"እኔ ቃል ተመልቻለሁና በውስጤም ያለ መንፈስ አስገድዶኛልና በተሃ ጠጅ እንደተሞላና ሊቀደድ እንደቀረበ አቁማዳ ሊፈነዳ እንደማይችል እንደ ወይን ጠጅ አቁማዳ እነሆ አንጀቴ ሆነ ጥቂት እንድተነፍሰ እናገራለሁ ከንፈሬን ገልጨ እመልሳለሁ
መጽሐፈ ኢዮብ 32፡ 18–20
🇨🇬 "በድቅድቅ ጨለማ (በቀቢጸ ተስፋ) ላሉት ብርሃን በራላቸው" እንዳለ መጽሐፍ እውነተኛ ኢትዮጵያዊያን የተዋሕዶ ልጆች ተስፋ ቆርጠን በጠፋንበት ዘመን እግዚአብሔር ድምጹን ያሰማን፣ ፈቃዱን ያሳወቀን በመጀመሪያይቱ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት የዛሬ 19 ዓመት በኅዳር 7 ቀን 1998 ዓ.ም እንደዚህች ባለችቱ ቀን ነበር። ይኸው ለእኛ ለኢ/ዓ/ብ ቤተሰቦች 19 ወርቃማ ዘመናት በእሳት መፈተኛ ሆነውን በንቅለ ተከላ ውስጥ እያለፍን እንገኛለን። አሁንም ቀሪውን አሳልፎ ሕግጋተ ሥላሴ ፀንቶ ኢትዮጵያ ለዓለም ገዢና ብርሃን ለምትሆንበት የትንሣኤው ዘመን ያድርሰን!! አሜን!
#ንስሐ እንግባ !
#ዛሬም
🇨🇬 አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (እውነትን አፍቅራት፤ አንግሣትም!!)
🇨🇬 ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ ማን ናት?
በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ተከታታይ ትምህርት
ክፍል - 2
ለኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች ብቻ !!
ሚያዝያ 11-2016 ዓ.ም
🇨🇬 በእንተ ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ ሣልሳዊ፦
👑 «...ንጉሠ - ነገሥት ቴዎድሮስ ኢትዮጵያዊ የተዋህዶ ኦርቶዶክስ ልጅ ነው ፡፡ በመልእክቶቹ ሁሉ እንደተናገረው ድሃ ጎስቋላ ሊቅ ያልሆነ ምናምንቴ ሰው ነው ፡፡ ስለሱ መመረጥ የታወኩ ነውም ብለው ለመቀበል የተቸገሩ እንዳሉ ግልፅ ነው ፡፡
👑 በቁጥር ቀላል ያልሆኑ በብዙ ምክንያቶች እራሳቸውን ቴዎድሮስ ነን ብለው አምነው የቆሙ ሰዎች አሉ ፡፡ ይህ ምንም አይደለም ሁሉ ወደፊት ስለሚገለጥ ወደ ብርሃንም ስለሚወጣ እንደዚህ ያሰቡበትንና ያመኑበትን መንገድ ስለሚገለፅ ብዙም ከዚህ በላይ መግለፁ ወቅታዊ አይሆንም ፡፡
👑 ንጉሡና ሌሎችም አባቶች እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ያሉት ፡፡ ከዋናው ከተማ ጀምሮ በሁሉም የአገሪቱ ክልል በተለያየ ጉዳይ እየተንቀሳቀሱ ሁሉንም ድርጊት ይከታተላሉ ፡፡ በመገለጡ ሰአት በቀዳማይ ምክትልነትና በምክትልነት በግራና በቀኝ የሚሆኑ በንጉሥ ማእረግ ያሉ ዛሬም አብረውት በሥራው ሁሉ እያገዙትና አብረውም እየሰሩ ነው ፡፡ ሌሎች 37 የሚሆኑ በንጉሥ ማእረግ ያሉ በየባእታቸው ሆነው ፤ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሕብረትና አንድነት በሁሉም እያገዙ የሚገኙ ናቸው ፡፡ ሁሉም ሊያውቀው የሚገባው ቢኖር ዘመናዊ መገናኛ እስካለ ድረስ ፤ በቴሌግራም የዮሐንስ ራእይ 20 ቻናል ላይ ስለሁሉም ሁኔታ በቀጥታ የሚገለፅበት ይሆናል ፡፡ የንጉሠ ነገሥቱም ፣ የንጉሦቹም ድምፅ የምትሰሙበት የሚገለጥበት ነው ፡፡ ከዚህ በተረፈ በኢትዮጵያ የአለም ብርሃን መልእክታት በግልፅ የምታገኙት ነው ። ቴሌግራሙም እስካለ ድረስ ነው የሚያገለግለው ፡፡ ከዚህ ውጪ የሚመጣ ነገር የለም ፡፡ ተስፋ የምታደርጉት የኢትዮጵያ ትንሳኤም ሆነ የንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስና አብረውት የሚገለጡት ንጉሦች እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ታላላቅ አባቶች መላውን ዓለም በተዋህዶ እምነት የሚመሩት በይፋ የሚገለፅበት የሚታወቅበት ይኸው መንገድ ብቻ ነው ፡፡ ከዚህ በዘለለ ሌላ እውነት አለን ካላችሁ በርቱ ቀጥሉበት እንላለን ፡፡ ዳኛው በሰማይ በመንበሩ ሆኖ ሁሉንም ስለሚመለከት እንደየታመንበት ፍርዱም ትእዛዙም አብረው ይገለጣሉ ፡፡
👑 በሌላ በኩል -- እንደ እውነቱ ከሆነ እኔን ለምትቃወሙ ቅሬታም የለብኝ እኔ ዛሬም ነገም የምለው የማምነው የምረዳው አምላኬም ያስተማረኝ እውነትና እውነትን ብቻ መግለፅ ነው ፡፡ ስለዚህ እኔ ከሁሉ የማንስ ነኝ ፡፡ በሁሉም ገፅታ ከኔ ትበልጣላችሁ ብዬ አስባለሁ ፡፡ ግን በምን መስፈርት እኔን እንደመረጠ እኔም ስለማልረዳ እናንተ ቅር የተሰኛችሁ ሁሉ መድሃኒያለምን ድንግልን ጠይቁ መልስን ታገኛላችሁ ፡፡ ይህን ያልኩት በዚህ ምክንያት እንዳትሰናከሉ በማሰብ ነው ፡፡
👑 ንጉሥ ዳዊትን ልኡል ሲመርጠው ታላላቅ ወንድሞቹን እንዳላስደሰተ ሁሉ ሳሙኤልንም ግራ አጋብቶአል ፡፡ ጌታ ግን ለሳሙኤል መልስ ሰጥቶታል መልሱም እግዚአብሔር ልብን እንደሚያይ ውጪያዊ ገፅታን እንደማይመለከት አረጋግጦለታል ፡፡ ነቢያትን በተለይም ሃዋሪያትን ጌታ የመረጠው ከተናቀው ሥፍራ እንደሆነ ሁሉም የሚያውቀው ነው ፡፡ በሥራዬ ለእግዚአብሔር ምንም የሠራሁት በምግባሬም ያስደሰትኩበት ሥራ የለኝም ። በአንድ ነገር ብቻ አስቦኝ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ ፡፡ እሱም የፈጠረኝን አምላኬን ከከፋው ሃጢያቴ ያዳነኝን እንደሰው የቆጠረኝን አምላኬን ውዳቂ ነው ብላ ያልተወችን እናቴን ድንግልን አብዝቼና በፍፁም ልቤ እወዳቸዋለሁ። ሌላ የማውቀው ሰርቼ ያስደሰትኩበት ምንም የለኝም ፡፡ እውነቱ ይህ ነው ፡፡
👑 እንግዲህ ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ ማነው ለምትሉ ሁሉ ፣ ለወዳጅም ለጠላትም ፤ ግራ ገባን ለምትሉ ከላይ ምንነቱን በመጠኑ እንድታውቁት ለማድረግ ጥሬአለሁ ፡፡ ጊዜው ሲደርስ የሱንም የሌሎችንም ማንነት በግልፅ የምታዩበት ጊዜ ይመጣል ፡፡ መታገሥ ነው ፡፡
👑 አንድ ነገር እርግጥ እንዲሆንላችሁ የምፈልገው ሁሉንም እውነት መገለፅም ቢሆን በራእይ ዮሐንስ 20 ቻናል ላይ በልጃችን በተከፈተው ገፅ ላይ የምትሰሙት ይሆናል ፡፡ መልእክታቱም ሁሉ አንዱ የኛ መግለጫ መስመር ናቸው ፡፡ እነዚህም ሁሉ በመከራው ክብደት ቢዘጉ ሌላ መንገድ እናዘጋጃለን ፡፡ በዚያን ሰአት መነቃነቅ ቀርቶ መደበቂያ የሚያጣው ከሃዲው ትውልድ ይጨነቅ እንጂ ! እኛ እውክታ የለብንም ፡፡
👑 ሌላው ጉዳይ ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ እኔ ነኝ የሚሉ እጅግ ብዙ ሰዎች እንዳሉ ይገመታል ፡፡ ብዙም ሲናገሩ እየተሰሙ ናቸው ፡፡ እኔም እየሰማሁ ነው ፤ ከመገረም ውጪ ምን ይባላል ፡፡ እርግጥ ነው ሁሉም ወደ ብርሃን ሲወጣ ማ ምን እንደሆነ ልኡልና ድንግል ስለሚገልጡት መታገሥና መጠበቁ መልካም ነው ብዬ አምናለሁ ፡፡
👑 እንግዲህ እውነቱን ለናፈቃችሁ ይኸው እውነቱን ገልፀናል ፡፡ በኛ ዘንድ ትመዘገቡ ዘንድ ባስታወቅነው መሰረት የተመዘገባችሁ ፤ ስለአመንበት መዝግበናል ፡፡ መታወቂያ የወሰዳችሁ መልካም አድርጋችኋል ፡፡ ለአገልግሎት ስለሆነ የወሰዳችሁት በሰአቱ ትጠቀሙበታላችሁ ፡፡ በመታወቂያው ላይ ያለው ፊርማ የኔው መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ፡፡...»
🇨🇬 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት ዘጠነኛ መልዕክት ገጽ 49–50
ተጻፈ ታኅሣሥ 21/2013 ዓ.ም
josephethiopia7?si=YgMMb8sSTOz9wtx1" rel="nofollow">https://youtube.com/@josephethiopia7?si=YgMMb8sSTOz9wtx1
Читать полностью…📗📙📕 አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ፥ የኢትዮጵያንና የተዋሕዶን ትንሣኤ እንመሰክራለን !
✝👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾✝👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾✝
🟩 t.me/AlphaOmega930 (👨👧👦ግሩፕ)
🟨 t.me/christian930 (👩👧👦ቻናል)
🟥 t.me/Ewnet1Nat (🗣ንጽጽር)
🟢 t.me/ethioBirhan (✨በልዩ ልዩ ቋንቋዎች)
🟡 t.me/Amharic_messages (🔑በአማርኛ ብቻ)
🔴 t.me/EthioLightContents (🗞ማውጫ)
💚 t.me/aleqayalew (✝አለቃ አያሌው ታምሩ)
💛 https://www.facebook.com/joseph.ethiopia1 (📲በፌስቡክ)
❤️ https://youtube.com/channel/UCfoPIJgkHyihgUwMhvOzWXw (📡በዩቱብ)
