በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
የመሬት አጠቃቀም ስርአት ወጥነት አለመኖር የብዝሀ ህይወት ላይ አደጋ ሆኗል ተባለ።
በምግብ ራስን ለመቻል እና ምርት በብዛት እና በስፋት ለማምረት የሚደረጉ ጥረቶች ምክንያት ብዝሃ ህይወት ችግር ገጥሞታል ተብሏል።
ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር መለሰ ማርዩ የደን መሬቶችን ወደ እርሻ መሬት መቀየር እና ረግረጋማ መሬቶች ላይ የሚደረጉ ሰፈራዎች በስፋት መታየታቸዉን አንስተዋል።
በኢትዮጵያ የስነ ምህዳር መናጋቶች መግጠሙን የሚናገሩት ዶ/ር መለሰ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተፈጠሩ የመሬት መንሸራተት አደጋዎች ለዚህ ማሳያ ነዉ ብለዋል።
ዘለቄታዊ ያልሆነ የመሬት አያያዝ እና አጠቃቀም እንዲሁም ከህግ ዉጪ የሆኑ የአስተራረስ ልኬት የብዝሃ ህይወት መሠረቱን አሳጥቶታል ተብሏል።
በምግብ ራስን ለመቻል በሚል ሀሳብ የተፈጥሮ ደን መሬትን በማጥፋት ለምግብ ሰብል ምርት ማዋል በጥናት ሊመራ የሚገባ ነዉ ሲሉም ገልፀዋል።
ዶ/ር መለሰ አያይዘዉም የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት የነባር አዝእርት ዘር ጥበቃ ላይ በሰፊዉ እየሰራበት መሆኑን አንስተዋል።
ተቋሙ የማህበረሰብ የዘር ባንክ ዉስጥ ነባር ዘሮች ከመያዝ ባሻገር ለአርሶ አደሮች እየሰጠ መሆኑ አሳዉቀዋል።
ቁምነገር አየለ
ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም
ብጉንጅ/ boils
የበሽታ መከላከል አቅማቸው የተዳከመ ሰዎች በዚህ ህመም የመጠቃት እድላቸው ሰፊ መሆኑ ይገለጻል፡፡
በጉርምስና ዕድሜ ላይ በሚገኙ ወጣቶች እና ጎልማሶች ላይ ይህ ችግር በብዛት እንደሚስተዋል ባለሙያዎች ያነሳሉ፡፡
እንዲሁም ከሴቶች ይልቅ በወንዶች ላይ በብዛት እንደሚታይ ይጠቀሳል፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊንየም ሜዲካል ኮሌጅ የቆዳና አባላዘር ክፍል - ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑትን ዶክተር ሳሚያ መተናን ናቸው ፡፡
ብጉንጅ ምንድን ነው ?
ብጉንጅ/ boils ማለት አንድና ከዚያ በላይ የሆኑ የፀጉር መዉጫ ቀዳዳዎች በባክቴሪያ ምክንያት ኢንፌክሽን በሚፈጥርበት ወቅት ቆዳ ስር በመቆጣት፣መግል በመያዝና በማበጥ ህመም እንዲከሰት የሚያደርግ ችግር ነዉ ይላሉ፡፡
እብጠቱ በፍጥነት በማደግና በመግል በመሞላት የህመም ስሜቱ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
መንስኤው ምንድን ነው ?
የበሽታው ዋነኛው መንስኤ” ስታፍሎኮካልስ” የተባለ የባክቴሪያ ዝርያ ሲሆን በአካባቢያችን በመገኘት ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል
የስኳር ህመም እና የሰዉነት የበሽታ መከላከል አቅም መቀነስ ሌሎቹ ተጨማሪ መንስኤዎቹ መሆናቸውንም ይናገራሉ፡፡
ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
- ህመም ያለዉ እብጠት
- በእብጠቱ ዙሪያ ያለው ቆዳ መቅላት
- እብጠቱ መግል እየሞላዉ ሲመጣ የእብጠቱ መጠን መጨመር
- ነጭ ወይም ቢጫ ነገር በእብጠቱ ጫፍ ላይ መታየት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ህክምናዎቹ ምንድን ናቸው
- ቶሎ ቶሎ መታጠብ (ንፅህናን መጠበቅ )
-የሚዋጡ እና በመርፊ የሚሰጡ ፀረ ባክቴሪያ መድሃኒቶችን መውሰድ
- የመግል መቋጠር ሲያጋጥም ደግሞ በአነስተኛ ቀዶ ጥገና ማውጣት
በሽታው ወደ ሰውነት ውስጥ ሰርፆ ታችኛው የቆዳ ክፍል ላይ ከገባ ደግሞ ተኝቶ የመታከም ህክምና ሊሰጥ እንደሚችል አንስተዋል፡፡
በመጨረሻም ህብረተሰቡ ንፅህናውን በአግባቡ በመጠበቅ ከበሽታው እራሱን መከላከል እንዳለበት አና በሽታው ሲከሰት ቁስሉ ላይ በአድ ነገር ከመጠቀም መቆጠብ እንደሚያስፈልግ ዶ/ር ሳሚያ ተናግረዋል፡፡
አቤል እስጢፋኖስ
ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም
6.4 ቢሊየን ትርፍ ማስመዝገቡን ዳሸን ባንክ ገለጸ፡፡
