🟢ልዩ ድምፅ ዝግጅት
👉 ሀሰን ናስራላህ ማንነው?
የዛሬ 19/01/2017 ዓ.ም
#Ethiopianews #Ethiopia #EwunetMedia
📩ጥቆማ
ሁሌም እውነት
🔴Man United 0-2 Tottenham
Brennan Johnson 3'
Dejan Kulusevski 47'
@EwunetMediaOfficial
🟢የድምፅ መረጃ
የዛሬ 19/01/2017 ዓ.ም
አበይት መረጃዎች
📩ጥቆማ
ሁሌም እውነት
🛑በኢትዮጵያ ኃይል የበዛበትና በንፁኃን ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንዲቆም አሜሪካ ጠየቀች
በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 79ኛው የተመድ ጉባዔ ጎን ለጎን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የአፍሪካ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ በኢትዮጵያ ኃይል የበዛበት የመንግሥት ምላሽና ንፁኃን ላይ ያነጣጠረ የታጣቂዎች ጥቃት እንዲቆም አሳሰቡ።
ረዳት ሚኒስትሯ ከሁለት ዓመታት በፊት የተካሄደውን የፕሪቶሪያ ስምምነት በተሳካ ሁኔታ እንዲፈጸም፣ ከአፍሪካ ኅብረት ጋር በመሆን ያለ ማቋረጥ ውትወታ እናደርጋለን ብለዋል።
በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ያለውን ግጭት በተመለከተ ያለንን ሥጋት በመግለጽ እንዲቆም በግል በሚደረግ ውይይትና በይፋ በሚኖሩ መግለጫዎች እየጠየቁ መሆኑን አስታውቀዋል።
ታጣቂዎች በንፁኃን ላይና በመንግሥት መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እያደረሱ መሆኑን ገልጸው፣ የመንግሥት ኃይል የበዛበት ምላሽ ግን ተቀባይነት እንደሌለው አስታውቀዋል፡፡
መንግሥታቸው በኢትዮጵያ መንግሥትና በታጠቁ ኃይሎች መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት የንፁኃን ሞት እንዲቆምና በስምምነት እንዲፈታ ጠይቀዋል።
በኒውዮርክ እየተካሄደ ካለው ጉባዔ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ (አምባሳደር)፣ ከአፍሪካ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ሞ ሊፊ ጋር ተገናኝተውን መምከራቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ታየ (አምባሳደር) በኢትዮጵያና አሜሪካ መካከል ጠንካራ ግንኙነት መኖሩን በመግለጽ፣ በቀጣይ የጋራ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ ቀጣይነት ያለው ውይይት አስፈላጊ መሆኑን ስለማንሳታቸው ተገልጿል።
ሚኒስትሩ ሶማሊያን በተመለከተ ከሞሊ ፊ ጋር በነበራቸው ውይይት ኢትዮጵያ ሽብርተኞችን በመዋጋት ረገድ በምታደርገው የተጠናከረ ጥረት ዙሪያ ገለጻ በማድረግ፣ ከድህረ አትሚስ በኋላ የሚኖረው የኃይል ሥምሪት ተግባራዊ ከመደረጉ አስቀድሞ የሥምሪቱ ማዕቀፍ በጥንቃቄ መሠራት እንዳለበት ተናግረዋል።
ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ በሶማሊያና ኢትዮጵያ መካከል ስላለው ውጥረት ከሪፖርተር ለተነሳላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ አሁን ላይ የሶማሊያ ጎረቤት አገሮች ጂቡቲ፣ ኬንያ፣ ኢትዮጵያ፣ ብሩንዲና ዑጋንዳ የሚያደርጉት ሚና ትልቅ ነው ብለዋል። በቀጣይ ሳምንት ከእነዚህ የውጭ አጋሮች ጋር ሶማሊያን በተመለከተ ውይይት እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል ።
ድኅረ አትሚስ ተልዕኮ ላይ ማን መካተት አለበት በሚለው ላይ ውይይት መደረጉንና ከሶማሊያ ወዳጆች ጋር በጋራ በሚደረግ ምክክር አልሸባብን ለመዋጋት ጥሩ ሞዴል መከተል እንዳለብን እናምናለን ብለዋል። አክለውም የሶማሊያ ሉዓላዊነት እንዲከበር እንፈልጋለን ብለዋል።
@EwunetMediaOfficial
🔴ለቸኮለ! ቅዳሜ መስከረም 18/2017 ዓ፣ም ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ታዬ አጽቀሥላሴ፣ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የባሕር በር ስምምነት የተፈራረመችው፣ በሱማሊያ ባለው ነባራዊ ኹኔታ ላይ ተመስርታ ነው በማለት ትናንት በተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ተናግረዋል። ሌሎች እገራትም ከሱማሌላንድ ጋር ተመሳሳይ ስምምነት መፈራረማቸውን የጠቀሱት ታዬ፣ ሱማሊያ በኢትዮጵያ ላይ ጠብ ለመጫር ምክንያት የላትም ብለዋል። ኢትዮጵያ፣ ሱማሊያ ከምታቅርብባት ውንጀላ ጋር የሚያገናኛት ነገር እንደሌለና ይልቁንም ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ለምታደርገው ጥረት ሱማሊያ እንድትተባበር ታዬ ጥሪ አድርገዋል። ታዬ፣ በአካባቢው ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ለሚደረገው ጥረት እንቅፋት የሚኾን እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አንዳንድ የውጭ ኃይሎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።
