ደቡብ ወሎ‼️
በደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ከትናንት ምሽት 2:00 አካባቢ ጀምሮ ከፍተኛ ውጊያ እንዳለ ከነዋሪዎቹ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
ወደ ከተማዋ ፋኖ እንደገባ ገልፀው መከላከያ ሰራዊት ደግሞ ወደ ህዝቡ ከባድ መሳሪያ እየተኮሰ ነው ብለዋል።
ደቡብ ወሎ‼️
በደቡብ ወሎ ዞን ውጫሌ ከተማ ከትናንት በስተያ ለሊት በፖሊስ ጣቢያው ላይ ድንገተኛ ጥቃት ተከፍቶ በወቅቱ በፖሊስ ጣቢያው ውስጥ በነበሩ የፖሊስ አባላት ላይ ሰብዓዊ ጉዳት ደርሷል።
እስረኞችን አስመልጠው ብዛት ያለው መሳሪያም ወስደዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በአምባሰል ወረዳ ልዩ ስሙ ድንብል መድሃኒዓለም በሚባል አካባቢ በአካባቢው ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የደፈጣ ጥቃት ተፈፅሞ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።
መራኛ‼️
በሰሜን ሸዋ ዞን መራቤቴ ከተማ የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ አድርጎ በተቀመጠባቸው አራት ቦታዎች ላይ ድንገተኛ ጥቃት ተፈፅሞ በርካታ ጉዳት ደርሷል።
ብዛት ያለው መሣሪያ ከነ ተተኳሹ ተማርኳል።
የፋኖ ተዋጊዎችም ይሄን ጥቃት ከፈፀሙ በኋላ ከከተማዋ ተሰውረዋል ተብሏል።
ጎንደር‼️
ማክሰኚት ሰሞኑን የነበረው ውጊያ ቆሞ የነበረ ቢሆንም ዛሬ ጠዋት 11:00 ገደማ ጀምሮ ውጊያ እየተደረገ ነው።
በዚህ ውጊያ የፋኖ ተዋጊዎች በፖሊስ ጣቢያው ላይ ጉዳት አድርሰዋል፣ ብዛት ያለው መሳሪያም ወስደዋል ብለዋል። ደንቢያ ደረሴ አካባቢም ተኩስ አለ።
ጎንደር‼️
በሰሜን ጎንደር አርባያ በለሳ ከወረዳዉ ወጣ ብሎ ወራሃላ ገብርኤል በመከላከያ ምሽግ እየተቆፈረ ማየታቸውን የአይን እማኞች ገልፀውልናል።
በዚህ የተነሳ ውጊያ ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል ነዋሪዎቹ ስጋት ገብቶናል ብለዋል።
ደቡብ ወሎ‼️
በደቡብ ወሎ ለጋምቦ ወረዳ ከመካነሰላም ወደ ጊምባ በመኪና ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ትናንት የደፈጣ ጥቃት ተፈፅሞ እጅግ ከፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት ደርሷል ብለዋል።
አምቡላንሶች በተደጋጋሚ ሲመላለሱም ተመልክተናል ብለዋል።
አዲስ አበባ‼️
ከመጪው የመስቀል በዓል ጋር ተያይዞ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቲሸርት ታሳትማላችሁ፣ግጭት ቀስቃሽ ፅሁፎችን ታዘጋጃላችሁ በሚል ህትመት ቤቶች ከፍተኛ ቁጥጥር እየደረገባቸው መሆኑን ከህትመት ቤት ሃላፊዎች የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።
ሽሮሜዳ አካባቢ አንድ በህትመት ስራ ላይ የተሰማሩ የህትመት ባለሙያ እንደገለፁልን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ያለው ቲሸርት በህትመት ቤቴ በመገኘቱ አሽግተውታል ብሏል።
update
ጎንደር ‼️
3ተኛ እና 6ተኛ ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ ከፍተኛ ውጊያ ከተደረገ በኋላ በፋኖ ተሰብሮ እስረኞች እንዲለቀቁ አድርገዋል ተብሏል፣መጋዘናቸው ተሰብሮ መሳሪያ ተወስዷል። በተለይ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ከፍተኛ ውጊያ ነበር ብለዋል።
መከላከያ ሰራዊት ቀራኒዮ መድሃኒዓለም አካባቢ ሆኖ ከባድ መሳሪያ እየተኮሰ ነው ብለዋል። ከተማዋ አብዛኛው በፋኖ አባላት ቁጥጥር ስር ናት ብለዋል። የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ የለም ሲሉ ከጎንደር ነዋሪዎች በስልክ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል። ህዝቡ ከቤት አልወጣም፣ድባቡ በጣም አሳዛኝ ነው ብለዋል።
ፋኖ ከከተማዋ ለመውጣት እንቅስቃሴም ጀምሯል ብለዋል በርካታ ሃላፊዎች በፋኖ ተገድለዋል ብለዋል፣ፓትሮል ሲያደርጉ የነበሩ አራት ፒካፕ መኪኖች ተቃጥለዋል።
update!
ጎንደር‼️
ዛሬ ለንጋት አጥቢያ ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ፋኖ ወደ ጎንደር ድጋሚ እየገባ ስለመሆኑ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።
ንጋት ላይ አይባ እና ደንቀዝ በተባሉ ከፍተኛ ቦታዎች ላይ ተኩስ እንደነበር ገልፀው በዚህም ፋኖ በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ሸዋ ዳቦ 3 ኛ ፓሊስ ጣቢያ፣ቀበሌ 16፣ቀበሌ 17 እና ማራኪ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የፋኖ አባላት መታየታቸውን ገልፀውልናል።
ማራኪ በሚባለው ሰፈር ሚሊሻዎችን ሲመራ የነበረ አባል ተገድሏል ተብሏል።
አሁን በዚህ ሰዓት በከተማዋ ከፍተኛ ተኩስ አለ ሲሉ የጎንደር ነዋሪዎች ገልፀዋል።
<< በመስቀል አደባባይ በሚከበረው የደመራ በዓል ፈተና ሊገጥም ይችላል >> - ቤተ ክርስቲያኗ‼️
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን << በመስቀል አደባባይ በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል የሚፈትኑ ጉዳዮች ሊገጥሙ እንደሚችሉ >> ተናግራለች።
የቤተ ክርስቲያኗ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ አቡነ አብርሃም << በበዓሉ ላይ የሚፈትኑ ጉዳዮች ሊገጥሙን ስለሚችሉ በትዕግስት ማለፍ አለብን >> ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ምንም እንኳን አቡነ አብርሃም < ፈተናዎች ሊገጥሙ እንደሚችሉ > ቢገልፁም በውል ፈተናዎች ምን እንደሆኑ፣ ከየትኛው አካል ፈተናው ሊመጣ እንደሚችል መረጃውን ባሰራጨው የቤተ ክርስቲያኒቱ ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ የተገለፀ ነገር የለም።
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ስራ አስኪያጁ በደመራ ወቅቱ የሚከናወኑ ተግባራትን የዘረዘረው ዘገባው ሰዓትን ማክበር ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጠው ማሳሰባቸውን አመልክቷል።
ሌላኛው ማሳሰቢያቸው << ሰንደቅ ዓላማን በተመለከተ ከፌዴራል እና ቤተ ክርስቲያን አርማ ያለበት ብቻ >> ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚገባ የተናገሩበት ነው።
አብነ አብርሃም የበዓሉ ዕለት አለባበስን በተመለከተ ባስተላለፉት መልዕክታቸው << ተንኳሽ መልዕክት መጠቀም አይገባም >> ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
በሌላ በኩል መንግስት በደመራ ዕለት << የተከተከሉ >> ሲል የጠራቸውን ተግባራት በዝርዝር ይፋ ማድረጉን ለመንግስት ቅርበት ያላቸው መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
በዚህም << ከተፈቀደላቸው 10 ሺሕ የሰንበት ተማሪዎች ማደራጃ መምሪያ ከታቀፉ ወጣቶች ውጭ እንደማንኛውም ምዕመናን መምጣት እንጂ የደንብ ልብስ ለብሶ ከበሮ እና ፅናፅል ይዞ ወደ መስቀል አደባባይ መምጣት አይቻልም >> የሚለው በመንግስት በኩል ከተከለከሉት ተግባራት መካከል ይገኝበታል።
ምንም እንኳን የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ይህን ቢልም ከቤተ ክርስቲያኗ በኩል ምን ያህል የሰንበት ተማሪዎች እንደሚሳተፉ ቀደም ሲል ዋቢ ከተደረገው የቤተ ክርስቲያኗ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዝርዝር መረጃ አልተጠቀሰም።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር << በበዓሉ ላይ የሚገኝ ሁሉም ሰው እንደሚፈተሽ >> ይፋ አድርጓል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በታችኞቹ የመንግስት መዋቅር በተለይም በወረዳ ደረጃ የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች መጪዎቹ << የመስቀል ደመራ እና ኢሬቻ >> በዓላት በሰላም ተከብረው ስለሚውሉበት ሁኔታ ምክክር መደረጉን አሻም ለማወቅ ችላለች።
አንድ ስማቸው ለደህንነታቸው ሲባል እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ የውይይት ተሳታፊ ለአሻም የመድረኩን ይዘት አጋርተዋታል።
እኚህ የመረጃ ምንጭ እርሳቸው በተሳተፉበት ውይይት << ስለአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን ስለመላው ኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ውይይት እንዲደረግ >> በርካታ ታዳሚያን ጥያቄ ቢያቀርቡም ከአወያዮቹ በኩል አወንታዊ ምላሽ እንዳላገኙ ገልፀዋል።
በኢትዮጵያ እየተፈፀመ ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ካናዳ ገለፀች።
በተለይም ደግሞ ከተደረሰው የሰላም ስምምነት ብኋላም ቢሆን የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች እየቀጠሉ መሆናቸውን ሁኔታው የበለጠ አሳሳቢ እንዳደረገው የካናዳ መንግስት ስጋቱ ገልፃል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አለም አቀፉ የሰብኣዊ መብት ጥሰት የባለሙያዎች አጣሪ ኮሚሽን በኢትዮጵያ ያወጣው ሪፓርት እየተፈፀሙ ያሉት ወንጀሎች የሚያሳይ መሆኑንም ካናዳ አስታውቃለች።
የተፈፀሙ እና እየተፈፀሙ ያሉት ወንጀሎች በገለልተኛ አካል ተጣርተው ተጠያቂነት ማረጋገጥ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ሚናው የጎላ መሆኑን የገለፀችው ካናዳ ተጠያቂነት በማረጋገጥ ረገድ ትኹረት ተስጥቶት ሊሰራበት እንደሚገባ አሳስባለች።
አብን የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ የሚፈጽሟቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች "በገለልተኛ አካል እንዲመረመሩ" ጠይቋል። አብን፣ ባስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሽፋን "አንድን ሕዝብ በማንነቱ ምክንያት ላልተገባ እንግልትና ሞት" የዳረጉ የመንግሥት አመራሮችና የጸጥታ አካላት በሕግ እንዲጠየቁም አሳስቧል። ጸጥታ ኃይሎች "አካላዊ ድብደባ"፣ "ውድ ንብረቶችን መቀማት"፣ "ማንገላታትና የማዋከብ ድርጊቶች" በስፋት እየፈጸሙ እንደኾነና በአዲስ አበባ ዙሪያ "ጅምር የፋብሪካ መጋዘኖች" የታሳሪዎች ማጎሪያ መኾናቸውን አብን ገልጧል። አብን፣ በብሄራቸው ብቻ ተመርጠው የታሠሩ፣ በግል ቂም፣ በፖለቲካ ልዩነትና ለጥቅም ማስፈጸሚያነት ሲባል በየቦታው የታሠሩ ዜጎች ጉዳያቸው ተመርምሮ በፍጥነት መለቅቅ አለባቸው ብሏል። በበሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አውራ ጎዳና ቀበሌ የፌደራሉና የአማራ ክልል መንግሥት የሕዝቡን ደኅንነትና ንብረት የመጠበቅ ሃላፊነታቸውን ባለመወጣት ለደረሰው ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት ተጠያቂነት እንዲሰፍንም ፓርቲው ጠይቋል።
Читать полностью…ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ
ጸሎተኛው፣ደጉ፣ርህሩሁና ታጋሹ አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ሰላማ ዛሬ መስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።ብፁዕ አባታችን ባደረባቸው ህመም ምክንያት በአዲስ አበባ ሀሌሉያ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንዳሉ ነው ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት።
የብፁዕነታቸው የሽኝት መርሐ ግብር በቋሚ ሲኖዶስ ሲወሰን ይፋ ይደረጋል ተብሏል።(EOTC)
ማክሰኚት‼️
በማክሰኚት ከፖሊስ ጣቢያው ጥቃት በተጨማሪ ሙያ እና ቴክኒክ ኮሌጅ አካባቢ በነበረ የመከላከያ ካምፕ ላይ በ ፋኖ ተዋጊዎች ድንገተኛ ጥቃት ተፈፅሞ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።
አምባሰል‼️
በደ/ ወሎ ዞን ውጫሌ ከተማ የሚገኘው የአምባሰል ወረዳ ፖሊሲ ፅ/ቤት ትናንት ጠዋት ጥቃት ተፈፆሞበታል።
በፖሊስ አባላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው መሳሪያ መጋዘን ተሰብሮ ተወስዷል።
ኬንያና አሜሪካ ትናንት ናይሮቢ ውስጥ ለአምስት ዓመታት የሚቆይ የመከላከያ ትብብር ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ ኢቢሲ ያስነበበን ዜና ⬇️
ይህን ልብ እንበል: ምዕራባውያን ሀገራት የተለያዩ ቀጠናዎች ላይ እንደ ዋና አጋር የሚቆጥሯቸው ሀገራት አሉ፣ ለምሳሌ በፊት በፊት በአፍሪካ ቀንድ ኢትዮጵያ ተመራጭ አጋር ነበረች፣ አሁን ቦታውን ኬንያ ተረክባለች።
በራሱ አለም ተለይቶ የሚኖር ሀገር የለም፣ ሰሜን ኮርያ እንኳን እንደ ቻይና እና ሩስያ ያሉ አጋር ሀገራት አሏት። ስለዚህ የሀገርን ጥቅም ባስጠበቀ እና ባስቀደመ መልኩ የሚከናወኑ ጂኦ-ፖለቲካዊ ስራዎች ትኩረት ይሻሉ።
ለምሳሌ ኬንያ በአዲሱ የአሜሪካ የአጋርነት ስምምነት በመከላከያ ቴክኖሎጂ፣ በጸረ-ሽብር፣ በጸረ-ጽንፈኝነት፣ በጋራ ወታደራዊ ልምምድና በባሕር ላይ ደኅንነት መስኮች በቢልዮን ዶላሮች የሚቆጠር የገንዘብ እና የመከላከያ ቁስ ድጋፍ እንደምታገኝ ይጠበቃል።
ወደእኛ ስንመጣ በቅርቡ እንኳን የሱዳኑ መሪ ለሀገሪቱ ጦርነት እልባት ፍለጋ ኤርትራን እና ኬንያን ጨምሮ 10 ሀገራት ሲሄዱ ወደ ኢትዮጵያ አልመጡም፣ በተመድ ጠቅላላ ስብሰባ ላይም በመሪ ደረጃ አልተካፈልንም፣ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ኬንያ አቅንተው ኢትዮጵያን ዘለዋል።
አማራ‼️
አማራ ሰይፍ ከመምዘዙ በፊት በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቆ ምላሽ አጥቷል። ስለጠየቀ ተቀልዶበታልም!
ገዥዎቹ በመግለጫዎቻቸው "በሰላማዊ መንገድ መጠየቅ እየተቻለ" የሚል ቀልድ ሁሉ እየጨመሩ ሲያፌዙ ነበር።
አማራው ጥያቄዎቹን ፍፁም በሰላማዊ መንገድ በተደጋጋሚ አቅርቧል።
"ይህ የመጨረሻ ሰልፋችን ነው" ብሎ አስጠንቅቋል።
ከእነዚህ ሰልፎች በኋላ አንዳንድ ቦታ ሰልፍ ሲወጣ እንኳን ቀልደውበት ነበር።
"የመጨረሻ ሰልፋችን ነው አላላችሁም?" እያሉ ሊያፌዙበት ጥረዋል።
ሰልፍ ሲወጣ ቀለዱበት፣ ሰይፍ ሲመዝ "በሰላማዊ" ወዘተ እያሉ እየለመኑ ነው።
በጎንደር ማክሰኚት ዙሪያ ልዩ ስሙ መገጭ በሚባለው አካባቢ ትናንት በነበረው ውጊያ ከፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት ደርሷል።
ጭንጫዬ በሚባለው አካባቢ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል ብለዋል።
የቀበሌዋ አመራሮችን አላገዛችሁንም በሚል ተገድለዋል ተብሏል።
ቆላድባ ዛሬም የቀጠለ ውጊያ አለ። በሚሊሻ ፅህፈቱ ላይ ጥቃት ተከፍቶ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።
በዚህ የተነሳ ከጎንደር ወደ ደቡብ ጎንደር የሚያስመጣው መንገድ ዝግ ነው።
ሁለት ዜናዎች
1፤
የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ትናንት ባካሄደው ስብሰባ የክልሉ ወቅታዊ ኹኔታ በአስተዳደራዊ "ውስጣዊ ድክመት" ሳቢያ አሽቆልቁሏል ብሏል። ማዕከላዊ ኮሚቴው የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ አለመኾኑን ገልጦ፣ የትግራይ ሕዝብ የሕልውና አደጋ ተጋርጦበት እንደሚገኝም ገልጧል። ማዕከላዊ ኮሚቴው፣ በፕሪቶሪያው ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በቅርበት ስለመስራትና ተጨማሪ ፖለቲካዊ ውይይት በማድረግ አስፈላጊነት ዙሪያ ውይይት ማድረጉንም ጠቅሷል። በሰላማዊ ትግል፣ በፓርቲው ውስጣዊ ድክመትና በቀጣይ የፓርቲውና የጊዜያዊ አስተዳደሩ ቀጣይ ፕሮግራሞች ላይ ጭምር መወያየቱን ፓርቲው አመልክቷል።
2፤
ዕሁድ'ለት በጎንደር ከተማ በመንግሥት ወታደሮችና በፋኖ ሚሊሻዎች መካከል በተደረገ ውጊያ ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች እንደተገደሉ ወይም እንደቆሰሉ የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ነዋሪዎች ቆስለው ሆስፒታል የገቡ ሰዎችን ወታደሮች ወዳልታወቀ ሥፍራ እንደወሰዷቸው መናገራቸውን የዘገበው ደሞ ቢቢሲ አማርኛ ነው። የፋኖ ታጣቂዎች ከከተማዋ ኹለት ፖሊስ ጣቢያዎች አባሎቻቸውን ጨምሮ "በመቶዎች የሚቆጠሩ" እስረኞችን አስፈትተናል ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል። በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት ትናንት እንደተቋረጠ መኾኑንና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ዝግ መኾናቸውን ዘገባው ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
ዋዜማ
ጎንደር‼️
ፋኖ ከጠዋቱ ጦርነት በኋላ ከተማዋን ለቆ ወጥቷል። ከሰዓት በኋላ ብዙም ተኩስ የለም።
በከተማዋ በርካታ አካባቢዎች መከላከያ ገብቷል።
ይህ ቢሆንሜ አሁንም ከፍተኛ ውጥረጥ አለ ብለዋል።
ጎንደር‼️
ጎንደር ከንጋት ጀምሮ እንቅስቃሴ ቆሟል ማለት ይቻላል። የከባድ መሳሪያ ድምፅ እየተሰማ ይገኛል ብለዋል። ያልተነሳ የፀጥታ ሀይሎች አስኬረን ተመልክተናል ብለዋል። አንድ የፓትሮል መኪና ተቃጥሏል።
ዛሬ አመሻሹን በሸገር ሲቲ 44 ማዞሪያ በርካታ ወጣቶች በጅምላ ታፍሰው መወሰዳቸውን የአይን እማኞች ገልፀውልናል።
በዚህ የተነሳ ከተማው ጭር ብሏል።
በአሸባሪው ሸኔ የተገደለውን ልጃቸውን እናትየውም ተከትለውት ሄዱ ፤ ስቃያቸው አበቃ ። አረፉ
*********************************
የዛሬ 3 ወር ገደማ ሶደሬ አካባቢ በሸኔ አባላት ታግቶ የተገደለው ሠዓሊ ሙሉጌታ ገ/ኪዳን እናት በመረረ ሀዘን ሲሰቃዩ ኖረው ትናንት አረፉ ። የቀብር ስነስርዓታቸው ዛሬ ከ5:00 - 6:00 ሰዓት ካራ ቆሬ መድሀኒዓለም ይፈጸማል ። በሠዓሊው ጓደኞች " አደዬ " እየተባሉ የሚጠሩት እናት ጓደኞቹን ባገኙ ቁጥር በእንባ እየታጠቡ " እኔስ መቼ ነው ልጄን የምከተለው ? ጥራኝ ልጄ " ሲሉ ይሰማሉ ። ሊጠይቋቸው የሚሄዱ ጓደኞቹ በሙሉ እስቸውን ማየት ሲያሳቅቃቸው ኖሯል ።
እናታችን ነፍስዎን ይማርልን ። አምላክ መላው ቤተሰቡን ያጽናናልን ።
20 የአሜሪካ ሴናተሮች ብልፅግና አገዛዝ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ተስማምተዋል።
በኦሮሚያ ክልል የተወረረው የሶማሊ ክልል ኃይሉን አስጠግቷል።
መከላከያ ኦነግ ሸኔ የኦሮሚያን ልዩ ኃይል በገፍ ሲማርክ እንደነበር አምኗል።