ethio360media | Unsorted

Telegram-канал ethio360media - Ethio 360 Media

37564

ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር !!!

Subscribe to a channel

Ethio 360 Media

ጎጃም‼️


በምስራቅ ጎጃም ዞን በእናርጅ እናውጋ ወረዳ ዛሬ ከፍተኛ ውጊያ ሲካሄድ ነው የዋለው።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ጋዜጠኛ ተመሰገን ደሳለኝ ታስሯል‼️

ዛሬ ሰኔ 20/2015 በሁለት ፖትሮል
መኪና በመጡ የፌደራል ፖሊሶች ከቤቱ ተወሰዷል።

12: 30 ላይ የመጡት የተመሰገን አሳሪዎች እስካሁን የት እንደወሰዱት ማወቅ አልተቻለም።
#Ethiopia

ሰኔ 20/2015

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የጥንቃቄ መረጃ ነው

"…ወደ ዐማራ ክልል ከዐማራ ፋኖ ጋር ይዋጉ ዘንድ የሚላኩ የደቡብ ልጆች በሙሉ ማለት ይቻላል እኛ ዐማራ ላይ አንተኩስም በማለታቸው የብራኑ ጁላ አመራር ደንግጧል። ጥቂት የማይባሉም ከነሙሉ ትጥቃቸው ወደ በረሃ ተቀላቅለዋል፣ ጠፍተው ወደ ቀያቸው ተመልሰው አደረጃጀት የፈጠሩም እንዳሉ ተሰምቷል። ጥቂቶችም በሰራዊቱ አዛዦች መረሸናቸው ተሰምቷል።

"…በዐማራ ክልል አሁን በብቸኝነት ከፋኖ ጋር እየተዋጋና እየረገፈ ያለው የኦሮሞ ወታደር ነው። እናም ይሄን ያዩት አዛዦች "የመከላከያ ሠራዊት ስብጥር (በብሔር ቅልቅል) እንዲሆን እንሻለን በማለታቸው ምክንያት ይሄው እንዲፈጸም የሚል ትዕዛዝ አውርደዋል።

"…የደቡቦች እንዲህ ከዐማራ ጋር ማበር ያስቆጣቸው የመከላከያ አዛዦች በደቡብ እና በዐማራ መካከል ሽብልቅ ለመክተት ልክ እንደ ትግራዩ አሁን በሃገር ደረጃ ለሚደረገው መርዶ ደቡቦችን በሚያረዱበት ጊዜ እገሌ የሚባለው ወታደር የሞተው በዐማራ ክልል በፋኖ ነው እየተባለ እንዲነገር እና ሕዝቡ በዐማራ ላይ ጥርሱን እንዲነክስ ሊያደርጉ እንዳቀዱ ነው የሚነገረው።

"…ከዐማራ ጋር በሚደረገው ኢ ፍትሃዊ ጦርነት የኦሮሞ ልጆችም ምንም ጥቅም አያገኙም። በዐማራ የሚደረገው ጦርነት ዐማራን አንድ የሚያደርገው፣ ሌሎች ብሔር ብሔረሰቦችም ነግ በእኔ ብለው ከዐማራ ጎን የሚቆሙበት መልካም ዕድል ለዐማራ የሚያመጣበት፣ የተኙ፣ ዳተኞች፣ ቸልተኛ ዐማሮች የሚነቁበት፣ ባንዳና ሆዳም አቃጣሪ የዐማራ ሾተላዮችም የሚጸዱበት፣ የኢትዮጵያ ትንሣኤም የሚፈጥንበት ነው ዐማራ የሚካሄደው ጦርነት። ይኸው ለሽሽ ባዩ ጎጃም እንኳ እንደ ጋለ ብረት ተቀጥቅጦ በሁለት ወገን የተሳለ ሰይፍ ሆኖ የለም እንዴ?

Читать полностью…

Ethio 360 Media

#ሰበር‼️

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ገለፁ‼️


የስራ ሀላፊነትን በፈቃድ ስለመልቀቅ

በ2011 ዓ.ም ታህሳስ ወር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ በመሆን ስራዬን ስጀመር ተቋማችንን ተአማኒ እና ራሱን ችሎ ምርጫን ማከናወን የሚችል ተቋም ለማድረግ በማለም ነበር። ባለፉት  አራት አመት ከስድስት ወራት ሶስት ህዝበ ውሳኔዎችን እና አገራዊ ምርጫን በማካሄድ እና ፓለቲካ ፓርቲዎችን በማስተዳደር የተሰጡኝን ሃላፊነቶች  ህጋዊነት ፍትሀዊነት እና ቅንነትን በተከተለ ሁኔታ ለማከናወን ስጥር ቆይቻለሁ።

ሆኖም ጤናዬን በሚገባ ለመጠበቅ የረጅም ጊዜ እረፍት የሚያስፈልገኝ ሆኖ በመገኘቱ ከ ነሀሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቦርድ ሰብሳቢነቴ በገዛ ፍቃዴ  መልቀቄን  ለተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ጽህፈት ቤት ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም አሳውቄያለሁ። በሚቀረኝ ጊዜ ያልተጠናቀቁ ስራዎችን የማጠናቀቅ እና አስተዳደራዊ ሽግግር የመፈፀም ሃላፊነቶችን የምወጣበት ይሆናል። 

ባለፉት አራት አመት ከ6 ወራት የምርጫ ቦርድን የማስፈጸም አቅምን ለመጨመር፣ ተአማኒነቱን ለማሳደግ ከሌሎች የቦርዱ አመራር አባላትና ከቦርዱ ሰራተኞች ጋር በጋራ ለፍተናል፣ ውጤቱን የሚመለከታቸው  አካላትና መራጮች  የሚመዝኑት ቢሆንም፣ በእኔ በኩል የቦርዱን ተአማኒነት በማሻሻል ረገድ፣ በተቻለ አቅምም የፓለቲካ ፓርቲዎችን እንቅስቃሴዎች ለማገዝ ባደረግነው ጥረት ስኬታማ ነን ብዬ አምናለሁ። በዚህም ወቅት አብረውኝ የነበሩ የቦርድ አመራር አባላትን፣ የቦርዱን ሰራተኞች በተለይም የየቀኑ ስራዬ በንሸጣ (inspiration) የተሞላ  እንዲሆን ያደረጉልኝ ታታሪ የቦርዱ ሴት ሰራተኞችን፣ የቦርዱ የረጅም አመት ሰራተኞች ሆነው ያፈሩትን ልምዳቸውን ለአዲስ ሰራተኞች በማካፈል ስራችንን ቀላል ላደረጉ ሁሉ ከፍተኛ ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ።
የፓለቲካ ፓርቲዎች አመራሮችም ቦርዱን እንደ አስተዳዳሪ እና እንደተቆጣጣሪ  ከማየት ይልቅ በጋራ እንደሚሰራ ቤተሰብ በመቁጠር የማያስደስታቸውን ውሳኔ በምንወስንበት ወቅትም ጭምር እምነታቸውን አልነሱንም። ለዚህም ለፓርቲዎች እና ለአመራሮቻቸው ከፍ ያለ ምስጋናዬን ላቀርብላቸው እወዳለሁ፡፡

