በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
የእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ ድልድል ይፋ ሆና !
አርሰናል ከ ኒውካስትል ዩናይትድ የመጀመሪያ ዙር በአርሰናል ሜዳ / መልስ በኒውካስትል ሜዳ
ቶተንሀም ከ ሊቨርፑል የመጀመሪያ ዙር በቶትንሃም ሜዳ / መልስ በሊቨርፑል ሜዳ ደርሷቸዋል።
የመጀመሪያ ዙር - January 6/7 የሁለተኛ ዙር - February 3/4
ፍፃሜ ዌምብሌይ ስታዲየም !
ጋዲሳ መገርሳ
ታኀሣሥ 11 ቀን 2017 ዓ.ም
3ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ዳኞች ማህበር መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በአዲስአበባ ከተማ በኢትዮጵያ ሆቴል አካሂደዋል ።
በጉባኤው ላይ ከ2011-2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በአቶ ቢኒያም ሂወት የማህበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሁም የፋይናንስ ሪፖርት በወይዘሮ ገነት ወርቅነህ ቀርቧል።
ማህበሩ ፕሬዚዳንት እና ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የመረጠ ሲሆን :-
1. አቶ አዲሱ ካሳ -አፋር - ፕሬዝዳንት
2. አቶ ተከተል ተክሌ -አዲስ አበባ - ም/ ፕሬዝዳንት
3. አቶ መላኩ መርመሮ- ሲዳማ - ፀሐፊ
4. አቶ ሰለሞን ወ/ሰንበንት- ድሬዳዋ - ሂሳብ ሹም
5. ወ/ሮ ሎሚ አዱኛ- ኦሮሚያ - ገንዘብ ያዥ
6. አቶ ኤፍሬም ኤልያስ- ደቡብ ኢትዮጵያ - አባል
7. ወ/ሮ ማህሌት ሹሚ -አፋር - አባል በመሆን ተመርጠዋል ።
በጉባኤው ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የፋሲሊቲና የማህበራት ማደራጃ ዳይሬክተር አቶ አሰፋ በቀለ ፣ኢንስትራክተር ሳሙኤል ብርሃኑ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስልጠና ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር ፣የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተሳትፎ እና ውድድር ዳይሬክተር አቶ አስፋው ዳኜ እንዲሁም ከክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ የማህበሩ አመራሮች እና ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝቷል ::
ጋዲሳ መገርሳ
ታኀሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
አማራ ባንክ ያበለፀገዉን አዲስ የዲጅታል ባንኪንግ አገልግሎት በይፋ ስራ አስጀመረ
ባንኩ " አባ ዲጂታል ይበልጥ ወደ እናንተ " በሚል ስታንዳርድ ኪዊአር፣ ከባ ስማርት ፓስ፣ አባ ስኩል ፔይ እና አባ ሞባይል ባንኪንግ በዛሬው እለት ለደንበኞች ማስተዋወቁ ነው የተነገረው።
ባንኩ ያበልጸገውን ፈጣን ምላሽ (QR) መተግበሪያ አባ ኪው አር (ABa QR) በሚል ስያሜ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ዮሃንስ አያሌው በይፋ ስራ አስጀመረዋል፡፡
መተግበሪያዉ ተገልጋዮች ማንኛውንም አይነት ግብይት ሲፈጽሙ የእጅ ስልካቸውን ብቻ ተጠቅመው በግብይት ማዕከሉ የሚገኘውን የነጋዴውን (QR Code) ቅኝት በማድረግ ያለ ጥሬ ገንዘብ ከማንኛውም የባንክ ሂሳባቸው በቀላሉ ክፍያ መፈጸም የሚችሉበት ነዉ ተብሎል ፡፡
በተጨማሪም በአባ ስኩል ፔይ ወላጆች የልጆቻቸውን የትምህርት ክፍያ መከታተል እና መቆጣጠር የሚችሉ ሲሆን ከመረጡት ባንክ ወይም እንደቴሌ ብር ካሉ የዋሌት ሂሳባቸውን በጊዜው መፈጸም የሚችሉበትን አማራጭ አማቅረቡም ተሰምቷል።
ባንኩ ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ሳፋሪ ኮም፣ ከብሔራዊ ስዊች፣ ከፋይናንስ ቴክኖሎጂ አቅራቢዎች፣ ክፍያ አመቻቾችና ገቢዎች ሚኒስቴር ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑ አስታዉቆል
አቤል እስጢፋኖስ
ታኀሣሥ 10 ቀን 2017
ሊባኖስ የእስራኤል ጦር በየቀኑ የተኩስ አቁም ስምምነቱን እየጣሰ ነዉ አለች
የሊባኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናጂብ ሚካቲ እስራኤል የገባችዉን ስምምነት አልፎ አልፎ እየጣሰች ነዉ ሲሉ ወቅሰዋል፡፡
ከተርክየዉ ፕሬዝዳንት ጋር መግለጫ የሰጡት ሚካቲ ስምምነቱ ከተደረሰ 3 ሳምንት ቢቆጠርም አሁንም ግን በእስራኤል በኩል ሲጣስ እየተመለከትን ነዉ ብለዋል፡፡
የእስራኤል ጦር ከሊባኖስ ምድር ሙሉ በሙሉ መዉጣት እንዳለበትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
