ሽሬ‼️
ትናንት ከሽሬ አቅጣጫ ምን እደጫኑ በግልጽ ባይታወቅም (ሬሽን/ተተኳሽ/) ስምንት መኪኖች ከትግራይ ሽሬ ተነስተው ወደ ጠለምት ፍየል ውሃ ወደ ሚባል አካባቢ ተንቀሳቅሰዋል ሲሉ የአዩዘሀበሻ ምንጮች ገልጸዋል።
ከዚህ በተጨማሪ አንድ መኪና የትግራይ ታጣቂዎች ጭምር አብረው ተከዜን ተሻግረዋል ብለዋል።
ነዋሪዎቹ በሁኔታው ግራ እንደተጋቡ ገልፀዋል።
መኪናው መሶቦ እና መከላከያ የሚል ፅሁፍ አለው ብለዋል።
ደ/ር ደብረፂዮን፣ ሞንጀሪኖ እና አለምገብረዋሃድ በሽሬ ከተማ በ29 ስብሰባ አድርገው አቅጣጫ አስቀምጠው ሄደዋል ሲሉ ምንጮች ገልጸዋል።
ሀረርጌ❗❗
ትናንት በሀረርጌ በአሰበ ተፈሪ አቅራቢያ መሳሪያ አስቀምጠው አካላዊ እንቅስቃሴ እያደረጉ በነበሩ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ በኦነግ ሸኔ ጥቃት መፈፀሙን ምንጮች ገልጸዋል።
ቅዱሲ ሲኖዶስ ይቅርታ ጠየቀ‼️
በክልል ትግራይ በተካሄደው ጦርነት ወቅት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊትና ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን እንደመሆኗ መጠን ፦
- ጦርነቱ እንዲቆም በወቅቱ መግለጫ ባለመሰጠቷ፣
- በጦርነቱ መካከል ወደ ትግራይ ክልል መግባትና መውጣት በሚቻልበት ወቅትም በክልሉ የሚገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንንና መላው ሕዝበ ትግራይን በአካል በቦታው ተገኝታ ባለመጠየቋና ባለማጽናናቷ፣
- ጦርነቱ ቁሞ በአገር አቀፍ ደረጃ እርቀ ሰላም ከወረደበት ጊዜ ጀምሮ ለደረሰው ጉዳት በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነውን ሰብአዊ ድጋፍ በውሳኔው መሠረት በወቅቱ ማድረስ ባለመቻሏ፣ በዚሁም የተነሣ በቤተ ክርስቲያኗና በመላው ሕዝበ ትግራይ መካከል ለተፈጠረው ቅሬታና አለመግባባት ቅዱስ ሲኖዶስ በይፋ ይቅርታ ጠይቋል።
"ሙሉ አማራ ክልል አዲስ የጦርነት ቀጠና ሆኗል ፤ ከፊል ኦሮሚያ በተመሳሳይ የጦር ቀጠና ናቸዉ።
ከ 200 ሺህ በላይ ሰዎች በመንግስት ቤታቸዉ ፈርሶ ሜዳ ላይ ወድቀዋል።
እንደ ብልጽግና ሹማምንት አባባል ህጋዊ ደሃ ተደርገዋል።
በሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በጦርነቱ እና በማንነት ጥቃት ተፈናቅለዋል።
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል።
ለዚህ ሁሉ ቀዉስ ዋነኛ ተጠያቂው የብልጽግና መንግስት እና የእርሶ (የጠ/ሚኒስተሩ ) የወደቀ አመራር ነዉ።
" የተከበሩ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ለ ጠ/ሚ አብይ ካነሷቸዉ ጉዳዮች መካከል
Via: ዳጉ ጆርናል
እስራኤል የኢትዮጵያ መንግሥት የዴር ሡልጣን ገዳም ይዞታን እንዲያስጠብቅ አሳሰበች ‼️
የኢትዮጵያ መንግሥት ኢየሩሳሌም የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ንብረት የሆነውን የዴር ሡልጣን ገዳም ይዞታ ማስጠበቅ አለበት ሲሉ፤ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