በመጨረሻም ይህን  ማህረሰቤን የማገልገል እድል አገኝ ዘንድ ቦርዱን በሰብሳቢነት ለመምራት በእጩነት ላቀረቡኝ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እንዲሁም እምነቱን ጥሎ ሀላፊነቱን ለሰጠኝ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡
ከልብ ከመነጨ በጎ ምኞት ጋር❗

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የራያ ዓዘቦ ተፈናቃዮችና የአሜሪካ ኢምባሲ ውይይት‼️


ያሳለፍነው ሮብ የአሜሪካ ኢምባሲ ተወካዮች አላማጣ ከተማ መጥተው ለማንነቱ ሰልፍ የወጣው አጠቃላይ ህዝብና የተለያየ የህብረተሰብ ክፍል አነጋግረው ሲመለሱ ፤ ከራያ ዓዘቦ የማንነት ታጋዮችም ጭምር በሰፊው ተወያይተዋል ።

ህወሃት የታጠቀ ወታደሩ ከራያ ዓዘቦ እንዲያስወጣና ራያ ዓዘቦ ላይ እየተፈፀመ ያለው ዘርፈ ብዙ ችግር አንስተው በመወያየት የአሜሪካ ኢምባሲ ጫና እንዲያደርግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል ።

በዚህ ሰዓት የራያ ዓዘቦ ህዝብ መሬት በከፍተኛ ሁኔታ በኢንቨስትመንት ስም ተሸንሽኖ እየተወሰደ ነው።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የሟቾቹ ቁጥር ሁለት ደርሷል‼️


ትላንት በግዳን ወረዳ በሙጃ ከተማ በነበረው የተኩስ ልውውጥ አንድ የሚልሻ ጽ/ቤት ሰራተኛ እና አንድ ፖሊስ ሲሞቱ የፖሊስ አዛዡ እና ሌሎች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ወልደያ ሪፈር ተብለዋል።

የቆሰሉት አጠቃላይ ስድስት ናቸው። በፋኖ በኩል የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ምንጮች ገልፀዋል። ከተማዋ ዛሬ ሰላም ነች።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

Update‼️


ትናንት በግምት ከቀኑ 11:00 አካባቢ በላስታ ላሊበላ ከተማ የብ/ጄኔራል አሳምነው ፅጌን አራትኛ አመት የሙት አመት መታሰቢያ በዓል አክብረዉ ሲለመሱ በነበሩ የፋኖ አባላት ላይ የግዳን ወረዳ የሚሊሻ እና የፖሊስ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ተቀናጅተው ፋኖዎቹ ወደ ሙጃ ከተማ ሲቃረቡ ተኩስ እንደከፈቱባቸው ትናንት ማታ መዘገባችን ይታወሳል።

በዚህ ከአንድ ሰዓት በላይ በቆየ የተኩስ ልውውጥ በርካታ ጉዳት ደርሷል። በዚህም የወረዳው የፖሊስ አዛዥን ጨምሮ የወረዳው የሚሊሻ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ከፍተኛ ጉዳት አስተናግደው ወደ ሌላ የህክምና ተቋም ሪፈር ተብለዋል።

አንድ የፀጥታ አባልም ሞቷል ሲሉ ምንጮች ገልፀዋል።

ከፋኖ በኩል ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ዋግነር ውጊያ ለማቆም መስማማቱን የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሴንኮ ተናገሩ‼️


ፕሬዝዳንት ሉካሼንኮ ከዋግነር መሪው ይቪግኒ ፕሪጎዥን ጋር በስልክ ተወያይተዋል።

የፕሬዝዳንት ሉካሼንኮ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ፥ ቀኑን ሙሉ በተደረገው ምክክርም  ፕሪጎዥን በሩሲያ ደም አፋሳሽ ግጭት ውስጥ ላለመግባትና የተጀመረውን ውጊያ ለማቆም መስማማቱን አስታውቋል።

የቅጥረኛ ወታደር ቡድኑ መሪ ተዋጊዎቹ የደህንነት ዋስትና እንዲሰጣቸው ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጡንም መግለጫው ማመላከቱን አርቲ አስነብቧል።

ፕሬዝዳንት ሉካሼንኮ ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋርም መወያየታቸው የተነገረ ሲሆን፥ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት የወጣው ዘገባ ውጥረቱን እንደሚያረግበው ይጠበቃል።

በዩክሬኑ ጦርነት ባክሙትን በመቆጣጠር ለሩሲያ ወታደሮች አስረክቦ የወጣው ዋግነር ትናንት ምሽት በተዋጊዎቼ ላይ ጥቃት ደረሰ በሚል በሩሲያ መከላከያ ሃይል ላይ ውጊያ መጀመሩን ገልጾ ነበር።

በደቡባዊ ሩሲያ የምትገኘውን ሮስቶቭ ከተማ በመቆጣጠርም ወደ ሞስኮ በመገስገስ ላይ መሆኑን ማሳወቁ ይታወሳል። #AlAin

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ 4ኛ አመት የመታሰቢያ ቀን በትውልድ ቀዬው ላስታ ላሊበላ በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ሰበር‼️