2፤ ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) በቀጣዮቹ አራት ዓመታት ለኢትዮጵያ ከሚያቀርበው የ3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ብድር 345 ሚሊዮኑን ለመልቀቅ ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ከስምምነት ላይ መድረሱን አስታውቋል። ስምምነቱን የተቋሙ ሃላፊዎች ካዩት በኋላ፣ ተቋሙ ገንዘቡን ወዲያውኑ እንደሚለቅ ገልጧል። አይ ኤም ኤፍ፣ የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ፖሊሲ ተግባራዊ መኾኑን ተከትሎ በአገሪቱ ባንኮች እና በጥቁር ገበያው መካከል የነበረው የምንዛሬ ተመን ልዩነት እጅግ እየጠበበ እንደሚገኝና በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያስከተለው መስተጓጎል አነስተኛ እንደኾነ ጠቅሷል። ድርጅቱ በመግለጫው፣ ልዑካኑ በአዲስ አበባ ከመስከረም 7 እስከ መስከረም 16 ለግምገማ በቆዩበት ወቅት፣ ከፋይናንስ ሚንስትሩ አሕመድ ሽዴ፣ ከሚንስትር ዴዔታው እዮብ ተካልኝና ከብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምኅረቱ ጋር ተወያይተዋል ብሏል።
3፤ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኮርፖሬሽን፣ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚገኙ አምራች ኩባንያዎች በተለያዩ ምክንያቶች ሲወጡ ተረክቦ ሥራቸውን ለመቀጠል ማሰቡን ሪፖርተር ዘግቧል። ኮርፖሬሽኑ ይህን ፖሊሲ ለመከተል የወሰነው፣ በዋናነት የሥራ ዕድሎች እንዳይዘጉና አምራቾች ጨርሶ ሥራ እንዳያቆሙ በማሰብ እንደኾነ መናገሩን ዘገባው አመልክቷል። ኮርፖሬሽኑ ችግር የሚገጥማቸውን ኩባንያዎች ገዝቶ ዕዳቸውን ተረክቦ ለማስተዳደር፣ በሥሩ የተለያዩ ኩባንያዎችን ለማቋቋም ጥናት እያካሄደ እንደኾነ ተገልጧል። ኮርፖሬሽኑ እስካኹን ያለው ሚና፣ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ማቋቋምና ለግል ባለሃብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ቦታዎችን መስጠት ነው።
4፤ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ ከመስከረም 21 ጀምሮ በአፋር ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረኮችን እንደሚያካሂድ አስታውቋል። በእጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረኩ፣ ከ49 ወረዳዎች የተውጣጡ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ወኪሎች፣ መንግሥታዊ ያልኾኑ ተቋማትና የማኅበራት ወኪሎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የክልሉ ተወካዮች እንደሚሳተፉ ተገልጧል። ኮሚሽኑ ባለፉት ሦስት ወራት፣ በአምስት ክልሎች እንዲኹም በአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳድሮች የአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፉን አጠናቋል። ኮሚሽኑ በቀጣዮቹ ሳምንታት፣ በሶማሌ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች የአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፉን ለማከናወን ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ገልጧል።
5፤ አሜሪካ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የተጠለሉ 333 ስደተኞችን ቅዳሜ'ለት መውሰዷን አስታውቃለች። አሜሪካ ስደተኞቹን ለማስፈር የወሰደቻቸው፣ ከስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት እና ከተመድ ስደተኞች ኮሚሽን ጋር በመተባበር ነው። አሜሪካ፣ ባለፈው ዓመት ብቻ ኢትዮጵያ ውስጥ የተጠለሉ 2 ሺሕ ስደተኞችን ተቀብላ ያሠፈረች ሲኾን፣ ተጨማሪ 2 ሺሕ 400 ስደተኞችን ከኢትዮጵያ ለመቀበል ዝግጅት እያደረገች መኾኗን ባለፈው ሰኔ አጋማሽ ገልጣ ነበር። አሜሪካ፣ ትናንት የወሰደቻቸውን ስደተኞች ዜግነት አልገለጠችም። በኢትዮጵያ ከ900 ሺሕ በላይ ኤርትራዊያን፣ ሱዳናዊያን፣ ደቡብ ሱዳናዊያንና ሱማሊያዊያን ስደተኞች ተጠልለው ይገኛሉ።
6፤ የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ ቱርክ ለኢትዮጵያ እና ሱማሊያ የባሕር በር ውዝግብ መፍትሄ የማፈላለግ ጥረቷን እንደምትገፋበት አስታውቋል። የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ይህን ያለው፣ የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሐካን ፊዳን ኒውዮርክ ውስጥ ከኢትዮጵያው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ታዬ አጽቀሥላሴ እና ከሱማሊያው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አሕመድ ፊቂ ጋር ትናንት በተናጥል ከተወያዩ በኋላ ነው። ሚንስቴሩ፣ ቱርክ ለውጥረቱ "ሚዛናዊ"፣ "አዋጭ" እና "ለኹለቱም አገራት ጠቃሚ የኾነ" መፍትሄ ለማስገኘት እየሠራች እንደኾነ ገልጧል።
📩ጥቆማ
ሁሌም እውነት
አርሰናል 2-1 ሌስተር ሲቲ
አርሰናል ከ ሌስተር ሲቲ የቀጥታ ስርጭት
📩ጥቆማ
ሁሌም እውነት
ተረጋገጠ
የሄዝቦላህ መሪ ሃሰን ናስራላህ መሞቱ ተረጋገጠ
የእስራኤል አየር ኃይል በቤሩት በወሰደው ጥቃት የሄዝቦላህ ሃሰን ናስራላህ መገደሉን ቡድኑ አረጋግጧል።
እስራኤል በበኳሏ ናስራላህ እስከወዳኛው ተሸኝቷል ብላለች።
ሃሰን ናስራላህ የተገደለው የእስራኤል ጦር ትናንት ምሽት በቤሩት ከተማ በወሰደችው መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት ነው።
ይህንን ተከትሎ የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት ወደከፋ ደረጃ ከፍ ብሏል።
ኢራንም እስራኤልን አስጠንቅቃለች።
@EwunetMediaOfficial
ሮድሪ ከውድድር አመቱ ውጪ ሆነ !
