የዶቼቬሌ ዘገባ ነው ከታች ያለው 👇
በአማራ ክልል ርዕሰ ከተማ ባህርዳር ሁለት ቦታ ቦምብ ፈንድቷል። ፍንዳታው ስላደረሰው ጉዳት ዝርዝር መረጃ እንዳልወጣ የባህርዳሩ ወኪላችን አለምነው መኮንን እስቱድዮ ልንገባ ስንል ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት አሳውቆናል።
#እኔም_ፋኖ_ነኝ ይህ ቻሌንጅ
እንዲጀመር የአማራ ወጣቶች ማህበር ዛሬ ከሰዓታት ጥሪ አቅርቧል። እና ምን እየጠበቃችሁ ነው ፌስቡክን፣ ቲክቶኩን፣ ቲዊተሩን እና ቴሌግራሙን "እኔም ፋኖ ነኝ" እያላችሁ ማታጥለቀልቁት። የደም ዋጋ እየከፈለ ለሚገኘው የአማራ ፋኖ ፍፁም አጋርነታችንና አንድነታችን #ሼር #ላይክ፣ #ፖስት በማድረግ ልናሳይ ይገባል። #እኔም_ፋኖ_ነኝ!
(አቶ ክርስትያን ታደለ)
የዐቢይ አሕመድ አስተዳደር በአማራ ሕዝብ ላይ እየፈፀመ ያለውን ወረራና የንፁኃን ግድያ በአስቸኳይ እንዲያቆም እያሳሰብሁ፤ የሰብአዊ መብት ተቋማት፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ እንዲሁም ሚዲያዎች መንግስት የቴሌኮም አገልግሎቶችን በመዝጋት ጭምር በአማራ ክልል በከባድ መሣሪያ ታግዞ በንፁኃን ዜጎች ላይ እየፈፀመ ያለውን ጭፍጨፋ እንድታወግዙና አገዛዙ ላይ ጫና እንድታሳድሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
ጋሸና እና እስታይሽ‼️
ትላንት ከጋሸና እና ከእስታይሽ መካከል 7:00 ጀምሮ በፋኖ እና በመከላከያ ከባድ ውጊያ እተካሄደ ነው። በዚህም በፀጥታ ኃይሎች ላይ ጉዳት ደርሷል።
ሽማግሌዎች በቦታው ቢሄዱም ፋኖዎች አሳፍረው መልሰዋቸዋል ተብሏል።
"ትጥቅ እንዲፈቱ ያደረግናቸው ታጣቂዎቻችን አካባቢያቸውን እንዲጠብቁ አደራጅተንና ስምሪት ሰጥተን ነው ወደ የአካባቢዎቻቸው የላክናቸው" ሲል ታደሰ ወረደ ተናግሯል።
ትጥቅ ሳይፈቱ አካባቢያቸውን በምን ሊጠብቁ ነው❓ ስለዚህ ትጥቅ አልፍቱም ማለት ነው።
በነገራችን ላይ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ትምህርት ሚኒስቴር እና ጤና ሚኒስቴር ወልቃይት እና ራያን በአማራ ክልላዊ መንግሥት ስር አድርጎ በመመደቡ ምክንያት ቅሬታቸውን ፅፈው ለየሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ (ለትምህርት ሚኒስቴር እና ለጤና ሚኒስቴር) ሳይቀር የመልስ ምቱን በደብዳቤ እየሰጡ ይገኛሉ።
የአማራ ክልላዊ መንግስት ደግሞ ዝምታን መምረጡ አስገራሚ ነው።
ጌታቸው ረዳ ዴንቨር ያደረገው ንግግር
ትግራይ ላይ የተደረገው ጦርነት በ”design” የተደረገ ነው አማራን አፋር ከተደረገው አይወዳደርም።
መከላከያ በወልቃይትና ራያ የአማራ አስተዳደር መዋቅሮችን የማፍረስ ግዳጅ ተሰጥቶት እየሰራ ነው ስራውን ጀምሯል In principle ፌደራል መንግስት ግዛቶቹን ለመመለስ ተስማምቷል።
በብዙ እስር ሽዎች የሚቆጠር ሰራዊት አለን
Via Gizaw Legesse
ትላንት ከምሽቱ 3:30 ጀምሮ በወልድያ ከተማ የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ገልፀዋል።
በከተማዋ በተለይ ፒያሳ ዳቦ ቤቱ አከባቢ የተጀመረው የተኩስ ልውውጥ አድማሱን እያሰፋ በአሬሮ፣ በመናኸሪያው ጀርባ፣ በቲንፋዝ እና በማረሚያ ቤቱ አከባቢ ከባድ የሆነ የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ መሆኑን ነው የአማራ ድምፅ ሚድያ የከተማዋ ነዋሪዎችን በማነጋገር ለማረጋገጥ የቻለው።
ምንጮቻችን አክለውም የተኩስ ልውውጡ በቡድን መሣሪያዎችም ጭምር የታገዘ ነው ያሉ ሲሆን፤ ነገር ግን ተኩሱ በማን እና በማን መካከል እንደሆነ ማረጋገጥ አልቻልንም ብለዋል።
ዘገባው የአማራ ድምፅ ሚዲያ ነው!
