በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
ሰሞኑን በተደረገዉ የነዳጅና የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ራይድ የዋጋ ጭማሪ ማድረጉን አስታወቀ
የራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት በመነሻ ያስከፍል በነበረዉ አገልግሎቱ ላይ የ 30 ብር ጭማሪ ማድረጉን አስታዉቋል።
የነዳጅ ዋጋ በመጨመሩ እና በቅርቡ የተደረገዉ የዉጪ ምንዛሪ ማሻሻያ ምክንያት መነሻ ከ ነበረዉ 100 ብር ከትላንት ጀምሮ 130 ብር መሆኑን የሃይብሪድ ዲዛይንስ እና ራንድ መስራችና ስራ አስኪያጅ ሳምራዊት ፍቅሩ በተለይ ለካፒታል ተናግረዋል ።
ከዚህ በተጨማሪ በአዲሱ የዋጋ ማሻሻያዉ በኪሎ ሜትር የ 1 ብር ጭማሪ መድረጉን ካፒታል ዘግቧል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም
ኦቪድ ሪል ስቴት ከራይድ ትራንስፖርት ጋር የራይድ ቤተሰብ መንደርን ለመገንባት ስምምነት ተፈራረመ።
ኦቪድ ሪል ስቴት ለራይድ ሹፌሮች የሚሆን የራይድ ቤተሰብ መንደር በገላን ጎራ ከተማ ለመገንባት በዛሬው ዕለት ስምምነት ተፈራርሟል።
ሁለቱ ተቋማት አዲስ እየተገነባ በሚገኘው የገላን ጎራ ከተማ ውስጥ ለራይድ አሽከርካሪዎች በአጭር ጊዜ ቤቶችን ገንብቶ ለማስረከብ ነው የተስማሙት።
ከዚህ በተጨማሪ ኦቪድ ሪል ስቴት ከሰዋሰው መልቲሚዲያ ጋርም ስምምነት ተፈራርሟል።
በዚህ ስምምነት ከሰዋሰው መልቲሚዲያ ጋር የተፈራረሙ አርቲስቶች በቅናሽ የቤት ባለቤት መሆን እንደሚችሉም ነው የተገለጸው።
ኦቪድ ግሩፕ ከሚያደርገው የቤት ዋጋ ቅናሽ በተጨማሪ ሰዋሰው መልቲሚዲያ የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
ኦቪድ ግሩፕ ከ70 ሺህ በላይ ቤቶችን በተለያዩ ሳይቶች እየገነባ መሆኑን የገለፁት የኦቪድ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ፍሬው በየነ፤ 60 ሺህ የሚሆኑት በገላን ጎራ ከተማ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ግሩፑ ለኩባንያዎች በሚደረግ ሽያጭ ቤቶችን ከተቋማት ጋር በመፈራረም እየገነባ መሆኑን ገልፀው፤ ከሃይብሪድ ዲዛይንስ ኃላ.የተ.የግ. ማህበር እህት ኩባንያ ከሆኑት ራይድ ትራንስፖርት እና ሰዋሰው መልቲሚዲያ ጋር መፈራረማቸውን ነው የገለፁት።
ኦቪድ ግሩፕ ከሁለቱ ተቋማት ጋር በገባው ስምምነት መሠረት 5 ሺህ ቤቶችን በ2 ዓመት ጊዜ ውስጥ ሰርቶ እንደሚያስረከብ አስታውቋል።
በእስከዳር ግርማ
መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ።
በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ ረፋድ 4 :00 ላይ ከጎሮ ወደ ኮዬ እየተጓዘ የነበረ ኮድ 3-69867 ቱርቦ የሆነ የጭነት ተሽከርካሪ ከከተማ አውቶቢስጋር ተጋጭቶ በደረሰ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በተጨማሪ በሰባት ሰዎች ላይ ቀላል እና ከባድ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በቤጂንግ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
አደጋው ዛሬ በረፋዱ 4 ሰዓት አካባቢ መድረሱን የገለጹት ኃላፊው የአደጋው መንስዔ እየተጣራ እንደሚገኝም አመልክተዋል።
የደረሰው አደጋ እጅግ አሰቃቂ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው የሞት አደጋ የደረሰባቸው ሁሉም ሴቶች እንደሆኑ እንዲሁም ዕድሜያቸውም ከ20 እስከ 52 የሚገመቱና ሦስቱ ሴቶች የአውቶቢስ ትኬት በመቁረጥ ላይ እያሉ አደጋው እንደደረሰባቸው ጠቁመው በተሽከሪካሪዎቹም ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል ብለዋል ።
መስከረም 29 ቀን 2017
የነገ የመስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ፕሮግራሞቻችን
Читать полностью…ኢትዮጵያ ለጋራ የውሃ ተጠቃሚነት አሁንም የፀና መርህ እንዳላት ተገለጸ
ኢትዮጵያ ለጋራ የውሃ ተጠቃሚነት ያላት መርህ አሁንም የፀና መሆኑን የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሐብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ገልፀዋል፡፡
በጅማ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ባለው 11ኛው የውሃ ዲፕሎማሲና የኮሙኒኬሽን ፎረም ላይ ሐብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) እንደገለፁት፤ “በአሁኑ ዘመን ውሃ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ እና ዲፕሎማሲ ሆኗል” ሲሉ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በዚህ አግባብ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን ገልጸው÷ ኢትዮጵያ ድንበር ተሻጋሪ ሀብቶቿን በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ለመጠቀም ያላት አቋም የፀና መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም መገናኛ ብዙሀን የኢትዮጵያን ዕውነት በማሳወቅ ሂደት ውስጥ ሚናቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።
