የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት “የህዝባዊ ቁጣ መገንፈል እና ተዛማጅ ጉዳዮችን” ሊያስከትል እንደሚችል ኢህአፓ አስጠነቀቀ‼️
በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ ያለው እና ወደ ሁለተኛ ምዕራፍ የተሸጋገረው የኮሪደር ልማት፤ የከተማይቱን ነዋሪዎች “ሰብአዊ መብቶች የጣሰ ነው” ሲል የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) ዛሬ በሰጠው መግለጫ ወቀሰ። በኮሪደር ልማቱ ሳቢያ“እያየለ የመጣው የህዝብ ብሶት እና ምሬት” በቸልታ ከታለፈ፤ “የህዝባዊ ቁጣ መገንፈል እና ተዛማጅ ጉዳዮችን” ሊያስከትል እንደሚችልም ፓርቲው አስጠንቅቋል።
አዲስ አበባ “ዓለም አቀፍ ደረጃዋን ጠብቃ የመልማቷ ጉዳይ ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ” እንዳልሆነ በዛሬው መግለጫ የጠቀሰው ፓርቲው፤ ይሁን እንጂ የከተማዋ ልማት እና እድገት “ከኗሪው ህዝብ መብት መከበር” እና “ከጥቅሞቹ መጠበቅ” ተነጥሎ ሊታይ እንደማይገባ አሳስቧል። ልማቱ “ከዜጎች አጠቃላይ የኑሮ መስተጋብር እና የኢኮኖሚ እድገት ጋር የተጣጣመ” መሆን እንደሚኖርበትም ፓርቲው በአጽንኦት አንስቷል።
የዛሬውን መግለጫ የሰጡት የኢህአፓ የአዲስ አበባ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አበበ አካሉ፤ በከተማይቱ እየተካሄደ ባለው የኮሪደር ልማት “የበርካታ ነዋሪዎች መኖሪያ ቤቶች፣ አነስተኛ እና ከፍተኛ የንግድ ድርጅቶች” መፍረሳቸውን ገልጸዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየወሰዳቸው ያላቸው እርምጃዎች “የነዋሪዎች ሁኔታ ያላገነዘቡ፣ ምቹ ጊዜን ያልጠበቁ እና ከግምት ያላስገቡ” መሆናቸውንም አመልክተዋል።
((እኛም ህዝባዊ አመፁ የማይቀር ነው እንላለን))
#መረጃ‼️
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከጨፍጫፊው ስርዓት ጋር በፕሬዚዳንትነት እንደማይቀጥሉ ታውቋል።
ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ለበርካታ ወራት በስራ ድርሻቸው ዙርያ በሚፈፀሙ አንዳንድ ድርጊቶች እና ከስራ አስፈፃሚው አካል ጋር ባላቸው ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት ደስተኛ እንዳልነበሩ ተሰምቷል።
የፕሬዝዳንቷ የስልጣን ዘመን በዚህ መስከረም ወር መጨረሻ ይጠናቀቃል።
ፕሬዝዳንቷ ዛሬ በx አካውንታቸው
"ዝምታን ለአንድ አመት ሞከርኩት" በሚል አነጋጋሪ ፅሁፍ ማሰራጨታቸው ይታወሳል።
=============
ሰበር ዜና!
“አገዛዙ ‘ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው’ አይነት ስትራቴጂ እየተከለ ነው፣ እኛ ደግሞ ጠላትን እየደመሰስነው ነው”ዋርካው ምሬ ወዳጆ
የአማራ ፋኖ በወሎ ዋና አዛዥ ዋርካው ምሬ ወዳጁ በወቅታዊ ጉዳይ ከኢትዮ 251 ሚዲያ ጋር ልዩ ቆይታ አድርጓል።
በቆይታውም በዛሬው ዕለት መስከረም 23 ቀን 2017 ዓ.ም. የአማራ ፋኖ በወሎ፣ የአማራ ፋኖ በጎጃም፣ የአማራ ፋኖ በጎንደር እና የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ በምንቀሳቀስባቸው ቀጠናዎች የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ያስቆምን ሲሆን እኛ በምንቀስቀስባቸው ሰሜን ወሎ ሙሉ በሙሉና ደቡብ ወሊ ቀጠና በከፊል የተዘጋ ሲሆን የኛ ክፍለጦሮችም በዋግኽምራና በላስታ የላስታ አሳምነው ኮር፣ በሰሜን ወሎ ራያና ሌሎች ቀጠናዎች ስድስት ክፍለጦሮች፣ በደቡብ ወሎ ደግሞ የአማራ ሳይንትበመቅደላ ክፍለጦርና ንጉስ ሚካኤል ክፍለጦሮች ሌሎች አደረጃጀቶቻን በጋራ ቅንጅት የጠላትን ኃይል ድባቅ እየመታነው ነው ሲል ገልጿል።
በዚህ ድባቅ የተመታው የጠላት ኃይል “ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው” የሚል ስትራቴጂ እየተከተለ ቢሆንም ያቀደው ሳይሳካለት ቀርቶ የራሱን የብልጽግና ኃይሎች ወደ ማሰር መግባቱን ተመልክተናል፣ በዚህ አጃምሎም ወጣቶችን፣ ሀኪሞችን፣ መምህራንን እና የሐይማኖት አባቶቹን ወደ ማሰር መግባቱንም እያየነው ሲል ገልጿል።
በተለይ በከተማ ውስጥ ሆናችሁ እየታሰራችሁ ያላችሁ አካላት መዳኛችን ፋኖነት መሆኑን አውቃችሁ በሙሉ አቅማችሁ ወደ ፋኖ ትግል እንድትገቡ ስል በአክብሮት ጥሪ አቀርባለሁ ሲል የአማራ ፋኖ በወሎ ዋና አዛዥ ዋርካው ምሬ ወዳጆ ገልጿል።
በመጨረሻም እያደረግን ያለነው ከፍተኛ ትንቅንቅ ነው የአማራ ሕዝብ በዚህ ታሪካዊ ተጋድሎ እንዲሳተፍ ማስታወስ እፈልጋለሁ ብሏል።
አስፈሪው ጦርነት ተጀመረ
ኢራን ከ180 በላይ ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል ተኮሰች‼️
ኢራን የአየር ክልሏን ሙሉ በሙሉ ዘግታለች።
ጥቃቱ የአየር ማረፊያዎች እና የጦር ሰፈሮችን ኢላማ ያደረገ ሲሆን
ቴል አቪቭ፣ አሽዶድ፣ ሃይፋ፣ ቤርሳቤህ፣ ምዕራብ እየሩሳሌም እና የጋዛ ሰርጥን ጨምሮ በሁሉም የእስራኤል ከተሞች የቅድመ ጥንቃቄ የደውል ድምጽ ተሰምቷል። ኢራን የሚሳኤል ጥቃቷን ካጠናቀቀች በኋላ አሁን ላይ የአየር ክልሏን ዘግታለች‼️
ኢራን ሁሉንም የሲቪል በረራዎች በማቆም ቴህራን የሚገኘውን የኢማም ኩሜኒ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን በመዝጋት የእስራኤልን አፀፋ በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤንጃሚን ኔታናያሁ ኢራን ወደ እስራኤል ከተኮሰች የእጇን ታገኛለች ሲሉ ትናንት መናገራቸው ይታወሳል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በበኩላቸው ኢራን በእስራኤል ላይ ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ እስራኤል እራሷን እንድትከላከል አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን ሲሉ ከደቂቃዎች በፊት በ X ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።
በተያያዘ ዜና የኢራቅ ታጣቂ ቡድን ዋሽንግተን ኢራንን ለማጥቃት ከእስራኤል ጋር ከተባበረች ኢራቅ በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ ኢላማ አደርጋለሁ ብሏል።
ቀጣይ ምን ይከሰት ይሆን❓
አብረን የምናየው ይሆናል)
=============
ለፋኖ አመራሮች ሰሞኑን የተዘጋጀውን ወጥመድ በጥንቃቄ እለፉት!
የሶማሊያ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን ቡድኖች አግዛለሁ የሚል ፕሮፖጋንዳ አሰራጭቶ ብልፅግና ደንበኛ ወጥመድ አድርጎታል። ሰሞኑን በርካታ ሚዲያዎች ወደ ፋኖ አመራሮች እንዲደውሉ ይደረጋሉ። የፋኖ አመራሮች ይህን ወጥመድ በጣም በጥንቃቄ ማለፍ አለባቸው።
1) በጣም ጠቃሚው አማራጭ ፋኖ በጉዳዩ ምንም መልስ ባይሰጥ ነው። አስፈላጊ አይደለም። የፋኖ ትኩረት ህዝቤን ነፃ ማውጣት ላይ ነው የሚል መሆን አለበት። የአማራ ህዝብ በርካታ ችግሮች ውስጥ በመሆኑ መፍታት ያለብን የራሳችን ጉዳይ አለ። ጊዜም ትኩረታችንም ለራሳችን አላማ ነው ማለት ያስፈልጋል።
2) ፋኖ እርዳታም፣ ድጋፍ ወዘተ የሚያገኘው ከህዝብ ነው። ስንቄና መጠለያዬ ህዝቤ፣ ትጥቅ የማገኘው ሰተት ብሎ ከመጣ ጠላት ነው ማለት በቂ ነው። ለድጋፍ ህዝብ፣ ለትጥቅ ጠላት በቂ ነው። አራት ነጥብ!
ማንም ተነስቶ አግዛለሁ ሊል ይችላል። ከእነ ሽመልስ አብዲሳ ጋር የተኮራረፈ የብልፅግና ቡድን "ፋኖን አግዛለሁ" ቢል "አዎ ያግዘኝ" አይባልም። ማንም አግዛለሁ፣ አላግዝም ስላለ፣ መግለጫ ስለሰጠ ብቻ ፋኖ መልስ መስጠት የለበትም። ጫካ ያሉ አመራሮች ስለ ጉዳዩ ላይሰሙ ስለሚችሉም "አልሰማሁም" ማለት ጤነኛ መልስ ነች። ጫካ ውስጥ ያለ ኃይል የሶማሊያን ጉዳይ የግድ መስማት የለበትም። "አልሰማሁም" ምክንያታዊ መልስ ነው!
3) የግድ ከሆነ በገደምዳሜው ማለፍን መልመድ ያስፈልጋል። የሉአላዊነትም ሆነ ሌላ ጉዳይ ስልጣን ሲያዝ የሚፈታ ጉዳይ ነው። ከውጭ ኃይሎች ጋር ያለ ግንኙነት ስልጣን ስንይዝ የምንፈታው እንጅ አሁን ባለንበት ሁኔታ የሚቻል አይደለም የሚል መልስ በቂ ነው። ለዚህ ሲባል የኢትዮጵያ ህዝብ ተባብሮ አገዛዙን እንዲያስወግድ ከዛ በኋላ የአገር ጥቅምና ሉአላዊነት ለማስከበር መስራት እንደሚቻል መግለፅ ይቻላል።
4) አገዛዙ ለህዝብም ለአገርም ለአገርና ህዝብ ጥቅም የማይቆም፣ የአገርንም የውጭ ፖለቲካን ያበላሸ መሆኑን ቆጠብ ብሎ መግለፅ ይቻላል።
እንዲህ ያሉ ወጥመዶች ጦሳቸው ብዙ ነው። ፋኖ በርካታ ስብጥር ያለው ህዝብ ድጋፍ ይሰጠዋል። መሰል የችኮላ አስተያየቶች ድጋፍ ይከፋፍላሉ። ለአገዛዙ የጎንዮሽ ፕሮፖጋንዳ ያመቻሉ፣ ስህተት ከተሰራ ለአመታት እየተከተሉ አይለቁም። ተመሳሳይ አጋጣሚዎች በኢህአፓ ዘመንም ተፈጥረዋል።
"የጠላቴ ጠላት ወዳጄ" የሚባል ድፍን አባባል አለ። ይህኛው ውስብስብ ነው። ፋኖ ሰሞኑን ለምርኮኞች እያደረገ ባለው ብስለት ልክ ለወጥመዱም ስክነት ያስፈልገዋል። የፋኖ አመራሮች ከስሜታዊ የቲክቶክ ደጋፊዎቻቸው መለየት አለባቸው። መሰል አጀንዳዎች የማናውቀውና ጥሻ የሆነ የዓለም ፖለቲካ ውስጥ ወሰዶ ይወሽቀናል። እጅግ አደገኛ ነው።
ለብሽሽቅ ከሆነ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያለው ኃይል በቂ ነው። የፋኖ አመራሮች ከዚህ ዘመናትን ሊከተላቸው ከሚችል ጉዳይ ራሳቸውን ማራቅ፣ ወጥመዱን በብስለት ማክሸፍ አለባቸው!
ፋኖ የአማራ ህዝብን ህልውና ማስጠበቂያ እንጅ የሌላ ኃይል ወዳጅነት መፍጠሪያ፣ ማስፈራሪያ፣ መደራደሪያ መሳሪያ አይደለም። ማንም ሳያማክረው "እረዳለሁ" ስላለ "አዎ ያግዘኝ" የሚል ኃይል አይሆንም።
ከበርካታ ሚዲያዎች ይደወላል። ጥንቃቄ አድርጉ። ቅርበት ያላችሁ ለፋኖ አመራሮች አድርሱ።
እገታ‼️
ዛሬ ጠዋት ከባህር ዳር አቅጣጫ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ከጠዋቱ 5 ሰዓት አካባቢ በኦሮሚያ ክልል በ #ፍቼ እና በ #ገርበጉራቻ መካከል ልዩ ስሙ# ደገም በምትባል አነስተኛ ከተማ ሲደርሱ ታጣቂዎች መኪናውን አስቁመው ብዛት ያላቸው አማራዎችን አግተው ወስደዋቸል‼️
በአውቶቡስ ውስጥ ተሳፍረው የነበሩ አንድ ትራፊክ ፖሊስ እና የመኪናው ሹፌር በታጣቂዎቹ ተገድለዋል።
ከተሳፋሪዎቹ ውስጥ ረዳቱን ጨምሮ ሌሎች ሰባት ሰዎች ያመለጡ ሲሆን ሌሎቹ ሙሉ ለሙሉ ታግተው ተወስደዋል።
ታወጀ‼️
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ገዜ ወረዳ የደረሰውን የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ ሕይወታቸው ላለፉ ዜጎች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከነገ ጀምሮ ለ3 ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ ሐዘን አውጇል።
ያ ሁሉ አማራ በአብይ አህመድ ሴራ እና ትእዛዝ በኦሮሚያ ሲጨፈጨፍ ምክር ቤቱ አይመለከተውም ማለት ነው ??
ለማንኛውም አደጋው ለደረሰባቸው ወገኖቻችን ፈጣሪን ነፍሳቸውን ይማር።
=======================
የብርጋዴር ጄኔራሉ መቀላቀልና በጉጉት የምንጠብቀው ይፋዊ ጥሪ!
ዛሬ ከተሰሙት የምስራቾች ውስጥ አደረጃጀቱ በነበረበት ወቅት የአማራ ልዩ ኃይል የዋሊያ ክፍለጦር አዛዥ የነበሩትና አሁን ደግሞ በሰራዊቱ የሰሜን ምዕራብ እዝ ውስጥ የነበሩት ብ/ጄኔራል ተዘራ ንጉሴ ፋኖን በይፋ የመቀላቀል ዜና ነው። ይህ ትልቅ የምስራች ነው፤ የብ/ጄ ተፈራ ማሞ ፋኖን የመቀላቀል ውሳኔና ዜና ብቻ ይዞት የመጣ እድል እንደሆነም እንረዳለን።
እንግዲህ ደግሞ ብ/ጄኔራል ተፈራ ማሞ በጨፍጫፊውና ፋሽስታዊው አገዛዝ ውስጥ ላሉ የአማራ ኃይሎችና የሰራዊቱ አባላት በይፋ "የፈልሳችሁ ውጡ" ጥሪ ሲያቀርቡ የሚፈጠረውን ማየት ነው። አሁን ከምንም በላይ ይህንን አጭርና ግልፅ በወታደራዊ ፕሮቶኮል የታጀበ የብ/ጄኔራል ተፈራ ማሞን ይፋዊ ጥሪ ከሁሉም በላይ በጉጉት የምንጠብቀው ነው። ጥሪው በቶሎ ቢቀርብ ደግሞ በእጅጉ አትራፊ ይሆናል ብለን እናምናለን።
አሁን አንድ እጃችን ግንባር የሚያፈርስ ነፍጥ፣ ሌላ እጃችን ደግሞ ፋሽስታዊ ተቋማቶቻቸውን የሚንድ መዶሻ ታጥቀዋል፤ በወሳኝ ጊዜያት ልንጠቀምበት የግድ ነው።
ኬንያውያን አዲሱን የሀገሪቱን የፋይናንስ እና ታክስ ህግ ተቃውመው ላለፉት ሶስት ቀናት ድምፃቸውን አሰሙ፣ ሰልፍ ወጡ፣ ህብረታቸውን አሳዩ
ይህን ተከትሎ የኬንያው ፕሬዝደንት "ህዝቡ የሚለውን ካዳመጥን በኋላ ህጉ ላይ ለውጥ አርገናል፣ የሀሳብ ልውውጥ ስላደረግን ደስ ብሎኛል፣ ዴሞክራሲያችን እየሰራ እንደሆነ ማሳያ ነው" አሉ። በዚህ ያልረካው ህዝብ አሁንም ተቃውሞውን እያሰማ ነው።
ተቃውሞውን ያሰማው የእኛ ህዝብ ቢሆንስ?
- የሽብር ድርጊት ለመፈፀም በህቡዕ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ
- ከሀገሪቱ ታሪካዊ ጠላቶች ተልእኮ በመቀበል ሀገሪቱን የብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ ሲያሴሩ
- በድብቅ መሳርያ በማስገባት እና በገዳማት ጭምር ወታደራዊ ስልጠና በመስጠት ሲንቀሳቀሱ... ወዘተ ተብለው በጅምላ ወደ ማጎሪያ።
አሳዛኝ ትውልድ።
ኤልያስ መሠረት
የፓርላማ አባል የነበሩት አቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአማራ ክልል ም/ቤት አባሉ ዮሐንስ ቧያለዉን ጨምሮ 14 የሽብር ተከሳሾች ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ‼️
የኢትዮጵያ መንግስት በአሸባሪነት ጠርጥሮ ካሰራቸዉና ክስ ከመሰረተባቸው 52 ተጠርጣሪዎች መካከል፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ክርስቲያን ታደለ እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል ዮሐንስ ቧያለዉን ጨምሮ 14 ተከሳሾች ትላንት መጋቢት 27/ 2016 ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት የቀረቡት የእምነት ክሕደት ቃላቸዉን ለመስጠት የነበረ ቢሆንም፤ በደል ደርሶብናል በማለታቸዉ ችሎቱ ተከሳሾች ያቀረቡትን አቤቱታ ሲያደምጥ መዋሉን ዶቸ ቬለ ዘግቧል።
በዚህም መሰረት አቶ ክርስትያን ታደለም በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት፤ «ወርቅ የአንገት ሃብል፣ ሁለት የጣት ቀለበት እንደተወሰደባቸው» ትላንት በዋለው ችሎት ላይ ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል ሲሉ አቶ ጠበቃ አቶ ሰለሞን ገዛኸኝን አስረድተዋል።
በተጨማሪም የሞባይላቸውን ቁልፍ እንዲከፍቱ« በሽጉጥ እንዳስፈሯሯቸው እና ጣታቸውን እንደተመቱ» አክለው አስረድተዋል ተብሏል።
የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ዮሀንስ ቧያሌው በበኩላቸው " አስኬረን መሃል አስቀምጠውኛል" ብዙ ስቃይ ደርሶብናል ሲሉ ተደምጠዋል።
ሰበር መረጃ‼️
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአሜሪካ የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት ጨርሰው ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ እንዳይገቡ መከልከላቸው ተሰምቷል።
ብፁዕነታቸው ከሳምንታት በፊት በቋሚ ሲኖዶስ እውቅና ወደ ሀገረ ስብከታቸው በመሄድ የአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ዓመታዊ በዓል፣ የከተራና የጥምቀት በዓላትን ከመንፈስ ልጆቻቸው ጋር ያከበሩ ሲሆን ለአዳጊ ሕጻናትም ማዕረገ ዲቁና መስጠታቸው ይታወቃል።
ብፁዕነታቸው በአሁኑ ሰዓት ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያው ይገኛሉ ሲሉ መረጃ ሰጭዎቻችን አድርሰውናል።
©ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት
የሚኖርበት ቤት ለልማት በሚል የፈረሰበት እና ስራ እንዳይሰራ የተከለከለ ወጣት ራሱን አጠፋ‼️
ነዋሪነቱ አዲስ አበባ ኡራኤል አካባቢ የሆነ አዲሱ ካሳሁን የተባለ ወጣት ከኡራኤል ቤተክርስቲያን ወደ አትላስ ሆቴል በሚወስደው መንገድ አካባቢ በሚገኘው 'በፀጋህ ሆስፒታል' ፊት ለፊት ነዋሪ ሲሆን ከትናንት በስቲያ ራሱን አጥፍቷል።
አዲሱ ነጠላ ከሚሸጥበት ኡራኤል ቤተከርስቲያን አካባቢ ስራ እንዳይሰራ ሁለት ግዜ በደንብ አስከባሪዎች ተባሮ እና ንብረቱም ተወስዶበት እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች እና የቅርብ ሰው ተናግረዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ከትናንት በስቲያ ምሽት ማታ ወደ ቤቱ ሲገባ የሚኖርበት ቤት በነጋታው ጠዋት እንደሚፈርስ ሲነገረው ተስፋ በመቁረጥ ስሜት እዛው ቤቱ ውስጥ ራሱን እንዳጠፋ ታውቋል።
የልጅ አባት የሆነው እና በቅርቡ የወለደች ባለቤት ያለው ወጣቱ ይህን ድርጊት ከፈፀመ በኋላ ትናንት ስድስት ሰአት ላይ በኡራኤል ቤተክርስቲያን ቀብሩ እንደተፈፀመ ሰምተናል።
#መሰረት ሚዲያ
=============
በኢትዮጵያ ያሉ ሁሉም ባንኮች በወለጋ ለሚከናወን የኮሪደር ልማት 615 ሚልዮን ብር አዋጡ ተባሉ ‼️
በኢትዮጵያ ያሉ ሁሉም ባንኮች ለወለጋ የኮሪደር ልማት 615 ሚልዮን ብር አዋጡ እንደተባሉ ተሰምቷል።
እነዚህ 31 ባንኮች በማህበራቸው በኩል፣ ማለትም በኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር አማካኝነት ለወለጋ የኮሪደር ልማት 615 ሚሊየን ብር እስከ መስከረም 25/2017 ድረስ እንዲያዋጡ በገንዘብ ሚኒስቴር ዴታ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ በኩል ተነግሯቸዋል።
በዚህ ዙርያ የተመለከትነው የባንኮች ማህበር ደብዳቤ እንደሚለው በወለጋ አካባቢ በህብረተሰብ ተሳትፎ በሌሎች ክልሎች እየተደረጉ ያሉ የልማት ክንውኖች በፀጥታ ምክንያት ሳይካሄዱ ቢቆይም አሁን አንፃራዊ ሰላም በመስፈኑ ልማቱን ለማካካሄድ ገንዘብ በማስፈለጉ "ወለጋ ኮሪደር ልማት" በሚል የንግድ ባንክ አካውንት ባንኮች ገንዘብ ገቢ እንዲያረጉ ተነግሯቸዋል።
በማህበሩ ሀላፊ አቶ ደምሰው ጣሰው የተፃፈው ይህ ደብዳቤ ባንኮቹ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር መስከረም 3 ቀን ባደረጉት ስብሰባ ይህን ገንዘብ ቃል እንደገቡ ይገልፃል።
በሌላ በኩል ስለ መዋጮው ዶ/ር እዮብ ተካልኝ መስከረም 9 የፃፉትን ደብዳቤም የተመለከትን ሲሆን ፕሮጀክቱ የነቀምት ከተማ የኮሪደር ልማትን ማእከል ያደረገ መሆኑን ገልፀው የሀሳቡ አመንጪ አብይ አህመድ እንደሆነ በደብዳቤያቸው አንስተዋል።
ለጉዳዩ ተገቢውን ትኩረት ሰጥተው ብሩን እንዲያስገቡ አሳስበዋል፣ አንዳንድ ባንኮችም ክፍያውን መፈፀም መጀመራቸው ታውቋል።
#መሰረት ሚዲያ
እኛ ደሞ እንላለን
============
ባንኮች አገልግሎት ሰተው የሚያተርፉት ከኢትዮጲያ ህዝብ ነው። ኮሪደር እየተሰራ ያለው በመላ ሀገሪቱ እስከሆነ ድረስ በምን አግባብ ነው ለወለጋ ብቻ የሚያዋጡት??
ካዋጡም ለሁሉም ክልሎች ነው መሆን ያለበት።
ይሄ አይን ያወጣ ድንቁርና እና ማን አለብኝነት ነው።
ደብረጽዮን ገብረሚካኤል(ዶ/ር) ከአገር እንዳይወጡ ተከለከሉ‼️
ደብረጽዮን ወደ አየርላንድ ሄደው ጥገኝነት ለመጠየቅ ሲዘጋጁ መረጃ ደረሰኝ ያለው የአብይ አህመድ መንግሥት ከአገር እንዳይወጡ እግድ አስተላልፎባቸዋል ተብሏል።
ደብረጽዮን በሕወሓት ውስጥ የተፈጠረውን ክፍፍል ተከትሎ በትግራይ ሕዝብ ባለቤትነት የተመዘገበው የ"ኤፈርት" ሃብት የኦዲት ምርመራ ሲደረግበት 13 ቢሊዮን ዶላር ጉድለት መገኘቱ በመረጋገጡ ከተጠያቂነት ለመሸሽ ከኢትዮጵያ ሊኮበልሉ ነው በሚል መታገዳቸው ተሰምቷል።
ሕወሓት ወደ ትግራይ ተሰባስቦ ሲገባ በድርጅቱ ውስጥ ከፍተኛ ውዝግብ ሲነሳበት የነበረው ጉዳይ የኤፈርት ሃብት ብክነት እንደነበር አንድ ምንጭ አስታውሰዋል።
የኤፈርት ገንዘብ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ባንኮች ውስጥ በተለያዩ ግለሰቦች ስም ተቀምጦ እንደነበርም ተናግረዋል።
የተቋሙ ገንዘብ ምንም እንኳን ኦዲት የሚደረግ ቢሆንም ለዘረፋ የተጋለጠ እንደነበር የሚገልጹ አካላት አሉ።
በአገር ውስጥ የኤፈርት ኃላፊ መሆናቸው የሚታወቀው ኃይሌ ሊባኖስ የተባሉ ሰው ሲሆኑ በውጭ አገራት የተከማቸውን ከፍተኛ ገንዘብ የሚያንቀሳቅሱት ደግሞ ከፍሥሐ ማንጁስ ጋር ተባብረው ነው።
በቅርቡ ጠፍቷል ከተባለው 13 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ 3 ቢሊዮኑ በጦርነቱ ወቅት መሳሪያ ከውጭ አገራት ተገዝቶበታል በሚል ሰነድ ቀርቦ እንዲወራረድ መደረጉን ምንጮች አትተዋል።
10 ቢሊየን ዶላሩን ደግሞ ከሕወሓት የጽሕፈት ቤት ኃላፊ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሔር (ሞንጆሪኖ) ጋር የፍቅር ግንኙነት እንዳላቸው የሚነገርላቸው ኃይሌ ሊባኖስ ይዘውት ወደ እንግሊዝ መሰወራቸውን ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡
አዲስ አበባ ከተማን እንታደግ!! (አስቸኳይ)
=============================
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ከታች ባለው ሊንክ ጆይን በማድረግ የአዲስ አበባን ከተማ ከመፍረስ እንዲሁም ህዝቡን ከእንግልት እና ስቃይ እንታደግ።
ግሩፑን ለከተማው ነዋሪ እንዲደርስ ሼር ያድርጉ
/channel/addisababaoldcity
ከጥቂት ሳምንታት በፊት ወደ አዲስ አበባ የተጠሩትን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ኢ/ር ስለሺ በቀለን እንዲተኩ የተመረጡት አምባሳደር ሌንጮ ባቲ በአሜሪካ መንግስት ተቀባይነት አጥተዋል።
አሜሪካ የኦቦ ሌንጮ ለታን የኢትዮጵያ በአሜሪካ አምባሳደርነት እንደማትቀበል አሳውቃለች።
ምክኒያቱ ደግሞ በኦቦ ሌንጮ ላይ ወሲባዊ ክስ ከዚህ ቀደም ስለነበረባቸው መሆኑ ታውቋልቀ።
ይሄ ለኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
==================
ቢቢሲ አማርኛ እንደዘገበው!!
===================
የብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደርን ላይ ማሻሻያ ማድረጉን ተከትሎ የብር የመግዛት አቅም በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በ57.93 በመቶ ተዳከመ።
ናይጄሪያ የ IMFን ምክረሀሳብ ተቀብላ የዶላር ዋጋን በገበያው እንዲተመን (Floating exchange) ውሳኔ ያሳለፈችው በቅርቡ ነበር፣በዚህም የናይጄሪያ መገበያያ የሆነው ኒያራ የመግዛት አቅሙ ቀድሞ ከነበረበት ከእጥፍ በላይ ተንኮታኩቶ ዛሬ አንድ ዶላር 1,595 ኒያራ ይመነዘራል። በዚህ የተነሳ ህዝቡ ኑሮው አስቸጋሪ ሆነበት፣የህዝቡ የተለመደ ምግባቸው (Staple food) የሆነው ሩዝ ከ50% እስከ 100% ጨመረ፣የሀገሪቱ መንግሥት ይህን ለማረጋጋት ደመወዝ ጨመረ፣ነዳጅን በድጎማ አቀረበ ግን ብዙም መፍትሔ አላመጣም።
የናይጄሪያ መገበያያ ገንዘብ በእጅጉ በመዳከሙ ኑሮ ሰማይ ወጣ፣ርሀብ ተስፋፋ፣ይባስ ብሎ የነዳጅ ድጎማውን መንግስት አነሳ ቀውሱ ተባባሰ፣ህዝቡ አሁን በአደባባይ ተቃውሞውን እያሰማ ነው፣እስካሁን ባለው መረጃ ሶስት ሰዎች ከፀጥታ ሀይሎች በተተኮሰ ጥይት ሞተዋል።
የአሜሪካ ኢምባሲ በኦሮሚያና በአማራ ክልል እየተባባሰ ከመጣው ግጭት ጋር ተያይዞ ሰውን አፍኖ ገንዘብ የመጠየቅ ጉዳይ አሳሳቢ ሆኗል ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የህግ የበላይነትም እየተዳከመ ነው ብሏል። በቅርቡ ከአማራ ክልል ደባርቅ ዩኒቨርስቲ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በታጣቂዎች መታገታቸውን በማስታወስ ይህ ተግባር በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል ብሏል።
=====================
ሰበር ዜና
አንጋፋው ወታደራዊ አዛዥ ጄኔራል ተፈራ ማሞ ለአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ፋኖን በይፋ ተቀላቀሉ። ጄኔራሉ ቀደም ሲል ህዝብን ከወያኔ ወረራ የታደጉ እንዲሁም የአማራ ልዮ ኃይልን፣ የአድማብተናን እና የሚሊሽያን መዋቅሮች ያደራጁና ያሰለጠኑ አንጋፋ ወታደራዊ መሪ ናቸው።
#መረጃ‼️ ተሸንፌያለሁ:-ሩቶ‼️
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ተቃውሞ ያስነሳባቸውን "የግብር ማሻሻያ" እቅዳቸውን መሰረዛቸውን ለመላው የኬንያ ህዝብ አሳውቀዋል። ህዝብን ልመራ ነው የተመረጥኩት፣ ህዝብ ከተቃወመኝ ማዳመጥ አለብኝ። "ተሸንፌያለሁ። ሀሳቤን ሰርዢያለሁ" ብለዋል። አዲሱ የግብር ማሻሻያ በኬንያ ፓርላማ በ195 አብላጫ ድምፅ እና 106 ተቃውሞ አድፅቆ ለዊሊያም ሩቶ መላኩ ይታወሳል። በዚህ ምክንያት በኬንያ ከፍተኛ ተቃውሞ መቀስቀሱን ተከትሎ ዛሬ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በፓርላማው የፀደቀውን የግብር ማሻሻያ ሰርዘናል፣አልፈርምም ብለዋል።
===========≠==========
የኛ ደንቆሮ ቢሆን ምን ይል ይሆን ነበር???
የአሜሪካ ኢምባሲ በኢትዮጵያ በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም መራዊ ከተማ የተፈፀመው ጥቃት በእጅጉ እንዳሳሰበው እና በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠየቀ‼️
የአሜሪካ ኤምባሲ በኢትዮጵያ ያለው ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆምም ጠይቋል።
በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ያሉት ግጭቶች፣ ከፍተኛ ሰብአዊ ሥቃይ እያስከተሉ መሆኑ በእጅጉ እንዳሳሰበው የገለጸው በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ፣ በአስቸኳይ እንዲቆሙ ጠይቋል፡፡
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጆሴ ማሲንጋ ሁለቱ ሀገራት የዲፕሎማሲ ግንኙነት የጀመሩበትን 120ኛ ዓመት አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደብዳቤ የጻፉት፣ አገራቸው በኢትዮጵያ ሰላም እና ልማት እንዲረጋገጥ ድጋፍ እያደረገች እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በአምባሳደሩ ስለተጻፈው ደብዳቤ ለአሜሪካ ድምፅ ማብራሪያ የሰጡት፣ በኤምባሲው የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ኃላፊ ናዮሚ ፌሎውስ፣ በኢትዮጵያ ያሉት ግጭቶች በሰላም እንዲፈቱ አገራቸው ጥረት እንደምታደርግ ተናግረዋል።
የ ዌልካም ኮርፕስ መረጃ ለ ኢትዮጵያን እና ኤርትራዉያን አዳዲስ መረጃ ያላችሁ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ግሩፑን ጆይን በማድረግ እንዲሁም ለሌሎች ሼር በማድረግ መረጃ ተለዋወጡ።
ሪፊውጂ ከ ሴፕተምበር 30 በፊት የተመዘገባችሁ ሆኖ ስፖንሰር ያጣችሁ እንዲሁም አሜሪካ ነዋሪ ሆናችሁ ስፖንሰር ማድረግ የምትፈልጉ በጎ ፍቃደኞች ወገኖቻችን ጠቃሚ መረጃ ተለዋወጡበት።
/channel/Welcomecorpsforethiopian