ethiofm107dot8 | Unsorted

Telegram-канал ethiofm107dot8 - Ethio Fm 107.8

20436

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Subscribe to a channel

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

እስራኤል የናስረላህን ተተኪ ገድያለሁ አለች፡፡

የእስራኤል መከላከያ ሃይል የቀድሞዉ የሄዝቦላህ መሪ ሃሰን ናስረላህ ተተኪ የሆኑትን ግለሰብ ከሶስት ሳምንት በፊት በአየር ጥቃት መግደሏን ገለጸች፡፡

እንደ እስራኤል መከላከያ ሃይል መረጃ ከሆነ ፤ሃሺም ሳይፈዲን በሊባኖስ ዋና ከተማ ደቡባዊ ክፍል በአየር ጥቃት ተገድለዋል፡፡

ሄዝቦላህ ግን እስካሁን በእስራኤል የተገለጸዉን የመሪዉን መሞት አላረጋገጠም፡፡

በጥቅምት 4 የአየር ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ ሄዝቦላህ ከመሪዉ ጋር እንዳልተገናኘ የገለጸ ሲሆን፤ የአሜሪካ ሚዲያዎች ግን ሳይፈዲን የጥቃቱ ኢላማ እንደነበር እየገለጹ ይገኛል፡፡

በወቅቱ የተፈጸመዉ የአየር ጥቃት ከተማዋን ያስደነገጠ መሆኑ ሲገለጽ ፤ በጥቃቱ የተፈጠረዉ ጭስ በቀጣዩ ቀን ማለዳ ድረስ ይታይ እንደነበርም ነዉ የተገለጸዉ፡፡

የእስራኤል መከላከያ ሃይል ባወጣዉ መግለጫ፤ ሳይፈዲንን ጨምሮ የሄዝቦላህ ኮማንደር አሊ ሁሴን ሃዚማም በቤሩት በደረሰዉ የአየር ጥቃት መገደላቸዉን አስታዉቋል፡፡

ሳይፈዲን ለዓመታት በእስራኤል መንግስት ላይ የሽብር ጥቃት እንዲፈጸም ሲያስተባብር የነበረ እንዲሁም ከባድ ከሆኑ ዉሳኔዎች ጀርባ ማዕከላዊዉ ሰዉ እሱ ነበር ስትል እስራኤል ትከሳለች፡፡

ህይወቱ ሲያልፍ የ 60 ዓመት ጎልማሳ የነበረዉ ሳይፈዲን ከእስራኤል በተጨማሪ በአሜሪካ እና ሳዑዲ አረቢያ በ2017 ‹‹አለም ዓቀፍ አሸባሪ››በሚል ተፈርጇል፡፡

እስከዳር ግርማ

ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ

አርሰናል ሻክታር ዶኔስክን 1ለ0 መርታት ችሏል።
አርሰናልን አሸናፊ ያደረገች ግብ ሪዝኒክ በራሱ ግብ ላይ አስቆጥሯል።
ሪያል ማድሪድ ከመመራት ተነስቶ ዶርትመንድን 5ለ2 መርታት ችሏል።
የሎስ ብላንኮዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ቪንሰስ ጁኒየር 3x ፣ ሩዲገር እና ቫዝኩዌዝ ከመረብ ሲያሳርፉ ለዶርትመንድ ማለን እና ጊቴንስ አስቆጥረዋል።
ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ የሰራው ቪንሰስ ጂኒየር የጨዋታው ኮከብ በመባል መመረጥ ችሏል።
በሌሎች ጨዋታዎች
- አስቶን ቪላ ቦሎኛን 2ለ0
- ስቱትጋርት ጁቬንቱስን 1ለ0 ሲያሸንፉ
- ፒኤስጂ ከፒኤስቪ ጋር 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።
ከበርካታ አመታት በኋላ ወደ ሻምፒየንስ ሊግ የተመለሰው አስቶን ቪላ ያደረጋቸውን ሶስት ጨዋታዎች በማሸነፍ ሻምፒየንስ ሊጉን እየመራ ይገኛል።

ጋዲሳ መገርሳ

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የአገልግሎት ክፍያዉ ላይ ጭማሪ ማድረጉን ገለጸ፡፡

ቦርዱ አዲስ የሚመሰረቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ በፊት ‹‹የሙሉ ዕዉቅና›› ለማግኘት ሲከፍሉ የነበረዉን 2 መቶ ብር ወደ 30 ሺህ ከፍ ማድረጉን አስታዉቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ አዲስ የሚመሠረቱ ፓርቲዎች ጊዜያዊ እውቅናን ለማግኘት ይከፍሉ የነበረውን 1መቶ ብር ወደ 15 ሺህ ብር ከፍ አድርጎታል፡፡

በአዲሱ የምርጫ ቦርድ የዋጋ ማሻሻያ አዲስ የሚቋቋሙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጊዜያዊ እና ሙሉ የዕውቅና ምስክር ወረቀቶችን ለማግኘት በድምሩ 45 ሺህ ብር መክፈል እንደሚጠበቅባቸዉ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

ከትናንት ሰኞ ጥቅምት 11 ጀምሮ ተግባራዊ የሆነው ይህ የዋጋ ማሻሻያ ቦርዱ ለፖለቲካ ፓርቲዎች በሚሰጣቸው ሦስት አገልግሎቶች ላይ ነው።

