ethiofm107dot8 | Unsorted

Telegram-канал ethiofm107dot8 - Ethio Fm 107.8

20436

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Subscribe to a channel

Ethio Fm 107.8

በሶሪያ አይ.ኤስ በድጋሚ እንዳይከሰት መስራት አለብን ሲሉ ብሊንከን አስጠነቀቁ

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በሶሪያ ውስጥ ያለው የእስላማዊ መንግስት ቡድን ዳግም እንዳያንሰራራ መደረግ አለበት ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በፕሬዚዳንት በሽር አላሳድ መንግስትና ህዝብ ቁጥጥር ስር ያሉ ከተሞችን ለመንጠቅ፤ የእስላማዊ መራሹ አማፅያን  ካለፉት ዓመታት ወዲህ የከፋ ሁከትና ውድመት በሃገሪቱ እያደረሰ መሆኑም ተገልጿል ።

ብሊንከን ከኔቶ ስብሰባ ጉባዬ ጎን ለጎን በብራስልስ ውስጥ እንደተናገሩት “በአሁኑ ጊዜ በሶሪያ ውስጥ ውጥረቱን መቀነስ በጣም ወሳኝ ነው።የንፁሃን ዜጎችን ደህንነት ማረጋገጥና ምናልባትም ከሁሉም በላይ ደግሞ ወደፊት የሚሄድ  የፖለቲካ ስራአት እንዲኖር ማስቻል ያስፈልጋል ።

ቢለኒከን አክለውም "እኛ  ፍላጎቶች በሶሪያ ውስጥ ዘላቂ ደህንነት እንዲኖር ነው፤በተለይም IS IS መልሶ እንዳይነሳ ማድረግና ተመልሶ እንደማይመጣ ማረጋገጥ ፅኑ ፍላጎት አለን" ሲሉ አብራርተዋል ።


በአሜሪካ የሚመራው ጦር በፈረንጆቹ በ2017 ኢራቅ ውስጥ፤ በ2019 ደግሞ በሶሪያ ያሉንት የእስላማዊ መንግሥት ቡድን ጠራርጎ ማስወጣቱም የሚታወስ ነው።

ሆኖም የጂሃዲስት ተዋጊዎች አሁንም ግዛታቸውን የመቆጣጠር እድል ባይኖራቸውም  በሩቅ በረሃማ አካባቢዎች ይንቀሳቀሳሉ ተብሏል ።

አቶኒዮ ቢሊንከን ፤ጂሃዲስቶችን ለመዋጋት በ2014 በአሜሪካ ጦር የተቋቋመው የአለም አቀፍ ፀረ-አይ.ኤስ ጥምረት አካል 900 የሚጠጉ ወታደሮች በሶሪያ፣ 2,500 የሚሆኑት ደግሞ በኢራቅ ውስጥ ተበትነዋል ብለዋል።

ከዚ ውጭ " በሶሪያ ውስጥ  አሸባሪዎቹን ለመዋጋት ብዙ  ያሰማራናቸው ታጣቂዎች አሉን ብለዋል ።

ልኡል ወልዴ

ኀዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የምዕራቡ ዓለም ወታደራዊ ድጋፍ ለዩክሬን የፈየደው ነገር እንደሌለ ስሎቫኪያ አስታወቀች

የስሎቫክያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጁራጅ ብላናር ዩክሬን ከምዕራባውያን አጋሮች የምታገኘው ከፍተኛ ዕርዳታ ቢሆንም፤ ኪየቭ ያመጣችው ለውጥ የለም ብለዋል።

የዩክሬን ጦር በሩሲያ ላይ እንዲያይል አሜሪካን ጨምሮ ሁሉም የምዕራባውያን አጋሮች ከፍተኛ የጦርና የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርርጉ ይታወቃል

ተግባሩ ለብዙዎች እልቂት ምክንያት እንጂ መፍትሔ አለመሆኑንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ለዚህ ግጭት ምንም ዓይነት ወታደራዊ መፍትሄ የለውም ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ሰላም እንዲወርድ በእውነት ግፊት ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ብሌናር ይህን ሃሳባቸውን ያጋሩት የኔቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በብራስልስ እያደረጉት ባሉት ውይይት ላይ ነው።

ይሁንና ሚኒስትሩ አብዛኞቹ የኔቶ አጋሮች አሁንም በዩክሬን ውስጥ ላለው ግጭት ከንግግር ይልቅ ወታደራዊ መፍትሄን እንደሚመርጡ ጠቁመዋል።

ልኡል ወልዴ

ኀዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

አድማስ ዲጅታል ሎተሪ 29ኛ ዙር ዕጣ ዛሬ ህዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በእድል አዳራሽ በህዝብ ፊት የወጥቷል

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

እስራኤል በማዕከላዊ ጋዛ የጦር ሰፈር እየገነባች መሆኗን አንድ ሪፖርት ይፋ አደረገ፡፡

እስራኤል በማዕከላዊ ጋዛ ሰርጥ ወታደራዊ ሰፈሮችን እየገነባች መሆኑንና ይህም በፍልስጤም ግዛት ውስጥ ያላትን ይዞታ ለማጠናከር የምታደርገዉን ጥረት እንደሚያሳይ ሪፖርቱ አስታዉቋል፡፡

ኒው ዮርክ ታይምስ የሳተላይት ምስሎችን እና የቪዲዮ ትንታኔዎችን መሰረት በማድረግ እንደዘገበው፤ የእስራኤል ሃይሎች በቅርብ ወራት ውስጥ ከ600 በላይ ህንፃዎችን በማፍረስ ቀጠና ፈጥረዋል ብሏል።