💡 እነዚህን አማራጮች ማግኘት ያልቻላችሁ ወገኖቼ በማስፈንጠሪያቸው (Link) በመቀላቀል (Join) በማድረግ አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ ድኅረ ገጽን መከታተል፤ ከልዑል እግዚአብሔር በቀጥታ ለመላው የአዳም ዘር የሚተላለፉ የቅዱሳን አባቶችን መልዕክታት ማግኘትና የዓለምን መጻኢ እጣፈንታና የፍርድ አፈጻጸም ሒደት መከታተል ትችላላችሁ ።
🔐 ድኅረ ገጾችን በመከታተል፦ #Like #Share #Add_Member #Subscribe #Comment ማድረግ ይቻላል ።
🟢🟡🔴
መስከረም 1 | ርእሰ ዐውደ ዓመት
#ርእሰ_ዐውደ_ዓመት
በግእዝ ዐውደ ዓመት ይባላል - ርእሰ ዐውደ ዓመት - የበዓላት ሁሉ የበላይ፣ ራስ ማለት ነው፡፡ በዓመቱ ውስጥ የሚውሉት በዓላትና አጽዋማት የሚወጡት መስከረም አንድን መነሻ አድርጎ ስለሆነ ርዕሰ ዐውደ ዓመት ተባለ።
[🌼] በዚህች ቀን ከ9ኙ ሊቃነ መላእክት አንዱ የከበረ መልአክ ራጉኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤል መስከረም 1 ቀን ከሊቃነ መላእክት በብርሃናት ላይ የተሾመበት ዕለት ነው።
ግንቦት 1 ቀን ለታላቁ አባት ለሄኖክ ምሥጢራትን የገለጸበት በዓሉ ነው፡፡
በብርሃናት ሁሉ ላይ የሰለጠነ መልአክ ነው። ነቢዩ ሔኖክ "ከቅዱሳን መላእክት አንዱ የሆነ ጸላዒ ዲያብሎስን የሚበቀለው ራጉኤል በብርሃናት ላይ የሰለጠነ ነው" ሲል ስለ እርሱ ተናግሯል፡፡
እግዚአብሔር ዓለምን ይቆጣጠር ዘንድ የሾመው ታላቅና ቅዱስ መልአክ ነው።
የመልአኩ ልዩ ቃልኪዳን፦
"የራጉኤል አምላክ ይቅር በለኝ በማለት አንዲት ቃልስ እንኳን ቢናገር እንደ ወዳጄ እንደ አብርሃም፣ እንደ ባለሟሌም እንደ ይስሐቅ፣ እንደ አከበርኩትም እንደ ያዕቆብ ክብርን ባለሟልነትን እሰጠዋለሁ። በራሱ ላይም አክሊል አቀዳጀዋለሁ። ረጅም ዘመናት ሰፊ፣ ወራትም እሰጠዋለሁ" ሲል ቃሉን ሰጥቶታል፡፡
[🌼] ዳግመኛም በዚህች ቀን ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ ሐዋርያ #ቅዱስ_በርተሎሜዎስ በአሸዋ ከረጢት ውስጥ ተከቶ ወደ ባሕር በመጣል ምስክር ሆኖ ዐረፈ።
[🌼] በዚችም ዕለት #ጻድቁ_ኢዮብ በፈሳሽ ውኃ ታጥቦ ከደዌው ሁሉ ተፈወሰ።
[🌼] ይህች ቀን የታላቁ የቊልዝም ሰው የሆነ ፍጹም ጻድቅ፣ ሰይጣንን አስሮ ዐሥራ አራት ሰው ሊይዙት የማችሉትን ደንጊያ ያሸከመው #የአባ_ሚልኪ የዕረፍት በዓሉ ነው።
#እንኳን_አደረሳችሁ።
T.me/Ewnet1Nat
🇨🇬 በዓለ ደብረ ታቦር (ቡሄ) | ተወዳጆች ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች እንኳን አደረሳችሁ !
🟩 🟨 🟥 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን 🟩 🟨 🟥
🗂 #_የኢትዮጵያ_የዓለም_ብርሃን መልእክቶች፦
የሚፈልጉትን ጽሑፉ ላይ አንዴ ሲነኩ ወደመልእክቱ ያመራዎታልና፥ አውርደው ያዳምጡ!