የእስራኤል መንግሥት የዴር ሡልጣን ገዳም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ይዞታ ነው ብሎ እንደሚያምንም አምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡
ነገር ግን ጉዳዩ የፖለቲካ ጥቅም ግጭት ያለበት በመሆኑ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመሆን ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት እንዳለበት ነው ያስታወቁት።
ከአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በገዳምነት ይጠቀሙበትና ይኖሩበት እንደነበር የሚነገርለት በእስራኤል ጎለጎታ ተራራ ላይ የሚገኘው የዴር ሡልጣን ገዳም፤ በተለያየ ጊዜ የባለቤትነት ጥያቄ ይነሳበታል፡፡
በተለይ የግብፅ ኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን የባለቤትነት ጥያቄ ስታነሳ ቆይታለች፡፡ በተደጋጋሚም ገዳሙ ውዝግብና ግጭቶችን ያስተናግዳል፡፡
ይዞታዉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እንደሆነ ቢነገርም፤ ግብጻውያኑም የይገባኛል ጥያቄ በማንሳት ለዘመናት ዉጥረትን የሚያስተናግድ ቦታ ነዉ፡፡
አምባሳደር አለልኝ ቀደም ባለዉ ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን አባቶች በገዳሙ ዉስጥ እንዲጠለሉ አንድ የግብጽ መነኩሴ በማስጠጋታቸዉ ግብጾቹ የእኛነዉ የሚል እሳቤ እንዳደረባቸዉና ከዚያ በኋላ የይገባኛል ጥያቄ ማንሳት መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡
አዲስ ማለዳ
"ሉዓላዊ መሬታችንን በማስፈራራት እናስመልሳለን "የወያኔ ጄኔራል ዮሐንስ ወልደጊዮርጊስ 😀
- የወያኔ ጄኔራል ዮሐንስ ወልደጊዮርጊስ
ጄኔራሉ ከትናንትና ወዲያ በአንድ የመፅሐፍ ምረቃ ላይ ተገኝቶ ነው ይሄን ያለው 👇👇
"ሉአላዊ መሬታችንን በግድም ቢሆን ማስመለስ አለብን። እንዴት እናስመልሳለን ለሚለው ደሞ ...
👉 በዲፕሎማሲ
👉 በስምምነት
👉 በማስፈራራት እናስመልሳለን።
ሰበር መረጃ‼️
የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አብዱ ዛሬ አመሻሹን በስራ ቦታው አቅራቢያ መገደሉን ምንጮች ገልፀዋል።
ከስራ ሲወጣ መኪናው ውስጥ እንዳለ ነው 11 ሰዓት አካባቢ የተገደለው።
በደጀን ወረዳ በትላንትናው ዕለት የተገደሉት የወረዳው የፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ዘውዱ ታደለና ምክትላቸው ኢንስፔክተር ወርቁ ሽመልስ እነዚህ ነበሩ።
Читать полностью…የትግራይ ታጣቂዎች ከፍተኛ መሪዎች፣ ኮለኔሎች እና መስመራዊ መኮንኖች ለየብቻቸው ሰሞኑን በአዲስ አበባ ስልጠና እየወሰዱ ነው።
የስልጠናው አላማ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ስለሚካተቱበት ሁኔታ ሲሆን ስልጠናውን እየሰጡ ያሉት የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ናቸው።
#በአውሮፓዊቷ ሀገረ ፈረንሳይ አንድ ወጣት በፓሊስ መገደሉን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው‼️