ኮሪደሩ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማዊያን ተፈናቃዮች ወደ ሰሜን ጋዛ እንዳይመለሱ ለማድረግ ጥቅም ላይ እንደዋለ ተገልጿል።

የፔንታጎን ቃል አቀባይ ፓት ራይደር ፤ስለ ሪፖርቱ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸዉ ጥያቄ ዘገባዎቹን አይቻለሁ ነገር ግን ማረጋገጥ አልቻልኩም ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ነገርግን አሜሪካ በዚያ ግንባር እስራኤላውያን አጋሮቿን ማማከሯን እንደምትቀጥል ገልጸዋል።

ቃል አቀባዩ ከዚህ ሁሉ ነገር በላይ አስፈላጊው ጉዳይ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ በመድረስ ታጋቾችን ማስለቀቅ እና ይህን አስከፊ ግጭት ማስቆም እንደሆነ ተናግረዋል ሲል ኒዉ ዮርክ ታይምስ አስነብቧል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ኀዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በሰባት ክፍሎች ያዘጋጃቸውን አጀንዳዎች ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዛሬ አስረከበ፡፡

አጀንዳዎቹ በ7 ክፍሎችና በ64 ዝርዝር ጉዳዮች ላይ የተዘጋጁ መሆናቸውም ተነግሯል፡፡

አጀንዳዎቹን የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕሮፌሰር) ከሌሎች ኮሚሽነሮች ጋር በጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አየለ ከተመራው የምክር ቤቱ የስራ አስፈፃሚ አባላት ልዑክ ተረክበዋል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መሥፍን አርአያ (ፕሮፌሰር) ኮሚሽኑ ከምክር ቤቱ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሞ በጋራ እየሠራ መቆቱን ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ በተቋማትና በማህበረሰብ ክፍሎች ተደራጅተው የሚቀርቡ አጀንዳዎችን በአግባቡ እንደሚጠቀምባቸውም አክለዋል፡፡

ሌሎች ተቋማትና ማህበራትም የተደራጁ አጀንዳዎቻቸውን እንዲያስረክቡ ነው ዋና ኮሚሽነሩ መልዕክት ያስተላለፉት፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አየለ በበኩላቸው ፖለቲካ ፓርቲዎች አካታች ሀገራዊ ምክክር እንዲደረግ ሚናቸውን መወጣት ይገባቸዋል ብለዋል።

የተደራጁት የፖለቲካ ፓርቲዎች አጀንዳዎች ለአካታችና አሳታፊ ሀገራዊ ውይይት የሚያግዙ እንደሚሆኑም አስረድተዋል።

ምክር ቤቱ ዛሬ ለኮሚሽኑ ያስረክባቸው አጀንዳዎች በምክርቤቱ በሙሉ ድምፅ የፀደቁ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራውን አጠናክሮ የቀጠለው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሁሉም ባለድርሻ አካላት በተለያዩ አማራጮች አጀንዳዎችን በስፋት መረከቡን እንደሚቀጥልም በመድረኩ ተገልጿል።


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ኀዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ 6 ማደያዎች ላይ እርምጃ ወስጃለሁ አለ፡፡

የነዳጅ ማደያዎች እለታዊ የነዳጅ አቅርቦት መጠን ይፋ መደረግ ከጀመረብት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን 6 የሚሆኑ ማደያዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ቢሮው አስታውቋል፡፡

በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የገበያ ጥናት፤ መረጃ እና ፕሮሞሽን ዳይሬክተር እንዲሁም የኮሙኒኬሽን ተወካይ አቶ ሙሰማ ጀማል ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ማደያዎቹ ነዳጅ እያለ የለም በማለታቸው እርምጃ የተወሰደባቸው ናቸው፡፡

ከተወሰደባቸው እርምጃ መካከል የማስጠንቀቂያ እና በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ የማድረግ እርምጃዎች ናቸው ብለዋል፡፡

ይህ ስራ መጀመሩ ህብረተሰቡ ግዜውን እንዲቆጥብ እና መብቱን እንዲያውቅ ማድረጉን ጠቅሰዋል፡፡

አዲስ አበባ በቀን 1.4 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ እንደሚያስፈልጋትም አንስተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የነዳጅ ማደያዎች እለታዊ የነዳጅ አቅርቦት መጠንን ጥቅምት ወር ላይ ይፋ ማድረግ መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡

ሐመረ ፍሬው

ኀዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የምዝገባ እና እድሳት ስራ 63 በመቶ መድረሱ ተገለፀ

በአዲስ አበባ ከተማ የ 2017 ዓ.ም የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ምዝገባ እና እድሳት ከጥቅምት 1 ጀምሮ እየተደረገ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ከ 5 አመት በፊት በ 10 ወረዳዎች ላይ ብቻ ይሰጥ የነበረዉ ይህ አገልግሎት በአሁን ወቅት በሁሉም ወረዳዎች ላይ መኖሩን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ ዶ/ር ሙሉጌታ እንዳለ ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል።

ህዳር 30 የሚጠናቀቀዉ የዚህ አመት የመድን ሽፋኑ የአዲስ አባላት ምዝገባ እና የነባር አባላት እድሳት ስራ 63 በመቶ መሰራት መቻሉን ለኢትዩ ኤፍም ገልፀዋል

ጤና ቢሮዉ በአገልግሎት ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመቀነስ አዲስ አባላት መስፈርቱን በማሟላት በቀሩት ቀናት ምዝገባ እንዲያደርጉ ጠይቋል።

