ethiofm107dot8 | Unsorted

Telegram-канал ethiofm107dot8 - Ethio Fm 107.8

20436

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Subscribe to a channel

Ethio Fm 107.8

የነገ የጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

መንግሥት የሎጂስቲክስ ዘርፉን ሙሉ በሙሉ ለውጭ ባለሀብቶች መክፈቱ የሃገር ውስጥ ባለሀብቶችን ከጫወታው ውጭ የሚያደርግ ነው ተብሏል።

የባቡር መሃንዲስና የሎጅስቲክ ባለሙያ የሆኑት ኢንጂነር መኮንን ጌታቸው ፤ውሳኔው የውጭ ባንኮችን ወደሃገር ውስጥ እንደ ማቀላቀል በሎጅስትክ ዘርፍ ቀላል አይደለም ነው ያሉት።

የሎጂስቲክ ዘርፉ ለሃገር ኢኮኖሚ እና ለዜጎች ህይወት መቀጠል ዋስትና በመሆኑ ምንም እንኳን የውጭ ድርጅቶች በመቀላቀላቸው በጎ ለውጦች የሚመጡ ቢሆንም የሃገር ውስጥ ለሃብቶች ሳይጠናከሩ ገበያውን ክፍት ማድረግ ትክክል አደለም ብለውናል።

መንግሥት ለውጭ ባለሀብቶች ዕድል ከመስጠቱ በፊት አገር በቀል የሆኑ ባለሀብቶች ራሳቸውን አጠንክረው እስከሚጓዙ ድረስ ዕገዛና የመሰረተ ልማት ስራዎችን እያከናወነ ቀስ በቀስ ክፍት ማድረግ አለበት ሲሉ ጠቁመዋል።

የአገር ውስጥ ባለሀብቶች የጎደላቸውን ነገር እንዲያሟሉ ዕድልና የጊዜ ገደብ ሊሰጣቸው እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ምክንያት በቀይ ባህርና በቀጠናው ዙሪያ ያሉ የታጠቁ ሃይላት ጥቃት ቢያደርሱ ፣እንቅስቃሴ ቢገድቡ የውጭ ተቋማት ሊሸሹ ይችላሉ ።

ይህ በመሆኑ የኢትዮጵያ ባህርና ትራንስፖርት ሎጅስቲክ የሚሰጡት መርከቦቻችን ለእኛ ኢንሹራንሶቻችን ናቸው ነው ያሉት።

መንግሥት በሎጂስቲክስ ዘርፉ 49 በመቶ የውጭ ባለሀብቶች እንዲገቡ ሕግ ያወጣ ቢሆንም፣ በቅርቡ ከተደረገው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ወዲህ ግን ዘርፉ ሙሉ ለሙሉ ለውጭ ባለሀብቶች መክፈቱ ይታወሳል።

ልዑል ወልዴ

ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የላይኛው የአየር ቧንቧ ካንሰር (laryngeal cancer)

የላይኛው የአየር ቧንቧ የካንሰር አይነት በብዛት እድሜያቸው ከ55 አመት በላይ የሆኑ ሰዎችን እንደሚያጠቃ ይነገራል፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ በላይኛው የአየር ቧንቧ ካንሰር በአመት 184,615 ሰዎች እንደሚያዙ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ከነዚህም ውስጥ 99,840 የሚሆኑት ለሞት እንደሚዳረጉ ያሳያል ፡፡

በአጠቃላይ በህይወት ዘመናቸው በዚህ የካንሰር አይነት የመያዝ እድላቸው ለወንዶች ከ200 ሰው 1 ሰው ሲሆን ለሴቶች ደግሞ ከ840 ሰው 1 ሰው መሆኑ ይገለፃል ፡፡

በጉዳዩ ላይ ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የአንገት በላይ ህክምና ስፔሻሊስት እና የመስማት ችግሮች ህክምና ልዩ ስፔሻሊስት የሆኑትን ዶ/ር ሚካኤል ከበደ ናቸው ፡፡

የአየር ቧንቧ ካንሰር ምንድን ነው?

ይህ የካንሰር አይነት ከላይ እሰከ ታች ያለውን የአየር ቧንቧችንን ሊያጠቃ እንደሚችል ይናገራሉ፡፡
የላይኛው የአየር ቧንቧ ደግሞ ድምፅ ማውጣት እና አየር ቧንቧን መጠበቅ ዋናው የዚህ አካል ስራ ነው ይላሉ ፡፡

የላይኛው የአየር ቧንቧ ካንሰር መንስኤው ምንድን ነው?

- ትንባሆ ማጨስ
- አልኮል መጠጥ መጠጣት
- የእድሜ መግፋት
- በቤተሰብ ውስጥ የዚህ ካንሰር አይነት ከነበረ የመከሰት እድሉን ሊጨምር እንደሚችል አንስተዋል፡፡

ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?

- የድምፅ መቀየር
- ጉሮሮ ውስጥ የሆነ ነገር እንደተቀረቀረ አይነት ስሜት መሰማት
- አንገት ላይ እብጠት
- ምግብ ለመዋጥ መቸገር
- የምግብ ፍላጎት መቀነስ
- ክብደት መቀነስ
- ትንታ
- የጆሮ ህመም

ምርመራዎቹ ምንድን ናቸው?

