የህዝብ ቁጥር ለመቀነስ ሲሆን በአፍሪካ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ሴቶች በክትባት መልክ እስከመጨረሻው እንዳይወልዱ(infertile) ተደርገዋል ይላል ዶክመንተሪው።
በዚህም ላለፉት 10 አመታት በአፍሪካ መካንነት (infertility rate)እና የፅንስ ውርጃ(fetus abortion) በእጅጉ እየጨመረ መምጣቱን የኬንያው ዶክተር ስቴፈን ካንጃራ በጥናት የተደገፈ መረጃ ሰጥተዋል።
ለዚህ ደግሞ WHO በአፍሪካ ላይ በክትባት መልክ የሚሰጣቸው የወሊድ መቆጣጠሪያዎች ሙሉ መሃን የሆኑ ሴቶችን እንዲበራከቱ አደርጓል ብሏል።
ይህ መረጃ ኢትዮጵያን ይጨምራል።
ሸዋሮቢት‼️
በሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ቆቦ 06 ቀበሌ ትናንት ምሽት ሁለት የፓሊስ አባላት እና አንድ የአካባቢ ሲቪል ሰው ፣ባልታወቁ ግለሰቦች በጥይት ተመተው ህይወታቸው አልፋል።
በሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ፓሊስ ጽ/ቤት ላይ ቦንብ ተወርውሮ በሰው ላይ ጉዳት ባያደርስም ፣በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል ሲሉ ምንጮች ገልፀዋል።
አዲስ አበባ አብነት‼
በአዲስ አበባ በዚህ ምሽት ከአብነት እና ከሰባተኛ በርካታ ወጣቶች በፌደራል ፖሊስ ተይዘው መወሰዳቸውን ምንጮች ገልፀዋል።
«የጸጥታ ሃይሎች እያሰሩን ገንዘብ እየወሰዱና እያሰቃዩን ነው» የሸገር ከተማ ነዋሪዎች‼️
የቀድሞ ፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የነበረው አሁን የሸገር ከተማ አስተዳደር ተብሎ በዘንድሮ አመት ምስረታ ያደረገ ከተማ ነው። ከተማዋ ከተመሰረተችበት አላማዎች አንዱ ህብረተሰቡን በልማት ተጠቃሚ ማድረግ አንዱ ነው። ከተማዋ በስሩ የተለያዩ ክፍለ ከተማ እና ወረዳዎች ተዋቅራ ተመስርታለች።
ነገር ግን ዘረፋ፣ ማስፈራራት እና በዘፈቀደ ማሰር የተለመደ እየሆነ መምጣቱን ነዋሪዎች ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ተናግረዋል የህብረተሰቡ ቅሬታ በፋስት መረጃ በዚህ መልኩ ይቀርባል።
እነዚህ ድርጊቶች በዋናነት የሚፈጸሙት በጸጥታ ሃይሎች ማለትም በፖሊስ፣ ሚሊሻ፣ የወንጀል መርማሪዎችና የጸጥታ ሃይሎች መሆኑን ነዋሪዎች ለቢቢሲ መናገራቸውን ፋስት መረጃ ተመልክቷል።
በቡራዩ ከተማ ከ15 ዓመታት በላይ የኖረው ነጋሳ ለቢቢሲ እንደተናገረው በጸጥታ ሃይሎች ሁለት ጊዜ ተይዞ እንዲፈታ ገንዘብ መክፈሉን ይናገራል። የመጀመሪያ ቀን መጠነኛ የመኪና አደጋ ደርሶብኝ ወደ ሆስፒታል እየሄድኩ በሚሊሻ ተያዝኩ ከዛ ፖሊሶች በፓትሮል ይዘውኝ ሄዱ ምንም ሳልጠየቅ ታስሬ ቆየሁ ከዛ 20ሺ ብር ከፍዬ ወጣሁ ከወጣሁ በኋላ 10ሺ ብር ከፈልኩ በአጠቃላይ 30ሺ ብር መክፈሉን ነጋሳ ለቢቢሲ ገልፇል። የታሰርኩበትን ምክንያት ስጠይቃቸው ከተማ ቁጭ ብለህ ለሸኔ ሎጂስቲክ ታመቻቻለህ የሚል ምላሽ ሰጡኝ ነው የሚለው።