በዘንድሮዉ የመድህን አገልግሎት ተጠቃሚዎች አዲስ አባላትን 10 በመቶ ለመጨመር እቅድ እንደተያዘ ለማወቅ ተችሏል።

ቢሮዉ ከዚህ ቀደም በሰጠዉ መግለጫ እንደገለፀዉ ከሆነ ክፍያዉን አስመልክቶ የመደበኛ መዋጮ መጠን 1 ሺ 500 ብር ሲሆን ለአዲስ አባላት የመመዝገቢያ 200 ብር ክፍያ ይኖራል ሲል አስታውቋል ።

በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ የደሃ ደሃ ለሚባሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ዉጪዉን ይሸፍናል ተብሏል።

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ምዝገባ እና እድሳት ስራን ህዳር 30 ያጠናቅቃል።

ቁምነገር አየለ

ኀዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ኢትዮጵያ  እራሷን ከውድድሩ አገለለች !

የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን በዩጋንዳ አዘጋጅነት ከሚካሄደው የሴካፋ ዞን የማጣሪያ ውድድር በበጀት እጥረት ምክንያት ራሷን ማግለሏን እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡

ባሳለፍነው ወር ላይ የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ሴካፋ ዞን ማጣሪያ የምድብ ተጋጣሚዎቿን ማወቋ ይታወሳል፡፡

በዚህም ብሔራዊ ቡድኑ በምድብ አንድ ከዩጋንዳ ፣ ታንዛኒያ እና ቡሩንዲ ጋር ተድልድሎ የማጣሪያ ውድድሩን በዩጋንዳ አዘጋጅነት ከታህሳስ 5 እስከ ታህሳስ 19/2017 ዓ.ም ለማድረግ ውስኖ ነበር፡፡

አሁን ላይ ኢትዮጵያ ራሷን ከ 17ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ሴካፋ ዞን ማጣሪያ ውድድር ማግለሏ ይፋ አድርጋለች፡፡

ኢትዮጵያ ከውድድሩ ራሷን ያገለለችው በበጀት እጥረት ምክንያት መሆኑን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለሴካፋ በላከው ደብዳቤ ገልጿል።
ይህንንም ተከትሎ የማጣሪያ ውድድሩ ምድብ አንድ በሶስት ሀገራት መካከል የሚካሄድ ይሆናል ተብሏል፡፡

ጋዲሳ መገርሳ

ኀዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ስርቆት ከ2.7 ሚሊየን ብር በላይ  ማጣቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለፀ።

በአዲስ አበባ ከተማ በጥቅምትና ህዳር ወር ብቻ  በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ በተፈፀመ ስርቆት ከ1.6 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት ደርሷል።

ከዚህ በተጨማሪ በከተማዋ ደቡብ ሪጅን አከባቢዎች በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ በተፈፀመ ስርቆት ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት መድረሱን የአገልግሎቱ የኮምኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ታየ ለጣቢያችን ተናግረዋል።

በተመሳሳይ በምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን በየካ ክፍለ ከተማ ከ3 መቶ ሺህ ብር በላይ የሚገመት የትራንስፎርመርና የኃይል ስርቆት ተፈፅሟል ብለዋል።

በጉለሌ፣ ኮልፌ፣ አራዳ፣ ቂርቆስና ልደታ ክፍለ ከተሞች በተፈፀመ የኬብልና የሌሎች መሰረተ-ልማቶች ስርቆት ከ2 መቶ ሺህ ብር በላይ ኪሳራ መድረሱንም ነው ስራ አስፈፃሚው የነገሩን።
  
በተለያዩ ጊዜያት በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ በሚፈፀም ስርቆት ምክንያት ለዜጎች ይቀርብ የነበረው የኃይል አቅርቦት መቋረጡ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል ብለዉናል።
     
በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝም አቶ መላኩ ነግረውናል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ኀዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በሲሚንቶ አቅርቦትና ግብይት ላይ የአሰራር ማሻሻያ ተደረገ፡፡

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሲሚንቶ ግብይት በራሳቸው በፋብሪካዎቹ ፍትሀዊ ዋጋ እንዲቀርብ ወስኗል፡፡

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ምርታቸውን በፍትሃዊ ዋጋ እንዲያቀርቡ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

ከዚህ ቀደም የሲሚንቶ ምርት የፋብሪካ መሸጫ ዋጋ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየተወሰነ ለገበያ ሲሰራጭ የቆየ ቢሆንም በአዲሱ የአሰራር ሂደት ግን አምራች ፋብሪካዎች ሙሉ ሀላፊነቱን በመውሰድ በነጻነት ምርታቸውን ለገበያ እንዲያቀርቡ እና ገበያውን እንዲያረጋጉ ሃላፊነት መስጠቱን ሚኒስቴሩ እውቁልኝ ብሏል፡፡

የሲሚንቶ ፋብሪካዎቹ የተሰጣቸውን ሀላፊነት በተጠያቂነት ስሜት እና በፍትሃዊ የዋጋ ተመን ማህበረሰቡን እንዲያገለግሉም መወሰኑን ገልጾ ከዚህ ቀደም አገልግሎት ላይ ይውል የነበረውን መመሪያ 940/2015 ማንሳቱን ይፋ አድርጓል ፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ኀዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት በሩብ አመቱ 95 ሺ ዩኒት ደም ማሰባሰብ መቻሉን ገለጸ

የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት በሩብ አመቱ 100 መቶ ሺ ዩኒት ደም ለማስባስብ ታቅዶ 95 ሺ ዩኒት ደም ማሰባሰብ መቻሉን ለጣቢያችን ገልጧል