ዳሸን ባንክ ባለፈው በጀት ዓመት 6.4 ቢሊየን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን አስታውቋል፡፡
ባንኩ ባለአክሲዮኖች 31ኛ መደበኛና 26ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በዛሬው እለት በሚሊንየም አዳራሽ ያካሄደ ሲሆን ያለፈው ዓመት የባንኩ የስራ አፈፃፀም፣ የዚህ በጀት ዓመት እቅድና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከባለአክሲዮች ጋር ተወያይቷል፡፡
በበጀት ዓመቱ የዳሸን ባንክ ተቀማጭ የገንዘብ መጠን የ30.9 ቢሊየን ብር እድገት ማስመዝገቡንና የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ መጠን 145.9 ቢሊየን ብር መድረሱን የዳሸን ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ዱላ መኮንን ተናግረዋል፡፡
ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ዘርፍ ለባንኩ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ያበረክተው ድርሻ 11.1 ቢሊየን ብር እንደነበርም ጠቁመዋል፡፡
የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ በበኩላቸው ያለፈው ዓመት ምንም እንኳን የተለያዩ ተግዳሮቶች ቢኖሩም ባንኩ ይህን ተቋቁሞ በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ጠቁመዋል፡፡
የዳሸን ባንክ አጠቃላይ ሃብት ባለፈው በጀት ዓመት የ27 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ ብር 183.7 ቢሊየን መደረሱን ገልፀዋል፡፡
ባንኩ ባለፈው በጀት ዓመት 1.44 ሚሊየን አዳዲስ ደንበኞችን ማግኘት እንደቻለና ይህም ለባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ ዕድገት የበኩሉን አስተዋፅኦ ማበርከቱንም ገልፀዋል፡፡
ባንኩ በአሁኑ ወቅት ከ6.7 ሚሊየን በላይ ደንበኞች እንዳሉትም ተመልክቷል፡፡
የውል ሰው ገዝሙ
ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም
የእስራኤል አየር ኃይል በሰሜናዊ የሊባኖስ አካባቢ በፈጸመው ጥቃት ከሀያ በላይ ሰዎች መገደላቸውን ሊባኖስ አስታውቃለች፡፡
የሊባኖስ የጤና ሚንስቴር እንደገለጸው እስራኤል ብዙም ዒላማ አድርጋው በማታውቀው በሰሜን ሊባኖስ በተፈጸመ የአየር ጥቃት ሳቢያ 21 ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል።
በዚሁ ጥቃት ሌሎች 8 ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ጥቃቱ የተፈጸመበት አካባቢ የእስራኤል ጦር ከሄዝቦላህ ጋር ከሚፋለምበት ሥፍራ ጋር በቅርበት የማይዋሰን እና በዋናነት የክርስቲያኖች መኖሪያ መንደር ነው።
ነዋሪዎች እንደሚሉት ይህ አካባቢ በአብዛኛው ከደቡብ ሊባኖስ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ሰዎች የሚኖሩበት ነው።
በጉዳዩ ላይ የእስራኤል ጦር እስካሁን ምላሽ አልሰጠም።
ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታያኔሁ ግን ሄዝቦላህን በየትኛውም የሊባኖስ አካባቢ “ከገባበት ገብተን እንፋለመዋለን” በማለት ዝተዋል።
“ሁሉም ነገር ዘመቻን ታሳቢ ያደረገ ነው። ይህንን በእስካሁኑ ጉዟችን አሻሽለናል።
በቀጣዮቹ ቀናትም የበለጠ እናሻሽለዋለን” ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትር ኔታኒያሁ ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም
የነገ የጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ፕሮግራሞቻችን
Читать полностью…በሄዝቦላህ የድሮን ጥቃት አራት የእስራኤል ወታደሮች ተገደሉ፡፡
በእስራኤል ጥቃት ደግሞ 51 ሊባኖሳዊያን መገደላቸዉ ነዉ የተገለጸዉ፡፡
በደቡባዊ ሃይፋ በሚገኘዉ የእስራኤል ወታደራዊ ካምፕ ላይ ሄዝቦላህ ባደረሰዉ የአየር ጥቃት አራት ወታደሮች መገደላቸዉ ተገልጿል፡፡
