እንኳን ወደዚህ ምስጢራዊና ድብቅ ጉዳዮችን ወደምናይበት ቻናል በደህና መጣችሁ! ይህንን አዲስ ቻናል በመቀላቀል አዳዲስ ቪዲዮ ስንለቅ እንዲደርሳችሁ ስንል እናሳስባለን፡፡ በዚህ ቻናል፦ አስገራሚ ክስተቶችን፣ ታሪኮችን፣ የታዋቂ ሰዎችን ታሪክ የምናይ ይሆናል፡፡ youtube.com/@EthioEnigma
About Us
Welcome to this channel which is dedicated to exploring intriguing conspiracies and captivating mysteries. Join us on a journey of curiosity and discovery as we delve into the enigmatic realms of the unknown.
In this channel we will see: interesting events, stories, celebrity stories.
Stay Tuned!
Ethio Enigma Hub
💒 የአለማየሁ ዋሴ መፅሐፍት 📚
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
➱ 1, እመጓ
➱ 2, ዝጓራ
➱ 3, መርበብት
➱ 4, ሰበዝ
➱ 5, ሜተራሊዮን
➲ ኦርቶዶክሳዊ መፅሐፍ ማውጫ 📖
➲ /channel/+bmWacGGbXvJjOTQ8
.
🤔 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ⁉️
📌 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
📌 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
📌 ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
📌 ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
📌 ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
📌 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
📌 ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
📌 ዘማሪ ዲ/ን ሮቤል ማቲያስ
📌 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
📌 ዘማሪት አቦነሽ አድነው
📌 ዘማሪት ዶ/ር ሔለን ተስፋዬ
እና የሌሎችንም ...........
ዘማሪዎችን መዝሙሮች እና አዳዲስ
መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር OPEN
የሚለውን ይጫኑት። 👇
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█ 🔰 ✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞ 🔰 █
█ 🔰 ✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞ 🔰 █
█ 🔰 ✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞ 🔰 █
█ 🔰 ✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞ 🔰 █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🔆 እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን!
👉 “ ሁለት ጊዜ ነው የዶሮ ልደት አንዱ በእንቁላል አንዱ በጫጩት ” እንዲሉ የእግዚአብሔር ወልድ ልደቱ ሁለቴ ነው። ማለትም ቅድመ ዓለም ዘእንበለእም(ያለ እናት) ከአብ፤ ድኅረ ዓለም ዘእንበለአብ(ያለ አባት) ከማርያም ተወልዷልና ነው።
👉 አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን በገነት 7 ዓመት ከ3 ወር ከ17 ዕለት በንጽሕና ፍጹም እንደ ፀሐይ እያበሩ፣ እንደ መላእክት እየኖሩ ሳለ በአሣቹ መንፈስ ከሳቱና ድል ከሆኑ በኋላ ለክብርና ለሕይወት ብቻ ተፈጥረው የነበሩት ዓይኖቻቸው ተከፍተው ለክብርና ለውርደት፣ ለሕይወትና ለሞት ሆኑ።..... መዳኛቸውንም እግዚአብሔር ተናገረ።
👉 በሴት እንደሳትክ ከልጅ ልጅህ ከሴት ተወልጄ፣ ከዛፍ ግንድ እንደበላህ በዛፍ ግንድ ተሰቅየ( ዕፅ የሐዩ ዕፅ ይቀትል ማለትም እንጨት ያድናል እንጨት ይገድላል ሚባለው ለዚህም ነው)፣ አሣቹ መንፈስ ዲያብሎስ በትዕቢትና በሴረኝነት እንዳሳተህ አሳቹን መንፈስ በትህትናና በፍቅር ድል ነሥቼ፣ በአንተ ምክንያት በተረገመችው ምድር ነፍስህን ወደ ሲኦል አግብቼ፣ ሥጋህ ገነትን አያያትም እኔ እንደተነሳው በፍጻሜ ሥጋህንና ነፍስህን አዋህጄ የማይሞት የማይበሰብስ መንፈሳዊ ሥጋ ሆኖ ይነሳል።.... የሚለው ሕያው ቃል መሠረት የተጣለበት ዕለት ናት።
👉 ዛሬ የዓለም ፈጣሪ አዳምና ሔዋንን እንዲሁም ዘሮቹን ለማዳን በገባው ቃል መሠረት ከሰማየ ሰማያት ወርዶ፣ በቅድስት ድንግል ማርያም ማኅጸን ያለ መለወጥ አድሮ፣ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ የተወለደበት ዕለት ነው ። በዚህች ዕለትም ለሰው ልጅ እውነተኛው ሰላም ስለተሰጠ መላእክት አመሰገኑ፤ የሰው መዳን ለእነርሱም ደስታቸው ነውና። የጥበብ ሰዎችም ከጥበብ ሀገራቸው ከምሥራቅ ተነስተው የሀገራቸውን ንጹሕ ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤና ሌሎችንም መባቸውን ሰግደው አቀረቡ፤ ኑኀ(ሩቅ) ዘመን ከአያቶቻቸው ዘንድ ታዘዋልና የሄሮድስን ሽንገላ እንጂ የአያቶቻቸው ጠቢባኑን ትንቢት አላቃለሉም፤ እነርሱም ጠቢባን ነበሩና ነው።
👉 በዓል ሽሮ የከበረ፣ ጦም ገድፎ የወፈረ የለም እንዲሉ፤ ጾሙን በሰላም ያስፈጸመን ልዑል እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን። በዓሉንም የበረከት ያድርግልን!
