በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
የ 2024 የአፍሪካ ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ምድብ ተጋጣሚዎች በሞሮኮ የእጣ ማውጣት ስነስርዓት ታውቋል ።
ኢትዮጵያን በአፍሪካ ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር የሚወክለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የምድብ ተጋጣሚዎቹን አውቋል።
ምድብ አንደ
1, ቲፒ ማዜንቤ ( ኮንጎ )
2, AS FAR " ( ሞሮኮ )
3, ኢግሌስ ዴ ላ መዲና ( ሴኔጋል )
4, ዩኒቨርስቲ ዌስተርንስ ኬፕ ( ደቡብ አፍሪካ )
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በምድብ ሁለት ክማሜሎዲ ሰንዳውንስ ( ደቡብ አፍሪካ ) ክቱታንካሙን ( ግብፅ ) ኢና ክኢዶ ኪዊንስ ( ናይጄሪያ ) ጋር ተደልድሏል።
በሁለት ምድብ የሚደረገው ውድድሩ ምድቡን አንደኛ እና ሁለተኛ በመሆን የሚያጠናቅቁ ክለቦች ግማሽ ፍፃሜውን ይቀላቀላሉ።
ኢትዮጵያ በውድድሩ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች እግርኳስ ቡድን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ትወከላለች።
የዘንድሮው የአፍሪካ ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ከጥቅምት 30 እስከ ኅዳር 14/2017 ዓ.ም ሞሮኮ ላይ እንደሚካሄድ ይታወቃል።
ጋዲሳ መገርሳ
ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም
የትግራይ ነጋዴዎች ከሰሜኑ ጦርነት በፊት የወሰዱትን የባንክ ብድር ወለድ እንዲከፍሉ መጠየቃቸዉ ቅሬታ እንደፈጠረባቸው ተሰምቷል።
በትግራይ ክልል ከተማ ደረጃ ያሉ ከፍተኛ የንግዱ ማህበረሰብ አካላት ከጦርነቱ በፊት ለመስራት ከባንክ የተበደሩትን ብር ከነወለዱ እንዲከፍሉ መጠየቃቸዉን የትግራይ ክልል ንግድ እና ኤክስፖርት ኤጀንሲ የህዝብ ግንኘነት ዳይሬክተር ተክሊሽ ገ/ህይወት ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል።
በጦርነቱ ምክንያት ባንኮች በአዋጅ መዘጋታቸዉን ተከትሎ በነጋዴዎች መከፈል የነበረበት የባንክ ብድር ሳይከፈል በመቅረቱ ነዉ ተብሏል።
በዚህም የተጠራቀመዉ የብድር ወለድ ነጋዴዎች ካላቸዉ የጠቅላላ ሀብት መጠን በላይ ሆኖ መገኘቱን የኤጀንሲው ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ገልፀዋል።
ከዚህ ቀደም የትግራይ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት በ2021 ከ31 ቢሊየን ብር የነበረው የንግድ ቤቶች አጠቃላይ ዕዳ አሁን ላይ ከ60 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ገልፆ ነበር።
አቶ ተክሊሽ እንደገለፁት አሁን ላይ ነጋዴዎቹ ባላቸዉ ገንዘብ ተንቀሳቅሰዉ እንዳይሰሩ የክሬዲት ገደብ መመሪያ ተግዳሮት መሆኑን ገልፀዋል።
ኤጀንሲው እነዚህን የነጋዴው ጥያቄዎች በመያዝ ከፊደራል መንግስት ጋር ንግግሮች እንደተደረጉ መሆኑን ገልፀዉ ሆኖም እስካሁን መፍትሄ አልተገኘለትም ብለዋል
በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል ከ 132 ሺህ በላይ ህጋዊ ነጋዴዎች ይገኛሉ።
ቁምነገር አየለ
ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል
1. ዶ/ር ጌዲዮን ጥሞቲዮስ፦ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ሚንስትር
2. ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ፦ የቱርዝም ሚንስቴር ሚንስትር
3. ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ፦ የፍትህ ሚንስቴር ሚንስትር
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram /channel/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
በኢትዮጵያ ከተወለዱ 1 ወር ሳይሞላቸዉ ከ1 መቶሺህ በላይ ጨቅላ ህጻናት ህይወታቸዉን ያጣሉ ተባለ፡፡
ከተወለዱ 28 ቀናት ሳይሞላቸዉ 1መቶ 21ሺህ 7መቶ 33 ጨቅላ ህጻናት ህይወታቸዉን እንደሚያጡ ሰምተናል፡፡
በUSAID- የጨቅላ ህጻናትና ህጻናት ጤና ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ዶክተር ያሬድ ታደሰ፤ለጨቅላ ህጻናቱ ሞት እንደ ምክንያት የተቀመጡ ሶስት ምክንያቶች መኖራቸዉን ይገልጻሉ፡፡
የመጀመሪያዉ ከመወለጃ ቀን ቀድሞ መወለድ፣ በወሊድ ወቅት መታፈንና የጨቅላ ህፃናት ኢንፌክሽን ናቸዉ።
ከማህጸን ከወጡ ባለዉ የመጀመሪያዉ 24 ሰአት ለሞት ተጋላጭ የሚሆኑበት እድል ሰፊ ነዉ የተባለ ሲሆን፤ በቤት ዉስጥ በሚወለዱበት ወቅት ለተለያዩ በሽታዎች ተጋላጭ እንደሚሆኑም ነዉ የተገለጸዉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በአመት ዉስጥ ዕድሜያቸዉ ከአምስት አመት በታች የሆኑ ከ 2 መቶ ሺህ በላይ ህጻናትም በሳንባ ምችና በተቅማጥ ህመም ህይወታቸዉን ያጣሉ ተብሏል፡፡
ጨቅላ ህፃናትን በቤት ዉስጥ እያሉ ጡት በማጥባትና በቂ ምግብ በመስጠት ፤ ለክትባት ወደ ጤና ተቋማት በሚሄዱበት ጊዜም በቂ ቫይታሚን እንዲያገኙ በማድረግ የጨቅላ ህጻናትን ሞት መቀነስ እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡
የጤና ሚኒስቴር የእናቶችና ህፃናት እንዲሁም የአፍላ ወጣቶች ጤናን በተመለከተ ከክልል እንዲሁም ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ለተወጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል ።
ሊዲያ ደሳለኝ
ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም
አሜሪካ በጋዛ 'የረሃብ ፖሊሲ' እንዳይኖር ለማረጋገጥ የእስራኤልን ድርጊት እየተከታተልኩ ነዉ አለች፡፡
እስራኤል በሰሜን ጋዛ የምትወስደውን እርምጃ እየተከታተልኩ ነው ያለችው አሜሪካ“የረሃብ ፖሊሲ” እየተከተለች እንዳልሆነም ለማረጋገጥ እየሰራሁ ነዉ ብላለች፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ መልዕክተኛ ‹‹የእስራኤል መንግስት ፖሊሲያችን ይህ አይደለም ብሎናል፤ ስለዚህ የእስራኤል እየወሰደች ያለችዉ እርምጃ ከዚህ መግለጫ ጋር የሚጣጣም መሆኑን እያየን ነዉ›› ብለዋል።
ይህ ንግግር ከረዥም ጊዜ ወዳጇ እና አጋሯ አሜሪካ የተሰነዘረ የቅርብ ጊዜ ንግግር ሲሆን ፤ቀደም ሲል እስራኤል የጋዛን እርዳታ በ30 ቀናት ዉስጥ የማታሳድግ ከሆነ ወታደራዊ ድጋፍ እንደምትቀንስ አሜሪካ ማስጠንቀቋ ይታወቃል፡፡
እስራኤል የእርዳታ መኪኖች ወደ ጋዛ እየገቡ ነው ያለች ሲሆን ሃማስ በአቅርቦቱ ላይ ጠለፋ ስለሚፈጽም እጥረት ማጋጠሙን ገልጻለች፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግን ሁኔታው "ተስፋ አስቆራጭ" ነዉ ሲል አስጠንቅቋል፡፡
እስራኤል በምስራቃዊ ሊባኖስ በአንድ ሌሊት ተጨማሪ የአየር ጥቃቶችን ማድረሷን እና በ10 ደቂቃ ውስጥ ሰባት ጥቃቶች መፈጸማቸዉንም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
አፎሚያ አሸናፊ
ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም
በ100 ሺህ ብር ጉቦ ስትደራደር የነበረችው የገቢዎች ቢሮ የታክስ ኦዲት ባለሙያ በቁጥጥር ስር ዋለች
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የካ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የታክስ ኦዲት ባለሙያ ሙስና ስትፈፅም እጅ ከፍንጅ ተይዛ በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር መዋሏን የከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
የጽህፈት ቤቱ ባለሙያ የሆነቸው አማረች በላቸው ማሞ ለግብር ከፋይ ግለሰብ ክሊራንስ ለመስጠት በ100 ሺህ ብር ጉቦ ስትደራደር ጥቆማ እንደደረሰው ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።
በደረሰው ጥቆማ መሰረት ክትትል በማድረግ 50 ሺህ ብር ቢሮ ውስጥ ስትቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዛ ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አመልክቷል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም
በሰሜኑ ጦርነት በርካታ ተንቀሳቃሽ ቅርሶች ከአልነጃሺ መስኪድ ተዘርፈዋል ተባለ።
በትግራይ ክልል የሚገኘዉ የአልነጃሺ ታሪካዊና ሀይማኖታዊ መካነ ቅርስ ሶስት አመታት በዘለቀዉ የሰሜኑ ጦርነት መንፈሳዊ ቁሳቁሶች እንዲሁም በመስጂድ የተቀመጡ የቅርስ ይዘት ያላቸዉ መገልገያዎች መጥፋታቸውን ጣቢያችን ሰምቷል።
ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የክልሉ የቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ሀይላይ በየነ አልነጃሺ መስኪድ በጦርነቱ መጠነ ሰፊ ጉዳትን ያስተናገደ ቅርስ ነዉ ብለዋል።
የትግራይ የቱሪዝም ቢሮ በመካነ ቅርሱ በዉስጡ የነበሩ ተንቀሳቃሽ ቅርሶች ላይ ዘረፋ እንደተፈፀመበት ማረጋገጥ መቻሉን ገልፀዋል።
በተጨማሪም በቅርሱ ይዞታ የከባድ መሳሪያ ጥቃት ሰለባ በመሆኑ ምክንያት አደጋ ላይ ወድቆ እንደነበር ተናግረዋል።
አቶ ሃይላይ እንደገለፁት ከሰሜኑ ጦርነት በፊት እድሳት እና የማስፋፊያ ስራዎች ተደርጎለት የነበረዉ ቅርሱ ባለበት አሁናዊ ሁኔታ በድጋሜ ጥገና ለማድረግ ጥናት መደረጉን አንስተዋል።
ከመስከረም ወር አንስቶ የቅርሱ ጥገና ለማስጀመር ጥረቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን የገለፁት አቶ ሀይላል ከሰሞኑ የቅርሱ ጥገና መጀመሩንም ገልፀዋል።
የአልነጃሺ ቅዱስ መስጂድን መልሶ ለመጠገን ከቱርክ ልማት ኤጀንሲ ጋር በትብብር ለመስራት መቻሉም ተገልፆል።
የቱርክ መንግሥት በቀድሞ የቅርሱ እድሳት ስራን መከናወኑ የሚታወስ ነዉ።
ቁምነገር አየለ
ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም
የኢራን ፕሬዝደንት መስዑድ ፔዜሺኪያን እስራኤል ጋዛና ሊባኖስ ዉስጥ የምትፈፅመዉን ግድያ እንድታቆም ወዳጆችዋ ግፊት ያደርጉባት ዘንድ ጠይቀዋል።
ፔዜሺኪያን ከኦማኑ ሡልጣን ሐቲም ቢን ታሪቅ ጋር በሥልክ ባደረጉት ዉይይት «ፅዮናዊ ሥርዓት» ያሏት የእስራኤል ደጋፊዎች በእስራኤል ላይ ተጨማሪ ግፊት ማድረግ አለባቸዉ ብለዋል።
የኢራን ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር አባስ አራግቺ በበኩላቸዉ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ ጋር ባደረጉት የሥልክ ዉይይት እስራኤል ኢራንን ብትመታ ኢራን ለ«ወሳኝና ለፀፀት ለሚዳርግ» አፀፋ ዝግጁናት ብለዋል።
እስራኤል የቴሕራንን የቅርብ ወዳጆች የሐማስና የሒዝቡላሕን መሪዎችን በተከታታይ መግደሏን ለመበቀል ኢራን ባለፈዉ ሳምንት እስራኤልን በ180 ሚሳዬል ደብድባለች።
