The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
ኢትዮ ቴሌኮም የስማርት ሲቲ (ስማርት ቢሾፍቱ) ፕሮጀክትን ዕውን ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ከከተማዋ አስተዳደር ጋር ተፈራረመ!
የስማርት ቢሾፍቱ ፕሮጀክት በምዕራፍ ከተማዋን ለማዘመን የሚያስችል የክላውድ፣ ጥሪ ማዕከል፣ ዳታ ሴንተር፣ እጅግ ከፍተኛ ፍጥነት እና ጥራት ያለው ኢንተርኔት፣ የኦፕቲካል ፋይበር እና ሌሎች የዲጂታል መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ፕሮጀክቱ የመዘጋጃ አገልግሎቶችን ጨምሮ ትምህርት፣ ጤና፣ ግብርና፣ ትራንስፖርት እና የግብር አሰባሰብ የመሳሰሉ አገልግሎቶችን ለማዘመን እንዲሁም አስተማማኝ ደህንነት ያላት ከተማን ዕውን ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው አጽንኦት ተሰጥቷል።
በተጨማሪም ሁሉንአቀፍ የዲጂታል ሶሉሽኖችን ተጠቃሚነት ከማሳደግ ባሻገር ክፍያዎችን በቴሌብር በቀላሉ በማስፈጸም ውጤታማነትን በእጅጉ ለማሳደግ የሚያስችል ሲሆን፣ ይህም ተገልጋዮች ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ እና የአኗኗር ዘይቤን ለመቀየር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተብራርቷል።
በተለይም ከተማዋን ለቱሪዝም መዳረሻነት፣ ለኮንፍራንስ ከተማነት፣ ለኢንዱስትሪ (Economic zone) እና የተለያየ ኢንቨስትመንት ያላትን አቅም በማሳደግ ተወዳዳሪነትን እንደሚጨምር እና የቢዝነስ እንቅስቃሴን በማሳለጥ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን እንደሚያሻሽል ተገልጿል።
#SmartCity #Bishoftu #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia #GSMA #ITU
🎦 ኦፕን ኤየር ሲኒማ በግዮን ሆቴል!
ከሚወዷቸው ጋር ጥሩ ጊዜ ለማሳለፍ ነገ እሑድ ኅዳር 01 ቀጠሮዎን በግዮን ሆቴል ያድርጉ!
❇️ VIP: 500 ብር
❇️ መደበኛ፡ 300 ብር ብቻ
የመግቢያ ትኬቱን በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr አሁኑኑ ይቁረጡ!
telebirr SuperApp➡️Payment➡️Event & Ticketing➡️Open Air Cinema
🗓እሑድ ኅዳር 01/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11፡30 ጀምሮ
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል፤ የማይረሳ ጊዜ ያሳልፉ!!
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
🎀 የሞባይል ጥቅል በቴሌብር በመግዛት ተጨማሪ 10% ስጦታ ያግኙ!
ቴሌብር ሱፐርአፕን ወይም *127# በመጠቀም የሞባይል ጥቅል ሲገዙ ተጨማሪ 10% ስጦታ ያገኛሉ።
🔗 ቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr ይጫኑ!
ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSupperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia
የሥራ ዕድሎችን በጉግል ያግኙ!
ጉግል ላይ የሚገኙበትን አካባቢ በትክክል በመሙላት በአቅራቢያዎ የሚገኙ የሥራ ዕድሎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
Secure Your Business With Our Comprehensive Managed Security Solutions!
🛡 Manage, monitor, detect, prevent, and respond to cyber threats effectively.
💼 Stay ahead in the ever-evolving cyber landscape.
🔧 Safeguard your digital assets and infrastructure.
Secure your business today!
For more, please visit: https://bit.ly/4a2y32x
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
✴️ የ28ኛው ዙር አድማስ ዲጂታል ሎተሪ አሸናፊዎች ታወቁ!
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው 28ኛው ዙር አድማስ ዲጂታል ሎተሪ በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዕድል አዳራሽ በሕዝብ ፊት ወጥቷል !
አሸናፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ🎉🎉
💁♂️ 29ኛው ዙር ቀጥሏል፤ በቴሌብር ወይም ወደ 605 A ብለው በመላክ በ10 ብር ዕድልዎን ይሞክሩ!
🍀 ዕድል ከእርስዎ ጋር ትሁን!
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት እና ኢትዮ ቴሌኮም በአጋርነት
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
⚽️🎬 እግር ኳስን እና ፊልሞችን ጨምሮ ከ125 በላይ ምርጥ ምርጥ ቻናሎችን ከኢጋዶ ፕላስ!!
🔥 ኢጋዶ ፕላስ የአገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ልዩ ልዩ የቀጥታ ፕሮግራሞች፣ የመረጃ እና የመዝናኛ አማራጮችን ጨምሮ በርካታ ቻናሎችን ይዞ ከተፍ ብሏል፡፡
✅ በሳምንታዊ እና ወርኃዊ አማራጮች ኢትዮ ገበታ *999# ላይ መዝናኛ አገልግሎት በሚለው አማራጭ ስር ይመዝገቡ፡፡
🔗 በሚደርስዎ ድረ-ገጽ ሊንክ እና የይለፍ ቃል ይግቡ ወይም መተግበሪያውን https://onelink.to/4bgmbj ያውርዱ፤ እንደልብዎ ይዝናኑ!
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSupperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia
በኩባንያችን ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የተመራ ልኡካን ቡድን ስማርት ሲቲ ፕሮጀክትን ጨምሮ የዲጂታል ሶሉሽኖች እና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ለማስፋፋት የሚያስችል ውይይት ከሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና የሆሳዕና ከተማ አስተዳዳር ከንቲባ ጋር አደረጉ።
#Hosaena #SmartCity #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU
እነሆ #5G በወላይታ ሶዶ!
በወላይታ ሶዶ የ5ጂ ሞባይል አገልግሎት ጅማሮ በተለያዩ ደማቅ መርሐ ግብሮች አብስረናል!
የዘመናችን የመጨረሻው እና እጅግ ፈጣን የ5ኛ ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ (5G) አገልግሎት መጀመር በወላይታ ሶዶ ማብሰራችንን ተከትሎ ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን እና የኩባንያችን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የታደሙበት፣ በከተማዋ ህዝብ አብሮነት የደመቀ አዝናኝ የ5ጂ ጅማሮ ማብሰሪያ የመንገድ ላይ ትርኢት መርሐ ግብሮችን አከናውነናል፡፡
የ #ወላይታ ሶዶ ከተማ ህዝብ እና በየደረጃው ያሉ ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች ላደረጉልን ሞቅ ያለ አቀባበል እንዲሁም ለነበረን ስኬታማ ቆይታ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን!!
#5ጂ_በወላይታ_ሶዶ
#ዲጂታል_ኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ
#5G #Wolaita #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
እነሆ #5G በሆሳዕና!
የሆሳዕና ከተማን የ5ጂ ሞባይል አገልግሎት ጅማሮ በተለያዩ ደማቅ መርሐ ግብሮች ለነዋሪዎች አብስረናል!
የዘመናችን የመጨረሻው እና እጅግ ፈጣን የ5ኛ ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት ጅማሮ ለማብሰር ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን እና የኩባንያችን ከፍተኛ ኃላፊዎች የተገኙበት እንዲሁም በከተማዋ ህዝብ አብሮነት የደመቀ የመንገድ ላይ ትርኢት እና ተያያዥ መርሐ ግብሮች አከናውነናል፡፡
የሆሳዕና ከተማ ህዝብ እና በየደረጃው ያሉ የመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች ላደረጉልን ሞቅ ያለ አቀባበል እና ለነበረን ውጤታማ ቆይታ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡
#5G_ለሆሳዕና
#ዲጂታል_ኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ
#5G #Hosaena #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
🌟 ገንዘብዎን በምቾትና በቅልጥፍና ይቀበሉ፤ ተጨማሪ 8% የገንዘብ ስጦታ ያግኙ!!