እስራኤል ባለፈዉ ወር በሊባኖስ ሄዝቦላህ ላይ ካደረሰችዉ ጥቃት ወዲህ በጦር ካምፑ ላይ የደረሰ ከፍተኛዉ ጥቃት መሆኑ ነዉ የተገለጸዉ፡፡
የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር እስራኤል በአገሪቱ ላይ በፈጸመችዉ ጥቃት 51 ሰዎች መገደላቸዉን አስታዉቋል፡፡
በጋዛ ፤በሃማስ የሚመራዉ መንግስት እንደገለጸዉ፤ እስራኤል ለመጠለያነት በተዘጋጀ ትምህርት ቤት ላይ ባደረሰችዉ የአየር ጥቃት 15 ህጻናትን ጨምሮ 22 ሰዎች ህይወታቸዉ አልፏል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
እስከዳር ግርማ
ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram /channel/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከፓርቲዎች የቀረበበት ክስን አግባብነት የሌለው ሲል ውድቅ አደረገ
ምክር ቤቱ ከአምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች የቀረበበትን ስልጣንን አለአግባብ የማራዘም ክስ ጊዜውን ያላገናዘበ እና ግልፅ ያልሆነ ሲል ለጣቢያችን ገልጿል።
የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ደስታ ዲንቃ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ የስልጣን ጊዜ ለማራዘም ሲል አመታዊ ስብሰባውን አዛውሮታል ተብሎ የተነሳው ሀሳብ ልክ ያልሆነ የቃል ኪዳን ሰነዱንም በደንብ ያላገናዘብ ነው ብለዋል ።
ምክር ቤቱ የተቆረጠ ቀን ባያስቀምጥም ጠቅላላ ጉባዔ ለማካሄድ ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡
የጋራ ምክር ቤቱ በአገራዊ ጉዳዮች፣ በበጀት እጥረት፣ እንዲሁም በሠራተኞች መልቀቅ ምክንያት ውጥረት ውስጥ በመሆኑ ምክንያት ነው የዘገየው ሲሉ አስረድተዋል።
ከሰሞኑ አምስት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ የጋራ ምክር ቤት አመራር “የህግ ጥሰት ፈጽሟል” ሲሉ ከሰዋል።
የጋራ ምክር ቤቱ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ እንዲያደርግ መጠየቃቸውም የሚታወስ ነው።
ጥያቄውን ያቀረቡት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፣ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ)፣ የዎላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ (ዎብን)፣ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) እና ህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ህብር- ኢትዮጵያ) ናቸው።
ለአለም አሰፋ
ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም
በአነፍናፊ ውሻ የታገዘ ህገ ወጥ የዱር እንስሳት ውጤቶች ዝውውር የሚቆጠጠር ማዕከል ተከፈተ
በአነፍናፊ ውሻ የታገዘ ህገ ወጥ የዱር እንስሳት ውጤቶችን ዝውውር ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ልዩ የቁጥጥር ማዕከል ሥራ መጀመሩ የኢትዮጵያ የዱር እስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ የዱር እስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ከአፍሪካን ዋይልድ ላይፍ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የተከፈተው ማዕከሉ÷ ህገ ወጥ የዱር እንስሳት ውጤቶችን ዝውውር ለመከላከል ያስችላል ተብሏል።
ማእከሉን የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በይፋ ሥራ ያስጀመሩ ሲሆን÷ በመርሀ-ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጂራ፣ የአፍሪካን ዋይልድ ላይፍ ፋውንዴሽን የስራ ሀላፊዎችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 2 ቀን 2017 ዓ.ም
ኮል ፓልመር የወሩ ምርጥ ተጨዋች ሆነ!
የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ2024/25 የውድድር ዘመን የመስከረም ወር ምርጥ ተጨዋች ይፋ ተደርጓል ።
እንግሊዛዊው የቼልሲ የፊት መስመር ተጨዋች ኮል ፓልመር የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የመስከረም ወር ምርጥ ተጨዋች በመባል መመረጥ ችሏል።
ኮል ፓልመር በወሩ ባደረጋቸው አራት የፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች አምስት ግቦችን አስቆጥሮ አንድ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።
በጋዲሳ መገርሳ
ጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram /channel/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
የነገ የጥቅምት 1 ቀን 2016 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ፕሮግራሞቻችን
Читать полностью…ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ ኮሪያ ጋር የሚያገናኟትን የመኪና እና የባቡር መስመሮችን በማቋረጥ ሁለቱን አገራት “ሙሉ በሙሉ ለመለያየት” መወሰኗን ገለጸች።
"ደቡባዊው ድንበር በዘላቂነት ይዘጋል" ያለው የአገሪቱ ጦር፤ በራሱ ድንበር በኩል ያሉ ቦታዎችን ጥበቃ እንደሚያጠናክር አስታውቋል።
በደቡብ ኮሪያ ውስጥ የሚደረጉ የጦርነት ልምምዶች እና የአሜሪካ የኒውክሌር ንብረቶች በአከባቢው በተደጋጋሚ መገኘታቸውን በመግለጽ እርምጃውን "ጦርነትን
ለመግታት ራስን የመከላከል እርምጃ" ሲል የኮሪያ ህዝብ ጦር (ኬፒኤ) ገልጾታል።
ውሳኔው በኮሪያ መካከል ያለው ውጥረት ከዓመታት በኋላ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት በዚህ ወቅት ያለውን ፍጥጫ መባባሱን ያሳያል።
“በኮሪያ ግዛት ላይ ያለው አስቸኳይ ወታደራዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮሪያ ኃይሎች የአገሪቱን ብሔራዊ ደኅንነትን በብቃት ለመጠበቅ የበለጠ ቆራጥ እና ጠንካራ እርምጃ እንዲወስዱ ይጠይቃል” ሲል ኬፒኤ በመንግስታዊው መገናኛ ብዙሃን ኬሲኤንኤ በኩል አስታውቋል።
መግለጫው በአብዛኛው የፒዮንግያንግ የይስሙላ እርምጃ ነው።
ቀደም ብሎም ቢሆን ከሰሜን ኮሪያ ወደ ደቡብ የሚወስዱ መንገዶች እና የባቡር ሃዲዶች እምብዛም ጥቅም ላይ አይውሉም።
መስመሮቹም በሰሜን ኮሪያ ባለስልጣናት ባለፈው ዓመት ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲፈርሱ ተደርገዋል።
ውሳኔው ከደቡብ ኮሪያ ጋር ያላትን ግንኙነት እንድትቀይር በፒዮንግያንግ ላይ ሰፊ ግፊት በጨመረበት እና በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ያበላሹ በርካታ ቀስቃሽ ክስተቶችን ተከትሎ የመጣ ነው።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም
ከአዲስ መንጃ ፈቃድ ውጭ ያሉ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ ጀምሮ ይታደሱ ተብሏል።
ከአዲስ መንጃ ፈቃድ እና ዕድሜያቸው ከ55 በላይ ከሆኑ ግለሰቦች ውጭ ያሉ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እድሳት ያድርጉ ተብሏል።
ተገልጋዮች መንጃፍቃዳቸውን በየአራት ዓመቱ እንዲያድሱም የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡
ባለሥልጣኑ ባለፉት 6 ዓመታት የመልካም አስተዳደር እና የፍትኃዊነት ጥያቄን ሲያስነሳ የነበረው የሁለት ዓመት እና የአራት ዓመት የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት ጥያቄ ምላሽ ማግኘቱን ገልጿል።
በዚህም ከአዲስ መንጃ ፈቃድ እና ዕድሜያቸው ከ55 በላይ ከሆኑ ግለሰቦች ውጭ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ጀምሮ በአራት ዓመት እንደሚታደሱ አስታውቋል፡፡
አዲስ መንጃ ፈቃድም ከሁለት ዓመት የሙከራ በኋላ፣ ባለው አሰራር መሠረት በየአራት ዓመቱ እንደሚታደስ ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ነገር ግን ዕድሜያቸው ከ55 ዓመት በላይ ለሆኑ ግለሰቦች በየሁለት ዓመት የሚታደስ ሆኖ ክፍያው የአራት ዓመቱ ክፍያ ግማሽ (50%) እንደሚሆን ተመላክቷል።
መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም
በትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ5 ሰዎቸ ላይይ የአካል ጉዳት ደርሷል።