በዚህም ሌላኛዉ ጭማሪ የተደረገበት አገልግሎት ደግሞ የተመዘገቡ ፖለቲካ ፓርቲዎች መሰረታዊ ሰነዶቻቸዉን በጉባዔ አሻሽለዉ ሲያቀርቡ ይከፍሉት የነበረዉ ክፍያ ነዉ፡፡

ይህን አገልግሎት ለማግኘት 30 ብር ይከፍሉ የነበሩ የተመዘገቡ ፓርቲዎች አሁን ላይ አገልግሎቱን ለማግኘት 5ሺህ ብር መክፈል እንደሚጠበቅባቸዉ ቦርዱ አስታዉቋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመመዝገብ እንዲሁም የመከታተል እና የመቆጣጠር ኃላፊነት በአዋጅ የተሰጠው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚጠይቀው ክፍያ ተመን ላይ ጭማሪ ማድረጉን ያስታወቀው ዛሬ ማክሰኞ መስከረም 12/2017 ዓ.ም. ነው።

እስከዳር ግርማ

ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች የማጠቃለያ ፕሮግራም አካሄደ

የኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ የ50ኛ ዓመት ክብረበዓል የማጠቃለያ ፕሮግራም አካሂዷል

ዛሬ ጥቅምት 12 የክብረበአሉን ማጠቃለያ መርሀ ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል ሲያካሂድ ላለፉት አስርት አመታት ያስመዘገባቸዉን ስኬቶችን በመዘከር አክብሮል ፡፡

ክብረ በዓል ተከታታይነት ያላቸው በርካታ ሁነቶችን በማከናወን ሲከበር የቆየ ሲሆን ድርጅቱ ያስመዘገባቸውን ስኬቶች፣ የድርጅቱ ደጋፊዎችና ሰራተኞች እያበረከቱ ያለውን አስተዋጽኦ እውቅና ለመስጠት የተዘጋጀ እንደሆነ ተገልጿል።

ሲያደርጋቸው የነበሩ እንቅስቃሴዎችም ድጋፍ ለማሰባሰብ ስራዉን ለማስተዋወቅ
በሚያበረታታ መልኩ የተቀረጹ ናቸው ተብሏል።

ድርጅቱ ከተመሰረተበት ከ1974 ዓ.ም ጀምሮ በህጻናት፣ ቤተሰቦቻቸውና በማህበረሰብ ላይ አዎንታዊ ለውጦችን በማምጣት ላይ የሚገኝ የልማት አጋር ነው።

አቤል እስጢፋኖስ

ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ በብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ሩሲያ ካዛን መግባታቸው ተገለጸ

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በብሪክስ (BRICS) የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ሩሲያ መግባታቸውን የአዘጋጇ የሩሲያዋ ታታርስታን ግዛት ፐሬዝዳንት ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

"የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ በ BRICS የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ካዛን ገብተዋል፤ በካዛን አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የግዛቷ ፕሬዝዳንት ሩስታም ሚኒካኖቭ አቀባበል አድርገውላቸዋል" ሲል መግለጫው አትቷል።

በካዛን በሚካሄደው የመሪዎች ስብሰባ ከ30 ሀገራት በላይ ተወካዮች ይታደማሉ መባሉን ከሩሲያ የዜና አገልግሎት ታስ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፤ የዩናይትድ አረብ ኤሚሬቱ ፕሬዝዳንት ቢን ዛይድ፣ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽክያን፣ የህንዱ ፕሬዝዳንት ናሬንድራ ሞዲ በካዛን ከተገኙ መሪዎች ይገኙበታል።

ኢትዮጵያ በተያዘው የፈረንጆቹ 2024 መጀመሪያ ላይ ቡድኑን በይፋ መቀላቀሏ ይታወቃል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር የመምህራን ደሞዝ በጊዜ አለመከፈል አሁንም ችግር ሆኖ መቀጠሉን ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር በአንዳንድ ክልሎች የመምህራን ደሞዝ በጊዜ አለመከፈል ብሎም እየተቆራረጠ በፐርሰንት መከፈል አሁንም ችግር መሆኑን አስታዉቋል፡፡

ማህበሩ 37ኛ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባዉን አካሂዷል፡፡

በዚህ ስብሰባ ወቅትም የኑሮ ዉድነት መምህራንን እየተፈታተነ መሆኑን ገልጾ፤ በአንዳንድ ክልሎች የመምህራን ደሞዝ በጊዜ አለመከፈል አሁንም ችግር ሆኖብኛል ብሏል፡፡

ያለመምህራን ዕውቅናና ፈቃድ በተለያዩ ምክንያቶች ደሞዝ እንደሚቆረጥ የተነሳ ሲሆን፤ ይሄንን የሚቃወሙ ደግሞ ማዋከብና ማንገላታት እንደሚደርስባቸዉ ተገልጿል፡፡

ሌላዉ በስብሰባዉ የተነሳዉ ጉዳይ ቀደም ብሎ የተጀመረው የመምህራን የመኖሪያ ቤት እና የመሥሪያ ቦታ በሚፈለገው ፍጥነት እየተከናወነ ያለመሆን ሲሆን፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ደግሞ ጭራሽ አለመጀመሩም ተነስቷል፡፡

