ethio_stories | Unsorted

Telegram-канал ethio_stories - Motivational Stories

253

Explaining life-sustaining sayings, stories, inspirational thoughts and ideas that encourage me to achieve success will be explored. Group @ethio_motive #To_make_any_comments_and_question      👉 @Ethio_motivatedbot

Subscribe to a channel

Motivational Stories

#What_can_I_do_to_change_this?
Although I don’t know your specific situation, I will say this: you’re young. You have time, and time is the most valuable thing in the world. In considering the most valuable resource, I would place time above money, above experience, above connections.
Why do you feel like your life is going nowhere? Are you comparing yourself to your peers? If so, stop it.
Right now you are stuck in the mindset of thinking about the things you don’t have, and that is a surefire way to make yourself miserable. Learn to love the things that you fill your time with. Work hard. Success will come.

Читать полностью…

Motivational Stories

You are under no obligation to remain the same person you were a year ago, a month ago, or even a day ago.

You are here to create yourself, continuously.

—Professor Richard Feynman
🔥 @Ethio_Stories 🔥

Читать полностью…

Motivational Stories

Life is much more than we think and stuck in-
Seek more,
dream more,
do more..
Life is too short for regrets..
You can think, thinking can give you an idea and with a proper action with right direction, you can apply the ideas to fulfill your dreams..





@Ethio_Stories

Читать полностью…

Motivational Stories

"Mistakes are Proof that you are trying"

@Ethio_Stories

Читать полностью…

Motivational Stories

#ሰዎች_ሲሳሳቱ . . .

በሕይወታችን በሚዛናዊነት ልንይዛቸው ከሚገቡን ወሳኝ ነገሮች መካከል በአካባቢያችን የሚገኙ ሰዎች፣ በተለይም የየእለት የኑሮ ስምሪታችን የሚያገናኘን ሰዎች ስህተት ሲሰሩ የምንሰጠው ምላሽ ቀንደኛው ነው፡፡ ከሰዎች ጋር የምናሳልፈው ጊዜ በበዛ ቁጥር ሰዎቹ ስህተት ሲሰሩ ማየታችን አይቀርም፡፡

የቤተሰብ አባሎቻችን፣ የትዳር አጋራች፣ የቅርብ ጓደኞቻችን፣ የስራ ባልደረቦቻችን፣ አለቆቻችን፣ የሃገር መሪዎቻችንና . . . ካለማቋረጥ ስህተትን ይሰራሉ፡፡ ለዚህ አይቀሬ ግላዊም ሆነ ማሕበራዊ ሂደት የምንሰጠው ምላሽ ሚዛናዊነት ለግልም ሆነ ለማሕበራዊ ስኬታችን እጅግ ወሳኝ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡

አብዛኛዎቻችን ከአስተዳደጋችን ለስህተታችን ምህረት ሳይደረግልን ከላይ ከላዩ ተጠብጥበን ስላደግን ሁኔታው አሁን ለሰዎች ስህተት ምህረት-የለሽ እንድንሆን ተጽእኖ አድርጎብናል፡፡ ስለዚህም፣ ለሁሉም ስህተት ጨከን ማለት ሚዛናችንን ስለሚያስተን መቼ ጠንከር፣ መቼ ደግሞ ለስለስ ማለት እንደሚገባን ማሰብ ታላቅ ሚዛናዊነትን ይሰጠናል፡፡

በቃ! የለመድነው መውቀስና መወቀስ፣ መምታትና መመታት፣ ማማትና መታማት፣ ስም ማጥፋትና ስም መጥፋት . . . ስለሆነ ስህተትን አይቶ በቀላሉ የማለፍን ጉዳይ ሆን ብለን ለራሳችን ካላስተማርነው በስተቀር ያስቸግረናል፡፡ ምንም ስህተትን በማያሳልፍና በተሳሳተን ሰው ላይ ልክ እንደወደቀ ዛፍ ሁሉም ሰው መጥረቢያውን በሚሰነዝርበት ሕብረተሰብ መካከል ስንኖር የምህረት፣ የይቅርታና አንዳንድ ጊዜ “ይሁን” ብለን አለፍ የምንል አይነት “አብሪ ኮከቦች” እንድነሆን የሚከተሉት ሃሳቦች ያግዙናል ብዬ አስባለሁ፡፡

አብዛኛውን ጊዜ ስህተት በሰሩ ሰዎች ላይ የመጨከን ዝንባሌችን የሚገናኘው ከማናውቃቸው ነገሮች የተነሳ ነው፡፡ ሶስቱን ዋና ዋና የማናውቃቸውን ነገሮች እንመልከት . . .

1. ይህ ሰው ይህንን ስህተት ላለመስራት ምን ያህል እንደታገለ አናውቅም፡፡
ሰዎች ስህተትን ሲሰሩ ያንን ስህተት ላለመስራት ምን ያህል እንደታገሉና እንደሞከሩ ብናውቅ ትንሽ ለስለስ እንልላቸው ነበር፡፡ እኛው ራሳችንም ብንሆን አንዳንድ ጊዜ አንድን ስህተት ላለመስራትና ላለመድገምም ጭምር ብዙ ታግለን ስላቃተን ብቻ ራሳችንን ስህተት ላይ እንደምናገኘው ማሰብ አለብን፡፡

2. ይህ ሰው ይህንን ስህተት እንዲሰራ ጫና ያሳደረበትን ከአቅሙ በላይ የሆነን ሁኔታ አናውቅም፡፡
አንዳንድ ጊዜ ሰዎች አንድን ስህተት እንዲሰሩ የሚያስገድዳቸው የራሳቸው የሆኑ ሁኔታዎችና የሚያልፉበት ነገር ይኖር ይሆናል፡፡ የሰዎቹ ጾታ፣ የእድሜ ደረጃ፣ የገንዘብ አቅም፣ የእውቀት ብቃት፣ ያለፈ ልምምድና የመሳሰሉት ሁኔታዎች የራሱ ውህደት (Chemistry) ስላለው ማንም ሰው ያንኑ ችግር በእነሱ ሁኔታ ሊጋፈጠው አይችልም፡፡ ይህንን ማሰብ ትንሽ ሰፋ እንድንልና ሚዛናዊ እንድንሆን ያግዘናል፡፡