በኮንታ ዞን ጨበራ ሻሾ ቀበሌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ5 ሰዎቸ ላይይ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡
አደጋው ትናንት ሌሊት 7 ሰዓት አካባቢ ከዮራ ሻሾ ቀበሌ በቆሎ ጭኖ ወደ አመያ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ ጨበራ ሻሾ ቀበሌ ላይ በመገልበጡ የደረው ነው፡፡
በዚህም የ2 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን÷ በ5 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን የአመያ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር በቀለ በለጠ ተናግረዋል፡፡
የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሚገኝ መጠቆማቸውንም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም
ለጤና መድህን ተጠቃሚዎች ከተማ አስተዳደሩ ከ1ቢሊዮን ብር በላይ ድጎማ እያደረገ ነው ተባለ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ለጤና መድህን ተጠቃሚዎች ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ድጎማ እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል።
በከተማ አስተዳደሩ በየአመቱ የጤና መድን ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ እንደሚገኝ ያስታወቀው ጤና ቢሮው በዚህ አመት ብቻ 2.5 ሚሊዮን ዜጎች ተጠቃሚ ለማድረግ ምዝገባ መጀመሩን አስታውቋል።
የጤና ቢሮው ሀላፊ ዶ/ር ዮሀንስ ጫላ እንደተናገሩት በጤና መድህን ስርአት ተመዝግበው አገልግሎት እየተሰጣቸው ለሚገኙ ዜጎች ለመድሀኒት ብቻ ጤና ቢሮው ለከነማ ፋርማሲ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ እየከፈለ ይገኛል ብለዋል።
ከዚህ በፊት የተመዘገቡና አዲስ ለሚመዘገቡ ዜጎች ለሚቀጥሉት ሁለት ወራት እድሳት እንዲያደርጉ እና እንዲመዘገቡ ጤና ቢሮው ገልጿል።
የጤና መድህን ስርአት የሚጠቀሙ ዜጎች የአገልግሎት እና የክፍያ ገደብ አልተቀመጠም ያሉት ሀላፊው ዜጎች እድሉን እንዲጠቀሙበት አሳስበዋል።
ሄኖክ ወ/ገብርኤል
ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም
የአለም የእጅ መታጠብ ቀን እየተከበረ ይገኛል።
አለም አቀፍ የእጅ መታጠብ ቀን በአለም ለ 16ኛ በሀገራችን ለ11ኛ ጊዜ "ህይወቴን ለመጠበቅ እጄን በሳሙና እና በውሃ እታጠባለሁ"በሚል መሪ መልክት በሀገራችን እየተከበረ ነው።
የዩኒሊቨር ኢትዮጵያ ማኔጅንግ ዳይሬክተር ጆርጅ አውሱ እንሳ፤ የዘንድሮ የአለም እጅ የመታጠብ ቀን "ህይወቴን ለመጠበቅ እጄን በሳሙና እና በውሃ እታጠባለሁ" በሚል መሪ ቃል ይከበራል ብለዋል።
ዳይሬክተሩ፤ 80 በመቶ የሚሆኑት ጀርሞች ከሰው ወደ ሰው እንዲተላለፉና የበርካታ ኢንፌክሽን ምክንያቶችም የእጅ ንጽህና ጉድለት መሆኑን ተናግረዋል።
በባህሪ ለውጥ ላይ የሚያተኩረውና በላይፍቦይ ሳሙና አነሣሽነትና መሪነት የሚሰጠው የንጽሕና አጠባበቅ ትምሀርት፣ እስክ ጥቅምት ወር መጨረሻ ድረስ የሚቀጥል ሲሆን በመላው ኢትዮጵያ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ጋር ለመድረስ ጥረት ይደረጋል ተብሏል ።
ልዑል ወልዴ
ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዉ በአነስተኛ ብድር እና ቁጠባ ተቋማት ላይ ጫና ፈጥሯል ተባለ።
በዝቅተኛ እና መካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ዜጎች የፋይናንስ ምንጭ የሆኑት ተቋማቱ የቁጠባ አገልግሎት ላይ ችግሮች መታየታቸው ተገልጿል።
ኢትዩ ኤፍም ያነጋገራቸው የልዩ ማይክሮ ፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን የኦኘሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘላለም መንገሻ እና የጣና ማይክሮ ፋይናንስ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ እንዳለ ማርቆስ የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከም ተከትሎ ማህበረሰብ ገንዘብን
በቁጠባ ከማስቀመጥ ይልቅ ቋሚ ንብረት ላይ እያዋለዉ መሆኑን አንስተዋል።
ይህ ሁኔታም ተቋማቱ ለደንበኞቻቸዉ ብድር የሚሰጡበትን እድል አጥቦታል ሲሉ ገልፀዋል።
ተቋማቱ በራሳቸው ካለባቸዉ የብድር አቅርቦት እጥረት አንፃር ደግሞ ጫናዉ ከፍ እንደሚልም አንስተዋል።
በተጨማሪም የፀጥታ ችግሮች ባሉባቸው አካባቢዎች ተጠቃሚዎች ገንዘብ ሙሉ ለሙሉ የማዉጣት አዝማሚያዎች መኖራቸዉን ገልፀዋል።
