ethio_edu_news | Unsorted

Telegram-канал ethio_edu_news - የኛ ትምህርት

891

Its All about Educational Stuff✊ for any comment @Amturnt

Subscribe to a channel

የኛ ትምህርት

• ጥቂት አዉራ፡፡ ስታወራ ቀስ ብትል መልካም ነዉ

• አንድ ቦታ ላይ ብዙ አትታይ፡፡ ስራህ ላይ አተኩር

• ምርጥ የሰዉነት አቋም ይኑርህ

• ተግባቢና የተረጋጋ ሰዉ ሁን

• ማንም ትክክል ነህ እንዲልህ አትጠብቅ፡፡ ማንም ደጋፊህ እንዲሆን አትጎትጉት

• ስላለህ ነገር ደጋግመህ እየተናገርክ የመጎረር ስሜትን አስወግድ

• ፀዳ በል፡፡ በደንም ልበስ፣ ፏ በል!

• ምርጥ አዳማጭና መፍትሄ አምጪ ሁን

• አደርገዋለሁ ያልከዉን ነገር አድርገዉ

• በጣም ደስ ሲልህ ወይም በጣም ስታዝን ዉሳኔ አትወስን

• ሴቶችን በአስተሳሰባቸዉ መዝናቸዉ

• የግል ጉዳይህን ላገኘኸዉ ሰዉ አትናር

• ሰዉ ስላንተ የፈለገዉን ቢያስብ ከማንነትህ ጋር አታገናኘዉ

• ሃላፊነት መዉሰድን አትፍራ

• ማንንም ለመጉዳት ብለህ ጉድጓድ ከመቆፈርም ይሁን ከማስቆፈር ራስህን አሽሽ

• የጎዱህንና ‘ምንም የለዉም!’ ብለዉ የራቁህን ሰዎች ስኬታማ በመሆን አሳያቸዉ

• ሃሳብህን ለማሳመን የሰዎችን ማንነት አትጉዳ፡፡ ትክክክል ብትሆን እንኳን ካመኑ ይመኑህ ካላመኑህ ጊዜዉ ያሳምናቸዋል

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

አንድ ወንድም ገጠመኙን አካፍሎናል።


በቀጣይ የለቀቃል
.
.
.
.

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

@@@@@ይቆጨኝ ነበረ@@@@@
''''''''''''''''''&&&&&&&''''''''''''''''
ከፍቅርሽ ከፍታ~ ላ'ፍቃሪ ከራቀው፤
ኩራት ከውበት ጋር~ ከተደባለቀው፤
ከሚታየው ርቆ~ የዝናሽ ቅርንጫፍ፤
ከጥላቻሽ አናት~ ከመፈቀርሽ ጫፍ፤
አላፈቅርም ብለሽ፣
አልወድህም ብለሽ፣
እንኳን~ ገፍትረሺው፤
እንኳን መሬት~ ጣልሺው፤
እንኳንም ባንቺ እጅ~ ልቤ ተሰበረ፤
ባላፈቅርሽ ኖሮ~ ይቆጨኝ ነበረ።

Tewedadari1⃣2⃣ AMANI

@fe_ash

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

የማያስተውል ልብ

የእግዚአብሔርም መፅሐፍ ሲናገር ቃላቱ

የማያስተውል ልብ ይሔ ነው መሻቱ

የፈጠረውን አምላክ ፈጣሪውን ትቶ

ፍጡሩን ያመልካል ሁሉንም ጎትቶ

ሴቷም ከሴቷ ጋር እራስዋን ስታረክስ

ወንዱም ከወንዱ ጋር እራሱን ሲያረክስ

አይተፋፈሩም ይደጋገፋሉ እርስ በእርሳቸው

ማነው ይሄንን ልብ ለነሱ የሰጣቸው

ነውሩን ደብቀው አምላክ እየተቹ

የአፀፋቸው ብዛት መች ሆነ መብቃቱ

ይቀጥላል ገና ገና ሀጥያታቸው

እዚህ ጋር ብቻ አያቆም ጉዳቸው

ሐሜትን ከውሸት ተንኮል ከመመኘት

ይኖ ሁሉ ደምረው ይፈጥራሉ ክፋት

ይቅርታን ማያውቁ ፍቅር የሌላቸው

ቅንጣት ርህራሄ የለም በልባቸው

አመፃን ደርበው በግፍ እየኖሩ

አምላክ የሚጠሉ የሚከራከሩ

ልባቸው ደንድኖ ጠጥሮ በትቢት

ነብሳቸው ተማምና በራሳቸው ትምክህት

በቅናት ብዛት ሠው እየገደሉ

ለወላጅ ማይታዘዙ ሆነው ማያስተውሉ

እግዜርን ለማወቅ ባልወደዱት ሁሉ

ለማይረባ አይምሮ ሠጣቸው ይላል ቃሉ

ስለዚህ ሁላችን እግዜሩን እንወቅ

ከማይረባ አይምሮ እኛስ እንጠንቀቅ ።

"እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይረባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አይምሮ አሳልፎ ሰጣቸው። ሮሜ 1:28"

Tewedadari8⃣ RUT MOSHE

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

If u think
If u think u are beaten, u are
If u think u are dare not, u dont
If u like to win, but think u can't
It's almost a cinch u won't
If u think u'll lose, u are lost, for out in the world we find sucess being with a fellow's will;
It's all in the state of mind.
If u think u are out casted, u are
U've got to think high to rise.
U've got to be sure of ur self before u can ever win aprize,
Life battles don't always go
To the stronger and faster man,
But sooner or later the man who wins
If the man who think he can.

Tewedadari6⃣ MAKI

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

          ለምን ልዘን

ወዳጅሽ ነኝ ያለ ጥሎ ስለሄደ
ሌላ ኮ ይመጣል ከልብ የወደደ
አስመሳይ ሲወጣ እውነትም ከመጣ
ሠውን አጣሁ ብዬ ለምን ራሴን ልቅጣ
በፍፁም አላዝንም ሰው ትቶኝ ቢሄድ
ብዙ እማራለው ከነሡ አካሄድ።

አንዳንዱ ጥላቻን ፤  አንዱ ደሞ ፍቅር
ግማሹ እምነትን ፤  ሌላው ክህደትን
ሲያሻው ትዕግስትን ፤ ሲለውም ንዴትን
አስተምሮኝ ይሄዳል ሁሉም የየራሡን።

የጨለመ እንዲሁ ፤ መልሶ ይነጋል
የተሠበረ እንዲሁ ፤ በሌላ ይቀየራል
የወደቀም እንዲሁ ፤ መልሶ ይነሳል
የሄደውም እንዲሁ ፤ በሌላ ይተካል