የዋግነር ጦር በራሺያ ላይ አመፀ‼️
የዋግነር ጦር አንድ የራሺያን ሄሊኮፕተር መቶ በመጣሉ በሞስኮው ውጥረት ነግሷል‼️


ዋግነር የሩሲያ ጦር ላይ ጦርነት አወጀ
የሩሲያ ባሕር ሃይልና ዋናው ጦር የፑቲንን ትዕዛዝ እየተጠባበቀ ነው።
>የዋግነር ጦር አዛዥ በሩሲያ ጦር የሮኬት ጥቃት ደረሰብኝ በሚል ዋግነር 25 ሺህ ጦሩን በተጠንቀቅ እንዲቆም አዟል።
>ዋግነር ለፑቲን አሁንም ታዛዥ ነኝ ቢልም የሩሲያ መንግስት ሽብር በመንዛት የእስር ማዘዣ አውጥቶበታል
የዋግነር ጦር ዋና አዛዥ ኢቬግኒ ፕሪጎዥኒ ከሩሲያ ጦር መሪዎች ጋር በግል እሰጥ አገባ ውስጥ ከገባ ወራት የተቆጠረ ሲሆን ለቅዳሜ አጥቢያ ሌሊቱን የሩሲያ ጦር በሮኬት ጥቃት 2 ሺህ ወታደር ፈጀብኝ በሚል ሰበብ "የፍትህ አብዮት" የሚል መጠሪያ በሰጠው የጦርነት አዋጅ የሩሲያ ጦር ላይ ጦርነት ያወጀው ይሄን ተከትሎ የሩሲያ የደህንነት ቢሮ ምን እንደተፈጠረ ሲገልጽ የዋግነር ጦር ያቀረበው የሮኬት ክስ ቪዲዮ ሃሰተኛ አሊያም ፌክ መሆኑን ጠቅሶ ይልቁንም በመልሶ ማጥቃት የተሰበረውን የዩክሬን ጦር የሚረዳ መፈንቅለ ጦር አዋጅ ነው ብሏል። ይሄን ተከትሎ ፕሪጎዥኒ 20 ዓመት በሚያስቀጣው የሃገሪቷ ህግ እንደሚጠየቅ አሳውቋል።
ዋግነር ይሄን ጦርነት ማወጁን ያየው የዩክሬን ጦር 2 ብርጌድ ጦር በባክሙት በኩል ማስጠጋቱን ተከትሎ የሩሲያ አየር ሃይል በስድስት ቦታዎች ላይ ከወትሮ በተለየ መልኩ የሚሳኤል ሩምታ ሲያዘንብ አድሯል። በዚህም ሙሉ ዩክሬን በሚባል መልኩ በአደጋ ግዜ ሳይረን እየተናወጠ ነው።
በሩሲያ ወደ ሞስኮ የሚወስደው መንገድ በሩሲያ ብሄራዊ ጦር ሙሉ በሙሉ ተዘግቷ። የዋግነር ጦር 25 ሺህ ወታደር ያቀፈ ነው ያለውን ጦር ወደ ሞስኮ አቅጣጫ እያስጠጋ መሆኑን በምስል አስደግፎ አውጥቷል።
የዋግነሩ መሪ ከቅርብ ግዚያት ወዲህ የሩሲያን ጦር የሚያስቂጡ አስተያየቶችን በተደጋጋሚ በመስጠት የምዕራባዊያን ሚዲያ የፊት ገጽ ሆኖ ሲወጣ መቆየቱን ተከትሎ ምናልባት ሌላ ተልዕኮ ተቀብሎ ይሆን? የሚል ጥያቄን አስነስቷል።
ይሄን ያዩት ጨካኝ የሚባሉት ጄኔራል አርማጌዶን ለዋግነር ጦር አብረን ተዋድቀን እንደዚህ አይነት ለውጭ ጠላት በር የሚከፍት ስራ ውስጥ መግባት የለብህም የውስጥ ቅራኔ ካለ በውይይት ይፈታል በፍጥነት ያስነሳኽውን ጦር ወደ ቦታው መልስ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የዋግነሩ አዛዥ ጸባችን ከጦሩ ጋር ነው በፑቲን ላይ ምንም አይነት ቅራኔ የለንም ቢልም ሩሲያ ከኔቶ ጋር እንዲህ ተፋጣ ጦሩን እያጠቃ ፑቲን እታዘዝሃለሁ የሚል የሞኝ ሽንገላ በፑቲን ቤት ተቀባይነት እንደማይኖረው በወጣበት የእስር ማዘዣ ታይቷል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ወለጋ‼️


በወለጋ አንገር ጉትን አቅራቢያ የምትገኘዋ በመንደር 13 ቀበሌ ማዶ በመሆን ፋኖን አምጡ በማለት ነዋሪዎቹ ተኩስ ተከፍቶባቸው መዋሉን ገልፀዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ሩቅ እንዳይመስላቹህ ይህ ከአዲስ አበባ 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ሙከ ጡሪ ውጫሌ ወረዳ ሰሜን ሸዋ ዞን ነው ኦነግ ከነ ሙሉ ትጥቁ በነፃነት የሚንቀሳቀሰው።


መከላከያ አማራ ክልል ዘመቻ ላይ ነው።
የኢትዮጵያ ሁኔታ እንቆቅልሽ ነው።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

የአሜሪካ ኢምባሲ ልዑካን በራያ አላማጣ ባደረጉት ጉብኝት ላይ ምን ታዘቡ❓

ጌታቸው ረዳን ያስቆጣው ይህ ይሆን❓


የአሜሪካ ኢምባሲ ልዑካን ከትናንት በስተያ በአላማጣ ከተማ በነበራቸው ጉብኝት ወቅት ከአካባቢው አመራሮች እና ወጣቶች ጋር ውይይት አድርገዋል።

በዚህ ውይይት ላይ ይህ የማንነት ጥያቄ  መኖሩን እንዳላወቁ፣በሰላማዊ ሰልፉ መደመማቸውን እና ይሄን እውነታ ለሚመለከተው አካል እንደሚያሳውቁ ልዑካኑ መንገራቸውን ገልፀዋል።

በዚህ የተነሳ ጌታቸው ረዳ እና የማይጨው አመራሮች ላይ ድንጋጤ እንደፈጠረ ተሰምቷል።

ጌታቸው ረዳ ምናልባት ሰሞኑን ጊዚያዊ አስተዳደሩን ስብሰባ ሊጠራ ይችላል ተብሏል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ጌታቸው ረዳ አሜሪካን ወቀሰ‼️


የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ የአሜሪካ ኢምባሲ ዲፕሎማቶች በአላማጣ ከተማ ጉብኝት ማድረጋቸውን በትዊተር ገጻቸው ባሠፈረው መልዕክት ተችቷል።

ጌታቸው "ዲፕሎማቶቹ የአማራ ኃይሎች የያዙትን አካባቢ መጎብኘታቸው፣ የትግራይ ግዛቶች በጽንፈኛ ኃይሎች የኃይል ቁጥጥር ስር መኾኑን እንደመቀበል ይቆጠራል ብለዋል።

ዲፕሎማቶቹ የአካባቢዎቹ ሕገወጥ አስተዳደር ባላሥልጣናት ባቀነባበሩት ድራማ ለምን እንደተሳተፉ ግልጽ አይደለም ያሉው ጌታቸው፣ ድርጊቱ አሜሪካ ለፕሪቶሪያው ግጭት ማቆም ስምምነት ያላትን ቁርጠኝነት የሚጻረርና ተቀባይነት የሌለው መኾኑን ገልፆል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የሰደን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ በታጣቂዎች ተገደሉ‼️


በ #ኦሮሚያ ክልል የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ሰደን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ በቀለ ቀጫ ማክሰኞ ሰኔ 13 2015 ዓ.ም በታጣቂዎች መገደላቸውን የወረዳው ኮሚኒኬሽን አስታወቀ፡፡

የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ኮሚኒኬሽን የሰዴን ሶዶ ገለፃ አቶ አስታዳሪው የተደገሉት በአዳማ ከተማ ስብሰባ ተሳትፈው ከተመለሱ በኋላ እሁድ ማታ 3፡00 አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች ኢሉ ወረዳ አስጎሪ ከተማ ከሚገኘው ቤታቸው ተወስደው ማክሰኞ እለት ተገለዋል ሲል ገልጧል፡፡

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በቡራዩ ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ የመጣ የጅምላ እስር መኖሩ ተገለፀ‼️


በቅርቡ በአዲስ አበባ ዙሪያ በተዋቀረው ሸገር ከተማ አስተዳደር ቡራዩ ክፍለ ከተማ የጅምላ እስር ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ መምጣቱን ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

በዚህም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እንደዚህ ዓይነት ተግባራት እየተበራከቱ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ድርጊቱን የሚፈጽሙት የኦሮሚያ ፖሊስ እና የአካባቢው ሚሊሻ አባላት መሆናቸን የገለጹት ነዋሪዎቹ፤ ወጣቶች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በየዕለቱ ወደ እስር ቤት በጅምላ እየተጋዙ ነው ብለዋል።

በከተማው ያሉ ወጣቶች ለእስር የሚዳረጉበት ዋነኛ ምክንያት፤ በብዛት ከወለጋ እንዲሁም ከተለያዩ የምዕራብ ሸዋ እና የሰሜን ሸዋ አካባቢዎች በጸጥታ ችግሮች ተፈናቅለው የመጡ በመሆናቸው፣ “ከኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ጋር ግንኙነት አላችሁ” በሚል ጥርጣሬ ነው ተብሏል።

ወጣቶቹን ከተለያዩ የመዝናኛ ሥፍራዎች ጭምር እንደሚታፍሱ እና ሲያዙም ኃይል የተቀላቀለበት ድርጊት እንዲሁም ሌሎች የመብት ጥሰቶች እንደሚፈጸምባቸው ተመላክቷል።

ድርጊቱ በከተማዋ ባሉ ድሬ፣ ከታ እና ማርያም በተባሉ ሰፈሮች በስፋት እንደሚፈጸምም ተጠቁሟል።

በዚህ የተነሳ በከተማው ያሉ እስር ቤቶች ከእስረኞች መሙላታቸው እና ቀሪዎቹ ደግሞ በክፍለ ከተማው የመሬት አስተዳደር ጽህፈት ቤት እና በተለያዩ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ታስረው እንደሚገኙ ነው የተገለጸው።

ወጣቶቹ ወደ እስር ቤት ከገቡ በኋላም ወደ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ከሦስት እስከ አራት ወራት እንደሚቆዩ ብሎም ዛቻ እና ከፍተኛ ድብደባ እንደሚያደርሱባቸውም ተጠቁሟል።

የክፍለ ከተማው መታወቂያ የሌለው ሰው በከተማዋ ለመንቀሳቀስ እጅግ አስቸጋሪ ነው ያሉት ነዋሪዎቹ፤ በዚህም ምክንያት ለእስር የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥራቸው ከፍተኛ ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በተጨማሪም ራሳቸው የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ያሰሯቸውን ሰዎች ጉቦ እየተቀበሉ እንደሚለቋቸው እና የመክፈል አቅም የሌላቸው ታሳሪዎች ደግሞ ለወራት በከፍተኛ ችግር ውስጥ ሆኖ በእስር እንደሚቆዩ ተጠቅሷል።

አዲስ ማለዳ

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ጋዜጠኛ ኤልያስ መሠረት እንደጻፈው‼️


እውነትእ ውነቷን ድርጊቱ የተከሰተው ባለፈው ሳምንት ሀሙስ ቀን በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ውስጥ ነው።
አንድ የአካባቢው ሚሊሺያ ራሳቸውን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግስት ደግሞ ሸኔ ብሎ በሚጠራቸው) ታጣቂዎች ይታገታል። ይህንን ምስኪን ሚሊሺያ መሳርያህን እና 100 ሺህ ብር አምጣ እና ትለቀቃለህ ይሉታል። እሱ ደግሞ መሳርያውን ደብቆ ቀብሮ ነበርና "ለመንግስት መልሻለሁ" ብሎ ይነግራቸዋል።

ከዛ ግን የሆነው ይገርማል... ታጣቂዎቹ ሚሊሺያው ፊት ሆነው በቀጥታ የደወሉት ለወረዳ አመራሮች ነበር (to be exact ለወረዳው ደህንነት አዛዥ)። ታጣቂዎቹ ሚሊሺያው መሳርያውን ለመንግስት መልሷል ወይስ አልመለሰም ብለው ሲጠይቁ የወረዳው አመራሮች "አልመለሰም" ብለው ይናገራሉ። 