3. ይህ ሰው በሚያልፍበት በተመሳሳይ ሁኔታ ብናልፍ እኛ ራሳችን ምን ያህል ስህተት ልንሰራ እንደምንችል አናውቅም፡፡
ሰዎች በመሪነት የውሳኔ ስህተት ሲፈጽሙ እኔ እንደ አንድ ዜጋ የፍርድ ቃል መናገር ሊቀለኝ ይችላል፤ መሪ ስላለሆንኩኝ፡፡ እኔ መሪ ብሆንና እሱ በሚያልፈበት ሁኔታ ባልፍ ግን ምን አይነት ስህተት እሰራ እሆን? በተመሳሳይ ሁኔታ ባልና ሚስቶች፣ ሴቶችና ወንዶች፣ መሪና ተመሪዎች፣ ነጋዴዎችና ገበያተኛዎች . . . ሊያስቡ የሚገባቸው እነሱ በዚያኛው ሰው ቦታ ቢሆኑ ሊሰሩ የሚገደዱት ስህተት ሊኖር የመቻሉን ጉዳይ ነው፡፡

በተቻለን መጠን ስህተትን ላለመስራት የመታገላችንን ጉዳይ ስናሰምርበት፣ ከዚያው ጋር በተቻለን መጠን ሰዎች ስሀተት ሲሰሩ የፍርድና የወቀሳ ሃሳብ ከመሰንዘራችን በፊት ግራና ቀኙን የማየት ሰፊነት የማዳበርንም ጉዳይ እንድናሰምርበት አሳስባለሁ፡፡

#DrEyob

@Ethio_Stories
@Ethio_Stories
@Ethio_Stories

Читать полностью…

Motivational Stories

#Learning
Rejection & The Fear of Rejection
You can't hate the people who reject you.
You can't let them get the best of you.
Nor can you bless the people who love you.
Everyone is acting out of his or her own self-interest.

The only truly safe thing you can do is
To try over and over again.
▪To go for it,
▪To get rejected,
▪To repeat,
▪To strive,
▪To wish.

Without rejection there is no frontier,
There is no passion, and there is no magic.

How we deal with rejection is a combination of several factors. It's not just about how healthy we are mentally. Or how healthy we are psychologically and emotionally.

There's the saying :
"Time heals all wounds." This is true.
But we can control to some extent how much time it takes. It takes a different amount of time for each person, depending on the number of factors we allow to affect us.


@Ethio_Stories
@Ethio_Stories

Читать полностью…

Motivational Stories

#የደስተኛነት_ምርጫ

አንደኛው ምርጫህ በኑሮህ የጎደለውን ነገር እየቆጠርክ ማዘንና መነጫነጭ ነው፡፡ ሌላኛው ምርጫህ ግን ከሌለህና ከጎደለህ ነገር ላይ ትኩረትህን በማንሳት ባለህ ነገር ደስተኛ ሕይወትን ለመምራት መወሰን ነው፡፡

አንድ ሰው እንዲህ ሲል ተናገረ …

ከ13ኛው ክፍለ-ዘመን በፊት የነበሩ አባቶቻችን ስኳር የሚባል ነገር አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች ነበሩ …

የ14ኛው ክፍለ-ዘመን አባቶቻችን የኤሌክትሪክ ምድጃ ቀርቶ ከሰል የሚባል ነገር እንኳን አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች ነበሩ …

ከ15ኛው ክፍለ-ዘመን በፊት የነበሩ አባቶቻችን በቅጡ የተጋገረ ዳቦ የሚባል ነገር አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች ነበሩ …

ከ16ኛው ክፍለ-ዘመን በፊት የነበሩ አባቶቻችን ድንች የሚባል ነገር ነገር አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች ነበሩ …

ከ17ኛው ክፍለ-ዘመን በፊት የነበሩ አባቶቻችን ቡና፣ ሻይና ሾርባ የሚባሉ ትኩስ ነገሮች አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች ነበሩ …

ከ18ኛው ክፍለ-ዘመን በፊት የነበሩ አባቶቻችን ኬክና የመሳሰሉት ጣፋጭ ምግቦች የሚባል ነገር አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች ነበሩ …

ከ19ኛው ክፍለ-ዘመን በፊት የነበሩ አባቶቻችን እንቁላል፣ ክብሪትና የኤሌክትሪክ ኃይል የሚባል ነገር አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች ነበሩ …

ከ20ኛው ክፍለ-ዘመን በፊት የነበሩ አባቶቻችን ተዘጋጅቶ የታሸገ ምግብ የሚባል ነገር አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች ነበሩ … (Unknown Source)

በዚህ ላይ መጨመር ካለብን ከላይ በተዘረዘሩት ክፍለ-ዘመናት ይኖሩ የነበሩ አባቶቻችንና እናቶቻችን ዛሬ የምናውቃቸውን የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች ነበሩ፡፡

ምናልባት ይህንን ጽሑፍ እያነበብክ ያለህበት የዓመቱ ስንተኛው ወር ላይ እንደሆነ ባላውቅም፣ እስቲ ዓመቱ ከገባ ጀምሮ እስከዛሬዋ ቀን ድረስ አለኝ በምትለውና ጎድሎኛል በምትለው ነገር አንጻር የነበረህን ዝንባሌ ለማስታወስ ሞክር፡፡ ምናልባት ስለሌለህ ነገር ስትበሳጭና ስሜትህ ሲቃወስ ራስህን አግኝተኸዋል ብዬ እገምታለሁ፡፡ አሁን በተያያዝከው ሕይወት ውስጥ የምትፈልገውን ነገር ሁሉ ያለማግኘትህ እውነታ

ደስተኛነትህን እንድታዘገየው ከተጫነህ የሕይወት ዘይቤ ምርጫህን ማስተካከል እንዳለብህ ጠቋሚ ነው፡፡
የሆነውን ሳይሆን ያልሆነውን ማሰላሰል በርካታ ጠንቆች አሉት፡፡ ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል፣ በሌለንና በጎደለን ነገር ላይ ብቻ ማተኮር ታላቅ የሆነን የስሜት ቀውስ ያስከትላል፡፡ የመነሳሳትና ወደፊት ለመቀጠል የሚኖረንን ግለት ያበርድብናል፡፡ በሁኔታው የሚኖረንን የመነጫነጭ ባህሪ በመመልከት የቅርብ ወዳጆቻችን ቀስ በቀስ እየራቁንና ከእኛ ጋር ለመሆን ያላቸውን ፍላጎት እያጡ ይሄዳሉ፡፡ እንግዲህ ከእነዚህና ከመሰል አጉል ተጽእኖዎች ለመዳን ትክክለኛው ምርጫ መከተል የግድ ነው፡፡

ዛሬ ለሌለህ ነገር እየሰራህና መለወጥ ወደምትፈልገው የተሻለ የባህሪይ ማንነት ለመለወጥ እየተጋህ ሳለህ፣ ባለህ ነገር ግን ደስተኛ መሆን ትችላለህ፡፡

(“ምርጫና ውሳኔ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ መጽሐፍ የተወሰደ)፡፡


@Ethio_Stories
@Ethio_Stories
@Ethio_Stories

Читать полностью…

Motivational Stories

ትላንትና ከፊት ያለውን ነገር ልወስን አይችልም፤ ስለዚህ ዛሬ አድስ ነገር መስራት ትችላለህ።



@Ethio_Stories

Читать полностью…

Motivational Stories

#This_is_my_motto_in_life.

Every master was once a beginner.

Every pro started as an amateur.

Every icon began as an unknown.

Every king was once a crying baby,

Every monument was once a sketch,

Make a beginning, take the first step.
If you don’t go after what you want, you’ll never have it.

If you don’t ask, the answer is always no.

If you don’t step forward, you’re always in the same place.

Have courage to take the first step in faith, you don’t have to see the whole staircase, just take the first step.

Dream big, work hard, stay humble & stay Blessed.

🔥 @Ethio_Stories 🔥

Читать полностью…

Motivational Stories

የመገፋት መዘዞች
(“የመገፋት ሕመም” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተቀነጨበ)፡፡

የመገፋት ስሜት ሰለባ መሆን በሰዎች ሕይወት ውስጥ ይህ ነው የማይባል መዘዝ ያስከትላል፡፡ በማንኛውም ማሕበራዊ ግንኙነትህ ውስጥ ለአንተና ለሌላው ሰው ግር የሚል ባህሪይን የምታንጸባርቅ ከሆነና ከሰዎች ጋር ያለህ ግንኙነት ጎርበጥባጣ ከሆነ ሌሎች የራስ-በራስ ምርመራ ከማድረግህ በፊት ከመገፋት አንጻር ያለህበትን ወቅታዊ ሁኔታ መመልከት ይበጃል፡፡

የመገፋት ስሜት በርካታ አሉታዊ ውጤቶች የሚኖሩት ሲሆን፣ ከሚያስከትላቸው መዘዞች መካከል ፈጥኖና ጎልቶ የሚታየው፣ የመነጠልና የብቸኝነት ስሜት ነው፡፡ ሰዎች እንደተገፉ ሲሰማቸው የመገለልና የብቸኝነት ጫና በስሜታቸው ላይ ይከመራል፡፡ የመገፋት መዘዝ ግን በብቸኝነት ስሜት ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ ከዚህ በታች በተጠቀሱት ነጥቦች እንደምንመለከተው መፍትሄ ያልተገኘለት የመገፋት ስሜት በርካታ ጣጣዎችን ይዞ ነው የሚመጣው፡፡

1. መገፋት ተመላላሽ ሕመምን ይሰጠናል
ቀደም ብለን እንደተመለከትነው አንጎላችን ለአጥንት ስብራት የሚመጣን የሕመም ስሜትና በመገፋት የሚመጣን የሕመም ስሜት እኩል ነው የሚያስተናግደው፡፡ ሆኖም፣ የመገፋት ስቃይ ከአካል ሕመም ስቃይ የሚለየው ወይም የሚብሰው በማንኛውም ጊዜ ትውስታው እንደገና የሕመሙን ስሜት ስለሚቀሰቅሰው ነው፡፡ ለምሳሌ፣ የዛሬ አስር አመት አጥንትን ሰብሮ የነበረ ሰው ያንን ደርሶበት የነበረውን ሁኔታ መለስ ብሎ ሲያስበው የአጥንት ሕመሙ ተመልሶ አያሰቃየውም፡፡ በተቃራኒው ግን የዛሬ አስር አመት የከባድ መገፋትና መገለል ሰለባ የነበረ ሰው እንደገና ሁኔታውን ሲያስታውሰው ይህ ነው የማይባል ስቃይ ሊመለስበት ይችላል፡፡

2. መገፋት ማሕበራዊ ቀውስ ውስጥ ይጨምረናል
አንድ ሰው በሚገፋበት ወይም በሚገለልበት ጊዜ ቀድሞ የነበረውን ማሕበራዊ ትስስር ያጣል፡፡ ይህ ከመገፋት የሚመጣ የመነጠል ስሜት ቀድሞ የነበረንን የመደላደል ስሜት ስለሚነጥቀን ያለን ማሕበራዊ ሕይወት ይናጋል፡፡ ከተደላለደ ማሕበራዊ ሕይወትና ግንኙነት ውጪ ሙሉ ሊሆን የማይችለው ማንነታችን ያንን ፍለጋ የሚያሳልፈው ጊዜና የሚያቃጥለው የስሜት ኃይል ይህ ነው አይባልም፡፡ በነበረን መገፋት የተሰማንን ሕመም ለማካካስና ሁኔታውን “ለመበቀል” በሌላ በሚገባ ወዳልታሰበበት ማሕበራዊ ሁኔታ ውስጥ ራሳችንን እናገኘዋለን፡፡ ከዚያም፣ ሌላ የመገፋት ዑደቱ ይቀጥላል፡፡

3. መገፋት የስሜት መዛባት ያስከትላል
መገፋት ቁጣ፣ ጠብ-ጫሪነትና የመሳሰሉት አይነት ለማሕበራዊ ግንኙነት ጸር የሆኑ ስሜቶችን እንድናዳብር ያጋልጠናል፡፡ በአንዳንድ ጥናቶች እንደተጠቆመው የእጽ ሱሰኝነት፣ ድህነት፣ እንዲሁም የወንበዴዎች ቡድን (Gang) አባልነት ከሚያስከትለው መዘዝ ይልቅ የመገፋት ቀውስ የሚያስከትለው መዘዝ ይልቃል፡፡ የተገፉ ወይም እንደተገፉ የተሰማቸው ሰዎች ሁኔታው ሲብስባቸው የጸበኝነትና የወንጀለኛነት ባህሪይ ይታይባቸዋል፡፡

4. መገፋት በራስ መተማመናችንን ይነካዋል
የመገፋትና የመገለል ሰለባ የሆኑ ሰዎች በራሳቸው ላይ ያላቸውን አመለካከት የመጣል ዝንባሌ ውስጥ ይገባሉ፡፡ አንድ አንድ ጊዜ የመገፋቱ ሁኔታ የተከሰተው ከእነሱ ስህተት ውጪ ሆኖ እንኳን ሁኔታውን ግን የሚያገናኙት ከራሳቸው ጋር ነው፡፡ ስለዚህም፣ “ሰዎች የገፉኝ እንደዚህ ስለሆንኩኝ ነው” ወደሚል ድምዳሜ ውስጥ ይገባሉ፡፡ ራስን መውቀስ፣ መገፋት በተሰማቸው መስክ አንጻር ለወደፊቱ ድፍረትን ማጣት፣ ራስን ማግለልና የመሳሰሉት የወረደ በራስ የመተማመን መገለጫዎች የዚህ ምልክቶች ናቸው፡፡

5. መገፋት የእውቀት ማእከላችንን ይነካዋል
በአንዳንድ ጥናቶች እንደታየው ሰዎች የቅርብ ጊዜ የመገፋት ልምምዳቸውን እንዲያስታውሱ ሲደረጉና የአእምሮ ብልህነት (IQ) ፈተና ሲሰጣቸው ውጤታቸው ዝቅተኛ ይሆናል፡፡ የመገፋትና የመገለል ሰሜትን የቅርብ ርቀት የማስታወስ ብቃትቸውና የውሳኔ አሰጣጥ ብቃታቸው ላይ ይህ ነው የማይባል ተጽእኖ እንዳለው ይታመናል፡፡


@Ethio_Stories
@Ethio_Stories
@Ethio_Stories

Читать полностью…

Motivational Stories

@Ethio_Stories

Читать полностью…

Motivational Stories

“የፈረቃ” ሕይወት

ከአማካኝ የሕብረተሰብ ክፍሉ ላቅ ያለ ስኬት ውስጥ መግባት ከፈለክ ነገሮችን የማፈራረቅ ጥበብን ማዳበር አለብህ፡፡ የፈረቃ ሕይወት ማለት የሕይወትን ዘርፈ-ብዙ አደራዎችንና እድሎችን ካለማቋረጥ የመለየትና የማፈራረቅ ብቃት ማለት ነው፡፡

ማድረግ በምንፈልገውና የግድ ማድረግ በሚገባን ነገር መካከል የመለየት ጥበብ ከስራ ጭንቅንቅ ነጻ የመሆንን ሁኔታ ሊያመቻችልን አይችልም፡፡ ነገሮችን ለይተንና አጣርተን እንኳ ማድረግ የሚገቡን ሃላፊነቶች ቁጥር እጅግ ብዙ ሊሆኑና ሸክም ሊበዛብን ይችላል፡፡

ስለሆነም፣ ጊዜያችንን በአግባቡ ለመጠቀምና እነዚህ ዘርፈ-ብዙ የሆኑ ሃላፊነቶችን ለመወጣት ልናዳብር ከሚገባን ብቃት አንዱ በአንድ ጊዜ በርካታ ተግባሮችን የማከናወን ብቃት ነው፡፡ ይህንን ብቃት ነው “የፈረቃ ሕይወት” በማለት የሰየምነው፡፡ ለምሳሌ፣ አንዳንድ ሰዎች ከ5 እና ከ10 ያላነሱ ትንንሽ ኳሶችን በእጃቸውና በአየር መካከል በማፈራረቅ እየወረወሩና እየቀለቡ ማስተናገድ ይችላሉ፡፡ አያንዳንዱን ኳሶች እንደ ሕይወት አደራና ተግባር ብንመስላቸው፣ አንዱን ኳስ ከሌላኛው ጋር በማፈራረቅና ተራ በማስያዝ ያዝ ለቀቅ የማድረግ ጥበብ ወሳኝ ነው፡፡ በዚህ ኳሶቹ ሁሉ ለዋነኛው የማፈራረቅ ትእይንትና ተግባር አስፈላጊ በሆኑበት ተግባር ላይ የሚከተሉት እውነታዎች የማይለወጡ ናቸው፡፡

1. በጊዜው በእጃችን ላይ ላለው “ኳስ” (ተግባር)ትኩረት መስጠት፡፡
ለምሳሌ፣ ማታ እቤቴ ስገባ ቤተሰብ የሚባል “ኳስ” እጄ ላይ ገብቷል፡፡ ጓደኝነት የተሰኘው “ኳስ” ደግሞ አየር ላይ (ውጪ) ነው ያለው፡፡ እቤት ገብቼ ቤተሰብ የተሰኘውን “ኳስ” ስጨብጥ በውጪ ትቼው መምጣት ያለብኝን የጓደኝነት “ኳስ” አብሬ ከያዝኩ ሚዛን ይዛባል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ሰዎች በስራ ቦታ ጨዋታን፣ በጨዋታ ስፍራ ደግሞ ስራን በመደባለቅ ፈረቃ መያዝ ያለባቸውን ጉዳዮች ያምታታሉ፡

2. የተለቀቁት “ኳሶች” (ተግባሮች) አንድ በአንድ እንደሚመለሱ ማስታወስ፡፡
ለምሳሌ፣ በስራ ቦታ ሆኜ ስራ የተሰኘውን “ኳስ” በእጄ ሳስገባ፣ በቤት የተውኩት የቤተሰቤ “ኳስ” ለጊዜው በአየር ላይ ቢሆንም እንኳ ተመልሶ መምጣቱና ያዘኝ ማለቱ እንደማይቀር ማሰብ አለብኝ፡፡ምንም እንኳ ለጊዜው የቤተሰብን “ኳስ” ለቀቅ አድርጌው ትኩረቴ ሁሉ ስራ በተሰኘው “ኳስ” ላይ ቢሆንም፣ የቤተሰብ ሃላፊነት ጉዳይ ከውስጠ-ህሊናዬ ሊጠፋ አይችልም፡፡ ተመልሶ መምጣቱ አይቀርምና፡፡

3. በእጅ ያለው “ኳስ” (ተግባር) ሊለቀቅ የሚገባበት ሰዓት እንዳለ አለመዘንጋት፡፡
ለምሳሌ፣ ከስራ ነጻ በሆንኩባቸው ቀናት የነበረኝን የእረፍትም ሆነ የጨዋታና የማህበራዊ ጊዜ በሚገባ ብደሰትበትም እንኳ እሁድ ደርሶ ሰኞን ሲጋብዝ እኔም ሰኞ ይዞ ለሚመጣ ውሃላፊነት ለመዘጋጀት በእረፍት ጊዜ በእጄ የገቡትን “ኳሶች” ለመልቀቅና የነገን “ኳስ” (ስራ) ለመያዝ መዘጋጀት የግድ ነው፡፡ ይህ ጥበብ ለጊዜው ታላቅ ትጋትን የሚጠይቅና አድካሚ ቢመስልም እንኳ ከተለመደ በኋላ ፍሬያማ ያደርጋል፡፡

4. በእጅ ያለውን “ኳስ” (ተግባር) እንደ ለቀቁ የተመለሰውን “ኳስ” (ተግባር) በመያዝ ሃሳብን ሙሉ በሙሉ በእርሱ ላይ መጣል፡፡
ለምሳሌ፣ ከአድካሚና ከፈታኝ የስራ ቀን በኋላ እቤቱ ገብቶ ያረፈና በመጨረሻም ወደ መኝታ የሚሄድ ሰው በስራ ቦታ ያልተሳኩትንና ፈታኝ የነበሩትን ሁኔታዎች ማውጠንጠን ሊቀናው ይችላል፡፡ በሌላ አባባል በአካል ከስራ መስኩ ቢለይም እንኳ በሃሳቡ የስራውን “ኳስ” እንደያዘው ነው፡፡ መሆን ያለበት ግን አሁን እረፍት የተሰኘውን “ኳስ” ማስተናገድና ሙሉ ማንነትን መስጠት ነው - እረፍትና እንቅልፍ የሕይወት ግዴታዎቻችን ናቸውና፡፡ በእጃችን ላይ ለገባው ተግባር ያለንን ሁሉ ትኩረት ሰጥተነው በሚገባ ከተገበርነው፣ ተራው ደርሶ ለመጣው አዲስ ተግባር ትኩረትን የመስጠት ድፍረት ይሰጠናል፡፡

5. የአንዱ “ኳስ” (ተግባር) መውደቅ የኳሶቹ (የተግባሮቹ) የፈረቃ ሂደት የሰጠንን ዋነኛ ዓላማ እንደሚነካው ማስታወስ፡፡
ለምሳሌ፣ የእንቅልፍና የእረፍት ጊዜውን ካለ አግባብ የሚጠቀምና ጠዋት ተነስቶ የስራ “ኳሱን” ማስተናገድ ሲገባው በመስነፍ ከስራ የማርፈድና የመቅረት አጉል ልማድ ያለበት ሰው፣ የስራን “ኳስ” በመጣሉ ምክንያት ሌሎቹንም “ኳሶች” የመጣል እድሉ የሰፋ ነው፡፡ ከስራ ማርፈድና መቅረት የሚያስከትለው ከስራ የመባረር ሁኔታ የስራ “ኳስን” ከማስጣሉ ባሻገር፣ የስራ አጥነት የሚያስከትለው የገንዘብ እጥረት ደግሞ የቤተሰቡን ሁኔታ ያናጋዋል፡፡ ይህ ሁኔታ የሚያስከትለው የእረፍት ማጣት ተጽእኖ ቀድሞውኑ አልለቅ ያለውን እንቅልፉን ሳይቀር ያስጥለዋል፡፡ ይህንን ዑደት መስበር የግድ ነው፡፡

አንድ ነገር አትዘንጋ፣ በሕይወት አስፈላጊና ወሳኝ የሆኑ ነገሮችን በማፈራረቅ ለእያንዳንዱ ተገቢ የሆነውን ትኩረት መስጠትን እስክትለምድ ድረስ በሕይወትህ አንዱን አያነሳህና ሌላውን እየጣልክ ስትዋዥቅ የምትኖር ሰው ትሆናለ፡፡ በማፈራረቅ ሂደት ውስጥ ተራው የደረሰ ተግባር ላይ ማተኮር አንዱ የስኬት ቁልፍ ነውና፡፡

“የጊዜ አጠቃቀም ጥበብ” ከተሰኘው መጽሐፍ ውስጥ የተወሰደ!



ይቀላቀሉ 👉 @Ethio_Stories

Читать полностью…

Motivational Stories

Can't stop laughing😂😂😂😂

Читать полностью…

Motivational Stories

for general knowledge😊

Читать полностью…

Motivational Stories

gin bezowchachu asibachu tawkalachu #Firehat tekami ende hone? 🤔🤔🤔
eski endezi eney #difret ena #firehat
#difret bezu gize be hiywote wust be akebabiyem hone be liyu liyu neger sewoch be difret bezu neger seyatefu ayalew le misale difret senor gid yelesh mehon. mn yimetal, mn yametal, mn endal hon nw, bane hiywot mn yagebachewal ende feleku behons who cares menamen bizu metkes yichelal enezi hulu gin ye mitelun nachew miknaytum degmo wedednim telanim andi ewuneta sw yale sw menor ayichelm. personal emotion adamach nw mn honew selezi be difretachin miknayt erasachinin bicha sayhon sewochinm le nata enchilalen.
#firehat sele firehat bezu malet enchilalen
hiywotn enkuan sele menferat le nage wastina endihonen belen zare lay bezu negerochin senadrg enitayalen dirgetu engedi positive&negative include yadergal gin nagen sele mn fera nw yanin menadrgew others setfera lerasehim le sewochm titenekekale le misale be akebabew agul action ke meyadreg ena andi le akebabiw sw ke mitenekekw ye tegnaw firehat yalebt yimeslachewal? melsun lenante tichewalew betely be life wust firehat betam bemibal dereja important nw keteleyayu addiction kehonu negrochim yaz yadergenal. #fetarin mefrat, #betesebin mefrat, #gorobetin mefrat, #akebabin mefrat #behalin ena #hagerin mefrat chimer yatekalelal malet nw. yehen setsef bechahen kuch biye selenzi hulet negeroch eyasebkugn nw
le tinsh dekika eski asebut🙇‍♂️🙇‍♀️🙇‍♂️🙇‍♀️
betinshu ene ehen alku enante degmo sihetet kalebgnim arimugn🤗👏 yibelt hasab kalachu be #bot bekul hasabachun askemtulin
#Group 👉 @ethio_motive
#le_manignawum_teyake_hasab👇
👉👉👉👉@Ethio_motivatedbot

#yekelakelun 👉 @Ethio_Stories
👉 @Ethio_Stories

Читать полностью…

Motivational Stories

ሰላም ሰላም እንዴት ናችሁ
ክዚህ በፊት ብዙ ነገር የተማራቹበት
ይሄ ቻናል እንዲመለስ ምትፈልጉ

Читать полностью…

Motivational Stories

#Tell_yourself_the_following_everyday:

🌱 I create my own reality

🌱 I am grateful for all that I have

🌱 I am happy & excited about life

🌱 I am healthy & full of energy

🌱 I am confident about who I am

🌱 I have inner peace & joy

#Share🔻
✨ @Ethio_Stories @Ethio_Stories

Читать полностью…

Motivational Stories

@Ethio_Stories

Читать полностью…

Motivational Stories

There is no going back. There is no drawing against the "tomorrow."
Therefore, there is never not enough time or too much time. Time management is decided by us alone and nobody else. It is never the case of us not having enough time to do things, but the case of whether we want to do it.




@Ethio_Stories
@Ethio_Stories

Читать полностью…

Motivational Stories

ሕዋ ላይ እንዴት ለአንድ ዓመት ይኖራል?

ጠፈርተኛ ስኮት ኬሊ ለአንድ ዓመት ያህል ሕዋ ላይ ኖሯል።

ከአራት ዓመት በፊት ከናሳ በጡረታ የተገለለው ስኮት ኬሊ ጠፈርተኛ ነው። ለአንድ ዓመት ያህል ሕዋ ላይ ኖሯል።

ጠፈርተኛው 'ኢንዱራንስ' የተባለ መጽሐፍ አሳትሟል ።

እአአ 2015 ላይ በሩስያው መንኮራኩር ውስጥ ከነበሩት አንዱ ነበር።

ከሩስያውያኑ ጌኔዲ ፓዳካላ እና ሚካሂል ኮርኒንኮ ጋር ሳሉ፤ አንድ ብረታማ ቁስ በሰከንድ 14 ኪሎ ሜትር እየተምዘገዘገ ወደ መንኮራኩራቸው እየተጠጋ መሆኑ ተነገራቸው። መንኮራኩራቸው ከተመታ በሕይወት የመትረፍ እድል አይኖራቸውም።

ስኮት እንደዚህ ያለ ለሕይወት የሚያሰጋ ነገር ሲገጥመው የመጀመሪያው አይደለም።

"አደጋ ቢደርስ ኖሮ ሦስታችንም በሚሊሰከንዶች ጊዜ ውስጥ እንደ አቶም በሚሊዮን አቅጣጫዎች እንበተን ነበር" ይላል።

የሕዋ ላይ ኑሮ ከምድር ጋር የሚያመሳስለው ጥቂት ነገር አለ። በቪድዮ መደዋወል፣ ማጽዳት ወዘተ. . .

በአብዛኛው ግን ሕዋ ፈታኝ ነው።

ስኮት ከ2007 አንስቶ ሦስት ጊዜ ወደ ሕዋ ተጉዟል። እውቅና ያተረፈው ግን ከ2005 እስከ 2016 በሕዋ ባደረገው ቆይታ ነው።

ከሱ በፊት ረዥም ጊዜ ሕዋ ላይ የኖረው አሜሪካዊ ጠፈርተኛ ማይክል ሎፔዝ 100 ቀናት ቆይቷል።

ስኮት ይህንን ክብረ ወሰን ሰብሯል።

ሌላ ስኮት የሚታወቅበት ነገር መንታ ወንድሙ ማርክ ነው። እንደሱው ናሳ ውስጥ ይሠራል።

ስኮት ሕዋ ላይ አንድ ዓመት ሲኖር አንድም ቀን ወደ መሬት ለመመለስ እንዳልጓጓ ይናገራል።

"ከአንድ ዓመት በላይ የሚያስቆየኝ ምክንያት ባገኝም እዛው እሆን ነበር" ነው የሚለው።

አንዳንድ ጠፈርተኞች ሕዋ ላይ ያለው የብቸኛነት ኑሮ የሥነ ልቦና ጫና ያሳድርባቸዋል።
መንታ ወንድሙ ማርክ እንደሱው ናሳ ውስጥ ይሠራል።

ስኮት ግን "ዋናው ነገር ራስን ማዝናናት መቻል ነው። ለሁሉም ሰው ቀላል ነው ማለት ግን አይደለም" ብሎ ያምናል።

ለሱ ከሕዋ ኑሮ ከባዱ እንደልብ ከመንኮራኩር መውጣት አለመቻል ነው። በጠባብ ቦታ ከሰዎች ጋር ለረዥም ጊዜ አብሮ መኖርም ቀላል አይደለም።

በሌላ በኩል ደግሞ ከሌሎች ጠፈርተኞች ጋር ጥብቅ ወዳጅነት ይፈጠራል።

ስኮት ሕዋ ላይ አብረውት ከኖሩ ጠፈርተኞች ጋር ምድር ሲመለስም በወዳጅነት ቀጥሏል። ዓለም አቀፉ የሕዋ ተቋም የአገሮች ትብብር ተምሳሌት እንደሆነ ይናገራል።

ሕዋ ላይ ሳለ ከሥራ በተጨማሪ ዘና ይልም ነበር። በተለይም የዝንጀሮ ልብስ መልበስ በጣም ያዝናናዋል።

የዝንጀሮ መልክ ያለውን ልብስ የሰጠው ናሳ የሚሠራው መንታ ወንድሙ ነው።

ወንድማማቾቹ ያደጉት ኒው ጀርሲ ሲሆን፤ ቤተሰቦቻቸው ፖሊሶች ናቸው።

ስኮት እና ማርክ ልጅ ሳሉ ጀምሮ አደገኛ ነገር መሞከር ይወዳሉ። በተደጋጋሚ ጉዳት ይደርስባቸውም ነበር።

ትምህርት ቤት ሲገቡ ማርክ ጎበዝ ሆነ። ስኮት በተቃራኒው ዝንጉ ነበር። ኮሌጅ ሲገቡ ማርክ ስኮትን ይመክረው እንደነበር ያስታውሳል።

ስኮት መጀመሪያ ላይ የውጊያ አውሮፕላን አብራሪ ሆነ።

በመጀመሪያው የገልፍ ጦርነት ወቅት ተሠማርቶም ነበር። 1996 ላይ ከወንድሙ ጋር ናሳን ተቀላቀለ።

ወንድማማቾቹ በአንድ መንኮራኩር አብራሪነት ተሳትፈዋል።

2003 ላይ ኮሎምቢያ የተባለ መንኮራኩር ወደ ምድር ሲመለስ ተከስክሶ ሰባት ጠፈርተኞች ሞተዋል።

ያ አጋጣሚ የመንኮርኩር በረራ አስጊነትን ያሳየ ነበር። የናሳ የደህንነት ፖሊሲም ተተችቷል።

ያኔ ከሞቱት ጠፈርተኞች አንዱ የስኮት ጓደኛ ነው።

ቢቢሲ ቃለ መጠይቅ ሲያደርግለት ዓለም አቀፍ የመንኮራኩር ደህንነት ጉባኤ ላይ ንግግር ለማድረግ ሲዘጋጅ ነበር።

ስኮት ለአንድ ዓመት ወደ ሕዋ ሊጓዝ እንደሆነ ሲነገር ትኩረታቸው ከተሳቡ መካከል የዘረ መል ተመራማሪዎች ይገኙበታል።

አንድ ሰው ዘለግ ላለ ጊዜ ሕዋ ላይ ሲኖር የሚያድርበትን ተጽዕኖ ለመረዳት፤ ስኮትን እና መንታ ወንድሙ ማርክን ለማነጻጸር ነበር ተመራማሪዎቹ ያሰቡት።

የስኮትን ሰውነት ምድር ላይ ከቀረው ወንድሙ ጋር በማወዳደር የሥነ ልቦና፣ በሽታ የመከላከል እና የዘረ መል መዋቅር ለውጡን ገምግመዋል።

የስኮት ዘረ መል መዋቅር ላይ የታየው ለውጥ ለጨረራ መጋለጡ ያሳደረበትን ተጽዕኖ ያሳየ ነበር።

ስኮት ከሕዋ ሲመለስ የክሮሞዞም፣ የደም፣ የሰውነት መጠን ለውጥም አሳይቷል። ወደ መሬት ከተመለሰ በኋላ ግን ወደ ቀደመው ተክለ ሰውነቱ ተመልሷል።

ስኮት ከሕዋ ከተመለሰ አራት ዓመታት አስቆጥሯል። በቆይታው ለውጥ ያስተዋለው እይታው እንደሆነ ይናገራል።

ተመራማሪዎች መንታዎቹ ላይ የሠሩት ጥናት፤ ሰዎችን ወደ ማርስ ለመላክ ለተያዘው እቅድም መረጃ ሰጥቷል።

ከመሬት 34 ሚሊዮን ማይል ወደምትርቀው ማርስ ተጉዞ ወደ ምድር ለመመለስ ዘጠኝ ወራት ይወስዳል።

ጠፈርተኞች ለጨረራ የሚጋለጡት በአስር እጥፍ ስለሆነ ለካንሰር ወይም ለሌላ ህመም ሊጋለጡ እንደሚችሉ ይሰጋል።

"ያለው አማራጭ ራስን መከላከያ መንገድ ማግኘት ወይም በፍጥነት ወደ ማርስ መድረስ ነው። ካልሆነ ግን ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል አምኖ መጓዝ ነው" ይላል ስኮት።

አሁን ከናሳ ጡረታ ወጥቶ ዴንቨር ውስጥ ከባለቤቱ ጋር ይኖራል። በተለያዩ መድረኮች ስለ ሕዋ ቆይታው ንግግር በማድረግ እና በመጻፍ ጊዜውን ያሳልፋል።

ከዚህ በኋላ ምናልባትንም ወደ ሕዋ የሚላክ የሮኬን መንኮራኩር አብራሪ ከተፈለገ ስኮት ይጠራ ይሆናል።


@Ethio_Stories
@Ethio_Stories

Читать полностью…

Motivational Stories

የሰዎችን ጎጂና አስቸጋሪ ባህሪይ ለማስቆም ከፈለክ . . .

ሰዎች ወጣ ያሉ ባህሪያቶች የመግለጣቸውን ሁኔታ የማያቆሙበት ዋነኛ ምክንያት የለመዱት የራሳቸው ባህሪይ መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ሆኖም ዛሬ የምንነጋገርበት ሌላኛው ምክንያት ግን የእኛው የራሳችን መዋጮ ስላለበት ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ ሰዎች ለሚያሳዩት ባህሪይ አንተ የምተሰጠው ምላሽ የሚቀጥለውን ባህሪያቸውን ይወስነዋል፡፡ እንዳብራራ ይፈቀድልኝ፡፡

ሰዎች ሁል ጊዜና እየደጋገሙ አንድን ትክክል ያልሆነና ለአንተም ደስ የማይልህን ባህሪይ የሚገልጡብህ ከሆነና ያንን ለማስቆም ከፈለክ ከሁሉም በፊት ማወቅ ያለብህ ሰዎች እንደዚያ የሚሆኑበትን ሁለት ምክንያቶች ነው፡፡

1. የሚፈልጉትን ነገር የሚያገኙበት መንገድ ነው
ሰዎች አንድን አጓጉል ባህሪይ የሚያሳዩበት አንዱ ምክንያት የሚፈልጉትን ነገር ለማግኘት የሚጠቀሙበት መንገድ ስለሆነ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ ከአንተ ልምምጥን ሲፈልጉ ያኮርፋሉ፤ አንድን ነገር እንድትለቅላቸው ከፈለጉ ይቆጣሉ፤ በስራቸው ሆነህ እንድትገዛላቸው ሲፈልግ ኃይለኛ ይሆናሉ፤ እንድትከተላቸው ሲፈልጉ ይሸሹሃል፤ አዝነህላቸው የማታምንበትን ነገር እንድታደርግላቸው ከፈለጉ ልሞት ነው፣ ልጎዳ ነው ይሉሃል . . . ፡፡ ስለዚህ እነዚህን ከላይ የጠቀሱትንና መሰል ባህሪያቸውን ለማስቆም ከፈለክ ቀላሉ መንገድ ያንን ባህሪይ በመግለጣቸው ምክንያት ከአንተ ለማግኘት የፈለጉትን ነገር በመከልከል አንተ ያመንክበትን ነገር ብቻ ማድረግ ነው፡፡

ለምሳሌ፣ አንድ ሕጻን በማልቀስ አንድን ነገር እንድናደርግ እስካስገደደን ድረስ አንድን ነገር በፈለገ ቁጥር ማልቀሱን አያቆምም፡፡ አንድን ነገር እንዲሰጠው ሲያለቅስ ግን የፈለገውን ነገር እንደማንሰጠው ብናሳየውና በዚያው አቋማችን ብንጸና ሕጻኑ እያለቀሰ አንድን ነገር ማስደረግን ያቆማል፡፡

2. የሚያደርጉት ነገር በቂ መዘዝ ወይም ቅጣት ስለማያስከትል ነው
ሰዎች አንድን ተቀባይነት የሌለውን ባህሪይ ሲያሳዩህ ከዚያ ካሳዩት ባህሪይ የተነሳ የሚከተላቸው መዘዝ፣ ቅጣት ወይም ችግር እስከሌለ ድረስ በዚያው ይቀጥላሉ፡፡ ለምሳሌ በሃገራችን ውስጥ ሰዎች ሁል ጊዜ ሰዓት ባለማክበር ምክንያት ምንም ነገር ስለማደርስባቸው ያንን ባህሪይ ይደጋግሙታል፡፡ በግላችንም ቢሆን ሰዎች የማይሆንና ተቀባይነት የሌለውን ነገር እያደረጉ በዚያ ምክንያት ምንም የሚከተላቸው ነገር ስለሌለ ያንን ነገር በመደጋገም ያደርጉታል፡፡ ስለዚህ ሰዎች በሕይወታችን የሚጎዳንን ነገር ሲያደርጉ ያንን እንዲያቆሙ ከፈለግን ባህሪያቸው የሚያስከትለው አንድ ቅጣት ሊኖረው ይገባል፡፡

አሁንም የሕጻኑን ምሳሌ ለመከተል ያህል፣ አንድ ሕጻን አንድን ጥፋት ሲያጠፋ ጥፋቱ ተገቢ የሆነ ቅጣትን ካላስከተለበት ጥፋትን ማድረግ ይቀጥላል፡፡ ለሚያጠፋው ጥፋት ተገቢ የሆነና “የሚያም” ቅጣት ከተሰጠው ግን ጥፋቱን መድገም ወይም እንደልቡ መሆንን ያቆማል፡፡

ከላይ የተጠቀሱትን መርሆች በመከተል መሸከም የሌለብህንና ለሕይወትህ፣ ለቤተሰብህ፣ ለስራ ቦታህና ለመሳሰሉት ጠንቅ የሆኑትን አጉል የሰዎች ባህሪይ ማስቆም፣ አለዚያም ቢያንስ መቀነስ ትችላለህ፡፡



@Ethio_Stories

Читать полностью…

Motivational Stories

ከ 69 አመት አዛዉንት ጋር ስለሆነ ጉዳይ እያወራን ተጨቃጨቅንና ትክክል መሆኔን በመረጃ አስረግጬ ብነግራቸዉም በፍፁም ሊያምኑኝ ስላልፈቀዱ እንዲህ አሉኝ

“ትልልቅ ከሆኑ ሰዎች ጋር እንደዚህ ችክ ብለህ አትከራከር...

ስማ እኛ ካንተ በላይ ሃገሩን እናዉቃለን! በእድሜያችን ብዙ ነገር ስላየን ቀደም ቀደም አትበል!”

ለምን እንደሆነ ባይገባኝም በእድሜ ተለቅ ያሉ ሰዎች ስህተታቸዉን በፍፁም ማመን አይፈልጉም...ለዚህ ነዉ ብዙ ሰዎች ’እድሜ ከፍ ባለ ቁጥር እየበሰልክ ትመጣለህ’ ሲሉ በፍፁም የማልቀበለዉ


@Ethio_Stories
@Ethio_Stories

Читать полностью…

Motivational Stories

በኑሮህ ላይ ለዉጥ እንዲኖር ስትፈልግ አደጋዉን ለመቀበል ፍቃደኛ ሁን ካልሆነ ለዉጥ ሳይሆን የተለመደ ኑሮ ትኖራለህ



@Ethio_Stories

Читать полностью…

Motivational Stories

It takes both rain🌦 and sunshine🌤 to create a 🌈Rainbow.

Our lives are no different.
🥊There is happiness and sorrow.
🥊There is the good and the bad,
🥊There is dark spots and bright spots.

🧘🏻‍♂When we can handle adversity well, it only strengthens us.
🌺We cannot control all events that happen in our lives, but we can control how we deal with them.


@Ethio_Stories
@Ethio_Stories
@Ethio_Stories

Читать полностью…

Motivational Stories

@Ethio_Stories

Читать полностью…

Motivational Stories

🙏ሰላም ለእናንተ🙏

✍ከመሞትክ በፊት ቀድመክ አትሙት✍

በድሮ ጊዜ ሁለት አገልጋዮች ትልቅ ጥፋትን ያጠፉና ለፍርድ በንጉሱ ፊት ይቀርባሉ፡፡ ንጉሱም የጥፋታቸውን ከባድነት ከተረዳ በኀላ ሁለቱም በሞት እንዲቀጡ ይወስንባቸዋል፡፡ ለመሞትም ሁለቱም መርዝ እንዲጠጡ ያዛል፡፡ እናም ለሁለቱም በዋንጫ ተቀድቶ ይሰጣቸውና ግጥም አድርገው ይጠጡታል፡፡

ከሰከንዶች በኀላ አንደኛው አገልጋይ እዛው ተንፈራፍሮ ይሞታል፡፡ አንደኛው ግን ምንም ሳይሆን ይቀራል፡፡ ለካ ንጉሱ ምንም እንኳን አገልጋዮቹ ከባድ ጥፋት ቢያጠፉም በሞት ሊቀጣቸው አላሰበም ነበር፡፡ ይልቁንም ምን ያህል መንፈሰ ጠንካራ መሆናቸውን ለመፈተን ሲል ሁለቱንም መርዝ ጠጥታችሁ ትሞታላችሁ በማለት ንፁ ወይን በዋንጫ እንደሰጣቸውና እንዲጠጡ ነበር ያደረገው፡፡

ነገር ግን ምንም እንኳን የጠጡት ንፁ ወይን ቢሆንም አንደኛው አገልጋይ ገና መርዝ ጠጥቶ እንደሚሞት ሲነገረው ልቡ እና መንፈሱ ቀድሞ በመሞቱ ምንም መርዝ በሌለበት ወይን ጠጥቶ ሞቷል፡፡

✍ወደ እኛ ህይወትም ስንመጣ ተመሳሳይ ነው፡፡ ብዙዎቻችን በየቀኑ በሚገጥሙን ጥቃቅን ውጣውረዶች የተነሳ ምንም የሚገድል ነገር በሌለበት ቀድመን እንሞታለን፡፡ ችግሮቻችን የቱንም ያህል የገዘፉ ቢሆንም የፈጠረን እና የማይተወን አምላክ ክንዶች ደሞ ከችግሮቻችን ሺ እጥፍ የበረቱና የገዘፉ መሆናቸውን እናስብ፡፡

ምንጭ~~Yegtm maebel
መልካም ቀን


SHARE & JOIN
.
@weludabrhan
@weludabrhan
@weludabrhan
👆👆👆❤️👆👆👆

Читать полностью…

Motivational Stories

If you 𝗙𝗔𝗜𝗟, never give up
Because it means
𝗙irst 𝗔ttempt 𝗜n 𝗟earning.

𝗘𝗡𝗗 is not the end,
In fact it means
𝗘ffort 𝗡ever 𝗗ies.

If you get 𝗡𝗢 as an answer,
Remember it means
𝗡ext 𝗢pportunity.

So,
Let's 𝗕𝗘 𝗣𝗢𝗦𝗜𝗧𝗜𝗩𝗘 ☑

✨ @Ethio_Stories

Читать полностью…

Motivational Stories

ትዕቢትና ውርደት አካልና ጥላ ናቸው። ስይለያዩ ሁልጊዜ ቀዳሚና ተከታይ ሆነው ተያይዘው ሲሄዱ ይኖራሉ።

Читать полностью…

Motivational Stories

Look at this pic 😳😳😳


@Ethio_Stories

Читать полностью…

Motivational Stories

እንዲ አይነት ጓደኛ ይስጠን አሜን!!☺️

Читать полностью…
Subscribe to a channel