እስራኤል ኢራንን ለመበቀል እየዛተች ነዉ።
የእስራኤሉ መከላከያ ሚንስትር ዮአቭ ጋላንት የሐገራቸዉ ብቀላ «ገዳይ፣ኢላማዉን መቺና ድንገተኛ» እንደሚሆን ፎክረዉ ነበር ሲል የዘገበው ሮይተርስ ነው።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም
"ውሌ በ23 ይጠናቀቃል ያኔ እለቅላችኋለው ምን እንደሚያስጨንቃችሁ አላውቅም " አሰልጣኝ ገብረ መድህን
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ገብረ መድን ኃይሌ ከጊኒ ጋር ያደረጉትን የደርሶ መልስ ጨዋታ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
ስብስባቸው ትልቅ አለመሆኑን የጠቆሙት አሰልጣኙ “ ሽንፈቱን የዓለም ፍጻሜ አታድርጉት “ ሲሉ “ ጊኒን የገጠምነው ትልቅ ቡድን ይዘን አይደለም ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ይዘን ነው “። ብለዋል
ከኮንትራት እና የብሔራዊ ቡድን ቆይታ ጋር በተያያዘ ምላሽ ሲሰጡም ውላቸው በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ በመጠቆም “ ያኔ እለቅላችኋለው ምን እንደሚያስጨንቃችሁ አላውቅም " የሚል ምላሽን ሰጥተዋል።
ውጤቱ መጋነን እንዴለለበት የገለፁት አሰልጣኙ “ 7ለ1 ተሸነፍን ተብሎ መጋነን የለበትም ክሬዲት ለማሳጣት እንዳይሆን 8 ለ0 ተሸንፈንም እናውቃለን " ሲሉ ተደምጠዋል።
ጋዲሳ መገርሳ
ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም
በአማራ ክልል ከ4 ሺ 3 መቶ በላይ የኮሌራ በሸታ ህሙማን ሪፖርት መደረጉ ተገለፀ፡፡
በአማራ ክልል በተለያዩ ዞኖች እና ወረዳዎች በተከሰተዉ የኮሌራ በሽታ ከመጋቢት 27/ 2016 ጀምሮ እስከ ጥቅምት 5/2017 ከ4 ሺ3 መቶ 81 ሰዎች በላይ በበሽታው መያዛቸውን የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡
በኢንስቲትዩቱ የበሽታዎች እና የጤና ሁኔታዎች ምላሽ አፈፃፀም ባለሙያ ሲስተር ሰፊ ደርብ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በበሽታው ከተያዙት ውሰጥ 66 የሚሆኑት ለሞት መዳረጋቸውን ገልፀዋል፡፡
በክልሉ 19 ዞኖች ላይ ወረርሺኙ መከሰቱን እና ከነዛም መካከል ምእራብ ጎንደር፣ ጎንደር ከተማ አስተዳደር፣ ባህርዳር ከተማ፣ማእከላዊ ጎንደር፣ሰሜን ጎጃም ፣ወልዲያ ከተማ፣ወልቃይት ጠገዴ ስቲት ሁምራ ዞን ተጠቃሽ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
ችግሩን ለመቅረፍ በተሰሩ ስራዎች የወረርሺኙ መጠን እየቀነሰ መምጣቱን የገለፁት ሲስተር ሰፊዳር በተመረጡ እና ወረርሸኙ በመጠኑ ጨምሮ በታየባቸው ሁለት ወረዳዎች የኮሌራ ክትባት ዘምቻ መካሂዱን ጠቅሰዋል፡፡
እንዲሁም የውሃ ማከሚያ ኬሚካል የማሰራጨት ስራ መስራቱን ነግረውናል ፡፡
የሚመለከታቸው አካላትም ተጨማሪ ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች የኮሌራ ክትባት የሚሰጥበት ሁኔታዎችን ቢያመቻቹ እና ህብረተሰቡ በብዛት ተሰብስቦ በሚኖርባቸው ስፍራዎች በቂ የሆነ የውሃ አቅርቦት ቢያዘጋጁ የሚል መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
አቤል እስጤፋኖስ
ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም
በህንድ ሐሰተኛ የቦምብ ጥቃት ማስፈራሪያ በመሰንዘሩ በርካታ በረራዎች ለረጅም ሰዓታት እንዲዘገዩ እና አቅጣጫቸውን እንዲቀይሩ ተደርገዋል፡፡
ባለፉት 48 ሰዓታት ውስጥ ቢያንስ 10 የሕንድ አውሮፕላኖች ላይ ሐሰተኛ የቦምብ ጥቃት ማስፈራሪያ በመሰንዘሩ ምክንያት በርካታ በረራዎች ለረጅም ሰዓታት እንዲዘገዩ እና አቅጣጫቸውን እንዲቀይሩ መገደዳቸውን ተዘግቧል፡፡
ከሰዓታት በፊት ከዴልሂ ወደ ቺካጎ የሚሄደው አውሮኘላን ለቅድመ ጥንቃቄ ሲባል በካናዳ አውሮኘላን ማረፊያ አርፏል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ሰኞ ዕለት ከሙምባይ የተነሱ ሦስት ዓለም አቀፍ በረራዎች ላይ የቦምብ ጥቃት ዛቻ በኤክስ (ትዊተር) ላይ ከተሰነዘረ በኋላ አቅጣጫቸውን እንዲቀይሩ ተደርጓል።
ከዚህ መልዕክት ጋር በተያያዘ ፖሊስ አንድ ታዳጊን በቁጥጥር ስር አውሏል።
በተመሳሳይ ማክሰኞ ሁለቱን የኤር ህንድ አውሮኘላንን ጨምሮ ሰባት በረራዎች ከX በተሰነዘሩ ዛቻዎች በረራቸው ተራዝሟል፡፡
በህንድ አየር መንገዶች ላይ የሚደርሰው የሃክስ ቦምብ ዛቻ የተለመደ ነው ያለው ቢቢሲ የመንግስት ሲቪል አቬዬሽን ጀነራል ዳይሬክቶሬት እና የሲቪል አቬዬሽን ደህንነት ቢሮ ሃላፊዎች እስካሁን ምንም ምላሽ አልተሰጠም ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በሕንድ አየር መንገዶች ላይ የሚሰነዘር ሐሰተኛ የቦምብ ጥቃት ዛቻ ያልተለመደ ነገር አይደለም፤ ነገር ግን ከሰኞ ጀምሮ አሁን በድንገተኛ ሁኔታ የጨመረውን የቦምብ ጥቃት ማስፈራሪያ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ግልፅ አይደለም።
አፎሚያ አሸናፊ
ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም
እስራኤል የጋዛን ዕርዳታ በ30 ቀናት ውስጥ የማታሳድግ ከሆነ የምታደርገውን ወታደራዊ ድጋፍ እንደምትቀንስ አሜሪካ አስጠነቀቀች፡፡
እስራኤል ወደ ጋዛ የሚገባውን የሰብዓዊ ዕርዳታ ተደራሽነት በአንድ ወር ውስጥ የማታሳድግ ከሆነ አሜሪካ ወታደራዊ ድጋፏን እንደምትቀንስ አሜሪካ አስጠነቀቀች።