በትርፍ ሰዓት ክፍያ ላይ ተደራራቢ ግብር መቆረጡ፣ረጅም ጊዜ አገልግሎት ያላቸው መምህራን የደረጃ እድገት ወይም የእርከን ጭማሪ አለመኖር እንዲሁም የመጽሐፍትና ሌሎች ግብአቶች እጥረት መኖሩም የተነሳ ጉዳይ ነዉ፡፡

የትምህርት ሚንስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ኮራ ጡሹነ፤ከመምህራን ጥቅማ ጥቅም ጋር በተያያዘ እየተነሳ ያለው ጥያቄ ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮችም የተጀመረው የትምህርት ሴክተር ሪፎርም ተጠናቆ ተግባራዊ ሲሆን እንደሚፈቱ ገልፀዋል።

እስከዳር ግርማ

ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በጎፋ ዞን 26 ሺህ ተፈናቃይ ዜጎች አሉ ተባለ፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን በደረሰው ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ 26 ሺህ የሚሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ከመኖሪያ አካባቢያቸው መፈናቀላቸውን የጎፋ ዞን አደጋ ስጋት ስራ  አመራር አስታውቋል፡፡

የዞኑ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ማርቆስ መለሰ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ለተፈናቃዮቹ ጊዜያዊ መጠለያ ተሰርቶላቸው በዛ ላይ እንደሚገኙ አንስተዋል፡፡

የአደጋው ሰለባ የሆኑ ሰዎችን መልሶ ለመቋቋምም በ3 ዙር የቤት ግንባታዎችን የማከናወን እቅድ ተይዞ ሰራዎች መጀመራቸውን ጠቅሰዋል፡፡

አሁን ባለው ሁኔታ በመጀመሪያ ዙር የ110 ቤቶች ግንባታ ተጠናቆ ቤቱን እንዲረከቡ የማድረግ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ነግረውናል፡፡

እንዲሁም በሁለተኛው ዙር ግንባታ 318 የሚሆኑ ቤቶችን ለመገንባት እንቅስቃሴ እያደረግን እንገኛለን ብለውናል፡፡

በሶስተኛው  ዙር ደግሞ ወደ 400 የሚጠጉ ቤቶችን ለመገንባት እቅዶች መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡

ለግንባታዎቹም የሚያስፈልገውን ፍቃድ ከክልሉ መንግስት በመጠየቅ 38 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ገንዘብ ስራዎችን በመስራት ላይ እንገኛለን ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በጎፋ ዞን ያለው የተፈናቃይ ቁጥር ከፍተኛ ስለሆነ ድጋፉ በደንብ ተጠናክሮ መቀጠል ካልቻለ ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ የሚል ስጋቶች መኖራቸውን አንስተዋል፡፡

አቶ ማርቆስ እስካሁን ለተደረጉት ድጋፎች ምስጋናቸውን አቅርበው አሁንም ህብረተሰቡን መልሶ ለማቋቋም ሁሉም ማህበረሰብ ከጎናችን ይቁም የሚል ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

ሐመረ ፍሬው

ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ዛሬ ማለዳ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው በተለያዩ ቀጣናዊ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

“የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ወደ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ” ሲሉም መልእክታቸውን አስፍረዋል፡፡አንቶኒዮ ጉተሬዝ በአመታዊው የመንግስታቱ ድርጅት እና የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ ለመታደም አዲስ አበባ ይገኛሉ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram /channel/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

እድሳቱ የተጠናቀቀው ታሪካዊው "አፍሪካ አዳራሽ" ዛሬ ይመረቃል

የ32 ሀገራት መሪዎች ተሰብስበው በመምከር የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን የመሰረቱበት ታሪካዊው "አፍሪካ አዳራሽ" እድሳት ሲደረግለት ቆይቶ ዛሬ ይመረቃል።

የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አዳራሹን በይፋ ይመርቁታል ተብሎ እንደሚጠበቅ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን መረጃ ያመለክታል።

እድሳቱ ከተመድ ጠቅላላ ጉባዔ በተገኘ 57 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ መከናወኑ ተገልጿል።

እድሳቱ ታሪካዊና ባህላዊ የኪነ ሕንፃ ይዘቶችን ጠብቆ የተከናወነ ሲሆን፤ ሕንፃው እንደ ኒው ዮርክ እና ጄኔቫ ቢሮዎች ሁሉ ቋሚ ዓውደ ርዕይና አባል ሀገራት ልዩ ሁነቶችን የሚያዘጋጁበት ስፍራ እንደተዘጋጀለትም ተጠቁሟል።

‘የአፍሪካ አዳራሽ' የተሰኘው ሕንጻ እኤአ በ1963 የ32 የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች መክረው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የመሰረቱበት ታሪካዊ አዳራሽ ነው።

የመጀመሪያውን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ጉባዔ ለማስተናገድ በቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ትዕዛዝ በፍጥነት የተገነባው ይህ ታሪካዊ አዳራሽ የአፍሪካውያን ቅርስ ነው።

በተለይም እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ በአዳራሹ መስኮቶች ላይ የሳሏቸው የመስታዋት ስዕሎች÷ የአፍሪካን የትናንት ጭቆና እና መጻኢ ተስፋ አመላካች እንደሆኑ ይነገራል።