የልዩ ማይክሮ ፋይናንስ የኦኘሬሽን ሀላፊ አቶ ዘላለም ከፀጥታ ችግሮች ጋር ተያይዞ በቅርንጫፍ ቢሮዎች ላይ ስጋቶች በመኖራቸው ለመዝጋት መገደዳቸውን ለጣቢያችን ተናግረዋል።
አቶ እንዳለ በበኩላቸው በገጠር የግብርና ዘርፍ ለሚኖሩ አገልግሎቶች የሰላሙ ሁኔታ በታሰበዉ ልክ ለመስራት ፈታኝ ሆኗል ብለዋል።
ቁምነገር አየለ
ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም
ሳፋሪኮም 'ኤምፔሳ ግሎባል' በተሰኘው በዓለም አቀፍ የክፍያ ስርዓቱ ኢትዮጵያን ማካተቱ ተገለጸ።
የኬንያው የስልክ ኔትዎርክ ኦፕሬተር የሆነው ሳፋሪኮም በ 'ኤም-ፔሳ ግሎባል' በተሰኘው አገልግሎቱ ኢትዮጵያን ማካተቱ ተገልጿል።
ይህም ደንበኞች ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ ልውውጥ እንዲያደርጉ የሚያስችላቸው ነው ተብሏል።
በኬንያ ያሉ ደንበኞች አሁን በኤም-ፔሳ ኢንተርናሽናል ሪሚታንስ በኩል ወደ M-Pesa ኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ ማስተላለፍ ይችላሉ ተብሏል።
በዚህ ትብብር፣ ሁለቱም ሀገራት ያሉ ደንበኞች የ M-Pesa ዋሌት ብቻ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን ይህም በኬንያ የሚኖሩ እና የሚሰሩ ኢትዮጵያውያንን እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚኖሩና የሚሰሩ ኬንያውያን ይጠቅማል ተብሏል።
የM-Pesa ኬንያ ደንበኞች ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ190 በላይ አገሮች በኤም-ፔሳ ግሎባል አገልግሎት አማካኝነት ገንዘብ መላክ እና መቀበል ይችላሉ ተብሏል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ በሚገዙበት እና በሚሸጡበት ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት ከሁለት በመቶ መብለጥ እንደሌለበት አሳሰበ።
ብሔራዊ ባንኩ ይህንን በተመለከተ ለንግድ ባንኮች በደብዳቤ ማሳወቁን ገልጿል።
አዲሱ የምንዛሬ ተመን አሰራር ይፋ መሆኑን ተከትሎ በውጭ ምንዛሬ ገበያው ላይ ያሉ ሂደቶችን ሲከታተል መቆየቱን የገለጸው ብሔራዊ ባንኩ፤ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ መካከል ያለው ልዩነት በዓለም አቀፍ አሰራር መሰረት መሆን እንዳለበት አመልክቷል።
በመሆኑም የውጭ ምንዛሬ መግዣና መሸጫ መካከል ያለው ልዩነት ከሁለት በመቶ በላይ መሆን እንደሌለበት አስታውቋል።
አሁንም ቢሆንም ባንኮች የምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ ዋጋቸውን በራሳቸውና ከደንበኞቻቸው ጋር ባላቸው ስምምነት ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ጠቁሟል።
ንግድ ባንኮች የምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ ዋጋቸውን በተናጠል በየቀኑ ማሳወቃቸውን መቀጠል እንዳለባቸው ጠቅሶ፤ ባንኮች ከውጭ ምንዛሬ ሽያጭ ጋር በተያያዘ የሚጠይቋቸውን ኮሚሽኖች ከምንዛሬ መሸጫ ጋር ሳይሆን በተናጠል ለደንበኞቻቸው እንዲያሳውቁሞ አዝዟል።
እስካሁን በነበረው አሰራርም ንግድ ባንኮች የምንዛሬ መሸጫ ዋጋቸውን ከኮሚሽኑ ጋር ደምረው ያስታውቁ እንደነበር አስታውሶ፤ ንግድ ባንኮች ሁለቱን ጉዳዮች እስከነገ ባለው ባለው ጊዜ ተግባራዊ ሊያደርጉት ይገባል ብሏል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም
የምግብ እና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ግምታዊ ዋጋቸው1ሚሊዮን 5 መቶ 40 ሺ ብር የሚሆ ህገወጥ የምግብ ምርቶችን መያዙን አስታወቀ።
በያዝነው ሩብ አመት ምግብን ከባአድ ነገር ጋር በመቀላቀል ፣ የመጠቀሚያ ጊዚያቸው ያለፈባቸው እና ከደረጃ በታች የሆኑ 1ሚሊዮን 5 መቶ 40 ሺ ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የተለያዩ የምግብ አይነቶች ለህብረተሰቡ ሳይሰራጩ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን አስታውቋል።
የባለስልጣኑ የጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በቃሉ አረጋ
ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የቁጥጥር ስራው ከኦሮሚያ ክልል በጅማ እና በአጋሮ ከደቡብ ምዕራብ ደግሞ በሚዛን አማን እና በቦንጋ ከተሞች ተከናውኗል።
ከተሰበሰቡት ምርቶች መካከል ጁሶች፣ ከረሜላ ፣ጨው፣ ፕላምኘሌት፣ቅቤ እና ማር ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል።
የቁጥጥር ስራውን በተሻለ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ የባለሙያ እጥረቶች መኖራቸውንም ሰምተናል።
የሚደረጉ የቁጥጥር ስራዎች ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ብቻ ተሰቶ የሚሰሩ ስላልሆነ ማህበረሰቡም 8482 ነፃ የስልክ መስመር ላይ ጥቆማዎችን በመስጠት መተባበር እንዳለበት ተጠይቋል።
ሐመረ ፍሬውየምግብ እና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ግምታዊ ዋጋቸው1ሚሊዮን 5 መቶ 40 ሺ ብር የሚሆ ህገወጥ የምግብ ምርቶችን መያዙን አስታወቀ።
በያዝነው ሩብ አመት ምግብን ከባአድ ነገር ጋር በመቀላቀል ፣ የመጠቀሚያ ጊዚያቸው ያለፈባቸው እና ከደረጃ በታች የሆኑ 1ሚሊዮን 5 መቶ 40 ሺ ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የተለያዩ የምግብ አይነቶች ለህብረተሰቡ ሳይሰራጩ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን አስታውቋል።
የባለስልጣኑ የጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በቃሉ አረጋ
ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የቁጥጥር ስራው ከኦሮሚያ ክልል በጅማ እና በአጋሮ ከደቡብ ምዕራብ ደግሞ በሚዛን አማን እና በቦንጋ ከተሞች ተከናውኗል።
ከተሰበሰቡት ምርቶች መካከል ጁሶች፣ ከረሜላ ፣ጨው፣ ፕላምኘሌት፣ቅቤ እና ማር ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል።
የቁጥጥር ስራውን በተሻለ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ የባለሙያ እጥረቶች መኖራቸውንም ሰምተናል።
የሚደረጉ የቁጥጥር ስራዎች ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ብቻ ተሰቶ የሚሰሩ ስላልሆነ ማህበረሰቡም 8482 ነፃ የስልክ መስመር ላይ ጥቆማዎችን በመስጠት መተባበር እንዳለበት ተጠይቋል።
ሐመረ ፍሬው
ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም
የሰንደቅ ዓላማ ቀን ዛሬ እየተከበረ ነው፡፡
17ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ዛሬ በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ ነው ፡፡የሰንደቅ ዓላማ ቀን የጥቅምት ወር በገባ በመጀመሪያው ሰኞ እንደሚከበር ይታወቃል፡፡
በዚህም መሠረት የዘንድሮው የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሐሳብ በዛሬው ዕለት እየተከበረ ይገኛል፡፡
ቀኑ በፌደራል የመንግሥት ተቋማት፣ በክልሎችና በሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች፣ በመከላከያ ሠራዊት ካምፖች እንዲሁም በኢትዮጵያ ኢምባሲዎችና ሚሲዮኖች ይከበራል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም
የነገ የጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ፕሮግራሞቻችን
Читать полностью…ኦክሎክ ሞተርስ ከቻይናው Global-Ucar Technology ጋር በጋራ አብሮ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡
ኦክሎክ ሞተርስ ከቻይናው Global-Ucar Technology Co. Ltd ጋር በ250 ሚሊዬን ዶላር ኢንቨስትመንት በጋራ ለመስራት በዛሬው እለት ተፈራርመዋል፡፡
በ1997 ዓ/ም ምስረታውን ያደረገዉ አክሎክ ሞተርስ ከ Global-ucar Technology Co.Ltd ጋር በሚቀጥሉት አምስት አመት ዉስጥ 20 ሺህ ተሽከርካሪዎችን ለደንበኞች ለማቅረብ ስምምነት ፈፅመዋል፡፡
በተጨማሪም አክሎክ ሞተርስ 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ እንደሆነም ገልፆል፡፡
ድርጅቱ ውሊንግ፣በውጅንና የጂቶር ምርት የሆኑ የተለያዩ ሞዴል ተሽከርካሪዎችን ሀገር ውስጥ በመገጣጠም ላይ እንደሚገኝም አስታውቋል፡፡
ኦክሎክ ሞተርስ ከአሥራ ስድስት በላይ የተለያዩ ሞዴል ተገጣጣሚ ተሸከርካሪዎችን ከውጭ በማስመጣት ሀገር ውስጥ ባስገነባቸው የተሸከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካዎቹ በመገጣጠም ለደንበኞቹ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝም በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ ተመላክቷል፡፡
በአቤል እስጢፋኖስ
መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም
ሄዝቦላህ በርካታ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ተኮሰ
ባለፉት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ ሄዝቦላህ ወደ ሰሜን እስራኤል ተጨማሪ ሮኬቶችን ሲተኮስ እንደነበር ኤፍፒ ዘግቧል፡፡
የእስራኤል ጦር ከሊባኖስ ወደ ላይኛው ገሊላ አካባቢ የተተኮሱ በአጠቃላይ 40 ሮኬቶች መገኘቱን ተናግሯል።
ጥቂቶቹ በእስራኤል ሚሳኤል መከላከያ የከሸፉ ሲሆኑ ሌሎቹ ግን መውደቃቸው ተነግሯል፡፡
ሄዝቦላህ በማያን ባሩክ ኪቡትዝ እና በቤቴ ሂሌል በሁለቱም የሊባኖስ ድንበር አቅራቢያ በሚገኙ የእስራኤል ወታደሮች ላይ ሮኬቶች መተኮሱን አረጋግጧል።
በትናንትናው ዕለት ሁለት የእስራኤል ሲቪሎች የተገደሉበትን የሮኬቶች ጥቃት መፈጸሙን ተናግሯል።
በሌላ ዜና በደቡባዊ ሊባኖስ ደርድጋይያ ከተማ ትናንት ምሽት በእስራኤል በተፈጸመ የአየር ጥቃት አምስት የጤና ባለሙያዎችን መሞታው ተነግሯል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም
ሰሞኑን በተደረገዉ የነዳጅና የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ራይድ የዋጋ ጭማሪ ማድረጉን አስታወቀ
የራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት በመነሻ ያስከፍል በነበረዉ አገልግሎቱ ላይ የ 30 ብር ጭማሪ ማድረጉን አስታዉቋል።
የነዳጅ ዋጋ በመጨመሩ እና በቅርቡ የተደረገዉ የዉጪ ምንዛሪ ማሻሻያ ምክንያት መነሻ ከ ነበረዉ 100 ብር ከትላንት ጀምሮ 130 ብር መሆኑን የሃይብሪድ ዲዛይንስ እና ራንድ መስራችና ስራ አስኪያጅ ሳምራዊት ፍቅሩ በተለይ ለካፒታል ተናግረዋል ።
ከዚህ በተጨማሪ በአዲሱ የዋጋ ማሻሻያዉ በኪሎ ሜትር የ 1 ብር ጭማሪ መድረጉን ካፒታል ዘግቧል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም
ኦቪድ ሪል ስቴት ከራይድ ትራንስፖርት ጋር የራይድ ቤተሰብ መንደርን ለመገንባት ስምምነት ተፈራረመ።
ኦቪድ ሪል ስቴት ለራይድ ሹፌሮች የሚሆን የራይድ ቤተሰብ መንደር በገላን ጎራ ከተማ ለመገንባት በዛሬው ዕለት ስምምነት ተፈራርሟል።
ሁለቱ ተቋማት አዲስ እየተገነባ በሚገኘው የገላን ጎራ ከተማ ውስጥ ለራይድ አሽከርካሪዎች በአጭር ጊዜ ቤቶችን ገንብቶ ለማስረከብ ነው የተስማሙት።
ከዚህ በተጨማሪ ኦቪድ ሪል ስቴት ከሰዋሰው መልቲሚዲያ ጋርም ስምምነት ተፈራርሟል።
በዚህ ስምምነት ከሰዋሰው መልቲሚዲያ ጋር የተፈራረሙ አርቲስቶች በቅናሽ የቤት ባለቤት መሆን እንደሚችሉም ነው የተገለጸው።
ኦቪድ ግሩፕ ከሚያደርገው የቤት ዋጋ ቅናሽ በተጨማሪ ሰዋሰው መልቲሚዲያ የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
ኦቪድ ግሩፕ ከ70 ሺህ በላይ ቤቶችን በተለያዩ ሳይቶች እየገነባ መሆኑን የገለፁት የኦቪድ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ፍሬው በየነ፤ 60 ሺህ የሚሆኑት በገላን ጎራ ከተማ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ግሩፑ ለኩባንያዎች በሚደረግ ሽያጭ ቤቶችን ከተቋማት ጋር በመፈራረም እየገነባ መሆኑን ገልፀው፤ ከሃይብሪድ ዲዛይንስ ኃላ.የተ.የግ. ማህበር እህት ኩባንያ ከሆኑት ራይድ ትራንስፖርት እና ሰዋሰው መልቲሚዲያ ጋር መፈራረማቸውን ነው የገለፁት።
ኦቪድ ግሩፕ ከሁለቱ ተቋማት ጋር በገባው ስምምነት መሠረት 5 ሺህ ቤቶችን በ2 ዓመት ጊዜ ውስጥ ሰርቶ እንደሚያስረከብ አስታውቋል።
በእስከዳር ግርማ
መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ።
በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ ረፋድ 4 :00 ላይ ከጎሮ ወደ ኮዬ እየተጓዘ የነበረ ኮድ 3-69867 ቱርቦ የሆነ የጭነት ተሽከርካሪ ከከተማ አውቶቢስጋር ተጋጭቶ በደረሰ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በተጨማሪ በሰባት ሰዎች ላይ ቀላል እና ከባድ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በቤጂንግ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
አደጋው ዛሬ በረፋዱ 4 ሰዓት አካባቢ መድረሱን የገለጹት ኃላፊው የአደጋው መንስዔ እየተጣራ እንደሚገኝም አመልክተዋል።
የደረሰው አደጋ እጅግ አሰቃቂ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው የሞት አደጋ የደረሰባቸው ሁሉም ሴቶች እንደሆኑ እንዲሁም ዕድሜያቸውም ከ20 እስከ 52 የሚገመቱና ሦስቱ ሴቶች የአውቶቢስ ትኬት በመቁረጥ ላይ እያሉ አደጋው እንደደረሰባቸው ጠቁመው በተሽከሪካሪዎቹም ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል ብለዋል ።
መስከረም 29 ቀን 2017
የነገ የመስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ፕሮግራሞቻችን
Читать полностью…