በአውሮፓ፤ በፈረንሳይ ከተማ፣ ትራፊክ ፖሊስ አንድ አልጀሪያዊ ወጣት ተኩሶ መግደሉን ተከትሎ፣ህዝብ በወሰደው የአፀፋ እርምጃ እስካሁን ከ 300 በላይ ፖሊሶች ጉዳት ደረሶባቸው ቁስለኛ ሆነዋል።
በመላው የፈረንሳይ ከተማ ከፍተኛ ህዝባዊ አመፅ ተቀጣጥሎ ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል።
አመፁ ያስደነገጠው የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት በሚዳያ ብቅ ብሎ ተማፅኖ አቅርቧል።
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
"…ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ላበደረው ንብረት የሐራጅ ሽያጭ አውጥቷል። አቅም ያላችሁ ተሳተፉም ብሏል።
•አበዳሪው ወይም የመያዢያ ሰጪ ስም፣ አበዳሪው ቅርንጫፍ፣ የሚሸጠው ንብረት ዓይነትና የሚገኝበት ቦታ፣ የሐራጁ መነሻ በብር፣ የሐራጁ ቀንና ሰዓትም ተገልጿል።
1ኛ፥ አቶ ዮናታን አኪሊሉ አንጀሎ አራት ኪሎ ፕሪሚየም፣ በስማቸው የተመዘገበ ሀዋሳ ምሥራቅ ከተማ የሚገኝ 400 ሜትር ካሬ ቦታ ያለው ባለ 3 ወለል መኖሪያ ቤት፣ የሐራጁ መነሻ ዋጋ በብር። 22 ሚሊዮን፣ የሀራጁ ቀንና ሰዓት በ17/2015ዓም ከ4:00–6:00 ሰዓት
2ኛ፥ አቶ ዮናታን አክሊሉ አንጄሎ/ ዜብራ ሓላ/የተ/የግ/ማ / 4ኪሎ ፕሪምየም/ በዜብራ ግሪል ሓላ/የተ/የግ/ማ ስም የተመዘገበ ሀዋሳ ከተማ ምሥራቅ ክፍለ ከተማ የሚገኝ 1,271.83 ሜትር ካሬ ይዞታ ያለው ባለ 4/ባለ 2 እና ባለ 1 ወለል ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ህንፃ፥ የሐራጁ መነሻ ዋጋ በብር 30 ሚልዮን፣ የሐራጁ ቀንና ሰዓት 17/11/2011 ዓም። ከቀኑ 8:00 ሰዓት እስከ 11:00 ሰዓት
3ኛ፥ አቶ ዮናታን አክሊሉ አንጄሎ ዜብራ ግሪል ሓላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ አበዳሪው ቅርንጫፍ 4ኪሎ ፕሪምየም፣ በዜብራ ግሪል ሓላ/የተ/የግ/ማ ስም እየተመዘገበ። አዲስ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኝ 500 ካሜ ይዞታ ያለው መኖሪያ ቤት፣ የሐራጁ መነሻ 25 ሚልዮን የሐራጁ ቀንና ሰዓት 17/11/ 2015 ከ4:00 እስከ 6:00 ሰዓት።
•እየተጫረታችሁ…!
ኢዜማ‼️
#ከ250 በላይ የሚሆኑ በተለያዩ ሃላፊነቶች ላይ የነበሩትን ጨምሮ በርካታ የኢዜማ አባላት ከፓርቲው መልቀቃቸውን አስታውቀዋል።
በኦሮሚያ ክልል የሕግ ታራሚዎች የሕክምና አገልግሎት እያገኙ አለመሆኑ ተገለፀ‼️
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ ክልል ባሉ የተለያዩ ማረሚያ ቤቶች አካሄድኩት ባለው የጥናት እና የክትትል ሥራ ከሕክምና አገልግሎት ጋር በተያያዘ በርካታ የመብት ጥሰቶች መኖራቸውን ገልጿል፡፡
በዚህም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጅማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በዳሳ ለሜሳ፤ "ኮሚሽኑ ማረሚያ ቤቶች ላይ ባካሄደው የዳሰሳ ጥናት እና ክትትል ከፍተኛ የሆነ የሕክምና አገልግሎት አለማግኘት ችግር እንዳለ ማወቅ ተችሏል።" ሲሉ ተናግረዋል።