እስራኤል በጋዛ በምታደርገው ጦርነት የጀርባ አጥንት የሆነችው አሜሪካ ይህንን ለማስተካከከል የ30 ቀናት ቀነ ገደብ ማስቀመጧን በደብዳቤ ገልጻለች።
እስራኤል በሰሜናዊ ጋዛ እንደገና በጀመረችው የተቀናጀ እና የማያባራ ጥቃት በርካታ ፍልስጤማውያን መሞታቸው እየተዘገበ ባለበት ወቅት ነው አሜሪካ ይህንን ጠንከር ያለ ነው የተባለውን ደብዳቤ ለአጋሯ እና ወዳጇ እሰራኤል የጻፈችው ብሏል አልጀዚራ።
አሜሪካ በጋዛ እያሽቆለቆለ ያለው የሰብዓዊ ሁኔታ ክፉኛ እንደሚያሳስባት የገለጸው ደብዳቤው አክሎም እስራኤል በሰሜን እና በደቡባዊ ጋዛ 90 በመቶ የሚሆነውን ሰብዓዊ እንቅስቃሴ መከልከሏን እንዲሁም ማገዷን ዕሁድ ጥቅምት 3/ 2017 ዓ.ም የተጻፈው ደብዳቤ አስፍሯል።
እስራኤል የደረሳትን ደብዳቤ እየገመገመችው እንደሆነ አንድ ባለስልጣኗ አስታውቀው አገራቸው “ይህንን በቁም ነገር እንደምትመለከተው” እና ከአሜሪካ አቻዎቻቸው ጋር “የተነሱባቸውን ስጋቶች” ለመፍታት አቅደናል ብለዋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም
በዛሬው ዕለት ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET248 ድሬዳዋ አየር ማረፍያ ለማረፍ በዝግጅት ላይ ሳለ በአውሮፕላኑ ውስጥ ጢስ ታይቱ እንደነበር የኢትዩጲያ አየር መንገድ አሳወቀ፡፡
በዚህም ምክንያት አውሮፕላኑ በድሬዳዋ አየር ማረፍያ በሰላም እንዲያርፍ በማድረግ መንገደኞችን ከአውሮፕላኑ ማውረድ መቻሉንም ባወጣው መረጃ ገልፃል፡፡
አየር መንገዱ ጢሱ የተነሳበትን ምክንያት በማጣራት ላይ ነው ብሏል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው ክስተት መንገደኞቹን ከወዲሁ ይቅርታ ጠይቋል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram /channel/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
ኩላሊት ከሞተ ሰው እንዲወሰድ የሚረዳው የህግ ማዕቀፍ መልስ ሳያገኝ ስድስት አመታት መቆጠሩ ተነገረ
የኩላሊት ንቅለ ተከላ ለማድረግ የኩላሊት ልገሳን ከቤተሰብ ውጭ እንዲለገስ የማይፈቅደው የኢትዮጵያ የጤና ህግ እንዲሻሻል ቢጠየቅም መልስ አለማግኘቱ ችግር እንደሆነ ተነግሯል።
በቅርቡ በተወካዮች ምክር ቤት የጤና ህጎች ረቂቅ አዋጅ መቅረቡ የሚታወስ ሲሆን ስለ ኩላሊት ልገሳ የሚያወራው ህግ ግን እስካሁን እንዳልቀረበ በኩላሊት ተካሚዎች ማህበር በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ኩላሊት ከሞተ ሰው እንዲወሰድ የሚረዳ የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር ላለፉት ስድስት ዓመታት እየተጠየቀ ቢቀጠልም እስካሁን ተግባራዊ መሆን እንዳልተቻለም አስታውቀዋል።
ከቤተሰብ የሚደረገው የልገሳ ሂደትም በለጋሽ በኩል በሚያጋጥሙ ህመሞች እና ከለጋሽ ጋር ባለመመሳሰል ምክንያት የንቅለ ተከላ አለመሳካቶች ይስተዋላሉ ተብሏል።
በተደጋጋሚ ለተወካዮች ምክር ቤት ረቂቁ ይቀርባል የሚል መልስ እንደሚሰጣቸው የሚናገሩት አቶ ሰለሞን እስካሁን ግን ጠብ ያለ ነገር የለም ሲሉ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ የአይን ብሌን ልገሳ ሰዎች በህይወት እያሉ ወደውና ፈቅደው በሚፈርሙት መሰረት ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ ልገሳ ማካሄድ እየተሰራበት እንደሚገኝ አንስተው ለኩላሊትም ተመሳሳዩን መደረግ ይገባዋል ብለዋል።
ለአለም አሰፋ
ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም
የኢራን አየር መንገድ ወደ አውሮፓ የሚያደርገውን በረራ ሙሉ በሙሉ ማቋረጡ ተሰማ
የኢራን ሲቪል አቪዬሽን እንዳስታወቀው ወደ አውሮፓ ህብረት አባል አገራት የሚደረጉ በረራዎች ተቋርጠዋል።
ቴህራን እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው የህብረቱን ማዕቀብ ተከትሎ ነው።
የአውሮፓ ህብረት የኢራን አየር መንገድ የጦር መሳሪያ ወደ ሩሲያ ያጓጉዛል በሚል ነው ማዕቀብ የጣለው።
ህብረቱ በተለይም ሚሳኤልና ድሮኖችን ለ ሞስኮ ያቀብላል ብሏል።
ኢራን ግን የአውሮፓ ህብረትን ክስ አትቀበልም።
በመሆኑም ሁኔታዎች እስከሚስተካከሉ ድረስ ወደ አውሮፓ የሚደረጉ በረራዎችን ለመሰረዝ መገደዷን ፕሬስ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
አባቱ መረቀ
ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም
እንግሊዛዊዉ ጃክ ዊልሸር የኖርዊች ሲቲን ዋና ቡድን ለማሰልጠን ከ ስምምነት ደርሷል ።
የአርሰናል ከ18 አመት በታች ቡድን አሰልጣኙ የኖርዊች ሲቲ ሀላፊነትን በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ እንደሚረከብ ተገልጿል።
የ32 አመቱ አማካይ ኖርዊች በቻምፒየን ሺፑ በነገው እለት ከስቶክ ሲቲ ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ ለመምራት ግን መድረስ እንደማይችል ተነግሯል።
የመድፈኞቹ ከ18 አመት በታች ቡድን ከ አስቶን ቪላ በሚያደርገው ጨዋታ ቡድኑን ይመራልም ተብሏል።
ዊልሺየር ባሳለፍነው ወር ኖርዊች ሲቲን በመልቀቅ ስቶክ ሲቲን የተቀላቀሉትን አሰልጣኝ ናርሲስ ፔላች እንደሚተካም ታውቋል።
የቀድሞ የመድፈኞቹ እና እንግሊዝ አማካይ የረጅም ጊዜ ኮንትራት እንደሚፈርም እና የካሳ ክፍያ ጉዳይ አሳሳቢ እንዳልሆነ ተነግሯል።
ጋዲሳ መገርሳ
ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም
እዉነት ሲንዋር መሞቱ ከተረጋገጠ አኔ በግሌ አይናፍቀኝም-የኔቶ ዋና ፀኃፊ ማርክ ሩት !
የጦርነቱ ፍጻሜ ሳይሆን የፍፃሜዉ መጀረመሪ ነዉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንየሁ ተናገሩ፡፡
አሁን ያህያ ሲነዋር ልክ እነደ ሀኒየ ሁሉ አሸልበዋል፡፡
ዕስራኤላዉያንና ወዳጆቻቸዉ ፈንጠዝያ ላይ ፍልስጤማዉያንና አጋሮቻቸዉ ደግሞ በሐዘን ተዉጠዋል፡፡
የፋርሶቹና የቀጠናዉ ሃይሎች መግለጫና የመልስ ምት እየተጠበቀ ነዉ፡፡
እስራኤል ከአንድ ዓመት በላይ ስታድነው የነበረው የሐማስ የፖለቲካ መሪ ያህያ ሲንዋር መገደልን ተከትሎ መገደሉ ትልቅ ድል ቢሆንም የጦርነቱ መጨረሻ አይደለም በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ተናገሩ።
ከጥቂት ወራት በፊት ቴህራን በሚገኘው መኖሪያ ቤት የተገደሉት የሐማሱን መሪ ኢስማኤል ሃኒያን ተክቶ የመሪነት ቦታ የያዘው ሲንዋር በደቡባዊ ጋዛ መገደሉን እስራኤል አስታውቃለች።
ሐማስ ስለ መሪው ግድያ እስካሁን የሰጠው መግለጫ የለም።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ወታደሮቻቸውን አወድሰው ለአገራቸው ትልቅ ድል መቀዳጀት ቢሆንም የጦርነቱ መጨረሻ እንዳልሆነ ግልጽ አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጋዛ ታግተው ያሉ እስራኤላውያንን ወደየቤታቸው እንደሚመልሱ ለቤተሰቦቻቸው ቃል ገብተዋል።
በደቡባዊ ጋዛ ራፋህ የእስራኤል ወታደሮች የተገደለው ሲንዋር በልዩ ሁኔታ በታቀደ ዘመቻ እንዳልተገደለ ተገልጿል።
ከስፍራው የተነሱ ምስሎች ሲንዋርን የሚመስል አስክሬን በታንክ በተመታ የህንጻ
ፍርስራሽ ስር የትጥቅ ልብስ ለብሶ አሳይተዋል።
የግለሰቡ አስክሬን ጭንቅላት ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች የተጋሩ አሰቃቂ ምስሎች ያሳያሉ።
የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት በወቅቱ ተገድሎ ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ ቢሰጥም ነገር ግን ከአንድ ዓመት በላይ ሲያድነው የነበረውን ግለሰብ ሞት ለማረጋገጥ ዲኤንኤ ምርመራ ማድረግ ነበረበት።
አቡ ኢብራሂም በሚል በስፋት የሚታወቀው ያህያ ሲንዋር፣ ሐማስ ባለፈው ዓመት መስከረም ወር መጨረሻ በእስራኤል ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ካቀነባበሩ አንዱ ነው።
ሲንዋር ከአውሮፓውያኑ 2017 ጀምሮ በጋዛ ሰርጥ የቡድኑ መሪ ሆኖ ሲያገለግል የቆየ ሲሆን፣ ከሃኒያ ግድያ በኋላ የቡድኑ ፖለቲካዊ ክንፍ ኃላፊም ሆኖ እየሠራ ነበር።
ሲንዋር ወደ ጋዛ እንደተመለሰ መሪ ሆነ።
ሲንዋር የሐማስ መሥራች መሆኑ እና ረዥም ዓመታትን በእስር ቤት ማሳለፉ መሪ እንዲሆን መንገድ ጠርጎለታል።
ተንታኞች በሐማስ ፖለቲካዊ እና በወታደራዊው ክንፍ አልቃስም ብርጌድ መካከል ቁልፉ ሁነኛው ሰው ሲንዋር ነው ይላሉ።
ይህም ብቻ አይደለም የሱኒ አረብ ድርጅት የሆነው ሐማስ፤ የሺዓ አገር ከሆነችው ኢራን ጋር ግንኙነት እንዲያደረጅ ያደረገ ቁልፉ ሰው ሲንዋር ነው ይባላል።
ተንታኞች የሚስማሙበት ዋናው ጥያቄ ግን እስራኤል አሁን እያካሄደች ያለውን ወታደራዊ ዘመቻ ስታጠናቅቅ ጋዛ ምን ትሆናለች የሚለው ነው።
አባቱ መረቀ
ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም
#ሰበር ዜና
የሐማስ መሪ ሲንዋር መገደሉን እስራኤል አሳወቀች
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሃማስ መሪ ያህያ ሲንዋር በጋዛ መገደሉን ተናግረዋል።
የሐማስ መሪ ዛሬ በእስራኤል ወታደሮች ተገድሏል ካሉ በኃላ ጥቅምት 7 ቀን ለተፈጸመው ጭፍጨፋ ዋና መሪ ሲሉም ገልፀውታል።
ካትዝ አያይዘውም “ይህ ለእስራኤል ጉልህ የሆነ ወታደራዊ እና የሞራል ስኬት እና መላው የነፃው አለም ትልቅ ድል ነው ብለዋል።
"የሲንዋርን መገደል ታጋቾቹ በአስቸኳይ እንዲፈቱ እድል ይከፍታል እናም በጋዛ ውስጥ አዲስ የውጥ መንገድ ይከፍታል - ያለ ሃማስ እና ያለ ኢራን ቁጥጥር"ነው ያሉት።
ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም
የነገ የጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ፕሮግራሞቻችን
Читать полностью…ለ 1.5 ሚሊዮን ግለሰዎች በነፃ "የሚልየነሮች መንገድ" የተሰኘ ተግባር ተኮር ስልጠና ሊሰጥ ነው።
ይህ "የሚልየነሮች መንገድ" የተሰኘውን ስልጠና በበይነ መረብ እና በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ራዲዮ ለማሰራጨት የበላይ አትክልትና አስቤዛ ማዕከል በዛሬው እለት ስምምነት አድርገዋል፡፡
በርካታ ወጣቶች ስራ አጥ በሆኑባት ሀገር እና ምን ልስራ ብለው ግራ በተጋቡበት በዚህ ወቅት እንዲህ አይነት ይዘቶች ለህዝቡ መቅረባቸው የሚበረታታ ነው ብለዋል የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ራዲዮ ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ መሰለ ገ/ህይወት ፡፡