ከዛማ ሰውየውን አንጠልጥለው እቤቱ አምጥተው ቆፍሮ ከደበቀበት አስወጡት፣ ስለዋሻቸው ገንዘቡን እጥፍ አርገው 200,000 ብር ወሰዱ፣ ከዛም ለቀቁት።

ጊንጪ ከተማ የሆነ ሌላ ታሪክ ልጨምር። ብዙዎችን የሚረዳ አንድ የካቶሊክ ትምህርት ቤት ነበር። ከሶስት ወር በፊት የካቶሊክ ቄሶችን እና ሲስተሮችን ታጣቂዎች አፍነው ወሰዱ፣ ከታገቱት መሀል ህንዳዊ ሲስተር ይገኙበታል። 300 ሺህ ብር በነፍስ ወከፍ ከፍለው አስለቅቀው ከዛ ግን ትምህርት ቤቱን ዘግተው ወጡ።

ተጨማሪ ታሪክ፣ የዛሬ 2 ሳምንት በፈረስ ለሸኔ መሳርያ ሊያቀብሉ ነበር የተባሉ ወጣት ተማሪዎች እዛው ምዕራብ ሸዋ ተያዙ። ልጆቹ በትናንትናው እለት እንዲያመልጡ ተደርጓል፣ ጥይት እንደያዙ የጠቆመው ግለሰብ ግን ለእስር ተዳርጎ ይገኛል። በአንድ በኩል መከላከያ እና ፖሊስ የህይወት መስዋዕትነት እየከፈሉ ውጊያ ቢያካሂዱም ጥይት እና የወታደር ኮሾሮ ጭምር ለታጣቂዎቹ እንዲደርሳቸው እያረጉ ያሉት የአካባቢው አመራሮች እንደሆኑ የሚደርሱኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ሌላኛው የሰማሁት ደግሞ ወደ ያቤሎ አቅራቢያ አንድ ግለሰብ ታግቶ ነበር፣ ገንዘብ አምጡ ተብሎ ብር ሲሰበሰብ ትንሽ ቀናት ፈጀ። በመጨረሻም ብሩ ሞልቶ ተላከ፣ ታጣቂዎቹ ግን ገንዘቡን ተቀብለው ታጋቹን ገደሉ።

ምነው ብሎ ቤተሰብ እያለቀሰ ሲጠይቅ "በተባላችሁበት ቀን ገንዘቡን አላመጣችሁም" ተባሉ።

*በነገራችን ላይ፣ ብዙም የማይወራለት ግን በየቤቱ እየተሄደ እየታገተ እና ስቃዩን እያየ ያለው የኦሮሚያ ህዝብ ጭምር ነው።

አንዳንዶች ድርጊቱ ሌሎች ላይ ብቻ ያተኮረ እንደሆነ የሚፅፉት እና የሚናገሩት ትክክል እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል፣ ሁሉም ፍዳውን እያየ ይገኛል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ወያኔን ለማስገባት ተብሎ ብርቱካንን ማስወጣት...

አይ ውርደት! አይ ክሽፈት! አይ ሽንፈት!

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ትግራይ‼️


ከሳምንት በፊት በዘገብነው መሰረት ህወሃት ሰሞኑን በጦርነቱ ወቅት የሞቱ አካላትን መርዶ መናገር ጀምሯል።

የእናት እንባ እና ስቃይ ያሳዝናል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

11 years ago‼️


World economic forum on Africa,Adiss Ababa Ethiopia, 2012‼️


#ሀቅ ይህንን ቪድዮ ከአመታት በፊት እንዳየሁት ባስታውስም ከሰሞኑ ቲክቶክ ላይ በስፋት ሲዘዋወር ተመለከትኩት እና ላጋራው ፈለግኩ።

ኢህአዴግ ዴሞክራሲያዊ ያልነበረ እና አሁን ላሉ አንዳንድ ችግሮች ጭምር ምንጭ እንደነበር ይታወቃል፣ መሪዎቹም ለዚህ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል።

ይህ እንዳለ ሆኖ የማይካደው ሀቅ ግን የፓርቲው እና የሀገሪቱ መሪ የነበሩት የቀድሞው ጠ/ሚር አቶ መለስ ዜናዊ  world class አእምሮ እና እውቀት ያላቸው መሪ ነበሩ።

ዴሞክራሲን በማስፋት ዘርፍ "የጋን ውስጥ መብራት" የነበሩ ናቸው ማለት ቢቻልም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ብቻ ሳትሆን በአለም እጅግ ፈጣን እድገት ካላቸው ሀገራት ተርታ ነበረች፣ እንደዛሬው ቢያንስ ሰው በቁሙ ሲቃጠል፣ ሲገደል እና ሲታገት በየቀኑ አንሰማም ነበር። ጥሩ ነገር ለሀገራችን ያምጣልን።


ለቪዲዮው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት🙏

Читать полностью…

Ethio 360 Media

Inbox❗ከናዝሬት/አዳማ‼️


ለምታደርሱን መረጃ በጣም ከልብ እናመሰግናለን ወደ መረጃዬ ስገባ ዛሬ ጠዋት 3 ስዓት አከባቢ በናዝሬት (አዳማ)ከተማ የህዝብ ቆጠራ ነው በማለት ቤት ለቤት እየዞሩ ነው፣ሙሉ ስም ከነአያት፣የአፍ መፍቻ ቋንቋ ፣ የትምህርት ደረጃ ፣ ሀይማኖት ፣ ብሄር ፣ ስልክ ቁጥር ፣ የምትሰራውን ስራ፣ ዕድሜ ይጠይቃሉ።

ህዝብ ቆጠራ ከሆነ ይህ ሁሉ መረጃ ይጠየቃልን❓

ህዝብ ቆጠራስ እንደሀገር መቼ ተጀመረ❓

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ቦታዎች በንጹሐን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ቅጥ ያጣ እገታ ግድያ ግፍና ሰቆቃ ገደቡን አልፏል‼️
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በኦሮሚያ ክልል ውስጥ እለት ከእለት እየጨመረ የመጣው የንጹሐን ዜጎች መፈናቀል፣ እገታ፣ አፈና እና ግድያ በከፍተኛ ሁኔታ ያስጨንቀዋል፡፡ በተለይ እራሱን "የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት" እያለ የሚጠራው ኦነግ ሸኔ የተባለው የሽብር ቡድን በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ዞኖች በዜጎች ላይ እያደረሰ ያለው ውድመት እና እንግልት ቀን በቀን እየተባባሰ መጥቷል፡፡

የተለያዩ ፖለቲካዊ ፍላጎቶችን በሰላም በድርድር እና በውይይት ለመፍታት መሞከር ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑ ላይ ግርታ ባይኖርም ለሰላም ነው እየተባለ ንጹሐን ዜጎች ላይ በጠራራ ጸሐይ እየደረሰ ያለው ቅጥ ያጣ አፈና፣ ግድያ፣ ግፍና ሰቆቃ ሊታገሱት ይገባል ማለት ሊሆን ፈጽሞ አይችልም፡፡

በጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም. የተፈረመውን የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተከትሎ ባወጣነው መግለጫ በተለያዩ አካባቢዎች ላይም ለሰላም ውይይትና ድርድር በር አንዲከፈት አሳስበን የነበረ ሲሆን ይህን ተከትሎም በጋምቤላ እና በቤኒሻንጉል ክልል የነበሩ ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ ትጥቅ እንደፈቱ ተዘግቧል፡፡ መንግሥትም የሰላም በሩን ከፍቶ በኦሮሚያ ክልል እየተንቀሳቀሰ ከሚገኘው ኦነግ ሸኔ ከሚለው አሸባሪ ቡድን ጋር ታንዛኒያ ላይ ሰላማዊ ውይይት እንደጀመረ ሲያሳወቅ ተስፋ አድረገን የነበረ ቢሆንም ከድርድሩ በኃላ የሽብር ቡድኑ ጥፋት እየባሰበት ሲመጣ እንጂ ሲቀንስ ወይም ጨርሶ ሲጠፋ አላስተዋልንም፡፡ ይህም ንጹሐን ዜጎች በገዛ ሀገራቸው ለአፈና እና ግድያ እየዳረጋቸው መደበኛ እለታዊ ሕይወታቸውን ተረጋግተው እንዳያከናውኑ እያደረጋቸው ነው፡፡

በመንግሥት በኩል የተለያዩ ምክንያቶችን በማቅረብ ቡድኑን ጨርሶ ለማጥፋት እንዳልተቻለ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስለጉዳዩ ሲጠየቁ፤ የሸኔ የሽብር ቡድንን አስቸጋሪ አወቃቀር በመጥቀስ እርምጃ ለመውሰድም ኾነ ለመደራደር የሚመሩት መንግሥት መቸገሩን ሲገልፁ ሰንብተዋል፡፡

በዚህ ወቅት የሽብር ቡድኑ አባል ነን የሚሉ ታጣቂዎች በወለጋ ሁለት ዞኖች፣ በምዕራብ፣ ምስራቅ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ በሱሉልታ ወረዳ ቦቁ ጎልባ፤ ኤካ ጋጆና፤ ቦቁ ሁሩታ እና ሞዬ ጋጆ በሚባሉ ቀበሌዎች፤ በዝዋይ፣ መቂ፣ ሰዴን ሶዶ ወረዳ፣ የአዳ ባርጋ ወረዳ፣ ኩዩ ወረዳ፣ ገርበ ጉራቻ፣ ዋጫሌ ወረዳ፣ በአዳማ፣ በመተሀራ፣ በምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፣ በአርሲ ዞን፣ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ በቅርብ እርቀት ላይ በሚገኙ ቦታዎች ላይ ንጿሃን ዜጎችን እያገተ እና እየገደለ ፣ የትራንስፖርት እና እቃ ማጓጓዣ መኪና ሹፌሮችን እያፈነ እና በርካታ የጸጥታ ስጋት የሆኑ ተግባራት እየፈጸመ እንዳሻው እየተንቀሳቀሰ የዜጎችን ህልውና እየተፈታተነ፣ ሀገራችንንም የምድር ሲኦል እያደረገ ነው፡፡ በሌሎች የሀገራችን አካባቢዎች ጭምር የሚንቀሳቀሰው ኦነግ ሸኔ፤ ኢሞራላዊ በኾነ መንገድ የሃይማኖት ሥፍራዎችን ሳይቀር እያዋረደ ነው።

ይህንን የሚያክል የሀገር ህልውና ችግር በየእለቱ እንደተራ ዜና እየሰሙ ማለፍ የማይቻልበት ደረጃ መድረሱን የሚመለከታችሁ የመንግሥት የጸጥታ መዋቅሮች ልብ ልትሉት ይገባል፡፡ በምንም መልኩ የዜጎች በሕይወት የመኖር ዋስትና በመንደር ሽፍቶች ሲገፈፍ በቸልታ ሊታለፍ አይችልም፡፡

መንግሥት የሚጠየቀውን መስዋዕትነት ኹሉ ከፍሎ የዜጎችን ደኅንነት ካላስጠበቀ፤ አስፈላጊነቱ ጥያቄ ውስጥ ሊገባ እንደሚችል መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሁሉም ሥፍራ በሰላም ወጥቶ መግባት፣ ተንቀሳቅሶ መሥራት፣ ያለሰቀቀን መኖር እና የደኅንነቱ መጠበቅ እንደ ዳገት ሊከብደው አይገባም፡፡

በተደጋጋሚ እንደገለጽነው የመንግሥት በጣም ትንሽ የሚባለው ኃላፊነት የሀገርን ሰላም እና ደኅንነት ማስጠበቅ ነው፡፡ ይህንን መሠረታዊ መንግሥታዊ ግዴታ አለመወጣት የአቅም ማጣት ወይም የግዴለሽነት ችግር ነው፡፡ መንግሥት ያለበትን ሁኔታ በግልጽ አሳውቆ፤ ሕዝብን በማስተባበር ዘመቻ በማካሄድ የሽብር ቡድኑን አደብ ማስገዛት ይጠበቅበታል፡፡ ይህንን አለማድረግ ግን የቸልተኝነት ወይም የግድያው ተባባሪነትን ማሳያ ከመኾን ያለፈ ትርጉም የለውም፡፡ እዚህ ጋር መረሳት የሌለበት ዋና ጉዳይ ግን መሰል አይነት በደሎች የሚፈጥሩት ብሶት ዜጎች በራሳቸው ተደራጅተው ሰላምና እና ደህንነታቸውን ወደ ማስጠበቅ ይገቡና ወደ አላስፈላጊ ትርምስ ውስጥ ሊያስገባን እንደሚችል ነው፡፡ ይህን ከግንዛቤ በማስገባት ነገ ዛሬ ሳይሉ አፋጣኝና የማያዳግም እርምጃ መውሰድ እንደሚኖርበት መንግስትን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