ቆቦ‼️
በመከላከያና በፋኖ መካከል ቆቦ ዙሪያ በአረፋ ጊዮርጊስ ከፍተኛ ተኩስ ልውውጥ እየተደረገ ነው። ትናንት ጀምሮ የተኩስ ልውውጡ ቆሞ የነበረ ቢሆንም አንደገና ተጀምሯል።
የፌደራል መንግስቱ የሰላም ስምምነቱን ጥሶ ከህወሓት ጋር ድብቅ ውል ይዟል። ይህን ድብቅ ውል ደብረፅዮን ይፋ አድርጎታል።
አባላቱን በጀሌ እያሰረገ ሲያስገባ የሰነበተው ትህነግ ለቀጣይ ወረራ ታጣቂዎቹ ወደ አማራ ክልል መሻገር ጀምረዋል።
መረጃ‼️
ቅዱስ ሲኖዶስ ሐምሌ 9 ቀን በትግራይ ክልል ይደረጋል የተባለው ሕገ ወጥ "ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት" ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የጣሰ እና ተገቢነት የሌለው በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲቆም አሳሰበ‼️
የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በትናንትናው ዕለት ባካሄደው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤው ሐምሌ 9 ቀን በትግራይ ክልል ይደረጋል የተባለው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ የሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 37 እና 38 የጣሰ እና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር ተገቢ ያልሆነ፣ የቤተ ክርስቲያንን ማዕከላዊ አስተዳደር የሚጥስ አንድነቷን የሚጎዳ ፤ በጦርነቱ ሀብት ንብረቱ የወደመበትን እና እጅግ የተጎዳውን ሕዝብ የማይጠቅም ተገቢነት የሌለው በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲቆም ወስኗል።
በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ችግር በውይይት እንዲፈታ ተደጋጋሚ ጥረት ማድረጉን የገለጸው ቅዱስ ሲኖዶሱ ተፈጠረ ለተባለው ችግር ይቅርታ የተጠየቀ ቢሆንም ለይቅርታው አዎንታዊ ምላሽ አለመሰጠቱ አሳዛኝ ነው ብሏል።
ባለፈው ሰኞ ወደ በቅዱስነታቸው የተመራው የሰላም ልዑክ ወደ በመቀሌ ተጉዞ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ቢሄድም ቤተ ክርስቲያኑ ተዘግቷል መቆየቱን የገለጸው ቅዱስ ሲኖዶሱ በትግራ ጊዜያዊ አስተዳደር ለልዑኩ ለተደረገው አቀባበል አመስግኗል።
በክልል ተከስቶ የነበረው ችግር በፌደራል መንግስቱ እና በጊዜያዊ አስተዳደሩ አማካይነት የተፈታ ቢሆንም የሰላም ባለቤት የሆነችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እስከአሁን ሰላም መፈለጓ ያልተቋረጠ ቢሆንም አለመሳካቱ የሚያሳዝን በመሆኑ ለሰላም የሚደረገው ጥረት ዘላቂ መፍትሔ እስከሚገኝ ድረስ የማያቋርጥ መሆኑን ያስታወቀው ቅዱስ ሲኖዶሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት እየተደረገ ያለውን ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ያልተከተለ የኤጲስ ቆጶስነት ምርጫ እንዲያስቆሙ ጭምር ጥሪውን አቅርቧል።
“ነጻነት ተፈጥሯዊ መብት ነው፤ የተነጠቅነውም ያስመለስነውም ተፈጥሯዊ መብታችንን ነው” ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ‼️
ከሐምሌ 5 እስከ ጥቅምት 24 በሁለት የተለያዩ ዓመታት ያየናቸው ሁለት ዓበይት ክስተቶች የአማራን ሕዝብ መሠረታዊ ትግል እና ድል ፈር ያስያዙ አጋጣሚዎች ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡ ዴሞክራሲያዊ ጥያቄን በሰከነ እና በሰለጠነ መንገድ መመለስ ያልቻሉ የዓለም አምባገነን መንግሥታት ያዩትን ውርደት በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር ትናንት የነበሩ አምባገነኖችም አይተዋል፡፡
ትውልዱ ከሀገር እና ሕዝብ በላይ የኾነ ፍጹም ምድራዊ ኃይል እንደሌለ በዚያች ተዓምራዊት ሌሊት በተግባር አይቷል፡፡ ግፈኞች የግፍ ቁናቸው ሞልቶ የሚያፈሰውን መከራ እና ሞት መቀበል ጀምረዋል፡፡ ሐቅን እስከ ህቅታ የያዙ እውነተኛ የሕዝብ ልጆች ደግሞ ለአይቀሬው ድል የሞት ሽረት ትግል አድርገዋል፡፡ በመጨረሻም እውነት እስከ ንጋት ድረስ ሳትጠበቅ ሕዝብ አሸናፊ የኾነበትን የድል ብስራት ዜና ሐምሌ 5 ምሽት ላይ ሰማ፡፡
በኢትዮጵያ ዘመናዊም ኾነ ጥንታዊ የሀገረ-መንግሥት ምስረታ ታሪክ የአማራ ሕዝብ ታላቅ አበርክቶ አለው ያሉን የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኅላፊ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የታላቅ አበርክቶው መገለጫ ራሱን በንቃት ከመጠበቁ እና የሌሎችንም አጥብቆ ከማክበሩ ይመነጫል ይላሉ፡፡ በየዘመኑ ያለፈው ሥርዓተ መንግሥት ሁሉ ከኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና ከሕዝብ ተጠቃሚነት አንጻር ሲታይ በርካታ ክፍተቶች ነበሩበት የሚሉት ኮሎኔል ደመቀ ባለፈው ሥርዓት ከነበረው ዝቅጠት የከፋ ክስተት የታየበት ጊዜ ግን አልነበረም ይላሉ፡፡
ባለፈው ሥርዓት የአማራ ሕዝብ ማንነቱ ተጨፍልቆ፤ ነጻነቱን ተነጥቆ ቆይቷል ያሉት ኮሎኔል ደመቀ ከበርካታ ዓመታት ውጣ ውረድ በኋላ በቅርቡ ማንነቱንም ፤ ነጻነቱንም ማስመለስ ችሏል ነው ያሉት፡፡ ያስመለሰውን ነጻነት አስጠብቆ እና ማንነቱን ጠብቆ ለመዝለቅ ከምንጊዜውም በላይ በሰከነ እና በበሰለ መንገድ መጓዝን ይጠይቃል ብለዋል፡፡ “ነጻነት ተፈጥሯዊ መብት ነው፤ የተነጠቅነውም ያስመለስነውም ተፈጥሯዊ መብታችንን ነው” ያሉት ኮሎኔል ደመቀ ከነጻነት ማግስት ለመልማት እና ለማደግ መሥራት ደግሞ ሌላው ተፈጥሯዊ ግዴታችን መኾን አለበት ብለዋል፡፡ ዞኑ በሙሉ አቅሙ እና ትኩረቱ ልማት ላይ መኾኑን በማንሳት፡፡
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ሕዝብ እና አሥተዳደር ከነጻነት ማግስት ጀምሮ በሰላም ማስጠበቅ እና በልማት ሞዴል አካባቢ ኾኗል ብለዋል፡፡ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም እና አንጻራዊ መረጋጋት ከሚስተዋልባቸው አካባቢዎች የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አንዱ ነው ያሉት ኮሎኔል ደመቀ የተገኘው ሰላም የሕዝቡ እና አሥተዳደሩ መናበብ እና መደጋገፍ የፈጠረው ጥምረት ውጤት ነው ብለዋል፡፡
ሕዝቡ ላለፉት ዓመታት ለማንነቱ እና ለነጻነቱ ዋጋ የከፈለ ሕዝብ በመኾኑ ያገኘውን ድል ለማጽናት በቁርጠኝነት እየሰራ መኾኑን ያነሱት ኮሎኔል ደመቀ የአማራ ሕዝብ ካለፈው መማር፣ አንድ መኾን እና ለዓላማ መጽናት ግድ የሚልበት ወቅት ላይ መኾኑን አንስተዋል፡፡ የአማራ ሕዝብ ትግል ከውስጥ ወደ ውጭ የሚያይ መኾን ይኖርበታል ያሉት መምሪያ ኅላፊው ውስጣዊ አንድነትን ማጠናከር ለነገ የማይባል የአማራ ሕዝብ የቤት ሥራ እንደኾነም አንስተዋል፡፡
አሚኮ
ሱዳን ወደ ሙሉ የእርስ በእርስ ጦርነት ለመግባት አፋፍ ላይ ነች ተባለ‼️
ሱዳን ከሦስት ወራት አስከፊ ግጭት በኋላ ወደ ሙሉ የእርስ በእርስ ግጭት ለመግባት አፋፍ ላይ መሆኗን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገልጿል።
ድርጅቱ ይህን ያለው ቅዳሜ ዕለት በኦምዱርማን ከተማ በተፈጸመ የአየር ጥቃት ከ20 በላይ ሰዎች መገደላቸውንና በርካቶች መቁሰላቸውን ተከትሎ ነው።
በአየር ጥቃት ጭምር ተባብሶ በቀጠለው የሱዳን ግጭት ከሦስት ሺሕ በላይ ሰዎች መሞታቸው እንዲሁም ጾታዊ ጥቃትና ዝርፊያ ተባብሶ መቀጠሉ ተመላክቷል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒ ጉቴሬዝ ቅዳሜ ዕለት በኦምዱርማን ከተማ የተፈጸመው የአየር ጥቃት በትንሹ የ22 ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉን ገልጸው፤ በሱዳን ጦርና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መካከል እየተካሄደ ያለው ፍልሚያ ሱዳን ወደለየለት የእርስ በእርስ ግጭት እያስገባት ነው ብለዋል።
ዋና ጸሃፊው አክለውም፤ የሱዳን ወደ እርስ በእርስ ጦርነት መግባት በቀጠናው አለመረጋጋት ያስከትላል ነው ያሉት።
እንደ ዓለም አቀፉ የስተኞች ተቋም መረጃ ሦስት ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ከቀያቸው ሲፈናቀሉ ከ700 ሺሕ ያላነሱ ሰዎች ደግሞ ወደ ጎረቤት አገራት ተሰደዋል።
በአገሪቱ ዳርፉር ግዛት በአሜሪካና የተወሰኑ ምዕራባውያን አገራት ዘንድ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ተጠያቂ የሆነበት ማንነት ተኮር ግጭት መኖሩም ነው የተጠቀሰው።