ከውሃ ዲፕሎማሲና እና ፖለቲካ ጋር በተገናኘ መነሻ ፅሁፍ ቀርቦም ውይይት እየተካሄደበት ይገኛል።
የተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ያቀፈው የውሃ ዲፕሎማሲና የኮሙኒኬሽን ፎረሙ ከሁለት ዓመት በፊት በውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስተባባሪነት የተጀመረ ነው።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም
ጀርመናዊው የቀድሞ የሊቨርፑል አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ የሬድ ቡል ተቋም የእግር ኳስ የበላይ ሀላፊ በመሆን መሾማቸው ይፋ ተደርጓል።
አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ከሚቀጥለው ጥር ወር ጀምሮ ስራቸውን ለመጀመር ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።
የርገን ክሎፕ በቀጣይ በኦስትሪያው የሀይል ሰጪ መጠጥ አምራች ተቋም ስራ ያሉትን ክለቦች እንደሚያማክሩ ተነግሯል።
የክለቦቹን የአጨዋወት ፍልስፍና ፣ የአሰልጣኝ እና ተጨዋቾች ዝውውር እንዲሁም ሌሎች ስፖርታዊ ጉዳዮችን የርገን ክሎፕ እንደሚያማክሩ ተዘግቧል።
“ ከሀያ አምስት አመታት በኋላ አሁን የመጣሁበት ሚና ተቀይሮ ሊሆን ይችላል ነገርግን ለእግርኳስ ያለኝ ፍቅር አይቀንስም “ ሲሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ተናግረዋል።
በቀጣይ ሬድ ቡልን በእግርኳሱ ዘርፍ ባላቸው ሚና መርዳት እንደሚፈልጉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ አያይዘው ገልጸዋል።
የጀርመኑ ክለብ ሌፕዚግን ጨምሮ ሳልዝበርግ ፣ ኒውዮርክ ሬድ ቡል እንዲሁም ሌሎች ክለቦች በተቋሙ ባለቤትነት የተያያዙ ክለቦች ናቸው።
አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በቀጣይ የጀርመን ብሔራዊ ቡድንን የማሰልጠን እድል ካገኙ የመልቀቂያ ፍቃድ እንደሚያገኙ ተጠቁሟል።
በጋዲሳ መገርሳ
መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም
በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ማስተካከያ(ጭማሪ) ተደረገ
"ከመስከረም 28/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በሥራ ላይ የሚውለውን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን ይመለከታል፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ታህሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ባስተላለፈው የነዳጅ ውጤቶች የዋጋ ግንባታ የአፈጻጸም ውሳኔ መሠረት የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በየጊዜው እየተስተካከለ ሥራ ላይ እንዲውል ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
በዚህም መሰረት በአለም ገበያ የታየውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መነሻ በማድረግ ከመስከረም 28/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በሥራ ላይ የሚቆይ የሁሉም የነዳጅ ውጤቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደርጓል፡፡" - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በ2016 የበጀት ዓመት ከ27 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ እንዳጋጠመው ተገለጸ
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በ2016 የበጀት ዓመት ከ27 ሚልዮን ብር በላይ ኪሳራ እንዳጋጠመው በ16ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተገልጿል።
በጠቅላላ ጉባኤው ላይ በቀረበው የፋይናንስ ሪፖርት እንደተገለጸው ከተለያዩ የገቢ ምንጮች 186 ሚልዮን 757 ሺህ 138 ብር ከ73 ሳንቲም ገቢ ተገኝቷል።
በአንፃሩ ለተለያዩ የፌዴሬሽኑ ስራዎች የወጣው ወጪ 214 ሚልዮን 90 ሺህ 240 ብር ከ93 ሳንቲም መሆኑ ተገልጿል።
በዚህም ከገቢ ወጪ 27 ሚልዮን 333 ሺህ 102 ብር ከ20 ሳንቲም ኪሳራ እንዳጋጠመው ተመላክቷል።
በዓመቱ ለሴቶች ዋናው እና የዕድሜ እርከን ቡድኖች 51 ሚልዮን 758 ሺህ 919 ብር ከ08 ሳንቲም ወጪ ሲሆን ለወንዶች ዋናው እና የዕድሜ እርከን ብሔራዊ ቡድኖች ደግሞ በአጠቃላይ 44 ሚልዮን 789 ሺህ 623 ብር ከ90 ሳንቲም ወጪ ሆኗል።
በተለይም ለወንዶች ብሔራዊ ቡድኑ የወጣው አብዛኛው ወጪ በሜዳው ማድረግ የሚገባውን ጨዋታዎች ከሜዳ ውጪ በማድረጉ የተመዘገበ መሆኑ ተገልጿል።
የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ በጉባኤው እንዳሉት ከሆነም ብሔራዊ ቡድኑ ሀገሩ ላይ ጨዋታዎችን ማድረግ ቢችል ኖሮ ቢያንስ ከ22 ሚልዮን ብር በላይ ወጪ ማዳይ ይቻል ነበር።
መጨረሻም የፌዴሬሽኑ ፕሬዝደንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ክለቦች የክለብ ላይሰንሲንግ መስፈርትን በሟሟላት በኩል አበክረው እንዲሰሩ የተናገሩ ሲሆን ይህን ተከትሎ በሚወሰዱ ውሳኔዎች ክለቦችን የጎጥ ጎጆ ውስጥም ከመክተት ሁሉም የቤተ ስራውን ይወጣ ሲሉ መልዕክታቸውንም አስተላልፈዋል።