- ሙሉ ምርመራ
- የ “ላሪንጎስኮፒ” ምርመራ
- ባዮፕሲ
- የራጅ ምርመራ

ህክምናዎቹ ምንድን ናቸው?

- በቀዶ ጥገና ማውጣት
- የጨረር ህክምና
- ኬሞቴራፒ ተጠቃሽ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡

በመጨረሻም ትምባሆ መጠቀም እና ከመጠን በላይ አልኮል መጠጣት ለላይኛው የአየር ቧንቧ ካንሰር የሚያጋልጡ ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች በመሆናቸው በተቻለ መጠን እነዚህን ነገሮች መጠቀም ማቆም እና መቀነስ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም በዚህ የካንሰር አይነት የተጠቃ አንድ ሰው ሊያሳይ ከሚችለው ምልክት መካከል አንዱ እና ዋነኛው የድምጽ መቀየር በመሆኑ ድምፃችን በተለያዩ ምክንያቶች ተቀይሮ 2 ሳምንት ካለፈው ወደ ህክምና ተቋም መሄድ እንደሚስፈልግ ዶ/ር ሚካኤል ገልፀዋል፡፡

ሐመረ ፍሬው

ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ለጤና መድህን ተጠቃሚዎች ከተማ አስተዳደሩ ከ1ቢሊዮን ብር በላይ ድጎማ እያደረገ ነው ተባለ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ለጤና መድህን ተጠቃሚዎች ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ድጎማ እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል።

በከተማ አስተዳደሩ በየአመቱ የጤና መድን ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ እንደሚገኝ ያስታወቀው ጤና ቢሮው በዚህ አመት ብቻ 2.5 ሚሊዮን ዜጎች ተጠቃሚ ለማድረግ ምዝገባ መጀመሩን አስታውቋል።

የጤና ቢሮው ሀላፊ ዶ/ር ዮሀንስ ጫላ እንደተናገሩት በጤና መድህን ስርአት ተመዝግበው አገልግሎት እየተሰጣቸው ለሚገኙ ዜጎች ለመድሀኒት ብቻ ጤና ቢሮው ለከነማ ፋርማሲ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ እየከፈለ ይገኛል ብለዋል።

ከዚህ በፊት የተመዘገቡና አዲስ ለሚመዘገቡ ዜጎች ለሚቀጥሉት ሁለት ወራት እድሳት እንዲያደርጉ እና እንዲመዘገቡ ጤና ቢሮው ገልጿል።

የጤና መድህን ስርአት የሚጠቀሙ ዜጎች የአገልግሎት እና የክፍያ ገደብ አልተቀመጠም ያሉት ሀላፊው ዜጎች እድሉን እንዲጠቀሙበት አሳስበዋል።

ሄኖክ ወ/ገብርኤል

ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የአለም የእጅ መታጠብ ቀን እየተከበረ ይገኛል።

አለም አቀፍ የእጅ መታጠብ ቀን በአለም ለ 16ኛ በሀገራችን ለ11ኛ ጊዜ "ህይወቴን ለመጠበቅ እጄን በሳሙና እና በውሃ እታጠባለሁ"በሚል መሪ መልክት በሀገራችን እየተከበረ ነው።

የዩኒሊቨር ኢትዮጵያ ማኔጅንግ ዳይሬክተር ጆርጅ አውሱ እንሳ፤ የዘንድሮ የአለም እጅ የመታጠብ ቀን "ህይወቴን ለመጠበቅ እጄን በሳሙና እና በውሃ እታጠባለሁ" በሚል መሪ ቃል ይከበራል ብለዋል።

ዳይሬክተሩ፤ 80 በመቶ የሚሆኑት ጀርሞች ከሰው ወደ ሰው እንዲተላለፉና የበርካታ ኢንፌክሽን ምክንያቶችም የእጅ ንጽህና ጉድለት መሆኑን ተናግረዋል።

በባህሪ ለውጥ ላይ የሚያተኩረውና በላይፍቦይ ሳሙና አነሣሽነትና መሪነት የሚሰጠው የንጽሕና አጠባበቅ ትምሀርት፣ እስክ ጥቅምት ወር መጨረሻ ድረስ የሚቀጥል ሲሆን በመላው ኢትዮጵያ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ጋር ለመድረስ ጥረት ይደረጋል ተብሏል ።

ልዑል ወልዴ

ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዉ በአነስተኛ ብድር እና ቁጠባ ተቋማት ላይ ጫና ፈጥሯል ተባለ።

በዝቅተኛ እና መካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ዜጎች የፋይናንስ ምንጭ የሆኑት ተቋማቱ የቁጠባ አገልግሎት ላይ ችግሮች መታየታቸው ተገልጿል።

ኢትዩ ኤፍም ያነጋገራቸው የልዩ ማይክሮ ፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን የኦኘሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘላለም መንገሻ እና የጣና ማይክሮ ፋይናንስ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ እንዳለ ማርቆስ የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከም ተከትሎ ማህበረሰብ ገንዘብን

በቁጠባ ከማስቀመጥ ይልቅ ቋሚ ንብረት ላይ እያዋለዉ መሆኑን አንስተዋል።
ይህ ሁኔታም ተቋማቱ ለደንበኞቻቸዉ ብድር የሚሰጡበትን እድል አጥቦታል ሲሉ ገልፀዋል።