የኢትዮጲያ ደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሃብታሙ ታየ እንዳሉት ክረምቱን ተከትሎ በተቆማት ደም ማሰባሰብ አስቸጋሪ ቢሆንም በአደባባይ ላይ በተሰራ የበጎ ፍቃድ እንቅስቃሴ ስራ 95 ሺ ዩኒት ደም ማሰባሰብ መቻሉን ገልፀዋል

ዳይሬክተሩ አክለውም ደም በባህሪው የመጠቀሚያ ጊዜ ያለው በመሆኑ ሁልጊዜም ቢሆን ህብረተሰቡ ደም መለገስ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

በዘንድሮ በጀት አመት 513 ሺህ ዩኒት ደም ለማሰባሰብ ታቅዶ እየተስራ መሆኑን የገለፁት የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሃብታሙ ታየ ለዚህም ከፍተኛ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡

አቤል እስጤፋኖስ

ኀዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የሰላም ሰራዊት የተባለዉ አደረጃጀት ላይ ቁጥጥር ይደረጋል ተብሏል

ህጋዊ ያልሆነ አሰራር ላይ የሚሳተፉ የሰላም ሰራዊት አባላት ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ሲል የከተማዉ የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ገልፆል።

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች ከህብረተሰቡ ክፍሉ የተወጣጡ አካላት ለፀጥታ ደህንነት ቢቋቋሙም ህገወጥ ድርጊት ሲፈፅሙ እንደሚገኙም ተገልፆል።

ጣቢያችን ያነጋገርናቸው የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ እነዚህ አደረጃጀቶች ማህበረሰቡን ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር እንዲጠብቁ የሚደረግበት ስምሪት ነዉ የሚሰጠዉ ብለዋል።

ጣቢያችን ከዚህ ቀደም ከከተማዋ ነዋሪዎች የሰላም ሰራዊቱ ላይ ሲነሱ የነበሩ ቅሬታዎችን ተንተርሶ ለቢሮዉ ባቀረበዉ ጥያቄ እስካሁን ቁጥሩ አነስተኛ ቢሆንም ለህብረተሰቡ ተፅዕኖ እያሳደሩ በተገኙ የአደረጃጀቱ አባላት ላይ ወደ ህግ የማቅረብ ስራ መስራቱን ቢሮዉ አስታዉቋል።

በመዲናዋ ከ 241 ሺህ በላይ የሰላም ሰራዊት ከህዝቡ የተዉጣጡ አባላት እንደሚገኙ የሰላም እና ፀጥታ ቢሮዉ ምክትል ሀላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ ተናግረዋል።

የሰላም ሰራዊት የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ሀይል በመንደር፣ በብሎክና በቀጠና ደረጃ የሚመደብ ነው ፡፡

በየመንደሩና አካባቢው የሚፈጠሩ ችግሮችን መፍታት፣ አጠራጣሪ ነገሮችን ሲሳይ ጥቆማ መስጠት፣ የመሬት ወረራና ሕገ-ወጥ ግንባታ መከላከልን ሀላፊነቶች አሉት ተብሏል፡፡

ቁምነገር አየለ

ኀዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በሶሪያ መንግስት ላይ አሜሪካ የጣለችው ማዕቀብ አይለወጥም ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳወቀ

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር ፤ሀገራቸው በሶሪያ መንግሥት ላይ የምትከተለውን ፖሊሲ እንደማትቀይርና በሀገሪቱ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ መቀየርም ሆነ ማንሳት እንደማትፈልግ ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ ይህን የተናገሩት በሰጡት መግለጫ ነው።

በሶሪያ ከፈረንጆቹ 2011 ግጭት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ፤ሀገሪቱ ከዩናይትድ ስቴትስ ፣ ከአውሮፓ ህብረትና ከተለያዩ መንግስታት ማዕቀብ ተጥሎባታል መቆየቷም የሚታወቅ ነው ።

የዩኤስ ማዕቀቦች እገዳን ያካተተና ሶስተኛ ወገኖችን የሚነካ መሆኑም ተገልጿል።

የዩናይትድ ስቴትስ ሁለተኛ ደረጃ ማዕቀብ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ2019 የተፈረመው የቄሳር ህግ ተግባራዊ እስኪሆነ ድረስ ገደቡ ይቀጥላል ነው ያሉት ።

ልኡል ወልዴ

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ኀዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የባይደን የመሪነት ዘመን ሊጠቃለል በቀሩት 50 ቀናት ውስጥ የዩክሬንን የጦር መሳሪያ ክምችት ለማሳደግ ይሰራል ተባለ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጄክ ሱሊቫን፤ የባይደን የመሪነት ዘመን ሊጠቃለል በቀረው የ50 ቀን እድሜ አሜሪካ የዩክሬንን የጦር መሳሪያ ክምችትን ለማሳደግ ትሰራለች ብለዋል።

በእነዚህ 50 ቀናት ውስጥ ዩክሬን በጦር ሜዳ አቋሟን ለማጠናከር የሚረዱ ሁሉንም መሳሪያዎች ለማቅረብ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የሚደረገዉ የመሳሪያ ድጋፍ ዩክሬን በጦር ሜዳ ብቻ ሳይሆን በድርድር ጠረጴዛው ላይም የበለጠ ጠንካራ እንድትሆን ይረዳታል ብለዋል፡፡