በጋዲሳ መገርሳ
መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም
የነገ የመስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ፕሮግራሞቻችን
Читать полностью…"ችግር ሲፈጠር ዝም ብለን አንመለከትም" የትግራይ ፀጥታ ኃይሎች
በተፃራሪ መግለጫዎች ምክንያት በትግራይ ውስጥ ማንኛውም የፀጥታ ችግር እና ስርዓት አልበኝነት እንዲፈጠር እንደማይፈቅድ የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች አስታውቋል።
የፀጥታ ሃይሉ ባወጣው አጭር መግለጫ " መስከረም 27 ቀን ጊዚያዊ አስተዳደሩን የሚመለከቱ ሁለት ተፃራሪ መግለጫዎች መውጣታቸውን ተከትሎ በህዝቡ ውስጥ የመረበሽ ስሜት ተፈጥሯል " ብለዋል።
" የትግራይን ሰላም እና ደህንነት እናረጋግጣለን " ያሉት የፀጥታ ኃይሎቹ " በተፃራሪ መግለጫዎች ምክንያት ስርአት አልበኝነት እንዲፈጠር አንፈቅድም ፤ ችግር ሲፈጠርም በዝምታ አንመለከትም " ሲሉ አሳውቀዋል።
በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው ህወሓት ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 13 የጊዚያዊ አስተዳደሩ የስራ ሃላፊዎች በማንሳት በሌሎች 14 የድርጅቱ አባላት እንዲተኩ መወሰኑን ከገለፀ በኋላ ጊዚያዊ አስተዳደሩ " የመንግስት ግልበጣ ነው " ያለው ተግባር የሚያርም " ህጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ " ሲል ማምሻውን አስታውቋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ህጋዊ ሰውነት ማግኘት አልቻልኩም አለ፡፡
የኢትዮጵየ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በዚህ አመት ህጋዊ የሆነ አካል እንዲኖረው ክምርጫ ቦርድ ጋር እንዲሁም ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆነን እየሰራ እንደሆነ ለጣቢያችን አስታውቋል፡፡
የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ደስታ ዲንቃ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ምክር ቤቱ በቃል ኪዳን ሰነዱ መሰረት መመሰረቱን አንስተው ነገር ግን ህጋዊ ሰውነት እንደሌለው ተናግረዋል።
አሁን ግን እንቅስቀሴ መጀመራቸውን እና ጥሩ ሂደት ላይ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
በዚህ ሂደት ራሱን የቻለ በጀት እየተመደበላቸው እንዳለሆነ የሚናገሩት አቶ ደስታ ዲንቃ የተለያዩ ስራዎችን በምንሰራበት ሰዓት ህጋዊ ሰውነታችሁን አሳዩን የሚል ጥያቄ በሚቀርብበት ሰዓት የምናቀርበው ሰነድ ባለመያዛችን ተቸግረናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ታዲያ አሁን ላይ ምከር ቤቱ የፋይናንስ ማኗል እና መሰል እቃዎችን ከሚመለከተው አካል በማስገባት እና በማዘጋጀት አንድ እርምጃ መራመድ መጀመራቸውንም አቶ ደስታ ጨምረው ነግረውናል፡፡
መጋቢት 5 ቀን 2011 ዓ/ም በቃል ኪዳኑ ሰነድ አማካኝነት የጋራ ምክር ቤቱ እንደተቋቋመ የሚታወስ ነው።
ይሁን እንጂ ምክርቤቱ ከተመሰረተ በኋላ ስራዎችን ለመስራት የህጋዊነት ጥያቄ እየተነሳባት መሆኑ በተደጋጋሚ ሲነሳ ቆይቷል።
በለአለም አሰፋ
መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም
ላለፉት ስድስት ዓመታት ኢትዮጵያን በፕሬዚዳንትነት ላገለገሉት ለክብርት ሣሕለ ወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ መንግሥት ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ መገናኛ ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የለውጡ አንዱ ዓላማ ሥርዓትን ማጽናት ነው። የሥራ ኃላፊዎች በሕግ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በተሰጣቸው ጊዜ ይወጣሉ።
ሌሎች ደግሞ በተራቸው እነርሱን ተክተው ሀገራዊ ዓላማን በትውልድ ቅብብል ከግብ ያደርሳሉ። የሀገር ግንባታ የሚሳካው በዚህ መንገድ ነው ብለዋል።
ላለፉት ስድስት ዓመታት ኢትዮጵያን በፕሬዚዳንትነት ላገለገሉት ለክብርት ሣሕለ ወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ መንግሥት ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ ካሉ በኃላ።
በሌላ በኩል ደግሞ፤ ዛሬ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው ኃላፊነት የተቀበሉት ክቡር ታዬ አጽቀ ሥላሴ ሀገርና ሕዝብን በላቀ ሁኔታ የሚያገለግሉበት የኃላፊነት ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ ሲሉ አስፍረዋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም
በዶክተር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራው ህወሓት አቶ ጌታቸው ረዳ ጨምሮ 13 የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ባለስልጣናትን ከስልጣናቸው እንዲወርዱ መወሰኑን አስታወቀ።
