"በተፈጸመው የድሮን ጥቃት 70 ሰዎች ሞተዋል፣ ከ55 በላይ ሰዎች ቆስለዋል" የዞኑ አመራር‼️
"ሆስፒታል መጥተው 26 ሰዎች ሞተዋል፣ ጥቃቱ በተፈጸመበት ቦታ የሞቱም አሉ" የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ‼️
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተሰላም ከተማ እሁድ ነሐሴ 07/2015 ከቀኑ አምስት ሰዓት ገደማ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በትንሹ 70 ሰዎች መሞታቸውንና ከ55 በላይ ሰዎች ቆስለው ወደ ሆሰፒታል መላካቸውን ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የዞኑ የሥራ ኃላፊ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
ጥቃቱ የተፈጸመው በመሀል ከተማ በሚገኘው አደባባይ በጭነት መኪና ላይ በነበሩ ወጣቶች ከመኪናው እየወረዱ ባሉበት ወቅት መሆኑን ነው የሥራ ኃላፊው የተናገሩት።
በመኪናው ውስጥ ተሰባሰበው የነበሩት የከተማዋ ወጣቶች፤ ሕጻናት እና የኹለተኛ ደረጃ ተማሪዎች መሆናቸውን በመግለጽም፤ "በተፈጸመው የድሮን ጥቃት በትንሹ የ70 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን አረጋግጠናል" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በጥቃቱ ከሞቱ ሰዎች በተጨማሪ በከተማዋ የሚገኙ አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ አንበሳ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አዋሽ ባንክ ሕንፃዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተጠቁሟል፡፡
የሥራ ኃላፊው አክለውም፤ ባለፈው ቅዳሜ ነሐሴ 06/2015 በቡሬ ከተማ በነበረው የተኩስ ልውውጥ በከባድ መሳሪያ አራት የቤተሰብ አባላት መገደላቸውን ገልጸዋል።
የፍኖተ ሰላም አጠቃላይ ሆሰፒታል ሥራ አስኪያጅ ማናየ ጤናው፤ እሁድ በተፈጸመው የድሮን ጥቃት 26 አስከሬኖች እና ከ55 በላይ ቁስለኞች ወደ ሆሰፒታል መግባታቸውን ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
"የሞቱትም የቆሰሉትም የታጠቁ ወታደሮች አይደሉም።" ያሉት ሥራ አስኪያጁ፤ "ወጣቶችና ህጻናት ናቸው" ሲሉ ገልጸዋል።
በጥቃቱ ሆሰፒታል የመጡት 26 አስክሬኖች ይሁኑ እንጂ ጥቃቱ ከተፈጸመበት ቦታ ሞተው ወደ ቤተሰቦቻቸው የተወሰዱ መኖራቸውንም ጠቁመዋል፡፡
አክለውም፤ ወደ ፍኖተሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል ከዚህ በፊት በደንበጫ እና በቡሬ አካባቢ በነበረው የተኩስ ልውውጥ ከ160 በላይ ቁስለኞች መግባታቸውን ጠቅሰው፤ በአሁኑ ወቀት የትራንስፖርት አገልግሎት ባለመኖሩ እንዲሁም የኦክስጅን እና የደም እጥረት በማጋጠሙ መዳን የሚችሉት ሰዎች እየሞቱ ነው ብለዋል፡፡
"ደም እና ኦክስጅን ለጤና ተቋማት እንዲቀርብ ካለተደረገ የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ይሄዳል።" ሲሉም ተናግረዋል፡፡
እሁድ ዕለት በአካባቢው በተለይም በቡሬ ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ ተራራ በመከላከያ ሠራዊትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ከፍተኛ ውጊያ ሲደረግ እንደነበርም ተመላክቷል።
አዲስ ማለዳ
ጎንደር❗
እርምጃ እንወስዳለን:-ሰብሳቢዎቹ❗👇
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ትናንት ከነዋሪዎቹ ጋር ስብሰባ ማድረጉን የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል። በዚህ ስብሰባ ላይ "ዘራፊው" በሚል ስያሜ የመድረኩ መሪዎች ንግግር ለማድረግ ቢሞክሩም ተሰብሳቢዎቹ ዘራፊ ልትሏቸው አይገባም በሚል ስብሰባው ተቃውሞ ገጥሞት የነበረ ቢሆንም እንደገና እንዲቀጥል ተደርጓል።