ኮሚሽኑ በ31 ማረሚያ ቤቶች ላይ ባካሄደው ጥናት የሕግ ታራሚዎች የሕክምና አገልግሎት ጋር በተያያዘ ጉድለቶች እንዳሉ እና ከሰብአዊ መብቶች አያያዝ ጋር በተገናኘም ክፍተቶች መኖራቸውን አስረድተዋል፡፡
ስለሆነም በበርካታ ማረሚያ ቤቶች የላቦራቶሪ አገልግሎት እንደማይሰጥ እና ታራሚዎች ለቀላል ሕመምም ቢሆን ወደ ሆስፒታል ሪፈር ተብለው እንደሚሄዱ ነው የገለጹት፡፡
ቀሪዎቹን ደግሞ የሕመም ምልክቶችን ብቻ በመጠየቅ ግምታዊ የሆኑ ሕክምናዎችን እንደሚሰጣቸውና ይህም ላልተፈለገ የጎንዮሽ ጉዳት እየዳረጋቸው መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
እንዲሁም እንደ ወለጋ እና ጉጂ በመሳሰሉ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች በሪፈር እንዲታከሙ ቢጻፍላቸውም፣ አካባቢው ሰላም ባለመሆኑ እንደልብ ተንቀሳቅሰው ለመታከም እንደማይችሉ ተናግረዋል፡፡
ለታራሚዎች የሚቀርቡ የምግብ እና ሌሎች ፍጆታዎች በበቂ ሁኔታ ኦለመቅረብ ሌላው የታዘብነው ክፍተት ነው ያሉት፣ ኃላፊው ይህም ሊሆን የቻለው ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተያይዞ መሆኑን ጠቁመዋል።
"በአንዳንድ ማረሚያ ቤቶችም ኃይል የተቀላቀለበት እርምጃ እና ኢሰብዓዊ አያያዝ በታራሚዎች ላይ እንደሚደርስ ባካሄድነው የዳሰሳ ጥናት አረጋግጠናል" ነው ያሉት።
ትግራይ‼️
በትግራይ ክልል እስካሁን ከ718 በላይ ዜጎች በርሀብ መሞታቸውን ዘጋርዲያን ዘግቧል። ከእነዚህ ውስጥ 350 የሚሆኑት በአንድ ዞን ብቻ የሞቱ ናቸው ብሏል።
ከባድ የእሳት አደጋ‼️
በሶማሌ ክልል ርእሰ መዲና #ጅግጅጋ ከተማ በንግድ ቦታ የተከሰተው የእሳት አደጋ ከፍተኛ የንብረት ጉዳት አስከትሏል።
በጅግጅጋ ከተማ አዲሱ ታይዋን ገበያ ተብሎ በሚጠራው የመገበያያ ስፍራ ለጊዜው መነሻው ያልተወቀ ከባድ የእሳት ቃጠሎ ታይቷል።
የድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ቡድን፣ የፀጥታ አካላት እና የህክምና ባለሙያዎች ቡድን በአደጋው ስፍራ በመሰማራት የእሳት አደጋው ወደሌሎች አከባቢዎች እንዳይዛመት በጋራ እየተረባረቡ ነው ተብሏል።
በአዳማ/ናዝሬት እየተካሄደ ያለው የህዝብና የቤት ቆጠራ ጉዳይ‼️
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በአዳማ ከተማ ሕዝብ ቆጠራ ማካሄድ መጀመሩ "ግርታ" እና "ስጋት" እንደፈጠረባቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ለዋዜማ ተናግረዋል።
የመንግሥት መረጃ መዝጋቢዎች ቤት ለቤት እየዞሩ የብሄር ማንነት፣ ሃይማኖት፣ የቤተሰብ ብዛት፣ ጾታና ሌሎች መረጃዎችን እየሰበሰቡ እንደኾነ ዋዜማ ያነጋገረቻቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
የከተማዋ ኮምንኬሽን ጽሕፈት ቤት ግን፣ መረጃዎቹን መሰብሰብ ያስፈለገው በቅርቡ በከፍተኛ ደረጃ የሰፋችውን ከተማ በአዲስ መልክ በክፍለ ከተማና ወረዳ ለማደራጀት መኾኑን ነግሮናል።
የብሄር ማንነትን በቆጠራው ለምን ማካተት እንዳስፈለገ አልታወቀም።
ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ያቀረቡት ሙሉ ጥያቄ
የተ/ም/ቤት አባል ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ፦
" ጠ/ሚ ዐቢይ ወደ መንበረ ስልጣን ከወጡበት ከመጋቢት 2010 ዓ/ም ጀምሮ እየተወሳሰቡ የሄዱት የሀገራችን ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች አሁን ላይ ወደ ሁለንተናዊ ቀውስ መሸጋገራቸውን ማሸፋፈን ወደማይቻልበት ደረጃ ደርሰዋል።
ብልፅግና መራሹ መንግስትዎ ፦
- የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላም ወጥቶ የሚገባበት ፣
- ነጋዴው ከቦታ ወደ ቦታ ተንቀሳቅሶ ሰርቶ እና ነግዶ የሚኖርበት
- ገበሬው ምርጥ ዘር እና ማዳበሪያ አግኝቶ አርሶ የሚበላበት እንዲሁም ከተሜውን የሚቀልብበት ሁኔታ መፍጠር አልቻለም።
የኢትዮጵያ ህዝብ በችጋር እየተጠበሰ፣ በረሃብ እየተሰቃየ ነው።
የኑሮ ውድነቱ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ወገናችንን ከእጅ ወደ አፍ የነበረውን ኑሮ እንኳን መግፋት ወደማይችልበት ደረጃ ደርሷል።
ኢኮኖሚው ታሟል፣ መካከለኛ ነዋሪ የነበረውም ተመቶ ወደ ድህነት ወለል ወርዷል።
ስራ አጥነት ተስፋፍቷል፣ የሀገራችን የነገ ተስፋ የሆኑ ወጣቶችም ሀገራቸው ውስጥ ተስፋ በማጣታቸው ስደትን ብቸኛ ምርጫ አድርገውታል።
ዜጎች በጠራራ ፀሀይ ይታገታሉ በሚሊዮን ብር ይጠየቅቸዋል፣ የመንግስት የፀጥታ መዋቅር በተለይም ፖሊስ ደግሞ አማራዎችንን እና የአማራ ልሂቃንን የአማራ ህዝብ ጥያቄዎችን በማንሳታቸውና መንግሥትን በተለያየ ማንገድ በመተቸታቸው ብቻ የፈጠራ ወንጀል እየተሰጣቸው በማንነታቸው በጅምላ ይታሰራሉ ፣ በጅምላ ይከሰሳሉ ፍርድ ቤት ነፃ ሲላቸው ፖሊስ ግለሰቦችን አስሮ ያቆያል።
የኢትዮጵያ መልካፖለቲካ በሙሉ ያዳረሰ በሚባል ደረጃ ሀገራችን ሁሉም አካባቢዎች የደም ምድር ሆነዋል።
ሙሉ አማራ ክልል አዲስ የጦርነት ቀጠና ተደርጓል፣ ከፊል ኦሮሚያ ክልል የጦርነት ቀጠና ሆኖ ባጅቷል፣ ትግራይ አማራ እና አፋር ፋይዳ ባልነበረው የብልፅግናና የህወሓት የሳጣን ጦርነት ምክንያት ደቋል። ቤኒሻንጉል ፣ጋምቤላ፣ አብዛኛው የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎችም ከሌሎች የተለየ አይደለም።
በማህበራዊ ዘርፍም ወንጀል ተበራክቷል፣ ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች / ዜጎች በመንግስት ቤታቸው ፈርሶ ጎዳና ላይ ወድቀዋል ፤ እንደ ብልፅግና ሹማምንት አባባል ' ህጋዊ ድሃ ተደርገዋል ' ።
በሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች በሰሜኑና በምዕራቡ ሀገራችን ክፍሎች በነበረው ጦርነት እና ማንነት ተኮር ጥቃቶች የውስጥ ተፈናቃይ ሆነው የሰቆቃ ኑሮን ይገፋሉ።
ባለፉት 5 ዓመታት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወታቸውን ተነጥቀዋል። ለዚህ ሁለንተናዊ ሀገራዊ ምስቅልቅል ቀውስ እና ውድመት ወይም ሀገራዊ መክሸፍ ዋነኛው ተጠያቂው የብልፅግና መራሹ መንግስት እና የእርሶ የወደቀ አመራር / failed leadership ነው።