መረጃ‼️
ዶ/ር ደብረፂዮን፣ሞንጀሪኖ እና አለምገብረዋሃድ በሽሬ ከተማ ሰኔ 29 ስብሰባ አድርገው አቅጣጫ አስቀምጠው ሄደዋል ሲሉ ምንጮች ገልጸዋል።
በዚህ ስብሰባ ላይ የአካባቢው አመራሮችን ጭምር በስብሰባው ተሳትፈዋል።
በዚህም ዶክተር ደብረፂዮን በአጭር ጊዜ ውስጥ የጠለምት አካባቢዎችን ተረክበው እንዲያስተዳድሩ ጠይቀዋል።
ይሄ ተፈፃሚ እንዲሆን የፌደራል መንግሥት በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ድጋፍ ያደርጋል ብለን እናምናለን ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በአካባቢው ያሉ የወርቅ እና የማዕድን ቦታዎችን እንዲቆጣጠሩም አዲስ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።
ደብረፂዮን ይህን ካለ ወዲህ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች በስፋት እየታዩ ነው።
በአዲስ አበባ ከ10,000 በላይ ሰዎች በማንነታቸው ተለይተው እንደታሰሩ ካሳ ተሻገር የተባሉ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል ለምክር ቤቱ አንስተዋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ደግሞ ቁጥሩ ተጋኗል ሲሉ መልስ ሰጥተዋል።
መቼም ዙንድሮ ጉድ ነው
የጥቁር ህዝቦች የድል አርማ የሆነው አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ❗
ይህ ፎቶ የኬኒያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ፓን አፍሪካን በአዲስ መልኩ እንገነባለን በማለት ዛሬ ባካሄዱት ስብሰባ ላይ የተነሳ ፎቶ ነው።
በራያና ጠለምት ጉዳይ ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ሀሳብ በመቅረቡ የጠለምት ተወካዮች ስብሰባ ረግጠው ወጡ
=======#=======
ሐሙስ ሐምሌ 27 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የአማራ ክልል መንግሥት ባለፈው ቅዳሜ ሐምሌ 22/2015 በባህር ዳር ከተማ በተደረገ ስብሰባ ላይ በራያ እና ጠለምት አካባቢዎች የሚነሳው የማንነት ጥያቄ በሕዝበ ውሳኔ እልባት እንዲያገኝ ሀሳብ ማቅረቡን ተከትሎ፤ ሀሳቡን አንቀበልም ያሉ የጠለምት ተወካዮች ስብሰባውን ረግጥው መውጣታቸውን አዲስ ማለዳ ከተሳታፊዎች አረጋግጣለች።
ስብሰባውን ረግጠው የወጡት የጠለምት አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ አባላት፤ “በስብሰባው ላይ “በጠለምት ሕዝበ ወሳኔ ይካሄዳል” እንዲሁም በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት “ጠለምት እና አካባቢው በመከላከያ ሠራዊት እና በፌደራል ፖሊስ ይተዳደራል” የሚል ሀሳብ በመቅረቡ ስብሰባውን ረግጠን ለመውጣት ተገደናል፡፡” ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
በታሪክ ይመዝገብ፤ ይልቃል ከፍያለ ለአብይ አህመድ የአማራን ህዝብ ዘለቄታዊ ጥቅምና ሰላም ወደ ጎን በመግፋት ወረራን በይፋ በደብዳቤ ጠይቋል!!!
Читать полностью…ትናንት በደቡብ ጎንደር ደብረታቦር ከተማ ዙሪያ በነበረው ተኩስ እስካሁን በደረሰኝ መረጃ አራት ሰዎች ሞተዋል። ሁለቱ ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል።
ዛሬ ጠዋት ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ እንደነበር እና ለፋኖዎቹ ቁርስ ሲያበሉ እንደነበር አይተናል ሲሉ ነዋሪዎቹ ገልፀዋል።
ህዝቡ በራሱ የመንግሥት ተቋማትን እየጠበቀ ነው ብለዋል።
መንገዱ እስካሁን ዝግ ነው።
ከተለያዩ አካባቢዎች በርካታ ወጣቶች ወደ ከተማዋ በመግባታቸው የከፋ እልቂት እንዳይከሰት ከፍተኛ ስጋት አለ።
ቀድሞ ልዩ ሀይል የነበሩ አሁን ላይ በአድማ ብተና ክልሉን እያገለገሉ የነበሩ ከእነትጥቃቸው መጥፋታቸውም ተሰምቷል።
የክልሉ የፀጥታ ችግር ከቀን ወደቀን አድማሱን እያረፋ መጥቷል።
ባህርዳር❗❗
ባሳለፍነው ሳምንት አርብ እና ቅዳሜ የወልቃይት፣ የጠለምት፣የራያ እና የዋግ ኮር አመራሮች ባህርዳር ለስብሰባ ተጠርተው ነበር። የዚህ ስብሰባ መሪዎች የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ እና የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ናቸው። የስብሰባው ዋና አላማ የማንነት ጥያቄ ባለባቸው አካባቢዎች በህዝበ ውሳኔ እልባት ማግኘት እንዳለበት፣አዋጪ የመፍትሔ አቅጣጫም እንደሆነ፣ዓለም አቀፍ ተቀባይነት እንደሚኖረው፣ ፖለቲካዊ ውሳኔ ቢወሰን እና በዚህ መሀል ህወሃት ጦርነት ቢከፍት ትልቅ የፕሮፓጋንዳ ግብዓት ይሆነዋል..... በሚል አቶ አገኘሁ ተሻገር ለማሳመን ሞክረዋል።
በዚህም የራያ አመራሮች በህዝበ ውሳኔው እንደሚስማሙ፣የወልቃይት እና የጠለምት አመራሮች ደግሞ ይህ መሬት ያለ ምንም የህግ ማዕቀፍ በግድ የተወሰደ ስለሆነ አሁን ወደ ቀድሞ ይዞታው ተመልሷል፣ ህዝበ ውሳኔ አንቀበልም በሚል ስብሰባውን ጥለው መውጣታቸውን አረጋግጠናል።
አቶ አገኘሁ ተሻገር የራያ እና የወልቃይት ጉዳይ ፋይሉ የተዘጋ ነው ማለታቸውን እናስታውሳለን።
==[=====================
ሞስኮ ዋናው እምብርት ላይ ፡ ሚገኘው፡ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ቢሮ ፡ በድሮን ተመታ።
የራሺያ መልስ ይከፋል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።
🔥#መረጃ‼️
የወልድያ ከተማ ምክትል ከንቲባ ዶ/ር ዳዊት መለሠ በራሳቸው ፈቃድ የሥራ መልቀቂያ ማስገባታቸው እየተነገረ ነው ።
ምክንያታቸው ፋኖ ላይ የተጀመረውን ጥቃት በመቃወም ነው እየተባለ ነው።
ዝርዝር ማብራሪያ አልተሰማም።
በዚህ ዜና ላይ ዝርዝሩን እናቀርባለን
በአማራ ላይ የተከፈተ ጦርነት ነው! ኢትዮጵያዊያን ሊያወግዙት የሚገባ ነው!
ምሬ ወዳጆን ከወገኑ ባልተናነሰ መከላከያ ያውቀዋል። መከላከያ ሰራዊት ከራያና አካባቢው ከሸሸ በኋላ ለምሬ ፋኖ ራዲዮና ሌሎች መሳርያዎችን ሰጥቶት ትህነግ በያዘው አካባቢ ጭምር እየገባ ያደራጀ፣ የተዋጋ ጀግና ነው።
በጦርነቱ ወቅት ለትህነግ ሙሉ መኪና መሳርያ ያስረከበ ጀኔራል አለ። ምሬ በተቃራኒው ከትህነግ ሲማርክ የከረመ ጀግና ነው።
ትህነግ በተደጋጋሚ ሲያጠቃው ለከረመ ህዝብ የደረሰው የምስራቅ አማራ ፋኖ ነው።
መከላከያ ሲከበብ ከበባ የሰበረ ኃይል ነው።
ሞሬ ወደ ትግል የገባው ሀብቱን በትኖ ነው። ለህዝብ ዋጋ ከፍሏል። በእነ ምሬ ላይ የተከፈተው ጦርነት በአማራ ህዝብ ላይ የተከፈተ ጦርነት ነው። ሶስት አመት ሙሉ ጦርነት በከረመበት ራያ ላይ የተከፈተው ጦርነት መላው አማራ ላይ የታወጀ ነው። የትህነግ ጦርነት ጋብ ሲል ህዝብ በገዥዎቹ ዘመቻ እየተሰቃየ ነው።
ባንክ አልዘረፉም። አገር አልከዱም። ሌላ ህዝብ አልወረሩም። በራያ ላይ የተከፈተው ጦርነት አማራን ለማዳከም የታቀደ ነው።
በትግል ላይ ነን የሚል አካል አንዳንድ ጉዳዮችን እንደ ድል አይቶ ከመዘናጋት ወረራው እንዲቆም፣ እንዲመከት ማድረግ ላይ ማተኮር አለበት።
ፋኖ ዋጋ እንደከፈለላቸው፣ እንዳተረፋቸው የሚያውቁ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እየከዱ ነው። የጦርነቱን አላማ ስለሚያውቁ ነው። የወረራውን ፀረ አማራ አላማ የሚያውቁ የሰራዊት አመራሮችና አባላት ጭምር አሁንም ይህን ወረራ መቃወም አለባቸው።
ያኔ! በርካቶች በሸሹበት መከታ የሆኑት እነ ምሬ ናቸው። ኢትዮጵያ ልትፈርስ ነው ሲባል ከግንባር የተገኙት እነ ምሬ ናቸው። አዲስ አበባ ሆነው ሲጨነቁ ለነበሩት እፎይታ የሰጡት እንደ ምሬ ያሉት ናቸው። የአማራ ብቻ ሳይሆኑ የአገር ባለውለታዎች ናቸው። ይህ ፀረ አማራ ዘመቻ መቆም አለበት። ኢትዮጵያዊያን ጭምር ሊያወግዙት ይገባል።
(ጌታቸው ሽፈራው )
ደብረብርሃን❗❗
የደብረብርሃን ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ምንውየለት ጭንቅሎ በተለምዶ ሰማያዊ ሆቴል ፊት ለፊት ዛሬ 11:00 አካባቢ ደረታቸው አካባቢ በክላሽ ጥይት ተመተው ወደ ሆስፒታል ቢገቡም ህይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም።
==[=====================
መንግሥት በኢንተርኔት ላይ በጣለው ገደብ ከ7 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ኪሳራ ደርሷል ተባለ‼️
የኢትዮጵያ መንግሥት ከየካቲት 04/2015 ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ባሉት አምስት ወራት በኢንተርኔት አገልግሎት ተደራሽነት ላይ በጣለው ሕጋዊ መሰረት በሌለው ገደብ ምክንያት በአገሪቱ የደረሰው የኢኮኖሚ ጉዳት ከ7 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ማለፉን የመብቶችና ዴሞክራሲ እድገት ማዕከል ገልጿል፡፡