📌 እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን!
✍ ሊቃውንት በቅኔያቸው ከልደት ጋር የተያያዘ ምን አመስጥሮት አስቀምጠውልን ይሆን? የሚለውን በቀጣይ ጽሑፌ አሰፍራችኋለሁ።
✍ ተጻፈ በታዳጊ ኃይለሚካኤል ደሣለኝ።
ቻናል - @EthiopeTowoderos
👉 ይህንን ቻናል በመቀላቀልና ሊንኩል ለሌሎች በማስተላለፍ ይተባበሩን🙏
t.me/All_Books_Ethiopia
https://youtu.be/AQ8yAo7s43w?si=js8vqcb6izVzPKIv
Читать полностью…🛑 እዚሁ ሀገራችን ላይ ተጠንቀቁ❗️ አስደንጋጭ ያልተሰማ የጥቁር አስማት ሴራ | የጨለማው አለም
https://youtu.be/AQ8yAo7s43w?si=js8vqcb6izVzPKIv
📌 ሊቃውንት በቅኔያቸው ከልደት ጋር የተያያዘ ምን አመስጥሮት አስቀምጠውልን ይሆን?
1. 👉 ሥላሴ:-
ለልደተ ክርስቶስ ወማርያም፣
ስብሐተ ናዝልፍ ይሜህረነ መምህር፣
ወይመርሐነ መራሒ መዝሙር።
ለአዳምሰ ዘተሠገወ እምድር፣
ዜናሁ ኀደግነ በኀጺር፣
ሶበሰ ይነውኅ አንቀጸ ነገር፣
በውስቴቱ እምተረክበ ነውር
👉 ትርጉም፦
ለክርስቶስና ለማርያም ልደት፣
ምስጋናን እናዘወትር ዘንድ፣ መምህር ያስተምረናል፣
መሪ መዝሙርም ይመራናል።
ከምድር ሰው የሆነ የአዳም ዜናን፣
ግን በአጭር ተውን፣
የነገር አንቀፅ ቢረዝም ግን፣
በውስጡ ነውር በተገኘ ነበር።
👉 ምስጢር:-
የመዝሙር ዘማሪ መዝሙሩን እያቀነቀነ ተቀባዮቹን እንደሚመራቸው የኢየሱስ ክርስቶስ መወለድና የቅድስት ማርያም መወለድ አስቀድሞ በምሳሌና በትንቢት ተነግሮ ስለተፈፀመ እንከን የሌለበት ሆነ። አንዳንድ አሳፋሪ ድርጊት ያለበትን ነገር አብራርቶ ከማቅረብ ይልቅ ሸፋፍኖ እንዲያልቅ ማድረግ በሽማግሌዎች ዘንድ የተለመደ ነው። የሰው ዘር ሁሉ አባት የሆነው አዳምም አትብላ የተባለውን በለስን በልቶ ያመጣው ፍዳ ለልጆቹ ተረፏቸው። ከዚህም የተነሳ የአባትነቱ ታሪክ የሚያስመሰግን አይደለም። በማለት ባለቅኔው አዳምና ሔዋን የበለስን ፍሬ በመብላታቸው ምክንያት በሰው ልጆች ሁሉ ላይ ተወስኗል የሚባለውን የሞት ፍርድ በቅኔያቸው ምስጢር ያስረዳል።
2. 👉 ሥላሴ፦
ታሰምዕ ለእዝነ ኵሉ፣
ፅንስት ዖፍ ድምፀ አእባን፣
እስከነ ሕማማ ትረስዕ እምከርሣ ጊዜ ወሊዶታ ዕጓለ፣
ከመትርከብ በሰሚዐ ዝንቱ ዕፍረት ወሣህለ።
ርግበ ነጋሢ ሰሎሞን ባሕቱ በዘተረኮቦታ ድንግለ፣
እምከርሣ ሕማም እስመ ሰሰለ፣
ጊዜ ወሊዶታ እምከርሥ ሕፃና ልዑለ፣
ለጾታሃ ኢያስምዐት ቃለ።
👉 ትርጉም፦
የፀነሰች ወፍ የድንጋዮች፤
ድምፅን ለሁሉ ጆሮ ታሰማለች፤
ከሆዷ ልጅን በመውለዷ ጊዜ ህመሟን እክስትረሳ ድረስ ይህን በመስማት እረፍትን፣ ይቅርታንና ሰላምን ታገኝ ዘንድ።
ነገር ግን የነጋሽ ሰሎሞን ርግብ ድንግልን ሆና በመገኘቷ ምጥ ከሆዷ ተወግዷልና፤
ከፍተኛ(የከበረ) ልጅዋን በመውለጃዋ ጊዜ፤
ለወገኖችዋ ቃልን አላሰማችም።
👉 ምስጢር፦
እንደ ግንደ ቆርቁር ያለች አንድ ወፍ አለች፤ ይህች ወፍ ፀንሳ በምትወልድበት ጊዜ የድንጋይ ድምፅ ስታሰማና ስትሰማ ህመሟ (ምጧ) ይቀልላታል ይባላል። ርግብ የተባለችው ቅድስት ማርያም በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ልጇ ክርስቶስን ስትወልድ እንደሌሎቹ ወላድ ሴቶች ምጥ የሌለባትና የምጥ ቃልን ያልሰማች ተባት የሌላት ርግብ ሆነች።
👉 ታሪክ፦
አንዲት ዖፈ ያሬድ የምትባልና ሦስት አይነት ድምፅ የምታሰማ ወፍ አለች፤ በምጧ ጊዜ ኪል እንደምትባል ስስ ድንጋይ ያለ ድምፅን ለሌሎቹ ሁሉ ታሰማለች። በዚህ ጊዜ ምጧ ይቀልላትና በቶሎ ትወልዳለች። ሌሎቹንም በድምጿ ቶሎ ይወልዳሉ ይባላል።
👉 እንግዲህ ሊቃውንት በረቀቁ ቅኔያቸው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ልደትና ተያያዥ ታሪኮችን እንዲህ አራቅቀው አመስጥረውልናል። እኔም ይሄው ከዓለም ሁከትና ግርግር ርቃችሁ ተራቀቁበት ብዬ ጽፌ ለጠፍኩላችሁ።
✍ ኃይለሚካኤል ደሣለኝ።( @HailemichaelDesalegn )
🔰 ቻናል - @EthiopeTowoderos
📚 " መልክአ ሚካኤል ወገብርኤል ካልዕ ጸሎቱና ገቢሩ "
በጥያቄያችሁ መሠረት ከሥራይ መተት፣ ዛር፣ ዓይነጥላ፣ ቡዳ፣ ጥላወጊ... ከርኩሳን መናፍሥት የሚጠብቀው ' መልክአ ሚካኤል ወገብርኤል ካልዕ' የተባለው ጸሎት ከነሙሉ ገቢሩ በPDF አዘጋጅቼ ይሄው በወደ ኋላ ጥንታዊ ጥበባት ቻናሌ ላይ ለቀቅኹት።
📌 በዚህ PDF ላይ ፦
ሙሉ ጸሎቱን፣ የጸሎቱን ጥቅም በአጭሩና ገቢሩን ታገኙታላችሁ፤ እንዲሁም ንባቡንና የጠለቀ ማብራሪያ የምትፈልጉ እዛው ፒዲኤፉ ላይ የምታገኙትን ሊንክ በመጫን ' ወደ ኋላ ጥንታዊ ጥበባት' ከሚለው የYouTube ቻናሌ ላይ የለቀቅኹትን ቪዲዮ ማየት ትችላላችሁ።
👉🏾 አስተያየት ካላችሁ በውስጥ መስመር @HailemichaelDesalegn ላይ ታገኙኛላችሁ።
👉🏾 ቻናል- @EthiopeTowoderos
📌New Video:
Watch " [ሳታዩት እንዳታልፉ] ከርኩሳን መናፍስት የሚጠብቅ ጥንታዊ ጸሎት - ከሥራይ፣ መተትና ዛር ዓይነጥላ የሚጠብቅ ንባቡና ገቢሩ! Wedehuala Ancient Wisdoms " on YouTube
👇👇👇
https://youtu.be/3ZqHkzJscOo
🔔 Watch " ተዓምራዊ ማእድናት በኢትዮጵያ - የ4 የከበሩ ድንጋዮች ጥቅምና መገኛ ስፍራ በኃይለሚካኤል Wedehuala Ancient Wisdoms " On YouTube
👇🏾👇🏾👇🏾
https://youtu.be/4MVMUywrliI