የአፍሪካ አዳራሽ በኋላ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን መስሪያ ቤት በችሮታ ተሰጥቷል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ዘመን ባንክ 3.77 ቢሊዮን ብር አተረፈ።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዘመን ባንክ ከግብር በፊት 3.77 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመስገቡንና የባንኩ ዓመታዊ  ትርፍም በ36.8 በመቶ ማሳደግ መቻሉን አስታውቋል።

ባንኩ የባለ አክሲዮኖች 16ኛ መደበኛ ጉባኤውን  በዛሬው እለት  በሚሊንየም አዳራሽ  ያካሄደ  ሲሆን ያለፈው ዓመት የባንኩ የስራ አፈፃፀም፣ የዚህ በጀት ዓመት እቅድና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች  ላይ ከባለአክሲዮች ጋር ተወያይቷል፡፡

የዘመን ባንክ  የቦርድ ሊቀመንበር ወ/ሮ እንዬ ቢምር ባንኩ  በተጠናቀቀው በጀት ዓመት እቅዱን ሙሉ በሙሉ በማሳካት ያገኘው ትርፍ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ1.01ቢሊዮን ብር ወይንም የ36.8 በመቶ ብልጫ አለው ብለዋል ።


የዘመን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ዘበነ በበኩላቸው ያለፈው ዓመት ምንም እንኳን የተለያዩ ተግዳሮቶች ቢኖሩም ባንኩ ይህን ተቋቁሞ በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ጠቁመዋል፡፡

አቶ ደረጄ የባንኩን አጠቃላይ ሀብት በ23.9 በመቶ በማሳደግ ወደ 59.2 ቢሊዮን ማሳደግ መቻሉን ተጡቁመዋል።

በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ መጠናቀቂያ ላይ የባንኩ አገልግሎት ሰጭ ቅርንጫፎች 125 መድረሱና የባንኩ የውጭ ምንዛሪ ግኝት 566 ሚሊየን ዶላር ደርሷል ብለውናል።

ባንኩ ከዓመት ዓመት በሁሉም የባንክ ሥራ አገልግሎት መመዘኛዎች እያስመዘገበ ያለውን ዕድገትና የፋይናንስ አቅሙን የበለጠ ለማጠንከር የተለያዩ ዕርምጃዎች እየወሰደ ይገኛልም ተብሏል ፡፡

ለዚህም ማሳያው የዘመን ባንክ የተከፈለ ካፒታል 7.5 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን ይህም ከቀደመው በጀት ዓመት በ2.45 ቢሊዮን ብር ከፍ ያለ ነው ያሉት ።

በአሁኑ ወቅትም አጠቃላይ የባንኩ የተፈረመ ካፒታል 14.97 ቢሊየን ብር መሆኑ ሪፖርታቸውን በአቀረቡት ወቅት ገልፀዋል።

ባንኩ ከዲጂታል የባንክ አገልግሎት አንፃር ቀድሞ በመንቀሳቀስ የሚጠቀስ ሲሆን በዲጂታል መንገድ የተንቀሳቀሰው የገንዘብ መጠን 66.9 በመቶ መድረሱን እና አሁንም የዲጂታል የባንክ አገልግሎቱን በማስፋት እንደሚሰራ ተነግሯል::

ልኡል ወልዴ


ጥቅምት  9 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የስፔን ሱፐር ካፕ ውድድር በሳውዲ አረቢያ ጄዳህ ይካሄዳል ።

ባለፉት ሶስት አመታት በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ሲካሄድ የቆየው የስፔን ሱፐር ካፕ ውድድር ዘንድሮ የቦታ ለውጥ በማድረግ በጄዳህ ከተማ እንደሚካሄድ ይፋ ተደርጓል።

የስፔን ሱፐር ካፕ ውድድር የዚህን አመት ጨምሮ በሳውዲ አረቢያ ሲካሄድ ይህ ለአራተኛ ጊዜ መሆኑ ተዘግቧል።

ውድድሩ በሳውዲ አረቢያ ጄዳህ ከተማ በሚገኘው ንጉስ አብደላህ ስታዲየም እንደሚካሄድ ተገልጿል።

- ሪያል ማድሪድ ከ ማዮርካ

- ባርሴሎና ከ አትሌቲክ ቢልባኦ

ውድድሩ ከታኅሣሥ 30 እስከ ጥር 4/2017 ዓ.ም የሚካሄድ ይሆናል።

ጋዲሳ መገርሳ

ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

አክሲዮን ያላቸው ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከ400ሺ እንደማይበልጥ ተገለጸ

ከ120 ሚሊየን በላይ ሰዎች በሚኖሩባት ኢትዮጵያ አክስዮን ያላቸው ዜጎች ቁጥር ከ400 ሺ እንደማይበልጥ የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ስራ አስፈጻሚ ጥላሁን እስማኤል (ዶ/ር) አስታውቀዋል።

“በአሁኑ ወቅት የባንኮችንና ኢንሹራንስ ኩባንያዎችን አክሲዮን የገዙ ኢትዮጵያውያን 400 ሺ የሚደርሱ ናቸው” ያሉት ስራ አስፈጻሚው÷ ከአሁን ቀደም አክስዮን መሸጥ ለሚፈልግ ሰው የሚያገለግል ማዕከላዊ ገበያ እንዳልነበር ተናግረዋል።

የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ወደ ስራ ለመግባት የሚያስችሉት አብዛኞቹን የዝግጅት ሥራዎች በመጠናቀቃቸው ሌሎች ነገሮች ካላስቆዩ፤ በሚቀጥለው ወር በይፋ ይጀመራል ብለዋል።

የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያው አስፈላጊ ግብዓቶች ግዢ መፈጸሙንና ቴክኖሎጂው ሙከራ ላይ እንደሚገኝ የገለጹት ሥራ አስፈጻሚው÷ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን ለማገበያየት አገናኝ አባላት (ደላሎች) እንደሚያስፈልጉ ገልፀዋል።

አገናኝ አባላት በካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ፍቃድ አግኝተው ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ አባል መሆን እንዳለባቸው በመግለጽ፤ ስለዚህ አንድም ሁለትም አገናኝ አባላት እንደተገኘ ገበያውን በይፋ ማስጀመር እንደሚቻል ተናግረዋል።

ገበያው አክሲዮናቸው መሸጫ መለወጫ መድረክ መሆኑን ጠቅሰው፣ የአክሲዮን ዋጋን በማቅረብ በሰከንዶች ውስጥ ከየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል፣ ውጪውንም ጨምሮ መግዛትና መሸጥ እንዲችሉ መድረክ ሆኖ እንደሚያገለግል አስረድተዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ

አርሰናል ሻክታር ዶኔስክን 1ለ0 መርታት ችሏል።

አርሰናልን አሸናፊ ያደረገች ግብ ሪዝኒክ በራሱ ግብ ላይ አስቆጥሯል።


ሪያል ማድሪድ ከመመራት ተነስቶ ዶርትመንድን 5ለ2  መርታት ችሏል።

የሎስ ብላንኮዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ቪንሰስ ጁኒየር 3x ፣ ሩዲገር እና ቫዝኩዌዝ ከመረብ ሲያሳርፉ ለዶርትመንድ ማለን እና ጊቴንስ አስቆጥረዋል።

ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ የሰራው ቪንሰስ ጂኒየር የጨዋታው ኮከብ በመባል መመረጥ ችሏል።

በሌሎች ጨዋታዎች

- አስቶን ቪላ ቦሎኛን 2ለ0

- ስቱትጋርት ጁቬንቱስን 1ለ0 ሲያሸንፉ

- ፒኤስጂ ከፒኤስቪ ጋር 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

ከበርካታ አመታት በኋላ ወደ ሻምፒየንስ ሊግ የተመለሰው አስቶን ቪላ ያደረጋቸውን ሶስት ጨዋታዎች በማሸነፍ ሻምፒየንስ ሊጉን እየመራ ይገኛል።

ጋዲሳ መገርሳ

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ የደረሰውን የእሳት አደጋ መንስኤ እየመረመረ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ

የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት የአዲስ አበባ ፖሊስ ከፌዴራል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራ ቡድን ጋር በመቀናጀት ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።

አደጋውን ለመከላከል እና በአደጋው ምክንያት ሌላ ወንጀል እንዳይፈፀም እንዲሁም የአደጋ ተከላከይ ሰራተኞች ተግባራቸውን በአግባቡ መወጣት እንዲችሉ እና ተጨማሪ ጉዳት እንዳያጋጥም የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የመከላከያ ሠራዊት፣ ሪፐብሊካን ጋርድ፣ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ የሠላምና ፀጥታ መዋቅር፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ሌሎች ተቋማትም ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ አደጋው እንዳይባባስ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል።

አደጋውን እንደ ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 33 ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን እና ከአደጋው ጋር በተያያዘ በ7 ሰዎች ቀላል በ2ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት  መድረሱን ፖሊስ አስታውቋል፡፡ 

አደጋውን ለመከለከል የፀጥታና ሌሎች ተቋማት እንዲሁም የአካባቢው ህብረተሰብ ላደረገው ድጋፍና ተባባሪነት ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ በደረው የእሳት አደጋ የተሰማውን ሃዘን ገልፆ ወደፊት በምርመራ የደረሰበትን ውጤት ለህዝብ እንሚያሳውቅም አስታውቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በ11 የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ የእግድ ውሳኔ ተላለፈ

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በጠቅላላ ጉባኤ፣ በኦዲት እና በሴት አባላት በሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ምክንያት ቦርዱ በተለያዩ ጊዜ በአስራ አንድ ፓርቲዎች ላይ የዕግድ ውሳኔ መስጠቱን አስታውቋል።

የዕግድ ውሳኔ የተሰጣባቸው ፓርቲዎች የገዳ ሥርዓት ለኦሮሞ ነጻነት ፓርቲ፣ የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ፣የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ፣ አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የጌዲኦ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የሐረሪ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የጋምቤላ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ዴሞክቲክ ኅብረት እና አገው ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ናቸው ።

በፓርቲዎቹ ላይ የተሰጠው የዕግድ ውሳኔ ውጤት ቦርዱ የተለየ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ፤ ለጊዜው ፓርቲዎችን ከማናቸውም ሕጋዊ እንቅስቃሴ ታቅበው እንዲቆዩ የሚያደርግ መሆኑን አስታውቋል።

ለአለም አሰፋ

ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

አሸዋ ቴክኖሎጂ ከ500 በላይ የዌብሳይት ቴፕሌት አበልፃጊዎችን አወዳድሬ ልሸልም ነው አለ።

አሸዋ ቴክኖሎጂ ለረጅም ጊዜ ሲሰራበት የቆየዉን የቴክኖሎጂ ዉጤት ከ500 በላይ አበልፃጊዎችን በማሳተፍ ዘርፉን ለማበረታታት ፕሮጀክት ቀርፆ መንቀሰቀስ መጀመሩን በዛሬዉ ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።

የአሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አ.ማ ዋና ስራ አስፈፃሚ እቶ ዳንኤል በቀለ ይሀንን የፈጠራ ዉድድር በ90 ቀን ዘመቻ ወደስራ ስናስገባ የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን የቴክሎሎጂ እድገት ካለበት ደረጃ በአጭር ጊዜ የከፍታ ማማ ላይ ለማድረስ አልመን ነዉ ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በውድድሩ ለሚሳተፉ ሰዎች በቅድሚያ የተወዳዳሪዎች ምዝገባ እንደሚካሄድ እና ምዝገባዉም እስከ ጥቅምት 30 እንደሚቆይ ገልፀዋል።

በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚገኙ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ተማሪዎችን እንዲሁም በዘርፉ በግላቸው የሚንቀሳቀሱ ከ500 በላይ ዌብሳይት አበልፃጊዎችን አወዳድሮ እንደሚሸልም እና ለወጣቶች የስራ ፈጠራ ሀሳባቸዉን ይዞ መምጣቱንም አንስተዋል።

ፕሮጀክቱ ለዜጎች የስራ እድል ከመፍጠር አንፃር፤ ለአገር ዉስጥ የምጣኔ ሀብት እድገትና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ መፍጠር እንደሚችል ተጠቁሟል ።

ዉድድሩ በአምስት የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚካሄድ እንደሆነና የዌብ ዲዛይነሮች ይህ እድል ሳያመልጣቸዉ እንዲመዘገቡ የሚል ጥሪያቸውን ሀላፊው አስተላልፈዋል ።

አሸዋ ቴክኖሎጂ ዘመኑን የዋጁ ድንቅ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን በማቅረብ በአጭር ጊዜ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ መሆኑን ተናግረዋል።

ሐመረ ፍሬዉ

ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስና ዶዳይ የኤሌክትሪክ ሞተር  ዘላቂ የትራንስፖርት አገልግሎትን ለመፍጠር ስምምነት ላይ መድረሳቸዉን አስታወቁ

የዶዳይ መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ ዩማ ሳሳኪ፤ይህ ስትራቴጂካዊ አጋርነት በኢትዮጵያ ዘላቂ የሆነ የትራንስፖርት አገልግሎት እድገትን ለማፋጠን የሚያግዝ ነዉ ብለዋል፡፡
እንዲሁም  የካርበን ልቀትን ለመቀነስና የከተማ እንቅስቃሴን ለማሳደግ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

ስራ አስኪያጁ በኢትዮጵያ ከ80 በመቶ በላይ ግለሰቦች በቀን ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ የሚያጠፉትን ከሦስት እስከ አራት ሰዓት ይቀርፋል ።

ከዚህ ውጭ ሰዎች ለነዳጅ ከሚያወጡት 50 በመቶ ለራሳቸው ጥቅም እንዲያውሉት ያስችላል ።


የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ በበኩላቸው ፣ ስምምነቱ ለብዙቹ ከመንቀሳቀሻነት ባሻገር  የስራ እድልን የሚፈጥር ነው ብለዋል።

አንድ ሞተር ሳይክል አንድ ስራ ይፈጥራል ነው ያሉት ።

መንግስት የአየር ብክለትን ለመቀነስ እየሄደበት ላለው ራዕይ አግዥ ነው ብለውታል።

በ2025 በአዲስ አበባ 100 ጣቢየዎችን በመትከል በሁለት ደቂቃ ውስጥ የዶዳይ ኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል ተጠቃሚዎች ቻርጅ የሚያደርጉበት ይገነባል ተብሏል ።

በቀጣይ ከአዲሳ አበባ ውጭ አዳማ እና ሃዋሳ ላይ ኩባንያውን ለማቋቋም እና በከተማ ውስጥ ሞተሮቹ ቻርጅ በሁለት ደቂቃ ውስጥ ሞልተው የሚሄዱበትን መሰረተልማት ይዘረጋል ተብሏል ።

ልዑል ወልዴ


ጥቅምት 11ቀን  2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ቱርክ በመፈንቅለ መንግሥት የምትፈልጋቸው ሃይማኖታዊ መሪ ፌቱላ ጉለን አረፉ

ከቱርክ ሸሽተው በአሜሪካ ለረጅም ጊዜ የኖሩት ጉለን ፔንሲልቬኒያ ውስጥ ሆስፒታል ከገቡ በኋላ ሕይወታቸው ማለፉን የቱርክ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

‘ጉለን ሙቭመንት’ የተባለው በቱርክ እና በዓለም ዙሪያ ተከታዮች ያሉት ተጽእኖ ፈጣሪ የእስልምና ሃይማኖት እንቅስቃሴ መሪ የሆኑት ፌቱላህ ጉለን አንዳንድ ጊዜ የቱርክ ሁለተኛው ኃያል ሰው እየተባሉ ይገለጻሉ።

የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲብ ታይብ ኤርዶዋን በአውሮፓውያኑ 2016 የተፈጸመውን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ የጉለን እንቅስቃሴ የመራው ነው በማለት የከሰሱ ሲሆን፣ ጉለን ግን አስተባብለዋል።

የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን አንካራ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “የጨለማው ድርጅት” መሪ ናቸው ኣሏቸው ጉለን መሞታቸውን የደኅንነት ምንጮች ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል።

ጉለን በቱርካውያን ዘንድ እውቅናን ያገኙት በአገሪቱ ያሉ ወጣቶች መንገዳቸውን በመሳታቸው ትምህርት ላይ ትኩረት መስጠት ወሳኝ ነው በሚል በሚያራምዱት አቋም ነው።

በተጨማሪም ጉለን አካታች የሆነ፣ ከራስ በላይ ለሌሎች የሚያስብ እና በሥራ የሚያምን እስላማዊ አመለካከትን በማራመድም ይታወቃሉ ይላል የቢቢሲ ዘገባ።

ከመፈንቅለ መንግሥቱ ጋር ተያይዞ በርካታ የአገሪቱ ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖች እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ ባለሥልጣናት እና የመንግሥት ሠራተኞች ለእስር ተዳርገዋል።

ከሃያ ዓመታት በፊት ከቱርክ ተሰደው ኑሯቸውን በአሜሪካ አድርገው የቆዩት ጉለን በመፈንቅለ መንግሥቱ ወቅትም እዚያው ነበሩ።

ቱርክ ጉለን ለፍርድ እንዲቀርቡ ተላልፈው እንዲሰጧት ብትጠይቅም የአሜሪካ ባለሥልጣናት ግን መጀመሪያ ግለሰቡ በመፈንቅለ መንግሥቱ ውስጥ መሳተፋቸውን የሚያሳይ ማስረጃ እንዲቀርብ ጠይቀዋል። በዚህም ጉለን እስከ ህልፈታቸው ድረስ በአሜሪካ ቆይተዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የ2017 የቴክኒክና ሙያ የመደበኛ ስልጠና ዘመን መቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ!

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ዘመን መቁረጫ ነጥብ በዛሬው እለት ይፋ ሆኗል፡፡

የተፈጥሮ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት በስልጠና ደረጃ 1 እና 2 ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 141 እና ከዚያ በታች ፤ ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች 137 እና ከዚያ በታች እንደሆነ ተገልጻል፡፡

ለሴት ተማሪዎች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 138 እና ከዚያ በታች ፤ ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች 134 እና ከዚያ በታች እንዲሁም ለሁሉም የአካል ጉዳተኞች የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም የማህበራዊ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት በስልጠና ደረጃ 1 እና 2 ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 139 ከዚያ በታች፤ ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች 135 እና ከዚያ በታች ያለ ነጥብ ነው፡፡

ለሴቶች በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 134 እና ከዚያ በታች፤ ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች 124 እና ከዚያ በታች በተመሳሳይ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

እስራኤል ሄዝቦላህን ይደግፋሉ ያለቻቸውን በመዲናዋ ቤይሩት እንዲሁም በደቡባዊ ሊባኖስ የሚገኙ ባንኮች ላይ የአየር ጥቃት ፈጸመች።

በአየር ጥቃቱ በቤይሩት ዳሂየህ ወረዳ እንዲሁም በደቡባዊ ሊባኖስ ቤካ ሸለቆ ከፍተኛ ፍንዳታ ተሰምቷል።

እነዚህ ስፍራዎች ሄዝቦላህ የሚቆጣጠራቸው ናቸው ተብሏል። የአየር ጥቃቶቹን ተከትሎ በደረሱ ፍንዳታዎች በሰዎች ሕይወት ላይ ጉዳት ስለማድረሱ እስካሁን አልተገለጸም።

የእስራኤል ጦር በቤይሩት 14 ሰፈሮችን ጨምሮ በመላዋ ሊባኖስ በ25 ስፍራዎች ላይ ሌሊቱን ሙሉ የአየር ጥቃት እንደሚፈጽም ቀደም ሲል አስጠንቅቆ ነበር።

የእስራኤል መከላከያ ኃይል ሄዝቦላህን የሚደግፉ ባንኮችን እንዲሁም የፋይናንስ ዘርፎችን ዒላማ አደርጋለሁ ብሏል።

“የሄዝቦላህ የሽብር ተግባራትን ለመደገፍ ጥቅም ላይ ከሚውሉ አካባቢዎች አጠገብ ያሉ ማንኛውም ነዋሪዎች ከእነዚህ ስፍራዎች መራቅ አለባቸው” ሲሉ የእስራኤል መከላከያ ቃለ አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ እሁድ ምሽት አስጠንቅቀው ነበር።

“በሚቀጥሉት ሰዓታት በርካታ ዒላማዎችን እንዲሁም ሙሉ ሌሊቱን ተጨማሪ ስፍራዎች ላይ ጥቃት እንፈጽማለን” ብለው ነበር።

ቃለ አቀባዩ አክለውም “በሚቀጥሉት ቀናት ኢራን የሲቪል ተቋማትን፣ ማኅበራትን እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ሽፋን በማድረግ የሄዝቦላህ የሽብር ተግባራትን እንዴት ድጋፍ እንደምታደርግ እናሳውቃለን” ሲሉ ገልጸዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

https://youtu.be/ZIIsIsDVOVU

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሃማስ ሲንዋር መገደሉን አረጋገጠ

በጋዛ የሃማስ ቢሮ ኃላፊ ክሃሊል ሃያ በሰጡት መግለጫ ያህያ ሲንዋር በእስራኤል የአየር ጥቃት መገደሉን አረጋግጠዋል፡፡

በሲንዋር ግድያ ጥልቅ ሃዘን ተሰምቶናል ያሉት ኃላፊዉ ሲነዋርን የምንጊዜም ጀግና ብለዉታል፡፡

ያህያ ሲንዋር ዕድሜ ልኩን ለፍልስጤማዉያን ነጻነት ህይዎቱን የገበረ የቁርጥ ቀን ልጅ ሲሉም አወድሰዋል፡፡

ሲነዋር እስከወዲያኛዉ ቢያሸልብም የእሱን ግብ እዉን ለማድረግ የሚያቆመን የለም ነዉ ያሉት ክሃሊል ሃያ፡፡

ኢራን በበኩሏ በሃማስ መሪ ግድያ የፍልስጤማውያን የትግል መንፈስ ይበልጥ ይጠናከራል እንጂ አይዳከምም ብላለች።

አባቱ መረቀ

ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ሙዝ ጭኖ ሲመለስ የነበረ ጀልባ ጫሞ ሐይቅ ሰምጦ ከተሳፈሩ  16 ሰዎች ውስጥ ሁለቱ መገኘታቸውን የጋሞ ዞን  ፖሊስ መምሪያ ገለፀ

ከኮሬ ዞን አቡሎ አርፋጮ ከሚባል አካባቢ ሙዝ ጭኖ ሲመለስ የነበረ ጀልባ ጫሞ ሐይቅ ሰምጦ ከተሳፈሩ  16 ሰዎች ውስጥ ሁለቱ መገኘታቸውን  የዞኑ  ፖሊስ መምሪያ ገለፆል

የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙት እና ገጽታ ግንባታ ድቪዥን  ኃላፊ ኮማንደር ረታ ተክሉ እንደገለጹት ትላንት ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ የጀልባውን አሽከሪካሪ እና 15 የቀን ሠራተኞችን ከሙዝ ጋር  ጭኖ  ከኮሬ ዞን አቡሎ አርፋጮ ወደ አርባምንጭ ሲጓዝ የነበረ ጀልባው መስጠሙን ተናግረዋል ።

በጀልባው ላይ ከነበሩ 16 ሰዎች ሁለቱ በጀርካን ላይ ተንሳፈው የተረፉ ሲሆን 14ቱ ባለመገኘታቸው ፖሊስ በፍለጋ ላይ መሆኑን ኮማንደር ረታ ተናግርዋል ።

15 ተሳፋሪዎች በሙሉ ሙዝ ለመጫን ከአርባምንጭ ዙሪያ አካባቢ የሄዱ መሆናቸውን  መሆናቸውን የጋሞ ዞን ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ባሳለፍነው መስከረም ወር ብቻ 48 ሰዎች የትራፊክ አደጋ ደርሶባቸዋል ተባለ፡፡

በ2017 አ.ም መስከረም ወር ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 48 ሰዎች ከሞት እስከ ቀላል አደጋ እንደደረሰባቸው የንፈስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የትራፊክ ቁጥጥር ማስተባበሪያ ሀላፊ የሆኑት ኢኒስፔክተር ዘለቀ ሽኩር ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ከነዚህ መካከል 6 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ እና 25 ሰዎች ደግሞ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው አንስተዋል፡፡

እንዲሁም 17 የሚሆኑ ሰዎች ቀላል ጉዳት አጋጥሟቸዋል ብለውናል፡፡

በአጠቃላይ በ2017 የመጀመሪያው ሩብ አመት 179 ሰዎች የትራፊክ አደጋ እንደደረሰባቸው ጠቅሰዋል፡፡

አደጋው ካለፈው ሩብ አመት ጋር ሲነፃፀር እጅግ በጣም ከፍተኛ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍም አንድም ሰው በትራፊክ አደጋ መንገድ ላይ እንዳይሞት በሚል መሪ ቃል የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የትራፊክ ቁጥጥር ማስተባበሪያ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የቁጥጥር ስራውን በተሻለ መልኩ መጀመራቸውን አንስተዋል፡፡

የተሻሻለው የቁጥጥር ስራ ወደ ተግባር የገባው ጥቅምት 4/2017 እንደሆነ እና ከክፍለ ከተማው የተውጣጡ ሰዎችን በማዋቀር ታንጎ የሚል መጠሪያ በመስጠት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ልዩ ተቆጣጣሪ በመሆን ህግ የማስከበር ስራ እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

አፎሚያ አሸናፊ

ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…
Subscribe to a channel