የኢትዮጵያውያን የሆነው ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ለሀገር፣ለትውልድ የሚጠቅም በመሆኑ አስፈላጊው እገዛ ያደርጋል ብለዋል።
የፕሮግራሙ አላማ ግለሰዎች ባሉበት ሆነው የህይወታቸውን ግብ መምታት እንዲችሉና ‹‹የአይቻልምን ስብዕናን›› ወደ ‹‹ ይቻላል ›› መንፈሰ መቀየር ነው ያሉት የበላይ አስቤዛና አትክልት የንግድ ድርጅት መስራች እና ስራ አስኪያጅ አቶ በላይ ሞሪድ ።"የሚሊየነሮች መንገድ ለመከተል ያለን ነገር በቂ ነው"ብለዋል፡፡
ይህ ማዕከል ከዚህ ልምድ በመነሳት በቀጣይ ሁለት ዓመታት ውስጥ ብቻ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዜጎችን በተግባርና በተጨባጭ ወደ ሚሊየነርነት የሚቀይር በልምድ የተረጋገጠ «የሚኒየነሮች መንገድ» የተሰኘ ፕሮጀክት በመንደፍ የቢዝነስ ፕላን በማዘጋጀት ለወጣቶች ፣ ለጀማሪ ነጋዴዎች እና በንግድ ሥራ ላይ ተሰማርተዉ ያሉ አምራችና አከፋፋዮች ሲጠቀሙበት የሥራ አጥ ቁጥርን በመቀነስ የስራ ባህላችንን ይበልጥ የሚያሳድግ ፕሮጀክት ላይ ኢንቨስት እያደረገ እንደሚገኝ ተነግሯል።
በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢች 5 ትላልቅ ድርጅቶች ከፍተን ከ70 ሺህ በላይ ደንበኛ አፍርተናል ለበርካታ ሰራተኞች የስራ እድል ፍጥረናል ብለዋል አቶ በላይ ሞሪድ፡፡
ይህ ፕሮግራም በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ዘወትር ቅዳሜ ከቀኑ 10 ሰዓት እስከ 12 ሰዓት ለሁለት ሰዓት የሚተላለፍ ሲሆን ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ .ም ጀምሮ ስርጭት ይጀምራል ተብሏል ።
ለአካል ጉዳተኞች፣ መስማትና ማየት ለተሳናቸው ግለሰዎች ስልጠናውን ሊከታተሉበት የሚችሉበት አማራጭ መዘጋጀቱ ተገልጻል፡፡
በስልጠናው ለመሳተፍ እንዴት መመዝገብ ይቻላል እና በምን አማራጭ የሚለው በቅርቡ እናሳውቃለን ብለዋል፡፡
ልኡል ወልዴ
ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም
የራስ መንገድ ፊልም በቴሌ ቲቪ መተግበሪያ ከዛሬ ጀምሮ መታየት ይጀመራል ፡፡
ፊልሙ በቴሌ ቲቪ መተግበሪያ እንዲታይ ከኢግልላዬን ሲስተም ቴክኖሎጂ ጋር ስምምነት ፊርማ ተካሂዶል፡፡
አንጋፋ ተዋንያን እና ባለሙያዎችን የተሳተፉበት የራስ መንገድ ፊልም በቴሌ ቲቪ መተግበሪያ ከዛሬ ጀምሮ መታየት እንደሚጀምር አዘጋጆቹ በዛሬ ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አሳወቀዋል፡፡
አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ በድርሰት እና በአዘጋጅነት የተሳተፈበት የራስ መንገድ ፊልም በሳቤሳ ፊልምስ ተሰርቶ፡ በዳይሪክተር ኦፍ ፎቶግራፊ ባለሙያነት ሰዉ መሆን ይስማዉ ተሳትፎበታል ፡፡
በተጨማሪም የሀገራችን እዉቅ ተዋናያዎች የሆኑት ሳምሶን ታደሰ ፡ፍፁም ፀጋዬ፡ሮማን በፍቃዱ እናሌሎችም የፊልም ባለሙያዎች ተዉነዉበታል ፡፡
የራስ መንገድ ፊልም pan African Filme festival ላይ ምርጥ 25 ዉስጥ በመግባት የምስክር ወረቀት አግኝቶል ፡፡
ቴሌ ቲቪ የሚባል አፕ የተመረጡ ደረጃቸውን የጠበቁ አማርኛ ፊልሞችን ለእይታ የሚያበቃ ሲሆን እነዚህን ፊልሞች ለማየት በሀገር ውስጥ በቴሌ ብር በውጭ ሀገር፣ በማስተር ካርድ፣ ቪዛ እና በአሜሪካን ኤክስፕረስ የክፍያ አማራጮች ክፍያዎችን መፈፀም ያስችላል፡፡
አቤል እስጢፋኖስ
ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም
የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ከታችኛው ተፋሰሰ አገራት በኩል ለሚነሱ ጥያቄዎች ኢትዮጵያ ብቻዋን እንዳትቆም የሚረዳ ነዉ ተባለ
የናይል ወንዝ ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ባለፉት አስርተ አመታት በርካታ ሂደቶችን አልፎ ከጥቅምት 3/2017 ዓ.ም ጀምሮ ህጋዊ ማዕቀፍ ሆኖ እንደሚተገበር ተነግሯል፡፡
አዲሱ የህግ ማዕቀፍ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ሆኖ ኢትዮጵያ ደግሞ ለናይል ወንዝ እያበረከተችው ባለው አስተዋጽኦ ልክ ተጠቃሚነቷን በከፍተኛ ደረጃ የሚያረጋግጥ ነው ተብሏል፡፡
በጉዳዩ ላይ ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት አምባሳደር ጥሩነህ ዜና የማእቀፉ ትግበራ የቅኚ ገዢወችን ሴራ ያስቀረ ነዉ ይላሉ፡፡
ኢትዮጵያ ከአባይ ወንዝ ተጠቃሚ ለመሆን ለአማታት ብቻዋን ስትሟገት ነበተር ሚሉት አምባሳደር ጥሩነህ የተፋሰሱ ሀገራት ወደ ትግበራ መግባታቸዉ ኢትዮጵያ ብቻዋን እንዳትቆም የሚያረገግጥ ነዉ ብለዋል፡፡
ግብጽና ሱዳን የማእቀፉ ተግባራዊ መሆንን እንደማይቀበሉ ባወጡት መግለጫ አስታዉቀዋል፡፡
ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያበ ቀጣይ ብዙ የቤት መስራት እንዳለባት አሳስበዋል፡፡
የማቅፉን ወደ ትግበራ መግባት አስመልክተዉ ማብራሪያ የሰጡት የዉሃና ኢነርጂ ሚኒስትርሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ በእኩል የመጠቀመን ጥያቄ የመለሰ ነዉ ብለዉታል፡፡
በስኬቱ ልክም ቅሬታ ያላቸው የናይል ተፋሰስ ሀገራት ወገኖች እንዳሉ የጠቀሱት ክቡር ሚኒስሩ የማዕቀፉ ዋና ዓላማ ማንንም ሳይጎዳ የሁሉንም የመጠቀም መብት ማረጋገጥነዉ፡፡
ትልቁ ቁም ነገር በትብብር፣ በመተጋገዝና በጋራ ማልማትና ማደግ እንዲሁም የተፋሰሱን ሀገራት ዜጎች እኩል ተጠቃሚ ማድረግ ማስቻል መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል ብለዋል፡፡
የህግ ማእቀፍ ስምምነቱ በአርባ አምስት አንቀጾች የተደገፉ አስራ አምስት ዋና ዋና መርሆዎች ያሉት ሲሆን፤ ከመጠቀም መብት ጋር የተገኛኙ ሀሳቦችን የያዘ፣ የውሃ ሀብትን መጠበቅ ፣ በመንከባከብና በማልማት ዘላቂነት ያለው አገልግሎት እንዲሰጥ የማድረግ ሀላፊነትንና አስገዳጅነትን ለሁሉም የተፋሰሱ ሀገራት የሚሰጥ ነዉ፡፡
አባቱ መረቀ
ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም
የአይደር ሪፈራል ሆሰፒታል ያጋጠመውን የመድሃኒት እጥረት ለመቅረፍ ከ200 ሚሊየን ብር በላይ ቢያስፈልገውም የተመደበለት ግን 30 ሚሊየን ብር ብቻ እንደሆነ ገለጸ።
በዓመት ከ 300 ሺ በላይ ለሚገመቱ ታካሚዎች አገልግሎት የሚሰጠውና ከ 8000 በላይ ቀዶ ህክምናዎችን እንዲሁም ከ 6-7 ሺ የሚገመቱ እናቶችን የሚያዋልደው የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል የሚሰጠው በጀት ተቋሙ የሚሰጠውን አገልግሎት እና የስራ ጫና ከግምት ውስጥ ያስገባ እንዳለሆነ የሆሰፒታሉ የፋርማሲ ዳይሬክተር አቶ ጣዕመ አረጋዊ ተናግረዋል፡፡
ሆስፒታሉ ያጋጠመውን የመድኃኒቶች እና የላብራቶሪ ግብዓቶች እጥረት ለመቅረፍ በፋርማሲ ባለሞያዎች ጥናት መሰረት 270 ሚሊየን ብር ያስፈልግ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን ነገር ግን የተመደበው በጀት ከ 20 ሚሊዮን ብር እንዳልበለጠ ነግረውናል፡፡
በ2016 በጀት አመት እስከ 300 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልገው ገልጾ 20 ሚሊዮን ብር ብቻ እንደተመደበላቸው ያስታወሱት ዳይሬክተሩ በዘንድሮ በጀት አመትም የበጀት አመዳደቡ አልተሻሻለም ብለዋል።
ተመሳሳይ አገልግሎት ለሚሰጡ ሆስፒታሎችህ ከአይደር የተሻለ በጀት እንደተመደበላቸው የነገሩን ዳይሬክተሩ የምንሰጠው አገልግሎት ተመሳሳይ ሆነ ሳሉ መለያየቱ እንዳሳዘናቸው ነግረውናል፡፡
ሆስፒታሉ የመድሃኒት ችግሮቹን ለመቅረፍ በኢትዮጵያ የመድሃኒት አቅርቦት ድርጅት እርዳታ በብድር ሲወስድ የቆየ ሲሆን የብድሩ መጠን ከ 50 ሚሊየን ብር በላይ በመሻገሩ ለ 2017 በጀት ዓመት ምንም ዓይነት መድሃኒት በብድር እንደማናገኝ ከመድሃኒት አቅርቦት ድርጅት ተነግሮናል ብለዋል።
ለአለም አሰፋ
ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ከሚያቀርባቸው መድኃኒቶች መካከል ከ2 መቶ በላይ የሚሆኑት በአገር ውስጥ የተመዘገበ አንድም አቅራቢ እንደሌላቸው ገለፀ።
አገልግሎቱ 9 መቶ 70 አይነት መድኃኒቶችን በ19 ቅርንጫፎቹ ለመንግስት የጤና ተቋማት ያሰራጫል።
ከእነዚህ መድኃኒቶች ውስጥ 2መቶ3 የሚሆኑት በአገር ውስጥ የተመዘገበ አንድም አቅራቢ እንደሌላቸው አገልግሎቱ ባደረገው ጥናት ማረጋገጡን አስታውቋል ።
ከዚህ በተጨማሪ 6መቶ24 ወይንም የአገልግሎቱን 71 በመቶ የመድኃኒት አቅርቦት የሚሸፍኑት የመድኃኒት አይነቶች በአገር ውስጥ የተመዘገበ በቂ አቅራቢ የላቸውም።
በሌላ በኩል 2መቶ53 ወይም 29 ከመቶ የሚሆኑት የመድኃኒት አይነቶች ደግሞ 5 እና ከዛ በላይ የተመዘገበ በቂ አቅራቢ ያላቸው መሆናቸውን አገልግሎቱ አስታውቋል።
ለመድኃኒት አይነቶቹ በቂ አቅራቢ ባለመኖሩ ለፀረ-ካንሰር፣ ለኩላሊት ፣ ለእናቶችና ህፃናት የሚሆኑ መድኃኒቶችን በቀላሉ ለማቅረብ እንደሚቸገር ነው የገለፀው።
አገልግሎቱ ከ3መቶ በላይ የመድኃኒት እና የህክምና መገልገያ ግብአት አቅራቢዎች ጋር ውል በማሰር አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝም አስታውቋል።
ከእነዚህ መሐል ስምንቱ የአገር ውስጥ የመድኃኒት እና የህክምና መርጃ መሳሪያ አምራቾች ናቸው።
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በቅርንጫፎቹ አማካኝነት ከ3ሺህ በላይ ለሚሆኑ የጤና ተቋማት የቀጥታ የመድኃኒት ስርጭት አገልግሎት ይሰጣል።
እስከዳር ግርማ
ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም
የነገ የጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ፕሮግራሞቻችን
Читать полностью…መንግሥት የሎጂስቲክስ ዘርፉን ሙሉ በሙሉ ለውጭ ባለሀብቶች መክፈቱ የሃገር ውስጥ ባለሀብቶችን ከጫወታው ውጭ የሚያደርግ ነው ተብሏል።
የባቡር መሃንዲስና የሎጅስቲክ ባለሙያ የሆኑት ኢንጂነር መኮንን ጌታቸው ፤ውሳኔው የውጭ ባንኮችን ወደሃገር ውስጥ እንደ ማቀላቀል በሎጅስትክ ዘርፍ ቀላል አይደለም ነው ያሉት።
የሎጂስቲክ ዘርፉ ለሃገር ኢኮኖሚ እና ለዜጎች ህይወት መቀጠል ዋስትና በመሆኑ ምንም እንኳን የውጭ ድርጅቶች በመቀላቀላቸው በጎ ለውጦች የሚመጡ ቢሆንም የሃገር ውስጥ ለሃብቶች ሳይጠናከሩ ገበያውን ክፍት ማድረግ ትክክል አደለም ብለውናል።
መንግሥት ለውጭ ባለሀብቶች ዕድል ከመስጠቱ በፊት አገር በቀል የሆኑ ባለሀብቶች ራሳቸውን አጠንክረው እስከሚጓዙ ድረስ ዕገዛና የመሰረተ ልማት ስራዎችን እያከናወነ ቀስ በቀስ ክፍት ማድረግ አለበት ሲሉ ጠቁመዋል።
የአገር ውስጥ ባለሀብቶች የጎደላቸውን ነገር እንዲያሟሉ ዕድልና የጊዜ ገደብ ሊሰጣቸው እንደሚገባ አንስተዋል፡፡
በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ምክንያት በቀይ ባህርና በቀጠናው ዙሪያ ያሉ የታጠቁ ሃይላት ጥቃት ቢያደርሱ ፣እንቅስቃሴ ቢገድቡ የውጭ ተቋማት ሊሸሹ ይችላሉ ።
ይህ በመሆኑ የኢትዮጵያ ባህርና ትራንስፖርት ሎጅስቲክ የሚሰጡት መርከቦቻችን ለእኛ ኢንሹራንሶቻችን ናቸው ነው ያሉት።
መንግሥት በሎጂስቲክስ ዘርፉ 49 በመቶ የውጭ ባለሀብቶች እንዲገቡ ሕግ ያወጣ ቢሆንም፣ በቅርቡ ከተደረገው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ወዲህ ግን ዘርፉ ሙሉ ለሙሉ ለውጭ ባለሀብቶች መክፈቱ ይታወሳል።
ልዑል ወልዴ
ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም
የላይኛው የአየር ቧንቧ ካንሰር (laryngeal cancer)
የላይኛው የአየር ቧንቧ የካንሰር አይነት በብዛት እድሜያቸው ከ55 አመት በላይ የሆኑ ሰዎችን እንደሚያጠቃ ይነገራል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ በላይኛው የአየር ቧንቧ ካንሰር በአመት 184,615 ሰዎች እንደሚያዙ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
ከነዚህም ውስጥ 99,840 የሚሆኑት ለሞት እንደሚዳረጉ ያሳያል ፡፡
በአጠቃላይ በህይወት ዘመናቸው በዚህ የካንሰር አይነት የመያዝ እድላቸው ለወንዶች ከ200 ሰው 1 ሰው ሲሆን ለሴቶች ደግሞ ከ840 ሰው 1 ሰው መሆኑ ይገለፃል ፡፡
በጉዳዩ ላይ ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የአንገት በላይ ህክምና ስፔሻሊስት እና የመስማት ችግሮች ህክምና ልዩ ስፔሻሊስት የሆኑትን ዶ/ር ሚካኤል ከበደ ናቸው ፡፡
የአየር ቧንቧ ካንሰር ምንድን ነው?
ይህ የካንሰር አይነት ከላይ እሰከ ታች ያለውን የአየር ቧንቧችንን ሊያጠቃ እንደሚችል ይናገራሉ፡፡
የላይኛው የአየር ቧንቧ ደግሞ ድምፅ ማውጣት እና አየር ቧንቧን መጠበቅ ዋናው የዚህ አካል ስራ ነው ይላሉ ፡፡
የላይኛው የአየር ቧንቧ ካንሰር መንስኤው ምንድን ነው?
- ትንባሆ ማጨስ
- አልኮል መጠጥ መጠጣት
- የእድሜ መግፋት
- በቤተሰብ ውስጥ የዚህ ካንሰር አይነት ከነበረ የመከሰት እድሉን ሊጨምር እንደሚችል አንስተዋል፡፡
ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
- የድምፅ መቀየር
- ጉሮሮ ውስጥ የሆነ ነገር እንደተቀረቀረ አይነት ስሜት መሰማት
- አንገት ላይ እብጠት
- ምግብ ለመዋጥ መቸገር
- የምግብ ፍላጎት መቀነስ
- ክብደት መቀነስ
- ትንታ
- የጆሮ ህመም
ምርመራዎቹ ምንድን ናቸው?
- ሙሉ ምርመራ
- የ “ላሪንጎስኮፒ” ምርመራ
- ባዮፕሲ
- የራጅ ምርመራ
ህክምናዎቹ ምንድን ናቸው?
- በቀዶ ጥገና ማውጣት
- የጨረር ህክምና
- ኬሞቴራፒ ተጠቃሽ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡
በመጨረሻም ትምባሆ መጠቀም እና ከመጠን በላይ አልኮል መጠጣት ለላይኛው የአየር ቧንቧ ካንሰር የሚያጋልጡ ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች በመሆናቸው በተቻለ መጠን እነዚህን ነገሮች መጠቀም ማቆም እና መቀነስ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
እንዲሁም በዚህ የካንሰር አይነት የተጠቃ አንድ ሰው ሊያሳይ ከሚችለው ምልክት መካከል አንዱ እና ዋነኛው የድምጽ መቀየር በመሆኑ ድምፃችን በተለያዩ ምክንያቶች ተቀይሮ 2 ሳምንት ካለፈው ወደ ህክምና ተቋም መሄድ እንደሚስፈልግ ዶ/ር ሚካኤል ገልፀዋል፡፡
ሐመረ ፍሬው
ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም