ethio360media | Unsorted

Telegram-канал ethio360media - Ethio 360 Media

37564

ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር !!!

Subscribe to a channel

Ethio 360 Media

ደቡብ ወሎ‼️


በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ ልዩ ስሟ ቁጭብላ በሚባል አካባቢ ትናንት ለሊቱን የተኩስ ድምፅ ሲሰማ እንደነበር ታውቋል።

በዚህም በዛሬው እለት ፋኖዎች ወደ ወገልጤና ከተማ ዘልቀው ገብተዋል።

መከላከያ ሰራዊትም ካምፑን ለቆ ወጥቷል።

በመንግስት የፀጥታ ሀይል የተደፈረች ወጣት እንዳለችም በተደጋጋሚ ጥቆማ ደርሶናል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ጆ ባይደን የቻይናው ፕሬዝዳንት አምባገነን ናቸው ሲሉ ተናገሩ‼️


በአምባገነን መንግስታት እና በቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ መካከል የጎላ ልዩነት የለም ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን መናገራቸውን አለምአቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ይሄን ያሉት ከሰሞኑ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን በቻይና ቤይጂንግ የነበራቸውን ጉብኝት አጠናቀው ወደ ዋሽንግተን መመለሳቸውን ተከትሎ ነው፡፡
========={{========
President Joe Biden called China’s leader Xi Jinping a dictator, a day after top US diplomat Antony Blinken visited Beijing to stabilize bilateral relations that China says are at their lowest point since formal ties were established.

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የቀድሞዋ አፈጉባኤ ኬሪያ ኢብራሂም መረጃ በማጥፋታቸው የራያ አለማጣ የማንነት ጥያቄ እንዲጓተት ምክንያት መሆኑ ተገለፀ‼️


የራያ አለማጣ ማህበረሰብ የማንነት ጥያቄ እልባት እንዲሰጠው በሚል ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የላከው ደብዳቤ በቀድሞ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ኬሪያ ኢብራሂም አማካኝነት እንዲጠፋ ተደርጓል ተብሏል።

የአላማጣ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ሞገስ እያሱ፤ የራያ አላማጣ የማንነት እና የበጀት ጥያቄ ከ2011 ጀምሮ ለፌደሬሽን ምክርቤት ሲቀርብ እንደነበር ገልጸው፤ “የወቅቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ኬሪያ ኢብራሂም የማንነት ጥያቄውን ለማዳፈን በማሰብ ለምክር ቤቱ የገባው መረጃ እንዲጠፋ አድርገዋል" ተናግረዋል።


በዚህም ለምክር ቤቱ የገባው መረጃ እንዲጠፋ መደረጉ፤ የራያ አላማጣ ማህበረሰብ የማንነት ጥያቄ መፍትሄ ሳያገኝ ለአራት ዓመታት እንዲጓተት ምክንያት ሆኗል ነው ያሉት።


“አፈጉባኤዋ ስልጣን ከለቀቁ በኋላ በገባው ደብዳቤ መሰረት የማንነት ጥያቄው መልስ እንዲያገኝ የፌዴሬሽን ምክር ቤቱን ስንጠይቅ፤ መረጃው መጥፋቱ ስለተነገረን ቅጂውን በድጋሜ ማስገባታቸውን ጠቁመዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ከራያ አላማጣ‼️


የአላማጣ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ ላይ ነች።

የአሜሪካ ኢምባሲ ልዑካን ዛሬ ወደ አላማጣ ከተማ ያመራሉ።

ህዝቡ የማንነት እና ሌሎች ጥያቄዎችን ለልዑኩ ለማስረዳት ዛሬ 2:00 ጀምሮ ሰላማዊ ሰልፍ ይካሄዳል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ባሳለፍነው ቅዳሜ ጠዋት ከደብረጉራች ከፍ ብሎ በአሊዶሮ በታጣቂዎች ከታፈኑ ከ40 በላይ ሾፌሮች መካከል‼️


ከደ/ማርቆስ:-
1ኛ) ጌታቸው
2ኛ) እሙየ አጥናፉ
3ኛ ) አካሉ መራ

ከ#አማኑኤል :-
4ኛ) ተመስገን አስሬ
5ኛ) አብርሀም አንለይ
6ኛ) ሞላ አማኑኤል /ወርቅማ /

ከአዲስ ቅዳም:-
7ኛ) አቢዎት አዳሙ (ጎባው)
8ኛ) አዲሱ የሻለም
9ኛ) ፋሲካው አማረ
10ኛ) ደዊት ልመንህ(አብዲሌ)
11ኛ) ሰለሞን ማሩ
12ኛ) ምናየ

ከደጀን ከተማ
13ኛ) ውዱ

ከሉማሜ :-
14ኛ) ይሁኔ በላቸው
ከወጀል
15ኛ) ኢብራሂም
ረዳት ከደጀን ዙሪያ/ጉብያ/ ነዋሪ የሆኑት(ወንድማማቾች)
16ኛ) ፀገየ አስናቀ እና
17ኛ) ምንይለዋል አስናቀ ከታገቱት ውስጥ ይገኙበታል።

አጋቾቹ ለቤተሰቦቻቸው እየደወሉ አንድ ሚሊየን ካላመጣችሁ እንገድላቸዋለን እያሏቸው ነው።

የሚመለከተው የመንግሥት አካል እና የፀጥታ አካላት ዝምታን መምረጣቸው ያሳዝናል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ተንቤን‼️


በትግራይ ክልል "ተንቤን ክልላዊ ፓርቲ" በሚል መጠሪያ አዲስ ፓርቲ መመስረቱን እና ምርጫ ቦርድ የምዝገባ ፈቃድ መስጠቱን አሳውቋል።

የተንቤን ተወላጆች ክልል እንሁን የሚል ጥያቄም እያነሱ ነው ተብሏል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ራያ‼️


የራያ አላማጣን ጨምሮ ከአምስት ወረዳዎች ከ150ሺ በላይ ፊርማ አሰባስበው ለፌደሬሽን ምክር ቤት አቅርበዋል።

ይህ የህዝበ ድምፅ አቤቱታ አዲሱ በጀት በአማራ ክልል በኩል እንዲለቀቅ እና የማንነት ጥያቄያችን እልባት እንዲሰጠው ሲል ፊርማ አሰባሳቢው ኮሚቴ በደብዳቤው ላይ ገልጿል።

የፌደሬሽን ምክር ቤት የሚሰጠው ምላሽ ይጠበቃል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የ9 አመት ልጅን "እኔ ነኝ የገደልኳት" ብላ ቃሏን የሰጠችው የቤት ሰራተኛ በዋስ ተለቃለች‼️


እስከ ሰኔ 12/2013 ዓ/ም ድረስ ገና የ9 አመት ልጅ ነበረች የአርቲስት ገነት ንጋቱ የወንድም ልጅ ሳምራዊት ታገል ንጋቱ
የዛሬ ሁለት ዓመት በመኝታ ክፍሏ ሞታ ተገኘች።

በወቅቱ ቤተሰቦቿ በምን ምክንያት እንደሞተች ግራ ቢጋቡም ለቅሶ ላይ እያሉ የቤት ሰራተኛቸው እኔ ነኝ የገደልኳት ብላ ቃሏን ሰጠች።

ሁሉም ቤተሰብ ተደናገጠ ልጂት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ አርገው ለሲቪል ፖሊሶች አስረከቧት ታሠረች ፍርድ ቤት ስትቀርብ ግን ነገሩ ሁሉ ተቀየረ።

የሳምራዊትን ቤተሰቦች ልብ የሚሠብር ዜና ሰሙ ገዳይዋ ምንም ማስረጃ አላገኘንባትም ተብላ ተለቀቀች በአሁን ሰአትም የ9 አመት ልጅ ገላ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ተንደላቃ እየኖረች ትገኛለች።

አባትየው ያለንን መረጃ ብንሰጥም ነጻ ብለዋታል ከእዚህ በኋላ ምንም ማድረግ ስለማንችል እኛ ይቅር ብለናታል።

የአርቲስት ገነት ንጋቱ ወንድም ፍትህን የምናገኘው ከፈጣሪ ስለሆነ በልጃችን ስም ፋውንዴሽን ከፍተን በልጃችን ስም የተቸገሩትን እንረዳለን ለእዚህ ደግሞ ገነት ንጋቱን አምባሳደር አድርገናል ብለዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ሸዋሮቢት❗

ትላንት ማታ 1:00 አከባቢ በሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋሮቢት ከተማ መግቢያ ኬላ አካባቢ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። በተኩሱ የቆሰሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት አሉም ብለዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በዛሬው የጠለምት አማራ ሰልፍ የተሰማው ግልፅ አቋም‼

#የማንነት ጥያቄያችን በበጀት ክልከላ አይገታም!

#ሴራና የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ድጋሜ እልቂትን እንጅ ሰላምን አያመጣም!

#አማራነታችንና ኢትዮጵያዊ መንፈሳችን በክፋት መዶሻ ቢወገርም አይደበዝዝም!

#ጠለምት ሰሜን ጎንደር እንጅ ትግራይ አይደለም።

# አማራ ነን አልን እንጅ አማራ እንሁን አላልንም!

#በማንነትና ርስታችን አንደራደርም!

#ከጠለምት ተፈናቅሎ ወደ ትግራይ የሄደ ተፈናቃይ የለንም!

#ማንነታችን ደም፣ ታሪክ፣ የተፈጥሮ ችሮታ እንጅ ለምርጫ ሊቀርብ አይገባም!

#የጠለምት አማራ ማንነት ጥያቄ የፍትሕ ወዳድ ኢትዮጵዬውያን ጥያቄ ነው!

#ማንነታችን አማራ፣ ድንበራችን ተከዜ ነው።

#የማይገባንን አልፈን አንጠይቅም። የራሳችን አሳልፈን አንሰጥም።

#ለእንግዶች እንጅ ለወንጀለኞች ቦታ የለንም!