አማካሪዉ አክለውም፤በፕሬዝዳንት ባይደን ከፍተኛ ወታደራዊ አቅርቦትን እንዲቆጣጠሩ ኃላፊነት እንደተሰጣቸዉም ተናግረዋል፡፡

ባይደን ስልጣናቸዉን እስኪያስረክቡ ድረስም ወደ ዩክሬን የሚደረጉ እያንዳንዱ የጦር መሳሪያና የገንዘብ ድጋፎች በኮንግረንሱ ፈቃድ ማግኘታቸዉንም አማካሪዉ ገልጸዋል፡፡

ልኡል ወልዴ

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ኀዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ካለንበት ጥልቅ የሆነ ችግር እንድንወጣ ድጋፍ ያስፈልገናል - የትግራይ ግብርና ቢሮ

ከጉዳቱ ቶሎ ለማገገም እንዲቻል መሰረታዊ ድጋፎች ያስፈልጋሉ ብሏል ቢሮው።

ድጋፎች ያስፈልጋሉ ካልሆነ ከጦርነት የተረፈው ተፈናቃይ እና ገበሬ የረሃብ አደጋ ላይ ነው ሲል ቢሮው አስታውቋል።

በክልሉ ያለው ጉዳት ከፍተኛ ቢሆንም የሚሰጠው ድጋፍ ግን እንደማይመጣጠን የነገሩን የቢሮው ምክትል ሃላፊ እና የተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ አስተባባሪ የሆኑት አቶ አለምብርሃን ሃሪፈዮ ናቸው።

ከሰው ሰራሽ ችግሮች በተጨማሪ የተለያዩ የተፈጥሮ ምክንያቶች መኖራቸውን የሚያነሱት አቶ አለምብርሃን፤ ዋጃ የሚባል ወፍ በአንዳንድ አከባቢዎች ተከስቶ ጥቃት ማድረሱንም ገልጸዋል።

ባለፈው ዓመት የክልሉ ግብርና ቢሮ 9መቶሺህ ኩንታል ማዳበሪያ ጠይቆ እንደነበር የገለፁት ሃላፊው፤ የተላከው የማዳበሪያ መጠን ወደ 4መቶ ሺህ ኩንታል እንደነበር አስታውሰዋል።

በዚህ ዓመት ወደ 1 ሚሊየን ኩንታል ማዳበሪያ ያስፈልገናል ብለን ጠይቀናል ብለውናል።

የማዳበሪያ ጉዳይ ያን ያህል ችግር አይደለም ያሉት ሃላፊው፤ ዋናው ችግር የአርሶአደሩ የመግዛት አቅም መሆኑን አንስተዋል።

ብድር የሚፈቀድበት ሁኔታም ባለመኖሩ ምክንያት አርሶአደሩ በጣም ትንሽ ይገዛል አልያም ምንም አይገዛም ብለዋል።

ይህም ምርት በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንስ ምክንያት ሆኗል ነው ያሉት።

የግብርና ሚኒስቴር ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ለቢሮው የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጉን ያነሱት ሃላፊው ፤ይሁን እንጂ ያን ያህል በቂ የሚባል ድጋፍ አይደለም ብለዋል።

በክልሉ 56 ወረዳዎች ላይ የግብርና ስራ እየተሰራ መሆኑንም አቶ አለምብርሃን ነግረውናል።

እስከዳር ግርማ

ኀዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሊቨርፑል ነጥብ ሲጥል  አርስናል፣ ሲቲ እና  ቼልሲ አሸንፉ!

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ14ኛ ስምንት መርሐግብሮች

የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ከኒውካስል ዩናይትድ ያደረገውን ጨዋታ 3ለ3 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

የሊቨርፑልን ግቦች መሐመድ ሳላህ 2x እና ጆንስ ሲያስቆጥር ለኒውካስል አይሳክ ፣ ሻር እና ጎርደን ከመረብ አሳርፈዋል።

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ያደረገውን ተጠባቂ የፕርሚየር ሊግ ጨዋታ 2ለዐ በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የመድፈኞቹን የማሸነፊያ ግቦች ዊሊያም ሳሊባ እና ጁሪየን ቲምበር አስቆጥረዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ በውድድር አመቱ በሊጉ አምስተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።


ማንችስተር ሲቲ  ከኖቲንግሃም ያደረገውን ጨዋታ በዴብሮይን ፣ ዶኩ እና ሲልቫ ግቦች 3ለ0 አሸንፏል።

ቼልሲ ከሳዝዝሀምፕተን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 5ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፈዋል።

የሰማያዊዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ዲሳሲ ፣ ንኩንኩ ፣ ማዱኬ ፣ ፓልመር እና ሳንቾ አስቆጥረዋል።

በሌላ ጨዋታ ኤቨርተን ከዎልቭስ ጋር ጨዋታውን አድርጎ 4ለ0 ማሸነፍ ችሏል።

ማንችስተር ሲቲ ከአንድ ወር በኋላ ወደ አሸናፊነት መመለስ ችሏል።

የሊግ ደረጃቸው

1 ሊቨርፑል :- 35 ነጥብ
2 ቼልሲ :- 28 ነጥብ
3  አርስናል:-28 ነጥብ
4 ማንችስተር ሲቲ :- 26 ነጥብ
11 ማንችስትር ዩናይትድ:- 19 ነጥብ

በጋዲሳ መገርሳ

ኀዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በኮንጎ የፅንፈኛ አማፂያኑ ኤዲኤፍ ቡድን ጥቃት ተጠናክሮ ቀጥሏል ተባለ።

ከእስላሚክ አማፂያን ጋር ግንኙነት እንዳለዉ የሚነገርለት ኤዲኤፍ በዛሬዉ እለት  በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል የ8 ወር ጨቅላ ህፃን ጨምሮ 9 ሰዎችን ገድሏል።