ምንም እኳን ላለፉት ጥቂት ዓመታት መንግሥት በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሽብር ድርጅቶች እንዲሁም በታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሴራ ተጨባጭ የሰላም እና ደኅንነት ቀውስ ውስጥ መግባቱን ብንገነዘብም፤ ባለንበት ወቅት በራሱ አንደበትና በመገናኛ ብዙኀን እንደምንመለከተው መንግስት ጠንካራ የፀጥታ መዋቅር ማደራጀቱን እና የማያዳግም የሰላም ማስከበር ሥራ እያከናወነ መኾኑን እየገለጸ ስለኾነ፤ የሸኔ የሽብር ቡድን እስካሁኗ ሰዓት ድረስ እንዳሻው መፈንጨት ምንም አይነት ምክንያት ሊቀርብበት የማይችል ሙሉ በሙሉ የመንግሥት የራሱ ድክመት መሆኑን ሊያምን ይገባል፡፡

በሕዝብ ይሁንታ የመንግስት መንበር ይዣለሁ ብሎ የሚያምን ኃይል ከመንግሥት ኃላፊነት ቀዳሚ የሆነውን መተላለፊያ ኮሪደሮች ማስከበር አለመቻል ሰበብ እንጂ ምክንያት ሊገኝለት አይችልም። እንዲህ አይነት አንገብጋቢ እና ቅድሚያ ሊሠጣቸው የሚገቡ ጉዳዮች ቢኖሩም አስቸኳይ እና አንገብጋቢ ባልሆኑ ችግሮች ላይ ትኩረት መሥጠቱ ዜጎችን ለከፍተኛ ጥርጣሬ ዳርጓል። በመኾኑም፤ ይህንን ሀገራዊ የኅልውና አደጋ በመገንዘብ የሚከተሉትን አስቸኳይ እና ዘላቂ እርምጃዎች እንዲወስድ እንጠይቃለን፡፡

1ኛ/ የፌደራል መንግሥት በየጊዜው የጥፋት ተልዕኮውን እያሰፋና የራሱን ኃይል ለማግዘፍ የሚፍጨረጨረውን ኦነግ ሸኔን አደብ ለማስያዝና ዜጎችን ከሰቆቃ ለመታደግ ያጋጠሙትን ተግዳሮቶች ለህዝብ በይፋ እንዲያሳውቅ!

2ኛ/ ባለፉት ጊዜያት በተደጋጋሚ እንደገለጽነው በራሱ ብልጽግና መንግሥት ውስጥ ተሰግስገው ለአሸባሪው ቡድን ሚስጥራዊ ድጋፍ በማድረግ የህዝብን ሰቆቃ የሚያባብሱና የቡድኑን እኩይ ተግባር በቸልታ የሚመለከቱ በተዋረድ ያሉ አካላትን ቁርጠኛ ሆኖ በመታገል ምንጩን እንዲያደርቅ!

3ኛ/ አሸባሪው ቡድን በዚህ ወቅት አፋፍሞ በየአቅጣጫው እየፈጸመ ያለውን መርህ አልባ እንቅስቃሴ ከወዲሁ እንዲሽመደመድ ካላደረገና ትጥቅ በፍጥነት ማስፈታት ካልቻለ የተጀመረውን ድርድር ማስቀጠል አዳጋች እንደሚሆንበት አጥብቀን መግለጽ እንሻለን።

በመጨረሻም እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩ አስቸኳይ የመፍትሔ እርምጃዎች ካልተወሰዱ በአሸባሪው ሸኔ ከዚህ ቀደም ለተፈጸሙትም ኾነ ከዚህ በኋላ ለሚፈጸም ግድያ፣ መፈናቀል፣ እገታ፣ ውድመት እና ሰቆቃ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ በየደረጃው ያሉ የፌደራል እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በህሊና፣ በሕግ፣ በሕዝብ እና በታሪክ ተጠያቂ እንደሚኾኑ ሊያውቁት ይገባል፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በሰሜን ወሎ ግዳን ወረዳ ሙጃ ከተማ አቅራቢያ ምሽቱን የተኩስ ድምጽ እንደሚሰማ ነዋሪዎቹ ገልፀዋል።

ተኩሱ የአሳምነው ፅጌን የመታሰቢያ ቀን አክብረው ሲመለሱ በነበሩ የፋኖ አባላት እና የመንግሥት የፀጥታ አካላት መካከል እንደሆነ ምንጮች ጠቁመዋል።


ከዚህ በተጨማሪ በደቡብ ወሎ አማራ ሳይንት ወረዳ የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ ውሏል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

በኦነግ ሸኔ ታግተው ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ለተጠየቁ ሹፌሮች ገንዘብ እየተሰበሰበ ነው ተባለ‼️


ከአምስት ቀን በፊት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኩዩ ወረዳ ገርበ ጉራቻ ከተማ አካባቢ ለታገቱ ከ50 በላይ ሹፌሮች፣ እገታውን የፈጸሙት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የጠየቁትን ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ህዝቡ እየሰበሰበ መሆኑን ከምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ መናገራቸው ተሰምቷል።
በዚህም በደብረ ማርቆስ እና ደንበጫ መካከል አማኑኤል ከተማ ላይ የታገቱ ሹፌሮች ይለቀቁልን በሚል ለሦስት ቀናት ያህል መንገድ ተዘግቶ እንደነበር የተጠቀሰ ሲሆን፤ መፍትሔ ባለመገኘቱ የታጋቾቹ ቤተሰቦች በየቦታው ጨርቅ አንጠፈው የተጠየቁትን ገንዘብ በመለመን ላይ ናቸው ተብሏል።

