ethiofm107dot8 | Unsorted

Telegram-канал ethiofm107dot8 - Ethio Fm 107.8

20436

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Subscribe to a channel

Ethio Fm 107.8

በትግራይ ክልል የአምቡላንስ እጥረት እንዳለ ተነገረ።

በትግራይ ክልል አገልግሎት ላይ ያሉ አምቡላሶች ከመቶ እንደማይበልጡ ሰምተናል።

ከጦርነቱ አስቀድሞ በክልሉ ከሶስት መቶ በላይ የህክምና ተሽከርካሪ አምቡላንሶች የነበሩ ሲሆን አሁን ላይ ከ100 ያልበለጡ መሆናቸዉንም ሰምተናል።

የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የእናቶች እና ህፃናት ጤና ዘርፍ ባለሙያዉ አቶ ገብረሀዋርያ ገብረ ክርስቶስ ባሉት አምቡላንሶች በምጥ ለተያዙ እናቶች በፍጥነት ለመድረስ በክልሉ ያለዉ የነዳጅ እጥረት ፈታኝ እንደሆነባቸዉ ገልፀዋል።

በዚህም እናቶችን ለማዋለድ እና እርዳታ ለመስጠት በያሉበት የህክምና ባለሙያዎች ለመላክ እየተሞከረ መሆኑን ባለሙያዉ ይገልፃሉ።

በክልሉ ያለዉ የጤና ስርአት አገልግሎት መፍረስ የነፍሰጡር እናቶች የቅድመ ወሊድ እንዲህም ወሊድ ሂደት ላይ እክል ሆኖ መቀጠሉ ተነስቷል።

በተለይም እናቶች የቅድመ ወሊድ ክትትሎች በሚፈለገዉ ልክ እያደረጉ አይደለም ተብሏል።

ከጦርነቱ በፊት በመንግስት ይሸፈኑ የነበሩ የህክምና ክፍያዎች አሁን ላይ ባለመኖሩ እናቶች ከፍለዉ አገልግሎት ለማግኘት እየተቸገሩ መሆኑን አቶ ገብረ ሀዋሪያ ገብረክርስቶስ ተናግረዋል።

የአምቡላንስ ÷ የሚድዋይፍሪ ባለሙያዎች እጥረት÷ የስልክ አገልግሎት አለመኖር ለወላድ እናቶች አስቸጋሪ ሁኔታ ፈጥሯል ችግሩም ከአቅማችን በላይ ነዉ ሲሉ ባለሙያዉ ተናግረዋል ።

ክልሉ በነበረበት የጦርነት ሁኔታ በጤና ተቋማት ላይ ከፍተኛ ዉድመት ማጋጠሙ ተከትሎ የመልሶ ግንባታ ስራዉ በተፈለገዉ ልክ እየሄደ እንዳልሆነ ሰምተናል።

የጤና ኬላዎቹን ለማቋቋም ከተለያዩ አጋዥ ተቋማት ጋር በመሆኑ ችግሩን ለመቅረፍ እየተሞከረ ነዉ ተብሏል።

ከዚህ ቀደም በክልሉ ተደርጓል የተባለ ጥናት እንዳመላከተዉ በወሊድ ምክንያት የሚሞቱ እናቶች ቁጥር ከጦርነቱ በፊት ከነበረዉ ማሻቀቡን ገልፆ ነበር።

ቁምነገር አየለ

የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከወር በፊት አገልግሎት መስጠት አቁሞ የነበረው የጨረር ማሽን መስራት መጀመሩ ተገለፀ።


ከዚህ ቀደም ለጣቢያችን ቅሬታ ያቀረቡ ታካሚዎች ከሁለት ሳምንት በኋላ ተመልሳችሁ ኑ መባላቸውን እና ተመልሰው ቢሄዱም ማሽኑ በመበላሸቱ እንደውልላችኋለን መባላቸውን ነግረውን ነበር።


በወቅቱ በሆስፒታሉ ቁጥር በተደጋጋሚ ብንደዉልም ቁጥሩ አይሰራም የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ፤በተደጋጋሚ እየሄድን ማሽኑ መች እንደሚሰራ ንገሩን ብንልም  መልስ የሚሰጠን አካል ማግኘት አልቻልንም ብለው ነበር።


ጣቢያችንም የታካሚዎችን ቅሬታ ይዞ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ክሊኒካል ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱረዛቅ መሀመድ ደውሎ ነበር፤ እርሳቸው እንደተናገሩት ከአንድ ወር በፊት አገልግሎት መስጠት አቁሞ የነበረዉ ማሽን ባሳለፍነዉ ሳምንት ታካሚዎችን መቀበል ችሏል።


አሁን ላይ ሆስፒታሉ እየተጠቀመበት የሚገኘዉ አንድ ማሽን መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር አብዱረዛቅ ፤ማሽኑ መበላሸቱ ሆስፒታሉ ተጨማሪ ማሽን እንደሚያስፈልገዉ ማሳያ ነው ብለዋል።


ለካንሰር ህመም የሚሰጠው የጨረር ህክምና ከተጀመረ በኋላ መቋረጥ የለበትም የሚሉት ዶ/ር አብዱረዛቅ፤ ጤና ሚኒስቴር ከዚህ በፊት ቃል የገባልንን ማሽን እንደ ትልቅ ተስፋ እየጠበቅን እንገኛለን ብለዋል።


የካንሰር ህክምና ትልቅ ወጭ የሚጠይቅ እና ብዙ ድጋፍ የሚያስፈልገው ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ በተለያዩ የባለድርሻ አካላት ሊደገፍ እንደሚገባውም ተናግረዋል።


ሊዲያ ደሳለኝ

የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሊቨርፑል ማንችስተር ሲቲን አሸነፍ !