ሌላኛው አቶ ገምታ የተባለ አስተያየት ሰጪ ለቢቢሲ ሲናገር “የጸጥታ ሃይሎች ሰላማዊ ዜጎችን ማሰር እና ገንዘብ መቀበል የተለመደ ተግባር አድርገውታል። ወንጀል የፈፀመ አካል ከተያዘ እና ከተጠየቀ እኛም አንቃወምም። ነገር ግን ከዚያ ውጪ ይህ እየሆነ ነው” ይላል ጋምታ
ገምታ መንግስት ሰራተኛ ሲሆን ከስራ ወጥቼ ወደ ቤት እየሄድኩ እያለ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ታፍኜ ታሰርኩ ይላል በእስር ቤት ቆይታውም “ወንጀለኛ መርማሪዎች እና ፖሊሶች ሰዎች ከእስር ቤት ለመውጣት ገንዘብ እንደከፈሉ የሚነግሩበት ኮድ [ምልክት] አላቸው” ብሏል። ብዙ ሰዎች ለመልቀቅ ገንዘብ ከፍለዋል ይላል።
ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ነቢራ ይባላል በሸገር ከተማ የግል ስራ አለው ከታሰረ በኋላ 100,000 ብር እንዲከፍል ቢነገረውም ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆኑ ለአራት ወራት ያህል ታስሯል።
"መንግስት ለፖሊስ የሚከፍለው ህዝብ ለመጠበቅ ነው እንጂ ህዝብን ለመዝረፍ አይደለም" የፀጥታ ሃይሎች ዘረፋው የእለት ቋሚ ስራቸው እየሆነ ነው ብሏል።
ምርመራ ክፍል አስገብተው ገንዘብ ነው የሚጠይቁት እምቢ ካልክ ሸኔ ነህ፣ መሳሪያ ትነግዳለህ እያሉ የማታውቀውን ነገር ይለጥፉበሃል ብሏል ረቢራ።
ሁሉም ታሳሪዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩት ፍርድ ቤት ቀርበው እንደማያውቁ ግማሹ ከፍሎ እንደወጣ አልከፍልም ያለው ለወራት ታስሮ እንደተለቀቁ ነው የሚናገሩት።
ቢቢሲ የሸገር ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ሃላፊ ኮማንደር ሌንጂሶ ጆቴ ከነዋሪው በጸጥታ ሃይሎች ላይ ስለቀረበው ክስ ጠይቋል ተጠይቀው ይህን ብሏል "የሸገር ከተማ 12 ክፍለ ከተማ እና 36 ወረዳዎች ያሏት ሲሆን እስካሁን ድረስ እንዲህ አይነት ቅሬታ አላገኘንም" ብሏል።
ጃንሆይ ከ60 አመታት በፊት ለአዕምሮ ጤና ይሆን ዘንድ አማኑኤል ሆስፒታል ሰሩ። ከሳቸው በኋላ የመጡት የአዕመሮን ጤና ከመንሳት ውጪ የሰሩት የለም።
(ነገረ ስራችሁ ሊያሳብደን ነውና ማረፊያችንን ስሩልን 😏 )
ሙክታሮቪች ኦስማኖቫ
"የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ከፍ ሲል ኢትዮጵያዊ ዝቅ ሲል አማራ ነዉ" ኮኔሬል ደመቀ ዘዉዱ
በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ሁመራ እና ማይካድራ ከተሞች ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል። ሰልፈኞቹ የወልቃይት እና የራያ አማራ ማንነት ጥያቄን የርእስት ማስመለስ ስም በመስጠት ወደ ኋላ መመለስ አይቻልም፣ ሀገር ርእስት ነዉ፣ ለርእስት መሞት ደግሞ ክብር ነዉ ብለዋል። በበጀት ክልከላ የሚጣል ማንነት፣ በፈተና ብዛት የሚዝል አማራነት የለም ሲሉም አስገንዝበዋል።
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ ማለፊያዉ ለሰልፈኞቹ ባስተላለፉት መልእክት የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ሕዝብ አሁናዊ ኹኔታዉ ፈተና ያለበት መኾኑን ተናግረዋል። በተለይም ለረጂም ጊዜ የማንነት ጥያቄው መልስ ያልተሰጠው፣ በጀት እስካሁን ያልተለቀቀለት እንዲሁም በአካባቢዉ የፍትሕ ሥርዓት ያልተዘረጋለት መኾኑን አንስተዋል። እነዚህን መሰል ችግሮች እንዲፈቱም ጠይቀዋል።
በሰልፉ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ እና የሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ደመቀ ዘዉዱ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ከፍ ሲል ኢትዮጵያዊ ዝቅ ሲል አማራ ነዉ፤ የሕዝቡ የወሰን እና የማንነት ጥያቄም በተገቢዉ መልኩ ምላሽ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።
የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ሕዝብ ጥያቄ በዋለ ባደረ ቁጥር ለሐሰት ፕሮፖጋንዳ፣ ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት አድሏዊ ፍርድ እየተጋለጠ መሆኑንም አንስተዋል። እንደ ኢትዮጵያዊነታችን በጀት፣ እንደ አማራነታችን ደግሞ ማንነታዊ እውቅና እንዲሰጥ በዚህ ሰልፍ እጠይቃለሁ ብለዋል።
በአዲስ አበባ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለትግራይ መልሶ ማቋቋም ገንዝብ አዋጡ እየተባለ መሆኑን እና ይህን የማያደርጉ ተማሪዎች መታወቂያቸው ተይዞ ፈተና ላይ አትቀመጡም የሚል ጫና እየደረሰባቸው እንደሆነ ቤተሰቦቻቸው ለኢትዮ ኒውስ ተናግረዋል።
Читать полностью…የብልፅግና መከላከያ ሠራዊት የብራኑ ጁላ፣ የአበባው ታደሰ፣ የአቢይ አህምድ፣ የዶር አብርሃም ሠራዊት በየጫካው፣ በየ ገዳሙ እንዲህ ነው ንፁሐንን የሚረፈርፈው።
ለዚህ ነው መከላከያ ሠራዊቱን የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይ ዐማራ እና ትግሬው አይወክለኝም እያለ ያለው።
ወልቃይት‼️‼️
በወልቃይት ጠገዴ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በዚህ መልኩ ዝግጅት እየተደረገ ነው።
✔የማንነት ጥያቄያችን ይመለስ
✔የሁለት አመት በጀት ይለቀቅልን
✔ በወልቃይት ህዝብ ላይ ግፍ እና በደል የፈፀመው የቀድሞ የህወሓት አመራሮች ለፍርድ ይቅረቡ... በሚል ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል።
ወልቃይት‼️
በመጪው እሁድ በወልቃይት በጀት ይለቀቅ፣የማንነት ጥያቄ ይመለስ፣በወልቃይት ህዝብ ላይ ግፍ እና በደል የፈፀሙ የቀድሞ የህወሓት አመራሮች ለፍርድ ይቅርቡ...በሚል ሰልፍ እንደሚካሄድ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።
"…እስከአሁን ድረስ የሟቾቹ ቁጥር በውል አልታወቀም። የይሁዲና የእስላም ስም በዝቷል፣ የትኛውም እምነት ከኦሮሙማ አይበልጥም ያለው የሽመልስ አብዲሳና የአዳነች አበቤ ጦር በአቢይ አሕመድ ትእዛዝ ዛሬ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ሙስሊም ወንድሞቻችን በዚህ መልኩ በግፍ ሲጨፈጨፉ ውለዋል።
"…ከወራት በፊት በሻሸመኔ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆችን በግፍ ያለ ርህራሄ የጨፈጨፈው የኦሮሙማው ጦር ዛሬ ደግሞ በአንዋር መስጊድ በዚህ መልኩ ያለ ርህራሄ ድምጻችን ይሰማ ያሉ አማኞችን ሲረፈርፍ ውሏል።
"…ዐማራ ናቸው ተብለው በግፍ በተወገዱት ሃጂ ሙፍቲ ምትክ ወደ ሥልጣን የመጡት የኦሮሞው ተወላጅ የሃጂ ኢብራሂም ቱፋው መጅሊስም ዝምታን መርጧል። በፊት በፊት በሃጂ ሙፍቲ ይመራ የነበረው መጅሊስን ለማዋረድ፣ ለማዋከብ ሲባል በጽንፈኞቹ የኦሮሞ የወሃቢይ ኡስታዞች በእነ አህመዲን ጀበል፣ አቡበከር፣ ካሚል ሸምሱ፣ ወዘተ በአፈ ቀላጤአቸው ስልጤው ሙጂብ አሚኖ አማካኝነት በዐማራ ክልል በሁለት ሰዎች ዕለታዊ ግጭት ምክንያት የተነሣን ፀብ በማቀጣጠል ዐማራን ለማዋረድ፣ ፋኖን ለማሳቀል እንቅልፍ አጥተው ይባዝኑ፣ ይባክኑ የነበሩት ሁሉ ዛሬ ጠፍተዋል። ግብፅ ዴይሊ ጋዜጣም ዝም ብሏል። ቱርክም መግለጫ አላወጣችም። ገዳይ ኦሮሞ ስለሆነ ሁሉም ዝም፣ ጭጭ ብለዋል።
• የሞቱትን ነፍስ ይማር። ኦርቶዶክስና እስላሞቹ በየተራ ከሚበሉ ተነጋግረው በአንድነት ይሄን በላ የሆነ ገዳይ አረመኔ አራጅ አገዛዝ በጊዜ ቢያስወግዱ መልካም ነው የሚሉ መተርጉማንም አሉ። የሆነው ሆኖ መሄጃ፣ መድረሻ፣ መግቢያ መውጫ፣ መተንፈሻ ያጣው የኢትዮጵያ ሕዝብ ማንም ቀስቅሶት፣ ማንም ገፋፍቶት ሳይሆን ለራሱ ሲል መፍትሄ ያበጅለታል፣ የብልፅግናንም ፍጻሜ ያቀርበዋል ተብሎም ይጠበቃል።
• እህህ እስከ መቼ…? አለች አዝማሪዋ ጂጂ… በእውነት ግን እስከ መቼ…?
በሸገር ከተማ “ሕገ ወጥ ናቸው” የተባሉ መስጊዶችን የማፍረሱ ሥራ እንደሚቀጥል የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አስታወቀ‼️
656 ቤተ እምነቶች ሕገ ወጥ ናቸው ተብሏል።
ሸገር ከተማን ዘመናዊና በፕላን ብቻ ግንባታ የሚካሄድባት ለማድረግ ሕግ ወጥ ግንባታዎችን የማፍረሱ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሸመልስ አብዲሳ ገልፆል።
አስሩ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ባለቤትነት ማረገጫ የታሪክ ሰነዶች ‼️
አንደኛ፤
1420ዎቹ እንደተጻፈ የሚታመነው መጽሓፈ አክሱም በግልጽ እንደሚያሰረዳን የትግራይ ግዛቶችና ወሰኖች የሚከተሉት ነበሩ፡- ተምቤን፣ ሽሬ፣ ስራዮ (Seraye) ሐማሴን፣ ቡር (Bur) ሳማ (Sama) አጋሜ፣ አምባ ሰናዕት (Amba Senait) ገራልታ (Geralta) እንደርታ እና ሰሃርት (Sahart) ናቸው:: መጽሓፈ አክሱም ‹‹Ethiopia: the Land, Its People, History and Culture›› በዮሐንስ መኮንን የተጻፈውን እና John R. Short ‹‹The World through Maps: A History of Cartography›› (ገጽ 352 ይመልከቱ) መጽሓፍት እንደዋቢነት ይጠቀሳል፡፡
ሁለተኛ፤
1634 ዓ.ም የተጻፈው የእማኑኤል በሬዳ መጽሓፍ ‹‹Tractatus tres historico-geographici (1634): A seventeenth century historical and geographical account of Tigray, Ethiopia (Aethiopistische Forschungen) 1634» እንደሚያስረዳው የትግራይ ወሰን ተከዜ እንጂ ተከዜን ተሻግረው ያሉት ወልቃይትና ጠገዴ እንዳልሆኑ ብግልጽ ሰፍሯል፡፡
ሦስተኛ፤
በዘመነ መሳፍንት ኢትዮጵያን ጎብኝቶ የነበረው የጀምስ ብሩስ መጽሓፍም በግልጽ የሚናገረው የትግራይ ወሰን ተከዜ እንጂ ተከዜን ተሻግረው ያሉት ወልቃይትና ጠገዴ እንዳልሆኑ ያመላክታል፡፡ ‹‹Travel to discover source of the Nile Volume 3›› ገጽ 582 የሰፈረውን ማብራሪያ ልብ ይሏል፡፡
አራተኛ፤
በአጼ ዮሓንስ ዘመንም የታሪክ ማስረጃዎች የሚያስረግጡት ያንኑ ነው:: የትግራይ ደንበር ተከዜ ነው፡፡ ወልቃይትና ጠገዴ በጎንደር ስር እንደነበሩ በግልጽ ፈረንሳዊው ፕሮፌሰረ ሬክለስ ጽፎታል፡፡
አምስተኛ፤
በአጼ ቴዎድሮስ ዘመንም ወልቃይትም ሆነ ጠግዴ በትግራይ ስር አልነበሩም:: በወቅቱ ወደኢትዮጵያ የመጡ የእንግሊዛዊያኑን የጉዞ ማስታወሻዎች ያጤኗል፡፡
ስድስተኛ፤
በጣልያን ግዜም የትግራይ ወሰን በደቡብ እንዳምሆኒ፣ በደቡብ ምስራቅ አበርገሌ፣ በምዕራብ ሽሬና አዲያቦ ነበሩ እንጂ ወልቃይት ጠገዴ ዋጃ ኮረም እና መሰል ቦታዎች በትግራይ ስር አልነበሩም፡፡
ሰባተኛ፤
‹‹ወልቃይትንና ጠገዴን ወደ ጎንደር የከለሉት አጼ ኃይለሥላሴ ናቸው፡፡ ይህም በነብላታ ኃይለማርያም ረዳ መሪነት የተካሄደውን የቀዳማይ ወያኔን አብዮት ለመበቀልበስና ሕዝቡንም ለመቅጣት ነው›› የሚለው መሰረት የሌለው ማስተባበያ ነው፡፡ ከጣሊያን ወረራ በፊትም ሆነ በጣሊያን ወረረና ድህረ ጣሊያን የትግራይ ወሰን ያው ተከዜ ነበር፡፡
ስምንተኛ፤
የትህነግ መሪዎችና ከታሪክ ጋር የተፋቱ የትግራይ ምሁራን ወልቃይትን በተመለከተ ‹‹የህዝብ ቁጥርና በሚናገሩት ቋንቋ ነው ወልቃይትንና ጠግዴን ወደ ትግራይ የከለልነው›› ሲሉ ይከራከራሉ፡፡ በመሰረቱ ከሆነ የዘርና የቋንቋ ክልልን ለመጀመርያ ግዜ ኢትዮጵያ ላይ የመሰረተው ጣልያን ነው:: ጣልያን ዘርን መሰረት ያደረገ ካርታ ሲሰራ የራሱን የዘርና የቋንቋ ጥናት አድርጎ ነበር:: በዚህም መሰረት ወልቃይትና ጠገዴን ወደ ትግራይ ሳይሆን ያካለላቸው ወደ ጎንደር ነበር:: ይህ የሆነው ወልቃት ጠገዴ አማራ በመሆኑ ነው፡፡ ይሄ ታሪክ ከተፈጸመ አንድ ትውልድ እንኳን አላለፈውም:: ‹‹ጎንደሬው በጋሻው›› በሚለው የገሪማ ታፈረ መጽሓፍ ላይ እንደተመለከተው በጣሊያን ወረራ ጊዜ አርበኛ ሁነው በአካባቢው የተፋለሙት የጎንደር አርበኞች ናቸው፡፡
ዘጠነኛ፡-
በዚህ ዘመን ያሉ እውቅ ኢትዮጵያንና ቀጠናውን በተመለከተ በርካታ መጽሃፍትን ያዘጋጁ ፕሮፌሰሮች ምስክርነታቸው ሰጥተዋል፡፡ ለአብነት የካምብሪጅ ዩኒቨርስቲው ክሪስቶፈር ክላፕማን ‹‹Transformation and Continuity in Revolutionary Ethiopia›› በተሰኘ መጽሓፋቸው ላይ የትግራይ ደንበር ተከዜ እንጅ ከዛ ተሻግሮ እንደማያውቅ ገልጸዋል፡፡
አስረኛ፡-
ዛሬም ድረስ በህይወት ያሉት የአጼ ዮሓንስ የልጅ ልጅ ልዑል ራስ መንገሻ ስዩምም እንዳረጋገጡት ‹‹የትግራይ ወሰን ተከዜ እንጂ ተከዜን ተሻግረው ያሉት ወልቃይትና ጠግዴ አይደሉም›› ሲሉ ለእውነትና ለታሪክ ያላቸውን ከፍ ያለ ቦታ በአንደበታቸው መስክረዋል፡፡
ከዚህ በላይ የቀረቡ የታሪክ ማጣቀሻዎች በሙሉ የትግራይ ወሰን ተከዜ እንጅ ከዛ ተሻግሮ እንደማያውቅ ያረጋግጣሉ፡፡
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ለዘመናት በጎንደር ክፍለ ሀገር ዳባት አውራጃ፤ ቀደም ሲል ደግሞ በበጌምድርና ስሜን ጠቅላይ ግዛት ይተዳደር የነበረ እንጅ አንድም ቀን በትግራይ ተከዜን ተሻግሮ እንደማያውቅ ታሪክ ምስክር ነው፡፡
ከ1983 በፊት የወልቃይት-ጠገዴ ሰቲት ሁመራ የአማራ ርስትና ግዛት ነበሩ፡፡ "ትግሬ እንጅ ትግራይ ተከዜን ተሻግራ እንደማታውቅ" የትግራይ ተወላጆች የግንባታ ስራ፣ ለቤተ-ክርስቲያን አገልግሎት፣ እንዲሁም የግብርና ሥራ ሰርተው ለመመለስ እንጅ ለነዋሪነት ከተከዜ ምላሽ መጥተው እንደማያውቁ ታሪክ ምስክር ነው፡፡
በወታደራዊው የደርግ አገዛዝ ዘመን ወልቃይት-ጠገዴ በመጀመሪያ የኢህአሠ/ፓ ቀጥሎም የትህነግ ጦር ወደ ሱዳን መተላለፊያና የጦርነት ቦታ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ትህነግ በሽምቅ ውጊያ በአካባቢው መንቀሳቀስ ከጀመረበት 1971/72ዓ.ም ጀምሮ በነባሩ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ህዝብ ላይ ጥቃት ሲያደርስበት ቆይቷል፡፡ ይህ ጥቃት በይበልጥ መዋቅራዊ ጉልበት ያገኘው የወልቃይት ጠገዴ ግዛት በጉልበት ወደ ትግራይ ከተጠቀለለ በኋላ ነው፡፡
#ሰበር‼️
ኤርትራ ከኢትዮጵያ እና ከጅቡቲ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ዘጋች ‼️
ኤርትራ ከኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ጋር የሚያገናኟትን አካባቢዎች ዘግታለች ሲል የብሪታንያ መንግስት ማስታወቁን ዳጉ ጆርናል ዘግቧል። በኤርትራ የሚገኙ የታላቋ ብሪታንያ አካል የሆኑ ሀገራት ዜጎችም ሀገሪቱን ለቅቀዉ እንዲወጡ አሳስቧል።
ኤርትራ ድንበሯን የዘጋችበትን ምክኒያት ያላሳወቀዉ የብሪታንያ መንግስት ፤ ከሱዳን ጋር የሚያዋስናት ድንበር ክፍት መሆኑን እና ወታደራዊ እንቅስቃሴ የሚደረግበት እንደሆነ ገልጿል።
ኦም ሀጀር የተሰኘዉ እና ኢትዮጵያን ከኤርትራ ጋር የሚያዋስነዉ ቦታ ከተዘጉት አካባቢዎች አንዱ ሲሆን በሰሜኑ ጦርነት ወቅትም ሆነ ከጦርነቱ በኋላ ክፍት የነበረ መሆኑ ይታወቃል። የብሪታንያ መንግስት እንዳስታወቀዉ ከሆነ ግን ኤርትራ በዚሁ በኩል ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ጨምሮ በባድመ እና አዲ ክዋህላ የተሰኙ አዋሳኝ ቦታዎችም ዘግታለች ብሏል።
የብሪታንያ መንግስት ዜጎቹ ከኤርትራ ድንበር 25 ኪሎሜትር ርቀት ባላቸዉ ማንኛቸዉም አካባቢዎች እንዳይንቀሳቀሱ መክሯል። በኤርትራ የሚገኙ ዜጎቹም ሀገሪቱን በአፋጣኝ ለቅቀዉ እንዲወጡ ፤ ወደ ሀገሪቱ ለመጓዝ ያሰቡም ጉዟቸዉን እንዳያደርጉ መምከሩን ዳጉ ጆርናል ከመግለጫው ተመልክቷል።
የብሪታንያ መንግስት ክልከላዉን ለማድረጉ ያስቀመጠው ምክኒያት ባይኖርም በኤርትራ ግን የሽብር ጥቃት ሊፈጸም ይችላል የሚል ስጋት እንደሌለዉ ባወጣዉ መግለጫ ተናግሯል።
ወልቃይት‼
በወልቃይት በኩል በዛሬው ዕለት በ18 ተሳቢ፣ በ20 ኦራል ከባድ መሳሪያ የጫኑ ፤ ቀይቦኔት ለባሾች ጄኔራል ድንኩል በሚባል መሪነት ወደ ተከዜ ጫፍ አንቀሳቅሷል።
ጄኔራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ግዛቶችን በአስቸኳይ ለመመለስ ጥረት እያደረግን ነው ማለቱ ይታወሳል።
ጃንሆይ ከ60 አመታት በፊት ለአዕምሮ ጤና ይሆን ዘንድ አማኑኤል ሆስፒታል ሰሩ። ከሳቸው በኋላ የመጡት የአዕመሮን ጤና ከመንሳት ውጪ የሰሩት የለም።
(ነገረ ስራችሁ ሊያሳብደን ነውና ማረፊያችንን ስሩልን 😏 )
ሙክታሮቪች ኦስማኖቫ
በምስራቅ ጎጃም ዞን በአንቀጸ ብፁዓን ቅድስት ሥላሴ ገዳም በሚኖሩ መነኮሳት ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈፀሙን ኢሰመጉ አረጋገጠ‼️
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በአንቀጸ ብፁዓን ቅድስት ሥላሴ እና ተክለሃይማኖት ገዳም በአካባቢው የታጠቁ ቡድን እየሰለጠኑ ነው በሚል ምክንያት ከጥር 22ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ያስታወቀ ሲሆን በዚህም ንፁሀን እንደተገደሉ ገልጿል።
ከግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም 4:00 ሰዓት ጀምሮ ከፍትኛ የሆነ የከባድ መሳሪያ ተኩስ እየተደረገ እንደሆነና በገዳሙ የሚገኙ መናንያን መነኮሳት ላይም የሰበዓዊ መብቶች ጥሰት መፈፀሙን አስታውቋል።
ከጦርነት ቀጠናው ሸሽተው ለመሄድ የሞከሩ ነዋሪዎችም "ተምቻ" ተብሎ በሚጠራው ወንዝ ለጎርፍ አደጋ እየሆኑ እንደሆነም ኢሰመጉ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤትም ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም በገዳሙ ተፈጠረ ስለተባለው አደጋ እያጣራ እንደሆነ ቢያስታውቅም እስከ አሁን ድረስ የደረሰውን አደጋና ተፈፀመ ስለ ተባለው የሰብአዊ መብት ጥሰት የደረሰበትን ውጤት አላስታወቀም።
የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች የሚፈጽሙት ሰዎችን የመሰወር ድርጊት እንዲቆም ኢሰመኮ ጠየቀ‼️
በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣው ሰዎችን አስገድዶ የመሰወር ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጠየቀ፡፡
ኢሰመኮ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ፣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የደረሱትን አቤቱታዎችና ጥቆማዎች መነሻ ባደረገው ክትትል በርካታ የአስገድዶ መሰወር ድርጊቶች መፈጸማቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡
የዚህ ድርጊት ሰለባ የሆኑ አብዛኛውቹ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው፣ ከሥራ ቦታና ከመንገድ ላይ በመንግሥት የጸጥታና ደኅንነት ሠራተኞች ያለ ፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ ወዳልታወቀ ሥፍራ ተወስደው የተሰወሩ መሆናቸውን ኢሰመኮ ጠቁሟል፡፡
ከተሰወሩት መካከል የተወሰኑት ሲያዙ በወንጀል ተጠርጥረው የሚፈለጉ መሆኑ ተነግሯቸው ወደ መደበኛ ፖሊስ ጣቢያ ከተወሰዱ በኋላ የተሰወሩ ሲሆን፤ ከፊሎቹ ደግሞ ምንም ሳይነገራቸው በጸጥታ ኃይሎች ተወስደው የተሰወሩ ናቸው ተብሏል።
ራጉኤል አይደል ወይ የአንዋር ጎረቤት??,
ይሄንን አንድነታችንን ነዉ ሊያጠፉብን የመጡት::
ክርስቲያን እና ሙስሊም በአንድነት መቆም እና መታገል አለበት ለብቻ መታገል ትርፉ በየተራ ማለቅ ነዉ‼
አሜሪካ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ከሩሲያ ጋር መደራደር እንደምትፈልግ ገለጸች‼️
አሜሪካ በኑክሌር ጦር መሳሪያ ጉዳይ ከሩሲያ ጋር መደራደር እንደምትፈልግ አስታውቃለች። ሩሲያ የኑክሌር ጦር መሳሪያን ለጎረቤት ሀገራት ለማስታጠቅ መወሰኗ ዋሸንግተንን እንዳሳሰበ ተገልጿል።
በተመሳሳይ ባሳለፍነው ሳምንት የአሜሪካ ከፍተኛ ወታደራዊ መሪዎች ከቻይና ጋር እንደራደር ቢሉም ቻይና ውድቅ አድርጋለች።
Inbox👇
<<በዚህ ምሽት ፖሊስ መብራት አጥፍቶ በየቤቱ እየዞረ ወጣቶችን መያዝ ጀምረዋል።
✔በኒ መስጅድ አካባቢ
✔አባተ ሜዳ
✔ሱማሌ ተራ
✔መርካቶ ጋዝ ተራ
✔አብነት ጭድ ተራ >>
በአንዋር መስጂድ የሞቱት ወንድሞችና ቁስለኞቹ እየወጡ ቢሆንም ይህ ወንድማችን ግን መታወቂያ ስለሌለውና የሚያውቀው ሰው በመጥፋቱ እስካሁን እሬሳው አልወጣም።
የሟቾች ቁጥር አምስት ሳይደርስ እንዳልቀረ ተናግረዋል።
ብጹዕ አቡነ አትናቴዎስ የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የኅሊና እስረኛው መምህር ኃይለ ማርያም ዘውዱ በታላቁ ቦሩ ሜዳ ጉባኤ ቤት የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ መምህር፣ የአንቀጸ ብርሃን አንድምታ ትርጓሜ መጽሐፍ ደራሲ፣ የሞዓ ተዋሕዶ መሥራች፣ የወሎ ዩኒቨርስቲ የግእዝ ቋንቋ ትምህርት ክፍል መሥራችና መምህር እንዲሁም በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የድኅረ ምረቃ (2ኛ ዲግሪ) ተማሪ በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለፌደራል ፖሊስ ልከዋል።
Читать полностью…