ተቋማቱ በራሳቸው ካለባቸዉ የብድር አቅርቦት እጥረት አንፃር ደግሞ ጫናዉ ከፍ እንደሚልም አንስተዋል።

በተጨማሪም የፀጥታ ችግሮች ባሉባቸው አካባቢዎች ተጠቃሚዎች ገንዘብ ሙሉ ለሙሉ የማዉጣት አዝማሚያዎች መኖራቸዉን ገልፀዋል።

የልዩ ማይክሮ ፋይናንስ የኦኘሬሽን ሀላፊ አቶ ዘላለም ከፀጥታ ችግሮች ጋር ተያይዞ በቅርንጫፍ ቢሮዎች ላይ ስጋቶች በመኖራቸው ለመዝጋት መገደዳቸውን ለጣቢያችን ተናግረዋል።

አቶ እንዳለ በበኩላቸው በገጠር የግብርና ዘርፍ ለሚኖሩ አገልግሎቶች የሰላሙ ሁኔታ በታሰበዉ ልክ ለመስራት ፈታኝ ሆኗል ብለዋል።

ቁምነገር አየለ

ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሳፋሪኮም 'ኤምፔሳ ግሎባል' በተሰኘው በዓለም አቀፍ የክፍያ ስርዓቱ ኢትዮጵያን ማካተቱ ተገለጸ።

የኬንያው የስልክ ኔትዎርክ ኦፕሬተር የሆነው ሳፋሪኮም በ 'ኤም-ፔሳ ግሎባል' በተሰኘው አገልግሎቱ ኢትዮጵያን ማካተቱ ተገልጿል።

ይህም ደንበኞች ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ ልውውጥ እንዲያደርጉ የሚያስችላቸው ነው ተብሏል። 

በኬንያ ያሉ ደንበኞች አሁን በኤም-ፔሳ ኢንተርናሽናል ሪሚታንስ በኩል ወደ M-Pesa ኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ ማስተላለፍ ይችላሉ ተብሏል።  

በዚህ ትብብር፣ ሁለቱም ሀገራት ያሉ ደንበኞች የ M-Pesa ዋሌት ብቻ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን ይህም በኬንያ የሚኖሩ እና የሚሰሩ ኢትዮጵያውያንን እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚኖሩና የሚሰሩ ኬንያውያን ይጠቅማል ተብሏል።

የM-Pesa ኬንያ ደንበኞች ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ190 በላይ አገሮች በኤም-ፔሳ ግሎባል አገልግሎት አማካኝነት ገንዘብ መላክ እና መቀበል ይችላሉ ተብሏል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ በሚገዙበት እና በሚሸጡበት ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት ከሁለት በመቶ መብለጥ እንደሌለበት አሳሰበ።

ብሔራዊ ባንኩ ይህንን በተመለከተ ለንግድ ባንኮች በደብዳቤ ማሳወቁን ገልጿል።

አዲሱ የምንዛሬ ተመን አሰራር ይፋ መሆኑን ተከትሎ በውጭ ምንዛሬ ገበያው ላይ ያሉ ሂደቶችን ሲከታተል መቆየቱን የገለጸው ብሔራዊ ባንኩ፤ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ መካከል ያለው ልዩነት በዓለም አቀፍ አሰራር መሰረት መሆን እንዳለበት አመልክቷል።

በመሆኑም የውጭ ምንዛሬ መግዣና መሸጫ መካከል ያለው ልዩነት ከሁለት በመቶ በላይ መሆን እንደሌለበት አስታውቋል።

አሁንም ቢሆንም ባንኮች የምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ ዋጋቸውን በራሳቸውና ከደንበኞቻቸው ጋር ባላቸው ስምምነት ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ጠቁሟል።

ንግድ ባንኮች የምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ ዋጋቸውን በተናጠል በየቀኑ ማሳወቃቸውን መቀጠል እንዳለባቸው ጠቅሶ፤ ባንኮች ከውጭ ምንዛሬ ሽያጭ ጋር በተያያዘ የሚጠይቋቸውን ኮሚሽኖች ከምንዛሬ መሸጫ ጋር ሳይሆን በተናጠል ለደንበኞቻቸው እንዲያሳውቁሞ አዝዟል።

እስካሁን በነበረው አሰራርም ንግድ ባንኮች የምንዛሬ መሸጫ ዋጋቸውን ከኮሚሽኑ ጋር ደምረው ያስታውቁ እንደነበር አስታውሶ፤ ንግድ ባንኮች ሁለቱን ጉዳዮች እስከነገ ባለው ባለው ጊዜ ተግባራዊ ሊያደርጉት ይገባል ብሏል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የምግብ እና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ግምታዊ ዋጋቸው1ሚሊዮን 5 መቶ 40 ሺ ብር የሚሆ ህገወጥ የምግብ ምርቶችን መያዙን አስታወቀ።

በያዝነው ሩብ አመት ምግብን ከባአድ ነገር ጋር በመቀላቀል ፣ የመጠቀሚያ ጊዚያቸው ያለፈባቸው እና ከደረጃ በታች የሆኑ 1ሚሊዮን 5 መቶ 40 ሺ ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው  የተለያዩ የምግብ አይነቶች ለህብረተሰቡ ሳይሰራጩ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን አስታውቋል።