በ26ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ  ሊቨርፑል ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያደረገውን  ጨዋታ  ሊቨርፑል 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች መሐመድ ሳላህ እና ዶምኒክ ስቦዝላይ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ግብፃዊው ተጨዋች መሐመድ ሳላህ በውድድር ዘመኑ ሀያ አምስተኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

መሐመድ ሳላህ በውድድር ዘመኑ በሁሉም ውድድሮች በሀምሳ ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል።

ሳላህ በአስራ አራት ግቦች ማንችስተር ሲቲ ላይ በሊጉ ብዙ ግብ ያስቆጠረ ቀዳሚው የሊቨርፑል ተጨዋች መሆን ችሏል።

ማንችስተር ሲቲ በውድድር ዘመኑ ስምንተኛ የፕርሚየር ሊግ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

የሊግ ደረጃቸው

1 ሊቨርፑል :- 64 ነጥብ
2 አርሰናል :- 53 ነጥብ
3 ኖቲንግሃም ፎረስት :- 47 ነጥብ
4 ማንችስተር ሲቲ :- 44 ነጥብ
5 ኒውካስል ዩናይትድ :- 44 ነጥብ
6 ቼልሲ :- 43 ነጥብ
7  አስቶን ቪላ :- 42 ነጥብ
12 ቶተንሀም :- 33 ነጥብ
15 ማንችስተር ዩናይትድ :- 30 ነጥብ

ጋዲሳ መገርሳ

የካቲት 16 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ዘ ታቦር ትሬዲንግ   የኮንስትራክሽን ግብአቶች  ማከፋፈያ የወርክ ሾፕ ምረቃ አካሄደ

ዘ ታቦር ትሬዲንግ ላለፉት ዓመታት ለቤት፣ ለተቋማትና ድርጅቶች የዘመኑ ቴክኖሎጂ ያፈራቸውን የግንባታና ዲዛይን ማስዋቢያ ማቴሪያሎችን በማከፋፈል በዘርፉ የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ የሚገኝ ተቋም ነው።

ድርጅቱ  ከ30 በላይ የኮንስትራክሽን ፊኒሽንግ እቃዎችን ማከፋፈል መጀመሩን ያሳወቀ ሲሆን ከነዚህም መካከል የወለል ምንጣፍ (SPC) ሙሉ በሙሉ ሴራሚክን የሚተካ በሀገራችን በኢትዮጵያ የሚመረት ለሴራሚክና ለወለል ምንጣፍ የሚሆኑ፣ ለጣራና ግድግዳ የሚያገለግል Wall Board & Foam Board እና Live ቦርድ እንደሚገኙበት ተገልጿል።

በዚህ መረኃ ግብር ልዩ ልዩ የግንባታ ማስዋቢያ የኮንስትራከሽን ማቴሪያሎች በአይነትና በጥራት በልዩ ቅናሽ ለገበያ የቀረቡ ሲሆን የግንባታ ማስዋቢያ ማቴሪያሎች የምርት ሂደትና ስለሚሰጡት አገልግሎት በባለሙያ ገለፃ ተደርጓል።



ዘ ታቦር ከሚሰራቸው የንግድ ስራዎች መካከልም  የግብርና ምርቶች ወደ ውጭ መላክ፣ የፋብሪካ ግብአት የሚሆኑ ምርቶችን ማስመጣት እና የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎችን እያከፋፈ የሚገኝ ድርጅት መሆኑም ተነስቷል።


ለዓለም አሰፋ

የካቲት 16 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የትራምፕና ፑቲን የፊት ለፊት ውይይት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጀመራቸውን ሩስያ አስታወቀች

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕና የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ፊት ለፊት የሚገናኙበት ስብሰባ ዝግጅት መጀመሩን የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታውቀዋል፡፡

ይህም በዩክሬን ጦርነት ምክንያት በምዕራባውያን ለተገለለቸው ሩስያ ትልቅ ለውጥን የሚያመጣላት ነው ተብሏል፡፡

ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ሰርጌይ ራያብኮቭ ለሃገራቸው የመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት የፑቲንና ትራምፕ የመሪዎች ስብሰባ በዩክሬን ያለውን ጦርነት ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ ጉዳዮች ላይም ያተኮሩ ሰፊ ውይይትን ያካተተ ይሆናል ብለዋል፡፡

ነገር ግን እንዲህ ዓይነቱን ስብሰባ ለማደራጀት ጥረቶች ገና ጅምር ላይ ናቸው ፣ እናም ይህንን ለማድረግ “በጣም የተጠናከረ የቅድመ ዝግጅት ሥራን ይጠይቃል” ብለዋል ።

ሪያብኮቭ አክለውም የዩናይትድናይትድ ስቴትስና የሩሲያ ልዑካን በከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል ለቀጣይ ንግግሮች መንገድ ለመክፈት "በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ" ሊገናኙ እንደሚችሉም ጠቁመዋል፡፡

የሁለቱ ሀገራት ተወካዮች ማክሰኞ እለት በሳኡዲ አርቢያ በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማስቆምና ዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነታቸውን ለማሻሻል ተስማምተዋል ።


በስብሰባው ላይ የዩክሬን ልዑክ ያልተሳተፈ ሲሆን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ኪየቭ ባልተሳተፈችበት የውይይቱ ምንም አይነት ውጤት ሀገራቸው እንደማትቀበል ገልጸው ባለፈው ረቡዕ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሊያደርጉ የነበረውን ጉዞም አራዝመዋል።


የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ማንችስተር ዩናይትድ ከሁለት ተከታታይ ሽንፈት በኋላ አንድ ነጥብ አሳካ!

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት መርሐግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከኤቨርተን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የኤቨርተንን ግቦች ቤቶ እና ዱኩሬ ሲያስቆጥሩ ለማንችስተር ዩናይትድ የአቻነት ግቦችን ብሩኖ ፈርናንዴዝ እና ኡጋርቴ አስቆጥረዋል።

ጋዲሳ መገርሳ

የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ግብፅ  የታላቁ የህዳሴ ግድብ  በተፋሰሱ አባል  ሀገራት እንዳይጎበኝ ስትጠይቅ፤  ኢትዮጵያ በበኩሏ ይህ የሀገራትን ነፃነት የሚጋፋ እና የማይሳካ ስትል ገለፀች።

የግብፁ የውሀ ሚኒስትር ሀኒ ሳሁሌ በአዲስ አበባ በተካሄደው  የናይል ሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር በናይል የተፋሰሱ ሀገራት  የተያዘውን የታላቁን የህዳሴ ግድብ የመጎብኘት እቅድ አባል ሀገራቱ እንዳይቀበሉት ጥያቄ አቅርበዋል።

ግብፅ ህዳሴን ከመጎበኘት በፊት የሚቀድመው ድርድሮች እና ስራዎች ሊጠናቀቁ ይገባል ስትል በውሀ ሚኒስትሯ በኩል ወቅሳለች።

ይህንን አስመልክተው ምላሽ  የሰጡት  የኢትዮጵያ ውሀ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ኢ/ር  ) "ግብፆች ከዚህ ቀደም ሲዋሹ ነበሩ አሁንም ያንኑ ነው እያደረጉ"  ይህ ደግሞ አይሳካላቸውም ሲሉም ተናግረዋል"።

ሚኒስትሩ  "ግብፆች እንደተለመደው ፉከራ ላይ ናቸው " ህዳሴን አሁን ላይ ማንም ሊቀለብሰው አይችልም ብለዋል"።

"ግብፆች ሲዋሹ ነበር ያ ውሸት እንዳይታይባቸው ህዳሴ እንዳይጎበኝ  በማድረግ  የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ላይ ተጠምደዋል" ካሉ በኃላ ።