ስፔናዊው የማንችስተር ሲቲ አማካይ ሮድሪ በቅርቡ ባጋጠመው ከባድ ጉዳት ምክንያት ከውድድር አመቱ ውጪ መሆኑን አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አረጋግጠዋል።
ተጨዋቹ ባለፈው ሳምንት ማንችስተር ሲቲ ከአርሰናል ባደረገው ጨዋታ “ ACL “ ጉዳት እንዳጋጠመው ይታወቃል።
የሮድሪ ጉዳት “ በጣም አስከፊ እና ከባድ ነው በዚህ አመት አንመለከተውም “ሲሉ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በይፋ አሳውቀዋል።
አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አያይዘውም ኬቨን ዴብሮይን ከነገው የኒውካስል ዩናይትድ ጨዋታ ውጪ መሆኑን ገልጸዋል።
#Ethiopianews #Ethiopia #EwunetMedia
ውድ ቤተሰቦቻችን ስለምታደርሱን ጥቆማና አስተያየት እናመሰግናለን የናንተ አስተያየት ለኛ ጥንካሬ ነውና ያልተመቻችሁ ነገር ሲኖር በዚህ አሳውቁን
📩ጥቆማ
ሁሌም እውነት
🟢የድምፅ መረጃ
የዛሬ 17/01/2017 ዓ.ም
ኢሳያስ ያወቁት የግብፅ የ24 ሰዓት ኦፕሬሽን
‹‹የሰራዊቱ ሚስጥር ባክኗል›› ህወሃት
‹‹አስታርቁን››ጌታቸው
የቦረናው አድማ ተነሳ
#Ethiopianews #Ethiopia #EwunetMedia
ውድ ቤተሰቦቻችን ስለምታደርሱን ጥቆማና አስተያየት እናመሰግናለን የናንተ አስተያየት ለኛ ጥንካሬ ነውና ያልተመቻችሁ ነገር ሲኖር በዚህ አሳውቁን
📩ጥቆማ
ሁሌም እውነት
🟢የድምፅ መረጃ 2
የዛሬ 16/01/2017 ዓ.ም
‹‹የዓባይ ነገር አብቅቷል›› የእስራኤል ጄኔራል
የኢትዮ ኤርትራ ድንበር ስጋት፣
የሶማሊያ ለውጥ
‘’ከተደመርን እናበራለን’’ ጠቅላዩ
#Ethiopianews #Ethiopia #EwunetMedia
ውድ ቤተሰቦቻችን ስለምታደርሱን ጥቆማና አስተያየት እናመሰግናለን የናንተ አስተያየት ለኛ ጥንካሬ ነውና ያልተመቻችሁ ነገር ሲኖር በዚህ አሳውቁን
📩ጥቆማ
ሁሌም እውነት
🟢የድምፅ መረጃ
የዛሬ 16/01/2017 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ግዛት የተመታው አውሮፕላን
የኤርትራ ሰው በአዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ጦርና የኤርፖርቱ ውዝግብ
ሶማሊያ እና ቱርክ ሌላ ስምምነት
በባህርዳር የሙሽራዋ መታገት
#Ethiopianews #Ethiopia #EwunetMedia
ውድ ቤተሰቦቻችን ስለምታደርሱን ጥቆማና አስተያየት እናመሰግናለን የናንተ አስተያየት ለኛ ጥንካሬ ነውና ያልተመቻችሁ ነገር ሲኖር በዚህ አሳውቁን
📩ጥቆማ
ሁሌም እውነት
📌ለቸኮለ ማለዳ! ሐሙስ መስከረም 16/2017 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ ኢሰመኮ፣ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች በግጭት ተሳታፊ የኾኑ ኹሉም አካላት ያለምንም ቅድመ ኹኔታ ተኩስ አቁም እንዲያደርጉና ለግጭቱ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲፈልጉ በድጋሚ ጠይቋል።
ኢሰመኮ፣በአማራ ክልል የግጭት ተሳታፊ ወገኖች የሰዎችን የመዘዋወር ነጻነትና በመጓጓዣ ላይ የሚጥሏቸውን ተገቢ ያልኾኑ ገደቦች እንዲያነሱ፣ ተፋላሚ ወገኖች በሚቆጣጠሯቸው አካባቢዎች ሰብዓዊ መብቶችን አክብረው እንዲንቀሳቀሱና በሲቪሎች ላይ ጥቃት ከማድረስ እንዲቆጠቡ አሳስቧል። መንግሥት በአማራና ኦሮሚያ ጥሰቶችን የፈጸሙና ባስፈጸሙ ኃላፊዎችና ታጣቂዎች ላይ ተዓማኒ የወንጀል ምርመራና የክስ ሂደት እንዲጀምርም ኢሰመኮ ጠይቋል። ኢሰመኮ ይህን ያሳሰበው፣ አዲስ ባወጣው የሩብ ዓመት የሰብዓዊ መብቶች ሪፖርት ነው።
በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን፣ ደባርቅ ከተማ የመንግሥት ኃይሎችና የፋኖ ታጣቂዎች መስከረም 6 ባካሄዱት ግጭት ቢያንስ 20 ሲቪሎች በተባራሪና ዒላማቸውን በሳቱ ጥይቶች እንደተገደሉም ኢሰመኮ ገልጧል። የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ሌሎች 9 ሰዎችን ከቤታቸው ወስደው እንደገደሉና 5ቱ ከገጠር ሄደው ሆቴል አልጋ የያዙ መምህራን እንደነበሩ ድርጅቱ አመልክቷል። ዒላማቸውን ባልጠበቁ ተኩሶችና በተባራሪ ጥይቶች 36 ሲቪሎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸው እንደታከሙና ኹለቱ እንደሞቱም ተገልጧል።
2፤ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች የመንግሥት ኃይሎችና ኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ሰሞኑን ተኩስ ልውውጥ እንዳደረጉ ዋዜማ ሰምታለች። ታጣቂዎቹ፣ በመከላከያ ሠራዊት ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት እንዳደረሱም ዋዜማ ከምንጮቿ ተረድታለች። መንግሥት፣ በቡድኑ ላይ ከመስከረም ጀምሮ ወታደራዊ ርምጃዎችን ለመውሰድ መወሰኑን ተከትሎ፣ በዞኑ ውስጥ ስልክ እና ኢንተርኔት ካቋረጠ አንድ ወር አልፎታል። ቡድኑ፣ በንጹሃን ላይ የሚያደርሰው ጥቃት ግን አኹንም ጋብ አላለም። ከአራት የዞኑ ወረዳዎች ወደ አዲስ አበባ የሚደረጉ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎችም ተስተጓጉለዋል።