በዚህም እስር እና አፈናው አለፍ ሲልም እርምጃ መውሰዱ እንደሚቀጥል ከአመራሮቹ በኩል የተገለፀ ሲሆን ተሰብሳቢዎቹ በበኩላቸው ፋኖ የሚታገለው ክልሉ ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን በአግባቡ መመለስ ባለመቻሉ ነው ብለዋል። እርምጃ እንወስዳለን፣ እናስራለን እያላችሁ የምትዝቱ ከሆነ ከህዝብ ጋር ትጣላላችሁ የሚል አስተያየት አንስተዋል።
አመራሮቹ ደግሞ የራያ እና የወልቃይትን ጉዳይ በህዝበ ውሳኔ ምላሽ ለመስጠት ጫፍ ላይ ሲደርስ ነው ይህ ጦርነት የተነሳው ያሉ ሲሆን አብይ አህመድም ይሄን አይክደንም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል ሲሉ የስብሰባው ተሳታፊዎች ገልፀዋል።
የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ወደ ሰሜን ሸዋ ደራ ወረዳ እየገቡ መሆናቸውን ነዋሪዎች መናገራቸው ተሰማ❗❗
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በወረዳው የገጠር ቀበሌዎች በስፋት እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ነዋሪዎች አስታውቀዋል፡፡
የወረዳው ነዋሪዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ወደ ወረዳው የገጠር ቀበሌዎች እየገቡ መሆናቸውን ገልጸው፤ ታጣቂዎቹ ከሰሞኑ በስፋት መንቀሳቀስ በመጀመራቸው ስጋት እየፈጠረባቸው መሆኑንም ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።
ታጣቂዎቹ ከዚህ ቀደም በወረዳው በተደጋጋሚ ባደረሱት ጥቃት በርካታ ዜጎች መገደላቸውንም ነዋሪዎቹ አስታውሰዋል።
በተጨማሪም በወረዳው የገጠር ቀበሌ ይኖሩ የነበሩ ዜጎች ታጣቂዎችን ሸሽት ወደ ወረዳዋ ከተማ ጉንዶ መስቀልና ወደሌሎች አካባቢዎች መሰደዳቸውን ተናግረዋል።
አሁን ላይ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች በወረዳው የገጠር ቀበሌ በሆኑ ባቡ ድሬ፣ ራቾና ድሬ መንቃታ አካባቢዎች በስፋት እየተንቀሳቀሱ መሆናቸው ነው የተነገረው።
ኦነግ ሸኔ ከኹለት ዓመት በፊት ጀምሮ ወደ ወረዳው በመግባት ዜጎችን በማገት ገንዘብ መቀበል እንዲሁም ግድያና ማፈናቀል እያደረሰ ነው ተብሏል።
በተለይም የደራ ወረዳን ከሰላሌ ጋር የሚያገናኘውን የጀማን ድልድይ በመቆጣጠሩ የወረዳዋ ነዋሪዎች በአማራ ክልል መርሐቤቴ ወረዳ በኩል ወደ አዲስ አበባ እንዲሄዱ መገደዳቸው ተገልጿል፡፡
የደራ ወረዳ ከአዲስ አበባ 2 መቶ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ወረዳ መሆኑ ይታወቃል።
"…በዝምታው፣ በትእግስቱ እንደ ሌለ የቆጠረውን፣ እንደ ፈሪ፣ ቆጥሮ ምንም የማያመጣ ቅዘናም፣ በጭባጫ፣ አዝማሪ ነው ብሎ በኦሮሞና ትግሬ አክቲቪስቶች ግምገማ ተነድቶ ቆስቁሶ የገጠመው ዐማራ የጋለ ብረት ምጣድ የሆነበት አረመኔው አቢይ አሕመድ በዶር ዳኛቸው አሰፋ ምክር በእነ ብርሃኑ ነጋ ግፊት የዐማራ ብልጽግናን አፍርሶ በእነዚህ ወጠጤ የብአዴን የእንግዴ ልጅ በሆኑት በአብኖች መሪነት አዲስ የሽግግር መንግሥት ሊመሠርት መሆኑ ተሰምቷል።
"…ዐማራ ጠሉ ዳግማዊ አለምነህ መኮን የሚባለውና በለሃጫም ስድቡ የሚታወቀውና ኦሮግሬ የሆነው አቶ በለጠ ሞላ፣ የድምጻችን ይሰማ የዐማራ ክልል ወኪል፣ በጎንደር የኦርቶዶክስና እስላም ዐማሮች ግጭት ጠማቂ፣ በእነ መላኩ አለበል ግፊት ሳይመረጥ ባለሥልጣን የሆነው ጣሂር መሀመድ ። በጎንደሬነቱ የወልቃይት መሬት በኮሎኔል ደመቀ ዘውድ የተቸረው፣ ብዙ በማቃጠሩ አሁን የፖስታቤት ተላላኪ የተደረገው ጋሻው መርሻና፣ ጆከሯ ወዳጄ ላሸነፈ የምትጫወተው የሱፌ ዐማራን ይረከቡና ብጥብጡን እናስቁመው መባሉን ነው ወፌ የምትነግረኝ።
"…ልጅየው አብንም፣ አባትየው ብአዴንም ሁላቸውም ተሰደው በአዲስ አበባ በጥገኝነት ተጠግተው ሳለ፣ ክርስቲያን ታደለን ሸቤ አስገብተው እነ በለጠ ሞላ ከጥቂት ብአዴኖች ጋር ተቀላቅለው ክልሉን ይመራሉ መባሉ ያበሳጫቸው አባት ብአዴኖችም በመዋቅራቸው በኩል የዐማራው ፋኖ ይባስ እንዲጠናከር ማዘዛቸውም ተሰምቷል። እንዲያውም ሰሞኑን ተአምር ሳናይ አንቀርም ነው የምትለው ወፌ። ይሄ በደብተራ ምክር በጠንቋይ ትእዛዝ የሚገዛ ዲክታተርም ጥጋቡ ይበርዳል እያሉ ነውም ተብሏል። አቢይን እኮ ነው።
~ ይኸው ነው…!