ታዲያ ለምን ልዘን ለምንስ ልከፋ
እግዜር ብቻ ካለ ነገ ለሚመጣ ሌላ አዲስ እንግዳ።

Tewedadari 3⃣ Soliyana.G

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

ውድድሩ ነገ 3:00ላይ ይጀመራል

❤️


ተወዳዳሪዎች እንድትዘጋጁ ስንል እናሳስባለን።


ነገ 3:00 ለይ ጠብቁን 😊

መልካም ውሎ።

#fV

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

ሰላም እንዴት ናቸው የ heavenly art mmbrs


አዲስ ነገር ይዤ መጥቻለሁ

❤️ገጥም የመፃፍ ችሎታ ያላቸው ❤️


ለናንተ ምረጥ ሀሳብ አቀረብኩላችሁ

እናንተ የፃፋችሁትን ገጥም ለውድድር በማቅረብ memberoch like በማድረግ ለናንተ የ mb ሽልማት ተዘጋጅቷል።

ስለዚህ መወዳደር ምትፈልጉ
@fev1bnAaE

@genet5 ላይ ላኩልን

የግጥም ችሎታቹን እያሳደጋችሁ የ mb ተሸላሚ ይሁኑ ስንል በታላቅ ደስታ ነው።
@fe_ash @fe_ash

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

Mewedader mtfelgu lakulin wddru tolo endijemr👍

@fev1bnAaE

@genet5 lay lakulin

❤️

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

Endesu srawechachun mastewawek mtfelgu
@genet5
@fev1bnAaE
Lay lkuln... ❤️

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

😔ግር ያላት ነብስ😔
📘ተከታታይ ልበ-ወለድ📘

✍ @Artisticallife 💐

. ክፍል 2⃣
............... """"""""""""""----------------

ሚሊ እና እስከዳርም ሮጠው ተከተሉኝ ልክ ቤት ስገባ አባቴ ጋቢ ለብሷል ሁሉም እኔን ሲያዩ ቀወጡት ወይኗ ወይኗ እያሉ ይጮሀሉ ማመን አልቻልኩም እናቴ ሞተች??? ግራ ገባኝ ልሳኔ ተዘጋ ከዛ ማስታውሰው የለም ስነቃ የራሴ ክፍል አስተኝተውኛል ጌታ ሆይ ህልም ነው በለኝ ከክፍሌ ስወጣ ቤቱ በሰዎች ሽርጉድ ተሞልቷል

በሰላሙ ቀን መተው የማያውቁ ዘመድ ተብዬዎች ጓሮውን ሞልተውታል ለቅሶ ሳይሆን ሰርግ ነበር ሚመስለው ።
አይ የኔ ነገር ይሄም አሁን ነው ትዝ ያለኝ በጣም ከፋኝ እናቴ እራበችኝ ቤቱ በሰው ተሞልቶ ለኔ ግን ባዶ ነበር እንዲህ እንዲያ እያለ ወራቶች ተቆጠሩ እህቴም ወንድሜም እናቴው ነበረች ብቸኝነቱ ናፍቆቷ ቀጣኝ አባቴ ስራ ላይ ትኩረት ስለሚያደርግ ትዝም አልለውም ለክፋት ሳይሆን በቃ እንደ እናቴ ቀርቦ ችግሬን አይጠይቀኝም ለቀበሌ ህዝብ ሚበቃ ያትልቅ ቤት ሊበላኝ ነው ።


ማህሌት እኛ ቤት መምጣት አላቆመችም እቤት ሚያስፈልገውን ትሰራራለች ግን ማንም እንደ እናቴ ሚሆንልኝ አጣው
💐💐 @Artisticallife 💐💐

የእናቴ ሞት ዛሬም ድረስ ይከነክነኛል ጤነኛ ነበረች ለሞት የሚዳርግ የቆየ በሽታ የለባት እንዴት ዝም ብላ ትሞታለች
በነገሰ
ራችን ላይ የአርት ቲም ልጆች በብዛት አብረን ነው ምንማረው 12 ክፍል ነን አናም በእረፍት ሰአት ምናምን እንወያያለን አብረን እናሳልፋለን ዛሬ አርብ ነው ብንለያይም ነገ ቅዳሜ ስለምንገናኝ ተደስተን ነው ምንለያየው ሚሊ ሊሸኘኝ ሌሎቹኝ ቻው ብሎ መጣ እንዴት ደስ እንዳለኝ እናቴ ከሞተች ዛሬ ገና ጀስ ሲለኝ ተሰማኝ ስለ ብዙ ነገር እነፈያወራን እየተቃለድን ሰፈር ደረስን ከዛ ቻው በቃ ብሎኝ ሄደ ከዛ ሚሊ ብዬ ጠራሁት ዞረ ግራ የገባው ይመስላል ቆሞ ያየኝ ጀመረ እየሮጥኩ ሄጄ አቀፍኩት አመሠግናለሁ ከእናቴ ሞት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አስደሰትከኝ አልኩት እንዴ ሩሀ አንቺን ደስ ካለሽ ሁሌመሸ ሸኝሻለሁ አለኝ እየተፍለቀለኩ እሺ አልኩትና ሄደ ገብቼ ቤትውስጥ እንደ እብድ መዝለል ጀመርኩ
ከዚያም ደወልኩለትና ረጅም ሰአት አወራን ብቻ ሚሊ ከምነግራችሁ በላይ መልካም ሰው ነው እንዲህ እንዲህ እያሉ ቀናቶች ገፉ ከሚሊ ጋር በጣም ተቀራርበናል ካልደወለልኝ ያመኝ ጀምሮአል በቃ ሚሊን ወድጄዋለሁ አልዋሻቹም እና ሚሊም የሚወደኝ ይመስለኛል ቃል በገባልኝ መሠረት ከትምህርት ቤት መልስ ይሸኘኛል ልክ ሰፈር ስንደርስ ቻው ሲለኝ ሚሊ ምነግርህ ነገር አለ አልኩት በጉጉት ስሜት ንገሪኛ ምን አለኝ? አሁን አደለም ነገ አልኩት ሳትነግሪኝ አትገቢም ብሎ ደረቀ እምቢ ብዬ እኔም ደረኩ ከዛም ነገ እንደምነግረው ቃል አስገብቶኝ ሄደ ተስማምቼ የማይደርስ የለ ከዚያም
የተቀጣጠርነው ከቸርቻችን አጠገብ ያለች ጁስ ቤት ናት ሁሁላችንም መሰብሰቢያችን ናት ሚሊ በጣም ከመጓጓቱ የተነሳ በልጆቹ ፊት ንገሪኛ ሩሀ አለኝ ሳኩና አነቃውት ሁሉም እንሰማለን ይነገረን ብለው ጮሁ ደፋሮች ብያቸው ለመውጣት ተነሳሁ ሚሊ ግን ስላላስቻለው በግድ ሌላ ቦታ አስቀመጠኝ እና እንድነግረው ለመነኝ
💐💐 @Artisticallife 💐💐