የባለስልጣኑ የጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ  አቶ በቃሉ አረጋ
ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት  የቁጥጥር ስራው ከኦሮሚያ ክልል በጅማ እና በአጋሮ ከደቡብ ምዕራብ ደግሞ በሚዛን አማን እና በቦንጋ ከተሞች ተከናውኗል።

ከተሰበሰቡት ምርቶች መካከል ጁሶች፣ ከረሜላ ፣ጨው፣ ፕላምኘሌት፣ቅቤ እና ማር ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል።

የቁጥጥር ስራውን በተሻለ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ የባለሙያ እጥረቶች መኖራቸውንም ሰምተናል።

የሚደረጉ የቁጥጥር ስራዎች ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ብቻ ተሰቶ የሚሰሩ ስላልሆነ ማህበረሰቡም 8482 ነፃ የስልክ መስመር ላይ ጥቆማዎችን በመስጠት መተባበር እንዳለበት ተጠይቋል።

ሐመረ ፍሬውየምግብ እና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ግምታዊ ዋጋቸው1ሚሊዮን 5 መቶ 40 ሺ ብር የሚሆ ህገወጥ የምግብ ምርቶችን መያዙን አስታወቀ።

በያዝነው ሩብ አመት ምግብን ከባአድ ነገር ጋር በመቀላቀል ፣ የመጠቀሚያ ጊዚያቸው ያለፈባቸው እና ከደረጃ በታች የሆኑ 1ሚሊዮን 5 መቶ 40 ሺ ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው  የተለያዩ የምግብ አይነቶች ለህብረተሰቡ ሳይሰራጩ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን አስታውቋል።

የባለስልጣኑ የጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ  አቶ በቃሉ አረጋ
ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት  የቁጥጥር ስራው ከኦሮሚያ ክልል በጅማ እና በአጋሮ ከደቡብ ምዕራብ ደግሞ በሚዛን አማን እና በቦንጋ ከተሞች ተከናውኗል።

ከተሰበሰቡት ምርቶች መካከል ጁሶች፣ ከረሜላ ፣ጨው፣ ፕላምኘሌት፣ቅቤ እና ማር ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል።

የቁጥጥር ስራውን በተሻለ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ የባለሙያ እጥረቶች መኖራቸውንም ሰምተናል።

የሚደረጉ የቁጥጥር ስራዎች ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ብቻ ተሰቶ የሚሰሩ ስላልሆነ ማህበረሰቡም 8482 ነፃ የስልክ መስመር ላይ ጥቆማዎችን በመስጠት መተባበር እንዳለበት ተጠይቋል።

ሐመረ ፍሬው

ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የሰንደቅ ዓላማ ቀን ዛሬ እየተከበረ ነው፡፡

17ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ዛሬ በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ ነው ፡፡የሰንደቅ ዓላማ ቀን የጥቅምት ወር በገባ በመጀመሪያው ሰኞ እንደሚከበር ይታወቃል፡፡

በዚህም መሠረት የዘንድሮው የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሐሳብ በዛሬው ዕለት እየተከበረ ይገኛል፡፡

ቀኑ በፌደራል የመንግሥት ተቋማት፣ በክልሎችና በሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች፣ በመከላከያ ሠራዊት ካምፖች እንዲሁም በኢትዮጵያ ኢምባሲዎችና ሚሲዮኖች ይከበራል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ኦክሎክ ሞተርስ ከቻይናው Global-Ucar Technology ጋር በጋራ አብሮ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ኦክሎክ ሞተርስ ከቻይናው Global-Ucar Technology Co. Ltd ጋር በ250 ሚሊዬን ዶላር ኢንቨስትመንት በጋራ ለመስራት በዛሬው እለት ተፈራርመዋል፡፡

በ1997 ዓ/ም ምስረታውን ያደረገዉ አክሎክ ሞተርስ ከ Global-ucar Technology Co.Ltd ጋር በሚቀጥሉት አምስት አመት ዉስጥ 20 ሺህ ተሽከርካሪዎችን ለደንበኞች ለማቅረብ ስምምነት ፈፅመዋል፡፡

በተጨማሪም አክሎክ ሞተርስ 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ እንደሆነም ገልፆል፡፡
ድርጅቱ ውሊንግ፣በውጅንና የጂቶር ምርት የሆኑ የተለያዩ ሞዴል ተሽከርካሪዎችን ሀገር ውስጥ በመገጣጠም ላይ እንደሚገኝም አስታውቋል፡፡

ኦክሎክ ሞተርስ ከአሥራ ስድስት በላይ የተለያዩ ሞዴል ተገጣጣሚ ተሸከርካሪዎችን ከውጭ በማስመጣት ሀገር ውስጥ ባስገነባቸው የተሸከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካዎቹ በመገጣጠም ለደንበኞቹ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝም በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ ተመላክቷል፡፡

በአቤል እስጢፋኖስ

መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሄዝቦላህ በርካታ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ተኮሰ

ባለፉት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ ሄዝቦላህ ወደ ሰሜን እስራኤል ተጨማሪ ሮኬቶችን ሲተኮስ እንደነበር ኤፍፒ ዘግቧል፡፡

የእስራኤል ጦር ከሊባኖስ ወደ ላይኛው ገሊላ አካባቢ የተተኮሱ በአጠቃላይ 40 ሮኬቶች መገኘቱን ተናግሯል።

ጥቂቶቹ በእስራኤል ሚሳኤል መከላከያ የከሸፉ ሲሆኑ ሌሎቹ ግን መውደቃቸው ተነግሯል፡፡

ሄዝቦላህ በማያን ባሩክ ኪቡትዝ እና በቤቴ ሂሌል በሁለቱም የሊባኖስ ድንበር አቅራቢያ በሚገኙ የእስራኤል ወታደሮች ላይ ሮኬቶች መተኮሱን አረጋግጧል።

በትናንትናው ዕለት ሁለት የእስራኤል ሲቪሎች የተገደሉበትን የሮኬቶች ጥቃት መፈጸሙን ተናግሯል።

በሌላ ዜና በደቡባዊ ሊባኖስ ደርድጋይያ ከተማ ትናንት ምሽት በእስራኤል በተፈጸመ የአየር ጥቃት አምስት የጤና ባለሙያዎችን መሞታው ተነግሯል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በዛሬው ዕለት ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET248 ድሬዳዋ አየር ማረፍያ ለማረፍ በዝግጅት ላይ ሳለ በአውሮፕላኑ ውስጥ ጢስ ታይቱ እንደነበር የኢትዩጲያ አየር መንገድ አሳወቀ፡፡


በዚህም ምክንያት አውሮፕላኑ በድሬዳዋ አየር ማረፍያ በሰላም እንዲያርፍ በማድረግ መንገደኞችን ከአውሮፕላኑ ማውረድ መቻሉንም ባወጣው መረጃ ገልፃል፡፡


አየር መንገዱ ጢሱ የተነሳበትን ምክንያት በማጣራት ላይ ነው ብሏል።


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው ክስተት መንገደኞቹን ከወዲሁ ይቅርታ ጠይቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram /channel/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ኩላሊት ከሞተ ሰው እንዲወሰድ የሚረዳው የህግ ማዕቀፍ መልስ ሳያገኝ ስድስት አመታት መቆጠሩ ተነገረ

የኩላሊት ንቅለ ተከላ ለማድረግ የኩላሊት ልገሳን ከቤተሰብ ውጭ እንዲለገስ የማይፈቅደው የኢትዮጵያ የጤና ህግ እንዲሻሻል ቢጠየቅም መልስ አለማግኘቱ ችግር እንደሆነ ተነግሯል።

በቅርቡ በተወካዮች ምክር ቤት የጤና ህጎች ረቂቅ አዋጅ መቅረቡ የሚታወስ ሲሆን ስለ ኩላሊት ልገሳ የሚያወራው ህግ ግን እስካሁን እንዳልቀረበ በኩላሊት ተካሚዎች ማህበር በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ኩላሊት ከሞተ ሰው እንዲወሰድ የሚረዳ የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር ላለፉት ስድስት ዓመታት እየተጠየቀ ቢቀጠልም እስካሁን ተግባራዊ መሆን እንዳልተቻለም አስታውቀዋል።

ከቤተሰብ የሚደረገው የልገሳ ሂደትም በለጋሽ በኩል በሚያጋጥሙ ህመሞች እና ከለጋሽ ጋር ባለመመሳሰል ምክንያት የንቅለ ተከላ አለመሳካቶች ይስተዋላሉ ተብሏል።

በተደጋጋሚ ለተወካዮች ምክር ቤት ረቂቁ ይቀርባል የሚል መልስ እንደሚሰጣቸው የሚናገሩት አቶ ሰለሞን እስካሁን ግን ጠብ ያለ ነገር የለም ሲሉ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ የአይን ብሌን ልገሳ ሰዎች በህይወት እያሉ ወደውና ፈቅደው በሚፈርሙት መሰረት ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ ልገሳ ማካሄድ እየተሰራበት እንደሚገኝ አንስተው ለኩላሊትም ተመሳሳዩን መደረግ ይገባዋል ብለዋል።

ለአለም አሰፋ

ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢራን አየር መንገድ ወደ አውሮፓ የሚያደርገውን በረራ ሙሉ በሙሉ ማቋረጡ ተሰማ

የኢራን ሲቪል አቪዬሽን እንዳስታወቀው ወደ አውሮፓ ህብረት አባል አገራት የሚደረጉ በረራዎች ተቋርጠዋል።

ቴህራን እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው የህብረቱን ማዕቀብ ተከትሎ ነው።

የአውሮፓ ህብረት የኢራን አየር መንገድ የጦር መሳሪያ ወደ ሩሲያ ያጓጉዛል በሚል ነው ማዕቀብ የጣለው።

ህብረቱ በተለይም ሚሳኤልና ድሮኖችን ለ ሞስኮ ያቀብላል ብሏል።

ኢራን ግን የአውሮፓ ህብረትን ክስ አትቀበልም።

በመሆኑም ሁኔታዎች እስከሚስተካከሉ ድረስ ወደ አውሮፓ የሚደረጉ በረራዎችን ለመሰረዝ መገደዷን ፕሬስ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

አባቱ መረቀ

ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የመሬት አጠቃቀም ስርአት ወጥነት አለመኖር የብዝሀ ህይወት ላይ አደጋ ሆኗል ተባለ።