ቴል አቪቭ የተኩስ አቁም ስምምነቱን እንድታቆምም ጠይቀዋል፡፡
በሊባኖስ ተቀስቅሶ የነበረዉን የእስራኤል ሄዝቦላ ጦርነት ለማስቆም የ60 ቀናት የተኩስ አቁም ስመምነት ላይ መደረሱ የሚታወስ ነዉ፡፡
አባቱ መረቀ
ታኀሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
የነገ የታኅሣሥ 11 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ፕሮግራሞቻችን
Читать полностью…በብሔራዊ ጥቅሞች ላይ መገናኛ ብዙሃን ከፍተኛ ጥንቃቄ እና ኃላፊነት በተመላበት መልኩ ሊሰሩ ይገባል አሉ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር ተገኘ ወርቅ ጌቱ (ዶ/ር)
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት "የመገናኛ ብዙሃን ሚና በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን" በሚል ርዕስ ጥናታዊ ፅሁፍ በማቅረብ የአጀንዳ ልየታ ለማድረግ ከመገናኛ ብዙሃን ከተወከሉ ባለሞያዎች ጋር በዛሬው ዕለት ውይይት ጀምሯል፡፡
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽር (ዶ/ር) ተገኘ ወርቅ ጌቱ ባደረጉት ንግግር በኦሮሚያ ክልል እየተደረገ ያለው የአጀንዳ ልየታ እንደተጠናቀቀ ከአማራ እና ትግራይ ክልሎች ውጪ በሌሉች ክልሎች እንደሚካሄድ ጠቅሰው፡፡በሁለቱ አካበቢዎች ግን ምቹ ሆኒታ እንደተፈጠረ ወዲያው ወደ ተግባር ይገባል ብለዋል፡፡
የመገናኛ ብዙሃን በተለይ እንዲህ ባሉት ሀገራዊ ጥቅችን በሚያስጠብቁ ሆነቱች ላይ አይነተኛ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባልም ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡
ሀገራዊ ምክክር ሂደቱ አካታችና አሳታፊ እንዲሆን መገናኛ ብዙሃን የምክክሩን አስፈላጊነትና ምንነት ላይ ግንዛቤ በመፍጠር እያደረጉ ያለው አስተዋጽኦ የሚበረታታ እንደሆነ ገልጸዋል።
በቀጣይም ብሔራዊና የህዝብ ጥቅምን በማስቀደም ገለልተኛ በሆነ መንገድ ለሀገራዊ ምክክሩ መሳካት የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።
የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ሊቀመንበር አቶ አማረ አረጋዊ ‹‹ ሚዲያው በብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ላይ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ጠቅሰው፡፡ ከምንም በላይ ግን ከውጤቱ የበለጠ አካሄዱ ላይ ጥንቃቂ እና ሙያዊ ስምግባር በጠበቀ መልኩ ስራዎች መሰራት ይገባል ብለዋል፡፡
በየደረጃው ያሉ አካላትም ጋዜጤኞች ከስጋት እና ከፍረሃት ነፃ ሆነው እንዲሰሩ ማድረግ ተገቢ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ይህ የምክክር መድረክ በነገው እለትም እንደሚቀጥል ከአዘጋጁቹ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ታኀሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
የመጀመሪያው ዓመታዊ የአየር ንብረት ለውጥ የፋይናንስ ጉባኤ ተካሄደ።
ጉባኤዉ ኢትዮጵያ ከአየር ንብረት ለዉጥ ጋር ተያይዞ እየተጋፈጠችዉ ባለዉ ችግር በመረዳት ያሉ የፋይናንስ አቅምን ክፍተቶችን ለመሞላት ያለመ ነዉ።
የአየር ንብረት ለዉጥ የፋይናንስ ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ ሲካሄድ የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ ተጠሪ ተቋማት ÷ ÷ የፋይናንስ ተቋማት እንዲሁም የአለምአቀፍ አጋር አካላት በተገኙበት የዉይይት መድረክ ተካሂዶበታል።
ኤፍ ኤስ ዲ ኢትዮጵያ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም ያዘጋጀው ይህ ጉባኤ በአየር ንብረት ለዉጥ ዙሪያ ያሉ የፋይናንስ ክፍተቶችን ለመሙላት እና ሀብት የማሰባሰብ አቅጣጫን ለመቅረፅ የሚያስችል ነዉ ተብሏል።
ይህን የአየር ንብረት ለዉጥ ላይ የሚወጡ ኘሮጀክቶች የሚቀረፁበት መንገድ ማስተካከል ለሀብት ለማሰባሰብ የሚቻልበትን እድል ያሰፋል የሚሉት የኤፍ ኤስ ዲ ኢትዩጵያ ዋና ዳይሬክተር ሂክመት አብደላህ ናቸዉ።
በግሉ ዘርፍ ለዚህ አላማ ፍላጎት እንዲኖር ማስቻል ያስፈልጋል የሚሉት ዋና ዳይሬክተሯ በመንግስት በኩል የፖሊሲ አሰራሮች እንዲኖሩ ማስቻል ይገባል ብለዋል።
በየአመቱ ይደረጋል የተባለዉ ይህ የአየር ንብረት ለዉጥ የፋይናንስ ጉባኤ በአለምአቀፍ የኮፕ ስብሰባዎች ላይ ቃል የተገቡ ጉዳዩችን ወደ ኢትዮጵያ የማምጣት እቅድ አለ ተብሏል።
ይህን ቃል የተገቡ ጉዳዩችን ወደ አፍሪካ ብሎም ወደ ኢትዩጵያ ለማምጣት ዝግጁነት የሚያስፈልግ ስለሚሆን ይሄ ጉባኤም እሱን የማሳካት አላማ እንደያዘ ለማወቅ ተችሏል።
ቁምነገር አየለ
ታኀሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
በፋይናንሱ ሴክተር የሚታየውን የሰለጠነ የሰው ሀይል ክፍተት ለመፍታት የሚያስችል የስልጠና ተቋም በይፋ ስራ ጀመረ
ናሽናል ፋይናንስ አከዳሚ፤ በፋይናንሱ ዘርፉ በተለይም በኢንሹራንስ ኢንዳስትሪ የአጭርና ረጅም ስልጠና ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ተገልጿል።
ናሽናል ፋይናንስ አከዳሚ በዚህ ዘርፍ እውቅና በማግኘትም የመጀመሪያውና ብቸኛው ተቋምም ሆኗል።
አካዳሚው የተቋቋመውም የፋይናነሱን ሴክተር የሰው ሃብት ፍላጎት ለመሙላት ልዩ ትኩረት እድርጎ የሚሰራ ከፍተኛ ትምህርት ተቋምም ሆነ የስልጠና ተቋም ባለመኖሩ ነው ሲሉም የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር መሰሉ አለሜ ተናግረዋል።
በመሆኑም ይህንን ክፍተት መሰረታዊ በሆነ መልኩ ለመሙላት የሚያስችል በኢንሹራንስ ዘርፍ የረጅም ጊዜ ስለጠና ማለትም "Professional Diploma in Insurance" ለመሰጠት የሚያስችል እውቅና አግኝቶ ስልጠና ለመጀመር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡
ለዚህ ስልጠና ማንኛውም የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው ሰው መሳተፍ እንደሚችልም ተነስቷል።
ይሀም ናሽናል ፋይናንስ አከዳሚን በኢንሹራንስኢንዳስትሪ የአጭርና ረጅም ስለጠና ለመስጠት እውቅና ያገኘ የመጀመሪያውና ብቸኛው ተቋም ያደርገዋል።
ተቋም በኢንሹራንስ ዘርፍ አሁን ላይ ማሰልጠን ቢጀምር በቅርቡ ደግሞ በባንክ እና በማይክሮ ፋይናንስ ዘርፍ ማሰልጠን እንደሚጀምሩም ነግረውናል።
ለዓለም አሰፋ
ታኀሣሥ 10 ቀን 2017
ሶሪያ ከዚህ በኋላ የግጭት አምባ እንደማትሆን የአማፅያን መሪው ተናግሯል
የሶሪያ አማፅያን መሪው አህመድ አል ሻራ አገሪቱ ለማንም ስጋት አትሆንም ግጭትም አንፈልግም ብሏል
ላለፊት በርካታ አመታት ደማስቆ የሰቆቃ ምድር መሆኗን ያስታወሰው አል ሻራ ከዚህ በኋላ ትኩረታችን ሠላም ላይ መስራት ነው ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል።
አገሪቱ ብዝሃነቷ ተጠብቆላት ዜጎችም በነፃነት የሚኖሩበት ሁኔታን ለመፍጠር እንደሚሰራም ቃል ገብቷል።
ሶሪያ በታሊባን እንደምትገዛው አፍጋኒስታን የምትሆንበት ምንም ምክንያት እንደሌለም አስታውቋል።
በተለይም ደግሞ ሴቶቾ የመማር ነፃነታቸውን እናከብራለን ነው ያለው።
ከጎረቤቶቻችን አገራት ጋርም በሠላም የመኖር ፍላጎት አለን ሲል መሪው ተናግሯል
አባቱ መረቀ
ታኀሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሚወሰኑ የፍቺ እና ጉዲፈቻ ውሳኔዎች በይፋ አገልግሎት መጀመራቸዉ ተገለጸ፡፡
በፍርድ ቤቶች የምዝገባው አገልግሎት በይፋ በአራዳ እና ቦሌ ምድብ ችሎቶች መጀመሩም ተሰምቷል፡፡
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከሚመዘግባቸው ኩነቶች መካከል በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔ የሚሰጥባቸው ጉዲፈቻ እና ፍቺ በፍርድ ቤቶቹ መመዝገብ መጀመራቸዉ ተገልጿል፡፡
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ፤ በአንድ ማዕከል አገልግሎቱ ከፍቺ እና የጉዲፈቻ ምዝገባ አገልግሎት በተጨማሪ የፋይዳ ምዝገባ በፍርድ ቤቶቹ እንደሚከናወን ጠቅሰዋል፡፡
በዕለቱ መርሃ ግብር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ-አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፣ የፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ፉዓድ ኪያር፣ የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል እንዲሁም የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ተገኝተዋል።
አፎሚያ አሸናፊ
ታኀሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
በግጭት ውስጥ ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው ያሉ ሴቶች ችግራችን በሀገራዊ ምክክሩ መፍትሔ ያገኛል ብለን እንጠብቃለን ሲሉ የኦሮሚያ ክልል የሴት ተወካዮች ተናገሩ ።
በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ባለው የምክክር መድረክ ላይ ኢትዮ ኤፍ ኤም ያነጋገራቸው የሴት ተወካዮች ምክክሩ በሴቶች ላይ የሚፈፀመው በደል ይፈታል ብለን እንጠብቃለን ብለዋል ።
በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች ባሉ ግጭቶች ቀዳሚ ተጠቂዎች ሴቶች መሆናቸውን የነገሩን የሴት ተወካዮቹ ፤ግጭቶች በምክክር ተፈተው በሴቶች ላይ ያሉ በደሎች ያበቃሉ ብለን እንጠብቃን ሲሉ ለጣቢያችን ተናግረዋል ።
ግጭት ባለባቸው የኦሮሚያ አከባቢዎች ሴቶች እየተጎዱ መሆኖቸውን ተሳታፊዎቹ አስረድተዋል።
አሁን የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር ከዚህ በፊት ለተፈፀሙና እየተፈፀሙ ላሉ በደሎች መፍትሔ ይሰጣል ብለን እንጠብቃለን ብለዋል።
ከዚህ በፊት በሴቶች ላይ ይደርሱ የነበሩ የፖለቲካ፣የኢኮኖሚና የማህበራዊ መገለሎች እንዲያበቁ ሴቶችም በፖለቲካ እንዲሳተፉ ምክክሩ ይረዳል ብለን እናስባለን ሲሉ ነግረውናል።
ልዑል ወልዴ
ታኀሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
የነገ የታኅሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ፕሮግራሞቻችን
Читать полностью…አጎዋ የሚራዘም ከሆነ ኢትዮጵያ ፖለቲካዋን መቃኘት ያስፈልጋታል ተባለ
አጎዋ የሚራዘም ከሆነ ኢትዮጵያ ወደ ገበያው ለመመለስ ፖለቲካዋን መቃኘት ያስፈልጋታል ሲሉ የኢንቨስትመንትና የቢዚነስ አማካሪ የሆኑት አቶ ይርጋ ተስፋዬ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ነግረውናል።
አማካሪው ኢትዮጵያ ከአጎዋ እንድትወጣ የተደረገው ከንግድ ጋር በተገናኘ ሳይሆ በፖለቲካ አማካኝነት ነው ብለውናል።
ይሁን እና አግዋ እንደ አውሮፓውያኑ በግንቦት 18 በ2000 ዓ.ም በአሜሪካ ኮንግረንስ የጸደቀ ሲሆን በ2025 ክለሳ እንደሚደረግበት በህጉ ሰፍሯል ።
አቶ ይርጋ ታዲያ ኢትዮጵያ ገበያው የሚራዘም ከሆነ ከአዲሱ የአሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ጋር አበክራ መስራት እንደሚገባትና አለም ኢትዮጵያን የሚመለከትበት መነፅር እንዲቀየር መስራት እንደሚገባ ተነግሯል፡፡
የአፍሪካ ዕድገት እና ዕድል ድንጋጌ (አግዋ) በአሜሪካ የተቀመጠውን መስፈርት የሚያሟሉና ከሰሃራ በታች ለሚገኙ አገራት ምርቶቻቸውን ከቀረጥ ነጻ ለአሜሪካ ገበያ እንዲያቀርቡ የሚያስችል ዕድል ወይም ችሮታ ነው።
ኢትዮጵያ በገበያው በርካታ ጠቀሜታ አግኝታ ነበር የተባለ ሲሆን በዛውም ልክ ከገበያው በመታገዷ ከፍተኛ ኪሳራ ገጥሟት ነበረም ብለውናል።
አማካሪው በመደምደሚያ ሃሳባቸው እንዲህ ያሉ እድሎች ሲገኙ ለኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ጠቃሚ ነው ያሉ ሲሆን በየትኛውም ቦታ፣ጊዜና ሁኔታ ከስጋት ለመዳን ግን በአለም ገበያ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቀጠል በምርትና አገልግሎት ጥራት ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የሰሜኑን ጦርነት ተከትሎ የፕሬዝዳንት ባይደን አስተዳደር የአገዋ ዕድል ተጠቃሚ የነበረችውን ኢትዮጵያን ማገዱ አይዘነጋም፡፡
ልዑል ወልዴ
ታኀሣሥ 9 ቀን 2017 ዓ.ም
የመንበረ ጸባዎት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከጥር 6/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል ተባለ
ታሪካዊ ይዘቱን ጠብቆ ዕድሳት ሲደረግለት የቆየው ካቴድራሉ በመጪው ወር ጥር 6/2017 ዓ.ም ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን በዛሬው ዕለት በተሰጠው መግለጫ ተገልጿል ።
መግለጫውን የሰጡት የካቴድራሉ ዋና አስተዳዳሪ ሊቀ ሥልጣናት አባ ሳራክ አድማሱ
እድሳቱ ወደ መጠናቀቁ ይገኛል በለዋል ።
ታቦተ ህጉም በጥር 6/2017 ዓ.ም ወደ መንበረ ክብሩ እንደሚመለስ አስታውቀዋል ።
የካቴደራሉን ምርቃት ዕዉን ለማድረግ ለተቋራጭ ድርጅቱ ያልተከፈለውን 47 ሚሊዮን ብር ዕዳ እንዲከፈል ምዕመናን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
ከምርቃቱ አስቀድሞ ባሉ ቀናት የምስጋናና የተለያዩ ባዛር እንዲሁም ጉባኤዎች እንደሚካሄዱም ተነግሯል ።
የዕድሳት ሥራው ታሪካዊ ይዘቱን ጠብቆ እንደተከናወነም ተገልጿል ።
ካቴደራሉ ከአክሱም ፅዮን ቀጥሎ ሁለተኛው ቅዱስ ስፍራና የሊቃነ ጳጳሳት ሹመትና ሲመተ በዓል የሚካሄድበት ቅዱስ ስፍራ ነው ተብሏል ።
የአርበኞችና፣የጥበብ ሰዎች የቅዱሳን ማረፊያም ነው።
ይህንን ታላቅ ካቴድራል መጠበቅ የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው አስታውቀዋል ።
አባቱ መረቀ
ታኀሣሥ 9 ቀን 2017 ዓ.ም
ማትያስ ፖግባ የሶስት አመታት የእስር ፍርድ ተላለፈበት !
ማትያስ ፖግባ የፈረንሳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፖል ፖግባ ወንድም የሶስት አመታት እስራት ፍርድ እንደተላለፈበት ተገልጿል።
በቡድን ከተደራጁ ሰዎች መካከል ወንድሙ አንዱ እንደነበረ ተገልጾ የነበረ ሲሆን ፖል ፖግባ በወቅቱ 13 ሚልዮን ዩሮ እንደጠየቁት አሳውቆ ነበር።
ከሁለት አመታት በፊት ፖል ፖግባ ዝርፊያ እና የተለያዩ ማስፈራሪያዎች በቡድን ከተደራጁ ሰዎች እንደደረሰበት ተናግሮ ነበር።
አሁን ላይ በድርጊቱ የተሳተፈው የፖል ፖግባ ወንድም በድርጊቱ ጥፋተኛ ሆኖ መገኘቱን ተከትሎ የሶስት አመት እስር እንደተፈረደበት ተነግሯል።
በወቅቱ ጓደኞቹ ፖግባን ወደ ቤታቸው በመጥራት እውቅናን ካገኘ በኋላ በገንዘብ እየረዳቸው እንዳልሆነ ገልፀው ገንዘብ ስጠን ማለታቸውንም ተናግሮ ነበር።
ጋዲሳ መገርሳ
ታኀሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
ዎልቭስ አሰልጣኝ ቪቶር ፔሬራ ሾመ !
በቅርቡ አሰልጣኝ ጋሪ ኦኔልን ያሰናበተው ዎልቭስ በምትኩ አዲስ አሰልጣኝ መሾማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።
ዎልቭስ ፖርቹጋላዊውን አሰልጣኝ ቪቶር ፔሬራ ከሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ሻባብ በመውሰድ በሀላፊነት ሾመዋል።
የ 56ዓመቱ አሰልጣኝ ቪቶር ፔሬራ ዎልቭስን ለአንድ አመት እና ስድስት ወራት ለማሰልጠን ፊርማቸውን ማኖራቸው ተነግሯል።
ጋዲሳ መገርሳ
ታኀሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
ከ7ሺህ በላይ ተሳታፊዎች የተሳተፉበትና በአዳማ ከተማ ላለፉት አራት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የህብረተሰብ ክፍሎች የምክክር መድረክ ተጠናቀቀ
የህብረተሰብ ክፍሎች የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ መጠናቀቁን አስመልክቶ ኮሚሽነር አምባዬ ኦጋቶ እና ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።
በኦሮሚያ ክልል የምክክር ሂደት የህብረተሰቡ የመደማመጥና የመወያየት ፍላጎት የሚደነቅ ነው ሲሉ ኮሚሽነር አምባዬ ኦጋቶ ተናግረዋል።
በምክክሩ ሂደት ሁሉም ድምፆች ሲደመጡ፣ አንዱ የሌላውን ሀሳብ ሲያዳምጥ ተመልክተናል፣ ይህም ምክክሩ ያዳበረው የዴሞክራሲ ባህል ነው ብለዋል።
በምክክሩ ሂደት ጠለቅ ያሉ የአጀንዳ ግብአቶች ተነስተዋል ያሉት ኮሚሽነሩ፤ የክልሉንና የሀገሪቱን ሰላም ሊያመጡ የሚችሉ አጀንዳዎች መቅረባቸውንም ተናግረዋል።
ተወካዮች ሲመረጡ በግልጽና በዴሞክራሲያዊ መንገድ መከናወኑ ትልቅ ትምህርት መሆኑንም ኮሚሽነሩ አስረድተዋል።
ከሎጂስቲክስ አኳያም ከ7ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ከመላው ኦሮሚያ ተጓጉዘው አዳማ መገኘታቸውና መስተናገዳቸው ትልቅ ስኬት ነው ተብሏል፡፡
ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ በበኩላቸው ግጭት በነበረባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ምክክር ማድረጋቸው ለሌሎች ክልሎችም ትምህርት የሚሰጥ ነው ብለዋል።
የምክክር ሂደቱ ለመግባባት፣ ለመተማመን እና ምክክርን ባህል ለማድረግ ተግባራዊ ትምህርት እንደተገኘበትም አብራርተዋል።
ልዑል ወልዴ
ታኀሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
ገዳ ባንክ በበጀት አመቱ ከታክስ በፊት 101 ሚሊዮን ብር አትርፍያለው አለ፡፡
ባንኩ በፈረንጆቹ 2023-24 790 ሚሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡
ይህም ከባለፈው ተመሳሳይ አመት ጋር ሲነፃጸር የ609 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተጠቅሷል፡፡
የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ የገንዘብ መጠኑ 4 ቢሊዮን መድረሱም ተገልጿል፡፡የደንበኞቹን ቁጥርም ወደ 2 መቶ 88 ሺ 174 ከፍ ማድረጉ ተነግሯል፡፡
እንዲሁም ባንኩ 25 አዳዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈት የቅርንጫፎቹን ብዛት ወደ 85 ከፍ ማድረጉ ተነስቷል፡፡
ገዳ ባንክ በበጀት አመቱ 2.9 ሚሊዮን ብር ብድር መስጠት መቻሉም ሰምተናል፡፡
ባንኩ እስካሁን 42 ሺ 930 የሚሆኑ የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ ማፍራት መቻሉን የባለ አክሲዮኖች ሶስተኛ መደበኛ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት ገልጿል።
ሐመረ ፍሬው
ታኀሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
"ኑ ቤታችንን እንስራ " ብሏል ጌርጌሴኖን የአእምሮ ህመማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል
ላለፉት 19 አመታት የአእምሮ ህመማንን ሲረዳ የቆየው ጌርጌሴኖን የአእምሮ ህመማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል ከጊዜ ወደ ጊዜ የህሙማኑ ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ከፍተኛ የቦታ ጥበት እንደገጠመው የማዕከሉ መስራች ሊቀ ህሩያን መለስ ገልጸዋል፡፡
ይህንን የቦታ ጥበት የተመለከተው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቦታ ድጋፍ በማደረጉ ጊዜያዊ መጠለያ በመስራት የህንጻ ግንባታ ቢጀምርም ከፍተኛ የሆነ የግንባታ እቃዎች መወደድ እና የአቅም ማነስ ተዳምሩ ስራዎችን በፍጥነት መስራት እንዳቃታቸው ተናረዋል፡፡
ሊቀ ህሩያን መለስ ማዕከሉ በዚህ ሰአት 700 የሚደርሱ የአእምሮ ህመማን ተቀብሎ መጠለያና ድጋፍ እየሰጠ መሆኑን ገልጸው አዲሱ ህንጻ ተገንብቱ ሲጠናቅቅ ድጋፍ የሚሰጣቸውን ህሙማን ቁጥር ወደ 5000 ለማሳደግ እቅድ አለን ብለዋል፡፡ ይሄንን ለማሳካት መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል፡፡
#ለጌርጌሴኖን የአእምሮ ህመማን #መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል ድጋፍ ማድረግ ለምትሹ
በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000649044183
በአቢሲኒያ ባንክ 1219 ወይም 1998
ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 1026600059494
በቴሌ ብር 500464 መጠቀም ትችላላችሁ
አፎሚያ አሸናፊ
ታኀሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
ፑቲን ለትራምፕ ዝግጁ ነኝ አሉ
የሩሲያዉ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተመራጩን የአሜሪካ ቀጣይ ፕሬዝዳንተ ዶናልድ ትራምን ለማግኘት ዝግጁ ነኝ ብለዋል፡፡
ከትራምፕ ጋር የምገናኝበትን ጊዜ ባላዉቀዉም ግን በፈለገበት ጊዜ ለመነጋገር ተዘጋጅቻለሁ ነዉ ያሉት፡፡
ትራምፕ የት እንድንገኛኝ እንደሚፈልግ አልነገረኝም ያሉት ፑቲን እኔ ግን የትም ይመቸኛል ማለታቸዉ ተሰምቷል፡፡
ላለፉት አራት አመታት ከዶናልድ ትራምፕ ጋር አዉርተዉ እንደማያዉቁም ፑቲን አንስተዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ፑቲን የ2024 አመት ከመጠናቀቁ በፊት ከጋዜጠኞች ጋር የመጨረሻዉን ቃለ ምልልስ ማድረጋቸዉን ታስ ዘግቧል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ በዩክሬኑ ጦርነት ዙሪያ ለመምከር ከፑቲን ጋር መነጋገር እንደሚፈልጉ መናገራቸዉ የሚታወስ ነዉ፡፡
ይሁን እንጅ ለበዓለ ሲመታቸዉ የቻይናዉን ፕሬዝዳንት ሲጋብዙ ፑቲንን አልጠሯቸዉም፡፡
አባቱ መረቀ
ታኀሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
እናት ባንክ ለእናቴ የስነ ፅሁፍ እና የአመቱ ድንቅ እናት የተሰኘ ዉድድር ማዘጋጀቱን አስታወቀ።
የአመቱ ድንቅ እናት ዉድድሩን ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲሆም ለእናት የተሰኘ ሀገራዉ የስነ ፁሁፍ ዉድድርን ለሁለተኛ ጊዜ ሊያወዳድር እንደሆነ በዛሬዉ እለት ይፋ አድርጓል።
የባንኩን ማህበራዊ እሴት ማዕከል ያደረጉ ሁለት ሀገር አቀፍ የውድድር መረሐ ግብሮችን ይፍ ሲያደርግ ባንኩ ለሀገርም ሆነ ለቤተሰብ ምሰሶ ለሆኑት የኢትዮጵያ እናቶች መታሰቢያ ይሆኑ ዘንድ እናት ተኮር ውድድሮች መሆናቸው ተነግሯል ።
በተመሳሳይ ለእናቴ በተሰኘው የጽሑፍ ውድድር ላይም ስለእናታቸው የሚያጋሩት ፍቅርን እና ስሜት ዳኞች አወዳድረው የሚያበላልጡበት ሳይሆን ተወዳዳሪዎች ለእናታቸው ያላቸውን ፍቅር እና አክብሮት እንዴት እንደገለፁ ስሜታቸውን ለሌሎች ለማጋባት እንዴት እንደጣሩ የሚዳኝበት መሆኑን አስታውቀዋል።
ውድድሩ የሚቆይበት ጊዜ ከታህሳስ 14 እስከ ጥር 14 ቀን 2017ዓ.ም ሲሆን ተወዳዳሪዎች ስራዎቻቸውን አቅራቢያቸው በሚገኙ የእናት ባንክ ቅርንጫፎች እና ከኢትዮጵያ ውጪ ያሉ ደግሞ በኢሜል አድራሻ ማስረከብ ይችላሉ ።
ሊዲያ ደሳለኝ
ታኀሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
እንደ ኖክና፤ ኦይል ሊቢያ ያሉ የነዳጅ አዳዮች በጎንደር ከተማዉ ሙሉ ለሙሉ ቤንዝል እያቀረቡ አይደለም ተባለ፡፡
የጎንደር ከተማ ንግድ ቢሮ ማግኘት ከሚገባዉ የቤንዚን አቅርቦት 20 በመቶ ብቻ እያገኘ መሆኑን ገለፀ።
የጎንደር ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ሀላፊ አቶ ቴዎድሮስ፤ ለጣቢያችን እንደተናገሩት የነዳጅ ዕጥረቱ ላለፉት 8 ወራት የተከሰተ እንደሆነና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰበት እንደመጣ ተናግረዋል።
የቤንዝል እጥረቱ ለከተማዋ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት እያመጣ እንደሆነም ገልፀዋል።
የፀጥታ ችግር መፈጠሩ ዋነኛ ምክንያት ነዉ ያሉን አቶ ቴዎድሮስ፤
በሌላ በኩል ወደ ከተማዋ ነዳጅ የሚያመጣ ቦቴ ከጅቡቲ ለመምጣት በትንሹ ከ 24 ቀን እስከ 30 ቀን እንደሚፈጅበት ገልፀዋል፤
ይህንንም በተደጋጋሚ ለነዳጅና ኢነርጅ ባለስልጣን ቅሬታ ማቅረባቸውን ነግረውናል።
ከተማዉ ላይ ያሉ ማደያዎች ለአጎራባች ወረዳዎችም የቤንዚን አገልግሎት እንደሚሰጡ የገለፁት ሃላፊው፤ በቂ ቤንዝን ባለመኖሩ ተሽከርካሪዎችንና እንቅስቃሴዉን እያዳከመ እንደሆነ ገልፀዋል።
እንደ ኖክና ኦይል ሊቢያ ያሉ የነዳጅ አዳዮች ባልታወቀ ምክንያት ለከተማዉ ሙሉ ለሙሉ ቤንዝል ለማቅረብ ፍቃደኛ አለመሆናቸውን ተናግረዋል።
አሁንም ቢሆን ተደጋጋሚ ጥያቄ እያቀረብን ነዉ ያሉን የንግድ ቢሮዉ ሀላፊዉ ፤በትንሹም ቢሆን ከተማዉ ላይ የደረሰዉን ቤንዝን ሙያተኞችን ይዘን ለተጠቃሚዉ እያደረስን እንገኛልን ብለውናል።
ሊዲያ ደሳለኝ
ታኀሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
በአማራ ትግራይ እና ኦሮሚያ ክልሎች የተከሰተው የግሪሳ ወፍ ወረርሺኝ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለ ተነገረ
በአማራ፤ ትግራይ እና ኦሮሚያ ክልሎች የተከሰተው የግሪሳ ወፍ ወረርሺኝ በአውሮፕላን በታገዘ የኬሚካል ርጭት በመታገዝ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የግብርና ሚኒስቴር የዕፅዋት ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ በላይነህ ንጉሴ ለጣቢያችን እንደተናገሩት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና ደቡብ ወሎ ዞኖች በኦሮሚያ ክልል ዝዋይ እንዲሁም በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች በመንጋ ደረጃ በተከሰቱት ወፎች ላይ የመከላከል ስራ በመሰራቱ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለ ገልፀዋል ።
የፌደራል እና የክልል መንግስታት በመቀናጀት ጉዳት ከመድረሱ በፊት አፋጣኝ የአውሮፕላን የኬሚካል ርጭት እርምጃ የወሰዱ ሲሆን፥ የቀሩት ደግሞ በአርሶ አደሩ የመከላከል አቅም መጥፋት የሚችሉ መሆናቸውን አስታውቀዋል ።
አርሶ አደሩ እንደዚህ አይነት ክስተቶች ሲያጋጥመው የአውሮፕላን የኬሚካል ርጭት ብቻ ከመጠበቅ በባህላዊ መንገድ የመከላከል አቅሙን ማዳበር እንደሚገባው ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
አቤል እስጢፋኖስ
ታኀሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
በአመት ለ2መቶ ሺ ደንበኞች ብድር ሰጥቻለው ሲል ስንቄ ባንክ ገለፀ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ሪፖርት እንደሚሳየው ደግሞ፤ በመቶ አመት ታሪክ በኢትዮጵያ ያሉ ባንኮች አጠቃላይ የሰጡት ብድር 3መቶ ሀምሳ ሺ ገደማ ነው ።
ሪፖርቱ እንዳመለከተው ይህ ቁጥር ማይክሮ፤ ፋይናንሶችን እና ሌላ ተቋማትን ሳይጨምር ነው።
የስንቄ ባንክ በዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ነዋይ መገርሳ በኩል ለጣቢያችን እንዳሉት ስንቄ ባንክ በ12 ወራት ለ2 መቶ ሺ ደንበኞች የብድር አገልግሎት ሰጥቻለው ብሏል።
በዚህም በባንኮች ታሪክ ከፍተኛውን ብድር መስጠታቸውን ነው አቶ ነዋይ የገለፁት።
ስንቄ ባንክ ከተቋቋመ ሶስት አመቱን ሊይዝ ሲሆን ለ1.1 ሚሊየን ደንበኞችም ብድሮችን መስጠቱን ገልጿል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው ስንቄ ባንክ አሁን ላይ በሀገሪቱ ካሉ ባንኮች 6ተኛ ደረጃን እንደያዘም ነግረውናል።
ለአለም አሰፋ
ታኀሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
በመዲናዋ ህገወጥ የከብት እርዶች እየጨመሩ ነዉ ተባለ።
በአዲስ አበባ ከተማ ከህገወጥ እርድ ጋር በተያያዘ በተደረገ ቁጥጥር ከ3 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ ስጋ መወገዱን ሰምተናል።
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በበጀት አመቱ አምስት ወራት ከአጋር የቁጥጥር ተቋማት ጋር በመሆን ታርዶ የተወረሰዉን ስጋ ማስወገዱን የተቋሙ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አታክልቲ ገ/ ሚካኤል ነግረዉናል።
ተቋሙ በጥቅምት ወር ብቻ ተደርጓል በተባለ ቁጥጥር 708 ኪ.ግ የበሬ እና 261 ኪ.ግ የበግና የፍየል ስጋ በህገ ወጥ መንገድ መታረዱን እና ማስወገድ መቻሉን ገልፀዋል።
የመጀመሪያው ሩብ አመት ጨምሮ 3774 ኪሎ ግራም ስጋ ከህገወጥ እርድ ተይዞ መወገዱን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊዉ አሳዉቀዋል።
የቁጥጥር ሂደቱ ይህን ህገ ወጥ ስራ የሚያከናውኑ አካላት ከድርጊታቸው የማይቆጠቡ ከሆነ ንግድ ፍቃዳቸውን በማሰረዝና ወንጀል መቅጫ ህግ መሰረት ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ከዚህ ቀደመ ህገወጥ እርድ የሚፈፅሙ አካላት ላይ የሚጣለው ቅጣት መሻሻሉንም የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታውቋል ።
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ይህንን ለመቀነስ ከሌሎች ተቋሞች ጋር በቅንጅት በመስራት በተሰጠው ስልጣን መሰረት በህገ ወጥ መንገድ ታርዶ የተወረሰውን ስጋ የማስወገድ ተግባር እያከናወነ ይገኛል ተብሏል።
ህብረተሰቡ በእንስሳት ሃኪም ተመርምሮ በህጋዊ ቄራዎች የታረደ መሆኑን እና ስጋው ላይ የማረጋገጫ ማህተብ መኖሩን ልብ ማለት ያስፈልጋል ሲል ድርጅቱ አሳዉቋል።
ቁምነገር አየለ
ታኀሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
በሀረር፣ ጅግጅጋ እና ሌሎች የምስራቅ ኢትዮጵያ ከተሞች ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገለፀ
በሀረር፣ ጅግጅጋ እና ሌሎች የምስራቅ ኢትዮጵያ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡
ከድሬዳዋ ቁጥር ሁለት - ሀረር- ጅግጅጋ የተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ባልታወቀ ምክንያት ኃይል ማስተላለፍ ማቋረጡን የምስራቅ አንድ ሪጅን የኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች መምሪያ ገልጿል።
የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ ወርዲ መሐመድ፤ በተከሰተው ችግር ምክንያት በሀረር፣ ጅግጅጋ እና በሌሎች የምስራቅ ኢትዮጵያ ከተሞች ኃይል ተቋርጧል ብለዋል።
ችግሩን ለመለየት ፍተሻ መጀመሩን የተናገሩት ዳይሬክተሩ፤ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩን በመጠገን አገልግሎቱን ዳግም ለማስቀጠል ይሰራል ነው ያሉት።
በኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ላይ የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትግዕስት እንዲጠብቁ ኃላፊው መጠየቃቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መረጃ ያመለክታል።
ታኀሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግሥት እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሽርክና ያቋቋሙት የኮንጎ አየር መንገድ ሥራ ጀመረ።
የኮንጎ አየር መንገድ በሁለት ቦይንግ 737 አውሮፕላኖች በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውስጥ ባሉ ሰባት ኤርፖርቶች በረራ በማድረግ አገልግሎት መጀመሩን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋ ያደረገው ትናንት ማክሰኞ ነው።
በኮንጎ አየር መንገድ ውስጥ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 49 በመቶ፣ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግሥት 51 በመቶ ድርሻ አላቸው።
ሁለቱ ሸሪኮች የተፈራረሙት ሥምምነት የአውሮፕላን ኪራይ እና አጠቃላይ ቴክኒካዊ ድጋፍን እንደሚያጠቃልል የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል።
በስምምነቱ መሠረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዜጎች የአውሮፕላን አብራሪዎች፣ የበረራ አስተናጋጆች፣ የአገልግሎት ሠራተኞች እና የቴክኒክ ባለሙያዎች እንዲሆኑ ያሰለጥናል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ታኀሣሥ 9 ቀን 2017 ዓ.ም
ኢትዮጲያ ክሪፕቶ ከረንሲን መጠቀም የሚያስችላትን ህግ ልታወጣ ትችላለች ተባለ።
ክሪፕቶ ከረንሲ በሀገር ውስጥ ለመገበያያ እንዲውል ተጠይቋል።
ይህንን በሚመለከት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ኢትዮጵያ ክሪፕቶ ከረንሲን ለመገበያያነት እንድትጠቀም የሚያስችል መመሪያ ልታወጣ እንደምትችል ጠቁመዋል።
የሀሽባል ማይኒንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የቢትኮይን ባለሞያ አቶ ቃል ካሳ የክሪፕቶ ከረንሲ በኢትዮጵያ በህግ ማዕቀፍ ቢፈቀድ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
ባለሞያው ከአኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ አሁን ላይ ቢትኮይን እና መሰል የዲጂታል መገበያያዎች ፍቃድ ባያገኝም የቢትኮይን ማይነሮች ግን በሀገር ውስጥ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።
በዚህ አመትም 20 የሚጠጉ ቢትኮይን ማይነሮች 55 ሚሊዮን ብር ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ማስገባት መቻላቸውን አቶ ቃል ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክም በብሄራዊ ባንክ ገዢው በኩል በዚህ ጉዳይ ላይ እንዳስታወቀው የክሪፕቶ ከረንሲን እና የዲጂታል ገንዘብን በኢትዮጵያ መጠቀም የሚያስችል መመሪያ ወደፊት ሊያወጣ እንደሚችል ጠቁመዋል።
ብሔራዊ ባንክ መመሪያውን የሚያወጣው በማዕከላዊ ባንኪንግ፣ በገንዘብ ፖሊሲ እና በገንዘብ አስተዳደር ያሉ ዓለም አቀፍ ለውጦችን እያየ መሆኑንን ገዢው አቶ ማሞ ተናግረዋል።
ለአለም አሰፋ
ታኀሣሥ 9 ቀን 2017 ዓ.ም