"ኢትዮጵያ የሚጠበቅባትን ግብዣ አድርጋለች የመቀበል እና ያለመቀበል ደግሞ የአባል ሀገራት ውሳኔ ነው ያሉት " ሚኒስትሩ ሀብታሙ (ኢ/ር)፤ ነገር ግን አንተ አትቀበል ብሎ ጥሪ ማድረግ ግን ሀገራትን ከመናቅ የመነጨ ነው ሲሉም ተችተዋል።

ግድቡ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ከንብረትና ከዕውቀታችን በመነሳት  የተሰራ መሆኑን ገልፀው ግድቡ የትብብር ምልክት እና አርአያነት ያለው መሆኑን የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አመልክተዋል።


ለዓለም አሰፋ

የካቲት 14 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ቀበሌዎች እና ገበሬ ማህበራት ኬላዎችን በማሰር ክፍያ እየጠየቁ ነዉ ተባለ፡፡

አሽከርካሪዎች በአጭር ኪሎሜትር ልዩነት በተደጋጋሚ ኬላዎች ላይ ክፍያ እየተጠየቁ መሆኑንም አስታዉቀዋል፡፡

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የጣና ከባድ መኪና አሽከሪካሪዎች ማህበር ዋና ጸሃፊ አቶ ሰጡ ብርሃን፤በአማራ ክልል በ2014 ላይ ኬላዎች ተነስተዉ ነበር ያሉ ሲሆን፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ወደ ነበረዉ አሰራር በመመለሱ ቀበሌዎች እና ገበሬ ማህበራት ሳይቀሩ ኬላዎች በማድረግ ክፍያ በመጠየቅ ላይ ናቸዉ ብለዋል፡፡

በአጭር ኪሎሜትር ልዩነት በተደጋጋሚ ኬላዎች ላይ ክፍያ እንጠየቃለን ይህ ለትራንስፖርት አገልግሎቱ ከባድ ተጽዕኖን እየፈጠረ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ይሄ ጉዳይ አሽከርካሪዎች ላይ ከሚያሳድረዉ ጫና ባልተናነሰ በሸማች ማህበረሰቡ ላይ የራሱን ተጽዕኖ እያሳደረ መሆኑንም ነዉ አቶ ሰጡ የተናገሩት፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ፤ በኢትዮጵያ ኬላ ይነሳ ተብሎ በመንግሥት ደረጃ ቢወሰንም በተለያዩ ምክንያቶች ግን 2መቶ83 ሕገወጥ ኬላዎች በመላዉ አገሪቱ ይገኛሉ ማለታቸዉ ይታወሳል ።

እነዚህ ኬላዎች የምርት ነፃ ዝውውርን በመገደብ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴዉ ላይም  አሉታዊ ጫና ያላቸው መሆናቸዉ በተደጋጋሚ ተነስቷል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

የካቲት 14 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ከጋዛ የተላከዉ አስከሬን የሺሪ ቢባስ አይደለም ሲል የእስራኤል መከላከያ ገለጸ፡፡

ወደ እስራኤል የተላከዉ አስከሬን ከምርመራ በኋላ የሺሪ ቢባስ አለመሆኑ ከተገለጸ በኋላ፤ እስራኤል ሃማስን የተኩስ አቁም ስምምነቱን ጥሷል በማለት ከሳለች፡፡

ከተላኩት አስከሬኖች መካከል ሁለቱ ወንድ ልጆቿ ሲሆኑ ፤ የቀረዉ ደግሞ የ84 ዓመቱ የሰላም አክቲቪስት ኦዴድ ልፍሺትዝ እንደነበሩ ጦሩ አስታዉቋል፡፡

አራተኛዉ አስከሬን ግን የሺሪም ሆነ የሌላ ታጋች አስከሬን አይደለም ሃማስ የጋዛን ሴት በአስከሬን ሳጥን ዉስጥ አድርጎ ነዉ የላከዉ ይህም የተኩስ አቁም ስምምነቱን የጣሰ ነዉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ ተናግረዋል፡፡

የሃማስ ቃል አቀባይ ኢስማኤል አል-ታዉባታ በኤክስ ባሰፈሩት መልዕክት፤ የሺሪን አስከሬን እስራኤል ባደረሰችዉ የአየር ጥቃት ምክንያት በፍርስራሾች ዉስጥ ሳይቀያየር አልቀረም ብለዋል፡፡

ቡድኑ ለሮይተርስ እንደተናገረዉ ፤ የተሳሳተ አስከሬን ወደ እስራኤል የተላከበትን ሁኔታ የምናጣራ ይሆናል ብሏል፡፡

ህፃናቱ እና እናታቸው የተገደሉት በእስራኤል የቦምብ ጥቃት ነው በማለት የቀድሞ መግለጫቸውን መድገማቸዉንም ነዉ የዘገበዉ፡፡

የእስራኤል መከላከያ ቃል አቀባይ ሺሪን ቢባስ በህይወት ትኑርም አትኑርም ወደ እስራኤል ልትመለስ ይገባል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡

ሺሪንም ሆነ በህይወት ያሉም ይሁኑም የሌሉ ሌሎች ታጋቾችን ወደ እስራኤል ለመመለስ በቁርጠኝነት እንንቀሳቀሳለን፤ ሃማስም ለዚህ ጭካኔ ለተሞላበት የተኩስ አቁም ስምምነት ጥሰቱ ሙሉ ዋጋዉን የሚከፍል ይሆናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ገልጸዋል፡፡

በጥቅምት 7 2023 በሃማስ ጥቃት የታገቱት እናት እና ልጆች በወቅቱ የ32፣ 4 ዓመት እና 9 ወር ዕድሜ ላይ ነበሩ፡፡

በእስራኤል የሞታቸው ዜና ከተሰማ በኋላ መላዉ እስራኤል በሃዘን ዉስጥ መዉደቋ ተገልጿል፡፡

የ34 ዓመቱ የልጆቹ አባት ያርደን ቢባስ በጥር 1 ቀን 2025 ከታገተበት በሃማስ መለቀቁ ይታወቃል፡፡

እስከዳር ግርማ

የካቲት 14 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የሙታንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል ገዳምን ለመደገፍ የሚረዳ የጉዞ መረሃ ግብር ተዘጋጀ፡፡

