ethiofm107dot8 | Unsorted

Telegram-канал ethiofm107dot8 - Ethio Fm 107.8

20436

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Subscribe to a channel

Ethio Fm 107.8

በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 125 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 125 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

ሚኒስቴሩ በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ከባለድርሻ አካላት ጋር ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ነው የገለጸው።

በትናንትው ዕለት 61 እንዲሁም ዛሬ ደግሞ 65 ዜጎቻችን ከሊባኖስ እንዲመለሱ ማድረግ መቻሉንም አያይዞ ጠቅሷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቤይሩት ከሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት ጋር በመሆን በቀጣይም ሌሎች ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ አስፈላጊውን ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

BALLON D'OR DAY

የፍራንስ ፉትቦል ጋዜጣ የሚዘጋጀው ስልሳ ስምንተኛው  ተጠባቂው የ2024 የባሎን ዶር ሽልማት ስነ ስርዓት ዛሬ ምሽት ይካሄዳል።

አንድ የእግርኳስ ተጫዋቾች በእግርኳስ ህይወቱ ሊያሸንፈው የሚፈልገው ትልቁ የግል ሽልማት ነው ።

የሽልማት ስነስርአቱ ዛሬ ምሽት በፈረንሳይ ርዕሰ ፓሪስ ይከናወናል ።

የዘንድሮው የ2024 የባሎን ዶር ሽልማት ያለፈውን የውድድር ዘመን ብቻ ያከተተ መሆኑ ተውቆዋል።

ሽልማት የሚበረከትባቸዉ ዘርፎች ፦

• ምርጥ ወንድ ተጨዋች
• ምርጥ ሴት ተጨዋች
• ምርጥ የወንዶች ክለብ
• ምርጥ የሴቶች ክለብ
• የኮፓ ሽልማት (ምርጥ ወጣት ተጨዋች)
• የያሺን ሽልማት (ምርጥ ግብ ጠባቂ)
• የሙለር ሽልማት (ምርጥ ግብ አስቆጣሪ)
• የሶቅራጥስ ሽልማት (ምርጥ የሰብአዊ ስራ)
• ምርጥ የሴቶች አሰልጣኝ
• ምርጥ የወንዶች አሰልጣኝ

ፕሮግራሙን  ዲዲየ ድሮግባ ይመራል ።

ጋዲሳ መገርሳ

ጥቅምት 18  ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ናይጄሪያ ሶስት ነጥብ ተወሰነላት !

የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ከሊቢያ ጋር የነበረው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ በፎርፌ እንዲሰጠው መወሰኑን ካፍ ይፋ አድርጓል።

ሊቢያ ላይ ሊደረግ የነበረው ጨዋታ የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን የገጠመውን መጉላላት ተከትሎ መሰረዙ አይዘነጋም።

ጉዳዩን ሲመረምር የነበረው የካፍ ዲሲፕሊን ኮሚቴ አሁን ላይ ናይጄሪያ ሶስት ነጥብ እና ሶስት ንፁህ ግብ እንዲሰጣት መወሰኑን አስታውቋል።

በተጨማሪም የሊቢያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የካፍን መተዳደሪያ ደንብ በመጣሱ ምክንያት 50,000 የአሜሪካን ዶላር የገንዘብ ቅጣት እንደተጣለበት ተገልጿል።



ጋዲሳ መገርሳ

ጥቅምት 16  ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የጥቅምት 16 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በ6 ዓመት ከ3 ወራት ጽኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ተወሰነ

የ70 ዓመቱ አዛውንት አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት “የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና ግጭት መቀስቀስ ወንጀል” በ6 ዓመት ከ3 ወራት ጽኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ተወሰነ።

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የህገ-መንግስትና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት አቶ ታዲዮስ ታንቱን በተከሰሱበትና ጥፋተኝነት በተባሉባቸው 3 ክሶች ነው የጽኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት የጣለባቸው።

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም “የጥላቻ ንግግር በማሰራጨት እና የእርስ በርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀል” ፈጽመዋል ተብለው በፍትህ ሚኒስቴር በተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ በኩል ተደራራቢ አራት ክሶች ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኩላሊት እጥበት አገልግሎት  ዋጋ መጨመር ለህሙማኑ ህይወት ማለፉ ምክንያት እየሆነ ነዉ ተባለ።

ከጥቂት ወራት በፊት በኢትዮጰያ የተደረገዉ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዉን ተከትሎ የኩላሊት እጥበት የሚሰጡ ተቋማት የህክምና ግብአቶችን አሁን ባለዉ የዉጭ ምንዛሬ በማስመጣታቸዉ ለታማሚወች የሚሰጡትን የኩላሊት እጥበት ዋጋ መጨመሩን የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ሰለሞን አሰፋ ለጣቢያችን ተናግረዋል።

ታካሚዎች በሳምንት ዉስጥ ከአስራ ሁለት እስከ አስራ አራት ሺ ብር  ለህክምና ያወጣሉ  ያሉት አቶ ሰለሞን  ዲያልሲስ የሚያደርጉ ታካሚዎች የአቅም ዉስንነት እየታየባቸዉ በመሆኑ  ህይወታቸዉ ማጣታቸዉን ይገልፃሉ ።

በየቀኑ ቁጥሩን መጥቀስ የሚያዳግት ዲያሌሲስ የሚያደረግ ሰዉ ነዉ የሚመጣዉ ያሉት አቶ ሰለሞን ለአንድ እጥበት ከ 3 እስከ 4 ሺ ብር እየተጠየቀ መሆኑን አስረድተዋል።

ይህን ተከትሎ ህሙማኑ የኩላሊት እጥበት መጠኑን ከሶስት ወደ አንድ ለማዉረድ እየተገደዱ ነዉ ተብሏል።

የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ማህበር አሁን ላይ የዲያሌሲስ ሴንተሮችን በየሆስፒታሉ ለመክፈት  እቅድ ይዞ   እየተንቀሳቀሰ መሆኑን  ተናግረዋል 

ሊዲያ ደስአለኝ

ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ቶታል ኢነርጂስ በአራተኛ ዙር ውድድር የአመቱ ምርጥ አዲስ ስራ ፈጣሪ አሸናፊዎችን አሳውቋል

የአመቱ ምርጥ አዲስ ስራ ፈጣሪ ውድድርን ካሸነፉት ውስጥ መንበሩ ዘለቀ በኢኖቭ አፕ ምድብ ውስጥ ሶላር መቀስ የተባለ መሳሪያ በመስራት ፣ ኤርሚያስ ተፈራ በሳይክል አፕ ምድብ ውስጥ ኤኮ ፓኬጅ እና ቦርሳ በመስራት እንዲሁም አዱኛ ንጋቱ በፓወር ከፕ ምድብ ምርጡ ዘላቂ እና ተመጣጣኝ የባዮ ጄል ነዳጅ በማምረት ተሸላሚ መሆን ችለዋል።

ፕሮጀክታቸውን ለማልማት ይችሉ ዘንድ የስራ ፈጣሪዎቹ ዳጎስ ያለ የገንዘብ ስጦታ የተበረከተላቸው ሲሆን በቢዲ ኮንሰልት አማካኝነት ፕሮጀክታቸውን እንዲያለሙ የግል ድጋፍ እንዲሁም አላማቸውን በተመለከተ ግንዛቤ ለማዳበር መንገድ ይመቻችላቸዋል ተብሏል።

ለውድድሩ 719 ሰዎች የተመዘገቡ እንዲሁም ከነዚህ ውስጥ የተሟላ ማመልከቻ ያቀረቡት 207 ሲሆኑ ፕሮጀክታቸውን ለሀገር ውስጥ ዳኞች ያቀረቡት 14 የፍጻሜ ተወዳዳሪዎች መሆናቸው ተጠቁሟል።

ውድድሩ በ32 ሀገራት ከሚገኙ ተሳታፊዎች የአመቱ ምርጥ አዲስ የስራ ፈጣሪ 100 አሸናፊዎች በሀገር ውስጥ እና የውጪ ሀገር ዳኞች ከተመረጡ በኋላ የሀገር ውስጥ አሸናፊዎቹ ድርጅቱ ባዘጋጀው ክብረ በአል የሽልማት ፕሮግራም ላይ ሽልማት እንደተሰጣቸሀውም ተዘግቧል፡፡

ለአለም አሰፋ

ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ጋንግሪን(gangrene)

ጋንግሪን አደገኛ እና ገዳይ የሆነ የጤና ችግር እንደሆነ  ይነገራል ፡፡
ስር የሰደደ የጤና እክል ያለባቸው እና የበሽታ መከላከል አቅማቸው የተዳከመ ሰዎች ለዚህ ሕመም ተጋላጭ መሆናቸው ይነሳል፡፡

የጋንግሪን ህመም በተለምዶ በእግር ላይ የሚስተዋል ቢሆንም በየትኛዉም የሰዉነታችን ክፍል ላይ የሚከሰት ህመም ነዉ፡፡

በጉዳዩ ላይ ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታልና በላንሴት አጠቃላይ ሆስፒታል የአጥንት ቀዶ ጥገና ፣ቅየራና የከፍተኛ ስብራቶች ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪም የሆኑት ዶ/ር ገለታው ተሰማ ናቸዉ።



#ጋንግሪን ማለት ምን ማለት ነዉ?
ከሙሉ አካላችን ተለይቶ የተወሰነ የሰዉነት ክፍላችን እየሞተ ወይም በድን እየሆነ መምጣት ነው ይላሉ፡፡

ይህም በዛ አካባቢ ያሉት የሰዉነት ክፍላችን በቂ የሆነ ደም ፣ ኦክስጅን  እና ምግብ ባለማግኘቱ የሚፈጠር እንደሆነ ይናገራሉ፡፡




#መንስኤዎቹ ምንድን ናቸው?
-  የስኳር ታማሚ መሆን
-  ኢንፌክሽን
-  በአደጋ ምክንያት የደም ስር መቆረጥ ተጠቃሽ መሆናቸውንም ባለሙያዉ ይናገራሉ፡፡


#የስኳር ህመምተኞችም ማድረግ ካለባቸው ጥንቃቄዎች መካከል የሚያጠብቃቸውን ጫማ ከመልበስ መቆጠብ እንደሆነ  አንስተዋል፡፡



#ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
-  እዛ አካባቢ ላይ መጥቆር እና
-  መድረቅ ዋናዎቹ መሆናቸዉንም ዶክተር ገለታዉ ነግረዉናል፡፡



#ህክምናዎቹ ምንድን ናቸው?
የሚሰጡት ህክምናዎች እንደየ ምክንያቱ እንደሚለያይም ባለሙያዉ ይናገራሉ፡፡
-  ለአንዳንድ ሰዎች የደም ስር ህክምና የሚሰጥ ሲሆን፤
-  ኢንፌክሽኑን ማከም
-  ከፍ ካለ ደግሞ የተጎዳውን አካል ማስወገድ ከህክምናዎቹ መካከል መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡


#በመጨረሻም የስኳር ህመምተኞች ተገቢውን የህክምና ክትትል ማድረግ እንዳለባቸው እና በህክምና ባለሙያዎች የሚሰጧቸውን የጥንቃቄ  መልዕክቶች መከተል እንዳለባቸዉ ዶ/ር ገለታው ተናግረዋል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ምርጫ ቦርድ ያደረገው የክፍያ መሻሻያ የተጋነነ ነው ሲል የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርታዎች የጋራ ምክር ቤት ተቸ

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ  ይፋ ያደረገው የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ ተገቢነት የሌለው  እና  የተጋነነ ነዉ ሲሉ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት  ሰብሳቢ አቶ ደስታ ዲንቃ  ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ሰብሳቢው  ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታም ፤ቦርዱ ያደረገው  የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ ሁሉንም ፓርቲ ያላማከለ እና ቀደሞውኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ምክክር ያልተደረገበት እንደሆነ ለጣቢያችን ገልጸዋል፡፡

ሰብሳቢው አያይዘውም የዚህ ክፍያ ማሻሻያ  አቅም የሌላቸውን የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያላገናዘበ እና የፖለቲካ ምህዳሩ ላይም የእራሱን ጠባሳ የሚያሳርፍ ነዉ ብለዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ወደፊት በፓርቲ ደረጃ ለመቋቋም ያሰቡ ህዝቦቸን መብት በተወሰነ መልኩ ሊገድብ እንደሚችል ገለጸው፤ይህ ማለት የመደራጀት መብትን በተወሰነ መልኩ የሚገድብ እንደሆነም ነግረውናል፡፡

የፖለቲካ ምህዳሩ አሁንም ሰፋ ያለ አለመሆኑን የነገሩን ዋና ሰብሳቢው ፤ ይህ ማሻሻያ ደግሞ ከዚህ በላይ የፖለቲካ ምህዳሩን እንዳያጠበው ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ  ለፖለቲካ ፓርቲዎች በሚሰጣቸው ሶስት አገልግሎቶች ላይ ከጥቅምት 11፤ 2017 ጀምሮ ጭማሪ ማድረጉን ማስታወቁ ይታወቃል፡፡

በአዲሱ "የክፍያ ማሻሻያ ተመን መሰረት" ለጊዜያዊ እውቅና 15ሺ ብር፣ ለሙሉ እውቅና 30ሺ ብር፣ ለሰነድ ማሻሻያ ደግሞ 5ሺ ብር እንደሚያስከፍል ቦርዱ መግለጹ ይታወሳል፡፡

ለዓለም አሰፋ

ጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከኤርትራ ጋር ጥቅምት 21 እና 24 ለሚያከናውናቸው የቻን ማጣርያ ጨዋታዎች ዝግጅት አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አስተላልፈዋል።

ጥሪው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድርን ባማከለ መልኩ የተከናወነ በመሆኑ ሊጉ የማይቋረጥ ሲሆን ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾችም ነገ ጥቅምት 14 ካዛንቺስ በሚገኘው ጁፒተር ሆቴል ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ ሪፖርት አድርገው በመሰባሰብ ዝግጅት እንዲጀምሩ ጥሪ ቀርቧል።


ጋዲሳ መገርሳ

ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞንሮቪያ መብረር ሊጀምር ነዉ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቋርጦት የነበረዉን ከአዲስ አበባ ወደ ላይቤሪያ ርዕሰ ከተማ ሞንሮቪያ የሚያደርገዉን በረራ ሊጀምር ነዉ።

አየር መንገዱ እንዳስታወቀዉ በሳምንት ሶስት ቀን ወደ ሞንሮቪያ የሚያደርገዉን የደርሶ መልስ በረራ በመጪዉ ሳምንት ይጀምራል።

ከአፍሪቃ ግዙፉ አየርመንገድ አዲስ የሚጀምረዉ በረራ የአፍሪቃን የንግድ፣የቱሪዝምና የባሕል ልዉዉጥን ለማሳደግ የሚያደርገዉ አስተዋፅኦ አካል ነዉ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀን 270 በረራዎችን ወደ መላዉ ዓለም ያደርጋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ዶናልድ ትራም እንግሊዝ በምርጫችን ጣልቃ እየገባች ነዉ አሉ

ዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ዘመቻ ቡድን እንዳስታወቀዉ የእንግሊዙ ገዢ ፓርቲ በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ጣልቃ እየገባ ነዉ ሲል ከሷል፡፡

የለንደን ባለስልጣናት በተደጋጋሚ ወደ አሜሪካ እያቀኑ ዲሞክራቶችን እየደገፉ ስለመሆናቸዉ ደርሼበታለሁ ብሏል የትራምፕ የህግ ክፍል፡፡

የሌበር ፓርቲ አመራሮች ካማላ ሃሪስ እንዲያሸንፉ ህገ ወጥ ሥራ እየሰሩ ነዉ ተብሏል፡፡

የለንድ አመራሮች ግን የትራምፕን ክስ መሰረተ ቢስ በሚል ማጣጣታላቸዉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የእንግሊዙ የመከላከያ ሚኒስትር ጆህን ሄሊ የትራም ምርጫ ቅስቀሳ ቡድን ትልቅ ስህተት ሰርቷል ብለዋል፡፡

ሪፐብሊካንን ወክለዉ እልህ አስጨራሽ ትግል ዉስጥ የሚገኙት ዶናልድ ትራምፕ ሩሲያን ጨምሮ በርካታ የዉጭ አገራት ጣልቃ እገቡ ነዉ በሚል እየከሰሱ ይገኛሉ፡፡

የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከሁለት ሳምንት በኋላ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

አባቱ መረቀ

ጥቅምት13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

መደበኛ ባልሆነ ማቆያ ቦታ እንዲቆዩ የሚደረጉ እና አስገድዶ መሰወር የሚደረግባቸዉ ተጎጂዎች እና ቤተሰቦቻቸዉ ፍትህ ሊሰጣቸዉ ይገባል- ኢሰመኮ

መደበኛ ባልሆነ ማቆያ ቦታ፣ ያሉበት ሳይገለጽ እንዲቆዩ የተደረጉ እና አስገድዶ መሰወር ሁኔታን ሊያቋቁም በሚችል ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ተጎጂዎች እና የተጎጂዎች ቤተሰቦችን በተመለከተ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ እና ፍትሕ ሊሰጣቸው ይገባል ሲል ኢሰመኮ ገለጸ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ፣ እንዲሁም በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የተለያዩ አካባቢዎች የአስገድዶ መሰወር ሁኔታን ሊያቋቁሙ በሚችሉ እና ያሉበት ሳይገለጽ በተራዘመ እስር ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ሁኔታ በተመለከተ በተለያየ ጊዜያት መግለጫዎችን ማዉጣቱን ገልጿል፡፡

እንዲሁም ሰኔ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት የድርጊቱ አሳሳቢነት የቀጠለ መሆኑን እና ይህንን ለማስቆም አፋጣኝ እርምጃዎች ሊወሰዱ እንደሚገባ በተደጋጋሚ ሲያሳስብ መቆየቱን አስታዉሷል፡፡

ኢሰመኮ በተለይም ከመስከረም ወር እስከ ጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም. በተካሄደው 57ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ የአስገድዶ መሰወር ድርጊቶች መስፋፋት አሳሳቢነት መቀጠል አስመልክቶ ያቀረበውን የሰብአዊ መብቶች ክትትል ሪፖርት ተከትሎ መንግሥት በሰጠው ምላሽ፣ የችግሩን አሳሳቢነት በማስታወስ “ኢትዮጵያ ይህንን ድርጊት በዘላቂነት ለማስቆም ዓለም አቀፍ ግዴታዎቿን መወጣትን ጨምሮ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እንደሚሠራ” (1፡48፡42 ላይ) በድጋሚ መግለጹን ተናግሯል፡፡

ኢሰመኮ ያሉበት ሳይገለጽ በተራዘመ እስር ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ እና የአስገድዶ መሰወር ሁኔታን ሊያቋቁሙ በሚችሉ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ሁኔታ በተመለከተ የሚያደርገውን ክትትል የሚቀጥል መሆኑን አስታዉቋል፡፡

በተለይም ከሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ተወስደው ያሉበት ቦታ ሳይታወቅ የቆዩ መሆናቸው የተገለጸ ከ52 በላይ የሆኑ ሰዎችን የተመለከቱ አቤቱታዎችን መርምሮ ይህ ሪፖርት እስከወጣበት ቀን ድረስ 44 ሰዎች ከ1 ወር እስከ 9 ወር በተለያዩ መደበኛ ባልሆኑ ቦታዎች ከቆዩ በኋላ መለቀቃቸውን ማወቅ ችያለሁ ብሏል፡፡

ኢሰመኮ መደበኛ ባልሆኑ ማቆያ ቦታዎች ውስጥ የሚደርሱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት ኃላፊዎችን እንዲሁም የተጎጂ ቤተሰቦችን፣ የዐይን ምስክሮችን እና የተለቀቁ ሰዎችን በማነጋገር መረጃዎችን እና ማስረጃዎችን ማሰባሰቡንም ገልጿል፡፡

ተጎጂዎች በአብዛኛው ሰሌዳ በሌላቸው ተሽከርካሪዎችና በታጠቁ ሲቪል ወይም የደንብ ልብስ በለበሱ የጸጥታ አካላት ተገቢውን የሕግ ሥነ ሥርዓት ባልተከተለ ሁኔታ በግዳጅ የተያዙ መሆናቸውን እና በእስር የቆዩበትን ቦታ የማያውቁ፣ በቂ ምግብና ውሃ የማይቀርብላቸው የነበሩ፣ እንዲሁም ለየብቻቸው ተለይተው ተይዘው የቆዩ መሆናቸውንም አስታዉቋል፡፡


ከተጎጂዎቹ መካከል የመለቀቃቸውን ሂደት ሲያስረዱ በምሽት ዐይናቸው ተሸፍኖ በተሽከርካሪ ከተጫኑ በኋላ በተለያዩ የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢዎች እንዲወርዱ ተደርገው እና “ለመጓጓዣ” በሚል ከ300 እስከ 1000 ብር ተሰጥቷቸው የተለቀቁ መኖራቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ሁሉም ተጎጂዎች በእራሳቸውና በቤተሰቦቻቸው ላይ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት፣ እንዲሁም ከፍተኛ የሥነ ልቦና ቀውስ መድረሱን እና በሥጋት መኖራቸውን ነግረዉኛል ሲል ኢሰመኮ አስታዉቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በኢትዮጵያ ያሉ የዝሆኖችን ቁጥር እና ሁኔታ  ለማወቅ የሚያስችል ጥናት  ሊካሄድ ነው ተባለ

በኢትዮጵያ ያሉ ዝሆኖችን በተለየ በባቢሌ  ያሉ የዝሆኖችን ቁጥር እና ያሉበትን ሁኔታ  ለማወቅ ፤ ጥንቃቄ ለማድረግ ጥናት ሊካሄድ እንደሆነ የአየአካባቢ ደን እና ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ገልጿል።

የባለስልጣኑ ዋና ሀላፊ የሆኑት አቶ ኩመራ ዋቅጅራ  ጥናቱ በዚህ ሳምንት በተቀናጀ መልኩ የሚመለከተው ባለድርሻ አካላት ባሉበት  ጥናቱ እንደሚካሄድም ተናግረዋል።

ከጥናቱ በኋላ  አሁን ላይ  ዝሆኖች ያሉበትን ሁኔታ በተመለከታ ሰፊ መረጃ ማግኘት እንደሚቻል አንስተው ጥናቱ በዚህ ሳምንት
እንደሚጀምር ነግረውናል፡፡

ሃላፊው አያይዘውም  በባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ ሲነሳ የነበረውን ችግር  የኢንቨስትመንት ድርጅት ከባቢሌ እንዲወጣ  ለባለስልጣኑ መወሰኑን ቢያነሱም ያሉ ችግሮች ግን አሁንም አለመቀረፋቸውን ነግረውናል፡፡

በሶማሊያ እና ኦሮሚያ ክልል ድንበር አዋሳኝ ቦታ ላይ የሚገኘውን የባቢሌን የዝሆኖች መጠለያ ችግር  ለመፍታተት አሁንም ጥረቶች መቀጠላቸውን ገልፀዋል።

በባቢሌ የዝሆን መጠለያ በዝሆኖች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ በተደረገው ህገወጥ ሰፈራ ዝሆኖች የሚኖሩበትና የሚራቡበት ቦታ በእርሻ፣ በከሰል ምርት፣ በመንገድና መኖሪያ ቤት ግንባታ ደን እየመነመነ በመምጣቱ  አሁንም ጉዳዩ  አሳሳቢ መሆኑንም ባለስልጣኑ ለጣቢያችን ገልጷል።

ለአለም አሰፋ

ጥቅምት 18  ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ታላቁ የኢትዮጵያ የእግርኳስ አባት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

በኢትዮጵያ እግርኳስ ስማቸው በወርቅ ቀለም በደማቅ ታሪካቸው ከተፃፈላቸው የእግርኳስ ሰዎች መካከል አንዱ የነበረው አሰልጣኝ አስራት ኃይሌ (ጎራዴው)ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ጥቅምት 16 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

Junior Open 2024 የታዳጊዎች የቴኒስ ውድድር ኢትዮጵያ ዛሬ ከቀኑ 9:00 በሂልተን ሆቴል ይጀመራል ።

ሀገራችን ኢትዮጵያን በአለምአቀፍ መድረኮች ላይ የሚወከሉ የቴኒስ ስፖርት ተጫዋቾችን ለማፍራት ለስፖርቱ ልዩ ፍቅር እና ችሎታ ያላቸው ታዳጊዎችን በዘርፉ ማሳተፍ ያስፈልጋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ በጣት የሚቆጠሩ ተቋማት በዘርፉ በስፋት በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ከነዚህ ተቋማት መካከል ታሪኩ እና ደስታ ቴኒስ ክለብ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል።

ተቋሙ ቴኒስን በመጠቀም ታዳጊዎች በሁለንተናዊ ስብዕና ታንፀው እንዲያድጉ እየሰራ ያለ ተቋም ነዉ።

በተቋሙ በቴኒስ ስፖርት የስልጠና ማዕቀፍ ውስጥ በተለይም ገቢያቸዉ አነስተኛ የሆነ ቤተሰብ ውስጥ ያሉ ታዳጊዎች እንዲታቀፉ በማድረግ በስፖርቱ፣ በትምህርት እና በአጠቃላይ ህይወታቸዉ ውጤታማ የሆኑ ዜጎችን ማፍራት ተችሏል።

ከሁለት አስርት አመታት በላይ ባስቆጠረዉ የስራ ጊዜዉ ታሪኩ እና ደስታ ቴኒስ ከለብ በተለያዩ የአለማችን ከፍል በስፖርት እና በስኮላርሺፕ ስኬትን ያስመዘገቡ ወጣቶችን ማፍራት ችሏል። በአሁኑ ሰዓትም በክለቡ ውስጥ 80 ያህል ታዳጊዎች ይገኛሉ።

ለእነዚህ እና በአጠቃላይ በሀገራችን ላሉ ታዳጊ የቲኒስ ስፖርተኞች የውድድር እድል ለመፍጠር እና የተሻለ ልምድ ለማስገኘት የሚያስችል ለሁሉም ከፍት የሆነ የቴኒስ ውድድር (TDKET Junior Open 2024) ለማካሄድ ዝግጅቱን ጨርሷል።

ውድድር በሶስት ምድብ ይደረጋል ከ10, ከ12 ኢና ከ14 አመት በታች
የውድድሩ አላማ

➢ ነገ ሀገራችን ኢትዮጵያን በታላላቅ መድረኮች የሚወከሉ ታዳጊ የቴኒስ ተጫዎቾችን ለማፍራት፤

➢ ለቴኒስ ስፖርት ልዩ ፍቅር እና ችሎታ ያላቸውን ታዳጊዎች ለማበረታታት፤

➢ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ጥሩ ጊዜ እንዲያሳልፉ ለማድረግ፤

➢ በሁሉም የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ታዳጊዎችን ለማሳተፍ፤

➢ የቴኒስ ውድድር ስፖርታዊ ጨዋነትን ለታዳጊዎች ከልጅነታቸው ጀምሮ ለማስተማር ወዘተ.

ውድድሩ
❖ ዛሬ ጥቅምት 15 - የውድድር የመከፈቻ መርሀግብር እና የመከፈቻ ጨዋታዎች

❖ ነገ ጥቅምት 16 - በሁለቱም ፆታ ውድድሮች ይካሄዳሉ

❖ እሑድ ጥቅምት 17 - የፍፃሜ እና የሽልማት እንዲሁም የመዝጊያ መርሀግብር

ጋዲሳ መገርሳ

ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የዛሬ የጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በኢትዮጵያ በዓመት ለካንሰር ህመም መድሃኒት ለመግዛት ከ1መቶ 70 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ይደረጋል ተባለ፡፡

የጤና ሚኒስቴር በዓመት ለካንሰር ህመም የሚዉል መድሃኒት ለመግዛት ከ1 መቶ 70 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደሚያደርግ ሰምተናል፡፡

በኢትዮጵያ የሴቶችን ህይወት በመንጠቅ በሁለተኝነት ደረጃ ላይ የሚገኘዉ የማህጸን በር ካንሰር የቅድመ ልየታ ምርመራ ከ1ሺህ 4መቶ በላይ በሚሆኑ የጤና ተቋማት እየተሰጠ ይገኛል ተብሏል፡፡

በጤና ሚኒስቴር የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሲስተር ታከለች ሞገስ፤ በየዓመቱ ከ8 ሺህ በላይ እናቶች በማህጸን በር ካንሰር እንደሚያዙ ተናግረዋል፡፡

በማህጸን በር ካንሰር ከሚያዙት እናቶች መካከል ደግሞ 5ሺህ 9መቶ 75 እናቶች ህይወታቸዉ እንደሚያልፍም ነዉ የገለጹት፡፡

በ2030 የማህጸን በር ካንሰር የማህበረሰብ ችግር የማይሆንበት ደረጃ ላይ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ስራ አስፈጻሚዋ፤ ከ2007 ጀምሮ እስካሁን ከ 2 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ሴቶች የቅድመ ልየታ ህክምና መከናወኑን ተናግረዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ለካንሰር ህመም መድሃኒት መግዣ በዓመት ከ1 መቶ 70 ሚሊየን ብር በላይ እንደሚያወጣ የገለጹት ሲስተር ታከለች፤ ይህንን ወጪ ለመቀነስ ቅድመ ልየታ ምርመራ በማድረግ ችግሩ ከመከሰቱ በፊት አስቀድሞ መከላከል እንደሚገባ ነዉ የገለጹት፡፡

የማህጸን በር ካንሰር ዕድሜያቸዉ ከ14 ዓመት በታች ለሆኑ ሴቶች ክትባት በመስጠት ቀድሞ መከላከል የሚቻል መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ እስከ ፈረንጆቹ ሚያዚያ 2024 ድረስ ከ7.7 ሚሊየን በላይ ሴቶች ክትባቱን ማግኘታቸዉ ተገልጿል፡፡

ከፈረንጆቹ 2025 ጀምሮ ደግሞ ዕድሜያቸዉ 9 አመት ለሆናቸዉ ሴቶች ክትባቱ እንደሚሰጥም ለማወቅ ችለናል፡፡

እስከዳር ግርማ

ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የነገ የጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ጋንግሪን(gangrene)

ጋንግሪን አደገኛ እና ገዳይ የሆነ የጤና ችግር እንደሆነ  ይነገራል ፡፡
ስር የሰደደ የጤና እክል ያለባቸው እና የበሽታ መከላከል አቅማቸው የተዳከመ ሰዎች ለዚህ ሕመም ተጋላጭ መሆናቸው ይነሳል፡፡

የጋንግሪን ህመም በተለምዶ በእግር ላይ የሚስተዋል ቢሆንም በየትኛዉም የሰዉነታችን ክፍል ላይ የሚከሰት ህመም ነዉ፡፡

በጉዳዩ ላይ ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታልና በላንሴት አጠቃላይ ሆስፒታል የአጥንት ቀዶ ጥገና ፣ቅየራና የከፍተኛ ስብራቶች ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪም የሆኑት ዶ/ር ገለታው ተሰማ ናቸዉ።



#ጋንግሪን ማለት ምን ማለት ነዉ?
ከሙሉ አካላችን ተለይቶ የተወሰነ የሰዉነት ክፍላችን እየሞተ ወይም በድን እየሆነ መምጣት ነው ይላሉ፡፡

ይህም በዛ አካባቢ ያሉት የሰዉነት ክፍላችን በቂ የሆነ ደም ፣ ኦክስጅን  እና ምግብ ባለማግኘቱ የሚፈጠር እንደሆነ ይናገራሉ፡፡




#መንስኤዎቹ ምንድን ናቸው?
-  የስኳር ታማሚ መሆን
-  ኢንፌክሽን
-  በአደጋ ምክንያት የደም ስር መቆረጥ ተጠቃሽ መሆናቸውንም ባለሙያዉ ይናገራሉ፡፡


#የስኳር ህመምተኞችም ማድረግ ካለባቸው ጥንቃቄዎች መካከል የሚያጠብቃቸውን ጫማ ከመልበስ መቆጠብ እንደሆነ  አንስተዋል፡፡



#ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
-  እዛ አካባቢ ላይ መጥቆር እና
-  መድረቅ ዋናዎቹ መሆናቸዉንም ዶክተር ገለታዉ ነግረዉናል፡፡



#ህክምናዎቹ ምንድን ናቸው?
የሚሰጡት ህክምናዎች እንደየ ምክንያቱ እንደሚለያይም ባለሙያዉ ይናገራሉ፡፡
-  ለአንዳንድ ሰዎች የደም ስር ህክምና የሚሰጥ ሲሆን፤
-  ኢንፌክሽኑን ማከም
-  ከፍ ካለ ደግሞ የተጎዳውን አካል ማስወገድ ከህክምናዎቹ መካከል መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡


#በመጨረሻም የስኳር ህመምተኞች ተገቢውን የህክምና ክትትል ማድረግ እንዳለባቸው እና በህክምና ባለሙያዎች የሚሰጧቸውን የጥንቃቄ  መልዕክቶች መከተል እንዳለባቸዉ ዶ/ር ገለታው ተናግረዋል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በኢትዮጵያ 39 በመቶ የሚሆኑት ከአምስት አመት በታች ያሉ ህጻናት የመቀንጨር ቸግር ገጥሟቸዋል ተባለ

ጤና ሚኒሲቴርና  ዩኒሴፍ  ባደረጉት ጥናት መሰረት ትግራይን ሳይጨምር  በኢትዮጵያ 39 በመቶ ከአምስት አመት በታች ያሉ ህጻናት የመቀንጨር ችግር  እንዳጋጠማቸው  ታዉቋል፡፡

በጤና ሚኒሲቴር የስርዓተ ምግብ ማስተባበሪያ ክፍል ፤የስርዓተ ምግብ መከታተል  የዴስክ ሃላፊ ቅድስት ወልደሰንበት፤ይህ ቁጥር የትግራይ ክፍል ጥናቱ ሲታይ ከዚህ ሊያልፍ እንደሚችል ስጋታቸዉን ገልፀዉልናል፡፡

ባለፉት በርካታ ዓመታት የመቀንጨር ምጣኔ የቀነሰ መስሎ ቢታይም፣ በቅርቡ በተደረገው ጥናት ከፍተኛ መሆኑ  ጠቁመዋል፡፡

ይህም 39 በመቶ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት የመቀንጨር፣ 11 በመቶ ያህሉ ደግሞ የመቀንጨር ምጣኔ እንደታየባቸው ተናግረዋል፡፡

ለዚህም ለልጆች የተመጣጠነ ምግብ እጥረት በርካታ ምክንያቶች አሉ ያሉት ሃላፊዋ፤  የተመጣጠነ ምግብ እጥረት፣ ድህነት፣ በቂ የጤና እንክብካቤ እጥረት፣ የጡት አለማጥባት፣ የንጽህና እጦትና የኑሮ ሁኔታ ዋና ዋናዎቹ  ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በሃገሪቱ ዉስጥ ያለዉም የሰላምና ፀጥታ ችግር አንዱ ምክንያት ነዉ ብለዉናል፡፡

ከአምስት ዓመት በታች በሆኑ ሕፃናት ላይ ከሚደርሰው ሞት ግማሽ ያህሉ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ሳቢያ የሚከሰት ነዉ፡፡

ከሞት የተረፉትም፣ የአዕምሮ ዘገምተኛ የመሆን ዕድላቸው የሰፋ ከመሆኑም ባሻገር፣ የመማር፣ የማሰብ፣ የመረዳትና የማስታወስ ችሎታቸውም ዝቅተኛ ነው ተብሏል፡፡

በአዋቂነት ዘመን በሚሰማሩበት ዘርፍ ሁሉ ውጤታማና አምራች ዜጋ እንደማይሆኑም ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ የምግብ ሥርዓት ትራንስፎርሜሽን አያያዝን በተመለከተ ዲዛይን ተደርጎ  ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ ነዉም ብለዉናል፡፡

ከዚህ ዉጭ ሁሉ ማህበረሰብ እዚህ ላይ ርብርብ ሊያደርግ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

ልዑል ወልዴ

ጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ይፋ ሲደረጉ በርከት ያሉ የቅጣት ውሳኔዎች ተላልፈዋል።

በተጫዋቾች ባሳለፍ ነው  ዕሁድ  ምሽት  በተደረገው  የኢትዮጵያ  ንግድ  ባንክ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ ከጨዋታው በኋላ ተጫዋች በመማታት በሚል ኤፍሬም ታምራት እና በረከት ወልዴ የአራት ጨዋታዎች ቅጣት
ተበይኖባቸዋል።

ተጫዋቾቹ ከጨዋታ ቅጣቱ በተጨማሪም እያንዳንዳቸው የሶስት ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ተላልፎባቸዋል።


በዚህም  ኤፍሬም  ታምራት   ክለቡ ከፋሲል ከነማ ፣ ከመቻል ፣ ከወልዋሎ አዲግራት እና ከኢትዮጵያ መድኅን የሚያደጋቸው ጨዋታዎች የሚያልፉት ሲሆን ፤ በረከት ወልዴ በበኩሉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ መድኅን ፣ ከአርባምንጭ ከተማ ፣ ከሲዳማ ቡና እንዲሁም ከመቻል የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች
ያልፉታል።

አንጋፋው የመቻል ተጫዋች ሽመልስ በቀለም ቡድኑ ከመቀሌ 70 እንደርታ ነጥብ በተጋራበት ጨዋታ ላይ የጨዋታውን ዳኞች አፀያፊ ስድብ ተሳድበሀል በሚል የሶስት ጨዋታዎች እና የሶስት ሺህ ብር ቅጣት ተበይኖበታል።


በዚህም መቻል ከወልዋሎ አዲግራት ፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ከአዳማ ከተማ ጋር የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ላይ የማይሰለፍ ይሆናል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ቡናው ራምኬል ጀምስ እና የአዳማ ከተማ አድናን ረሻድ በሳምንቱ ጨዋታዎች ላይ የቀይ ካርድ መመልከታቸውን ተከትሎ ከአምስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ታግደዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ ዋና አሰልጣኝ በፀሎት ልዑል ሰገድ ዛሬ 10:00 ላይ በድሬዳዋ ስታድየም እንዲገኝ ሲል የዲሲፕሊን ኮሚቴው አሳውቋል።

እንዲሁም የቅዱስ ጊዮርጊስ ምክትል አሰልጣኝ ሳምሶን ሙሉጌታ እና የቡድን መሪው አዳነ ግርማ ደግሞ በመጪው ቅዳሜ 6:15 ላይ በድሬዳዋ ስታድየም እንዲገኙ ጥሪ ተላልፎላቸዋል።

በተጨማሪም የመቀሌ 70 እንደርታው መድኃኔ ብርሀኔም ዛሬ 10:30 ላይ በተመሳሳይ በድሬዳዋ ስታድየም እንዲገኝ ጥሪ ቀርቦለታል።


ጋዲሳ መገርሳ

ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ኢትዮጵያ ከ ኤርትራ ጋር የምታደርጋቸው የደርሶ መልስ ጨዋታዎች በደቡብ ሱዳን ጁባ  የከናወናሉ።

በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ማጣርያ ኢትዮጵያ ከ ኤርትራ ጋር የምታደርጋቸው የደርሶ መልስ ጨዋታዎች በደቡብ ሱዳን ጁባ ብሔራዊ ስታዲየም የሚከናወኑ ሲሆን የጨዋታ ቀኖቹ ላይም ለውጥ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት ጥቅምት 21/2017 እና ጥቅምት 24/2017 ጨዋታዎቹ የሚከናወኑ ይሆናል።


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ማጣርያ የሚያደርጋቸው ጨዋታዎችን በአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት እየተመራ እንዲያከናውን የኢ/እ/ፌ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባ ውሳኔ አሳልፏል።

አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ላለፉት 12 ወራት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኝ ሆነው ሲሰሩ እንደቆዩ የሚታወቅ ሲሆን ቡድናችን ከኤርትራ ጋር የሚያከናውናቸውን ጨዋታዎች ጨምሮ የቻን ማጣርያን በጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት የሚመሩ ይሆናል።

ጋዲሳ መገርሳ

ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ቲቧ ኩርቱዋና ሮድሪጎ ከኣሌ ክላሳኮ ጨዋታ ውጪ  ሆኑ!

ቤልጂየማዊው  ግብ ጠባቂ ቲቧ ኩርቱዋ በተደረገለት ምርመራ ትላንት ምሽት ጉዳት እንዳጋጠመው መረጋገጡን ክለቡ አሳውቋል።

ኩርቱዋ ያጋጠመው ጉዳት ለሳምንታት ከሜዳ ሊያርቀው እንደሚችል ተዘግቧል።

ሎስ ብላንኮዎቹ በኤል ክላሲኮ ጨዋታ አንድሬ ሉኒንን በግብ ጠባቂነት የሚጠቀሙ ይሆናል። 

ሌላኛው  ብራዚላዊው  የፊት መስመር ተጨዋች ሮድሪግ በትላንት ምሽቱ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ጉዳት እንዳጋጠመው በህክምና ምርመራ መረጋገጡ ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ ሮድሪጎ ሪያል ማድሪድ ከቀናት በኋላ ከባርሴሎና ጋር የሚያደርገው ተጠባቂው የኤል ክላሲኮ ጨዋታ የሚያመልጠው ይሆናል።

ተጠባቂው የኤል ክላሲኮ ፍልሚያ ቅዳሜ ምሽት 4:00 ሰዓት በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም የሚደረግ ይሆናል።

ጋዲሳ መገርሳ

ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ በመካከለኛዉ ምስራቅ ጦርነት ዙሪያ ከኢራኑ ፕሬዝዳንት ጋር መምከራቸዉን አስታወቁ

በሩሲያ ካዛን እየተካሄደ በሚገኘዉ የብሪክስ ጉባኤ ላይ እተሳተፉ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኢራኑ ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዝሽኪያን ጋር መምከራቸዉን አስታዉቀዋል፡፡