(ዘመድኩን በቀለ)
ከአማራ ክልል ወቅታዊ ጉዳይ ጋር በተገናኘ አዲስ አበባ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት እነዚህ ብቻ አይደሉም።በየትምህርት ቤቱ በጅምላ የታሰሩት በሺህ ይቆጠራሉ።የጅምላ እስራቱ በወንጀል አድራጎት ሳይሆን ከአማራ ክልል የተሰጠ መታወቂያ በያዘ መሆኑ ተሰምቷል።
Читать полностью…ተዘጋጅታለች…!
"… ET Q400 አውሮፕላን እየተዘጋጀች ነው። የዓለም መንግሥታት ጠንካራው ደጋፊዬ እንደሆነ የሚገምቱት የዐማራ ሕዝብ እንደከዳኝ፣ እንደወጋኝም በስፋት እየዘገቡ ነው። ስለዚህ ወደ ጎንደር ከሄድኩ የሚስቱ አማቾች ጋር ተብዬ ለሌላ ሃሜት እዳረጋለሁ። እናም እኔና ዳንኤል ከተመስገን ጥሩነህ እና ከአበባው ታደሰ ጋር ሆነን ወደ በህርዳር እንሂድ ባለው መሠረት የጎን ኮዷ ET-ARN የሆነች አውሮጵላን ተዘጋጅታለች።
"…ዐማራን ብአዴንን አባርሬ እናንተ ከምትፈልጓቸው፣ ከምትወዷቸው፣ ከምትመርጧቸው ጋር አብሬ ለመሥራት እፈልጋለሁ ብዬ እናንተን ብአዴኖችን አርታኢሌ ካልከተትኳችሁ ምን አለበሉኝ። አሁኑኑ በዐማራ ክልል የሽግግር መንግሥትም አቋቁማለሁ። እንደምንም የዐማራን ቁጣ በልምጭም፣ በካሮትም በቄስም በሼክም ብዬ ማብረድ አለብኝ ነው እያለ ያለው። ሚዲያው ስለ ሰላም ያውራ። ዐማራን የሚሳደቡ ይታቀቡ፣ ይታሠሩ። ፍጠኑ ጊዜ የለንም። የምነግራችሁን እንደ ቀልድ አትዩት። ፍጠኑ።
"…ወዳጄ ዐማራ አይጥመድህ…! አይ ዐማራ በአንድ ሳምንት እንዲህ ወጥ በወጥ ታደርገው?
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለዐማራ ሕዝብ…!
(ዘመድኩን በቀለ)
የመራሹ ብልፅግና አሳዛኝ ዜና❗❗
ትናንት በሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ የለን በምትባል ቀበሌ ለፋኖ መረጃ ትሰጣላችሁ በሚል 10 ንፁሃን ዜጎች ተገድለዋል።
በዚህም አስኬረን ቅጠል አልብሰን ነው የዋልነው ያሉ ሲሆን ዛሬ ስርዓተ ቀብራቸው እየተፈፀመ ነው።
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ምክትል ሊቀመንበር ከኃላፊነታቸውን መልቀቃቸውን አስታወቁ‼️
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ምክትል ሊቀመንበር መልካሙ ሹምዬ በገዛ ፍቃዳቸው ከፓርቲው ምክትል ሊቀመንበርነት እና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቃቸውን አስታወቁ፡፡
ምክትል ሊቀመንበሩ ለፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ በፃፉት ደብዳቤ ኃላፊነታቸውን ለመልቀቃቸው ከአብላጫ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጋር ያላቸው የአቋም ልዩነት እየሰፋ መሄዱ ምክንያት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የጄኔራል ተፈራ ማሞ ባለቤት ወ/ሮ መነን ኃይሌን ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት "ለጥያቄ ትፈለጊያለሽ" በማለት ፌደራል ፓሊሶች እንደወሰዷት ቤተሰቦቿ ለዘሐበሻ ገለፁ።
Читать полностью…አገዛዙ ደስተኛ ነው!
ይህ አገዛዝ የቀረው ከሰራዊቱ ጋር በግልፅ መግጠም ነበር። በአጭሩ በጦርነት የተንከራተተው፣ የተናቀው፣ በተደጋጋሚ የተከዳው ሰራዊትና የሰራዊት አመራር በአገዛዙ ተማርሮ ነበር። ሰራዊቱ ያኔ የተመታው በብልፅግና ችግር ነው። በጦርነቱ ወቅት የተፈፀመበት ደግሞ ተነግሮ አያልቅም። አገዛዙ በቅርቡ ከተማረሰው ሰራዊት መፈንቅለ መንግስት ፈርቶ ነበር። ታዲያ ሰራዊቱ መፈንቅለ መንግስት ካደረገ ደጀኑ የአማራ ህዝብና ኤርትራ ነው የሚል ስጋት ነበረው።
አሁን ከአማራ ህዝብ ጋር አቀያየመው። ዛሬ አማራ መከላከያን የመታ አስመስለው የክልል ብልፅግናዎች ያወጡት የሀሰት መግለጫ በደንብ ለማዳማት፣ ትርክት ለመትከል፣ ከአሁን በኋላ እየተጠራጠረ እንዲቀጥል ስለሚፈልጉ ነው። ሰራዊትና ህዝብ እንዲለያይ ለማድረግ ነው።
ሰራዊት ህዝብ ጋር ከተጣላ የሚጠጋው ከአገዛዙ ነው። ወይንም ህዝብ ይደግፈኛል ብሎ አገዛዙ ላይ አፈሙዝ አያዞርም። አገዛዙ ይህን ወቅት እንደ ስኬት የሚያየው ቀጣዩ መፈንቅለ መንግስት ቀርቶልኛል ብሎ ስለሚያስብ ነው። ይህ በመረጃ የተደገፈ ጉዳይ ነው። የሰራዊቱን መከፋት በደሞዝም በሌላ ጥቅማጥቅምም ማከም አይችልም። ብቸኛው ሰራዊቱን የራሱ ጠባቂ የሚያደርግበት ስልት ከህዝብ ጋር ማቀያየም ነው። በሰሞኑ ችግር ውጤታማ ስራ ሰራሁ ብሎ ያስባል።
ሌላው ይቅር! የተማረኩት የሰራዊቱ አባላት የሚሉትን ስሟቸው። በአገዛዙ ተማርረዋል። አገዛዙ አሁን የሰራዊቱን ትኩረት አስቀይሻለሁ ብሎ ያምናል። ነገር ግን ሁሉም ሲገባው የሚብሰው አገዙዙን ነው። ማንንም አሞኝቶ እስከ መጨረሻው መቀጠል አይችልም።
ሸዋሮቢት‼️
ሸዋሮቢት በፋኖ ቁጥጥር ስር ከገባች ዛሬ አራተኛ ቀኗን ይዛለች። በከተማዋ የባጃጅ እንቅስቃሴ አለ። በአካባቢው የመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች የሉም።
በአዲስ አበባ በርካታ እስር ቤቶች በመሙላታቸው ምክንያት የኮከበ ፅባህ(በቀደሞው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት) መከማቸታቸው የታወቀ ሲሆን
ዛሬ አመሻሹን በአውቶብስ አፍሰው እየጫኑ ወዳልታወቀ ስፍራ ሊያጓጉዟቸው መሆኑ ተሰምቷል።
ሽሬ❗❗❗
1- በጉዳት ተቀንሰው የተሸኙ የሽሬ ወጣቶችን በየቤቱ እየዞሩ ዳግም እያስታጠቋቸው ነው።
2- ከ3 ቀን በፊት(ሀሙስ) ሽሬ ሱር ካምፕ ውስጥ የነበሩትን ታጣቂዎቻቸውን ወደ ተከዜ አስጠግተው አስፍረዋል።
ዜና እስር‼
የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን)በመወከል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የኾኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ ትናንት ምሽት አዲስ አበባ ውስጥ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ ታውቋል።አቶ ክርስቲያን በህ/ተ/ም/ቤት ያለመከሰስ መብታቸው አለመነሳቱ ተሰምቷል።ፖሊስ ለምን እንዳሠራቸው ግን ለጊዜው አልታወቀም ሲል ዘገባ ጠቁሟል።
በተጨማሪም የአዲስ አበባ ም/ቤት አባል ዶ/ር ካሳ ተሻገር እና ድምፃዊ ዳኜ ዋለ መታሰራቸው ተሰምቷል።
አዲስ አበባ❗❗
አዲሱ ገበያ የሚገኘውን የአማራ ባንክ store አሽገው እቃ አናስወጣም መሳሪያ ደብቃችሁ ሊሆን ይችላል በማለት ባንኩ ስራ መስራት አልቻለም።
‹‹ መንግስት በአማራ ክልል እያካሄደ ያለውን ጦርነት ‹ ተራ ሽፍታና ወንበዴ › ለማጥፋት ከሚል የተረት ተረት ስያሜ ወጥቶ ሕዝብን ይቅርታ ይጠይቅ - ለድርድር ይቀመጥ ›› - መኢአድ‼️
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የአዲስ አበባ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ‹‹ መንግስት በአማራ ክልል እያካሄደው ያለውን ጦርነት ‹ ተራ ሽፍታና ወንበዴ › ለማጥፋት ከሚል የተረት ተረት ስያሜ ወጥቶ፣ የጦርነቱን ምንጭ በግልፅ ተረድቶ ሕዝብን ይቅርታ እንዲጠይቅና ዘላቂ ሰላም እንዲያሰፍን ›› ጠይቋል፡፡
መኢአድ ነሐሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣውና ለአሻም በላከላት መግለጫ ‹‹ በአማራ ክልል በተከሰተው ቀውስም ሆነ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ለሚፈጠሩ ችግሮች መፍትሔው የጠብ-መንጃ አፈሙዝ እንደማይሆን አምናለሁ ›› ብሏል፡፡
መግለጫው አክሎም ‹‹ በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ጦርነት ሕዝብን ለከፋ ችግር ከመዳረጉም በላይ ውጥረቱ የበለጠ እየሰፋ ሀገራችንን ልትወጣው ከማትችለው አዘቅት ውስጥ ከመግባቷ በፊት መንግስት ›› ቢወስዳቸው ያላቸውን ‹‹ መፍትሔዎች ›› ዘርዝሯል፡፡
‹‹ ችግርን በችግር መፍታት አይቻልም ›› ያለው መኢአድ በአዲስ አበባና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ‹‹ በፖሊቲካዊ አመላከከታቸው እና በማንነታቸው ምክንያት ብቻ ›› ታሰረዋል ያላቸው ዜጎች እንዲፈቱ ጠይቋል፡፡
መንግስት ‹‹ ታጥቀው ከሚንቀሳቀሱም ሆነ በሰላማዊ መንገድ ከሚታገሉ ፖለቲካ ፓርቲዎችና ሊህቃን ጋር እውነተኛና ግልፅ ውይይት እንዲያደርግም ›› ጥሪ አቅርቧል፡፡
በስልጣን ላይ ባለው መንግስት ብቻ የሚፈታ የሕዝብ ጥያቄ የለም የሚለው መኢአድ ‹‹ ስለሕዝባችን ይገደናል ›› ከሚሉ ወገኖች ጋር ለእውነተኛና ግልፅ ድርድር ‹‹ በአፋጣኝ ›› እንዲቀመጥ ጠይቋል፡፡
‹‹ በአማራ ክልል በጎንደርና ሸዋ ሮቢት ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጪ ሰላማዊ ሰዎች በፀጥታ ሐይሎች ሰለመገደላቸው ተዓማኒነት ያላቸው መረጃዎች ደርሰውኛል ›› - ኢሰመኮ‼️
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ‹‹ በአማራ ክልል፣ ጎንደርና ሸዋሮቢት በርካታ አካባቢዎች ከፍርድ ቤት ትዕዛዘው ውጪ ሰላማዊ ሰዎች በፀጥታ ሀይሎች መገደላቸውን የሚያመላክቱ ተዓማሚነት ያላቸው መረጃዎች ደርሰውኛል ›› ብሏል፡፡
ኮሚሽኑ ይህን ያለው ነሐሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም በአማራ ክልል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ለአሻም በላከላት ባለአራት ገፅ መግለጫ ላይ ነው፡፡
ኢሰመኮ ‹‹ ተፋላሚ ሀይላት ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ግጭቶችን እንዲያቆሙ፣ ለሰላማዊ ንግግር ስፍራ እንዲያመቻቹና ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ›› ጥሪ አቅርቧል፡፡
በአማራ ክልል ያለው ግጭት በሰብዓዊ መብቶች ላይ እያሳደረ ያለውን ተፅዕኖ እየተከታተለ መሆኑን የገለፀው ኮሚሽኑ ‹‹ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከመደንገጉ በፊትና በኋላ ከአዲስ አበባና ከሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መረጃዎች እየተቀበልሁ ነው ›› ብሏል፡፡
በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ‹‹ ከባድ የመድፍ ተኩስ ጭምር ጥቅም ላይ የዋለባቸው ከፍተኛ ውግያዎች እየተካሄደ መሆናቸውን አረጋግጬያለሁ ›› ያለው ኮሚሽኑ ‹‹ በዚህም ሞት ሰላማዊ ሰዎች እና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ›› በመግለጫው አመልክቷል፡፡
መግለጫው ሲቀጥል ‹‹ መንገድ ለመዝጋት የሞከሩ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ጭምር መገደላቸውን ›› ይፋ አድርጓል፡፡ ‹‹እስር ቤቶችና ፖሊስ ጣቢያዎች ተሰብረዋል፤ የጦር መሣሪያዎችና ጥይቶች ተዘርፈዋል፤ ቅድመ ፍርድ ያሉ እና ታራሚዎች አመልጠዋል ›› ሲል አመልክቷል፡፡
የአማራ ክልል መንግስት አመራሮች ‹‹ የጥቃት ዒላማ ›› መሆናቸውንም በዚሁ መግለጫው ጠቁሟል፡፡
‹‹ በተለያዩ አካባቢዎች እንደ ኤሌክትሪክ ሐይል፣ ውሃ፣ ባንክ፣ ሆስፒታል፣ ትምህርት ቤቶች፣ ሰልክ፣ ኢነንተርኔት ያሉ መሠረታዊ አገልገሎቶች መሰተጓገላቸውንም ›› አክሏል፡፡
‹‹ በደብረ ብርሃን ከተማ ለሁለት ቀናት፣ በአራት ብዙ ህዝብ በሚኖርባቸው አካባቢዎች በተካሄደ ከፍተኛ ውግያ በሆስፒታል፣ ቤተ ከርስቲያን፣ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በስራ ቦታዎች ያሉ ሰለማዊ ሰዎች በመድፍና ተኩስ ልውውጥ ተገድለዋል ›› ባይ ነው፡፡
ኢሰመኮ ‹‹ እንደ ደብረብርሃን፣ ፍኖተ ሰላምና ቡሬ ባሉ ከተሞች ‹ የአየር ድበደባዎች › በመፈፀሙ ሰላማዊ ሰዎች፣ በመኖሪያ ቤቶችና ሕዝብ በሚበዛበቸው ስፍራዎች ጉዳት መድረሱን ›› አመልክቷል፡፡
ይህ የኮሚሽኑ መግለጫ ሲቀጥል ‹‹ በባህርዳር ከተማ በርካታ አካባቢዎች ሰላማዊ ሰዎች በየጎዳናውና ከቤታቸው ውጪ ተግደለዋል፤ አንዳንድ ወጣቶችን ደግሞ ለመደብደብና ለመግደል ፍለጋ ሲደረግ እንደነበረ የሚያመላክቱ ተዓማኒ መረጃዎች ደርሰውኛል ›› ሲል ይፋ አድርጓል፡፡
የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቱ በአማራ ክልል ብቻ የተገደበ አለመሆኑን የሚጠቅሰው ኮሚሽኑ ‹‹ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአማራ ተወላጆችን እያሰረ መሆኑን ›› ገልፆል፡፡
በርካታ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ያተተው የኮሚሽኑ መግለጫ አምስት ያህል ምክረ ሀሳቦችን ቢደረጉ ሲል በመግለጫው አስቀምጧል፡፡
ከእነዚህም መካከል ‹‹ የፌደራሉ መንግስት የጅምላ እስሩን እንዲያቆም፣ ክህግ አግባብ ውጪ የታሰሩት ሁሉም እንዲፈቱ፣ ኮሚሽኑን ጨምሮ ሌሎች ተቋማት በየእስር ቤቶቹ ጉብኝት ለማድረግ ያልተገደበ መንገድ እንዲመቻችላቸው ›› የጠየቀበት ይገኝበታል፡፡
‹‹ የመንግስት ባለስጣናትን ጨምሮ ተሰመኒነት ያላቸው ግለሰቦች ሰላማዊ መንገዶችን ከመጠቆም ይልቅ ግጭቱን ከሚያጋግሙ መግለጫዎች እንዲቀቆጠቡ ›› ጥሪ አቅርቧል፡፡
በመጨረሻም በኢትዮጵያ ያሉ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ)፣ የአፍሪካ ህብረት፣ የተባባሩት መንግስታትና ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ግጭቶቹ እንዲቆሙ ድጋፍ እንዲያደርጉ፣ የመነጋገሪያ ስፋራዎችን እንዲያመቻቹ ጠይቋል፡፡
Asham Tv
ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ የአማራ ህዝብ ትግል ይቀጥላል አሉ::፣,
ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ ከሰሞኑ በፀጥታ ሃይሎች የታሰሩትን ባለቤታቸውን ወ/ሮ መነን ሀሃይሌን እስካሁን ለማየት እንዳልተፈቀደላቸው ገልፀዋል።
ጀነራሉ ከአዲስ ድምፅ ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ አያይዘው ያነሱት ሌላኛው ጉዳይ የአማራ ክልሉ ወቅታዊ ሁኔታን ነው።
ጀነራል ተፈራ የብልፅግና አላማ አጠቃላይ የአማራን ህዝብ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ አስፈትቶ በምርኩዝ ማስኬድ ነው ብለዋል።
የአማራ ህዝብ የተከፈተበትን ጥቃት ነው የተከላከሉት ያሉት ብርጋዴር ጀነራሉ የመሳሪያ ብልጫ ስላለውም ንፁሃን ተጎድተዋል ሲሉ ገልፀዋል።
የአማራ ህዝብ መፍትሄ የሚያገኘው በትግል ነው ያሉት ጀነራሉ፣ መመራት ያለበት በራሱ ልጆች ነው ሲሉም ተደምጠዋል።
ጀነራሉ የአማራ ህዝብ ከጫፍ እስከጫፍ ተነቃንቋል ያሉም ሲሆን ዳር ሆኖ በመንጫጫት የሚመጣ ነገር የለም ብለዋል።
"መንግስት የወሰነው ውሳኔ የጎዳው ራሱን ነው፣ የአማራ ልዩ ሃይል ትጥቅ እንዲፈታ ሲወስን አማራ ትጥቅ በትጥቅ ሆኗል" ብለዋል።
ህክምና መከልከላቸው እንደቀጠለ መሆኑን አንስተው የእርሳቸው ችግር ግን የአማራ ህዝብ እየደረሰበት ካለው ችግር እንደማይብስ ገልፀዋል።
ዘገባው የሮሃ ቲቪ ነው❗
የዋሽንግተን ፖስት ዘገባ‼️
ዋሽንግተን ፖስት ፋኖን አሸባሪ የሚያስብለው በፋኖ የተፈፀመ ድርጊት አለማገኘቱን ዘገበ።
ዋሽንግተን ፖስት ወርለድ ኒውስ፣ ጆርዳን ጋዜጣ የህንዱ ቻካር ታይምስ በተመሳሳይ ሰአት ስለፋኖ ይዘውት ባወጡት ዘገባ ላይ ታጣቂዎቹ በውጊያ ስምሪት ላይ ሆነው በነሱ የተደፈረ እንስት፣ የተዘረፈ ሀብት በግፍ የተገደለ ንፁሀን፣ በሙርኮ ላይ ያለ ወታደር እራሱ እንዳላገኙ ነው የዘገቡት።
በተለይ ጆርዳን ጋዜጣ ይዞት በወጣው ሀተታው ፋኖ በሽምቅ ተዋጊነት ራሱን ያጎላበት ባለው ህዝባዊ ወገንተኝነት ነው ብሏል።
ዋሽንግተን ፖስት በበኩሉ ፋኖ አደገኛ የማጥቃት አቅም እንዳለው ዘግቦ ቡድኑ በሰሞኑ ያደረገው ውጊያ የአቅም መፈታተሽን ለማወቅና ያለበትን የመሳሪያ ችግር ለማሟላት እንጅ የጨበጣ ውጊያ አለማድረጉን ነው የዘገው።
ጋዜጣው አክሎም መንግስት ፋኖን ደመሰስኩ ቢልም በመንግስት የተገደለ የፋኖው ቁጥር ለድምሰሳ አይበቃም ብሏል።
በተቃራኒው ፋኖ የገደላቸውና የማረካቸውን የመንግስት ሀይሎች ብዙ መሆናቸውን ነው የዘገበው።
የአውሮፓ ህብረት ልዑክ #በኢትዮጵያን ጨምሮ 19 ሀገራት #በአማራ ክልል ያለው የፀጥታ ሁኔታ አሳስቦናል አሉ ‼️
የአውሮፓ ህብረት ልዑክ በኢትዮጵያን ጨምሮ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ 19 ሀገራት ኤምባሲዎች በአማራ ክልል ያለው የፀጥታ ሁኔታ አሳስቦናል ሲሉ በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታወቁ።
የአውሮፓ ህብረት ልዑክ በኢትዮጵያ እና #የኦስትርያ፣ #የቤልጂየም፣ #የቼክ ሪፐብሊክ፣ #የዴንማርክ፣ #የፈረንሳይ፣ #የጀርመን፣ #የሃንጋሪ፣ #የአየርላንድ፣ #የኢጣሊያ፣ #የሉክሰንበርግ፣ #የማልታ፣ #የኔዘርላንድስ፣ #የሮማንያ፣ #የፖላንድ፣ #የፖርቹጋል፣ #የስሎቬንያ፣ #የስፔን እና #የስዊዲን ኤምባሲዎች ሰሞኑን በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ሁከትና የዜጎች ሞትና አለመረጋጋት አሳስቧቸዋል ብለዋል በጋራ ባወጡት የፕሬስ መግለጫ።
ሁሉም ወገኖች ሲቪሎችን እንዲጠብቁ፣ ጉዳት ለደረሰባቸው ህዝቦች የተሟላ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ቀጣይነት ያለው ሰብአዊ ተደራሽነት እንዲረጋገጥ የጠየቁት ሀገራቱ የውጭ ዜጎች ከግጭቱ አከባቢ ለቀው እንዲወጡ እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንዲተላለፉ እንዲፈቀድ ሲሉ አሳስበዋል።
የሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም በሚቀጥልበት ጊዜ ውስብስበ ጉዳዮችን በሰላማዊ ውይይት ለመፍታት በጋራ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
ግጭቱ ወደሌሎች የሀገሪቱ ክልሎች ተዛምቶ ብጥበጥ እንዳይፈጥር ተገቢው መከላከል እንዲደረግ እናበረታታለን ብለዋል።
አለም አቀፉ ማህበረሰብ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የረዢም ግዜ የመረጋጋት ግብ ድጋፉን እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።
ጎንደር‼️
በጎንደር አዲስ ዘመን ዛሬም በከፍተኛ ሁኔታ በፋኖ እና በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች መካከል ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እንዳለ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።
በአዲስ አበባ ሰሞኑን በርካታ የአማራ ተወላጆች ታስረዋል።
ኮተቤ የሚገኘው ወንዲራድ ትምህርት ቤት እጅግ በርካታ እስረኞች እንዳሉ እና ለመጠየቅም እጅግ አስቸጋሪ ነው ብለዋል።
ትናንት ደግሞ በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ የአማራ ተወላጆች ታስረዋል።
አብዛኞቹ በጉልበት ስራ ላይ የተሰማሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።
የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ዶር ይልቃል ከፋለ ልዩ አማካሪ የነበሩት #አቶ_ደሳለኝ_አስራደ ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸው ተሰምቷል፡፡
=[=====================
ትናንት ሸዋሮቢት ከተማ 3 ንፁሃን መገደላቸው ተሰምቷል።
ንፁሃኑ ከመንግስት የፀጥታ ሀይሎች በተተኮሰ ጥይት እንደተመቱ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
#ሼር_ፖስት! ይህን የምጽፍላችሁ በባሩድ ጭስ ውስጥ ነው። አሁን በዚህ ሰዓት ባህር ዳር በቅርብ ርቀት በምትገኘው
"ጉብሪት" ላይ ሄሊኮፍተር አውርዳቸው የሄደችውን ወታደሮች ፋኖ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል። በተመሳሳይ በኮሎኔል ጌታው መኮነን የሚመራው አያሌው መኮነን የፋኖ ብርጌድ ከ30 በላይ የፌዴራል ፖሊሶችን ከባህርዳር 65 ኪ.ሜ. ቁንዝላ ከተማ አካባቢ ከነመሣሪያቸው ማርኳል። ፋኖ አያሌው ብርጌድ በድል እየገሠገሠ ይገኛል።
-ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ የኦህዴድ ብልፅግና ሠራዊት ባህርዳር ከተማን የጦር አውድማ አድርጓታል። ንፁሐን በየቦታው
ጨፍጭፏል። የተባበሩት አካባቢ መትረየስ ጠምደው ከተማውን እያረሱት ይገኛሉ። ከላይ ከደንባቄ ተራራ ቁልቁል ወደ ከተማዋ ከባባድ የመድፍ ቅምቡላ እየወደቀ ነው።
-ፋኖ የሚችለውን እያደረገ ነው። 50 ዓመት በሙሉ ሲሳደድ፣ ሲፈናቀል፣ በጨቋኝ-ተጨቋኝ ትርክስት ሲከሰስ የኖረውን የዐማራ ህዝብ ፈጽሞ ከመጥፋት ለማዳን ደሙን እያፈሰሰ፤ አጥንቱን እየከሰከሰ ነው። በከፍተኛ የአሸናፊነት ስሜት (Sense of invincibility) ወደፊት እየገሠገሠ ነው። እንደ ፊታውራሪ ገበየሁ ተክሌ "...ስሸሽ ከኋላዬ ከተመታሁ አሞራ ይብላኝ" እያለ መድፉን፣ መትረየሱን፣ ቦንቡን ጥሶት እያለፈ ነው።
"የዘሜ ታናሽ ተላይነህ ወንዱ
በልቡ አስተኛው በየመንገዱ" እያለ በመፎከር ላይ ነው።
-አሁን ባህርዳር ሁለት ችግር ብቻ ናቸው ፈተና የሆኑት። የመጀመሪያው ኦህዴድ ብልፅግና በኮማንድ ፖስቱ ያደራጃቸው የቀበሌ፣ የክፍለ ከተማ፣ የወረዳ፣ የዞንና የክልል ካድሬዎች መረጃ በመስጠት፣ በማሳበቅ ባንዳነታቸውን በሚገባ እያስመሰከሩ ነው። ለነዚህ ካድሬዎች የዐማራ መፈናቀል፣ መሞት፣ መሰደድ ጉዳያቸው አይደለም። ዛሬ ታማኝነታቸው አረጋግጠው ነገ የሥልጣን እድገት እናገኛለን ብለው በተስፋ የሚኖሩ ከንቱዎች ናቸው።
ሁለተኛው በአሁኑ ሰዓት ለከተማው ህዝብ ፈተና የሆኑት ስግብግብ ነጋዴዎች ናቸው። በእያንዳንዱ የምግብ አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ዋጋ በመጨመር ከአገዛዙ ባልተናነሰ ሁኔታ ህዝቡን እያስመረሩ ስለሆነ ሊያርፉ ይገባል። ሲሆን ይህን ችግር በጋራ ለመሻገር ቢተባበሩ ጥሩ ነበር፤ አለበለዚያ ግን በምግብ አቅርቦቶች ላይ ከፍተኛ ዋጋ መጨመር አገዛዙን እንደማገዝ ይቆጠራል። ዛሬ ከጥዋቱ ጀምሮ በውሸት ውሃ ተበክሏል ብለው ያስቀመጡትን ምርታቸውን ሲሸጡ አርፍደዋል። ከዚህ በላይ ነውር፣ ለህዝብ ደንታቢስነትና ስግብግብነት የለም። መቆም አለበት።
የድል ዜናዎች ተዘርዝረው አያልቁም። ባጭሩ ግን ሁሉም አስፈላጊውን ድጋፍ ያድርግ። ብልፅግና ያሰማራቸው ሌቦች የፋኖን ስም ለማጠልሸት ስለተሰማሩ ሁሉም አካባቢውን ነቅቶ ይጠብቅ። በየአካባቢው ይደራጅ። ይህን ፀረ-ዐማራ፣ ፀረ-ኢትዮጵያዊ፣ ፀረ-ሃይማኖት፣ ፀረ-ሥልጣኔ፣ ፀረ-ሰው አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ግብአተ መሬቱን ለመፈጸም ሁሉም ሚናውን መወጣት አለበት።
ድል ለዐማራ ህዝብ!
ድል ለኢትዮጵያ!
Tadeletibebu
"ጦርነት መፍትኄ አይኾንም፤ ከትናንት እንማር፤ ችግሮችን በውይይት እንፍታ!"
ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ።
ሸዋ❗❗
የሰሜን ሸዋ ዞን የመራቤቴ ወረዳ ሚሊሻ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ከትናንት በስተያ ሚሊሻዎችን ሰብስቦ ጉዳዩ ከአቅም በላይ በመሆኑ ሚሊሻዎች ወደ ቀያቸው በመመለስ የእርሻ ስራቸውን እንዲያከናውኑ እና ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ማድረጉን የአዩዘሀበሻ ምንጮች ገልጸዋል።
የከተማዋ አመራሮችም ወደ ደብረብርሃን እና አዲስ አበባ እንደሄዱ ተገልጿል።