በቅርቡ ጉባኤ ያደረገው ይህ የህወሓት ቡድን በምትካቸው የሚሰሩ ያላቸውን አዳዲስ ሹመቶችንም ሰጥቷል።
ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በሊቀመንበርነት የሚመሩት የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ቡድን ዛሬ እንዳስታወቀው መስከረም 24 ቀን 2017 ዓ/ም ባደረገው የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ህወሓትን ወክለው በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ያሉ ባለስልጣናት ከሓላፊነታቸው እንዲወርዱ መወሰኑ ይፋ አድርጓል።
በጊዚያዊ አስተዳደሩ ሃምሳ ሲደመር አንድ ድርሻ እንዳለው የገለፀው የህወሓት ቡድኑ፥ ህወሓትን ወክለው በግዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ፣ የዞን አስተዳደር እና ኤጀንሲዎችና ኮሚሽኖች ያሉ ባለስልጣናት መቀየሩን አስታውቋል።
በዚህ መሰረት የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ እንዴት እና በማን ይተካሉ የሚለው ከፌደራል መንግስቱ እና ከሚመለከታቸው አካላት በመግባባት ይፈፀማል ሲል ህወሓት ዛሬ ባወጣው መግለጫው ይፋ አድርጓል።
ከዚህ በተጨማሪ አቶ በየነ ምክሩ፣ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት፣ ዶክተር ሓጎስ ጎደፋይ ጨምሮ ሌሎች በህወሓት ውክልና ወደ ግዚያዊ አስተዳደሩ የገቡ ባለስልጣናት ማውረዱን የገለፀው የፓርቲው መግለጫ በምትካቸው ደግሞ እነ ዶክተር አብርሃም፣ አቶ አማኑኤል አሰፋ፣ ዶክተር ፍስሃ ሃፍተፅዮን እና ሌሎችን ለተለያዩ ሐላፋነቶች መሾሙ ያትታል።
በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባላት እና ሌሎች በቅርቡ አካሂደውት በነበረ "ህወሓት ማዳን" የተሰኘ ስብሰባ፥ ጉባኤ ያደረገው ህወሓት በሕገወጥነት ፈርጀው በቅርቡ ሌላ ጉባኤ እንደሚያደርጉ ገልፀው እንደነበረ ይታወሳል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም
አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው በአብላጫ ድምፅ ተሹመዋል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ- ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram /channel/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
ከአዲስ መንጃ ፈቃድ ውጭ ያሉ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ ጀምሮ ይታደሱ ተብሏል።
ከአዲስ መንጃ ፈቃድ እና ዕድሜያቸው ከ55 በላይ ከሆኑ ግለሰቦች ውጭ ያሉ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እድሳት ያድርጉ ተብሏል።
ተገልጋዮች መንጃፍቃዳቸውን በየአራት ዓመቱ እንዲያድሱም የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡
ባለሥልጣኑ ባለፉት 6 ዓመታት የመልካም አስተዳደር እና የፍትኃዊነት ጥያቄን ሲያስነሳ የነበረው የሁለት ዓመት እና የአራት ዓመት የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት ጥያቄ ምላሽ ማግኘቱን ገልጿል።
በዚህም ከአዲስ መንጃ ፈቃድ እና ዕድሜያቸው ከ55 በላይ ከሆኑ ግለሰቦች ውጭ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ጀምሮ በአራት ዓመት እንደሚታደሱ አስታውቋል፡፡
አዲስ መንጃ ፈቃድም ከሁለት ዓመት የሙከራ በኋላ፣ ባለው አሰራር መሠረት በየአራት ዓመቱ እንደሚታደስ ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ነገር ግን ዕድሜያቸው ከ55 ዓመት በላይ ለሆኑ ግለሰቦች በየሁለት ዓመት የሚታደስ ሆኖ ክፍያው የአራት ዓመቱ ክፍያ ግማሽ (50%) እንደሚሆን ተመላክቷል።
መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም
በትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ5 ሰዎቸ ላይይ የአካል ጉዳት ደርሷል።
በኮንታ ዞን ጨበራ ሻሾ ቀበሌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ5 ሰዎቸ ላይይ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡
አደጋው ትናንት ሌሊት 7 ሰዓት አካባቢ ከዮራ ሻሾ ቀበሌ በቆሎ ጭኖ ወደ አመያ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ ጨበራ ሻሾ ቀበሌ ላይ በመገልበጡ የደረው ነው፡፡
በዚህም የ2 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን÷ በ5 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን የአመያ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር በቀለ በለጠ ተናግረዋል፡፡
የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሚገኝ መጠቆማቸውንም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም
ዋልያዎቹ ተጋጣሚያቸውን አውቀዋል !
የ 2024 የቻን አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ድልድል በግብፅ ካይሮ ተካሂዷል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን " ዋልያዎቹ " በማጣሪያው በመጀመሪያው ዙር ከኤርትራ ብሔራዊ ቡድን ጋር ተደልድለዋል።
- የመጀመሪያው ዙር :- ኢትዮጵያ ከ ኤርትራ
- ሁለተኛው ዙር :- ኢትዮጵያ / ኤርትራ ከ ታንዛኒያ / ሱዳን
የመጀመሪያ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ ከጥቅምት 15-17 ባሉት ቀናት እንዲሁም የመልስ ጨዋታዎች ከጥቅምት 22-24/2017 ባሉት ቀናት ይደረጋል።
የሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ ከ ታህሳስ 11 - 13 እንዲሁም የመልስ ጨዋታዎች ከታህሳስ 18-20/2017 ባሉት ቀናት ይካሄዳል ።
የ 2024 የአፍሪካ ሀገራት ሻምፒዮን ሽፕ ( ቻን ) ውድድር ከጥር 24 እስከ የካቲት 21/2017 ዓ.ም ይካሄዳል።
የዘንድሮው የቻን ውድድር በኬንያ ፣ ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ አዘጋጅነት በአስራ ዘጠኝ ክለቦች መካከል የሚካሄድ ይሆናል።
በጋዲሳ መገርሳ
መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ ለአንድ ወር የሚቆይ የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ የምዝገባ ዘመቻ በነገው ዕለት ይጀመራል
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽህፈ ቤትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባን በጋራ እንደሚያካሂዱ አሰታወቁ።
ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ ዘሚካኤል ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፣ በአዲስ አበባ የብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገ ዘመቻ ይጀመራል።
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በአዲስ አበባ ከተማ ባጠረ ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ ጠቅሰው፣ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባው ምንም አይነት ክፍያ የለውም ብለዋል።
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የዲጂታል ስትራቴጂ 2025 እቅድ አካል ነው በማለት የሁሉንም ነዋሪ ረቂቅ ባዮሜትሪክ መረጃን በመውሰድ ወደ ልዩ መለያ ከመቀየር ባለፈ ከተሞችን፣ ክልሎችንና ዞኖችን አጣጥሞ ለማስኬድ የሚያስችል ስርዓት ነው ተብሏል።
በመሆኑም የተቀላጠፈ ዘመናዊ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የሲቭል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ስርአት ጋር በተቀናጀ መልኩ ለመተሳሰር ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር ለመስራት ተስማምተዋል።
በመሆኑም ከነገ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ዋና መስሪያ ቤቱን ጨምሮ በኤጀንሲው በሁሉም ወረዳዎች እና ክፍለከተሞች የፋይዳ ምዝገባ እንደሚጀመር ተገልጿል።
ምዝገባው ካሁን በፊት የተመዘገቡ ኗሪዎችን እንደማይመለከት ተገልጿል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም
ኬንያ፣ ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ በጋራ ለሚያዘጋጁት የ2024 የአፍሪካ ሀገራት ሻምፕዮና የማጣርያ ጨዋታዎች ድልድል በነገው ዕለት ይፋ የሚደረግ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንም በነገው ዕለት ተጋጣሚውን የሚያውቅ ይሆናል።
ከጥር 24 እስከ የካቲት 21 2017 በሦስቱ ጎረቤት ሀገራት ለሚካሄደው ውድድር የሜዳ እና ከሜዳ ውጭ ጨዋታዎች ያካተተ የሁለት ዙር የማጣርያ ውድድሮች የሚከናወኑ ሲሆኑ የመጀመርያው ዙር የማጣርያ ጨዋታ በጥቅምት ወር ከ15 እስከ 17 ባሉት ቀናት የሚከናወን ሲሆን የመልሱ ጨዋታ ደግሞ ከጥቅምት 22 እስከ 24 ባሉት ቀናት ይከናወናል።
ብሄራዊ ቡድናችን የመጀመርያው የማጣርያ ጨዋታ የሚሻገር ከሆነ ደግሞ የሁለተኛው ዙር የመጀመርያ የማጣርያ ጨዋታ ከታህሳስ 11 እስከ 13 ባሉት ቀናት አከናውኖ የመልሱን ጨዋታ ከታህሳስ 18 እስከ 20 ባሉት ቀናት ይከውናል።