እየፈራሁና አየተርበተበትኩ መምጣት ጀመርኩ ከዚያም የ አይን አውጣነቴ ብዛት እወድሀለሁ አልኩት እንዴ ምን ችግር አለው እኔም እኮ እህቴ....ሲል አቋረጥኩት እንደሱ አይደለም አፈቅርሀለው አልኩት ልጁ ደንግጦ ተነሳ ተቀመጠ ሩሀ ልክ ነሽ በጤናሽ ነው አለኝ
ደነገጥኩና አዎን አልኹት እያየሁት ተቀያየረ አንቺ ያምሻል እኔ እኮ እህቴ ነሽ ብዬ ነው ምጃጃለው በሀዘን ተጎድተሻል ብዬ እንጂ ስሚ ብዙ አላማ ያለኝ ሰው ነኝ በዚህ ሰአት ከአንቻጋ ፍቅር ምናምን እያልኩ አልጃጃልም ብሎኝ እርፍ የምር ከፋኝ አልወድሽም እኮ የአባት ነውእንዲ ያበሸቃቅጠኝ ሲጮህ ስለነበር ሁሉም ያለውን ሰምተዋል ወይ ውርደት አስቡት ሴት ሆኜ ምን አንቀለቀለኝ የጥናታችን ሰአት ደረሰ ና በተረበሸ መንፈስ ገባን ሚሊ ምንም ቢናደድ ጥሎኝ ይሄዳል ብዬ አላሰብኩም ነበር

💐💐 @Artisticallife 💐💐

እየከፋኝ ወደ ቤት ሄድኩ ማህሌት ሰሞኑን እኛ ቤት ማደር ከጀመረች ሰነባብቷል እሁድም ቸርች ሄጄ ከፕሮግራም በኋላ ላናግረው ስል እንዴት ገላምጦኝ እንዳለፈ ።እንዴ ፍቅር ሀጢያት ነው እንዴ በእርግጥ ሚሊ መንፈሳዊነቱን ብወድለትም ሁኔታው እያስገረመኝ ነው አንድ ቀን ደስታን አጣጥሜ አላውቅ እናቴን ሳልጠግባት አጣው ከሚሊ ጋር መቀራረባችን አሱም ሚወደኝ እስኪመስለኝ ነበር ግን በዛ ሁሉ ሰው ፊት ከፍ ዝቅ አርጎ ውርደት አከናነበኝ ክላሴ ተኝቼ ነው ይህን ሁሉ ማሰላስለው በብዛት ሳሎን መቀመጥ አለመደብኝም ድብርቱ ሲጠናብኝ ግን ነገ ሰኞ ስለሆነ ደብተሮቼን አሰነዳድቼ Tv ለማየት ወደ ሳሎን አቀናሁ እንደነገርኳቹ እናቴ ከሞተች ሳሎን ተቀምጬ አላውቅም ልክ ስገባ ግን የማየውን ማመን አልቻልኩም አባቴ እና ማህሌት ....................

💐💐 @Artisticallife 💐💐
......ይቀጥላል........

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Join&shear💐 @Artisticallife
🙏ተባረኩ🙏
--------------"""""""""""""""""-----------------

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

Endesu srawechachun mastewawek mtfelgu
@genet5
@fev1bnAaE
Lay lkuln... ❤️

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

@Neba166

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

@Neba166

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

<< ውሾቹ ይጮኻሉ ግመሉ ግን ጉዞውን ቀጥሏል >>

📚📚📚

ደራሲ ዓለማየሁ ገላጋይ መልክአ ስብሀት የሚለው መጽሐፍ ላይ ስለ ጋሽ ስብሐት ይህንን አስፍሮ እናገኛለን...

<< ቀኑን በውል በማላስታውሰው አንድ ማለዳ ነው። እኔና ስብሐት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ አካባቢ አንድ በረንዳ ላይ ቁጭ ብለን ማኪያቶ እንጠጣለን። ድንገት አንድ እንደነገሩ የለበሰ ወጣት መጥቶ ፊታችን ተደቀነ። ቀና ብለን አየን። የልጁ ሙሉ ትኩረት ስብሐት ላይ ነበር። እጁን ለሰላምታ ዘርግቶ ስብሐትን ጨበጠና እራሱን አስተዋወቀው። የአንድን ነፃ ጋዜጣ ሥም ጠቅሶ "ዋና አዘጋጅ ነኝ" አለው።



<< ጥሩ >> አለ ስብሐት
<< ባለፈው ሳምንት አንድ ባለጌ እዚህ ጋዜጣ ላይ ሰድብዎት ነበር። አንብበውታል? >>
<< አንብቤዋለሁ >>
<< ታድያ መልስ ይስጡታ፤ እኔ ፅሁፉን አወጣልዎታለሁ >>
<< አያስፈልግም >>
<< ለምን? >> ድርቅርቅ ያለ ጥያቄ አቀረበ
<< ጋዜጠኛ ሆነህ ጥያቄ አታባክን፤ አያስፈልግም ተባልክ፤ አለመፈለግ ምክንያት ላይኖረው ይችላል። ቢኖረውም ላንተ መንገር ላይስፈልግ ይችላል...ወዘተ >> አለው።
<< አይደለምኮ...ልጁ ባለጌ ነው...መልስ ያስፈልገዋል >>
<< ፅሁፉን ያወጣህለት አንተ አይደለህ? >>
<< አዎ >>
<< ይኸውልህ፤ ብሽቅ ሀበሻ አይደለሁም እንጂ ብሆን ኖሮ ካንተ ጋር ነበር የምፋለመው። ሰድቦ ከፃፈብኝ አትሞ ያስነበበኝ እንዲሉ አበው። >>
ልጁ በክርክር የስብሐትን እምቢታ ሊዘልቀው አልቻለምና ጥሎን ሄደ። ስብሐት ወደእኔ ዞር አለና
<< እኛ ስንታኮስ እሱ ጥይት ሊሸጥ አስቦ፤ አልያዘለትም እምጵፅ >>
<< እኔ ደግሞ >> አልኩት ስብሐትን << እኔ ደግሞ የመሰለኝ እራሱ ነው የፃፈው >>
<< አልፃፈውም >>
<< በምን አወቅህ? >>
<< ባለፈው እግረ መንገድ ላይ ፀሐፊው ብቻ የሚገባውን መልእክት አስተላልፌአለኋ። >>
<< ምን የሚል መልእክት? >>
<< ውሾቹ ይጮኻሉ፣ ግመሉ ግን ጉዞውን ቀጥሏል። >>


📚📚📚

ምንጭ ፦ "መልክአ-ስብሃት…ገጽ 15-16"

📖📖📖

በነገራችን ላይ "ውሾቹም ይጮኻሉ ግመሎቹም ይሄዳሉ" የሚለው አባባል የአረብ ነጋዴዎች አባባል እንደሆነ "የኔ ጀግና" የሚለው የሙሃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት መጽሐፍ ላይም ሰፍሮ እናገኛለን። አረቦች በግመሎቻቸው የንግድ እቃዎቻቸውን ጭነው በሚሄዱበት ሰዓት የበረሃ ውሾት በጣም ቢጮሁባቸውም እነሱ ላይ ድንጋይ በመወርወር ጊዜን አያባክኑም፤ ምክንያቱም የውሾቹ መጮህ ግመሉን ከጉዞው አያቆመውምና።
በአንድ ወቅት የእንግሊዝ መሪ የነበረው ዊንስተን ቸርችልም ይህንን ብሎ ነበር...
"ባንተ ላይ ለሚጮህ ውሻ ሁሉ እየቆምክ ድንጋይ የምትወረውር ከሆነ ከአላማህ በቶሎ አትደርስም" ንግግሩ እውነታን ያዘለም ነው። መልስ ለሚገባው እንጂ ለተናገረ ሁሉ መልስ መስጠት አግባብ አይደለም የጊዜ ብክነትም ነው። ምክንያቱም አንዳንዶች የሚጮሁት ትክክለኛ ጥያቄን እና መልእክትን ይዘው ሳይሆን እኛን ከመስመራችን አስወጥተው ከራሳቸው ጎራ ለመመደብ ነውና። ስለዚህ የጋሽ ስብሐት መልእክትም ለኔ ያ ይመስለኛል መልስ መስጠት ሲኖርብህ ብቻ መልስ ስጥ እንጂ ባንተ መልስ ለሚነግድ እና ለሚያተርፍ መጠቀሚያ አትሁን ነው።

📖 ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል
✍ ንባብ ለሕይወት

@fe_ash
@fe_ash

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

.🕠በዕውነት ጊዜ ንጉስ ነውን???👩‍🍳🕵

ጀንበር ልጠልቅ ነው! እኔም ብቻዬን ብዙም ሰው የማያዘወትረውን ረዘም ያለ ቀጭን መንገድ 🎧በ earphone መዝሙር እያዳመጥኩ እየሄድኩ ሳለ ሁለት በዕድሜ አቻ👯‍♂ የሚሆኑ ሰዎች ተጠጋግተው ቆመዋል .........እኔም በውስጤ ምነው እነዚህ ሰዎች 🗣🗣ኮረና ጉንፋንም አልመሰላቸው! እያልኩ 🎶የመዝሙሩን ድምጽ እየቀነስኩ ቀረብኩ......እነርሱም ክርክር ያዘለ ወግ ይዘዋል መሰል በሽታውን ረስተውታል.......በዚህ መኃል አንደኛው ሰዉዬ ራስ ምታት የያዘው ይመስል ደም-ስሮቹ ቆመውበት ከፍ ባለ ድምፅ 🎤"ግድ የለም ጊዜ ንጉስ ነውና ይሰጣል ይነሳልም! ፣ ዛሬ ላንተ እንደሰጠ ነገ ለኔ ይሰጥ ይሆናል ....
ወይ አንቺ ጊዜ ለአንዱ ሹመትን
ትሰጭ የለም ወይ ለሌላው ሽረትን "እያለ ራሱን እያነቀነቀ ሄደ ..........እኔም እየተጓዝኩ ጊዜ ነው?ወይስ ጌታ ነው? ንጉስ ብዬ ራሴን ጠየኩ መልስም አላገኘሁምና .....ጥያቄውም እንደህሊና ጩኸት ከፍ ያለ ግን ደግሞ ለጎረቤት የማይሰማ ሆኖ ተቸገርኩ.......ከዚያም ቤት እንደዋዛ ቁጭ ያለው መጽሐፍ ቅዱስ ለጥያቄ ሁሉ መልስ ነውና ገና በመጽሐፉ ጅማሬ መልስ አገኘሁ።
መልሱም እንዲህ ነው ፦
ጊዜ ለሁሉም ፍጡር መለኪያ ሲሆን ለእግዚአብሔር ግን አገልጋይ ነው። የአገራችን ሰዎች "ጊዜ ንጉስ ነው ፣ጊዜ ይስጥልን "ይላሉ ። ይህ አበባል ምንም ብያግባባን እንኳን ጊዜን ሰጭም ነሽም ያደረገ ስለሆነ ብዙ ሰው እግዚአብሔርንና ተግቶ ሥራን መስራት ትቶ እጁን አጣጥፎ ከጊዜ ደግነትን እንድጠብቅ አድርጎታል።
ጊዜ በራሱ ምንም ነገር ሊያድል የሚችል ሰጭ ወይም ነሽ አይደለም ፤መስጠትንም ሆነ መከልከል የሚችለው የጊዜ ፈጣሪ ፣ለጊዜ መነሻንም ሆነ መድረሻን ያበጀ ፣ከዘመን ውጭ የሆነ ፣በዘመን ውስጥ የሚሰራ ፣የጊዜ ንጉስ፣የዘመን ጌታ ፣የቀኖች ባለቤት እግዚአብሔር ነው ...............ጊዜ ለሰው ልጆች በሙሉ እንደ ቁመት መለኪያ ሜትር ፣እንደ ክብደት መለኪያ ኪሎግራም የተሰጠ የዕድሜ መለኪያ ነው። ................(..ዘፍ 1,ዮሐ 1:3,መዝ 90,መክ 3:1)

....ተፃፈ በወልዴ ልጅ ወንዱ
በወረሃ ግንቦት በቀነ አሃዱ........

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

#አንተ የልቤ ሌባ

ልቤን ሰርቀህብኝ ርቀህ ኮበለልክ
እኔ እንዳላገኝህ በፍቅሬ ተከለልክ
እሱስ መስሎህ እንጂ መቼም ከእኔ አትርቀኝ
አይኔ ባያይህም በልቤ አለኸኝ
ምንም አልፈልግም ፍቅርህ ነው የራበኝ
ፍቅርህ በኔ ነግሶ ዝም አላስብል ቢለኝ
ብዕሬን አነሳሁ ላንተ ቅኔ ልቀኝ
ቅኔ ልቀኝልህ ቃላት ብፈልግም
ላንተ የሚሆን አጣው ፍቅሬ አይገልፅህም
እንደ እህል እንደ ውሃ አይኔ ይራብሀል
ድምፅህ የጠፍ ዕለት ልቤ ይሸበራል
ምንም ቃላት ባጣ ፍቅሬን የሚገልፅልኝ
ሰማይ ላይ አፈጠጥኩ ፈልጌ ሚመክረኝ
ሰማይ ላይ ያለ አንድ ኮከብ አየው
ከሌሎቹ ልቆ
እናም ቃል ገባልኝ ፍቅሬን ሊፅፍልኝ በክዋክብት አድምቆ
ልክ እንደ ጨረቃ ስትሄድ እየሄደ ስትቆም የሚቆም
ላንተ ብቻ የሚታይ የፍቅሬ ቃል ቀለም
ይሄን ቃል ገብቶልኝ ከአይኔ ተሰወረ
ሳላመሰግነው ከኮከቦቹ ጋር ተቀነባበረ
እጅግ ደስ ብሎኝ አይኔን እያማተርኩ
ፅሁፍን ፈለኩት
ውይይይ ላንተ ብቻ እንደሚታይ ቀድሞ የነገረኝ በድንገት ትዝ አለኝ።
እንደው የኔ ፍቅር ስታየው ምን አሰብክ
የራበኝን ፍቅር ልትመግበኝ ወሠንክ
የኔ የልቤ ሌባ በጣም እወድሃለሁ ❤️
ላንተ ያለኝን ፍቅር የትኛውም ቃላት ችሎ እንኳን አይገልፀውም

Tewedadari1⃣3⃣HANNA
@Fe_ash

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

ምድር ተናገረች
H.S

ምድር ጉዷ በዛ
ታሪኳዋ ተንዛዛ
ምድር ማቅ ለበሰች
አብዝታ አልቅሳ
ህዝቦቿ በተራ
ረገፉ በገራ
የመጣው ማእበል
ሳይሰስት ሳይራራ
ጠራርጓቸው ሄደ
ሁሉን በየተራ
ያኔ ስነግራቹ
ተው እያልኳቹ
አያዘልቅ ይህ መንገድ
ብዬ ስመክራቹ
አልሰማ ብላቹ
ይኸው ጉድ ሆናቹ
አለች ተናገረች
ምድር አፍ አውጥታ
ምድር አለቀሰች
አነባች አብዝታ
ለራሷ ሳታስብ
ለህዝቦቿ ሰግታ

እንዴት ተሳናቹ
ማሰብ አርቃቹ
እውቀት ፍልስፍና
ሁሉን ጀምራቹ
ያለፍቅር ደስታ
ያለ ህብረት ስኬት
ያለ አንድነት ተድላ
የለም ታውቃላቹ

ታድያ ለምን ይሆን
ይህ ክፋታቹ
በዘር በሀይማኖት
መነካከሳቹ
አለች ተናገረች
ምድር አፍ አውጥታ

እኔም በተራዬ
በአይኔ እንባ አዝዬ
መች ነው የሚያቆመው
ይህ ጉድ ሚያበቃው
ብዬ ስጠይቃት
ምድርን በፍርሀት
እሷምእንዲ ህአለች......................

የክፋት መርዛቹን
መርጨት ካቆማቹ
ትላልቅ ሀያላን
ሀገርን ትታቹ
የራሳቹን ሀገር
ውድድ ካረጋቹ
ሁሉም የኔ የኔ
ማለት ከተዋቹ
ሁሉን ለኔ ለኔ
ማለት ካቆማቹ
ያኔ ሁሉም ያልፋል
ማዕበሉም ይሰክናል
ሁሉም በየተራ
ቀስ ብሎ ይነጉዳል
አለች ተናገረች
ምድር አፍ አውጥታ
😔😔😔😔😔
Tewedadari9⃣WELWA SEID

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

ሀገር ማለት ምስጢር
ጦቢያ ማለት ቅኔ
ስትሰጥ ምትኖር የማታውቅ ለኔ
ስሙዋ ሁሌ ሰም ነው
ትርጉሟ ወርቅ ነው
ይሄ ወርቅነቷ ያልተነገረላት
ስንቶች ለሷ ብለው ደም የገበሩላት
ቅኔዋ ገብቷቸው ዋጋ የከፈሉላት
ሀገሬ ውበት ናት ቀለም የሞላባት
ኢትዮጵያ ማለት ለአለም እንቁ ናት
ግን ዋጋዋ ያልገባቸው ጎለው አጎደሉዋት
የልጆቹዋን ሀዘን እሹሩሩ ባለች
ክህደት ቀጥፈቱን ችላቸው በኖረች
አይራቡ ልጆቼ ብላ ባጎረሰች
እማይገባትን ያህል ተጎሰቋቆለች
ዛሬስ ተነስቶዋል ጦቢያን ሊያጠፉዋት
እማያልቅ ዉበቷን መጠው ሊጨርሷት
ልጆችዋን በሙሉ ከጉያዋ ነጥቀው
እስኮላር እያሉ አፍሰው ወሰዱባት
እውነት ለዚች ሀገር ይሄ ነዉ ሚገባት?
እቺ ምስኪን ሀገር ጀርባዋ የጎበጠው
ጉልበቷ የቆሰለው ልጇ ቀና እንዲል ነወ
ወትሮም ከጅ ያለ ወርቅ ቁጥሩ ከመዳብ ነዉ
ባይገባቸው እንጂ ምድሯ ፍቅር ነው
እኛን ልትኖረን ተንገዳግዳ ብትቆም
ልደግፍሽ የለ ላይ ለይዋን በኩርኩም
እንደ ሻማ ሆና ለኛ ብርሀን ልትሰጥ ራሱዋን ባቀለጠች
ቀና ያለች ሀገር ዛሬ አንገቷን ደፋች
እልፍ ዉሀን ይዛ ልጁዋ ተጠማው ሲል
ለም መሬት እያላት ልጁዋ ተራብኩ ሲል
እቺ እናት ሀገር ምን ተሰምቷት ይሆን
ውለታዋን መርሳት ፀፀት እንዳይሆንብን
ዉበት ተፈጥሮዋን ድህነት በልቶታል
እዉነት ደግነቷን ጥላቻ አጥፋቶታል
በሀዘን በህመም ፊቷ አፈር ቢመስልም
ይቺ ቅኔ ሀገር እንዲ አንገቷን ደፍታ
መቼም አትቀርም
ፍቅር የቸራት አምላክ እንዲሁ አይተዋትም
ቅርብ ነዉ ዘመንዋ ጦቢያ ትንሳኤዋ
በዘመን ሸራ ላይ ይሰፋራል ታሪኳ
የነ ናምሩድ ሀገር የነ ኢቴል ሀገር
ቅኔ ነው ትረጉሟ ድንቅ ነዉ ውበቷ።
Tewedadari7⃣FKR

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

🇪🇹ሀገር🇪🇹
ሀገር ሀገር አሉ
ውስብስብ ነው ውሉ
ሜዳና ገደሉ ጋራ ሸንተረሩ
ከተማና ቅየው ሰፈሩ መንደሩ
መድመቅያህ የሆነው ያ መልከአምድሩ
ማንነት እኮ ነው የሀገር አፈሩ
አፈርህን ሲነኩ ሀገርህን ነው የነኩ
ታጥቀህ ተነስና በላቸው አትንኩ
ውብ መልከአምድሩ ቢሆንም ሀገሩ
በዚ ብቻ አይፈታ የሀገር ሚስጥሩ
ሀገርማ.........
አይደለም መሬቱ
ወንዙና ተራራው
አይደለም ግዑዙ
ውቅያኖስ ፏፏቴው
ድንበሩ አይደለም
የሀገር ትርጉም።
ሀገርማ........
ብዙ ነው ነገሩ
ውስብስብ ነው ግብሩ
አድምጠኝ ወጣት ሆይ.........
ሀገርማ ላንተ ናት እኮ ህዝቦቿ
አንተ ስትወልድ ያነሱህ እጆቿ
እልል ያሉልህ አንተን ተቀብለው
መሬት ያወጁልህ እትብትህን ቀብረው
አብልተው ያሳደጉህ ያላቸውን ቆርሰው
ስትድህ በዳዴ እሠይ እሠይ ብለው
ለዚህ ያደረሰህ ሀገርህ ህዝብህ ነው
አርቀህ አስበው ይሄ ነው ሀገርህ
መሆኑን አትርሳ ህዝቦቿ ወገንህ
ስትታመም ግዜ አልረዳህ ተራራው
ሜዳው ሸንተረሩ ሸለቆ ና ጋራው
አልደረሱልህም አይዞህ ባይህ ሆነው
በደስታህ ግዜ አልሆኑልህ ድምቀት
ግና ወገንህ ነው ማይተውህ በእውነት
ስትታመም ግዜ ደግፎ አስታሞ
ላንተ የሚለፋ እራሱን አድክሞ
ስትሞት አልቅሶ በወጉ አክብሮ
ቀባሪህ ህዝብ ነው ጉድጓድህን ቆፍሮ
እናልህ ወገኔ ህዝቦችህን ውደድ
በዘር ምናምንቴ ከቶ አትሸወድ
የሁሉ መነሻ አንድ ሆኖ እያለ
በዘር ተከፋፍሎ ህዝቤ ተጋደለ
ብሔር ብሔረሰብ ነው እኮ መዋብያ
ቢገባህ ልዩ ውበት ለውዲቷ ጦብያ
አትርሳ ምክንያቱን ለመረዳት ለአድዋ ድሉ
ነው በአንድ መንፈስ ስለተጋደሉ
አንውጣ ከሀገር በዲቪም በስደት
ምን ምቾት ቢሞላ አይሆነን እንደናት
ባንተ ተስፋ አላት ውዲቷ ሀገርህ
የድርሻህን አድርስ እንደ ዜግነትህ
የባዕድ ሀገር ፍቅር ከልብህ ይውጣና
ሀገርህን ውደድ በንፁ ልቦና
ወጣት ሆይ ተነሳ በአንድነት ዝመት
ሀገርን ለመውደድ ለማጥፋት ድህነት
ብለብዙ ታሪክ አለችን ውብ ሀገር
ያባቶቻችን ደም ያቆማት በክብር
ለስርዓት ያደረች ባሕል ወግ ያኖራት
የሀይማኖት ድምቀት በዝቶ የታየባት
ከታሪኳ ዶሴ ብዙ ያልተዜመላት
ይች ሀገራችን እጅጉን ኩራት ናት
የቀደምት ታሪክ የሠው ዘር መገኛ
ገና ምን ታየና ትደምቃለች በኛ
ለእናት ሀገራችን እኛም ነን አርበኛ
ብዙ ተስፋ አላት ታላቋ ኢትዮጵያ
ትውልድ ያደምቅሻል ውዷ አቢሲኒያ።😘
Tewedadari5⃣ REEHI

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

☞እንዴት ቻሉበት ግን☜
እንዴት ቻሉበት ግን
እንዴት አስቻላቸው
እንዴት አይችሉበት
የወንድሞች ከሳሽ እየመከራቸው
ሆነው ባልጋቸው ላይ
ሳሉ በመኝታ
ምነው በጎውን ቢያይ
ምናባቸው ላፍታ
ፅልመት እየሳሉ
ሐዘን የሚያለብሱ
ጉርጓድ ምሰው ቀብረው
አፈር ሚመልሱ
ያላቸው ሸንጋይ እጅ
ውሉ ማይታወቅ
ከላይ እያቀፈ
በስውር የሚያንቅ
እንዴት ቻሉበት ግን
በስውር እጃቸው
ከፍለው ሁለት ጎራ
አማዘውን ካራ
ባላወቅነው ነገር ሰንፋጅላቸው
በኛ መጨራረስ ደለበ ኪሳቸው
ሲያረጅ ጎራዴአችን
ሆነው ሞረዳችን
ሲያልቅብን ጎራዴ
ሰያቀርቡልን ባንዴ
ሲሸጡልን በገፍ
ሲፈስ ደም እንደ ጎርፍ
እንዴት አስቻላቸው
እንዴት አይችሉበት
ደም አፍሳሹ መንፈስ
ገብቶ በልባቸው
እንዴት ቻሉበት ግን
አንድ የነበርነውን
ከፍለው ብዙ ቦታ
እንዳላጫረሱን
እያስሳቡን ቃታ
እጃቸው ቢገባ
የፈለጉት እንቁ
እንደ ተቆርቋሪ
ይሉናል ታረቁ
የአዞ እንባ እያነቡ
የአዞ ጥርሳቸውን
አየደባበቁ
እንዴት አስቻላቸው
እንዴት አይችሉበት
የጨለማው ገዢ
እየመከራቸው
ፍርድ አይመጣ ይመስል
የማይደርስ ቀኑ
ሺ ቢዘባነኑ
ትእግስት ስለበዛ
ግፋቸው ቢበዛ
የቁጣውም ጽዋ
ስትፈስስ ሞልታ
እነዚህ ግፈኞች
ይጠፋሉ ባፍታ
ፍርዱን በጽድቅ ሲገልጥ
ጻድቅ ፈራጅ ጌታ፡፡
Tewedadari2⃣HENOK

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

ጓደኝነት
ሰላምታዬ ከልቤ ነው።እንደምን አመሻችሁ በዛሬ ውሎዬ አንድ ነገር እያሰብኩ ነበር።ልንገራችሁ እናንተም አንብቡት።ወንድም እህቶቼ ተሰብስበው የኢትዬጲያ ልጆች እያዩ ነበር እርግጠኛ ባልሆንም አንቺም አብረሻቸው እያየሽ ነው እንደምትሉኝ😁 አደለም እኔ የራሴን ስራ እየሰራው ነበር ትኩረቴንም እሱ ላይ ነበር ያደረኩት ግን አንድ ነገር ትኩረቴን ሰረቀው።ምን እንዳትሉኝ ልነግራችሁ ስለሆነ እናም የመጀመሪያው ፕሮግራም አልቆ ወደ ቀጣዩ ፕሮግራም ተሸጋገሩ።የጀመረው ኘሮግራም ስለ "እርሳስ"አፈጣጠር ነበር።እና ይህን ከጓደኝነት ጋር ምን ያገናኘዋል ብትሉኝ መልስ አለኝ።አድምጡኝ እርሳስ ያለ ማጥፊያ አይፈጠርም ምክንያቱም ስህተቱን የሚያጠፋለት ማጥፊያው ስለሆነ።አንዳቸው ለአንዳቸው አስፈላጊ ናቸውና።እኛስ ? አዎ እኛስ? የኛን ስህተት የሚያስተካክሉልን ጓደኞች አሉን ይህ ብቻ አይደለም እኛስ ጓደኞቻችንን ከተሳሳቱበት መንገድ እንመልሳቸዋለን ወይስ ስህተታቸውን ሳያርሙ እንዲቀጥሉ ዝምታን መርጠናል?እራሳችንን እንጠይቅ እኔ ከራሴ ጋር በደንብ እያወራው ነው።እኔ ለጓደኞቼ መልካም ነኝ የሚለውንም ጨምሮ ይህን ስላቹ በጓደኝነት ጊዜ ውስጥ እነሱ ለኔ በችግሬ ጊዜ ደርሰውልኛል።እኔስ ?
እነሱ እኔን ከጥፋቴ መልሰውኛል።እኔስ?
እነሱ ለኔ መልካም ሆነው ተገኝተዋል።እኔስ?
ብዙ ብዙ ነገሮች አሉ ግን እኔስ የሚለውን አትርሱ አስተውሉ መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ አስተውሉ።አንድ ነገር ሳረሳ ልንገራቹ በጓደኝነት ውስጥ "ይቅርታ"የምትለዋ ቃል ወሳኝ ናት ይቅርታ መጠየቅም እንዲሁም ይቅር ማለትን አትርሱ።ይሄ ሁሉ የኔ ሀሳብ ነው እናንተስ ምን ትላላቹ አስቡበት።
ተባረኩልኝ🙏
#Janet
@Artisticallife

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

1de ስሙኝማ እዚ ቻናል ላይ የሚለቀቀው የትኛውም link የኛ አለመሆኑን እንገልፃለን።


ካሁን በኋላ link አናበዛባችሁም።🙏🙏🙏🙏
❤️

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

Endesu srawechachun mastewawek mtfelgu
@genet5
@fev1bnAaE
Lay lkuln... ❤️

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

😔ግር ያላት ነብስ😔
📘ተከታታይ ልበ-ወለድ📘

✍@Artisticallife 💐

ክፍል 3⃣
---------------""""""""""""""--------------------


.............የማየውን ማመን አልቻልኩም አባቴ እና ማህሌት ሶፋው ላይ ልክ በፊት የእናቴን ፀጉር እንደሚያሻሽላት ፍቅር በፍቅር ሆነው አየሁ ደነገጥኩ እናቴ ገና ከመሞቷ አመት ሳይሞላት ያውም የገዛ ጓደኛዋን? አባቴ ምን ነክቶታልእሷስ የጓደኛዋን ባል አታፍርም ሆ... ይሄን ሁሉ ማስበው ፊት ለፊታቸውተገትሬ ነው እነሱ እንኳን ሊያዩኝ ሰው እንዳለም አላስተዋሉም ተመልሼ ወደ ክላሴ ገባው ምን ልበላቹ በቃላት የማልገልፀው ህመም ልቤን ተሰማኝ ሀዘን ላይ ሀዘን ተፈራረቀብኝ እነኚ ሰዎች አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንዲማ አይቀራረቡም እናቴ እያለችም የሆነ ነገር ቢጀምሩ እንጂ ውስጤ የተለያዩ ነገሮችን በማውጣት በማውረድ ዝሏል የሚገርመው ማልቀስ አልፈልግም ግን እንባዬ ገደብ በሌለው መልኩ ይወርዳል ። ምነው አምላኬ ፈረድክብኝ ምነው ሀዘን እንዲያቆራምተኝ ፈቀድክለት ውስጤ ዛለ በሀዘን ጠወለኩ የምናገረው ሁሉ ጠፋኝ እንባዬ ሊቆም አልቻለም ።

💐💐 @Artisticallife 💐💐

አእምሮዬ ሰላም ናፈቀው ሳወጣና ሳወርድ እንቅልፍ ወስዶኝ ኖሯል ድንገት ነቃሁ ጨልሟል በቀን ስለተኛሁ የክፍሌ መብራት አልበራም አልጋዬ አጠገብ ያለው ሳጥን ላይ እጄን ሰድጄ ስዳብስ ስልኬ አበራሁት እና ሰአት ሳይ ከለሊቱ 9ሰአት ይላል ቀን በሚሊ ንዴት ምሳ አልበላሁም እራቴንም በአባቴ እና በማህሌት ምሬት ሳልበላ ተኛሁ ረሀቡ እየሞረሞረኝ ነው እናቴ እኮ ብተኛ እንኳን ቀስቅሳ ታበላኝ ነበር ሁሉም አጋጣሚዎች ለሀዘን ይዳርጉኛል አይኔ በጣም ከማልቀሴ የተነሳ አብጧል በቃ ከለቅሶ ውጪ ምንም አይቀናኝም ኡፍፍፍፍፍፍፍ አሁንስ ደከመኝ ማንም ሊያፅናናኝ የሚቀርበኝ የለም ችግሬን ሚጠይቀኝም የለም በለቅሶ እራሴን ነው ምጎዳው እየራበኝ እንደምንም ተኛሁ ሰው በራሱ ቤት ባዕድ ይሆናል? እናት ለዘላለም ትኑር ❤️❤️

💐💐 @Artisticallife 💐💐

እናም ዛሬ ሰኞ ነው ስለራበኝ በጠዋት ተነስቼ ቁርሴን በልቼ ወደት/ት ቤት ሄድኩ ክላስ ስገባ ጀሚላ አብራኝ ምትቀመጥ የክላስ ልጅ ናት ገና አይታኝ ሩሀ ምነው አሞሻል አለችኝ? ምነው አልኳት ጠቋቆርሽብኝ ደግሞም ደካከምሽ አለችኝ እናቴ ነበረች እንደደበረኝ ስትነግረኝ ጠቋቆርሽ ምትለኝ እንባ እያነቀኝ ሄጄ ተቀመጥኩ ጀሚላ መልካም ሴት ናት ትንሽ ስለ ወንጌል ሳነሳባት ትናደዳለች እንጂ ቢሆንም ትሰማኛለች የሆንኩትን ሳልነግራት አለቀሰች ስነግራት ደግሞ እኔ ዋናዋ እያለሁ እሷ ባሰች እኔው ላባብላት ሞከርኩ ትንሽ ተረጋጋን እና አስተማሪ ገብቶ አስከረፍት ሁለታችንም መማር አልቻልንም ልክ እረፍት ሲደርስ ከነ ሚሊ ጋ ምንሰበሰብበት ቦታ ከሁሉም ቀድሜ ሄድኩ በተራ ተራ አየመጡ ተሰባሰብን ሰላምታ እየተለዋወጥን ቀልድ ሳቅ ተጀመረ በዚህ ሁሉ ሰአት ሚሊ አልመጣም ነበር ሚስቁት ሚቀልዱት አንድ አይሰማኝም የሚሊን መምጣት በጉጉት እየጠበኩ መንገድ መንገዱን አያለው ልክ ሊደወል ባለቀ ሰአት ሚሊ መጣ ደስ አለኝ አቤት ሞገስ እንዴት እንደሚያምር እኮ ልክ ሲደርስ እኔ ፈገግ እንዳልኩ ነው ሁሉንም ሰላም አላቸው ና እኔን እንደማያውቀኝ ዝም አለኝ እንዴት እንደከፋኝ ምን ብዬ ላስረዳቹ

💐💐 @Artisticallife 💐💐

ባለቀ ሰአት ስለመጣ ወደ ክፍል ልንገባ ሁላችንም ተነሳን ሚሊ እና እስከዳር እየቀለዱ ተቃቅፈው አልሄዱም እነቂያት እነቂያት አለኝ ቀናሁ እንዴ? ኸረ በክርስቲያን አያምርም ደግሞ ለኔ ምንም ግድ ለማይሰጠው ሰው የምን እንዲ መሆን ነው ብዬ እልና ሳያቸው ጨጓራዬ ጨሰብቻ ምን አለፋቹ በንዴት መፈንዳት ነው የቀረኝ
💐💐 @Artisticallife 💐💐

ከእረፍት በኋላ መማር ስላቃተኝ አስፈቅጄ ወደ ቤቴ ገባሁ ።

..............ይቀጥላል.............
Join & share 👇👇👇👇
💐💐 @Artisticallife 💐💐
💐💐 @Artisticallife 💐💐

------------"""""""""""""""""""""----------
🙏 ተ ባ ረ ኩ 🙏

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

😔ግር ያላት ነብስ😔
📘ተከታታይ ልበ-ወለድ📘

✍ @Artisticallife 💐
ክፍል1⃣
ዛሬ ቀኑ ቅዳሜ ነው ቅዳሜን ለእኔ ለየት የሚያደርገው የart ቲማችን የፀሎት እና የጥናት ቀናችን ነው ለዛም ነው በጠዋት የነቃሁት አሁን ከጠዋቱ 11:56 ይላል ትንሽ ብርድ ስለሆነ እስከ 1 ሰአት ልተኛ ብዬ በኤርፎን የቤቲን ምህረቱን አስቤ አቤት ስል..... የሚለውን መዝሙር እያዳመጥኩ ተመስጫለሁ ሳላውቅ በዚያው አሸለበኝ ሩሀ .. ሩሀ ... አንቺ ሩሀ ባንኜ ተነሳሁ እናቴ የክፍሌን በር እየደበደበች ትጠራኛለች ስሜ ሩሀማ ነው እናቴ ና የቅርብ ጓደኞቼ ሩሀ ይሉኛል ።
💐💐 @Artisticallife 💐💐

በሩን ከፈትኩላት አይኔን እያሻሸው ስወጣ አንቺ ልጅ 3 ሰአት ሆነልሽ ቅዳሜ መሆኑን ረሳሽ በይ ተነሽ ብላኝ ሄደች እሺ ብያት ወደ መኝታዬ ሄድኩና ኤርፎኑን ከስልኬ ነቅዬ መፅሀፍትና የመዋቢያ እቃዎቼን የማስቀምጥበት መደርደሪያ ላይ አረኩት መኝታዬን አነጣጥፌ ፒጃማዬን ቀይሬ ቅዳሜን የሚመጥን አለባበስ ለብሼ ወጣሁ ፊቴን ታጥቤ ወደ ሳሎን ሳቀና እቤት እንግዳ አለ ማህሌት ነበረች ማህሌት የእማ ጓደኛ ናት በቃ እኛ ቤት አትጠፋም አንዳንዴማ ከእኛ ጋር ምትኖር ነው ሚመስለኝ ጠዋት ስነሳ አላጣትም ከእማ ጋር አብረው ወደ ቢሮ ይሄዳሉ ማታ እኔ ክላሴ ስገባ እሰበ ቤት ናት ብቻ ባጭሩ የእማ ጓደኛ ናት

💐💐 @Artisticallife 💐💐

እየሳቁብኝ እስከ 3 ሰአት እንቅልፋም እያሉ አበሸቁኝ ቁርሴን በልቼ የማጥበውን ልብስ ላወጣ ክላሴ ገባሁ ከዛ እማ ጠርታኝ አባትሽ አንድ ሁለት ልብስ ትጠብልኝ ብሏል ብላኝ የመኝታ ቤታቸውን ቁልፍ ሰጠችኝ የቆሸሹ ልብሶችን ሁሉ ወሰድኩና ቁልፉን መልሼላት ልብስ ሳጥብ አረፈድኩ 9ሰአት እስኪሆን ጨንቆኛል አሰሬ ሰአት አያለሁ ሻወር ወስጄ ፀጉሬን ተሰርቼ የማይደርስ የለ ወደ ጓጓሁለት ቸርች ሄድኩ 8:40 ይላል ሰአቴ ስደርስ ሚሊ እና ናቲ የአዳራሹ ውሀ ልክ ላይ ተቀምጠው እየተሳሳቁ ስልካቸውን ይጎረጉራሉ ከእሩቅ አይተውኘሸ ፈገግ አሉልኝ ሶስታችን ሰአት በማክበር እንታወቃለን አጠገባቸው ስደርስ ሁለቱም ከተቀመጡበት ተነስተው ሰላም አሉኝ ና እንድቀመጥ ጋበዙኝ ትንሽ እንደቆየን ከነአን እና ሀና መጡ ቲማችን በጣም ደስ የሚል ነው በነገራችን ላይ ሚሊዮን{ሚሊ} የቲማችን መሪ ነው በቃ ደስ የሚል መንፈሳዊነቱ አስተሳሰቡ ለቲማችን ወሳኝ ሰው ነው ከማውቃቸው ሰዎች ሁሉ ይለያል ብቻ ምን አለፋቹ በጣም ጥሩ ልጅ ነው ከዛም ፕሮግራማችንን ጀመርን ደስ በሚል ሁኔታ 11:30 አበቃን እንደ አመላችን ፎቶ እየተነሳን እየሳቅን መጓዝ ጀመርን የኛ ቤት ከቸርቻችን ትንሽ ይርቃል የሚሊና የእስከዳር አንድ ሰፈር ስለሆነ ሁለቱ እኔን ሊሸኙኝ ለሶስት እየተሳሳቅን ሰፈሬ ደረስን ሰፈር ስንደርስ ያልጠበኩት ነገር አጋጠመኝ ሶስታችንም ደነገጥን ሚሊ ሩሀ ምንድነው አለኝ እኔ ምን አውቃለሁ አልኩት በተቆራረጠ ትንፈሽ ድንኳን ተጥሎ በር ላይ ብዙ መኪና ነበር እራሴን መቆጣጠር አልቻልኩም እየሮጥኩ ወደ ጊቢ ገባሁ ሚሊ እና አስከዳርም እሮጠው ተከተሉኝ ልክ ቤት ስገባ..........
.......ይቀጥላል......

💐💐 @Artisticallife 💐💐
----------"""""""""""""""""""""""----------
☝️☝️☝️join& share👆👆👆

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

@neba166

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

@Neba166

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

@neba166

Читать полностью…

የኛ ትምህርት

ከጋብሮቮዎች



.....ምሳ ከበሉ በኋላ አጥንቱን ለጥርስ መሰቅሰቂያ ያጠራቅሙታል ይባላል ።ለቤታቸዉ ጢስ ማዉጫ መጥረጊያ እንዳገዙ ድመቶቻቸዉን ጢስ መዉጫዉ ዉስጥ ይወረዉራሉ ይባላል ።ቤት ሲከረዪ በተቻለ መጠን የመንገድመብራት መስኮታቸዉ አጠገብ መኖሩን አረጋግጠዉ ነዉ።ማታ ማታ የዶሮ ቤታቸዉ ላይ መብራት ያበራሉ ዶሮዎቻቸዉ ቀን መስሏቸዉ እንቁላል እንዲጥሉላቸዉ😂 ።ለንግድ ወደ ዉጪ አገር ሲሄዱ ሾርባ የሚያዘጋጁት በህብረት አንድ ማሰሮ ዉስጥ ነዉ።ሆኖም እያንዳንዳቸው የረሱ ቁራጭ ስጋ😜 ለይ ልዩ ምልክት ያደርጋል ያንዱን ስጋ ሌላው እንዳይበላበት።
ከወደዱት ሼር ያርጉ

* * * * *
📝 feven ነኝ
ምንጭ ➺ቀልዶች ከጋብሮቮ ምድር ከተሰኘው መፅሐፍ።
Tnk u😍
@fe_ash
@fe_ash
@fe_ash
@fe_ash

Читать полностью…
Subscribe to a channel