ገዢው ፓርቲ ብልፅግናን አመጣለሁ እያለ ቢምል ቢገዘትም በተግባር ለኢትዮጵያ ህዝብ ያመጣለት ግን ጉስቅልና ሆኗል።
ብልፅግና ሀገርን ከቀውስ ማውጣት ካልቻለ እና ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም የብልፅግና / የአገዛዙ አገልጋይ በመሆናቸው እና የችግሩም አካል በመሆናቸው ከፓርቲዎቹ የሚጠበው መፍትሄ አይኖርም።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ለወደቀው የእርሶ እና የብልፅግና ፓርቲዎ አመራር መፍትሄው ምንድነው ? የሀገራዊ ቀውስ መፍትሄ አፈላላጊ ጉባኤ እንዲዘጋጅ አድርገው ስይረፍድ ለሀገራዊ ቀውሱ መላ ቢበጅ አይሻልም ወይ ? እንደእኔ እንደ አንድ የህዝብ ተወካይነቴ ብልፅግና ፓርቲ መራሹም ሆነ ፓርላማው ሀገራችን ከገባችበት የፖለቲካ ቅርቃር ማውጣት ስለማይችሉ ስልጣኖን ለጊዜያዊ ሲቪል አስተዳደር እንዲያስረክቡ ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትም በኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀፅ 60 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት በምክር ቤቱ ፍቃድ ምክር ቤቱን እንዲበትኑ እና ለአዲስ ምርጫ መንገዱን እንዲጠርጉ መጠየቅ እፈልጋለሁ።
በቤኒሻንጉል ክልል የኢቦላ ቫይረስ እንዳይከሰት ስጋት መኖሩ ተነገረ‼️
በደቡብ ሱዳን እና በሱዳን የኢቦላ ቫይረስ ተጠርጣሪዎች መገኘት እና ሞት መመዝገቡን ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ ይገባል የሚል ስጋት እንዳለ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቃል።
በተለይ በሱዳን የተፈጠረውን የእርስ በእርስ ግጭት ተከትሎ የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ወደ ክልሉ በአጎራባች ወረዳዎች በኩል በከፈተኛ ሁኔታ ከመግባታቸው ጋር ተያይዞ በሽታው ሊገባ እንደሚችል ተገልጿል።
የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ጤና ቢሮ የህብተሰብ ጤና ጣቢዎች ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ ፍቃዱ አየለ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በሱዳን ዳባላይ በምትባል ስፍራ ከ150 በላይ በበሽታው የተጠረጠሩ ሰዎች እንዳሉ የተነገረ ሲሆን እሱን ለማጣራት ከዓለም የጤና ድርጅት እና ከሌሎች አካላት አካላት ጋር በመሆን ጥናት እየተደረገ ይገኛል።
(ብስራት ራድዮ)
ኢሰማኮ በኦሮሚያ ክልል ይፈፀማሉ ባላቸው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ፖሊስን ተቸ‼️
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ የኦሮሚያ ፖሊስ፥ በተጠርጣሪዎች ላይ የመብት ጥሰት እየፈጸመ ነው፤ ሲል ተቸ።
በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የጅማ ቅርንጫፍ ቢሮ ሓላፊ አቶ በዳሳ ለሜሳ፣ አሁንም በክልሉ የተለያዩ የፖሊስ ጣቢያዎች፣ የወንጀል ተጠርጣሪዎች ለፍርድ ሳይቀርቡ ለወራት እንደሚቆዩና በኢ-መደበኛ ቦታዎች ሳይቀር ተጠርጣሪዎች እንደሚታሰሩ፣ በክትትላችን ደርሰንበታል፤ ብለዋል።
ነዋሪዎች አሁንም፣ “በክልሉ የጸጥታ ነባራዊ ሁኔታ” በሚል ተጠርጥረው ታስረው የተፈቱና በእስር ላይ ያሉም እንዳሉ ታውቋል።
መረጃ‼️
የፍትሕ መጽሔት ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ምስጋን ዝናቤ ሀገር ጥሎ መሰደዱን ፍትህ መፅሄት በማህበራዊ ትስስር ገጿ አስታወቀች።
ጋዜጠኛው ሀገር ጥሎ እንዲሰደድ ያደረገው በደህንነቶች ምክንያት ህይወቱ አደጋ ላይ በመውደቁ መሆኑን ጭምር አብራርታለች።
በዚህ ምክንያትም የህትመት ስራዎቼን ለህዝብ ለማድረስ አስቸጋሪ አድርጎብኛል ብላለች።
ትህነግ የፌደራል መንግስቱን አጋልጦታል‼️
የፌደራል መንግስቱ ህወሓት ትጥቅ ፈትቷል ቢልም ትህነግ ግን የቀበራቸውን ከባድ መሳርያዎች እያወጣ ነው።
የሰላም ስምምነቱም፣ የፌደራል መንግስቱ ደባም በአደባባይ የተጋለጠባቸው እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ይገኛል።
በሱዳን፣ በጠለምት፣ በወልቃይት፣ በኤርትራ ድንበሮች ትህነግ የጀመራቸው በከባድ መሳርያ ጭምር የታገዙ ስልጠናዎች የፌደራል መንግስቱም ውሸትን እና ክህደትን ያጋለጡ ናቸው።
እንደዚህ አይነት ጋዜጠኞችም አሉ !
የአሚኮ ጋዜጠኛ ሀብታሙ ሙሃባ በዛሬ የአማራ ቴሌቪዥን ዜና «አሸባሪው ፋኖ» የሚል ዜና እንዲያነብ ሲቀርብለት ይህን አይነት ዜና አላነብም በማለት ስቱድዮ ለቆ ወጥቷል።
ከ500 ሺህ እስከ 1ሚሊዮን ብር ከፍለዉ የተለቀቁ ሹፌሮች ‹ያገቱን ታጣቂዎች የመንግስት ፀጥታ ሐይሎችን የደንብ ልብስ የለበሱ ናቸው› አሉ‼️
ሰኔ 10 ቀን 2015 ዓ.ም መንግስት ሸኔ በሚለው ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ በሚጠራው ታጣቂ ቡድን አባላት ከ30 በላይ የከባድ መኪና አሽከርካሪና ረዳቶች መታገታቸውን አሻም ከሰለባዎቹ መረዳት ችላለች፡፡
ለአጋቾቹ የተጠየቁትን ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለው የተለቀቁት ሰለባዎቹ እንደሚሉት ‹እገታውን የፈፀሙት ታጣቂዎች የመንግስት የፀጥታ ሀይሎችን የደንብ ልብስ የለበሱ ናቸው › ስሜና ድምፄ ለደህንነቴ ሲባል ይቆየኝ ያለና ታግቶ 500 ሺህ ብር ከፍሎ የተለቀቀ ረዳት በበኩሉ ‹ ሸኔ ከተባለዉ ታጣቂ ቡድን አምልጠን 7 ሰአት የፈጀ ጉዞ ካደረግን በኋላ በክልሉ ሚሊሻ ተይዘን ከ100 እስከ 150 ሺህ ብር ለእኛ ካልከፈላችሁን ለሸኔ አሳልፈን እንሰጣችኋለን በሚል አግተዉ ቤተሰብ ጋር እያሥደወሉን ገንዘብ ተቀብለዉ ለቅቀዉናል › ሲል ተናግሯል፡፡
ሌላኛው ሰለባ ደግሞ ‹መንግስት ሸኔ ሲል የሚጠራቸዉ ቡድን አባላት ናቸዉ ያገቱን ያሉ ሹፌርና ረዳቶች አጋቹ ቡድን ወስዶ በአርሶ አደር ቤት አስቀምጦ እየመገበ ገንዘብ ቤተሰቦቻችን እንዲያመጡ በየደቂቃዉ ያስደዉላል› ሲሉ ይናገራሉ፡፡
አሻም ያነጋገረቻቸው ወላጅ ልጃቸውን ከአጋቾቹ ገንዘብ በመክፈል ያስለቀቁ አንድ ወላጅ ደግሞ ያለፉበትን ውጣ ውረድ ለአሻም አሰረድተዋታል፡፡ለልጃቸው ሲሉ ‹ቤታቸውን ሽጠዋል፤ በእምነት ተቋማት፣ ነጠላ ዘርግተው› ለምነዋል፡፡
በፈረንጆች 2022 ብቻ በኢትዮጵያ በረሃብና በበሽታ ከ200 ሺሕ በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ‼️
በፈረንጆቹ 2022 ዓመት ብቻ በኢትዮጵያ በረሃብ እና ከረሀብ ጋር ተያይዘው ከሚከሰቱ በሽታዎች በተያያዘ ከ200 ሺሕ በላይ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።
በዚህም በኢትዮጵያ በረሃብና ተያያዥ በሽታዎች የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በየዓመቱ እየጨመረ መምጣቱ የተጠቀሰ ሲሆን፤ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ለእርዳታ የሚልኩት እህል ለግል ጥቅም ሲውል እና በገበያ ላይ ሲሸጥ አረጋግጠናል በሚል የሰብዓዊ እርዳታ መቋረጡም፣ በዚህ ወቅት በረሃብ እና በበሽታ ለሞቱ ሰዎች እንደ ዋና ምክንያት ተጠቅሷል።
እንዲሁም በዚያው ዓመት በተፈጠሩ ግጭቶች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺሕ በላይ መሆኑን ግሎባል ፒስ ኢንዴክስ በድኅረ ገጹ አስነብቧል፡፡
ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት የእርስ በርስ ግጭት ከምን ጊዜውም በላይ መባባሱ የተገለጸ ሲሆን፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ታጣቂዎች እና ንጹሃን መገደላቸውም ተመላክቷል።
እንደ አጠቃላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰባ ዘጠኝ አገራት ላይ በተደረገ ጥናት መሰረት ከግጭት ጋር በተገያያዘ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ዘጠና ስድስት በመቶ መጨመሩ ነው የተገለጸው።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ሲደረግ በነበረው ውጊያ ከ83 ሺሕ በላይ ዩክሬናውያን ሕይወታቸው ማለፉን እና በርካታ የአገሪቱ ዜጎች ደግሞ ለስደት መዳረጋቸውም ተጠቅሷል፡፡
ደቡብ ወሎ‼️
በሰሜን እና በደቡብ ወሎ አዋሳኝ አካባቢ
ልዩ ስሙ "ሳጋት" በሚባል ቦታ እንዲሁም በወረኢሉ አካባቢ ከትላንት ሌሊት 5:00 ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ ተኩስ እየተካሄደ እንደሆነ ምንጮች ገልጸዋል።
ደቡብ ጎንደር‼️
በደቡብ ጎንደር ዞን እብናት ትናንት በፋኖ እና በወረዳው የፀጥታ አካላት በነበረው ውጊያ ከፖሊስ እና ከአድማ ብትና የሟቾቹ ቁጥር አምስት ደርሷዋል። ከእነዚህ ሟቾች ውስጥ የወረዳው የሚሊሻ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሻንበል ሲሳይ ይገኝበታል(ስርዐተ ቀብሩ ዛሬ ተፈፅሟል)። ዛሬ ረፋድ ድረስ ሌሎች አስኬረናቸው ያልተነሳ እንዳለ የአይን እማኞች ገልፀዋል።
ከወጣት ፋኖዎች በከል ደግሞ 9 የሚሆኑት ከቀላል እስከ ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል።
ይህን ተከትሎ በወረዳው ዛሬም ውጥረት ነግሷል።
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በሙሉ፥ እንኳን ለ1444ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
መልካም በዓል‼️