ገዳሙ ያለበትን ችግር ለመቋቋም ከመጋቢት 25 እስከ ሚያዝያ 2017 ዓ.ም ወደ ገዳሙ የበረከት ጉዞ መዘጋጀቱን የገዳሙ አስተባባሪ ኮሚቴ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በምስራቅ ጎንደር ሙታንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል ገዳም በችግር ውስጥ ወድቀው ለነበሩ መነኮሳት 11 ሚሊዮን ብር እና በአይነት 1 ሚሊዮን 2 መቶ ሺህ በር መሰብሰብ መቻሉንም ኮሚቴው አስተውቋል፡፡

የገዳሙ የአዲስ አበባ ከተማ የሚዲያ አስተባባሪ ኮሚቴ አቶ ሙሉቀን አሰፋ፤ እነዚህ ድጋፎች የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና በጠበቀ መልኩ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን እና ማህበራዊ መገናኛ ላይ በተሰራ የማስታወቂያ ስራ ነው ብለዋል።

ገዳሙን የመርዳት ዘመቻው ከተጀመረ አስራ አንድ ወር ሆኖታልም ሲሉ ተናግረዋል።

በመጀመሪያ ዙር በተሰበሰበ ገንዘብ 170 ሜትር ተራራ ተቦርቡሮ ለእናቶችም ለአባቶችም ለእንቅስቃሴ አስቸጋሪ የነበረው ቦታ በአርማታ ደረጃ ተሰርቶለት ለገዳማዊያን እንቅስቃሴ ምቹ እንዲሆን ተደርጓል ብለዋል።

በአካባቢው ምንም አይነት የመብራት አገልግሎት በላመኖሩ የሶላር መብራት ፣የእናቶች ቤት፣የማዕድ ቤት ፣ለገዳማዊያኑ የእደ-ጥበባት ውጤቶችን ማምረቻ የሼድ ግንባታ፣ የሸማ ስራ ሙያ እንዲሰለጥኑ በማድረግ ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ ለስራው የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች እና የጥሬ እቃ ግብዓቶችን የማሟላት ስራ ተሰርቷል ብለዋል።

ባለፉት ወራት በተለይ የእናቶችን ችግር ከመቅረፍ በኩል ሰፊ ስራ ተሰርቷል ያሉት ኮሚቴዎቹ ፤ በአባቶች በኩል የቅዱስ ሚካኤል ህንፃ ቤተክርስቲያን ግንባታን ጨምሮ ፣የአባቶች ቤት ግንባታ፣የአብነት፣ዓለማዊ ት/ቤት፣ እና የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ጣቢያ ግንባታ ስራ ለማከናወን ገዳሙ እንቅስቃሴ መጀመሩ ገልጸዋል።

እነዚህን ስራዎች ከዳር ለማድረስ ከመጋቢት 25 እስከ ሚያዝያ ሁለት ቀን 2017 ዓ.ም ወደ ገዳሙ የበረከት ጉዞ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።

ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በተገኙበት ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ይዘጋጃል መባሉን ሰምተናል።

የገዳሙን እንቅስቃሴ በተመለከተ በዛሬው እለት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ የምዕራብ ሃረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ እንጦስ እና የገዳሙ መነኮሳት እና መምህራነ ወንጌል ተገኝተዋል።

ልኡል ወልዴ

የካቲት 14 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የካቲት 14 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የካቲት 14 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ለ9ኛ ጊዜ የተዘጋጀው ኢትዮ ኸልዝ አውደርዕይ እና ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል።

በአስራ አንድ አገራት የሚገኙ ኩባንያዎች በጉባኤው እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

አውደርዕዩ በጤና እንክብካቤ ፣ በህክምና መገልገያዎች እና የመድኃኒት እሴት ሰንሰለት ትኩረት የሚያደርግ ነው።

በዚህ ሁነት ላይ ከ11 አገራት የተውጣጡ ከ90 በላይ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት መሆኑም ተገልጿል።

በጤና ዘርፉ ከተሰማሩ የንግድ ማህበረሰብ አካላት እና የጤና ባለሙያዎች ጋር በጤና እንክብካቤ ተደራሽነት እና ጥራት ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክር እንደሆነም ነው የተገለጸው።

አምራቾች ፣ አስመጪዎች ፣ ወኪሎች እና አገልግሎት ሰጪዎችም ከ4ሺህ በላይ ለሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች ምርት እና አገልግሎቶቻቸውን ማስተዋወቅ የሚችሉበት ነው ተብሏል።

በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሚዘጋጀው 4ኛው አለምአቀፍ የአቅራቢዎች ጉባዔም ከኢትዮ ኸልዝ ጎን ለጎን የሚካሄድ መሆኑም ተገልጿል።

ኢትዮ ኸልዝ ዓለምአቀፍ አውደርዕይ እና ጉባኤ ከየካቲት 13 እስከ 15 2017 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል።

እስከዳር ግርማ

የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በአማራ ክልል በተከሰተ የኮሌራ ወረርሽኝ 238 ሰዎች ሲያዙ  የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።

በአማራ ክልል  ከታህሳስ 24 ቀን 2017 ዐ/ም ጀምሮ ዳግመኛ በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ 238  ሰዎች ሲያዙ  የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉ  የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገልጷል።

በክልሉ የተከሰተው ወረርሽኝ በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ላይ ሲሆን  በአሁኑ ጊዜ  ወረርሽኙ  በመስፋፋት በጎንደር ፣በባህርዳር፣በገንደውሀ ወረዳ እና በምዕራብ ጎጃም ቡሬ ከተማ ላይ መከሰቱን በኢንስቲትዩቱ የበሽታዎችና የጤና ሁኔታዎች ምላሽ አሰጣጥ ባለሙያ ሲስተር ሰፊ ደርብ ተናግረዋል ፡፡

የኮሌራ ወረርሽኙ በድጋሚ  ታሕሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም የተከሰተ መሆኑን ያነሱት ሲስተር ሰፊ ደርብ  ከታሕሳስ 24 እስከ የካቲት 5 ባሉ ጊዜያት ብቻ 238 የሚሆኑ ዜጎች በወረርሽኝ መያዛቸውን አስታውቀዋል ፡፡

በተጨማሪም በወረርሽኙ ምክንያት የአራት ሰዎች ሕይወት  ማለፉን ነግረውናል ፡፡

ወረርሽኙ እንዳይዛመት ህመምተኞች በተገኙበት   የመኖሪያ አካባቢዎች ላይ ክሎሪን በመርጨት  የብክለት መከላከል ስራዎች በክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኩል እየተሰራ መሆኑ ተነስቶል ፡፡

የአደጋ ስጋት ተግባቦት የጤና ትምህርት በተከሰተባቸው እና በተስፋፋባቸው አካባቢዎች በመስጠት ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ እየተሰራ መሆኑ  ተነግሮል ፡፡