"እኛም ግራ ገብቶናል" ያሉ አንድ የሥራ ኃላፊ፤ "አብዛኛው ሹፌሮች የታገቱት ከዚህ አካባቢ ስለሆነ ሕዝቡ ልጆቻችን ይፈቱልን በማለት መንገድ ተዘግቶ ነበር።" ካሉ በኋላ፣ "ሕግ እና መንግሥት ባለበት አገር ሰው ታግቶ በሚሊየን ክፈሉ እየተባለ ነው፣ አጣርታችሁ ለመንግሥት ይፋ አድርጉ የሚሰማ ካለ።" ሲሉ ተደምጠዋል።
አክለውም፤ "ከታገቱት ውስጥ ዕድል ቀንቶት ለአንድ ሰው አንድ ሚሊየን ከፍሎ የሚለቀቅ አለ። አልፎ አልፎ እየከፈሉ እየተለቀቁ ነው፣ ክፍሎ ያልተለቀቀም አለ" ብለዋል።
ከ50 በላይ ሹፌሮች ታግተው ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ነው የተጠየቀው ያሉት የሥራ ኃላፊው፤ "በዚህ ኑሮ ውድነት ምንም የሌለው ድሃ ልጆቹን ለማትረፍ በየቦታው ጨርቅ አንጥፎ እየለመነ ነው። የሚመለከተው አመራር ማብራሪያ ይስጥ።" ሲሉ አሳስበዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ጫንጮ‼️

በጫንጮ ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት አንድ አይሱዙ ቅጥቅጥ ሰርቢሥ የደርባ ሰራተኞች ከኳሪ ወደ ፋብሪካ በጉዞ ላይ እያሉ በሸኔ መታገታቸውን ምንጮች ገልጸዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ዘምዘም ባንክ‼

✔ዘምዘም ባንክ በልደታ ክፍለ ከተማ የዋና መስሪያ ቤቱ ሕንጻ ለመገንባት 4,135.66 ካሬ ሜት ቦታ በሊዝ መረከቡን አስታውቋል።

✔ህንፃው በ2 ቢሊየን ብር ወጭ የሚሰራ ሲሆን አራት ምድር ቤቶች ያሉት G+30 ሆኖ እንደሚገነባ መታቀዱም ተነግሯል።

✔ባንኩ አሁን ላይ 75 ቅርንጫፍ የከፈተ መሆኑን ጠቁሟል። የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑም ከ4.5 ቢሊየን ብር በላይ እንደደረሰ አስረድቷል።ጥቅል ሀብቱ ደግሞ 6·9 ቢሊየን ደርሷል ተብሏል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ዳንሻ‼️


የትግራይ ሰራዊት አባላት ዳንሻ አካባቢ በሚገኘው የእግረኛ እና የመካናይዝድ ጦርን መቀላቀላቸውን የአይን እማኞች ገልፀዋል።

ሰሞኑን በ6 የጭነት መኪና መጥተው የተቀላቀሉ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 3ቱ መኪና መካናይዝድ 3ቱ መኪና ደግሞ እግረኛ እንደሆኑ ታውቋል።

የአከባቢው አመራሮችም ይህ መረጃ እንዳላቸው እና እንቅስቃሴውን እየተከታተሉት መሆኑን ገልፀዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ምዕራብ ደንቢያ ጯሂት‼️


በምዕራብ ደንቢያ ጯሂት ትናንት በፋኖ አባላት እና በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች መከላከያ የተኩስ ልውውጥ የተደረገ ሲሆን በዚህ የተኩስ ልውውጥ የመንግሥት የፀጥታ አካላት ተጭነው የመጡበትን መኪና ጥለውት በመሸሻቸው የፋኖ አባላቱ መኪናውን ለአካባቢው የከተማ አስተዳደር ማስረከባቸውን ምንጮች ገልጸዋል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ሸኔ ስሙን ቀየረ‼️

ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በማለት የሚጠራው ኦነግ ሸኔ "እኛ ሸኔ አይደለንም" ብሏል።"ሸኔ የሌላ ሀኃይል ነው እኛ ጃለኔ ነን "ማለቱ ተሰምቷል።

በስማችን መጥራት ግድ ነው ማለቱ ተነግሯል።

Читать полностью…

Ethio 360 Media

ደብረብርሃን‼️

የበላይነህ ክንዴ ቢዝነስ ግሩፕ ፌቤላ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ሥራ ጀመረ ‼️


በደብረ ብርሃን ከተማ የተገነባው የበላይነህ ክንዴ ቢዝነስ ግሩፕ ፌቤላ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ወደ ማምረት ሥራ መሸጋገሩ ተገልጿል።

ፋብሪካው በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ሚኒባስ፣ ሚድባስ እና የከተማ አውቶብስ ተሽከርካሪዎችን ማምረት መጀመሩ ነው የተነገረው፡፡

ፋብሪካው እስካሁን ለ150 ዜጎች ቋሚ ለ100 ዜጎች ጊዜያዊ የሥራ እድል ተጠቃሚ መድረጉን የገለጹት፤ የበላይነህ ክንዴ ቢዝነስ ግሩፕ የፌቤላ የመኪና መገጣጠሚያ ኢንዱስትሪ ሥራ አስኪያጅ መሀመድ አህመድ፤ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባም ለ440 ዜጎች ቋሚ፣ ለ250 ለሚሆኑ ዜጎች ጊዜያዊ በአጠቃላይ ከ700 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል እንደሚፈጥር ጠቁመዋል፡፡

ፋብሪካው በመጀመሪያ ዙር 216 መኪኖችን ለመገጣጠም አቅዶ እየሰራ መሆኑን የገለጹት ሥራ አስኪያጁ፤ ከ20 ቀን በኋላ የሚገጣጥማቸውን በኤሌክትሪክና በነዳጅ የሚሰሩ መኪናዎች ለገበያ ማቅረብ እንደሚገምር ተናግረዋል፡፡

ፋብሪካው በቀን 4 በነዳጅና በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖችን መገጣጠም እንዲሚችልና፤ ጥሬ እቃውን ለጊዜው ከቻይና እና ከአውሮፓ በማምጣት እንደሚገጣጠሙም ገልጸዋል፡፡

የኤሌክትሪክ መገጣጠሚያ ፋብሪካው 2 ቢሊየን ብር ወጪ እንደረደረገበትም ተነግሯል፡፡

Читать полностью…
Subscribe to a channel