ይህንን ያስታወቁት የሀገሪቱ ባለስልጣናት ከሟቾቹ ግድያ በተጨማሪ በርካቶች ታግተዉ መወሰዳቸዉን ገልፀዋል።

አማፂያኑ በመንደሩ በርካታ ቤቶችን በማቃጠል ከፍተኛ ዉድመት ማድረሳቸዉ ተያይዞ ተገልፆል።

በኮንጎ ስጋት የሆነዉ ቡድኑ ከአይኤስ የአማፂያን ቡድን ጋር ግንኙነት ያለዉ ነዉ።

ከአንድ ቀን አሰቀድሞ በሰሜን ኪቩ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃቶች መፈፀሙን የጦሩ ቃል አቀባይ በሰጡት መግለጫ ላይ ጠቅሰዋል።

በምስራቅ ኮንጎ የተለያዩ ቡድኖች ለስልጣን ÷ የዉድ ማእድናት ሀብቶች ጋር በተያያዘ በትጥቅ ትግል ዉስጥ ናቸዉ።

ሆኖም የኤዲኤፍ ጥቃቶች ግን ከሀገሪቱ ዋና ከተማ እንዲሁም ወደ አጎራባች ግዛቶች ተጠናክሮ  እየተዛመተ ነዉ ተብሏል።

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ፅህፈት ቤት በባለፈዉ ወር ባወጣዉ ፅሁፍ በምስራቅ ኮንጎ እነዚህ አማፂ ቡድኖች ስጋት መሆናቸዉን ጠቅሷል።

ፅህፈት ቤቱ ይህ አማፂ ቡድን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸዉን እና ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ህፃናት አፍኗል ሲል ከሷል።

ቁምነገር አየለ

ኀዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የሶሪያ አማፅያን አራት ማዕከላዊ ከተሞችን መቆጣጠራቸውን ተገለጸ

የሶርያ መንግስት ወታደሮች የተወሰነ ግዛትን ማስመለሳቸውን ቢገልፁም ፤ አማፅያኑ አራት ማዕከላዊ ከተሞችን ይዘዋል ተብሏል ።

የሶሪያ አማፅያን ድል እየተቀዳጁ መሆኑም ነው የተዘገበዉ።

የተቃዋሚ ተሟጋቾች እንዳሉት ወደ ሃማ ከተማ ለመግባት የሚያግዙ አራት ቦታዎችን አማፂያኑ የተቆጣጠሩ ሲሆን፤ ይህም ወደ ማእከላዊ ሃማ ለመግባት የሚያስችላቸዉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአማፅያኑ ቡድኖች ዋና ደጋፊ የሆኑት የቱርኩ ፕሬዝዳንት ኤርዶሃን ፤ የሶሪያ መንግስት ሁኔታው የበለጠ እንዳይባባስ ለመከላከል ከፈለገ "በእውነተኛ የፖለቲካ ሂደት ውስጥ" መሳተፍ አለበት ካሉ በኋላ አመጹ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል፡፡

የሶርያ የእርስ በርስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ የበሽር አል አሳድ መንግሥት በአማጽያኑ ከተነጠቀው የሀገሪቱ ግዛት ሁለት ሦስተኛውን መልሶ ከእጁ ማስገባት ችሎ ነበር ተብሏል ዘገባዉ የኤፒ ነዉ ።

ልዑል ወልዴ

ኀዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

አርስናል ከ ማንችስትር ዩናይትድ ( የኢትዮጵያዌያን ድርቢ)

ምሽት 5፡15 ላይ በኤምሬትስ ስቴድየም

የ14ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብሮች ሲደረጉ ምሽት 5፡15 ላይ አርሰናል በኤምሬትስ ከማንቼስተር ዩናይትድ ጋር የሚያደርጉት ፍልሚያ በጉጉት ይጠበቃል፡፡

የለውጥ መንገዳቸውን በስፔናዊው አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የጀመሩት መድፈኞቹ ባለፉት ሦስት ዓመታት ለፕሪሚየር ሊጉ ዋንጫ ክብር ከጫፍ ደርሰው ሳይሳካቸው ቀርቷል፡፡

እንዲሁም ማንቼስተር ዩናይትድን ከስኮትላንዳውዩ ስመጥሩ ስኬተማ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉስን በኋላ ወደ ቀድሞ ክብሩ የሚመልሰው አልተገኘም።

ከሆላንዳዊው አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ ስንብት በኋላ በተሾሙት ፖርቹጋላዊ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም እየተመሩ በመነቃቃት ላይ የሚገኙት ቀያይ ሰይጣኖቹ ዛሬ ለአርሰናል ፈተና ሊሆኑ እንደሚችሉም ተገምቷል፡፡

በ13ኛ ሣምንት የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች ሁለቱም ቡድኖች ተጋጣሚዎቻቸውን በሰፊ የግብ ልዩነት ማሸነፋቸው ደግሞ የዛሬውን ጨዋታ ተጠባቂ አድርጎታል፡፡

አርሰናል ከፕሪሚየር ሊጉ መሪ ሊቨርፑል ላለመራቅ እንዲሁም ማንቼስተር ዩናይትድ በአዲሱ አሰልጣኝ ያገኘውን የአሸናፊነት ስሜት ይዞ ለመቆየት ጨዋታውን የማሸነፍ ግዴታ ውስጥ ገብተዋል ፡፡