አቤል እስጢፋኖስ

የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ከጣሪያ እና ግድግዳ ግብር ከ 3 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን  የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ

በአዲስአበባ ከተማ ከ ሀምሌ ወር ጀምሮ አስከ የካቲት ወር አጋማሺ የጣራ እና ግድግዳ ግብር አሰባሰብ  ከ 3 ቢሊዮን ብር በላይ መገኘቱን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል

በስድስት ወር የግብር ስብሰባ አፈፃፀም 62 ከመቶ ግብር ከፋዬች ግብር እንደከፈሉ የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሰዉነት አየለ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል ፡፡

ከቦታ እና ከቤት ጋር የተያያዘ ዉዝፍ እና የዘንድሮዉ አመት አጠቃላይ ከ 6 ቢሊዬን ብር በላይ ግብር መሰብሰቡን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ገልፀዋል ፡፡

የጣራ እና ግድግዳ ግብር እስከ የካቲት 30 ያልከፈሉ ነዋሪዎች የ 5 በመቶ ቅጣት እስከ እነ ወለዱ እንደሚከፍሉ አስጠንቅቀዋል ፡፡

ግብር ያልከፈሉ የተሰጣቸውን ጊዜ በመጠቀም በአግባቡ እንዲከፍሉ አቶ ሰዉነት አየለ አሳስበዋል ፡፡

አቤል እስጢፋኖስ

የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ዘለኒስኪ ሥልጣኔን ለመልቀቅ ዝግጁ ነኝ አሉ፡፡

የዩክሬይኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘሌንስኪ ለአገራቸው ሠላም የሚያመጣ ከሆነ ሥልጣናቸውን እንደሚለቁ አስታወቀዋል።

ይህን ምርጫ ዘለንስኪ ያቀረቡት ሩሲያ በዩክሬን ላይ ሙሉ ጦርነት የጀመረችበትን የሶስት አመት መታሰቢያ ዋዜማ አስመልክቶ በኪየቭ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

ፕሬዚዳንቱ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት "የኔ ከሥልጣን መልቀቅ ሠላም የሚያመጣ ከሆነ ለመልቀቅ ዝግጁ ነኝ" ብለዋል።

ከሥልጣን የሚለቁት ግን አገራቸው በምላሹ የኔቶ አባል የምትሆን ከሆነ ብቻ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በዘለንስኪና እና ትራምፕ መካከል ያለው አለመግባባት እየሰፋ መሄዱ ፣ለዘለኒስኪ እንዲህ ያለ አማራጭ አንዱ ምክንያት ነው እየተባለም ይገኛል።

የቀድሞው ኮሜዲያን እና የአሁኑ የዩክሬይን ፕሬዚዳንት ዜሌንስኪ የኔቶን አባልነት የማያገኙ ከሆነ የሠራዊታቸው ቁጥር በእጥፍ ማደግ እንደሚኖርበት መናገራቸው አይዘነጋም።

ልኡል ወልዴ

የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሰበታ አግሮ ኢንዱስትሪ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ተቀበለ

ለረጅም ጊዜያት ወተት እና የወተት ተዋፅኦ ምርቶችን በማቀነባበር የሚታወቀው  ሰበታ አግሮ ኢንዱስትሪ  (ማማ ወተት)   የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ከኢትዮጵያ ተስማሚነት እና ምዘና ድርጅት ተቀብሏል።

አለም ዓቀፍ የጥራት ስራ አመራር ስርዓት ሰርቲፋይድ መሆኑ  ምርቱን ከሀገር ውጭ በመላው ዓለም ለማቅረብ ያግዘዋል ተብሏል።

ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ የተሰማራው ማማ ወተት ከ50 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል እንደፈጠረ የሰበታ አግሮ ኢንዱስትሪ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉጌታ ይመር ተናግረዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እንዳለው መኮንን፥ ሰበታ አግሮ ኢንዱስትሪ ላለፉት ሦስት አስርት ዓመታት የብራንድ ሥሙን አስጠብቆ የቆየ መሆኑን ተናግረዋል።

አቤል እስጢፋኖስ

የካቲት 16 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የፍልስጥኤማዉያኑ ታጣቂ ቡድን ሃማስ ስድስት የእስራኤል ታጋቾችን በይፋ ለቀቀ።

የመጀመሪያው ዙር የታጋች እስረኛ ልውውጥ ስምምነት አካል እስራኤል በበኩሏ ከ520 በላይ ፍልስጥኤማዉያን እስረኞችን ትለቃለች ተብሏል።

ሃማስ ቤተ እስራኤላዊ አቬራ መንግስቱን ጨምሮ ስድስቱን ታጋቾች በደቡባዊ ጋዛ ራፋ እና ማዕከላዊ ጋዛ ኑሰሪያት የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ በተከናወነ ይፋዊ ስነስረዓት ለዓለማቀፉ የቀይ መስቀል ድርጅት አስረክቧል።

ከሁለት ልጆቿ ጋር በታጣቂ ቡድኑ ታግታ የነበረችው እና በስፋት መነጋገሪያ ስትሆን የነበረው ሺሪ ቢባስም በሕይወት መኖሯ ተረጋግጦ ለእስራኤላዉያኑ ዕፎይታ መስጠቱን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

እስራኤል እና ሃማስ የመጀመሪያው ዙር የታጋች እስረኛ ልውውጥ ሳይጠናቀቅ እስራኤል ስምምነቱን የሚንዱ ዕርምጃዎች እየወሰደች ነው ሲል ለዛሬ ይዞ የነበረውን ታጋቾች የመልቀቅ ዕቅድ ለሌላ ጊዜ ማሸጋገሩን አስታዉቆ ነበር ።

ዉሳኔውን ተከትሎ ግን  እስራኤል ወታደሮቿን ዳግም ልታሰማራ እንቅስቃሴ መጀመሯን ተከትሎ ሃማስ ወደ ስምምነቱ ማዕቀፍ ለመመለስ ከተስማማ በኋላ ታጋቾችን በይፋ ለቋል።

ባለፈው የጥር ወር የተጀመረው የእስራኤል ሃማስ የተኩስ አቁም እና የታጋች እስረኛ ልውውጥ የፊታችን የመጋቢት ወር ያበቃል።


የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

አርሰናል ሽንፈት አስተናግደዋል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከዌስቶሀም ዩናይትድ ጋር ያደረገውን የሊግ መርሐግብር 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

የዌስትሀም ዩናይትድን የማሸነፊያ ግብ ጃሮድ ቦውን ማስቆጠር ችሏል።

መድፈኞቹ ከአስራ አምስት የፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች በኋላ የመጀመሪያ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

አርሰናል በዘንድሮው የውድድር ዘመን ተጨዋቾቹ በአምስት አጋጣሚዎች ቀይ ካርድ ተመልክተዋል።


በሌሎች ጨዋታዎች


ቶተንሀም ኢፕስዊች ታውንን በጆንሰን 2x ፣ ስፔንስ እና ኩሉሴቭስኪ ግቦች 4ለ1 ማሸነፍ ችለዋል።

- ብራይተን ሳውዝሀምፕተንን 4ለ0
- ክሪስታል ፓላስ ፉልሀምን 2ለ0 እንዲሁም
- ዎልቭስ በርንማውዝን 1ለ0 ማሸነፍ ችለዋል።


ጋዲሳ መገርሳ

የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

"ተነጣጥለን ረዥም መጓዝ አይቻልም " አሉ
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ  ።

በናይል ወንዝ ፍትሃዊና ምክንያታዊ የውሃ አጠቃቀም ስርዓት እንዲሰፍን ሁሉም የቡኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ተጠይቋል።

ይህ የተባለው 19ኛው የሪጅናል ናይል ቀን የተፋሰሱ ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮችና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በዛሬው እለት በሳይንስ ሙዚየም እየተከበረ ባለበት ወቅት ነው።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር  ዶ/ር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ በጉባዬው የተገኙ ሲሆን፤ "የአባይ ትብብርን ማጎልበት፣የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እና ለጋራ ልማት "በሚል መርህ ይከበራል ብለዋል።

ሚስትሩ በጉባዔው ላይ ኢትዮጵያ ለዓባይ ወንዝ ፍትሐዊ አጠቃቅምና ቀጣናዊ የጋራ ልማት መረጋገጥ የማይናወጥ አቋም አላትም ብለዋል።

የናይል ተፋሰስ ኮሚሽን መቋቋም ለአባል ሀገራት የጋራ ልማት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ዶ/ር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ገልጸዋል፡፡

ኮሚሽኑ የተፋሰሱ ሀገራት የልማት ትብብር በህግና ስርዓት እንዲመራ ከማድረጉ በተጨማሪ ለጋራ ጥቅም የሚውሉ ግድቦችን ለመስራት ያስችላል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በናይል ወንዝ ፍትሃዊና ምክንያታዊ የውሃ አጠቃቀም ስርዓት እንዲሰፍንና በናይል ሀገራት መካከከል ትብብርን ማዕከል ያደረገ ግንኙነት እንዲፈጠር ጥረት አድርጋለች አሁንም ትቀጥላለች ብለዋል፡፡

የናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፍሎሬንስ አዶንጎ፤ የመሰባሰባችን ዋነኛው አላማችን የተፋሰሱን ሀገራት የልማት ትብብር ማጠናከር ነው ብለዋል፡፡

በጉባዔው የተፋሰሱ ሀገራት እና ትብብር ያደረጉ ሁሉ  በጋራ ለማደግ ያላቸውን ፍላጎት የሚያመላክት ነው ሲሉ  ገልፀዋል።

ሌሎችም ቆም ብለው የመተባበር እና ያለመተባበር የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ማገናዘብ ተገቢ ነው፤ተነጣጥለን ረዥም መጓዝ አይቻልም ብለዋል።

የናይል ቀን በየዓመቱ  ፌቡራሪ 22 በተፋሰሱ ሀገራት ይከበራል፡፡

የናይል ተፋሰስ ኮሚሽን በተፋሰሱ አባል ሀገራት ስምምነት መሰረት በቅርቡ እውን ይሆናል መባሉን ሰምተናል፡፡


ልኡል ወልዴ

የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ለጋዛ ተፈናቃይ ዜጎች የሚዉሉ15 ተንቀሳቃሽ ቤቶች ወደ ጋዛ እያመሩ ነዉ ተባለ።

በጋዛዉ ጦርነት ምክንያት ወደ ሩብ ሚሊየን የሚጠጉ ቤቶች እንደወደሙ ተመድ ግምቱን አስቀምጧል።

በትናንትናዉ እለት ተንቀሳቃሽ ቤቶቹን ለመገንባት ይረዳሉ የተባሉ ቁሳቁሶችን የጫኑ መኪኖች የግብፁን የራፋህ በር እንዳቋረጡ የግብፅ የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል።

ከነዚህ የእርዳታ ጭነት መኪኖች እንዲሁም ሌሎች አቅርቦቶች ወደ ጋዛ ከመሻገራቸዉ በፊት በእስራኤል ቁጥጥር ስር ባለዉ ኬረም ሻሎም ማቋረጫ ባለ የፍተሻ ቦታ ምርመራ ይጠብቀዋል ተብሏል።

በዚህም  ተንቀሳቃሽ ቤቶቹ ወደ ጋዛ መቼ እንደሚገቡ መረጃዉ አልጠቀሰም።

በተያያዘም ከ20 ሺህ በላይ ድንኳኞች ለተፈናቀሉ ዜጎች መጠለያ እንዲሆን ተልኳል ተብሏል።

በጋዛ ውስጥ ይገኙ ከነበሩ ህንፃዎች 70 በመቶ ያህል  የሚጠጉት  ሕንፃዎች ውድመት እንደደረሰባቸው ተገልፆል ።

የጋዛ ጦርነት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በጋዛ እና ሊባኖስ ከ 50,000 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ይገለፃል። 

የጋዛን ጦርነት ባቆመው በእስራኤል እና በሃማስ መካከል ባለፈው ወር ተግባራዊ የሆነው የተኩስ አቁም ስምምነት መጋቢት ላይ ማብቂያዉን የሚያደርግ ነዉ ።

ዘገባዉ:- የአልቃሄራ ኒዉስ ነዉ።

ቁምነገር አየለ

የካቲት 14 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ አስራ ስድስቱን የተቀላቀሉ ክለቦች የጥሎ ማለፍ ድልድል እጣ ማውጣት ስነስርዓት በአሁኑ ሰዓት እየተካሄደ ይገኛል።


- አስቶን ቪላ ከ ክለብ ብሩጅ

- ዶርትመንድ ከ ሊል

- ሪያል ማድሪድ ከ አትሌቲኮ ማድሪድ

- ባየር ሙኒክ ከ ባየር ሌቨርኩሰን

- ፒኤስቪ ከ አርሰናል

- ፌይኖርድ ከ ኢንተር ሚላን

- ባርሴሎና ከ ቤኔፊካ

- ሊቨርፑል ከ ፒኤስጂ

የፔዤ እና ሊቨርፑል አሸናፊ ከ  ብሩጅ እና ቪላ አሸናፊ  ጋር  
አርሰናል እና ፒኤስቪ አሸናፊ ከ አትሌቲ እና ሪያል  አሸናፊ  ጋር 

የባርሳ  እና ቤንፊካ ከ ሊል እና ዶርቱመንድ አሸናፊ  ጋር

የፌይኖርድ እና ኢንተር ከ ሊቨርኩሰን እና ባየርንአሸናፊ  ጋር  በሩብ ፍፃሜ  ይፋልማሉ፡፡



የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎቹ 
- የመጀመሪያው ዙር ጨዋታዎች የካቲት 25 እና 26/2017 ዓ.ም ይደረጋሉ።

- የመልስ ጨዋታዎች ከአንድ ሳምንት በኋላ መጋቢት 2 እና 3/2017ዓ.ም የሚደረጉ ይሆናል።

ጋዲሳ መገርሳ

የካቲት 14 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኦሮሚያ ክልል የመንግስትን የሰላም ጥሪ ለተቀበሉ የቀድሞ የኦነግ አመራሮች ሹመት ሰጥቷል፡፡

በዚህ መሰረትም፡-

1. አቶ ያደሳ ነጋሳ--------- በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ

2. አቶ ኦሮሚያ ረቡማ --------- የኦሮሚያ ክልል ዓቃቤ ሕግ ምክትል ሃላፊ

3. አቶ ቶሌራ ረጋሳ --------- የኦሮሚያ ክልል ጸጥታና አስተዳደር ቢሮ ምክትል ሃላፊ ሆነው መሾማቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የካቲት 14 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሉሲዎቹ የመጀመሪያውን ዙር ጨዋታቾውን ዛሬ ይከናወናሉ።


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከዩጋንዳ ጋር የሚደረገውን ለ2026 የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ በዛሬው ዕለት ይከናወናል።

ብሔራዊ ቡድኑ በአሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ እየተመራ የመጨረሻ ልምምዱን ትናንት መስራት ችሏል።

በዛሬው ጨዋታ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አረንጓዴ ማልያ፣ ቢጫ ቁምጣ እና ቀይ ካሶተኒ ለብሶ ወደ ሜዳ ሲገባ ዩጋንዳዎች ቀይ መለያ የሚጠቀሙ ይሆናል።

በዩጋንዳ እና ኢትዮጵያ መካከል የሚደረገው የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ የመጀመርያ ዙር ጨዋታ ዛሬ ካምፓላ በሚገኘው ሀምዝ ስታዲየም ከቀኑ 10:00 ላይ ይከናወናል።

ጋዲሳ መገርሳ

የካቲት 14 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ኢት-ኮፊ ከሚያገኘዉ ትርፍ 10 በመቶዉን ለማህበራዊ ድጋፍ እንደሚሰጥ ተናገረ።

ኢት ኮፊ ቴስት ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ከሚያገኘዉ ትርፍ 10 በመቶዉን ለማህበራዊ ድጋፍ እንደሚሰጥ አስታዉቋል፡፡

የማህበሩ ዳይሬክተር አቅሌሲያ ሰለሞን ፤ የሚቀርበዉ ቡና እሴት ተጨምሮበት ወደ ውጭ የሚላክ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በስሩ ከ1መቶ በላይ ሰራተኞችን የያዘዉ ኢት-ኮፊ ፤ ከሚያገኘዉ ትርፍም 10 በመቶዉን ለማህበራዊ ድጋፍ እንደሚያዉለዉ ነዉ የገለጹት፡፡

ቡናው በውጭ አገራት ጥሩ ተቀባይነት አለዉ ያሉት ዳይሬክተሯ፤ አራት አይነት ዘመናዊ የቡና ማሽኖች እንዳሉትም አንስተዋል፡፡

ማህበሩ በዛሬዉ ዕለት ባለ አምስት ወለል ህንጻ ያስመረቀ ሲሆን፤ በዉስጡም ኢትዮጵያን የሚገልጹ ስፍራዎችን የያዘ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ይህ መሆኑም ለቱሪዝም ዘርፉ የራሱ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ዳይሬክተሯ ገልጸዋል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በሐማስ ታግተው የተገደሉ አራት ዜጎቿን አስከሬን እስራኤል ተቀበለች

ሃማስ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 7 2023 በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ካገታቸው በኋላ ሕይወታቸው ያለፈውን የአራት እስራኤላውያን ታጋቾች አስከሬን አስረክቧል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንዳሳወቀው የአራቱ ታጋቾች አስከሬን በጋዛ ወደሚገኘው የእስራኤል ጦር ተላልፏል፡፡

ጦሩ የሟቾችን ስም ከፎረንሲክ ምርመራ በኋላ አረጋግጣለሁ ብሏል።

ሃማስ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ እናት እና ሁለት ልጆቿን እንደሚያካትት የተነገረ ሲሆን፣ የቤተሰቡ እጣ ፈንታ በእስራኤላውያን ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ ነበር።

የመጨረሻው ልጅ ክፊር ሲታገት የዘጠኝ ወር ልጅ ነበር።

ሃማስ ካስረከባቸው አስከሬኖች መካከል አራተኛው የ84 ዓመቱ አንጋፋ የሰላም ታጋይ የኦዴድ ሊፍሺትዝ ነው ብሏል።

የተኩስ አቁም ስምምነት ባለፈው ወር ከተጀመረ በኋላ ቡድኑ የሞቱትን ታጋቾች ሲያስረክብ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ "የመላው ሕዝብ ልብ በሐዘን ደምቷል" ካሉ በኋላ፣ እስራኤል ከ"ጭራቆች" ጋር እየተፋለመች ነው ሲሉ አክለዋል።

በሕይወት ያሉ ስድስት ታጋቾች ቅዳሜ ሊፈቱ እንደሚችሉ ተነግሯል።

ምንም እንኳ እስካሁን ይፋዊ ማረጋገጫ ባይገኝም ሺሪ፣ ክፊር እና ወንድሙ ኤሪኤል እንዴት እንደሞቱ አይታወቅም።

ሃማስ ታጋቾቹ በጥቅምት 2023 እስራኤል ባደረገችው የአየር ጥቃት መገደላቸውን ገልጿል።

በወቅቱ የእስራኤል የጦር ካቢኔ አባል የነበረው ቤኒ ጋንትዝ ስለጉዳዩ ምንም ማረጋገጫ እንደሌለ ተናግሯል።

እኤአ ከጥር 19 ጀምሮ በስራ ላይ በዋለው የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት የታጋቾችን አስከሬን ለመስጠት ስምምነት ላይ ደርሷል።

እስራኤል በሃማስ እጅ ሳሉ የተገደሉ ታጋቾች ቁጥር ስምንት እንደሚሆኑ አረጋግጣለች።

የተኩስ አቁም በተጀመረባቸው የመጀመሪያዎቹ 6 ሳምንታት መጨረሻ ላይ ሃማስ 33 ታጋቾችን ሲለቅ እስራኤል በምላሹ 1,900 የሚጠጉ እስረኞች ለመልቀቅ ተስማምተዋል።

በዚህ ወር መጀመርያ ላይ ቀሪዎቹ ታጋቾች የሚፈቱበት እና ጦርነቱ በዘላቂነት የሚያበቃበት ሁኔታ ላይ ንግግር ይጀመራል ቢባልም እስካሁን የታየ እንቅስቃሴ የለም።

ሃማስ እስካሁን 24 ታጋቾችን ሲለቅ፣ እስራኤል ከ1,000 በላይ እስረኞች አስረክባለች።

በጥቅምት 7 የተወሰዱ ሰባ ሰዎች አሁንም በጋዛ ታግተው ይገኛሉ።

ከአስር አመታት በፊት የተወሰዱት ሌሎች ሶስት ታጋቾችም በእስር ላይ ናቸው።

አሁንም በጋዛ ከሚገኙት ታጋቾች መካከል ግማሽ ያህሉ በሕይወት እንዳሉ ይታመናል።

የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ከ 13 ሚሊየን በላይ ዕድሜያቸዉ ከ5 ዓመት በታች ለሚሆኑ ህጻናት የፖሊዮ ክትባት ሊሰጥ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ሚኒስቴር እና ከክልል ጤና ቢሮዎች ጋር በመተባበር ለ13.8 ሚሊየን ህጻናት የፖሊዮ ክትባት ለመስጠት ዝግጅቱን መጨረሱን አስታዉቋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ በክትባት ዘመቻዎች ወቅትበቁጥር የተለዩ ከ 18 ሚሊየን በላይ ዕድሜያቸዉ ከአምስት አመት የሆኑ ህጻናት መኖራቸዉን ገልጿል፡፡

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የፖሊዮ ወረርሺኝ ምላሽ አስተባባሪ ሚኪያስ አላዩ ፤ከአምስት ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ህፃናት በታህሳስ ወር የፖልዮ ክትባት መዉሰዳቸዉን ነግረዉናል፡፡

በታህሳስ ወር በአማራ፣ አፋር፣ ጋምቤላ እና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክትባት መሰጠቱን አስታዉሰዉ ፤ አሁን ላይ እነሱን ሳይጨምር በ9 ክልሎች እና በ1 ከተማ አስተዳደር ላይ ክትባቱ እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡

በዚህኛዉ ዙር በሚደረገዉ የክትባት ዘመቻም ለ13 ነጥብ ስምንት ሚሊየን በላይ ህፃናቶች ክትባቱን የመስጠት ዕቅድ መያዙንም ነዉ ያነሱት፡፡

ክትባቱ ከየካቲት 14 እስከ የካቲት 17 ለተከታታይ አራት ቀናት የሚሰጥ ቢሆንም፤ እንደ የአካባቢዉ ሁኔታ ቶሎ ተደራሽ የማይሆኑ ህፃናት የሚኖሩ ከሆነ ክትባቱ የሚራዘም መሆኑንም ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ትራምፕ የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት "አምባገነን" ሲሉ ዘለፉ

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪን "አምባገነን" ብለው መጥራታቸው የሁለቱን መሪዎች መቃቃር ይበልጥ አባብሶታል።

ትራምፕ ይህንን ያሉት ዜሌንስኪ ኪየቭ የተገለለችበት እና በሳዑዲ አረቢያ ለተደረገው በአሜሪካ እና ሩሲያ ንግግር በሰጡት ምላሽ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት በሚተዳደረው በሞስኮ "የሐሰት መረጃ ላይ ነው" በማለት ከወቀሱ በኋላ ነው።
ፍሎሪዳ ውስጥ በሳዑዲ በሚደገፈው የኢንቨስትመንት ስብሰባ ላይ ትራምፕ እንደተናገሩት ዜሌንስኪ "በጣም ጥሩ የነበሩበት ብቸኛው ነገር ጆ ባይደንን በከንቱ ማታለል ላይ ነው" ብለዋል።

ትራምፕ 'በትሩዝ ሶሻል' ልጥፍ ላይ ተመሳሳይ ቃል ከተጠቀሙ ጥቂት ሰዓታት በኋላ በፍሎሪዳ ሲናገሩ ዜለንስኪን "አምባገነን" ሲሉ ጠርተዋቸዋል።

"ምርጫ ለማድረግ ፈቃደኛ አይደለም። በዩክሬን ብዙም አይፈለገም። እያንዳንዱ ከተማ እየፈረሰ እንዴት ከፍ ሊል ይችላል?" ሲሉ ትራምፕ ተናግረዋል።

የዘለንስኪን መንግሥት "ስምምነቱን አፍርሷል" ሲሉ በመክሰስ ከዩክሬን የከበሩ ማዕድናት ለማግኘቱ ያደረጉትንም ሙከራ ጠቅሰዋል።

ትራምፕ ዘለንስኪ "መጥፎ ሥራ ሠርቷል፣ አገሩ ፈርሳለች፣ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ያለምክንያት ሞተዋል" ሲሉ "የትሩዝ ሶሻል" ልጥፋቸውን አስተጋብተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ "ጦርነቱን በተሳካ ሁኔታ ለማቆም ከሩሲያ ጋር ድርድር እያደረገች ነው" ብለዋል።

የዋይት ሀውስ ባለስልጣን የትራምፕ ልጥፍ ለዘለንስኪ ለሰጡት የ"ሃሰት መረጃ" አስተያየቶች ቀጥተኛ ምላሽ ነው ብለዋል።

ማክሰኞ የአሜሪካ እና የሩሲያ ባለስልጣናት ከሩሲያ የዩክሬን ወረራ በኋላ የመጀመሪያ ደረጃ ፊት ለፊት ተገናኝተው ንግግሮችን አድርገዋል።

የዩክሬን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አርሴኒ ያሴንዩክ የትራምፕን አስተያየት ተከትሎ ሩስያ "አሁን ፈንጠዝያ ላይ ነች" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

"ቮልዲሚር ዘለንስኪ ሕጋዊ ፕሬዚዳንት ናቸው" ያሉት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር "በወታደራዊ ሕግ ስር ምርጫ ማካሄድ አንችልም" ብለዋል።

የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…
Subscribe to a channel