“ፖለቲካዊ አለመረጋጋቶችን ተከትሎ፤ ከ2008 ወዲህ የበይነመረብ ግንኙነትን ማቋረጥ በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣ ችግር ነው” ያለው ማዕከሉ፤ የበይነመረብ ግንኙነት መቋረጡ የዴሞክራሲና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕድገት ጸር መሆኑን አመላክቷል፡፡
መንግሥት ዋና ዋና የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች በኢትዮጵያ እንዳይጎበኙ እገዳ መጣሉ ሕጋዊ መሰረት የሌለው ነው ሲልም ገልጿል፡፡
የበይነመረብ ግንኙነት መቋረጥ ትኩረት ሊያገኝ ባለመቻሉም የሰብዓዊ መብቶች እሴቶችን እንዲሁም በሕገ መንግሥቱ የተጠበቁ የሰብዓዊ መብቶችንና ነፃነቶችን እየገፈፈ መሆኑንም ነው የጠቀሰው።
በዚህም በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ በተጣለው ገደብ ከ140 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር በላይ የኢኮኖሚ እንዲሁም፤ 27 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር የውጭ ቀጥታ የምርት ገበያ ኪሳራ ማድረሱን እና 2 ሺሕ 372 ሰዎች ሥራ እጥ እንዲሆኑ ማድረጉንም ገልጿል፡፡
በዚህም የበይነመረብ ግንኙነት መቋረጥ ዘመናዊ ንግዶችን በማደናቀፍ ኢኮኖሚው በየጊዜው በሚሊዮን ዶላሮች እንዲያጣ እንደሚያደረገውና፤ የምርጫ ተዓማኒነትን የሚያጎድል መሆኑን ማዕከሉ ገልጿል።
ማዕከሉ በኢትዮጵያ የበይነመረብ ግንኙነትን የማቋረጥ ተግባር “ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ እና መረጃ የማግኘት መብቶችን” እያደናቀፈ መሆኑን ገልጾ፤ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ይህንን የመንግሥትን ሕጋዊ መሠረት የሌለው ተግባር በፍርድ ቤት ሊሞግቱት እንደሚገባም አሳስቧል።
እንዲሁም የኢትዮጵያ ሕዝብ የበይነመረብ ግንኙነት ማቋረጥን መቃዎም አለበት ያለው ማዕከሉ፤ በኢንተርኔት ገደብ የሚጣለው የመረጃ የማግኘት ማዕቀብ እንዲነሳ የራሱን ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁሟል፡፡
የትግራይ ኃይሎች ጠለምት በመግባታቸው ተኩስ ተከፍቶ እንደነበር ተገለፀ‼️
በአማራ እና ትግራይ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ የሕወሓት ታጣቂዎች በመከላከያ ሠራዊት አባላት ታጀበው በምዕራብ ጠለምት ወረዳ ሲንቀሳቀሱ፤ ተኩስ ተከፍቶ እንደነበር የጠለምት አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ገልጿል፡፡
የኮሚቴው ሰብሳቢ ጸጋየ እሸቴ፤ “ትጥቅ ያልፈቱና በአማራ እና ትግራይ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች የሚንቀሳቀሱ የሕወሓት ኃይሎች በመከላከያ ሠራዊት ታጀበው ወደ ጠለምት እየገቡ ነው፡፡” ብለዋል፡፡
በዚህም ሐምሌ 02/2015 ረፋድ ላይ በሕወሓት ታጣቂዎችና በአካባቢው በሚገኙ የፋኖ፣ ሚሊሻና ልዩ ኃይል አባላት መካከል ለ30 ደቂቃ ገደማ የቆየ ተኩስ ለውውጥ መደረጉን ተናግረዋል።
አክለውም “ታጣቂዎቹ በጠለመት ተከዜ ዙሪያ አዲስ ጦርነት ለመጀመር ልዩ ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡ በመከላከያ ሠራዊት ታጅበውም ጠለምት ገብተው ይወጣሉ፡፡” ሲሉ ተደምጠዋል።
“ከአንድ ሳምንት በፊት የሕወሓት አመራሮች በሽሬ ከተማ ጠለምትንና ራያን በአጭር ጊዜ ወደ ትግራይ ክልል ለማካተት ሲመካከሩ ነበር” ያሉት ጸጋዬ፤ ከእሁድ ሐመሌ 02/2015 ጀምሮ በመከላከያ ሠራዊት የታጀቡ እስናይፐር እና ዲሽቃ የታጠቁ የሕወሓት ኃይሎች በስፋት ሲገቡ ነበር ብለዋል።
በዚህም የሕወሓት ታጣቂዎች በስምንት መኪና በመከላከያ ሠራዊት አባላት ታጅበው ሲገቡ በአካባቢው ካሉ የፋኖ፣ ሚሊሻና ልዩ ኃይል አባላት ጋር ዲማ እና ፍየል ውሃ በተባሉ ቦታዎች ላይ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ተገልጿል።
ትጥቅ ያልፈቱ የሕወሓት ታጣቂዎችን የመከላከያ ሠራዊት አባላት ስንቅ እና ትጥቅ እያቀበሏቸው መሆኑና፣ በጦር መሳሪያ አጅበው ወደ ጠለምት እንዲገቡ እገዛ ማድረጋቸው ሕዝቡን አስቆጥቷል ነው የተባለው።
በጠለምት ሦስት ቀበሌዎች እስካሁን ከሕወሓት ኃይሎች ነጻ አለመውጣታቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ጠለምትን እና ራያን እንዲሁም ወልቃይትን ለመቆጣጠርም ጥረት እያደረጉ ነው ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በዚህም በጠለምትና አካባቢው ሰሞኑን ውጥረት መንገሱ ነው የተጠቆመው።
የአላማጣ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ዘርፍ ኃላፊ ሞገስ እያሱ በበኩላቸው፤ “የሕወሓት ኃይሎች በአካባቢው ሁከት ለመፍጠር ሙከራ እያደረጉ ነው፡፡” ሲሉ ገልጸው፣ በራያ እና አላማጣ አቅራቢያ ሕወሓት በርካታ የታጠቀ ኃይሉን እያስጠጋ መሆኑን ተናግረዋል።
ለኹለት ዓመት የዘለቀው የሰሜኑ ጦርነት ፕሪቶሪያ ላይ በተደረገ የሰላም ስምምነት የተጠናቀቀ ሲሆን፣ በሰላም ስምምነቱ መሰረት የሕወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ እንዲፈቱ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
ሆኖም ይህን ስምምነት ወደ ጎን በመተው ታጣቂዎቹ በትግራይ እና አማራ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች በተደጋጋሚ ትንኮሳዎችን እየፈጸሙ ይገኛሉ የሚል አቤቱታዎች ይቀርባሉ።
የኮንዶሚኒየም ወረራ ❗️
በኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ማንነታቸዉ ያልጣወቀ ሰዎች የተዘግጉ ቤቶችን ቁልፍ ሰብሮ በመግባት ወረራ እየፈፀሙ ነዉ ተባለ‼️
በሸገር ከተማ አስተዳደር በሚገኘዉ ኮዬ ፈጩ ኮንደሚኒየም ለባለዕድለኞች በተላለፉ ቤቶች ዉስጥ ማንነታቸው የማይታወቁ ሰዎች ቁልፍ ሰብሮ በመግባት ወረራ እየፈፀሙ መሆኑን የኮንደሚኒየሙ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በኮንደሚኒየሙ የዕጣ ዕድለኞች ሆነዉ ለባለቤቶቹ ቁልፍ ተላልፎ ነገር ግን ተቆልፎ የተቀመጡ ቤቶች እና እስከአሁን ለባለዕድለኞች ባልተላለፉ ቤቶች ላይ የማይታወቁ ሰዎች ወረራ እየፈፀሙ ነዉ ተብሏል።
ይህን ድርጊት ለመከላከል ጥረት በሚያደርጉ የኮንደሚኒየሙ የጥበቃ ሰራተኞች ላይም ዛቻና ማስፈራሪያ በማድረስ በሀይል እንደሚገቡ ነዉ የተገለፀዉ። ነዋሪዎቹ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት ተዘግተው የተቀመጠን ቤት በሀይል ሰብረዉ ገብተው ወረራ ሲፈፅሙ አንድም የመንግስት አካል ሊያስቆማቸዉ የሞከረ የለም ሲሉ ተደምጠዋል።
ከመጋቢት 2015ጀምሮ በኮንደሚኒየሞቹ ላይ ከፍተኛ ወረራ እየተካሄደ መሆኑን በመጠቆም ጉዳዩን ለሚመለከተው አካል በተደጋጋሚ ብናቀርብም መፍትሄ ሊገኝ አልቻለም ሲሉ ተናግረዋል። በዚህም ወደ ኮንዶሚኒየሞቹ የሚገቡ እና የሚወጡ ሰዎች ማንነት ባለመታወቁ ህጋዊ ነዋሪዎችን ስጋት ዉስጥ እንደከተተ ተነግሯል።
===[==================
ሰበር መረጃ‼️
አማራ ክልል ከወልቃይት እና ከራያ አካባቢዎች አስተዳደሩን እንዲያስወጣ መታዘዙ ውዝግብ አስነስቷል።
ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን ይዘን እንመለሳለን።
ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በፍርድቤት ሊከሰስ ነው‼️
ከሰሞኑ የአማርኛን የትምህርት ክፍልን እዘጋለሁ ብሎ በእነ ዶ/ር ንጉስ ታደሰ በኩል የእውር ድንብር ውሳኔ ያሳለፈው ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በፍርድቤት ክስ ሊመሰረትበት እንደሆነ ተሰምቷል።
ዩንቨርስቲው አማርኛ ቋንቋን ጨምሮ የባህል ማዕከሉን የአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ታሪክ ጥናት ማዕከልን፣ ታሪክንና ሌሎች 18 ዲፓርትመንቶችን እዘጋለሁ በማለት ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል።
ይህን ተከትሎም ዩኒቨርሲቲው ክስ ሊመሰረትበት መሆኑን እና በቅርቡ ፍርድቤት ሊቀርብ እንደሆነም ታውቋል።
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ 18 ትምህርት ክፍሎችን ለመዝጋት በሂደት ላይ መሆኑ በዩኒቨርስቲው ማኅበረሰብ ጥያቄ አስነስቷል‼️
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ከአማርኛ ቋንቋ፣ ከታሪክ፣ ከማንነት፣ ከባህል እና ከአገር በቀል እውቀቶች ጋር የተያያዙ የማኅበራዊና ሥነ ሰብ፣ የተፈጥሮ ቀመር፣ ሳይንስ እና የስነ ትምህርት ኮሌጆችን መዝጋቱ ተቃውሞ አስነስቷል፡፡
ዩኒቨርስቲው በአራት ኮሌጆች ሥር የሚገኙ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ድግሪ የሚሰጡ 18 ትምህርት ክፍሎችን መዝጋቱን ተከትሎ፤ የዩኒቨርስቲው መምህራን የተቃውሞ ደብዳቤ ለደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ቦርድ አስተዳርር ጽ/ቤት አስገብተዋል፡፡
አዲስ ማለዳ የዩኒቨርስቲው መምህራን ለቦርዱ ያስገቡትን የተቃውሞ ደብዳቤ የተመለከተች ሲሆን፤ መምህራኑ ለቦድሩ ባስገቡት ደብዳቤ የዩኒቨርስቲው አመራር “በልየታ እና በልህቀት ማዕከል ያልተካተቱ ናቸው” በሚል ሰበብ በማኅበራዊ እና በተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጆች ሥር የሚገኙ ትምህርት ክፍሎችን፣ እንዲሁም የሕግና የሥነ ትምህርት ኮሌጆችን እንደሚዘጋ እና መምህራኑንም ከሥራ እንደሚያግድ አሳውቆናል ብለዋል፡፡
መምህራኑ በደብዳቤያቸው ውሳኔውን ኢ-አመክኗዊና ኢ-ሕገ መንግስታዊ ነው ያሉት ሲሆን፤ የአማርኛ ትምህርት ክፍል እና የትምህርት ክፍሉ መምህራን ከዛሬ ሐምሌ 1/2015 ጀምሮ የሥራ ስንብት ደብዳቤ እንደሚደርሳቸው ተነግሯቸዋል ተብሏል፡፡
የዩኒቨርሲቲው አመራር መምህራንና፣ ተማሪዎችን፣ እንዲሁም የዞኑን ማኅበረሰብ እና ባለድርሻ አካላትን ሳያወያይ፤ የፌዴራል እና የክልሉን የሥራ ቋንቋ በማን አለብኝነት እና በንቀት መዝጋቱ ተገቢነት የሌለው ውሳኔ በመሆኑ፣ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት አስቸኳይ የመፍትሄ እርምጃ እንዲወስዱ መምህራኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከዘጋቸው የትምህርት ክፍሎች ጋር በተያያዘ ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ገለጻ እንዲያደርግ በተደጋጋሚ በዩኒቨርሲቲው የመምህራን ማኅበር ቢጠየቅም ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል ተብሏል፡፡
እንዲሁም በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሊሸፈኑ የማይችሉትን የማኅበራዊና ሥነ ሰብ፣ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ እንዲሁም የሥነ ትምርት ኮሌጆችን ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ባልዘጉበት ሁኔታ ከዩኒቨርሲቲው እና ከአካባቢው ማኅበረሰብ ፍላጎትና ምርጫ ውጪ በጥድፊያ እንዱዘጉ መደረጉ፣ በክረምት ፕሮግራም ብቻ ከ18 ሺሕ በላይ ተማሪዎች እንዳይማሩ ያደርጋል ተብሏል፡፡
የዩኒቨርሲቲው አመራር የአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ታሪክ ጥናት ማዕከልን ጨምሮ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የተቋቋሙትን የባህል ማዕከል መዝጋቱን የተቃወሙት መምህራኑ፤ የዩኒቨርስቲው ማኅበረሰብ ስለ ውሳኔው በግልጽ መረጃ እንዲሰጥና የተዘጉ ት/ት ክፍሎች እንዲከፈቱ ጠይቀዋል፡፡
አዲስ ማለዳ በጉዳዩ የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ንጉስ ታደሰን የነጋገረች ሲሆን፤ ጥያቄ የተነሳበት ውሳኔ በትምህርት ሚኒስቴር የተወሰነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከአማርኛ ትምህርት ክፍል ጋር በተገናኘ መምህራን ያነሱት ጥያቄ ተገቢነት የለውም ያሉት ፕሬዚደንቱ፤ "ባለፉት ሦስት ዓመታት አማርኛ ትምህርት ክፍልን የመረጠ ተማሪ ባለመኖሩ ት/ት ክፍሉ ለመዘጋት በቅቷል።" ብለዋል፡፡
መምህራኑ ከሥራ ይታገዳሉ የተባለው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የጠቆሙት ፕሬዝደንቱ፤ "ትምህርት ሚኒስቴር በጥናት በወሰነው መሰረት ወደ ሌላ ዩኒቨርስቲ ሽግሽግ ይደረጋል እንጂ ከሥራ የሚሰናበት መምህር የለም።" ሲሉም ጨምረው ተናግረዋል፡፡