በሌሎች የእለቱ መርሐ-ግብሮች
ምሽት 4፡30

ኤቨርተን ከ ዎልቭስ

ማንቼስተር ሲቲ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት

ኒውካስል ዩናይትድ ከ ሊቨርፑል

ሳውዝሃምፕተን ከ ቼልሲ

ምሽት 5:15

አርስናል ከ ማንችስትር ዩናይትድ

አስቶንቪላ ከ ብሬንትፎርድ

በጋዲሳ መገርሳ

ኀዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የህዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

አቶ ጌታቸው ረዳን እንደሚከስ አስታውቆ የነበረው የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም  መቀሌ ቅርንጫፍ ሃሳብ ቀይሪያለሁ አለ


የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም  መቀሌ ቅርንጫፍ  "በቀድሞ የትግራይ ፖሊስ አባላት" ጉዳይ ከፕሬዝዳንቱ ጋር  ተገናኝተው ለመምከር ቀጠሮ መያዛቸው ተነግሯል ።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም መቀሌ ቅርንጫፍ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ   ላይ ሊመሰርት የነበረውን ክስ በመተው ክፕሬዝዳንቱ ጋር ለመነጋገር  ቀጠሮ መያዙን ገልጿል።

የትግራይ ቅርጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፀሀዬ እምባዬ  ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት  ጉዳዩ በካቢኔ እንደተወሰነ ነግረውን ፤ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የቀድሞ ፖሊሶችን አቤቱታ በተመለከተ በካቢኔው በኩል ተወስኖ  ከፕሬዝዳንቱ ጋር ለንግግር ሊቀመጡ እንደሆነ ነግረውናል።

አሁን ላይ በአማካሪ በኩል  ጉዳዩ ለካቢኔ ተመርቶ ውሳኔ የተሰጠ ሲሆን በአማካሪያቸው በኩል  በሶስት ቀናት ውስጥ ንግግሩን ለማድረግ መታቀዱን አስታውቀዋል ።

በጊዜያዊ አስተዳደሩ ላይ የቀረበው ክስ፤ የቀድሞ የትግራይ ፖሊስ አባላት አለአግባብ ከሥራ ገበታቸው የተባረሩ በመሆኑ ወደ ነበሩበት ቦታ እንዲመለሱና ደሞዛቸውም እንዲከፈላቸው" የሚል ነው፡፡

ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኃላ ሁሉም የመንግሥት ሠራተኛ ወደ ሥራ የተመለሰ መሆኑን ያነሱት አቶ ፀሐዬ፤ ፖሊሶቹ ግን ደምወዝ እንዳላገኙና ወደ ሌላ ሥራም እንዳይገቡ  መሸኛ ጭምር እንዳልተሰጣቸው  ነግረውናል፡፡

ለአለም አሰፋ

ኀዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በመዲናዋ አንድ ቀን በተደረገ አሰሳ ከ120 ማደያዎች 6ቱ ብቻ አገልግሎት ሲሰጡ ተገኙ

በአዲስ አበባ አንድ ቀን በተደረገ አሰሳ ከ120 ማደያዎች ስድስቱ ብቻ አገልግሎት ሲሰጡ መገኘታቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ዛሬ በተካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስምንተኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ በነዳጅ የአቅርቦት እና የስርጭት ችግር መኖሩን ገልጸዋል፡፡

የሥርጭት ችግርን ለመቅረፍ የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን የጠቀሱት ካሳሁን (ዶ/ር)፤  አክለውም 68 የሚሆኑ ነዳጅ ማደያዎች ነዳጅ እያላቸው የለም ሲሉ መገኘታቸውንም አብራርተዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል፡፡

ከ105 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ላይ በመላው ሀገሪቱ እርምጃ መወሰዱንና ከዚህ ወስጥ ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑት በእስራት አንዲቀጡ ተደርጓል።

መንግስት ከፍተኛ በጀት በመመደብ በሚያስገባው ነዳጅ ላይ እንዲህ ዓይነት አካሄዶች ሊቀጥሉ አይገባም ያሉት ሚኒስትሩ፤ ቁጥጥር እየተደረገ  ጠንካራ እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።


ኀዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የህዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የተመጣጠነ ምግብ ዕጥረትን ለማስቀረት የስንዴ ዱቄት እና የምግብ ዘይትን በቫይታሚን ለማበልፀግ የሚሰራ ትብብር በኢትዮጵያ ይፋ ተደረገ።

ሚለርስ ፎር ኒውትሪሽን ቴክኖ ሰርቭ ከተሰኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን ትብብሩን በኢትዮጵያ አስጀምረዋል።

ጥምረቱ የስንዴ ዱቄት አምራች እና የምግብ ዘይት ፋብሪካዎችን በቫይታሚን በማበልፀግ የተመጣጠነ ምግብ ዕጥረትን ለመቀነስ እንደሚሰራ ተገልጿል።

ሚለርስ ፎር ኒውትሪሽን ባለፈው አንድ አመት ጊዜ ውስጥ ለ1መቶ40 ፋብሪካዎች የቴክኒካል ድጋፍ እና ለተጨማሪ 40 ፋብሪካዎች ደግሞ ስልጠና መስጠቱንም የሚለርስ ፎር ኒውትሪሽን የኢትዮጵያ ፕሮግራም ማኔጀር አቶ እያቄም አምሳሉ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ከተመጣጠነ ምግብ ዕጥረት ጋር በተያያዘ 39 በመቶ ህፃናት የቀነጨሩ ሲሆን፤ 22 በመቶ ደግሞ መሆን ካለባቸው ክብደት በታች ናቸው።

እነዚህ ቁጥሮች ለህፃናት ጤናማ ዕድገት የሚያስፈልጉትን ንጥረ ነገሮች ህፃናቱ እንዲያገኙ ለማድረግ መስራት አስፈላጊ መሆኑን የሚያሳይ ነው ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ አገራችን ከተመጣጠነ ምግብ ዕጥረት ጋር በተያያዘ 16.5 በመቶ አመታዊ ጂዲፒ ወጪ ታደርጋለች።

ይህንን ለማስቀረት በማሰብ በየዕለቱ ልንመገባቸው የምንችላቸው የምግብ ግብዓቶችን በቫይታሚኖች በማበልጸግ እንደሚሰራ ነው አቶ እያቄም የተናገሩት።

ሚለርስ ፎር ኒውትሪሽን ኢትዮጵያን ጨምሮ በኬንያ፣ ናይጄሪያ፣ ታንዛኒያ ፣ ፓኪስታን፣ ባንግላዴሽ ፣ ህንድ እና ኢንዶኔዥያ የሚገኙ አምራቾችን የሚደግፍ ነው።

በእነዚህ አገራት የሚገኙ የስንዴ፣ በቆሎ፣ ሩዝ እና የምግብ ዘይት ምርቶችን በቫይታሚን ያበለፅጋል።

በፈረንጆቹ 2026 በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ የ1 ቢሊየን ዜጎችን የስርዓተ ምግብ ሁኔታ የተሻለ ለማድረግ እየሰራ ይገኛልም ተብሏል።

እስከዳር ግርማ

ኀዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በኡጋንዳ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር 28 ደርሷል።

በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል ከሳምንታት በፊት በደረሰ የመሬት መንሸራተት ከ100 በላይ ሰዎች እስካሁን ደብዛቸዉ ጠፍቷል።

የሟቾች ቁጥር እስካሁን 28 መድረሱ የገለፀዉ የሀገሪቱ ፖሊሲ ከሟቾቹ ዉስጥ ህፃናትም ይገኙበታል ብለዋል።

የዩጋንዳ ቀይ መስቀል ማህበር የነፍስ አድን ስራዎች እየሰራ ቢሆንም የሟቾች ቁጥር ከዚህ ከፍ ሊል እንደሚችል ስጋቱን ገልፆል።

ከጥቅምት ወር ጀምሮ ሀገሪቱ ያስተናገደችዉ ከባድ ዝናብ በተለያዩ አካባቢዎች የጎርፍ መጥለቅለቅ እና የመሬት መንሸራተት አስከትሏል።

አሁን አደጋዉ ባጋጠመበት አካባቢ በ ፈረንጆች 2010 የሰዎችን ህይወት የቀጠፈ ተመሳሳይ አደጋ ያጋጠመበት ነዉ ተብሏል።

የሀገሪቱ ባለስልጣናት የአካባቢውን ነዋሪ ከአደጋ ለመጠበቅ ጥረት ቢያደርግም የተሳካ አለመሆኑ ተጠቅሷል።

ዘገባዉ የ ሮይተርስ ነዉ።

ቁምነገር አየለ

ኀዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የህዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በኢትዮጵያ ከ6 መቶ ሺህ በላይ ሰዎች ኤች አይ ቪ በደማቸዉ ዉስጥ ይገኛል ተባለ፡፡

በየዓመቱም ከ7ሺህ በላይ አዳዲስ ሰዎች በቫይረሱ ይያዛሉ ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባካሄደዉ ጥናት በአገራችን ከ6መቶሺህ በላይ ሰዎች ከቫይረሱ ጋር ሲኖሩ፤ ከ10 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ በዚሁ ህመም ምክንያት ህይወታቸዉ ያልፋል፡፡

በተደረገዉ ጥናት መሰረት ከ15 ዓመት በላይ በሆኑ ሰዎች የቫይረሱ የስርጭት ምጣኔ 0.87 በመቶ ሲሆን፤ በዚህ ስሌት መሰረት ነዉ በአገራችን ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ፣ እንደ አዲስ የሚያዙ እና ህይወታቸዉ የሚያልፉ ሰዎች ቁጥር ይፋ የተደረገዉ፡፡

የስርጭት ምጣኔዉ እንደ አገር ከክልል ክልል የሚለያይ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በዚህም ከፍተኛ የስርጭት ምጣኔ ያለባቸዉ ክልሎች አዲስ አበባ፣ ጋምቤላ ፣ ሐረሪ፣ ድሬዳዋ፣ ትግራይ እና አማራ ክልሎች ናቸዉ፡፡

ዝቅተኛ የስርጭት ምጣኔ የታየዉ በሶማሌ ክልል ሲሆን ፤ በክልሉ ያለዉ የስርጭት ምጣኔ 0.17 በመቶ ነዉ ተብሏል፡፡

በክልሎች ዉስጥም በከተማ እና በገጠር ያለዉ የስርጭት ምጣኔ የተለያየ ሲሆን፤ በከተማ 2.9 በመቶ ሲሆን በገጠር ደግሞ 0.4 በመቶ መሆኑን ለማወቅ ችለናል፡፡

በቅርቡ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያደረገዉ ጥናት የአፍላ ወጣት ሴቶች የኤች.አይ.ቪ የስርጭት ምጣኔ 1.7 በመቶ እንደሆነ አሳይቷል።

አፎሚያ አሸናፊ

ኀዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የህዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ተሾሙ

የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው መሾማቸው ታውቋል።

የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ከሕዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳዳር ሆነው መሾማቸው ገልጿል ።

ይሁን እንጅ የት እንደመደቡ አልተገለፀም።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ኀዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…
Subscribe to a channel