በምግብ ራስን ለመቻል እና ምርት በብዛት እና በስፋት ለማምረት የሚደረጉ ጥረቶች ምክንያት ብዝሃ ህይወት ችግር ገጥሞታል ተብሏል።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር መለሰ ማርዩ የደን መሬቶችን ወደ እርሻ መሬት መቀየር እና ረግረጋማ መሬቶች ላይ የሚደረጉ ሰፈራዎች በስፋት መታየታቸዉን አንስተዋል።

በኢትዮጵያ የስነ ምህዳር መናጋቶች መግጠሙን የሚናገሩት ዶ/ር መለሰ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተፈጠሩ የመሬት መንሸራተት አደጋዎች ለዚህ ማሳያ ነዉ ብለዋል።

ዘለቄታዊ ያልሆነ የመሬት አያያዝ እና አጠቃቀም እንዲሁም ከህግ ዉጪ የሆኑ የአስተራረስ ልኬት የብዝሃ ህይወት መሠረቱን አሳጥቶታል ተብሏል።

በምግብ ራስን ለመቻል በሚል ሀሳብ የተፈጥሮ ደን መሬትን በማጥፋት ለምግብ ሰብል ምርት ማዋል በጥናት ሊመራ የሚገባ ነዉ ሲሉም ገልፀዋል።

ዶ/ር መለሰ አያይዘዉም የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት የነባር አዝእርት ዘር ጥበቃ ላይ በሰፊዉ እየሰራበት መሆኑን አንስተዋል።

ተቋሙ የማህበረሰብ የዘር ባንክ ዉስጥ ነባር ዘሮች ከመያዝ ባሻገር ለአርሶ አደሮች እየሰጠ መሆኑ አሳዉቀዋል።


ቁምነገር አየለ

ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ብጉንጅ/ boils

የበሽታ መከላከል አቅማቸው የተዳከመ ሰዎች በዚህ ህመም የመጠቃት እድላቸው ሰፊ መሆኑ ይገለጻል፡፡

በጉርምስና ዕድሜ ላይ በሚገኙ ወጣቶች እና ጎልማሶች ላይ ይህ ችግር በብዛት እንደሚስተዋል ባለሙያዎች ያነሳሉ፡፡

እንዲሁም ከሴቶች ይልቅ በወንዶች ላይ በብዛት እንደሚታይ ይጠቀሳል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊንየም ሜዲካል ኮሌጅ የቆዳና አባላዘር ክፍል - ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑትን ዶክተር ሳሚያ መተናን ናቸው ፡፡

ብጉንጅ ምንድን ነው ?


ብጉንጅ/ boils ማለት አንድና ከዚያ በላይ የሆኑ የፀጉር መዉጫ ቀዳዳዎች በባክቴሪያ ምክንያት ኢንፌክሽን በሚፈጥርበት ወቅት ቆዳ ስር በመቆጣት፣መግል በመያዝና በማበጥ ህመም እንዲከሰት የሚያደርግ ችግር ነዉ ይላሉ፡፡

እብጠቱ በፍጥነት በማደግና በመግል በመሞላት የህመም ስሜቱ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡


መንስኤው ምንድን ነው ?

የበሽታው ዋነኛው መንስኤ” ስታፍሎኮካልስ” የተባለ የባክቴሪያ ዝርያ ሲሆን በአካባቢያችን በመገኘት ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል

የስኳር ህመም እና የሰዉነት የበሽታ መከላከል አቅም መቀነስ ሌሎቹ ተጨማሪ መንስኤዎቹ መሆናቸውንም ይናገራሉ፡፡


ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?

- ህመም ያለዉ እብጠት
- በእብጠቱ ዙሪያ ያለው ቆዳ መቅላት
- እብጠቱ መግል እየሞላዉ ሲመጣ የእብጠቱ መጠን መጨመር
- ነጭ ወይም ቢጫ ነገር በእብጠቱ ጫፍ ላይ መታየት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ህክምናዎቹ ምንድን ናቸው

- ቶሎ ቶሎ መታጠብ (ንፅህናን መጠበቅ )
-የሚዋጡ እና በመርፊ የሚሰጡ ፀረ ባክቴሪያ መድሃኒቶችን መውሰድ
- የመግል መቋጠር ሲያጋጥም ደግሞ በአነስተኛ ቀዶ ጥገና ማውጣት

በሽታው ወደ ሰውነት ውስጥ ሰርፆ ታችኛው የቆዳ ክፍል ላይ ከገባ ደግሞ ተኝቶ የመታከም ህክምና ሊሰጥ እንደሚችል አንስተዋል፡፡

በመጨረሻም ህብረተሰቡ ንፅህናውን በአግባቡ በመጠበቅ ከበሽታው እራሱን መከላከል እንዳለበት አና በሽታው ሲከሰት ቁስሉ ላይ በአድ ነገር ከመጠቀም መቆጠብ እንደሚያስፈልግ ዶ/ር ሳሚያ ተናግረዋል፡፡