✅ ከባህርማዶ በቴሌብር ሬሚት እና በቪዛ የተላከልዎን ሐዋላ በቴሌብር ሲቀበሉ በአቢሲኒያ ባንክ ዕለታዊ ተመን
✅ በዌስተር ዩኒየን (Western Union)፣ ኦንአፍሪክ (onafriq) እንዲሁም ቱንስ (Thunes) የተላከልዎን ደግሞ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዕለታዊ የምንዛሬ ተመን ይደርስዎታል፡፡
💁♂️ በተጨማሪም 8% የገንዘብ ስጦታ ያገኛሉ፡፡
🗓 እስከ ኅዳር 21//2017 ዓ.ም
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSupperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia
በኩባንያችን ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የተመራ ልኡካን ቡድን የዲጂታል ሶሉሽኖች እና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ለማስፋፋት የሚያስችል ውይይት ከሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና የሆሳዕና ከተማ አስተዳዳር ከንቲባ ጋር አደረጉ።
በዚህም ወቅት የስማርት ሲቲ ፕሮጀክትን ጨምሮ የአገልግሎት ክፍያዎች፣ ትምህርት፣ ጤና፣ ግብር፣ ቱሪዝም የመሳሰሉ ዘርፎችን በዲጂታል በማዘመን የሆሳዕና ከተማን ለነዋሪዎች፣ ለኢንቨስትመንት እና ጎብኝዎች ምቹ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
ኩባንያችን በከተማዋ መልሶ ማልማት ከመስተዳድሩ ጋር በቅንጅት በመስራት የቴሌኮም መሠረተ ልማቶችን ከማዘዋወር ባሻገር ቀጣይ የከተማዋን እድገት መሰረት ያደረገ ማስፋፊያ እያከናወነ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በማህበራዊ ኃላፊነት ረገድም በአረንጓዴ አሻራ እና አነስተኛ የኑሮ ደረጃ ላላቸው ተማሪዎች የደብተር ልገሳ በማከናወን አርአያነት ያለው ተግባር እየፈጸመ በመሆኑ ምስጋና ቀርቧል፡፡
የሆሳዕና ከተማ ህዝብ፣ የዞን እና የከተማ አስተዳደር ላደረጉልን የሞቀ አቀባበል እንዲሁም ለነበረን ስኬታማ ቆይታ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡
#ዲጂታልኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ
#Hosaena #SmartCity #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU
የ5ጂ ሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በ #ቢሾፍቱ መጀመሩን በማስመልከት የተለያዩ ደማቅ የመንገድ ላይ መርሐ ግብሮች አከናውነናል!
የዘመናችን የመጨረሻው እና እጅግ ፈጣን የ5ኛ ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በ #ቢሾፍቱ መጀመሩን ማብሰራችንን በማስከተል ከከተማዋ ነዋሪዎች እና ደንበኞቻችን ጋር በአብሮነት የደመቀ አዝናኝ የ5ጂ መንገድ ላይ ትርኢት እና የኮንሰርት መርሐ ግብሮች ተካሄደዋል፡፡
የ #ቢሾፍቱ ከተማ ሕዝብ፣ የከተማ መስተዳድር እና በየደረጃው ያሉ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች የ5ጂ መርሐ ግብራችን ደማቅ እና ስኬታማ እንዲሆን ስላደረገላችሁልን ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡
#5G #ቢሾፍቱ
#ዲጂታል_ኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ
#5G #Bishoftu #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
#5ጂ በቢሾፍቱ!! ተጀመረ!!
ኩባንያችን የዘመናችን የመጨረሻው እና እጅግ ፈጣን የሆነው የአምስተኛው ትውልድ (5ጂ) የሞባይል አገልግሎት በቢሾፍቱ ከተማ በይፋ ማስጀመሩን ስናበስር ታላቅ ደስታ ይሰማናል!
በዛሬው እለት ይፋ ያደረግነው የ5ጂ ሞባይል ኔትወርክ ኩሪፍቱ ወተር ፓርክ፣ በምስራቅ ኢንዱስትሪ ዞን፣ ሰንሻይን፣ ግራር ሜዳ እና የረር የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማህበር የሚገኙ አካባቢዎች የሚሸፍን ነው፡፡
የአገልግሎቱ ተግባራዊ መሆን እያደገ የመጣውን የደንበኞች ዳታ ፍላጎት ለማስተናገድ ከማስቻሉ ባሻገር ተሞክሮን የሚጨምሩ የዲጂታል ሶሉሽኖችን በማቅረብ የዜጎችን ህይወት ለማዘመን እና ቢዝነስን ለማቀላጠፍ እንዲሁም አዳዲስ የዲጂታል ሥራ እድሎችን በመፍጠር የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ያረጋግጣል፡፡
የ5ጂ አገልግሎት ከፍተኛ ፍጥነት ያለው፣ ዳታ የማስተላለፍ መዘግየትን በእጅጉ በመቀነስ ፋብሪካዎችና ኢንዱስትሪዎችን ከማዘመን በተጨማሪ ለሀገራችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ እንደ ግብርና፣ ጤና፣ ትምህርት፣ ማዕድን፣ ትራንስፖርት ያሉ ዘርፎችን አሰራር በማቀላጠፍ ተወዳዳሪነትን ይጨምራል፡፡
ክቡራን ደንበኞቻችን የ5ጂ አገልግሎትን ለማግኘት የሚያስችሉ ቀፎዎች በመጠቀም በእጅግ ፈጣኑ ኔትወርክ አስደሳች ተሞክሮ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በደስታ እንገልጻለን፡፡
ቀደም ሲል የ5ጂ ሞባይል ኔትወርክ አገልግሎትን በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ጂግጂጋ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ባህር ዳር፣ ሐዋሳ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሆሳዕና እና አርባ ምንጭ ከተሞች ማስጀመራችን ይታወሳል፡፡
አዲስ ፍጥነት፣ አዲስ ምቾት፣ አዲስ አኗኗር!
#ዲጂታል_ኢትዮጵያን ዕውን በማድረግ ላይ
ለተጨማሪ: https://bit.ly/48PskNK
#Bishoftu #5G
⛳️ ⚽️ በፋንታሲ ስፖርት ጌሞች እየተዝናኑ ይሸለሙ!
💡 ራስዎ በሚመሠርቱት ቡድን እየተጫወቱ በሰበሰቡት ነጥብ ልክ የአየር ሰዓት ሽልማት ያገኛሉ፤ በፋንታሲ ስፖርት ጌሞች ዘና ለማለት ወደ 7074 ok ብለው ይላኩ፤ በሚደርስዎት የምስጢር ቁጥር አገልግሎቱን ያስጀምሩ!
💁♂️ ለ3 ቀናት በነጻ፤ ከወደዱት በቀን 2 ብር ብቻ!
🔗 ጨዋታዎቹን https://11players.et ላይ ያገኟቸዋል፡፡
🛑 ለማቋረጥ Stop ብለው ወደ 7074 ይላኩ።
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
🎉✨ በሚወዱት ዜማ ዘና እያሉ ዕድልዎን ይሞክሩ!!
ለጥሪ ማሳመሪያ ተመዝግበው ሙዚቃዎችን ወይም መንፈሳዊ ዜማዎችን እንደገዙ ከ645 ለሚደርስዎት ጥያቄዎች ትክክለኛ ምላሽ በመስጠት ዕድልዎን ይሞክሩ!
📺 ስማርት ቴሌቪዥኖች
💻 ላፕቶፖች
📱 5ጂ ስማርት ስልኮችና ሳምሰንግ ታብሌቶች
🎁 እንዲሁም በርካታ የሞባይል ጥቅሎችን በሽልማት ያግኙ!
ለመመዝገብ 822 ወይም *822# ይደውሉ አልያም http://www.crbt.et ይጎብኙ!
🗓 እስከ ታኅሣሥ 28/2017 ዓ.ም ብቻ!
#CRBT
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
የኢትዮ ቴሌኮም 10% አክሲዮን ሽያጭ ብስራትን ተከትሎ 100 ሚሊዮን መደበኛ አክሲዮኖች እየተሸጡ ይገኛሉ!
የአንድ ሼር ዋጋ 300 ብር፣ ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን 9,900 ብር (33 አክሲዮኖች)፣ ከፍተኛው 999,900 ብር (3,333 አክሲዮኖች) ነው፡፡
የአክሲዮን ሽያጩ በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr ይከናወናል፤ እርሶም የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል፡፡
ለተጨማሪ: https://bit.ly/3Y9JUae ይመልከቱ!
የደንበኛ ሳቢ መግለጫውን https://teleshares.ethiotelecom.et/ ያንብቡ፡፡
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
የኢትዮ130 6ኛ ዙር ዕድለኞች እንኳን ደስ አላችሁ! 🎉🎉
💡 ሽልማቱ እንደቀጠለ ነው፤ ጥቅልና የአየርሰዓት በመግዛት፣ የአገልግሎት ክፍያዎችን በቴሌብር በመፈጸም እንዲሁም ገንዘብ በመላክና በመቀበል ተጨማሪ የጨዋታ ዕድሎችን ያግኙ!
🚘 6 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖች
🛺 7 ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች
💰 በየቀኑ የ20 ሺህ ፤ በየሳምንቱ የ50 ሺህ እና 100 ሺህ ብር ገንዘብ ሽልማቶች በቴሌብር
📱 ዘመናዊ ስማርት ስልኮች እንዲሁም
🎁 በርካታ የሞባይል ጥቅሎች!
✅ በቴሌብር ሱፐርአፕ ኢትዮ130 መተግበሪያ ወይም ለኢትዮ ፕሮሞ *130# ለኢትዮ ላኪ ስሎት *131# በመደወል ይመዝገቡ!
ለተጨማሪ መረጃ፡ https://bit.ly/3Y0pGzs ይጎብኙ!
#130_ዓመታትን_በጽናት_ታላቅ_አገርና_ሕዝብ_በማገልገል_ላይ
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
ጥቅምትን ለአበበች ጎበና ቻሪቲ!
👐 በዚህ ወር በማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችን በሚቀላቀሉ አዲስ ተከታዮች (Followers) ብዛት ልክ 30 ብር እንዲሁም በሚጋሩ ልጥፎች (Share) ልክ 10 ብር ለአበበች ጎበና ቻሪቲ እንለግሳለን!
🤝 እርስዎም ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይከተሉ፤ ፖስቶቻችንን ያጋሩ፤ ለወገን ድጋፍ ይተባበሩ!
ቴሌግራም | ፌስቡክ | ኢንስታግራም | ሊንክዲን | ዩትዩብ | ethio_telecom?lang=en">ቲክቶክ
በተጨማሪም በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr ለበጎአድራጎት በሚለው አማራጭ የፈቀዱትን የገንዘብ መጠን በመለገስ ለወገንዎ ተስፋ ይሁኑ!
🤌 ዘላቂ የጋራ ማኅበራዊ ኃላፊነት ለወገን ብሩህ ተስፋ!
#MatchingFundForSustainableFuture
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
በኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የተመራ ልኡክ የአርባ ምንጭ ከተማን ስማርት ሲቲ ፕሮጀክት ለመተግበር እንዲሁም መሰረተ ልማት በቅንጅት ለማከናወን የሚያስችል ውይይት ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፣ ከዞኑ ዋና አስተዳዳሪ፣ ከከተማዋ አስተዳዳር ከንቲባ እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር አድርጓል።
#SmartCity #ArbaMinch #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
#5G በአርባ ምንጭ!
እነሆ በ #አርባ_ምንጭ ከተማ የ5ጂ ሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት ጅማሮን በተለያዩ ደማቅ መርሐ ግብሮች አብስረናል!
ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን እና የኩባንያችን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በታደሙበት መርሐ ግብር የዘመናችን የመጨረሻው እና እጅግ ፈጣን የ5ኛ ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በ #አርባ_ምንጭ መጀመሩን ማብሰራችንን በማስከተል ከአርባ ምንጭ ከተማዋ ነዋሪዎች ጋር በአብሮነት የደመቀ አዝናኝ የ 5G መንገድ ላይ ትርኢት መርሐ ግብር አከናውነናል፡፡
የ #አርባ_ምንጭ ከተማ ህዝብ እና በየደረጃው ያሉ ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች ላደረጉልን ሞቅ ያለ አቀባበል እንዲሁም ለነበረን ውጤታማ ቆይታ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡
#5G #አርባ_ምንጭ
#ዲጂታል_ኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ
#5G #ArbaMInch #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
5ጂ በአርባ ምንጭ በይፋ ማስጀመራችንን ተከትሎ በኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የተመራ ልኡክ የአርባምንጭ ከተማን በስማርት ሲቲ እና ዲጂታል ሶሉሽኖች ያለመ ውይይት ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፣ ከዞኑ ዋና አስተዳዳሪ፣ ከከተማዋ አስተዳዳር ከንቲባ እና የሥራ ኃላፊዎች ጋር አደረገ።
የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት የደረሰበት ደረጃ የቀረበ ሲሆን ከተማዋን ለነዋሪዎቿ፣ ለጎብኚዎች እና ለኢንቨስትመንት በሴፍ ሲቲ ሶሉሽን ምቹ እና ደህንነቷ የተጠበቀ ለማድረግ የሚያስችል ፍሬያማ ውይይት ተደርጓል፡፡
ውይይቱ ኩባንያችን የዘረጋውን ግዙፍ መሰረተ ልማት በመጠቀም የመስተዳድሩን መሬት አስተዳደር ጨምሮ እንደ ትምህርት፣ ጤና፣ ግብር፣ ቱሪዝም ያሉ ቁልፍ አገልግሎቶችን በዲጂታል ሶሉሽኖች ማዘመንን ያካተተ ነው፡፡
ለሀገራችን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እውን መሆን መደላድል የሆነውን የዲጂታል መታወቂያ ለዜጎች ለማዳረስ ኩባንያችን ለሚያደርገው ጥረት የትብብር ጥሪ የቀረበ ሲሆን፣ በዚህም ኩባንያችን ለዜጎች የስራ እድል እየፈጠረ እንደሚገኝም ተብራርቷል፡፡
የከተማዋ የኮሪደር ልማት ከመስተዳድሩ ጋር በቅንጅት እየተከናወነ መሆኑ የተወደሰ ሲሆን ይህም አገልግሎት እንዳይቋረጥ እና ሀብት እንዳይባክን ሚና መጫወቱ ተገልጿል፡፡
በመጨረሻም ኩባንያችን በዲጂታል ላይብረሪ፣ በችግኝ ተከላ እና ለዝቅተኛ ገቢ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት መርጃ መሳሪያ በመለገስ ላከናወነው አርአያነት ያለው ተግባር ምስጋና ቀርቧል።
ለተደረገልን አቀባበል እና ለነበረን ውጤታማ ቆይታ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን!
መልካም የሥራ ሳምንት !
#Monday #MondayMotivation
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
በኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የተመራ የኩባንያችን ልኡክ የወላይታ ሶዶ ከተማን በዲጂታል ሶሉሽኖች ለማዘመን ያለመ ውይይት ከወላይታ ሶዶ ከተማ መስተዳድር ከንቲባ እና ኃላፊዎች ጋር አድርጓል።
ዋና ስራ አስፈጻሚያችን የቴክኖሎጂን ትሩፋት አሟጦ በመጠቀም ተቋማትን በዲጂታል መፍትሔዎች በማዘመን የዜጎችን ሕይወት ለማቅለል ኩባንያችን ለሚያደርገው ጥረት የመስተዳድሩ እና የባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
በከተማዋ የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት እውን ለማድረግ በተጀመረው ስራ፣ ቢሮዎችን በስማርት ኦፊስ ማዘመንን ጨምሮ የአገልግሎት ክፍያዎች፣ ትምህርት፣ የግብር አሰባሰብ፣ ቱሪዝም እና የከተማዋን ደህንነት በዲጂታል በማዘመን ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡
በውይይቱ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን በማፋጠን ረገድ እንዲሁም በማህበራዊ ኃላፊነት በወላይታ የተከናወኑ ተግባራት በመስተዳድሩ የተደነቀ ሲሆን ይህም በኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡
#ዲጂታልኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ
#Wolaita #SmartCity #GSMA #ITU #WorldBank #OECD