#አማራነታችንና ኢትዮጵያዊ መንፈሳችን በክፋት መዶሻ ቢወገርም አይደበዝዝም!

#የዋልድባ መነኮሳትን ጭፍጨፋ አንረሳውም!

#በመንግስት ኃይል ታጅቦ ለህወሓት የሚቀርብ የሎጅስቲክ ድጋፍ በአስቸኳይ ይቁም!

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ሩሲያ የኑክሌር ጦር መሳሪያዎችን በጎረቤት ሀገር ቤላሩስ ማስቀመጥ መጀመሯን ፕሬዝዳንት ፑቲን አረጋገጡ‼️

ፕሬዝዳንት ፑቱን ሁለም ነገር በእቅዳቸው መሰረት እየሄደ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህ ድርጊት ኔቶን እና አሜሪካን አሳስቧል ተብሏል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በኦሮምያ ክልል በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ትናንት ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የስምንት ሰዎች ህይወት ማለፉን ነዋሪዎችና የኪረሙ ወረዳ ኮምኒኬሽን አስታውቀዋል።  እነዚሁ ታጣቂዎች ዋስቲ በተባለች አንድ የገጠር ቀበሌ ውስጥ በርካታ የቁም እንስሳት መዝረፋቸውም ተነግሯል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ሰሜን ሸዋ‼️


በሰሜን ሸዋ ዞን ጅሁር ወረዳ አርሶአደሮች የማዳበሪያ አቅርቦት እጥረት በመከሰቱ ለዞኑ አቤቱታ አቅርበዋል።


የጅሁር ወረዳ ከብት ከማድለብ በተጨማሪ ከፍተኛ የሰብል ምርት የሚመረትበት ወረዳ መሆኑን ሁሉም ያውቀዋል።


የማዳበሪያ አቅርቦት ችግሩን ዞኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር በአስቸኳይ ችግሩን መቅረፍ አለበት። በዚህ ሰዓት አመራሩ ነው ወደ ገበሬው መሄድ ያለበት እንጂ ገበሬው ወደ አመራር መጥቶ ችግሩን የሚናገርበት ወቅት አይደለም።

(አዩዘሀበሻ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የ አርበኛ ዘመነ ካሴ አስቸኳይ መልእክት‼

Читать полностью…

Ethio 360 Media

መረጃ‼️


በምዕራብ ጎጃም ደምበጫ ከተማ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ መኖሩን ተከትሎ የሰው ህይወት ጠፍቷል።

ይህን ተከትሎ ደምበጫ፣ ጅጋ እና ፍኖተ ሰላም ላይ መንገድ መዘጋቱ እና ህዝባዊ ተቃውሞ ተደርጓል። ፍኖተ ሰላም ላይ 2 ወጣቶች ሲገደሉ ከ4 በላይ ቆስለዋል ተብሏል።


ትናንት ማታ 12:30 ጀምሮ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የፋኖ አባላት እና በመከላከያ ሰራዊት መካከል የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

መለኞቹ‼️😳


"መለኞቹ" ፊልም የተሠራላቸውን ፌደራል ፖሊሶች- የእነ ሽመልስ አብዲሣ ሸኔ አስሮ እያንደፋደፋቸው ነው።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በደብረ ኤልያስ በሚገኙ አራቱ ገዳማት ውስጥ አንድ መነኩሴ ብቻ መገኘታቸው ተገለጸ‼️


በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወረዳ ሥር ባሉ አራት ገዳማት ላይ በደረሰው ከፍተኛ ጉዳት፤ በገዳማቱ አንድ መነኩሴ ብቻ መገኘታቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስታውቃለች፡፡

በገዳማቱ ከግንቦት 18 እስከ 23/2015 ለተከታታይ አምስት ቀናት “የታጠቁ ኃይሎች በገዳሙ ውስጥ ይገኛሉ” በሚል በተደረገ ኦፕሬሽን እስካሁን ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካታ መነኮሳት መሞታቸውን፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓበርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የገዳማት አሥተዳደር መምሪያ ኃላፊ መጋቤ ካህናት አባ ሀብተጊዎርጊስ አሥራት ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡

ኃለፊው አክለውም፤ በአራቱም ገዳማት አቢያተ ክርስቲያናት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ለአዲስ ተናግረዋል፡፡ በዚህም በገዳሙ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች “ሕግ ማስከበር” ያሉትን ዘመቻ ከማካሄዳቸው በፊት በርካታ መነኮሳት እና አገልጋዮች ይኖሩ እንደነበር ገልጸው፣ የገዳማት አስተዳደር መምሪያው ወደ ሥፍራው ባቀናበት ወቅት የተገኙት አንድ መነኩሴ ብቻ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

“መሞታቸው ከታወቀው መነኮሳቱና አገልጋዮች ውጭ ሌሎቹ የት እንደገቡ አይታወቅም፡፡” ያሉት ኃላፊው፤ በገዳሙ ውስጥ ባለው ሰፊ የአትክልት እርሻ በርካታ ያልተቀበሩ አስከሬኖች መኖራቸውንና በአካባቢው ከፍተኛ የአስከሬን ሽታ መኖሩንም ተናግረዋል፡፡

የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች “በገዳሙ የታጠቁ ኃይሎች መሽገዋል” በሚል ኦፕሬሽን ቢያደርጉም፤ በተለያዩ ጊዜያት ሽፍታዎች የገዳሙን ንብረት ለመዝረፍ ወደ ሥፍራው ይመጡ ስለነበር፣ መነኮሳቱ ምሽግ ቆፍረው ንብረቱን ከዝርፊያ ለማዳን እና ሕይወታቸውንም ለመታደግ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ኃላፊው ተናግረዋል፡፡
በተደረገው ዘመቻ ጉዳት የደረሰባቸው አቢያተ ክርስቲያናት የሥላሴ፣ ኪዳነምሕረት፣ የኤልያስ እና የጊዎርጊስ መሆናቸውን በመጥቀስ፤ አቢያተ ክርስቲያናቱ የውጭ ክፍላቸው ጨምሮ ቅኔ ማሕሌቱ፣ ቅድስቱ እና ቤተመቅደሱ ላይ የደረሰው ድብደባ እጅግ ከፍተኛ መሆኑንም አስረድተዋል።
“በተለይ በኪዳነምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን ላይ የደረሰው ጉዳት ከኹሉም የከፋ ነው፡፡” ያሉት ኃላፊው፣ ንዋተ ቅድሳትን ጨምሮ የቤተ መቅደስ መገልገያዎች መውደማቸውን እና ጉልላቱም ተመትቶ መውደቁን ገልጸዋል።

አዲስ ማለዳ “በገዳማቱ ውስጥ ራሳቸውን “የኢትዮጵያ ዓለም ብርሃን” ብለው የሚጠሩ አካላት አሉ”” ተብሎ ስለሚነሳው ገዳይ ላነሳችላቸው ጥያቄም፤ “እነዚህ አካላት በትክክል በገዳሙ ውስጥ አሉ ለማለት ባያስደፍርም በአንዱ ቤተክርስቲያን ላይ የእነሱ አርማ ያለበት ሰንደቅ ዓላማ ታይቷል” ብለዋል።

አሁን ላይ በአራቱም አቢያተ ክርስቲያናት መንፈሳዊ አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ መቋረጡንም ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡ የተጎዱትን አቢያተ ክርስቲያናት መልሶ ለመጠገን እና የጉዳት መጠኑን በሚገባ ለማወቅ በመንበረ ፓትርያርክ፣ ጠቅላይ ቤተ ክህነት እና አገረ ስብከቱ የጋራ ውይይት እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የአለማጣ ከተማ ነዋሪዎች መንግስት የማንነት ጥያቄቸውን ሕጋዊ እንዲያደርግላቸው በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ‼️


የአለማጣ ከተማ ነዋሪዎች  የአማራ ማንነት ጥያቄቸውን መንግስት በሕግ እንዳረጋግጥላቸው በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀዋል።

የከተማዋ ነዋሪዎች  በሰላማዊ ሰልፉ አማራ ነን እንጂ አማራ እንሁን አላልንም፣ የፌደራል መንግስት ተቋማት ዲስትሪክት  ወደ ሰሜን ወሎ ዞን ይዛወሩልንና ሌሎች የተለያዩ መፈክሮችን አሰምተዋል።

ሳይፈልጉ በሀይል አካባቢያቸው ወደ ትግራይ ተካሎ በነበረበት ሰላሳ አመታት የሰው ልጅ ሊፈፅመው የማይችል ሰብዓዊነት የጎደለው ግፍ ሲፈጽምባቸው እንደነበር ገልፀው አሁን ላይ ግን በነፃነት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ተናግረዋል።

የማንነት ጥያቄያቸው ሕጋዊ ሆኖ  እንድረጋገጥላቸው በሰላማዊ ሰልፉ ጠይቀዋል ሲል የዘገበው የሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን ነው።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ራያ አላማጣ‼️


ነገ በራያ አላማጣ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደረግ ምንጮች ተናግረዋል።

ነገ የአሜሪካ ኢምባሲ ልዑካን ወደ አላማጣ ከተማ ያመራሉ ተብሏል።

በዚህም ህዝቡ የማንነት ጥያቄዎችን በግልጽ ለልዑካን ቡድኑ ለማሳየት ሲባል ሰላማዊ ሰልፍ ሊኖር እንደሚችል ገልፀዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ትግራይ‼️


ህወሃት ለሰኔ 15 የተዋጊዎቹን ሞት ለወላጆቻቸው መርዶ ለመንገር የያዘውን ቀጠሮ ሰርዟል።

በአንዴ ቢነገር አደጋ አለው በማለት በ4 ዙር የመርዶ መርሀግብር ለመተግበር አቅዷል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አማኑኤል ከተማ‼️


በደንበጫ እና በደብረማርቆስ ከተማ መካከል ላይ በምትገኘው አማኑኤል ከተማ ከፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት እስካሁን የአንድ ወጣት ህይወት መጥፋቱን መረጃ ደርሶናል፣ ሶስት ሰዎች ቆስለዋል፣የከተማ አስተዳደሩ ገቢዎች ፅፈት ቤትም ጉዳት ደርሶበታል።

ዛሬ ረፋዱን በከተማዋ የተኩስ ድምፅ ይሰማ እንደነበር ነዋሪዎቹ ገልፀዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ማቻከል‼️


በደብረማርቆስ እና ደንበጫ መሃል ላይ አማኑኤል አካባቢ መንገድ ተዘግቷል።

ከትናንት በስቲያ ከደብረጉራቻ ከፍ ብሎ አሊደሮ በሚባል አካባቢ በርካታ ሹፌሮች እና እረዳቶች ታፍነው በመወሰዳቸው ምክንያት ተቃውሞ ነው ተብሏል።

በተለይ ከጎጃም ከአዲስቅኝ እና ከአማኑኤል ብቻ ከ12 በላይ ሹፌሮች የእገታው ሰለባ መሆናቸው ነው ለአዩዘሀበሻ የገለፁት።

በታጋቾቹ ስልክ እየደወሉ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ አምጡ እንደተባሉ እየተናገሩ ነው።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ ሒዩማን ራይትስዎች ለሕወሓት ወግነዋል አሉ‼️


የወልቃይት ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አስተባባሪ እና የወቅቱ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የመብቶች ተሟጋቹ ሒዩማን ራይትስ ዋች ባወጣው ሪፖርት የቀረበባቸውን ክስ አጣጥለውታል፡፡


ሂዩማን ራይትስ ዋች ግንቦት 24፣ 2015 ባወጣው ሪፖርት በምዕራብ ትግራይ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላም በርካታ የትግራይ ተወላጆች በግዳጅ መፈናቀላቸውን፣ ብዙዎችም በእስር ላይ እንደሚገኙ እና ግድያዎችም እንደሚፈጸሙ በማመልከት ለዚሁ ተግባር ተጠያቂ ናቸው በማለት ከጠቀሳቸው ግለሰቦች መካከል ኮለኔል ደመቀ ዘውዱን በሥም ጠቅሷል፡፡

የመብት ተሟጋቹ ድርጅት በሪፖርቱ የኢትዮጵያ መንግሥት በዚህ ወንጀል ተጠያቂ የሚሆኑት ፀጥታ ኃይሎችን እና ባለሥልጣናትን ከሥራ በማገድ ምርመራ አድርጎ እንደ አግባቡ በሕግ ተጠያቂ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቦ ነበር፡፡

በዚሁ ድርጊት ሥማቸው የተጠቀሰው ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ ስለ ሪፖርቱ ተጠይቀው ‹‹የወልቃይት ጠገዴ አማራ ሕዝብ ለዘመናት ከፍተኛ ግፍ ሲፈጸምበት አይተው እንዳላዩ ሲያልፉ›› ኖረዋል ያሉ ሲሆን፣ ‹‹አሁን የራሳቸው አጀንዳ ሲሆን ግን ግለሰብ እስከ መወንጀል መድረሳቸውን ስመለከት የህወሓት ቃል አቀባይ እንጂ የመብት ተሟጋች ሆነው አልመጡም›› ሲሉ የመብት ተቆርቋሪ ድርጅቱን በወገንተኝነት ከሰዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የ“ኦነግ” ሸኔ ታጣቂዎች ከአዲስ አበባ 75 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ በምትገኝ ወረዳ አንድ ቀበሌ መቆጣጠራቸው ተገለጸ‼️


ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው እና በመንግሥት ኦነግ ሸኔ ተብሎ በአሸባሪነት የተፈረጀው ታጣቂ ቡድን አባላት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ዋጫሌ ወረዳ፣ አርብ ሰኔ 9/2015 ተኩስ ከፍተው አንድ ቀበሌ መሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውን አዲስ ማለዳ ከአካባቢው ነዋሪዎች ሰምታለች። 

በዚህም ታጣቂዎቹ በወረዳው ሥር ካሉ የገጠር ቀበሌዎች አንዷ የሆነችውን ጉምቢቹ ቀበሌ አርብ ዕለት ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥራቸው ሥር ማድረጋቸውን የተገለጸ ሲሆን፤ የቀበሌው ነዋሪም በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ናቸው ተብሏል።

በተጨማሪም በዕለቱ ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ገደማ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን 75 ኪሎሜትር እርቀት ላይ ከምትገኘዋ የወረዳው ከተማ ሙከጡሪ በመግባት ኹለት ሰዎችን አፍነው ሲወስዱ አንድ ሰው ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰው መሰወራቸው ተገልጿል።

በአካባቢውም ከሰላሳ ደቂቃ በላይ ከፍተኛ የተሰኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበር ነዋሪዎች ጨምረው ገልጸዋል።

የታጣቂ ቡድን አባላት በአካባቢው በተለይም ከአንድ ዓመት ወዲህ በስፋት እንደሚንቀሳቀሱና በፈለጉት ሰዓት በመምጣት ነዋሪዎችን አፍነው እንደሚወስዱ ነው የተገለጸው፡፡

ነዋሪዎቹን በተለያዩ ጊዜያት አፍነው ከወሰዱ በኋላም "ከ200 ሺሕ እስከ 1 ሚሊዮን ብር ክፈሉ" እያሉ እንደሚደራደሩ ነው የተገለጸው፡፡

ከአንድ ሳምንት በፊት የወረዳው የባህል እና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሌሊት ላይ በታጣቂዎች በመሳሪያ ተመትተው መገደላቸው የተጠቀሰ ሲሆን፤ የአካባቢው ነዋሪዎችም ከሚኖሩበት ቀዬ በየዕለቱ እንደሚፈናቀሉ ተመላክቷል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ጫንጮ❗

6 የሞኤንኮ ሰራተኞች ለሥራ ደርባ ሲሚንቶ ፋብሪካ በሄዱበት በሸኔ ታገቱ። ሸኔ ሰራተኞቹን ለመልቀቅ 6 ሚሊዮን ብር ክፈሉ ማለቱን ምንጮች ገልጸዋል።

በ8/10/2015 ሐሙሥ ዕለት ከቀኑ9:30 ከኳሪ(ቆላ) ሥራ ውለው ወደ መኖሪያ (ፋብሪካው) ሲመለሱ በፋብሪካውና ኳሪው መካከል ባለ አነሥተኛ መንደር አካባቢ ባለው ተራራ ሥር መታገታቸውን ነው ምንጮች የገለፁት።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

#በሰሜን ወሎ ዞን የሚገኙ ከ58 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች በረሀብ እየተሰቃዩ ነው‼️


በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ከተለያዩ የወለጋ ዞኖች በተለይ ከምስራቅ ወለጋ በብዛት የተፈናቀሉ ሰዎች፤ በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ የሰሜን ወሎ ዞን የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና መምሪያ ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል፡፡ 

የዞኑ የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና መምሪያ ኃላፊ ዓለሙ ይመር፤ በሰሜን ወሎ ዞን አጠቃላይ የተፈናቃይ ቁጥር ከ58 ሺሕ 600 በላይ መድረሱን ተናግረዋል።       

ከአጠቃላይ ተፈናቃዮች ውስጥ 18 ሺሕ 213 የሚሆኑት በዞኑ ባሉ ዘጠኝ መጠለያ ጣቢያዎች እንደሚገኙ ጠቅሰው፤ ቀሪዎቹ ደግሞ በተለያዩ አካባቢዎች በህብረተሰቡ ውስጥ ተበትነው እንደሚገኙ ገልጸዋል።

የተፈናቃዮቹ ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ እንደመጣ እና ይህ ዘገባ እየተጠናቀረ ባለበት ሰዓት ብቻ 246 ተፈናቃዮች ወደ መጠለያ ካምፑ እየገቡ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡

በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮች በብዛት ሴቶች፣ ሕጻናት እና አረጋዊያን መሆናቸውን የጠቆሙት ኃላፊው፤ ተፈናቃዮች የምግብ፣ የመድኃኒት፣ የአልባሳት እና የመኝታ አገልግሎት እያገኙ እንዳለሆነ ተናግረዋል፡፡
በተለይም ሀብሩ ወረዳ ጃራ ቀበሌ በሚገኘው መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ከ10 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች መኖራቸው ተጠቁሟል።

የጃራ መጠለያ ጣቢያ የተፈናቃዮች ተወካይ ሲሳይ መላኩ ተፈናቃዮቹ ካለፉት ኹለት ዓመታት ጀምሮ ከተለያዩ የወለጋ ዞኖች በተለይም ከምስራቅ ወለጋ በተፈጠረው የሰላም ችግር ምክንያት ተፈናቅለው በመጠለያ ካምፑ የሚገኙ ናቸው ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡
አክለውም፤ ተፈናቃዮቹ ሐሙስ ሰኔ 8/2015 ያሉበትን አስቸጋሪ ሁኔታ መንግሥት እንዲያይላቸው እና ድጋፍ እንዲያደርግላቸው በዚያው በካምፑ አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን እና ድምጻቸውን ማሰማታቸውንም አስረድተዋል፡፡

ሆኖም በአካባቢው የነበሩ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ተፈናቃዮቹን በኃይል ወደ መጠለያ ጣቢያቸው እንደመለሷቸው ነው ኃላፊው የገለጹት።

ከዚህ ቀደም በተለያዩ አካላት ሲደረግ የነበረው የሰብዓዊ ድጋፍም አሁን ላይ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ከቆመ ከሦስት ወራት በላይ ማስቆጠሩን ጠቅሰዋል።

ተፈናቃዮቹ በረሃብ እና በበሽታ ክፉኛ እየተሰቃዩ መሆኑን ጠቁመው፤ በአስጊ ሁኔታ ላይ ያለውን የተፈናቃዮች ሕይወት ለመታደግ መንግሥትና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የትግራይ ታጣቂዎች በአንድ ሳምንት ውስጥ በጠለምት አምስት ንጹሃን ሰዎችን መግደላቸው ተገለፀ‼️


በአማራ እና ትግራይ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በሚንቀሳቀሱ የሕወሓት ታጣቂዎች ከባለፈው ግንቦት ወር መጨረሻ ጀምሮ እስከ ትናንት ሰኔ 08/2015 ድረስ ባሉት ቀናት አምስት ንጹኃን ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ፡፡

በሰሜን ጎንደር ዞን የምዕራብ ጠለምት ወረዳ ሰላም እና ደህንነት ኃላፊ አለባቸው አለሙ፤ በጠለምትና ተከዜ ዙሪያ በሚንቀሳቀሱ በርካታ የሕወሓት ታጣቂዎች ንጽሃን መገደላቸውን እና ብዙዎችም መፈናቀላቸውን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

ኃላፊው አክለውም፤ በተከዜ አዋሳኝ የሚገኙ የጠለምት ነዋሪዎች በሕወሓት ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ትንኮሳ እየተፈጸመባቸው መሆኑን ገልጸው፤ የሕወሓት ኃይሎች መድፍን ጨምሮ ሞርታር፣ ዙ-23 እና ሌሎች ከባድ መሳሪዎችን ታጥቀው እንደሚንቀሳቀሱ ጠቅሰዋል።

“ታጣቂዎቹ ያለምንም ምክንያት ንጹሃን የአማራ ተወላጆችን ለይተው እያጠቁ ነው፡፡” ያሉት ኃላፊው፤ ነዋሪዎቹ በሚደርስባቸው ትንኮሳ ከቀያቸው እየተፈናቀሉ መሆኑንም ገልጸዋል።

እንዲሁም በምስራቅ ጠለምት ወረዳ ሥር የሚገኙት ሜዳ፣ ምድረ አምሾ፣ እና ደገብራይ የሚባሉ ሦስት ቀበሌዎች አሁንም ድረስ በሕወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ሥር በመሆናቸው ሕብረተሰቡ ለከፋ ችግር ተጋልጧል ነው የተባለው።

የጠለመት አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ ጸጋዬ እሸቴ በበኩላቸው፤ ትጥቅ ያልፈቱ እና በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የሕወሓት ኃይሎች በተደጋጋሚ በሚያደርሱት ጥቃት ነዋሪዎች እየተሰቃዩ ነው ብለዋል፡፡
አክለውም፤ የሕወሓት ኃይሎች በዋልድባ ገዳም እና መነኮሳት ላይ ሳይቀር ጥቃት እያደረሱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ስለሆነም የሕወሓት ታጣቂዎች በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ እያደረሱት ያለውን ማንነት ተኮር በደል ለማውገዝ በጠለምት እና አካባቢው በመጭው እሁድ ሰኔ 11/2015 ሰላማዊ ሰልፍ ሊደረግ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
እንዲሁም የሰልፉ ዓላማ በሕወሓት የታሰሩ የጠለምት አማራ ተወላጆች በአሰቸኳይ እንዲፈቱ ብሎም በሕወሓት የተያዙ ሦስት ቀበሌዎች እንዲለቀቁ ለመጠየቅም ነው ተብሏል።
በመጨረሻም በጠለምትና ዙሪያው በሚገኙ ምዕራብ ጠለምት፣ ምስራቅ ጠለምት፣ አዲርቃይ እና ማይጸብሪ ወረዳዎች መንግሥት በአስቸኳይ በጀት እንዲመድብላቸውም ተጠይቋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

አንድ የአይናችን ማረፊያ፣ የባንዲራችን ተሸካሚ፣ የጥቁር ህዝቦች የስኬት ምልክት እና የውጭ በር ከፋቻችን የሆነው አየር መንገዳችን ላይ ደግሞ ምን ታስቦ እንደሆነ አልገባኝም።
ዛሬ በደረሰኝ የተረጋገጠ መረጃ መሰረት የአየር መንገዱ የቀድሞው ስራ አስፈፃሚ፣ እስከ ሁለት ቀናት በፊት ደግሞ የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት አቶ ግርማ ዋቄ ካለፍላጎታቸው በመንግስት ከስራቸው እንዲነሱ ተደርገው በምትካቸው የአየር ሀይል ጀነራል ተሹመዋል።
አቶ ግርማ በደቡብ አፍሪካ አየር መንገድ ለአመራርነት በ20 ሺህ ዶላር የወር ደሞዝ ሲጠሩ "እኔ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ አባል ነኝ፣ የጥቅም ግጭት ሊፈጠር ስለሚችል ይቅርብኝ" ብለው ሀገራቸውን ያስቀደሙ በአቪዬሽን ዘርፍ እጅግ የካበተ ልምድ ያላቸው ግለሰብ መሆናቸውን የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፣ በስማቸውም በየአመቱ ሽልማት ይሰጣል።

የጦር ጀነራልን ንግድ ላይ መሾም ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል በሜቴክ ታይቷል፣ በዛ ላይ የቦርድ ሰብሳቢ ከአውሮፕላን ግዢ እስከ ሰፋፊ የስትራቴጂ እቅዶች ላይ ውሳኔ የሚሰጥ ቁልፍ አካል ነው። በአየር መንገድ እና በአየር ሀይል መሀል ሊኖር የሚችል የማኔጅመንት መሳሳብ እና የጥቅም ግጭት በራሱ ማሰብ ይቻላል።

ሲጀምር፣ በቅርቡ በነበረው አስከፊ ጦርነት ወቅት በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ስሙ በብዙ የሚነሳ ተቋምን ሀላፊ የስኬታማ አለም አቀፍ አየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ አርጎ መሾም ምን ይፈይዳል? ሲቪል ሆኖ ብቃቱ እና ልምዱ ያለው ሌላ ሰው ጠፍቶ ነው?

አላማው ምን እንደሆነ ግልፅ ባይሆንም ዝም ማለት ግን ይከብዳል።

(ኤሊያስ መሰረት)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

"ትጥቅ አይፈቱም" ዶ/ር ደብረጽዮን❗👇


ከሶስት ቀናት በፊት ጌታቸው ረዳ እና ዶክተር ደብረፂዮን ከትግራይ የዲያስፖራ አባላት ጋር በ zoom ውይይት አካሂደዋል። በዚህ ውይይት ላይ ጌታቸው ረዳ በትግራይ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፀሙ አካላትን ተጠያቂ ለማድረግ እንሰራለን ያለ ሲሆን ከትግራይ ዲያስፖራ በኩል ለምን ከብልፅግና(አብይ አህመድ) ጋር ትሰራላችሁ የሚል ጥያቄ የተነሳላቸው ሲሆን "ግንኙነት አቋርጡ አይባልም፣እኛ የምንሰራውን እንሰራለን፣ እናንተም ግፉበት የሚል ምላሽ ሰጥቷል።
የኤርትራ ሰራዊትን በተመለከተ ከፌደራል መንግሥት ጋር ተናጋግረናል፣ በዚህም የኤርትራ ሰራዊት ከትግራይ ግዛቶች እንዲወጣ ከስምምነት ደርሰናል ሲል አስረድቷል።
ዶክተር ደብረፂዮን ደግሞ አሁን ሰላም ስለሆነ ነው እንጂ ለታጣቂዎቻችን አስፈላጊውን ስንቅ እና ሎጂስቲክስ እናሟላለን። ትጥቅም አይፈቱም ሲል ተደምጧል።
የዲያስፖራ አባላቱ በርካታ ገንዘብ አዋጥቶ እንደላከ እና በዚህ ለተሳተፉ አካላት እውቅና እንደሚሰጡ ተናግረዋል።
ህወሃት በጊዜያዊ አስተዳደሩ ውስጥ 80% ድርሻ አለው፣ስጋት እንዳይገባችሁ ብሏል።
እንዲሁም ህወሃት የህገደንብ (መተዳደሪያ ደንብ) ማሻሻያ እንደሚያደርግ እና አዳዲስ አመራሮች ወደፊት እንደሚመጡ ዶክተር ደብረፂዮን ለዲያስፖራው አባላት አስረድተዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

"በሌላ አርቲስት የስነ ጥበብ ተቃውሞ የተነሳ ዮናስ ብርሃነ መዋን ማሰር እና በዋስ የመፈታት መብት መከልከል ሕግን የጣሰ እና ተቀባይነት የሌለው ነው።" የኢሰመኮ ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ‼️


በሌላ አርቲስት የስነ ጥበብ ተቃውሞ የተነሳ ዮናስ ብርሃነ መዋን ማሰር እና በዋስ የመፈታት መብት መከልከል ሕግን የጣሰ እና ተቀባይነት የሌለው ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ ገለጹ።

ኮሚሽነር ዳንኤል በፌስቡክ ድረ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ ባሳፍነው አርብ ሰኔ 2/2015 በፖሊስ በቁጥጥር ሥር የዋለው የፊልም አዘጋጅ ዮናስ ብርሃነ መዋ ከእስር እንዲለቀቅ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም፤ በሌላ አርቲስት የስነ ጥበብ ተቃውሞ የተነሳ ዮናስ ብርሃነ መዋን ማሰር እና በዋስ የመፈታት መብት መከልከል ሕግን የጣሰ እና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ገልጸዋል። የአርቲስቷ ስነ ጥበብ ተግባር በነፃነት የመናገር መብት አካል እንደሆነና ዮናስ ብርሃነ መዋ በፍጥነት ከእስር ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቅ ሲሉም ጠይቀዋል።

የ"ጉማ አዋርድ" አዘጋጅ ዮናስ ብርሃነ አርብ ምሽት በስካይ ላይት ሆቴል ከተካሄደው የሽልማት ሥነ ስርዓት በኋላ በመንግሥት የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋሉ ይታወሳል።

Читать полностью…
Subscribe to a channel