ከዚህ ቀደም ከተከናወኑ ሰባት ውድድሮች በሦስቱ መሳተፍ የቻለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአልጄርያ አስተናጋጅነት ከተካሄደው የ2023 ውድድር በኋላ በተከታታይ ውድድሮች ላይ ለመሳተፍ ማጣርያውን ያከናውናል።
በጋዲሳ መገርሳ
መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም
ስምንቱ የአዲስ አበባ የሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ስራ ፕሮጀክቶች
1. ካሳንቺስ- እስጢፋኖስ-መስቀል አደባባይ- ሜክሲኮ- ቸርችል-አራት ኪሎ ኮሪደር እና መልሶ ማልማት ስራ (የኮሪደሩ ርዝመት 40.4 ኪ/ሜ)
2. ጫካ ፕሮጀክት (ሳውዝ ጌት)- መገናኛ- ሃያ ሁለት- መስቀል አደባባይ ኮሪደር (የኮሪደሩ ርዝመት 7.1 ኪ.ሜ)
3. ሲኤምሲ- ሰሚት- ጎሮ- ቦሌ ቪአይፒ ተርሚናል ኮሪደር እና የአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል ኮሪደር (የኮሪደሩ ርዝመት 10.8 ኪ.ሜ)
4. ሳር ቤት-ካርል አደባባይ-ብስራተ ገብርኤል-አቦ ማዞሪያ-ላፍቶ አደባባይ-ሃና ፉሪ ኮሪደር (የኮሪደሩ ርዝመት 15.9 ኪ.ሜ)
5. አንበሳ ጋራዥ- ጃክሮስ- ጎሮ ኮሪደር ( የኮሪደሩ ርዝመት 3.1 ኪ.ሜ)
6. አራት ኪሎ- ሽሮ ሜዳ- እንጦጦ ማርያም- እጽዋት ማዕከል ኮሪደር (የኮሪደሩ ርዝመት 13.19 ኪ.ሜ)
7. ቀበና ወንዝ ዳርቻ ልማት ኮሪደር (የኮሪደሩ ርዝመት 20 ኪ.ሜ)
8. እንጦጦ-ፒኮክ ወንዝ ዳርቻ ኮሪደር (የኮሪደሩ ርዝመት 21.5 ኪ.ሜ)
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ ለ628ሺህ ያህል ህጻናት የፖሊዮ ክትባት መሰጠት ተጀመረ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የልጅነት ልምሻ ወይም የፖሊዮ ክትባት በዘመቻ መልክ መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ዮሐንስ ጫላ እንደተናገሩት የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) ቫይረስ በተበከለ ምግብና ውሃ አማካኝት የሚመጣ እና ሕፃናትን ለዘላቂ አካል ጉዳት ብሎም ለሞት የሚዳርግ አደገኛ በሽታ መሆኑን ገልጸዋል።
ጤና ቢሮው ይህንን ለመከላከል በከተማ ደረጃ ከመስከረም 27 ቀን ጀምሮ እስከ 30/2017 ዓ.ም የሚቆይ እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑ ከ628 ሺህ በላይ ህጻናት ክትባት ይሰጣል ብለዋል።
የክትባት ዘመቻው ቤት ለቤት በትምህርት ቤት፣ በሕጻናት ማቆያ፣ በማሳደጊያ እና በሌሎች ሕጻናት በሚገኙባቸው ቦታዎች ሁሉ በዘመቻ መልክ ክትባት ይሰጣል ነው ያሉት።
የፖሊዮ በሽታን መከላከል የሚቻለው በመደበኛ በጤና ተቋማት እና በዘመቻ መልክ የሚሰጠውን ክትባት ሁሉም እድሜቸው ከ5 አመት በታች ያሉ ሕጻናት መከተብ ሲችሉ እንደሆነም ዶክተር ዮሐንስ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በአገር አቀፍ ደረጃ የፖሊዮ ቫይረስን ለመከላከል የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት በከተማዋ ለሚገኙ ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ሕጻናት በሙሉ ክትባት በመስጠት ወረርሽኝ እንዳይከሰት ለማድረግ የክትባት ዘመቻውን ከአንድ ወር በኋላ በሁለተኛ ዙር እንደሚሰጥም ተናግረዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም
የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ከ3መቶ ሺህ በላይ ለሆኑ ህጻናት የፖሊዮ ክትባት ሊሰጥ ነዉ፡፡
የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ዕድሜያቸዉ ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ከ3መቶ46 ሺህ በላይ ህጻናት ክትባቱን ሊሰጥ መሆኑን ለጣቢያችን አስታዉቋል፡፡
ጤና ቢሮዉ በሸገር ከተማ አስተዳደር በሚገኙ 12 ክፍለከተሞች እና 36 ወረዳዎች ዉስጥ ለሚገኙ ህጻናት ቤትለቤት ክትባቱን እንደሚሰጥም ነዉ የገለጸዉ፡፡
በኦሮሚያ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ስጋት መከላከል ባለሙያ አቶ ዳንኤል በቀለ ለጣቢያችን እንደገለጹት በከተማ አስተዳደሩ ከዛሬ ጀምሮ ክትባቱ ይሰጣል፡፡
ክትባቱ ከቤት ለቤት በተጨማሪ ህጻናቱ በተገኙበት የሃይማኖትም ሆነ የትምህርት ተቋማት ዉስጥ እንደሚሰጥ ነዉ የነገሩን፡፡
ክትባቱ አሁን ላይ በዘመቻ የሚሰጠዉ በሸገር ከተማ አስተዳደር መሆኑን ያነሱት አቶ ዳንኤል፤ በኦሮሚያ ክልል ግን ክትባቱ በመደበኝነት እየተሰጠ እንደሚገኝ እና በሸገር ከተማም እንደሚቀጥል ነግረዉናል፡፡
ለክትባቱ ቅድመ ዝግጅት ከ2 ወራት በፊት መጀመሩን ያነሱት ባለሙያዉ ፤ የሚከትቡ እና የሚያስተባብሩ ወደ 1ሺህ 2መቶ የሚሆኑ ባለሙያዎች ስልጠና መዉሰዳቸዉን እና 72 ተቆጣጣሪዎችም ወደ ስራ መግባታቸዉን ተናግረዋል፡፡
አዲስ አበባን ጨምሮ በአማራ፣ አፋር፣ እና ጋምቤላ ክልሎች ለተከታታይ አራት ቀናት ክትባቱ በአገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ ይገኛል፡፡
እስከዳር ግርማ
መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም
ታላቁ ሩጫ በዓለም አትሌቲክስ የውድድር ደረጃዎች ውስጥ ተካተተ
የዓለም አትሌቲክስ አስተዳዳሪ ዎርልድ አትሌቲክስ የ2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10 ኪሎ ሜትር ሩጫን የሌብል ደረጃ ያለው የጎዳና ላይ ውድድር ሲል ዕውቅና ሰጥቶታል።
የአዓለም አትሌቲክስ የሌብል ደረጃ ሲል የሰየማቸው ውድድሮች በጥራት ዝግጅቶችን ከማድረግ፣ ደህንነታቸው የተጠበቀ ከመሆን እና የተሳታፊዎች ውድድሩ ላይ የነበራቸው ቆይታ፣ የከተማ አስተዳደሮች ለዝግጅቱ ያላቸውን ድጋፍ፣ እንዲሁም ዝግጅቱ በአትሌቲክስ ውድድር ዘርፍ አበረታች መድኃኒት ላይ ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑ ተጠቅሷል።
እጅግ በርካታ የሩጫ ውድድሮች ባሉበት ዓለም ይህንን የሌብል ደረጃ ማግኘት ዝግጅቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ያሳየውን ዕድገት እና በዓለማችን ካሉ ቀዳሚ እና ተመራጭ የጎዳና ላይ ውድድሮች መካከል መሆኑን እንደሚያሳይ ተጠቁሟል።
የዓለም አትሌቲክስ አስተዳዳሪው አካል (World Athletics) ውድድሮችን በመመዘን በየዓመቱ ደረጃዎችን የሚሰጥ ሲሆን፤ የመሮጫ ኮርስ ልኬት፣ የውድድር ሠአት ምዝገባ እና የስመጥርና ታዋቂ አትሌቶች ተሳትፎ ከግምት ውስጥ የሚገቡ ጉዳዮች ናቸው ተብሏል።
24ኛው ዙር ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪሜ ህዳር 8 ቀን 2017 በ50 ሺህ ተሳታፊዎች እንደሚካሄድ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መረጃ ያመለክታል።
በጋዲሳ መገርሳ
መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም
ባለፉት 3 ወራት 24ሺ 4 መቶ 28 ዜጎች ከፍልሰት ተመልሰዋል ተባለ።
ከሀምሌ 1 እስከ መስከረም መጨረሻ ከተለያዮ ሀገራት 24 ሺ 4 መቶ 28 ፍልሰተኞች ወደ ሀገር ውስጥ መመለሳቸውን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስተር አስታውቋው።
ከተመላሾቹ መካከል 23 ሺ 5 መቶ 44 የሚሆኑት ከሳዉዲ አረቢያ መሆኑን በሚኒስተር መስሪያ ቤቱ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከል እና የተመላሽ ዜጎች ድጋፍ እና ክትትል መሪ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ደረጄ ተክይበሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።
ከየመን ደግሞ 8 መቶ 10 ፍልሰተኞች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን አንስተዋል።
ከእነዚህ ውስጥ 22 ሺ 3 መቶ 48 ቱ ወንዶች እንደሆኑ እና 1ሺ 8 መቶ 33 የሚሆኑት ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን ጠቅሰዋል ።
ተመላሾቹንም ወደነበሩበት አካባቢ የመመለስ ስራዎች ተሰርተዋል ብለውናል።
ህብረተሰቡም መደበኛ ያልሆነውን የፍልሰት አማራጭ መጠቀም ከፍተኛ ጉዳት እዳለው በመገንዘብ ከእንደዚህ አይነት ድርጊት እንዲቆጠቡ የሚል መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
በሐመረ ፍሬው
መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም
የነገ የመስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ፕሮግራሞቻችን
Читать полностью…አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ማን ናቸው ?
የመጀመሪያ ድግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት አግኝተዋል።
እንግሊዝ ከሚገኘው ላንክስተር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በዓለም አቀፍ ግንኙነት እና በስትራቴጂ ጥናት ሁለተኛ ድግሪያቸውን ወስደዋል።
በተለያዩ ሀገራት አጫጭር የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ፖለቲካል ሳይንስ ሥልጠናዎችን እና ኮርሶችን ወስደዋል።
አምባሳደር ታዬ፤ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ መምሪያ የሥራ ክፍል ፣የምዕራብ አውሮፓ ዋና ክፍል ኃላፊ፣የኢንፎርሜሽን ተጠባባቂ ዳይሬክተር፣ስቶክሆልም የኢፌዲሪ ኤምባሲ በአማካሪነት፣በዋሽንግተን የኢፌዲሪ ኤምባሲ በአማካሪነት።
በሎስአንጀለስ ቆንስል ጀነራል፣ በ1998ዓ.ም ባለሙሉሥልጣን አምባሳደርነት ተሹመዋል፣ በሎስአንጀለስ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት ማዕረግ የቆንስላ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ በአውሮፓ እና አሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል፣ በ2008 ዓ.ም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ሰርተዋል።
በግብፅ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ተጠሪ ሆነው አገልግለዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ሲሰሩ የነበሩት አምባሳደር ታዬ፤ በቅርቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው መሹማቸው የሚታወስ ሲሆን በዛሬው እለት ደግሞ የፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የሥራ ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎ አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሹመዋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት በ2016 በጀት ዓመት 1.8 ቢሊየን ብር የመድኃኒት ዕዳ መሰብሰብ አልቻልኩም አለ።
የመቀሌ እና የሽሬ ቅርንጫፎች ከ 4መቶ10 ሚሊየን ብር በላይ ያልከፈሉት ዕዳ አለባቸው ተብሏል።
በበጀት አመቱ በአዲስ አበባ፣ ትግራይ፣ አማራ፣ ደቡብ፣ ኦሮሚያ እና ሌሎች ክልሎች የሚገኙ 20 ከፍተኛ የጤና ተቋማት ብድራቸውን መመለስ አለመቻላቸው ነው የተገለፀው።
ገንዘቡ ባለመሰብሰቡ የጥሬ ገንዘብ ዕጥረት እንዲኖር አድርጓል ያሉት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ፤ ይህ መሆኑ መደበኛ መድሀኒቶችን እንዳናቀርብ አድርጎናል ብለዋል።
ተቋማቱ ዕዳቸው ከአንድ አመት እስከ አምስት አመት ጊዜ የቆየ መሆኑንም ዶ/ር አብዱልቃድር ገልጸዋል።
አገልግሎቱ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በነበረው ግጭት ለሽሬ እና መቀሌ ቅርንጫፎች ከ1 ቢሊየን 1መቶ 35 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የህክምና ግብአቶችን ማሰራጨቱን አንስተዋል።
ከዚህ ውስጥ 4መቶ10 ሚሊየን ብር የሚሆን የዱቤ ብድር እንዳልተመለሰ ነው ያስታወቁት።
ከዛሬ 5 ዓመት በፊት ብድር የወሰዱ ተቋማት አሁን ላይ ገንዘቡን ቢመልሱ እንኳን የብሩ የመግዛት አቅም ከአሁኑ ጋር የሚገናኝ ባለመሆኑ የታቀዱ የመሰረተ ልማት ስራዎች እንዲጓተቱ ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል።
በእስከዳር ግርማ
መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም