ethio81 | Unsorted

Telegram-канал ethio81 - ዮቶድ

244

-ስለ ኢትዮጵያ ልዩ ሚስጥራት እና ጥበባት -ኢትዮጵያን አፅንቶ ስለ የያዛት ሃይማኖት -በኢትዮጵያ እና በሃይማኖቷ ላይ ስለ ሚሰራው ድብቅ ሴራ -ስለ መጪው ምርጥ ኢትዮጵያዊ ንጉሥ እና ስለ አስከፊው የመከራ ዘመን

Subscribe to a channel

ዮቶድ

Watch "ሊቀ መዘምራን ቴውድሮስ ዬሴፍ( new ethiopian Orthodox mezmur tedros yosef" on YouTube
https://youtu.be/KAZqDDDmfUY

Читать полностью…

ዮቶድ

ሆሳዕና በአርያም - hosanna bearyam - Ethiopian orthodox Tewahdo mezmur
https://youtu.be/vqm93uC9pNo

Читать полностью…

ዮቶድ

እንጨት ቁጭ ብሎ ሰው እየነደደ
ሕግ አዋቂ ቆሞ ሌባ እየፈረደ
አሳ መረብ ጥሎ ሰው እያጠመደ
አንበሳ በጅቦች እየተሳደደ
የእርግቦች ማሕፀን ጊንጥ አየፀነሰ
ሰማይ ጭስ አርግዞ እሳት እያፈሰሰ
ሰው እየተጋዘ አውሬ እየነገሰ
ቀሳውስት ተወግዘው ሌባ እየቀደሰ
እምዬ ማቅ ለብሳ ሌባ እየደነሰ
ይህ ሁሉ ሲሰራ መላው ጠፍቶን እኛ
ኧረ ወዴት ገባህ የሰማዩ ዳኛ
@ethio81
@ethio81
@ethio81

Читать полностью…

ዮቶድ

#ኤረር_ተራራ
በአለማችን ላይ ድብቅና ምስጢራዊ ተብለው ከሚነሱ ታላላቅ ስፍራዎች መካከል አንዱና የቀዳሚነት ደረጃ ይዞ የሚገኘው ኤረር ተራራ ነው፡፡ ምንም እንኳን ይህ ተራራ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት የሚገኝ ቢሆንም አብዛኛው ሰው እንዲሁ እንደዘበት ስለዚህ ተራራ የሚነገሩ ንግርቶችን ከማድመጥ በዘለለ ስለዚህ ታላቅ ስፍራ የሚያውቀው ነገር የለውም፡፡

ለማንኛውም ኤረር ተራራ
1. የአዳም ርስት ሀገር ማዕከላዊ ስፍራ
2. የመጨረሻውን ዘመን መምጣት አብሳሪ የሆነው የቅዱስ ሩፋኤል መቀመጫ ስፍራ
3. የታላቁ የሊቀ ካህን መልከጸዲቅ ስድስቱ የክብር ዕቃዎችን መጠበቂያ ስፍራ
4. የማዕከለ ሰብዕ መሰብሰቢያ ስፍራ
5. የእነዚህ ህዝቦች መጓጓዣ የሆኑት ክንፍ ያላቸው ፈረሶች መገኛ ስፍራ
6. የታላቁ የስውራን መንፈስ መውጫ ስፍራ
7. የኢትዮጵያ የዳግም ትንሳኤ ሀሳብ መነሻ ስፍራ
8. #የህይወት_መፀሀፍ (መፀሀፈ ራዚኤል)አባታችን አዳም ከገነት ከወጣ ቡሀላ ቅዱሳን መላእክት ያስተማሩት የሰማያተ ሰማይ ብሎም የምድራዊ ሰማያት ሚስጥራትን ጥበባትን ለልጆቹ #ለኢትዮጵያን ማስተማርያ ይሆን ዘንድ በ እግዜብሔር ፍቃድ በድንጋይ ላይ በግእዝ ቋንቋ ፅፎ አስቀመጠላቸው ይህ መፀሀፍ መፃፈ ራዚኤል ብለን የምንጠራው ነው።ይህም መፀሀፍ በዚ በኤረር ተራዎች ከመሬት በታች በሆነው ስውሩ ስፍራ ይገኛል።ኢትዮጵያ ድሮ ታልቅ የሆነችበት ሚስጥር ይሔን መፀሀፍ በመጠቀሟ ነው።

9. በስተመጨረሻም የሰው ወገኖች ሁሉ መሰብሰቢያ ስፍራ ነው፡፡

እነዚህ እኛ የጠቀስናቸውን እና አሁን ልንጠቅሳቸው ያልፈለግናቸውን ምስጢራት ኤረር ተራራ ይዞ ይገኛል፡፡ እኛም በዘመናችን ስለዚህ ስፍራ በተገለጠልን እና በተረዳነው መጠን እነዚህ ምስጢራት በዚህ ዘመን የሚገኝ የሰው ልጅ እንዲያገኛቸውና እንዲጠቀምባቸው ለማድረግ በዚህ ስፍራ ላይ ሙሉ ጊዚያችንን ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን፡፡

ከእነዚህም ስራዎቻችን መካከል ከዚህ ታላቅ ተራራ በአራት አቅጣጫ ከሚፈልቁት ምንጮች መካካል አንደኛውን በተገለጠን እና በተሰጠን ጥበብ መጠን ለሰው ልጆች አገልግሎት እንዲሰጥ አድርገናል፡፡
ምንጭ፡ጤንነት ሰጠኝ
👇👇👇share
@ethio81
@ethio81
@ethio81

Читать полностью…

ዮቶድ

ጉንደ መስቀል
ይቺ ጥንታዊ ከተማ እግዚአብሔር የሚያውቃት መንግስትና ህዝብ ግን ከአይኑ የተሰወረችበት እስኪ መስል ድረስ ዛሬም የእድገቷ ነገር አፄ ዘርዓያዕቆብ ዘመን ነች። ወጀ ቀድሞ ነገራችን ስንመለስ ጉንደ መስቀል በሰሜን ሸዋ ሀገር በደራ ወረዳ የምትገኝ ከተማ ነች። ይች ከተማ ጉንደ መስቀል ተብላ በማን እንደ ተሰየመች በእርግጥ የሚናገር የለም። እኛ ግን ማን ሰየማት ሳይሆን ለመን ተሰየመች የሚለው ብንመለከት መልካም ነው እላለሁ። ጉንደ መስቀል ማለት የመስቀሉ ግንድ እንደማለት ነው። በዝች ከተማ ውስጥ ጥንታዊ ታሪካዊና ምስጢራዊ ታላቅ ገዳም ይገኛል ይህገዳም መ
ከከተማዋ አናት ላይ በሚገኝ ከፍታ ላይ ለከተማዋ ግርማ ሞገስን ስቶ የተቀመጠ ነው። መስቀለ ኢየሱስ ገዳም ይባላል። በአፄ ዘርዓያዕቆብ ዘመን እንደተመሰረተ አሳማኝ መረጃዎች አሉ የከተማዋ ስያሜም ከዚህ ጋር የተያያዘ እንደሆነ እገምታለሁ። አፄ ዘርዓያዕቆብ በራዕይ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል" መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ አስቀምጥ የሚለውን ራዕይ ባየ ጊዜ መስቀለኛ ቦታ ፍለጋ ኢትዮጵያን ለበርካታ ዓመት ሲዞር እንደነበር ታሪክ ይናገራል ታድያ መስቀለኛ ቦታ ፍለጋ ከተዟዟሩበት የሀገራችን ክፍሎች አንዷ ጉንደ መስቀል ከተማ ነች በዝጅ አካባቢ በደረሰ ጊዜ አንድ ተአምር እንደተከሰተ ይወሳል አሁን መስቀለ ኢየሱስ ገዳም በታነፀበት ተራራ ላይ በደረሱ ጊዜ ቅዱስ መስቀሉ ከካህናት እጅ ተነጥቆ በዚ ተራራ ላይ ወደ ቲቻ በመምታት በተአምር እንደተቀመጠ ይነገራል ታድያ አፄ ዘርዓያዕቆብ መስቀለኛው ቦታ ይህ ነው መስቀሉ ምልክት አሳይቷል በማለት በዚያ እንደተቀመጡ ይነገራል ታድያ በድጋሚ በተኙ ጊዜ "መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ አኑር የሚል ራዕይ በድጋሚ ተመልክተዋል። ይህ ታሪክ ነው ለከተማዋም ለገዳሙም መመስረት ምክንያት የሆነው። መስቀሉም ከዚህ ስፍራ ተነስቶ ወደ ጊሸን መስከረም 21 ገብቷል። ወደ ዋናው ነገራችን ስንመለስ። ይሄ ታሪክ ግማድ(ግማሽ) መስቀል የሚለውን ነገር በትንሹም ቢሆን ገፎ የሚጥል ይመስላል ምክንያቱን እናስተውል። እግዚአብሔር በራዕይ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል" መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ አስቀምጥ አለው እንጂ " አንብር ግማድ መስቀልየ በዲበ መስቀል"ወይም ግማሽ መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ አስቀምጥ አላለውም። በማስተዋል መመልከት ያለብን እግዚአብሔር ቅዱስ መስቀሉን በሙላት መስቀሌን እያለ ሲጠራው እንጂ ግማደ መስቀሌን እያለ ስጠራ አንመለከትም ታድያ እኛ ስለምን ግማድ(ግማሽ) እንለዋለን? ከዚ አያይዤ ማንሳት የምፈልገው ነገር ከተማዋ በራሷ ቅዱስ መስቀሉ እንዳረፈባት እንዲታሰብ ስም ሲሰይሙላት ጉንደ መስቀል አሏት እንጂ ግማደ መስቀል አላሏትም ጉንደ መስቀል የሚለው ስያሜ ደሞ የመስቀሉን ሙላት እንጂ ክፋይነት አይወክልም ጉንደ ማለት ሙሉ ግንድ እንደማለት ሲሆን ግማድ ማለት ደግሞ የግንድ ክፋይ ግማሽ እንደማለት ነው።
ታድያ አንዳንድ መፅሐፍቶቻችንና ታሪኮቻችን ላይ የግብፅ ጳጳሳት የራሳቸውን ሚና እንደተጫወቱ ያሳያል። ምክንያቱም አያሌ የዓለም ሀገራት ግማደ መስቀል(የመስቀል ክፋይ አለኝ) እያሉ እስካሁንም ድረስ ይናገራሉ ግብፅም ጭምር ይህ የመስቀሉ ቁራጭ እንዳላት ትናገራለች የተለያዩ የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያኖችም ይሄው የመስቀሉ ቁራጭ አለን ሲሉ ይሰማል። ታድያ አንድ የፕሮቴስታንት ፓስተር አለን የሚባለው ቁራጭ ሁሉ ቢሰበሰብ አንድ መርከብ ይሰራል ሲልም ተሳልቆ ነበር። ታድያ እኒህ ሀያላን ሀገራት ቁራጩ አለን እያሉ ሲነታረኩ ኢትዮጵያ ሙሉ መስቀሉ አለኝ ብትል ለነሱ ውርደት አደለምን?? ስለዚህ ዋናው መፍትሄው በእስክንድርያ በኩል ኢትዮጵያን አፏን ማስያዝ ነው እሷም እንደሌላው ቁራጩ ግማዱ ነው ያለኝ እንድትል ማድረግ ነው። የሆነው ሆኖ መስቀል የፋሲካ አልያም የገና የቅርጫ ከብት አይደለም የአለም ሀገራት የሚከፋፈሉት። መስቀል የአዲስ ኪዳን የክርስቶስ ስጋና ደም የተፈተተበት ቅዱስ መሰዊያ ታቦት ነው ታድያ ማን ነው ይህን መለኮት ያረፈበትን መስቀል ለመቆራረጥ የሚደፍር?
መልካም ቀን

@ethio81
@ethio81
@ethio81

Читать полностью…

ዮቶድ

🇪🇹🇪🇹🇪🇹ኢትዮጵ/ኢትኤል🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ኢትዮጵያ መጠሪያዋን ከየት አገኘች?


በመፅሃፍ ቅዱስ ላይ እንደተጠቀሰው ሊቀ ካህኑብ መልከፄዴቅ ሶስት ወንድ ልጆች ነበሩት ከነኛ ልጆች አንዱ ደግሞ ኢትኤል ነበር ኢትኤል በመንፈስ ተመርቶ ካለበት ከሳሌም እስራኤል ወደ ጣና ላይ እንዲሰፍር ታዘዘ። ኢትኤል ጣና ሲደርስ ስሙን ቀይሮ ኢትዮጵ እንዲባል ሆነ። ኢትዮጵ ማለት ፦ ኢት - ስጦታ ማለት ሲሆን ዮጵ ደግሞ ቢጫ ወርቅ ማለት ነው። ኢትዮጵ የቢጫ ወርቅ ስጦታ! ኢትኤል ማለት ደግሞ የእግዚአብሄር ስጦታ ማለት ነው። የሃገራችን መጠሪያ የመጣው ከንጉስ ኢትዮጵ በኃላ ነበር በኢትዮጵ ኢትዮጵያ ተባለች።
ሃገራችን ኢትዮጵያ የሚለውን ስያሜ ከማግኘቷ በፊት እንቆጳግዮን ተብላ ትጠራ ነበር። በነገደ ዮቅጣን አግአዝያን የሚባሉት አቡሳውያን እንቆጳግዬን የሚለውን ወደ እንቆጳፅዮን ቀይረውታል። እንቆጳግዮን - የአባይ ወርቅ ፤ እንቆጳፅዮን - የፅዮን ወርቅ ማለት ነው።

ንጉስ ኢትዮጵ በግዮን ወንዝ ዳርቻ ላይ የድንጋይ ወንበር አስቀምጦ የልጅ ልጆቹ በሚነግሱበት ግዜ ቅብኣ መንግስቱን እንዲነግሱበት ሲል በክብር አስቀምጦታል። ንጉስ ኢትዮጵ ከአባቱ መልከፄዴቅ የተረከባቸውን መፅሃፍት እየተረጎመ አስቀምጧቸዋል ለልጆቹም ስርአተ ክህነት እና የቅብአ መንግስትን ግብር አስተምሯቸው እስከወዲያኛው ድረስ እንዲተላለፍ አድርጒል። ኢትዮጵ የግዮን ወንዝ የሚደርስባቸውን መሬቶች በሙሉ የኢትዮጵያ ግዛት እንዲሆኑ ያደረገ ሃያል ንጉስ ነበር።

ብዙ ሰዎች ንጉስ ኢትዮጵን ከ ኢትዮጲስ ጋር አንድ አድርገው ሲመለከቱ ይስተዋላል ስህተት ነው። ንጉስ ኢትዮጲስ ኢትዮጵ ከነገሰ ከብዙ ዘመናት በኃላ የነገሰ ንጉስ ነበር በ1856 አ.አ የነገሰ ንጉስ ነው።

የኢትዮጵያውያን ሁሉ አባት ኢትዮጵ በተወለደ በ150 አመቱ አርፏል። ልጆቹም አባቱ መልከፄዴቅ ካስፈለፈለው ዋሻ ውስጥ ወስደው እንደቀበሩት የታሪክ ድርሳናት ይዘግባሉ።

@ethio81
@ethio81
@ethio81

Читать полностью…

ዮቶድ

Watch "መድኃኔዓለም መዝሙር | ተዋህዶ new Orthodox mezmur 2020 ( Medhanialem )nati kiya tube" on YouTube
https://youtu.be/Z_ILaBzgeCs

Читать полностью…

ዮቶድ

Watch "የግሸኗ እናቴ - እሰይ ስዕለቴ ሰመረ - Esey silete semere (gishen) Ethiopian Orthodox mezimur" on YouTube
https://youtu.be/ZpyHjd-XqYU

Читать полностью…

ዮቶድ

እምቦጭን ከነአካቴው የሚያጠፋ መድሐኒት መገኘቱ ተገለፀ።‼️

የእምቦጭን አረም በሀገር በቀል እውቀት በመታገዝ ከነአካቴው ለማጥፋት የሚያስችል ፀረ-እምቦጭ መድሐኒት መገኘቱን የኢትዮጵያ ሊቃውንትና ምሁራን ማህበር ዛሬ በሰጠው መግለጫ አብስሯል።ይሄ በፈሳሽ መልክ የተዘጋጀ ፀረ እምቦጭ መድሐኒት በተረጨ በ24 ሰአታት ውስጥ የአምቦጭ አረምን ለማክሰም ይችላል የተባለ ሲሆን በ 30 ቀናት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ያስወግደዋል ተብሏል።መድሐኒቱ የተገኘው ስለ ዕፅዋት ከሚመራመረው ዕፀ ሕይወት የዕፅዋት ጥናትና ምርምር ማዕከል መሆኑን መግለጫውን የሰጠው የኢትዮጵያ ሊቃውንትና ምሁራን ማህበር ያስታወቀ ሲሆን መድሐኒቱን ወደ ተግባር አስገብቶ እምቦጭን በቀጣይ 3 አመታት ለማስወገድ ሕጋዊ ስምምነት ማድረጉን ገልጿል።ፀረ እምቦጭ ዕፅዋቱን ያገኘው ማዕከል መስራች መሪ ጌታ በላይ አዳሙ ዕውቀቱን የቀሰሙት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ስር ከሚገኙ ጠበብት ሊቃውንት መሆኑን በዕለቱ ተናግረዋል።

ፀረ እምቦጭ መድሐኒቱ ኦርጋኒክ በመሆኑ በሰው ላይም በስነ ፍጥረት ላይም ምንም አይነት የቀጥታም ሆነ የጎንዮሽ ጉዳት አያስከትልም ብለዋል።አረሙ ከዚህ በላይ ሳይስፋፋ በተፈለገው ፍጥነት ወደ ትግበራ ለመግባት ይረዳን ዘንድ ለምናደርጋቸው አውደ ጥናቶችና ተያያዥ ተግባራት በተለይ የመንግስት አካላትና የግል ባላሀብቶች እንዲሁም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የራሱን አስተዋፅኦ በማድረግ ከጎናችን እንዲቆም ጥሪ እናስተላልፋለን ሲል ማህበሩ መልዕክቱን አስተላልፏል።ጣና ሀይቅ 3 ሺህ 672 ኪሎ ሜትር ስፋት የነበረው ሲሆን ወደ 3 ሺህ ኪ.ሜ ወርዷል።በእምቦጭ ምክንያት፤ የሀዋሳና የዝዋይ ሀይቅ ተደምሮ የሚያክለው የሀይቁ ክፍል ወይም 125 ሺህ 579 የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳዎችን የሚያክል የቦታ ስፋት ወደ የብስነት መቀየሩን መረጃዎች ያሳያሉ።

@ethio81
@ethio81
@ethio81

Читать полностью…

ዮቶድ

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ግማደ መስቀሉ ወይስ ጉንደ መስቀሉ?
ክፍል አንድ
ኢትዮጵያ ሀገሬ በረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ።

ኢትዮጵያ ማለት ለአለም እንቆቅልሽ የሆነች ልጆቿ ግን ያላወቋት የእግዚአብሔር የምስጢር እቃ ቤት ነች።
አለም የኢትዮጵያንን ቀደምት ስልጣኔም ሆነ የኢትዮጵያን ታሪክ አፍና ደብቃዋለች አያሌ የታሪክ ተመራማሪ ነን ባዮች የኢትዮጵያ ታሪክና ስልጣኔ እንቆቅልሽ የሆነባቸው ቢመስልም ነገር ግን ስለዝች ሀገር ከመናገር ዝምታን መርጠዋል በዚህም አላበቃም ታሪኳን ለመበረዝና ለማጥፋት ያልተቆፈረ ጉድጓድና ያልተፈነቀለ ድንጋይ የለም።
በየዘመናቱ ለጦርነት ቢመጡ ብራና ቢሰርቁ ታሪክ ቢበርዙ ቢያጠፉ ከኢትዮጵያውያን ልብ ግን ኢትዮጵያዊነትን ሊበርዙና ሊሰርቁ ሊያጠፉትም አይችሉም አልቻሉምም።
ወዳጄ ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዥንጉርጉርነቱን እንደማይቀይር ታላቁ መፅሐፍ የመሰከረላት ሀገር እንደ ሆነች ማን በነገራቸው።
ፈረንጅ የኢትዮጵያን ታሪክ ሲያጠና ኢትዮጵያ የማን እረስት እንደ ሆነች አላነበበ ይሆን?
የስንት ቅዱሳን ሀገር እንደሆነች አልሰማ ይሆን?
እረ ማን ነው የእመቤታችን የአስራት ሀገር እንደ ሆነች ሹክ የሚልልኝ?
ወደ ቀድሞው ነገር እንመለስና የኢትዮጵያ ታላቅ ሀገርነት እንግብግብ ያደረገው የምዐራቡ ዓለም በተለያየ ጊዜ ታሪክ ሲበርዝ የቅዱስ መስቀሉን ነገርንም ነካክቶት አልፏል።
በምንኖርባት ዓለም ውስጥ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ደም ክቡር ስጋ የተፈተተበት ቅዱስ መስቀል እኔ ጋ ነው ያለው ብላ በኩራትና በድፍረት የምትናገር ሀገር ከኢትዮጵያ ውጪ ማንም የለም።
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ጉንደ መስቀሉ ወይስ ግማደ መስቀሉ?
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ግማሹ የቀኙ ክፍል መስቀል(ግማደ) ወይስ ሙሉው ቅዱስ መስቀል?

አለም የቅዱስ መስቀሉ መጥፋት ነገር ገራ ቢገባት ታሪክ ፈጥራለች።
326 ዓ.ም አካባቢ እሌኒ ቅዱስ መሰቀሉን እነዳገኘችውና ለበረከት ቆርሳ እንደወሰደችው በመናገር የቅዱስ መስቀሉን ክብር ታሪክን በመበረዝ አዋርደዋል ወገኔ ቅድስት እሌኒ እኮ ያገኘቸው ክቡር ደም ቅዱስ ስጋ የተሰዋበትን መስቀል እንጂ ለበረከት የሚሆን ህብስት አደለም ምን ታሪክ መበረዣ ቢጠፋ ለበረከት ቆርሳ ወሰደች ማለት በእውነት ያሳፍራል። የቅዱስ መስቀሉንም ክብር ያዋርዳል የቅድስት እሌኒንም ክብር ይነካል ይህ በዚህ አልቆመም አለም ቅዱስ መስቀሉ የት እንዳለ ቢጠፋት እኔ ጋ ነው ያለው የምትል ሀገር ባትገኝ እኔም ለበረከት ቆርጬ ወስጃለሁ እኔም ለበረከት ቆርጬ ወስጃለሁ የሚሉ በርከት ያሉ ሀገራት ናቸው። ይህንንመ ተረት ተረት መሠረት አድርገው ብዙ ቤተክርስቲያናት እኔጋ ቁራጩ አለ እኔም ለበረከት ወስጃለሁ የሚሉ ጥቂት አደሉም። አንዳንድ መናፍቃንም እንዲህ በዚ ጉዳይ ብዙ ተችተዋል አንዳንዶቹ አለ የሚባለው ክፍልፋይ ከመብዛቱ የተነሣ የሚያነሡት ትችት አለ፡፡ ጆን ካልቪን «ሁሉም ክፍልፋዮች ከመስቀሉ የወጡ ከሆነ፤ እነዚህን ሁሉ ብናሰባስባቸው አንድ መርከብ የግድ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ወንጌል ግን ይህንን መስቀል አንድ ሰው እንደ ተሸከመው ይነግረናል» ብሎ ነበር፡፡
በስተኋላ ግን ፆሟን ስትፈታ ቅዱስ መስቀሉ እኔ ጋ ነው ያለው በክብር አስቀምጬዋለሁ የምትል ሀገር እምዬ ኢትዮጵያ ብቅ ስትል ለበረከት ቆርጬ ወስጃለሁ የሚሉ ምዕራባውያንና የመሳሰሉትን አብያተ ክርስቲያናት ወደ ውርደት የሚመራ ውሸታሞች የሚያስብል ስለነበር በግብፅ ጳጳሳት ሴራ እጇን ተጠምዝዛ እኔም ግማደ መስቀሉ(ቁራጭ መስቀሉ ነው) ያለኝ እንድትል ተገዳለች። ጉንደ መስቀል (ሙሉው መስቀል) የሚለውን ሁሉ እየቀየሩ ግማደ መስቀል(ቁራጭ መስቀል) እንዲባል ግብፃውያን ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።
አንዳንድ የታሪክ መፀሀፍት ቅድስት እሌኒ ሦስት መስቀል እንዳገኘችና ለመለየት እንደተቸገረችና የጌታዋን ቅዱስ መስቀል ለመለየት ድውያንን በማምጣት እላያቸው ላይ በመጫን ለመፈወስ ስትሞክር ሦስቱም መስቀል ድውይ እንደፈወሱ እና በመጨረሻ ሙት አምጥታ ስታስቀምጥበት የጌታ መስቀል ብቻ ሙቱን እንዳስነሳ ይናገራል። ይህ ታሪክ እንኳ አሁን አሁን አየተበረዘ ሶስቱም ድውይ አልፈወሰም የጌታ ብቻ ነው የፈወሰው ከዛም ከጌታ መስቀል ላይ እሌኒ ቆርጣ ወስዳለች የሚል እንግዳ ትምህርት አምጥተው ሰንቅረዋል። ይህም ከጌታ መስቀል ውጪ ማንኛውም ክርስቲያን የሚይዘው መስቀል ምንም ጥቅም የለውም ወደሚል ስህተት ይመራል። ዞሮ ዞሮ የመስቀሉ ቁራጭ አለን የሙሉት አካላት የወሰዱት የመስቀል ቁራጭ በግራና በቀኝ ተሰቅለውበት የነበረው መስቀል ቁርጥራጭ መሆኑን ስላወቁ ለመደበቅ ነው። ወገኔ የጌታ ደም የነጠበበትን የጌታ ደም የወዛውን የጌታ ደም ያረሰረሰውን መስቀል ማን ነው ደፍሮ የሚቆርጠው?? ወዳጄ ስማኝ ታሪክህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ ለበረከት እያሉ አግባብ በሌለው መንገድ መስቀልን ቆራርጠው የተከፋፈሉት የፈያታዊ የማንን እንጂ የሐዲስ ኪዳን ታቦት ምሳሌ ሆኖ ቅዱስ ስጋና ደም የተፈተተበትን ቅዱስ መስቀል አደለም።ይህ ቁርጥራጭ ቀድሞ ለኢትዮጵያም ደርሷታል እስካሁን ድረስም በኤርትራ ገዳም ውስጥ አለ። አለም ይህን አምኖ መቀበል ቢያቅተው ኢትዮጵያ የቅዱስ መስቀል መንበር መሆኗን መቀበል እንቅ እንቅ ቢያረጋቸው በግብፃውያን ሴራ የኛን ታሪክ ሸፍነው የነሱን ፈጠራ በጎረቤት ነገረውን ለኛው የውሸትን ታሪክ አሳመኑን። ይህን ስል ያለ ማስረጃ ያለ ጥናት አደለም ከበቂ ማስረጃና መረጃ ጋር በማስደገፍ እንጂ እሱን በክፍል ሁለት አንድ ባንድ እንመለከተዋለን። ዛሬ የቅዱስ መስቀሉን ታሪክ ለማጥፋት እንዲህ የሚጥሩት ነገ ደሞ ወደ ታቦተ ፅዮን መዞራቸው አይቀሬ ነው ። ክፍል ሁለት ከማስረጃ ጋር እስከመለስ መልካም ጊዜ።
@ethio81
@ethio81
@ethio81

Читать полностью…

ዮቶድ

Watch "አበባየሆሽ - እንቁጣጣሽ - Abebayehosh - Enkutatash ልዩ የበአል መዝሙር - Ethiopian new year mezimur" on YouTube
https://youtu.be/zTgsA5F7rLk

Читать полностью…

ዮቶድ

ዝክረ ዘርአ ያዕቆብ.....#share

*ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ.በረራ (አዲስአበባን) የቆረቆሯት የቀዳማዊ ዳዊት አራተኛ ልጅ ነው።የተወለደው ፈጠጋር ውስጥ ጥልቅ ከሚባለው ሥፍራ ነው።ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ዘንድ ተምሯል።በግሼን ብሉይና ሐዲስን መጻሐፍት ትርጓሜ በመማር እንዲሁም ሲኖዶስን በማጥናት አሳልፏል።

*.በ1426 ዓ.ም ዐፄ አምደ እየሱስ ሲያርፍ በግዝት ከነበረበት ግሽ አምጥተው ተጉለት ውስጥ "ደጎ"ላይ "ዐፄ ቆስጠንጢኖስ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ "ብለው አነገሡት።
ዐፄ ዘርዓያዕቆብ በነገሠ በሰባት ዓመቱ ከአምሐራ መጥቶ ተጉለት ውስጥ እጉባ በሚባል ቦታ ከተመ።ሰሜን ሸዋ ሰላ ድንጋይ የምትገኘውን ደብረ ምጥማቅ ያሰሯት በዚህን ጊዜ ነበር።የአሕመድ በድላይን አመጽ የሰማውም ታኅሣሥ 21 ቀን በደብረ ምጥማቅ የእመቤታችንን በዓል እያከበረ እያለ ነበረ።(Les chronuques da zar'a Yaeqob et de Ba'ede maryam,88፤ encyclopedia Aethiopica,vol.ll,34-35)

*በዐፄ ዘርአ ያዕቆብ 3 ሃይማኖታዊ ችግሮች ነበሩ።እነርሱም፦

ሀ~ኤዎሳጣቴዎሳውያን፦ ቅዳሜን እንደ እሁድ ካላከበርን የሚሉ፣

ሁ~ደቂቀ እስጢፋ፦ቀደም ብሎ በዐፄ ያግብዐ ጽዮን ዘመን የነበረውን ጭቅጭቅ እንደገና አንሥተው ለሰውና ለማላእክት፣ለሥዕል እና ለመስቀል አንሰግድም የሚሉ እና

ሂ~ዘሚካኤላውያን፦አምላክ መንፈስ እንጂ እንደፍጡር መልክ የለውም የሚሉ ናቸው።

*.ዐፄ ዘርያ ያዕቆብ መጽሐፍ አዋቂና ለሃይማኖቱ ቀናተኛ ከመሆኑ ባሻገር እነዚህ ሰዎች ሕዝቡን በተለይም መንግሥቱን የሚከፋፍሉት መስሎት ትልቅ ሥጋት አደረበት።ጉዳዩን ትኩረት በመስጠት ከኤዎስጣቴዎሳውያን ጋራ የቅዳሜን መከበር ፈቅዶ ሌሎቹን ግን በካህናት በጉባኤ እየሰበሰበ ስሕተታቸውንአሳያቸው፤አስፈረደባቸው፤አጠፋቸው።ተዓአምረ ማርያምን ወደ ግዕዝ አስተረጎመ።በዓመት 33 ቀኖች በቅድስት ማርያም ስም ዓመት በዓል ሆነው እንዲከበሩ ዐወጀ።እምነቱን የሚያንጸባርቁ ብዙ መጻሕፍትንም ደረሰ፤ዋና ዋናዎቹ መካከል፦

1.መጽሐፈ ብርሃን፣ 7.መጽሐፈ ሚላድ፣
2.መጽሐፈ ሥላሴ፣ 8.መጽሐፈ ባሕርይ፣
3.ተዓቅቦ ምሥጢር፣ 9.ጦማረ ትስብእት፣
4.ስብሐት ፍቁር፣ 10.መልክአ ፍልስታ
5.ተአምራተ ማርያም 11. ድርሳነ መላእክት....
6.እግዚአብሔር ነግሠ

*በእግዚአብሔር ነግሠ ግጥም ውስጥ ይኩኖ አምላክን፣ዐምደ ጽዮንን እና ቴዎድሮስን ያነሳል።
"የባህር ዕንቁ ለሆነው፤
ምርጡን ይኩኖ አምላክን ሰላም እላለሁ።
ኢትዮጵያን እንደ ፀሐይ አበራት።
ጌታ ሆይ ከአሸበረቀችው ሀገርህ፥
የበጉ ውበት ከሚያበራባት አስገበው።"

*በሰሜን እስከ ምፅዋ ደሴት በምሥራቅ እስከ ዘይላ ወደብ አመፀኞችን ዘምቶ ስላስገበረው ዐምደ ጽዮን እንዲህ ሲል ገጥሞለታል።
"የአመፀኞች ጎማጅ የሆነውን፥
ዐምደ ጽዮንን ሰላም እለዋለሁ።
በሁሉ ቦታ አብያተ ክርስቲያናት ሠራ፤
ንግሡን ለአምላክ በትክክል ባስገዛ ጊዜ፥
ከባሕር እስከ ባሕር ፈረሱን አስኬደ።"

7.ዐፄ ዘርአ ያዕቆብ ዋና ሥራ የኢትዮጵያን የቤተመንግስት የሹም ሽር አወቃቀር፥ የፍርድ ስርአቱን ማሻሻል እና ወታደራቸውን በዝርዝር መከፋፈል ነበር።በዝርዝር የተከፈሉ ወታደሮች ስማቸው፦

1.በፀር ዋጀት፣ 11.በድል ደመና፣
2..በድል ሾተል፣ 12.በፀር ሾተል፣
3.ድብ ምልዓት፣ 13.ዣን ምልዓት፣
4.በድል መብረቅ፣ 14.በድል መስቀል፣
5.በአዳል ዣን፣ 15.አቄት በአምባ፣
6.በአዳል ዋዠት፣ 16.ጸመና አምባ፣
7.በባሕር ዋገት፣ 17.በአዳል መብረቅ፣
8.ዣን አሞራ፣ 18.ዣን ጸገና፣
9.ዣን ገደብ 19.ዣን ቀንጠፋ...

*በዚህ በተደራጀ ፈረሰኛ እግረኛ ባለጦር፥ባለቀስት፥ ባለ ሰይፍ ጀሌ ዐፄ ዘርዓያቆብ የዓምደ ጽዮንን የአገር ግምባታ ፖሊስና ተግባር የበለጠ በማጠናከር አገሮችንና ክፍለ ሀገራትን በሙሉ በአንድ ማዕከላዊ መንግሥት ስር አደራጀ፥በዘመኑ የቀይ ባህር የዳህላክ ደሴት፣በአዴን ባህረሰላጤ የዜላ ወደብ ጨምሮ በአፍሪካ ቀንድ በአዴን ባህረሰላጤ ጠረፍና በሕንድ ውቅያኖስ ዳርቻ የበርበሮች ምድር ጨምሮ በማዕከላዊ መንግሥት ሥር አደረገ።የአዳሎችን በድላይ ተዋግቶ አሸነፋቸው።

*ዘርዓ ያዕቆብ የቤተክርስቲያን ሥርዓት አቋቁመዋል፣የሳታት ጸሎት አስጀምረዋል፣መካነ ጎልጎታ፤መካነ ማርያምን፤በሰሜን ሸዋ የሚገኘው ደብረ ብርሃን ሥላሴ፣በሰሜን ሸዋ ተጉለት ይገኝ የነበረው ደብረ ምጥማቅ፣በአምሐራ ዳሕያ በሚባል ቦታ የመሠረተው ደብረ ነጎድጓድ አሠርተዋል።

*በሰሜን ሸዋ ተጉለት ይገኝ የነበረው ደብረ ምጥማቅ የተሰራችው በዚህ ምክንያት ነበረ።ላይላይ ግብፅ ክርስቲያኖቹ ሰንደፋ ከሚባል ቦታ ደብረ ምጥማቅ(ዴር አል-መግጠስ) በምትባል ቦታ ላይ በሡልጣን በርስበይ (1422-1438) ትእዛዝ ቤተ ክርስቲያኗን አፈረሷት።የዘመኑ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስ (1422-1438) በክርስቲያኖቹ ላይ የደረሰባቸውን በደል ለዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ላኩበት።ዘርዓ ያዕቆብ ለሡልጣኑ "አዚህ ኢት ያሉትን እስላሞች ማንም አይነካቸውም።ሌላው ቀርቶ እንደ ሌላው ሕዝብ ግብር እንኳን አናስገብራቸውም እናንተ ግን የሃይማኖት ነፃነት ትገፍፋላችሁ"የሚሉ ቃላትና ሡልጣኑ የማይሰማ ከሆነም ለመበቀል እንደሚችል የሚያመላክት ጠንካራ ደብዳቤ ጻፈለት።ለግብጻዊያን ክርስቲያኖች ማጽናኛ ትሆን ዘንድም በፈረሰችው ቤተ ክርስቲያን ስም እዚህ ኢትዮጵያ እጉባ ላይ "ደብረ ምጥማቅ" የምትባል ቤተ ክርስቲያን ሠራ።በዚያ ላይ በዚያን ጊዜ የአደሉን ንጉሥ በድላይን ድባቅ መምታቱ በክርስቲያኑ ዓለም ስለተሰማ ሡልጣን ጀቅማቅ ተደናግጦ ከሊቀ ጳጳሳቱ ጋር ቶሎ ታረቀ።(ጌታቸው ኃይሌ,ደቂቀ እስጢፋኖስ፣52-53)

*ባጠቃላይ ዐፄ ዘርዓያዕቆብያ ስርዓትና ደንብ"፣የመንግስት አወቃቀር፣የጦር አደረጃጀት፣የሹማምንት አሿሿምና ተግባር፣የመንፈሳዊ ክብረ በአላትና የጸሎት አይነቶችን ጨምሮ፤በርካታ ነገሮች ከነበሩበት ጨምረውና አሻሽለው በ34 አመታቸው ልክ በዛሬዋ ቀን ጳጉሜ 3 ቀን 1460 ዓ.ም. አረፉ።በኋላ ላይ አስክሬናቸው በጣና ሐይቅ ደሴተ ዳጋ እንዲያርፍ ተደርጓል

@ethio81
@ethio81
@ethio81

Читать полностью…

ዮቶድ

++ ዛሬ ነገ ነው? ++

‘‘አባዬ ዛሬ ነገ ነው?’’ አለ አቡሽ አባቱን ከተኛበት እየቀሰቀሰ

አባት እየተበሳጨ ‘ምንድን ነው የምትለኝ?’ አለ፡፡
ልጅ ‘ዛሬ ነገ ነው ወይ?’
አባት እንቅልፉ ስላልቀቀው ‘ሂድና እናትህን ጠይቃት በቃ ልተኛበት’ አለና እየተበሳጨ ፊቱን ሸፈነ፡፡

ልጅ ወደ እናት ሔዶ ያንኑ ጥያቄ ደገመላት
‘’እማዬ ዛሬ ነገ ነው?’’ እናት ፈገግ አለች
‘ምን ማለት ነው ደግሞ ዛሬ ነገ ነው? ማለት?’’ አለች የልጅዋን የተጋለጠ ደረት እየሸፈነች
‘ትናንት አስተማሪያችን ‘ነገ ትምህርት የለም’ ብላን ነበር ፤ ዛሬ ነገ ነው?’’
እናት ‘እ እ አዎ ልክ ነህ ዛሬ ነገ ነው’ አለች እየሳቀች፡፡

ይህ ለሕጻኑ ጥያቄ የተሰጠ መልስ ለእኛም ሳያስፈልገን አይቀርም፡፡ ብዙዎቻችን የምንኖረው ለነገ ነው፡፡ ለነገ እንማራለን ፣ ለነገ እንሠራለን ፣ ለነገ እንገነባለን፡፡ የተፈጠርነው ለዘላለማዊነት ነውና እንደምንኖር አስበን ማቀዳችን ባልከፋ፡፡ ነገር ግን ላላየነው ነገ ስናስብ ያየናትን ዛሬ እንዘነጋታለን፡፡ ለነገ ደመና የዛሬን ፀሐይ እንገፋታለን፡፡ እንዳቀድን እንዳለምን ለመኖር ስንዘጋጅ እንሞታለን፡፡ መጽሐፍ ‘’ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ፥ ተመልከቱ፥ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና’ ‘ነገ ለራሱ ያስባልና ለነገ አትጨነቁ! ይላል፡፡ /ያዕ 4፡15 ፤ ማቴ 6፡34/

ሰይጣን ከሚጠቀምበት ሰውን ማጥቂያ መሣሪያም አንዱ ‘ነገ’ በሚል ቃል ማዘናጋት ነው፡፡ ነገ እማራለሁ ፣ ነገ እሔዳለሁ ፣ ነገ የታመመ እጠይቃለሁ ፣ ነገ ንስሓ እገባለሁ ፣ ነገ ወደ እግዚአብሔር እመለሳለሁ ፣ ነገ ይሄንን መልካም ነገር እሠራለሁ ነገ ነገ ነገ
ፈርኦን የሚባለው ጨካኝ ንጉሥ በመቅሠፍት ጓጉንቸር ተወርሮ ነበር፡፡ በመጨረሻም እስራኤልን እለቃለሁ ሲል ሙሴ ፦ ጓጉንቸሮቹ ከቤትህ እንዲጠፉ መቼ ልጸልይልህ? አለው፡፡ ፈርኦንም ፦ ነገ አለ፡፡

እንግዲህ ዛሬን ከጓጉንቸሮች ጋር ማደር ፈልጓል ማለት ነው፡፡ ወዳጄ በሕይወትህ ውስጥ ጓጉንቸሮች ምንድን ናቸው? ምን ዓይነት ክፉ አመል አለብህ ፣ ምን ዕረፍት ያሳጣህ ፣ ሰላም የነሳህ ነገር አለ? አልላቀቅ ያለህ ሱስ ፣ አልስተካከል ያለህ ድክመት ፣ አልድን ያለህ ቁስል ምንድን ነው? እርሱን መቼ ትላቀቀዋለህ? መቼ መዳን ትሻለህ? ነገ ካልከኝ ፈርኦን መሆንህ ነው? ‘አቤቱ አሁን አድን’ ካልክ ደግሞ እንደ ዳዊት ትሰማለህ

ነገ ይህንን ሱስ እተዋለሁ ፣ ነገ ይህን ልማድ እላቀቃለሁ ፣ ነገ ይህን መልካም ነገር አደርጋለሁ የሚል ቀጠሮ ሠርቶ አያውቅም፡፡ ነገ እንላለን እንጂ የሚገርመው በማግሥቱም መልሳችን ነገ ነው፡፡ ‘ዱቤ ዛሬ የለም ነገ ነው’ እንደሚለው የብልጥ ባለሱቅ ማስታወቂያ ነገ ስንሔድ ነገ እየተባለ የምንፈልገውን ሳንሠራ የማንፈልገውን እየሠራን እንኖራለን፡፡ ወዳጄ ነገ የአንተ አይደለችም ‘የተወደደው ሰዓት አሁን ነው’ መኖርህን ሳታውቅ ቀጠሮ አትሥጥ፡፡ ኃይልህ በአሁን ላይ ብቻ ነው፡፡ ማንም ሊሠራባት የማይችላት ሌሊት ሳትመጣ አሁንን ተጠቀምባት፡፡

አሁኑኑ ተነሥ ያሰብከውን መልካም ነገር ለመሥራት ፣ ክፉውን ነገር ለመተው ነገ አደርገዋለሁ አትበል
ትናንት ኅሊናህ ሲጠይቅህ ‘ነገ አደርገዋለሁ’ ብለህ ነበር ፤ ዛሬም ‘ነገ’ አትበል ምክንያቱም ሕጻኑ እንዳለው ‘ዛሬ ነገ ነው’

ዲያቆን natinael Solomon

@ethio81
@ethio81
@ethio81

Читать полностью…

ዮቶድ

Watch "ስለ ድንግል ማርያም ክብር - በመምህር ምህረተአብ አስደናቂ አስተምህሮት - memehir mihreteab asefa" on YouTube
https://youtu.be/XgCrLeonAAg

Читать полностью…

ዮቶድ

ይኩኖ አምላክ.....

*ይኩኖ አምላክ የአማርኛን ቋንቋ ብሄራዊ ቋንቋ እንዲሆን በይፋ ያወጀ፥ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥትን ያስቀጠለ የአማሮች አባት ነው።ይኩኖ አምላክ ከዛግዌ ዘመነ መንግሥት በኋላ በስደት የቀጠለው የአኩስም መንግሥት ዘር ነው።በስደት የቀጠለው የአኩስም ዘር፦

1.ማኅበረ ውድም

2.አግብአ ጽዮን

3.ጽንፈ አርአድ

4.ነጋሽ ዛሬ

5.አስፍሕ

6.ያዕቆብ

7.ባሕር አስገድ

8.እድም አስገድ

9.ተስፋ ኢየሱስ

10.ይኩኖ አምላክ ናቸው።

*ከላይ የዘረዘርናቸው የአኩስም ነገሥታት የአንበሳ ውድም የልጅ ልጆች በድልነዓድ ዘመነ መንግሥት ሥልጣን ወደ ሮሐ ከተዛወረ በኋላ የአገው ነገሥት 330 አመት ኢትዮጵያን ሲገዙ  በስደት በተለይም በመንዝ በዱርና በዋሻ እየተደበቁ ዘመናትን አሳልፈዋል።

*የቤተ አምሓራ-አምባሰል ገዥ የነበረው እድም አስገድ ገድለ አቡነ ዜና ማርቆስ ላይ እንደተገለጠው የወግዳ ገዥ የማቴዎስን ልጅ እምነ ጽዮንን አግብቶ  መቆናኛ (ሰገራት) ሲኖር ቀስውጦስ፣ተስፋ ኢየሱስን፣ገብረ ክርስቶስን፣
እና ሴት ልጃቸውን ማርያም ዘመዳን ወለደ።ቀስውጦስ በስብከተ ወንጌል ተሠማራ፥ገብረ ክርስቶስ ዘቢታንያን የዳግና ገብረ ክርስቶስ ገዳም መሠረተ፥ማርያም ዘመዳ ታዋቂውን አቡነ ዜና ማርቆስ ወለደች።

*ተስፋ ኢየሱስ የቤተ አምሓራ ገዥ ለነበረው አዛዥ ክላ አገልጋይ ነበረ።ተስፋ ኢየሱስ ይኖር የነበረው ሰገራት ውስጥ መሆነኛ ሲሆን ይኩኖ አምላክ የተወለደውም ከዚሁ መሆነኛ ልዩ ቦታው "ፍላጎ"ከተባለች ቦታ ላይ ነው።የአቡነ ኢየሱስ ሞዓ ገድል ይኼን ያረጋግጣል።አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ከይኩኖ አምላክ ጋርም ይዛመዳሉ።

*መሆነኛ የሚባለው አካባቢ ከኩታበር ከተማ በስተደቡብ ያለው ተራራ ነው።ዛሬም ዛሬም "ቤተ መንግሥት፣አማራ ሰፈር፣ አማራ መስፈሪያ፣ አማራ ካብ"በመባል የሚጠሩ ሰፈሮች አሉ፡፡“ሰገራት” ደግሞ አሁን ከኩታበር ሰሜን ምእራብ አቅጣጫ የሚገኝ አካባቢ ነዉ፡፡ ከየቁንባ ጀምሮ እስከ ንፋሳት ገደማ ሰገራት በመባል አሁንም ይጠራል፡፡

*ይኩኖ አምላክ ነአኩቶ ለአብ ደግፎ ስለተዋጋ በይትባረክ መሎጥ ላይ ታስሮ ከእስርቤት ቤት ከአመለጠ በኋላ ወደተማረበት ሐይቅ ገዳም መምህር ኢየሱስ ሞዓ ዘንድ መጥቶ በዚያም የቤተ አምሐራን ሕዝብ አደራጅቶ ከፍተኛ ትግል በማድረግ የዛግዌውን ይትባረክን ሐምሌ 7 ቀን 1263 ዓ.ም.ጣና አካባቢ ጦርነት ገጥሞ ከአሸነፈው በኋላ በአማራ ግዛት በምትገኘው ግሼን  ላይ በሺህ የሚቆጠር ሕዝብ በተገኘበት በ1263 ዓ.ም.ነገሠ።

*ጉሣዊ ርዕሳቸውም "ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ" ተባለ፥ ስማቸው ዐፄ  ይኩኖ አምላክ በሚል የግዕዝ ስም ተሰጣቸው፥ትርጓሜው "አምላክ ጠባቂና ረዳት ይሁነው"ማለት ሲሆን መንግሥቱም ከሮሐ ወደ ተጉለት፣ከዛግዌ ወደ ቤተ አምሐራ ፣ከነአኩቶ ለአብ ወደ ይኩኖ አምላክ ተዛወረ።

*ይኩኖ አምላክ በወርቅ ዙፋን ሲቀመጥ የዛግዌ ዘር መስፍን በብር ዙፋን አስቀምጦ ከግብር ነጻ በማድረግ በላስታና በዋግ ሾማቸው።ይኩኖ አምላክ የመጀመሪያ መናገሻውን ያደረገው አማራ ሳይንት  ተድባበ ማርያም አካባቢ ደብረ ታቦር ተራራ ላይ ሲሆን በዛግዌ ዘመነ መንግሥት የሠራዊቱና የሕዝቡ ቋንቋ የነበረውን አማርኛን በይፋ ብሔራዊ ቋንቋ እንዲሆን አወጀ።ከዚህ ዘመን ጀምሮ አማርኛ ቋንቋ በሥነ ጽሑፍ ሕዳሴው ዘመን የበለጠ ተስፋፋ፤የመንግሥትገዥዎች፥አስተዳዳሪዎች፥የጦር መሪዎች እና አስተማሪዎች የማዕረግ ስማቸው በአማርኛ ሆነ።            

*ለዐፄ ይኩኖ አምላክ ወደ ሥልጣን መምጣት ቁልፍ ሰው የነበሩት አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ናቸው።ከእርሳቸው ሲማር እውቀትና እውቅና አግኝቷል።በኋላም ከመሎጥ እስርቤት አምልጦ አማራን ማደራጀት የጀመረው ሐይቅ ላይ ነበረ።ይህን የሐይቅ ገዳም ውለታ ለመመለስ ይኩኖ አምላክ አምስት ዐንቀጽ ያለው ዐዋጅ ዐውጆ ነበር።ይህም ዐዋጅ፦
1.የንጉሥ ደብዳቤ ሲላክ መነኮሳቱ ተቀምጠው እንዲሰሙ
2.በተሰጠው ጉልት የነገሥታቱ ልጆች እንዳይገቡበት፣
3.ገዳሙ የተማጽኖ ገዳም እንዲሆን
4.የገዳሙን ርስት ማንም ትውልድ ቆጥሮ እንዳይካፈለውና
5.መነኩሴ ላልሆነ ሰው የገዳሙ ርስት እንዳይሰጥ የሚገልጡ ናቸው።በዚህም ምክንያት ዐቃቤ ሰዓትነት እስከ 16ኛው መክዘ አጋማሽ ድረስ በሐይቅ እስጢፋኖስ አበ ምኔቶች እጅ ቆይቷል።ዐቃቤ ሰዓትነት በቤተመንግሥት ክሀነቱ ጉዳዮች ላይ የመወሰንና የንጉሡን የመገናኛ ሰዓት የመወሰን ሥልጣን ነበረው።

*ይኩኖ አምላክ እንደነገሠ ከየመንና ከግብፅ ሡልጣኖች ጋር ግንኙነት አድርጓል።በግብፅ ሳራካኖች የየብስና የባህር መተላለፊያዎች ሲዘጉ ከ1250 ዓ.ም.ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ ጳጳስ ባለመምጣቱ ጳጳስ እንዲላክላቸው በነገሡበት አመት በ1263 ዓ.ም.ለግብፅ ሡልጣን ባይባራስ (1253-70 ዓ.ም) በየመኑ ገዥ አል ማሊክ አል ሙዘፋር በኩል ደብዳቤ ልከው እንደነበር ተረጋግጧል።የየመኑ ገዥ ደብዳቤውን ወደ ካይሮ ልኮ የይኩኖ አምላክን መልእክተኞች ግን በየመን አቆያቸው።በዚህም ምክንያት ባይባራስ ደብዳቤው እንጂ ጉዳዩን የሚያስረዱ መልእክተኞች አልመጡም ብሎ መልሶታል።

*ይኩኖ አምላክ ኢትዮጵያ ጳጳስ እንዲኖራት ከነበራቸው ከፍተኛ ጉጉት የተነሳ እንደገና በኢየሩሳሌም በኩል ወደ አንጾኪያ-ሶርያ እና ለቆስጥንጥንያው ንጉሥ ሚካኤል ፓሌዎሎግ 8ኛ ከቀጭኔ ገጸ-በረከት ጋር ደብዳቤ መላካቸው ታውቋል።ይኩኖ አምላክ ወደ ካይሮ፥ሶርያ እና ቆስጠንጢኒያ የላኩት ደብዳቤ ምንም እንኳን አንዳንድ መረጃዎች ከአንጾኪያ ጳጳስት ተልኮላቸዋል ቢሉም በልጃቸው ዐፄ ውድም ረዓድ በ1306 ዓ.ም.መጨረሻ ከእስክንድርያ  አቡነ ዮሐንስ ሁለተኛ የተባሉ ጳጳስ ተልኳል።

*ይኩኖ አምላክ በውጭ ግንኙነት በኩል እንደልፋታቸው ጳጳስ ባይመጣላቸውም በላሊበላ አቅራቢያ የጨረቃ ተራራ በመባል በሚታወቀው አቡነ ዮሴፍ ተራራ ላይ  ቋጥኝ አስፈልፍለው ያሳነጿት ገነተ ማርያም መታወቂያቸው ናት።ደጇፏ ላይም የይኩኖ አምላክ ፊርማ እና የእጅ ጽሑፋቸው ይገኛል።በኋላም ቤተ መንግሥቱን ከሳይንት ወደ ተጉለት እንዳዛወሩት ታውቋል።አንድ መግቢያ በር ያላት ተጉለት (ሰወን፥ጸወን፥ማረዴ)፣መንዝ የአኩስም ነገሥታት መደበቂያ፥የዐፄ ልብነ ድንግል ልጅ አቤቶ ያዕቆብ መሸሸጊያ በጥቅሉ የአማርኛ መዳኛ ቁልፍ ቦታ ናቸው።ተጉለት የዐፄ ዓምደ ጽዮን፥ዐፄ ይሥሐቅና የሌሎችም የአማራ ነገሥታት መቀመጫም ነበረች።

*ዐፄ ይኩኖ አምላክ በጥቅሉ ሲገለጥ ሐይቅ ገዳም ተማረ፥የአማራን ሕዝብ አደራጅቶ የዛግዌውን ይትባረክ ከሥልጣን በማስገወድ ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥትን ሐምሌ 7 ቀን 1263 ዓ.ም.አስመለሰ፥የአማርኛን ቋንቋ ብሔራዊ ቋንቋ እንዲህን በይፋ አወጀ፥ወደ ግብፅ፥ሶርያና ቆስጠንጢንያ ደብዳቤ ላከ፥ገነተ ማርያምን አሳነጸ፥ቤተ መንግሥቱን ወደ ተጉለት አዛወረ፥ያግብዐ ጽዮንን ወለደ፥በመጨረሻም ሰኔ 16 ቀን 1277 ዓ.ም.ሞተ።ዐጽመም በዐፄ በዕደ ማርያም ዘመን በ1461 ዓ.ም.ተወስዶ አትሮንስ ማርያም አረፈ።

ዋቢ፦
1.ገድለ አቡነ ዜና ማርቆስ
2.ገድለ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ
3.ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፣ባሕረ ሐሳብ፣232-233
4.ዳንኤል ክብረት፣የቤተ ክርስቲያን መረጃዎች፣48-49፣አራቱ ኃያላን,፣70

👉እርሶ ያወቁትን እውቀት ሌሎች ያውቁ ዘንድ ቻናላችንን ሼር በማድረግ ጓደኛዎን ይጋብዙ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇 👇👇👇👇👇
@ethio81
@ethio81
@ethio81

Читать полностью…

ዮቶድ

https://vm.tiktok.com/ZMRBQ85Gy/

Читать полностью…

ዮቶድ

💚💛❤️
ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ፥
ኢትዮጵያ ፦ ከቃሉ ፍቺ ለአምላክ የሚሰጥ ቢጫ ወርቅ/ ልዩ ወርቅ ማለት ነው፡፡ በርግጥ የውጪ ሰዎች የተቃጠለ ፊት ብለው ተርጉመውታል፡፡
ኢትዮጵያ ተዘርዝሮ ከማያልቅ ድርሳኗ በጣም በጥቂቱ ፦ ለሙሴ ጥበብን ያስተማረ የዮቶር አገር ፣ የሙሴ ሚስት የዮቶር ልጅ የሲጳራ አገር ፣ የመጀመሪያው ካህን የመልከጼዴቅ አገር ፣ ኖኅ ራሱንና ልጆቹን ከንፍር ውኃ ያዳነበት መርከቡን ያሳረፈበት የአራራት ተራራ መገኛ ፣ አፍሪካን ከጫፍ እስከ ጫፍ ኢትዮጵያ ብላ ትገዛ የነበረች የንግሥት ኢተያ አገር ወዘተርፈ ብለን ልንናገርላት የምንችልላት አገር ነች፡፡
💚💛❤️
ኢትዮጵያዊነትስ ?

@ethio81
@ethio81

Читать полностью…

ዮቶድ

Watch "የጥምቀት መዝሙር 2013 ክፍል 1- Ye Timket Mezimur - New Ethiopian Orthodox Tewahido mezimur 2021 Part 1" on YouTube
https://youtu.be/s0n6Qe3PEew

Читать полностью…

ዮቶድ

➛➛ሀገር እንወዳለን➛➛
━━━━━━━✦✗✦━━━━━━━━
━━✦እጅግ ድንቅ እይታ ናት አድምጧት!
Ye Daniel kret iyetewachi kemil yete wesede
━━━━━━✦✗✦━━━
━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
@ethio81
@ethio81
@ethio81

Читать полностью…

ዮቶድ

ዮቶር ማን ነው?
የሰው ልጆች ጥበብ ፣ ባህል፣ እምነት እና ታሪክ ለአንድ
ሀገር ዘላቂ እድገት እና ለውጥ የህልውና መሰረቶች
ናቸው። ዘመን ተሻጋሪ የሆነ አኩሪ ባህል እና ታሪክ ያለው
ህዝብ በእያንዳንዱ ቀጣይ ስራዎቹ ጀርባ የብርታትና
የአብሮነት መንፈስን በማጎናጸፍ በተሰማራበት የህይወት
መስክ ሁሉ የስኬት ምንጭ ናቸው። ታሪክ የሌለው
ህዝብ መነሻ የሌለው ነው። መነሻውን የማያወቅ ደግሞ
መድረሻው ምን መሆን እንዳለበት ለመወሰን
ያዳግተዋል። “የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ፣” አይደል
የሚባለው? ኪነ-ጥበብ ደግሞ ጠቅለል ባለ መልኩ
ስንገልጸው ልክ እንደ መስታዎት ፍንትው አድርገው
የሕዝብን ሁኔታ፣ የአኗኗር ዘይቤን ፣ ባህልን፣ ፍቅርን፣
ብሶትን፣ አንድነትንና ታሪክን በተከሽኑ ህብረ -ቀለማት
እና ዜማዎች አዋህዶ በማቅረብ ማንነትን ማሳየት እና
መስበክ፥ ሰውንም ያለጉልበት ማሳመን የሚችል ነው።
ወደ አነሳሁት ርዕስ ልመለስ፡ ዩቶር ማነው? ዩቶር
መጽሓፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኝ የሰው ስም ነው።
“ዮቶር” /ራጉኤል/ የተባለው ሰው ኢትዮጵያዊ ሲሆን
በጊዜው የጣና ሀይቅና የአባይ ዙርያ አካባቢ መጠርያ
ስም “ሞርያም” ይባል ነበር። ዮቶርም የሞርያም ካህን
ነበር በዚህ ጊዜ ሙሴ ከግብፅ ከፈርኦን ፊት ወደ
ኢትዮጵያ /ሞርያም/ ምድር መጥቶ ይቀመጣል።
7 ሴት ልጆች የነበሩት ዮቶር ከአባይ ወንዝ ከብቶችን
ውሃ እንዲያጠጡ ልጆቹን ሲልክ ሙሴን አግኝተው
ይመለሳሉ። ሙሴና ዮቶር ሲገናኙ ደግሞ ዮቶር ሲፓራ
የተባለችውን ሴት ልጁን ለሙሴ ይድርለታል ….ሁለት
ልጆችንም ወለደ፡፡ አልዓዛር እና ጌርሳምን ኦሪት ዘጸአት፡
18፥ 3-4። ኢትዮጲያዊው ካህን ዮቶር እና ሙሴ አማት
እና አማች ሆኑ ማለት ነው።
ኦሪት ዘኁልቅ 12፥1፡ ላይ እንዲህ የሚል ቃል ይገኛል
‹‹ሙሴም ኢትዮጵያዩቱን አግብቷልና ባገባት
በኢትዮጵያዩቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በርሱ ላይ
ተናግሩ። እነርሱም በእዉኑ እግዚአብሔር በሙሴ ብቻ
ተናግሯልን፧ በእኛስ ደግሞ የተናገረ አይደለምን አሉ
እግዚአብሔርም ሰማ…

ሙሉውን ቃል ማንበብ ይቻላል።

ካህኑ ዮቶር ከዘመናት በኋላ የልጅ ልጆቹንና የሙሴን
ሚስት (ሲጳራን) ይዞ ሙሴን ሊጎነኘው ሄዷል፡፡ ሙሴም
ዕብራዊያንን ይዞ ከግብጽ ምድር ሥለወጣ እና ዮቶርም
እግዚአብሔርን ሊያመሰግን በተገናኙበት ጊዜ፤ ሙሴ
በዕብራዊያንን ላይ ተስፋ ቆርጦ እና ለማስተዳደርም
አስቸግረውት ሲሰቃይ፤ ሕዝብን የማስተዳደርን ጥበብ፣
ዘዴ እና ሥልጣኔ ዮቶር አስተምሮታል ኦሪት ዘጸአት፡
18፥ 14-26።
መሪው በእግዚአብሄር ፊት ለሕዝቡ ይቆማል
ሥርዓቱንም ሕጉንም ያስተምራል፤ ያሳያል
መሪውም ከሕዝቡ መካከል አዋቂዎችን
ይመርጣል፤ (እግዚአብሔርን የሚፈሩትን፤
የታመኑትን፤ የግፍንም ረብ የሚጠሉትን፤)
እነርሱንም አለቃ አድርጎ ይመርጣል
በሕዝብ ላይ ይፈርዳሉ፤ ከዚህ የበለጠውንም
(የከበዳቸውንም) ወደ መሪው ይወስዱታል፤
ለመሪውም ሸክሙን ያቀሉለታል…
ዮቶር ይህንን ጥበብና ሥርዓት ለሙሴ አስተማረው።
እንግዲህ እናስተውል፡ ሕዝብን የማስተዳደር ጥበብ
ግሪካዊያን የዲሞክራሲን ጽንሰ ሐሳብ ከመስበካቸው
በፊት፡ዮቶር /ራጉኤል/ ለሙሴ ሕዝብን በዲሞክራሲያዊ
ሁኔታ የማስተዳደር ጥበብ አስተምሮታል፤ ይህም የሆነው
ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት በሀገራችን መከናወኑን
ስናስብ ካህኑ ዩቶር ኢትዮጵያውያን የሰው ልጅ ስልጣኔ
ምንጭ መሆናቸው አስረጂ የሚሆን ታላቅ አባት ነበር።
ታሪኩ እንዲህ እያለ ይቀጥላል……

@ethio81
@ethio81
@ethio81

Читать полностью…

ዮቶድ

አዲስ የ ዮቶድ ቻናል you tube ተቀላቀሉ መዝሙር ,ስብከት

Читать полностью…

ዮቶድ

ጥያቄ
በመንገድ_ላይ_ስንጓዝ_ቤተክርስቲያን_እንሳለማለን_እና_ሚስጢሩ_ምንድን_ነው?
መልስ

መሳለም የሚለው ቃል ሰላምታ መስጠትን የሚወክል ቃል ነው፡፡ "ወደ ዘካርያስም ቤት ገብታ ተሳለመቻት" ሉቃ.1:40 እንዲል፡፡

በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ግቢ ከመግባታችን በፊት ወይም ከሩቁ መሳለም፦

✞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያለው ነው፡፡ "ወደ ቂሳርያም በደረሰ ጊዜ ወጥቶ ለቤተ ክርስቲያን ሰላምታን ከሰጠ በኋላ ወደ አንጾኪያ ወረደ፡፡" ሐዋ. 14:22 እንዲል፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ሰላምታ መስጠት ለቤተ እግዚአብሔር ያለንን ፍቅርና ክብር የምንገልጥበት ነው፡፡

✞ ቤተ ክርስተቲያን ሄደን በምንሳለምበት ጊዜ መላ ገጻችንን በትምዕርተ መስቀል አምሳል ነውና ወንጌልን እንሰብክበታለን፡፡ #ይሀውም_ከላይ_ወደታች_ስናደርግ_ወልደ_እግዚአብሔር_ከሰማየ_ሰማያት_መውረዱን_ከድንግል_ማርያም_መወለዱን_በምድር_መመላለሱን_ማስተማሩን_ሲያመለክት_ከግራ_ወደ_ቀኝ_ማድረጋችንም_በርደተ_መቃብር_ርደተ_ሲዖል_ሳለን_ጌታችን_በሞቱ_ከባርነት_ከሲኦል_ግራ_ወደ_ገነት_ቀኝ__ማስገባቱን_ድኅነተ_ዓለም_በወልደ_እግዚአብሔር_ሞት_መፈጸሙን_የምንመሰክርበት_ነው፡፡ ማቴ 10:32 ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንደዚህ በስርዓቶቿ ሳትናገር እንኳ ታስተምራለች፡፡

👉ቤተ መቅደሱን እንዲሁ በውስጡና በዙሪያው ያለውን የነካ ስለሚቀደስበት
“የቅብዐት ዘይትን ወስደህ ማደሪያውን በእርሱም ያለውን ሁሉ ትቀድሳለህ ቅዱስም ይሆናል” ሲል ለሙሴ አዞታል ዘጸ. 40፥9 እግዚአብሔር ቤተ መቅደሱና በዙሪያው ያሉ ሁሉ እንዲቀደሱ አዟል፡፡ደብተራ ኦሪት ሲተከል የሰሎሞን ቤተ መቅደስ ሲሰራ ዙሪያው በቅብዓ ቅዱስ ተቀድሷል የቤተ መቅደሱ ደጃፍ መሳለም መሳም የሚያስፈልገው ለዚህ ነው፡፡ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ ደጃፉ በቅብዓ ሜሮን የከበረ የተቀደሰ ስለሆነ የሚሳለመው የሚስመው የሚተባበሰው ሁሉ ይቀደሳል፡፡

👉ቤተ መቅደስ የክርስቶስ ማደሪያ ስለሆነ በሌላ በኩል ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካል ዘርፉ ልብሱ መቅደሱ ናት፡፡ ኤፌ. 5፥23፡፡ አካል ከራስ ጠጉር እስከ እግር ጥፍር ያለውን ሁሉ እንደሚይዝ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካል ናት ሲባል የቤተ ክርስቲያኑ አካል ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ ስለዚህ አካሉ የሆነችው ይህች ቤተ ክርስቲያን/ቤተ መቅደስ/ መሳለም መተባበስ የጌታችንን የልብሱን ዘርፍ በመንካቷ አስራ ሁለት ዓመት ሙሉ ደም ሲፈሳት ኖራ እንደተፈወሰችው ሴት የእምነት ጥንካሬ ምልክት ነው ሉቃ.8፥43-48፡፡በእምነት ለሚሳለም በእምነት ለሚኖር ሰው የቤተክርስቲያን ደጃፎቿ ዐጸዱ በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ያለው ጠበል አጥሩ ቅጥሩ ውስጡ ውጪው ሁሉ ፈውስና መድኃኒት ይሆነዋል፡፡

👉ቤተ መቅደሱ የመለኮት ማደሪያ ስለሆነ ቤተ ክርስቲያን/ቤተ መቅደሱ/ የመለኮት ማደሪያ ነው፡፡በሰማይ በክብር የሚኖር እግዚአብሔር በቤተ መቅደሱን በረድኤት ያድራል፡፡ ቤተ መቅደሱን የክብሩ መገለጫ አድርጎታልና፡፡ “አሁንም ስሜ ለዘለዓለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መርጫለው ቀድሻለውም ዐይኖቼና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ” 2ኛ ዜና./7፥16

“ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን” መዝ 131፥7 እንዲል ቤተ መቅደሱ የእግዚአብሔር ማደሪያ ስለሆነ ደጃፉ አጥሩ ቅጥሩ ሁሉ የተቀደሰ በበረከት የተሞላ ነው፡፡ ስለዚህ ወደ ቤተ መቅደስ የሚቀርብ ሰው ይህን እያሰበ ይሳለማል፡፡ ስለዚህ ሰው ሁሉ የቤተ ክርስቲያን ደጃፏን /ደጀ ሠላሟን/
“#ሠላም_ለኪ_ቤተ_ክርስቲያን_ማኅደረ_መለኮት_አምሳለ_ኢየሩሳሌም_ቅድስት_ተማኅጸነ_በታቦተ_እግዚአብሔር ”
(ቅድስት የምትሆን የሰማያዊ ኢየሩሳሌም አምሳል የሆንሽ የመለኮት ማደርያ ቤተ ክርስቲያን ሆይ ሠላምታ ይገባሻል) እያልን ደጃፏን አጥሯን የምንሳለመው፡፡

@ethio81
@ethio81
@ethio81

Читать полностью…

ዮቶድ

"ሰይጣን የማይነካው ዕቃ "

በአንድ ሐገር ድንገት የአንድ" ጠንቋይ ዝና ከዳር ዳር ተሰማ ። ሰውዬው የማያሳየው ምትሐት የለም። አንበሳ ላለ አንበሳ፣ ነብር ላለ ነብር፣ የሞተ ዘመዴን ላለ የሞተ ዘመዱን፣ የጠፋብኝን ዕቃ ከቤት ፈልገህ አምጣልኝ ላለ ዕቃውን ያመጣለታል። እንደሚታወቀው አጋንንት ከክብራቸው የተዋረዱ መላእክት ናቸው። መላእክት ደግሞ በፈለጉት ሁኔታ መገለጥ ይችላሉ። ይህ ጠንቋይ የሚሰጣቸውን ገጸ ባሕርይ ተቀብለው አንዴ አንበሳ፣ አንዴ ነብር፣ አንዴ ሰው እየሆኑ የሚተውኑት እንግዲህ አጋንንቱ ነበሩ

የዚህ ጠንቋይ ዝና ወደ ንጉሱ ደረሰ። ንጉሱ ደግሞ ክርስቲያን ቢሆንም ከመጸሐፍ ቅዱስ ይልቅ እንዲህ ያለ ተአምር እዚህ ቦታ ተፈጸመ ሲባል ለማየት የሚሮጥ ሰው ነበር። ተአምር የሚወድ ሰው ደግሞ ክርስቲያንም ቢሆን ሰይጣን በሚሰራው ምትሐት መታለሉ የማይቀር ነው። ስለዚህ ይህ ንጉስ የተማረውን መጽሐፍ ቅዱስ ዘንግቶ በጠንቋዩ ምትሐት አመነ

ይህንን የሰሙ የንጉሱ ንስሐ አባት ነገሩን ሰምተው ወደ ቤተ መንግሥት ሲሮጡ ደረሱ። ሲደርሱ ንጉሡ ከቁም ነገር አልቆጠራቸውም። እሱ የጠንቋይ ትርዒት ማየት ቀጠለ።
"እስቲ አሁን ደግሞ እእእ ነጭ ፈረስ አምጣልኝ" ማለቱን ቀጠለ በነገሩ ያዘኑት "ኧረ ንጉሥ ሆይ ይተዉ፡ ይህ እኮ የሰይጣን ምትሐት ነው " ብለው ሊያስረዱት ሲሉ በቁጣ አስቆማቸው።
ተአምር የሚከተል ሰው መቼስ ቢነግሩት አይሰማም። ጭራሽ እንዲያው ለንስሐ አባቱ እንዲህ አላቸው

" የሰይጣን ስራ ነው አትበሉ፤ ቅናት ነው ይኼማ,,,, ይልቅ እርስዎም የሚፈልጉትን ነገር ይጠይቁት ያምጣልዎት!"አላቸው።
ጠንቋዩ «የፈለጉትን ላምጣልውት,,,,,ምን ይፈልጋሉ,,,, " የሞተ ዘመድ አለዎት,,,,, ወይስ ከቤትዎ,,,, » አላቸው በኩራት።
ካህኑ ውስጣቸው በመንፈሳዊ ቅናት ተቃጠለ። « እንግዲያውስ የፈለኩትን ማምጣት ከቻልህ ወደ ቤተ መቅደስ ሔደህ ልብሰ ተክህኖዬ ውስጥ መስቀል አለ እርሱን ይዘህልኝ ና » አሉት

ይህን ግዜ ጠንቋዩ ገና ድግምቱን ሲጀምር አጋንንቱ እላዩ ላይ ሰፍረው ጣሉት።በካህኑ ፊት ወደቀ። ሰይጣን ምንም ነገር ማምጣት ይችል ይሆናል። መስቀሉን ግን ማምጣት አይችልም። አባቶቻችን ሰይጣን እንኳን መስቀል ቀርቶ መስቀለኛ መንገድም አይወድም ይላሉ

የጌታችን ቅዱስ መስቀል ሆይ ቅዱስ ዳዊት እንዳለ «ብከ ንወግዖሙ ለኩሎሙ ጸርነ»
«በአንተ ጠላቶቻችንን እንወጋቸዋለን!

✝✝✝ጥልን በመስቀሉ ገደለ✝✝✝

✝✝✝ መልካም በዓል✝✝✝
@ethio81
@ethio81
@ethio81

Читать полностью…

ዮቶድ

Watch "የመስቀል መዝሙሮች - Ye Meskel Mezimur" on YouTube
https://youtu.be/2aO0ZZLUSH4

Читать полностью…

ዮቶድ

🌼🌻🌻🌻🌻
ያለፈውን ስህተት ዛሬም እንዳትደግም
አመቱ ሊታደስ ሲመጣ መስከረም
ከስህተት መንገድህ የሀገሬ ሰው ታረም

🌼🌻 መልካም አዲስ አመት ፳፻፲፫🌼🌻

Читать полностью…

ዮቶድ

ስለቅድስት ቤተክርስቲያን ሲል ደሙን ያፈሰሰው ዲያቆን የወገን ያለ ድረሱልኝ እያለ ይጣራል
~~~~~~~~~~~~~~~~
ከቻሉ ይርዱን ፤ካልቻሉ ግን share በማድረግ ለሚረዱ ምዕመናን መልእክታችንን ያድርሱልን
~~~~~~~~~~~~~~~

ስሙ ዲያቆን ዘለዓለም ኤገዶን ይባላል። በአርባምንጭ ዙርያ ወረዳ የኦቾሎ ላንቴ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ ነው። በኦቾሎ ላንቴ ቀበሌ በቤተክርስቲያን የጥምቀተ ባህር የልኬት ክርክር ምክንያት አከባቢው ላይ የቤተክርስቲያን ፈተናዋ እጅግኑ ብዙ ናቸው። ይህኝህ ፈተናዎች ዛሬም ድረስ መቋጫ አልተገኘላቸውም ።የቤተክርስቲያን ምዕመናን ፅንፍ በያዙ የሌላ ቤተእምነት ሰዎች ቤት ንብረታቸው ወድሞ፤ስዕለ አድኖዎች ተቀደው፣የሙዳን ምፅዋት ሳጥኖች ተሰባብረው ከፍተኛ ውድመት ቅድስት ቤተክርስቲያን አሳልፏለች። በአንደኛው ውድቅት ለሊት ግን የመከራው ብትር በዲያቆን ዘለዓለም ኤገዶን ላይ ያርፍ ዘንድ ግድ ሆነ። ለእሁድ አጥቢያ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን ለአገልግሎት በሚሄድበት ሰዓት ማንነታቸው የማይታወቁ ግለሰቦች ተሰብስበው አቅደው አልመው እና ክፉ ሰዓት መርጠው በአሳች ስፍራ ክፉኛ ድብደባ አድርሰውበታም። በተደጋጋሚ ጭንቅላቱ ላይ በብረት በመመታቱ ምክንያት የራስ ቂል ስብራት እና ከፍተኛ የደም መፍሰስ ስለገጠመው በህይወት ይተርፋል ተብሎ አልተገመተም ነበር ።ነገር ግን የጠላት ሐሳብ ሳይሆን ቀርቶ ከአርባምንጭ እስከ ምዕራብ አባይ ባሉ አጥቢያዎች በየአውደምህረቱ በተሰበሰበ ከ120ሺህ ብር በላይ ወጪ ከአላትዮን እስከ አርባምንጭ ሆስፒታል ታክሞ የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ይገለጥ ዘንድ ወንድማችን በህይወተ ስጋ መትረፍ ቻለ። ዛሬ ላይ ግን ተጨማሪ ህክምናዎችን ለማድረግ አቅም ስላጣ በቅዳሴ አገልግሎት ላይ ሳለ እራሱን ስቶ በመውደቅ ታሟል። ቤተሰቡንም የሚያስተዳድረው በጉልበት ሥራ ስለሆነ ይህ እንቅስቃሴው የቀደመውን ጉዳቱን እያገረሸበት በተደጋጋሚ እየጣለው ለከፍተኛ ጉዳት ዳርጎታል።በመሆኑ እግዚአብሔር ትለግሱ ዘንድ የመበልፀግን ፀጋ ያደላችሁ ምዕመናን ይህን ወንድማችንን እንደአቅማችሁ ትታደገት ዘንድ ቅድስት ቤተክርስቲያን ታሳስባለች፤ ደግነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር እንደማበደር ይቆጠራልና በመላው ዓለም የምትገኙ ማህበረ ምዕመናን የወንድማችንን ህይወት ላይ በመረባረብ የተሻለ ህክምና እንዲያገኝ እና ወደሚመኘው የመቅደስ አገልግሎት እንዲመለስ ልባዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ለህክምና ዲያቆኑ ህይወቱን ለመምራት የሚያስፈልገው ከ100ሺህ ብር በላይ ስለሆነ ከ100 ብር ጀምሮ ቃል መግባት የምትፈልጉ ወይም ከታች በተጠቀሰው የሂሳብ አካውንት ገንዘብ ገቢ የምታደርጉ ምዕመናን ለሌላው ሰው ተነሳሽነት ይረዳ ዘንድ የባንክ ስሊፑን በገፃችን የውስጥ መስመር ከክርስትና ስማችሁ ጋር እንድትልኩልን ቅድስት ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች ።

// የዲያቆን ዘለዓለም አጊዶ የባንክ ሂሳብ ቁጥር
የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ አርባምንጭ ቅርንጫፍ
1000341056393

// ለበለጠ መረጃ ፦ 0929139185 //

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ዮቶድ

ከሲና ተራራ ግርጌ በወርቅ የተሠራው በበረሀ የተጓዘውና የዮርዳኖስን ወንዝ የተሻገረው ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመግባት እስራኤላውያን ያደረጉተን ትግል በድል ያጠናቀቀላቸው በንጉሥ ዳዊት ዘመነ መንግስት ወደኢየሩሳሌም የተወሰደው በ955 ቅ.ል.ክ አካባቢ በንጉስ ሰሎሞን በተሰራው ቤተመቅደስ ተቀምጦ የነበረው ይህ የቃል ኪዳን ታቦት ነው ዛሬ በነዚያ ጫካዎች(በኢትዮጵያውያን ታቦታት) መካከል ያለው።...... እኔ ለራሴ ለዚህ የተገባሁ አይደለሁም ገና በረሃውን እያቋረጥኩ እያለሁ አውቄዋለሁ ወደ ማደሪያው ቤተመቅደስ እንደቀረብኩም አውቄዋለሁ። ወደማደሪያው ቤተመቅደስ እንደቀረብኩም አውቄዋለሁ። አሁንም አውቃለሁ። ይህም ቢሆን ግን ልቤ ደስተኛ ነው ነፍሴ ትደሰታለች ሥጋዬም እንደዚሁ በተስፋ ታርፋለች።"
ግርሀም ሀንኮክ ምንም እንኳ ብዙ ያልተረዳውና ያልገባው ብዙ ነገር ቢኖርም። ግን ብዙ ካልገባውና ካላወቀው ነገር አንድ ነገር አውቋል። አባቶቻችን ያሉንን ሀብቶች የሚጠብቁበት ልዩ ሀይል የላቸውም በመትረየስ አልያም በከባድ መሳሪያ አይደለም አባቶቻችን ያሉንን ሀብቶች አስጠብቀው ያስቀመጡልን በብልሀት ነው። የጥቁሮች ስልጣኔና የጥቁሮችን ባለታሪክ መሆን የማይዋጥላቸው ነጮች ሁልጊዜም ቢሆን እራሳቸውን ከጥቁር በላይ አድርገው ስለሚያስቡ በብዙ ሴራ ሀገራችንን ሲፈትኗት ቢታይም የኢትዮጵያ ሸማ የኢትዮጵያ ውበት የኢትዮጵያ ማንነት የሆነችው ቅድስት ቤተክርስቲያን ግን ዛሬም ሀብቶቿን በብዙ ጫካዎች ውስጥ አኑራ ለሚመለከታት ብቻ አብርታ ትታያለች። የአፍሪካውያን የረጅም ጊዜ ባለ ታሪክነት ለማይዋጥላቸው ለነጮች ግን እድሜ ልካቸውን ሲኳትኑ ይኖራሉ። ኢትዮጵያ ግን ትነሳለች ብርሀኗንም ለአለም ትገልጣለች።
@ethio81
@ethio81
@ethio81

Читать полностью…

ዮቶድ

[ደብረ ታቦር]
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
❖ ይኽ በዓል ከጌታችን 9ኙ ዐበይት በዓላት አንደኛው ሲኾን በዓሉ
በየዓመቱ ነሐሴ 13 ላይ በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ ታሪኩ በ3ቱ ወንጌላት ላይ
የተጻፈ ሲኾን ጌታችን አምላችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሌሎቹን ሐዋርያትን ከእግረ
ደብር (ከተራራው ሥር) ትቶ የምስጢር ደቀ መዛሙርት የሚባሉት ሦስቱን
(ጴጥሮን፣ ያዕቆብን፣ ዮሐንስን) ይዟቸው ወደ ታቦር ተራራ በመውጣት የሞተውን
ሙሴን ከ1644 ዓመታት በኋላ አስነሥቶ፤ የተሰወረውን ኤልያስንም ከብሔረ
ሕያዋን አምጥቶ የሕያዋን አምላክና የሙታን አሥነሺያቸው ርሱ መኾኑን
የገለጸበት ታላቅ ምስጢር የተከናወነበት ነው፡፡ (ማቴ 17፡1-9)።
❖ ጌታ 8ቱን ሐዋርያት ይዟቸው ያልወጣበት በይሁዳ ምክንያት ነው
ምክያቱም ከምሥጢረ መንግሥቱ ቢለየኝ ከሞቱ ገባኹበት ባለ ነበርና ነው፤
ነገር ግን በተራራው ላይ ለ3ቱ የተገለጸው ምስጢር ከተራራው ሥር ላሉት
ከይሁዳ በስተቀር ተገልጾላቸዋል፤ ለእኛም እንደ ሐዋርያት ምስጢሩን ጥበቡን
ይግለጽልን፡፡
❖ ብዙ ተራሮች ሳሉ የታቦር ተራራን የመረጠበት
1)አስቀድሞ የጌትነት ክብሩ በዚያ ተራራ ላይ እንደሚገልጽ ነቢዩ ዳዊት በመዝ
88፡12 ላይ “ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚኣከ ይትፌሥሑ” (ታቦርና አርሞንኤም
በስምህ ይደሰታሉ) በማለት ጌታ በዚያ ተራራ ላይ ብርሃኑን ሲገልጽ የብርሃኑ
ነጸብራቅ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ እንደሚታይ የተናገረውን ትንቢት
ለመፈጸም ነው፡፡
❖ ሌላው ታቦር በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ 12 ጊዜያት ሲጠቀስ በተለይ በመሳ
4 እና 5 ላይ እንደተጻፈው አስቀድሞ በብሉይ ኪዳን የእስራኤል ጠላት የነበረው
ሲሳራን መስፍኑ ባርቅ በተራራው ላይ ድል ነሥቶበት ነቢይቱ ዲቦራም በተራራው
ላይ በደስታ አመስግናበታለች ዘምራበታለች፤ በተመሳሳይ መልኩ የእስራኤል
ዘነፍስ የክርስቲያኖችን ጠላት የኾነውን ዲያብሎስን የኹላችን ፈጣሪ ንጉሠ
ነገሥት ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነቱን ገልጦ ድል ስለነሣው ነቢያት ሐዋርያት
ምእመናን የሚያመሰግኑት ስለኾነ ለምሳሌነቱ ተስማሚነት ያለውን የታቦርን
ተራራን መርጦታል፡፡
❖ ለምን ሙሴንና ኤልያስን ከነቢያት መኻከል መረጠ? ቢሉ
ሀ) በማቴ 16፡13 ላይ ሐዋርያትን ስለማንነቱ እንደጠያቃቸው እንደመለሱለት
ኹሉ በእውነት ጌታችን የሙሴና የኤልያስ ፈጣሪ መኾኑን ሲገልጽላቸው ነው።
ለ) በዘፀ 33፡17-23 ላይ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ካለው ጥልቅ
ግንኙነት የተነሣ “እባክኽ ክብርኽን አሳየኝ” ብሎ ልመናን አቀረበ፤
እግዚአብሔርም "ወአነብረከ ውስተ ስቊረተ ኰኲሕ ወእከድን እዴየ በላዕሌከ
እስከ አኃልፍ" (በሰንጣቃው ዐለት አኖርሃለኍ፤ እስካልፍ ድረስ እጄን በላይኽ
እጋርዳለኍ፤ ካለፍኍ በኋላ እጄን አንሥቼልኽ ጀርባዬን ታያለኽ፤ ፊቴ ግን
አይታይም) ብሎታል (ዘፀ ፴፫፥፲፯-፳፫)፡፡
❖ ይኸውም ጀርባ በስተኋላ እንደሚገኝ ኹሉ በኋላ ዘመን አካላዊ ቃል
ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ በታቦር ተራራ ላይ እንደሚገለጽለት
ሲያመለክተው ነው።
❖ ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብም ስለ ታቦር በሚተነትነው መጽሐፉ ሙሴ በቃዴስ
ባለው በመሪባ ውሃ ከእስራኤል ጋር በበደለው በደል ምክንያት ምድረ ርስት
ኢየሩሳሌም እንዳይገባ አይቷት ብቻ በናባው ተራራ ላይ እንዲያርፍ ኾኗል (ዘፀ
፴፪፥፶፪፤ ዘፀ ፴፬፥፩-፰)፡፡
❖ ይኽ ለሙሴ አሳዛኝ ቢኾንም በኋላ ዘመን አካላዊ ቃል ክርስቶስ
ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሙሴ በፊት በሩቁ ያያት ግን ያልገባባት
በምድረ ርስት በኢየሩሳሌም ያለች ታቦር ተራራ ላይ አምጥቶት በዘመነ ብሉይ
በአካለ ሥጋ ያልገባባትን ርስት እንዲገባባት አድርጎታል፤ ይኸውም አዳምና
ልጆቹ በአካለ ሥጋ ያጡትን ርስታቸው ገነትን በአካለ ነፍሳቸው ዳግመኛ
ሊያገባቸው እንደመጣ የሚያመለክት መኾኑን በስፋት አስተምሯል፡፡
❖ ጌታችን በብሉይ ኪዳን ከነበሩት ከነቢያት ሙሴንና ኤልያስን በሐዲስ
ኪዳን ከነበሩት ከሐዋርያት ሦስቱን በታቦር ተራራ ላይ ማውጣቱ፦
1) የታቦር ተራራ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ በመኾኗ ሲኾን በቤተ ክርስቲያናችን
ብሉይ ኪዳንና ሐዲስ ኪዳን እንደሚነገሩ ለማመልከት
2) በተራራ በተመሰለች በጉባኤ ቤት ብሉይና ሐዲስ እንደሚነገሩ ለመግለጽ፡፡
3) ሌላው የታቦር ተራራ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ስትኾን ይኸውም ጌታ
ነቢያትንና ሐዋርያትን በተራራዋ ላይ መሰብሰቡ መንግሥተ ሰማያትን ነቢያትም
ሐዋርያትም እንደሚወርሷን ለማመልከት
4) ሙሴ ያገባ ሲኾን ኤልያስ ድንግል ነውና መንግሥተ ሰማያትን ደናግልም
ያገቡም እንደሚወርሷት ለማጠየቅ ነው፡፡
5) እንደ ያዕቆብ ዘሥሩግ ትርጓሜ ሙሴ ኦሪት ዘፍጥረትን ሲጽፍ “በመጀመሪያ
እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ” (ዘፍ 1፡1) እንዳለ፤ ዮሐንስም
“በመጀመሪያ ቃል ነበር” (ዮሐ 1፡1) ብሎ እንደ ሙሴ አምላክነቱን የሚመሰክር
ነውና ሙሴ አስቀድሞ የጻፈልኝ፤ አኹንም ዮሐንስ አምላክነቴን የሚጽፍልኝ እኔ
ነኝ ሲል ነው፡፡
6) ሙሴና ኤልያስ ይመሳሰላሉ፤ ይኸውም በሲና ተራራ 40 ቀንና ሌሊት
እንደጾመ ኤልያስም በደብረ ኮሬብ 40 ቀንና ሌሊት የጾመ ነውና፨
7) ሙሴ ንጉሡ ፈርዖንን የገሠፀ እንደነበር ኤልያስም ንጉሡ አክዐብን የገሠፀ
ነውና፨
8) ሙሴ ከንጉሡ ፈርዖን ፊት ሸሽቶ እንደሄደ ኤልያስም ከንግሥቲቱ ኤልዛቤል
ፊት ሸሽቶ ሄዶ ነበር።
9) ዳግመኛም ሰማይኑን ዝናብ እንዳያዘንም በተሰጠው ሥልጣን ባሰረውና ከ3
ዓመት ከ6ወር ቆይታ በኋላ እንዲዘንብ በፈታው ኤልያስን እንዳመጣ ኹሉ
የማሰር የመፍታት ሥልጣን ሥልጣነ ተሰጥቶት “እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ
ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም
አይችሉአትም የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር
የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ
በሰማያት የተፈታ ይሆናል” (ማቴ 16፡18-19) ላለው ለጴጥሮስን ታላቅ ሰማያዊ
ሥልጣን መስጠቱን ለማመልከት አምጥቷቸዋል፡፡
❖ በቤተ ክርስቲያንና በሀገራችን ያለው መንፈሳዊ አከባበር ደማቅ ነው፤
ይኽ በዓል በቤተ ክርስቲያን በማሕሌት በቅዳሴ በትምህርት የሚከበር በዓል
ሲኾን በሀገርኛ የቡሄ በዓል ይባላል፤ ቡሔ ማለት ሊቁ ደስታ ተክለ ወልድ
በመዝገበ ቃላት ላይ ሲገልጹት ቧ ብሎ በደብረ ታቦር የተገለጠው የጌታችንን
የፊቱን ብርሃን ጸዳል የልብሱን እንደ በረዶ ነጭ መኾን ያስረዳል ስለዚኽ
የብርሃን፣ ብርሃናዊ ማለት ነው፡፡
❖ በዚህ በዓል በታቦር የታየው የብርሃኑ ምሳሌ የሚሆን ችቦ ይበራል፤
ሌላው በዚኽ በዓል ሰሞን በገጠር ከተራራ ላይ እረኞች ሕጻናት ዥራፍ እየገመዱ
ማስጮኻቸው ጌታ በተራራ ላይ ብርሃኑን በገለጸ ጊዜ አብ በደመና ኾኖ “እርሱ
ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” ባለ ጊዜ ሐዋርያት
በድምፁ ደንግጸው መውደቃቸውን ለማመለክት ነው፡፡
❖ ሌላው ሙሉሙሉ ዳቦ መጋገሩ በትውፊት እንደምንረዳው ጌታ ብርሃኑን
ሲገልጽ ብርሃኑ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ ያበራ ስለነበር እረኞች ሌሊቱ ኹሉ
ቀን መስሏቸው እዛው ስለዋሉ ቤተሰቦቻቸው “ኅብስት” ይዘውላቸው ሄደዋልና
የዚያ ምሳሌ እንደኾነ ይነገራል፡፡
[በደብረ ታቦር ላይ ብርሃኑን የገለጠው አምላካችን ክርስቶስ ምስጋና ይግባው]፡፡
[መልካም በዓል]


👉እርሶ ያወቁትን እውቀት ሌሎች ያውቁ ዘንድ ቻናላችንን ሼር በማድረግ ጓደኛዎን ይጋብዙ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇 👇👇👇👇👇
@ethio81
@ethio81
@ethio81

Читать полностью…

ዮቶድ

Watch "እግዚአብሔርን ጠራሁት በሀዘኔ ግዜ - ዘማሪ ቴወድሮስ ዮሴፍ - Ethiopian Orthodox Mezmur - Zemari Tewodros Yosef" on YouTube
https://youtu.be/FCrL4iAOhNw

Читать полностью…

ዮቶድ

የኤዶም ምድር .....#share

*እንኳን ወደ ኤዶም ምድር በሠላም መጣችሁ።ሰከላ ጥንታዊ ስሟ ኤዶም ይባላል።በዘፍጥረት ከኤዶም በስተምሥራቅ ገነት ትገኛለች።ገነትን ከሚያጠጡ አራቱ አፍላጋት አንዱ ግዮን ነው።ግዮን ከኤዶም ወይንም ከሰከላ መንጭቶ ኢትዮጵያን 7 ጊዜ ይዞራል።(ዘፍ 2፥1-13)

*አዳም ከአባቱ ከመሬት ተፈጠረ።የተፈጠረበት አፈር "ስውሩ አፈር" ይባላል።የተፈጠረበት ቦታ "ኤልዳ" ትባላለች።ኤልዳ አሁንም ጎጃም ውስጥ አስሌዳውያን ( ኤልዳውያን) የሚባል  ቦታ አለ።ኤልዳ ከግዮን በቅርብ ርቀት የምትገኝ ናት።አዳም የ30 ዓመት ጎልማሳ ሆኖ ኤልዳ ላይ ከተፈጠረ በኋላ በኤዶም በስተምሥራቅ ወደምትገኘው እንዲሁም የግዮን ወንዝ ወደሚያረሰርሳት ገነት  በ40ኛ  ቀኑ ፈጣሪው አስገባው።አዳም በገነት የኖረው ለሰባት ዓመት ነው።

*በዘፍጥረት ግዮን (አባይ) ዙሪያ  የሚያበራ ዕንቁና የሚያብረቀርቅ ዕንቁም ይገኝበታል።ይኼ ቦታ በጎጃም በስተምዕራብ  "ፋዞግሊ" የሚባለው የወርቅ ማውጫ ሳይሆን እንዳልቀረ ሳይንሳዊ ጥናቶች እየወጡ ናቸው።
"ፋዞግሊ" የሚባለው የወርቅ ማውጫ ቦታ ንጉሥ ድግናዣን  ለመቆጣጠር 100 ሺህ  የሚያህል ሠራዊት ይዞ በበጌምድር በኩል ሲዘምት በአሸዋ ተውጦ ቀርቷል። ዐፄ ካሌብ በአገዎች ያስጠብቀው ነበር።በደቡብ ገናና የነበረው የዳሞት መንግሥትም ይህንን የወርቅ ማውጫና የወርቅ ጎዳና ለመቆጣጠር ወደ ሰሜን ተጉዞ ነበረ።የዛግዌ መሥራች መራ ተክለ ሃይማኖትም በዚህ የወርቅ ጎዳና ጥበቃ ላይ ከተሠማሩት ኃያላን የጦር አዛዦች መካከል አንዱ ነበረ።

*አዳም በሰባተኛ አመቱ ከገነት ከተባረረ በኋላ በአጠቃላይ በምድር ላይ የኖረው 930 ዓመት ነው። የተቀበረው ኮሬብ በሚባል ቦታ ነው።በኢትዮጵያ ኮሬብ የሚባሉ ብዙ ቦታዎች አሉ።በታሪክ የሚታወቀው ግን አምሓራ ሳይንት የሚገኘው ነው።የዮቶር (ካህን ራጉኤል) መኖሪያ እንደነበሩ አሳማኝ ማስረጃዎች እየወጡ ናቸው።ሙሴ በግ የሚጠብቅበት የነበረ ተራራ ተብሎ ይታመናል።

*ግዮን ሰከላ (ኤዶም)  ከሚገኘው ግሽ ከተባለው በደን የተሸፈነ ረግረጋማ ቦታ ላይ ይመነጫል።ግሽ ተራራ 2800 ወደ ላይ ይረዝማል።ከተራራው ግርጌ 100 ሜትር ፈንጠር ብሎ አባይ ይወለዳል፡፡ግዮን በሰከላ (በኤዶም) የስያሜ ምንጭም ነው፡፡የአማራ ሕዝብ የበኩር ልጁን "አባይነህ" ይላሉ ታላቅ ነህ ለማለት ነው።

*ግሽ  ላይ  የጻዲቁ አቡነ ዘርአብሩክ ገዳም ይገኛል።ጻዲቁ አቡነ ዘርአብሩክ በ17ኛው መክዘ ግሽ አባይ  ላይ ተቀምጠው ሲጸልዩና  ሲያስተምሩ፤ሲያጠምቁበትና ሲፈውሱበት ነበረ። አቡነ ዘርዐ ብሩክ በዚህ ዓይነት የቅድስና ተግባር ቆይተው መጽሐፎቻቸውን በጨርቅ ሸፋፍነው በዓባይ ምንጭ ውስጥ ደብቀዋቸው ወደ ጎንደር ሔዱ።ከሰባት ዓመት በኋላ ወደ ቦታው ተመልሰው መጽሐፎቻቸውን ለማግኘት  ከምንጩ አናት ላይ ቆመው፣ለዐራት ጊዜ  ጸሎት አድርሰው ከጨረሱ በኋላ “ግሥዒ ግዮንመጻሕፍትየ” (ግዮን ሆይ መጽሐፎቼን ትፊ) ሲሉ መጽሐፎቹ አቧራ እንደለበሱ፤ ርጥበት ሳይኖርባቸው ተንኳፈው ወጥተዋል፡፡ከዚያም ለጓደኛቸው፤ “አባ ይህንን ተአምር እይ” በማለት አሳዩዋቸው፡፡ከዚህ በኋላ የቦታው ስም  በግእዝ ግሥዒ ዓባይ ያሉት ቃል ተቀይሮ ግሽ ዓባይ እንደተባለ፤ቦታውም ከገነት ወደ ዓለም እንደ ቧንቧ በሚፈስሰው ጸበል የተባረከና የተቀደሰ፤ ልዩ ምሥጢርም ያለው  ውኃ  እንደሆነ አባቶች ያስረዳሉ።

*በዚህ ዓይነት የግሽ ዓባይ  ጸበል ከውኃው አናት ላይ ሲነሣ እንደ ትንሽ ምንጭ ይሆንና እዚያው ሰከላ (ኤዶም) ትንሽ ወረድ ሲል ደግሞ ማዕበል እየሆነ የግልገል ዓባይን ድልድይ ያቋርጥና በጣና ላይ እየሰፈፈና ቁልቁል ወደ ጢስ ዓባይ እየጎረፈ፤ በደጀን በኩል ወደ ሱዳን ካርቱም፤ ግብጽና ወደ ሜዲትራንያን ባሕር ወርዶ ይቀላቀላል፡፡

*ከዚህ ጋር በተያያዘ፦

1.ኖህ ከማየ አይኅ የጥፋት ውኃ ልጆቹ፣ሚስቱና የልጆቹ ሚስቶች የዳኑት በመርከብ ነው።የኖኅ መርከብ ማየ አይኅ መጉደል ሲጀምር በ7ኛ ወር ከወሩም በ27ኛው ቀን በአራራት ተራሮች ላይ ተቀመጠች።የኖኅ መርከብ ሐመር ያረፈችበት  ስሙ ሉባር ተራራ ይባላል።አራራት ተራራ ደግሞ የሚገኘው ከዚሁ ጣና ውስጥ ነው።ኖኅ መርከቧ በአረፈችበት አራራት (ዘጌ) አካባቢ ወይን ሲተክል ኖረ። አካባቢውን ሳይለቅ ከጥፋት ውኃው በኋላ 350 ዓመት ኖረ።በኋላም የተቀመጠው በእንተላ፣በአይዋርካ፣በሽሌ፣በአይከል ቀሪ ዘመኑን የገፋ ሲሆን ጭልጋ ሳለ ሚስቱ እሜቴ አይከል አረፈች።የኖኅ ሚስት እሜቴ አይከል የተቀበረችው ጭልጋ ላይ ነው።በዚህም የጭልጋ ዋና ከተማ በስሟ አይከል ተባለች።ጭልጋ የአራራት ተራራ አዋሳኝ መሆኑ ይታወቃል።

2.ከእሜቴ አይከል እረፍት በኋላ ኖኅ  ጎንደር ላይ ብዙ ዘመን ፈጣሪውን እያመሰገነ እየቀደሰ ኖረ።በ950 ዓ.ዓ ኖህ ሲሞት እዛው ጎንደር ላይ ተቀበረ።መቃብሩ ላይ ምንጭ ፈልቆ በርካታ ሰዎችን ይፈውስ ነበር።ከዚያም ለኖህ መታሠቢያ ይሆን ዘንድ አምላክ በቤተመንግስት አሳቦ የኖህ የመቃብር ሐውልት እንዲታነጽ ፈቀደ።ይህም በኋለኛው ዘመን በንጉሥ ፋሲለደስ የታነጸው የፋሲል ግንብ ነው።

3.በሌላው ዓለም በየትኛውም ስፍራ ወይም ምድር በተባለችው ፕላኔት ላይ በየትኛውም አገርና አህጉር የማይገኙ በኖኅ መርከብ ውስጥ ከነበሩት  7ቱ አጥቢ እንስሳት እንደ ዋሊያ፣ቀይ ቀበሮ፣ጭላዳ ዝንጀሮ የመሳሰሉት እና 13ቱ አእዋፋት የሚገኙት ከኢትዮጵያ 1ኛ ከአፍሪካ 4ተኛ ደረጃ ላይ በተቀመጠው የከፍታ መጠኑ 4620 ሜትር በሆነው በራስ ደጀን ተራራ ነው።ደጀን ተራራ በ1970 ዓ.ም.በዩኔስኮ አማካኝነት በአለም የቅርስ መዝገብ ላይ ተመዝግቧል።

4.ሊቀ ነብያት ሙሴን የአመራርነት ጥበብ የተማረው ከአማራ ካህን ዮቶር (ራጉኤል) ነው።ልጁንም ሲጳራ አግብቶ አልአዛር እና ጌርሣም የሚባሉ ልጆችንም ወልደዋል። መሴ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ያረፈው በጥንቱ በጌምድር ግዛት ምድያም  ነው። ምድያም በዛሬው አማራ ሳይንት ውስጥ መደጊም ተብሎ የሚጠራው ቦታ ነው።
በግ ማርባት በምድያም (በቤጌምድር) ምድር የተለመደ ነው።የአማራ ክፍል የሆነው በጌምድርም የበግ ሀገር የተባለው በግ በማርባት ስለሚታወቅ ነው።በጌምድር  ወይንም ሽሜ  የአማራ ሀገር ነበር።እስከ ተድባባ ማርያም ድረስ በጌምድር ይባል ነበር።በታሪከ ነገሥት "ወዘዐምሐራ ወዘበጌምድር"ይለዋል።ምድያም የሚባል ቦታ በጂዎግራፊያዊ ማስረጃዎች በሲና ሰርጥ ደቡባዊ ክፍል ይገኛል።ይኼም አካባቢ በሲና ተራራ አጠገብ በመሆኑ ግመል እንጅ በግ ሊያረባ አይችልም።

5.የሌዋዊያን ካህናት ከእስራኤል በመጀመሪያው ፓትርያርክ አዛሪያስ መሪነት  የመዝሙረኛው ዳዊት የወንድም ልጅ ሳቤቅ ጨምሮ ወደ ኢትዮጵያ ታቦተ ጽዮንን ተከትለው ከመጡት አስራ ሁለት ሺህ ነገደ እስራል ሁለት ሺህ አመስት መቶዎቹ  ተከዜን ተሻግረው   ወደ አምሐራ ሳይንት መጡ።ሊቀ ካህን አዛርያስ በጣና ቂርቆስ ሊቀካህን በመሆን መንፈሳ አገልግሎት ሰጥተዋል።ዛሬም ድረስ  አራት ማዕዘን ቅርጽ ያለውና ከአናቱ ላይ እንደ ሙቀጫ የተቦረቦረው ድንጋይ ለዚህ ህያው ማሳያ ነው።የኦሪታውያን የብረት መስዋዕት ማቃጠያም ይገኛል።

6.የጣና ቂርቆስ ገዳም ለሙሴ የተሰጠው የቃል ኪዳን ታቦቱ 800 ዓመት ቆይታበታለች።እንደገና ድንግል ማርያም ልጇን ይዛ ወደ ምድረ ግብጽ በተሰደደችበት ወቅት ለ3 ወራት ከ10 ቀን በዚሁ ገዳም ከልጇ ጋር ቆይተውበታል።ድንግል ማርያም በገዳሙ የነበራትን ቆይታ አጠናቃ ስትመለስ “ፀአና በደመና” በደመና ጫናት የተባለው በጊዜ ብዛት ለአሁኑ የሀይቁ መጠሪያ ስም

@ethio81
@

Читать полностью…
Subscribe to a channel