በዉይይታቸዉም በመካከለኛዉ ምስራቅ ያለዉን ጦርነት ለማስቆም ኢትዮጵያ እንደምታግዝ መግለፃቸዉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል፡፡

በብሪክሱ ጉባኤ ላይ የቻይና፤ የህንድ፤የኢራን፤የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች፤የግብፅና የደቡብ አፍሪካን ጨምሮ የበርካታ አገራት መሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

የባህሪ መታወክ(personality disorder)

የባህሪ መታወክ(personality disorder) የሚጀምረው ስብዕናችን እያደረገ ሲመጣ ወይም አዕምሯችን በሚበስልበት በጉርምስና ዕድሜ ላይ መሆኑ ይነገራል፡፡

እንዲሁም የተለመደ እና ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የስነ ልቦና ችግር መሆኑ ይጠቀሳል፡፡

የሰው ልጅ ማንነት በአስተሳሰብ እና በድርጊቶች ላይ ተጽእኖ በሚያሳድሩ ልዩ ባህሪያት የተሰራ እደሆነ ይነሳል፡፡

የስብዕና መታወክ ያለባቸው ሰዎች ለመሥራት እና ከሌሎች ጋር አወንታዊ ግንኙነት ለመመሥረት ሊከብዳቸው እንደሚችል በባለሙያዎች ይገለፃል፡፡

በአለማችን ላይ 7.8 በመቶ የሚሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎቸ የዚህ ችግር ሰለባ መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በጉዳዩ ላይም ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የስነልቦና ባለሙያ የሆኑት አቶ ልዑል አብርሀም ናቸው፡፡

የባህሪ መታወክ(personality disorder) ምን ማለት ነው

የተዛባ የሆነ አመለካከት ፣ የተዛባ የሆነ ድርጊት ፣የተዛባ የሆነ አስተሳሳብ እና ባህሪ አንድ ላይ ሲደመሩ የሚመጣ ነው ይላሉ ፡፡

የተዛባ ስንል ደግሞ ቀን በቀን ባለው ህይወታችን ውስጥ ወጣ ያለ ባህሪያት ስናሳይ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡

መንስኤዎቹ ምንድን ናቸው?

- በቤተሰብ ይህ ችግር ካለ
- ያደግንበት አካባቢ
- ተፅዕኖ የመቋቋም አቅማችን ተጠቃሽ ናቸው

ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?

- ተጣራጣሪ መሆን(ሰዎችን አለማመን)
- ሰዎችን ለመቅረብ አለመፈለግ
- ነገሮችን እንደ አዲስ ለመሞከር መፍራት
- አንዳንዴ ከሌላው ሰው የተሻልን ነን ብሎ ማሰብ ተጠቃሽ ናቸው ፡፡

ነገር ግን ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች ብዙውን ጊዜ እነዚህን ነገሮች ስለማያስተውሏቸው እንደዚህ አይነት የስነ ልቦና ችግር እንዳለበት ላይገነዘቡ እንደሚችሉ ይናገራሉ፡፡

የሚያመጣው ተፅዕኖ ምንድን ነው?

- የተጠራጣሪነት ስሜት ስላላቸው ከሰዎች ጋር ለመቀላቀል መቸገር
- ምቹ ያልሆነ የስራ ቦታ እንዲፈጠርባቸው ማድረግ
- ከማህበራዊ ህይወት መገለል ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ባለሙያው ያነሳሉ፡፡

ህክምናዎቹ ምንድን ናቸው?

የስነ ልቦና ባለሙያን በማግኘት የስነ ልቦና ህክምና ማድረግ ዋነኛው ነው ይላሉ፡፡

በመጨረሻም ችግሩን ለመከላከል ልጆችን በምናሳድግበት ሰዓት በጥሩ መልኩ ማሳደግ የተሻለ ማንነት ይዘው እንዲወጡ ለማድረግ እንደሚረዳ እና ይህ የስነ ልቦና ችግር በቀላሉ ከተደረሰበት ወዲያው መቅረፍ የምንችለው ስለሆነ በጊዜ ባለሙያዎችን ማማከር እንደሚገባ ባለሙያው ተናግረዋል፡፡

ሐመረ ፍሬዉ

ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Ethio Fm 107.8

በኢትዮጵያ ባለፈዉ አመት ከአንድ ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ህፃናት ክትባት አልወሰዱም ተባለ።

ሙሉ ለሙሉ ክትባት ካልወሰዱት ህጻናት በተጨማሪ ክትባቱን ጀምረዉ ያቋረጡ መኖራቸዉንም ሰምተናል፡፡

በጤና ሚኒስቴር የክትባት ፕሮግራም ሀላፊ የሆኑት አቶ መስፍን ካሴ፤ ባለፈዉ ዓመት ክትባት ካልወሰዱት ከአንድ ሚሊየን በላይ ህጻናት በተጨማሪ ክትባቱን ጀምረዉ ያቋረጡ እንዳሉ ጥናቶች ያሳያሉ ብለዋል።

ይህንን ለማስተካከል ክትባት የመስጠቱ ስራ እየተሰራ ይገኛል ያሉት አቶ መስፍን፤ 65 በመቶ የሚሆነዉ የክትባት ፕሮግራም በጤና ጣቢያና በሆስፒታሎች እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከህክምና ቦታዎች ርቀዉ ለሚገኙ ደግሞ የጤና ባለሙያዎች ያሉበት ድረስ በመሄድ ክትባቱን እየሰጡ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡

ክትባት ያላገኙትን ህፃናት ክትባት እንዲያገኙ በዘመቻ መልክ እየሰራን እንገኛለን ያሉት ሃላፊዉ፤ ዜሮ ዶዝ ከሚባለዉ ክትባት ወደ 16 በመቶ የሚሆነዉን ተደራሽ ሆኗል ብለዋል።

ማህበረሰቡን ስለ ክትባት ጥቅም በማሳወቅ የህጻናትን ሞት ለመቀነስ የተለያዩ ስራዎች ከሃይማኖት አባቶች እና ከጤና ባለሙያዎች ጋር እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም

Читать полностью…
Subscribe to a channel