3፤ የትግራይ ቴሌቪዥን፣ አንዳንድ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎችና አንቂዎች በትግራይ ቲቪ ማኅደር ውስጥ የተከማቹ ከዘር ማጥፋት ወንጀል ጋር የተያያዙ ሰነዶች ኾን ተብሎ እንዲወድሙ እየተደረገ ይገኛል በማለት በተደጋጋሚ አሠራጭተውታል ያለውን መረጃ አስተባብሏል። ጣቢያው፣ መረጃው ሙሉ በሙሉ ያልተደረገ መኾኑን ገልጧል። ጣቢያው አያይዞም፣ በጦርነቱ ወቅት በትግራይ ሕዝብ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚያሳዩ ምስሎችና ሰነዶች እንዲኹም የትግራይ ተዋጊዎችን ተጋድሎ የሚያሳዩ ኹሉም ሰነዶች በክምችት ክፍሉ ውስጥ ተቀምጠው እንደሚገኙ አረጋግጧል።
4፤ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ቱርክ ኤርትራዊያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው በግዳጅ መመለስ እንድታቆም በድጋሚ ጠይቋል። ድርጅቱ፣ ኤርትራዊያን በግዳጅ ወደ አገራቸው ከተመለሱ፣ በአስቸጋሪ እስር ቤቶች እስርና ሥቅየት እንደሚጠብቃቸው ገልጧል። ቱርክ በቅርቡ 300 ያህል ኤርትራዊያን ስደተኞችን በግዳጅ ወደ አገራቸው መልሳለች ተብሏል። በቱርክ ሕግ መሠረት፣ በቀጥታ የጥገኝነት ማመልከቻ ማቅረብ የሚችሉት አውሮፓዊያን ብቻ ሲኾኑ፣ ለሌሎች ስደተኞች የሚሰጣቸው የስደተኝነት መብት በቅድመ ኹኔታ የታሠረ ነው።
5፤ በሱማሊያ የጣሊያን ኢምባሲ፣ ከሞቃዲሾ ለኹሉም የጉዞ ማመልከቻዎች የሸንገን ቪዛ መስጠት ማቆሙን አስታውቋል። ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የሚፈልጉ ባለጉዳዮች፣ ናይሮቢ የሚገኘውን የጣሊያን ኢምባሲ እንዲያነጋግሩ ኢምባሲው አሳስቧል። ኢምባሲው ቪዛ መስጠት ያቆመበትን ምክንያት አልገለጠም። ኾኖም የሱማሊያ ዜና ምንጮች ኢምባሲው ሸንገን ቪዛ መስጠት ያቆመው፣ የሱማሊያ ባለሥልጣናትና ዲፕሎማቶች በተጭበረበሩ ፓስፖርቶች በርካታ ሰዎችን በሕገወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ በማስወጣታቸው እንደኾነ መስማታቸውን ጠቅሰው ዘግበዋል።
@EwunetMediaOfficial
🟢የድምፅ መረጃ 2
የዛሬ 15/01/2017 ዓ.ም
‘’ጦሩን ማንም አያዘውም’’ ደብረጺዮን
በሶማሊያ ተቃዋሚዎች እየታጠቁ ነው፣
ጂቡቲን ያስደነገጠው የኢትዮጵያውያ ውሳኔ
ስለ ጂጂ የተሰማው
==================
ነገ ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪዎች ዝግ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ
ውድ ቤተሰቦቻችን ስለምታደርሱን ጥቆማና አስተያየት እናመሰግናለን የናንተ አስተያየት ለኛ ጥንካሬ ነውና ያልተመቻችሁ ነገር ሲኖር በዚህ አሳውቁን
📩ጥቆማ
ሁሌም እውነት
🟢ለቸኮለ ማለዳ! ረቡዕ መስከረም 15/2017 ዓ፣ም ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ ጸጥታ ኃይሎች ሰሞኑን በአዲስ አበባ ወጣቶችን በጅምላ እያሠሩ መኾኑን ዋዜማ ተረድታለች።
2፤ ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመሩት የሕወሓት ክንፍ፣ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ውስጥ የሚታዩትን ችግሮች ለመፍታት ወደ ተግባር እንደሚገባ ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
3፤ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ፣ በተያዘው ዓመት ዕድሜያቸው ከ4 እስከ 6 ዓመት የኾናቸውን 1 ሚሊዮን 760 ሕጻናትን ለመመዝገብ ታቅዶ፣ 324 ሺሕ ብቻ እንደተመዘገቡ አስታውቋል፡፡
4፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን፣ የግንባታዎች "የሴት ባክ" ሕግ ወይም ሕንጻዎች ከመንገድ የሚኖራቸውን ርቀት የሚወስነው መመሪያ በክፍለ ከተማ አመራሮች ተሳታፊነት ጭምር እየተጣሰ መኾኑን አስታውቋል።
5፤ የቀድሞው የሱዳን ፕሬዝዳንት አል በሽር፣ ለሕክምና ከካርቱም 340 ኪሎ ሜትር ወደምትርቀው ሰሜናዊቷ ሜሮይ ከተማ እንደተዛወሩ ሮይተርስ ዘግቧል።
ውድ ቤተሰቦቻችን ስለምታደርሱን ጥቆማና አስተያየት እናመሰግናለን የናንተ አስተያየት ለኛ ጥንካሬ ነውና ያልተመቻችሁ ነገር ሲኖር በዚህ አሳውቁን
📩ጥቆማ
ሁሌም እውነት
🟢ለቸኮለ! ማክሰኞ መስከረም 14/2017 ዓ፣ም ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ታዬ አጽቀሥላሴ፣ “የውጭ ኃይሎች” ወደ ሱማሊያ የሚልኩት ጦር መሳሪያ በአሸባሪዎች እጅ ሊወድቅ ይችላል በማለት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፖለቲካና የሰላም ግንባታ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሐፊ ሮዝሜሪ ዲካርሎ ጋር ከኒውዮርኩ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ በተጓዳኝ በተነጋገሩበት ወቅት ስጋታቸውን ገልጸዋል።
2፤ የሱማሊያ መንግሥት፣ የውጭ ኃይሎች ለሱማሊያ የሚሰጧት የጦር መሳሪያ ድጋፍ በአሸባሪዎች እጀ ሊገባ ይችላል በማለት ኢትዮጰያ ያንጸባረቀችውን ስጋት አጣጥሎታል።
3፤ ደብረጺዮን ገብረሚካኤል፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጀነራል ጻድቃን ገብረተንሳይን "ሥልጣን ለመጠቅለል" እና "የቆየ ቂማቸውን ለመወጣት" ይፈልጋሉ በማለት ቅዳሜ'ለት መቀሌ ውስጥ በተካሄደ ሕዝናዊ ስብሰባ ላይ ወቅሰዋል።
4፤ በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤት፣ በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እስራኤል በአገሪቱ ላይ በከፈተችው የአየር ጥቃት ዒላማ ሊኾኑ ከሚችሉ አካባቢዎች ራሳቸውን እንዲያርቁ አሳስቧል።
5፤ የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ኢትዮጵያዊያኑ ፍስሃ ተክሌ እና አብርሃም ማዕረግ እንዲኹም "ዘ ካቲባ ኢንስቲትዩት" የተባለ የኬንያ ሲቪክ ተቋም፣ ፌስቡክ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወቅት ማንነት-ተኮር ጥቃትና ግድያ እንዲስፋፋ አስተዋጽዖ አድርጓል በማለት በሜታ ኩባንያ ላይ ያቀረቡትን ክስ የመመልከት ሥልጣን ይኖረው እንደኾነ ውሳኔውን ይሰጣል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።
6፤ ግብጽ ለሱማሊያ የጦር መሳሪያ ድጋፍ መላኳን በይፋ አምናለች። የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ታሚም ካሊፍ፣ ሱማሊያ ጸጥታና መረጋጋት ለማስፈን፣ ሽብርተኝነትን ለመዋጋትና ሉዓላዊነቷን ለማስከበር ለምታደርገው ጥረት፣ ግብጽ የላከችው የጦር መሳሪያ ትናንት ሞቃዲሾ ወደብ መድረሱን አስታውቀዋል።
ውድ ቤተሰቦቻችን ስለምታደርሱን ጥቆማና አስተያየት እናመሰግናለን የናንተ አስተያየት ለኛ ጥንካሬ ነውና ያልተመቻችሁ ነገር ሲኖር በዚህ አሳውቁን
📩ጥቆማ
ሁሌም እውነት
🔴Man United 0-3 Tottenham
Brennan Johnson 3'
Dejan Kulusevski 47'
Dominic Solanke 77'
ማንችስተር ዩናይትድ በሜዳው በቶትንሀም ተሸነፈ
በስድስተኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ከቶትንሀም ጋር ተጫውቷክ።
የሰሜን ለንደኑ ቶትንሀም በኦልድትራፎርድ ያደረገውን ጨዋታ 3 ለ0 ማሸነፍ ችሏል።
የቶትንሀም የማሸነፊያ ጎሎችን ጆንሰን፣ ኩሉሴቪስኪ እና ሶላንኬ አስቆጥረዋል።
የማንችስተር ዩናይትድ አምበል እና የጨዋታ አቀጣጣይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ በ42ኛው ደቂቅ በቀይ ካርድ ተሰናብቷል።
ዩናይትድ ሽንፈት ማስተናገዱን ተከትሎ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ በውጤት ማጣት ጫና ውስጥ ገብተዋል።
ፕሪሚየር ሊጉን ሊቨርፑል በ15 ነጥብ ሲመራ የአምናው የሊጉ አሸናፊ ማንችስተር ሲቲ እና አርሰናል በእኩል 14 ነጥብ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ በሰባት ነጥብ በ12 ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
@EwunetMediaOfficial
🟢ልዩ የድምፅ መረጃ
👉 ሰበር እስራኤል ወደ ኢራን ልትገሰግስ ነው!
የዛሬ 19/01/2017 ዓ.ም
#Ethiopianews #Ethiopia #EwunetMedia
📩ጥቆማ
ሁሌም እውነት
🛑ነባር ተመዝጋቢዎች እያሉ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለልማት ተነሽዎች መሰጠታቸው ቅሬታ አስነሳ
የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የቤት አቅርቦት ችግር እንጂ ተመዝጋቢዎቹ አልተረሱም ይላል
ለ21 ዓመታት ኮንዶሚኒየም ይደርሰናል ብለው ሲቆጥቡ የቆዩ የኮንዶሚኒየም ነባር ተመዝጋቢዎች ዕጣ ሳይወጣላቸው፣ ቤቶቹ ለልማት ተነሽዎች በመሰጠታቸው ቅሬታ አቀረቡ፡፡
ከ1997 ዓ.ም. ጀምሮ የኮንዶሚኒየም ቤቶችን በዕጣ ለማግኘት ሲጠባበቁ የቆዩ በርካታ ተመዝጋቢዎች እያሉ፣ ለልማት ተነሽዎች ቤቶች መሰጠታቸው ኢፍትሐዊ እንደሆነ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
ለልማት ተነሽዎች ለምን ቤት ተሰጣቸው እንደማይሉ የተናገሩት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ ለረዥም ዓመታት ፍትሐዊነት በጎደለው መንገድ ለእነሱ ሳይሰጣቸው መቅረቱ እንዳሳዘናቸው አሳድረዋል፡፡ ለልማት ተብሎ ቤታቸው የፈረሰባው ዜጎች ቤት ሲሰጣቸው የ1997 እና የ2005 ዓ.ም. የኮንዶሚኒየም ቤቶች ተመዝጋቢዎች ጉዳይ በዝምታ መታለፉ ቅሬታ እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል፡፡
የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ እስኪያልቅ ድረስ ለምን በመንግሥት የተሠሩ ቤቶች አይሰጡንም ያሉት ተመዝጋቢዎቹ፣ ለሁለት አሠርት ዓመታት ቤት ለማግኘት በመጠበቃቸው በተለየ ሁኔታ በከተማ አስተዳደሩ ሊስተናገዱ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ የቤት ኪራይና የልጆች ትምህርት ቤት ክፍያዎች ጣራ በመንካታቸው፣ ለችግር ተዳርገናል ያሉት ተመዝጋቢዎች፣ የኢትዮጵያ ዜጋ አይደለንም ወይ ሲሉም ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡
ለዓመታት ምላሽ በተነፈገው ጥያቄያቸው ምክንያት በመንግሥት ላይ ያላቸው እምነት መሟጠጡን ገልጸዋል፡፡
ተመዝጋቢዎቹ ለሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም፣ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትና ሌሎች ተቋማት ቅሬታቸውን ቢያሰሙም እስካሁን መፍትሔ እንዳላገኙ አክለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ አጠቃላይ የቤቶች ግንባታ ከሁለትና ከሦስት ዓመት ተኩል በኋላ የብድር አቅርቦት ችግር ተጨማሪ ግንባታ ማድረግ አላስቻለም፡፡
ችግሩ እስኪፈታ ድረስ ግንባታ እንደማይካሄድ፣ ኮርፖሬሽኑ ያለበትን ውዝፍ ዕዳ እስኪከፈል ድረስም ሲያገኝ የነበረው ብድር መከልከሉን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ካለበት ዕዳ ውስጥ 36 ቢሊዮን ብር ተመላሽ ማድረጉን ገልጸው፣ ቀሪ 37.7 ቢሊዮን ብር ያልተከፈለ ውዝፍ ዕዳ እንዳለበትና ለመክፈልም የተለያዩ አማራጮችን እያጤነ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር የሚሰጠው ለማጠናቀቂያ ሥራ ብቻ እንደሆነ፣ ለሰፊ የቤት ግንባታ ግን ተጨማሪ ብድር እንደማይሰጥ ጠቁመዋል፡፡
ዕጣ ያልወጣላቸው የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች እያሉ ለምን ለሌሎች ይሰጣል ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ለልማት ተነሽዎች ቅድሚያ መስጠትን መመርያው የሚያዝና የሚደግፈው መሆኑን ገልጸው፣ ነገር ግን የኮንዶሚኒየም ዕጣ ጠባቂዎችን ወደ ጎን ከመግፋት ጋር መገናኘት የለበትም ብለዋል፡፡
የቤት አቅርቦት ጉዳይ የ1997 እና የ2005 ዓ.ም. የቤት ተመዝጋቢዎች ችግር ብቻ ሳይሆን፣ በአጠቃላይ በቤት አቅርቦቱ በአማራጭ የቤት ልማት ላይ እየተሠሩ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
ከተለመዱት 40/60 እና 20/80 ቤቶች በተጨማሪ በ70/30 ፕሮግራምና በማኅበር ቤቶች አቅም ያላቸው እንዲገነቡ የሚያስችል አሠራር መዘርጋቱን ተናግረዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ እስካሁን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ሲገነባ የነበረው በቦንድ ግዥ እንደነበረ፣ አሁን ግን የከተማ አስተዳደሩ ካለው በጀት ላይ እየመደበ ብድሩን እየከፈለና ለኪራይ የሚሆኑ ቤቶች እየገነባ ነው ብለዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ መንግሥትና ባለሀብቶች ተቀናጅተው የሚገነቧቸው ቤቶች መኖራቸውንና ለዝቅተኛ የኅብረተሰብ ክፍሎች እየተሰጡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎችን በተመለከተ ቁጠባ ያቋረጡ እንዳሉ ገልጸው፣ ‹‹ነገር ግን አሁንም ኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች የሉም ወይም ጨርሰን ሰጥተናል አላልንም፤›› ብለዋል፡፡
የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች ቅሬታ ትክክል መሆኑን የገለጹት አቶ ሽመልስ፣ ነገር ግን ከተማው ያለበትን የቤት አቅርቦት ችግር ሲፈታ የተመዝጋቢዎቹን ችግርም በዚያው እንደሚፈታ ገልጸዋል፡፡
‹‹የነባሩ የዕጣ አወጣጥ ሒደት ቆሟል ወይም አልቆመም ብለን መናገር አንችልም፤›› ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ምናልባት የባንክ ብድር ከተመለሰ እንደገና በሌላ ብድር ቤቶች ተገንብተው ለዕጣ ጠባቂዎች ለመስጠት ጥረት እንደሚደረግ ጠቁመዋል፡፡
የተመዝጋቢዎች ዕጣ የማውጣት ሒደት ይቀጥላል ወይም አይቀጥልም የሚለው በቤት አቅርቦት ሁኔታው እንደሚወሰን ገልጸዋል፡፡
እንደ አቶ ሽመልስ ገለጻ፣ ከኮሪደር ልማት ተነሺዎች በአንድም በሌላም መንገድ ቢጣራ ተመዝጋቢዎች አሉ፡፡ ለኮሪደር ልማት ተነሽዎች የ40/60 እና የ20/80 ቤቶች ተሰጥተው አልቀው ወደ ኪራይ ቤት እየተገባ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የሕግና የአስተዳደር በደል ምርመራ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ መንግሥቱ ቀና በበኩላቸው፣ በ1997 ዓ.ም. ኮንዶሚኒየም ለማግኘት ተመዝግበው ዕጣ ያልወጣላቸውን በተመለከተ ኮርፖሬሽኑ በደብዳቤ መጠየቁን ገልጸዋል፡፡
ይሁን እንጂ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢቀርብም ምላሽ አለመገኘቱን አቶ መንግሥቱ ገልጸው፣ እንደገና በደብዳቤ ተጠይቆም ምላሽ ካልተገኘ ወደ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለማምራት መታቀዱን ተናግረዋል፡፡
‹‹ኮርፖሬሽኑ ለኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች ዕጣ ያላወጣበት ምክንያት ይህ ነው ብለው ስላልነገረን ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ አልቻልንም፤›› ብለዋል፡፡ ጉዳዩ ገና በሒደት ላይ እንደሚገኝና ለከተማ አስተዳደሩ ደብዳቤዎች እየተጻፉ መሆናቸውንና በሚፈለገው ልክ ምላሽ ካልተገኘ ግን ወደ ፓርላማ እንደሚያመሩ አስረድተዋል፡፡
የተመዝጋቢዎቹ ችግር ከዓመት ዓመት እየተላለፈ ያለ ችግር መሆኑን፣ ዜጎች ምላሽ እንዲያገኙ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሥራ መጀመርን ተቋማቸው እየተጠባበቀ እንደሚገኝ አቶ መንግሥቱ ገልጸዋል፡፡
@EwunetMediaOfficial
🟢የድምፅ መረጃ
የዛሬ 18/01/2017 ዓ.ም
አበይት መረጃዎች
📩ጥቆማ
ሁሌም እውነት
FT አርሰናል 4-2 ሌስተር ሲቲ
አርሰናል ከ ሌስተር ሲቲ የቀጥታ ስርጭት
📩ጥቆማ
ሁሌም እውነት
አርሰናል 1-0 ሌስተር ሲቲ
አርሰናል ከ ሌስተር ሲቲ የቀጥታ ስርጭት
📩ጥቆማ
ሁሌም እውነት
🟢የድምፅ መረጃ
የዛሬ 18/01/2017 ዓ.ም
አበይት መረጃዎች
📩ጥቆማ
ሁሌም እውነት
😢በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ !
አረጋዊው ካህን ከነቤተሰቦቻቻው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ !
መስከረም 17 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሞጆ ሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት መ/መ/ቀ/ወልደ ኢየሱስ አያሌው የተባሉ አረጋዊ ካህን ከነባለቤታቸው 4 ቤተሰቦቻቸው ጋር በአንድ ቀን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገለዋል።
መ/መ/ቀ/ወ/ኢየሱስ አያሌው በላስታ ላሊበላ ልዩ ቦታው ጥል አስፈሬ ቅዱስ ገብርኤል አካባቢ የተወለዱ ሲሆን ከ1976 ዓ.ም ጀምሮ በሞጆ ሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት በቢቃ ደ/መ/ቅ/ሚካኤል ቤተ ስርስቲያን ለ 41 ዓመታት ያህል ከዲቁና እስከ እልቅና ድረስ በትሕትና ሲያገለግሉ የነበሩ ቢሆንም በቀን 16/01/2017 ዓ.ም በሽምግልና ዘመናቸው ውድ ባለቤታቸውን ጨምሮ ከሦስት ልጆቻቸው ጋር እጅግ ልብ ሰባሪ እና ዘግናኝ በሆነ አሰቃቂ ሁኔታ የተገድሉ ሲሆን ለረጅም ጊዜ ባገለገሉበት በቢቃ ደ/መ/ቅ/ሚካኤል ቤተ ክስርስቲያን ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል።
ከልጆቻቸውም አንዱ ዲያቆን መልአክ ወልደ ኢየሱስ የአባቱን ፈለግ ተከትሎ የቤተ መቅደሱ አገልጋይ ነበር።
በዛሬው ዕለት መስከረም 17 ቀን 2017 ዓም ክቡር መ/ሰ/ቆ/አባ ሰይፈ ገብርኤል ገረመው የወረዳው ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ የአድባራትና የገዳማት አስተዳዳሪዎች በተገኙበት በሞጆ ደ/ብ/ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የጸሎተ ፍትሐት እየተከናወነ ይገኛል።
ከሞጆ ሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የደረሰው መረጃ ዋቢ አድርጎ የዘገበው የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት ነው።
#Ethiopianews #Ethiopia #EwunetMedia
ውድ ቤተሰቦቻችን ስለምታደርሱን ጥቆማና አስተያየት እናመሰግናለን የናንተ አስተያየት ለኛ ጥንካሬ ነውና ያልተመቻችሁ ነገር ሲኖር በዚህ አሳውቁን
📩ጥቆማ
ሁሌም እውነት
🙈በንጽህና ጉድለት ምክንያት የፈረሰው ትዳር
😐ባልየው ገላዬን በወር አንዴ ብቻ ነው የምታጠበው ማለቱን ተከትሎ የጥንዶቹ ትዳር ፈርሷል
ልብሶቹን ሳይቀር አቆሽሾ መልበስ የሚፈልገው ይህ ባልም የሚስቱን ፍላጎት እና ስሜት ማክበር ባለመቻሉ ትዳሩ ፈርሷል፡፡
በሕንድ ከዕምነት ጋር በተያያዘ ሰውነትን እና ልብሶችን ቶሎ ቶሎ አለመታጠብ የሚዘወተር ሲሆን ይህ ባልም ገላውን የማይታጠበው ከዚሁ ጋር በተገናኘ እንደሆነ ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
የባልየው ቤተሰቦች ወደ ሚስት ቤተሰቦች በመሄድ ጥንዶቹን ሊግባቡ እና ሊያስታርቋቸው ቢሞክሩም ቢሞክሩም ባለትዳሮቹ ወደ ቀድሞ ትዳራቸው ሊመለሱ እንዳልቻሉም ተገልጿል፡፡
ከዚህ በፊት በታይዋን የሚኖሩ ባልና ሚስት ከዚሁ ከንጽህና ጋር በተያያዘ ለፍቺ የተዳረጉ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ሚስትየው ሻወር የምትወስደው በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ በመሆኑ ነበር፡፡
ይህች እንስት የጥርሷን እና ጸጉሯን ንጽህና በሳምንት አንድ ጊዜ ብቻ እንደምትጠብቅ የተገለጸ ሲሆን የባህሪ ለውጡ ከሰርጋቸው በኋላ መሆኑን ባልየው በወቅቱ ለፍርድ ቤት ተናግሯል፡፡
#Ethiopianews #Ethiopia #EwunetMedia
ውድ ቤተሰቦቻችን ስለምታደርሱን ጥቆማና አስተያየት እናመሰግናለን የናንተ አስተያየት ለኛ ጥንካሬ ነውና ያልተመቻችሁ ነገር ሲኖር በዚህ አሳውቁን
📩ጥቆማ
ሁሌም እውነት
📸የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር በምስል
ውድ ቤተሰቦቻችን ስለምታደርሱን ጥቆማና አስተያየት እናመሰግናለን የናንተ አስተያየት ለኛ ጥንካሬ ነውና ያልተመቻችሁ ነገር ሲኖር በዚህ አሳውቁን
📩ጥቆማ
ሁሌም እውነት
😢28 ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ
ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ተነስቶ ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን ሲጓዝ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ አደጋ የሁለት ሕጻናትን ጨምሮ 28 ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ።
የመኪናውን አሽከርካሪ ጨምሮ 19 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ መሆናቸውን የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።
ትናንት ረቡዕ መስከረም 16/2016 ዓ.ም. ከሶዶ ከተማ የተነሳው “ኤፍ.ኤስ.አር” የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ “በአብዛኛው ለበዓል” ሲጓዙ የነበሩ ከ50 በላይ ሰዎችን ጭኖ እንደነበር የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ፍሰት ቁጥጥር እና አደጋ መከላከል ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ወልዴ ቢሊሶ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ተሽከርካሪው ከቀኑ ሰባት ሰዓት ገደማ አደጋው የደረሰበት በወላይታ ዞን በሚገኘው ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ሲደርስ መሆኑን እንደሆነም ገልጸዋል።