⚡️, መልእክት 1 ተጻፈ ኅዳር 7/1998ዓ.ም
⚡️, መልእክት 2 ተጻፈ ግንቦት 27/2000ዓ.ም
⚡️, መልእክት 3 ተጻፈ መጋቢት 19/2001ዓ.ም
⚡️, መልእክት 4 ተጻፈ የካቲት 1/2002ዓ.ም
⚡️, መልእክት 5 ተጻፈ መስከረም 21/2004ዓ.ም
⚡️, መልእክት 6 ተጻፈ ታኅሣሥ 19/2007ዓ.ም
⚡️, መልእክት 8 ተጻፈ ታኅሣሥ 21/2011ዓ.ም
⚡️, መልእክት 9 ተጻፈ ታኅሣሥ 21/2013ዓ.ም
➥ቁጥር 9_ክፍል 1
➥ቁጥር 9_ክፍል 2
➥ቁጥር 9_ክፍል 3
➥ቁጥር 9_ክፍል 4
➥ቁጥር 9_ክፍል 5
⚡ መልእክት 10 (ክፍል 1-7) ተጻፈ ጥር 7/2015 ዓ.ም
°°°°° °°°°° °°°°° °°°°° °°°°°
⚡️, ከመልእክት 1—6 & 8 በጽሑፍ (PDF)
⚡️, መልእክት 9 በጽሑፍ (PDF)
⚡, መልእክት 10 በጽሑፍ (PDF)
⚡️, ደብዳቤዎች በድምፅ
⚡️, ደብዳቤዎች በጽሑፍ(PDF)
⚡️, ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን በየጊዜው የተሰጠና የተላለፈ ምክር፣ ማሳሰቢያ፣ መመሪያ፣ መግለጫ፣ ትዕዛዝ፣ ትምህርቶች ወዘተ በቅደም ተከተል
°°°°° °°°°° °°°°° °°°°° °°°°°
☑️ መልእክታቱን በተለያየ ቋንቋ በአንድ ስፍራ ለማግኘት t.me/ethioBirhan መከታተል የሚችሉ ሲሆን ለዚህ ቻናል የተሠራውን ማውጫ ደግሞ t.me/EthioLightContents ላይ ማግኘት ይቻላል!
🌿 እንዲሁም ሁሉንም ኢ/ዓ/ብ መልዕክታት ፤ ትምህርቶችና መግለጫዎች... ብቻ በአማርኛ ቋንቋ የቀረቡትን በቅደም ተከተል ከተለቀቁበት ጊዜ ጋር በቀላሉ ለማግኘት t.me/Amharic_Messages ላይ መከታተል ይችላሉ።
🇨🇬 እነሆ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ፤ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፥ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል።
አይጮኽም ቃሉንም አያነሣም፥ ድምፁንም በሜዳ አያሰማም።
የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም፥ የሚጤስንም ክር አያጠፋም፤ በእውነት ፍርድን ያወጣል።
በምድርም ፍርድን እስኪያደርግ ድረስ ይበራል እንጂ አይጠፋም፤ አሕዛብም በስሙ ይታመናሉ።
ሰማያትን የፈጠረ የዘረጋቸውም፥ ምድርንና በውስጥዋ ያለውን ያጸና፥ በእርስዋ ላይ ለሚኖሩ ሕዝብ እስትንፋስን፥ ለሚሄዱባትም መንፈስን የሚሰጥ አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።
እኔ እግዚአብሔር በጽድቅ ጠርቼሃለሁ፥ እጅህንም እይዛለሁ እጠብቅህማለሁ፥ የዕውሩንም ዓይን ትከፍት ዘንድ የተጋዘውንም ከግዞት ቤት በጨለማም የተቀመጡትን ከወህኒ ቤት ታወጣ ዘንድ ለሕዝብ ቃል ኪዳን ለአሕዛብም ብርሃን አድርጌ እሰጥሃለሁ።
ትንቢተ ኢሳይያስ 42 ፥ 1–7
🇨🇬 ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ ማን ናት?
በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ተከታታይ ትምህርት
ክፍል - 3
ለኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች ብቻ !!
ግንቦት- 23-2016 ዓ.ም
126) እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !!
🇨🇬 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መግለጫ ለኢ/ዓ/ብ ቤተሰቦች ብቻ !!