አቤል እስጢፋኖስ

ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

6.4 ቢሊየን ትርፍ ማስመዝገቡን ዳሸን ባንክ ገለጸ፡፡

ዳሸን ባንክ ባለፈው በጀት ዓመት 6.4 ቢሊየን  ብር  ትርፍ  ማስመዝገቡን   አስታውቋል፡፡

ባንኩ ባለአክሲዮኖች 31ኛ መደበኛና 26ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን  በዛሬው እለት  በሚሊንየም አዳራሽ  ያካሄደ  ሲሆን ያለፈው ዓመት የባንኩ የስራ አፈፃፀም፣ የዚህ በጀት ዓመት እቅድና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች  ላይ ከባለአክሲዮች ጋር ተወያይቷል፡፡

በበጀት ዓመቱ የዳሸን ባንክ ተቀማጭ የገንዘብ መጠን የ30.9 ቢሊየን ብር እድገት ማስመዝገቡንና የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ መጠን 145.9 ቢሊየን ብር መድረሱን የዳሸን ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ዱላ መኮንን ተናግረዋል፡፡

ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ዘርፍ ለባንኩ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ያበረክተው ድርሻ 11.1 ቢሊየን ብር እንደነበርም ጠቁመዋል፡፡

የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ በበኩላቸው ያለፈው ዓመት ምንም እንኳን የተለያዩ ተግዳሮቶች ቢኖሩም ባንኩ ይህን ተቋቁሞ በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ጠቁመዋል፡፡

የዳሸን ባንክ አጠቃላይ ሃብት ባለፈው በጀት ዓመት የ27 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ ብር 183.7 ቢሊየን መደረሱን ገልፀዋል፡፡

ባንኩ ባለፈው በጀት ዓመት 1.44 ሚሊየን አዳዲስ ደንበኞችን ማግኘት እንደቻለና ይህም ለባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ ዕድገት የበኩሉን አስተዋፅኦ ማበርከቱንም ገልፀዋል፡፡ 

ባንኩ በአሁኑ ወቅት ከ6.7 ሚሊየን በላይ ደንበኞች እንዳሉትም ተመልክቷል፡፡


የውል ሰው ገዝሙ

ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የእስራኤል አየር ኃይል በሰሜናዊ የሊባኖስ አካባቢ በፈጸመው ጥቃት ከሀያ በላይ ሰዎች መገደላቸውን ሊባኖስ አስታውቃለች፡፡

የሊባኖስ የጤና ሚንስቴር እንደገለጸው እስራኤል ብዙም ዒላማ አድርጋው በማታውቀው በሰሜን ሊባኖስ በተፈጸመ የአየር ጥቃት ሳቢያ 21 ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል።

በዚሁ ጥቃት ሌሎች 8 ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ጥቃቱ የተፈጸመበት አካባቢ የእስራኤል ጦር ከሄዝቦላህ ጋር ከሚፋለምበት ሥፍራ ጋር በቅርበት የማይዋሰን እና በዋናነት የክርስቲያኖች መኖሪያ መንደር ነው።

ነዋሪዎች እንደሚሉት ይህ አካባቢ በአብዛኛው ከደቡብ ሊባኖስ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ሰዎች የሚኖሩበት ነው።

በጉዳዩ ላይ የእስራኤል ጦር እስካሁን ምላሽ አልሰጠም።

ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታያኔሁ ግን ሄዝቦላህን በየትኛውም የሊባኖስ አካባቢ “ከገባበት ገብተን እንፋለመዋለን” በማለት ዝተዋል።

“ሁሉም ነገር ዘመቻን ታሳቢ ያደረገ ነው። ይህንን በእስካሁኑ ጉዟችን አሻሽለናል።

በቀጣዮቹ ቀናትም የበለጠ እናሻሽለዋለን” ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትር ኔታኒያሁ ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በሄዝቦላህ የድሮን ጥቃት አራት የእስራኤል ወታደሮች ተገደሉ፡፡

በእስራኤል ጥቃት ደግሞ 51 ሊባኖሳዊያን መገደላቸዉ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

በደቡባዊ ሃይፋ በሚገኘዉ የእስራኤል ወታደራዊ ካምፕ ላይ ሄዝቦላህ ባደረሰዉ የአየር ጥቃት አራት ወታደሮች መገደላቸዉ ተገልጿል፡፡

እስራኤል ባለፈዉ ወር በሊባኖስ ሄዝቦላህ ላይ ካደረሰችዉ ጥቃት ወዲህ በጦር ካምፑ ላይ የደረሰ ከፍተኛዉ ጥቃት መሆኑ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር እስራኤል በአገሪቱ ላይ በፈጸመችዉ ጥቃት 51 ሰዎች መገደላቸዉን አስታዉቋል፡፡

በጋዛ ፤በሃማስ የሚመራዉ መንግስት እንደገለጸዉ፤ እስራኤል ለመጠለያነት በተዘጋጀ ትምህርት ቤት ላይ ባደረሰችዉ የአየር ጥቃት 15 ህጻናትን ጨምሮ 22 ሰዎች ህይወታቸዉ አልፏል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

እስከዳር ግርማ

ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram /channel/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከፓርቲዎች የቀረበበት ክስን አግባብነት የሌለው ሲል ውድቅ አደረገ

ምክር ቤቱ ከአምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች የቀረበበትን ስልጣንን አለአግባብ የማራዘም ክስ ጊዜውን ያላገናዘበ እና ግልፅ ያልሆነ ሲል ለጣቢያችን ገልጿል።

የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ደስታ ዲንቃ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ የስልጣን ጊዜ ለማራዘም ሲል አመታዊ ስብሰባውን አዛውሮታል ተብሎ የተነሳው ሀሳብ ልክ ያልሆነ የቃል ኪዳን ሰነዱንም በደንብ ያላገናዘብ ነው ብለዋል ።

ምክር ቤቱ የተቆረጠ ቀን ባያስቀምጥም ጠቅላላ ጉባዔ ለማካሄድ ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡

የጋራ ምክር ቤቱ በአገራዊ ጉዳዮች፣ በበጀት እጥረት፣ እንዲሁም በሠራተኞች መልቀቅ ምክንያት ውጥረት ውስጥ በመሆኑ ምክንያት ነው የዘገየው ሲሉ አስረድተዋል።

ከሰሞኑ አምስት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ የጋራ ምክር ቤት አመራር “የህግ ጥሰት ፈጽሟል” ሲሉ ከሰዋል።

የጋራ ምክር ቤቱ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ እንዲያደርግ መጠየቃቸውም የሚታወስ ነው።

ጥያቄውን ያቀረቡት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፣ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ)፣ የዎላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ (ዎብን)፣ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) እና ህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ህብር- ኢትዮጵያ) ናቸው።

ለአለም አሰፋ

ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በአነፍናፊ ውሻ የታገዘ ህገ ወጥ የዱር እንስሳት ውጤቶች ዝውውር የሚቆጠጠር ማዕከል ተከፈተ

በአነፍናፊ ውሻ የታገዘ ህገ ወጥ የዱር እንስሳት ውጤቶችን ዝውውር ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ልዩ የቁጥጥር ማዕከል ሥራ መጀመሩ የኢትዮጵያ የዱር እስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ የዱር እስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ከአፍሪካን ዋይልድ ላይፍ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የተከፈተው ማዕከሉ÷ ህገ ወጥ የዱር እንስሳት ውጤቶችን ዝውውር ለመከላከል ያስችላል ተብሏል።

ማእከሉን የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በይፋ ሥራ ያስጀመሩ ሲሆን÷ በመርሀ-ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጂራ፣ የአፍሪካን ዋይልድ ላይፍ ፋውንዴሽን የስራ ሀላፊዎችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 2 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ኮል ፓልመር የወሩ ምርጥ ተጨዋች ሆነ!

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ2024/25 የውድድር ዘመን የመስከረም ወር ምርጥ ተጨዋች ይፋ ተደርጓል ።

እንግሊዛዊው የቼልሲ የፊት መስመር ተጨዋች ኮል ፓልመር የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የመስከረም ወር ምርጥ ተጨዋች በመባል መመረጥ ችሏል።

ኮል ፓልመር በወሩ ባደረጋቸው አራት የፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች አምስት ግቦችን አስቆጥሮ አንድ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

በጋዲሳ መገርሳ

ጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram /channel/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የጥቅምት 1 ቀን 2016 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ ኮሪያ ጋር የሚያገናኟትን የመኪና እና የባቡር መስመሮችን በማቋረጥ ሁለቱን አገራት “ሙሉ በሙሉ ለመለያየት” መወሰኗን ገለጸች።

"ደቡባዊው ድንበር በዘላቂነት ይዘጋል" ያለው የአገሪቱ ጦር፤ በራሱ ድንበር በኩል ያሉ ቦታዎችን ጥበቃ እንደሚያጠናክር አስታውቋል።

በደቡብ ኮሪያ ውስጥ የሚደረጉ የጦርነት ልምምዶች እና የአሜሪካ የኒውክሌር ንብረቶች በአከባቢው በተደጋጋሚ መገኘታቸውን በመግለጽ እርምጃውን "ጦርነትን

ለመግታት ራስን የመከላከል እርምጃ" ሲል የኮሪያ ህዝብ ጦር (ኬፒኤ) ገልጾታል።
ውሳኔው በኮሪያ መካከል ያለው ውጥረት ከዓመታት በኋላ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት በዚህ ወቅት ያለውን ፍጥጫ መባባሱን ያሳያል።

“በኮሪያ ግዛት ላይ ያለው አስቸኳይ ወታደራዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮሪያ ኃይሎች የአገሪቱን ብሔራዊ ደኅንነትን በብቃት ለመጠበቅ የበለጠ ቆራጥ እና ጠንካራ እርምጃ እንዲወስዱ ይጠይቃል” ሲል ኬፒኤ በመንግስታዊው መገናኛ ብዙሃን ኬሲኤንኤ በኩል አስታውቋል።

መግለጫው በአብዛኛው የፒዮንግያንግ የይስሙላ እርምጃ ነው።
ቀደም ብሎም ቢሆን ከሰሜን ኮሪያ ወደ ደቡብ የሚወስዱ መንገዶች እና የባቡር ሃዲዶች እምብዛም ጥቅም ላይ አይውሉም።

መስመሮቹም በሰሜን ኮሪያ ባለስልጣናት ባለፈው ዓመት ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲፈርሱ ተደርገዋል።

ውሳኔው ከደቡብ ኮሪያ ጋር ያላትን ግንኙነት እንድትቀይር በፒዮንግያንግ ላይ ሰፊ ግፊት በጨመረበት እና በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ያበላሹ በርካታ ቀስቃሽ ክስተቶችን ተከትሎ የመጣ ነው።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…
Subscribe to a channel