አደጋው የደረሰበት “ግርባ ወንዝ” ተብሎ የሚጠራው አካባቢ የሚገኘው መንገድ “ዳገታማ እና በጣም አስቸጋሪ” መሆኑን የሚያስረዱት ኢንስፔክተር ወልዴ፤ ተሽከርካሪው ዳገቱን በመውጣት ላይ እንዳለ “እንደተንሸራተተ” አብራርተዋል።
“አሁን ያለው መረጃ ተሽከርካሪው ተንሸራርቷል (ስትራፕ) [የሚል] ነው።
ተሽከርካሪው ተንሸራትቶ በጣም ረጅም ርቀት ያለውን ቁልቁለት ተገለባብጦ ወንዝ ውስጥ በመግባቱ ነው አደጋው የተከሰተው” ሲሉ ሁኔታውን ገልጸዋል።
እስካሁን ባለው መረጃ መሠረትም በዚህ አደጋ 28 ሰዎች ሕይወታቸው እንዳለፈ እና 19 ሰዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ ኃላፊው ተናግረዋል።
ሕይወታቸው ካለፈ ሰዎች መካከል ዕድሜያቸው ከስድስት እስከ ስምንት ዓመት የተገመቱ ሁለት ሕጻናት እንደሚገኙበት ኢንስፔክተር ወልዴ አስታውቀዋል።
“ተሽከርካሪው ውስጥ ልጅ እና እናት ነበሩ። ሕጻን ልጅ ሲሞት እናትየው ተርፋ ህክምና ላይ ነች” ሲሉ ሕይወቱ ስላለፈው አንድ ሕጻን ልጅ ጠቅሰዋል።
ሌላኛው ሕጻን ልጅ ደግሞ ሲጓዝ የነበረው ከአክስቱ ጋር እንደነበር አክለዋል።
እንደ ኢንስፔክተር ወልዴ ገለጻ በተሽከርካሪው ውስጥ ተሳፍረው የነበሩት ሰዎች በአብዛኛው የዳውሮ ዞን ነዋሪዎች ሲሆኑ ሕይወታቸው ካለፈው ሰዎች መካከል የአንድ ሰው አስከሬን ወደ ሐዋሳ ተልኳል።
በአደጋው ምክንያት ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎችን ማንነት የመለየት ሥራ ረቡዕ እስከ ሌሊቱ ስምንት ሰዓት ድረስ ሲከናወን እንደነበር የዳውሮ ዞን የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ ሲሳይ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች አስከሬን ዛሬ [ሐሙስ] ጠዋት ወደየቤተሰቦቻቸው እንደተሸኘም አቶ ከበደ ገልጸዋል።
ከአደጋው ከተረፉት 19 ሰዎች መካከል አስራ አራቱ የደረሰባቸው ጉዳት ከባድ እንደሆነ የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ፍሰት ቁጥጥር እና አደጋ መከላከል ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ወልዴ ገልጸዋል።
አምስት ሰዎች ደግሞ ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው የገለጹት ኃላፊው፤ በህክምና ላይ ከሚገኙት ግለሰቦች መካከል የመኪናው አሽከርካሪ እንደሚገኝበት ጠቅሰዋል።
አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች በወላይታ ዞን በሚገኙት ሶዶ ክርስቲያን እና በሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች እንዲሁም በዳውሮ ዞን ታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል እየታከሙ እንደሆነ የዳውሮ ዞን የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ ተናግረዋል።
ሕይወታቸው ካለፈ እና አደጋ ከደረሰባቸው ሰዎች በተጨማሪ “ምንም ጉዳት” ሳይደርስባቸው ከአደጋው የተረፉ “ስድስት” ተሳፋሪዎች መኖራቸውን ኢንስፔክተር ወልዴ ገልጸዋል።
“ስድስት ሰዎችን በአካል አግኝተን አነጋግረናል። እኔ ጋር ባለው መረጃ በአካል ያነጋገርናቸው ስድስት የሚሆኑ ሰዎች በሰላም፣ ምንም ሳይሆኑ ከዚያ ውስጥ ወጥተዋል” ብለዋል።
በወላይታ ዞን የደረሰው ይህ አደጋ፤ በዚህ ሳምንት ወንዝ ውስጥ በገባ ተሽከርካሪ የተነሳ የሰዎች ሕይወት ያለፈበት ብቸኛው ክስተት አይደለም።
ማክሰኞ መስከረም 14/2017 ዓ.ም. ምሽት በጋምቤላ ክልል ጉዞ ላይ የነበረ “አምቡላንስ” ተሽከርካሪ ወንዝ ውስጥ በመግባቱ ሰባት ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ ሌሎች ሰባት ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው የክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ከጋምቤላ ከተማ ወደ ኑዌር ዞን ሲጓዝ የነበረው ተሽከርካሪ በጂካዎ ወረዳ አደጋው ደረሰበት “የባሮ ወንዝ ጊዜያዊ ድልድይን ጥሶ በወንዝ ውስጥ በመግባቱ” እንደሆነ የጽህፈት ቤቱ መረጃ ጠቅሷል።
በአደጋው “ወዲያኑ” ሕይወታቸው ካለፈ ሰዎች መካከል የጤና ባለሙያዎች እንደሚገኙበት ተገልጿል።
@EwunetMediaOfficial
✈️ ውድ ቤተሰቦቻችን
የናንተው የመረጃ ምንጭ የሆነውን ይህን የቴሌግራም ቻናል ለማሳደግ የእርስዎን እገዛ እንፈልጋለን።
ቻናሉን ከታች ባለው ሊንክ በመግባት እና ቡስት በማድረግ አሁኑኑ ያጋሩት።
"ሁሌም እውነት"
/channel/EwunetMediaOfficial?boost
🟢የድምፅ መረጃ 2
የዛሬ 15/01/2017 ዓ.ም
የሚጠበውቀው የፋኖዎች መግለጫ
ሶማሊያ ስለጦር ድጋፉ
ኢጋድ ግብፅን ተቃወመ
የአዲስ አበባው አፈሳ
#Ethiopianews #Ethiopia #EwunetMedia
ውድ ቤተሰቦቻችን ስለምታደርሱን ጥቆማና አስተያየት እናመሰግናለን የናንተ አስተያየት ለኛ ጥንካሬ ነውና ያልተመቻችሁ ነገር ሲኖር በዚህ አሳውቁን
📩ጥቆማ
ሁሌም እውነት
🟢የድምፅ መረጃ 2
የዛሬ 14/01/2017 ዓ.ም
ከ4 ኪሎ ለአልሲሲ የተላከው ማስጠንቀቂያ
ግብጽ ማብራሪያ ሰጠች
‹‹ደብረጺዮን ጥሩ ዋሽቷል›› ጻድቃን
እስራኤል በሊባኖስ ዘግናኝ ጥቃት
#Ethiopianews #Ethiopia #EwunetMedia
ውድ ቤተሰቦቻችን ስለምታደርሱን ጥቆማና አስተያየት እናመሰግናለን የናንተ አስተያየት ለኛ ጥንካሬ ነውና ያልተመቻችሁ ነገር ሲኖር በዚህ አሳውቁን
📩ጥቆማ
ሁሌም እውነት
🟢የድምፅ መረጃ
የዛሬ 14/01/2017 ዓ.ም
የግብፅ ኤርትራና ሶማሊያ አደገኛ ምክክር
አሜሪካ ሶማሌላንድ ገባች
ሶማሌላንድ ተቆጣች
‹‹ከሀገር ውጣ ብለውኛል›› ደብረጺዮን
ውድ ቤተሰቦቻችን ስለምታደርሱን ጥቆማና አስተያየት እናመሰግናለን የናንተ አስተያየት ለኛ ጥንካሬ ነውና ያልተመቻችሁ ነገር ሲኖር በዚህ አሳውቁን
📩ጥቆማ
ሁሌም እውነት